You are on page 1of 2

ሽምግልና (የዕርቅ ደብዳቤ)

ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከተው በቀን 07/05/2011 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡45 አካባቢ በደረሰ

አለመግባባት ማለትም በተበዳይ አቶ መላኩ ወ/ኪዳንና በበዳይ አቶ ታደለ አምዳሚካኤል በተፈጠረ ጊዜያዊ

አለመግባባት በዳይ ማለትም ታደለ አምዳሚካኤል ተበዳዪን መላኩ ወ/ኪዳንን በቦክስና ከኋላ ጭንቅላቱን
በድንጋይ ፈንክቶታል ሆኖም ይሔን ጉዳይ እኛ ሽማግሌዎች ሁለቱን ግለሰቦችን እምናውቃቸውና
እምንቀራረብ በመሆናችን የተፈጠረውንም ችግር ከሁለቱ ወገኖች አጣርተንና ሁለቱም ወገኖች ከዚህ በፊት
ምንም አይነት ጠብ እንዳልነበራቸውና እንዳውም ጓደኞችና አብሮ አደግ የነበሩ ሲሆን የተፈጠረውም ግጭት
እለታዊ እና አጋጣሚ ስለነበረ እኛ ሽማግሌዎች ሁለቱን ግለሰቦችን መክረንና ገሰፅን በዳይንም ካሳ ለተበዳይ
ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ በቀን 11/05/2011 እንዲከስ ተደርጎ የሁለቱም ቤተሰቦች በተገኙበት እርቅ
አውርደውል፡፡ ተበዳይም ይቅር ብሎ በዳይም ይቅርታ ጠይቆ የለቱን የእራት ግብዣ ተደርጎ ፕሮግራም
ተጠናቋል፡፡

ስለሆነም ተበዳይ አቶ መላኩ ወ/ኪዳን ክሱም እንዲቋረጥና የጤናቸውም ጉዳይ በህክምና የተመለሰ ስለሆነና
ሀኪምም ምንም እሚያሰጋ ነገር የለም ብሎ ማስረጃ ሰጥቶቸዋል፡፡

ስለዚህ ሁለቱ ግለሰቦች በመስማማታቸውና አቶ መላኩ ወ/ኪዳን ጉዳቱ ተሸሏቸው የዕለት ተለት እንቅስቃሴ
ማድረጋቸውን ስላቀጠሉ እኛም ሽማግሌዎች እርቁን ስለጨረሰን እነርሱም በመልካም ፍቃድ
በመስማማተታቸው ክሱ እንዲቋረጥና መዝገቡ እንዲዘጋ ስንል ለወረዳ 12 ልዩ ስሙ (ካራ ፍተሻ) ፖሊስ
ጣቢያ ይህን የዕርቅ ደብዳቤ እንዲታይልን ስንል በትህትና እኛ ሽማግሌዎች በማክበር እንጠይቃለን፡፡
ለምትሰጡንም መልካም ትብብር ከወዲሁም እናመሰግናለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

ሽማግሌዎች ፊርማ

1. አቶ አበባየሁ ግርማ __________


2. አቶ ሀይለአብ በዛብህ __________
3. አቶ አላመየሁ __________
4. አቶ ቴድሮስ ምትኩ __________

ተበዳይ
አቶ መላኩ ወ/ኪዳን __________
በዳይ
ታደለ አምደ ሚካኤል __________

You might also like