You are on page 1of 1

መጋቢት 28/ 2009 ዓ.

ለሰነዶች ማረጋጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ


በኢ.ፌ.ድ.ሪ ፍትህ ሚንስቴር
አዲስ አበባ
የውክልና ስልጣን ማስረጃ
ወካይ …………………….. ወ/ሮ እልፍነሽ ዋሬ ድንገቶ/ ዜግነት ኢትዩጲያዊ/
አድራሻ፡- አ.አ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤት ቁጥር 223
ተወካይ …………………. ወ/ሪት የኔነሽ ለማ አስፋው / ዜግነት ኢትዩጲያዊ/
አድራሻ ፡- አ.አ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤት ቁጥር 223

እኔ ወካይ ለተወካይ ልጄ የምሰጠው የውክልና ስልጣን ተወካይ እንደ እኔ በመሆን በስሜ ተመዝግቦ የሚገኘውን የሚንቀሳቀስ ሆነ የማይንቀሳቅስ ንብረት
በተመለከተ እንዲጠብቁ፣ እንዲቆጣጠሩ ፣ እንዲያስተዳድሩ፣ ውል እንዲዋዋሉ፣ እንዲሸጡ፣ እንዲለውጡ፣ ስም እንዲያዞሩ፣ በስሜ ስጦታ ማስተላለፍም
ሆነ መቀበል እንዲችሉ በስሜ የሚንቀሳቀስ ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዲገዙ፣ ስሙን ወደ ስሜ እንዲያዛውሩ፣ ገንዘብና ሰነድ ፈርመው እንዲቀበሉ፣
የማይቀሳቀስ ንብረት እንዲረከቡልኝ፣ ንግድ ፍቃድ እንዲያወጡ፣ እንዲያሳድሱ፣ ዘርፍ እንዲቀይሩ ፣ አስፈላጊ ሲሆን ተመላሽ እንዲያደርጉ፣በማህበርም ሆነ
በሊዝ ተደራጅተው ለቤት፣መስሪያም ሆነ፣ ለድርጅት ማቋቋሚያ እንዲሁም በማህበር በስሜ እንዲፈርሙ፣ ማህበር እንዲያቋቅሙ ፣ግብርም ሆነ
ማንኛውንም ለመንግስት የሚከፈሉ፣ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ፣ እንዲያከራዩ፣ እንዲያኮናትሩ፣የኪራይ ገንዘብ እንዲቀበሉ ፣ የኪራይ ውል እንዲዋዋሉ እና
ውሉን እንዲያፈርሱ፣ ፣የብድር የመያዣና የአክሲዎን ውል እንዲዋውሉ፣ በስሜ የሚሰጠኝን ምትክ ቦታሆነ የካሳ ክፍያ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልተው
እንዲቀበሉ ፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ፍቃድ በስሜ እንዲያወጡ፣ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ እንዲከፍሉ ፣ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በቀበሌ፣
በክ/ከተማ፣ በወረዳ የሚያስፈልገውን ፎርማሊቲ አማልተው እንዲመዘግቡልኝ፣ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ማንኛውንም ክፍያዎችን እንዲከፍሉ ፣ካርታ፣
ፕላን፣ ደብተር፣ ፈርመው እንዲቀበሉ፣የግንባታ ፍቃድ እና ፕላን ማሻሻያ እንዲያወጡ ፣የግንባታ ስራዎችን ባለሙያ ቀጥረው ግንባታ እንዲአካሂዱ፣
ለግንባታው የሚያስፈልገውን ማቴሪያል እንዲገዙ፣ ስልክ፣ ውሀ፣መብራት እንዲያስገቡ፣በማንኛውም ባንክ በስሜ አዲስ የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ፣ ገንዘብ
እንዲያስገቡ፣ እንዲያወጡ፣ በስሜ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዲገዙ፣ ወደ ስሜ እንዲያዛውሩ ቦሎ ክላውዶ እንዲያስደርጉ፣ ሊብሬ
እንዲያዞሮ፣ ታርጋ እንዲቀይሩ፣ የጅቡቲ እና የሱዳን መግቢያ እንዲያወጡ በስሜ ከማንኛውም ባንክ ኤቲኤም እና ቪዛ ካርድ እንዲያወጡ፣ እንዲጠቀሙ
በስሜ ተመዝግቦ የሚገኘውን አካውንት እንዲያንቀሳቅሱ፣ በስሜ በማንኛውም ባንክ ነባርም ሆነ አዲስ ባንክ ሂሳብ ከፍተው እንዲያንቀሳቅሱ፣ ገንዘብ ገቢና
ወጪ እንዲያርጉ አዲስ ቼክ እንዲያወጡ፣ ቼክ ላይ እንዲፈርሙ ቼክ እንዲፈርሙ ፣ ቼክ እንዲመነዝሩ፣ ቼክ እንዲሰጡ፣ ቼክ እንዲቀበሉ፣ ገንዘብ በጥሬ፣
በቼክም በሲፒኦ፣ እንዲከፍሉ፣ እንዲያሰሩ፣ እንዲያስለቅቁ፣ ማንኛውም በስሜ የተዘጋጀ ክፍያ በቼክም ሆነ በጥሬ ገንዘብ ሰነድ ላይ ፈርመው እንዲቀበሉ፤
በስሜ የሞባይል ባንኪንግ እና ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት እንዲጠቀሙ ሲም ካርድ እንዲያወጡ ሲም ካርድ ቢጠፋ እንዲያዘጉ፣ እንዲያስከፍቱ በስሜ
ተመዝግቦ የሚገኘውን የዲያስፖራ አካውንት እንዲያወጡ እንዲያንቀሳቅሱ እንዲያስገቡ የባንክ እስቴትመንት እንዲያሰሩ የኢንቨስትመንት ፍቃድ
እንዲያወጡ፣በስሜ ንግድ ፍቃድ እንዲያወጡ፣ ፍቃድ እንዲያሳድሱ፣ ንግድ ስራ ዘርፍ እንዲቀይሩ ቲን ነምበር እንዲያወጡ፣ ዋና ምዝገባ እንዲመዘግቡ እና
ዋና ምዝገባ እንዲያድሱ ለንግድ የሚሆኑ እቃዎችን ከመንግስትም ሆነ ከግል ድርጅቶች በንግድ ፍቃዴ እንዲገዙ እንዲረከቡ ቫት ሪፖርት እንዲያደርጉ
አስፈላጊውን ፎርሟሊቲ አሟልተው ንግድ ፍቃዱን እንዲመልሱ፣ ከማንኛውም ባንክ እንዲበደሩ፣ ከባንክ ጋር ውል እንዲዋዋሉ እዳ እንዲከፍሉ፣ ከውጭ
ሀገር በስሜ የሚላክ እቃም ሆነ መኪና እንዲያስገቡ፣ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያስገቡ ፣ ከውጭ ሀገር በስሜ ተመዝግቦ የሚመጣውን እቃም ሆነ መኪና
አስፈላጊውን የጉምሩክ ፎርማሊቲዎችን አሟልተው እንዲረከቡ፣ ሊብሬ እንዲያወጡ፣ ሰሌዳ እንዲያስለጥፉ፣ የመሀንዲስ ፍቃድ ብቃት ማረጋገጫ
እንዲያወጡ፣ እንዲያሳድሱ በስሜ የማይንቀሳቅስ ንብረት እንዲገዙ፣ ስሙን ወደስሜ እንዲያዞሩ፣ በስሜ ተመዝግቦ የሚገኘውን የሚንቀሳቀስ ሆነ
የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በባንክ ሆነ በአበዳሪ ድርጅቶች፣ ከማንኛውም ባንክ፣ ከግለሰብ በዋስትና አስይዘው ገንዘብ በማበደርም ሆነ መበደር እንዲችሉ፣
ከማንኛውም ፈንድ ብድር እንዲበደሩ፣ የብድር ውል እንዲዋዋሉ፣ በመያዛም ሆነ ባለማያዣ በስሜ መበደርም ሆነ ማበደር እንዲችሉ፣ የሚንቀሳቀስ ሆነ
የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በዋስትና አሲዘው ከአበዳሪ ድርጅቶች ከገንዘብ አበዳሪ ተቋማት እና ከገንዘብ አበዳሪ ግለሰብ ገንዘብ እንዲበደሩ፣ ገንዘብ
እንዲያበድሩ፣ መንግስታዊ ክፍያዎችእንዲከፍሉ ማስረጃ እንዲሰጡ እና እንዲቀበሉ፣ ኢንሹራንስ እንዲገቡ ከኢንሹራንስ ጋር ውል እንዲዋዋሉ፣ ሰነድ ላይ
እንዲፈርሙ ክፍያዎች እንዲከፍሉና እንዲቀበሉ ፣ ምትክ ቦታ እንዲረከቡልኝ ካሳ እንዲቀበሉልኝ ከመንግስት አካልም ሆነ ከግለሰብ እንዲቀበሉልኝ
ከመንግስት አካልም ሆነ ከግለሰብ እንዲሁም ከግል ድርጅት ማግኘት የሚገባኝን ማንኛውንም ገንዘብም ሆነ ጥቅማ ጥቅም አስፈላጊውን ፎርማቲ
አሟልተው ውል በመዋዋል እንዲቀበሉልኝ፡፡ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ /ቤት ጋር ያለኝን ማንኛውምን ጉዳይ እንዲፈጼሙ እንዲያስፈጽሙ፣ እንደኔ ተጠሪ
እንዲሆኑ በስሜ ማንኛውንም እቁብ እንዲገቡ ተሳስበው ድርሻዬን እንዲቀበሉ ማንኛውምን ውል እንዲዋዋሉ፣ ሰነድ ፈርመው እንዲቀበሉ፣ የስምምነት
ውል እንዲዋዋሉ ሰነድ እንዲፈርሙ፣ ማንኛውም ኢዩጲያ ካሉ ባንኮች የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ፣ እንዲያንቀሳቅሱ የውጭ ምንዛሬ እንዲያስፈቅዱ ፣
እንዲመነዝሩ፣ ሰነድ እንዲፈርሙ፣ ገንዘብ እንዲከፍሉና እንዲቀበሉ፣ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልተው የጡረታ ገንዘብ (ፕሮቪደንት ፈንድ) እንዲቀበሉ፣
በስሜ ኩባንያ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እንዲያቋቁሙ ቃለ ጉባኤ ላይ እንዲፈርሙ ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሾሙ የዋና የስራ አስኪያጅን የስራ
ዘመን እንዲያራዝሙ ስብሰባ እንዲሰበስቡ የመመስረቻ ጽሁፍና የመተዳሪያ ደንብ እንዲፈርሙ አክሲዬን እንዲገቡ ፣ እንዲገዙ በማንኛውም አክሲዬንም ሆነ
ኩባንያ ያለኝን ድርሻዬን እንዲቀበሉ፣ እንዲያስተላልፉ፣ እንዲሸጡ፣ እንዲለውጡ፣ ስም እንዲያዞሩ፣ ተጨማሪ አክሲዬኖች እንዲገዙ፣ የጨረታ ሰነድ
እንዲገዙ ጨረታ እንዲጫረቱ፣ ተመላሽ ሂሳብ እንዲቀበሉ የውጭ ጉዳይ ማህተም እንዲያስመቱ፣ በክ/ከተማ ቀርበው ማንኛውንም ጉዳይ እንዲፈጽሙና
እንዲያስፈጽሙ፣ ማንኛውንም የት/ት ማስረጃ እንዲያወጡ፣ እንዲያረጋግጡ፣ ከማንኛውም ዩንቨርስቲ ዶክመንት አውጥተው እንዲልኩልኝ በአጠቃላይ
በመንግስታዊ መ/ቤትም ሆነ ህዝባዊ ድርጅቶች፣ የግል መ /ቤቶች አስተዳደር መ/ቤት በቴሌኮም ኮርፖሬሽን ሙባይል መምሪያ ፣ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን፣
በፖስታ ቤት፣ በውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን፣ በኢምባሲዎች፣ በኢምግሬሽን መ /ቤት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣ በገቢዎችና ጉምሩክ በመንገድ ትራንስፖርት
በቀበሌ በክ/ከተማ በወረዳ በሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር በማህበራዊ ዋስትና ባለስልጣን መ /ቤት በኢትዩጲያ ልማት ባንክ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ
ቤቶች ኤጀንሲ ኪራይ ቤቶች በፖሊስ ጣቢያ በማዘጋጃ ቤት በመሬት አስተዳደር ያለኝን ጉዳዬች እኔ ቀርቤ መፈጸም እና ማስፈጸም የሚገባኝን ጉዳዬች
ተከታትለው እንዲፈጽሙና እንዲያስፈጽሙ በ 20/80 በ 40/60/በማህበራት/ ኮንዶሚኒየም ቤት እንዲመዘግቡ ፎርሞችን እንዲሞሉ በእጣ የሚደርሰኝን
ኮንዶሚኒየም በእጣ የሚደርሰኝን መኖሪያ ቤት በፊርማቸው እንዲረከቡ ቁልፍ እንዲቀበሉ፣ ውል እንዲዋዋሉ፣ ገንዘብ ከኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ጋር
ኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤት የብድር ውል ስምምነት እንዲያደርጉ የብድር ውል ላይ እንዲፈርሙ ከቤቶች ኤጀንሲ ጋር ውል እንዲፈጽሙ
የኮንዶሚኒየም ውል ባቋርጥ የባንክ ሂሳብ አዘግተው ሂሳብ ወጪ እንዲያደርጉ በምከሰስበትም ሆነ በምከስበትም ማንኛውም ጉዳይ ቢችሉ ራሳቸው ካልቻሉ
የህግ ጠበቃ ወክለው እንዲከራከሩ መልስ እንዲሰጡ፣ ቃለ መሀላ እንዲያቀርቡ፣ አፈጻጸም እንዲከታተሉ ማረጋገጫ እንዲፈርሙ ይግባኝ እንዲጠይቁ ውሳኔ
እንዲያስወስኑ ይግባኝ እንዲያወጡ እንዲያስገቡ ለሚመለከተው ክፍል እንዲያስተላልፉ እንዲሁም በፍርድ በውርስም በስጦታ የሚሰጠኝም ሆነ
የሚደርሰኝን የሚንቀሳቀስ ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሆነ ገንዘብ እንዲቀበሉ፣ እንዲሸጡ፣ እንዲለውጡ ውል እንዲዋዋሉ፣ የሽርክና ውል እንዲዋዋሉ፣
አስፈላጊ ሲሆን ሶስተኛ ወገን መወከልም ሆነ መሻር እንዲችሉ ይህንን ሙሉ የውክልና ስልጣን በፍ /ብ/ሕግ ቁ 2204/2205 በፍ/ስ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 58 መሰረት
መስጠቴን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡

የወካይ ፊርማ -----------------------

You might also like