You are on page 1of 7

የሰ.መ.ቁ.

130410
ታህሳስ 30 ቀን 2010 ዓ.ም

ዳኞች፡...
1.ዳኜ መላኩ
2. ተኽሊት ይመሰል
3. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)
4. ቀነዓ ቂጣታ
5. ፀሐይ መንክር

አመልካች፡-.....አቶ ሱፍያን አቡበከር ቀርበዋል


ተጠሪዎች፡-.....1.አቶ ክፍሉጋሼ የቀረበ የለም
2. ወ/ሮ ዘዉዴ መኩሪያ

ይህ መዝገብ የተቀጠረዉ ለምርመራ ሲሆን ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡


ፍርድ
ይህ የሰበር ጉዳይ የይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ለችሎቱ ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን
አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.233491
22/9/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ
እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ፡፡
የጉዳዩ መነሻ ሲታይ በአደኣ ወረዳ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች 1 ኛ የመቃወም ተጠሪ እና
የአሁን ተጠሪዎች የመቃወም አመልካቾች፣ በዚህ ችሎት የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነዉ
የቢሾፍቱ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት አጄንሲ 2 ኛ የመቃወም ተጠሪ ሆኖ
ሲከራከሩ ነበር፡፡ የጉዳዩ መነሻ የአሁን አመልካች የቢሾፍቱ ከተማ መሬት ልማትና
ማኔጅመንት አጄንሲ ላይ ባቀረበዉ ክስ መሆኑን የሥር ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል፡፡
የወረዳዉ ፍ/ቤት ከሳሽ እና ተከሳሽን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ በቢሾፍቱ ከተማ ቀበሌ 01 ክልል ዉስጥ የሚገኘዉን 9936
ካ.ሜ የሆነዉን ቦታ ተከሳሽ ለከሳሽ እንዲያስረክብ በማለት ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡
ይህን ዉሳኔ ተከትሎ የመቃወም አመልካቾች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት ባቀረቡ
አቤቱታ ለክርክር ምክንያት የሆነዉ ይዞታ የ 1 ኛ የመቃወም ተጠሪ የአቶ ሱፊያን
አቡበከር ሳይሆን የእኛ ነዉ፣ ይዞታዉ ከእጃችን ወጥቶ አያዉቅም፣ በዚህ ጉዳይ
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.163687 በ 11/2/2006 ዓ.ም ዉሳኔ
የሰጠ በመሆኑ 1 ኛ የመቃወም ተጠሪ በተሰረዘ ካርታ መክሰስ መብት የለዉም፣ ስለዚህ
የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዲሻርልን በማለት ጠየቋል፡፡
በዚህ የመቃወም ማመልከቻ ላይ 1 ኛ የመቃወም ተጠሪ አቶ ሱፊያን አቡበከር ባቀረበዉ
መልስ ለክርክር ምክንያት የሆነዉ ይዞታ በሕግ አግባብ የተሰጠኝ ነዉ፣ ካርታ
አልተሰረዘም፣ ይዞታዉ ከ 1983 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1996 ዓ.ም ግብር እየከፈልኩኝ
ስጠቀምበት ነበር፣ የመቃወም አመልካቾች መብት ሳይኖራቸዉ ነዉ ይህን መሬት
ወጥተዉ ያረሱት በማለት ተከራክሯል፡፡ 2 ኛ የመቃወም ተጠሪ የብሾፍቱ ከተማ መሬት
ልማትና ማኔጅመንት አጄንሲ ባቀረበዉ መልስ ከዚህ በፊት የ 1 ኛ ተጠሪ ካርታ መሰረዙ
ተረጋግጦ ከይዞታዉ መብት እንደሌለዉ ዉሳኔ የተሰጠ በመሆኑ የ 1 ኛ ተጠሪ ክስ
ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል፡፡
የአደኣ ወረዳ ፍ/ቤት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ ለክርክር
ምክንያት የሆነዉ ይዞታ በተመለከተ ለ 1 ኛ የመቃወም ተጠሪ የተሰጠዉ ካርታ
ያልተሰረዘ መሆኑን ማህደሩ ያረጋግጣል፣ የመቃወም አመልካቾች በይዞታዉ ላይ
ባለመብት ቢሆኑም መሬታቸዉን ለሌላ ሰዉ አሳልፈዉ የሰጠዉን አካል ከሶ ከሚጠይቁ
በስተቀር 1 ኛ የመቃወም ተጠሪ በሕገ ወጥ መንገድ ይዟል የሚያስብል ስላልሆነ፣ ከዚህ
በፊት የተሰጠዉ ዉሳኔ የሚያፈርስ ምክንያት ስለሌለ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሀ/ቁ.360/1/ መሰረት
ጸንቷል፡፡ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበለትን ይግባኝ ዉድቅ በማድረግ
የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል፡፡
የሥር የመቃወም አመልካቾች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለኦሮሚያ
ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡ ሲሆን ችሎቱ ግራ ቀኛቸዉን
በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ ከዚህ በፊት ይህ ችሎት በመ.ቁ.163687 በ 11/2/2006 ዓ.ም
በሰጠዉ ዉሳኔ ለ 1 ኛ ተጠሪ አቶ ሱፊያን አቡበከር ካርታ ቀሪ ሆኖ የተሰረዘ መሆኑን፣
ይዞታዉ በእጁ ሳይኖር ግብር መክፈሉ ብቻ ባለመብት እንደማያደርገዉ እና አቶ ሱፊያን
በዚህ ይዞታ ላይ መብት የለዉም በማለት የሥር ፍ/ቤቶችን ዉሳኔ በመሻር ዉሳኔ ሰጥቶ
እያለ የሥር ፍ/ቤቶች በዚህ ጉዳይ ድጋሚ አጣርተዉ ዉሳኔ መስጠታቸዉ መሰረታዊ
የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በማለት የሥር ፍ/ቤቶችን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል፡፡
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ፡፡
የአሁን አመልካች በ 3/5/2009 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ ለክርክር ምክንያት የሆነዉ
ይዞታ ብሾፍቱ ከተማ በሕግ አግባብ የተሰጠኝ ካርታም ተሰጥቶኝ እና ከ 1983 ዓ.ም
ስጠቀምበት የነበረ ሆኖ ሳለ፣ ለአመልካች የተሰጠ ካርታ ያልተሰረዘ መሆኑን ተረጋግጦ
እያለ፣ በዚህ ጉዳይ ከዚህ በፊት ዉሳኔ ተሰጥቷል የተባለዉ እና አሁን የቀረበዉ ክርክር
የተለያዩ ጭብጦችና ተከራካሪ ወገኖች በመሆኑ አስቀድሞ ዉሳኔ ተሰጥቷል የሚያስብል
ነገር በሌለበት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔ
መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ ኪሳራ እንዲወሰንልኝ
በማለት በዝርዝር አመልክቷል፡፡
የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን በማየት ፣በዚህ ጉዳይ ከዚህ በፊት ዉሳኔ ያገኘ ጉዳይ ነዉ
በማለት ዉሳኔ የመስጠቱን አግባብነት ለመመርመር ሲባል አቤቱታዉ ያስቀርባል
በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዲያቀርቡ ባዘዘዉ መሰረት ተጠሪ በ 5/7/2009 ዓ.ም
በተጻፈ መልስ፡ በዚህ ጉዳይ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
የሰጠዉ ዉሳኔ የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር ስህተት የሌለዉ በመሆኑ እንዲጸናልን ወጪና
ኪሳራ እንዲወሰንልን በማለት በዝርዝር ተከራክሯል፡፡ የአሁን አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል፡፡
የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ ተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችሎት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር
አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዲሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል
ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል፡፡ እንደመረመርነዉ
የአሁን አመልካች ከዚህ ቀደም ይህን ይዞታ በተመለከተ የአሁን ተጠሪዎችን ጨምሮ
በአራት ሰዎች ላይ ክስ አቅርበዉ ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.163687 በ 11/2/2006 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ ለአሁን አመልካች
የተሰጠዉ ካርታ የተሰረዘ መሆኑን በሥር ፍ/ቤት የቀረበ ማስረጃ እንደሚያረጋግጥ
በማመልከት፣ ይዞታዉም በአመልካች እጅ ሳይገባ እስከ 2004 ዓ.ም ግብር መክፈሉ
ባለመብት እንደማያደርገዉ እና አመልካች በተሰረዘ ካርታ ይዞታዉን በተመለከተ ክስ
ማቅረብ አይችልም በማለት ዉሳኔ የሰጠ መሆኑን የሥር ዉሳኔ ግልባጭ ያመለክታል፡፡
የአሁን አመልካች ከዚህ ዉሳኔ በኋላ ባቀረበዉ አዲስ ክስ ካርታዉ እንዳልተሰረዘ እና
የብሾፍቱ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ኤጄንሲ ይህን ይዞታ እንዲያስረክበዉ
ዳኝነት በመጠየቁ፣ ኤጄንሲዉ የአመልካች ክስ ተቀባይነት እንደሌለዉ በመግለጽ
ቢከራከርም፣ የሥር ፍ/ቤት ለአመልካች የተሰጠ ካርታ እንዳልተሰረዘ እና ኤጄንሲዉ
መሬቱን እንዲያስረክብ ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡ የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ ይህን ዉሳኔ
በመቃወም የመቃወሚያ ማመልከቻ አቅርበዉ ቢከረከሩም፤ የሥር ወረዳ ፍ/ቤት እና
ከፍተኛ ፍ/ቤት አስቀድመዉ ካርታዉ እንደተሰረዘ እና ለክርክር ምክንያት በሆነዉ ይዞታ
ላይ ዉሳኔ ተሰጥቷል በማለት ያቀረበዉን መቃወሚያ በማለፍ ዉሳኔ መስጠታቸዉን
መገንዘብ ይቻላል፡፡ ነገር ግን የክልል ሰበር ሰሚ ችሎት ይህን ሁኔታ በመገንዘብ የአሁን
አመልካች ከዚህ ቀደም ዉሳኔ በተሰጠበት ጉዳይ አዲስ ክስ ማቅረብ እንደማይችል
መወሰኑን የሥር ዉሳኔ ያሳያል፡፡
በዚህ መሰረት ይህ ችሎት ጉዳዩን እንደመረመረዉ የአሁን አመልካች ከዚህ ቀደም
የአሁን ተጠሪዎችን ጭምሮ በአራት ሰዎች ላይ ክስ አቅርበዉ ዉሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.5 /1/ መሰረት ድጋሚ አዲስ ክስ የሚያቀርብበት የሕግ አግባብ
የለም፡፡ የአሁን አመልካች ካርታዉ እንደተሰረዘ እና በዚህ ካርታ ይዞታዉን ለመጠየቅ
መብት እንደሌለዉ ዉሳኔ ተሰጥቶ እያለ ተከራካሪ ወገን በመቀየር የብሾፍቱ ከተማ
መሬት ልማትና ማኔጅመንት አጄንሲ ላይ ክስ ስላቀረበ ብቻ የክርክሩ ጭብጥና ተከራካሪ
ወገን ስለሚለያይ የዚህን ድንጋጌ መስፈርት አያሟላም፣ ከዚህ ቀደም ዉሳኔ ተሰጥቷል
የሚያስብል አይደለም በማለት ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም፡፡ ስለዚህ የአሁን
አመልካች ያቀረበዉ ክስ ከዚህ ቀደም ዉሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ ስለሆነ አዲስ ክስ ለማቅረብ አይችልም፡፡
ሲጠቃለል የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የአሁን አመልካች
ያቀረበዉ ክስ ከዚህ በፊት ዉሳኔ በተሰጠበት ጉዳይ ነዉ በማለት የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ
በመሻር አመልካች ያቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ በሕግ አግባብ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሕግ
ስህተት የተፈጸመበት ስላልሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል፡፡
ውሳኔ
1. የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 233491
22/9/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስላልሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.348 /1/ መሰረት
ጸንቷል፡፡
2. የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ፡፡
3. ግራ ቀኛቸዉ በዚህ ችሎት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻሉ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሩ/ለ
የሰ/መ/ቁ. 95995
ካቲት 10 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች:-
አልማው ወሌ
ዓሊ መሐመድ
ረታ ቶለሳ
አዳነ ንጉሴ
ሙስጠፋ አህመድ
አመልካች፡-ወ/ት ሞሚና ሡልጣን ኮርዋላ - ቀረቡ
ተጠሪ፡- የለም
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡
ፍርድ
ጉዳዩ የአባት ስም ይስተካከልልኝ ጥያቄን የሚመለት ሲሆን የተጀመረውም አመልካች ከአሁን ቀደም በወላጅ አባታቸው
ስም ሞሚና ሡልጣን ኮርዋላ ተብለው እና በአሳዳጊ አባታቸው ስም ሞሚና ወርቁ ይብሬ ተብለው በሁለት የአባት ስም
ይጠሩ እንደነበረ እና አሁን ግን በትክክለኛው አባታቸው ስም መጠራት እንደፈለጉ በመግለጽ ሞሚና ወርቁ ይብሬ ተብለው
መጠራታቸው ቀርቶ ሞሚና ሡልጣን ኮርዋላ ብቻ ተብለው እንዲጠሩ ይወሰንላቸው ዘንድ በመጠየቅ ለአ/አበባ ከተማ
የመ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት የክስ አቤቱታ ነው፡፡
ፍ/ቤቱም አቤቱታውን እና የቀረበውን የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኃላ አመልካች አሁንም ቢሆን ሞሚና ሡልጣን ኮርዋላ
ተብለው የሚጠሩ መሆኑን ከሰነድ ማስረጃዎቹ መገንዘብ መቻሉን ገልጾ አመልካች እየተጠሩበት ባለው የአባት ስም
እንድጠራ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም በማለት መዝገቡን በፍ.ስ.ስ.ሕ.ቁ. 231(1)(ሀ)
መሰረት በብይን ዘግቶአል፡፡
አመልካች ለዚህ ችሎት አቤቱታ ያቀረቡትም ለከተማው የበላይ ፍ/ቤቶች ያቀረቡት ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት
በማጣቱ ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ አመልካች በሁለት የአባት ስሞች እንደሚጠሩ በሰነድ ማስረጃ
በተረጋገጠበት ሁኔታ ያቀረቡት የአባት ስም ይስተካከልልኝ ጥያቄ የክስ ምክንያት የለውም ተብሎ በስር ፍ/ቤቶች ውድቅ
የመደረጉን አግባብነት ለመመርመር ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ ተደርጎአል፡፡ የጉዳዩ አመጣጥ እና የአመልካች ክርክር
ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የአመልካች የዳኝነት ጥያቄ የክስ ምክንያት የለውም ተብሎ በስር ፍ/ቤቶች
የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች
ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡
በዚህም መሰረት ፍ/ቤቶች የቀረበላቸውን የክስ አቤቱታ ተቀብለው ክርክሩን መስማት ከመጀመራቸው በፊት በክስ
ማመልከቻው ላይ የተገለጸው ጉዳይ የሚያስከስስ መሆን አለመሆኑን ማርጋገጥ የሚገባቸው መሆኑ እና በክስ ማመልከቻው
ላይ የተገለጸው ጉዳይ የማያስከስስ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የክስ አቤቱታው ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸውመመለስ የሚገባቸው
መሆኑ በፍ.ስ.ስ.ሕ.ቁ 231(1)(ሀ) ስር ተደንግጎ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው፡፡ይሁን እንጂ በዚህ ድንጋጌ መሰረት
ጉዳዩ የሚያስከስስ አይደለም ተብሎ ተቀባይነት ከማጣቱ በፊት በክስ ማመልከቻው ላይ የተገለጸው ጉዳይ
በርግጥም የማያስከስስ መሆኑ በአግባቡ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
ቀደም ሲል እንደተገለጸው የአመልካቿ የዳኝነት ጥያቄ ከአሁን ቀደም በወላጅ አባታቸው ስም ሞሚና ሡልጣን
ኮርዋላ ተብለው እና በአሳዳጊ አባታቸው ስም ሞሚና ወርቁ ይብሬ ተብለው በሁለት የአባት ስም ይጠሩ
እንደነበረ እና አሁን ግን በትክክለኛው አባታቸው ስም መጠራት እንደፈለጉ በመግለጽ ሞሚና ወርቁ ይብሬ
ተብለው መጠራታቸው ቀርቶ ሞሚና ሡልጣን ኮርዋላ ብቻ ተብለው እንዲጠሩ እንዲወሰንላቸው ሲሆን
ይጠሩበት በነበሩት ሁለቱም የአባት ስሞች የተዘጋጁ ወይም ከመንግስታዊ ተቋማት የተሰጡ ሰነዶችንም
በማስረጃነት ማቅረባቸውን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል፡፡
በመሰረቱ እያንዳንዱ ሰው አንድ የቤተዘመድ ስምና አንድ ወይም ብዙ የግል ስሞች እና የአባት ስም
እንደሚኖረው፣እንዲሁም ለልጁ የአባት ስም የሚሆነው የአባቱ የግል ስም እንደሆነ በፍ.ሕ.ቁ.32(1) እና 36(1)
ድንጋጌዎች ተመልክቶአል፡፡
አንድ ሰው በተለያዩ ምክንያቶች በአባቱ ብቻ ሳይሆን በአሳዳጊው ስም ጭምር ሊጠራ የሚችልባቸው
አጋጣሚዎች መኖራቸው የሚታወቅ ሲሆን እንዲህ ዓይነቱ ሰው ተገቢ ሆኖ ባገኘው ጊዜ በአሳዳጊው ስም ጭምር
መጠራቱ ቀሪ ሆኖ ከላይ በተጠቀሰው የፍትሐብሔር ሕጉ ድንጋጌ መሰረት በአባቱ ስም ብቻ እንዲጠራ
የመወሰን መብት ያለው በመሆኑ ይህንኑ መብቱን በፍርድ ለማረጋገጥ የሚያቀርበው የዳኝነት ጥያቄ የክስ
ምክንያት የለውም የሚባልበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም፡፡
አመልካች ክሱን ያቀረቡት በሚጠሩበት የአሳዳጊያቸው ስም የተሰጡ ሰነዶችን ወደሚጠሩበት አባታቸው ስም
በሕግ አግባብ ለማስቀየር እና እነዚሁ ሰነዶች በሚሰጡት መብት ለመገልገል ጭምር መሆኑን ከክርክራቸው ይዘት
መገንዘብ የሚቻል በመሆኑ ሞሚና ወርቁ ይብሬ ተብለው መጠራታቸው ቀርቶ ሞሚና ሡልጣን ኮርዋላ ብቻ
ተብለው እንዲጠሩ ባቀረቡት የዳኝነት ጥያቄ መሰረት ሊሰጥ የሚችለው ውሳኔ በአመልካቿ መብት ላይ
የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት አይኖርም ሊባል የሚችል ሆኖ አላገኘነውም፡፡ ሲጠቃለል ክሱ የቀረበለት የአ/አበባ
ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት የቀረበለትን የክስ ማመልከቻ እና ማስረጃ መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት የሚገባው
ሆኖ እያለ በክስ ማመልከቻው ላይ የተገለጸው ጉዳይ የሚያስከስስ አይደለም በማለት ሲል የሰጠው እና
በከተማው የበላይ ፍ/ቤቶች በትዕዛዝ የፀናው ብይን የክስ ማመልከቻውን እና የፍ.ስ.ስ.ሕ.ቁ 231(1)(ሀ) ድንጋጌን
ይዘትና ዓላማ በአግባቡ ያላገናዘበ እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ
ተሰጥቶአል፡፡
ዉሳኔ
1. አመልካች ያቀረቡት የክስ ማመልከቻ የክስ ምክንያት የለውም ሲል መዝገቡን በፍ.ስ.ስ.ሕ.ቁ. 231(1)(ሀ) መሰረት
በመዝጋት የአ/አበባ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 2908 በ 07/12/2005 ዓ.ም. የሰጠው እና በከተማው ፍ/ቤቶች
ይ/ሰሚ እና ሰበር ችሎቶች እንደቅደም ተከተሉ እና በመ.ቁ. 20742 በ 27/12/2005 ዓ.ም.እና በመ.ቁ.21123
በ 27/02/2006 ዓ.ም. በትዕዛዝ የፀናው ብይን በፍ.ስ.ስ.ሕ.ቁ. 348(1)መሰረት ተሽሮአል፡፡
2. አመልካች ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ላይ የተገለጸው ጉዳይ የክስ ምክንያት ያለው መሆኑን ተገንዝቦ ጉዳዩን
በማንቀሳቀስ የቀረበለትን የክስ ማመልከቻ እና ማስረጃ መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዳዩ
በፍ.ስ.ስ.ሕ.ቁ. 341(1)መሰረት ወደ አ/አበባ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት እንዲመለስ ወስነናል፡፡
3. በዚሁ መሰረት ይፈጸም ዘንድ የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይላክ፡፡
4. ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቶአል፡፡
File no: 030410
Diseembar 30, 2010

Gars:
1. Diiri addeege
2. Waxay u egtahay cirfiid
3. Teferi Gebre
4. Cake maalin
5. Qorax dhaca

Codsade: - Mudane Sufian Abubaker


XIRIIRADA: 1. Majiro wax sharci ah oo loogu talagalay Mr. Klugesche
2. Marwo Zoucher McCoy
Rikoorkan waxaa loo Mudeyay baaritaan go’aankan soo socda ayaan kasoo saarnay.
                                Go'aan
Jabintaani waxay quseysaa dacwada muranka badan leh iyo kiiska hada jira
Codsadaha Maxkamadda Sare ee Gobolka Oromada, Kiiska Lambar 233491
22/9/2008 maxaa yeelay amarkan waxaa sameeyay qalad sharciga aasaasiga ah
Adiga ayay ku jirtaa inaad baartid cabashadaada in wax laga beddelo.
Iyada oo ku saleysan kiiska, Qareenka Rafcaanka Qareenka 1aad ee Qareenka Rafcaanka Qeybta
Racfaanka iyo
Codsadayaasha diida sheegashada hada jirta, ee aan qayb ka aheyn murankan
Wakaaladda Horumarinta iyo Maareynta Dhulka ee Bishoftu ee Magaalada Wakiilka 2aad ee
Mucaaradka
Waxay ku doodayeen. Asal ahaan kiiska ayaa ah tilmaameha hadda ee horumarinta dhulka
magaalada Bishoftu iyo
Nuqul ka mid ah go'aanka hoose wuxuu muujinayaa eedeymaha Hay'adda Maareynta.
Maxakamada wareega waxay taageertay go'aankii dacwoodaha ee dib loogu celiyay dacwoodaha
dacwoodaha, oo ku yaal 9936 kiloomitir kiiloomitir, oo ku yaalo Kebeleufu Kuntale 01 Gobolka.
Rafcaan qaadayaasha sida ku xusan go’aankan waxaa la soo saaray iyadoo la raacayo Qeybta
358 ee Sharciga
Codsi ku saabsan Haysashada Khilaafka 1aad ee Kadaba Sheegashada, Mudane Sufian
Waa annaga, ma ahan Abuu Bakar, nuxurka ayaa ka baxsan gacantayaga, kiiskan
Maxkmadda Rafcaanka ee maxkamada sare ee oromada lambar 163687 Dec 11, 2006
Wakiilka 1aad ee Mucaaradka xaq uma leh inuu dacwado khariidad la tirtiray, sidaa darteed
Wuxuu codsaday in go'aanka laga noqdo.
Codsiga waxaa gudbiyay Sufian Abu Bakr 1aad ee dacweysanaha 1aad
A: Waxyaabaha ku saabsan mowduuca muranku waa sharci ahaan aniga ayaa i aqoonsaday,
Khariidadda
Lama tirtirin, waxaan bixinayay canshuur ilaa iyo 1983 ilaa 1996
Waan istcimaalayay, sheeganayasha xaq uma lahan inay adeegsadaan dhulkan
Wuxuu sheeganayaa inuu baxo oo iska iloobo. Wakiilka 2-aad ee Mucaaradka Dhulka
Magaalada Bishoftu
Mawduuca doodda iyo dooda sababta oo ah waxay dacwaynaysaa Hay'adda Horumarinta iyo
Maareynta
Ma buuxiyo shuruudaha Xeerkan, maadaama ay go’aamiyeen xisbi
Dooddiisa ah inuusan danaynayn waa mid aan la aqbali karin. Sidaas xaadirka ah
Dacwad-ooguhu ma cusboonaysiin karo maxaa yeelay waa arrin horay loo go'aansaday.
Soo Koobid: Codsadaha Kiisaska Maxkamadda Sare ee Gobolka Oromada
Go'aanka maxkamadaha hoose ayaa ah in dacwadaha ka dhanka ah iyada horay loo go'aansaday
Go'aanka xigta waxaa la sameeyay maxaa yeelay go'aanka lagu tuurayo mooshinka dacwad-
oogaha ee xil ka qaadista dacwadaha ka dhanka ah dacwoodaha ma ahayn khalad aasaasi ah oo
sharciga ah.
Waa salaaman tihiin
Amar
1. Maxkamadda Sare ee Gobolka Oromada 233491
22/9/2008, amarkiisa kuma xadgudbayn sida uu dhigayo qodobka 348 (1) sababta oo ah ma
ahayn qalad sharciyeed oo asaasi ah.
2. Ka hel koobiga go'aankan maxkamadaha.
3. Gacanta bidix wuxuu sheegan karaa kharashyada iyo khasaaraha ay maxkamadani soo food
saartay.
Diiwaanka waa la xiray.
Waxay leedahay saxiixa shan garsoore oo aan la aqrin

You might also like