Professional Documents
Culture Documents
የመኖሪያ ቤት እና የእርሻ ቦታ ስጦታ
የመኖሪያ ቤት እና የእርሻ ቦታ ስጦታ
እኛ ስጦታ አድራጊዎች ወ/ሮ ደሜ ሀይሌ ለልጃችን ለአቶ ካብታሙ አርጋ በዚህ በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 28 አንቆርጫ
ቀበሌ ገበሬ ማህበር ክልል ውስጥ አዋሳኞቹም በምስራቅ ቶሎሳ ይዞታ በምእራብ ወንዝ በሰሜን አቶ ወንዱ መንግስቱ
በደቡብ ወ/ሮ ደሜ ሀይሌ የሚያዋስነውን ከይዞታችን ላይ ቀንሼ የሰጠሁት ቤት መሆኑን በስሙ አዛውሮ እንዲጠቀምበት
የሰጠነው ሲሆን ይህን ስጦታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2427 መሰረት የሰጠሁት መሆኑን በፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡
እኔም ስጦታ ተቀባይ አቶ ካብታሙ አርጋ ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በዚህ በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 28 አንቆርጫ
ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ከሚገኘው ይዞታቸው ላይ ቀንሰው የሰጡኝን የመኖሪያ ቤት በስሜ አዛውሬ እንድጠቀምበት
የሰጡኝ ሲሆን ይህን ስጦታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2436 መሰረት የሰጠችን መሆናኔን በፊርማችን አረጋግጣለሁ፡፡
እኛም እማኞች ስጦታ አድራጊዎች በትክክለኛ አእምሯቸው ማንም ሰው ሳያስገድዳቸው ይህን የስጦታ ውል ለአቶ
ካብታሙ አርጋ ስጦታ ተቀባይ ካላቸው ይዞታ ላይ ሲሰጡ ያየን በቦታው የነበርን መሆናችንን በውሉ ላይ ፈርመናል፡፡ ይህ
የስጦታ ውል በአራት ኮፒ ተፅፎ በግራና ቀኝ በስጦታ አድራጊዎች እና በስጦታ ተቀባይ እጅ ተቀማጭ ይሆናል፡፡
1. -------------------------------------------- 1. ----------------------------------------
የምስክሮች ስምና ፊርማ
1. --------------------------------------------
2. --------------------------------------------
3. --------------------------------------------