You are on page 1of 22

እ”"D” ÅI“ S׋G<

ከዉል ዉጪ ኃላፊነት ህግ ላይ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ

ህዳር 2012 ዓ.ም


የኃላፊነት አይነቶች በጠቅላላው
ኃላፊነት የሚለዉ ቃል የሚያመለክተዉ ተጠያቂነትን ወይም ግዴታን ሲሆን እሱም ጠቅለል ባለ መልኩ
በሁለት ልንከፍለው እንችላለን፡-

የወንጀል ኃላፊነት /criminal liability/

ይህ ኃላፊነት የሚኖረዉ በወንጀል ሕጉ እንዳይደረግ የተከለከለዉን በማድረግ ወይም እንዲደረግ


የታዘዘዉን ባለማድረግ ነዉ፡፡ለምሳሌ ስርቆት የተከለከለ ሆኖ ሰርቆ መገኘት እንዲሁም ግብር ክፈል
ተብሎ አለመክፈል ወዘተ
የፍ/ብሔር ኃላፊነት /civil liability/

ይህ ኃላፊነት በሌላ ሰው ላይ በጥፋት ወይም ያለጥፋት በሚደርስ ጉዳት የገንዘብ እና የህሊና ጉዳቱን
ለመካስ የሚጣል ግዴታ ወይም ሃላፊነት ነው፡፡

የፍ/ብሔር ኃላፊነት ሁለት ዓይነት ነዉ፡-

ሀ. በዉል ላይ የተመሠረተ ኃላፊነት ፡-

ለ. ከዉል ዉጭ ኃላፊነት፡-
ከውል ውጪ ሃላፊነት ማለት ምን ማለት ነው?
ከዉል ዉጭ ኃላፊነት ማለት በሰዎች መካከል ምንም ዓይነት የዉል ግንኙነት ሳይኖር በሌላ ሰዉ ላይ
ለሚያደርስ ጉዳት ኃላፊ መሆን ማለት ነዉ፡፡

የጉዳት ምንድ ነዉ

ጉዳት ማለት በሰው ጥቅም ወይም ሀብት ላይ የሚደርስ ጉድለት ወይም ኪሳራ ሲሆን በገንዘብ
የሚተመን ወይም የማይተመን ሊሆን ይችላል፡፡

በፍትሐብሄር ህግ ጉዳት ግልጽ የሆኑ ጉዳቶች ና የህሊና ጉዳት በመባል ለሁለት ተከፍሎ ተቀምጧል፡፡
(የፍ/ህ/ቁ/2090 እና 2105)
የገንዘብ
ኪሳራ/present
material
ግልጽ የሆኑ የሆኑ የህሊና ጉዳት
/moral
ጉዳቶች
damage

ወደፊት ሊደርስ የሚችል


ጉዳት/future
damage
ከውል ውጭ ስለሚደርስ የጉዳት ኃላፊነት ሕግ ምንነት

 የውል ግንኙነት ሳይኖር ወይም ውል ላይ ባልተመሰረተ ግንኙነት በአንድ በሕግ በተጠበቀ የሰው

ጥቅም ወይም መብት ላይ ጉዳት ሲደርስ ለዚህ ጉዳት ኃላፊነት የሚያርፍበትን አካል የሚለይ ና

ጉዳቱ በካሣ መልክ እንዲስተካከል የሚያደርግ ሕግ ነዉ

 ሕጉ የውል ግንኙነትን የማይመለከት በመሰረቱም ሆነ በውጤቱ ከውል ሕግ የሚለይ የፍትሐብሄር

ሕግ አካል ነዉ፡፡
ከዉል ዉጭ ኃላፊነት ምንጮች

ጥፋት ባይኖርም እንኳ በአንዳንድ በሌሎች ሰዎች ጥፋት


በራስ ጥፋት በሌላ ሰዉ ላይ ጉዳት በሕግ ተለይተዉ በተጠቀሱ በሌላ ሰዉ ላይ ጉዳት
በማድረስ( Fault based አድራጎቶች ወይም ሥራዎች ወይም
liability) ንብረቶች አማካይነት በሌላ ሰዉ ላይ ሲደርስ (vicarious
ጉዳት ሲደርስ (strict liability) liability)
በራስ ጥፋት የሚመጣ ኃላፊነት/Fault Based Liability
የመጀመሪያው የኃላፊነት ምንጭ በራስ ጥፋት በሌላ ሰው ጥቅም ላይ ወይም መብት ላይ
ጉዳት ማድረስ ነው፡፡
በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2ዐ29 ስር እንደተመለከተው ጥፋት ታስቦ ወይም በቸልተኝነት
እንዲሁም ተግባርን በመፈጸም ወይም ባለመፈጸም ሊከሰት ይችላል፡፡
ጥፋት የተባሉ ጉዳዩች ምን ምን ናቸዉ
ከፍትሀብሄር ሕጉ ከቁጥር 2ዐ3ዐ እስከ ቁጥር 2ዐ64 በዝርዝር የተቀመጡ ናቸዉ
እነርሱም፡
-የሞያ ጥፋት /
Professional -መልካም ጠባይ ውጪ -የመጉዳት አሳብ
Fault/ -ሕግን ስለ መጣስ

-የበላይ ትዕዛዝ -የዉል አለመፈጸም -በሥልጣን አላግባብ


መጠቀም እና የመሳሰሉት
ሲሆን
-የእጅ እልፈትና ድብደባ

-የመዘዋወር ነፃነትን -የባልና ሚስትን መብት


መንካት -ስም ማጥፋት መንካት

-በሰዉ ቤትና መሬት


መግባትና ንብረት
-ትክክል ያልሆነ መረጃ መድፈር /Trespass/
-ከድርድር በኃላ የመዋዋል -ዉል እንዳይፈጸም
መስጠት እና የመሳሰሉት
ሀሳብን መተዉ ማድረግ
ናቸዉ፡፡
የቀጠለ…
ሕጉ ጥፋት ያላቸውን ነገሮች አውቆ አስቦበት ወይም በቸልተኝነት በማድረግ ወይም ባለማድረግ ፈጽሞ በሌላ ሰው ጥቅም ወይም መብት ላይ
-የአካል ጉዳት
-የሕይወት መጥፋት
-ሰብአዊ ክብር
-የንብረት ጉዳት
ማድረስን የሚመለከት ነው፡፡
በጥፋቱ ጉዳቱን ያደረሰው ሰው ተጐጂውን የመካስ የሕግ ኃላፊነት አለበት፡፡
ጥፋት ሳይኖር የሚመጣ ኃላፊነት/strict liability/

ሁለተኛው የኃላፊነት ምንጭ ምንም ጥፋት ሳይኖር የሚደርስ ጉዳት ኃላፊነት ሲኖር ነው፡፡

ይህ ኃላፊነት የሚመጣው ሕጉ ጥፋት ብሎ ከዘረዘራቸው ጉዳዩች ውጪ ጥፋት ባልሆነ ስራ

ወይም የያዘው ወይም የራሱ የሆነ ነገር በሌላ ሰው ጥቅም ወይም መብት ላይ ጉዳት

የሚያደርሰውን ሁኔታ የሚመለከት ነው፡፡

በዚህ ዓይነት ኃላፊነትን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች በፍትሐብሄር ሕግ ከቁጥር 2ዐ66 እስከ

2ዐ89 በዝርዝር የተቀመጡት ናቸዉ


የቀጠለ….

• እራስን ወይም ሌላ ሰውን፣ የራስን ወይም የሌላ ሰውን ሀብት በእርግጥ ሊደርስበት ከሚችል አደጋ

ለማዳን ሲከላከል በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ማድረስ፣

• ከፍተኛ ጉልበት ያለው የኤሌክትሪክ መስመር በመዘርጋት፣ የመሬት የተፈጥሮ መልክን በመቀየር አደገኛ

የሆኑ የኢንዱስትሪ ስራዎችን በመስራት ጉዳት ሲደርስ፣


 በኢ.ኤ.አገልግሎትና እና በአቶ ወልዱ ገ/ስላስ መካከል በነበረዉ የካሳ ክርክር የፌዴራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚዉ ችሎት በቅጽ 11 መዝገብ ቁጥር 57904 በቀን 15/04/2003 ዓ.ም
በሰጠዉ ዉሳኔ ኢ.ኤ.አገልግሎት የዘረጋቸዉ የኤሌክትሪክ መስመር ገመዶች ለሚያደርሱት ጉዳት
ከኃላፊነት ነጻ ሊሆን የሚችለዉ ጉዳቱ የደረሰዉ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በተጎጂዉ ጥፋት
መሆኑን በማስረዳት ብቻ እንደሆነ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል ፤ፍ/ብሔር ህገ አንቀጽ
2086 (2) ላይም ተደንግጎ ይገኛል
 የፌዴራል ሰበር በቅጽ 13 መዝገብ ቁጥር 65395 በሰጠዉ ዉሳኔ ኢ.ኤ.አገልግሎት ማናቸዉንም
ኤሌክትሪክ የማመንጨት፣ የማስተላለፍ ፣ብሎም የመሸጥ ሥራዎች በሚያከናዉንበት ወቅት ሁሉ
የአካባቢን ጥበቃን በሚመለከት የወጡ ህግጋትን የማክበር ግደታ ያለበት እንደሆ ግልጽ የህግ ትርጉም
ሰጥታል ፤ አዋጅ 810/2006ዓ.ም አንቀጽ 13 ላይም ተደንግጎ ይገኛል
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች ፖል ለመትከል ጉድጓድ ቆፍሮ ሳይሸፈን ወይም ሳይከደን
ሰዉ ወይም እንስሳት ገብተዉበት ጉዳት ሲደርስባቸው፣
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚዘረጋቸዉ የኤሌክትሪክ መስመር በአዋጅ 810/2006 ዓ.ም
የወጣዉና ደንብ ቁጥር 447/2011 እንዲሁም መመሪያ ቁጥር 1/98 ዓ.ም በወጣዉ የመስመር
ዝርጋታ እስታንደርድ ጠብቆ አለመዘርጋት በሰዉና በንብረት ላይ ለሚያደርሰዉ ጉዳት ድርጅቱን
ተጠያቂ ያደርጋል፡፡
በዚህኛው የሃላፊነት አይነት ካሳ ለማግኘት ጉዳት መድረሱን ና መንስኤዉን ብቻ ማስረዳት ይበቃል
ካሳ እንዲከፍል የሚከሰሰዉ ሰዉ ጥፋተኛ አለመሆኑን በማስረዳት ከኃላፊነት ሊድን አይችልም፡፡
እንዲሁም ጉዳቱ የደረሰው ከአቅም በላይ ከሆነ ምክንያት ነው በማለት ከሃላፊነት ነፃ መውጣት
አይቻልም፡፡
ከኃላፊነት መዳን የሚቻለዉ ጉዳቱ የደረሰው በተበዳዩ ጥፋት መሆኑን በማሳየት ብቻ ነው፡፡
በመኪናዎችና ባለሞተር ተሸከርካሪዎች የሚደርስ ጉዳት፡
የአንድ መኪና ወይም የአንድ ባለሞተር ተሸከርካሪ ባለቤት የሆነ ሰዉ መኪናዉ አደጋ ያደረሰ እንደሆነ
ባለሀብቱ አላፊነት አለበት፡፡ በሰዉም ላይ ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ባለተሸከርካሪ ወይም
ባለሞተር ላደረሰዉ ጉዳት ተበዳይን የመካስ ግደታ አለበት ፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት አደገኛ ሁኔታዎች የተባሉት በሰዉና በንብረት ላይ አደጋ ካደረሱ ተጎጂዉ በሕግ
የመካስ መብት አለዉ፡፡
ጉዳት አድራሹ ነፃ መሆን የሚቻለዉ በፍ/ብሔር ህግ ቁጥር 2086 (2) መሠረት ጉዳት የደረሰዉ
በከፊል ወይም በሙሉ ከተበዳዩ ጥፋት የተነሣ መሆኑን ካረጋገጠ ብቻ ነው፡፡
ሕንፃዎች የሚያደርሱት አደጋዎች

የአንድ ሕንጻ ባለቤት ሕንጻዉ ሊያደርስ ይችላል ተብሎ ያልታሰበ ድንገተኛ ነገር ቢያደርስ ወይም
በእርጅና ወይም ከሕንጻዉ ላይ የሚወድቁ ነገሮች በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ
ተበዳይ በሕንጻዉ ባለቤት የመካስ መብት አለዉ፡፡ የህጉም ዓላማ አንድ ምክንያታዊ የሆነ ሰዉ
( Reasonable man) የሚሰራቸዉ ሥራዎች በእንዝላልነት ወይም በቸልተኝነት ሥራዉን
በሚሰራበት ጊዜ በሌላ ሰዉ ላይ ጉዳት እንዲያደርስ ስለማይፈቅድ የሕንጻዉ ባለቤትም በእንዝላልነት
ወይም በቸልተኝነት በሚያደርገዉ የሕንጻ አያያዝ በሰዉና በንብረት ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ
እንዲያደርግ ነዉ፡፡
ያለጥፋት ኃላፊነት ክስ የሚቀርቡ መከላከያዎች

የተጎጅዉ ጥፋት ማስረዳት

የዉል ግንኙነት እንዳለ ማሳየት እና

ጥቅም የሌለዉ ግንኙነት ናቸዉ፡፡


ለሌሎች ሰዎች ጥፋት ኃላፊነት (vicarious Liability)
ይህኛዉ የኃላፊነት ምንጭ ደግሞ ሌላ ሰው ስለሚያደርሰው ጉዳት ኃላፊነት መውሰድን
የሚመለከት ነው፡፡
የዚህ ኃላፊነት መሠረቱ የጉዳት አድራሹ ሰው ና ኃላፊነትን የሚሸከመው ሰው ሕጋዊ
ግንኙነት ነው፡፡

በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 212ዐ እስከ 2137 ከተቀመጡ ድንጋጌዎች እንደምንረዳው ይህ


ግንኙነት ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅና በቤተሰቡ ወይም በልጁ ጠባቂ ወይም አሳዳጊ፣
በአሰሪና በሰራተኛ ፣ በደራሲና በአሳታሚ መካከል ያለው ግንኙነት ነው፡፡
ጉዳት አድራሹ ሰው በጥፋቱ ወይም ጥፋት ሳይኖር በሚያደርሰው ኃላፊነት በሌላ ሰው
መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዳት ሲያደርስ በሕጉ ላይ የተቀመጠው ሁኔታና ግንኙነት ሲኖር
ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነትን የሚሸከመው በጉዳት አድራሹ ፋንታ ሕጉ ኃላፊ የሚያደርገው
ሰው ነው፡፡
ለሠራተኞች ጥፋት አሠሪዉ ያለበት አላፊነት
 በአሠሪ የተቀጠረ ሠራተኛ ሥራዉን በሚሠራበት(በሚያከናዉንበት) ጊዜ ጥፋት የሠራ እንደሆነ
ለደረሰዉ ጉዳት አሠሪዉ አላፊ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች
የመስመር ዝርጋታ እየሠሩ እያሉ የግለሰቦች ግቢ ያለፍቃድ ከገቡ ላደረሱት ጥፋት ድርጅቱ ተጠያቂ
ነዉ፡፡
 ጥፋቱን ለመፈጸም የቻለዉ ሥራዉን ለማከናወን ሳይሆን የተሰጠዉን ሥልጣን ጥፋቱን ለመፈጸም
ምቹ ሁኔታ ስለፈጠረለት ብቻ እንደሆነ አሠሪዉ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ ለምሳሌ፡-የኢትዮጵያ
ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኛ ድርጅቱ ባወጣዉ ተራ መጠበቅያ (waiting list) በማዛባት ጥቅም
በመቀበል ወይም ሌላዉን ለመጥቀም ተራ አዛብተዉ ተራኛ ላልሆነ ሰዉ ቆጣሪ ቢያስገባ ሠራተኛዉ
ተጠያቂ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ለግሉ ጥቅም ለማግኘት ሲሰራ ጉዳት ቢያደርስ ድርጅቱ
ምን መሰራት አለበት
 በኤሌክትሪክ ዙሪያ የወጡ የተለያዩ ህጎችን መረዳት እና መገንዘብ
 የሚሰሩ ስራዎችን ህጎቹ በሚያሥቀምጡት መሰረት እንዲሰሩ ማድረግ
 ወቅቱን የጠበቀ ቀጣይነት ያለዉ የጥገና ስራዎችን ማከናወን
 ወቅቱን የጠበቀ የቁጥጥር እና የምርመራ ስራዎችን ማከናወን
 ለሚቀርቡ ጥቆማወች ወቅታዊ ምላሽ መስጠት
 ተሸከርካሪዎችን ደህንንት መጠበቅ
 የንብረት ቁጥጥር ማድረግ
 የግንዛቤ ስራዎችን መስራት ወዘተ…..

በካሳ የምናወጣዉን ገንዘብ መቀነስ ያሥችላል


አመሰግናለዉ

You might also like