Professional Documents
Culture Documents
የሐይቅ ዳር ዕድር ቃለ መሐላ
የሐይቅ ዳር ዕድር ቃለ መሐላ
ቀን፦ 14/06/2016.ዓ.ም
ሀዋሳ
ተከሳሽ፦ አቶ ካቻው ሙኤ
በከሳሽና በተከሳሽ መካከል በአለው የአፈፃፀም ክስ ከፍ/ቤቱ ለአፈ/ተከሳሽ መጥሪያ የተላከና መጥሪያውን የአፈ/ከሳሽ
ለማድረስ በአደረኩት ጥረት በቀን. 10/06/2016.ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 የአፈ/ተከሳሽ መጥሪያውን በምስክሮች ፊት
ለመቀበል ፈቃደኛ አልነበረም 2 ኛ/ በቀን 11./06/2016.ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 የተከሳሽ ያለበት ቤት ድረስ በመሄድ
በፖሊስ አባል በሻምበል ተመስገን አማካይነት ለመስጠት በተደረገው ጥረት የአፈ/ተከሳሽ ሆን ብሎ የፍ/ቤቱን መጥሪያ
ላለመቀበል " ከቤት የለም" በማስባል እየሸሸና እየተደበቀ በማስቸገሩ በተጨማሪ የአፈ/ተከሳሽ ለአቅመ ሄዋን የደረሰች
ልጁም መጥሪያውን ላለመቀበል እምቢተኛ ሆናለች በመሆኑም የአፈ/ከሳሽ የፍ/ቤቱን መጥሪያ በዚህ ቃለ መሀላ
ተመላሽ ለማድረግ ችያለሁ።
ስለዚህ ክቡር ፍ/ቤቱ በአፈ/ተከሳሽ ሆን ብሎ መጥሪያ ላለመቀበልና ፍርዱንም ላለመፈፀም እየሸሸ በመሆኑ የተከበረው
ፍ/ቤት በህጉ መሠረት ትዕዛዝ እንዲሰጥልኝ አመለክታለሁደ
አቤቱታው እውነት ነው
2 ኛ/አቶ ግርማ ማሞ
3 ኛ/ ሻምበል ተመስገን