You are on page 1of 4

የመ/ቁ 301347

ቀን 02/08/2014 ዓ/ም

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት


ለልደታ ምድብ 14 ኛ ፍ/ብሔር ችሎት
አ/አበባ
ከሳሽ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
አድራሻ አ/አበባ
ተከሳሽ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ
አድራሻ አ/አበባ
ከሳሽ ባቀረቡት የክስ አቤቱታ ላይ የተሰጠ መልስ
በከሳሽ የቀረበ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
ከሳሽ በክሱ ላይ ተከሳሽ ናቸዉ ብሎ ያቀረበዉ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ነዉ ብለዋል፡፡
ነገር ግን በፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 በአንቀፅ 3(1) እና በአንቀፅ 6(40)
መሰረት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህግ ሰዉነት ያለዉ በመሆኑና በኮሚሽኑ ስምም እንደሚከስ እና
እነደሚከሰስ በግልፅ ያስቀምጣል፡፡ስለሆነም ከሳሽ መክሰስ ያለባቸዉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን እንጅ
የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል የህግ ሰዉነትም ሆነ በራሱ ስም የመከሰስም ሆነ የመክሰስ የህግ
ስልጣን ስለሌለዉ የተከበረዉ ፍ/ቤት ክሱን ዉድቅ እንዲያደርግልን፡፡ፍ/ቤቱ ይህን የሚያልፈዉ ከሆነ
ከሳሽ ክሳቸዉን አሻሽለዉ በትክክለኛ አድራሻ እንዲያስተካክሉ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን ስንል እንጠይቃለን፡፡
ፍ/ቤቱ በተከሳሽ የቀረበዉን መቃወሚያ የሚያልፈዉ ከሆነ

 ከሳሽ በአቤቱታቸዉ ላይ በተራ ቁጥር 1.1 እና 1.2 ላይ የተጠቀሰዉ የቤት አድራሻ ለመፈለግ ጥረት
ብናደርግም ከሳሽ የጠቀሱት አድራሻ በአሁኑ የአ/አበባ ከተማ አደረጃጀት በቀበሌ ደረጃ የተዋቀረ
አድራሻ ባለመኖሩ ፈልገን ለማግኝት ተቸግረናል፡፡ሆኖም ከሳሽ እንደሚሉት ፌደራል ፖሊስ ወንጀል
መከላከል ዘርፍ ይህንን ከላይ የተጠቀሰዉን ቤት በህገ-ወጥ ተይዞብኛል የሚሉት ትክክል አይደለም ፡፡
እኛ በ/አበባም ይሁን በክልል የሚገኙ የፖሊስ ሰራዊቶቻችንን የምናስቀምጠዉ ከቤቶች
ኮርፖሬሽንም ይሁን ከግለሰቦች ባለቤቶች ጋር ህጋዊ ዉል ፈፅመን እንጅ ኮሚሽኑ እያወቀ በህገ-ወጥ
የመንግስትም ይሁን የግል መኖሪያ ቤትን ይዘን አናዉቅም ይህንን የተባለዉን ቤትም አልያዝንም፡፡
የተከበረዉ ፍ/ቤት ቦታዉ ተይዟል ቢባል እንኳ መጠየቅ ያለባቸዉ እዛዉ ቦታዉ ላይ ይዘዉት
የተቀመጡትን ግለሰቦች እንጅ ተከሳሽንም አይደለም፡፡
 ሌላዉ በተራ ቁጥር 1.3 ላይ ከሳሽ የገለፁት ወደ ዋናዉ መስሪያ ቤት የፃፉት 01 ገፅ ደብዳቤ
በክሳቸዉ ላይ አያይዘዋል፡፡ሆኖም በፃፉት መሰረት ሄዶ ለማረጋገጥ ቢሞከርም ከሳሽ ተያዘብኝ
የሚሉት ቤት በእኛ በፌደራል ፖሊስ ሰራዊት እንዳልተያዘ እና የሚሉትም አካባቢ የፌደራል ፖሊስ
ሰራዊት እንዳልተቀመጠ እየታወቀ ይህንን ክስ ማቅረባቸዉ ተገቢ አይደለም፡፡አባሎቹ ተቀምጠዋል
ቢባል እንኳ ደብዳቤዉ የተፃፈዉ በቀን 21/09/2012 ዓ/ም ሆኖ እያለ ከሳሽ በክሳቸዉ ላይ ከሐምሌ
01/2013 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 30/2013 ዓ/ም ድረስ እና ከታች በጠየቁት ዳኝነት ላይ ደግሞ
ከመስከረም 1/2013 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 30/2013 ዓ/ም በመያዙ ኪሳራ ደርሶብናል በማለት
ከደብዳቤዉ ጀምሮ እስከ ተለያዩ ቀናት ድረስ የጠቀሱት እርስ በርሱ የሚጋጩ ወራችና
ዓመተምህተቶችን በመጥቀስ የማይገባቸዉን ክፍያ ከመጠየቃቸዉ በተጨማሪ ከሳሽ መቼና እንዴት
እንደተያዘባቸዉ እንኳ በትክክል ሊገልፁ ባለመቻላቸዉ የተከበረዉ ፍ/ቤት ክሱን ዉድቅ በማድረግ
በነፃ እንዲያሰናብተን ስንል እንጠይቃለን፡፡
 ከሳሽ በተራ ቁጥር 1.4 ላይ ያቀረበዉ አቤቱታ ከሐምሌ 01/2013 ዓ/ም እስከ ታህሳስ
30/2014 ዓ/ም ድረስ ኪሳራ እንደደረሰባቸዉ ገልፀዋል፡፡ይህ ማለት ከሳሽ ቦታዉ መቼ
እንደተያዘባቸዉ ካለመወቃቸዉ በላይ ከታች ተራ ቁጥር 2.2 ላይ እንዳሉት ከመስከረም
01/2013 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 30/2013 ዓ/ም ድረስ ተይዞባቸዉ ከሆነ ከላይ በተራ ቁጥር 1.4 ላይ
ደግሞ ቀን ሲጠቅሱ ከሐምሌ 01/2013 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 30/2014 ዓ/ም ድረስ ተይዞብናል ተብሎ
አቤቱታ ቀርቧል፡፡ይህ ማለት በመሃል ከታህሳስ 30/2013 ዓ/ም እስከ ሐምሌ 01/2013 ዓ/ም ድረስ
ለ 08 ወራት በማን ስር ነበር?ወይስ የፖሊስ ሰራዊቶቹ ለቀዉ ከ 08 ወር በኋላ ተመልሰዉ ይዘዉት
ነዉ?ወይስ በሌላ ሰዉ ተይዞ ነዉ? የሚለዉን በትክክል ያላስረዱ በመሆኑና በክሱ አቤቱታ በተራ
ቁጥር 1.4 እና በጠየቁት ዳኝነት ተራ ቁጥር 2.2 ላይ ያለዉ የወራና የዓመተምህረት አቆጣጠር
እርስበርሱ የሚጋጭ ስለሆነ የተከበረዉ ፍ/ቤት ይህንን እንዲያይልንና እንዲመረምርልን፡፡
 ከሳሽ በተራ ቁጥር 1.5 ላይ ያቀረበዉ አቤቱታ ተከሳሽ ሁልጊዜም ቢሆን የሰራዊት መኖሪያ
ካምፕም ይሁን የተለያዩ ፅ/ቤቶች ከመንግስትም ይሁን ከግል ባለቤቶች ቦታ ስንይዝ በሃገራችን
የዉል ህግ መሰረት በኪራይ ዉል እንጅ ከሳሽ እንደሚሉት በማን አለብኝነት የማንንም ንብረት
ሰብረን ልንገባ አንችልም፡፡የተከበረዉ ፍ/ቤት እንደሚያዉቀዉ በአ/አበባም ይሁን በተለያዩ የክልል
ከተሞች ከሳሽ የሚያስተዳድራቸዉን ቤቶችም ይሁን ሌሎች ንብረቶች ከመጠበቅና ከወንጀል
ድርጊቶች ከመከላከል ዉጪ ከሳሽ እንደሚሉት በህገ-ወጥና በማን አለብኝነት እንደማንይዝ ማንም
ተቋምም ይሁን ግለሰብ የሚያረጋግጠዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ስለዚህ ከሳሽ በህገ-ወጥ መንገድ ተያዘብኝ
የሚለዉ ንብረት እኛ ያልያዝንና በዚህም ክስ ከዉል ወጪ ኃላፊነትም ይሁን በህገ-ወጥ ቦታ
መያዝም ልንጠየቅ አይገባም፡፡
 ሌላዉ ከሳሽ ከላይ በክሳቸዉ ላይ ቤቱን ለሌላ 3 ኛ ወገን አስተላልፈን እያለ ተከሳሽ ይህንን ያራሱ
ያልሆነዉን ንብረት ሊይዝ አይገባም የኪራይ ኪሳራም ደርሶብኛል የሚለዉ በመጀመሪያ ደረጃ
ከተባለዉ ግለሰብ ጋር ህጋዊ ዉል ተደርጎ ቤቱ በስሙ እንዲተላለፍ ከተደረገ በኋላ ከዚህ
ቀን፣ወር፣ዓ/ምህረት ጀምሮ ይህን ያህል ገንዘብ በወር መክፈል አለበት የሚለዉ ህጋዊ የሆነ ዉል
ባልተደረገበትና ቤቱ በህግሒደት ባልተላለፈበት ከሳሽ ይህን ያህል ኪሳራ ደርሶብኛልና ሊከፈለኝ
ይገባል ብሎ ክስ ማቅረቡ ትክክለኛ የህግ ስርዓት ያልተከተለ በመሆኑ የተከበረዉ ፍ/ቤት ይህንንም
በአግባቡ እንዲያይልና እንዲመረምርልን እንጠይቃለን፡፡

በመሆኑም የተከበረዉ ፍ/ቤት የምንጠይቀዉ ዳኝነት

1.ከሳሽ በህግ ሰዉነት ያልተሰጠዉን የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ የከሰሱ በመሆኑ ክሱን ዉድቅ
እንዲያደርግልን ይህን የሚያልፈዉ ከሆነ በዚህ ጉዳይ መጠየቅም መከሰሰም ያለበት በአዋጅ ቁጥር 720/2004
በአንቀፅ 3(1) እና በአንቀፅ 6(40) መሰረት የኢትዬጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን እንጅ ወንጀል መከላከል
ዘርፍን ባለመሆኑ የተከበረዉ ፍ/ቤት ከሳሽ ክሳቸዉን አሻሻለዉ እንዲያቀርቡልን ትዕዛዝ እንዲሰጥልን
እንጠይቃለን፡፡
2.የተከበረዉ ፍ/ቤት ይህንን አያልፈዉም እንጅ የሚያልፈዉ ከሆነ ከሳሽ ተያዘ የሚሉት ቤት በትክክለኛ
አድራሻ ያልተገለፀ እና እኛም ያላወቅነዉ መሆኑ እንዲሁም ይህንን የተባለዉን ቤት ያልያዝን ስለሆነ
የተከበረዉ ፍ/ቤት ከክሱ በነፃ እንዲያሰናብተን ስንል እንጠይቃለን፡፡
3.ከሳሽ በተራ ቁጥር 1.4 ላይ ያቀረቡት የኪሳራ ስሌት ያቀረቡበት ወርና ዓ/ምህረት ከክሱ ጋር እርስበርሱ
የሚጋጭ እና ተከሳሽ መልስ ለመስጠት እናዳያመቸዉ ተደርጎ የቀረበ በመሆኑ የተከበረዉ ፍ/ቤት ክሱን ዉድቅ
አድርጎልን ከክሱ በነፃ እንዲያሰናብተን እና ወጪና ኪሳራችንን በምናቀርበዉ ዝርዝር መሰረት ከሳሽ
እንዲከፍሉ እንዲደረግልን ስንል እንጠይቃለን፡፡
4.ተከሳሽ ያዘ የተባለዉ ቤት ከመቼ ጀምሮ እንደተያዘ? በማን እንደተያዘ? በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ ትክክለኛ
ፍትህ እንዲሰጠን ስንል ክቡር ፍ/ቤቱን እንጠይቃለን፡፡
ከላይ ያቀረብነዉ መልስ እዉነት መሆኑን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 92 መሰረት እናረጋግጣለን፡፡

ገበየሁ ነጋሽ
ም/ኢ/ር
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ነገረ-ፈጅ

የመ/ቁ 301347

ቀን 02/08/2014 ዓ/ም

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት

ለልደታ ምድብ 14 ኛ ፍ/ብሔር ችሎት

አ/አበባ

ከሳሽ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

አድራሻ አ/አበባ

ተከሳሽ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ

አድራሻ አ/አበባ

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 መሰረት የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር

1.ወንጀል መከላከል ዘርፍ ህጋዊ ሰዉነት የሌለዉ በመሆኑ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ብቻ ህጋዊ ሰዉነት ያለዉና
መክሰስ መከሰስ እንደሚችል የሚገልፅ ከአዋጅ ቁጥር 720/2004 ላይ የተወሰደ 04 ገፅ ኮፒ
ቁጥር-----------------------------

ቀን ------------------------

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት

ለልደታ ምድብ 14 ኛ ፍ/ብሔር ችሎት

አ/አበባ

ጉዳዩ፡-የክስ መልስ ስለመላክ ይመለከታል፡፡

በከሳሽ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና በተከሳሽ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ
በመዝገብ ቁጥር 301347 መካከል ባለዉ የፍትሐብሔር

You might also like