You are on page 1of 2

ቀን --------------------------

ለኦሮሞ ብሔረሰብ አስ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

ከሚሴ

ከሳሽ ---- ኡመር ኑሬ ሀሰን ተወካይ-ሀሰን ኑሬ ሀሰን አድረሻ ጎዳ

ተከሳሽ -- 1 ኛ/ አብደላ ሸህ ሰያር አድራሻ ጎዳ

2 ኛ/ ሸህ ሰያር አሊ አድራሻ ጎዳ

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 222 መሰረት የቀረበ ነው

ሀ/ ፍርድ ቤቱ ክሱን የማየት ስልጣን አለው

ለ/ ከሳሽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33 መሰረት የመክሰስ መብት አለኝ

ሐ/ ከሳሽ እና ተከሳሽ በህግ ችሎታ የላቸውም አልተባለም

መ/ የምከራከረው በወኪሌ ወይንም በጠበቃ ነው

ሠ/ የክሱ ምክንያት በእምነት ለተከሳሽ በአካውንቱ ያስገባሁለትን ብር 1,066,000 (አንድ ሚሊዬን ስልሳ ስድስት ሺ)
እንዲከፍሉኝ የቀረበ ክስ ነው

የክሱ ዝርዝር በአጭሩ

ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት 1 ኛ እና 2 ኛ ተከሳሽ አባት እና ልጅ ሲሆኑ ከእነዚሁ ተከሳሾች ጋር በነበረኝ መተማመን
በቀን 22/11/2013 ዓ.ም ብር 1,066,000 (አንድ ሚሊዬን ስልሳ ስድስት ሺ) በአንደኛ ተከሳሽ አብደላ ሸህ ሰያር
አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሰንበቴ እና በከሚሴ ቅርንጫፍ ገቢ አድርጌለት ወስዷል. አከፋፈሉንም በተመለከተ
የ 1 ኛ ተከሳሽ ወንድሞች እንዲሁም የ 2 ኛ ተከሳሽ ልጆች የሆኑት ሰኢድ ሸህ ሰያር እና አህመድ ሸህ ሰያር ይሰጡሃል
በማለት ሃላፊነቱንም እነዚህ 1 ኛ እና 2 ኛ ተከሳሾች በግልፅ ወስደዋል በወሰዱት ሃላፊነትም መሰረት ለ 1 ኛ ተከሳሽ ገቢ
ካደረኩት ጠቅላላ ገንዘቤ ከብር 1,066,000 (አንድ ሚሊዬን ስልሳ ስድስት ሺ) ላይ ብር 250,000 (ሁለት መቶ ሀምሳ ሺ)
ሲሰጡኝ ቀሪውን ብር 816,000 (ስምንት መቶ አስራ ስድስት ሺ) ለ 5 ተከታታይ ወር እኔም ሆንኩ የሀገር ሽማግሌዎች
ተከሳሾች ያለባቸውን ገንዘብ እንዲከፍሉ ቢጠይቁም ያልተገባ ምክንያት በመስጠትና ዛሬ ነገ እያሉ ገንዘቤን ሊከፍሉኝ
ባለመቻላቸው በመጉላላትና በመንከራተት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰብኝ እገኛለሁ.

የተከበረውን ፍ/ቤት የምጠይቀው ዳኝነት

1 ኛ/ በሁለቱም ተከሳሾች ሃላፊነት እና በአንደኛ ተከሳሽ የግል አካውንት ገቢ ካደረኩት ብር 1,066,000 (አንድ
ሚሊዬን ስልሳ ስድስት ሺ) ላይ የተከፈለኝ ብር 250,000 (ሁለትመቶ ሃምሳ ሺ) ብቻ በመሆኑ ተከሳሾች በገቡት
ሃላፊነት መሰረት በፍ/ብ/ሕ/አንቀጽ 1896 መሰረት የማይከፈልና የማይነጣጠል ሃላፊነት ስላለባቸው ቀሪውን ብር
816,000 (ስምንት መቶ አስራ ስድስት ሺ) ይከፈለው ተብሎ እንዲወሰንልኝ.

2 ኛ/ ለዚህ ክስ ያወጣሁትን ወጭና ኪሳራ በቁርጥ የጠበቃ አበል 10% እና የዳኝነት ክፍያ በታሪፍ መሰረት
ተከሳሾች ይክፈሉ እንዲባልልኝ.

ያቀረብኩት ክስ እውነት መሆኑን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 92 መሰረት አረጋግጣለሁ.

ከሳሽ ኡመር ኑሪ ተወካይ ሀሰን ኑሬ ሀሰን

You might also like