You are on page 1of 10

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ
የአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት
The Federal Democratic Republic of Ethiopia
Attorney General
Addis Ketema Office

ቁጥር
Ref. No
ቀን
Date
ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ልደታ ምድብ ይግባኝ ሰሚ ወንጀል ችሎት
አዲስ አበባ
የአ/አ/ጠ/ዐ/ህ/ቁ/00379/13
የመምሪያ ፖ/ወ/ቁ/117/12/13
የፍ/ቤ/መ/ቁ/91842
 ይግባኝ ባይ፡-የፌዴራል ጠ/ዐ/ህግ
 መልስ ሰጭ፡- አወቀ ፀዳሉ አለምነው ዕድሜ 45 ዓመት
አድ፡- አ/ከ/ከ/ቀበሌ 32 የቤ.ቁ አልጋ ተከራይ
ይግባኙ የቀረበ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አዲስ ከተማ ወ/ም/ችሎት በቀን 29/12/2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት በመዝገብ ቁጥር
91842 የሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ነው
ይግባኙ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 185 መሰረት የቀረበ ነው
ይግባኙ በህግ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ የቀረበ ነው፡፡
የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ
ይግባኝ ባይ በቀን 27/12/12 ዓ/ም ፅፎ በአቀረበው ክስ መልስ ሰጭው እቃው የተገኘው በአንድ ንብረት ላይ በተፈፀመ
ወንጀል ምክንያት መሆኑን እያወቀ በቀን 17/12/12 ዓ/ም ከንጋቱ በግምት 11፡00 ሰዓት ሲሆን በአ/ከ/ክ/ከ/ ወረዳ 7
ቀበሌ 13/15 ልዩ ቦታው ጎጃም በረንዳ አካባቢ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮፖሬሽን አዲስ አበባ ቀላል ባቡር
ትራንስፖርት የሆነ ሁለት የእሳት ማጥፊያ የሁለቱ ዋጋ ግምቱ 5000/አምስት ሺ ብር/ ይዞ የተገኘ በመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ
የወንጀል ህግ አንቀጽ 683/ስር በመተላለፍ የከባድ መሸሸግ ወንጀል ፍፅሟል የሚል ሲሆን ተከሳሽ በችሎት ቀርቦ ክሱን
ክዶ በመከራከሩ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ከተሰጠው በኋላ ምስክሮች እንደክሱ አልመሰከሩም በማለት ተከሳሽ
በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/ 141 መሰረት በነፃ እንዲሰናበቱ ተወስኗል፡፡
የቅሬታ ነጥቦች
1. በዐቃቤ ህግ በኩል ሶስት የሰው ማስረጃዎች ቀርቦ እንደ ክስ አቀራረባችን አስረድቷል፡፡ 1 ኛ ምስክር ማህደር
ክፍሌ የድርጅቱ ተወካይ በመሆን የተሰረቀ ንብረት የድርጅቱ መሆኑን አስረድታ ንብረቱ የድርጅቱ መሆኑ እና
የዋጋ ግምቱ ደግሞ በቀን 22/12/12 ዓ/ም ከድርጅቱ በተፃፈ ደብዳቤም ተገልጿል፡፡ 2 ኛ እና 3 ኛ ምስክሮች
ደግሞ መልስ ሰጭው ንብረቱን ይዞ እንዳለ እጅ ከፍንጅ የያዙ እና መልስ ሰጭው ንብረቱን ወደ ወሰደበት ቦታ
ወስዶ እንደሰጣቸው መስክሮ እያለ ተከሳሽ እቃው የተሰረቀ መሆኑን እያወቀ እቃውን አልወሰዱም መሬት ላይ
ወድቆ አነሱ እንጅ በማለት ተከሳሽ ነፃ መላቱ ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም ተከሳሽ ድርጊቱን መፈፀሙን
ከተረጋገጠ የሀሳብ ክፍል የሚገመተው ከድርጊቱ ስለሆነ ተከላከል መባል አለበት፡፡

‘’ለህግ ፣ለፍትህ፣ለርትዕ !’’


ዘ/መ ፋክስ ፖ.ሣ.ቁ ስልክ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
FAX 0115-51-77-75 P.O.Box 1370 Tel. 0112-78-12-91 Addis Ababa-Ethiopia
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ
የአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት
The Federal Democratic Republic of Ethiopia
Attorney General
Addis Ketema Office

ቁጥር
Ref. No
ቀን
Date
2. የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የአሳብ ክፍሊን አላስረዱም እንኳን ቢባል ፍ/ቤቱ አንቀጹን ቀይሮ በወ/ህ/አንቀጽ
680/1/ስር ወድቆ የተገኘ ንብረት የራስ ማድረግ ወንጀል እንዲከላከል ብሎ ብይን መስጠት ስገባ በነፃ ማሰናበቱ
አግባብ አይደለም፡፡ ምክንያቱም በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 113 መሰረት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ክስ ከቀረበበት ውጭ
ሌላ ወንጀል ካስረዱ እና ምስክሮች የአስረዱት ወንጀል ክስ ከቀረበበት ወንጀል ዝቅተኛ ቅጣት የሚያስቀጣ
ከሆነ ፍ/ቤቱ አንቀጹን መቀየር እንደሚችል ያስረዳል፡፡ በተያዘ ጉዳይ ላይም መልስ ሰጭው ንብረቱን ወድቆ
አግኝቶ እንደወሰደ ለፍ/ቤት የእምነት ክህደቱ ቃሉን ሰጥቶ እያለ እና ምስክሮችም እቃውን በተከሳሽ እጅ ላይ
ይዞ ተከሳሽም እቃውን ወደ አገኘበት ድረስ ወስዶ ያሳያቸው መሆኑ መስክሮ እያለ ተከሳሽን በወንጀል ህግ
አንቀጽ 680/1/ ስር ተከላከል ማለት ሲገባ በነፃ መለቀቁ አግባብ አይደለም፡፡
ከፍ/ቤቱ የሚንጠይቀው ዳኝነት
ፍ/ቤቱ መልስ ሰጭውን በነፃ በብይን መሰናበቱ ከላይ በገለፅናቸው ምክንያቶች ስህተት ስለሆነ ተከሳሽ ተከሶ
በቀረበበት የወንጀል ህግ አንቀጽ 683/ሐ/ እንዲከላከል ትዕዛዝ እንዲሰጥልን ይህም የሚታለፍ ከሆነ በአንቀጽ
680/1/ስር እንዲከላከል ትዕዛዝ እንዲሰጥልን በአክብሮት እንይቃለን፡፡
ተስፋዬ ጉዲሳ
በፌ/ጠ/ዐ/ህግ
ዐ/ህግ

ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይ/ሰ/ችሎት
አዲስ አበባ
የፍ/መ/ቁ ፡- 260021
አ/ከ/ም/ፅ/መ/ቁ ፡-089/13
የአ/ከ/ፖ/ወ/መ/ቁ ፡- 185/12/13
ይግባኝ ባይ ፡- የፌ/ጠ/ዐ/ህግ
መልስ ሰጭ ፡- ዘላለም ሙላቱ ባዳ እድሜ 39 ዓመት
አድ፡ ን/ስ/ላ/ክ/ከ ወረዳ 2 የቤ/ቁ ተከራይ
በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 189/1/ መሠረት የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ
1/ የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ

‘’ለህግ ፣ለፍትህ፣ለርትዕ !’’


ዘ/መ ፋክስ ፖ.ሣ.ቁ ስልክ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
FAX 0115-51-77-75 P.O.Box 1370 Tel. 0112-78-12-91 Addis Ababa-Ethiopia
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ
የአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት
The Federal Democratic Republic of Ethiopia
Attorney General
Addis Ketema Office

ቁጥር
Ref. No
ቀን
Date
ይግባኝ ባይ በቁጥር 089/2013 ፅፎ ባቀረበው የክስ አቤቱታ መልስ ሰጭ በሚወጣበት ወይም ለባንክ
በሚቀርብበት ቀን በቂ ገንዘብ አለመኖሩን እያወቀ በቀን 23/12/10 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 5፡ዐዐ ሰዓት አካባቢ
ለግል ተበዳይ ተሰማ ቱፋ የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ቼክ ቁጥሩ A1319284 የሒሳብ ቁጥሩ
00110113435-87 በሆነ ቼክ 1,000,000/አንድ ሚሊዮን /ብር በቀን 23/08/2012 ዓ.ም የሚመነዘር በማለት
ፅፎና ፈርሞ ከሰጠው በኋላ ቼኩ በቀን 14/12/2012 ዓ.ም ለክፍያ ሲቀርብ በቂ ገንዘብ የለውም የተባለ በመሆኑ
የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ አውጥቷል የሚል ክስ አቅርቧል ፡፡ የስር ፍ/ቤቱም በፍ/መ/ቁ 260021 ጉዳዩን
አከራክሯል ፡፡ በዚህም መሠረት የመ/ሰጭን መቃወሚያ በማለፍ ክስ ከተሰማ በኋላ መ/ሰጭ ክደው
ስለተከራከሩ የዐ/ህግ ምስክሮች ቀርበው ተሰምተዋል ፡፡ የስር ፍ/ቤት መ/ሰጭን እንዲከላከል ብይን ከሰጠ በኋላ
መ/ሰጭ የመ/ምስክሮችን አቅርቦ አስምቷል፡፡
የስር ፍ/ቤቱም በቀን 26/04/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት መ/ሰጭን የተከሰሰበትን ድንጋጌ ማለትም የወ/ህ/ቁ
693/1/ን ወደ 693/2/ በመቀየር በቸልተኝነት ጥፋተኛ በማለት በብር 1500/አንድ ሺህ አምስት መቶ/
እንዲቀጣ ወስኗል ፡፡
ይህ የይግባኝ አቤቱታም ይህን ውሳኔ ማለትም መ/ሰጭ አስቦ የሚይዝበት በቂ ገንዘብ የሌለው ቼክ በመስጠት
ተከሶ እያለ የስር ፍ/ቤት ወደ ቸልኝነት በመቀየር ጥፋተኛ መባሉ አግባብነት የሌለው በመሆኑ የቀረበ ነው፡፡

2/ የቅሬታ ነጥቦች
1/ ከክርክሩ እንደምንረዳው መ/ሰጭ ቼኩ ላይ የገንዘብ መጠን ፅፎ እና ፈርሞ ለግል ተበዳይ መስጠቱን
ሳይክድ በቼኩ ላይ ግን ቀን አለመኖሩን ብቻ እንዲሁም ቼኩን የግል ተበዳይ ዕቁብ ሰብሳቢ በመሆኑ
ለመተማመኛ የሰጠው መሆኑን እና ቀንና ዓ/ም አልፃፈኩም በማለት ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍ/ቤት
በተደረገው ክርክር ፍ/ቤት ቼኩ ለመተማመኛ መስጠቱ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እና ቀንና ዓ/ም
ሳይፅፍ መስጠቱ ግን ቸልተኝነት እንጂ ታስቦ የሚፈፀም ወንጀል አለመሆኑን ገልጾ ፍርድ ሰጥቷል ይሁንና
መ/ሰጭ ክፍያውን በስማቸው አዘው የገንዘብ መጠን አስቀምጠው እና ፊርማ ፈርመው ቼክ ሰጥተው
እያለ ቀን እና ዓ.ም አልተፃፈም በሚል ምክንያት ቸልተኛ ብሎ ፍርድ መስጠት የወ/ህ/ቁ 693/1/ ስር
የተመለከተውን የወንጀል ፍሬ ነገር መቋቋሚያ ያላገናዘበ እንዲሁም የቼኩን ህጋዊነት በተመለከተ ፍ/ቤቱ
ባላከራከረበት እና መ/ሰጭም ባልካደበት ሁኔታ ፍ/ቤቱ ድንጋጌውን ቀይሮ በቸልተኝነት ጥፋተኛ ማለቱ

‘’ለህግ ፣ለፍትህ፣ለርትዕ !’’


ዘ/መ ፋክስ ፖ.ሣ.ቁ ስልክ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
FAX 0115-51-77-75 P.O.Box 1370 Tel. 0112-78-12-91 Addis Ababa-Ethiopia
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ
የአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት
The Federal Democratic Republic of Ethiopia
Attorney General
Addis Ketema Office

ቁጥር
Ref. No
ቀን
Date
ተገቢ ካለመሆኑ በላይ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/ሰሚ ችሎት በፍ/መ/ቁ 980660 በቀን 17/09/2007 ዓ.ም በዋለው
ችሎት እና በፍ/መ/ቁ 126646 በቀን 28/3/2010 አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተሰጠበትን ጉዳይ ባለገናዘበ
መልኩ የተሰጠ ፍርድ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው፡፡
3/ የምንጠይቀው ዳኝነት
የስር ፍ/ቤት በይግባኝ ችሎት ክስ የቀረበበትን የወ/ህ/ቁ 693/1/ን በመየቀር በወ/ህ/ቁ 693/2/ መሠረት
ጥፋተኛ በማለት የተሰጠውን ፍርድ በመሻር የተከበረው ፍ/ቤት መ/ሰጭን በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር
ጥፋተኛ እንዲወስንልን በማለት እንጠይቃለን ፡፡

ዳንኤል ፀጋዬ
በፌ/ጠ/ዐ/ህግ ዐ/ህግ

በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት


ለአራዳ ይግባኝ ሰሚ ችሎት
አዲስ አበባ
የፍ/መ/ቁ ፡- 85922

‘’ለህግ ፣ለፍትህ፣ለርትዕ !’’


ዘ/መ ፋክስ ፖ.ሣ.ቁ ስልክ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
FAX 0115-51-77-75 P.O.Box 1370 Tel. 0112-78-12-91 Addis Ababa-Ethiopia
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ
የአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት
The Federal Democratic Republic of Ethiopia
Attorney General
Addis Ketema Office

ቁጥር
Ref. No
ቀን
Date
አ/ከ/ም/ፅ/መ/ቁ ፡-03465/11/13
የፖ/ወ/መ/ቁ ፡- 1019/11
ይግባኝ ባይ ፡- የፌ/ጠ/ዐ/ህግ
ተጠሪ ፡- 1 ኛ ብርቱካን አባይነህ
2 ኛ ሜሮን ወ/ሚካኤል
3 ኛ ናትናኤል ወ/ሚካኤል
 በፌ/ጠ/መ/ደ/ፍ/ቤት የአ/ከ/ክ/ከ መድብ 1 ኛ ወንጀል ችሎት በሰው ውሳኔ ላይ የቀረበ የይግባኝ
አቤቱታ ነው፡፡
 ይግባኝ አቤቱታው ግዜው ጠብቆ የቀረበ ነው
 ፍ/ቤቱ ይግባኙን ተቀብሎ ለማየት ስልጣን አለው
የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ
ከሣሽ ዐ/ህግ በቀን 10/10/2013 ዓ.ም ፅፎ ባቀረበው የክስ አቤቱታ ተከሣሾች የወንጀለ ህጉን አንቀፅ 32/1/ሀ/
እና 555/ሐ/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በግል ተበዳይ ላይ ድብደባ በመፈፀመ የግል ተበዳይ
በፈፀም የግል ተበዳይ ዳሌ አጥንት ስብራት በማድረሳቸው በጋራ በመሆን የከባድ አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል
ፈፀሟል በማለት የከሰሰ ሲሆን ፍ/ቤቱም ተከሣሾች አስቅርበው ክሱ ተሰምቶ ተከሣሾች ወንጀሉን
አልፈፀምንም ብለው በመከራከራቸው የዐ/ህግ ምስክር ተሰምቶ ተከሣሾች በተከሰሰቡት ድንጋጌ ስር ሊከላከል
ይገባል ተስምቶ በማለት ብይን መስጠቱ ይታወሳል ፡፡ ተከሣሾችም 03 የግራ መ/ምስክር ከሰማ በኋላ በቀን
21/07/13 በዋለው ችሎት ተከሣሾች የቀረበባቸውን ክስ እና ማስረጃ የተከለከሉ በመሆኑ በወ/ስ/ስ/ህግ አንቀፅ
149/2/ መሠረት በነፃ ሊሰናበቱ ይገባል በማለት ለይግባኝ ቅሬታ መነሻ የሆነውን ውሳኔ ሰጥቷል ፡፡

የስር ፍ/ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ላይ ያለን ቅሬታ በአጭሩ


1/ የተከሣሽ ምስክሮች የዐ/ህግን ማስረጃ ያልተከላከሉ ስለመሆኑ ፡- ተከሳሾች 03 መ/ምስክር አቅርበው
ያሰሙ ሲሆን 1 ኛ ምስክር ወንጀሉ ተፈፀመ በተባለበት ቀን ጠዋት ወደ መርካቶ የሄዱ መሆኑን በመግለፅ
ከጠዋቱ 1፡2 ዐ ሰዓት ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ የግል ተበዳይ ወንድም 3 ኛ ተከሣሽን በድንጋይ ሲያባርር
ማየታቸውን እና 2 ኛ ተከሣሽ ደግሞ በር ላይ ቆመው የነበሩ መሆኑን በመግለፅ በወቅቱ የግል ተበዳይ የግል
ንብረታቸው የሆነውን ንብረት በመስባበር ላይ ሳሉ ወድቀው የተጎዱ መሆኑን መስክረዋል ፡፡ በመስቀለኛ ጥያቄ

‘’ለህግ ፣ለፍትህ፣ለርትዕ !’’


ዘ/መ ፋክስ ፖ.ሣ.ቁ ስልክ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
FAX 0115-51-77-75 P.O.Box 1370 Tel. 0112-78-12-91 Addis Ababa-Ethiopia
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ
የአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት
The Federal Democratic Republic of Ethiopia
Attorney General
Addis Ketema Office

ቁጥር
Ref. No
ቀን
Date
ተጥይቀው ሲመለሱ እርሳቸው ወደ ቦታው የደረሱት ፀቡ ከተጀመረ በኋላ መሆኑን የጉዳዩን መነሻ የማያውቁ
መሆኑን መስክርዋል ፡፡ ይህ የሚያሳየው ምስክሯ ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ላይ በቦታው ቆማ ነበረች
ብለዋል ፡፡ እኝህ 2 ኛ ምስክርም በተሳሳይ የጉዳዩን መነሻ የማያውቁ እና ፀቡ ሲጀመር በቦታው ያልነበሩ
መሆኑን መስክረዋል ፡፡ 3 ኛ መ/ምስክርም በተመሳሳይ መልኩ ከክሱ ላይ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 1፡3 ዐ ላይ
የግል ተበዳይ ወንድም 3 ኛ ተከሣሽን ሲያባርር ያየ መሆኑን እና ወደ ፀቡ ቦታ ስሄድ የግል ተበዳይ ንብረት
እያወደሙ ማየታቸውን ገለፀው የፀቡን መነሻ ያላዩ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
የመ/ምስክሮች የምስክርነት ቃል ስንመለከት ሶስቱም ምስክሮች ፀቡ ከተፈጠረ /ወይም ወንጀሉ ከተፈፀመ
/በኋላ ወደ ቦታው የመጡ መሆኑ የገለፀ በመሆኑ እነሱ ከመምጣታቸው በፊት የተፈፀመውን ነገር የማያውቁ
መሆኑን እና የፀቡን መነሻ ያላዩ መሆኑን የገለፁ በመሆኑ በተከሣሾች ላይ የቀረበውን ክስ እና ማስረጃ
አልተከላከሉም ፡፡ በሌላ በኩል ዐ/ህግ ወንጀሉ ተፈፅሟል በማለት ከስ የቀረበው ከንጋቱ 12፡45 በመሆኑ እና
3 ቱም ምስክሮች ወደ ፀቡ ቦታ መጥተናል ያሉት ከጠዋቱ 1፡2 ዐ በኋላ መሆኑ ሲታይ ምስክሮቹ ፀቡ
በተፈጠረበት ሰዓት በቦታው ያልነበሩ መሆኑን ያሳያል ፡፡
ስለሆነም የመ/ምስክሮቹ ወንጀሉ የተፈፀመበት ቦታ ላይ የደረሱት ወንጀሉ ተፈፀመ ከተባለበት በኋላ ከ 35
ደቂቃ በኋላ በመሆኑ እና ምስክሮቹም እኛ በመድረሳችን በፊት የተፈፀመውን አናውቅም ብለው መስክረው
እያለ የስር ፍ/ቤት ተከሣሾች የቀረበባቸው ክስ ተከላክለዋል ማለቱ ከፍተኛ የማስረጃ ስህተት የተፈፀመበት
መሆኑን ያመለክታል ፡፡
2/ የስር ፍ/ቤቱ በግምት ላይ ተመስርቶ ውሳኔ የሰጠ ስለመሆኑ ፍ/ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት መሠረት ያደረገው
በተበዳይ ላይ የደረሰው ጉዳት በድብደባ ሳይሆን ንብረት በማወድም ላይ ሳሉ በመውደቃቸው ነው የሚል ነው፡፡
ዐ/ህግ የግል ተበዳይ ላይ የዳሌ አጥንት ስብራት ጉዳት ሊደርስ የቻለው በተከሣሾች በተፈፀመባቸው ድብደባ
መሆኑን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጦ ሳለ የተከሳሾች 1 ኛ ምስክር ተበዳይ የተጉዱት የለስላሳ ሳጥን
ሲወረውር ወድቀው ነው ብለው ግምታቸውን መናገራቸውን ብቻ መሠረት በማደረግ በተበዳይ ላይ ደረሰ
የተባለው ጉዳት ሊደርስ የቻለው በመውደቃቸው ነው እንጂ በተከሳሾች ተግባር አይደለም ማለት ተገቢነት
የጎደለው እና በማስረጃ ላይ ያልተመሰረተ ነው፡፡

የምንጠይቀው ዳኝነት

‘’ለህግ ፣ለፍትህ፣ለርትዕ !’’


ዘ/መ ፋክስ ፖ.ሣ.ቁ ስልክ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
FAX 0115-51-77-75 P.O.Box 1370 Tel. 0112-78-12-91 Addis Ababa-Ethiopia
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ
የአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት
The Federal Democratic Republic of Ethiopia
Attorney General
Addis Ketema Office

ቁጥር
Ref. No
ቀን
Date
የስር ፍ/ቤቱ መልስ ሰጪወች የቀረበባቸውን ክስ ተከላክለዋል በማለት በነፃ ሊሰናበቱ ይገባል በማለት የወሰነው
ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች መሠረታዊ የማስረጃ ምዘና ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው
ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በመሻር ተከሣሾችን ጥፋተኛ በማለት ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲጥልባቸው
ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን ፡፡

ያሬድ ሰይፉ
በፌ/ጠ/ዐ/ህግ
ዐ/ህግ

በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት


ለአራዳ ይግባኝ ሰሚ ችሎት
አዲስ አበባ
የፍ/መ/ቁ ፡- 93533
አ/ከ/ም/ፅ/መ/ቁ ፡-01020/13
የመርካቶ ፖ/ወ/መ/ቁ ፡- 229/13

ይግባኝ ባይ ፡- የፌ/ጠ/ዐ/ህግ አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት


መልስ ሰጪ ፡- ካህሳይ ተስፋዬ ገ/እግዚአብሔር
አድ፡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 12 የቤ/ቁ ፖሊስ ካምኘ
በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ -185 እና ተከታዮቹ የቀረበ የይግባኝ ቅሬታ አቤቱታ ነው፡፡
መግቢያ
ሀ/ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን የማየት የፍሬነገርና የህግ ስልጣን አለው፡፡
ለ/ የፌ/መ/ፍ/ቤት አዲስ ከተማ መድብ ችሎት መ/ቁ 93533 ነው
ሐ/ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት ውሳኔ የሰጠው በቀን 18/8/13 ዓ.ም ነው፡፡ ግልባጭ
እንዲሰጠን የጠየቅነው በዚሁ ቀን ሲሆን ግልባጩ ኮፒ ሆኖ የተሰጠን የጠየቅነው በቀን 19/8/13 ዓ.ም ነው፡፡
መ/ ግልባጩ የተሰጠን በቀን 3/9/13 ዓ.ም ነው፡፡
ሠ/ ይግባኙ የይርጋ ጊዜው ከማለፉ በፊት የቀረበ ነው፡፡
የይግባኙ አመጣጥ ባጭሩ

‘’ለህግ ፣ለፍትህ፣ለርትዕ !’’


ዘ/መ ፋክስ ፖ.ሣ.ቁ ስልክ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
FAX 0115-51-77-75 P.O.Box 1370 Tel. 0112-78-12-91 Addis Ababa-Ethiopia
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ
የአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት
The Federal Democratic Republic of Ethiopia
Attorney General
Addis Ketema Office

ቁጥር
Ref. No
ቀን
Date
የአሁን ይግባኝ ባይ በመልስ ሰጪ ላይ በስር ፍ/ቤት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 555/ለ/ን በመተላለፍ
መልስ ሰጪ የግል ተበዳይ በላይ አብሽሮን በቦክስ በመምታት የላይኛው አንድ የመንጋጋ ጥርሱ እንዲወልቅ
በማድረጉ ከሰው አካል ህወሳቶች መካከል አንዱን አጉድሏል በማለት በሰው አካል ላይ ከባድ ጉዳት ማድረስ
ወንጀል ክስ ለችሎቱ አቅርቦ ችሎቱም የከሳሽን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ከሰማና ከመራው በኋላ
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 24 በመ/ቁ 168166 የሰጠውን የህግ ትርጉም መነሻ በማድረግ ተከሣሹ
ጉዳቱን ያደረሰው መሳሪያ ተጠቅሞ ባለመሆኑ በወ/መስ/ስ/ህ/ቁ 113/2/ መሠረት እንዲከላከል ብይን የሰጠ
ቢሆንም ተከሣሹ ተከላከል ከተባለ በኋላ በዋስትና ወጥቶ ችሎት ሊቀርብ ባለመቻሉና ፖሊስም ተከሣሹን
ማግኘት ያልቻለ መሆኑን በመግለፅ ችሎቱ የተከሣሽን የመከላከል መብቱን አልፎ በወ/ህጉ አንቀፅ 556/1/ ስር
ተከሣሹ በ 6 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ ወስኗል ፡፡
ይህ ይግባኝ ሊቀርብ የቻለውም የስር ፍ/ቤት ክሱን ከወ/ህጉ አንቀፅ 55/5 ለ/ ወደ 556/1/ ስር
የቀየረበት ብይን ላይና በተሰጠው ቅጣት ላይ ቅር በመሰኘት ነው፡፡
የይግባኝ ቅሬታ ነጥቦች
የግለሰቦች አካል ደህንነት መብት በህገ-መንግስቱ ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው አለማቀፍ ስምምነቶችና
በወንጀል ህጋችን ጥበቃና ከለላ ያገኘ መብት ነው፡፡ ወደ ተያዘው ጉዳይ ስንመጣ የአሁን ይግባኝ ባይ በመልስ
ሰጪ ላይ የወ/ህጉን አንቀፅ 555/ለ/ ን በመተላለፍ በከባድ አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ክስ የመሰረተው በግል
ተበዳይ ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ ነገር ግን የስር ፍ/ቤት ክሱን ወደ
556/1/ ወደ ቀላል ጉዳት ማድረስ ወንጀል የቀረበት አግባብ የተከተለ አይደለም ፡፡ ይህንን ልንል የቻልበት
ምክንያቶች ፡-
1 ኛ/ የወንጀለ ህጉ አንቀፅ 555// አቀራረፁንና ይዘቱን ስንመለከተው የጉዳት አድራሹን የመሳሪያ መጠቀም
አለመጠቀም ሳይሆን የደረሰው ጉዳት ከባድ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ ከባድ የአካል ጉዳት
ዓይነቶችን ደግሞ የወ/ህጉ በአንቀፅ 555/ሀ/,/ለ/ና ሐ/ ስር በዝርዝርና አመልካች በሆነ መልኩ ተገልፀው
ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በወ/ህ/ጉ አንቀፅ 555/ለ/ ይመለከታል የስር ፍ/ቤትም ይህን በማለፍ የጥርስ
መውለቅ ጉዳት በተፈጥሮ ሊተካና ሊድን የማይቻል ጉድለት መሆኑን እያወቀ ክሱን ቀላል ጉዳት ነው በማለት
ወደ ወ/ህጉ አንቀፅ 556/1/ መቀየሩ ተገቢ አይደለም ፡፡
2 ኛ/ የስር ፍ/ቤት አንቀፁን ሲቀይር ለብይኑ መነሻ ያደረገው የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በቅፅ-24 በመ/ቁ
-168166 የሰጠውን ትርጉም መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የሰበር ውሳኔ ከተያዘው ጉዳይ ጋር

‘’ለህግ ፣ለፍትህ፣ለርትዕ !’’


ዘ/መ ፋክስ ፖ.ሣ.ቁ ስልክ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
FAX 0115-51-77-75 P.O.Box 1370 Tel. 0112-78-12-91 Addis Ababa-Ethiopia
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ
የአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት
The Federal Democratic Republic of Ethiopia
Attorney General
Addis Ketema Office

ቁጥር
Ref. No
ቀን
Date
የሚለያየው መሠረታዊ ልዩነት ከመኖሩም በተጨማሪ የሰበር ሰሚው ውሳኔም ከህግ አንፃር ትክክል አይደለም
፡፡ ይህንን የምንልበት ዋናው ምክንያት ሰበር ሰሚ ችሎቱ በዚህ መዝገብ ላይ ትርጉም የሰጠበት የአጥንት
ስብራት ሆኖ ሊድን በሚችል ጉዳይና በወ/ህጉ አንቀፅ 555/ሐ/ መሠረት በቀረበ ጉዳይ እንጅ ይህን የሰበር
ድንጋጌ በተመሳሳይ በመውሰድ በወ/ህጉ አንቀፅ 555/ለ/ መሠረት ለቀረቡ ክሶች ጭምር ተግባራዊ ማድረግ
የዜጐችን በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠውን የአካል ደህንነት መብት የማያረጋግጠና አሰተማሪ የሆነ ትርጉም
አይደለም ፡፡ ሌላው የወ/ህጉ አንቀፅ 555 በሙሉ የደረሰ ጉዳትን እንጅ ጉዳት አድራሹ ወንጀሉን ለመፈፀም
የተጠቀሰውን መሳሪያ ከግምት የማያስገባ በመሆኑ እጁን ተጠቅሞ በቦክስ አንድ ጥርስ መውለቅና ዓይን
ማጥፋት ወንጀል ቢፈፅምም የተጠቀመው መሳሪያ የለም በማለት ክሱ ወደ 556/1/ የሚቀየርበት ሂደት ህግን
የተከተለ አይደለም ፡፡
3 ኛ/ መሳሪያ ተጠቅሞ ከባድ አካል ጉዳት ሲያደርስና መሳሪያ ሳይጠቀም በተመሳሳይ ሁኔታ ከባድ አካል ጉዳት
ቢደርስ በተለያየ ድንጋጌ የምንቀጣ ከሆነ ለግል ተበዳዮች የፍትህ የማግኘት መብት ላይ መለያየትና በተከሣሾች
ላይ የሚጣሰው ቅጣት የተለያየ እንዲሆንና ወጥነት የሌለው የቅጣት ስርዓት እንዲዘረጋ በር የሚከፍት ነው፡፡
ይህም የወ/ህጉን ዓላማ የሚጥስ ነው፡፡
4 ኛ/ የሰውና የህክምና ማስረጃዎች በግልፅ የደረሰው ጉዳት ከባድ መሆኑን እና በወ/ህጉ አንቀፅ 555/ለ/ ስር
የሚሽፈን መሆኑን በማያሻማ መልኩ እያመለከቱ እያለ የማስረጃ ምዘና መርህን ባለተከተለ መልኩ ክሱን ወደ
556/1/ የስር ፍ/ቤት መቀየሩ መሠረታዊ የህግ ትርጉም ስህተት ያለበት መሆኑን ያሳያል ፡፡
ከይግባኝ ሰሚ ችሎቱ የምንጠይቀው ዳኝነት
ከላይ በይግባኝ ቅሬታ ነጥቦችን ያነሳናቸውን የህግና የፍሬ ነገር ክፍተቶች መሠረታዊ በመሆናቸው ፡-
1. የስር ፍ/ቤት በወ/ህጉ አንቀፅ 555/ለ/ የቀረበው ክስ በወ/ህጉ አንቀፅ 556/1/ ስር የቀየረበት ብይን
እንዲሻርልን ፡፡
2. መልስ ሰጭ በወ/ህጉ አንቀፅ 555/ለ/ ስር ጥፋተኛ እንዲባልልንና አስተማሪና ተገቢ ቅጣት
እንዲወሰንልን በማክበር እንጠይቃለን፡፡

ግርማው መኮንን
በፌ/ጠ/ዐ/ህግ
ዐ/ህግ

‘’ለህግ ፣ለፍትህ፣ለርትዕ !’’


ዘ/መ ፋክስ ፖ.ሣ.ቁ ስልክ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
FAX 0115-51-77-75 P.O.Box 1370 Tel. 0112-78-12-91 Addis Ababa-Ethiopia
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ
የአዲስ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት
The Federal Democratic Republic of Ethiopia
Attorney General
Addis Ketema Office

ቁጥር
Ref. No
ቀን
Date

‘’ለህግ ፣ለፍትህ፣ለርትዕ !’’


ዘ/መ ፋክስ ፖ.ሣ.ቁ ስልክ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
FAX 0115-51-77-75 P.O.Box 1370 Tel. 0112-78-12-91 Addis Ababa-Ethiopia

You might also like