You are on page 1of 7

5 ኛ ተካሳሽ እኔ አቶ መንሱር ጃማል ለተከሰሱበት ክስ የክርክር መቆሚያ መቅረብ

ይሆናል ።

ክሱ:- የሰይት ተቆጣጣሪ መሐንዲስ እንዳመሆኑ መጣን ይህንን ህጋ ወጥ ድርጊት


ተቆጣጥሮ ማስቆም ስገባው እሱ ግን ግምት በመውጣት እገዛ ከማድረጉም በላይ
ገዥ በማስፈጸም ።

1 ኛ የተከበረው ፍ/ቤት

የመከላከያ ምስክሮቼ የውሃ መስመር ዝርጋታ ስራው በውሃ አገልግሎት ድርጅት በቦርድ
አመራር የሚመራ መሆኑን ያስራዱ ስሆን እነሱ ,ስራአስኪያጅ,ምትክል ስራ አስኪያጅ ,የሥራ
ህዳት መሪ ,ከንቲባ,የቦርድ አበላት ተቆጣጥሮ ማስቆም ስልጣን የሌለኝ መሆኑን ያስረዱ
በመሆኑ እናም አቃቤ ምስክሮች የመሰከሩ ነገር የሌላ እንዲሁም የተቋሙ መቋቋም አዋጅ
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የከተሞች ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት
ድርጅት አዋጅ ቁጥር 170/2009 አንቀጽ 9 እስከ 20 እና የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ክልል መንግሥት የከተሞች ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ደንብ ቁጥር 160/2010
አ/ም አንቀጽ 5 የድርጅቱ አመራሮች ስልጣንና ተግባር እነ በግልጽ አስቀምጧል ።
5 ኛ ተካሳሽ እኔ ዝርጋታውን ተቆጣጥሮ ማስቆም ስልጣንና ተግባር /ሀላፊነት አላዉኝ? ማንን?
,በምን ?,ምን በማድረግ ?,በምን ሀላፊነት ?,አዋጅ /ደንቡ/መዋቅሩ ይፈቀድለታል?

ግዥ በማስፈጸም ስልጣንና ተግባር አለውኝ? ማንን ?,በምን ሥራ? ,ምንበማድረግ? ,በምን


ሀላፊነት? ,አዋጅ /ደንቡ/መዋቅሩ/የሥራ መዳብ ይፈቀድለታል?የሚሉ ጥያቄዎችን ከአዋጁና
ደንብ ጋር በመሣላሣል የበላይ ሀላፊዎችን የመቆጣጠርና የማስፈፀም ስልጣንና ተግባር የእኔ
ሥራ አለመሆኑን አዋጅና ደንብ እያስረዳ ሆኖ ሰሌ ለተቋሙ አመራር በህግ የተሠጠውን
የስልጣን ወሰንን ማለፉንና 5 ኛ ተከሳሽ ስራ ድርሻ አለመሆኑን መረዳት ይቻላል ።

1 ኛ እኔ የድርጅቱ አመራር /ሀላፍ አይዶላውም ።ለእኔ ለውሃ ፕሮጀክት ሥራ የተሠጠን


ስልጣን ተግባር /የመምራት ሀላፊነት/ውክልና የላንም።የድርጅቱ ሰራታኛ ናን። በህብረተሰብ
ስምምነቱ መሣራት አሠሪዎች/የበላይ አመራሮች ስምርት የሚሠራ ሠራተኛ /የደቡብ
ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የከተሞች ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት
ድርጅት አዋጅ ቁጥር 170/2009 አንቀጽ 24 መሠረት የሚተዳደር ሠራተኛ ነኝ።የተቋሙ
የአስተዳደር ህግ ስነ ሥርዓት መሠረት እኔን አይመለከተኝም ።

2 ኛ የቦርድ አባል አይዶለውም።ይህ ሆኖ ሰሌ ተሳትፎ አሌ ከመላት ውጭ ምንም አይናት


ድርጊት የሚያሥረዳ ነጋር የሌላባት , የእኔን ስራ ስልጣን /ሠራተኛ ድርሻ ያላጋናዛባ መሆኑ
የተከበረው ፍ/ቤት 5 ኛ ተካሳሽ እኔ ሰይት መሐንዲስ መሆኔን ዝርጋታ ስራወን ተቆጣጥሮ
ማስቆምና ግዥውን የመስፈጻም ስልጣንና ተግባር /ሀላፊነት የእኔ መሆኑን ምንም አይነት
ህጋዊ ማስረጃ ያላቀረበ የተመሠከራ ነገር የሌለብኝ በመሆኑ እንድሁም ያቀረብኩትን ህጋዊ
ማሰረጃ የውሃ አገልግሎት ድርጅት አዋጅና ድንብ የእኔ ስልጣንና ተግባር አለመሆኑን
የሚያስረዳ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ዋናው በትዘዝ አድያስመጣና ኮፕ ያቀረብኩት በማገናዘብ በነፃ
እንዲያሰናብተኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ

2 ኛ የተከበረው ፍ/ቤት

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የከተሞች ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት
ድርጅት አዋጅ ቁጥር 170/2009

አንቀጽ 9 ንኡስ አንቀጽ 11,አንቀጽ 14 ንኡስ አንቀጽ 1,4,7,10,15 እና አንቀጽ 17 ንኡስ


አንቀፅ 1,2,8,10,15

1 ኛ አዳዲስ ግንባታ /ዝርጋታ ተቆጣጥሮ ማስቆም

2 ኛ ግዥና ፈይናንስ ስርአቱን መቆጣጠር እኛ

3 ኛ ውል የመዋዋል ሀላፊነት/ስልጣን የቦርድ እና ቦርድ ውክልና የሠጣቸውን የውሃ አገልግሎት


ድርጅት አመራር(የበላይ ሀላፊዎች )እንጂ የእኔ ሥራ ስልጣን አለመሆኔን በግልጽ ያሰረዳል
።የተመሠከረብኝ ነገር የላም።ሀላፊነት/ስልጣን መን, በመን ሰም, በመን ፍቀድ መድረግ /በመን
ሀላፍናት/በአጣቃላይ የድርጅቱ አመራሮች እነማን እንደሆኑ በግልጽ አስቀምጠዋል ።ይህም
ተቋሙ የተቋቋመው በአዋጅ /በደንብ /በመዋቅር በመሆኑበግልጽ ሆኖ ሳሌ እኔን ዝርጋታው
ተቆጣጥሮ መስቆም,ግዥውን በማስፈጸም እና ውል በመዋዋል በማለት ተብሎ በቀረበው የእኔ
የስራ ሀላፊነት /ስልጣን አላመሆኑን ያስረዳል ።አዋጅና ደንብ ኮፕ የቀረብኩትኝ የተከበረው
ፍ/ቤት ይህንን በመገናዛብ ከክሱ በናጸ እንድያሠናብታን በአክብሮት እጣይቃላው።

3 ኛ የተከበረው ፍ/ቤት

በኢትዮጵያ የፕሮጀክት ስራ አሠራር ህጎች ሶስት አካላት ስሆን አሠር ,ተቋራጭ እና አማካሪ ያላው ስሆን
የሰይት ተቆጣጣሪ መሐንዲስ ዳግም የአማካሪ አካል ስሆን ስራ ተቆጣጥሮ የማስቆም ህገዊ ስልጣን ያላው
,በህጋዊ አከል ተመዝግቦ ፍቀድ የተሠጠው ,ውክልና ያላው ስሆን እኔ የድርጅቱ የበላይ ቦርድ አመራር
የመቆጣጠር ስልጣን የሌለኝ መሆኑን

ኮንስትራክሽን አማካሪዎች የአሠራር መመርያ ቁጥር 881/2014 አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 5,6,11 እና
አንቀጽ 9 መሠረት ካጨምቡላ እስካ ጤና ጠቢያ የውሃ መሥመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ዝርጋታውን /ግንባታውን
ተቆጣጥሮ የማስቆም ፍቃድ/ስልጣን /ውክልና የሌለውን በመሆኑ ይህንን ፍ/ቤቱ በመገንዘብ በነጸ
እንዲያሰናብተኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

4 ኛ የተከባራው ፍ /ቤት

ከጫምቡላ እስካ ጤና ጠቢያ የውሃ መሥመር ዝርጋታ ፕሮጄክት ግምት እንዲያቀርብ


በተጠያኩት መሣረት እኔ 5 ኛ ተከሰሽ ግምት ያቀረቡት :.

1 ኛ 6 ኤንች ዪፕብስ ቱቦ ፕኤን 16

2 ኛ 6 ኤንች ዪፕብስ ገስኬት ፕኤን 16 እና ሌሎች እቃዎች ጭምር እኔ ግምት ያወጣሁት


መሆኑን የመከላከያ ምስክሮቼ ያስረዱ እና የአቃቤ ምስክር አመሠከከርም የእኔን የመከላከያ
ምስክሮቼ የሚደግፉ በመሆኑ እንዲሁም የሰነድ ማስረጃ ሀላባ ቁልቶ ከተማ ውሃ አገልግሎት
ድርጅት ያወጣሁት ግምት በደብዳቤ ቁጥር ሀወ 11-14/879 በቀን 1/9/2014 አ /ም ጋር ሁላት
ገጽ የተያያዘ ግምት ሰነድ ላይ በስሜና በፍርማዬ ያወጣሁት ያስረዳል ። ከዝም ግምት ሰናድ
ውጭ ሌላ አንድም ግምት ሰነድ ያወጣሁት የላም ፣ያዛጋጃሁት ደረሰኝ የላም ወይም, አንድም
ሌላ ግምት ሰነድ እንዲያዘጋጅ ያዛዛኝ የለም።በሌላ በኩል

1 ኛ 6 ኤንች ዪፕብስ ቱቦ ፕኤን 10


2 ኛ 6 ኤንች ዪፕብስ ገስኬት ፕኤን 10

ግምት አላዘጋጃውም,አልገዛውም,የተመሠካራ ነጋር የላብንም።

የመከላከያ ምስክሮቼ 6 ኤንች ዪፕብስ ቱቦ ፕኤን 10 እና 6 ኤንች ዪፕብስ ገስኬት ፕኤን 10


ግምት እኔ 5 ኛ ተከሰሽ አላመሆኔን ያስረዱ በመሆኑ እናም የአቃቤ ምስክሮች አንድም
የመሰካራ ነገር የሌላብኝ እንዲሁም የሰነድ ማስረጃ ሀላባ ከተማ ዉሃ አገልግሎት ድርጅት የእቃ
መጣየቅያ ዳረሠን ቁጥር 01836 በቃን 19/9/2014 አ/ም እና ግዥ መጣየቅያ ደራሠን ቁጥር
0737 እንዲውም በደብዳቤ ቁጥር ሀወ 11.04/980 በቃን 22/9/2014 አ/ም 6"ዪፕብስ ቱቦ
ፕኤኝ 10 እና ዪፕብስ ጋስኬት ፕኤን 10 ግምቱን ማን እንዳወጣ ,ማን ሠናዱን እንዳዘገጃ
እናማን እንዳጸዳቁ በስምና በፍርማ በግልጽ እያሣየ ከላው ህጋዊ ሰናድ መሥራጀ እኔ 5 ኛ
ተከሳሽ አለመሆኔን መረጋገጥና መረዳት ይቻላል።የተከበረው ፍርድ ቤት 6 ኤንች ዪፕብስ ቱቦ
ፒኤን 10 እና ጋስኬት ፒኤን 10 እንዲገዛ ግምት በመወጣት ያዘጋጀውሁት እኔ 5 ኛ ተከሳሽ
አለመሆኔን ህጋዊ የሰነድ ማሰረጃ እያስረዳ ሆኖ ሰሌ,እንድሁም አንድም የአቃቤ ምስክር
በልመሰከራበት እና የኦዲት ሪፖርት እኔ 5 ኛ ተከሳሽ አለመሆኔን እያስረዳ በላበት የአቃቤ
ምስክሮች አማሠከከር እኔን የሚደግፉ በመሆኑ እንድሁም በእኔ ላይ የቀረበው አንድም ሠነድ
ማስረጃ በሌለበት መሆኑን እና በክሱ ተያይዞ የቀረበው ኦዲት ሰነድ ማስረጃ በምንም ቱቦ ግዥ
ዲርግት /የገንዛብ ንክክ የሌለን መሆኑን እያረጋገጠ ሆኖ ሰሌ የታከበራው ፍ/ቤት ኮፕ ያቃራኩት
ስሆኝ ኦርጅናል ከውሃ አገልግሎት ድርጅት በትዛዝ በመሥመጣት መረጋገጥ የሚችል በመሆኑ
ይህንን በመገናዛብ ከክሱ በናጸ እንድያሠናብታን በአክብሮት እጣይቃላው።

5 ኛ የተከበረው ፍ/ቤት

ሀላባ ዞን ፖልስ መምሪያ ሀለባ ቁልቶ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤትን ሀለባ ቁልቶ ከተማ
ውሃ አገልግሎት ድርጅት የግዥና ሂሳብ ምርመራ ውጤት እንዲያቀርብ በቁጥር
624/72/71 በቀን 28/11/2014 አ/ም በሠጠው ትዛዝ በክልሉ የግዥ አፈጻጸም
መመሪያ ቁጥር 28/2010 መሠረት ኦዲት ተድርጎ ባቀረበው ጠቅላላ ኦዲት ውጤት
ላይ እኔ 5 ኛ ተካሳሽ ምንም አይነት የተግባር ሆና የገንዘብ ጉደለት የሌላ መሆኑን
እያረጋገጠ ሆኖ ሳሌ እንዲሁም የሀላባ ቁልቶ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የሀገር
ውስጥ የጫራታ ኮምቴ ሰናድ በምን ቀን ,ዬት ቦታ , ለሞን አላማ,ስብሳባ ተሳብስቦ በመወያየት
ውሳኔ ሀሳብ ያቀረቡ እናማን እንዳነበሩ በስምና በፈርማ እያረጋገጠ መን አጽድቆ የታገዘ ቱቦ
መሆኑን በግልጽ በህጋዊ ማህተም የተደገፈ የሰነድ ማስረጃ እያስረዳ ሆኖ ሰሌ ምንም አይናት
የተግባር ተስትፎ የሌላብን መሆኑን እና ኮፕ ያያዝኩት ስሆን ኦርጅናሉ በውሃ
አገልግሎትድርጅት ያለህ በመሆኑ በትዛዝ በመሥመጣትእኔ 5 ኛ ተከሳሽ የጨረታ ኮምቴ
አለመሆኔን በመረጋገጥ እና ይህንን በማገናዛብ ከክሱ በናጸ እንድያሠናብታን በአክብሮት
እጣይቃላው።

6 ኛ የተከበረው ፍ/ቤት

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የከተሞች ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት
ድርጅት አዋጅ ቁጥር 170/2009 አንቀጽ 25 መሠረት እኔ 5 ኛ ተከሳሽ ሥራ አለመሆኔን
እያስረዳ ሆኖ ሳሌ አቃቤ ህግ ለክሱ ያቀረበው የኦድት የሠናድ መሥራጃ ለእኔ መከላከያ
ማሰረጃ በመሆኑ አንዲት የተግባር ጉደለት በቀረበው ኦድት ግንት የሌላብኝ መሆኑ እና የአቃቤ
ምስክሮች አማሠካካርም የእኔን መከላካያ ምስክሮቼን የሚዳግፍ መሆኑ ይህም ዳግም ከላይ
ተራቁጥር 4 ኛ,5 ኛ ላይ የጠቀስኩት ሰናዶችንና ዳራሰኖች እውነት መሆኑን የኦድት ርፖርት
የሚያስረዳ በመሆኑ የተከበረው ፍ/ቤት ይህንን በመገናዛብ ከክሱ በናጸ እንድያሠናብታን
በአክብሮት እጣይቃላው።

7 ኛ የተከበረው ፍ/ቤት እኔ የገባሁት ውል የሌላ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ውሉን በትዘዝ አስመጥቶ


እንዲያዩ እፈልጋለሁ ።

በአጠቃላይ ያቀረብኩት የሠው መከላከያ ምስክሮቼ በደንብ የተከለከሉብኝና ያስረዱ በመሆኑ


እንዲሁም ያቀረብኩት የሠነድ ማሰረጃ ይህንን የሚያስራዳ ስሆን የአቃቤ ምስክሮች
አመሠካካርም እኔን መከላከያ ምስክሮቼንና የሠነድ ማሰረጃ የሚደገፉ ስሆን ከሳሽ አቃቤ ህግ
በእኔ ለይ አንድም የሰነድ ማስረጃ ያላቀረበ በመሆኑ የተከበረው ፍ/ቤት እኔ 5 ኛ ተከሳሽ ላይ
በዳንብ አይቶና አገናዝቦ ከቀራባብኝ ክስ በነጻ እንዲያሰናብተኝና ጉዳትና የሞራል ከሳዬኝ
እንድጠብቃኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ ።
ለሀላበ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀን 19/8/2015

ቁልቶ

ጉደይ:. መካለከያ ማሰረጃ ዝርዝርና ስለመቅብ ይሆነናል ።

ከላይ በተገለጸው መሠረት እኔ የሕግ ተከሳሽ መንሱር ጃማል በተከሰስኩበት የወንጀል ክስ ጉደይ ፍርድ ቤት መከላከያ
ማስረጃ ይዤ እንድቀርብ ለቀን 25/08/2015 ባዘዘው መሠረት የመከላከያ ምስክሮች

የሠው ምስክሮች

1/ አብድራህማን ሙህድን 3/ ጌቱ ማሞ

2/ ሸምሱ በድሩ 4/ መኣዛ ብርሃኑ

የሠነድ ማስረጃዎች

1 ኛ/ እኔ 5 ኛ ተከሳሽ ያቀረብኩት ግምት በደብዳቤ ቁጥር ሀወ 11.14/879 ጋር የተያያዘ በድምሩ 3 ገጽ ኮፕ(ዋና


በተቋሙ)

2 ኛ/ በላይ ሀላፊዎች የቀረበው ሌላ ግምት በደብዳቤ ቁጥር ሀወ 11.04/980 አንድ ገጽ ኮፕ(ዋና በተቋሙ)
3 ኛ/ የሀላባ ቁልቶ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የእቃ መጣያቅያ ላይ ሌላ ግምት የተሞላበት ደርሰን ቁጥር 01836
አንድ ገጽ ኮፕ

4 ኛ/ የሀላባ ቁልቶ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የእቃ ግዥ መጣያቅያ ደርሰን ቁጥር 0737 አንድ ገጽ ኮፕ (ዋና
በተቋሙ)

5 ኛ/ የሀላባ ቁልቶ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቱቦ እንዲያመጣ የተላከው በላሙያ የሚያሳይ ዳብዳቤ አንድ ገጽ ኮፕ
እና የእቃ ማስራከብያ ደርሰን ቁጥር 0653 አንድ ገጽ ኮፕ(ዋና በተቋሙ)

6 ኛ /የሀላባ ቁልቶ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የጨረታ ኮምቴ የሚያሳይ አንድ ገጽ ኮፕ

7 ኛ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/የከተሞች ውሃና ፍሰሽ አገልግሎት ድርጅት አዋጅ 170/2009 አስራ ስምንት ገጽ ኮፕ

8 ኛ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/የከተሞች ውሃና ፍሰሽ አገልግሎት ድርጅት ደንብ 160/2010 አስራ ሶስትገጽ ኮፕ

9 ኛ/ የኮንስትራክሽን አማካሪዎች የአሠራር መመርያ ቁጥር 881/2014 የአስራ ሰባት ገጽ ኮፕ

10 ኛ/ በክሱ ለይ ተያይዞ የቀረበውን የኦዲት ሪፖርት እንዲታይልኝ።

11 ኛ/ የጨረታ ኮምቴ ቱቦ የገዛበት ፕሮፎርማ በፍርድ ቤት ትዛዝ ተቃርቦ ከፋይሉ ጋር ተያይዞ እንድታይሊኝ።

ከሠላምታ ጋር መንሱር ጃማል

You might also like