You are on page 1of 2

ቀን - 12/02/2016 ዓ.

የጥብቅና ስምምነት ውል

ውል ሰጪ ፡ ኮ/ር ኃ/ወይን --------------

አድ. አቃ/ቃ/ክ/ከ/ወ/02/ የቤ.ቁ------

ውል ተቀባይ ፡ አቶ መውለድደግ ሥራብዙ

የጥብቅና ፍቃድ ቁጥር 5105/15

አድ. የካ/ክ/ከ/ወ/11 የቤ.ቁ-------

የውሉ አላማ

ውል ሰጭ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የፍ/ብር ችሎት በማቀርበው ክስ ውል ተቀባይ ተገቢውን ክስ በማቅረብና
በችሎት በመገኘት ተገቢውን ክርክር ለማቅረብ፣የጥብቅና የማማከር አገልግሎት ለመስጠት ነው፡፡

የውል ሰጭ ግዴታ

1. ለክርክሩ አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ማቅረብ፣

2. አጠቃላይ የአገልግሎት ክፍያ-------------- ብር ውል ሰጭ ለውል ተቀባይ ለመክፍል ተስማምቷል፡፡

3. የአከፋፈል ሁኔታ ውል ሰጭ የመጀመሪያ ክፍያ የሆነው ግማሽ ክፍያ ይህ ውል በተደረገበት ዕለት ለመክፈል የተስማማን
ሲሆን ሁለተኛው ክፍያ የመደበኛው ክስ በፍ/ቤት መስማት ተጀምሮ የግራ ቀኝ ምስክሮች ለመስማት ፍ/ቤቱ ከያዘው
ቀጠሮ 2 (ሁለት) ቀናት በፊት ቀሪ ክፍያውን ውል ሰጭ ለውል ተቀባይ ከፍሎ የሚያጠናቅቅ ሲሆን ጉዳዩ ከተከሳሽ ጋር
በሚደረግ ዕርቅ ቢቋረጥ በውሉ የተገለፀው ሙሉ ክፍያ ውል ሰጭ ለውል ተቀባይ ይከፍላል ፡፡

የውል ተቀባይ ግዴታ

1. ለውል ሰጪ የጥብቅና ሙያውን መሠረት ያደረግ በጽሁፍ ክስ ማቅረብ እና የቃል ክርክር በቀጠሮ ቀን በችሎት በመገኘት
ማቅረብ፣ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ ማስረጃዎች ጊዜው ጠብቆ ማቅረብ ነው፡፡

2. የክርክሩን ሂደት ለውል ሰጭ ወይም ለወከሉት ሌላ ሰው መረጃ መስጠት፣

ውሉ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች

1. ክርክሩ በፍ/ቤት ሲጠናቀቅ፣

2. ተዋዋይ ወገኖች ውሉን በስምምነት ማቋረጥ ይችላሉ፡፡

3. ተዋዋዮች በውሉ ላይ የተገለፁ ግዴታዎች ጊዜው ጠብቀው ካልፈፀሙ፣

4. አለመግባባት ቢፈጠር በስምምነት ወይም በእርቅ ለመፍታት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ነገርግን ከተዋዋይ ወገኖች አንዱ በውሉ
የተመለከተውን ግዴታ በተቀመጠው ጊዜ ካልተወጣ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ ይችላሉ፡፡
ውል ሰጭ ውል ተቀባይ

ኮ/ር ኃ/ወይን -------------- አቶ መውለድደግ ሥራብዙ

ውሉ ሲደረግ የነበሩ ምስክሮች

1.

2.

You might also like