You are on page 1of 5

የመዝገብ ቁጥር 03543

የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም

ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

ንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት

አዲስ አበባ

ከሳሾች…1 ኛ አቶ ናጃህ ቶውፊቅ አድራሻ፡-አ/አ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09

2 ኛ አቶ ይማም እንድሪስ አድራሻ፡-አ/አ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 01

3 ኛ አቶ አሊ ሀሰን አድራሻ፡-ሐረሪ ክልል ቀበሌ 17

4 ኛ አቶ አህመድ ሱልጣን አድራሻ፡- ድሬዳዋ ቀበሌ 09

5 ኛ አቶ መሀመድ አባስመል አድራሻ፡-አ/አ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 13

6 ኛ ወ/ሮ ንግስቲ መሀሪ አድራሻ፡-አ/አ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 03

ተከሳሾች..1 ኛ አቶ ባህሩ ሱሩር አንዳሮ አድራሻ፡-አ/አ ልደታ ክ/ከተማ ወረደ 06

2 ኛ አቶ ኢብራሂም ቃሲም አድራሻ፡-አ/አ ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 01

3 ኛ አቶ ሻፊ ሰማን አድራሻ፡-ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06

4 ኛ አቶ ቃሲም ተማም ከማል አድራሻ፡-አ/አ አዲስ ከተማ ወረዳ 01

5 ኛ ይቦኬር ሪል እስቴት አክሲዮን ማህበር

አድራሻ፡-አ/አ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር 272

ከሳሾች በጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፎ ላቀረቡት የክስ አቤቱታ ከ 5 ኛ ተከሳሽ ማህበር የቀረበ መልስ
ነው፡፡
የከሳሾች ክስ በ 5 ኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበው፡- 5 ኛ ተከሳሽ የማህበሩን ንብረት በማህበሩ ስም
ባለማስመዝገቡ እና የአባላቱን ጥቅም ባለመጠበቁ ወይም ባለማስከበሩ በሚል የቀረበ ክስ ነው፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
1. በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 33 & 36 እና 244 መሰረት ተጣምሮ ክስ መቅረቡ አግባብነት የሌለው
ስለመሆኑ በተመለከተ-
 5 ኛ ተከሳሽ ማህበር ከ 1 ኛ-4 ኛ ተከሳሽ ግለሰቦች ጋር በጋራ ክስ ሊቀርብን የሚያስችል የክስ
ምክንያት የሌለ ሲሆን ከሰሾች በክስ አቤቱታቸው ላይ በዝርዝር ያቀረባቸው የዳኝነት ጥያቄ
የአክሲዮን ማህበር አባላት መብታቸውን የሚነካ ድርጊት በማህበሩ አስተዳዳሪዎች ተፈጽሟል
በሚል በመሆኑ በዚህ አግባብ የቀረበው የዳኝነት ጥያቄ 5 ኛ ተከሳሽ የሚመለከተ ሳይሆን
በቀጥታ አስተዳዳሪዎችን በመሆኑ እነዚህ አስተዳዳሪዎች ደግሞ በዚህ መዝገብ ክስ

1
የቀረበበባቸው ስለሆነ የተከበረው ፍ/ቤት በማህበሩ ላይ ከአስተዳዳሪዎች ጋር በማጣመር
የቀረበው ክስ ከሥነ ሥርዓት ህጉ ውጪ አግባብነት የሌለው ስለሆነ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.33፡244(2)መ እና 36 መሰረት የከሳሾች ከስ ተብራርቶ እና በኃላፊነታችን
መጠን በተናጥል ክሱ እንዲቀርብ ከሳሾች ይህን ማድረግ ካልቻሉ መዝገቡ ተዘግቶ
እንድንሰናበት በትህትና እጠይቃለሁ፡፡
2. 5 ኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበ ክስ የክስ ምክንያት የሌለው ስለመሆኑ፡- ከሳሾች የማህበሩ
አስተዳዳሪዎች ላይ በግልጽ ክስ አቅርበው ባሉበት ሁኔታ የማህበሩን ንብረት በማህበሩ ስም
ባለማስመዝገቡ እና የአባላቱን ጥቅም ባለመጠበቁ ወይም ባለማስከበሩ በሚል በጋራ በማህበሩ ላይ
ከሳሾች ክስ ለማቅረብ የሚያስችል የህግ ድጋፍ የላቸውም፡፡ ከሳሾች ከመነሻው በ 5 ኛ ተከሳሽ ላይ
ያቀረቡት ክስ በ 5 ኛ ተከሳሽ ላይ ያላቸውን መብት እና ጥቅም በግልጽ በማረጋገጥ የቀረበ ክስ
አይደለም፡፡ የከሳሾች የዳኝነት ጥያቄ ሊረጋገጠ እና ሊፈጸም የሚችለው ከ 1 ኛ -4 ኛ
ተከሳሾች አማካኝነት ነው፡፡ ከሳሾች መብትና ጥቅም ያላቸውም በእነዚህ ሰዎች
አማካኝነት ስለሆነ በማህበሩ ላይ በቀጥታ ያላቸው መብትና ጥቅም በግልጽ ተለይቶ
ያልተመላከተበት አቤቱታ የክስ ምክንያት እንደሌለው የሚቆጠር በመሆኑ የከሳሾች ክስ
የክስ ምክንያት የለውም በማለት መዝገቡን በመዝጋት እንዲያሰናብተኝ እጠይቃለሁ፡፡
(ሰ/መ/ቁ.136775/38419)
3. የከሳሾች ክስ ተገቢው ዳኘነት ተከፍሎ መቅረብ የሚገባው ስለመሆኑ ፡- ከሳሾች የክሱ
ርዕስ በሚል በዝርዝር ከገለጻቸው የዳኝነት ጥያቄዎች መሀከል “በማህበሩ ካፒታል
እና በማህበሩ አባላት ከተገኘ መዋጮ የተሰራ ህንጻ የማህበሩ ንብረት መሆኑ ተረጋግጦ
ውሳኔ እንዲሰጥ” በሚል ያቀረቡት የዳኝነት ጥያቄ በፍርድ ሊረጋገጥ የሚችለው
ከሳሾች በቅድሚያ ይህን ንብረት የገንዘብ ግምቱ በግልጽ የሚታወቅ ስለሆኑ ተገቢውን
ዳኝነት በመክፈል ክስ ሲያቀርቡ ስለሆነ በቅድሚያ የንብረቱ ግምት ተገልጾ ዳኝነት
እንዲከፈል እንዲደረግ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡
4. 2 ኛ ከሳሽ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብትና ጥቅም የሌላቸው ስለመሆኑ፡- 2 ኛ
ከሳሽ አቶ ይማም እድሪስ አሊ በህግ አግባብ የተመዘገበ የአክሲዮን ሽያጭ ውል
ማስረጃ በክሳቸው ባላቀረቡበት የአክሲዮን ማህበር አባል ስለመሆናቸው የሚያስረዳ
በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የሽያጭ ውል ወይም ቃለ ጉባኤ ማስረጃ ያላቀረቡ

2
በመሆኑ ይህን ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት ወይም ጥቅም እንዳላቸው
ስላላረጋገጡ የ 2 ኛ ከሳሽ ክስ ውድቅ እንዲደረግልኝ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያው የሚታለፍ ከሆነ በአማራጭ የቀረበ የፍሬ ነገር ክርክር፡-
የመከላከያ መልስ
1. ከሳሾች በክሳቸው ተራ ቁጥር 1.4 ላይ “ 5 ኛ ተከሳሽ ማህበር ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከአባላቱ
ተጨማሪ መዋጮ ከመቀበል ውጪ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ አያውቅም፤ የውጪ ኦዲተር በጠቅላላ
ጉባኤ አልሾመም፤ የማህበሩን ሂሳብ ለጠቅላላ ጉባኤ አላሳወቅም የማህበሩን ወጪ፡ ኪሳራ እና ዕዳ
ከሳሾች አያውቁም” በሚል ለቀረበው ከመነሻው ከሳሾች ይህ ጥያቄ ለማቅረብ በአግባቡ ተገኝተው
ጥያቄ አቅርበው አያውቁም፡፡ ማህበሩ ተገቢውን መዋጮ ከአባላቱ መሰብሰብ ቢገባውም ሁሉም
አባላት በሚባል መልኩ የሚፈለግባቸውን ክፍያ በወቅቱ እየከፈሉ አይደለም፡፡ በአጠቃላይ ከሳሾች
ማህበሩ መዋጮ ከመሰብሰብ ውጪ ስራውን አልሰራም ቢሉም ከሳሾች መዋጮ በመክፈል እንኳን
ኃላፊነታቸውን አልተወጡም፡፡
2. የከሳሾች ጥያቄ በአጠቃላይ ማህበሩ ከህግ ውጪ እየሰራ ነው ቢሉም የማህበር
የዳይሬክተሮች ቦርድም ሆነ የማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ አንድ ማህበር ከተቋቋመ ጀምሮ
ተደርጎ አያውቅም በሚል ምክንያት ብቻ አንድ ማህበር እንዲፈርስ ሊወሰን የማይገባ ስለመሆኑና
በንግድ ህጉ መሰረት እንደበቂ ምክንያት ሊወሰድ የማይችል ስለመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መ/ቁ.127352 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡
3. ከሳሾች በክሳቸው በማህበሩ ስም እየተሰራ ያለው ህንጻ የማህበሩ ላማድረግ በሚል ክስ
ያቀረቡ ሲሆን ከመነሻው ህንጻው የማህበሩ መሆኑ ካልተካደ በማህበሩ ስም ለማድረግ
በሚል ክስ መቅረቡ በራሱ አግባብነት የለውም፡፡ የአክሲዮን ማህበሩ የተቋቋመ
ቢሆንም በአባላት ደካማ እንቅስቃሴ እና መዋጮ በወቅቱ ባለማዋጣት እና
ግዴታቸውን ባለመወጣት ምክንያት ማህበሩ ስራ መስራት አልቻለም፡፡ የአክሲዮን
ማህበሩ የተቋቋመ ቢሆንም የንግድ ፈቃድ ወጪ በማድረግ ወደ ስራ ባለመግባቱ
የከሳሾች ጥያቄ የህግ መሰረት የለውም፡፡
4. ከሳሾች ድርጅቱ እየሰራው ያለውን ህንጻ እንኳን ስራ ለማስቀጠል ማህበሩ ካፒታሉን
የቸረሰ በመሆኑ በአሁን ሰዓት አባላት መዋጮ ማድረግ ካልቻሉ ስራ መቀጠል
አይችልም፡፡ ይህ እየተሰራ ያለው ህንጻ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ በማህበሩ ስም
ያልተመዘገበ ነው፡፡ የማህበሩ ህንጻ ያለመመዝገብ መዘግየት በአባላት መዋጮ በወቅቱ
ባለመክፈል እና ማህበሩ ላለፎት 3 ዓመታት የተቋቋመበትን ዓላማ ማሳካት ባለመቻሉ
ምክንያት የመጣ ሲሆን ይህ ደግሞ የአብዛኛው አባላት ግዴታ ባለመወጣት ምክንያት
የተፈጠረ ችግር ነው፡፡
5. በአጠቃላይ ከሳሾች ያቀረቡት ክስ ተመርምሮ ውሳኔ ቢሰጥ ተቋውሞ የሌለን ሲሆን
ነገር ግን የከሳሾች ክስ ቅሬታ ነጥቦች 5 ኛ ተከሳሽ የሚመለከተ ሳይሆን ሁሉንም

3
አባላት ከሳሽን ጨምሮ የሚመለከተ በመሆኑ በ 5 ኛ ተከሳሽ ላይ ያለአግባብ የቀረበው
ክስ ውድቅ ተደርጉ በዚህ ክስ ምክንያት 5 ኛ ተከሳሽ ወጪ ያደረግኩትን የጠበቃ አበል
እና ልዩ ልዩ ወጪዎች በቁርጥ ከሳሾች እንዲከፍሉ እንዲወሰንልኝ በትህትና
እጠይቃለሁ፡፡
የቀረበው ምላሽ በእውነት ነው፡፡
የ 5 ኛ ተከሳሽ ጠበቃ

ኤርሚያስ መኮንን

የመዝገብ ቁጥር 03543

የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም

ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

ንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት

አዲስ አበባ

ከሳሾች…1 ኛ አቶ ናጃህ ቶውፊቅ አድራሻ፡-አ/አ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09

2 ኛ አቶ ይማም እንድሪስ አድራሻ፡-አ/አ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 01

3 ኛ አቶ አሊ ሀሰን አድራሻ፡-ሐረሪ ክልል ቀበሌ 17

4 ኛ አቶ አህመድ ሱልጣን አድራሻ፡- ድሬዳዋ ቀበሌ 09

5 ኛ አቶ መሀመድ አባስመል አድራሻ፡-አ/አ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 13

6 ኛ ወ/ሮ ንግስቲ መሀሪ አድራሻ፡-አ/አ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 03

ተከሳሾች..1 ኛ አቶ ባህሩ ሱሩር አንዳሮ አድራሻ፡-አ/አ ልደታ ክ/ከተማ ወረደ 06

2 ኛ አቶ ኢብራሂም ቃሲም አድራሻ፡-አ/አ ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 01

3 ኛ አቶ ሻፊ ሰማን አድራሻ፡-ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06

4 ኛ አቶ ቃሲም ተማም ከማል አድራሻ፡-አ/አ አዲስ ከተማ ወረዳ 01

5 ኛ ይቦኬር ሪል እስቴት አክሲዮን ማህበር

4
አድራሻ፡-አ/አ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር 272

የማስረጃ ዝርዝር መግለጫ

ከሳሾች በማስረጃ ተራ ቁጥር 1,2 እና 3 ላይ የዘረዘራቸው ማስረጃዎች ለ 5 ኛ ተከሳሽም


በማስረጃነት እንዲያዝልኝ እጠይቃለሁ፡፡

የቀረበው የማስረጃ ዝርዝር መግለጫ በእውነት ነው፡፡

የ 5 ኛ ተከሳሽ ማህበር ጠበቃ

ኤርሚያስ መኮንን

You might also like