Professional Documents
Culture Documents
T
T
ይህ የቅጥር ውል ስምምነት የተፈረመው በፓርክላንድ ኮሌጅ /ከዚህ በኋላ ቀጣሪ እየተባለ በሚጠራው/ እና በአቶ/ወሮ
________________________ /ከዚህ በኋላ ተቀጣሪ/ እየተባለ/ች በሚጠራው መካከል ሲሆን ከዚህ በታች የተቀጣሪው
ሙሉ አድራሻ ተቀምጧል፡፡
የተቀጣሪው ስም : _______________________________
ፖ.ሣ.ቁጥር : _________________________
በአዋጅ ቁጥር 377/96 በአንቀጽ 4, 5,6,7,8 የአሰሪና ሰራተኞች አዋጅን መሠረት በማድረግ በውል ሰጭና በውል ተቀባይ
መካከል ለተወሰነ ጊዜ የሚመሰረት የስራ ውል ሲሆን የሚከተለውን የውል ስምምነት በመፈፀም ለዚህ ስምምነት አንቀጾች
ለመገዛት ተስማምተዋል፡፡
1. ቅጥር
የተመደበለትን ኮርስ በገለፃና በሌላ የማስተማሪያ ዘዴዎች በተግባር በማሳየት ማስተማርና እንዲሁም
የቁጥጥር ስራና ሌሎች ስራዎችን ከኮሌጁ ዲንና ከት/ክፍሉ ኃላፊ በሚደርሰው መመሪያ መሠረት
ያከናውናል፡፡
የኮሌጁን ስራ ለማከናወን በተለያዩ ኮሚቴዎች ፣ክበባት፣ ማህበራት ወይም/እና በት/ክፍል ሲመረጥ ወይም
ሲሾም ይሰራል፡፡
የሚሰጡትን ስራዎችና ተግባራት ሙያዊ ባህሪን በተላበሰ መልኩ በአካዳሚያዊ ደረጃዎች፣ ዓላማዎችና
አግባብ ባለው የኮሌጁ አካል በተቀመጠው የኮሌጁ አጠቃላይ መመሪያና ፍልስፍና መሠረት ይከውናል፡፡
በተለያዩ ጊዜያት ለሚያስተምራቸው ኮርሶች TTLM በማዘጋጀት ለዲን ቢሮ ማስገባት፡፡
ተቀጣሪው የሚኖረው ዝቅተኛውና ከፍተኛው የማስተማሪያ ሰዓቶች ገደብ በኮሌጁ ሕግ መሠረት
የሚወሰን ይሆናል፡፡
2. ደመወዝ
ተቀጣሪው ወርሃዊ ደመወዝ ብር______/_____________________________የሙያ አበል ብር
________/______________________________________ እና የወንበር አበል ብር
_________/_________________________ በአጠቃላይ ብር _____/__________________
በኢትዮጵያውያን ዘመን አቆጣጠር በወሩ መጨረሻ ይከፈለዋል፡፡
ከሚከፈለው ደመወዝ ላይ ሥራ ግብር ይቆርጣል፡፡
በዚህ ውል ቁጥር ሦስት ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ተቀጣሪው በራሱ ፍቃድ ከስራው ሲቀርና
የሚያቀርበው የሕክምና ማስረጃ ከሌለ ለቀረበት ቀን ክፊያ አይፈፀምም ፡፡
ለሠራተኛው ክፍያ የሚፈፀመው ኮሌጁ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ወይም ከትምህርት ሚኒስቴር ዕውቅና
አግኝቶ ሥራ ሲጀምር ነው፡፡
ተቀጣሪው ያልሰራበት የስራ ቀን /ሰዓት/ አይከፈለውም፡፡
በበዓላት ቀን ለተሰሩ ሥራዎች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 67 መሠረት ይከፈለዋል፡፡
3. የሕክምና ፍቃድ
ቀጣሪው ከዚህ እንደሚከተለው በተገለፀ ሁኔታ የሕመም ፍቃድ ክፍያን በትምህርት ዘመን ወቅት ይሰጠዋል፡፡