Professional Documents
Culture Documents
Beretukan Bekele
Beretukan Bekele
መ/ቁ -145657
ቀን -23/03/2015 ዓ.ም
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ 10 ኛ ፍ/ብሄር ችሎት
አዲስ አበባ
2.1 1 ኛ ተከሳሽ ከህግ ውጪ ከእናታችን ወ/ሮ ፀዳለ ወርቁ በውርስ ያገኘነውን ይዞታ ያለምንም የካሳ ክፍያ እና ምትክ ቦታ
ሳይሰጠን በ 2012 ዓ.ም ለ 2 ኛ ተከሳሽ ክርክር የተነሳበት ይዞታ ላይ እርግጠኛ ባንሆንም ካርታ ሰርቶ የሰጠው መሆኑን
የሰማን በመሆኑ እና 2 ኛ ተከሳሽ በይዞታው ላይ ከህግ ውጪ በቆርቆሮ አጥሮ ይዞታውን የያዘብን ስለሆነ ሁለቱም
ተከሳሾች ይዞታውን ለቀው እንዲያስረክቡን በሚል የቀረበ ክስ ነው ከሳሾች ይዞታውን ካሳ እና ምትክ ሳይሰጠን ከእጃችን
እንዲወጣ ተደረገብን ይበሉ እንጂ በይዞታው ላይ መብት እና ጥቅም እንዳላቸው በማስረጃ ባላረጋገጡበት ይህንን
ያረዳልናል ብለው ያቀረቡት የእርሻ መሬት የግብር ደረሰኞችም ቢሆኑ በግብር ደረሰኝ አካራካሪው ይዞታ ላይ ያለን መብት
ለማስረዳት የማይቻል እና ደረሰኞቹ ክርክር ለተነሳበት ይዞታ ስለመገበራቸው የማያመለክቱ እና በህግ ፊትም የፀና
ውጠየት የላቸውም፡፡ ሌላኛው ከሳሾች ወራሾች ነን ብለው ያያያዙት ማስረጃም የየትኛውን የሟቾች ንብረት እንደወረሱ
የማያመለክት እና ሟቾች ያልነበራቸውን መብት ወራሾች ሊወርሱ ስለማይችሉ እንዲሁም ስልጣን ባለው አካል ክርክር
ለተነሳበት ቦታ ባለመብት ስለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ባላቀረቡበት ይህንን ክስ ለመመስረት ስለማይችሉ እንዲሁም
ክርክር ያስነሳው ይዞታ መሬት ባንክ የገባ የመንግስት ቦታ በመሆኑ ከሳሾች በይዞታው ላይ መብት እና ጥቅም እንዳላቸው
የሚያሳይ ማስረጃ ባላቀረቡበት የቀረበ ክስ በመሆኑ እና ቦታው መሬት ባንክ የገባ የመንግስት ይዞታ በመሆኑ የከሳሾች
አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግልን እንጠይቃለን፡፡
2.2 ከሳሾች በአቤቶታቸው ላይ እርግጠኛ ባንሆንም 1 ኛ ተከሳሽ ለ 2 ኛ ተከሳሽ ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ ካርታ ሰርቶ
የሰጠው መሆኑን የሰማን ሲሆን በዚህ መሰረትም የተሰጠው ካርታ እንዲመክንልን በሚል ያቀረቡት አቤቱታ በዋናነት
በቦታው ላይ መብት እና ጥቅም የሌላቸው እና ይዞታው መሬት ባንክ የገባ የመንግስት ቦታ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በይዞታው
ላይ መብት እና ጥቅም አላቸው እንኳን ቢባል ካርታ ተሰርቶ መሰጠት አለመሰጠቱን ዕንኳን በቅጡ ሳያውቁ በሰሚ ሰሚ
ያለ በቂ ማስረጃ ጉዳዩን ቀጥታ ወደ ፍ/ቤት ይዞ መምጣት አግባብነት የሌለው እና የፍርድ ቤቶችን ጊዜ በማይመለከታቸው
እና ባልሆነ ነገር ጊዜ ከመውሰዱ ውጪ በእኛ በኩልም ምንም አይነት ካርታ ሰርተን ለ 2 ኛ ተከሳሽ ያልሰጠን በመሆኑ
ከሳሾችም ካርታ ተሰርቶ ስለመሰጠቱ በማስረጃ ያያያዙት ምንም ነገር ሳይኖር የቀረበ ክስ በመሆኑ ከሳሽ ከተከሳሽ ላይ
የሚጠይቀውን ጥቅም ወይም መብት በማረጋገጥ አቤቱታ ማቅረብ ሲገባቸው እና በእኛ በኩል ካርታ ሰርተን ያልሰጠን
በመሆኑ 1 ኛ ተከሳሽ በጉዳዩ የምንከሰስበት ምክንያት ስለማይኖር የከሳሾች አቤቱታ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ተደርጎ አላግባብ
ተከሰን ለተጉላላንበት በቂ ኪሳራ በቁርጥ እንዲተኩልን እንጠይቃለን፡፡
መ/ቁ -145657
ቀን -23/03/2015 ዓ.ም
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ 10 ኛ ፍ/ብሄር ችሎት
አዲስ አበባ
የሰነድ ማስረጃ
1. ቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ጽ/ቤት ቦታው መሬት ባንክ የገባ መሆኑን የገለፀበት 01 ገፅ
ኮፒ ዋናው በጽ/ቤቱ የሚገኝ
ቁጥር-ቦ/ክ/ከ/ፍ/ጽ/ቤት/----------
ቀን 23/03/2015 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ለህግ ጉዳዮች ክርክር
ዳይሬክቶሬት ለምክትል ቢሮ ሃላፊ
ጉዳዩ፡- በምንልክላችሁ ክርክር ሂደቱ ሰበር ላይ ያለ መዝገብ በፍ/ቤት የመጨረሻ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ጉዳዩ
በድርድር እና በውይይት እንዲያልቅ በእናተ በኩል ጥረት እንዲደረግ ማሳወቅን ይመለከታል፡፡
በከሳሽ ኢትዮ ቴሌኮም እና በተከሳሽ ቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ጽ/ቤት መካከል ሲካሄድ የነበረው ከውል ውጪ
ሀላፊነት ክርክር የከሳሽ ክስ የተከሳሽ መ/ቤት መልስ እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ 8 ኛ ፍ/ብሔር ችሎት በመ/ቁ 139652 ሰኔ
30 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው የፍ/ቤቱ ውሳኔ እንዲሁም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አያስቀርብም ያለበት ውሳኔ
ተያይዞ የቀረበ እና ጉዳዩ አሁን በፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ቅሬታ ያቀረብን ሲሆን የመጨረሻ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት በእናተ በኩል
ጉዳዩ በድርድር እና በውይይት እንዲያልቅ በእናተ በኩል ጥረት እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡
ከሠላምታ ጋር
ግልባጭ
በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር
ለፍትህ ጽ/ቤት
ለሕግ ጉዳዮች ክርክር ዳይሬክቶሬት
አዲስ አበባ
መ/ቁ -235372
ቀን 23/03/2015 ዓ.ም
ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት
አዲስ አበባ
አመልካች በዚህ መዝገብ ላይ በስር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረት አፈፃፀም ስለመጣብን በሰበር ሰሚው ችሎት ውሳኔ
እስኪያገኝ ድረስ የአፈፃፀም መዝገቡ ታግዶ እንዲቆይልን በሚል የዕግድ አቤቱታ አስገብተን በዚህም መሰረት
በዚህ ችሎት የተቀጠረው የወደፊት ቀጠሮ እግድ ስለጣ በተሰብሮ እንዲታይ በሚል ቅሬታ ለማቅረብ ለ
21/03/2015 ጠዋት የተቀጠረ ቢሆንም መዝገቡን ስናስከፍት መዝገቡ 1 ኛ ሰበር አጣሪ እንደሚታይ የተነገረን
እና ይህ መዝገብ ወደ ሶስተኛ ሰበር አጣሪ ስለመዘዋወሩ የተነገረን መረጃ ባለመኖሩ ምክንያት እኛ በሰዓቱ
በዚያን እለት 1 ኛ ሰበር አጣሪ እየተጠባበቅን እያለ መዝገቡ በሶስተኛ ሰበር አጣሪ ታይቶ አመልካች በቀጠሮ ቀን
ስላልቀረቡ በመደበኛው ቀጠሮ እንዲቀርቡ ተብሎ ትዛዝ የተሰጠ በመሆኑ ይህ ደግሞ ቀጠሮ እሩቅ እና ተገደን
እንድንፈፅምም አፈፃፀም ችሎቱ ትዕዛዝ ስለሚሰጥበት ከተፈፀመም የምንተይቀው ዳኝነት ትርጉም
ስለማይኖረው 1 ኛ ሰበር አጣሪ የነበሩት መዝገቦች ወደ 3 ኛ ሰበር አጣሪ መዞራቸው ስላልተነገረን እና
ስላላወቅን 1 ኛ ሰበር አጣሪ በዕለቱ ቦታው ላይ ተገኝተን ስንጠባበቅ የነበረ መሆኑን ከግንዛቤ ገብቶልን
የተከበረው ፍ/ቤት ቅሬታ እንድናቀርብ እና የስር ፍ/ቤት መዝገብ እንዲታገድልን እንጠይቃለን፡፡
ስለ አመልካች