Professional Documents
Culture Documents
Balecha Guremu
Balecha Guremu
መ/ቁ -145803
ቀን -19/03/2015 ዓ.ም
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ 6 ኛ ፍ/ብሄር ችሎት
አዲስ አበባ
2.1 የ 1 ኛ ተከሳሽ ሃላፊዎች ስልጣንን ያላግባብ በመጠቀም ከህግ ውጪ ያለምንም የካሳ ክፍያ እና ምትክ ቦታ
ሳይሰጠን በ 1997 ዓ.ም ከይዞታችን እና ከንብረታችን በማፈናቀል የእርሻ መሬታችን እና ንብረታችንን
በመውሰድ አሁን ክስ ያቀረብንበትን ይዞታ ከእጃችን እንዲወጣ እና ለአረንጓዴ መናፈሻነት አግልግሎት እንዲውል
አድርገዋል በሚል የቀረበው ክስ
ከሳሾች ይዞታውን ካሳ እና ምትክ ሳይሰጠን በጉልበት ከእጃችን እንዲወታ ተደረገብን ይበሉ እንጂ በይዞታው ላይ
መብት እና ጥቅም እንዳላቸው በማስረጃ ባላረጋገጡበት መብት እና ጥቅም አላቸው እንኳን በቀድሞ ስሙ ቦሌ
ኮተቤ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ስር ሲተዳደር ለነበረ ይዞታ በጉልበት ከይዞታቸው ያፈናቀላቸው የአሁን 1 ኛ ተከሳሽ
ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት እና ማስረጃ ባልቀረበበት እንዲሁም ቦታውን ማስለቀቅን በተመለከተ የ 1 ኛ ተከሳሽ
ስልጣን እና ሃላፊነት እንዳልሆነ እየታወቀ እንዲሁም ከሳሾች በክሳቸው ላይ በግልፅ አምነው የገለፁት ነገር
የአጥር ዕድሳት በሚል የግንባታ ፍቃዱን የሰጠው የአሁን 1 ኛ ተከሳሽ ሳይሆን የወረዳው ግንባታ ፍቃድ እና
ቁጥጥር ጽ/ቤት መሆኑን አረጋግጠው የገለፁት በመሆኑ እንዲሁም ቦታው ለግሪን ኤሪያነት እንዲውል ያደረገው
የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን በመሆኑ 1 ኛ ተከሳሽ በጉዳዩ ገብተን ውሳኔ
ያልሰጠን በመሆኑ በጉዳዩ የምንከሰስበት ምክንያት ባይኖርም ክሱ ይመለከታችኋል እንኩዋን ቢባል ክርክር
ያስነሳው ይዞታ መሬት ባንክ የገባ የመንግስት ቦታ ሲሆን ለአሁን 2 ኛ ተከሳሽ በጊዜያዊነት ቦታውን እንዲያለማ
ለአረንጓዴ ልማት በሚል በጊዜያዊነት የተላለፈ በመሆኑ ከሳሾች በይዞታው ላይ መብት እና ጥቅም እንዳላቸው
የሚያሳይ ማስረጃ ባላቀረቡበት የቀረበ ክስ በመሆኑ እና ቦታው መሬት ባንክ የገባ የመንግስት ይዞታ በመሆኑ
የከሳሾች አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግልን እንጠይቃለን፡፡
2.2 ከሳሾች ነባር አርሶ አደር እና የአርሶ አደር ልጆች መሆናችንን በአርሶ አደር ኮሚቴ አረጋግጠናል ያሉት ተቀባይነት
የሌለው እና በማስረጃም ያልተደገፈ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በወረዳው ውስጥ ነባር አርሶ አደር እና የአርሶ አደር
ልጆች ናቸው ቢባል እንኳን ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ አርሶአደር ስለመሆናቸው ባልተረጋገጠበት እንዲሁም
በይዞታው ላይ መብት እንዳላቸው ያረጋግጥልናል ብለው ያቀረቡት የእርሻ መሬት ግብር ደረሰኞችም ቢሆኑ
በግብር ደረሰኝ አካራካሪው ይዞታ ላይ ያለን መብት ለማስረዳት የማይቻል እና ደረሰኞቹ ክርክር ለተነሳበት ይዞታ
ስለመገበራቸው የማያመለክቱ እና በህግ ፊትም የፀና ውጠየት የላቸውም፡፡ ሌላኛው ከሳሾች ወራሾች ነን ብለው
ያያያዙት ማስረጃም የየትኛውን የሟቾች ንብረት እንደወረሱ የማያመለክት እና ሟቾች ያልነበራቸውን መብት
ወራሾች ሊወርሱ ስለማይችሉ እንዲሁም ስልጣን ባለው አካል ክርክር ለተነሳበት ቦታ ባለመብት ስለመሆናቸው
ህጋዊ ማስረጃ ባላቀረቡበት ያከራከረው ይዞታ ተወስዶብናል እንዲሁም በንብረት እና ቤታችን ላይ ጉዳት
ደርሶብናል የሚሉት በ 1997 ዓ.ም ሲሆን ይዞታው የከሳሾች አለመሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይዞታው የከሳሾች ነው
እንኳን ቢባል በቦታው ላይ ምንም አይነት ቤትም ሆነ ንብረት ያልነበረ መሆኑ እና በይዞታው ላይ የነበረን ቤት እና
ንብረት ወድሞብናል የሚለው አቤቱታ ከእውነት የራቀ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በይዞታው ልይ ቤት እና ንበረት
ነበር ቢባል እንኳን ለደረሰው ጉዳት የጉዳት ካሳ እና ምትክ ቦታ ይሰጠን ቅሬታ ማቅረብ የነበረባቸው ይዞታው
አእጃችን ወጣ ከሚሉበት ከ 1997 ዓ.ም አንስቶ በሁለት አመት ውስጥ በቂ ምክንያት ካለ ደግሞ ግፋ ቢል በአስር
አመት ውስጥ በመሆኑ እና በዚህ ጊዜ ገደብ ውስጥ ቅሬታ አቅርበው ምላሽ ስለማጣታቸው ምንም አይነት
ማስረጃ ሳያቀርቡ አስራ ስምንት(18) ዓመት በላይ ካለፈ በኋላ ቆይተው ክስ ማቅረባቸው ይርጋ ስለሚያግደው
በከሳሾች የተጠየቀው የይዞታ ይመለስልኝም ሆነ የካሳ ሊሰጠኝ ይገባል አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ
የከሳሾች አቤቱታ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ተደርጎ አላግባብ ተከሰን ለተጉላላንበት በቂ ኪሳራ በቁርጥ እንዲተኩልን
እንጠይቃለን፡፡
መ/ቁ -145803
ቀን -19/03/2015 ዓ.ም
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ 6 ኛ ፍ/ብሄር ችሎት
አዲስ አበባ
የሰነድ ማስረጃ
1. የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ክርክር የተነሳበት ቦታ ከነይዞታ ካርታው ጭምር በግሪን ኤሪያነት እንዲለማ
ለ 2 ኛ ተከሳሽ በቀን 24/07/2013 ዓ.ም የሰጠበት ደብዳቤ 2 ገፅ ኮፒ ዋናው በጽ/ቤቱ የሚገኝ
2. የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ጽ/ቤት ለ 2 ኛ ተከሳሽ ለግነባታ በሚል ፍቃድ የሰጠበት
01 ገፅ ኮፒ ዋናው በጽ/ቤቱ የሚገኝ
3. ቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት ቦታው መሬት ባንክ የገባ እና በጊዜያዊነት ለ 2 ኛ
ተከሳሽ እንዲያለማው በሚል የተሰጠ መሆኑን የገለፀበት 01 ገፅ ኮፒ ዋናው በጽ/ቤቱ የሚገኝ
4. ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ ካሳ ስለመበላቱ እና ክርክር ያስነሳውን ይዞታ በአርሶአደርነት ይዘው
ሲጠቀሙበት የነበሩ ሰዎች እነማ እንደነበሩ የሚያስረዳልንን ማስረጃ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 145 መሰረት ከአ.አ
መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፍ/ቤቱ በትዕዛዝ እንዲያስቀርብልን፡፡
5. የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ፅ/ቤት ክርክር ያስነሳው ይዞታ በ 1988 እና በ 1997 በተነሳ
አየር ካርታ ቦታው ላይ የተገነባ ቤት መኖር አለመኖሩን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 145 መሰረት አታርቶ ምላሽ
እንዲሰጥ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን፡፡
መ/ቁ -53375
ቀን -04/04/2015 ዓ.ም
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ 5 ኛ ውርስ ሀ ችሎት
አዲስ አበባ
በህዳር 13 ቀን 2015 ዓ.ም በተሰጠው ዕግድ ላይ ከቦሌ ክ/ከተማ የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት የተሰጠ
አስተያየት
በዚህ መዝገብ ላይ የተጠየቀው ቦታ በወራሾች መካከል ክርክር ሊካሄድበት የማይችል እና የሟች አቶ ደምሴ ጩቄ
የውርስ ሀብትም ያልሆነ እና በመንግስት እጅ ስር የሚተዳደር በከተማው መዋቅራዊ ፕላን መሰረት በወረዳ ደረጃ
ለመናፈሻነት በሚል በግሪን ኤሪያነት የተያዘ የመንግስት ቦታ በመሆኑ ወራሾች በዚህ ይዞታ ላይ መብት እና ጥቅም
ሳይኖራቸው ቦታው ላይ የሚደረገውን የልማት ስራ ለማደናቀፍ ዕግድ እንዲሰጥላቸው መጠየቃቸው ተገቢነት የሌለው
እና የተጀመረውን የልማት ሂደት እያደናቀፈብን በመሆኑ የተሰጠው ዕግድ እንዲነሳልን እየጠየቅን በይዞታው ላይ
ወራሾች መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው አላቸው እንኳን ቢባል በወራሽነት መዝገብ ላይ የእነሱ ያልሆነን ንብረት
በውርስ ሪፖርት ላይ ማካተት የማይችሉ እና በሌላ ክስ የመፋለም ክርክር የሚቀርብበት እንጂ በዚህ መዝገብ ተጣቶ
ውሳኔ የሚሰጥበት አለመሆኑ እንዳለ ሆኖ መታየት ይቻላል የሚባል ከሆነም በዚህ መዝገብ ላይ ጣልቃ ገብተን
መብታችንን እንድናስከብር ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን፡፡
መ/ቁ -145803
ቀን -19/03/2015 ዓ.ም
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ 6 ኛ ፍ/ብሄር ችሎት
አዲስ አበባ
ከሳሾች-------1 ኛ/ ባልቻ ጉርሙ
2 ኛ/ ሰቦቃ ገመቹ
3 ኛ/ ማሞ አቦዬ
4 ኛ/ ገነት ክፈለው
5 ኛ/ ዳንኤል በቀለ
6 ኛ/ ዮሃንስ በቀለ
7 ኛ/ ተዋበች ፈንታ
8 ኛ/ እሜቱ አሰፋ
9 ኛ/ አዲስ አሰፋ
10 ኛ/ ቢኒያም አሰፋ
አድራሻ፡- ቦል ክ/ከተማ ወረዳ 07
ተከሳሾች፡ -------1 ኛ/ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ
2 ኛ/ ሾላ አክሲዮን ማህበር
አድራሻ፡- ቦል ክ/ከተማ ወረዳ 07
በቀን 18/05/2015 ዓ.ም ለፍ/ቤቱ በቀረበው የትዕዛዝ ውጤት ላይ ከ 1 ኛ ተከሳሽ የተሰጠ አስተያየት
1. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማት
አስተዳደር ጽ/ቤት በጋራ ክርክር ያስነሳው ይዞታ በልዩ ስሙ ጃክሮስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው
ስፋቱ 10፣137 ካ.ሜ የሆነው ቦታ በማን ስም ተመዝግቦ እና በማን ይዞታ ስር ተካቶ እንደቆየ ተጣርቶ
እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ ባዘዘው መሰረት በ 2 ኛ ተከሳሽ በውስጡ ባሉ ነዋሪዎች በአረንጓዴ ልማት እየለማ ያለ
መሆኑን እና ለ 2 ኛ ተከሳሽ ከ 1992 ዓ.ም ጀምሮ በፈር ግሪን በሚል ተመላክቶ የተሰጠ ቢሆንም በይዞታ
ማረጋገጫ ካርታ ወሰን ውስጥ ያልተካተተ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ይህም የሚያሳየው ክርክር ያስነሳው ይዞታ
ከ 1992 ጀምሮ በ 2 ኛ ተከሳሽ ተይዞ የቆየ መሆኑን እና በ 1 ኛ ተከሳሽ በኩል መሬት ባንክ እንዲገባ የተደረገ
በጊዜያዊነት ለግሪን ኤሪያ ልማት በሚል ለማህበሩ የተሰጠ መሆኑን የሚያሳይ እና በቀረበብን ክስ ላይ
የሰጠነውን ምላሽ የሚያጠናክር ውጤት የቀረበ ሲሆን 1 ኛ
ተከሳሽ ክርክር ያስነሳው ይዞታ መሬት ባንክ የገባ መሆኑን ጠቅሰን በማስረጃነትም አያይዘን ያቀረብነው
ሰነድ የሚያስረዳልን በባለቤትነት ደረጃ ቦታው የመንግስት መሆኑን የሚያሳይ እና ቦታውን ከመያዝ እና
ከማልማት አንፃር ለ 2 ኛ ተከሳሽ የተሰጠ መሆኑን የቀረበው ውጤት የሚያጠናክርልን በመሆኑ እና ከሳሾች
ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ መብት እና ጥቅም እንዳላቸው የሚያሳይ ምንም አይነት ማስረጃ ባለመኖሩ
የቀረበው ውጤት ላይም ከሳሾች በቦታው ላይ ሲገለገሉበት እንደነበር እና የነሱ እንደነበር የቀረበ ነገር
ባለመኖሩ የከሳሾች ክስ ውድቅ እንዲደረግልን እንጠይቃለን፡፡
2. በሁለተኛ ደረጃ እንዲጣራ በፍ/ቤቱ የታዘዘው ከዚህ በፊት ይዞታው የማን እንደነበር እና በዚህ ይዞታ ላይ
ካሳ እና ምትክ የተሰጠ መሆን አለመሆኑን እንዲገለፅ ባለው መሰረት በ 1990 ዎቹ ከይገባኛል ነፃ የተደረገ
መሬት (ቦታ) እንደነበር እና ከ 1990 በፊት ባለቤትነቱ የማን እንደነበር ማወቅ አልተቻለም በሚል ምላሽ
የቀረበ ሲሆን በዋናነት ከ 1990 በፊት ይዞታው በማን እጅ እንደነበር የሚረጋገጠው በሚመለከታቸው
ተቋማት በሚቀርብ የሰነድ ማስረጃም ጭምር እንደሆነ እና በከሳሾች በኩልም ከሚመለከተው አካል
ይዞታው የእነሱ እንደነበር የሚገልፅ ምንም አይነት ማስረጃ የሌላቸው እና የግብር ደረሰኝ በማለት
እንዲሁም የሰው ምስክሮች በሚል ካቀረቡት ውጪ እንደማስረጃ ያያያዙት ነገር የሌለ እና በፍ /ቤቱ በተሰጠ
ትዕዛዝ ላይ በቀረበው ውጤት ላይም ስለከሳሾች የይዞታው ባለቤት ስለመሆናቸው ማስረጃ ባልቀረበበት
የባለቤትነት መብትን በሰው ምስክር ብቻ ማረጋገጥ የማይቻል እና የግብር ደረሰኞቹም ክርክር በተነሳበት
ይዞታ ላይ ስለመገበራቸው የሚያሳይ ነገር ባለመኖሩ እንዲሁም ይዞታው ከ 1990 በፊት የከሳሾች ነበር
እንኳን ቢባል እስካሁን መብት እና ጥቅማቸውን ለማስከበር ምንም አይነት ጥረት ሳያደርጉ ከ 25 ዓመት
በኋላ ይህንን ዳኝነት መጠየቅ እንደማይችሉ እና ለተጎዱ አርሶ አደሮች ተጠቃሚነት በሚል የወጣውን
መመሪያ ቁጥር 20/2013 አላግባብ በመተርጎም ከቅን ልቦና ውጪ አላግባብ ለመበልፀግ በሚል የቀረበ ክስ
በመሆኑ የከሳሾች አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው እና በፍ/ቤቱ በተሰጠ ትዕዛዝ ላይ በቀረበው ውጤት ላይም
መረዳት የሚቻለው ይህንን በመሆኑ የከሳሾች ክስ ውድቅ እንዲደረግልን እየጠየቅን ይህ የቀረበው አስተያየት
በእውነት የቀረበ መሆኑን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 92/3/ መሠረት እናረጋግጣለን፡፡