You are on page 1of 6

በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት

የሕግ ጉዳዮች ክርክር ዳይሬክቶሬት


BOLE SUB-CITY ADMINISTIRATION JUSTICE OFFICE
LITIGATION AFFAIRS DIRCTORATE

መ/ቁ --41189
ቀን-26/10/2015 ዓ.ም
ለአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት
አዲስ አበባ

ይግባኝ ባዮች------ 1 ኛ/ አቶ አሌክሳንደር ሆኽ ቮልከር


2 ኛ/ አቶ ሚሊዮን ቶማስ ስህነ
አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤ.ቁ 2291/ለ
መልስ ሰጪ------- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት
አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13

1. ይግባኝ ባይ ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ላቀረቡት አቤቱታ ከመልስ ሰጪ የተሰጠ የመከላከያ መልስ ነው፡፡

1.1---ክርክር የተነሳበት ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሰ ሳይሆን አሁን የተሰራ እና በስህተት የኪራይ ውል የተደረገበት ስለሆነ
የኪራይ ውሉ ይሰረዝልን የሚል ሆኖ ሳለ የስር ፍ /ቤቱ በፍሬ ጉዳይ ደረጃ ቤቱን ማን እንደሰራው እና የተወረሰ መሆን አለመሆኑ
ተጣርቶ ውሳኔ የሚያገኝ ጉዳይ በመሆኑ ከወዲሁ የአሁን ይግባኝ ባዮች መብት እና ጥቅም የላቸውም በማለት በመቃወሚያ ውድቅ
መደረጉ ተገቢነት የለውም የሚለውን በተመለከተ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ /መ/ቁ 45161 ለረጅም ጊዜ መንግስት ተረክቦ ሲያስተዳድረው የነበረ ቤት
ሊመለስልኝ ይገባል በማለት ክስ ያቀረበ ወገን በአዋጅ 47/67 የተፈቀደለት ስለመሆኑ ወይም ከአዋጅ ውጪ ተወስዶብኛል የሚል
ከሆነም ለሚመለከተው አካል አቤቱታ አቅርቦ ውሳኔ አግኘረቶ ባለመብት መሆኑ ካልተረጋገጠ ክስ ባቀረበበት ቤት ላይ መብት ወይም
ጥቅም እንደሌለው ይቆጠራል በሚል በግልፅ በቅፅ 10 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ እንዲሁም ክርክር ያስነሳው
ይዞታ በ cis መረጃ መሰረት በአዋጅ 47/67 የተወረሰ የመንግስት ቤት በመሆኑ የከሳሾች ወላጅ እናት የግል ቤት ነበር ሊባል
የማይችል ከመሆኑም በላይ ከሳሾችም ቢሆኑ የወራሽነት ማስረጃ አቀረቡ እንጂ ይህ ቤት የወላጅ እናታቸው የነበረ እና የወረሱት
ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ በፍ/ቤት የፀደቀ የውርስ አጣሪ ሪፖርት ባልቀረበበት በተጨማሪም የአሁን ይግባኝ ባዮች ወላጅ እናት የሆኑት
ወ/ሮ መኪያ አህመድ ሰኢድ ከ 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከመልስ ሰጪ መ/ቤት ጋር የኪራይ ውል በመግባት እንዲሁም የአሁን 2 ኛ ይግባኝ
ባይ በተመሳሳይ ከመልስ ሰጪ ጋር የኪራይ ውል ገብቶ እያለ እና ቤቱን መልስ ሰጪ ለረዥም ጊዜ ሲያስተዳድረው የነበረ ኪራይ
ቀመስ የመንግስት ቤት በመሆኑ ውሉ ፈራሽ ተደርጎ ቤቱ ሊመለስልን ይገባል የሚል ክርክር ይግባኝ ባዮች ማቅረብ

የማይችሉ እና ቤቱ ይመለስልኝ የሚል የባለቤትነት ዳኝነት ለመጠየቅ መብት እና ጥቅም ስለሌላቸው በስር ፍ /ቤት በአግባቡ ተመርምሮ
በብይን የይግባይ ባዮች አቤቱታ ውድቅ መደረጉ በአግባቡ እና በአሁን ይግባኝ ባይ ቤቱ በማ እንደተሰራ ሳያረጋግጥ ነው በብይን
አቤቱታችን ውድቅ የተደረገው የተባለውን በተመለከተ ፍ /ቤቱ በሚገባ ማህደሮችን አስቀርቦ ይዞታው የመንግስት መሆኑን የአሁን
መልስ ሰጪ ካያያዝነው ማስረጃ የተመዘነ እና የቤት ኪራይ ውሉ ላይ ያሉት ሶስት ክፍል ቤት እና በተጨማሪ የተሰሩት ቤቶች የግል
ቤት ናቸው በማለት የቀረበው ክርክር ተገቢነት የሌለው እና በውሉ ላይም የተጠቀሱትም ሆነ በተጨማሪነት ተሰሩ የተባሉት ቤቶች
የቀበሌ ቤት በሆነው የቤ.ቁ 2291/ለ ፓርሴል ውስጥ የተገነቡ እና በመርህ ደረጃ በቀበሌ ቤት ግቢ ውስጥ ያለፍቃድ ግንባታ
መገንባት የማይቻል እና ተገንብቶም ከተገኘ የሚፈርስ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በቀበሌ ቤት ይዞታ ውስጥ የተገነባ እስከሆነ ድረስ
አስተዳደሩ የማፍረስም ሆነ የቀበሌ ቤቱ አካል ሆኖ እንዲቀጥል የመወሰን ስልጣን ያለው በመሆኑ እንዳይፈርስ ከተወሰነ የመንግስት
ቤት ሆኖ የሚቀጥል እንጂ የይግባኝ ባዮች የይገባኛል ጥያቄ ሊያቀርቡበት የማይችል እና ቤቱ የመንግስት መሆኑን አምነው ከተዋዋሉት
ውል የሚቃረን እና ከቅን ልቦና ውጪ ያቀረቡት መሆኑን ስለሚያሳይ በይዞታው ላይ ማን ቤቱን ሰራው ለሚለው በዋናነት በመንግስት
ይዞታ በቀበሌ ቤትነት በተሰጠ ይዞታ ላይ በግለሰቦች ጭምር ቤት የሚሰራ ከሆነ ይህ ከታወቀ ጀምሮ ቤቱ እንዲፈርስ የሚደረግ
ወይንም የመንግስት የቀበሌ ቤት ሆኖ እንደሚቀጥል የቤቶች መመሪያ በግልፅ ባስቀመጠበት ሁኔታ የቀረበ አቤቱታ በመሆኑ ውድቅ
እንዲደረግ እና የስር ፍ/ቤት በአግባቡ መርምሮ ነው ብይን የሰጠው በማለት ውድቅ እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡

1.2 የኪራይ ውል ግንኙነቱ የተጀመረው ቀደም ሲል ቢሆንም ቀሪ የሆነ እና አዲስ ኪራይ ውል ስለተደረገ ክሱን በይርጋ ቀሪ
የሚያደርገው አይደለም የሚለውን በተመለከተ
በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 1845 መሰረት በማናቸውም የፍ/ብሄር ጉዳዮች ውልን አስመልክቶ የሚቀርብ ክስ በ 10 ዓመት ውስጥ ክስ ካልቀረበ
የመክሰስ መብት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ተደንግጎ ባለበት ሁኔታ ይግባኝ ባዮች ባቀረቡት ክስ ላይ አላግባብ የተደረገው የኪራይ ውል
ሊፈርስ ይገባል በማለት የሚከራከሩት በሀምሌ 11 ቀን 2004 ዓ.ም የተደረገን የቤት ኪራይ ውል ሲሆን ይህን አቤቱታ የጠየቁት
ደግሞ 10 ዓመት በላይ ካለፈ በኋላ ስለሆነ ክስ ማቅረባቸው ይርጋ ስለሚያግደው በፍ /ስ/ስ/ህ/ቁ 244/2/ሠ መሰረት መዝገቡ በብይን
እንዲዘጋልን በማት የተከራከርን እና ፍ/ቤቱም በሚገባ የተገነዘበው ሲሆን በዚህ ረገድ በይግባኝ ባዮች የቀረበው መከራከሪያ
በ 2004 ዓ.ም ተደርጎ የነበረው ውል ተቋርጦ የቆ ውል ነው የሚለው መከራከሪ ተቀባይነት የሌለው እና ይግባኝ ባዮች ወደውል
ክርክር በተነሳበት ቤት ላይ ደረጉበት እና እንደመነሻ መወሰዱ ተገቢነት ለው እና ውሉ ቀሪ ሆኑዋል የሚል መከራከሪያ ሊቀርብ የሚገባ
ባለመሆኑ የይግባኝ ባዮች አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ የስር ፍ/ቤት ብይን እንዲፀናልን እንጠይቃለን፡፡

ከላይ ያቀረብነው መልስ በእውነት የቀረበ


ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 92/3 መሰረት እናረጋግጣለን፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት


የሕግ ጉዳዮች ክርክር ዳይሬክቶሬት
BOLE SUB-CITY ADMINISTIRATION JUSTICE OFFICE
LITIGATION AFFAIRS DIRCTORATE
መ/ቁ --71868
ቀን-26/04/2015 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ ፍ/ብሔር ችሎት
አዲስ አበባ

ከሳሾች------ 1 ኛ/ አቶ አሌክሳንደር ሆኽ ቮልከር


2 ኛ/ አቶ ሚሊዮን ቶማስ ስህነ
አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤ.ቁ 2291/ለ
ተከሳሽ------- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት
አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13

ከሳሾች ታህሳስ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ላቀረቡት አቤቱታ ከተከሳሽ የተሰጠ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና በአማራጭ
የቀረበ መልስ ነው፡፡

2. የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ

1.1---የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ /መ/ቁ 45161 ለረጅም ጊዜ መንግስት ተረክቦ ሲያስተዳድረው የነበረ ቤት
ሊመለስልኝ ይገባል በማለት ክስ ያቀረበ ወገን በአዋጅ 47/67 የተፈቀደለት ስለመሆኑ ወይም ከአዋጅ ውጪ ተወስዶብኛል የሚል
ከሆነም ለሚመለከተው አካል አቤቱታ አቅርቦ ውሳኔ አግኘረቶ ባለመብት መሆኑ ካልተረጋገጠ ክስ ባቀረበበት ቤት ላይ መብት ወይም
ጥቅም እንደሌለው ይቆጠራል በሚል በግልፅ በቅፅ 10 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ እንዲሁም ክርክር ያስነሳው
ይዞታ በ cis መረጃ መሰረት በአዋጅ 47/67 የተወረሰ የመንግስት ቤት በመሆኑ የከሳሾች ወላጅ እናት የግል ቤት ነበር ሊባል
የማይችል ከመሆኑም በላይ ከሳሾችም ቢሆኑ የወራሽነት ማስረጃ አቀረቡ እንጂ ይህ ቤት የወላጅ እናታቸው የነበረ እና የወረሱት
ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ በፍ/ቤት የፀደቀ የውርስ አጣሪ ሪፖርት ባልቀረበበት በተጠማሪም የአሁን ከሳሾች ወላጅ እናት የሆኑት ወ /ሮ
መኪያ አህመድ ሰኢድ ከ 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከተከሳሽ መ/ቤት ጋር የኪራይ ውል በመግባት እንዲሁም የአሁን 2 ኛ ከሳሽ በተመሳሳይ
ከተከሳሽ ጋር የኪራይ ውል ገብቶ እያለ እና ቤቱን ተከሳሽ ለረዥም ጊዜ ሲያስተዳድረው የነበረ ኪራይ ቀመስ የመንግስት ቤት በመሆኑ
ውሉ ፈራሽ ተደርጎ ቤቱ ሊመለስልን ይገባል የሚል ክርክር ከሳሾች ማቅረብ የማይችሉ እና ቤቱ ይመለስልኝ የሚል የባለቤትነት ዳኝነት
ለመጠየቅ መብት እና ጥቅም ስለሌላቸው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33(2) መሰረት ፍርድ ቤቱ የከሳሾችን አቤቱታ በብይን ውድቅ
እንዲያደርግልን፡፡

1.2---ከሳሾች በክስ ርዕሳቸው ላይ የኪራይ ውል እንዲፈርስ በሚል አቤቱታ ያቅርቡ እንጂ በክስ ዝርዝራቸው ላይ በስተመጨረሻ
በ 2 ኛ ከሳሽና በተከሳሽ መካከል የተደረገው ውል ፈርሶ ቤቱ የከሳሾች ነው ተብሎ እንዲወሰንልን በማለት ዳኝነት የጠየቁ ሲሆን ይህ
ደግሞ የሚያሳየው ከሳሾች የጠየቁት ዳኝነት የተቀላቀለ እና ውል ሊፈርስ ይገባል አቤቱታ ላይ ክርክር ያስነሳው ቤት የከሳሾች ነው
እንዲባልልን በሚል የመፋለም ክርክር ማቅረባቸው ተገቢነት የሌለው እና ውል ይፍረስልኝ ክርክር እና የመፋለም ክርክር ለየብቻ
ዳኝነት የሚጠየቅባቸው እንጂ አንድ ላይ ሊቀርቡ ስለማይችሉ የከሳሾችን አቤቱታ ፍ/ቤቱ ውድቅ እንዲያደርግልን፡፡

1.3-- ክሱ በይርጋ የታገደ ስለመሆኑ፡- በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 1845 መሰረት በማናቸውም የፍ/ብሄር ጉዳዮች ውልን አስመልክቶ የሚቀርብ
ክስ በ 10 ዓመት ውስጥክስ ካልቀረበ የመክሰስ መብት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ተደንግጓል ስለሆነም ከሳሾች ባቀረቡት ክስ ላይ
አላግባብ የተደረገው የኪራይ ውል ሊፈርስ ይገባል በማለት የሚከራከሩት በሀምሌ 11 ቀን 2004 ዓ.ም የተደረገን የቤት ኪራይ ውል
ሲሆን ይህን አቤቱታ የጠየቁት ደግሞ 10 ዓመት በላይ ካለፈ በኋላ ስለሆነ ክስ ማቅረባቸው ይርጋ ስለሚያግደው በፍ /ስ/ስ/ህ/ቁ
244/2/ሠ መሰረት መዝገቡ በብይን እንዲዘጋልን፡፡
መቃወሚያችን የሚታለፍበት የህግ አግባብ ካለ በአማራጭ የቀረበ መልስ፡፡
2.1 ከሳሾች የሟች ወላጅ እናታችን ወ/ሮ መኪያ አህመድ ወራሾች መሆናችንን ያረጋገጥን እና እናታችን መጀመሪያ በውል ይዛ
የነበረውን የቀበሌ ቤት ጤናችን ላይ ችግር በማስከተሉ ተለዋጭ አሁን ክርክር ያስነሳውን የቤ .ቁ 2291/ለ የተሰጠን እና ይህ ቤት
በአዋጅ ቁጥር 47/67 ያልተወረሰ እንዲሁም በወቅቱ ያልነበረ ከ 1983 ዓ.ም ወዲህ የተሰራ የግል ቤታችን ቢሆንም ተከሳሽ የቀበሌ
ቤት ነው በሚል የቤት ኪራይ ውል አላግባብ በ 06/12/2014 ዓ.ም እንድንዋዋል አድርጎናል የሚለውን በተመለከተ ክርክር ያስነሳው
ይዞታ በ cis መረጃ መሰረት በአዋጅ 47/67 የተወረሰ የመንግስት ቤት በመሆኑ የከሳሾች ወላጅ እናት የግል ቤት ነበር ሊባል
የማይችል ከመሆኑም በላይ ከሳሾችም ቢሆኑ የወራሽነት ማስረጃ አቀረቡ እንጂ ይህ ቤት የወላጅ እናታቸው የነበረ እና የወረሱት
ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ በፍ/ቤት የፀደቀ የውርስ አጣሪ ሪፖርት ስላላቀረቡ ወራሽነታቸው አሁን ክርክር ከተነሳበት ቤት ጋር ግንኙነት
የሌለው እና ክርክር ያስነሳው ቤት እና ይዞታ በአዋጅ ቁጥር 47/67 ያልተወረሰ ነው የሚለው አቤቱታቸው ተቀባይነት የሌለው
ከመሆኑም በተጨማሪ የአሁን ከሳሾች ወላጅ እናት የሆኑት ወ /ሮ መኪያ አህመድ ሰኢድ ከ 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከተከሳሽ መ/ቤት ጋር
የኪራይ ውል በመግባት እንዲሁም የአሁን 2 ኛ ከሳሽ በተመሳሳይ ከተከሳሽ ጋር የኪራይ ውል ገብቶ እያለ እና ቤቱን ተከሳሽ ለረዥም
ጊዜ ሲያስተዳድረው የነበረ ኪራይ ቀመስ የመንግስት ቤት በመሆኑ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ መንግስት ተረክቦ ሲያስተዳድረው የነበረ
ቤት ሊመለስልኝ ይገባል በማለት ክስ ያቀረበ ወገን በአዋጅ 47/67 የተፈቀደለት ስለመሆኑ ወይም ከአዋጅ ውጪ ተወስዶብኛል የሚል
ከሆነም ለሚመለከተው አካል አቤቱታ አቅርቦ ውሳኔ አግኘረቶ ባለመብት መሆኑ ካልተረጋገጠ ክስ ባቀረበበት ቤት ላይ መብት ወይም
ጥቅም እንደሌለው የሚቆጠር በመሆኑ ከሳሾችም ስለመፈቀዱ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ እና ከሳሾች ክርክር ያስነሳው ቤት
ባለቤቶች ስለመሆናቸው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 1195 መሰረት የተሰጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት(ካርታ)ደብተር ግብር
የተከፈለበት የላቸውም አላቀረቡም የባለቤትነት መብትም አልተፈጠረላቸውም

በተጨማሪም በቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት ባለው በቅፅ 008 መረጃ ቋት ውስጥ ክርክር ያስነሳው ቤት በቀበሌ
ቤት ስም የተመዘገበ እና የሚታወቅ ሲሆን የአሁን ከሳሾች ወላጅ እናት የሆኑት ወ /ሮ መኪያ አህመድ ሰኢድ ከ 2004 ዓ.ም ጀምሮ
ከተከሳሽ መ/ቤት ጋር የኪራይ ውል በመግባት እንዲሁም የአሁን 2 ኛ ከሳሽ በተመሳሳይ በቀን 29/11/2013 ዓ.ም ከተከሳሽ ጋር
የኪራይ ውል ገብቶ እያለ እና ቤቱን ተከሳሽ ለረዥም ጊዜ ሲያስተዳድረው የነበረ ኪራይ ቀመስ የመንግስት ቤት መሆኑን ፍ /ቤቱ
ካያያዝነው ማስረጃ የሚረዳው ሆኖ ተከሳሽ ከ 2 ኛ ከሳሽ ጋር የገባው የኪራይ ውል ይፍረስ የተባለው አቤቱታ በግልፅ ከሳሾች
በፍቃዳቸው የፈፀሙትን የኪራይ ውል መሰረት በማድረግ ቤቱን ተከራይተው እየኖሩበት እያለ እና የኪራይ ክፍያ እየተከፈለበት ያለ
ሆኖ እያለ ኪራዩን መቀጠል ካልፈለጉ ቤቱን ለመንግስት እስረክበው መልቀቅ እንደሚችሉ እና በዚህ ረገድ ያቀረቡት መከራከሪያ ቀደም
ሲል የተደረገውን የመንግስት ቀበሌ ቤት ኪራይ ውል በመካድ የቀረበ አቤቱታ በመሆኑ ውድቅ እንዲደረግልን፡፡

2.2---የቤት ኪራይ ውሉ ላይ ያሉት ሶስት ክፍል ቤት እና በተጨማሪ የተሰሩት ቤቶች የከሳሾች የግል ቤት ናቸው በማለት የቀረበው
ክርክር ተገቢነት የሌለው እና በውሉ ላይም የተጠቀሱትም ሆነ በተጨማሪነት ተሰሩ የተባሉት ቤቶች የቀበሌ ቤት በሆነው የቤ .ቁ
2291/ለ ፓርሴል ውስጥ የተገነቡ እና በመርህ ደረጃ በቀበሌ ቤት ግቢ ውስጥ ያለፍቃድ ግንባታ መገንባት የማይቻል እና ተገንብቶም
ከተገኘ የሚፈርስ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በቀበሌ ቤት ይዞታ ውስጥ የተገነባ እስከሆነ ድረስ አስተዳደሩ የማፍረስም ሆነ የቀበሌ ቤቱ
አካል ሆኖ እንዲቀጥል የመወሰን ስልጣን ያለው በመሆኑ እንዳይፈርስ ከተወሰነ የመንግስት ቤት ሆኖ የሚቀጥል እንጂ ከሳሾች
የይገባኛል ጥያቄ ሊያቀርቡበት አይችሉም በመሆኑም ቤቱ የመንግስት መሆኑን አምነው ከተዋዋሉት ውል የሚቃረን እና ከቅን ልቦና
ውጪ ያቀረቡት መሆኑን ስለሚያሳይ የከሳሾች ክስ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ሆኖ ያላግባብ ተከሰን ለተጉላላንበት በቂ ኪሳራ በቁርጥ
እንዲተኩልን እንጠይቃለን፡፡

ከላይ ያቀረብነው መልስ በእውነት የቀረበ


ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 92/3 መሰረት እናረጋግጣለን፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት


የሕግ ጉዳዮች ክርክር ዳይሬክቶሬት
BOLE SUB-CITY ADMINISTIRATION JUSTICE OFFICE
LITIGATION AFFAIRS DIRCTORATE

መ/ቁ --71868
ቀን-26/04/2015 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ ፍ/ብሔር ችሎት
አዲስ አበባ

ከሳሾች------ 1 ኛ/ አቶ አሌክሳንደር ሆኽ ቮልከር


2 ኛ/ አቶ ሚሊዮን ቶማስ ስህነ
አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤ.ቁ 2291/ለ
ተከሳሽ------- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት
አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13

በፍ/ሥ/ሥ/ህግ/ቁጥር 233 እና 234 መሰረት የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር


የሰነድ ማስረጃ
1. የአሁን ከሳሾች ወላጅ እናት የሆኑት ወ/ሮ መኪያ አህመድ ሰኢድ ከ 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከተከሳሽ መ/ቤት ጋር
የኪራይ ውል የገቡበት 2 ገጽ ኮፒ ዋናው በጽ/ቤት የሚገኝ
2. 2 ኛ ከሳሽ በቀን 29/11/2013 ዓ.ም ከተከሳሽ ጋር የኪራይ ውል የገቡበት 2 ገጽ ኮፒ ዋናው
በጽ/ቤት የሚገኝ
3. 2 ኛ ከሳሽ ቤቱ በስሙ እንዲዞር የጠየቀበት እና ተከሳሽም ስም ዝውውር
እንዲደረግላቸው የገለፀበት 2 ገጽ ደብዳቤ ኮፒ ዋናው በጽ/ቤት የሚገኝ
4. ቤቱ የቀበሌ ቤት ስለመሆኑ የሚያስረዱ የ cis እና gis መረጃ 2 ገጽ ኮፒ ዋናው
በጽ/ቤት የሚገኝ

ከላይ ያቀረብነው ማስረጃ ዝርዝር በእውነት የቀረበ


ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 92/3 መሰረት እናረጋግጣለን፡፡

You might also like