You are on page 1of 113

ቀን ------------------------------

በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት
ለሰበር ሰሚ ችሎት
አዲስ አበባ ፣
አመልካቾች፡- 1 ኛ. ተሾመ እንዳለ
2 ኛ. ላምሮት እንዳለ
3 ኛ. አብርሃም /አለማየሁ/ እንዳለ
አድራሻችን፡- ደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ወ/ገነት ወረዳ ኬላ 01 ቀበሌ
ተጠሪ፡- ወ/ሮ መሠለች እንዳለ
አድራሻችን፡- ደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ወ/ገነት ወረዳ ኬላ 01 ቀበሌ
- የሥር የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 2944
- የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 29721
- የደቡብ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መ/ቁጥር 60069
በፌዴራል አዋጅ ቁጥር 25/88 መሠረት የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው፡፡
ሀ/ የአቤቱታው አቀራረብ
- የሰበር አቤቱታው የቀረበበትን የመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የደቡብ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 60069 በቀን 07/02/2006 በዋለው ችሎት ነው፡፡
- ከፍ/ቤቱ የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በወንዶገነት ወረዳ ኬላ ማዘጋጃ ቤት በኩል ሊደርሳት ይችላል፡፡
- የስር ፍ/ቤት የውሳኔ መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ --- ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ/ ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው ሟች ወላጅ እናታችን ወ/ሮ አስናቀች በየነ በወንዶ ገነት
ወረዳ ኬላ 01 ቀበሌ ውስጥ በግል ጥረቷ ስፋቱ 292 x 80 የሆነ ስፋት ባለው ይዞታ ላይ አንድ ሦስት ክፍል
ያለው ትልቅ ቤትና አንድ ኩሽና ቤት በመስራት ከእንሰት ጀምሮ የተለያዩ አትክልቶችን ጭምር በመትከል
ለመንግሥት የሚገባውን ሕጋዊ ግብር በስሟ በመገበር እየተጠቀመች ሳለ ባደረባት ህመም ከዛሬ 27
ዓመታት በፊት በሞት ስትለይ የአንደኛ አመልካች እድሜ 6 ዓመት የሁለተኛ አመልካች ዕድሜ 4 ዓመት
የ 3 ኛ አመልካች ደግሞ አንድ ዓመት ስንሆን ከላይ በስም ተጠቃሽ የሆነችው የእናታችን ልጅ እህታችን
በወቅቱ ለአቅመ ሔዋን የደረሰች ስለነበረ በሟች እናታችን ቦታ ተተክታ ለአቅመ አዳምና ሔዋን
እስክንደርስ የጋራ የውርስ ሀብት በሆነው በእናታችን ቤት አሳድጋን 2 ኛ አመልካችም ከዚሁ ቤት ውስጥ
ተድራ የውርስ ሀብቱ ክፍፍል ሳይደረግና ሳይነጣጠል በስምምነት ካቆየነውና ለዘመናት ከኖርንበት ቤት ውስጥ
ሁከት ያነሱብኝ ስለሆነ ሁከት

ይወገድልኝ ስትል ያቀረበችውን ተቀብሎ የተመለከተው የስር የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት ተጠሪ በአቤቱታ ላይ ገልፃ
ከማቅረብ ውጪ የተፈጠረ ሁከት ስለመኖሩ ባቀረበቻቸው ማስረጆቿ እንኳን ባልተመሰከረበትና ባቀረብነው
የመ/ምስክሮቻችን የፈጠርነው ሁከት አለመኖሩ ተገልፆ ከመመስከሩ በተጨማሪ በሟች ወ/እናታችን የጋራ
የውርስ ሀብት በሆነው የፈጠርነው ሁከት አለመኖሩን ተገልፆ የተጠሪ ምስክሮች ጭምር ደግፈውን
የሰጡትን የምስክርነት ቃል ተቀባይነት በማሳጣት ሁከት ይወገድ ተብሎ ከጋራ የውርስ ቤት ውስጥ
እንድንወጣ የተሰጠውን አሳዛኝ ፍርድ በይግባኝ የተመለከተው የሲ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ለማጣራት ያደረገው
አንዳች ጥረት ሳይኖር አፅንቶ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት መሆኑን በመግለፅ ለደቡብ
ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ብናቀርብም ለማጣራት የተደረገ ጥረት ሳይኖር ፀንቶ በመወሰኑ
ፍርዱን ለማስለወጥ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው፡፡
ሐ) በሥር ፍ/ቤቶች የተፈፀመ መሠረታዊ የሕግ ስህተትና እንዲታረምልን
የምንጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ
1. ሁከት ተፈጠረበት በተባለው የጋራ የውርስ ሀብት በሆነው ቤት ላይ የሥር ከሣሽ በአሁኗ ተጠሪ ምስክሮች
ጭምር ሁከት አለመፍጠራችንና በስምምነት ክፍፍል ሳናደርግ አብረን መቆየታችንን በመግለፅ ደግፈውን
የመሰከሩ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ባቀረብነው የሰው የመከላከያ ምስክሮች ሁከት ተፈጠረብኝ ተብሎ
በተጠሪ በቀረበው የጋራ የውርስ ሀብት ውስጥ ተወልደን እናታችን በሞት ስትለይ በተጠሪ እህታችን እጅ
ያደግን ሲሆን 2 ኛ አመልካች በዚሁ ቤት ተድራ በትዳር ምክንያት ከቤት ብትወጣም በስምምነት 1 ኛ እና
3 ኛ አመልካቾች አብረን ያለን መሆናችን ከበቂ በላይ በማስረገጥ ያደረግነውን ክርክርና የተሰጠውን
የምስክርነት ቃል ተቀባይነት በማሳጣት ተጠሪ በግሏ የስም ዝውውር አድርጋ በስሟ ሳታዞርና ካርታ ፕላን
በስሟ በማሠራት ለዘመናት ይዛ እንደቆየችና የግል ንብረቷ እንደሆነ ተቆጥሮ ከጋራ የውርስ ሀብታችን ቤት
ውስጥ እንድንወጣ መደረጉ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ በእራሷ ማስረጆች ጭምር በስምምነት በአንድ
ቤት የቆየን መሆናችንና የፈጠርነውም ሁከት አለመኖሩን ተገልፆ የተሰጠውን የምስክርነት ወደ ጎን በመተው
የተሰጠውን ፍርድ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች ለማረም ያደረጉት አንዳች ጥረት ሳይኖር ማፅናቱ መሠረታዊ
የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በጥልቀት ታይቶ እንዲታረምልን፡፡
በተጨማሪ አንድ ተከራካሪ ተገቢነት ያለው የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ አቅርቧል ለማለት ለክርክሩ
መንስዔ የሆነው ንብረት በእጁ አድርጎ መገኘትና በዚሁ ንብረት ላይ በእውነት ለማዘዝ እንድችል የንብረቱ
አያያዝ ያልተጭበረበረ መሆን እንዳለበት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1140፣1149 (1) በመጥቀስ በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 9 በመ/ቁጥር 36645 ላይ ከገጽ 32 – 34 እንዲሁም በጉልበት ገብተው አልወጣም
አሉኝ በማለት ሁከት ይወገድልኝ ተብሎ በሥር ፍ/ቤት የቀረበው ክስ ሁከት ይወገድልኝ ሳይሆን

የመፋለም ክስ መሆን እንዳለበት በዚሁ ቅፅ በመ/ቁጥር 42861 ከገፅ 268 - 269 ላይ የሕግ ትርጉም ከተሰጠበት
የሕግ ድንጋጌ ውጪ በመሆን የተሰጠ ፍርድ ነው በተጨማሪም ለትክክለኛው ፍትህ ሲባል
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 91 መሰረት ከፍርድ በፊት ክሱ ሁከት ይወገድልኝ ሳይሆን የመፋለም ክስ መሆኑን
በመግለፅ ተሻሽሎ እንዲቀርብ መደረግ ሲገባው በሁከት ይወገድ ሊታይ የማይገባውን በማየት የተሰጠ ፍርድ
አለመታረሙ ስህተት ነው፡፡
2. በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1149(1) መሰረት የሚቀርብ የሁከት ይወገድልኝ ጥያቄ /ክስ/ መስተናገድ ያለበት ጥያቄ
አቅራቢው ‹‹ሁከት ይወገድልኝ›› ያለበትን ይዞታ(ቤት) በእጁ አድርጎ የሚያዝበትና በፍ/ብ/ህግ/ቁጥር 1195
(1) መሰረት ደግሞ የይዞታ ማረጋገጫ የባለይዞታነት የምስክር ወረቀት ወይንም በስሙ ያለውን
(የተሰራውን) የቤቱን ካርታ ፕላን አያይዞ ሲያቀርብ ብቻ መስተናገድ ያለበት ከመሆኑም በተጨማሪ
አመልካቾች ወ/እናታችን በሞት ስትለይ መብታችንን ማስከበር የማንችል ሕፃናትና በሥር ከሣሽ በአሁኗ
ተጠሪ ታላቅ እህታችን እጅ ስር ባለንበት ጊዜ ከሟች ወይም ከጋራ አውራሽ እናታችን ስም ይገበር
የነበረውን ወደ እራሷ በማዞር ለተወሰነ ጊዜ በስሟ ስለገበረች በጋራ ከምንኖርበት ከውርስ ሀብት ቤት ውስጥ
ከቅን ልቦና ውጪ በመሆን ለማስወጣት ያቀረበችው መሆኑን በመግለፅ ያደረግነውን ክርክር ተቀባይነት
በማሳጣት የተሰጠ ፍርድ አለመታረሙ ስህተት ነው፡፡
በአጠቃላይ ሁከት ፈጠራችሁ በሚል ለዘመናት ከኖርንበት ከሟች ወ/እናታችን ቤት ለቀን እንድንወጣ
እየተወሰነ በሌላ በኩል ውሳኔው የውርስ ጥያቄ ማቅረብ እንደማያግደን ተጠቅሶ የተሰጠው ውሳኔ እርስ በርሱ
የሚጋጭና በየትኛውም የሰው ማስረጃ ሁከት መፍጠራችን አልተመሰከረም በሌላ በኩል እናታችን በሞት
የተለየችው ከ 27 ዓመታት በፊት ሲሆን ተጠሪ ወራሽነቷን ያረጋገጠችው ደግሞ በመ/ቁጥር 2971 በቀን
24/7/2005 ዓ/ም ክሱን ባቀረበችብን ወቅት ነው፡፡ ይሔ ማለት ደግሞ ወራሽነቷን በሕጉ በተመለከተው ጊዜ
ገደብ ውስጥ በማረጋገጥ በስሟ ካርታ ፕላን አሰርታ በግሏ ይዛ ባልቆየችበት በጋራ ሀብታችን የተሰጠው
የሁከት ይወገድ ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) መሰረት የስር
ፍ/ቤቶች ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተሽሮ እንዲወሰንልን በአክብሮት እናመለክታለን፡፡
ቀን -------------------ዓ.ም
በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት
ለሰበር ሰሚ ችሎት
አዲስ አበባ ፣
አመልካች ፡- ታረቀኝ ጥሩነህ
አድራሻ ፡- ደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ሀዋሣ ከተማ ምስ/ክ/ከተማ ቴሶ ቀበሌ
ተጠሪ ፡- ወ/ሮ ሰናይት መለሠ
አድራሻ ፡- ደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ሀዋሣ ከተማ ምስ/ክ/ከተማ ቴሶ ቀበሌ
- የሥር የምስራቅ አካባቢ ምድብ ችሎት መ/ቁጥር 906/05
- የሀዋሣ ከተማ ከ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 14065
- የደቡብ ክ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መ/ቁጥር 59978
በፌዴራል አዋጅ ቁጥር 25/88 መሠረት የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው፡፡
ሀ/ የአቤቱታው አቀራረብ
- የሰበር አቤቱታው የቀረበበትን የመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የደቡብ ክ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 59978 በቀን 15/2/06 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በተጠሪ ጠበቃ አማካኝነት ወይም በአድራሻዋ በኩል ሊደርሳት
ይችላል፡፡
- የስር ፍ/ቤቶች መዝገብ የውሳኔ ትክክለኛ ቅጂ --- ገፅ ተያይዞ ቀርቧል፡፡
ለ/ ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የሰበር አቤቱታ ለዚህ ፍ/ቤት ሊቀርብ የቻለው ተጠሪ ከሆነችው ባለቤቴ ጋር የነበረን ጋብቻ በፍርድ የፍቺ
ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የፍቺ ውጤት የሆነውን የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ቀርቦለት የተመለከተው የምስራቅ አካባቢ
ምድብ ችሎት ቀደም ሲል ከተጠሪ በፊት ከነበረችው ባለቤቴ ወ/ሮ ሽቶ ደሣለኝ ጋር የነበረን ጋብቻ በፍርድ
ውሳኔ ተሰጥቶ የጋራ ንብረታችንን በፍርድ ተከፋፍለን የያዝኩትን የግል ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን የአሁኗ
ተጠሪ በ 1 ዓመት የትዳር ቆይታ ዘመኗ ውስጥ ያፈራሁት የጋራ ንብረቴ ስትል ዘርዝራ ያቀረበቻቸው ንብረቶች
በየካቲት 19/2003 ዓ.ም ባደረግነው የጋብቻ የውል ስምምነት ላይ ባልተገለፀበትና ከጋብቻ በፊት የተፈራው
ንብረት የጋራ ባልተባለበት በሀዋሳ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 12966 ላይ በግልፅ ተዘርዝሮ ከቀረበው ላይ
በክፍፍል የደረሰኝንና ከመ/ሰጪ በፊት በራሴ አካውንት ቁጥር ሀዋሣ ዳሽን ባንክ አላሙራ ቅርንጫፍ
ያስቀመጥኩትን ገንዘብ ስቴትመንት ሳይቀርብ እንዲሁም በጋብቻ ከመጣመራችን በፊትም ይሁን በኋላ
የሌለኝንና ያልገዛሁትን ባለሦስት እግር ባጃጅ የባጃጅ ባለቤት ስለመሆኔ የሚያረጋግጥ የባለቤትነት ማረጋገጫ
ሰነድም ይሁን ሌላ ተረጋግጦ የቀረበ ሰነድ በሌለበት የሌለንና በቆይታዋ ወቅት ያላፈራችውን እንዳፈራች ተደርጎ
ክፍፍል እንዲደረግ የተሰጠ ውሳኔ ከመሆኑም በተጨማሪ ተጠሪ በሌለሁበት ከቤቴ ይዛ የተሰወረችውን ገንዘብና
ከቤቴ ከወጣች በኋላ በአብሲኒያ ባንክ ሀዋሣ ቅርንጫፍ በተጠሪ ስም የተቀመጠውን የጋራ ገንዘብ ብር 34,000
እና በመ/ሰጪ ስም በሀዋሣ ከተማ ም/ክ/ከተማ ቴሶ ቀበሌ ውስጥ በወ/ሮ እቴነሽ ሰብሳቢነት በ 1 ዕጣ በቀን 10
ብር በ 2 ዕጣ በሳምንት 140 ሲጣል የነበረውን ከሰብሳቢዋ እጅ የሶስት ወር ገንዘብ ብር

2,940 ከወሰደችው ውስጥ ድርሻዬን ብር 1470 እንዲከትከፍለኝ እንዲሁም በሀዋሣ ከተማ በሐይቅ ዳር ክ/ከተማ
ገበያ ዳር በወ/ሮ ሀና ሰብሳቢነት በሳምንት 320 x በ 63 ዕጣ ብር 20,180 ወስዳ ለግሏ ከተጠቀመችው የጋራ
ገንዘብ ውስጥ ድርሻዬን ብር 10,090(አሥር ሺህ ዘጠና ብር) በተጨማሪም በትዳር አብረን በነበርንበት ጊዜ ወ/ሮ
ሰላም ተብላ ከምትጠራዋ አንዲት ሴት 9 ግራም የአንገት ወርቅ ሀብል በመያዣነት በመያዝ ከጋራ ገንዘባችን ብር
3,000 ካበደረች በኋላ የወሰደችውን ግማሹን ብር 1500 በድምሩ ከጋራ ገንዘባችን ድርሻዬን እንድትከፍለኝ
እንዲወሰንልን ያቀረብኩትን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ጭምር በሕግ አግባብ ሳይጣራ በዝምታ መታለፉን በመግለፅ
የተሰጠውን ውሳኔ ለማሳረም በደረጃው ላሉ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች ባቀርብም ለማጣራት የተደረገ አንዳች
ጥረት ሳይኖር ታልፎ የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ፍርዱን ለማስለወጥ የቀረበ
የሰበር አቤቱታ ነው፡፡
ሐ/ በሥር ፍ/ቤቶች የተፈፀመና እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ
1. የደቡብ ክልል የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 101 እና 102 ላይ በግልፅ በተደነገገው የሕግ ድንጋጌ መሰረት ባልና ሚስቱ
በጋራ ያፈሯቸውን ንብረቶች እኩል በዓይነት ሊከፋፈሉ እንደሚችሉ ከተደነገገው ድንጋጌ ውጪ ቀደም ሲል
ከተጠሪ በፊት ከነበረችው ባለቤቴ ጋር በመ/ቁጥር 12966 ላይ በክፍፍል ያገኘሁትን ቁሳቁሶች በሙሉ ተጠሪ
እንድትካፈል የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ ከቀድሞ ባለቤቴ በክፍፍል ያገኘሁት የግል
ንብረቴ ስለመሆኑ ክፍፍል የተደረገበት የመ/ቁጥር 12966 በግልፅ እያስረዳ ወይንም ከተጠሪ ጋር በነበረን የጋብቻ
ውላችን ላይ የጋራ ተብሎ ባልተገለፀበት ተጠሪና ቤተሰቦቿ የሰጡትን ቃል ብቻ መነሻ በማድረግ ከልጅነት እስከ
እውቀት ያፈራሁት ንብረት በነበራት በአንድ አመት የቆይታ ጊዜ ውስጥ በጋራ እንዳፈራች ተደርጎ የተሰጠው
አሳዛኝ ፍርድ ሳይታረም አፅንቶ መወሰኑ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሊታረም የሚገባው ነው፡፡
2. ከተጠሪ በፊት ከነበረችው ባለቤቴ ወ/ሮ ሽቶ ደሣለኝ ጋር በፍርድ ተካፍዬ ካገኘሁት የግል ንብረቴ ጋር በቤቴ
የሌለውን ባለሦስት እግር ባጃጅ ተካፋይ እንድትሆን የተሰጠ አስገራሚ ፍርድ ከመሆኑም በተጨማሪ
ስለተንቀሳቃሽ ተሸከርካሪዎች ሊቭሬ ባለቤትነትና የልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ተሸከርካሪዎች ባለሃብትነት
የመኪና ፣የማሽን፣ የሞተር ሳይክልና ወዘተ የመሳሰሉት በተገቢው ሕጋዊ አካል በሚሰጡ አካል ሰነዶች ብቻ
መረጋገጥ የሚገባ ከመሆኑም በላይ ባላሦስት እግር ባጃጅ ተሸከርካሪ እንደመሆኑ መጠን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር
1186(2) እና የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 360/67 አንቀፅ 4 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 107/69 መሰረት
ባለሀብቱ ባለደብተሩ ነው ይሁንና በክፍፍል ውስጥ የተካተተው የሠሌዳ ቁጥር ደህ 1420 ባለሦስት እግር ባጃጅ
የሌለኝና ግዥ የተፈፀመበት ሰነድ እንኳን መቅረብ ባልቻለበት እንዲሁም ከሀዋሣ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት
ጭምር የእኔ ስለመሆኑ መግለጫ ባልተገኘበት ሲያሽከረክር አይተነዋል በሚል በተሰጠ የሐሰት የምስክርነት ቃል
ክፍፍል ውስጥ የተካተተበት አግባብ ሳይጣራ መታለፉ

በሕግ ላይ ያለኝን ከፍተኛ እምነት ያዛባ መሆኑን በመግለፅ እንዲታረምልኝ ያቀረብኩት አቤቱታ ሳይታይ
ማፅናቱ አግባብ ባለመሆኑ ተጣርቶ የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ እንዲወሰንልኝ ፡፡
3. ተጠሪ በ 2/7/04 ከቤቴ ብር 25.000 ይዛ መሰወሯን ለሀዋሣ ከተማ ምስ/ክ/ከተማ ቴሶ ቀበሌ በእለት ሁኔታ
ስለማስመዝገቤ ማስረጃ የቀረበ ከመሆኑም በተጨማሪ ከቤቴ ከወጣች በኋላ አብሲኒያ ባንክ ሀዋሣ ቅርንጫፍ
በተጠሪ ስም ያስቀመጥነውን ገንዘብ ብር 34,000 አውጥታ ለግል ጥቅም ማዋሏን ከባንኩ እስቴትመንት መረጃ
በማስቀረብ ለደረሰኝ የሚገባውን ድርሻዬ እንዲሁም ከቤተ ይዛ ወጣችውን ባቀረብኳቸው የሰው ማስረጃዎች
ያስረዳሁት ብር 25.000 ግማሹን ፣ በሀዋሣ ከተማ ም/ክ/ከተማ ቴሶ ቀበሌ በወ/ሮ እቴነሽ ቤት በ 2 ዕጣ
ባለስምንት ብር 140 ሲጣል የነበረውንና በሰብሳቢዋ እጅ የተቀመጠ የ 3 ወር ገንዘብ ብር 2,940 ግማሹን
እንዲሁም በሀዋሣ ከተማ በሐይቅ ዳር ክ/ከተማ ገበያ ዳር በወ/ሮ ሀና ሰብሳቢነት በሳምንት ብር 320 x በ 63
ዕጣ ብር 2018 ወስዳ ለግል ጥቅሟ ያዋለች በመሆኑ በአጠቃላይ በግሌ የሚደርሰኝን ድርሻ ገንዘብ 42,560
(አርባ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ስድሳ ብር) እንዲከፍለኝ ያቀረብኩትን የተከሳሽ ከሣሽነት ክሴን ያለበቂ
ምክንያት ተቀባይነት በማሳጣት የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት እንኳን ለማጣራት የተደረገ ጥረት ሳይኖር
አፅንቶ መወሰኑ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሊታረም የሚገባው ነው፡፡
4. የተከበረውን ፍ/ቤት የምጠይቀው ዳኝነት
- ተጠሪ ትካፈል የተባለው ቁሳቁስ ቀደም ሲል ከነበረችው ባለቤቴ ወ/ሮ ሽቶ ደሣለኝ ጋር በሀዋሣ ከተማ
የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 12966 ላይ ክፍፍል ተደርጎ ያገኘሁት የግል ንብረቴ ስለመሆኑ መዝገቡ የሚያስረዳ
ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145 በትዕዛዝ በማስቀረብ ተጣርቶ እንዲወሰንልኝ ያቀረብኩት አቤቱታ
መታለፉ ስህተት በመሆኑ እንዲታረምልኝ፡፡
- ባለሦስት እግር ባጃጅ የተባለው የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊቭሬ ደብተርም ሆነ ግዥ የተፈፀመበት ሰነድ
ባልቀረበበት ሲነዳ አይተነዋል በሚል በሐሰት ምስክርነት የሌለን ንብረት በክፍፍል ውስጥ እንዲካተት ተደርጎ
የተሰጠው ውሳኔ ሳይታረም ማፅናቱ ከፍተኛ የህግ ግድፈት ስለሆነ እንዲሻርልኝ፣
- ከተጠሪ በ 2/7/04 ዓ.ም ስለመውጣቷ ከም/ክ/ከተማ ቴሶ ቀበሌ ማረጋገጫ በትዕዛዝ የቀረበ ከመሆኑም በተጨማሪ
ከቤቴ ከወጣች በኋላ ከአብሲኒያ ባንክ ያወጣችውን ገንዘብ ብር 34,000 ለጋራ ጥቅም አዋሉ ተብሎ የተሰጠው
ውሳኔ አግባብነት በጥልቀት ተጣርቶ ድርሻዬን እንድትከፍለኝ ያቀረብኩት ታልፎ የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት
ሳይጣራ ማፅናቱ አግባብ ባለመሆኑ በጥልቀት ታይቶና ተጣርቶ እንዲሻርልኝ ፣
በአጠቃላይ የግል ንብረቴን ያለአግባብ ተጠሪ እንድትካፈል የሰጠው ውሳኔ አግባብ ባለመሆኑ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) መሠረት ሙሉ በሙሉ በመሻር ከጋራ ንብረታችን ለግል ጥቅሟ አውላ
የቀረውን ብር 42,560 እንድትከፍለኝ ያቀረብኩትን የአመልካች ክስ ውድቅ የተደረገበትን አግባብ ሳይጣራ
መወሰኑ አግባብ ባለመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ያስተላለፉትን ውሳኔ በመሻር እንደአቤቱታ አቀራረቤ
እንድትከፍለኝ እንዲወሰንልኝ ስል አመለክታለሁ፡፡
አመልካች ታረቀኝ ጥሩነህ
ቀን 30/01/2006
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት
ለሰበር ሰሚ ችሎት
ሀዋሣ ፣
አመልካቾች ፡- 1 ኛ. ቱንጌሳ ቱንቡሎ
2 ኛ. ሁሬሳ ቱንቡሎ
አድራሻችን፡- ሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ ጋራሃ ሪቃታ ቀበሌ
ተጠሪዎች፡- 1 ኛ. ጋሮ ቱንቡሎ አድራሻ ሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ ጋራሃ ሪቃታ ቀበሌ
2 ኛ. ወ/ሮ አስቴር ድማ አድራሻ ፡- ሸበዲኖ ወረዳ ጋራጋልኦ ቀበሌ
- የሥር የሀዌላ ቱላ የመጀ/ደ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 06421
- የሀዋሣ ከፍ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር
በክልሉ አዋጅ ቁጥር 43/1994 መሠረት የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው፡፡
ሀ) የአቤቱታው አቀራረብ
 የሰበር አቤቱታው የቀረበበትን የመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የሀዋሣ ከፍ/ፍ/ቤት ነው፡፡
 ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 14490 በቀን 27/1/2006 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
 ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በተጠሪዎች አድራሻ በቀበሌ በኩል ሊደርሳቸው ይችላል፡፡
 የሥር ፍ/ቤቶች የውሳኔ መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ 83 ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ) ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው የሟች ወላጅ አባታችን ንብረት የሆነውና በቱላ
ክ/ከተማ ጋራሃ ሪቃታ ቀበሌ ውስጥ በስተሰሜን ለአቶ ደዋላ ዳላቻ በስተደቡብ ለአቶ ታከለ ታባሮ
በስተምስራቅ ለአቶ መኮና ጆፌ በስተምዕራብ ለአቶ ሽታዬ ዶንጋሞ ከሚያዋስነው የእርሻ ይዞታ ውጪ
ያለውን ከአባታችን ሞት በኋላ የአመልካቾች ወላጅ እናት፣ የ 1 ኛ ተጠሪ ወላጅ እናት እና በሥር ፍ/ቤት ጣልቃ
ገብ የሆነችው 2 ኛ ተጠሪ 3 ቱም ሴቶች የሟች አባታችን ሕጋዊ ሚስቶች ስለነበሩ በአካባቢ ሽማግሌ
ለ 3 ቱም እኩል ክፍፍል ተደርጎ በሟች ወላጅ እናታችን እግር ተተክተን ተካፍለን የቀረውና ክርክር ያስነሳው
በይደር ክፍፍል ሳይደረግ በአባታችን ስም እየተገበረ የቆየውን የጋራ የውርስ ሀብት የሆነውን እንደቀድመው
በስምምነት ሽማግሌዎች ክፍፍል ሊያደርጉ ሲሉ የአሁኑ 1 ኛ ተጠሪ ሟች በሕይወት በነበረ ጊዜ ኮንትራት
ወስጄ ተሠርቶ የሚገኘውን እኩል እየተጋራን የነበረና ይዤ ያቆየሁት ነው ሲል ለክፍፍሉ ፈቃደኛ ባለመሆኑ
በመጀመሪያ ደረጃ ጉዳዩን አይቶ ውሳኔ በሰጠው ፍ/ቤት የውርስ ንብረት ተጣርቶ ክፍፍል እንዲደረግልን
ባቀረብነው አቤቱታ መሠረት 2 ኛ ተጠሪ ይዞታውን ሟች በሕይወት በነበረ ጊዜ የሰጠኝ ለእኔ በመሆኑ ክፍፍል
ሊደረግ አይገባም ስትል መቃወሚያ በማቅረቧ ከ 3 ታችን ተከራካሪ ወገን የተውጣጡ ሽማግሌዎችና ከፍ/ቤት
የተወከለ ሰው ባለበት የውርስ ንብረቱ ተጣርቶ የተያዘውን ሪፖርት ሳይነበብ የመረጥናቸው ሽማግሌዎች
አንብበው መረዳት የማይችሉትን ፊርማው ሲከናወን ተከራካሪዎች ከስፍራው ዞር እንድንል ተደርጎ
ለተጠሪዎች ተመቻችቶ በተሰራው ሪፖርት ያስፈረሟቸው ከመሆኑም በተጨማሪ ሪፖርቱን አይተን አንብበን
እንድንፈርምበት እድሉ ሳይጠን ተዘጋጅቶ ለፍ/ቤቱ ከቀረበ በኋላም ሪፖርቱ ኮፒ ተሰጥቶን አስተያየት
እንድንሰጥበት በተደጋጋሚ በችሎት ያቀረብነውን ጥያቄ ተቀባይነት

በማሳጣት 1 ኛ ተጠሪ ወንድማችንም ይሁን 2 ኛ ተጠሪ የእንጀራ እናታችን ከሟች የተሰጣቸው ልዩ ኑዛዜ
በሌለበትና ከውርስ ሳንነቀል የሟች አባታችን የውርስ ንብረት ከሆነው በከፊል ተካፋይ እንድንሆን ተደርጎ
የተቀረውን ተጠሪዎች ብቻ ይዘው እንዲጠቀሙ የተሰጠውን አሳዛኝ ፍርድ ለማስለወጥ ይግባኝ ሰሚ ለሆነው
ፍ/ቤት አቤቱታ ብናቀርብም ለማጣራት የተደረገ ጥረት ሳይኖር አፅንቶ በመወሰኑ መሠረታዊ የሕግ
ስህተቶችን በመዘርዝር ፍርዱን ለማስለወጥ የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡
ሐ) በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልን የምንጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ
1 ኛ) ክርክር ያስነሳው የውርስ ንብረት ከተከራካሪ ወገኖች በተውጣጡ ሽማግሌዎችና ከፍ/ቤቱ የተወከለው ሰው
ባለበት በተጣራ ጊዜ የሟች ወላጅ አባታችን መሆኑ ያልተካሄደና በሌላ በማናቸውም መልኩ ተላልፎ
የተሰጣቸው ወይም እንደ 1 ኛ ተጠሪ አባባል አባታችን በሕይወት በነበረ ጊዜ በኮንትራት ተቀብሎ በጋራ እየሰራ
መሆኑን የምገልፅ ማስረጃ አልቀረበም በተጨማሪም ክርክር ካስነሳው ይዞታ ውጪ የነበረውን የጋራ የውርስ
ሀብት በስምምነት በሽማግሌ ለ 3 ቱ የሟች ሚስቶች ክፍፍል ተደርጎ የክርክሩ አካል የሆነውን በቀጣዩ ጊዜ
ክፍፍል እንደምደረግ በሽማግሌ ስገለፅ ተስማምተው ከመለየት ያለፈ የተነሳ ተቃውሞ በሌለበትና
በፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1060 መሰረት የውርስ ሀብት አካል የሆነው በሕግ ክፍፍል ተደርጎ የየድርሻ እስካልተለየና
አከፋፈሉም እስካልተፈፀመ ድረስ ውርሱ በወራሾች መካከል ሳይነጣጠል የጋራ የውርስ ሀብት ሆኖ እንደምቆይ
ከተደነገገው የሕግ ድንጋጌ ውጪ ታልፎ የአባታችንን የውርስ ተካፋይ እንዳንሆን በማድረግ ተጠሪዎች ብቻ
ይዘው እንዲቀሩ የተሰጠው ውሳኔ በሕግ ላይ ያለንን ከፍተኛ እምነት ያዛባና መሠረታዊ የሕግ ስህተት
የተፈፀመበት በመሆኑ እንዲታረምልን ፣
2 ኛ) ተጠሪዎች ክርክር ካስነሳው ይዞታ ውጪ ከሌሎች እናታችንን ጨምሮ ከአባታችን ሚስቶች እኩል ተካፍላ
ስታበቃ በስጦታ የተላለፈልኝ ስትል ከመግለፅ ያለፈ አያይዛ ያቀረበችው ሰነድ በሌለበትና እንዲሁም 1 ኛ
ተጠሪም በበኩሉ የተሰጠው የተለየ ኑዛዜ እስከሌለ ድረስ አብላጫው ንብረት ልያገኙ የምችሉበት የሕግ አግባብ
የለም፡፡
በተጨማሪ 2 ኛ ተጠሪ የሚስትነቷን ከሌሎች የአባታችን ሚስቶች ጋር እኩል ከመከፈል ያለፈ ጠቅልላ በውርስ
መልክ ልትወስድ የማትችል ከመሆኑም በላይ በአጣሪ ተጣርቶ ቀረበ የተባለው ሪፖርት ደርሶን የበኩላችንን
አስተያየት ሳንሰጥና ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡት የሰው ማስረጃዎቻችን የሰጡት ቃል በትክክል
ሳይመዘገብ ታልፎ የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ባለመሆኑ የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔን በመሻር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር
343 መሠረት ለክሱ ውጤት የሆነው ጭብጥ ተይዞ መዝገቡ ወደ ሥር ፍ/ቤት ተመልሶ በድጋሚ ንብረቱ
እንዲጣራና ተጣርቶ በሚቀርበው ሪፖርት ላይ የበኩላችንን አስተያየት እንድንሰጥ ጭምር እንዲወስንልን
በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
አመልካቾች 1 ኛ. ቱንጌሳ ቱንቡሎ
2 ኛ. ሁሬሳ ቱንቡሎ
ቀን ------------------------------
ለሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
ይ/ባዮች፡- 1 ኛ. ሀይሉ ኦይቻ አድራሻ ወ/ገነት ወረዳ ዩዎ ቀበሌ
2 ኛ. ባሪሶ ሎልቱ ›› ሲዳማ ማረሚያ ተቋም
3 ኛ. አማኑኤል ሀይሉ ›› ሲዳማ ማረሚያ ተቋም
4 ኛ. ባንዳ ኦይቻ ›› ሲዳማ ማረሚያ ተቋም
5 ኛ. ማርሳ ኦይቻ ›› ›› ›› ››
መ/ሰጪ፡- ዐቃቤ ሕግ
- የሥር የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 3526
በወ/መ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁጥር 189 መሰረት የቀረበ የወንጀል የይግባኝ አቤቱታ
ሀ/ የአቤቱታው አቀራረብ
- የይግባኝ አቤቱታው የቀረበበትን ፍርድ የሰጠው የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በወ/መ/ቁጥር 3526 በቀን 07/01/06 ዓ/ም በዋለው ችሎት የተሰጠ ነው፡፡
- የሥር ፍ/ቤት የውሳኔ ትክክለኛ ቅጂ ------ ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ/ ለይግባኝ አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የወንጀል የይግባኝ አቤቱታው ለዚህ ፍ/ቤት ሊቀርብ የቻለው ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾች የወ/መ/ሕግ/ቁጥር
32(1) (ሀ) 604 ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ በወ/ገነት ወረዳ ዩዎ ቀበሌ ውስጥ እርስ በእርስ ተጋግዘው በ 1 ኛው
ተከሣሽ መሪነት በግል ተበዳይ ነኝ ባይ በጠና ሎልቱ ቤት በሩን በጉልበት ሰብረው ገቡ በማለት የቀረበባቸው ሲሆን
በ 2 ኛው ክስ 1 ኛ እና 3 ኛ ተከሳሾች የኢ/ፌ/ዲ/ሪ/የወ/ሕግ አንቀፅ ቁጥር 32(1) (ሀ) 556 (2) (ሀ) ስር
የተደነገገውን የተላልፈው በ 1 ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በግል ተበዳይ በጠና ሎልቱ ቤት ገብተው
በእጃቸው በያዙት ዱላ ደብድበው ጉዳት አደረሱበት የሚል ነው፡፡ 3 ኛው ክስ አምስቱም ተከሳሾች የአሁኖቹ
ይ/ባዮች የኢ/ፌ/ዲ/ሪ/የወ/ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ) 689 ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ በ 1 ኛ ክስ ላይ በተጠቀሰው
ቀንና ሰዓት የቤት ቁሳቁስ ከጥቅም ውጪ አደረጉ የሚል ነው ፡፡ 4 ኛው ክስ አምሰቱም ይ/ባዮች
የኢ/ፌ/ዲ/የወ/ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ) 713 ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ የተላልፈው እርስ በእርስ በመተጋገዝ
ከላይ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት የግል ተበዳይንና ቤተሰቡን አውጠተው በማባረር ቤት ውስጥ ያሉትን ዕቃዎች 1.
ፍራሽ በብር 2000 የተገዛውን 2. ብርድልብስ በብር 400 የተገዛውን 3 ኛ/ ሁለት አንሶላ በብር 200 የተገዛውን
ቦቆሎ 1 ኩንታል በብር 600 የተገዛውን ቦሎቄ አንድ ኩንታል በብር 1200 የተገዛውን የሴቶች ልብስ ሁለት ሙሉ
ልብስ፣ ሁለት ነጠላ አንድ ሻርብ የሕፃናት ልብስ የወንዶች ልብስ አጠቃላይ ወደ ገንዘብ ቢለወጥ 8000
የሚያወጣውንና ብር 15,000 ከሳጥን ወስደው በመጠቀማቸውና የሰውን ንብረትና ሀብት በጉልበት አወደሙ
ሲል ያቀረበብንን ክስ ፍ/ቤት በመቅረብ የተጠቀሰብንን የወንጀል ድርጊት አለመፈፀማችንን በመግለፅ ክደን
ተከራክረናል፡፡

ዐቃቤ ህግም ያስረዱልኛል ሲል ያቀረባቸው የግል ተበዳይ ነን ባዮችና ቤተሰቦቻቸው ቀርበው በአምስቱም
ይ/ባዮች አንዱ ግለሰብ የግል ተበዳይ ነኝ ባይ መደብደቡንና በክሱ የተጠቀሰውን ንብረት አይነታቸውን በመግለፅና
ማን ምን እንደወሰደ ጭምር በመግለፅ ለዛው ከምሽቱ 2 ሰዓት በአምስት ሰው አንዱ እየተደበደበ በምንገኝበትና
እጅግ አስጨናቂና የሞት ሽረት በሆነበት አደገኛ ሰዓት ላይ እያንዳንዱ ስንት ጊዜ የት ቦታ ላይ እንዳሳረፉበትና
እንደመቱት እንዲሁም የቤት ቁሳቁሱን ዓይነት በመግለፅ የወሰደውን ሰው ጭምር ተገልፆ የተሰጠው አስገራሚ
የምስክርነት ቃል በርካታ ጊዜ ተወስዶ ከፍተኛ ጥናትም ተደርጎበት የተሰጠ ምስክርነት ለመሆኑ ሕግን
ከሚተረጉም አካል ቀርቶ ከአንድ ገበሬ የማይሰወር እውነት ነው፡፡
ይሁንና በዐቃቤ ሕግ የቀረበውን ክስም ሆነ በከፍተኛ ጥናት ላይ በመመርኮዝ የተሰጠውን የሐሰት የምስክርነት
ቃል በግል ተበዳዮች ነን ባዮች 1 ኛ ይ/ባይ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት በመጎዳቱ ሀዋሣ ሪፌራል ሆስፒታል በዕለቱ
ከምሽቱ 2 ሰዓት አምጥተን ጠዋት መመለሳችንን ባቀረብነው የመ/ማስረጆቻችን የምስክርነት ቃል ሙሉ በሙሉ
በማስተባበል ያሰማነውን የምስክርነት ቃል በወ/መ/ሕግ/ቁጥር 149(1) መሠረት የማስረጃዎቻችን ቃል
ተቀባይነት ያላገኘበትን አጭር የፅሁፍ መግለጫ በውሳኔው ሳይገለፅ በዝምታ ታልፎ የጥፋተኝነት ውሳኔ
ተላልፎብን 1 ኛ እና 5 ኛ በ 2 ዓመት የፈተና ጊዜ ገደብ 2 ኛ፣ 3 ኛ እና 4 ኛ ብር 500 መቀጮና እያንዳንዳቸው
እንዲከፍሉና በ 6 ወር የእስራት ቅጣት ታስረው ይቀጡ ተብሎ የተሰጠውን አሳዛኝ ፍርድ ቅር በመሰኘት ፍርዱን
ለማስለወጥ የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
ሐ/ በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ
1. በተከሳሾች በአሁኑ ይ/ባዮች ላይ በዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸው ክስ በግልፅ የሚያመለክተው ድብደባና ንብረት
መውሰድ ሲሆን የተባለውን የወንጀል ድርጊት ለአራት በመክፈልና የተለያዩ የወንጀል ሕግ አንቀፆች ላይ
እንዲወድቅ ተደርጎ በአራት ክስ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ በአራቱም የጥፋተኝነት ውሳኔ አሰጥቶ ከፍተኛውን
የእስራት ቅጣት ታስሮ እንዲቀጡ ለማድረግ የቀረበ አስገራሚ ክስ ለመሆኑ በዐቃቤ የክስ ቻርጅ ላይ ተዘርዝረው
የቀረቡት ክሶች አስረጂ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ፍ/ቤቱ አከራክሮ ፍርድ ከመስጠቱ በፊት ለትክክለኛው ፍትህ
አሰጣጥና የወንጀል ሕጉ ዓላማ ጥፋተኞች ከድርጊታቸው ተፀፅተው ሰላማዊና አምራች ዜጋ ማድረግ ነው
ከሚለውም አንፃር አንድን ድርጊት አራት ክስ በማስደረግ የቀረበውን በወ/መ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁጥር 113(1) መሰረት
ተከሳሹ ድርጊቱን ለመፈፀሙ ይበልጥ ማስረጃ ያለው በሚመስለው ጊዜ ወይም ምስክሮች ይበልጥ ያስረዱበታል
ተብሎ በተገመተ ጊዜ ሁሉ ክሱን በወ/መ/ሕግ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 119 (1) መሰረት እንዲለወጥ ማዘዝ ሲችል
ከዐቃቤ ህግ የቀረበለትን ብቻ በማየት ለማጣራት ያደረገው አንዳች ጥረት ሳይኖር በአምስቱም ክሶች ላይ
የጥፋተኝነት ውሳኔ በመስጠት ያስተላለፈው የቅጣት ውሳኔ ከፍተኛ ስህተት ያለበት ሊታረም የሚገባው ነው፡፡
2. ዐቃቤ ሕግ አቅርቦ ያሰማቸው የግል ተበዳይ ነኝ ባዮችና ቤተሰቦቻቸውም በአምስቱም ክሶች ላይ በዝርዝር
የተጠቀሱትን የወንጀል ድርጊቶች በአንድ በተመሳሳይ ሰዓትና ጊዜ ማለትም በ 1 ኛው ክስ

ላይ እርስ በእርስ በመመካከርና በመተጋገዝ በወ/ገነት ወረዳ ዩዎ ቀበሌ ውስጥ በ 20/06/2005 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት
የግል ተበዳይ በጠና ሌልቱ ቤት በር ሰብረው ገቡ ሲሉ ከ 2 – 4 ባሉ ክሶች ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት በዚሁ
ሰዓት ተፈፀመ ሲሉ የሐሰት የምስክርነት ቃል ይሰጡ እንጂ በአንድ በተመሳሳይ ሰዓት አራት የወንጀል ድርጊት በአንድ
ጊዜ ልፈፀም አይችልም፡፡ ፍ/ቤቱም ፍርድ ለመስጠት ከመቸኮሉ አስቀድሞ ለትክክለኛው ፍትህ አሰጣጥና ዜጎች
በፍትህ ላይ ያላቸውን አመለካከት የተዛባ እንዳይሆን በጥንቃቄ የዐቃቤ ህግ ማስረጃ የምስክርነት ቃል ከእነ ሙሉ
ይዘቱ መመዘኑ በመርህ ደረጃ ለእውነተኛው ፍትህ አሰጣጥ አጋዥ ከመሆኑም በተጨማሪ ከእነ ሙሉ ይዘቱና
መልዕክቱም ጭምር ሳይመዘን የተሰጠው ፍርድ ከፍተኛ የሕግ ስህተት ያለበት ነው፡፡
3. ዐቃቤ ሕግ አቅርቦ ካሰማቸው ምስክሮች የግል ተበዳይ ነኝ ባይ በጠና ሌሊቱ በአሁኑ ይ/ባዮች በአምስቱም ይ/ባዮች
በአንድ ጊዜ እየተደበደበ በሞትና በሕይወት መካከል ባለበት ሰዓት ለዛውም ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ የይግባኝ ባዮችን
የእያንዳንዱን ስም በመጥቀስ ማን የት ቦታ ስንት ጊዜ እንደመታወና በአምስቱም ሰዎች ላይ የዱላ ውርጅብኝ
እየወረደበት ይ/ባዮችን ስም በመጥቀስ እጌሌ እሄን ወሰደብኝ በማለት ከገንዘብ ጀምሮ ከቤቱ የቤት ቁሳቁስ
እንደተወሰደበት በመጥቀስ የሰጠው የምስክርነት ቃል ሲመዘን እንኳን በአምስት ሰው በዱላ የምደበደብ ሰው ቀርቶ
ሰላማዊ ታዛቢ ሰው እንኳን ዘርዝሮ መግለፅ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ምስክርነቱ ሆን ተብሎ በከፍተኛ ጥናት የተሰጠ
የሐሰት የምስከርነት ቃል ነው፡፡ በተጨማሪም በሌሎች በዐቃቤ ሕግ ምስክሮች የተሰጠውም ቃል በተመሳሳይ መልኩ
የማያውቁትንና ያላዩትን በጥናት ላይ ተመርኩዘው የሰጡት የምስክርነት ቃል ነው ፡፡ ለዚሁም አስረጂ ሊሆን
የሚችለው ከቤት ተወሰደ የተባለው ቦቆሎ ቦሎቄና ሌሎች የቤት ቁሳቁሶችን ለማዳን የይድረሱልኝ ጩኸት እንኳን
በመጮህ በአካባቢው ሕዝብ ለማስያዝ ያደረጉት ጥረት አለመኖሩ ምስክርነቱ ሆን ተብሎ የሐሰት ምስክርነት
በመስጠት ይ/ባዮችን ጥፋተኛ አስደርጎ ለማሳሰር ያለመ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
ስለዚህ ፍ/ቤቱ የምስክሮችን ቃል በሕግ መመዘንና ማጣራት ሲገባው አልፎ እንድንከላከል ብይን ቢሰጥም
ባቀረብናቸው የሰው የመከላከያ ምስክሮቻችን ቃል 1 ኛ. ይ/ባይ በአሁኑ የግል ተበዳይ ነኝ ባይ ተደብድቦ ህይወቱን
ለማዳን ሀዋሣ ሪፌራል ሆስፒታል ለህክምና ወስደን እዛው በማደር በማግስቱ በ 21/06/05 መመለሳችን ተረጋግጦ
የተመከሰረ ሲሆን በዚሁ በግል ተበዳ ነኝ ባዮች 1 ኛ ይ/ባይ በደረሰበት ከፍተኛ የአካል ጉዳት በወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት
በወ/መ/ቁጥር 2837 ላይ በቀን 4/8/05 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ 6 ወር እስራት ቅጣት 2 ኛው ደግሞ በመ/ቁጥር 2924
በቀን 01/8/2005 ዓ/ም በዋለው ችሎት በ 3 ወር የእስራት ቅጣት ታስረው የተቀጡ መሆናቸውን የሚያመለክት
የፍ/ቤት የውሳኔ ትክክለኛ ቅጂ በማያያዝ ልመሰክሩብኝ የማይችሉ መሆናቸውን ጭምር በመግለፅ ያደረግነው ክርክር
ተቀባይነት በማሳጣት የተላለፈብን የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ
በኢ/ፌ/ዲ/ሪ/ወ/ሕግ አንቀፅ 23(2) መሰረት ወንጀል ተፈፀመ ለማለት የሀሳብ የድርጊትና የሕግ መጣስ ስራዎች
በአንድነት ተሟልተው መገኘታቸውና ከጥርጣሬ ውጪ በሆነ መንገድ በእውነተኛ በአይን ማስረጃ ሲረጋገጥ ብቻ
ነው፡፡ በተጨማሪም በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 መሠረት ያላደረገ
አሳዛኝ ውሳኔ ከመሆኑም በላይ ተደበደበ ብሎ ዐቃቤ ሕግ በክሱ ከመግለፅ ያለፈ የጉዳቱን መጠን የሚገልፅ የሕክምና
ሰነድ ባልቀረበበት የተሰጠ አሳዛኝ ፍርድ ነው፡፡
ስለዚህ የሥር ፍ/ቤት በሕግ አግባብ በጥልቀት ሳይመረምር ያስተላለፈብንን የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ
በወ/መ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195 (2) (ለ) (1) መሰረት ሙሉ በሙሉ በመሻር በነፃ እንዲያሰናብተን እንዲወሰንልን
በአክብሮት እናመለክታለን፡፡
ይ/ባዮች
1. ሀይሉ ኦይቻ ---------
2. ገሪሶ ሎልቱ ---------
3. አማኑኤል ሀይሉ --------
4. ባንዳ ኦይቻ ----------
5. ማርሳ ኦይቻ -------
ቀን --------------------------------
ለሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
የመስቀለኛ ይ/ባይ፡- ሀይሉ ኦይቻ
አድራሻ ወ/ገነት ወረዳ ዩዎ ቀበሌ
የመስቀለኛ ይግባኝ መ/ሰጪ፡- 1 ኛ. በላይ ቤጤና
2 ኛ. በጠና ሎልቱ
አድራሻ ወ/ገነት ወረዳ ዩዎ ቀበሌ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 340 መሰረት የቀረበ የመስቀለኛ የይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
ሀ) የአቤቱታው አቀራረብ
- መስቀለኛ ይግባኝ መ/ሰጪዎች በወንዶገነት ወ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 3288 ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ቅር ተሰኝቶ ነሐሴ
30 ቀን 2005 ዓ/ም የተፃፈ የይግባኝ ቅሬታ ለዚህ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ባቀረቡበት ይግባኝ ላይ ተጠሪ መ/ሰጪ
የሆንኩት ከላይ በተገለፀው የሥነ ሥርዓት ሕግ መሰረት የመስቀለኛ የይግባኝ አቤቱታዬን በመዘርዝር አቀርባለሁ፡፡
- ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በመ/ይ/መ/ሰጪዎች አድርሻ ወ/ገነት ወረዳ ዩዎ ቀበሌ አማካኝነት ለማድረስ
እችላለሁ፡፡
ለ) ለመስቀለኛ ይግባኝ ምክንያት የሆነው ጉዳይ
በሥር ፍ/ቤት ከሳሽ በሆንኩት በአሁኑ ይ/ባይ ላይ የመ/ይ/መ/ሰጪዎች አስበውና አቅደው ውድና መተኪያ
የሌላትን ሕይወቴን ለማጥፋት በማሰብ ባደረሱብኝ የመግደል ሙከራ ወንጀል ከፍተኛ የሆነ የአካል ጉዳት
አድርሰውብኝ 1 ኛ መ/ሰጪ በወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት በወ/መ/ቁጥር 2837 ላይ በቀን 4/8/05 በዋለው ችሎት በ 6 ወር
የእስራት ቅጣት እንዲቀጣ 2 ኛ መ/ሰጪ በመ/ቁጥር 2924 በቀን 01/8/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ 3 ወር
የእስራት ቅጣት ታስሮ እንዲቀጣ በፍርድ የተወሰነባቸው ሲሆን እኔም ከእግ/ር በታች በሕክምና እና በሰው
ብርታት ሕይወቴ ሊተርፍ ቢችልም በከፍተኛ የደም መፍሰስ የተጎዳውን ሰውነቴን ለመጠገን ከልጅነት እስከ
እውቀት ያፈራሁትንና ያለኝን ገንዘብ የተለያዩ ገበያዎች በመሔድ ከነጋዴዎች ቅቤና ሌሎች ለሰውነት ግንባታ
የሚሆኑኝን በብር 20,882 አውጥቼ በመግዛት ተጠቅሜ ወደነበርኩበት ጤንነት እንኳን ሙሉ በሙሉ
ባይመልሰኝም በጥቂቱ አገግሜ በመ/ይ/መ/ሰጪዎች ምክንያት የወጣውን ወጪ በፍርድ ለማስከፈል
ያቀረብኩትን አቤቱታ በሕግ አግባብ በጥልቀት አይቶ መርምሮ እንደክስ አቀራረቤ መወሰን ሲገባው ለቅቤ ብር
1000 ፣ለእርድ ከብት ብር 15000፣ለቆጮ ብር 500፣ለትራንስፖርት ብር 300፣ለህክምና ብር 382፣በካሣ
100፣ለጠበቃ አበል 1000 ድምር 5682 እዲከፈለኝ የተሰጠውን አሳዛኝ ፍርድ ቅር በመሰኘት ፍርዱን
ለማስለወጥ የቀረበ የመ/ይ/አቤቱታ ነው፡፡

ሐ) በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ


1. በመ/ሰጪዎች በደረሰብኝ ጉዳት ለሰውነት ማገገሚያ በሚል ከተለያዩ ገቢዎች ከተለያዩ ነጋዴዎች በሕጋዊ
የመተማመኛ ሰነድ የገዛሁበትን አያይዤ ላቀረብኩት ማስረጃ በሥር ተከሣሾች በኩል የቀረበ ማስተባበያ
በሌለበት የወቅቱን የኑሮ ሁኔታና ግብይት ከግምት ሳይገባ ፍ/ቤቱ በእራሱ ተነሳሽነት የጠበቃ አበል ጨምሮ ብር
5,682 ብር ብቻ እንዲከፈለኝ የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ ለዳኝነት የተከፈለውን ብር 806
ብር ታልፎ የተሰጠው ፍርድ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡ ስለሆነም በማስረጃ ተደግፎ ለቀረበው ክስ ማስተባበያ
በሥር ፍ/ቤት ያልቀረበ በመሆኑ ተሻሽሎ በሥር ፍ/ቤት ያቀረብኩትን ገንዘብ እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ ፣
2. መ/ሰጪ ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ፅፎ ለፍ/ቤቱ ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ደርሶኝ በመመልከት
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕሕቁጥር 339 (3) መሰረት ተዘርዝሮ የቀረበ መልስ
የመ/ይ/መ/ሰጪዎች በሥር ፍ/ቤት ይ/ባይ ለመንግሥት መክፈል የሚገባውን በታሪፍ ሳይከፍል ፋይል ተከፍቶ
ዳኝነት ተሰጠ በሚል የፍ/ቤትን አሠራር ጭምር በመንቀፍ የቀረበው የሐሰት አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው
ስለመሆኑ
2.1 በሥር የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት በቀን 29/09/05 ዓ.ም የአሁኑ የመ/ይ/መ/ሰጪዎች በፍርድ እንዲከፍሉኝ
ላቀረብኩባቸው ብር 20,882 የገንዘብ ክስ ፋይል ከመከፈቱ በፊት በቀን በ 4/10/05 ዓ.ም በደረሰኝ ቁጥር
056135 በሆነው ላይ ባቀረብነው ገንዘብ ልክ በታሪፍ ብር 806 (ስምንት መቶ ስድስት ብር) ለፋይናንስና
ኢኮኖሚ ል/ቢሮ የከፈልንበት ሰነድ እንደ መ/ይ/መ/ሰጪዎች አባባል ሳይሆን በሥር ፍ/ቤት መዝገብ ላይ የሚገኝ
ከመሆኑም በተጨማሪ ደረሰኙ በእጃችን ይገኛል ፡፡ ፍ/ቤቱ ማጣራት ከፈለገ ከወ/ገነት ወ/ፋ/ኢ/ል/ቢሮ
በማስጠየቅ በትዕዛዝ አስቀርቦ በማየት በሐሰት የቀረበ ተቀባይነት የሌለው ነው እንዲባልልን፡፡
የጠበቃ አበል በፍርድ በተወሰነው ገንዘብ ብር 5682 ልክ በታሪፍ 468.20 ብቻ መከፈል ሲገባው 1000 መባሉ
አግባብ አይደለም የተባለውን በተመለከተ
2.2 በአሁኑ በመ/ይ/መ/ሰጪዎች ላይ በሥር ፍ/ቤት ያቀረብኩባቸው የገንዘብ ክስ ብር 20.882 ሲሆን እንደ
አባባላቸው የጠበቆች የአገልግሎት ዋጋ በተለይም ግምቱ ለአነስተኛ የገንዘብ ክስ በሁለቱ ወገኖች ስምምነት
የሚፈፀም እንጂ እንደ ዳኝነት ገንዘብ ታሪፍ የወጣለት አይደለም፡፡
ይሁንና በከፍተኛ የገንዘብ ክሶች ላይ በጠበቆች የሥነ ምግባር ደንብ መመሪያ አዋጅ 29/97 ላይ 10%
እንደሚከፈል ተደንግጓል፡፡ ምንም እንኳን በተያዘው ጉዳይ በሥር ፍ/ቤት ላቀረብኩት አነስተኛ ገንዘብ 10%
የጠበቃ አበል ይከፈል እንኳን ቢባል የጠበቃ አበል ልከፈል የሚገባው 2088 ብር እንጂ በመ/ይ/መ/ሰጪዎች
የተገለፀው አይደለም ለዚሁም አንድ ጠበቃ ውል የሚዋዋለው ጉዳዩን ከመጀመሩ አስቀድሞ ለሚያቀርበው
ጉዳይ እንጂ ገና ለሚወሰነው ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም እንዲባልልኝ ::

በተከሳሾች በደረሰብኝ ጉዳት ለማገገሚያ የተወሰነልኝ ብር 4,682 ያለማስረጃ ድጋፍ የተወሰነ


ነው የተባለውን በተመለከተ
በተከሣሾች አማካ Ne ነት በደረሰብኝ የመግደል ሙከራ ሕይወቴ ቢተርፍም በጉዳቱ ከፍተኛ ደም
የፈሰሰኝ ሲሆን የሰውነቴን አቋም ወደነበረበት ሙሉ ለሙሉ መመለስ ባይቻልም በመጠኑም ቢሆን
ከተለያዩ ገበያዎች ከነጋዴ ለምግብነት የሚውሉ የገዛኋቸውን በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ ብር 20,882
(ሃያ ሺህ ስምነት መቶ ሰማኒያ ሁለት ) ብር ላቀረብኩት የአሁኑ የመ/ይ/መ/ሰጪዎች የሰጡት ማስተባበያ
ሳይኖር ፍ/ቤቱ በእራሱ ተነሳሽነት በመቀነስ የሰጠው ውሳኔ የመ/ይ/መ/ሰጪዎችን አቤቱታ በሕግ ላይ
ተመስርቶ ያቀረቡ ተቀባይነትም የሌለው ነው፡፡
በአጠቀላይ የመ/ይ/መ/ሰጪዎች ያቀረቡት አቤቱታ የሕግ መሠረት የሌለው ስለሆነ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሮ በመ/ይ/አቤቱታችን ላይ የተጠቀሰው ተጣርቶ
እንዲወሰንልኝ ስል በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡
ቀን ---------------------------
ለሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
ይግባኝ ባዮች፡- 1 ኛ. ተሾመ እንዳለ
2 ኛ. ላምሮት እንዳለ
3 ኛ. አብርሃም /አለማየሁ/ እንዳለ
አድራሻችን፡- ወ/ገነት ወረዳ ኬላ 01 ቀበሌ
መልስ ሰጪ፡- ወ/ሮ መሠለች እንዳለ
አድራሻ ፡- ወ/ገነት ወረዳ ኬላ 01 ቀበሌ
- የሥር የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 3591
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 327 መሠረት የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
- የይግባኝ አቤቱታው የቀረበበትን ፍርድ የሰጠው የወንዶገነት ወረዳ ፍ/ቤት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 3591 በ 3/01/2006 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በመ/ሰጪ አድራሻ በኩል ሊደርሳት ይችላል፡፡
- የሥር ፍ/ቤት የውሳኔ መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ ------ ገጽ ተያይዟል፡፡
ለ/ ለይግባኝ አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የይግባኝ አቤቱታ ለዚህ ፍ/ቤት ሊቀርብ የቻለው ሟች ወላጅ እናታችን ወ/ሮ አስናቀች በየነ በወንዶገነት
ወረዳ ኬላ 01 ቀበሌ ውስጥ በግል ጥረቷ ስፋቱ 292x80 የሆነ ስፋት ባለው ይዞታ ላይ አንድ ሦስት ክፍል ያለው
ትልቅ ቤትና አንድ ኩሽና ቤት በመስራት ከእንሰት ጀምሮ የተለያዩ አትክልቶች ጭምር በመትከል ለመንግሥት
የሚገባውን ህጋዊ ግብር በስሟ በመገበር እየተጠቀመች ሳለ ባደረባት ሕመም ከዛሬ 27 ዓመታት በፊት በሞት
ስትለይ የአንደኛ አመልካች ዕድሜ 6 ዓመት የሁለተኛው እድሜ 4 ዓመት የ 3 ኛው ደግሞ አንድ ዓመት ሲሆን
ከላይ በስም ተጠቃሽ የሆነችው የእናታችን ልጅ እህታችን መ/ሰጪ በወቅቱ ለአቅመ ሔዋን የደረሰች ስለነበረ
በሟች እናታችን ምትክ ተተክታ ለአቅመ አዳምና ሄዋን እስክንደርስ የጋራ የውርስ ሀብት በሆነው በእናታችን
ቤት አሳድጋን 2 ኛ ይ/ባይም ከዚሁ ቤት ውስጥ ተድራ የውርስ ሀብቱ ክፍፍል ሳይደረግና ሳይነጣጠል በስምምነት
በመኖር ላይ ሳለን መ/ሰጪ እንደግል ንብረት በመቁጠር ለ 3 ኛ ወገን በሽያጭ አሳልፋ ለመሸጥ ስትዋዋል አይተን
የጋራ ንብረታችን እንደመሆኑ መጠን ሳታማክሪን እንዴት ለ 3 ኛ ወገን በሽያጭ ይተላለፋል በሚል ስንጠይቃት
ከልጅነታችሁ ጀምሮ አሳድጋአችኋለሁ አይመለከታችሁም ይሄ ንብረት የግሌ ነው በማለት ላቀረብንላት ጥያቄ
ምላሽ ልትሰጠን ባለመቻሏ የሟች እናታችን ሕጋዊ ወራሾች መሆናችንን በወ/ገ/ወ/ፍ/ቤት በሥራ ፋይል ቁጥር
03588 በቀን 16/8/01 ዓ.ም በዋለው ችሎት በፍርድ አረጋግጠን ስለነበር ክፍፍል ሳይደረግና ሳይነጣጠል በጋራ
ተይዞ የቆየው የጋራ የውርስ ሀብታችን አጣሪ ተቋቁሞና ተጣርቶ የሟች እናታችን የውርስ ሀብት በየድርሻችን
ተለይቶ ክፍፍል እንዲደረግልን ያቀረብነውን አቤቱታ ተቀብሎ የተመለከተው የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት ቀደም ሲል
ሁከት ይወገድልኝ ስትል በሌላ መ/ቁጥር 0994 ላይ የይርጋ ጥያቄን ጭምር በማንሳት ያቀረበችውን በማየት
የተፈጠረ ሁከት ካለ እንዲወገድና የጋራ የውርስ ሀብት የክፍፍል ጥያቄን የማንሳት መብታችንን ጠብቆ በፍርድ
የተወሰነው ውሳኔ በይግባኝ ያልተሻረ ከመሆኑም በተጨማሪ ሁከት ይወገድ በተባለው ላይ

ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በአቤቱታ ቀርቦ የመ/ቁጥር 60069 ተከፍቶ ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ለ 7/2/06 ዓ/ም ለውሳኔ
ቀጠሮ ተይዞ ይገኛል፡፡
ይሁንና ይግባኝ የተባሉትን የውርስ ሀብት የክፍፍል ጥያቄ የሥር ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244 ሥር
በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ሊቀርቡ ከሚገባቸውና በዝርዝር ከተገለጹት ውጪ በዋናው ክርክር ጊዜ
መነሳት የሚገባውን በማንሳት በ 1977 ዓ.ም በኑዛዜ የተላለፈላት ስለሆነ ይርጋ ያግደዋል በሚል ከሕፃንነታችን
ጀምሮ እስከዛሬ ካለንበት ቤት እንድንወጣና በቤቱም መብት እንደሌለን ተደርጎ የተሰጠውን ብይን ቅር በመሰኘት
ለማስለወጥ የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
ሐ) በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልን የምንጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ
1/ የይግባኝ ባዮችና የመ/ሰጪ ወላጅ እናት ከዛሬ 27 ዓመታት በፊት በሞት በተለየች ጊዜ ይ/ባዮች ሕፃናት በመሆናችን
በመ/ሰጪ ታላቅ እህታችን እጅ በዚሁ የጋራ የውርስ ሀብት በሆነው ቤት ያደግን ሲሆን 2 ኛ ይ/ባይ በመ/ሰጪ
እህታችን አማካኝነት ተድራ አግብታ በትዳር ያለች ከመሆኗም በተጨማሪ ይ/ባዮች የጋራ የውርስ ሀብት
ከሆነው ቤት ጋር ተያይዞ ካለው የእንሰትና የአትክልቶች ውጤት በጋራ አላባውን እየተጠቀምን ክፍፍል ሳይደረግና
ሳይነጣጠል የቆየውን የውርስ ሀብት ለ 3 ኛ ወገን በሽያጭ ለማስተላለፍ ስትሞክር አይሸጥም ብለን ተቃውሞ
በማንሳታችን ከቤት አስወጥታን ለመሸጥ በማሰብ ሁከት ይወገድልኝ በማለት በሥር የወ/ገነት ወረዳ ፍ/ቤት
ያቀረበችው አቤቱታ በመ/ቁጥር 0994 ላይ ሁከት ይወገድ በማለት የውርስ ንብረት የመጠየቅ መብታችን
ተጠብቆ በፍርድ በተወሰነው መሠረት ያቀረብነውን የውርስ ሀብት የክፍፍል ጥያቄም ሆነ ጉዳያችንን
የወ/ወ/ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ተካልኝ መኮንን መዝገባችንን ማየት እንደማይችሉና በሌላ ዳኛ ጉዳዩ
መታየት እንዳለበት ተገልፆ በቁጥር ሲ 5/840/03 በቀን 03/10/05 ዓ.ም በወቅቱ ተወክለው በነበሩት
በም/ፕሬዝዳንት ፊርማ ለፍ/ቤቱ የተላከውን ትዕዛዝ ባለመቀበልና በመጣስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244 ሥር
በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የማይቀርበውንና በዋናው ክርክር ላይ መነሳት ያለበትን የኑዛዜ ጥያቄ
በመቀበል በ 1977 ዓ/ም በኑዛዜ የተሰጣት በመሆኑ ይ/ባዮች ጥያቄውን ሊያቀርቡ አይገባም በሚል በብይን
መዝገባችን መዝጋቱ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ የስር ተከሣሽ የአሁኗ መ/ሰጪ እህታችን በመጀመሪያ
ደረጃ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244 (2) (ለ) (ሐ) እና የፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1000 (1) እና (2) በመጥቀስ ያቀረበችውን
ተመልክተን በ 4/13/05 ዓ.ም በተፃፈ አስተያየት በፊደል (ለ) ሥር ያለው ክሱ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ
የተወሰነ ነው የሚል ሲሆን በፊደል (ሐ) ስር ያለው ደግሞ ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍ/ቤት ቀርቦ ክርክር ላይ
ያለ መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡ ስለዚህ የቀረበው የውርስ የክፍፍል ጥያቄ እንደ መ/ሰጪ አባባል አስቀድሞ
በፍ/ቤት ውሳኔ ያላገኘና በሌላ በየትኛውም ፍ/ቤት ቀርቦ እየታየ ያለመሆኑን በመግለፅ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244
ስር የተጠቀሰው ከእውነት የራቀ የማስረጃም ድጋፍም የሌለው ሐሰት በመሆኑ ውድቅ ሊደረግ

የሚገባው መሆኑን እንዲሁም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000 (1) እና(2) ተጠቅሶ የቀረበውም ቢሆን በንዑስ ቁጥር (1) ላይ
ያለው የወራሽነት ጥያቄ የማቅረቢያ ጊዜ እንጂ የውርስ ሀብት ንብረት የክፍፍል ጥያቄ የሚቀርብበት አለመሆኑን
ለመግለፅ የፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአመልካች እነ ጽጌ ወ/መስቀል 6 ሰዎችና በተጠሪ ስዩም
መስፍን መካከል በቅፅ 10 በመ/ቁጥር 38533 ከገፅ 27 -28 የሕግ ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ ከተያዘው ጉዳይ
የማይገናኝና የይርጋ ጥያቄን የማያስነሳ ነው በንዑስ ቁጥር (2) ላይ የተገለፀው ደግሞ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 996 -
1062 ድረስ ባለው የሕግ ድንጋጌ መሰረት የሚታይ ከመሆኑም በተጨማሪ አንድ ሕጋዊ ወራሽ በሕጉ
በተመለከተው ጊዜ ገደብ ወራሽነቱን እስካረጋገጠና የውርስ አከፋፈሉ እስካልተፈፀመ ድረስ ውርሱ በወራሾች
መካከል ሳይነጣጠል የቆየ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1062 ድንጋጌ መሠረት በማናቸውም ጊዜ የውርስ ሀብት
የክፍፍል ጥያቄ መቅረብ እንዳለበት በሕጉ የተደነገገና ይ/ባዮች ወራሾች ወራሽነታቸውን አረጋግጠው የክፍፍል
ጥያቄ በቀረበበት ቤት ውስጥ ከመ/ሰጪ ጋር አብረው እስከቆዩ ድረስ የጋራ ወራሾች በማናቸውም ጊዜ ቢሆን
የክፍፍል ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1060 መሰረት ማቅረብ የሚችሉ እንደሆነና በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000 (1) (2) ስር
የይርጋ ድንጋጌ ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1062 መሠረት በማናቸውም ጊዜ የሚቀርብ መሆኑን በመግለፅ
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 38533 ላይ የሕግ ትርጉም የሰጠበት መሆኑን በመግለፅ አስተያየታችን በፅሁፍ
ብንሰጥም ፍ/ቤቱ ለማጣራት ያደረገው አንዳች ጥረት ሳይኖር አልፎ በብይን በመዝጋት መብታችን መንፈጉ
አግባብ አይደለም፡፡
2/ ጥቅምት 8 ቀን 1977 ዓ/ም በተደረገ ኑዛዜ ተላልፎ የተሰጡት በመሆኑ በይርጋ ይታገዳል
ተብሎ የተሰጠውን ብይን ሕግን ያልተመረኮዘ ስለመሆኑ
ወላጅ እናታችን ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየቷ በፊት በ 1977 ዓ/ም ኑዛዜ የተበረከተልኝ ትበል እንጂ ኑዛዜው
ስለመደረጉም ሆነ ስለመኖሩ በሥር ፍ/ቤት ክርክር ውስጥ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ የማናውቅና ያልነገረችን
ከመሆኑም በተጨማሪ ኑዛዜው በእራሱ እምነት የማይጣልበት በወ/እናታችን የተሰጠ አይደለም ፡፡ ይሁንና ኑዛዜ
ተደረገላት ወይም በኑዛዜ ተሰጣት እንኳን ቢባል በፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 903 መሰረት ኑዛዜ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ
እስከ 7 ዓመት ድረስ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ቀርቦ ካልጸደቀ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ በግልፅ የተደነገገ
ከመሆኑም በተጨማሪ በኑዛዜው ላይ ከወራሽነት እስካልተነቀልን ጊዜ ድረስ የሟች እናታችንን የውርስ ንብረት
እኩል የማንወርስበት ምክንያት የለም፡፡ በተጨማሪም መ/ሰጪ አለኝ ያለችውን ኑዛዜ ያወቅነው ሁከት
ይወገድልኝ ስትል በሥር የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 994 ላይ አያይዛ ባቀረበችብን ጊዜ ሲሆን የኑዛዜው ሰነድ
በፎርማሊቲ ረገድ ጉድለት ያለበት ነው፡፡ በይዘት ረገድም ከኑዛዜው መረዳት የምቻለው የይ/ባዮችና ተጠሪ ወላጅ
እናት ሟች አስናቀች በየነ ጥቅምት 8 ቀን 1977 ዓ.ም በተፃፈ ጽሁፍ ኑዛዜ አደረገች በተባለት ሰነድ ላይ ክርክር
ያስነሳው ይዞታ የመ/ሰጪ አባት የሠራው ነው በማለት የእናታችን የሚስትነቷ ድርሻ ሳይቀነስ በሙሉ

ጠቅልላ እንድትይዝ ሆን ተብሎ ከቅን ልቦና ውጪ በሐሰት የተዘጋጀ ከመሆኑም በተጨማሪ በሥር የወ/ገነት
ወ/ፍ/ቤት ሁከት ይወገድልኝ ስትል ባቀረበችብን መ/ቁጥር 994 ላይ ክርክር ያስነሳው ይዞታ ከእናታችን ወንድም
በስጦታ ተበርክቶላት በግል ገንዘቧ የሠራችው ንጹህ ንብረቷ ስለመሆኑ በእራሷ ማስረጃዎችም ጭምር
ተረጋግጦ ከተሰጠው የምሰክር ቃል በተቃረነ መልኩ በሐሰት ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው በተጨማሪም
በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 881 መሰረት ግልፅ ኑዛዜ ማሟላት ከሚገባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ የማስረጆች ሙሉ ስምና
ፊርማቸው ነው በቀረበው ሰነድ በማስረጃነት ከተጠቀሱት ውስጥ ማቴዎስ ኃይሌ እና ቄስ መምሬ ስሜ የጣት
አሻራ ፊርማቸውም ሆነ በእጅ ፅሁፍ የተፈረመ ፊርማ አለመኖሩ ኑዛዜው ሕጉን ተከትሎ ያልቀረበ ተቀባይነት
የሌለውና በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 913 መሰረት የውርስ ሀብት ለተወላጅ መስጠቱ የክፍያ ደንብ እንጂ የኑዛዜ ስጦታ
ተብሎ እንደማይቆጠርና የሌላው ወራሽ መብት ከ 1/4 ኛ ወይንም ከሩብ በታች መሆን እንደሌለበትና በዚህ
መልኩ የተደረገው ኑዛዜም ፈራሽ ሊሆን እንደሚችል በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1123 (1) መሰረት በግልፅ የተደነገገ
ከመሆኑም በተጨማሪ በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 10 ላይ በመ/ቁጥር 50901 ላይ ከተሰጠው
የሕግ ትርጉም ውጪ የተሰጠ አሳዛኝ ፍርድ በመሆኑ እንዲሻርልን ፡፡
የተከበረውን ፍ/ቤት የምንጠይቀው ዳኝነት
1. በሥር ፍ/ቤት መዝገባችንን በብይን አይተው የዘጉት ዳኛ ጉዳያችንን እንዳያዩና በሌላ ዳኛ እንዲታይልን በሚል
ለዚሁ ፍ/ቤት አመልክተን በቁጥር ሲ 5/84/0/03 በቀን 03/10/2005 ዓ.ም በአድራሻ ለወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት በወቅቱ
የም/ፕሬዝዳቱ ተወካይ በነበሩት ዳኛ ፊርማ ወጪ ተደርጎ በተላከው ደብዳቤ በአቤቱታችን መሠረት እንዲያዩና
በሌላ ዳኛ እንዲታይ የተላከውን ትዕዛዝ ወደጎን በመተው መ/ሰጪ በመጀመሪያ ደረጃ ካቀረበችው ተቃውሞ
ውጪ በፍሬ ጉዳይ የሚነሳውን ጉዳይ በማንሳት መዝገባችንን በብይን ዘግተው በሕግ የምናገኘውን መብት
መንፈጉ አግባብ ባለመሆኑ እንዲታረምልን ፣
2. በሥር ፍ/ቤት መ/ሰጪ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244 (2) (ለ)(ሐ) እና የፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1000 (1) እና (2)ን
በመጥቀስ በመጀመሪያ ደረጃ ለቀረበው መቃወሚያ በ 4/13/05 ዓ/ም ፅፈን መቃወሚያው በሕግ አግባብ
ያልቀረበና በተጠቀሱት ሕጎች ስር ያለውን ፅንሰ ሀሳብ ያላሟላ ባለማወቅና ባለማስተዋል የቀረበ መሆኑን
በመግለፅ አስተያየት በፅሁፍ በማቅረብ በመቃወሚያው ላይ የተጠቀሰውን በማለፍ በክርክር ጊዜ የሚነሳውን ፍሬ
ጉዳይ (የኑዛዜ) ማስረጃ አግባብነት ላይ የተደረገ ክርክር ሳይኖር ከልጅነት እስከ እውቀት ከመ/ሰጪ ጋር በአንድ
ቤት እያደርን የውርስ አካል ከሆነው እንሰትና ሌሎች አትክልቶች የሚገኘውን የአላባ ጥቅም በማግኘት
እየተጠቀምን ሳለ በይርጋ ቀሪ ነው በሚል የተሰጠው ብይን ሕግን ያልተከተለ ከመሆኑም በተጨማሪ
የፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1060 የሚቃረን አሳዛኝ ፍርድ ተሽሮ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(1) መሰረት ወደኋላ
መዝገቡን በማስረጃ ተጣርቶ በድጋሚ እንዲወሰን እንዲታዘዝልን ፣
3. የሥር ፍ/ቤት በዋናው ክርክር የሚነሳውን የኑዛዜ ጉዳይ በማንሳት በብይን ከመዝጋት ያለፈ የተባለው ኑዛዜ
ፎርማሊቲውን አሟልቶ መቅረብ አለመቅረቡን በተለይም በፍ/ብ/ህግ/ቁጥር 1723 መሰረት በ 7 ዓመት ጊዜ
ውስጥ ስልጣን ባለው አካል ዘንድ ቀርቦ የተመዘገበ ስለመሆኑና ስላለመሆኑ እንኳን ባልተረጋገጠበትና የግራ
ቀኛችን ማስረጃ ሳይሰማ የተሰጠውን ብይን የወጪ ኪሣራ መብታችንን በመጠበቅ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348
(1) መሰረት ተሽሮ እንዲወሰንልን በአክብሮት እናመለክታለን፡፡
ቀን ------------------------------
ለሰገን አካባቢ ሕ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት
ሶያማ ምድብ ችሎት
ሶያማ

ከሣሽ፡- መሐመድ ውሌ
ተከሳሾች፡- እነ መሐመድ በኮ 53 ሰዎች
ተከሣሾች ለቀረበባቸው ክስ ----------- ዓ.ም ፅፈው ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
በመመልከት ከተከሣሽ የተሰጠ አስተያየት
የተከሣሾች የመጀመሪያ ደረጃ የመቃወሚያ ይዘት በአጭሩ
ከሣሽ ኢንቨስተርና አቅም ያለው ሆኖ ሳለ የመንግሥትን ገቢ ለማስቀረት በማሰብ በድሃ ደንብ ፋይል
ማስከፈቱ አግባብ አይደለም እንዲሁም ክርክር ያስነሳው ይዞታ የቀድሞ የሰገን ከላለ በመሆኑ የመክሰስ
መብት የለውም የሚል ነው፡፡
1 ኛ) ተከሣሾች የመንግሥትን ገቢ ለማስቀረት በደሃ ደንብ ፋይል ተከፈተ በሚል ሳያጣሩና ሳያረጋግጡ ፍ/ቤቱን
ጭምር በመኮነን ቢያቀርቡም በተከሣሾች ላይ ላቀረብኩባቸው የገንዘብ ክስ በሕጉ መሰረት በገንዘቡ መጠን
በታሪፍ ብር ------------------- በደረሰኝ ቁጥር -----------ከፍዬ የተከፈተ እንጂ እንደተከሣሾች አባባል በነፃ
ዳኝነት ሳይከፈል የተከፈተ ፋይል አይደለም ፡፡
2 ኛ) የመክሰስ መብት የለውም በሚል ፍ/ቤቱንም ሆነ ከሣሽን ሊያሳምን የምችል በማስረጃ ሳይደገፍና
በፍትሐብሔር ሥነ ስርዓት ሕጋችንም ላይ ስለመጀመሪያ መቃወሚያ አቀራረብ በግልፅ ከተመለከተው
ውጪ የቀረበ ቢሆንም ላቀረቡት ሀተታ፡-
ሀ) በቡርጂ ወረዳ ከልቾ ቀበሌ ውስጥ የምገኝ ባዶ የመንግሥት መሬት መኖሩን የወረዳው አስተዳደር በማረጋገጥ
በገጠር የመሬት ደንብ ቁጥር 24/96 መሠረት የኢንቨስትመንት መሬት ኪራይ ውል ከወረዳው አስተዳደር
ጋር ከመጋቢት 9 ቀን 2000 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 25 ዓመታት ተፈራርመ በሕጋዊ መንገድ በያዝኩት
የኢንቨስትመንት መሬት /ይዞታ/ ላይ ያለኝን መዋዕለ ነዋይ በማፍሰስ የተለያዩ የአትክልት ዝርያዎችን
በመትከል ለውጤት ያበቃሁት ውስጥ በሀይል በመግባት በእሳት ዶግ አመድ በማድረግ አቃጥለው ከጥቅም
ውጪ አድርገው በመያዛቸው በቡርጂ ወ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 0637/04 በቀን 7/1/04 ዓ/ም በዋለው ችሎት
በሐይል ከያዙበት ለቀው እንዲወጡና ሁከት እንዲወገድ የተሰጠው ውሳኔ እስከ ክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት ድረስ ደርሶ ፀንቶ የተወሰነና በይዞታው ላይ ባለመብት መሆኔ በፍርድ ተረጋግጦ የተወሰነልኝ
ከመሆኑም በተጨማሪ

በመቃወሚያነት የቀረበው ጉዳይ ቀደም ሲል በፍርድ ውሳኔ ያገኘ ጉዳይ በመሆኑ በተከሣሾች ላይ ክስ
የማቅረብና የተከራየሁበትም የኪራይ የውል ዘመኑ ማብቂያ ጊዜ እስካላበቃ ድረስ ይዞታውን
የማስጠበቅ ግዴታ ጭምር ያለብኝ ስለሆነ የተከሣሾች መቃወሚያ የሕግ መሠረት የሌለው ከመሆኑም
በተጨማሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244 መሠረት በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ላይ የሚቀርቡ
መቃወሚያዎችን መስፈርት ያላሟላና የፍ/ቤቱንም ሆነ የከሳሽን ጊዜ በማባከን ከማቅረብ ያለፈ
በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የማይቀርብና ተቀባይነትም የሌለው በመሆኑ በሕግ ላይ ተመርኩዞ
ያልቀረበውን የተከሳሾችን መቃወሚያ በብይን ውድቅ በማድረግ ወደ ዋናው ክርክር መግባት እንድችል
እንዲበየንልኝ ስል በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡
አስተያየቴም በእውነት የቀረበ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሰረት በቃለ መሀላ
በማረጋገጥ አቀርባለሁ፡፡
ቀን ----------------------------
ለወንዶገነት ወ/ፍ/ቤት
ጩኮ
አመልካቾች ፡- 1. ተሾመ እንዳለ
2. ላምሮት እንዳለ
3. አብርሃም እንዳለ
ተጠሪ ፡- መሠለች እንዳለ
ነሐሴ 23 ቀን 2005 ዓ/ም ተፅፎ ከተጠሪ በቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ከአመልካቾች
የተሰጠ አስተያየት
ተጠሪ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244 (2) (ለ) (ሐ) እና የፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1000 (1)እና (2) በመጥቀስ ክሱ በይርጋ
ሕግ ቀሪ ነው በሚል ያቀረበችውን መቃወሚያ በተመለከተ
1) የተጠቀሰው የሥነ ሥርዓት ሕግ 244 (2) በፊደል (ለ) ሥር ያለው ክሱ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ
የተወሰነ ነው የሚል ሲሆን በፊደል (ሐ) ስር ያለው ደግሞ ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍ/ቤት ቀርቦ በክርክር ላይ
ያለ መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡
ሀ) ይሁን እንጂ ክስ የቀረበበት የውርስ ንብረት አስቀድሞ በፍርድ ቤት ውሳኔ ያገኘ ጉዳይ አይደሉም፡፡ ነገር
ግን በአመልካቾችና ተጠሪ መካከል በተከሰተው አለመግባባት ተጠሪ በዚሁ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር ላይ ሁከት
ይወገድልኝ ስትል ያቀረበችውን ክስ ፍ/ቤቱ ሁከት ይወገድ ብሎ ሲወስን የጋራ የውርስ ንብረት ክፍፍል መብት
ተጠብቆ ውሳኔ ከማሳለፍ ያለፈ አሁን የቀረበው የውርስ ጥያቄ ቀደም ሲል በዚህ ፍ/ቤትም ይሁን በሌላ ፍ/ቤት
ያልቀረበ በመሆኑ የተጠሪ መቃወሚያ የሕግ ድጋፍ የሌለው ነው፡፡
ለ) በፊደል (ሐ) ስር ያለው ደግሞ ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍ/ቤት ቀርቦ በክርክር ላይ መሆኑን የሚገልፅ
ነው፡፡
በመሠረቱ ያቀረብነው የውርስ ሀብት የክፍፍል ጥያቄ በየትኛውም ሌላ ፍ/ቤት ቀርቦ እየታየ የሚገኝ
አይደለም ለዚሁም ተያይዞ የቀረበ ሰነድ የለም፡፡ ስለዚህ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244 ሥር የተመለከተውን
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የማያሟላና የማስረጃም ድጋፍ የሌለው መሰረተቢስ ሀተታ በመሆኑ ውድቅ
ተደርጎ ወደዋናው ክርክር ውስጥ መግባት እንድንችል እንዲበየንልን፡፡
2) የፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1000 (1) እና (2) ድንጋጌ በመጥቀስ ያቀረበችውን የይርጋ ጥያቄ በተመለከተ
ሀ) የፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1000 (1) የወራሽነት ጥያቄ የማቅረቢያ ጊዜ ሲሆን ከፍ/ብ/ህግ/ቁጥር 996 እስከ 1062 ባሉት
የሕግ ድንጋጌዎች የወራሽነት ጥያቄ በማቅረብ መብትን ከማረጋገጥ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

በተጨማሪም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1060 ድንጋጌ ሥር ደግሞ የውርስ አከፋፈል እስካልተፈፀመ ድረስ ውርሱ
በወራሾች መካከል ሳይነጣጠል እንደሚቆይ ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ከሣሾች የሟች ወላጅ እናታቸውን በሕጉ
በተመለከተው ጊዜ አረጋግጠው ከቆዩ በኋላ የውርስ ንብረቱን የክፍፍል ጥያቄ ማቅረባቸው በፍ/ብ/ህግ/ቁጥር
1000(1) እና (2) ሥር የይርጋ ድንጋጌ ስር የሚታገድ ሳይሆን በፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1062 ድንጋጌ መሰረት
በማናቸው ጊዜ የሚቀርብ መሆኑንና የወራሽነት መብት መረጋገጥ ያለበት በፍ /ብ/ህግ/ቁጥር 1000 (1)
መሰረት ሟች በሞተበት በ 3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ መሆን እንዳለበት የፌዴራል ጠ /ፍ/ቤት በአመልካች እነ
ፅጌ ወ/መስቀል 6 ሰዎችና በተጠሪ ስዩም መስፍን መካከል በመ/ቁጥር 38533 ከገፅ 27 – 28 ላይ የሕግ ትርጉም
የሰጠበት ስለሆነ የተጠሪ /ተከሳሽ/ መቃወሚያ በሕግ ላይ ተመስርቶ ያልቀረበ ተቀባይነት የሌለው ስለሆነ
በብይን ውድቅ ተደርጎ ወደ ዋናው ክርክር ውስጥ መግባት እንድንችል እንዲበየንልን ፣
3) ጥቅምት 8 ቀን 1997 ዓ/ም ከወ/እናታችን ኑዛዜ ተላለፈልኝ ስትል ከመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ጋር
ቀላቅላ ያቀረበችውን በተመለከተ
ሀ) ወ/እናታችን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታ በ 10/02/75 ዓ/ም የቀብር ሥነ ሥርዓቷ የተፈፀመ ሲሆን ተጠሪ
/ተከሣሽ/ ኑዛዜ የተላለፈልኝ የምትለው ደግሞ ወ/እናታችን በሕይወት ሳለች ጥቅምት 8/1977 ዓ/ም
ከእናታችን በሞት ከመለየቷ 2 ዓመት በፊት ተሰጠኝ ስትል ያቀረበችውም ቢሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 903
መሰረት ኑዛዜው ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ እስከ 7 ዓመት ድረስ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ወይም የፍርድ መዝገብ
ላይ ተፅፎ ካልፀደቀ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ በግልፅ በሕጉ የተደነገገ ከመሆኑም በተጨማሪ ተከሣሽ
የወ/እናታችን ህጋዊ ወራሽ ስለመሆኗ በሕጉ ላይ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ማለትም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000
(1) በተመለከተ ጊዜ ውስጥ ብቻ ማረጋገጥ እንደምችል የፌዴራል ጠ /ፍ/ቤት የሕግ ትርጉም በሰጠበት ጊዜ
ውስጥ መብቷን ያላረጋገጠች ስለሆነ በብይን መቃወሚያዋ ውድቅ ተደርጎ በጋራ በአንድ ቤት ውስጥ በመኖር
እየተጠቀምን የምንገኘው የውርስ ሀብት ተጣርቶ መብቷን ሳታረጋግጥ ያቀረበችውን ክርክር ተቀባይነት
በማሳጣት የአመልካቾች የውርስ ሀብት ነው እንዲባልልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
አስተያየቴም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሠረት በቃለ መሀላ በማረጋገጥ አቀርባለሁ፡፡
ቀን ------------------------------
ለሀዋሣ ከተማ የጠበቆች ሲቪል ማሕበራት ውል
ምዝገባና ክትትል የሥራ ሂደት
ሀዋሣ ፣
አመልካቾች፡- 1 ኛ . ወ/ሮ ገነት ዳሳ
2 ኛ. ማጋኔ ዲዳሞ
አድራሻችን ወንዶገነት ወረዳ ወተራና ቀጨማ ቀበሌ
የምናመለክተውም ጉዳይ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
አመልካቾች በወንዶገነት ወረዳ ወተራና ቀጨማ ቀበሌ ልዩ ስሙ አኖ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ ህጋዊ
የመንግሥት ግብር በ 2 ኛ አመልካች ስም እየገበርንበት ስንጠቀም ያቆየነውን የግል ይዞታችንን ሌጋሞ ደብሶ
በመባል የሚታወቀው ድንበርተኞችን ከሕግ ውጪ ጠቅልዬ ልያዝ በማለት በወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር
06709 የጋራ ንብረታችንን 2 ኛ አመልካችን ብቻ ለይቶ በመክሰስ ያሰጠው ፍርድ መብቴን የሚጎዳ መሆኑን
በመግለፅ ባቀረብኩት አቤቱታ ፍርዱ ተነስቶ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ጭምር ተጣርቶ ተወስኖልን እንደዱሮአችን
እየተጠቀምን የምንገኘውን ይዞታችንን የድንበርተኛችንና የተሟጋቻችን ጠበቃ የሆኑት አቶ አደፍርስ ተፈራ
በቀን 30/01/2005 ዓ/ም ፅፈው ለሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታቸው ከፍ/ቤቱ ለአሁኑ
አመልካቾች የሚላከው የመጥሪያ ትዕዛዝ በአድራሻችን ወተራና ቀጨማ በኩል ሊደርሰን እንደሚችል ገልፀው
አቤቱታው አቅርበዋል፡፡
በዚሁ መሰረት 1 ኛ ከሥር ወንዶገነት ወረዳ ፍ/ቤት ጀምሮ በአቶ አደፍርስ ተፈራ ጠበቃው አማካኝነት በሲ/ዞን
ከፍ/ፍ/ቤት ያቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ በመ/ቁጥር 27176 በቀን 6/2/05 በቀበሌያችን አማካኝነት እንዲደርሰን
ከፍ/ቤት የተላከልንን የመጥሪያ ትዕዛዝ ለቀበሌው ሳይሰጡና ቀበሌውም የላከው መግለጫ ሳይኖር እስር ቤት
ታስሮ ባለው ደንበኛቸው ስም አቤቱታ በማዘጋጀትና በማስፈረም መጥሪያውን ልቀበሉ ፈቃደኛ አይደለሙ
በማስባል ሲሟገተን የቆየው ሌጋሞ ዴቢሶ በሌላ በቀረበበት ወንጀል በወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት በወ/መ/ቁጥር 1977
በቀን 15/2/05 ዓ/ም በዋለው ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፎበት በ 1 ዓመት ከ 6 ወር የእስራት ቅጣት ታስሮ
እንዲቀጣ ተወስኖበት በእስር ቤት ያለውን ግለሰብ ጥብቅና የቆሙለትን ሰው እንዳልታሰራና ነፃ ሰው እንደሆነ
በማድረግ በ 19/2/05 እስር ቤት ባለው ደንበኛቸው ስም ፅፈው ፍ/ቤቱን ጭምር በማታለልና በማጭበርበር
መከሰሳችንን ሳናውቅ በሌለንበት በማስወሰን ልጆቻችንን የምናስተዳድርበትን ብቸኛ ይዞታችንን በሕገ ወጥ
መንገድ ለ 3 ኛ ወገን እንዲተላለፍብን በማድረጋቸው ፡፡
2 ኛ በፍርድ ቤት ውሳኔ ታስሮ በነበረው ደንበኛቸው ስም በቀን 19/2/05 ዓ/ም አቤቱታ ፅፈው በማስገባት ቃለ
መሀላውንም በአካል ቀርቦ እንደሰጠ በማስመሰል ፍ/ቤቱን ጭምር በማሳሳት እኚሁ የሕግ ባለሙያ በዕለቱ
በችሎት መቅረባቸው በመዝገቡ ላይ የተፃፈ ከመሆኑም በላይ ደንበኛው እስር ቤት እያለና በቀበሌያችን
አማካኝነት ፍ/ቤት መጥሪያ እንዲደርሰን ከተፃፈው

ውጪ ከቅን ልቦናና ለገንዘብ ካላቸው ከፍተኛ የአፍቅሮተነዋይ ፍላጎት በመነጨ በገንዘብና ጥቅም ተደልለው
በሌለንበት በማስወሰን ንብረታችንን /ይዞታችን / አሳጥተውናል፡፡
በአጠቃላይ የሕግ ባለሙያ ጠበቃ/ የፍትህ አጋዥ ትልቅ ሀይልና ተቋም ከመሆኑም በተጨማሪ መንግሥት
በየጊዜው ፍትህን ተደራሽ በማድረግና የተበላሸውንም አሰራር በማቃናት በመልካም አስተዳደር ዙሪያ በርካታ
ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በመስራት ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲያደርግ የቆየና እያደረገም በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት
እኝህ ጠበቃ ለቆሙለት ሙያና ለጠበቆች የሥነ ምግብር መመሪያ ተገዥ በመሆን ለህሊናቸው መስራት
ሲገባቸው በተቃራኒው መንገድ በመጓዝ በቀበሌያች አማካኝነት እንዲደርሰን የተላከልንን መጥሪያ በመውሰድ
ሳያደርሱ በ 15/2/05 ዓ/ም በፍርድ ታስሮ በነበረው ደንበኛቸው ስም የሐሰት ቃለ መሀላ በማዘጋጀት ደንበኛቸው
አመልካቾችን አፈላልጎ እንዳጣ በማድረግ ባቀረቡት አቤቱታ በሌለንበት ታይቶ እንዲወሰን በማድረግ
መተዳደሪያች የሆነውን ይዞታ ከእጃችን እንዲወጣ በማድረግ ከይዞታው የሚገኘውን ጫት ከደንበኛቸው ጋር
እየሸጡ በመጠቀም ላይ የሚገኙ ስለሆነ በፈፀሙት ከባድ የሥነ ምግባር ጥፋት በሕግ እንዲጠየቁና ለሌሎችም
ምሳሌና ሊያስተምራቸው የሚችል እርምጃ እንዲወሰድባቸው እያመለከትን፡-
ሀ. ከሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ባለንበት ወ/ገነት ወተራና ቀጨማ ቀበሌ አማካኝነት የመጥሪያ ትዕዛዝ እንዲደርሰን
የተላከልንን -- ገፅ
ለ. በወንዶ ወረዳ ፍ/ቤት ተፈርዶበት እስር ቤት ውስጥ እያለ በጠበቃው አማካኝነት ችሎት በአካል ቀርቦ ቃለ መሀላ
እንዲሰጠ በማስመሰል መጥሪያውን ሊቀበሉኝ አልቻሉም በማለት በ 19/2/05 ዓ/ም የተፃፈ ከእነ አማርኛ
ትርጉም --- ገፅ
ሐ. የጠበቃው ደንበኛ በጠበቃው አማካኝነት ለፍ/ቤት ቃለ መሐላ ፅፎ ከማቅረቡ 4 ቀን በፊት በ 15/2/05 ዓ/ም በፍርድ
1 ዓመት ከ 6 ወር የተፈረደበትን የሚገልፅ ሰነድ ---- ገጽ
መ. ፍ/ቤቱን ያሳሳተው የሐሰት ቃለ መሀላ በቀረበ በ 19/2/05 ዓ/ም እኚሁ ጠበቃ ችሎት መቅረባቸው በውሳኔው ላይ
ቀርቧል ተብሎ የተገለፀበት ከእነ ትርጉሙ -- ገፅ
ሠ. በቀረበው የሐሰት ሰነድ መነሻ በፍርድ መብታችንን ያጣንበት ውሳኔ --- ገፅ
ለደንበኛው የተወከሉበት የውክልና ማስረጃ --- ገፅ በድምሩ -- ገፅ አያይዘን እያቀረብን በሕግ ተጣርቶ ተገቢውና
ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ስንል በአክብሮት እናመለክታለን፡፡
አመልካቾች፡- 1 ኛ . ወ/ሮ ገነት ዳሳ -------
2 ኛ. ማጋኔ ዲዳሞ --------
ቀን -------------------------------
ለሲዳማ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
ከሣሾች፡- 1. ወ/ሮ ገነት ዳሳ
2. ማጋኔ ዲዳሞ
አድራሻ፡- ወ/ገነት ወረዳ ወተራና ቀጨ ማ ቀበሌ
ተከሣሽ፡- ሌጋሞ ዴቢሶ
አድራሻ፡- ወ/ገነት ወረዳ
በሐሰት ተዘጋጅቶ በቀረበ ሰነድ የተሰጠውን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 6 (1) (ሀ) መሠረት እንደገና ዳኝነቱ
ታይቶና ተጣርቶ ለማስወሰን የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡
ሀ) የአቤቱታው አቀራረብ
- ውሳኔው እንደገና ታይቶ ዳኝነት እንዲሰጥበት የተጠየቀው ፍርድ የሰጠው በዚሁ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 27176 በቀን
27/02/05 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- ከፍ/ቤቱ የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ ከተከሣሽ አድራሻ --------------- ቀበሌ አማካኝነት ለማድረስ
እንችላለን፡፡
- አቤቱታችንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 223 መሠረት ተሟልቶ ቀርቧል፡፡
ለ) የአቤቱታችን ዝርዝር በአጭሩ
አመልካቾች በወንዶገነት ወረዳ በወተራና ቀጨማ ቀበሌ ልዩ ስሙ አኖ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ በስተሰሜን
ለሕዝብ መንገድ በስተደቡብ ለተጠሪ ሌጋሞ ዴቢሶ በስተምስራቅ ለአቶ ዳባ ቤንዶ በስተምዕራብ ለተጠሪ ሌጋሞ
ደቢሶ የሚያዋስነውን 30x120=3,600 ካሬ ሜትር የሆነ ስፋት ያለውን የእርሻ ይዞታችንን ለበርካታ ዓመታት
በመያዝ በ 2 ኛ አመልካች ስም የመንግሥት ግብር እየገበርን ያቆየነውን ተጠሪ ከቅን ልቦና ውጪ በመሆን
ይዞታችንን ለመቀማት በሥር የወንዶ ገነት ወ/ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁጥር 06709 ላይ 2 ኛ አመልካችን ከሶ ያሰጠው
ፍርድ ሳልከሰስና መልስ ሳልሰጥ የተሰጠው ውሳኔ መብቴን የሚነካ መሆኑን በመግለፅ ፍርዱ ተነስቶ ወደ ዋናው
ክርክር ገብቼ በማስረጃ ተጣርቶ እንዲወሰን 1 ኛ አመልካች ባቀረብኩት አቤቱታ መሠረት የሰውና የሰነድ ማስረጃ
ተጣርቶ በ 2 ኛው አመልካች የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ በፍርድ ተወስኖልን ባለመብት መሆናችን የተረጋገጠበትን
ውሳኔ ለማስለወጥ የተጠሪ ጠበቃ አደፍርስ ተፈራ በ 30/01/2005 በፃፈው ይግባኝ አቤቱታው ለአሁኑ አመልካቾች
ከፍ/ቤት የሚላከው የመጥሪያ ትዕዛዝ በቀበሌያችን በኩል እንደሚደርሰን ጭምር በመግለፅ ያቀረበው 27176 የሆነ
የይግባኝ የፍትሐብሔር መዝገብ ተከፍቶ ከታየ በኋላ ያስቀርባል ተብሎ ለሁለታችንም አመልካቾች በቀን
06/02/05 ወጪ ተደርጎ 12 ገፅ የተላከልን ቢሆንም ለተባለው ወተራና ቀጨማ ቀበሌም የመጥሪያ ትዕዛዙ
ሳይደርስና ከቀበሌውም የተላከ መግለጫ በሌለበትና ተጠሪ ቀደም ሲል በፈፀመው ወንጀል በወንዶገነት ወ/ፍ/ቤት
በወ/መ/ቁጥር 1977 በቀን 15/02/05 ዓ/ም በዋለው ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎበት በአንድ ዓመት ከ 6 ወር
እስራት ታስሮ እንዲቀጣ ተወስኖበት ሀዋሣ ማረሚያ ተቋም እስከሚላክ ድረስ በወ/ገነት ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ
እያለ ከእስር ቤት ውጪና ነፃ እንደሆነ ሰው

ተቆጥሮ በፍርድ የ 1 ዓመት ከ 6 ወር እስራት ከተወሰነበት ከ 4 ቀን ቆይታ በኋላ በጠበቃው አቀነባባሪነት በ 19/2/05
ዓ/ም በተፃፈ ቃለ መሀላ አመልካቾች መጥሪያውን ልቀበሉኝ አልቻሉም በሚል መሰሎቹን ማስረጃ በመቁጠር
በሕግ ቁጥጥር ሥር በነበረው በአሁኑ ተጠሪ ፊርማ በሐሰት በቀረበው አቤቱታ ፍ/ቤቱን ጭምር በማሳሳትና
በማታለል በሌለንበት ያሠጠውን ፍርድ ያወኩት ከሀዋሳ ማረሚያ ተቋም ታስሬ ከነበርኩበት ወጥቼ ይዞታዬን
ከጎበኘሁ በኋላ በ 16/12/05 ዓ/ም በአረም የተበላሸውን ጫቴን ለማረም ወደ ይዞታዬ ስገባ አይቶኝ የሥር ወ/ገነት
ወረዳን ውሳኔ በይግባኝ አሽሬአለሁ የይዞታው ባለመብት መሆኔን አረጋግጫለሁ ሲል ባስነሳው ሁከት ለማወቅ
በመቻላችን የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡
ሐ) የተከበረውን ፍ/ቤት የምንጠይቀው ዳኝነት
1 ኛ/ ተጠሪ በወ/ገነት ወረዳ ፍ/ቤት በወ/መ/ቁጥር 1977 በቀን 15/2/05 ዓ/ም በዋለው ችሎት የ 1 ዓመት ከ 6 ወር
የእስራት ቅጣት ተወስኖበት እስር ቤት እያለ አመልካቾች መጥሪያውን ሊቀበሉኝ አልቻሉም የሚል እስር ቤት
በገባ በ 4 ኛው ቀን በ 19/2/05 በጠበቃው አማካኝነት በተፃፈ አቤቱታ ቃለ መሀላ ላይ ፈርሞ ባቀረበው የሐሰት
ሰነድ ፍ/ቤቱን አታሎና አጭበርብሮ በሌለንበት ያሰጠው ውሳኔ ስለሆነ እንደገና ታይቶ ዳኝነትን እንዲሰጠን ፡፡
2 ኛ/ በሌለንበት እንዲወሰን በተጠሪ ተፈርሞ የቀረበው ቃለ መሀላ በቀረበ ዕለት የተጠሪ ጠበቃ አደፍርስ ተፈራ
በችሎት ቀርቧል ተብሎ የተመዘገበ ከመሆኑም በተጨማሪ ጠበቆች የፍትህ አጋዥ አካል ሆነው ሳሉ ሕግን
በመተርጎም ለሕብረተሰቡ እውነተኛውን ዳኝነት እንዲሰጡ በሕዝብና በመንግሥት አመኔታ የተጣለባቸውን
ዳኞችን በማታለልና በማጭበርበር መብታችን ያሣጡትን ጠበቃ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና እንዲማሩበትም
ጭምር ለክልሉ ፍትህ ቢሮ የጠበቆችና የድስፕሊን ኮሚቴ እንዲመራልን እንዲሁም ተጠሪ በሰው የማታለልና
የማጭበርበር ስራው እንዲጠየቅ ለዐቃቤ ህግ ተመርቶ በወንጀል እንዲጠየቅ እንዲደረግልን፣
3 ኛ/ ከፍ/ቤት የተላከልንን የመጥሪያ ትዕዛዝ በቀበሌያችን ወተራና ቀጨማ በኩል እንዲደርሰን ቢፃፍም ለቀበሌው
ሳይደርሰው የተላከ ሕጋዊ መግለጫ በሌለበት ተጠሪና ጠበቃው በሐሰት በተንኮል አቀነባብረው ባቀረቡት የሐሰት
ሰነድ በሌለንበት የተሰጠው ፍርድ ከፍ ተብሎ በተጠቀሰው ሕግ መሰረት እንደገና ታይቶ ዳኝነት እንዲሰጠን፣
4 ኛ/ ተጠሪ በቃለ መሀላ አስደግፎ ባቀረበው አቤቱታ ላይ በማስረጃነት የተጠቀሱት በወንጀል ከሳሼ ያስፈረድኩባቸውና
የተጠሪ ወ/እናት ከመሆናቸውም በተጨማሪ በሐሰት በቀረበ ሰነድ በሌለንበት መወሰኑን ያወኩትም በ 16/12/05
ዓ/ም ይዞታው ለእኔ ነው የተወሰነልኝ ከይዞታዬ ውጣ ብሎ በፈጠረው ሁከት ለማወቅ የቻልኩ ስለሆነ ቀደም ሲል
በሐሰት በቀረበ ሰነድ ፍ/ቤቱን ጭምር በማሳሳት የተሰጠው ፍርድ በድጋሚ እንደገና ታይቶና ተጣርቶ ዳኝነት
እንዲሰጠን ስንል በአክብሮት እናመለክታለን፡፡
አቤቱታችንም በእውነት የቀረበ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁጥር 92 መሰረት በቃለ መሀላ በማረጋገጥ
እናቀርባለን፡፡ ከሣሾች፡- 1. ወ/ሮ ገነት ዳሳ
2. ማጋኔ ዲዳሞ
ቀን -------------------------------

ለሲዳማ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት


ሀዋሣ ፣

ከሣሾች፡- 1. ወ/ሮ ገነት ዳሳ


2. ማጋኔ ዲዳሞ
አድራሻ፡- ወ/ገነት ወረዳ ወተራና ቀጨማ ቀበሌ
ተከሣሽ፡- ሌጋሞ ዴቢሶ
አድራሻ፡- ወ/ገነት ወረዳ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 223 መሰረት የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
የሰነድ ማስረጃ
1. በአድራሻችን ወተራና ቀጨማ ቀበሌ በኩል ከዚህ ፍ/ቤት የተላከልን የመጥሪያ ትዕዛዝ እንዲደርሰን
የተላከበት 5 ገፅ
2. መጥሪያ እንዲደርሰን ከተላከለት ቀበሌ ውጪ በወ/ገነት ፍ/ቤት ወ/መ/ቁጥር 1977 በቀን 15/2/05 ዓ/ም
በዋለው ችሎት በፍርድ ተፈርዶበት እስር ቤት ከገባበት 4 ኛው ቀን በኋላ በ 19/2/05 ዓ/ም መጥሪያ
ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም ሲል በሐሰት ያቀረበው ቃለ መሀላ 2 ገፅ በወቅቱ እስር ቤት ስለመሆኑ
የሚገልፅ የፍ/ቤት ውሳኔ 2 ገፅ በድምሩ 9 ገፅ ተያይዟል፡፡
የሰው ማስረጃ
1. በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 261 (2) መሰረት ከሣሾች
2. ዘሪሁን ሰንበቶ
3. ፍሊሞስ ዲዳሞ
4. በላቸው በቀለ ናቸው፡፡
የማስረጃ መግለጫውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሰረት በቃለ መሀላ ተረጋግጦ ቀርቧል፡፡
ከሣሾች
1. ወ/ሮ ገነት ዳሳ ---------
2. ማጋኔ ዲዳሞ---------
ቀን 24/12/2005 ዓ/ም
ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
ይግባኝ ባይ ፡-ኢንስፔክተር አደን ማሬ
አድራሻ፡- ዲላ ማረሚያ ተቋም
መ/ሰጪ ፡- የክልሉ ሥ/ፀ/ሙ/ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ
- የሥር የሰ/አ/ሕ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት ሶያማ ምድብ ችሎት መ/ቁጥር 01946
በወ/መ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁጥር 189 (1) መሰረት የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
ሀ) የአቤቱታው አቀራረብ
- የይግባኝ አቤቱታው የቀረበበትን ፍርድ የሰጠው የሰ/አ/ሕ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት ሶያማ ምድብ ችሎት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 01946 በቀን 16/12/05 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- የሥር ፍ/ቤት የውሳኔ መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ 134 ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ) ለይግባኝ አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የይግባኝ አቤቱታ ለዚህ ፍ/ቤት ሊቀርብ የቻለው የክልሉ የሥ/ፀ/ሙ/ከሣሽ ዐቃቤ ሕግ በቁጥር
56/2951 በቀን 13/10/05 ዓ/ም ፅፎ ለሥር ፍ/ቤት 1 ኛ ክስ የወ/ሕግ/ቁጥር 32(1) ሀ) 33 እና 407(2) ላይ
የተመለከተውን በመተላለፍ የታርጋ ቁጥር ኮድ 3-11656 የሆነ ቅጥቅጥ አይሱዙ መኪና በኮንትሮባንድ ዕቃ
መጫን ምክንያት ተይዞ በቡርጂ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ እንዲትቆይ በተደረገበት የኮንትሮባንድ እቃ መደበቂያ
/ሻግ/ ከተገጠመበት እንዲፈታ አስደረገ የሚል ሲሆን 2 ኛው ክስ ደግሞ የወ/ሕግ/ቁጥር 32(1) (ሀ) 408(1)
ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በቡርጂ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ሆኖ ሲሰራ በቡርጂ መስመር ወደ
አማሮ የሚገቡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን እንዳይገባ ለማስደረግ ከኢት/ንግድ ባንክ ያቬሎ ቅርንጫፍ ከአቶ
አማዶ አድክሬ የተላከለትን ብር 2500 ፈርሞ በመቀበሉና ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለእራሱ ለማስገኘት
በፈፀመው የጉቦ መቀበል ወንጀል ተከሶዋል የሚል ነው፡፡ ፍ/ቤትም በመቅረብ የተጠቀሰብኝን ድርጊቶች
አለመፈፀሜንና ጥፋተኛ አለመሆኔን በመግለፅ ክጄ ተከራክሪያለሁ፡፡ ዐ/ሕግም የወንጀል ድርጊቱን
ያስረዱልኛል ሲል አቅርቦ ያሰማቸው የሰው የምስክርነት ቃል ባቀረብኳቸው የሰውና የመከላከያ ማስረጃዎቼ
የምስክርነት ቃልና በሰነድ ማስረጃ በሚገባ በማስተባበል ያሰማሁትን ያለአንዳች በቂና ሕጋዊ ምክንያት
ተቀባይነት በማሳጣት በ 16/12/05 ዓ/ም በዋለው ችሎት የጥፋተኝት ውሳኔ በመስጠት በ 4 ዓመት ከ 5 ወር
የእስራት ቅጣት ታስሬ እንዲቀጣና ብር 4000 መቀጮ እንዲከፍል የተላለፈብኝ ውሳኔ ቅር በመሰኘት
ፍርዱን ለማስለወጥ የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
ሐ) በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ
1 ኛ/ በ 1 ኛው ክስ የኮንትሮባንድ ዕቃ ጭኖ በቡርጂ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ሥር ከዋለው አይሱዚ መኪና
ላይ በድብቅ የተገመጠውን የኮንትሮባንድ ዕቃ መጫኛ መደበቂያ ሻግ በ 12/12/04 አስፈታ ተብሎ በዐቃቤ ሕግ የክስ
ቻርጅ ላይ በፅሁፍ ከመግለፅ ያለፈ በየትኛውም የዐቃቤ ሕግ

ማስረጃ በእኔ ትዕዛዝ ሻጉ መፈታቱን ያልተመሰከረ ከመሆኑም በተጨማሪ በ 1 ኛው የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ኮን/ል
ዘዳግም የተባለውን መኪና የምጠግኑ ሰዎች ስለሚመጡ አትከልክሏቸው ብሎ አዘዘን ሲል 3 ኛው ደግሞ ይግባኝ ባይ
አስቀድሞ ሞተር ይዞ ከግቢ ሲወጣ አየሁት እንጂ ከዚያ በኋላ አላየሁትም በማለት 1 ኛው የሰጠውን የምስክርነት ቃል
በማፍረስ ሲመሰክር የተቀሩት ያልመሰከሩብኝ ከመሆኑም በላይ መኪናውን የምጠግኑ ሰዎች ሲመጡ አትከልክሏቸው
ብሎ ትዕዛዝ መስጠቱንና ሻጉ ሲፈታ የመካኒክ ሙያ ያለው 3 ኛው ማስረጃ አብሮት ከሰሰው ሰው ውጪ ይ/ባይን
አለማየቱን ሲገልፅ በፍ/ቤቱ ማጣሪያ መኪናው ካለበት በርቀት ማየቱን በመመስከር ዐቃቤ ሕግ በ 1 ኛ ክስ ላይ
ያስረዱልኛል ሲል ከገለፀው ድርጊት እጅግ በተለየ መልኩ በመግለፅ በክሱ ቻርጁ ላይ የተገለፀውን ድርጊት በመግለፅ
አልመሰከሩም በተጨማሪም የዐ/ሕግ ማስረጃዎች የምስክርነት ቃል እርስ በእርሱ የምጣረስና የአንዱን ሌላኛው
የሚያስፈርስ በመሆኑ ሳይመሰክሩ እንደመሰከሩ ተቆጥሮ ይታለፍ በሚል ከዐቃቤ ሕግ በቀረበው አስተያየት
የታለፉትም ቢሆኑ ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ከሰጡት ውጪ የተለየ አስተያየት የታለፉትም ቢሆኑ ቀርበው
የምስክርነት ቃላቸውን ከሰጡት ውጪ የተለየ እንደማይመሰክሩ በከሣሽም ጭምር በመገለፁ የተነሳ እንደከሣሽ የክስ
መሰረት ተመስክሮዋል የሚያሰኝ ካለመሆኑም በተጨማሪ ሻጉ ተፈታ በተባለበት በ 12/12/04 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል
ቦረና ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ ከመደባ ቀበሌ ከቡርጂ ሶያማ የመጡ ለቦች መያዛቸውን ተገልፆለት ከሌሎች አመራሮች
ጋር በመሆን በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ከተያዙት ሌቦች ውስጥ አንደኛው በመጥፋቱ ሲፈልጉ ቆይቶ ሌባውን
አግኝተው በመያዝ በ 11 ሰዓት ልጆቹን በመያዝ ወደ ሶያማ መመለሱንና በዕለቱ በኦሮሚያ ክልል አብረው
መዋላቸውን በመግለፅ አስረግጦ በመመስከር የተከላከለ ከመሆኑም በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ቡሌ ሆራ
ወረዳ መዲባ ቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤትም በ 12/12/04 ዓ/ም በቀበሌው ሊቀመንበር ረኖ ሮባ ተብሎ በሚጠራው
ግለሰብ ተረጋግጦ የተፃፈውን ደብዳቤ (የሰነድ ማስረጃ) በመከላከያነት ባቀርብም የተባለ አንዳች ነገር ሳይኖር
በዝምታ የታለፈ ከመሆኑም በላይ በወ/መ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁጥር 149 (1) መሠረት ማስረጃው ተቀባይነት ያላገኘበትን
አጭር የፅሁፍ መግለጫ በውሳኔው ሳይገለፅና ስለሰነድ ማስረጃ የተባለ ነገር ሳይኖር የቀረበብኝን ክስ በሰውና በሰነድ
ማስረጃ ከበቂ በላይ አስረግጬ በማስረዳት ተከላክዬ ሳለሁ ታልፎ የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ማሳለፉ አግባብ
ባለመሆኑ በጥልቀት ተመርምሮ እንዲሻርልኝ ፡፡
2 ኛ/ ዐቃቤ ሕግ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወ/ሕግ አንቀፅ 32 (1) (ሀ) እና 408 (1) የተደነገገውን በመተላለፍ በፖሊስ አዛዥነቱ
አማዶ አድክሬ ከተባለው ግለሰብ ላይ ለኢት/ንግድ ባንክ ያቬሎ ቅርንጫፍ ኢት/ንግድ ባንክ ከሶያማ ቅርንጫፍ በኩል
የተላከለትን ጉቦ ብር 2500 ወስደ በሚል የባንክ እስሊፕ በማስረጃነት አቅርቦ በማያያዝ ለቀረበብኝ ክስ ገንዘቡን
የላከው የእህቴ አረጋሽ ማሬ ልጅ መሐመድ ቦጋለ ተብሎ የሚጠራው ሞያሌ ገጠር አካባቢ በመኖር ሠርቶ
ከሚያገኘው ገንዘብ በየጊዜው /በየዓመቱ/ ለእናት አባቱና ሚስቱን ጨማሮ ለልጆቹ ጭምር በእኔ አጎቱ አማካኝነት
ትክክለኛና ታማኝ ሰው ሲያገኝ በሰው በኩል ሰው ባላገኘ ጊዜ ደግሞ በጓደኛው ባንክ አስገብነት

በስሜ ልኮ ለቤተሰቡ ገንዘቡን አድርሼላቸው መጠቀማቸውን አርሶ አደር የሆነው ወ/አባቱ ቦጋለ ማሞ ቀርቦ
የምስክርነት ቃሉን በመስጠት የዐ/ሕግን ክስ በማስተባበል መሰከረ፡፡ ከሣሽም በክሱ እንደገለፀው ጉቦ አለመሆኑን
በግልፅ ከማስረዳቴም በተጨማሪ ጉቦ በባንክ በኩል ላከ የተባለው አማዶ አድክረ ቀርቦ በእርግጥ በክሱ ላይ
እንደተጠቀሰው ጉቦ መሆኑን ባላስረዳበትና ባልመሰከረበት እንዲሁም ጉቦ ተቀበለ በሚል ቀርቦ የምስክርነት ቃል
የሰጠ ሰው በሌለበት በባንክ ቤት ተቀብለሃል በሚል የተሰጠው የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ አግባብ ካለመሆኑም
በተጨማሪ በዐቃቤ ሕግ ክስ ላይ ብር 10,000 መውሰዴ ባልተገለፀበት አብሮኝ በ 2 ኛ ተከሳሽነት በተከሰሰው ላይ
የዐቃቤ ሕግ ማስረጆች በውሳኔው መዝገብ /በችሎት ሥራ/ ገፅ 7 ላይ ሌላኛው ሰው የተባለውን ገንዘብ
ገብቼላቸዋለሁ ብሎ ነገረኝ ሲል 3 ኛው የዐ/ህግ ምስክር በሰሚ ሰሚ የሰጠው ምስክርነት እንደዋነኛ ማስረጃ
በመቀበል በክስ ቻርጅ ላይ ያልተጠቀሰውን በመግለፅ ቅጣቱን አክብዶ ለማሳሳር በማሰብ የገንዘብ መጠን ተገልፆ
ቅጣቱ ከብዶ የተጣለብኝ የእስራት ቅጣትና የገንዘብ መቀጮ በሕግ ላይ ያለኝን ከፍተኛ እምነት ያዛባና ከፍተኛ
ቅሬታ ያሳደረብኝ ጉዳይ ነው፡፡
በተጨማሪ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ 1/2002 መሠረት
የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ከፍርድ በፊት መስጠት ሲገባኝ ፍ/ቤቱ የእራሱን የቅጣት ውሳኔ ከጣለ በኋላ አስተያየት
ጠይቆ በመቀበል አሻሽሎ ለመወሰን ቢሞክርም በክሱ ላይ ያልተጠቀሰውንና ያልተከሰስኩበትን ገንዘብ በማከል
ጥፋተኛ አድርጎ ያስተላለፈው የ 4 ዓመት ከ 5 ወር የእስራት ቅጣትና ብር 4000 በሕግ አግባብ ያልታየ ልታረም
የሚገባው ከመሆኑም በተጨማሪ በሪከርድነት ተመዝግቦ የቀረበብኝ ሰነድ ባለመኖሩ ቅጣቱ እስራቱ በኢፊዲሪ
የወ/ሕግ አንቀፅ 194 መሠረት ታግዶ ከእስር ቤት እንዲለቀቅ ያቀረብኩትን አቤቱታ ተቀባይነት በማሳጣት የቅጣት
ውሳኔ ማሳለፉ አግባብ አይደለም፡፡
በአጠቃላይ የወንጀል ሕግ ዓላማ ጥፋተኞች ተፀፅተው ከድርጊታቸው በመቆጠብ ሰላማዊና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ
ማድረግ እና ማብቃት እንደሆነ የምታመን ሲሆን በተያዘው ጉዳይ ይ/ባይ በቀረበብኝ ክስ በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ
ያልተመሰከረብኝና ባቀረብኳቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃ በሚገባ ክሱን ያስተባበልኩ ስለሆነ የሥር ፍ/ቤትን
የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195 (2) (ለ) (1) መሰረት በመሻር በነፃ እንዲያሰናብተኝ
ወይንም ቅጣቱን በኢ/ፌ/ዲሪ የወ/ሕግ አንቀፅ 194 መሰረት በማገድ ከእስር ቤት መውጣት እንዲችል
እንዲወሰንልኝ ስል በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡
ይግባኝ ባይ
የሕግ ታራሚ ኢ/ር አደን ማሬ
ነሐሴ 24 ቀን 2005 ዓ/ም
ለሀዋሣ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት
የምስራቅ አካባቢ ምድብ ችሎት
ሀዋሣ ፣

አመልካች ወ/ሮ አለሚቱ ተሾመ


አድራሻ ሀዋሣ ም/ክ/ከ/ውቅሮ ቀበሌ
ተጠሪ፡- አቶ ደሳለኝ መስቀሌ
አድራሻ ሀዋሣ ም/ክ/ከተማ ውቅሮ ቀበሌ
ጉዳዩ፡- በክልሉ የቤተሰብ አዋጅ ቁጥር 75/96 አንቀፅ 212 መሰረት ተጠሪው ቀለብ እንዲቆርጥልኝ የቀረበ
አቤቱታ ነው፡፡
- ፍ/ቤቱ አቤቱታውን ተቀብሎና ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት በቀጥታ ሥልጣን አለው፡፡
- ከሣሽና ተከሳሽ የሕግ ችሎታ የላቸውም አልተባለም፡፡
- ከዚሁ ፍ/ቤት ለተከሣሽ የሚላከውን የፍ/ቤት ትዕዛዝና መጥሪያ የደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን
ድርጅት ጽ/ቤት በኩል እንዲደርሰው እንዲታዘዝልኝ እጠይቃለሁ፡፡
የቀረበው አቤቱታ በአጭሩ
1.1 እኔ አመልካች ከተጠሪው ጋር ከጋብቻ ውጭ ባደረግነው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሕፃን ደግነሽ ደሣለኝ
የተባለችውን ሚያዚያ 6 ቀን 2005 ዓ/ም ወልጃለሁ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተጠሪው ልጅቷ የእኔ አይደለችም ብሎ በመካዱ አባትነቱ እንዲረጋገጥልኝ ለሀዋሣ
ከተማ ከፍተኛው ፍ/ቤት አቤቱታ አቅርቤ የተከበረው ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 14347 በቀን 22/12/05 በዋለው
ችሎት በክልሉ የቤተሰብ አዋጅ ቁጥር 75/96 አንቀፅ 158 (1) እና 159 መሰረት የአባትነት ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
ስለዚህ በዚህ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ተጠሪው የልጄ የቀለብ ተቆራጭ በአንቀፅ 212 መሰረት
እንዲወሰንልኝ የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡
ፍ/ቤቱን የምለምነው ዳኝነት
2.1 ከላይ በአቀረብኩት አቤቱታዬ መሰረት የሕፃን ደግነሽ ደሣለኝ በቂ የቀለብ ተቆራጭ ተጠሪው እንዲቆርጥልኝ
ውሳኔ እንዲሰጠኝ እያመለከትኩኝ ይህ የቀረበው አቤቱታ እውነት መሆኑን በፍ/ህግ/ሥ/ሥ/ቁጥር 92 መሰረት
በቃለ መሀላ አረጋግጣለሁ፡፡
አመልካች

ወ/ሮ አለሚቱ ተሾመ


ነሐሴ 24 ቀን 2005 ዓ/ም

ለሀዋሣ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት


የምስራቅ አካባቢ ምድብ ችሎት
ሀዋሣ ፣

አመልካች ወ/ሮ አለሚቱ ተሾመ


አድራሻ ሀዋሣ ም/ክ/ከ/ውቅሮ ቀበሌ
ተጠሪ፡- አቶ ደሳለኝ መስቀሌ
አድራሻ ሀዋሣ ም/ክ/ከተማ ውቅሮ ቀበሌ
በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 223 መሰረት የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር
የሰነድ ማስረጃ
1. ሁለት ገፅ ፎቶ ኮፒ የአባትነት ውሳኔ የተሰጠበት ዋናው በሀዋሣ ከተማ ከፍተኛው ፍ/ቤት ይገኛል፡፡
የሰው ማስረጃ
1/ ትዝታ ሙሬ አድራሻ ሀዋሣ ከተማ
2/ ሐረጉ ሙሉሳ ›› ›› ››
3/ ዘሪቱ ጥበቡ ›› ›› ››
ይህ የቀረበው አቤቱታ እውነት መሆኑን በፍ/ህግ/ሥ/ሥ/ቁጥር 92 መሰረት በቃለ መሀላ አረጋግጣለሁ፡፡
አመልካች

ወ/ሮ አለሚቱ ተሾመ


ቁጥር -------------------------------
ቀን --------------------------------

ለ ------------------------------------- ድርጅት
ለአቶ/ወ/ሮ --------------------------------------
ሻሸመኔ

ጉዳዩ፡- ስፖንሰር /ትብብር/እንዲደረግልን ስለመጠየቅ ፣


ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው አዲስ ራዕይ ሕፃናትና ኤች አይ ቪ ኤድስ ተንከባካቢ
ማሕበር በሻሸመኔ ከተማ ወገን ለወገን ደራሽ በሚል መሪ ቃል በሕገወጥ የሕፃናት ዝውውርና በኤች
አይ ቪ ኤድስ የተያዙ ሕፃናትና ወጣቶች እንዲሁም አረጋዊያንን ይህ ማሕበር መጠነ ሰፊ ሥራዎችን
ከመንግሥት ጎን ለጎን አብሮ እየሰራ እንክብካቤና ጥበቃ ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ይህንን
አላማ ለማራመድ መንግሥት የበኩሉን አስተዋጽኦ ቢያደርግም የከተማው ባለሀብትና ድርጅት
ለከተማ የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ ሁሉ እነዚህ ሕፃናትና ወጣቶች ሰብስበን መሠረታዊ ፍላጎቶች
ለማሟላት የገንዘብ እጥረት ስለገጠመን በድርጅትዎ በኩል የበኩሉዎን አስተዋፅኦ ወይም ስፖንሰር
እንዲያደርጉ እየጠየቅን ስለሚደረግልን መልካም ትብብር ሁሉ በቅድሚያ እናመሰግናለን፡፡

‹‹ ሕገ ወጥ የሕፃናት ዝውውርና
ኤች አይ ቪ ኤድስን በጋራ እንከላከል ››
ቀን -------------------------------
ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
ይግባኝ ባዮች፡- 1. ፍላቴ ኦትሶ
2. ኦንቻ ሻጋራ
3. አስፋው ሻጋራ
4. እንዳለ ፍላተ
5. ማኔ ማልካቶ
አድራሻ፡- ሎካ አባያ ወረዳ አርገዳ ሀሮድንቶ ቀ/ገ/ማሕበር
መ/ሰጭዎች ፡- 1. መኮንን ቅጤሳ
2. ባጄሶ ቅጤሳ
3. ከርሶ ቅጤሳ
አድራሻ፡- ሎካ አባያ ወረዳ አርገዳ ቀ/ገ/ማሕበር
- የሥር የዳሌ ወረዳ ፍ/ቤት መ/ቁጥር 05508
- የሥር የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 29444
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 327 መሰረት ቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው
ሀ) መግቢያ
- የይግባኝ አቤቱታው የቀረበበትን የመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 29444 በቀን 17/11/05 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- ለመ/ሰጪዎች ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ የ 1 ኛ እና 2 ኛው በ 3 ኛው መ/ሰጪ አማካኝነት
ሊደርሳቸው ይችላል፡፡
- የፍ/ቤት የውሳኔ መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ 70 ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ/ ለይግባኝ አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የይግባኝ አቤቱታ ለዚህ ፍ/ቤት ሊቀርብ የቻለው በአርጋዳ ቀበሌ ውስጥ የሁለት ቀበሌ ሕዝብ ለከብት
ግጦሽ (ሣር) የምጠቀምበትን ያልታረሰ ድንግል መሬት የአሁኑ መ/ሰጪዎች በላዩ ላይ ያሠፈርነውንና የግላችን
በሆነው ውስጥ ዘልቀው በመግባት አትክልቶችን ነቃቅለው ከጥቅም ውጪ አደረጉብን ሲሉ በሐሰት በዐቃቤ ሕግ
በወንጀል ቀደም ሲል በሎካ አባያ ወ/ፍ/ቤት ቀርቦብን የነበረውን የወንጀል ክስ በጥልቀት በማስረጃና ስፍራው ድረስ
በመሄድ አጣርቶ መሬቱ የሁለት ቀበሌ ለከብት ግጦሽ የሚጠቀሙበት ያልታረሰ መሆኑን ጭምር አጣርቶ ምንም
የተነቀለም ሆነ የታረሰ ነገር አለማየቱንና መሬቱም ያልታረሰ ድንግል መሆኑን በማየት በሐሰት ከቀረበብን የወንጀል
ክስ በነፃ ከተሰናበትን በኋላ ንብረት ወደመብን ሲሉ በፍትሐብሔር ክስ በሥር ዳሌ ወ/ፍ/ቤት ያቀረቡብንን የንብረት
ግምት (የገንዘብ ክስ) በፍ/ቤቱ ተጣርቶ ለ 2 ኛ ጊዜ በፍርድ በነፃ ብንሰናበትም በይግባኝ ተቀብሎ የተመለከተው
የሲዳማ ዞን በየትኛውም የመንግሥት ተቋም
ተጨፈጨፈ የተባለው የንብረት ግምት በግብርና ባለሙያ ተገምቶ ባልቀረበበት የአሁኑ መ/ሰጪዎች
በመሰላቸው መልኩ በእራሳቸው ስሌት በማስላት በሐሰት ያቀረቡትን ብቻ በመመልከት እያዳንዳችን ብር 778
(ሰባት መቶ ሰባ ስምንት) ብር ይክፈሉ ተብሎ የተሰጠውን አስገራሚ ፍርድ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ
ያቀረብነው የይግባኝ አቤቱታችን ነው፡፡
ሐ) በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልን የምንጠይቀው ዳኝነት
1. በአንድ ይዞታ ላይ የሰፈረ አትክልት በሌላኛው ወገን መጨፍጨፉ ከተነገረ በመጀመሪያ መጨፍጨፉ ሊረጋገጥ
የሚገባ ከመሆኑም በተጨማሪ የተጨፈጨፈው አትክልት አይነት የእድገት ደረጃው ወይንም ለውጤት የደረሰ
ከሆነ የአንዱ ኪሎ ግራም በአካባቢው ዋጋ ምን ያክል ልሸጥ እንደምችል ጭምር ተረጋግጦ ጉዳዩ
በሚመለከተው የወረዳው ግብርና ጽ/ቤትና ግብይት ጽ/ቤት ባለሙያዎች በሚገባ ተረጋግጦ ሲቀርብ ብቻ
ልወሰን ሲገባው መ/ሰጪዎች ባቀረቡት መነሻ በየትኛውም ባለሙያ ሳይረጋገጥ እንድንከፍል የተጣለብን ውሳኔ
በሕግ ላይ ያለንን ከፍተኛ እምነት ያዛባ አሳዛኝ ፍርድ በመሆኑ በጥልቀት ተጣርቶ እንዲሻርልን፣
2. በመ/ሰጪዎች ተጨፈጨረብን ብለው ያቀረቡት አትክልት ሐሰትና በላዩም ላይ አታክልት አለመኖሩን
እንዲሁም ስፍራው ድንግልና ሁለት ቀበሌዎች ለከብት የሚጠቀሙበት ስፍራ መሆኑን ቀደም ሲል በሎካ አባያ
ወ/ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ያልተለወጠና የተጨፈጨፈ ንብረት (ይዞታ) በስፍራው መኖሩ
እስካልተረጋገጠና አትክልቱም ግምት በሚመለከተው የመንግሥት ተቋም ባለሙያ ባልታየበት በይሆናል
የተሰጠው ውሳኔ በእጅጉ ያሳዘነን ከመሆኑም በተጨማሪ ሕብረተሰቡ ፍ/ቤቶች በሚሰጡት ውሳኔዎች ላይ
አመኔታ እንዳይኖረው የሚያደርግ ስለሆነ እንዲታረምልን፣
3. በአጠቃላይ በምትክ ዳኛ ተረጋግጦዋል በሚል ሃሳብ ብቻ ፍርድ ከመሰጡት በፊት ለትክክለኛው ፍትህ አሰጣጥ
ያመች ዘንድ በባለሙያ ግምታቸው ተረጋግጦ ሊቀርብ ይገባ ነበር፡፡
ስለዚህ የስር ፍ/ቤት ምንም እራሱን እንደ ግብርና በባለሙያና ግብይት ጽ/ቤት ጭምር በመቁጠር
በየትኛውም ባለሙያ ግምት ያልወጣለትንና ንብረት አለመጨፍጨፉም በፍርድ ተረጋግጦና በይግባኝ
ባልተሻረበት እንድንከፍል የተጣለብንን ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቀጥር 348(1) መሰረት በመሻር
እንዲወሰንልን በአክብሮት እናመለክታለን፡፡
ይ/ባዮች 1. ፍላቴ ኦትሶ --------
2. ኦንቻ ሻጋራ ----------
3. አስፋው ሻጋራ ---------
4. እንዳለ ፍላተ ---------
5. ማኔ ማልካቶ -----------
ቀን ---------------------------
ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን
ሀዋሣ ፣
ይግባኝ ባይ፡- ኮ/ብል አወል ሌንጅሾ
አድራሻ ፡- ሀዋሣ ከተማ ታቦር ክ/ከተማ
መ/ሰጪ፡- ሀዋሣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ
አድራሻ ፡- ሀዋሣ ከተማ
በክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን የሥነ ምግባር መመሪያ አንቀፅ 23 መሠረት የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
ሀ) የአቤቱታው አቀራረብ
- የይግባኝ አቤቱታው የቀረበበትን ውሳኔ የሰጠው የሀዋሣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ነው፡፡
- ውሳኔው የተሰጠው በቁጥር 5873/3/14 በቀን 11/11/05 ዓ.ም ነው፡፡
- የውሳኔው ትክክለኛ ቅጂ -- ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ) ለይግባኝ አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህን የይግባኝ አቤቱታ ለማቅረብ የተገደድኩት በሀዋሣ ከተማ ታቦር ክ/ከተማ ዱሜ ቀበሌ ፖሊስ ሴክተር
ኦፊሰር በመሆን ተመድቤ እየሰራሁ ሳለሁ በ 19/10/05 ዓ.ም የዕለቱ ተረኛ መኮንን በመሆን ስራዬን ለማከናወን
የሚረዳኝን 0072 የሆነ የፖሊስ ፓትሮል መኪና በታቦር ክ/ከተማ ግቢ ሹፌሩን ጨምሮ 4 አባሎች በመሆን
በቀጠናችን ውስጥ በመንቀሳቀስ መደበኛ ስራችን በማከናወን ላይ ሳለን ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ
በርቀት ታርጋ ያልተለጠፈለት ባጃጅ በከፍተኛ ፍጥነት እየሄደች መሆኑን በማብራት በማየት ተከታትለን
በቁጥጥር ስር ለማዋል ባለን ፅኑ ፍላጎት የተነሳ በዕለቱ ሾፌር ኮ/ብል ቶሎማ አመሎ አሽከርካሪነት እየሄድን
ያየናት ባጃጅ ከእይታችን ውጪ ሆና ከቀጠናችን ውጪ ልታወጣን መቃረቧን በማየት ወደ ኋላ እንደመለስን
ሾፌሩን ብጠይቀውም ፈቃደኛ ሳይሆን በእራሱ ጊዜ እየሄደ ሳለ ከፊት ለፊቱ ባለው ክምር አፈር ላይ ወድቆ
በመገልበጥ በእኔም ሆነ አብረውኝ በነበሩ አባሎች ላይ ጉዳት አድርሶ በወደቅንበት ጥሎ ከሄደ በኋላ ሌላኛው
የዕለቱ ተረኛ ፓትሮል ተረኛ በነበሩት አባሎች ተነስተን ወደ አዳሬ ሆስፒታል በመሄድ ሕይወታችን ልተርፍ
የቻለ ቢሆንም የሀዋሣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ከኮሚሽኑ የሥነ ምግባር መመሪያና ደንብ ውጪ
ደረጃውን ባልጠበቀ መልኩ ከሥራና ከደመወዝ በማገድ በደብዳቤ ስለገለፀልኝ ቅር ተሰኝቼ ያቀረብኩት
የይግባኝ/የይቅርታ/ አቤቱታ ነው፡፡

ሐ) የተከበረውን ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የምጠይቀው ዳኝነት


1/ በክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን የሥነ ምግባር ደንብ ክፍል 3 አንቀፅ 20 ንዑስ ቁጥር 3.2.2 በከባድ የዲስፒሊን
ቅጣቶች አወሳሰድን በተመለከተ ከሀ - ሐ ተዘርዝሮ ከሚገኘው ድንጋጌ ውጪ ደረጃውን ያልጠበቀ
የመጨረሻ ቅጣት ከስራ እንድሰናበት የተጣለብኝ ቅጣት ከሥነ ምግባር መመሪያ ዓላማና ግብ ውጪ
ከመሆኑም በተጨማሪ በእኔና በቤተሰቦቼ ላይ የሞት አዋጅ ከማወጅ ያልተናነሰ አሳዛኝ ውሳኔ በመሆኑ
በጥልቀት ታይቶ እንዲሻርልኝ፣
2/ በቁጥር 905/13/26 በቀን 20/10/05 ዓ.ም ከክ/ከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት ተፅፎ በደረሰኝ የክስ ቻርጅ ላይ
ታርጋ የሌላት ባጃጅን በማሳደድ በታርጋ ቁጥር 0072 በሆነው የመንግሥት መኪና ላይ ጉዳት አደረሰ
የሚል ሲሆን በውሳኔ ላይ ደግሞ የጭነት መኪና በማለት በክስ ቻርጁ ላይ ከተጠቀሰው ውጪ
የመሰላቸውን በመግለፅ የተጣለብኝ ውሳኔ መሆኑን በማየት በጥልቀት ታይቶ ውሳኔው ሙሉ ለሙሉ
ተሽሮ ወደመደበኛ ስራዬ እንድመለስ እንዲወሰንልኝ ስል በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡

አመልካች

ኮ/ብል
አወል ሌንጅሾ
ቀን 9/11/2005 ዓ.ም
ለሀዋሣ ከተማ ከፍተኛው ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
ይግባኝ ባዮች ፡- 1/ ማርቆስ ግዴሣ
2/ እንግዳየሁ አንበርብር
3/ ትግሮ ቲቦ
4/ መላኩ መለሰ
5/ ቡርሣ ድርፍቶ
6/ ማርቆስ ሱያላ
አድራሻ፡- ቱላ ክ/ከተማ ሀዌላ ወንዶ ቀበሌ
መ/ሰጪዎች፡- 1. ተስፋዬ ኤያሞ
2. ዘካሪያስ ገኖ
አድራሻቸው ፡- ቱላ ክ/ከተማ ሀዌላ ወንዶ ቀበሌ
- የሥር የቱላ የመ/ደ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 06531
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 327 መሰረት የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው
ሀ/ የአቤቱታው አቀራረብ
 የይግባኝ አቤቱታው የቀረበበትን ፍርድ የሰጠው የቱላ የመ/ደ/ፍ/ቤት ነው፡፡
 ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 06531 በቀን 14/10/2005 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
 ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በመ/ሰጪዎች አድራሻ በቀበሌያቸው አማካኝነት ለማድረስ
እንችላለን፡፡
 የሥር ፍ/ቤት የውሳኔ መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ --- ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ/ ለይግባኝ አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የይግባኝ አቤቱታ ለዚህ ፍ/ቤት ሊቀርብ የቻለው ቁጥራችን 254 የምንሆን ሰዎች እያንዳንዳችን በየወሩ
ብር 10 (አሥር ብር) በአንድ ዕጣ እቁብ ለመጣል በመስማማት ዕቁብተኛው ደረሶት ከበላ በኋላ በማናቸውም
መልኩ ቢያቋርጥ ክፍያው እስኪጀመር ድረስ ዋናውን ገንዘብና በየወሩ በዕጣው ልክ ቅጣት ብር 10 እንዲሁም
ሳይበላ ላቋረጡ ደግሞ ቅጣት ብር 5 እንዲከፍሉ ከተስማማነው የቃል ስምምነት ውጪ መ/ሰጪዎች
በእራሳቸው ፍላጎት ያለዕቁብተኛው ፈቃድና ስምምነት በወር አንዴ ስንጥል የቆየነውን አራት ጊዜ ሲጣል
እንደቆየን በማድረግና በማስመሰል በየወሩ የሚከፈለውን የአንድ እጣ ዋጋ ገንዘብ እና የቅጣት ዋጋ በ 4 በማባዛት
1 ኛ ይ/ባይ በተከሰሰበት ጉዳይ መልስ ሳይሰጥ በሌለበት ዕዳ 23 x 40 = 920 እና ቅጣት 80x 23 = 1840+ 920
=2760 2 ኛ ይ/ባይ ያልከፈለውን በማለት 23 እጣ x 40=920 እና ቅጣት 23 x 80 =1840 + 920 = 2760
3 ኛው ያልከፈለውን በማለት 23 ዕጣ x 40 =920 እና ቅጣት 23 x 80= 1840+920=2760 4 ኛ ያልከፈለውን
በማለት በ 13 ዕጣ x40=520 ቅጣት በ 13x80
=1040+ 520 = 1560 5 ኛው በ 23 ዕጣ x 40 =920 ቅጣት 23 x 80 = 1840 + 920 =2760 6 ኛው ደግሞ በ 12
ዕጣ x 40 =480 ቅጣት 12 x 80 = 960 + 480 = 1440 ሲሆን ያለአግባብ እንድንከፍል ላቀረበብን
ክስ ከ 1 ኛው ይ/ባይ በስተቀር በፅሁፍ ባቀረብነው መልሳችን በክሱ ላይ የተጠቀሰውንና የማናውቀውን በቃል
ካደረግነው የስምምነት ቃላችን ውጪ ከመሆኑም በተጨማሪ 1 ኛ ተከሳሽ ምንም በሌለበት የተወሰነበት
ቢሆንም በዕቁባችን ደንብ መሰረት ከ 4 ኛ እና 6 ኛ ይ/ባዮች በስተቀር የተቀረነው በየወሩ የምንከፍለው ብር 10x
23 ተባዝቶ እያዳንዳችን ዋናውን ዕዳ ብር 230 ቅጣቱም በተመሣሣይ መልኩ 10x 23 ተባዝቶ 230 መክፈል
ሲኖርብን ያለአግባብ እንዲንከፍል የተሰጠ ፍርድ ከመሆኑም በተጨማሪ 4 ኛ ይ/ባይ ያልከፈለውን የ 13 ዕጣ
x10=130 ብር ዋናው ዕዳ ቅጣቱም በተመሳሳይ መልኩ 130 ብር ሲሆን 6 ኛው ይ/ባይ የ 12 ዕጣ x10 ብር 120
ዋናው ቅጣቱንም በተመሣሣይ መልኩ መክፈል ያለበት ሲሆን ለትክክለኛው ፍትህ ሲባል ባቀረብነው
የመ/መልሳችን ላይ በዝርዝር ባቀረብነው የሰው ማስረጃዎቻችን እንዲሰማልን እንዲሁም የዕቁብተኞች ዋና
ባህር መዝገብ በመ/ሰጪዎች እጅ ስለሚገኝ በትዕዛዝ በማስቀረብ ተጣርቶ እንዲወሰንልን ያቀረብነውን
አቤቱታና ክርክር ተቀባይነት በማሳጣት ማስረጃ ሳይሰማ በመ/ሰጪዎች የሐሰት አቤቱታ ብቻ ያልበላነውንና
ዕቁብተኛው ተስማምቶ ባላፀደቀው ስምምነት እንድንከፍል የተሰጠውን አሳዛኝ ፍርድ ቅር በመሰኘት ውሳኔውን
ለማስለወጥ የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
ሐ) በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልን የምንጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ
1/ በሁለት ተከራካሪ ወገኖች መካከል የሚነሱትን ሙግቶች አከራክሮ ትክክለኛውንና እውነተኛውን ፍትህ ለመስጠት
የግራ ቀኙን ማስረጃ አስቀርቦ መስማቱ አማራጭ የሌለው ትክክለኛ አካሄድና መፍትሔ ከመሆኑም በተጨማሪ
የሕጉን ዓላማ ለማሳካት ዋና ግቡም ዜጎች በፍ/ቤቶች በሚሰጡ ውሳኔዎች/ ፍትህ/ ህብረተሰቡ አመኔታ
እንዲኖረው የሚያደርግ ህጋዊ አሰራር ነው፡፡
ስለሆነም በተያዘው ጉዳይ እንዲሰማልን ያቀረብነውን የሰው ማስረጃ የምስክርነት ቃል እንዳይሰጡና
እንዳይሰማ ተደርጎ በመ/ሰጪዎች የሐሰት ክስ ብቻ ሳይጣራ መወሰኑ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ በሕግ ላይ
ያለንንን ከፍተኛ እምነት ያዛባ አሳዛኝ ፍርድ በመሆኑ ውሳኔው ሙሉ በሙሉ

ተሽሮ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341 (1) መሠረት መዝገቡ ወደ ኋላ ተመልሶ በድጋሚ ተጣርቶ እንዲወሰን
እንዲታዘዝልን ፣
2. ቁጥራችን 254 የሆን የአካባቢ ነዋሪዎች አንድ ላይ ተስማምተን በየወሩ ብር 10 (አሥር ብር) እቁብ ለመጣል
ያስቻለንን ስምምነት በቃል ተነጋግረን በመስማማት ስንጀምር ዕቁብ በልቶ ባቋረጠው ሰው ግለሰብ ላይ
ክፍያውን እስክጀምር ድረስ ብር 10 በየወሩ እንደዋናው ዕዳ እንዲከፍል እንዲሁም ጀምሮ ሳይበላ ያቋረጠው
ሰው ላይ ቅጣት ብር 5 በየወሩ ዕቁቡ እስክያልቅ
ድረስ እንድንከፍል ከመስማማት ያለፈ እንደ መ/ሰጪዎች አባባል በፅሁፍ የተደረገ የውል ስምምነት /ደንብ/ የለንም
የስር ፍ/ቤትም ካቋረጥንበት ጊዜ ጀምሮ 10 x 23 = 230 x 2= 460 በቃል ባደረግነው ስምምነት መሠረት
ከምከፈል ውጪ ተጨማሪ ሊያስከፍለን የምችልና የምንገደድበት ደንብ በሌለበት ያለአግባብ ከ 4 ኛ እና 6 ኛ
ይ/ባዮች ውጪ እያንዳንዳችን ብር 2760 እንድንከፍል መደረጉ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ ፍ/ቤቱን
ሊያሳምን የምችል ሰነድ ከመ/ሰጪዎች ባልቀረበበት የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ባለመሆኑ እንዲሻርልን፣
3. 4 ኛው መ/ሰጪ በ 13 ዕጣ x 10 =130 ቅጣት ብር 10x በ 13 ዕጣ =260 ብቻ የሚከፍል 6 ኛው መ/ሰጪ በ 12 ዕጣ
10x120 ቅጣት ብር 10 x120 ዕጣ= 240 ብቻ መክፈል ሲገባ ያለአግባብ መ/ሰጪዎች በእራሳቸው ስሌት
አስልተው ያቀረበትን እንድንከፍል መደረጉ ከፍተኛ የሕግ ስህተት ያለበት ሊታረም የሚገባው ነው፡፡
መ/ በአጠቃላይ የተከበረውን ፍ/ቤት የምንጠይቀው ዳኝነት
1/ ለትክክለኛው ፍትህ አሰጣጥ ያመች ዘንድ ከመከላከያ መልሳችን ላይ ዘርዝረን ያቀረብነውን ማስረጃዎቻችን
እንዲሰማልን ያቀረብነው ጥያቄ ፍ/ቤቱ ተቀባይነት በማሳጣት በቀረበብን ክስ መጠን የመከላከል ሕገ
መንግሥታዊ መብታችንን በመጣስ የተሰጠ አሳዛኝ ፍርድ በመሆኑ እንዲሻርልን ፣
2/ በሥር ፍ/ቤት ያለአግባብ እንድንከፍል የተጣለብን ዋናው የዕቁብ ገንዘብና የቅጣት ገንዘብ በመ/ሰጪዎች ክስ
ከመግለፅ ያለፈ በደንብም ሆነ ምንም አይነት ሰነድ ባልቀረበበት በይሆናል የተሰጠ አሳዛኝ ፍርድ ስለሆነ
ውሳኔው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) መሠረት ሙሉ በሙሉ ተሽሮ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 341 (1)
መሰረት ወደ ኋላ ተመልሶ በድጋሚ እንዲወሰንልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ይግባኝ ባዮች ፡- 1/ ማርቆስ ግዴሣ


2/ እንግዳየሁ አንበርብር
3/ ትግሮ ቲቦ
4/ መላኩ መለሰ
5/ ቡርሣ ድርፍቶ
6/ ማርቆስ ሱያላ
ቀን 4/11/2005 ዓ.ም
ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
ይግባኝ ባይ ፡- በቀለ ሆንጃ
አድራሻ፡- ሀዋሣ ዙሪያ ዶሬ ባፋኖ ኡዶ ቀበሌ
መ/ሰጪ ፡- መሠረት ዘንባባ
አድራሻ፡- ሀዋሣ ዙሪያ ወረዳ ዶሬ ባፈኖ ኡዶ ቀበሌ
- የሲ/ዞ/ከ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 28819
በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 327 መሠረት የቀረበ ይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
ሀ) መግቢያ
- የይግባኝ አቤቱታው የቀረበበትን የመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 28819 በቀን 22/09/2005 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በመ/ሰጪ አድራሻ ቀበሌ በኩል ሊደርሳት ይችላል፡፡
- የስር ፍ/ቤት የውሳኔ መዝገብ ትክክኛ ቅጂ -- ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ/ ለይግባኝ አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የይግባኝ አቤቱታ ለዚህ ፍ/ቤት ሊቀርብ የቻለው መ/ሰጪ አስረግዞ ላስወለደኝ ሕፃን በረከት በቀለ
ተብሎ ለሚጠራው አባትነት ይወሰንልኝ ስትል ያቀረበችው አቤቱታ ደርሶኝ እንደ ከሣሽ አባባል ሳይሆን
መደበኛ የመምህርነት ስራዬን በምሠራበት ሀዋሣ ዙሪያ ወንዶ ጢቃ 1 ኛ እና 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት በመምህራኖች
ዶርም ውስጥ ለምንኖረው በርካታ መምህራን እንጀራ ለመጋገር ተቀጥራ እየሰራች መቆየቷንና የተለየ
ግንኙነት የሌለኝ መሆኑን በመግለፅ ያቀረበችው አቤቱታ የሐሰትና በማስተምርበት መምህራን ጓደኞቼና
ተማሪዎች ብሎም በአካባቢው ማሕብረሰብ ዘንድ ያለንን መልካም ግንኙነት ለማጥፋት በሚል ከማቅረብ
ያለፈ አባትነት በፍርድ ለማስነገር በህግ ላይ ተደንግገው ከሚገኙትና ተሟልተው መቅረብ ከነበረባቸው
ድንጋጌዎች አንዱን እንኳን አሟልታ ባልተገኘችበት ቤተሰቦቿን አስቀርባ ባሰጠችው የሀሰት የምስክርነት ቃል
ብቻ አባት ነህ ተብዬ በቁርጥ ብር 200 (ሁለት መቶ) ኪሳራ ጭምር እንድከፍል የተጣለብኝን አስገራሚ ፍርድ
ለማስለወጥ የቀረበ ይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
ሐ) በስር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ
1/ አባትነት በፍርድ ለማስነገር በደቡብ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/96 አንቀፅ 158 (1) ከሀ - ረ በዝርዝር
የተቀመጠውን ድንጋጌ አሟልቶ ሲቀርብ ብቻ ከመሆኑም በተጨማሪ መ/ሰጪ ያቀረበችው ግን በተቃራኒው
አንድም ማስረጃ ባላሟላችበት እንዲሁም አባትነት በሕግ ግምት ከምታወቅበት መንገድ አንዱ የጋብቻ መኖር
ሲሆን ይህ ካልሆነ ወይም ከሌለ ደግሞ እንደባልና ሚስት አብሮ መኖራቸው መረጋገጥና በዚሁ ጊዜ ውስጥ
ለተወለደ ልጅ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና በይሆናል የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ በሕግ
ላይ ያለኝን ከፍተኛ እምነት ያዛባ አሳዛኝ ፍርድ ስለሆነ እንዲሻርልኝ ፣
2. ስለአባትነት በሚደረገው ክርክር ስምምነት ያልተገኘ እንደሆነና ልጁ በተፀነሰበት ጊዜ ከነበረው ባል ወይም
ሴትየዋ ልጁን ስትወልድ አብሮአት የነበረ ሰው የልጁ አባት ልሆን እንደሚችል በቤተሰብ ህግ አንቀፅ 163
ላይ በግልፅ ተደንግጎ ከሚገኘው ድንጋጌ ውጪና ከመ/ሰጪ ጋር ግንኙነት ያለን ስለመሆኑ የሚያስረዱ
አንዳች ሰነድ ባልቀረበበት የተሰጠ ፍርድ ከመሆኑም በተጨማሪ በደፈናው ወልጄለታለሁ በሚል በቀረበ
የሐሰት አቤቱታ በማላውቀውና ለማንም ለተወለደ ልጅ አባት ነህ ተብዬ የምጠራበት የሕግ አግባብ
በሌለበት የተሰጠው ፍርድ ሚዛናዊነት የጎደለው ሊሻር የሚገባው ነው፡፡
መ/ የተከበረውን ፍ/ቤት የምጠይቀው ዳኝነት
1. ለትክክለኛው ፍትህ ሲባል በሰው ማስረጃ ብቻ አባትነትን ማረጋገጥ እንደማይቻልና በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎትተ በመ/ቁጥር 44612 ላይ የሕግ ትርጉም ተሰጥቶበታል፡፡
ስለዚህ በዲኤን ምርመራ መረጋገጥ እንዳለበት የተገለፀ መሆኑን በመግለፅ የሕፃኑና የእኔ የደም ናሙና
ተወስዶ ምርመራ ተደርጎ በሚገኘው ውጤት መሠረት እንዲወሰንልኝ ያቀረብኩት አቤቱታን ተቀባይነት
በማሳጣት የተሰጠ ውሳኔ መሆኑን ፣
በሥር ፍ/ቤት አቅርቤ ያሰማኋቸው የሰው ምስክሮቼ የምስክርነት ቃል በትክክል ሳይመዘገብ የታለፈ
ከመሆኑም በተጨማሪ በሲዳምኛ ተፅፎ የቀረበው መልሴ በአማርኛ ተተርጉሞ ከመዝገቡ የተያያዘው
በእጅጉ ልዩነት ያለው ስለሆነ ዋናው መዝገብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 145 መሰረት በትዕዛዝ በማስቀረብ
የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በመሻር መዝገቡ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 343(1) መሰረት ወደ ኋላ
በመመለስ የሕፃኑን የደም ናሙና እና የይግባኝ ባይ ዲኤን ምርመራ ተደርጎ በሚገኘው ውጤት መሰረት
እንዲወሰንልኝ እንዲታዘዝልኝ በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡

ይግባኝ ባይ

በቀለ ሆንጃ
ቀን -------------------------
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት
ለሰበር ሰሚ ችሎት
ሀዋሣ ፣
አመልካች፡- ገዛኸኝ መኩሪያ
አድራሻ፡- አርቤጎና ወረዳ ያዬ 01 ቀበሌ
ተጠሪዎች፡- 1 ኛ/ ወ/ሮ ብርቄ ወ/ማርያም
2 ኛ/ አሩሣ ግንቦ
አድራሻ ፡- አርቤጎና ወረዳ ያዬ 01 ቀበሌ
- የሥር የአርቤጎና ወ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር
- የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር
በአዋጅ ቁጥር 43/1994 መሠረት የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው
ሀ/ የአቤቱታው አቀራረብ
- የሰበር አቤቱታው የቀረበበትን የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠው የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር ------------- በቀን ----------- ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በተጠሪዎች አድራሻ ቀበሌ በኩል ለማድረስ እችላለሁ፡፡
- የሥር ፍ/ቤቶች መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ -- ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ/ ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው በሲዳማ ዞን አሮሬሳ ወረዳ ያዬ ቀበሌ ውስጥ ከዛሬ 30
አመታት በፊት በ 1975 ዓ.ም የከተማው ማስተር ፕላን ከመውጣቱ በፊት ለመኖሪያ ቤት መሥሪያ 500 ካ.ሜ
ስፋት ያለውን እንዲሁም ለድጎማ ቅጥር መምህራን ድጎማ እንዲሆን ተብሎ የእርሻ ቦታ 1000 ካ.ሜ ይዞታ
ተሰጥቶኝ ለመኖሪያ ቤት በተሰጠኝ 500 ካሬ ሜትር ላይ ለመንግስት የሚገባውን ግብር በመገበር ከቆየሁት
ይዞታዬ ላይ ድንበርተኛዬ የሆነችው 1 ኛ ተጠሪ በ 16/05/04 ዓ/ም በተደረገ የቤት ሽያጭ በ 500 ካ.ሜ ላይ
የተሰራውን የግል ቤቷን ለ 2 ኛ ተጠሪ በሽያጭ አሳልፋ ሸጥኩ ስትል በሰነዱ ላይ ትግለፅ እንጂ በሽያጭ ተላልፎ
የተሰጠው 1108.8 ካ.ሜ ሲሆን ከዚሁ ውስጥ 120 ካ.ሜ ከግል ይዞታዬ ወደ እራሷ አካታ ያደረገችውን ሽጭ ውል
በመቃወም በሕግ አግባብ ተጣርቶ ውሉ ፈርሶ ወደነበረበት እንዲመለስ ያቀረብኩትን አቤቱታ ተቀብሎ
የተመለከተው የአረቤጎና ወ/ፍ/ቤት ሳያጣራ ካቀረብኩት የዳኝነት ጥያቄ ውጪ እንደይዞታ ክርክር በማድረግ
የግራ ቀኛችንን ማስረጃ ተቀብሎ ሳይሰማና ጉዳዩን በጥልቀት ሳይመለከት የሰጠውን አሳዛኝ ፍርድ ለማስለወጥ
ለይግባኝ ሰሚው ሲ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት አቤቱታዬን ዘርዝሬ ባቀርብም ለማጣራት የተደረገ አንዳች ጥረት ሳይኖር
አፅንቶ በመወሰኑ የተነሣ የተፈፀመውን መሠረታዊ የሕግ ግድፈቶችን በመዘርዝር በሁለቱም ፍ/ቤቶች
የተሰጡትን ውሳኔ ለማስለወጥ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው፡፡
ሐ/ በሥር ፍ/ቤቶች የተፈፀሙና እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥቦች በአጭሩ
1/ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ተቀብሎ በተመለከተው አርቤጎና ወ/ፍ/ቤት ባቀረብኩት አቤቱታ ላይ 1 ኛ ተጠሪ
በሽያጭ ለ 2 ኛ ተጠሪ አሳልፋ ቤቷን ስትሸጥ ድንበርተኛዬ በመሆኗ ከይዞታዬ 120 ካ.ሜ ወደ እራሷ አካታ
የሸጠች መሆኑንና በሽያጭ ውሉ ላይ 500 ካ.ሜ ብቻ እንደሸጠች አስመስላ ያቀረበችው አግባብ አለመሆኑን
እንዲሁም የተደረገው ሽያጭ መብቴን የሚነካና የምጎዳ መሆኑን በመግለፅ ውሉ ፈርሶ ወደ ነበረበት እንዲመለስ
ያቀረብኩትን በግራ ቀኛችን ማስረጃ ተጣርቶ መወሰን ሲገባው በዝምታ ታልፎ የተሰጠ ፍርድ ከመሆኑም
በተጨማሪ በሽያጭ ተላልፎ ለ 2 ኛ ተጠሪ የተሰጠው የሽያጭ ሰነድ ላይ እንደተጠቀሰው በ 500 ካ.ሜ ላይ
የሰፈረ ንብረት ብቻ ነው ወይስ ከዚያ በላይ የሚለውን ጭብጥ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ በሚያመች መልኩ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 132 መሠረት ከሁለታችንም ተከራካሪ ወገኖች በተውጣጡ ወይንም ፍ/ቤቱ ምትክ ዳኛ
ስፍራው ድረስ በመላክ ከአካባቢ ሽማግሌዎች ጠይቆ በማጣራት የመስክ ሪፖርት ጭምር በመያዝ አጣርቶ
መወሰን ሲገባው እንደይዞታ ክርክር በማስመሰል ከተጠየቀው ዳኝነት ውጪ የተሰጠ ሚዛናዊነት የጎደለው ውሳኔ
ከመሆኑም በተጨማሪ በተከራካሪ ወገኖች ዳኝነት የተጠየቀበትን ጉዳይ ፍ/ቤቶች በግልፅ በመቀበል ወይም
ባለመቀበል ውሳኔ ሊሰጡ የሚገባ ከመሆኑም በላይ በተዋዋይ ወገኖች ወይንም በማናቸውም ያገባናል ባይ ወገን
አቤቱታ በቀረበ ጊዜ ውሉ መፍረስ ሲገባው ፍ/ቤቱ በራሱ አነሳሽነት የአቤቱታውን ጭብጥ ቀይሮ መወሰን
እንዳሌለበት በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 10 በመ/ቁጥር 43825 ላይ የሕግ ትርጉም
ተሰጥቶበታል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ በፌዴራል አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 (1) መሠረት በአገሪቱ ባሉ
በየትኛውም ባሉ ፍ/ቤቶች ሁሉ ውሳኔው አስገዳጅነት ያለው በመሆኑ ውሳኔዎቹ ተሽሮ ውሉ ወደነበረበት
እንዲመለስ እንዲወሰንልኝ፣
2/ በሁለቱ ተጠሪዎች መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ የውል ስምምነት ከቅን ልቦና ውጪ የተደረገና 1 ኛ ተጠሪም
የእራሷ ያልሆነውን 120 ካ.ሜ ይዞታዬን በሽያጭ ያለአግባብ አካታ መሸጧን በመግለፅ ውሉ ፈርሶ ወደነበረበት
እንዲመለስ ካቀረብኩት አቤቱታ ውጪ ፍ/ቤቱ ማዘጋጃው መግለጫ እንዲያቀርብ በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት
በ 01/01/05 ዓ.ም ፅፎ ለፍ/ቤቱ ባቀረበው ሪፖርቱ የአመልካች ይዞታ በማለት 46 x 24.70 ፣46x
14.30፣46x9.50 ድምር 743 ካ.ሜ እንደተሰጠኝ በማስመሰል ከማቅረብ ያለፈ ከማዘጋጃ ቤቱ የተጠቀሰውን
ካ.ሜ በመግለፅ ተጠቅሶ የተሰጠኝ ሰነድ በሌለበት እንዲሁም በማዘጋጃ ቤቱ ፋይል ቁጥር 46 ላይ ቀደም ሲል 30x
50= 1500 ካ.ሜ መሆኑንና በኋላም በቁጥር 1008/04 በቀን 05/06/04 ዓ/ም ማዘጋጃ ቤቱ በአድራሻ በፃፈልኝ
ደብዳቤ የተሻሻለ የይዞታ ግብር ስለማሳወቅ በሚል የተሸሻለው ይዞታ በሚል 647.50 ካ.ሜ በማለት በአንድ
እየገለፀልኝ በሌላ በኩል ደግሞ ከ 1 ኛ ተጠሪ ጋር ባለው ከፍተኛ የጥቅም ትስስር የተነሳ ስዕላዊ መግለጫ በማለት
ከአንድ ተቋም ሁለት ዓይነት መግለጫ መቅረቡ ድርጊቱ ምን ያህል የተቀነባበረ ለመሆኑ አመልካች ከመሆኑም
በተጨማሪ የ 1 ኛ ተጠሪ ይዞታ በማለት 46 x 24.60፣46x 27.30፣46 x20.40 ድምር 1108.8 ካ.ሜ በማለት
ካላት 500 ካ.ሜ

በላይ ተፅፎ የቀረበውን የሐሰት ሪፖርት ብቻ በማየት ውሳኔ ማስተላለፉ አግባብ ካለመሆኑም በላይ
ባላመለከትኩትና ባልጠየኩት ዳኝነት የተሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 182 (2) ድንጋጌ ሥር
የተመለከተውን የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የዳኝነት አሰጣጥ የስልጣን አድማስ በግልፅ የሚፃረር አሳዛኝ ፍርድ
መሆኑን በግልፅ እየታየ አፅንቶ መወሰኑ አግባብነት የለውም፡፡
ስለሆነም ባልተጠየቀ ዳኝነት ውሳኔ ማሳለፉ አግባብ አለመሆኑ ተገልፆ በጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 8
ላይ በመ/ቁጥር 36848 ላይ የሕግ ትርጉም የተሰጠበት መሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ያለአግባብ ያስተላለፉት ውሳኔ
ስህተት ያለበት በመሆኑ እንዲታረምልኝ፣
3/ 1 ኛ ተጠሪ ለ 2 ኛ ተጠሪ በሽያጭ ውሉ ላይ 500 ካ.ሜ በማለት አስተላልፋ ከሰጠችው ውጪ አጠቃላይ የእኔ 120
ካ.ሜ ይዞታ ጨምሮ 1108.8 ካ.ሜ የሸጠች መሆኑንና በውሉ ላይ ያለውና በሽያጭ ተላልፎ የተሸጠው
የማይገናኝ መሆኑን ጭምር የሚያውቁና ቀደም ሲልም በመካከላችን በተከሰተው የድንበር ግጭት የተነሣ
በመካከላችን ገብተው ያስታረቁን የአካባቢ ሽማግሌዎችን አቅርቤ እንዳሰማ ያደረኩትን ክርክር ተቀባይነት
በማሳጣት የተሰጠ ውሳኔ ከመሆኑም በተጨማሪ ማዘጋጃ ቤቱ በ 01/01/05 ለፍ/ቤቱ በፃፈው ስዕላዊ መግለጫ
እስከዛሬ ድረስ ፕላን ያልወጣለትን ስፍራ ፕላን እንደወጣለት በማስመሰል 1 ኛ ተጠሪን ለመጥቀም በማሰብ
ከተጠየቀው ውጪ የቀረበው የሐሰት መግለጫ ላይ የበኩሌን አስተያየት እንዳልሰጥ እድል ሳይሰጠኝ የተሰጠ
ፍርድ ሳይታረም ማፅናቱ ከፍተኛ የሆነ ሕግ ግድፈት ያለበት ከመሆኑም በላይ ቀደም ሲል ከሁለታችንም ወደ ኋላ
50 ሜትር ርቀት ላይ ያለውን ይዞታ ተሸንሽኖ ለአካባቢ ሕዝብ ከተሰጠው ውጪ ክርክር ያስነሳው ይዞታ እስከዛሬ
በእጄ የሚገኝና ለማንም ተላልፎ ያልተሰጠ መሆኑን በመግለፅ በማስረጃ ሳይጣራ እንዲሁም ማዘጋጃ ቤቱ
ያቀረበው ሪፖርት ከእውነት የራቀ ሐሰት መሆኑን በመግለጽ ያደረኩትን ክርክር ተቀባይነት በማሳጣትና
ለትክክለኛው ፍትህ አሰጣጥ ያመች ዘንድ ተጣርቶ እንዲወሰንልን ያደረኩትን የፍትህ ልመና ባለመቀበል የተሰጠን
አስገራሚ ፍርድ ለማረም የተደረገ ጥረት ሳይኖር ማፅናቱ በሕግ ላይ ያለንን ከፍተኛ እምነት ያዛባ ፍርድ በመሆኑ
እንዲታረምልኝ፣
4/ ከማዘጋጃ ቤቱ በቀረበው የሐሰት ሪፖርት ላይ የሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች ድንበር በአጥር ሽማግሌ ከልሎታል
ተብሎ የተሰጠው መግለጫ ሐሰት መሆኑንና በሽማግሌ የተከለለ ነገር አለመኖሩን እንዲሁም ኮርች በተባለው
ነገር የተከለለ መሆኑን በማስረዳት በማስረጃ እንዲጣራልኝና ስፍራው ድረስ ምትክ ዳኛ እንዲያጣራልኝ
ባቀርብም ለማጣራት አንዳች የተደረገ ጥረት ሳይኖር የተሰጠው ፍርድ ሊታረም የሚገባውና ስህተት ያለበት
ከመሆኑም በተጨማሪ በጥልቀት ታይቶ ለትክክለኛው ፍትህ ሲባል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 132 መሰረት በምትክ
ዳኛ እስፍራው ድረስ በመሄድ አጣርቶ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሠረት
ተሽሮ እንዲወሰንልኝ ሲል በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡
አመልካች

ገዛኸኝ መኩሪያ
ቀን ----------------------------------

ለሀዋሣ ከተማ አስተዳደር ፍትህና ፀጥታ መምሪያ


የጠበቆች ሲቪል ማኅበራት ፈቃድ
ውል ምዝገባና ክትትል ዋና የሥራ ሂደት
ሀዋሣ ፣
ጉዳዩ፡- ውክልና ስለመስጠት ፣
የውክልና ሥልጣን ሰጭዎች፡- አልጌ ሪማ ብዮ ማሕበር አስፈፃሚ ኮሚቴ
1. አቶ አበራ ታቦር ሊቀመንበር
2. አቶ ለማ ጌታቸው ፀሐፊ
3. አቶ በየነ አወቀ አባል
አድራሻ ፡- አልጌ ሪማ ቀ/ገ/ማሕበር ዜግነት ፡- ኢትዮጵያዊያን
የውክልና ሥልጣን ተቀባይ፡- 1. አቶ አበራ ታቦር
2. አቶ ይርጋው አብረሃም
3. አቶ ቱሉ ለቤሣ
አድራሻ፡- አልጌ ሪማ ቀ/ገ/ማሕበር ዜግነት ኢትዮጵያዊያን
እኛ የውክልና ሥልጣን ሰጭዎች በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ሻላ ወረዳ አልጌሪማ ቀ/ገ/ማሕበር
የሚገኘው ከመንግሥት በሰኔ ወር 1989 ዓ/ም 800 (ስምንት መቶ ) ሄክታር የእርሻ መሬት በቁጥር 545 ሰዎች
አደራጅተው ተሰጥቶን ይዞታን እስከ ዛሬ ድረስ አርሰን አልምተን ሰርተን ለመንግስት ግብር ከፍለን ያለውን
ይዞታው የኦሮሚያ ነው በመባል እና የኦሮሞ ተወላጅ አይደላችሁም በማለት በቀን 12/07/2005 ዓ/ም በጉልበት
የተነጠቅነውን ይዞታችንን አስተዳደራዊም ሆነ በሕግ ተወካዮች እንደእኛ በመሆን ለጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ፣
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ለኢህአዲግ ቢሮ እና ለሚመለከተው አካል ጭምር
አቤቱታችንን እንዲሰሙና እንዲያስወስኑ በስማችን ማንኛውንም ማመልከቻዎች ጽፈውና ፈርመው
እንዲያቀርቡ በአጠቃላይ ከላይ የተገለፀውን የእርሻ መሬትና እኛን በተመለከተ መፈፀም የሚገባውን
ማናቸውም አስተዳደራዊና ህጋዊ ጉዳዮችን እንዲፈፅሙና እንዲስፈፅሙልን በፍ/ሕ/ቁ 2199 እና 2204 መሰረት
ይህንን የውክልና ሥልጣን የሰጠናቸው መሆኑን በየፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡
የውክልና ስልጣን ሰጭዎች ስምና ፊርማ

1. -------------------------------------------
2. -------------------------------------------
3. -------------------------------------------
4.

ቀን 21/12/2005 ዓ.ም
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ጠ/ፍ/ቤት
ለሰበር ሰሚ ችሎት
ሀዋሣ ፣
አመልካች ፡- ታረቀኝ ጥሩነህ
አድራሻ ፡- ሀዋሣ ከተማ ምስ/ክ/ከተማ ቴሶ ቀበሌ
ተጠሪ ፡- ወ/ሮ ሰናይት መለሠ
አድራሻ፡-
- የሥር የምስራቅ አካባቢ ምድብ ችሎት መ/ቁጥር 906/05
- የሀዋሣ ከተማ ከ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 14065
በአዋጅ ቁጥር 43/94 መሠረት የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው፡፡
ሀ/ የአቤቱታው አቀራረብ
- የሰበር አቤቱታው የቀረበበትን የመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የሀዋሣ ከተማ ከፍ/ፍ/ቤት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 14065 በቀን 3/12/05 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በመ/ሰጪ ጠበቃ አማካኝነት ሊደርሳት ይችላል፡፡
- የስር ፍ/ቤት መዝገብ የውሳኔ ትክክለኛ ቅጂ --- ገፅ ተያይዞ ቀርቧል፡፡
ለ/ ለይግባኝ አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የይግባኝ አቤቱታ ለዚህ ፍ/ቤት ሊቀርብ የቻለው መ/ሰጪ ከሆነችው ባለቤቴ ጋር የነበረን ጋብቻ በፍርድ
የፍቺ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የፍቺ ውጤት የሆነውን የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ቀርቦለት የተመለከተው የምስራቅ
አካባቢ ምድብ ችሎት ቀደም ሲል ከመ/ሰጪ በፊት ከነበረችው ባለቤቴ ወ/ሮ ሽቶ ደሣለኝ ጋር የነበረን ጋብቻ
በፍርድ ውሳኔ ተሰጥቶ የጋራ ንብረታችንን በፍርድ ተከፋፍለን የያዝኩትን የግል ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን
የአሁኗ መ/ሰጪ በ 1 ዓመት የትዳር ቆይታ ዘመኗ ውስጥ ያፈራሁት የጋራ ንብረቴ ስትል ዘርዝራ ያቀረበቻቸው
ንብረቶች በየካቲት 19/2003 ዓ.ም ባደረግነው የጋብቻ የውል ስምምነት ላይ ባልተገለፀበትና ከጋብቻ በፊት
የተፈራው ንብረት የጋራ ባልተባለበት በሀዋሳ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 12966 ላይ በግልፅ ተዘርዝሮ
ከቀረበው ላይ በክፍፍል የደረሰኝንና ከመ/ሰጪ በፊት በራሴ አካውንት ቁጥር ሀዋሣ ዳሽን ባንክ አላሙራ
ቅርንጫፍ ያስቀመጥኩትን ገንዘብ ስቴትመንት ሳይቀርብ እንዲሁም በጋብቻ ከመጣመራችን በፊትም ይሁን
በኋላ የሌለኝንና ያልገዛሁትን ባለሦስት እግር ባጃጅ የባጃጅ ባለቤት ስለመሆኔ የሚያረጋግጥ የባለቤትነት
ማረጋገጫ ሰነድም ይሁን ሌላ ተረጋግጦ የቀረበ ሰነድ በሌለበት የሌለንና በቆይታዋ ወቅት ያላፈራችውን
እንዳፈራች ተደርጎ ክፍፍል እንዲደረግ የተሰጠ ውሳኔ ከመሆኑም በተጨማሪ መ/ሰጪ በሌለሁበት ከቤቴ ይዛ
የተሰወረችውን ገንዘብና ከቤቴ ከወጣች በኋላ በአብሲኒያ ባንክ ሀዋሣ ቅርንጫፍ በመ/ሰጪ ስም የተቀመጠውን
የጋራ ገንዘብ ብር 34,000 እና በመ/ሰጪ ስም በሀዋሣ ከተማ ም/ክ/ከተማ ቴሶ ቀበሌ ውስጥ በወ/ሮ እቴነሽ
ሰብሳቢነት በ 1 ዕጣ በቀን 10 ብር በ 2 ዕጣ በሳምንት 140 ሲጣል

የነበረውን ከሰብሳቢዋ እጅ የሶስት ወር ገንዘብ ብር 2,940 ከወሰደችው ውስጥ ድርሻዬን ብር 1470 እንዲከትከፍለኝ
እንዲሁም በሀዋሣ ከተማ በሐይቅ ዳር ክ/ከተማ ገበያ ዳር በወ/ሮ ሀና ሰብሳቢነት በሳምንት 320 x በ 63 ዕጣ ብር
20,180 ወስዳ ለግሏ ከተጠቀመችው የጋራ ገንዘብ ውስጥ ድርሻዬን ብር 10,090(አሥር ሺህ ዘጠና ብር)
በተጨማሪም በትዳር አብረን በነበርንበት ጊዜ ወ/ሮ ሰላም ተብላ ከምትጠራዋ አንዲት ሴት 9 ግራም የአንገት
ወርቅ ሀብል በመያዣነት በመያዝ ከጋር ገንዘባችን ብር 3,000 ካበደረች በኋላ የወሰደችውን ግማሹን ብር 1500
በድምሩ ከጋራ ገንዘባችን ድርሻዬን እንድትከፍለኝ እንዲወሰንልን ያቀረብኩትን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ጭምር
በሕግ አግባብ ሳይጣራ በዝምታ መታለፉን በመግለፅ ይግባኝ ሰሚ ለሆነው ለሀዋሣ ከፍ/ፍ/ቤት አቤቱታዬን
ዘርዝሬ ባቀርብም ለማጣራት የተደረገ አንዳች ጥረት ሳይኖር ታልፎ የተሰጠውን አሳዛኝ ፍርድ ለማስለወጥ
የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው፡፡
ሐ/ በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ
5. የክልላችን የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 101 እና 102 ላይ በግልፅ በተደነገገው የሕግ ድንጋጌ መሰረት ባልና ሚስቱ በጋራ
ያፈሯቸውን ንብረቶች እኩል በዓይነት ሊከፋፈሉ እንደሚችሉ ከተደነገገው ድንጋጌ ውጪ ቀደም ሲል ከመ/ሰጪ
በፊት ከነበረችው ባለቤቴ ጋር በመ/ቁጥር 12966 ላይ በክፍፍል ያገኘሁትን ቁሳቁሶች በሙሉ መ/ሰጪ
እንድትካፈል የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ ከቀድሞ ባለቤቴ በክፍፍል ያገኘሁት የግል
ንብረቴ ስለመሆኑ ክፍፍል የተደረገበት የመ/ቁጥር 12966 በግልፅ እያስረዳ ወይንም ከመ/ሰጪ ጋር በነበረን
የጋብቻ ውላችን ላይ የጋራ ተብሎ ባልተገለፀበት መ/ሰጪና ቤተሰቦቿ የሰጡትን ቃል ብቻ መነሻ በማድረግ
ከልጅነት እስከ እውቀት ያፈራሁት ንብረት በነበራት በአንድ አመት የቆይታ ጊዜ ውስጥ በጋራ እንዳፈራች ተደርጎ
የተሰጠው አሳዛኝ ፍርድ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሊታረም የሚገባው ነው፡፡
6. ከተጠሪ በፊት ከነበረችው ባለቤቴ ወ/ሮ ሽቶ ደሣለኝ ጋር በፍርድ ተካፍዬ ካገኘሁት የግል ንብረቴ ጋር በቤቴ
የሌለውን ባለሦስት እግር ባጃጅ ተካፋይ እንድትሆን የተሰጠ አስገራሚ ፍርድ ከመሆኑም በተጨማሪ
ስለተንቀሳቃሽ ተሸከርካሪዎች ሊቭሬ ባለቤትነትና የልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ተሸከርካሪዎች ባለሃብትነት
የመኪና ፣የማሽን፣ የሞተር ሳይክልና ወዘተ የመሳሰሉት በተገቢው ሕጋዊ አካል በሚሰጡ አካል ሰነዶች ብቻ
መረጋገጥ የሚገባ ከመሆኑም በላይ ባላሦስት እግር ባጃጅ ተሸከርካሪ እንደመሆኑ መጠን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር
1186(2) እና የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 360/67 አንቀፅ 4 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 107/69 መሰረት
ባለሀብቱ ባለደብተሩ ነው ይሁንና በክፍፍል ውስጥ የተካተተው የሠሌዳ ቁጥር ደህ 1420 ባለሦስት እግር ባጃጅ
የሌለኝና ግዥ የተፈፀመበት ሰነድ እንኳን መቅረብ ባልቻለበት እንዲሁም ከሀዋሣ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት
ጭምር የእኔ ስለመሆኑ መግለጫ ባልተገኘበት ሲያሽከረክር ይዘነዋል በሚል በተሰጠ የሐሰት የምስክርነት ቃል
ክፍፍል ውስጥ የተካተተበት አግባብ ሳይጣራ መታለፉ በሕግ ላይ ያለንን ከፍተኛ እምነት ያዛባ በመሆኑ
እንዲታረምልኝ፣

7. ተጠሪ በ 2/7/04 ከቤቴ ብር 25.000 ይዛ መሰወሯን ለሀዋሣ ከተማ ምስ/ክ/ከተማ ቴሶ ቀበሌ በእለት ሁኔታ
ስለማስመዝገቤ ማስረጃ የቀረበ ከመሆኑም በተጨማሪ ከቤቴ ከወጣች በኋላ አብሲኒያ ባንክ ሀዋሣ ቅርንጫፍ
በመ/ሰጪ ስም ያስቀመጥነውን ገንዘብ ብር 34,000 አውጥታ ለግል ጥቅም ማዋሏን ከባንኩ እስቴትመንት
መረጃ በማስቀረብ ለደረሰኝ የሚገባውን ድርሻዬ እንዲሁም ከቤተ ይዛ ወጣችውን ባቀረብኳቸው የሰው
ማስረጃዎች ያስረዳሁት ብር 25.000 ግማሹን ፣ በሀዋሣ ከተማ ም/ክ/ከተማ ቴሶ ቀበሌ በወ/ሮ እቴነሽ ቤት
በ 2 ዕጣ ባለስምንት ብር 140 ሲጣል የነበረውንና በሰብሳቢዋ እጅ የተቀመጠ የ 3 ወር ገንዘብ ብር 2,940
ግማሹን እንዲሁም በሀዋሣ ከተማ በሐይቅ ዳር ክ/ከተማ ገበያ ዳር በወ/ሮ ሀና ሰብሳቢነት በሳምንት ብር 320
x በ 63 ዕጣ ብር 2018 ወስዳ ለግል ጥቅሟ ያዋለች በመሆኑ በአጠቃላይ በግሌ የሚደርሰኝን ድርሻ ገንዘብ
42,560 (አርባ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ስድሳ ብር) እንዲከፍለኝ ያቀረብኩትን የተከሳሽ ከሣሽነት ክሴን
ያለበቂ ምክንያት ተቀባይነት በማሳጣት የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት እንኳን ለማጣራት የተደረገ ጥረት
አለመኖሩ ግድፈት ነው፡፡
8. የተከበረውን ፍ/ቤት የምጠይቀው ዳኝነት
- ተጠሪ ትካፈል የተባለው ቁሳቁስ ቀደም ሲል ከነበረችው ባለቤቴ ወ/ሮ ሽቶ ደሣለኝ ጋር በሀዋሣ ከተማ
የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 12966 ላይ ክፍፍል ተደርጎ ያገኘሁት የግል ንብረቴ ስለመሆኑ መዝገቡ የሚያስረዳ
ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145 በትዕዛዝ በማስቀረብ ተጣርቶ እንዲወሰንልኝ ያቀረብኩት አቤቱታ
መታለፉ ስህተት በመሆኑ እንዲታረምልኝ፡፡
- ባለሦስት እግር ባጃጅ የተባለው የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊቭሬ ደብተርም ሆነ ግዥ የተፈፀመበት ሰነድ
ባልቀረበበት ሲነዳ አይተነዋል በሚል በሐሰት ምስክርነት የሌለን ንብረት በክፍፍል ውስጥ እንዲካተት ተደርጎ
የተሰጠው ውሳኔ ሳይታረም ማፅናቱ ከፍተኛ የህግ ግድፈት ስለሆነ እንዲሻርልኝ፣
- ከተጠሪ በ 2/7/04 ዓ.ም ስለመውጣቷ ከም/ክ/ከተማ ቴሶ ቀበሌ ማረጋገጫ በትዕዛዝ የቀረበ ከመሆኑም በተጨማሪ
ከቤቴ ከወጣች በኋላ ከአብሲኒያ ባንክ ያወጣችውን ገንዘብ ብር 34,000 ለጋራ ጥቅም አዋሉ ተብሎ የተሰጠው
ውሳኔ አግባብነት በጥልቀት ተጣርቶ ድርሻዬን እንድትከፍለኝ ያቀረብኩት ታልፎ የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት
ሳይጣራ ማፅናቱ አግባብ ባለመሆኑ በጥልቀት ታይቶና ተጣርቶ እንዲሻርልኝ ፣
በአጠቃላይ የግል ንብረቴን ያለአግባብ ተጠሪ እንድትካፈል የሰጠው ውሳኔ አግባብ ባለመሆኑ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) መሠረት ሙሉ በሙሉ በመሻር ከጋራ ንብረታችን ለግል ጥቅሟ አውላ
የቀረውን ብር 42,560 እንድትከፍለኝ ያቀረብኩትን የተከሣሽ ክስ ውድቅ የተደረገበትን አግባብ ሳይጣራ
መወሰኑ አግባብ ባለመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ያስተላለፉትን ውሳኔ በመሻር እንደአቤቱታ አቀራረቤ
እንድትከፍለኝ እንዲወሰንልኝ ስል አመለክታለሁ፡፡
አመልካች ታረቀኝ ጥሩነህ
ቀን ---------------------------
ለሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
ከሣሽ መሠረት ዘንባባ
ተከሣሽ፡- በቀለ ሆንጃ
ከሣሽ በቀን 14/08/05 ዓ/ም ፅፋ ያቀረበችብኝን ክስ ተመልክቼ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 234 ፣231 (1) ሀ) እና
244 (2) (መ) መሠረት ከተጠሪ የተሰጠ መልስ
የከሣሽ የክስ ይዘት በአጭሩ
ከ 2003 ዓ.ም ጀምሮ በነበረን የፍቅር ግንኙነት አርግዤለት ሕፃን በረከት በቀለ ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ
ብወልድለትም አባትነቱን አምኖ ባለመቀበሉ አባትነቱ በፍርድ ይወሰንልኝ የሚል ነው፡፡
1. በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበ መቃወሚያ
አመልካች በነበረን የፍቅር ግንኙነት አታሎኝ አብረን ተጋብተን እንኖራለን በማለት አስረግዞ አስወለደኝ
ከማለት ያለፈ በደቡብ ክልል አዋጅ ቁጥር 75/1996 አንቀፅ 49(2) መሰረት በማዘጋጃ ቤት በክብር መዝገብ
ሹም ፊት፣ በሃይማኖት ሥርዓትና በባህል ከሦስቱ የጋብቻ ሥርዓቶች በአንዱ እንኳን የተደረገ የጋብቻ ሰነድ
ተያይዞ ባልቀረበበት እንዲሁም ግንኙነት አለን ስትል የገለፀችውን ሊያስረዳላት የሚችል አንድ ሰነድ በሌለበት
በማገኛት አነስተኛ የመምህር ደመወዜ አቅሜ ደካማ የሆኑ ተጧሪ ወላጆቼን በመጦርና በመደገፍ በምኖርበት
ማሕበረሰብ ዘንድ ያለኝን ታማኝነትና አክብሮት በማሳጣት ስሜን ለማጥፋት ሆን ተብሎ ከክፉ ልቦና በመነጨ
በቀረበ የሐሰት ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 231 (1) (ሀ) መሠረት የማያስከስሰኝ ከመሆኑም በተጨማሪ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244 (2) (መ) መሠረት በማስረጃ ተደግፎ ባልቀረበ ጉዳይ ውስጥ ገብታ ልትከራከርም ሆነ
ክስ ልታቀርብ አይገባትም ተብሎ ወጪ ኪሣራዬ ተጠብቆ መዝገቡ በብይን እንዲዘጋልኝ እጠይቃለሁ፡፡
2. በአማራጭ ከተከሳሽ የተሰጠ መልስ
2.1 ተወለደ በተባለው በልጁ እናትና በወንድየው መካከል በሕግ የታወቀ ግንኙነት እንዳለ ወይም የተወለደው በሕግ
በታወቀ ግንኙነት ፀንቶ ባለበት መሆኑን ማሳየት የግድ የሚል ከመሆኑም በተጨማሪ በቤተሰብ ህጉ የታወቀ
ግንኙነት የሚባሉ ግንኙነቶች ጋብቻ አንዱ ስለመሆኑ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 35 (2) እንዲሁም
በሕግ በታወቀ ግንኙነት የሚባለው ጋብቻ ሳይፈፀም እንደ ባልና ሚስት አብሮ ሲኖር ብቻ የተወለደ ካልሆነ
በስተቀር ግንኙነት አላቸው ወይም ልጅ ተወለደለት ሊያስብል እንደማይችል በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት በመ/ቁጥር 44612 ላይ የሕግ ትርጉም የተሰጠበት ከመሆኑም በተጨማሪ በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ደግሞ በአዋጅ ቁጥር

454/97 አንቀጽ 164 መሰረት በአገሪቱ ባሉ ፍ/ቤቶች ሁሉ ገዥና አስገዳጅነት ያላቸው በመሆኑ የከሣሽ ክስ
በሕግ ላይ ተመስርቶ ያልቀረበ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡
2.2 እንደ አመልካች /ከሣሽ/ አባባል ሳይሆን በምሰራበት የወንዶ ጢቃ 1 ኛና 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን ዶርም
ከበርካታ መምህራኖች ጋር ስለምኖር በጉሩፕ በተመላላሽ ሠራተኛነት እንጀራ ጋጋሪነት ተቀጥራ ስታገለግለን
የቆየች መሆኗን ከማየት ያለፈ የተለየ ግንኘት የለኝም በጠቀሰችው 2003 ዓ.ም ደግሞ ለት/ቤቱም ገና
እንግዳና አዲስ በመሆነ ከመቅስፈት ከከሣሽ ጋር ግንኙነት ላደርግ የምችልበት ምክንያት የለም ፡፡ በተጨማሪም
አባትነትን በፍርድ ለማስነገር በደቡብ የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 158(1) ከሀ-ሠ ተዘርዝረው ከተቀመጡት የሕግ
ድንጋጌዎች አንዱን እንኳን ያላሟላና በማስረጃነትም ተያይዞ የቀረበ ሰነድ የለም፡፡
ስለሆነም ሌላ ሁኔታ ስለመኖሩ ከፍ ተብሎ በተጠቀሰው ሕግ ከመተለከቱት ውጪ አባትነት በፍርድ ቤት
ውሳኔ ሊታወቅ እንደማይችል በቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 160 ላይ በግልፅ የተደነገገ ስለሆነ ክሱ ታማኝነት ባለው
መልኩ በማስረጃና በሕግ ተመርኩዞ ያልቀረበ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡
2.3 አባትነት በሕግ ግምት የሚታወቅበት መንገድ በተዘዋዋሪ ጋብቻ መኖሩን ወይም ጋብቻ ሳይፈፅሙ እንደባልና
ሚስት አብሮ መኖርን በማስረዳትና በቤተሰብ ህግ አንቀፅ 163 (ለ) መሠረት ልጁ ተፀንሶ ሲወለድ አብሮአት
የሚኖረውን ሰው በማስረዳት እንጂ በደፈናው ወልጄለታለሁ በሚል በሚቀርብ የሐሰት ክስ ባለመሆኑ ክሱ
በሕግ አግባብ ያልቀረበ ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም በተጨማሪ በመካከላችን አንዳች የፍቅር ግንኙነት
ሳይኖር ፍ/ቤቱን አሳስታ ለማስፈረድ ያቀበችው ስለሆነ ለትክክለኛው ፍትህ አሰጣጥ ያመች ዘንድ /ዲኤን/
የደም ምርመራ እንዲደረግ ታዞ በሚገኘው ውጤት መሰረት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 463 መሠረት ወጪ
ኪሣራዬን የመጠየቅ መብቴ ተጠብቆ እንዲወሰንልኝ ስል በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡
መልሴም በእውነት የቀረበ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሰረት በቃለ መሀላ በማረጋገጥ
አቀርባለሁ፡፡

መልስ አቅራቢ

በቀለ ሆንጃ
ቁጥር ---------------------------
ቀን ------------------------------

ለሀዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት


ሀዋሣ ፣

ጉዳዩ፡- የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ደሕ 02848 የሆነ ተሽከርካሪ ዕገዳ ስለመግለጽ


በቁጥር 26843/05 በቀን 14/08/05 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ የተሽከርካሪ ባለንብረት አቶ አሸብር
ተካ ዋስ እንዲሆን ተሽከርካሪው ታግዶ እንዲቆይ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም የተጠቀሰው ተሸከርካሪ ተለዋጭ ትዕዛዝ እስኪመጣ ድረስ መሸጥ፣ መለወጥ፣ ለ 3 ኛ
ወገን አሳልፎ መስጠት የታገደ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር
ቀን 14/08/2005 ዓ.ም
ለሀዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
ይግባኝ ባዮች፡- 1. ጂግሶ ሲአቶ አድራሻ ቱላ ክ/ከተማ ጨፋሲኔ ቀበሌ
2. ሳቶ ሳምሮ ›› ›› ›› ››
3. ማራሣ ጋብሦ ›› ›› ›› ››
4. ወርሣ ወታሳ ›› ›› ›› ››
5. ካሣሁን ካቸራ ›› ›› ›› ››
6. በላይነሽ ጁጊሣ ›› ›› ›› ››
7. አዲሱ ወታሣ ›› ›› ›› ››
8. ማሣራ ሃያሞ ›› ›› ›› ››
መ/ሰጪ ፡- ዐቃቤ ሕግ
- የሥር የቱላ ክ/ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 06408
በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 189 መሠረት የቀረበ የወንጀል የይግባኝ አቤቱታ
ሀ/ መግቢያ
- የይግባኝ አቤቱታው የቀረበበትን ፍርድ የሰጠው የቱላ ክ/ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በወ/መ/ቁጥር 06408 በቀን 8/08/05 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- የሥር ፍ/ቤት የውሳኔ መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ --- ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ/ ለይግባኝ አቤቱታችን ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የይግባኝ አቤቱታ ለዚህ ፍ/ቤት ሊቀርብ የቻለው ዐቃቤ ሕግ በቁጥር 348/05 በቀን 25/7/05 ፅፎ
ባቀረበው የሐሰት ክስ የግል ተበዳይ ነኝ ባዮችን በተለይም 1 ኛ ተበዳይን ከ 1 -3 ያሉ ተከሳሾች ወርውረው
አንቀው በመያዝ መሬት ላይ ጥለው ሲደበድቡ 2 ኛ እና 3 ኛ በመደብደብ 4 ኛው በሳንጃ የቀኝ እጁዋን ጠቋሚ
ጣቷን ስወጋት 3 ኛ ተበዳይን ከ 5 -8 ያሉት ተከሳሾች ጩኸት ሰምተው የደረሰውን 5 ኛ እና 6 ኛ ተከሳሾች
በገጀራ ቢለዋ እና በሳንጃ ግራና ቀኝ እጇን ጣት በመውጋት ጉዳት ሲያደርሱበት 7 ኛ እና 8 ኛ ተከሳሾች
በመተባበር በድንጋይ ወርውረው ጀርባውን በመደብደባቸው ተባብረው በሕብረት የአካል ጉዳት አደረሱ ሲል
የሐሰት የሰው ምስክሮችን በማስቀረብ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፀመ ተብሎ ዐ/ሕግ በክስ ቻርጁ ከገለፀው
29/6/2005 ዓ/ም በ 28/6/2005 ዓ.ም የአሁኑ ይግባኝ ባዮች የወንጀል ድርጊቱን ፈፀሙ ሲሉ ምሰክሮች
ያላዩትንና የማያውቁትን ምስክርነት መስጠታቸው ሳይጣራ የቀረበብን አስገራሚ ክስ ፍ/ቤት በመቅረብ
የተጠቀሰብንን ድርጊት አለመፈፀማችንን በመግለፅ ክደን የተከራክርን ቢሆንም ዐቃቤ ሕግ የግል ተበዳይ ነኝ
ባዮችን በማስቀረብ ያሠጠውን የምስክርነት ቃል ባቀረብነው የሰው የመከላከያ ማስረጃዎቻችን ድርጊቱን
እንዳልፈፀምን በመግለፅ ከበቂ በላይ በማስረገጥ ያሳመነውን የምስክርነት ቃል ተቀባይነት በማሳጣት
የጥፋተኝት ውሳኔ በመስጠት የተጣለብንን የቅጣት ውሳኔ ለማስለወጥ የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡

ሐ/ በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ


1. የተባለው ድርጊት ስለመፈፀሙ ዐቃቤ ከግል ተበዳይ ነኝ ባዮች ውጪ ገለልተኛና ነፃ በሆነ የአይን
ማስረጃዎች ያሠጠው የምስክርነት ቃል ሳይኖርና ከገለልተኛ ወገን የተሰጠ ምስክርነት በሌለበት እጅግ
ታአማኝነታቸው ጥርጣሬን በሚፈጥር መልኩ የተሰጠን የምስክርነት ቃል ሚዛን ይደፋል በማለት ተቀብሎ
የተጣለብን የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በሕግ ተጣርቶ ያልታየ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡
2. አቅርበን ባሠማናቸው የመከላከያ ማስረጃዎቻችን ቃል 1 ኛ እና 5 ኛ ተከሣሾች በወቅቱ በስፍራው
ያለመኖራቸውና ድርጊቱን ያለመፈፀማቸውን ሲመሰክር የተቀሩት ተከሣሾች በግል ተበዳይ ነኝ ባዮች
የተከሰተውን የመቃብር ማፍረስ ወንጀል በማስረጃ በማስደገፍ በሕግ ለማቅረብ በማሰብ ፎቶ ግራፍ
ለማስነሳት ከመሞከር ያለፈ በማንም ሰው ላይ ጉዳት ያላደረሱና የፈፀሙት የወንጀል ድርጊት አለመኖሩን
በመግለፅ ከበቂ በላይ አስረግጠው በመመስከር የዐቃቤ ሕግን ክስና የሰው የምስክርነት ቃል በማስተባበል
የተሰጠውን ያለአንዳች ምክንያት ተቀባይነት በማሳጣት የተሰጠ አስገራሚ ፍርድ ነው፡፡
በተጨማሪም በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 149(1) መሠረት የመከላከያ ማስረጃዎች ቃል ውድቅ ሲደረግ
የተሰጠው የምስክርነት ቃል ተቀባይነት ያላገኘበት ሕጋዊ ምክንያት እንኳን በውሳኔ መዝገብ ላይ መግለፅ
ባልተቻለበት ሁኔታ አስረግጠን ያሰማነው የምስክርነት ቃል ተቀባይነት በማሳጣት የተጣለብን የጥፋተኝነትና
የቅጣት ውሳኔ አግባብ አይደለም፡፡
በአጠቃላይ በወንጀል ጉዳይ አንድን ሰው ጥፋተኛ ለማድረግ ከጥርጣሬ ውጪ በሆነ መንገድ በበቂ ማስረጃ
ሊረጋገጥበት ይገባል ተብሎ በወንጀሉ ህጋችን ላይ ተደንግጎ ባለበት ሁኔታ ዐ/ሕግ ከጥርጣሬ ውጪ በሆነ
መንገድ በገለልተኛ ወገን የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈፀማችን አረጋግጦ ባላስረዳበት እኛም የዐ/ሕግን ክስና
የማስረጃን ቃል በሚገባ ባስተባበልንበት ሁኔታ ፍ/ቤቱ የጥፋተኝነትና የቅጣት ማሳለፉ አግባብ ባለመሆኑ
ተጣርቶ በወ/መ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195 (2) (ለ) (1) መሠረት ሙሉ በሙሉ በመሰረዝ በነፃ እንዲያሰናብተን
በአክብሮት እናመለክታለን፡፡
ይግባኝ ባዮች ፡- 1. ጂግሶ ሲአቶ
2. ሳቶ ሳምሮ
3. ማራሣ ጋብሦ
4. ወርሣ ወታሳ
5. ካሣሁን ካቸራ
6. ካሣሁን ካቻራ
7. አዲሱ ወታሣ
8. ማሣራ ሃያሞ
ቀን 01/08/2005 ዓ/ም
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሥልጣን
ለደቡብ ሪጅን
ሀዋሣ ፣
አመልካቾች 1. ቃዋቶ ጉራራ አድራሻ ፡- ቡርሣ ወረዳ 01 ቀበሌ
2. ቶሼ ዋጄ ›› ›› ›› ›› ››
3. ሀምሳለ ሀሪሶ ›› ›› ›› ›› ››
4. ክፍሌ እሽኔ ›› ›› ›› ›› ››
5. ክፍሌ ሃርቃ ›› ›› ›› ›› ››
የምናመለክተው ጉዳይ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
አመልካቾች ዋና የመኖሪያ አድራሻችን በሆነው ቡርሳ ወረዳ 01 ቀበሌ ውስጥ ከረዥም ዓመታት ጀምሮ
በነዋሪነት የምንታወቅ ሲሆን መንግስት አገራችን ኢትዮጵያ በአላማችን ካደጉትና መካከለኛ የገቢ ምንጭ
ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በሚደረገው ርብርብ አመልካቾችም እንደዜጋ ያለንን መዋእለ ንዋይ
በማፍሰስ ሰርተን አካባቢያችንን በማልማት ለእራሳችንም በመጠቀም ለሀገራችን የበኩላችን አስተዋፅዖ
ለማበርከት በማሰብ በዚሁ ቡርሳ ወረዳ ቡርሳ ከተማ ውስጥ ለእህል ወፍጮ አገልግሎት የሚሆን ግንባታ
አጠናቀን ቀደም ሲል ቡርሳ በወረዳ ደረጃ ከማደጓ በፊት በዳሌ ወረዳ ይርጋዓለም ከተማ ውስጥ በሚገኘው
የኢት/ኤሌክትሪክ ኃይል ባለስልጣን ይርጋዓለም ዲስትሪክት ከ 1999 ጀምሮ አመልካቾች ሁላችንም
የሚጠበቅብንን ሁሉ በማሟላት ሕጋዊ ውል ካገባን በኋላ ለእህል ወፍጮ አገልግሎት የሚሆን ቆጣሪ ገብቶልን
ሥራችንን እስከ መጋቢት ወር 2005 ዓ.ም ድረስ በመሥራት ለአካባቢያችን ሕብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ
በማበርከት ለመንግስትም በገቢያችን መጠን ገቢ እያስገባን የዜግነት ግዴታችንን እየተወጣን ሳለን ምንነቱን
በውል በማናውቀው ምክንያት የቡርሳ ወረዳ ኤሌክትሪክ ዲስትሪክ ሥ/አስኪያጅ ማስረጃ ተካ የተባለው
ማብራት ቆርጦብን የአካባቢው ሕብረተሰብ- ያገኝ የነበረውን የእህል ወፍጮ አገልግሎት እንዳያገኝና ቀደም
ሲል ወደነበረበት ችግር እንድመለስ ያደረገ ከመሆኑም በተጨማሪ እኛም በሰራነው ልክ ለመንግሥት
የሚያስገባውን ገቢ በማስቀረት በሀገር ገቢም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚሳድር ስለሆነ የደረሰብንን ከፍተኛ ችግር
ስፍራው ድረስ በመሔድ ተጣርቶ የተቋረጠው ማብራት እንዲቀጠልልንና ሕብረተሰባችንን ማገልገል
እንድንችል እንዲደረግልን ስንል በአክብሮት እናመለክታለን፡፡ አመልካቾች 1. ቃዋቶ ጉራራ
2. ቶሼ ዋጄ
3. ሀምሳለ ሀሪሶ
4. ክፍሌ እሽኔ
5. ክፍሌ ሃርቃ
ቀን -----------------------------
ለሀዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ታቦር አካባቢ ምድብ ችሎት
ሀዋሣ ፣
አመልካች ፡- ወ/ሮ ሚሚ ዓለሙ
አድራሻ፡- ሀዋሣ ከተማ ታቦር ክ/ከተማ ጢልቴ ቀበሌ
ተጠሪ፡- አቶ ቢሊሶ ብርሃኑ
አድራሻ፡- ሀዋሣ ከተማ ታቦር ክ/ከተማ ጢልቴ ቀበሌ
በደቡብ ክልል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/96 በአንቀፅ 90 መሠረት ጋብቻ በፊቺ እንዲፈርስ
እንዲወሰንልኝ ለመጠየቅ የቀረበ አቤቱታ
ሀ. ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን አለው፡፡
ለ. ለተጠሪ የሚላከውን መጥሪያ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በታቦር ክ/ከተማ ጢልቴ ቀበሌ ጽ/ቤት በኩል
እንዲደርሰው እንዲታዘዝልኝ፡፡
ሐ. ለአቤቱታው ምክንያት የሆነው ዝርዝርና አመልካች ፍ/ቤቱን የምጠይቀው ዳኝነት ከዚህ
እንደሚከተለው በዝርዝር ይቀርባል ፡፡
የአቤቱታው ዝርዝር በአጭሩ
አመልካች እና ተጠሪ ታሕሣሥ 19 ቀን 2000 ዓ.ም በሲዳማ ባህል በባህላዊ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ሕጋዊ
ጋብቻ ፈፅመን በጋብቻ ተሳስረን እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ ለ 5 ዓመታት በጋብቻ የቆየንና የጋብቻችን ውጤት
የአብራካችን ክፋይ የሆነችውን ህፃን ምህረት ቢሊሶ የተባለችውን ዕድሜዋ 4 ዓመት የሆናትን ልጅ ወልደናል፡፡
በአሁኑ ሰዓትም አመልካች ከፀንስኩ ሶስት ወር ሆኖኛል፡፡ አመልካችና ተጠሪ በጋብቻ በቆየንበት ዘመን
ትዳራችን መተሳሰብና መከባበር መቻቻል የተሞላበት የነበረ ቢሆንም ተጠሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቀድሞ
ባሕሪውን በመቀየር በጋብቻችን ውስጥ ሊኖር የሚገባውን የመከባበር፣የመተጋገዝ፣ለትዳሩ እንደአቅሙ
አስተዋፅዖ የማድረግ ግዴታውን ወደ ጎን በመተው ለቤቱ ቀለብ የማይሰጥ ፣ዘውትር ጠጥቶ እየመጣ
የሚጨቀጭቅ ፣ቤቱንና ትዳሩን ትቶ ውጪ አድሮ የሚመጣ እና ሰክሮ በመጣ ቁጥር አመልካችን
የሚደበድበኝ፣በሴትነት ክብር የማይሰጠኝ ሲሆን አመልካችም ይህን አለመግባባት ለመፍታትና ከተጠሪ ጋር
አብሬው ለመኖር በማሰብ በጎረቤት ሽማግሌዎች ተጠሪ በተደጋጋሚ ባስመክረውም የቀድሞ ባህሪውን
ሊቀይር ያልቻለና ይባስ ብሎ በቀድሞ ባህሪው የቀጠለ በመሆኑ በዚህ ሁኔታ አመልካች ከተጠሪ ጋር በጋብቻ
መኖር ስለማልችል በመካከላችን ያለው ጋብቻ እንዲፈርስ የፍቺ ውሳኔ እንዲሰጠኝና ከጋብቻችን የተወለደው
ልጅ የቀለብ ተቆራጭ እንዲደረግ እንዲሁም የአመልካች እና የተጠሪ ጋብቻ በፍቺ እንዲፈርስ የፍቺ ውሳኔ
እስኪሰጥ ድረስ ጊዜያዊ የቀለብ ተቆራጭ ተጠሪ ለአመልካች እንዲያደርግ እንዲወሰን አመልካች ይህን አቤቱታ
ለማቅረብ ተገድጄያለሁ፡፡
አመልካች ፍ/ቤቱን የምጠይቀው ዳኝነት
1. በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለው ጋብቻ በፍቺ እንዲፈርስ ውሳኔ እንዲሰጥና ለጋብቻው መፍረስ
ምክንያት የሆነው ተጠሪ መሆኑን አመልካች በማቀርበው ማስረጃ ተረጋግጦ ተጠሪ ለአመልካች በክልሉ
የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/96 በአንቀፅ 95(2) መሰረት የሞራል ካሣ እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ፣
2. ከአመልካችና ከተጠሪ የተወለደችውን ልጅ በተመለከተ ልጅቱ ዕድሜዋ 4 ዓመት ስለሆነ ተጠሪ ለልጅቱ
በወር በወር ቀለብ እንዲቆርጥላትና ልጅቱ ከአመልካች ጋር እንድትኖር እንዲወሰን፣
3. በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለው ጋብቻ በፍ/ቤት የፍቺ ውሳኔ እስከሚያገኝ ድረስ ተጠሪ ጊዜያዊ
ቀለብ እንዲቆርጥ እንዲታዘዝ፡፡
ከዚህ በላይ የተመለከተው እውነት መሆኑን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሠረት አረጋግጣለሁ፡፡

አመልካች

ወ/ሮ ሚሚ ዓለሙ
ቀን 08/08/2005 ዓ.ም
ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ርዕስ መስተዳድር ጽ/ቤት
ሀዋሣ ፣

አመልካቾች ፡- የኢት/የሲዳማ ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ምዕመናን


አድራሻ፡- ወ/ገነት ወረዳ አባዬ ቀበሌ
የምናመለክተውም ጉዳይ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
አመልካቾች የኢት/የሲዳማ ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ አጥቢያ ቤተክርስቲያናችን በፍትህ ሚኒስቴር
የኃይማኖት ድርጅቶችና ማሕበራት በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት
አግኝቶ ሲንቀሳቀስ በቆየው የኢት/ቃለ ብርሃን ሀዋሣ ቤተክርስቲያን ሥር በርካታ አጥቢያ
ቤተክርስቲያኖች ተመስርተው ሕዝቡ ከእግዚአብሔር አምላኩ ጋር በፀሎት በመገናኘት ለሀገር ሰላም፣
ለአገር መሪዎች ለእራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ብሎም ለአለም ሰላም ጭምር ሌት ተቀን በፍጹም
መፈቃቀድና በሰላም በፍቅር ላይ በመመስረት ሲያመልክና ሲፀልይ በቆየው ማሕበረሰብ ውስጥ ከሕዝብ
ይልቅ ለእራሳቸው ጥቅምና ፍላጎት ያደሩ ቀደም ሲል ከ 1 ዓመት በፊት የአጥቢያችን አባል የነበሩና
በእራሳቸው ጊዜ አፈንግጠው በመውጣት የወንዶ ክልል ቃል ብርሃን በሚል የስም ስያሜ አጥቢያ
በመመስረት ይሔንኑ ስያሜ የሚገልፅ ማሕተም በማስቀረፅ እንዲሁም መዘምራን ጭምር በማደራጀት
ከአጥቢያችን ተለይተው የሚገኙ እነ አበራ ካለቃ 5 ሰዎች ለበርካታ ዘመናት በአንድ ላይ አብሮ
እያመለከና እየፀለየ በቆየው የአጥቢያችን ምዕመናን ውስጥ በመግባት ሕዝብን በጎሳ በማከፋፈል ቁጥሩ
ከ 500 በላይ የሚሆነውን ሕዝብ የሚያመልክበትን ከሕዝቡ ፍላጎት ውጪ በሕዝብ ሳይመረጡ
መሪዎቻችሁ እኛ ነን በማለት እንዲያገለግሉን የመረጥናቸውን ግለሰቦች እራሳቸው ሰብሳቢ፣ሻሚና ሻሪ
በማድረግ በያዙት የሐሰት ቃለ ጉባዔ የተወገዱ ናቸው በማለት ሕዝቡን በማመስ የማያባራና ከፍተኛ
የሆነ የደም መፋሰስ ለማስከተል ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጋቸውን በመመልከት የአምልኮ ፈቃድ ለሰጠው
በፍትህ ሚኒስቴር የሃይማኖቶች ድርጅቶችና ማሕበራት ዳይሮክተሬት ዳይረክተር በማሳወቃችን የተነሳ
ለዋናው ኢት ቃል ብርሃን ቤተክርስቲያን ሀዋሣ እና በኢት/ያ ቃል ብርሃን ቤተክርስቲያን በአመራሮች
መካከል በተፈጠረው አለመግባባት አመራሮቹ በሁለት ወገን በመከፈላቸው ማለትም አንደኛው ወገን
እነ ጢሞቴዎስ በራሳ ሥር የሚገኙ እነ አበራ ከለቃ 5 ሰዎች ሁለተኛ ወገን እነ መንገሻ ጤካሞ ሥር
ለሚገኙ ከመሰል ድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የማይቆጠቡ

ከሆነ ግን ለሚከሰተው ችግር ሁሉ ተጠያቂ መሆናቸው ተጠቅሶ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮና
ለክልሉ ሴክተር መ/ቤቶች ሁሉ ክትትል እንዲደረግ በማለት በቁጥር H/G ፈ/ሀ/367/05-362 በቀን
27/3/2005 ዓ.ም ተፅፎ ወጪ በሆነ ሰርኩላር ደብዳቤ የተገለፀ ቢሆንም እኛ የአሁኑ አመልካቾች
ቤተ/ያን ምዕመናን ላይ እየደረሰ ያለውን በደልና ሊደርስብን ያለው ከፍተኛ ችግር እንዲያውቁልን
ለደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ፍትህ ቢሮ፣ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ፖሊስ ኮሚሽን ፣ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ፀጥታ
ጽ/ቤት ፣ ለሲዳማ ዞን ፍትህና ፀጥታ ጽ/ቤት ፣ የፌዴራል የሕዝብ እንባ ጠባቂ ጽ/ቤት ፣ የፌዴራል
የሕዝብ ደህንነትና መረጃ ጽ/ቤት ብንገልፅም የኢት/ቃል ብርሃን ቤተክርስቲያን ሀዋሣ እና እራሳቸውን
የወ/ገነት ክልል ቤ/ያን ብለው የሚጠሩት የእነ ጢሞቴዎስ በራሳ ወገን ነን ባዮች ቀደም ሲል
ከተላለፈው መመሪያ ውጪ በሆነ መንገድ ሃይማኖትን ሽፋን ማድረግ አቶ አበራ ከለቃ በወንዶ ገነት
ወረዳ የሲሀዴድ (የሲዳማ ሀዲቾ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት) ምክትል ሊ/መንበር በመሆኑ የድርጅቱንና
የራሱን ድብቅ ተግባራቸውን ለማሳካት ከመሰሎቹ ጋር በመሆን በምዕመኑ ውስጥ ከፍተኛ የደም
መፋሰስ እንዲፈጠር እየሰሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ውድና መተኪያ የሌለውን የሰው ሕይወት
ከመጥፋቱ በፊት መንግሥት በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ ከክፉ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ተገቢውን
የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ የሕዝቡን ሕይወት እንዲታገድልን ስንል በታላቅ አክብሮት
እናመለክታለን፡፡

አመልካቾች

የኢት/የሲዳማ ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ


አጥቢያ ቤተክርስቲያን ምዕመናን
ቀን 26/07/2005 ዓ.ም
ለሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ
ሀዋሣ ፣
አመልካች ፡- ወ/ሮ እልፌ ቱንሲሳ
አድራሻዬ፡- ቡርሣ ወረዳ ማጣና ሙርሻኖ ቀበሌ
መልስ ሰጪ፡- አቶ ዘርፉ ሸለሞ
የቡርሣ ወረዳ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት
የአቤቱታዬ ዝርዝር መግለጫ በአጭሩ
1 ኛ. እኔ አመልካች ባለቤቴ ከሆነው አቶ ታደለ ሄለቆ ጋር ለረዥም ዓመታት በትዳር ቆተንና ስምንት ልጆች ወልደን
የኖረን ስንሆን ኑሮአችን የተመሠረተው በእርሻ ስራ ነው፡፡ የእርሻ ይዞታችን በሁለቱ ወረዳ ማለትም ከቡርሣና
በቦና ወረዳ ይገኛል፡፡ በሁለቱም ቦታዎች ቤት ያለን ሲሆን ዋና መኖሪያችን ቡርሣ ወረዳ በሚገኘው ቀያችን
ነው፡፡
2 ኛ. ይሁን እንጂ ባለቤቴ እኔ ሳልፈቅድና ሳላውቅ በጋብቻ ላይ ጋብቻ ደርቦ ወ/ሮ አዋዉ ዱሞ የተባለችውን ባሏ
የሞተባትን ከቡርሣ ወረዳ ጡጎ ቀበሌ መስከረም 24 ቀን 2005 ዓ.ም አግብቶ ቦና ወረዳ በሚገኘው ቤቴ
ያስቀመጠ መሆኑን ለመረዳት ችያለሁ፡፡
3 ኛ. በዚህ ምክንያት ቡርሣ ወረዳ ምርመራና ክስ ንዑስ የስራ ሂደት በሁለቱም ላይ ክስ መስርቼ ወደ ቦና ወረዳ ፖሊስ
ተፅፎ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ወደ ቡርሣ ወረዳ በአጃቢ ተላኩ ፡፡
4 ኛ. ተከሣሾች ምርመራና ክስ የስራ ሂደት ቀርበው የዕምነት ቃላቸውን ሰጡ ፡፡ 1 ኛ ተከሳሽ የነበረው ባለቤቴ አምኖ
ቃሉን ሰጠ፡፡ መዝገቡ ወደ ቡርሣ ወረዳ ፍ/ቤት ተላልፎ የዐ/ሕግ ማሰረጃዎች በክሱ ጭምጥ መሠረት
አረጋግጠው መሰከሩ ፡፡ ፍ/ቤቱ ተከሣሾች መከላከያ እንዲያቀርቡና እንዲከላከሉ ብይን ሰጠ፡፡ ይህንን መዝገብ
የያዙት የፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት እና መልስ ሰጪ የሆኑት አቶ ዘርፉ ሸለሞ ናቸው፡፡
5 ኛ. ተከሳሾች ከአራት ጊዜ በላይ መከላከያ መልስ እንዲያቀርቡ እድሉ ተሰጣቸው፡፡ በተሰጣቸው እድል ሊጠቀሙ
አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም እኚሁ የፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት ለጥር 7 ቀን 2005 ዓ.ም በችሎት ላይ ለውሳኔ ቀጠሮ
ያዙ፡፡
6 ኛ ተከሳሾች ውሳኔ በሚሰጥበት ቀን ሽማግሌዎችን ሰብስበው ተማፅነው ከፍ/ቤት ነገሩን ለማየት ለሽማግሌዎች
እንዲሰጥ ጠይቀው ለሽማግሌዎች ተሰጠ፡፡
7 ኛ. የሀገር ሽማግሌዎች ጉዳዩን አይተው ተከሳሹ ባለቤቴ ጥፋተኛ ነኝ ብሎ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነችውን ከቤት
አወጣለሁኝ ብሎ ውል ሰጥቶና ፈርሞ ጉዳዩ በእርቅ አለቀ፡፡
8 ኛ. በቀነ ቀጠሮው ሽማግሌው ሪፖርት ሲያቀርቡ ጥፋተኛ መሆኑን አምነው ከቤት እንዲያወጣ ካላወጣ መቀጮ
ብር አሥር ሺህ እንደሚከፍል ውል እንደሰጠ ለችሎቱ አስረድቶ ውሉንም ለዳኛው ሰጡ፡፡

የፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት ከእውነተኛ ፍትህ አሰጣጥ ውጪ ተከሳሹን ለመርዳት ይህን ውል በፈረምክ ሰዓት ነው
በራስህ ላይ የእሳት ፍም ያኖርከው በማለት በሽማግሌ ፊት ተናገሩ በችሎትም ላይ የቤቱን ቁልፍ ከተከሣሽ
ተቀብለው ለእኔ ለአሁኗ አመልካች ሰጡኝ የፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት ሁለተኛ ተከሣሽ ከቤት መውጣቷ ተረጋግጦ
ፋይል ለመዝጋት ቀጠሮ ሰጡ ፡፡ ይሁን እንጂ እኔ ለማወቅ ባልቻልኩት መንገድ በተደረገ ትስስር ተከሣሽዋ ወ/ሮ
አዋዉ ዱሞ ከቤት እንዳትወጣ ተደረገ ፡፡
9 ኛ. በተሰጠው ትዕዛዝና ቀጠሮ መሠረት ከቤት አለመውጣቷን ሪፖርት ለማድረግ ችሎት ስንቀርብ የፍ/ቤት
ፕሬዝዳንት ከሕግ ትርጉም ውጪ ተከሳሽ አምነው ውል የሰጡትን ውሳኔ ለመስጠት ያደረውን በሽማግሌም
ያለቀውን እንደገና ወደ ኋላ መልሰው መከላከያ እንዲያቀርቡ አዘውና መከላከያ አዳመጥኩ ብለው ተከሳሾች
ጥፋተኛ ነን ብለው ውል የሰጡትን ጉዳይና ራሳቸው የፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንቱ የቤቴን ቁልፍ ያስረከቡኝን ጉዳይ
በ 24/5/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛ አይደለም በማለት መዝገቡን ዘጉብን ፡፡
10 ኛ. በወቅቱ ተከሣሹ ባለቤቴ ወደ ቤት አላስገባ ብላኛለች ብሎ ሲናገር የፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት በችሎት ላይ ሽማግሌ
ባለበት እጇን ወደ ኋላ አስረህ ወደ ቤትህ ከዛሬ ጀምሮ ግባ ብሎ የመግደል እርምጃ በድፍረት እንዲወስድብኝ
አዘዙ ፡፡
11 ኛ. ወ/ሮ አዋዉ ዱሞ ባሏዋ የሞተባት ስትሆን አሟሟቱ በምን እንደሆነ ያልታወቀውን ሳይመረመር እጄን አስሮ
ወደ ቤቴ እንድገባ መታዘዙና አጠቃላይ የፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት ፍርደ ገምድላዊ ውሳኔ መፈጠሬን አስመርሮኝ
ለሁለት ሳምንታት በጤና ታምሜ ተኛሁ፡፡
12 ኛ. የሕግ እውቀት የሌለኝ በመሆኑ ይህ የይግባኝ መጠየቂያ ጊዜ አለፈብኝ፡፡ ስለሆነም የጋብቻ ፍቺ ጥያቄ
ለማቅረብ አቤቱታ አዘጋጅቼ የካቲት 20 ቀን 2005 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ ለወረዳ ፍ/ቤት አቀርብኩ፡፡ የፍርድ
ኦፊሰሮች የዳኝነት 100 ብር እንደምከፍል ነገሩኝ፡፡
13 ኛ. ይህን የዳኝነት ብር ለማግኘት ችግር ያለብኝ ስለሆነ የቤተክርስቲያኔ እረኛ መልክዕክት ልኬ እንዲያመጡልኝ
አስደርጌ ይዘው ግቢ እንደገቡ ይህችን ሴትየው ልትረዳ ነው የመጣኸው ብለው አሰሩዋቸው፡፡ በዚህ ምክንያት
አቤቱታዬን እስከአሁን በእጄ ይገኛል፡፡
የሲዳማ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ
የፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት እኔ ሴት አቅመ ደካማ የሆንኩትን ሥልጣናቸውን መከታ አድርገው ከሕግ ድጋፍ ውጪ
የወንጀል መ/ቁጥር 05726 የሆነውን ተከሳሾች አምነው ቃል የሰጡትን እንዲሁም በሽማግሌዎች ፊት
አምነው ውል የሰጡትን ጉዳይ ይህን ውል ስትፈርም በጭንቅላትህ ላይ ፍም አኖርክ በማለት በመቆጨት
ተናግረው እንደባሪያ አሳዳሪ ሥርዓት እጇን

ወደ ኋላ አስረህ ግባ በማለት ባለቤትዋ በምን ምክንያት እንደሞተ ከማይታወቅ ሴት ጋር የቆየውን


ሳይመረመር በሕይወቴ ላይ ፈርደው መዝገቡን ከዘጉብኝ በኋላ ለፍት/ሔር ክስ የዳኝነት ብር ይዘውልኝ
የመጡትን አስረው የዜግነት መሠረታዊ መብቴንና ነፃነቴን እንዲሁም ከወንዶች እኩል ፍትህ የማግኘት
ሕገ መንግሥታዊ መብቴን ገፈውኛል፡፡
ስለሆነም ዳኛው ለፈፀመብኝ በደል ለመ/ሰጪው ፕሬዝዳንት መጥሪያ ደርሶአቸው መልስ እንዲሰጡና
ከአመኑ በአመኑ መሠረት ካላመኑ በዘረዘርኳቸው የሰነድና የሰው ማስረጃዎች ተረጋግጦ በዚህ ጉባዔ
ተገቢው ውሳኔ እንዲወሰንባቸው ለዚህ እንግልት ዳርገው ለፈፀሙብኝ በደል ወጪና የሞራል ካሣዬን
እንዲከፍሉኝ እንዲታዘዝልኝ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡
አመልካች

ወ/ሮ እልፌ ቱንሲሳ


ማስረጃዎች
1 ኛ. የፅሁፍ ማስረጃ
1.1 የእርቅ ውል 2 ገፅ ኮፒ
2 ኛ. የሰው ማስረጃ
2.1 አቶ ኤልያስ ቡንካና
2.2 አቶ ዳዊት መጋኔ
2.3 አቶ ታፈሰ ዴቢሶ
ግልባጭ ፣
 ለሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳር ጽ/ቤት
 ለሲዳማ ዞን ደኢህዴን ጽ/ቤት
 ለሲዳማ ዞን ሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤት
ሀዋሣ ፣
መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም
ለሀዌላ ቱላ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ቱላ ፣
ከሣሽ ፡- ወ/ሮ ሸርባቱ ቃምሶ
ተከሳሽ፡- ጁግሳ ሶአቶ
ከሣሽ በቀን 20/07/2005 ዓ.ም ፅፋ ያቀረበችው የወጪ ኪሳራ ክስ ደርሶኝ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 234 መሰረት ከተከሣሽ የተሰጠ መልስ
የክሱ ይዘት በአጭሩ
ቀደም ሲል ከተከሣሽ ጋር በነበረኝ በፍትሐብሔር የይዞታ ክስ ክርክር በፍርድ ሲወሰንልኝ ክሱ ያስከተለውን ወጪ
የመጠየቅ መብቴ በመጠበቁ ያወጣሁት ወጪ ገንዘብ ብር 1854 እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው፡፡

1. ከሣሽ ከተከሣሽ ጋር በነበረኝ ክስ ከጨፌ ኮቲጀቤሳ ቱላ ለ 10 ቀጠሮ ደርሶ መልስ የተመላለስኩበት 20x10=200
ይከፈለኝ ከማለት ያለፈ አያይዛ ያቀረበችው ማስረጃ የለም በተጨማሪም ከሀዋሣ እስከ ቱላ ትራንስፖርት ብር 6
ሲሆን ደርሶ መልስ ብር 12 ብቻ በመሆኑ መዝገብ ላይ ካለው ቀጠሮ ልክ ብቻ ተሰልቶ ሊቀርብ ሲገባው በማስረጃ
ያልተደገፈ በከሣሽ ፍላጎትና ስሌት ተሠልቶ የቀረበው ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡
2. የቁርስና ምሳ በ 10 ቀጠሮ ተባዝቶ 30x10= 300 እንዲከፍል የተጠየቀውም አግባብነት የለውም ፡፡ ምክንያቱም
ችሎት የሚጀምረው ከ 3፡30 እስከ 4 ሰዓት ከመሆኑም በተጨማሪ ከሣሽ ከሚገኝበት ቱላ ለመምጣት ከ 20 ደቂቃ
በላይ የማይፈጅ በመሆኑ ቁርስ ቤት ተበልቶ ምሳ ወደ ቤት የሚደረስበት ቅርብ ቦታ ሆኖ ሳለ በእራሱ ስሌት አስልቶ
ያለአንዳች የማስረጃ ድጋፍ ያቀረበው የሕግ ድጋፍ የሌለው ነው፡፡
3. ለፅሁፍ በባለሙያ የተከፈለ ብር 150 እንዲከፍል የቀረበው ታማኝነት የሌለው ነው የቀረበው ፅሁፍ በባለሙያ
ተሰርቶ የቀረበ ቀርቶ በራፖር ፀሐፊ የተዘጋጀ አለመሆኑን አቤቱታው የሚያስረዳ ከመሆኑም በተጨማሪ ተያይዞ
የቀረበ ማስረጃም የለም፡፡
ለሁለት ማስረጃዎቼ ብር 200+ 200= 400 የሰጠሁበት ይክፈለኝ ሲል ያቀረበውም ቢሆን ለእነ ማን መቼ ስንት
ብር እንደሰጠ የሚያመለክት ሰነድ ተያይዞ ባልቀረበበት በደፈናው በሰው ላብና ድካም ለመክበር ካለው ምኞት
የተነሣ የቀረበ የሐሰት ክስ ለመሆኑ አቤቱታ በእራሱ ገላጭ ነው ፡፡
በተጨማሪ በክሱ ምክንያት ማግኘት የነበረብኝ ብር 500 ሲል ያቀረበውም የማስረጃ ድጋፍ የሌለውና
ከማስረጃ ዝርዝር ጋር ተቀላቅሎ መቅረብ የሌለበት በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡
በአጠቃላይ ከሣሽ ያልደከመበትን የሰውን ላብና ድካም ከቅን ልቦና ውጪ በማስረጃ ያልተደገፈ የሐሰት ክስ
በማቅረብ ፍርድን ለማዛባት ያቀረበች በመሆኑ ተቀባይነት በማሳጣት ወጪዬን በቁርጥ እንዲከፈለኝና መዝገቡም
በፍርድ ተዘግቶ እንዲሰናበት አመለክታለሁ፡፡
መልሴም በእውነት የቀረበ ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሠረት በቃለ መሀላ በማረጋገጥ አቀርባለሁ፡፡

መልስ አቅራቢ

ጁግሳ ሶአቶ
ቀን -----------------------------------
ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ጠ/ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
ይግባኝ ባዮች ፡- 1 ኛ. ዘሪሁን ሰንበቶ
2 ኛ. እስራኤል ሃሪሶ
3 ኛ. የኢት/የሲዳማ ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ ቃል ብርሃን ምዕመናን
አድራሻችን ወ/ገነት ወረዳ አባዬ ቀበሌ
መ/ሰጪ ፡- የወንዶገነት ክልል ቃለ ብርሃን ቤተ/ያን
አድራሻ፡- ወ/ገነት ወረዳ አባዬ ቀበሌ
- የሥር የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 25202
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 327 መሠረት የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው
መግቢያ
- የይግባኝ አቤቱታው የቀረበበትን ፍርድ የሰጠው የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 25202 በቀን 28/06/05 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ መ/ሰጪ በሚገኝበት አባዬ ቀበሌ በኩል ሊደርሰው ይችላል፡፡
- የሥር ፍ/ቤት የውሳኔ መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ -- ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ) ለይግባኝ አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የይግባኝ አቤቱታ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው ቁጥራችን ከ 500 ሕዝብ በላይ የምንሆን በሲዳማ ክልል
የቦርታ ሲና ኢላላ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ተብሎ በሚጠራው ቤተክርስቲያናችን ውስጥ 1 ኛ ይ/ባይ በሰብሳቢነት
2 ኛው ይ/ባይ ደግሞ በሽምግልና በምዕመኑ ተመርጠን ለዓመታት ስናገለግል በቆየንበት አጥቢያ ውስጥ የመ/ሰጪ
ቤተክርስቲያን ተወካይ ነን ሲሉ እራሳቸውን የሰየሙት እነ አበራ ካለቃ ተብለው የሚጠሩትና 5 ሰዎች ከዛሬ
አንድ ዓመት በፊት በአጥቢያችን በአባልነት አብረውን ሲያመልኩ ቆይተው ያለምዕመኑ (ሕዝቡ) ፈቃድና ምርጫ
እንዲሁም ከአጥቢዋ እውቅና ውጪ ሰብሳቢም፣ቃለ ጉባዔ ያዥ ሻ D ሚና ሻሪ እራሳቸውን በማድረግ በሐሰት
አቀነባብረው ባቀረቡት ቃለ ጉባዔ በሕዝቡ ተመርጠን ከምናገለግልበት ቤተክርስቲያን ተወግደዋል በማለት
ምርጫ እናስመርጣለን በሚል በምዕመኑ ውስጥ ገብተው ለመቀስቀስ ያደረጉት ሙከራ ሊሳካላቸው ባለመቻሉ
‹‹መሣሪያ እራሱ ገሎ ይጮሃል እንደሚሉት ››እራሳቸው በአምልኮ ሰዓት ገብተው የፈጠሩትን ሁከት ወደ ጎን
በተመው በፍርድ ሁከት ይወገድልን ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታ ተቀብሎ የተመለከተው የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ቀደም ሲል በ 09/08/2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት በመ/ሰጪ የቀረበውን ክስ ተመልክቶ የአሁኑ ይ/ባዮችን
አያስከስሳቸውም በማለት በብይን መዝገቡን ዘግቶ ካሰናበተን በኋላ በይግባኝ የተመለከተው ይሄው ጠ/ፍ/ቤት
በማስረጃ ተሰምቶ ይወሰን በማለት በነጥብ ወደ ኋላ በመመለሱ የተነሣ ከአጥቢያችን የሲዳማ ክልል ቦርታ ሲና
ኢላላ አጥቢያ ቤተክርስቲናችን አፈንግጠው በመውጣት እራሳቸውን የወ/ገነት ክልል ቃል ብርሃን ቤተክርሰቲያን
በሚል አዲስ የስም ስያሜ በመሰየም እያመለኩ የሚገኙበትና ሁለት የተለያዩ አጥቢያዎች መሆናቸውን በመግለፅ
ከመከራከራችን በተጨማሪ በእራሳችን አጥቢያ ውስጥ በሃይል በመግባት አዲስ ምርጫ እናስመርጣለን በሚል
በአምልኮ ሰዓት በመረበሻቸው ሕዝቡ ወደንና ፈቅደን በመረጥናቸው ሰዎች እየተገለገልን የምንገኝ በመሆኑ
አዲስ የሚደረግ ምርጫ የለም በማለት ድምጹን በማሰማቱና በአካባቢው የፀጥታ ሃይል እርዳታ ጭምር ሊከሰት
የነበረው የደም መፋሰስ መቅረቱን ጭምር ከምዕመኑ ውስጥ የተወሰኑትን በማስቀረብ ምስክርነት
ከማሰማታችን በተጨማሪ ለትክክለኛው ፍትህ አሰጣጥ ያመች ዘንድ አጥቢያችን ወደምትገኝበት ድረስ በመሄድ
ተጣርቶ እንዲወሰንልን ያቀረብነው የፍትህ ልመና ያለአንዳችን በቂና ሕጋዊ ምክንያት ተቀባይነት በማሣጣት
የተሰጠውን አሳዛኝ ፍርድ ለማስለወጥ የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡
ሐ) በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልን የምንጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ
1. የመ/ሰጪ ቤተክርስቲያን ወኪል ነን ባዮች ከአጥቢያችን አፈንግጠው በመውጣት የወንዶገነት ክልል ቃል ብርሃን
ቤተከርስቲያን በሚል የሚጠራ አጥቢያ በመመስረት ይህንኑ የስም ስያሜ የሚገልፅ ማሕተም በማስቀረፅ
እንዲሁም ለመሠረቱት ቤተከርስቲያናቸው አገልግሎት የሚያስፈልጉ ኳየር /መዘምራን/ እና የመሳሉትን
አሟልተው እያመለኩ ሳለ ቀደም ሲል

ከነበሩበትና በእራሳቸው ጊዜ አፈንግጠው ከወጡበት አጥቢያችን የሲዳማ ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ ቃል ብርሃን
ቤተክርስቲያናችን ውስጥ እንዳሉ በማስመሰል እራሳቸውን ሰብሳቢ ፣ቃለ ጉባዔ ያዥ፣ ሻሚና ሻሪ በማድረግ
በሥነምግባር ብልሹነት ከአጥቢያችን እንደተወገድን በመግለፅ የያዙት ቃለ ጉባዔ የሐሰት መሆኑንና
እንዳልተወገድን ገልፀን ከመከራከራችንም በተጨማሪ ቀደም ሲል ከ 4 ዓመት በፊት በሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ከመ/ሰጪ ተወካይ ነን ባዮች ጋር በነበረን ክስ ከአጥቢዋ የተወገዱ በመሆናቸው ክስ ሊያቀርቡም ሆነ
በአጥቢያው ጉዳይ ገብተው ሊከራከሩ መብትና ጥቅም የላቸውም ሲሉ ያቀረቡት መቃወሚያ በመ/ቁጥር
13715 በቀን 23/10/2001 ዓ.ም በዋለው ችሎት የኢት/የቃል ብርሃን ቤተክርስቲያን ሀዋሳ ለሁለት ከተከፈለው
አባላት ወይም ምዕመናን ተመርጠው የውል ስምምነት እስከገቡ ድረስ የውሉን ስምምነት ለማስፈፀም ሙሉ
ሃላፊነት ከአባሎቻቸው የተሰጣቸው መሆኑንና ከአባሎቻቸው የተሰጣቸው ውክልና እስካልተነሳ ድረስ
ምዕመኑን /አባላቱን/ ወክለው መከራከር ይችላሉ በማለት መቃወሚያቸው ውድቅ ተደርጎ የተሰጠው ብይን
በይግባኝ አለመሻሩን በመግለፅ የመ/ቁጥር 13715 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145 መሠረት ፍ/ቤቱ አስቀርቦ
በመመልከት አጣርቶ እንዲወሰንልን ያደረግነውን ከርክር ተቀባይነት በማሣጣት አላመባረራቸውን የሰነድ
ማስረጃ አቅርበው አልተከራከሩም በሚል የተሰጠው በሕግ ላይ ያለንን ከፍተኛ እምነት የሚያዛባና ቁጥሩ
ከ 329 በላይ በሆነው ሕዝብ ምዕመናንና የመ/ሰጪ ተወካይ ነን ባዮች ቤተሰቦች ጋር ከፍተኛ የሆነ
ያለመግባባትን የሚያስከትል አሳዛኝ ፍርድ ስለሆነ ተጣርቶ እንዲሻርልን፡፡

2. የመሰጪ ተወካዮች ነን ባዮች በእራሳቸው ጊዜ ቀደም ሲል ከነበሩበት የሲዳማ ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ ቃል
ብርሃን አጥቢያችን አፈንግጠው ከወጡ በኋላ የወንዶገነት ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ የቃል ብርሃን የሚል ሌላ
ቤተክርስቲያን በመመስረት እራሳቸውን ከአጥቢያችን መለየታቸውን በ 11/03/2004 ያዝን ባሉት ቃለ ጉባዔ
ይ/ባዮችንና ሌሎችን አስወገድን ሲሉ እራሳቸውን ሻሚና ሻሪ በማድረግ ያቀረቡት ቃለ ጉባዔ ላይ የወንዶገነት
ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ የቃል ብርሃን አጥቢያ ቤ/ያን የሚል ማሕተም አሳርፈው ካቀረቡ በኋላ ከ 1 ዓመት
በፊት አፈንግጠው በመውጣት የተለዩትን ቤተክርስቲያን እንደግል ንብረታቸው በመቁጠር መልሰው ሁከት
ይወገድ ብለው ማቅረባቸው አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1149 (2) መሠረት ሁከት
ይወገድልኝ በሚል የሚቀርብ ክስ በፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1140 መሠረት በእጅ የተያዘና በእውነት የሚያዙበት ብቻ
እንደሆነ የተደነገገ ከመሆኑም በላይ ከ 1 ዓመት በፊት በእራሳቸው ጊዜ አፈንግጠው ጥለው በመሄድ ሌላ
ቤተክርስቲያን መመስረታቸውን የሚገልፅ ማሕተም በመቅረፅ ያዝን ባሉት ቃለ ጉባዔ ላይ አሳርፈው
እስካላቀረቡና ከአጥቢያችን መለየታቸውን እራሳቸው ባቀረቡት ክሳቸው የወንዶ ገነት ክልል ቃል ብርሃን
በማለት የስም ስያሜውን ለይተው አስከቀረቡ ድረስ ሁከት ይወገድልኝ በሚል ክስ ሊያቀርቡ የሚችሉበት
የሕግ አግባብ አለመኖሩን በመግለፅ ከመከራከራችንም በተጨማሪ ለትክክለኛውና እውነተኛው ፍትህ ሲባል
በፍ/ብ//ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 132 መሰረት አጥቢያዋ አለችበት ድረስ በመሄድ ምዕመኑን ሕዝቡን በመጠየቅ
ተረጋግጦ እንዲወሰን ያደረግነውን ክርክር ተቀባይነት በማሳጣት መወሰኑ አግባብ ባለመሆኑ ተጣርቶ ውሳኔው
ተሽሮ እንዲወሰንልን ፣

3. ባቀረብናቸው የመከላከያ ማስረጃችን ከአጥቢያዋ አለመባረራችንንና አፈንግጠው ከወጡ በኋላ ቁጥራቸው


ከ 15 የማይበልጡ ሰዎችን በማደራጀት ከዋናዋ ቤተክርስቲያን ሀዋሣ ጥቂት መሰሎቻቸውን በመያዝ ለሕዝቡ
ሳያሳውቁና በቤተክስቲያኒቷ ደንብ መሠረት ምርጫ ካለ አስቀድሞ ምዕመኑ/ሕዝቡ/ እየፀለየ እንዲቆይ
መደረግ የነበረበትን ስነሥርዓት ባልተከተለ መልኩ በአምልኮ ሰዓት ድንገት በመግባት አምልኮውን በማስቆምና
በማስተጓጎል ምርጫ እናደርጋለን በሚል ያነሱትን ሁከት ሕዝቡ እንደማይቀበል በመግለፅና በፀጥታ አስከባሪ
እርዳታ የብዙዎች ሕይወት መታደጉንና ይግባኝ ባዮች ሳንሆን የመ/ሰጪ ተወካዮች ነን ባዮች እራሳቸው ሁከት
መፍጠራቸውን በመግለፅ አስረግጠው የሰጡትን የብዙሃኑን የምስክርነት ቃል ተቀባይነት በማሳጣት የወጪ
ኪሳራ የመጠየቅ መብታቸው ተጠብቆ ሁከት ይወገድ ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ባለመሆኑ በሕግ አግባብ
በጥልቀት ተጣርቶ እንዲሻርልን፡፡
የተከበረውን ፍ/ቤት የምንጠይቀው ዳኝነት
- በእራሳችን የሲዳማ ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ አጥቢያ ቤተክርስቲያንናችን ምዕመናን ተመርጠን ስናገለግል
ለበርካታ ዓመታት ከቆየንበት የመ/ሰጪ ተወካይ ነን ባዮች እራሳቸውን በመለየት ሌላ አጥቢያ መስርተው
በማምለክ ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ስለመሆናቸው 3 ኛ ይ/ባይ (ምዕመናን) በአቤቱታችን ከመግለፃችንም
በተጨማሪ ባቀረብናቸው የሰው ማስረጃዎች ጭምር ከአጥቢያችን አፈንግጠው የወጡና በአባልነትም ይሁን
በአመራር ደረጃ የማይታወቁ መሆናቸውን ከበቂ በላይ አስረግጠን ያሰማነውን የሰው የምስክርነት ቃል
ተቀባይነት በማሳጣት ሁከት ይወገድ ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ባለመሆኑ እንዲሻርልን ፡፡
- የመ/ሰጪ ተወካዮች ነን ባዮች ያለ የሲዳማ ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ ቃል ብርሃን ቤተክርስቲያን ምዕመናን
እውቅና ውጪ በቃለ ጉባዔ ያስወገድናቸው ሲሉ የገለጹት ቀደም ሲል በሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር
13715 ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ በነበረን ክስ ቀርቦብን ለነበረው መቃወሚያ በብይን ተቀባይነት በማሳጣት
በፍርድ ውድቅ የተደረገበት ሰነድ በትዕዛዝ ቀርቦ ተጣርቶ እንዲወሰንልን ያቀረብነውን አቤቱታ ተቀባይነት
በማሳጣት የተሰጠበት አግባብ እንኳን በውሳኔው ሳይገለፅ ከሲዳማ ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ አጥቢያዋ
አለመባረራቸውን አልገለጹም በሚል የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ባለመሆኑ የመ /ቁጥር 13715 የሆነው መዝገብ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 145 መሰረት ከሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በትእዛዝ ቀርቦ ተጣርቶ ውሳኔው ተሸሮ
እንዲወሰንልን፣
- መ/ሰጪን ለመደገፍ በሥር ፍ/ቤት ጣልቃገብ የሆኑት እነ ጢሞቴዎስ የኢት/ቃል ብርሃን ቤተክርስቲያን ሀዋሣ
ፈቃዱ ሳይታደስ እራሳቸውም በምዕመኑ ሳይመርጡና ሕጋዊ ሳይሆኑ እንዲሁም በፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር
እውቅና የሌላቸው ከመሆናቸው በተጨማሪ በምዕመኑ መካከል ከፍተኛ የሆነ የደም መፋሰስ እንዲፈጠር
በማድረግ ቤ/ያንቷ ከተቋቋመችበት ዓላማ ውጪ እየሰሩ መሆናቸው ተጠቅሶ ከፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር
የሃይማኖቶችና እምነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ለሴክተር መ/ቤቶች ሁሉ
ክትትል እንዲደረግ ጭምር መገለፁን በመግለፅ ያደረግነውን ክርክር ተቀባይነት በማሳጣት የተሰጠው ውሳኔ
አግባብ ባለመሆኑ እንዲታረምልን፡፡
- የኢት/የሲዳማ ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ ቃል ብርሃን ቤተክርስቲያን ምዕመናን ክሱ በቀጥታ የሚመለከተንና
ገብተን ካልተከራከርን የሚጎዳን መሆኑን በማየት በክሱ ውስጥ ገብተን የሥር ተከሣሾች የአሁኑ 1 ኛ እና 2 ኛ
ይ/ባዮች በእኛ ምዕመኑ የተመረጡ ሕጋዊ ሰዎች መሆናቸውንና ቁጥራችን ከ 329 የማያንስ ምዕመናን ስምና
ፊርማ እንዲሁም የአጥቢያችንን የስም ስያሜ የሚገልፅ ማሕተም ያረፈበትን ሰነድ ጭምር አያይዘን
በማቅረብ ያደረግነውን ክርክርና በምዕመኑ የተሰጠውን ምስክርነት ተቀባይነት በማሳጣት የተሰጠው ውሳኔ
አግባብ አይደለም፡፡
- በአጥቢያችን በምዕመኑ በጎ ፍቃድ ተመርጠን ለበርካታ ዓመታት እያገለገልን የቆየን መሆናችንን በመግለፅ
አስረግጠን ከማስመስከራችንም በተጨማሪ ለትክክለኛው ፍትህ አሰጣጥ ሊያመች በሚችል መልኩ ቁጥሩ
ከ 500 የማያንስ ምዕመናን መርጠውን እያገለገልን የቆየን ስለመሆናችን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁጥር 132 መሠረት
አጥቢያዋ አለችበት ወ/ገነት ወረዳ አባዬ ቀበሌ ድረስ በመሔድ ተጣርቶ የስር ፍ/ቤት ሁከት ይወገድ ሲል
ያለአግባብ የወጪ ኪሳራ የመጠየቅ መብት ጠብቆ የሰጠውን አሳዛኝ ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1)
መሠረት ሙሉ በሙሉ በመሻር እንዲወሰንልን በአክብሮት እናመለክታለን፡፡

ይ/ባዮች
1. ዘሪሁን ሰንበቶ
2. እስራኤል ሀርሶ
3. የኢት/የሲዳማ ክልል የቦርታ ሲና ኢላላ ቃል ብርሃን ምዕመናን
የመ/ቁጥር 24948
መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም
ለሀዋሣ ከተማ የመጀ/ደ/ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣

የአፈ/ከሣሽ፡- አቶ በረከት ፍቃዱ ሕጋዊ ወኪል አቶ አማኑኤል ባታሞ


አድራሻ፡- ሀዋሣ ከተማ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፍላደልፊያ ቀበሌ
የአፈ/ተከሳሽ፡- የሀዋሣ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
አድራሻ፡- ሀዋሣ ባህል አዳራሽ ክ/ከተማ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 463 እና 464 መሠረት ብር 10,455 (አሥር ሺህ አራት መቶ ሀምሣ አምስት ብር)
ተከሣሽ እንዲከፍል የቀረበ የወጪ ኪሣራ ክስ ነው፡፡
1. የክሱ ዝርዝር በአጭሩ
1.1 በአፈ/ከሣሽ እና በአፈ/ተከሣሽ መካከል ስላለው የባጃጅ መኪና ታርጋ ቁጥር 02725 ደ/ሕ የአፈ/ከሣሽ
ንብረት በሆነችው የአፈ/ተከሣሽ ፒካፕ ቶዮታ ታርጋ ቁ 0073 የሆነችው ገጭታ ከጥቅም ውጪ በማድረጓ
ምክንያት ተከሷል 2 ኛ ተከሣሽ ረዳት/ሣ ከክሱ ውጪ እንዲሆን ተደርጎ 1 ኛ ተከሣሽ የሀዋሣ ከተማ ፖሊስ
መምሪያ ባለቤትነቱ ተጠያቂ ስለሆነ ብር 26,070.00 (ሃያ ስድስት ሺህ ሰባ ብር) ለአፈ/ከሣሽ እንዲከፈል
ውሳኔ ሰጥቶ የአፈ/ከሣሽን የወጪ ኪሣራ መብት አስጠብቆ መዝገቡን ዘግቷል፡፡
2. የአፈ/ከሣሽ የምጠይቀው ዳኝነት
2.1 የአፈ/ከሣሽ ለፍ/ቤቱ ክስ፣ ለዳኝነት የከፈልኩት ብር 2,270.00 (ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ብር)
2.2 የአፈ/ከሣሽ ለሕግ ባለሙያ ለጠበቃ የከፈልኩት 6,400.00 (ስድስት ሺህ አራት መቶ ብር)
2.3 የአፈ/ከሣሽ ለውክልና ቴምብር የከፈልኩት 35.00 (ሰላሣ አምስት ብር)
2.4 ለክሱ የአፈ/ከሣሽ ያወጣሁት ለጽሕፈት፣ለፎቶ ኮፒ እና ለልዩ ልዩ ወጪዎች ለፎቶ ግራፍ ብር 850(ስምንት
መቶ ሀምሣ ብር)
2.5 ለአፈ/ከሣሽ ለምስክሮች የተከፈለ አበል 400.00
2.6 በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ለማንዴላ ባጃጅ ጥገና ጋራዥ ምርመራ ባለሙያ የተከፈለ 500.00 (አምስት መቶ ብር)
ብቻ በድምሩ ወጪ ኪሳራ ያወጣው ብር 10,455 (አሥር ሺህ አራት መቶ ሀምሣ አምስት ብር)
እንዲከፍል እንዲወሰንልኝ እጠይቃለሁ፡፡
የቀረበው ክስ በእውነት የቀረበ ነው፡፡
የመ/ቁጥር 24948
መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም

ለሀዋሣ ከተማ የመጀ/ደ/ፍ/ቤት


ሀዋሣ ፣

የአፈ/ከሣሽ፡- አቶ በረከት ፍቃዱ ሕጋዊ ወኪል አቶ አማኑኤል ባታሞ


አድራሻ፡- ሀዋሣ ከተማ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፍላደልፊያ ቀበሌ
የአፈ/ተከሳሽ፡- የሀዋሣ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
አድራሻ፡- ሀዋሣ ባህል አዳራሽ ክ/ከተማ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 223 መሠረት የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር
1. የሰነድ ማስረጃ
1. ለዳኝነት የተከፈለ ደረሰኝ 1 ገፅ ኮፒ ፡፡
2. የጥብቅና አገልግሎት የተከፈለ 3 ገፅ ኮፒ ፡፡
3. ለጽሕፈት እና ለኮፒ ልዩ ልዩ ወጪዎች የተከፈለ 10 ገፅ ኮፒ ፡፡
4. ለምስክሮች የተከፈለ እና ለባጃጅ ምርመራ ሥራ እና ለፎቶ ግራፍ የተከፈለው በትዕዛዝ
የሚቀርብ፡፡
5. የዚሁ ፍ/ቤት ውሳኔ የወጪ ኪሣራ መብት የተጠበቀልኝ 11 ገፅ ፎቶ ኮፒ

2. የሰው ማስረጃ
ምስክሮች ለባጃጅ ለምስክር የተከፈለ እና ለፎቶ ኮፒ ስለመክፈሉ የሚያስረዳ
1. አቶ መስፍን ባትሮ አድራሻ፡- ሀዋሣ ታቦር ክ/ከተማ
2. አቶ አማኑኤል ባታሞ አድራሻ፡- ሀዋሣ ታቦር ክ/ከተማ
3. አቶ አማኑኤል ገ/ወልድ አድራሻ ሀዋሣ ታቦር ክ/ከተማ

ጭብጡ ካልተለወጠ በቀር ማስረጃዬን አበቃሁ፡፡


ቀን 06/07/2005 ዓ.ም

ለሀዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት


ሀዋሣ ፣

አመልካቾች፡- 1. ሐጢያ ዲጌሳ


2. መክብብ ማርቆስ
አድራሻ፡- መናኸሪያ ክ/ከተማ ፒያሣ ቀበሌ
ተጠሪ ፡- ሽመልስ ማርቆስ
አድራሻ ፡- ሐይቅ ዳር ክ/ከተማ ጉዱማሌ ቀበሌ
ሀ/ አርዕስት፡- የውርስ ንብረት ተጣርቶ ክፍፍል እንዲደረግ ለማስወሰን የቀረበ
ለ/ ፍ/ቤቱ ተቀብሎ ለመወሰን ሥልጣን አለው፡፡
ሐ/ ለተጠሪ የሚላክለትን መጥሪያ እንደርሳለን፡፡
ሀ. የአቤቱታችን ዝርዝር
የ 1 ኛ አመልካች እህትና የ 2 ኛ አመልካች የሴት አያቴ የወ/ሮ ቀባዲ ዲገሳ እህት ወ/ሮ ብርቄ ዲገሳ
ባደረባት ሕመም በሕክምና ስትረዳ ቆይታ በ 24/06/2003 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታ የቀብር ሥነ
ሥርዓት በ 25/06/2003 ዓ.ም በሀዋሣ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መፈፀሙንና
አመልካቾችም በፍ/ህግ/ቁጥር 843 እና 844(2) መሰረት የሟች ወ/ሮ ብርቄ ዲጌሳ ሁለተኛ ደረጃ
ወራሽነታችንን በፍርድ አስወስነን ማስረጃ ይዘናል ፡፡ ስለዚህ ፡-
ለ. የምንጠይቀው ዳኝነት
በሟች ወ/ሮ ብርቄ ዲገሳ ስም በሀዋሣ ከተማ በመናኀሪያ ክ/ከተማ በፒያሣ ቀበሌ በ 396 ካሬ ሜትር
የሰፈረ ባለ 5 ክፍል ዋናው ቤት ከ 10 ሰርቪሶች ጋር በተጠሪ እጅ ስለሚገኝ አጣሪ ተሹሞ ተጣርቶ
የየድርሻችንን እንድንከፋፈል እንዲወሰን እናመለክታለን፡፡
ያቀረብነው እውነት መሆኑን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሰረት እናረጋግጣለን፡፡

አመልካቾች 1. ሐጢያ ዲጌሳ ------------


2. መክብብ ማርቆስ ------------
ቀን 06/07/2005 ዓ.ም

ለሀዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት


ሀዋሣ ፣

አመልካቾች፡- 1. ሐጢያ ዲጌሳ


2. መክብብ ማርቆስ
አድራሻ፡- መናኸሪያ ክ/ከተማ ፒያሣ ቀበሌ
ተጠሪ ፡- ሽመልስ ማርቆስ
አድራሻ ፡- ሐይቅ ዳር ክ/ከተማ ጉዱማሌ ቀበሌ
አመልካቾች ላቀረብነው አቤቱታ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 መሰረት የምናቀርበው ማስረጃ ዝርዝር መግለጫ
ሀ. የሰነድ ማስረጃ
1. በ 18/06/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት የተሰጠ የሁለተኛ ደረጃ ወራሽነት ማስረጃ 3 ገፅ
ከነመሸኛው ዋናው በእጃችን ይገኛል፡፡
ያቀረብነው እውነት መሆኑን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሰረት እናረጋግጣለን፡፡

አመልካቾች
1. ሐጢያ ዲጌሳ -----------
2. መክብብ ማርቆስ ------------
ቀን 10/07/2005 ዓ.ም

ለሀዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት


ታቦር ክ/ከተማ ምድብ ችሎት
ሀዋሣ ፣

ከሣሽ ፡- አቶ ለገሠ ቡቻቻ


ተከሳሽ፡- አቶ ብርሃኑ ፉቄ
በፍ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁጥር 234 መሠረት የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር
የሰነድ ማስረጃ
1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአቢሲኒያ ባንክ ከዕዳ የተረፈውን ብር 35.000 (ሰላሳ አምስት ሺህ) ለአሁኑ
ተከሳሽ እንዳይሰጠኝ እኔ ለአቶ ለገሠ ቡቻቻ የዋስትና ዕዳ እቀበላለሁ ብሎ ቃለ መሀላ አቅርቦ
ያሳገደበት ገጽ 1 ፎቶ ኮፒ ዋናው በሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሚገኝ፡፡
2. የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለአብሲኒያ ባንክ ከዕዳው የተረፈ ቀሪ ገንዘብ ለእኔ እንዳይሰጥ ታግዶ
እንዲቆይ ያደረገው ትዕዛዝ ፎቶ ኮፒ 1 ገፅ ዋናው ሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የሚገኝ ፡፡
የሰው ማስረጃ
1. ወ/ሮ አልማዝ ቀቀቦ
2. ወ/ሪት አይናለም ብርሃኑ
3. ተማሪ ቢኒያም ብርሃኑ ናቸው፡፡
ቀን -------------------------------
በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ለሃይማኖችና እምነት ዳይረክቶሬት
አዲስ አበባ ፣

ጉዳዩ፡- በአድራሻ ለኢት/ቃለ ብርሃን ቤተክርስቲያን ሀዋሣ በግልባጭ ለተለያዩ የክልሉ ሴክተር መ /ቤትና ለእኔ
ጭምር ተፅፎ በደረሰኝ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰረት ተገቢውን የማስተካከያ እርምት ለማድረግ ከአቅም
በላይ የሆነ ችግር የገጠመኝ መሆኑን ስለማሳወቅ
በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የሃይማኖት ድርጅቶችና ማሕበራት ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ
ሲንቀሳቀስ በቆየው የኢትዮጵያ ቃለ ብርሃን ሀዋሣ ሥር በርካታ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ተመስርተው ሕዝቡ
ከእግዚአብሔር አምላኩ ጋር በፀሎት በመገናኘት ለሀገር ሰላም፣ ለአገር መሪዎች ለእራሳቸውና
ለቤተሰቦቻቸው ብሎም ለአለም ሰላም ጭምር ሌት ተቀን በፍጹም መፈቀዳድና በሠላም በፍቅር ላይ
በመመስረት ሲያመልክና ሲፀልይ በቆየው ማሕበረሰብ ውስጥ ከሕዝብ ይልቅ ለእራሳቸው ጥቅምና ፍላጎት
ያደሩ ጥቂት የቤተክርስቲያንቱ አመራሮች ክርስቶስ ኢየሱስ ከዘር ፣ከነገድ፣ ከቋንቋ ሳይለይ በደሙ ዋዥቶ
አንድ ያደረገውን ሕዝብ በጎሳ በመለያየት ከፍተኛ ሁከትና ችግር መፍጠራቸውን ጽ/ቤትዎ አረጋግጦ 1 ኛ.
ለአቶ ጢሞቴዎስ በራሳ 2 ኛ ለአቶ ገዛኸኝ ግዛቸው 3 ኛ. ለአሁኑ አመልካች መንገሻ ጤካሞ ሕዝቡ ተረጋግቶና
በሰላም የመኖር ሂደቱን ከማወክ ተቆጥባችሁ በውላችሁ መሰረት ፈፅማችሁ እንድትቀርቡ ይህ ባይሆንና ጉዳዩ
አይነቱን ለውጦ ወደ አለአስፈላጊ ግጭት ተቀይሮ ዋጋ የሚያስከፍል ሂደት ቢከሰት የወንጀልም ሆነ
የፍትሐብሔር ሃላፊነት ጭምር እንዳለብንና ከተጠያቂነት ነፃ እንደማንሆን ተገልፆ ለክልሉ ሴክተር መ/ቤቶች
ሁሉ በግልባጭ አውቀው ክትትል እንዲያደርጉ ጭምር በተገለፀው መሰረት ፡-
ሀ. የኢት/ቃል ብርሃን ሀዋሣ ቤተክርስቲያን ውስጥ የስራ አመራር የቦርድ አባል ሆነው የሚሰሩት አቶ መኮንን ቢዶ
እስከ ጽ/ቤትዎ ድረስ በአካል በመቅረብና በመገኘት እራሱን የቤተክርስቲያን ሥራ አስኪያጅ አድርጎ የሾመው
አቶ ገዛኸኝ ግዛቸው ችግር እየፈጠረ ከአጥቢያዎችና ከማሕበሩ ግንኙነት እንዳይኖረን እያደረገ የሚገኝ ነው
በማለት ቢገልፅም ከአዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ የእነ መንገሻ ጤካሞ ቡድን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እስካሁን
እየተከሰተ ለሚገኘው ችግር ጥፋተኞች እኛ ነን በማለት በደብዳቤ ይቅርታ ጠይቁን በማለት ሰላም ለማውረድ
ፈቃደኛ አለመሆኑን፣
ለ. የኢት/ቃል ብርሃን ሀዋሣ ጽ/ቤት ቤተክርስቲያን አባልና ሰብሳቢ የሆነው አቶ ጢሞቴዎስ በራሳን በደረሰን ትዕዛዝ
መሰረት ከማሕበራችን የጎደለውን ወደ ጠቅላላ ጉባዔ ጨምረን ውሉን ፈፅመን ሪፖርት እንዳደርግ ብዬ
በተደጋጋሚ ባናግረውም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶዋል ፡፡

በተጨማሪም ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖቶችና እምነት ዳይረክቶሬት ከተሰጠው ትዕዛዝ


ውጪ በመሆን የሲዳማ ክልል ቦርታ ሲና ኢላላ ቃል ብርሃን አጥቢያ ቤተክርስቲን ምዕመን ፈቃድና
ፍላጎት ውጪ በሀይል በፖሊስ አስገድደው ምርጫ በማሳደረግ ለዘመናት በእግዚአብሔር ፊት በመፀለይ
ተከባብሮና በእግ/ር ፍቅር ተማምቶ በሚኖረው ሕበረተሰብ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የጎሳ ግጭት ተፈጥሮ
የሚያባራ የደም መፋሰስ እንዲኖር አቶ ገዛኸኝ ግዛቸው እና አቶ ጢሞቴዎ በራሳ በከፍተኛ ሁኔታ
እየተንቀሳቀሱ ስለሆነና በትዕዛዙ መሰረት ውሉን ለመፈፀም ከአቅሜ በላይ ስለሆነ ይህን ሪፖርት
ለማቅረብ የተገደድኩ ሲሆን ከላይ በዝርዝር የጠቀስኩት ችግር ተከስቶ ሕዝቡ ወደአልተፈለገ የደም
መፋሰስ ውስጥ እንዳይገባ ጽ/ቤትዎ በጉዳዩ ጣልቃ በመግባት የማስተካከያና የእርምት እርምጃ ጭምር
ቢወሰድ መልካምና የተሻለ ነው በማለት የማጠቃለያ ሀሳቤን በአክበሮት እገልፃለሁ፡፡

አመልካች

መንገሻ ጤካሞ
ቀን ---------/2005 ዓ.ም
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት
አዲስ አበባ ፣
አመልካቾች ፡- 1 ኛ. ወ/ሮ ገነት ጋዜ
2 ኛ. ወ/ሪት እቴነሽ ጋዜ
3 ኛ. ›› ስንታየሁ ጋዜ
4 ኛ. ›› ገበያነሽ ጋዜ
5 ኛ. አቶ ደሣለኝ ጋዜ
6 ኛ. ወ/ሪት ሲናሬ ጋዜ
7 ኛ. ›› ብርቱካን ጋዜ
8 ኛ. አቶ ደረጀ ጋዜ
አድራሻችን፡- ደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ኬላ 01 ቀበሌ
ተጠሪ፡- ወ/ሮ እታለማሁ ጥላሁን
አድራሻ ፡- ደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ኬላ 01 ቀበሌ
- የስር የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር
- የሥር የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር
- የሥር የደቡብ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መ/ቁጥር 57996
በአዋጅ ቁጥር 25/1988 መሠረት ለፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት የቀረበ አቤቱታ ነው
ሀ/ መግቢያ
 የሰበር አቤቱታው የቀረበበትን የመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የደቡብ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ነው፡፡
 ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 57996 በቀን 14/06/2005 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
 ከፍ/ቤቱ ለተጠሪ የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በአድራሻዋ በኩል ለማድረስ እንችላለን፡፡
 የሥር ፍ/ቤቶች መዝገብ ትክክለኛ የውሳኔ ቅጂ -- ገፅ ተያይዞ ቀርቧል፡፡
ለ/ ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን በወንዶ ገነት ወረዳ አባዬ ቀበሌ
ገ/ማሕበር ውስጥ ልዩ ስሙ ቦርታ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ በስተሰሜን ለሙዴ ካለቃ ፣በስተደቡብ ለአቶ
መንግሥቱ በደሌ በስተምስራቅ ለዋርቆ ዋርሳሞ በስተምዕራብ ለሰንበቶ ቡኩኬ በግምት 2000 ካ.ሜ ላይ የሰፈረ
የጫት አታክልት ያለበትን የእርሻ ማሳ ሟች ወላጅ አባታችን ወላጅ እናታችን ከሆነችው ደራሮ ጎባሮ ጋር በርካታ
ዓመታት ይዘው በመጠቀም ላይ ሳለ ወላጅ አባታችን ባደረበት ህመም በ 1985 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት
ከተለየበትም ጊዜ ጀምሮ ክፍፍል ሳይደረግ በታላቅ ወንድማችን ጋሼ ጋዜ ስም የመንግስት ግብር በመገበር በጋራ

ይዘን እየተጠቀምን የቆየነው የጋራ የውርስ ሃብታችንን የአሁኗ ተጠሪ አባታችን በሞት ከተለየበት 19 ዓመት
ቆይታ በኋላ 2 ኛው ሚስቱ ስለሆንኩ ይገባኛል ስትል ያነሳችው ጥያቄ አግባብ አለመሆኑንና የሚገባትን እንኳን
ቢሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1845 መሰረት በ 10 ዓመት ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ ስለሆነ በይርጋ ቀሪ መሆኑን በመጥቀስ
በመጀመሪያ ጉዳዩን ተቀብሎ በተመለከተው የወንዶገነት ወ/ፍ/ቤት አጠናክረን ባቀረብነው አቤቱታና ክርክር
ታይቶ የተሰጠ ፍትሃዊ ውሳኔን በይግባኝ ተቀብሎ የተመለከተው የሲ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤትም ውሳኔውን በማፅናት
የሰጠውን ውሳኔ በይግባኝ የተመለከተው የደቡብ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሁለቱንም ፍ/ቤቶች ውሳኔ
በመሻር ከወላጅ አባታችን ሞት በፊትም ይሁን በኋላ በመያዝ በታላቅ ወንድማችን ጋሼ ጋዜ ስም የመንግሥት
ግብር በመገበር የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ጭምር አስወጥተን ስንጠቀም የቆየነውን ያለአግባብ ከእጃችን
ተነጥቆ ተጠሪ ጠቅልላ በመያዝ እንድትጠቀም የተሰጠውን አሳዛኝ ፍርድ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት
በመሆኑ ለማሳረም የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡
ለ) በይግባኝ ሰሚው የፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ
ነጥብ በአጭሩ
1. ተጠሪ ባለቤቴ እያለች የምትጠራው ሟች ወላጅ አባታችን ጋዜ ሐጦ በሞት ከተለየበት 1985 ዓ.ም ጀምሮ
ክርክር ያስነሳውን በጋራ እየተጠቀምን የቆየን ከመሆኑም በተጨማሪ ተጠሪ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ተቀብሎ
በተመለከተበት ወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት አቤቱታ ክስ ያቀረበችበት ጊዜ ሲሰላ ድፍን 19 ዓመት ሲሆን በዚህ ዓመታት
ሁሉ ይዞታውን ይዘን ስንጠቀም ያልቀረበን ጉዳይ በ 19 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ክስ ለማቅረብ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር
1845 መሠረት በአጠቃላይ የይርጋ ሕግ የማይፈቀድና ቀሪ ከመሆኑም በተጨማሪ በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት በቅፅ 6 ከገፅ 239 – 248 ላይ በአመልካች ተገኝ ይማም እና በተጠሪዎች እነ ካሣሁን ደሣለኝ መካከል
የተሰጠውን ውሳኔ ለማጣራት የተደረገ አንዳች ጥረት ሳይኖር ወላጅ እናታችንን ጨምሮ 10 ቤተሰብ ለበርካታ
ዓመታት ይዘን ስንጠቀም ያቆየነውን ለአንድ ዓመት እንኳን በመያዝ በስሟ የመንግስት ግብር ላልገበረችና
አያይዛም ያቀረበችው ሰነድ በሌለበት ተሽሮ የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ የደቡብ
ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ተሸሮ የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤትና የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት ውሳኔዎች ፀንቶ
እንዲወሰንልን፣
2. በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1677 (1) መሠረት ግዴታው ከውሉ የተገኘ ባይሆንም በፍትሐብሔር ሕጉ አራተኛው መጽሐፍ
አንቀፅ 12 ሥር የተመለከቱት ስለ ውሎች በጠቅላላው የተቀመጡት ድንጋጌዎች በግዴታው ላይ ተፈፃሚነት
ያላቸው ከመሆናቸውም በተጨማሪ ከላይ በተጠቀሰው አንቀፅ ሥር ከተመለከቱት ደንቦች የተለዩ ድንጋጌዎች
በሕግ ተመልክቶ ከተገኘ በተለይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች አግባብነት እንደሚኖራቸው በተጠቀሰው በፍ/ሕግ
ቁጥር 1672(2) እና

በ 1845 መሠረት በ 10 ዓመት ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ አለመሆኑ ተጣርቶ የተሰጠ ፍትሐዊ ውሳኔ ስለመሆኑ ተጠሪ
በሥር የደቡብ/ክ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበችው አቤቱታ የሚያስረዳ ነው፡፡ በተቃራኒው መንገድ 19
ዓመት ሙሉ ይዛ እንደቆየችና ከ 18 ዓመት ቆይታ በኋላ አመልካቾች የውርስ ጥያቄ እንዳነሳን ተደርጎ ባልተጠየቀ
ዳኝነት የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ የተሰጠው ፍርድ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተሽሮ እንዲወሰንልን ፣
3. ተጠሪ እንደ አባባሏ የሟች አባታችን ሚስት ከሆነች በመካከላቸው ነበር የተባለው ጋብቻ ደግሞ የፈረሰው ሟች
አባታችን በሞት በተለየበት በ 1985 ዓ.ም ነው ማለት ነው በፍትሐብሔር ሕጉ ጋብቻ ሲፈርስ በሁለቱም
ተጋቢዎች መካከል ያለው ንብረት ሕጉ በሚያዘው መሠረት መከፋፈል እንዳለበትና በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 684
መሠረት ከተጋቢዎቹ እያንዳንዱ የግል ሀብቱ መሆኑን በማስረዳት ድርሻውን በዓይነት መውሰድ እንደምችል
ተደንግጓል፡፡
ይህ ማለት ደግሞ በተፈለገው ጊዜ ሁሉ ተነስቶ የክፍፍል ጥያቄ ማንሳት እንደማይቻልና በይርጋ ሕግ
አይገዛም ማለት አለመሆኑን እንዲሁም በሞትም ይሁን በሁኔታዎች የተለዩ ተጋቢዎች ንብረት ሣይከፋፈል
ረዥም ጊዜ መቆየት እንደማይችሉና በቤተሰብ ሕግ ግልፅ ድንጋጌ ሳይኖር ሲቀር በውል ሕግ መርሆች ወይም
ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ማድረግ የውል ሕግ አንቀፅ 1677 ም የሚፈቅድ ነው፡፡
ስለሆነም የባልና ሚስት የንብረት ክርክር የተለየ የይርጋ ጊዜ ስለሌለው በዚህ ድንጋጌ መሰረት በውል ሕግ የይርጋ
ድንጋጌዎች ይገዛል ማለት ነው፡፡
ይህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪ በስር በደቡብ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታዋ ላይ እንደገለፀችው ሟች
አባታችን ከዚህ ዓለም በሞት የተየው በ 1985 ዓ.ም ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ሆኖ ሳለ ተጠሪ ክሷን በሥር ወንዶ
ገነት ወ/ፍ/ቤት ያቀረበችው በ 2004 ዓ.ም ከ 19 ዓመት ቆይታ በኋላ በመሆኑ በአጠቃላይ በይርጋ ሕግ
በፍ/ህግ/አንቀፅ 1845 መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ከመሆኑም በተጨማሪ
በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 4 ከገፅ 80 – 83 ላይ በአመልካች ወ/ሮ ድንቄ ተድላ እና
በመ/ሰጪዎች እና አባተ ጫነ 2 ሰዎች መካከል የሕግ ትርጉም የተሰጠበትን ጭምር በመግለጽ ያደረግነው ክርክር
ተቀባይነት በማሳጣት ተሽሮ የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው፡፡
በአጠቃላይ ክርክር ያስነሳው ይዞታ ከአባታችን ሞት በኋላ በጋራ ይዘን እየተጠቀምን መቆየታችንን በሰነድም
ሆነ በሰው ማስረጃ ተረጋግጦ የተሰጠውን ፍትሃዊ ውሳኔ መሻሩ አግባብ ባለመሆኑ በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን
ወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት የመ/ቁጥር 1194 የሆነው መዝገብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 145 መሰረት በትዕዛዝ ቀርቦ ታይቶና
ተጣርቶ የስር የደቡብ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሮ
የስር የሲ/ዞን /ከፍ/ፍ/ቤትና የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቶ እንዲወሰንልን በአክብሮት እናመለክታለን፡፡
ቀን ------------2005 ዓ.ም
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት
አዲስ አበባ ፣
አመልካች፡- ሙላቱ ታጳቶ
አድራሻ ፡- ወ/ገነት ወረዳ ወተራና ቀጨማ ቀበሌ
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ብዙነሽ አሩሳ
አድራሻ ፡- ወ/ገነት ወረዳ ወተራና ቀጨማ ቀበሌ
- የሥር የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 1408
- ›› የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 27047
- የደ/ክልል/ጠ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 58345
- የደ/ክ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መ/ቁጥር 58762
በአዋጅ ቁጥር 25/1998 መሠረት የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው
 የሰበር አቤቱታው የቀረበበትን የመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የደ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ነው፡፡
 ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 58762 በቀን 21/06/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
 ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በተጠሪ አድራሻ በኩል ለማድረስ እችላለሁ፡፡
 የሥር ፍ/ቤቶች የውሳኔ መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ 12 ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ) ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው ከዛሬ 45 ዓመታት በፊት ለመንግሥት የሚገባውን ህጋዊ
ግብር በስሜ በመገበር ይዤ እያሳረስኩ ከሚገኘው የእርሻ ውጤት ቤተሰቤን ሳስተዳድር የቆየሁበትን ብቸኛ
የእርሻ ይዞታዬን ምንነቱን በውል በማላውቀው ጉዳይ የአሁኗ ተጠሪ ለረዥም ጊዜ እኩል አሳርሳለሁ በማለት
ይዞታውን በሃይል ይዞብኛል ስትል ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ተቀብሎ በተመለከተው የወተራና ቀጨማ ቀበሌ
የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ካቀረበች በኋላ መልሳ ለወንዶ ገነት ወ/ፍ/ቤት በ 1/01/2004 ዓ.ም በጉልበት
ተያዘብኝ ስትል ሁከት እንዲወገድላት የቀረበውን አቤቱታ አግባብነት ለማጣራት ያመች ዘንድ ለመሬት
አጠቃቀም ኮሚቴ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ እኩል እሰራለሁ በማለት ይዞት ቆየ የተባለበትንና ፍ/ቤት በቀረበው
አቤቱታ ደግሞ በ 2004 ዓ.ም በሐይል ተያዘብኝ ተብሎ የተገለጹ ሁለት አባባሎችን ለትክክለኛው ፍትህ
አሰጣጥ በሚያመች መልኩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 132 መሠረት ይዞታው አለበት ስፍራ ድረስ በመሔድ
ለማጣራት የተደረገ ጥረት ሳይኖር የተሰጠውን ውሳኔ በይግባኝ የተመለከተው የደ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በሕግ አግባብ በጥልቀት ሳይመለከተው ሽሮ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ፍርዱን
ለማስለወጥ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው፡፡
ሐ) በደ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተፈፀመና እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥብ
በአጭሩ
1. በወ/ገነት ወረዳ ወተራና ቀጨማ ቀበሌ የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ይዞታውን ረዥም ጊዜ
በመያዝ እኩል እየሰራሁ እንደቆየሁ በተጠሪ እየተገለፀ በሌላ በኩል ደግሞ በሐይል ተያዘብኝ ተብሎ
ሁከት እንዲወገድ የቀረበው ከቅን ልቦና ውጪ ፍ/ቤቱን ጭምር በማሳሳት የተዛባ ፍርድ አሰጥቶ
ባለመብት ለመሆን የቀረበ የሐሰት አቤቱታ ከመሆኑም በተጨማሪ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1149 (2)
መሰረት በሀይል የተያዘውን ይዞታ ለማስለቀቅ በ 2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ መቅረብ እንዳለበት
በግልፅ የተመለከተና በዚሁ ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ከተደነገገው ድንጋጌ ውጪ
የተሰጠ አሳዛኝ ፍርድ ከመሆኑም በተጨማሪ ተጠሪ ባለችበት ቀበሌ የመሬት አጠቃቀም ኮሚቴ
ያቀረበችውን አቤቱታና ፍ/ቤት ደግሞ ቀይራ ያቀረበችውን አቤቱታ አግባብነት ለማጣራት የተደረገ
አንዳች ጥረት ሳይኖር የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ውሳኔ ተሽሮ የተሰጠው ፍርድ አግባብነት እንኳን
ለማጣራት የተደረገ አንዳች ጥረት ሳይኖር የጠ/ፍ/ቤትን ውሳኔ ማፅናቱ አግባብ ባለመሆኑ
እንዲታረምልኝ ፡፡
2. ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ተቀብሎ በተመለከተው የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት አቅርቤ ያሰመኋቸው
የመከላከያ ማስረጃዎቼ ቃል በትክክል ሳይመዘገብ ታልፎ የተዛባና ተጠሪን ሊረዳት በሚችል መልኩ
ሆን ተብሎ በማስረጆቼ ያልተነገረን ቃል በማስፈር የተሰጠ አሳዛኝ ፍርድ መሆኑን በመግለፅ
ለትክክለኛው ፍትህ አሰጣጥ ያመች ዘንድ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አስቀርቦ ምስክርነታቸውን
እንዲያዳምጥ እንዲታዘዝልኝ ያቀረብኩትን የፍትህ ልመና ተቀባይነት በማሳጣት የተሰጠው ፍርድ
መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ከመሆኑም በተጨማሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 132 መሰረት
ይዞታው ያለበት ድረስ በመሔድ ተጣርቶ እንዲወሰንልኝ ያቀረብኩትን አቤቱታና ክርክር ተቀባይነት
በማሳጣት የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር መወሰኑ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሕግ
አግባብ ተጣርቶ እንዲሻርልኝ ፡፡
3. ከ 45 ዓመታት በላይ በመያዝ አርሼ ከሚገኘው የእርሻ ውጤት ልጆቼን የማስተዳድርበትን
ለማይገባው ሰው ከእጄ ተነጥቆ መስጠቱ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ በአገራችን ባለው የሕጎች
ሁሉ የበላይ በሆነው ሕገመንግስትም ሆነ በገጠር የመሬት አዋጅ ቁጥር 110/99 ሥር የተጠበቀውን
የዜጎችን ከይዞታቸው ያለመፈናቀል መብት ጭምር የጣሰ አሳዛኝ ፍርድ በመሆኑ በሕግ አግባብ
በጥልቀት ተመርምሮና ተጣርቶ የደ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) መሠረት በመሻር የሲ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቶ እንዲወሰንልኝ
ስል በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡
አመልካች
ሙላቱ ታጳቶ
ቀን 26/06/2005 ዓ.ም
ለሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ሀዋሣ
ይግባኝ፡- ሀቢብ መሐመድ
መ/ሰጪ ፡- ከድር ሺፋ
አመልካች በ 29/05/2005 ዓ.ም ፅፎ ያቀረበብኝን አቤቱታ ተመልክቼ የበኩሌን መልስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር
339 (3) መሠረት በመዘርዘር እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡
የይግባኝ ባይ አቤቱታ በአጭሩ
ከብር 500 በላይ የሚቀርብ ክስ በውል የተመሠረተ መሆን ሲገባው ከሕጉ ደንጋጌና ትርጉም ውጪ በሐሰት
በቀረበብኝ ክስ የሰባት ኩንታል ፉርኖ ዱቄት ብር 6230 እንድከፍል በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ተሽሮ
የወጪ ኪሣራ መብቴ ተጠብቆ ይወሰንልኝ የሚል ነው፡፡
1. ከይግባኝ ባይ ጋር ካለን የእስልምና እምነት የተነሣ በፍጹም መተማመን በእምነት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ
የሆነ የንግድ ልውውጥ ስናደርግ ከመቆየታችንም በተጨማሪ ለዚሁም አስረጂ ልሆን የምችለው ሽጦ በእምነት
እንዲሰጠኝ ከሠጠሁት 56 ኩንታል ፉርኖ ዱቄት ውስጥ 49 ኩንታል ፉርኖ ዱቄት ያለ ውል /ሰነድ/ በእምነት
ወስዶ ሽጦ እንደሰጠኝ እስካመነ ድረስ ቀደም ሲል በመካከላችን ስንገበያይበት ያልነበረውን ጉዳይ(ውል)
እንደሚያስፈልግ በመግለፅ የ 7 ኩንታል ዱቄት በውል ባልተመሠረተ እንድከፍል የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት
የለውም ሲል ያቀረበው የሕግ ድጋፍ የሌለው ነው፡፡ ምክንያቱም የ 49 ኩንታል ዱቄት በእምነት ወስዶ
መክፈሉን እስካመነ ድረስ በመካከላችን ጠንካራ የሆነ መተማመን መኖሩን የሚያመለከክት ነው፡፡ በመሆኑም
አቤቱታ በሕግ ላይ ተመስርቶ ያልቀረበ ተቀባይነትም የሌለው ነው፡፡
2. 56 ኩንታል ፉርኖ ዱቄት አቶ አህመድ መጋዘን ካስቀመጥኩበት በአህያ ጋሪ በመጫን ሱልጣን ተብሎ
ለሚጠራው የመ/ሰጪ ሠራተኛ የሆነው መረከቡን አረጋግጦ እንደደረሰው በስልክ የነገረኝ ከመሆኑም
በተጨማሪ የፉርኖ ዱቄቱ የተቀመጠበት መጋዘን ባለቤትና ጭነው ዱቄቱን ለመ/ሰጪ ሱቅ ድረስ ያመላለሱ
ሠራተኞችን ጭምር በማስቀረብ አረጋግጠው የምስክርነት ቃላቸውን በመስጠታቸው የተሰጠ ፍትሐዊ ውሳኔ
ከመሆኑም በተጨማሪ መ/ሰጪና ያቀረባቸው ማስረጃዎቹ በሰጡት ምስክርነት ደግሞ በመካከላችን በእምነት
የንግድ ልውውጥ ከመደረጉ ያለፈ ከቀድሞውኑ በውል ላይ የተመሠረተ የንግድ ልውውጥ መኖሩን
አላስረዱም፡፡
በዚሁ መሠረት መ/ሰጪ የፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 2472(3) በመጥቀስ ከብር 500 የኢትዮጵያ ብር በላይ በፅሁፍ
መደረግ ሲገባው ያለ ውል በቀረበ ክስ የተሰጠ ውሳኔ አግባብ አለመሆኑን መግለፁ የሕግ ድጋፍ የሌለው ነው
በአጠቃላይ የጠቀሰው ሕግ በብድር የተሰጠ ገንዘብ ከብር

500 በላይ በፅሁፍ መሆን እንዳለበት የተጠቀሰ እንጂ በእምነት በተደረገ የንግድ ልውውጥ ሥራ የተደነገገ
ባለመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡
በተጨማሪ በሥር ፍ/ቤት በማስረጃነት አስቀርቤ ያሰማኋቸው ምስክሮቼ ቃል እንደ መ/ሰጪ አባባል ሳይሆን
በትክክል አስረግጠው የሰጡት የምስክርነት ቃል ከመዝገቡ ስለሚገኝ ማረጋገጥ የሚቻል ይሆናል፡፡
ስለሆነም ከመ/ሰጪ ጋር ለበርካታ ዓመታት በነበረኝ የንግድ ሥራ ልውውጥ በሰነድ ወይም በውል ሳይሆን
በመተማመን ላይ በተመሠረተ ከፍተኛ እምነት የተነሣ በርካታ ኩንታል ፉርኖ ዱቄቶችን አምጥቼ በመስጠት
እየሸጠ ሲያስረክበኝ የቆየ ከመሆኑ በተጨማሪ ክርክር ባስነሳ ጉዳይም የሰጠሁትን 56 ኩንታል የፉርኖ ዱቄት
ያለውል በእምነት ከሰጠሁት ውስጥ 49 በማመን ለ 7 ኩንታል በውል ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ሳይኖረን
የቀረበ ክስ በሚል ያቀረበው መቃወሚያም ሆነ አቤቱታ የሕግ ድጋፍ የሌለው በመሆኑ ተቀባይነት በማሳጣት
ወጪ ኪሣራዬ ተጠብቆ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቶ እንዲወሰንልኝ በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡
አስተያየቴም በእውነት የቀረበ ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሰረት በቃለ መሀላ በማረጋገጥ
አቀርባለሁ፡፡
መ/ሰጪ ፡- ከድር ሺፋ
ቀን 20/6/2005 ዓ.ም
ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት
ሀዋሣ ፣
አመልካች ፡- ዳንኤል ሙሴ
አድራሻ፡- ሀዋሣ ከተማ ምስራቅ ክ/ከተማ
ተጠሪ፡- ሰብለወርቅ ከበደ
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቀበሌ 18
- የሥር የምስራቅ ምድብ ችሎት መ/ቁጥር 918
- የሀዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መ/ቁጥር 13396
በአዋጅ ቁጥር 43/94 መሠረ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው
- የሰበር አቤቱታው የቀረበበትን የመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የሀዋሣ ከተማ ከፍ/ፍ/ቤት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 13396 በቀን 03/05/05 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- ከፍ/ቤቱ ለተጠሪ የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በአድራሻው በኩል ለማድረስ እችላለሁ፡፡
- የሥር ፍ/ቤቶች መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ -- ገፅ ተያይዟል፡፡
ለ/ ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው ተጠሪ ከበደ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ በሚል በሚታወቀው
ድርጅቱ ባለኝ የቧንቧ ሙያዬ ለመሥራት ሚያዚያ 14 ቀን 2004 ዓ.ም የሎካ አባያ የመጠጥ ውሃ መስመር ዝርጋታ
በተለያዩ ኢንች ቧንቧዎች አጠቃላይ 4206 ሜ ቁመት ያለውን ቧንቧ በብር 17,000 (አስራ ሰባት ሺህ ብር)
የአገልግሎት ክፍያ ገንዘብ ተከፍሎኝ ለመሥራት ከተስማማነው ውስጥ ብር 13,000 ከፍሎኝ ቀሪ ገንዘብ ብር
4,000 ቀርቶኝ ሳለ ከተከሣሽ ጋር ባለን ቅርበት የተነሳ ተጨማሪ ውል ሳያስፈልግ ከሰኔ ወር 2004 ዓ.ም ጀምሮ
1 ኛ. ባለ ½ ኢንች ቧንቧ በሜትር 1509 የሰራሁ ሲሆን በገንዘብ ሲሰላ የ 1 ሜትር ብር 3 x 1509 = 4527 2 ኛ/ ባለ
2 ኢንች ባለ 2 ½ ኢንች ቧንቧ በሜትር 581 የሠራሁ ሲሆን በገንዘብ ሲሰላ የ 1 ሜ 5 ብር x 581 = 2,905 3 ኛ.
ባለ 3 ኢንች ቧንቧ በሜትር 182 የሰራሁ ሲሆን በገንዘብ ሲሰላ የ 1 ሜ 5 x 1824= 9120 አጠቃላይ ከውል ውጭ
የሰራሁት ብር 19,000 በውል ሳይከፈለኝ የቀረ ገንዘብ ብር 4,000 በድምሩ 23,000 (ሃያ ሶስት ሺህ ብር) በፍርድ
ለማስከፈል በሰነድና በሰው ማስረጃ አስደግፌ ያቀረብኩለትን አቤቱታ በመጀመሪያ ደረጃ ተቀብሎ የተመለከተው
የምስራቅ ምድብ ችሎት ተከሣሽ የቀረበበትን ክስ ሳይክድ ያመነ ከመሆኑም በተጨማሪ እንደክስ አቀራረቤ ከላይ
በዝርዝር የተጠቀሰውን በውልና ከውል ውጪ ስለመሥራቴ የተጠሪ የመ/ማስረጃዎች ጭምር ደግፈውኝ
በመመስከር አረጋግጠውልኝ ሳለ በውል የሠራሁትን ያለአንዳች ምክንያት ተቀባይነት በማሳጣት የተሰጠውን
አስገራሚ ፍርድ ለማረም የተደረገ አንዳች ጥረት ሳይኖር ፀንቶ የተሰጠውን ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት
ያለበት ስለሆነ ለማሳረም የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡

በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ


1. ተጠሪ የቀረበበትን ክስ ሳይክድ ገንዘብ እንዳለበት አምኖ ነገር ግን የተጋነነ ነው በማለት በመልሱም ሆነ
በክርክር ወቅት ከማቅረብ ውጪ የጠየቁት የዳኝነት ገንዘብ የተጋነነ ስለመሆኑ በሰነድም ሆነ በሰው
ማስረጃ ባላስተባበለበት የተሰጠው ፍርድ አሳዛኝና በሕግ ላይም ያለኝን ከፍተኛ እምነት ያዛባ
ከመሆኑም በተጨማሪ የተሰራው ስራ ጥራቱን የጠበቀ አለመሆኑን ከመግለፅ ያለፈ እንደውላችን
ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ሰርቼ ያላስረክብኩት ከሆነ በፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1772 መሰረት የሰጠኝ የፅሁፍ
ማስጠንቀቂያ የለም፡፡
በተጨማሪም በውላችን መሠረት ሥራው ተሰርቶ አልቆ ካልተረከበ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ምላሽ
ባያገኝ ከቀረ ደግሞ እንደውሉ እንዲፈፀም ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ከሶ ማስፈፀም ሲገባው በተገቢውና
በሕጋዊ መንገድ ያደረገው አንዳች ነገር ሳይኖር ላቀረብኩት ክስ እንደመከላከያነት ለመጠቀም በማሰብ
ያቀረበው አግባብነት የሌለው መሆኑን በመግለፅ ያደረኩትን ሕጋዊ ክርክር ተቀባይነት በማሳጣት የተሰጠው
ፍርድ አለመታረሙ አግባብ ባለመሆኑ እንዲታረምልኝ ፣
በአጠቃላይ ከበቂ በላይ በሰነድና ባቀረብኳቸው የሰው ማስረጃዎቼ አጠናክሬ ያደረኩትን ክርክር
ተቀባይነት በማሳጣት የተሰጠው ፍርድ ሳይታረም ማፅናቱ አግባብ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)
መሠረት የሥር የምስራቅ ምድብ ችሎት ውሳኔ ተሻሽሎ እንዲወሰንልኝ፡፡

አመልካች

ዳንኤል ሙሴ
ቀን 22/06/2005
ለወንዶ ገነት ወ/ፍ/ቤት
ጩኮ ፣
ከሣሽ፡- ወ/ሮ ገነት ጉራሮ
ተከሳሾች፡- 1. ንጉሴ ዳላቾ
2. ሀየሶ ሀንቃሞ
ከሣሽ 13/06/2005 ዓ.ም ፅፋ ያቀረበችውን አቤቱታ ተመልክተን የበኩላችንን የመከላከያ መልስ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 234 እና 244(2)(መ) መሠረት በመዘርዘር እንደምከተለው እናቀርባለን፡፡
1. በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበ መቃወሚያ
1.1 ክርክር ያስነሳው ጉዳይ (ይዞታ) ግንቦት 13/09/2005 ዓ.ም በተደረገ የእኩል አራሽነት የውል ስምምነት
ለተከታታይ 5 ዓመታት በአሁኗ ከሣሽና ባለቤቷ በፍጹም ፈቃደኝነትና ስምምነት ላይ የተመሠረተ ውል
ከሁለታችንም ወገን የቀረቡ የአይን እማኞች ባሉበት በመስማማት የአሁኗ ከሣሽ ከባለቤቷ ጋር በውል ሰጪነት
ፊርማ የሰጠችውን ውል በእራሷ ጊዜ ለማፍረስ በመፈለግ በውሉ ላይ እንዳልፈረመች በመግለፅ ያቀረበች
ከመሆኗም በተጨማሪ በፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1808 ላይ የተጠቀሰውን የውል ማፍረስ ጥያቄ የማያሟላና
በውላችን መሠረት የ 5 ዓመቱ ጊዜ ገደብ እስኪደርስ ድረስ ከሣሽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244(2) (መ)
መሠረት በጉዳዩ ውስጥ ገብታ ለመከራከር አይገባቸውም ተብሎ ወጪ ኪሣራችን ተጠብቆ መዝገቡ ተዘግቶ
ከክሱ እንድንሰናበት እንጠይቃለን፡፡
2. በአማራጭ ከተከሳሾች የተሰጠ መልስ
2.1 ክርክር ያስነሳው ይዞታ የሚገኝበት አራቱም አዋሳኞች ተጠቅሶ ከ 13/09/2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ
15/09/2009 ዓ.ም ድረስ ለ 5 ዓመት በከሣሽና ባለቤቷ በጎ ፈቃድና እውቅና የተደረገ መሆኑን በውሉ ላይ
የተጠቀሱና ከግራ ቀኙ የቀረቡ ማስረጃዎች ቀርበው የሚያስረዱ ከመሆኑም በተጨማሪ ለ 5 ዓመታት ወዳና
ፈቅዳ የገባችው(የሰጠችውን) ውል ከቅን ልቦና ውጪ በሆነ የሐሰት አቤቱታ አሰርዛ ለሌላ ሰው ለመስጠት
ካላት ፍላጎት የመነጨ ክስ ስለሆነ በማስረጃ ተረጋግጦ ክሱ በእውነት ላይ ተመርኩዞ ያልቀረበ ተቀባይነት
የሌለው ነው እንዲባልልን ፣
2.2 በፍ/ብ/ሕግ/ቁጥር 1808 (1) እና (2) ላይ ተመርኩዞ የሚቀርብ የውል ይፍረስልኝ ክስ(ጥያቄ) ከውል ፈቃድ
መስጠት ጉድለት ወይም ከተዋዋዮች ወገኖች በአንደኛው ችሎታ ማጣት ወይንም ከሕግ ውጪ የሆነ ነው
ወይም ለሕሊና ተቃራኒ ነው ወይም ለውል አፃፃፍ የተደነገገው ፎርም አልተጠበቀም ብሎ ከተዋዋዮቹ አንዱ
ወይም ማንኛውም ጥቅም ያለው ሰው ጥያቄ ከማቅረብ ያለፈ ወዶና ፈቅዶ የእራሱን አሻራ ፊርማ አሳርፎ
በመስማማት የተሰጠ ሕጋዊ ውል ሊፈርስ የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም፡፡

በተጨማሪ የ 5 ዓመት የውል ጊዜ ገደብ ሳያልቅ ከምሰራበት ማሳ በሐይል አስወጥታኝ ለ 3 ኛ ወገን


የኮንትራት ውል ለመስጠት በማሰብ ከቅን ልቦና ውጪ የቀረበብን ክስ የሕግ ድጋፍ የሌለው በመሆኑ ወጪ
ኪሣራችን ተጠብቆ መዝገቡ በፍርድ ተዘግቶ እንድንሰናበት እንጠይቃለን፡፡
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 234 (1) (ረ) መሰረት የቀረበ የተከሳሽ ከሳሽ አቤቱታ
ከሣሽና ባለቤቷ ጋር የእርሻ መሬት በእኩል ለመጠቀም ውል ተስማምተን በይዞታው ገብቼ ሰርቼ
ያለማሁትንና ለውጤት ያደረሰኩትን የጫት ተክል ምርት እንዳልጠቀምና ከይዞታው እንዳልገባ በመከላከላችን
በቀበሌ አመልክተን ጉዳዩ በድርድር ወይም በሕግ እልባት እስኪያገኝ በማለት ለማረጋጋት ሲባል ለጊዜው
በይዞታው ማንም እንዳይገባ የተደረገውን ክልከላ በመጣስ ግምቱ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ/ ልያወጣ
የምችል ጫት በመስበር እጅ ከፍንጅ ተይዞ በአባዬ ቀበሌ በኩል ተሽጦ ገንዘቡ በቀበሌ የሚገኝ ስለሆነ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145 መሰረት የተሸጠበት በትዕዛዝ እንዲቀርብ ተደርጎ ሊደርሰን የሚገባው ተሰልቶ
እንዲሰጠን እንዲወሰንልን እንጠይቃለን ፡፡
ከሣሽ ያለአንዳች ህጋዊ ምክንያት ወደ ክስ ውስጥ አስገብቶን ላልተፈለገ ወጪ የዳረገን በመሆኑ የወጪ
ኪሣራችንን የመጠየቅ መብታችን ተጠብቆ እንዲወሰንልን፣
አቤቱታችንም በእውነት የቀረበ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሰረት በቃለ መሀላ በማረጋገጥ
እናቀርባለን፡፡

መ/አቅራቢዎች
1.ሐየሶ ሀንቃሞ
2.ወርቁ ሌዳሞ
ቀን 22/06/2005

ለወንዶ ገነት ወ/ፍ/ቤት


ጩኮ ፣

ከሣሽ፡- ወ/ሮ ገነት ጉራሮ


ተከሳሾች፡- 1. ንጉሴ ዳላቾ
2. ሀየሶ ሀንቃሞ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 223 መሰረት የቀረበ የማስረጃ መግለጫ
የሰው ማስረጃ
1 ኛ. ጋትሶ አሩሳ
2 ኛኛ ወንድሙ ማጌ
3 ኛ. ሀርቃ ዋጭፎ
4 ኛ. ተመስገን ጌታቸው
5 ኛ. ዋርሳሞ ጥቃሞ ናቸው፡፡
የሰነድ ማስረጃ
በግንቦት 15/9/2004 የተደረገ ውል ስምምነት 2 ገፅ ተያይዟል፡፡

መ/አቅራቢዎች
1. ሐየሶ ሀንቃሞ
2. ወርቁ ሌዳሞ
ቀን 7/08/2005 ዓ.ም
ለወንዶገነት ወረዳ ፍ/ቤት
ጩኮ
ከሣሽ፡- በላይ በጤና
ተከሳሾች፡- 1. ኃይሉ ኦይቻ
2. በሪሶ ሎሊቱ
3. ማርሳ ኦይቻ
ከሣሽ በቀን 13/07/2005 ዓ.ም በተፃፈ አሻሽሎ ያቀረበብን የፍትሐብሔር ክስ ደርሶን ተመልክተን የበኩላችን
የመከላከያ መልስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 234፣209 እና 244 (2) (መ) መሰረት ተዘርዝሮ ከተከሳሾች የተሰጠ
መልስ
1. በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበ መቃወሚያ
1.1 ከሣሽ ያልሠራበትና ያልደከመበትን በሰው ላብና ድካም የተገኘውን ገንዘብ (ነዋይ) ለማግኘት ካለው ብርቱ
ፍላጎትና ምኞት የተነሳ ከቤተሰቡ ጋር የተጠቀመበትን በእራሱ ስሌት በማስላት እንዲከፈለው ያቀረበው የገንዘብ
መጠን ተገቢውን ዳኝነት ሳይከፈል የቀረበ የሐሰት ክስ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 209 (1) መሠረት
አቤቱታው ስነሥርዓትን ተከትሎ ያልቀረበ ነው ተብሎ በመሠረዝ መዝገቡ ተዘግቶ እንድንሰናበት እንጠይቃለን፡፡
1.2 ከሣሽ በወ/ገነት ወረዳ ዮዎ ቀበሌ ውስጥ በ 1 ቦታ ካለው የጫት እርሻ ይዞታው በዓመት 3 ጊዜ ሲሸጥ ቢያንስ ከብር
50.000 ሺህ በላይ የሚያስገኝ እንዲሁም ከ 20 በላይ የቀንድ ከብቶች ያሉትና በሀዋሣ ዙሪያ ወረዳ ሩከሳ ቀበሌ
ውስጥ ካለው ሰፊ የእርሻ ይዞታው በዓመት ከ 60 ኩንታል በላይ ገቢ የሚያገኝና በቂ አቅም እያለው ለመንግስት
የሚገባውን ገቢ ለማስቀረት በማሰብ ካለበት ዮዎ ቀበሌ የተሰጠው ማስረጃ አግባብነት የሌለው ከመሆኑም
በተጨማሪ ከቀበሌ የሚሰጥ የድህነት ማስረጃ ተረጋግጦ ሊሰጥ የሚገባው ከቀበሌ ማሕበራዊ ፍ/ቤት ከሣሽ ምንም
ገቢ የሌለው ነፃ ደሃ መሆኑ ሶስት የሰው ማስረጃ አስቀርቦ በማስመስከር ድህነቱ በቀበሌ ማሕበራዊ ፍ/ቤት
ተረጋግጦ ማስረጃ የሚሰጥ እንጂ በቀበሌ ሊ/ርም ይሁን በሲ/አ/ክያጅ ሊሰጥ የሚችልበት አግባብ የለም፡፡
ስለዚህ ከሣሽ የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል የተከፈተው ክስ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ የዳኝነት ገንዘብ
ባለመክፈሉ በእራሱ ስሌት በማስላት ከፍተኛ ገንዘብ ለማስከፈል ከሥነ ሥርዓት ውጪ የቀረበ ነው፡፡
በዚሁ መሠረት ከሣሽ በቂ አቅም ያለው በመሆኑና በሐሰትም ያቀረበው የድህነት ማስረጃ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 475 (1) መሠረት ተሰርዞ በንዑስ ቁጥር (2) መሰረት ተገቢውን ዳኝነት እንድከፍል
እንዲታዘዝልኝ፣
2. በአማራጭ ከተከሳሾች የተሰጠ የመከላከያ መልስ
2.1 ከሣሽ ለደረሰብኝ ጉዳት ታክሜ ብር 1366 አወጣሁ በማለት ለማስከፈል ክስ ከማቅረብ ያለፈ በህጋዊ ማስረጃ
ተደግፎ ያልቀረበ ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም በተጨማሪ ከተጠቀሰው ገንዘብ ውስጥ በጥቁር ውሃ ክሊኒክ
የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ በሚል ወረቀት ላይ ብር 265 ተብሎ የቀረበውም ቢሆን የክሊኒኩ ማህተም ያላረፈበት
ሲሆን መድሃኒት ገዛውበት ሲል አያይዞ ያቀረባቸው ሁለት ደረሰኞች ደግሞ መቼ በስንት ዓ.ም እንደተገዛ
የማይገልፅ ነው፡፡

በተጨማሪም ለደረሰብኝ ጉዳት ቅቤና ሰውነትን ሊገነቡ የሚችሉ የተለያዩ ነገሮችን ገዛው ሲል ያቀረበውም
ቢሆን በአንድ ዓይነት የእጅ ፅሁፍ የተፃፈ ታአማኝነት የጎደለው ነው፡፡እንዲሁም ከጥቁር ውሃ ክሊኒክ ተገኘ
የተባለውም ይሁን መድኃኒት ተገዛበት የተባለው የሐሰት ሰነድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 223 መሰረት ከክስ
ማመልከቻው ጋር ተያይዞ ያልቀረበ ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም በላይ ማስረጃውም ሲመዘን በሐሰት
ተቀነባብሮ በቀረበ ማስረጃ ተከሳሾችን ለማስከፈል ከማቅረብ ያለፈ ሚዛን የማይደፋ ተቀባይነትም የሌለው ነው፡፡
2.2 ከሣሽ በእራሱ ስሌት በመሰለው መልኩ በማስላት 1 ኛው ተከሣሽ ብር 70,000 (ሰባ ሺህ) 2 ኛው እና 3 ኛው
ተከሳሾች በወንጀል ነፃ ቢለቀቁም በሚል እያንዳንዳቸው ብር 35,000 x 2 = 70,000 = ሶስቱም ተከሣሾች
በድምሩ 140,000 (አንድ መቶ አርባ ሺህ ) ይከፈለኝ በማለት እራሱም እርግጠኛ ያልሆነበትን በትንሹ ሲል
ያቀረበብን ስሌት ሆን ተብሎ ከቅን ልቦና ውጪ በመሆን በየትኛውም ህጋዊ በሆነ የመንግስትም ይሁን የግል
ሆስፒታል ታክሞ የጉዳቱ መጠን በህክምና ቦርድ ተረጋግጦ ባልቀረበበትና ቀደም ሲልም በሐሰት ለማስወንጀል
በማሰብ በመርማሪ ከሣሽ ለማስከሰስ ሙከራ ስላደረገ ብቻ የአካል ጉዳት ካሣ ገንዘብ እንዲከፈለው ያቀረበው
በማስረጃ ያልተደገፈና በሕግ ላይ ተመርኩዞ ያልቀረበ ተቀባይነትም የሌለው ከመሆኑም በተጨማሪ ደረሰብኝ ሲል
የገለፀው የጉዳት መጠን በታወቀ ሆስፒታል በሕክምና ቦርድ የተረጋገጠበት ሰነድ ተያይዞ አለመቅረቡ ክሱ የሐሰት
ለመሆኑ አመልካች ነው፡፡
2.3 ለራፖር ፀሐፊ ብር 50 የተባለውም ለምን ጉዳይ መቼ እንደተፃፈ የማይገልፅና ማስረጃም የሌለው ከመሆኑም
በተጨማሪ በታወቀ የመንግስት ሆስፒታል የጉዳቱ መጠን በቦርድ ኮሚቴ ተረጋግጦ ባልቀረበ ሰነድ የህልና ጉዳት
እንዲከፈለው ያቀረበውም የሕግ ድጋፍ የሌለው ነው፡፡
2.4 በወንጀል ጉዳይ በመሠረትኩባቸው ክስ ለማስረጆች አበል ብር 120 የተከፈለና ከዩዎ ወደ ሀዋሳ በተለያየ ጊዜያት
ተመላለስኩ በማለት ብር 2000 ከፈልኩ ሲል ከመናኸሪያ ወያሎች ዘንድ ደረሰኝ ሰብስቦ በመፃፍ ያቀረበው
ታአማኝነት የሌለውና ምን ያህል በሰው ላብና ድካም ለመክበር ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት የሚያሳይ ከመሆኑም
በተጨማሪ ለእራሱ ጉዳይ በወደደው ጊዜ ለተመላለሰበት ከሣሾች ከፋይ ልሆኑ የሚችሉበት አግባብ የሌለ
ከመሆኑም በተጨማሪ ለየትኛውም ጉዳይ ቢሆን ይህን ያህል አመላልሶ ሊያስከፍል የሚችል ጉዳይም አልነበረም፡፡
በአጠቃላይ ከሣሽ ያቀረበብን የገንዘብ ክስ 140,000 በማስረጃ ያልተደገፈ ከመሆኑም በተጨማሪ የገንዘብ ካሣ
ለማቅረብ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2000 እና በተከታታይ ባሉ የሕግ ድንጋጌዎች መሠረት በሰነድ ማስረጃ ከማስረዳት
ያለፈ በሌላ ማስረዳት አይቻልም፡፡ በተጨማሪም ተያይዞ የቀረበውም ሰነድ በሕግ የማስረጃ ዝርዝር ሊቀርብ
በሚችልበት የሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት ተያይዞ ሳይቀርብ ሆን ተብሎ የሐሰት ክስ በማቅረብ መደበኛ ስራችንን
በመፍታት ላልተፈለገ ወጪ የዳረገን ስለሆነ የወጪ ኪሳራችንን የመጠየቅ መብታችን ተጠብቆ መዝገቡ ተዘግቶ
እንድንሰናበት እንጠይቃለን፡፡
በተጨማሪም የወንጀል ጉዳይ ተቀብሎ ክስ የመመስረት ሥልጣን ያለው በመንግስት የተወከለ መርማሪ ከሣሽ
/ዐቃቤ ሕግ) ብቻ ሆኖ ሳለ እንደፍትሐብሔር ጉዳይ ሁሉን እንደፈፀመ በማስመሰል የቀረበው ፍ/ቤቱን ጭምር
አሳስቶ የተዛባ ፍርድ ለማሰጠት ያለመ ክፉ ልቦና ያለው ለመሆኑ የአመልካች አቤቱታው በራሱ ገላጭ ነው፡፡ስለዚህ
አቤቱታው በእውነት ያልተመሰረተ ተቀባይነትም የሌለው ነው እንዲባልልን ፣
አቤቱታችንም በእውነት የቀረበ ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሠረት በቃለ መሀላ በማረጋገጥ
እናቀርባለን፡፡ መ/ሰጪዎች፡- 1. ኃይሉ ኦይቻ
2. በሪሶ ሎሊቱ
3. ማርሳ ኦይቻ
ቀን 7/08/2005 ዓ.ም

ለወንዶገነት ወረዳ ፍ/ቤት


ጩኮ

ከሣሽ፡- በላይ በጤና


ተከሳሾች፡- 1. ኃይሉ ኦይቻ
2. በሪሶ ሎሊቱ
3. ማርሳ ኦይቻ

በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 223 መሰረት የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር መግለጫ


የሰው ማስረጃ
1) በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 261 (2) መሰረት ተከሣሾች
2) አቶ ማርቆስ ዲርፋቶ
3) አቶ ዲርፋቶ ጉጆ
4) አቶ ዳዊት ሐሚጦ ናቸው፡፡
የማስረጃው መገልጫ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሰረት በቃለ መሀላ ተረጋግጦ የቀረበ
ነው፡፡
ተከሳሾች፡- 1. ኃይሉ ኦይቻ
2. በሪሶ ሎሊቱ
3. ማርሳ ኦይቻ
ቁጥር ------------------------------
ቀን -------------------------------

ለባህል አዳራሽ ክ/ከተማ ማዘጋጃ ቤት


ሀዋሣ ፣

በአመልካች ወ/ሮ ፋንታዬ ደምሴ እና እነ ድጋፌ ዘርጋው 13 ሰዎች መካከል ስላለው የውርስ ሀብት
ክርክር ጉዳይ በሟች አቶ ዘርጋው ጩኮ ስም በ 1971 ዓ.ም የተሰጠ የቤቱ ፕላን እና በቀን 24/06/73
ዓ.ም የተፃፈ ማመልከቻ ከግል ማሕደራቸው ታይቶ ከቤቱ ፕላን ጋር አብሮ ተያይዞ ለ 18/06/2005
ዓ.ም በፖስታ ታሽጎ እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡

ቁጥር ------------------------------
ቀን -------------------------------

ለባህል አዳራሽ ክ/ከተማ ማዘጋጃ ቤት


ሀዋሣ ፣

በአመልካች ወ/ሮ ፋንታዬ ደምሴ እና እነ ድጋፌ ዘርጋው 13 ሰዎች መካከል ስላለው የውርስ ሀብት
ክርክር ጉዳይ በሟች አቶ ዘርጋው ጩኮ ስም በ 1971 ዓ.ም የተሰጠ የቤቱ ፕላን እና በቀን 24/06/73
ዓ.ም የተፃፈ ማመልከቻ ከግል ማሕደራቸው ታይቶ ከቤቱ ፕላን ጋር አብሮ ተያይዞ ለ 18/06/2005
ዓ.ም በፖስታ ታሽጎ እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
ቀን 01/06/2005
ለታቦር ክ/ከተማ ምድብ ችሎት
ሀዋሣ ፣

የአፈፃፀም ከሣሽ፡- ፍቃዱ ገብሬ


የአፈፃፀም ተከሳሽ ፡- ፍሰሐ ጌታቸው
አመልካች በቀን 23/05/05 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ እንደፍርዱ ይፈፀምልኝ ሲል ያቀረበውን አቤቱታ ተመልክቼ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 386(2) መሠረት ከተከሣሽ የተሰጠ መልስ
1. እንዲለቅ የተወሰነውን የከሳሽን የኪራይ ቤት ለመልቀቅ የተዘጋጀው ቢሆንም እስካሁን ያለቀኩበት
ምክንያት ሀዋሣ ማዘጋጃ ቤት ለከነማው ስፖርት ኮሚሽን ሀዋሣ ከተማ ሎጊታ አካባቢ በሚገኘው
እስታዲየም ዙሪያ ካሠራቸው ቤቶች ውስጥ አንደኛውን ክፍል ተከራይቼ ቁልፍ የተረከብኩ ቢሆንም
የማብራት መስመር ተዘርግቶ ቆጣሪ ያልገባ ከመሆኑም በተጨማሪ /ካሽ ሪጅስተር / ደግሞ
ያለመብራት ስለማይሰራ ቆጣሪው እስኪገባ ድረስ ጊዜ እንዲሰጠኝ እንዲታዘዝልኝ ፣
2. በአሁኑ ሰዓት መንግሥት የሚያደርገውን ከፍተኛ ልማት ነጋዴዎች በካሽ ሪጅስተር እየተጠቀሙ
ወጪያቸውንና ገቢያቸውን ጭምር ለይተው በማወቅ ተገቢን ግብር በመክፈል የበኩላቸውን
አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ የሚገኙ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ከላይ በዝርዝር እንደገለፅኩት
እንደፍርዱ አሁኑኑ ለከሣሽ ቤቱን ባስረክብ ሥራ ፈትቼ ሰርቼ እንደዜጋ ለሀገርም ጭምር የማስገኘው
ገቢ የሚቋረጥ ከመሆኑም በላይ ቤተሰቤም ለከፍተኛ ችግርና ረሃብ ስለሚጋለጥ የተከራየሁት ቤት
ቆጣሪ ገብቶ ሥራ እስክጀምር ድረስ ጊዜ እንዲሰጠኝ፣
በአጠቃላይ የአፈፃፀም ከሣሽን ቤት ለመልቀቅ የተዘጋጀሁ ስለመሆኔ የአድራሻ ለውጥ በማለት አዲስ
ተከራይቼ ወደምገባበት ቤት ለውጥ ማድረጌን በመግለፅ በጨርቅ ፅፌ ከሣሽም ጭምር የሚያውቅ ከመሆኑም
በተጨማሪ የተከበረው ፍ/ቤት ትክክለኛውን ትዕዛዝ ለመስጠት ያመች ዘንድ አባባሌን ከኢ/ኤሌክትሪክ ደቡብ
ሪጅን ማረጋገጥ የሚቻል ስለሆነ በዝርዝር በገለፅኩት መሠረት ጊዜ እንዲሰጠኝ ስል በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡
መልሴም በእውነት የቀረበ ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሠረት በቃለ መሀላ በማረጋገጥ
አቀርባለሁ፡፡
መልስ አቅራቢ (የአፈፃፀም ተከሳሽ)

ፍሰሐ ጌታቸው
ቀን ------------------------

ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ጠ/ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣

አመልካች፡- ወ/ሮ ትዕግስት ንጋቱ


አድራሻ፡- ሀዋሣ ከተማ
የማመለክተው ጉዳይ ከዚህ እንደሚከተለው ነው
እነሆ እኔ አመልካች ባለቤቴ ባደረሰብኝ ከፍተኛ በደል የተነሣ በመካከላችን የነበረው የባልና ሚስት ግንኙነት
በፍርድ ተቋርጦ የጋራ ንብረት ክፍፍል ማድረግ እንድንችል ተወስኖ የንብረት ክፍፍል ለማድረግ ጉዳዩን
በመጀመሪያ ደረጃ ተቀብሎ በተመለከተው የወንዶገነት ወ/ፍ/ቤት አቤቱታ አቅርቤ ጉዳዩ በመታየት ላይ
ሳለ የቀድሞ ባለቤቴ ለሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ባቀረበው አቤቱታ በመካከላችን የባልና ሚስት ግንኙነት
የሌለን መሆኑን በመግለፅ የተወሰነልኝ ካሣና ቀለብ እንዲሁም የንብረት ክፍፍል መብት ጭምር እንዲሻር
ላቀረበው በአንፃሩ የመ/ይግባኝ በማቅረብ የተወሰነልኝ ካሣና ቀለብ እንዲሻሻልልኝና ቀደም ሲል
በመካከላችን የልጅ መውለድ ችግር አጋጥሞን አዲስ አበባ ከተማ ወደሚገኘው ጋንድ ሆስፒታል ድረስ
በመሄድ የታከምንበት ሰነድ ግንኙነት እንዳለን በይበልጥ የሚገለፅ በመሆኑ እንዲታይልኝ በስር
የሲ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት አቅርቤ ተቀባይነት ያላገኘሁ ስለሆነ ለትክክለኛው ፍትህ አሰጣጥ ያመች ዘንድ በዚህ
ፍ/ቤት ካቀረብኩት የይግባኝ አቤቱታ ጋር በአንድ ላይ እንዲታይልኝ ስል በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡

አመልካች

ወ/ሮ ትዕግስት ንጋቱ


ቀን 30/5/2005 ዓ.ም
ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጠ/ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣
ይግባኝ ባይ ፡- ወ/ሮ ትዕግስት ንጋቱ
አድራሻ ፡- ሀዋሣ ከተማ
መልስ ሰጪ ፡- መንግስቱ ደኡና
አድራሻ ፡- ወ/ገነት ወረዳ ጩኮ ከተማ
- የሥር የወ/ገነት
ወ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር 2325
- የሲ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
መ/ቁጥር
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ/ቁጥር 327 መሠረት የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ
- የይግባኝ አቤቱታው የቀረበበትን የመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የሲ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 27829 በቀን 30/5/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው፡፡
- ከፍ/ቤቱ ለመ/ሰጪ የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በወ/ገነት ወረዳ ጩኮ ቀበሌ አማካኝነት
በኩል ሊደርሰው ይችላል፡፡
- የስር ፍ/ቤቶች የውሳኔ መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ 47 ገፅ ተያይዟል፡፡
ሀ/ ለይግባኝ አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የይግባኝ አቤቱታ ለዚህ ፍ/ቤት ሊቀርብ የቻለው ከመስከረም ወር 2000 ዓ.ም ጀምሮ ከ 3 ቱም የጋብቻ
ስርዓቶች በአንዱ ያደረግነው የጋብቻ የውል ስምምነት ሳይኖር በፍጹም መፈቃቀድ ላይ በመመስረት በነበረን
ከፍተኛ የፍቅር ግንኙነት እንደባልና ሚስት በአንድ ጣሪያ ስር ተስማምተንና ተዋደን አብረን ስንኖር በወንዶገነት
ወረዳ ጩኮ ከተማ ውስጥ በ 25/9/2004 ዓ.ም የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በ 12/2/2004 ዓ.ም በተፃፈ ውል ደግሞ
የከተማ የቤት መሥሪያ ቦታ ተስማምተን በሁለታችንም ስም በመግዛትና በርካታ ተንቀሳቃሽና ቋሚ ንብረቶችን
በማፍራት በወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 1410 በሆነው መዝገብ ላይ በጋራ የገዛነውን የቤት ሽያጭ የውል
ስምምነት በማፀደቅ አብረን ተስማምተን ሳለን ምንነቱን በውል በማላውቀው ጉዳይ በ 14/3/05 ዓ.ም ከምሽቱ
3 ሰዓት ላይ በያዘው ሽጉጥ ሳልገልሽ ከቤት ውጪ በማለት በለበስኩት የሌሊት ቢጃማ ያባረረኝ መሆኑን
በመጥቀስ በመካከላችን የነበረው የባልና ሚስት ግንኙነት በፍርድ እንዲቋረጥ እንዲሁም በለበስኩት ቢጃማ
በኖርኩበት ማሕበረሰብ ዘንድ ሠራተኛዬ ነች በማለት በቢጃማ ያባረረኝ ስለሆነ ካሣ እንዲከፍለኝና ንብረት
ክፍፍል በማድረግ የየድርሻችን እስክንይዝ ድረስ ቀለብ እንዲቆርጥልኝ ጭምር ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ
ተቀብሎ በተመለከተው የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት ላቀረብኩት አቤቱታ መ/ሰጪው በሰጠው ምላሽ ሚስት ሳትሆን
ሠራተኛ ነች ብሎ ክዶ በማቅረቡ የተነሣ በመካከላችን የባልና ሚስት ግንኙነት ስለመኖሩ የሰው ማስረጃ
አረጋግጦ ከሰጠው የምስክርነት ቃል በተጨማሪ በጋራ የገዛነው የመኖሪያ ቤት የሽያጭ ውል ስምምነት በወ/ገነት
ወ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 1410 ላይ በፍርድ የፀደቀበት ሰነድ ጭምር ቀርቦ
ከታየ በኋላ እንደባልና ሚስት በመሆን አብሬው የቆየሁ ሚስቱ መሆኔ ተረጋግጦ በመካከላችን ያለው ግንኙነት
በፍርድ እንዲቋረጥ ሲወስን ከ 2000 ዓ.ም ጀምሮ ያፈራነውን የጋራ ንብረት የመካፈል መብቴ ተጠብቆ
ሠራተኛዬ ነች በማለት ክዶ በመከራከር ላደረሰብኝ የሞራል ውድቀት ብር 2,500 እንዲሁም የንብረት ክፍፍል
ተደርጎ የየግላችንን እስክንይዝ ድረስ በየወሩ ብር 500 ወርሃዊ ቀለብ እንዲቆረጥልኝ ከተወሰነ በኋላ መ/ሰጪ
ለሲ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት ውሳኔውን ለማሻር ይግባኝ ሲያቀርብ የተወሰነልኝ ካሣና ወርሃዊ ቀለብ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ
ተሻሽሎ እንዲወሰንልኝ ያቀረብኩትን የመስቀለኛ ይግባኝ ጥያቄ ጭምር ተቀባይነት በማሳጣት የስር የወንዶገነት
ወረዳ ፍ/ቤትን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በመሻር የአንድ ወር ቀለብ እንኳን ሳላገኝ በየዘመድ አዝማዱ ቤት
በመንከራተት ላይ ሳለሁ ይልቁንም መ/ሰጪ ያወጣውን ወጪና ኪሳራ ጭምር እንድከፍል የተሰጠውን አሳዛኝ
ውሳኔ ለማስለወጥ የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡
2/ በሥር ፍ/ቤት የተፈፀመና እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥብ በአጭሩ
1. ከመ/ሰጪ ጋር የጋብቻ ውል ላይ ሳንፈራረም አብረን ለተከታታይ 5 ዓመታት እንደባልና ሚስት መቆየታችን የክልሉ
የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/96 አንቀፅ 120 ቁጥር 1፣2፣4 ላይ በተመለከተው የሕግ ድንጋጌ መሠረት በሰው
ማስረጃ ተረጋግጦ የተመሰከረ ከመሆኑም በተጨማሪ አብረን በነበርን ጊዜ ለጋራ ጥቅማችን የገዛናቸው የመኖሪያ
ቤትና በከተማ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ በፍርድ ቤት ጭምር አስቀርበን ያፀደቅነው ሰነድ ጭምር ቀርቦ ታይቶ
የተረጋገጠ ከመሆኑም በተጨማሪ ከ 2000 ዓ/ም ጀምሮ በጋራ ያፈራናቸው ንብረቶች እንድንካፈል የተወሰነውንና
መ/ሰጪ በአንፃሩ ግንኙነታችንን በመካድ በብር 400 የቀጠርኳት ሠራተኛዬ ነች በማለት በኖርኩበት ማሕበረሰብ
ዘንድ ያለኝን ከፍተኛ የሆነ አክብሮትና ታማኝነት በማሳጣት ላደረሰብኝ የሞራል ውድቀት እንዲከፍለኝ
ተወስኖልኝ የነበረውን ብር 2,500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ) የካሣ ገንዘብ ካደረሰብኝ የሞራል ውድቀት ጋር
ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ተሻሽሎ እንዲወሰንልኝ ያቀረብኩትን የመስቀለኛ ይግባኝ አቤቱታ ጭምር ተቀባይነት
በማሳጣት ሙሉ በሙሉ በመሻር ወጪ ኪሣራ ለመ/ሰጪ እንድከፍለው የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ባለመሆኑ
እንዲታረምልኝ ፣
2. ከ 2000 ዓ.ም ጀምሮ ከመ/ሰጪ ጋር ያፈራሁትን የጋራ ንብረት ክፍፍል አድርገን የየግላችን ንብረት እስክንይዝ
ድረስ በወንዶገነት ወረዳ ጩኮ ከተማ ውስጥ ተከራይተን በምንሰራበት ምቾት ሆቴል ውስጥ እስከ ሌሊቱ 11 ሰዓት
ድረስ ተሰርቶ የምገኝ እጅግ ቢያንስ ብር 4000 በየቀኑ እንዲሁም የጋራ ቤታችንን በማከራየት በየወሩ ከሚገኘው
ብር 2000 (ሁለት ሺህ) ብር ጋር ተመጣጣኝ ያልሆነና የወቅቱን የኑሮ ሁኔታ ያላገናዘበውን እንዲከፍለኝ
የተወሰነልኝ የወር ቀለብ ብር 500 (አምስት መቶ) ብር በእጅጉ የሚጎዳኝ መሆኑን በመግለፅ ተሻሽሎ
እንዲወሰንልኝ ያቀረብኩትን የመስቀለኛ ይግባኝ ተቀባይነት በማሳጣት የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ካለመሆኑም

በተጨማሪ በክልሉ የቤተሰብ ሕግም ሆነ በሀገሪቱ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 258 መሠረት ቀለብ ያለመስጠት
የወንጀል ሀላፊነትን ጭምር የሚያስከትል ሆኖ ሳለና ረሀብ ለደቂቃ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑ እየታወቀ እንዲሁም
ካፈራሁት ንብረት በለበስኩት የሌሊት ቢጃማ መውጣቴን ጭምር በሥር የወ/ገ/ወ/ፍ/ቤት ተረጋግጦ
የተሰጠውን ውሳኔ በመሻር የተሰጠው ፍርድ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ የሥር የሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
የንብረት፣የቀለብ እና በካሣ ላይ የተሰጠውን ፍትሃዊ ውሳኔ በመሻር ለመ/ሰጪ የወጪ ኪሳራውን እንዲከፍል
የተሰጠው ውሳኔ በሕገ መንግሥቱ ሴቶች ከወንዶች እኩል እውነተኛውንና ትክክለኛውን ፍትህ ያገኛሉ
የሚለውን ድንጋጌ የጣሰ አስገራሚ ፍርድ ስለሆነ የጋራ ንብረት በክፍፍል ማግኘት እንዳልችልና ወጪ ኪሳራ
ለመ/ሰጪ እንድከፍል የተሰጠውን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) መሠረት ተሽሮ የሥር የወ/ገነት
ወ/ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቶ እንዲወሰንልኝ እንዲሁም በካሣና በቀለብ ጥያቄ ላይ የሲ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ
በመሻር የወ/ገነት ወረዳ ፍ/ቤት ውሳኔ ተሻሽሎ እንዲወሰንልኝ በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡
ቀን 18/3/2005 ዓ.ም
ለወንዶ ገነት ወረዳ ፍ/ቤት
ጩኮ ፣
አመልካች፡- ወ/ሮ ትዕግስት ንጋቱ
አድራሻ ፡- ወ/ገነት ወረዳ ጩኮ ከተማ
ተጠሪ፡- መንግስቱ ደኡና
አድራሻ ፡- ወ/ገነት ወረዳ ጩኮ ከተማ
ከተጠሪ ጋር እንደባልና ሚስት የነበረን ግንኙነት በደቡብ ክልል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/1996
አንቀፅ 90 (1) መሠረት በፍርድ ለማቋረጥ የቀረበ አቤቱታ
 ፍ/ቤቱ አቤቱታውን ተቀብሎ ለማየት ስልጣን አለው፡፡
 አመልካችና ተጠሪ በሕግ ፊት ችሎታ የላቸውም አልባልንም፡፡
 ተጠሪ በአቤቱታው ተጠያቂ የሚሆንበትን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 222 (1) (ሸ) መሠረት በመዘርዘር
አስረዳለሁ፡፡
 ከፍ/ቤት የሚላከውን የመጥሪያ ትዕዛዝ በተጠሪ አድራሻ ጩኮ ቀበሌ በኩል ሊደርስ ይችላል፡፡
 አቤቱታው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 223 መሠረት ተሟልቶ ቀርቧል፡፡
የአቤቱታዬ ዝርዝር በአጭሩ
ከላይ በተጠሪነት ከተገለፀው ግለሰብ ጋር ከዛሬ 5 ዓመት በፊት በነበረን የፍቅር ግንኙነት በግሌ በንግድ
ተሰማርቼ ከምሰራበት የንግድ ስራዬ ላይ አብረን በባልና ሚስትነት ተጣምረን/ተጋብተን/ በጋራ እየሰራን እንኑር
ብሎ ስለአግባባኝ በአንድ ጣሪያ ሥር እንደባልና ሚስት በመሆን ተስማምተን ለተከታታይ 5 ዓመታት አብረን
ኖረናል፡፡
በዚሁ የቆይታ ዘመናችንም ውስጥ በምንሰራው የንግድ ስራችን በርካታ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን
አፍርተን በመኖር ላይ ሳለን ምንነቱን በውል በማላውቀው ጉዳይ ተጠሪ የነበረውን መልካም ባሕሪ በመቀየር
በጋራ አፍርተን ያገኘነውን በመደበቅ ከስምምነታችን ውጪ ለፈለገው ጉዳይ ሲያውል ለምን ይሆናል በሚል
እንደባለቤት አስተያየት ሳቀርብለት ምን አገባሽ በማለት ለበርካታ ጊዜ ደብድቦ ከቤት ሲያባርረኝ በተደጋጋሚ
በአካባቢ ሽማግሌ እየተመከረ ወደ ቤቴ ተመልሼ ለመኖር ጥረት እያደረግኩ ብቆይም ከተጠናወተው መጥፎ
ባህሪው ተፀፅቶ የሞቀ ትዳርችንን የበለጠ በማሞቅ አብረን እየሰራን በትዳር እንቀጥላለን በሚል በየጊዜው
የሚደርስብኝን ድብደባና ማስፈራራት ወደ ጎን በመተው አንድ ቀን ተስተካክሎ በሰላም ትዳራችንን እንመራለን
በሚል በትዕግስት ለመጠበቅ ብሞክርም በ 14/3/05 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት በያዘው ሽጉጥ ሳልገልሽ ውጪ
በማለት በለበስኩት በሌሊት ቢጃማ ደብድቦ ከአባረረኝ በኋላ በማግስቱ በ 15/3/2005 ዓ/ም በቤተሰቤ
ለማስጠየቅ ጥረት ባደርግም ሊያናግራቸው ባለመቻሉ ሕይወቴን ለማዳን በቤተሰቤ ተጠልዬ እገኛለሁ፡፡

ስለዚህ የተከበረውን ፍ/ቤት የምጠይቀው ዳኝነት

- በቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/96 አንቀፅ 94 ላይ በባልና ሚስት መካከል የተደነገገውን


የመከባበር፣የመተማመንና በታማኝነት አብሮ የመኖር ግዴታውን በመጣስ በለበስኩት የሌሊት ቢጃማ
በውድቀት ሌሊት አባሮኝ ከፍተኛ የሞራል ውድቀት ያደረሰብኝ በመሆኑ በአንቀፅ 95 መሠረት ካሣ
ከፍሎኝ በተጠሪ ጥፋተኝነት ግንኙነታችን በፍርድ እንዲቋረጥ እንዲወሰንልኝ፣
- በዚሁ ጩኮ ከተማ ምቾት ሆቴል ተከራይተን ከምንሰራው የቀን ገቢ ቢያንስ ከ 4000 ብር በላይ የምገኝና
ካለን የጋራ የቤት ኪራይ (ሰርቪስ ቤቶች) በወር ከ 2000 ብር የማያንስ ገቢ የሚገኝ ስለሆነ ውሳኔው
እስኪሰጥ እና ወደ ንብረት ክፍፍል ገብተን ድርሻዬን በፍርድ እስካገኝ ድረስ ቀለብ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ
የጤና መከታተያ የአልባሳት ፣ለቤት ኪራይና ለቀለብ የሚሆነኝን ወርሐዊ ቀለብ እንዲቆርጥልኝ
እንዲታዘዝልኝ ጭምር በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡
አቤቱታዬም በእውነት የቀረበ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሠረት በቃለ መሀላ በማረጋገጥ
አቀርባለሁ፡፡
ቀን 18/3/2005 ዓ.ም

ለወንዶ ገነት ወረዳ ፍ/ቤት


ጩኮ ፣

አመልካች፡- ወ/ሮ ትዕግስት ንጋቱ


አድራሻ ፡- ወ/ገነት ወረዳ ጩኮ ከተማ
ተጠሪ፡- መንግስቱ ደኡና
አድራሻ ፡- ወ/ገነት ወረዳ ጩኮ ከተማ
በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 223 መሰረት የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር መግለጫ
የሰው ማስረጃ
5) በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 261 (2) መሠረት አመልካች
6) ወ/ሮ ምንትዋብ ገ/ዮሐንስ
7) አቶ ንጋቱ ተገኝ
8) ቤቴልሔም ገ/ሚካኤል
9) አሸናፊ ማገኔ ናቸው፡፡
የማስረጃው መገልጫ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92 መሰረት በቃለ መሀላ ተረጋግጦ የቀረበ
ነው፡፡
ቀን --------------------------------
ለሲዳማ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ሀዋሣ ፣

ይግባኝ ባይ፡- ባቢሶ ባጢሶ


አድራሻ፡- ወ/ገነት ወረዳ ጩኮ ከተማ
መ/ሰጪ፡- ወ/ሮ ትዕግሥት ደግፌ
አድራሻ፡- ወ/ገነት ወረዳ ጩኮ ከተማ
- የሥር የወ/ገነት ወረዳ ፍ/መ/ቁጥር 1928
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 327 መሠረት የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው
- የይግባኝ አቤቱታው የቀረበበትን ፍርድ የሰጠው የወ/ገነት ወ/ፍ/ቤት ነው፡፡
- ፍርዱ የተሰጠው በፍ/መ/ቁጥር 1928 በቀን 14/5/05 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው ፡፡
- ከፍ/ቤት ለመ/ሰጪ የሚላከውን የመጥሪያ ትእዛዝ በጩኮ ከተማ ቀበሌ በኩል ሊደርስ ይችላል፡፡
- የስር ፍ/ቤት የውሳኔ መዝገብ ትክክለኛ ቅጂ 62 ገፅ ተያይዟል፡፡
1. ለይግባኝ አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዳይ
ይህ የይግባኝ አቤቱታ ለዚህ ፍ/ቤት ሊቀርብ የቻለው መ/ሰጪ ከሆነችው የልጆቼ እናት ባለቤቴ ጋር
የነበረኝ ጋብቻ በፍርድ የፍቺ ውሳኔ ተሰጥቶ የንብረት ክፍፍል ለማድረግ በቀረበው አቤቱታ መሠረት
የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ተጣርቶ እኩል በዓይነት ክፍፍል ማድረግ ሲገባው መ/ሰጪ የሞተር ብስክሌት
፣ በጩኮ ከተማ የቤት መሥሪያ ቦታ እንዲሁም በሸበዲኖ ወረዳ ውስጥ የእርሻ ማሳ አለን ስትል በችሎት
ከመግለፅ ያለፈ የተባለው ንብረት በትክክል ስለመኖሩ ተጣርቶ ባልቀረበበት እንዲሁም በይግባኝ ባይም
ይሁን በመ/ሰጪ ስም የተመዘገበበት ወይንም ግዥ የተፈፀመበት ሰነድ እንኳን ባልቀረበበት በእጄ የሌለውን
ክፍፍል ይደረግ ተብሎ የተሰጠውን አሳዛኝ ውሳኔ ለማስለወጥ የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ነው፡፡
2. በይ/ሰሚው ፍ/ቤት እንዲታረምልኝ የምጠይቀው የቅሬታ ነጥቦች በአጭሩ
2.1 በስሜ የተመዘገበ የባለቤትነት ሊቭሬም ሆነ የሞተር ብስክሌት ግዥ የተፈፀመበት ሰነድ ባልቀረበበት
እንዲሁም የጋራ ንብረት በተጣራ ጊዜ ስለመኖሩ ባልተመዘገበበትና በአይን ማስረጃ ተረጋግጦ
ባልተመሰከረበት መኖሩ በመ/ሰጪ ስለተገለፀ ብቻ የሌለውን እንዳለ በማስመሰል ክፍፍል እንዲደረግ
የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ባለመሆኑ ተጣርቶ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ተሽሮ እንዲወሰንልኝ፣

2.2 በሸበዲኖ ወረዳ ውስጥ የእርሻ ይዞታ መኖሩን ከመግለፅ ያለፈ የት ቀበሌ እንደሚገኝ ለይታ መናገር
ባልቻለችበትና ከሁለታችን በአንዳችን ስም እንኳን የተገበረበትን ሰነድ አያይዛ ባላቀረበችበት እንዲሁም
ወንድሞቿም ይዞታ እንዳላቸው መ/ሰጪ ስትናገር ሰማን ከማለት ያለፈ በትክክል ስለመኖሩ አረጋግጠው
ሳይመሰክሩ የሌለንን ይዞታ እንዳለ ተደርጎ ክፍፍል እንዲደረግ የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ባለመሆኑ
እንዲታረምልኝ፣
2.3 በጩኮ ከተማ የጋራ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ መኖሩን ከመግለፅ ያለፈ በአጣሪ ተለይቶ ታውቆ ተመዝግቦ
ባልቀረበበት በመ/ሰጪ መኖሩ በመነገሩ ብቻ የሌለን ንብረት ክፍፍል እንድናደርግ የተሰጠው ውሳኔ አግባብ
ካለመሆኑም በተጨማሪ ለትክክለኛው ፍትህ አሰጣጥ በሚያመች መልኩ አለ ተብሎ በሐሰት ከመ/ሰጪ
የተገለፀውን ንብረት ከይዞታው ጀምሮ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 132 መሠረት ስፍራው ድረስ በመሄድ
ለማጣራት የተደረገ ጥረት ሳይኖር የሌለን ንብረት ክፍፍል እንዲደረግ የተሰጠው ፍርድ አግባብነት የሌለው
ነው፡፡
በተጨማሪም ከመ/ሰጪ ጋር ቀደም ሲል በትዳር በቆየንበት ጊዜ ከነበረን ሁለት የጋራ ቤት ውስጥ 1 ኛውን
በመሸጥ ድርሻዋን በመውሰድ ተለይታኝ ውጭ ሀገር በመሔድ ከረዥም ቆይታ በኋላ በመምጣት ድርሻዬን
በመሸጥ የልጆቼን ማሳደጊያ ለማሳጣት ከቅን ልቦና ውጪ ያቀረበችብኝ ክስ መሆኑን በመግለፅ ያደረኩትን
ክርክር ተቀባይነት በማሳጣት የተሰጠ ውሳኔ ከመሆኑም በተጨማሪም ክፍፍል እንድናደርግ የተሰጠው
ውሳኔ ባቀረብኳቸው የሰው ማስረጃ ከላይ በዝርዝር የተጠቀሰው ንብረት እንደሌለን በመግለፅ
ባቀረብኳቸው የሰው ማስረጃ ከበቂ በላይ አስረድቼ ሳለሁ ታልፎ የተሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር
348 (1) መሠረት ተሽሮ እንዲወሰንልኝ ስል በአክብሮት አመለክታለሁ፡፡
ቁጥር ----------------------------
ቀን -------------------------------

ለሚመለከተው ሁሉ
ባሉበት

ጉዳዩ፡- ተጠርጣሪ ተይዞ እንዲላክልን ስለመጠየቅ ፣

ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደሞከርነው ይሄይስ ወንድሙ የተባለው በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችን
ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገር እልካለሁኝ በማለት እያታለለ ገንዘብ እየተቀበለ መቆየቱን
በማስረጃ በማረጋገጥ በተጠርጣሪ ላይ በቁጥር 13496 በቀን 22/05/2005 ዓ.ም ከሀዋሣ
ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የመያዣ ትዕዛዝ አውጥተናል፡፡
ስለሆነም ተጠርጣሪውን ካገኛችሁ ይህንን ደብዳቤ ለያዘው ም/ሣጅን መሠለ አርጅኖ እጅ
እንድትልኩልን የተለመደ የሥራ ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር
መ/ቁጥር ------------------------
ቀን ------------------------------
ለሀዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
መሀልና ሐይቅ ዳር ምድብ ችሎት
ሀዋሣ ፣

አመልካች ፡- ወ/ሮ ስንቄ ደዶ


ተጠሪ፡- አቶ መንግሥቱ መና
በቀን 19/09/05 የክርክር ማቆሚያ በፍ/ቤቱ በፅሁፍ እንድናቀርብ በታዘዝነው መሠረት ከአመልካች የቀረበ
የክርክር ማቆሚያ ነው፡፡
በአመልካች የቀረበው የክስ ምክንያት በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ ከ 1990 ዓ/ም ጀምሮ
በሁኔታዎች ተቋርጧል እንዲባልልኝ በማለት ያቀረብኩት ሲሆን በእኔና በተጠሪ መካከል ከ 15 ዓመት በላይ
ተለያይተን በተለያየ መኖሪያ የምንኖር እና በዚህም ጊዜ ተጠሪ 1 ኛ/ ወ/ሮ አየለች 2 ኛ/ ወ/ሮ በላይነሽ የተባሉ
ሁለት ሚስት ማግባታቸውና ከእኔ አመልካች ጋር ከ 1990 ዓ/ም ጀምሮ ምንም ዓይነት የባልና ሚስት ግንኙነቶች
እንዲሁም የመረዳዳት የመተጋገዝ ግዴታዎችን በሁለታችን መካከል የሌለ በመሆኑ ጋብቻው ከ 1990 ዓ/ም
ጀምሮ በሕጋዊ መንገድ ተቋርጧል እንዲባልልኝ በማለት ክስ አቅርቤ ፤እንደ ክሴ የሚያስረዱልኝን 6(ስድስት
ማሰረጃዎችን) ከክሴ ጋር በማቅረብ በተመሳሳይ መልኩ የመሰከሩልኝ ሲሆን ምስክሮቼ በተመሳሳይ መልኩ
የመሠከሩት 1 ኛ) አመልካች እና ተጠሪ ከ 1990 በፊት ተለያይተን እንደምንኖር በዚህም ጊዜ በመካከላችን
ምንም ዓይነት የባልና ሚስት ግንኙነቶች እንዳልነበረ እና አሁንም እንደሌለ ፤ 2 ኛ ተጠሪ ከእኔ አመልካች ጋር
ተለያይቶ በሚኖርበት ጊዜ የተለያዩ ሚስቶች አግብቶ እንደሚኖር፤በሰፈር ውስጥ ለረዥም ዓመታት አይተውት
እንደማያውቁ የመለያየታችን ምክንያትም ሌላ ትዳር መመስረቱን አስረድተዋል፡፡ 3 ኛ ከ 1990 ዓ/ም በፊት
ተጠሪ ከሚሰራበት መ/ቤት ለልጆች ቀለብ የሚቆርጥ የነበረ መሆኑን እና ከ 1990 ዓ/ም በኋላ ተጠሪ ለልጆች
ቀለብ የሚቆርጠውን እንዳቆመ ምክንያቱም በማለት ያቀረቡት አመልካች እና ተጠሪ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ
ስለተለያዩ በመሆኑ በማለት በሚገባ አስረድተዋል፡፡
የተጠሪ ምስክሮች በተመሳሳይ መልኩ እንደ አመልካች ክስ አቀራረብ አስረድተዋል ያስረዱትም ከ 1990 ዓ.ም
ጀምሮ በፍ/ቤት ትዕዛዝ አመልካች እና ተጠሪ ተለያይተው እየኖሩ እንደሚገኙ በዚህም ጊዜ ተጠሪ አመልካችን
እየረዳት መሆኑን እና አለመሆኑን እንደማያውቁ ፤ በዚህም ወቅት ማለትም ከ 1990 ዓ/ም 2 ኛ እና 3 ኛ
ምስክሮች በቦታው እንዳልነበሩ፤ ቡዙህን ጊዜ ከተጠሪ ጋር እንደማይገናኙ፡፡ በተለይ የተጠሪ 2 ኛ ምስክር
በሥራቸው ምክንያት ቡዙህን ጊዜ ሰፈሩ ውስጥ እንደማይገኙ እና ተጠሪን በድንገት እንጂ ሰፈሩ ውስጥ እንደ
ሰፈርተኛ እንደማይገናኙ መስክረዋል፡፡
3 ኛ የተጠሪ ምስክር በምስክርነት በሚሰጥበት ጊዜ እንደተናገረው ከአመልካች ጋር በአሁኑ ጊዜ መልካም
ግንኙነት እንደሌለው እና እንደ ተጣሉ የገለፀ ሲሆን ይህም የሚያስረዳሁ 3 ኛ ተጠሪ በእውነት ለመመስከር
የማይችል መሆኑን በግልፅ የሚያመለክት ነው፡፡
በአጠቃላይ በአመልካች የቀረበው ክስ በሚገባ ሁኔታ በምስክሮቼ የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች ከተጠሪ ጋር
ከ 1990 ጀምሮ አብረን እንደማንኖር እና የመረዳዳት የመተጋገዝ ግዴታዎችን በሁለታችን መካከል እንደሌለ እና
ተጠሪ ሌላ ሚስት ማግባቱን በተመሳሳይ ተመስክሯል፡፡ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 5 በመ/ቁጥር
31891 በሰጠው ውሳኔ በባልና ሚስት መካከል ያለ ጋብቻ በፍ/ቤት በተሰጠ የፍቺ ውሳኔ ፈርሷል ባይባልም
የተጋቢዎች ተለያይቶ ለረጅም ጊዜ መኖር በዚህም ጊዜ ከተጋቢዎች አንዱ ሌላ ትዳር መስርቶ መገኘት
የቀድሞው ጋብቻው በሕጋዊ መንገድ ተቋርጧል ሊባል ይቻላል በማለት የሕግ ትርጉም በተመሳሳይ ጉዳይ የሰጠ
በመሆኑ ይህም በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በጋብቻ ውስጥ ያሉ ባልና ሚስት ሊፈፅሙት ይገባል በማለት
በቤተሰብ ሕግ የተቀመጡትን ግንኙነቶች እንዲሁም አብሮ የመኖር የመተሳሰብና የመተጋገዝ ግዴታዎችን ከቀን
23/09/1990 ዓዓም ጀምሮ የተቋረጠ በመሆኑ በሁለታችን መካከል ያለው ግንኙነት /ጋብቻ/ ከ 1990 ጀምሮ
በህጋዊ መንገድ ተቋርጧል እንዲባልልኝ በማክበር እናመለክታለን፡፡

ስለአመልካች
03/01/2005 ዓ.ም

በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2226 መሠረት የተፈፀመ ጅምር የመኖሪያ ቤት ከነ


እርሻው ሽያጭ ስምምነት ውል

አንቀፅ 1
የተዋዋዮች ማንነት መግለጫ
ከዚህ ቀን ጀምሮ ሻጭ ተብለው በሚጠሩ፡-
1 ኛ/ አቶ ሀየሞ ሀርጋሞ
2 ኛ/ ወ/ሮ በቀለች ሌለ
አድራሻ ወ/ገነት ወረዳ ዩዎ ቀበሌ
ወል ተቀባይ ተብሎ በሚጠራው ፡- አቶ መንገሻ ጤካሞ
አድራሻ ወ/ገነት ወረዳ ዩዎ ቀበሌ
በሆኑት መካከል በሕግ የሚፀና የጅምር የመኖሪያ ቤት ከነ እርሻው ሽያጭ ስምምነት ውል
ተፈፅሟል፡፡
አንቀጽ 2
የጅምር ቤቱና እርሻው አድራሻ
ይህ የሽያጭ ውል የሚፈጸምበት ጅምር ቤትና እርሻ የሚገኘው በወ/ገነት ወረዳ ዩዎ ቀበሌ፡-
 በምሥራቅ --------------------------------------------------
 በምዕራብ ----------------------------------------------------
 በሰሜን ------------------------------------------------------
 በደቡብ ------------------------------------------------------
ተወስኖ የሚገኘውን ቁመቱ ------------------------ ጎኑ ---------------- በሆነው ይዞታ ላይ የሚገኘውን
ጅምር ቤትና እርሻ ጫት፣እንሰት፣ዋንዛ እና የለያዩ ዛፎችን ጭምር ነው፡፡

አንቀፅ 3
የሽያጩ ዋጋና የአከፋፈሉ ሁኔታ
የዚህ ሽያጭ ጠቅላላ ዋጋ ብር 32,500 /ሰላሣ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ሲሆን ጠቅላላውን ክፍያ
በዛሬው ዕለት ውል ተቀባዩ ለውል ሰጭዎች አጠቃልሎ ከፍሏል፡፡ ውል ሰጭዎች(ሻጮቹም) ተቀብለዋል፡፡
አንቀጽ 4
የውል ሰጭዎች ግዴታ
ውል ሰጭዎች ይህ ሽያጭ የተፈፀመበትን ቤትና እርሻ ወይም ይዞታው ይገባኛል ባይ ሌላ ሶስተኛ ወገን
ተከራካሪ ቢመጣ ሙሉ ኃላፊነትን ወስደው የመከራከርና የውል ተቀባዩን መብት የማስከበር ፣ይህንንም
የውል ስምምነት የማክበር ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
አንቀጽ 5
የውል ተቀባይ ግዴታ
ውል ተቀባይም በዚህ ስምምነት መሠረት ከዚህ በኋላ የገዛውን ቤትና እርሻ በባለቤትነት ይዞ የመጠቀምና
ይህንን ውል የማክበር ግዴታ ይኖርበታል፡፡

አንቀጽ 6
የውሉ አቋም
Date _________________

CURRICULUM VITAE (CV)


1. Personal details
Full name :- Belete Bekele Fetera
Date of birth:- Jul .29/1983 E.C
Place of birth:- Shebedino Worda
Age:- 22
Marital status:- Single
Nationality :- Ethiopian
Present address:- Shebedino Mobile 0916619530
2. Education Qualification
 1 -6 M/Qutala primary school 1991-1996 E.C
 7-8 Hawela Tula Primary school 1997 – 1998 E.C
 9-10 Leku Secondary & preparatory school 1999-2000 E.C
 11-12 Hawassa Tabor Secondary & preparatory school 2001-
2002 E.C
 1st degree (BA) in economics from Adama science &
Technology university 2003-2005 E.C
3. Work Experience
My work experience is zero year.
4. Language

Language Speaking Writing Reading Listening


Sidamic Very good Very good Very good Very good
English Good “ “ Good
Amharic Very good “ “ Very good
5. Hobby
Reading book specially bible, magazine and watching films.
6. Reference
1. Mr Asrat Ginjamo mobile 0916452092
2. Mr. Alemayehu Atena mobile 0913222468
Date _________________

CURRICULUM VITAE (CV)


2. Personal details
Full name :- Debub Ejamo Eyamo
Date of birth:- Nov .15/1983 E.C
Place of birth:- Wondo Tikka
Age:- 22
Marital status:- Single
Nationality :- Ethiopian
Present address:- Hawassa Mobile 0916065678
2. Education Qualification
 1 -7 Wondo Tikka primary school 1991-1997 E.C
 8 Sunshine Primary and secondary school 1998 E.C
 9-10 Adventist Secondary & preparatory school 1999-2000 E.C
 11-12 Hawassa Tabor Secondary & preparatory school 2001-
2002 E.C
 1st degree (BA) in management from Adama science &
Technology university 2003-2005 E.C
3. Work Experience
My work experience is zero year.
4. Language

Language Speaking Writing Reading Listening


Sidamic Very good Very good Very good Very good
English Good “ “ Good
Amharic Very good “ “ Very good

5. Hobby
Reading book specially bible, magazine and watching films.
6. Reference
1. Mr Mathewos Ejamo mobile 0916040750
2. Mr. Wondimu Torba mobile 0911765740
3. Mr. Melkamu Belete mobile 0926046650
Date ________________________
Address Tariku Aregata Nanebo
Tel + 2510916809332

To _____________________________

Application Letter

Dear /sir/ madam

I am writing this letter to apply vacancy declared by your


organization I am a holder of BA degree in accounting and
finance from Adama sciences and Technology University.

I am very interested to work in your organization and hope to


get favorable condition. I feel would be an asset for the
organization in given opportunity to serve the organization and
public.

With regards

Tariku Aregata
Date ________________________
Address Tariku Aregata Nanebo
Tel + 2510916809332

To _____________________________
Position _______________________

Application Letter

Dear /sir/ madam

I am writing this letter to apply vacancy declared by the


____________________________ position on your organization I am a
holder of BA degree in accounting and finance from Adama
sciences and Technology University.

I am very interested to work in your organization in a position


identified above and hope to get favorable condition. I feel
would be an asset for the organization in given opportunity to
serve the organization and public.

With regards

Tariku Aregata
ቀን 9/01/2006 ዓ.ም
ለሀዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
አዲስ ከተማ አካባቢ ምድብ ችሎት
ሀዋሣ ፣

አመልካቾች ፡- 1 ኛ. ወ/ሮ አበራሽ አሰፋ


2 ኛ. አቶ በላቸው አሰፋ (ተተኪ ወራሽ ወ/ሪት ካሰች በላቸው)
አድራሻችን ሀዋሣ
ተጠሪ፡- አቶ አዛዥ ወ/ጊዮርጊስ
ፅፎ ባቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ከአመልካቾች የቀረበ የጽሁፍ መልስ ፡፡
ተጠሪ አመልካቾች ባቀረቡት በውርስ ይጣራ አቤቱታ ላይ በፍ/ሕግ/ቁጥር 1000 (1) መሠረት ያነሳውን
የይርጋ ጥያቄን በተመለከተ፡- በፍፁም ተቀባይነት የሌለው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነው፡፡ ምክንያቱም
የሕግ ቁጥር 1000 (1) እንደሚለው ከሆነ የውርስ ንብረቶች በተከሣሽ መያዛቸውን ካወቀ ሦስት ዓመት
ካለፈ በኋላ ስለወራሽነት ጥያቄ አይነሳም የሚል ሲሆን በንዑስ ቁጥር (2) ላይ ደግሞ ሟቹ ከሞተበት ከሣሹ
በመብቱ ለመሥራት ከቻለበት ቀን አንስቶ አሥራ አምስት ዓመት ካለፈ በኋላ ይልና ከዘር የወረደ ርስት
ካልሆነ በቀር የተባለው የውርስ ጥያቄ ተቀባይነት አያገኝም የሚል የሕግ ክፍሎች የሚያስረዱት ቢሆንም
የአሁኑ የክስ መነሻ የሆነው የውርስ ይጣራ ክርክር ቢፈፀም ከላይ ከተጠቀሰው ከሕግ ቁጥር ጋር የሚገናኝ
ጉዳይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሟች እናታችን ይኼ ችግር በተወላጆች መብት ላይ እንደሚመጣ ከወዲሁ
ጠንቅቃ ስለምታውቅ ብቻ ለሞት በተቃረበው ጭንቅላት የሰፈር ሽማግሌዎችን በማስጠራት ባለቤቴ አቶ
አዛዥ በ 1984 ዓ.ም ከእኔ ተለይቶ የእኔ ኑሮ እንዴት እንደሆነ ወደ ኋላ ተመልሶ ሳያይ ከቀረ ዘመኑ ቆጥሮአል፡፡
ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት አቶ አዛዥ ለሥራ ጉዳይ በሄደበት ቦታ ሌላ ሚስት አግብቶ እንደሚኖር በወሬ ደረጃ
ሰምችያለሁ፡፡ በዚህ ምክንያት በኋላ ከእኔ ሞት ወዲህ ልጆቼን የእኔ ድርሻ እንዳይከለከል ስለዚህ ምስክር ሁኑ
የእኔ ድርሻ ለልጆቼ ሰጥችያለሁ በማለት በሠፈር ሽማግሌዎች ፊት ሰጥታኝ ነው የሞተችው፡፡ ስለሆነም
ከእናታችን ሞት ወዲህ በአጠቃላይ ከተጠሪ ይዞታ ጭምር በታማኝነት በማስተዳደር እስከ መስከረም ወር
2004 ዓ.ም ድረስ አድርሰናል፡፡ ምክንያቱም ተጠሪ ከምሠራበት ቦታ ጡረታ ወጥቶ እስከምመጣበት ድረስ
ይሁን እንጂ ከምሠራበት ቦታ ጡረታ ወጥቶ ቢመጣም የራሱ ድርሻ ይዞታ ቢሆንም አመልካቾችን አስፈቅዶ
ነው እንጂ መብት አለኝ ብሎ እንደማንኛውም ባለይዞታ ዘሎ አልገባም፡፡ ተጠሪ ከሌላ ሚስት ጋር መጥቶ
ከገባ በኋላ ሟች እንዳለችው አመልካቾች የእናታቸውን ድርሻ ይዘን እስከአሁን ድረስ እንገኛለን፡፡

ይኼ ማለት ደግሞ ቢፈፀም ይርጋ ያግዳል የሚያስብል አይደለም፡፡ እንዲሁም ተጠሪ ባለፈው በዚህ ችሎት
ፊት ቀርቦ በቃል ሲያስረዳ ምን ብሎ ነው ያስረዳው፡፡ የእናታቸው ድርሻ ከሆነ በእጃቸው ነው ያለው፡፡
ስለዚህ መቼ ከለከልኳቸው መቼ ጠየቁኝ የሚል የእምነት ቃል ሰጥቷል፡፡ ይኼ ማለት ደግሞ አመልካቾች
እስከአሁን ድረስ የሟች የእናታችን ድርሻ በእጃችን ይዘን እንገኛለን ማለት ነው፡፡ በመሠረቱ አመልካቾች
የእናታችን ድርሻ በሠፈር ሽማግሌዎች ፊት እንደወሰድን እስከአሁን ድረስ በእጃችን ላይ የሚገኝ ቢሆንም
በተጠሪ እና በወ/ሮ አባይነሽ አንጅሎ መካከል በነበረው ክስ ምክንያት ተጠሪ በእኛ ይዞታ በኩል ያለውን ቦታ
ለመሸጥ እያደረገ ያለው ጥረት ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሣ ፍ/ቤቱን አሳውቀን ሕጋዊ እንሁን በሚል አዝማሚያ
ያቀረብነው አቤቱታ ነው እንጂ በፍፁም ይርጋ ሕግ በአመልካቾች መብት ላይ የሚነሳበት የሕግ አግባብ
የለውም ፡፡ ስለሆነም አመልካቾች በመነሻውም የእናታቸውን ድርሻ በእጃቸው ይዞ እንደሚገኙ በዚህ ችሎት
ፊት ተጠሪም በአንደበቱ አረጋግጦ ያለፈ ነገር ስለሆነ የተከበረው ፍ/ቤት በአመልካቾች መብት ላይ የይርጋ
ጥያቄ መነሳቱ አግባብ አይደለም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን በብይን ውድቅ አድርጎ ወደ
ዋናው ክርክር እንዲያስገባልን እንጠይቃለን፡፡
ህዳር 2 ቀን 2006 ዓ/ም

የሞተር ብስክሌት ሽያጭ ስምምነት ውል

You might also like