You are on page 1of 2

Hojii Tajaajila Hiikkaa Afaanii Aliyyii Nugusee

አልዪ ንጉሴ የቋንቋ ትርጉም ሥራ አገልግሎት


Aliyi Nigussie Language Translation Service

ቁጥር፡ 244509
ቀን፡ 22/09/2015
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት
አዲስ አበባ
ይግባኝ ባይዋ፡ ወ/ሮ ምስራቅ አለሙ
አድራሻ፡ ምስራቅ ባሌ ዞን፣ ግኒር ከተማ፣ አገምሳ ቀበሌ
መልስ ሰጭዎች፡ 1ኛ ወ/ሮ የሻረግ ተፈራ
አድራሻ፡ ምስራቅ ባሌ ዞን፣ ግኒር ከተማ፣ ኤጄርሳ ዋሪ ቀበሌ
2ኛ ወጣት ቡሽ ሙላት ለማ
አድራሻ፡ ምስራቅ ባሌ ዞን፣ ግኒር ከተማ፣ ኦዳ ቀበሌ
ይህ የአሁኑ መልስ ሰጭዎች በቅሬታዬ ላይ በቀን 26/08/2015 በጽሑፍ ያቀረቡት 3(ሶስት) ገጽ የደረሰኝ
መልስ ላይ፣ የመልስ መልስ ማቅረቤን ይሆናል፡፡
የመልስ መልስ ዝርዝር በዝርዝር
በ1ኛ ዝርዝር ላይ ከቀረበው መልስ ጋር ተያይዞ፤ እኔ ሕፃን ማክቤል ሙላት የሚባለውን ያገኘሁት፣ ከሟቹ
ጋር እንደ ባልና ሚስት እየኖረን እና የሞተም ትዳር ውስጥ አብረን እያለን የሞተ እና የእሱ ለቅሶንም
ያጣውለት እኔ ነኝ፡፡ ይህን መሬት አስመልክቶ ከመጀመሪያ ጀምሮ KIO ለሶስት (3) ዓመት በላይ ሳይለማ
ስለቀረ፣ ወደ ካዝና ለመመለስ ሂደት ላይ ያለው የመጀመሪያ መብት ለእኔ እንደምገባኝና ለማልማት ችሎታ
እንደአለኝ የገለፅኩትና የኢንቨስትመንት ፈቃድና የይዞታ ባለቤትነት የተሰጠኝ ነው፡፡ በፍርድ ቤቱ የእሱ
ሚስት መሆኔን ያረጋገጥኩት እና የዚህ ሟች ልጅ አሳዳጊ መሆኔን ያረጋገጥኩት፣ ያን የመጀመሪያ መብት
እንዲያገኝ እንደ ማስረጃ ተጠቀምኩ እንጂ፣ ፍርድ ቤቱ አስገድዶ ያስፈፀመልኝ አንድም የለኝም፡፡ ምክንያቱም
ፍርድ ቤቱ የኢንቨስትሜንት መሬት አስገድዶ ለማስፈፀም ሥልጣን የለውም፣ ውሣኔ መስጠት የሚችለው ያን
መሬት የማልማት ችሎታ ያለው KIO አይተው፣ መርምረው የአስተዳዳሪ ውሣኔ ይሰጣል እንጂ፣ ስለዚህ
በዚህ በኩል መልስ ሰጭዎች ያነሱት መልስ የሕግ አግባብነት ስለሌለው ውድቅ ነው፡፡
በ2ኛ ዝርዝር ላይ ከቀረበው መልስ ጋር ተያይዞ፤ ይህ መሬት ላይ እኔ የአሁኑ ይግባኝ ባይዋ
የኢንቨስትመንት ፈቃድና የይዞታ ባለቤትነት ሥልጣን ባለው አካል ተሰጥቶኝ በእጄ ያለኝ ነው፡፡ ይህ መሬት
ደግሞ በእጄ ያለው፣ የይዞታ እና የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከላዩ ያለኝ፣ የሚገብርበት እና ለመንግስት
የሚያስፈልገውን ክፍያ ከፍዬበት፣ ተሰጥቶኝ ያለው ነው፡፡ ይህ መሬት የኢንቨስትሜንት ቦታ መሆኑ
ተረጋግጦ ባለበት፣ ሟቹም ያለውን መብት አጥቶ ባለበት፣ የአርሶአደር መሬት ያልነበት ቦታ፣ ያለአግባብ
በኢንቨስትሜት ተቃራኒ በመሄድ፣ ፍቃዴንም ሰርዞ፣ ወራሾች በእኩል ይካፈሉ በማለት የተሰጠው ውሣኔ
መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለው እና መልሳቸውም የሕግ መሠረት የሌለው ስለሆነ ውድቅ ነው፡፡
በ3ኛ ዝርዝር ላይ ከቀረበው መልስ ጋር ተያይዞ፤ መልሳቸው ትክክል እንዳልሆነ እኔ ለልጄ የእሱ ድርሻ ብዬ
የጠየኩት አንድም ነገር የለም፡፡ ለእሱ የማይገባ የውርስ ድርሻ ያስተላለፍኩለትም የለም፡፡ መሬቱ
የኢንቨስትሜንት መሬት ስለሆነ፣ እኔ ደግሞ የሟቹ ሚስት ስለሆንኩኝ፣ ይህ መሬት ወደ ሌላ ሰው
Hojii Tajaajila Hiikkaa Afaanii Aliyyii Nugusee
አልዪ ንጉሴ የቋንቋ ትርጉም ሥራ አገልግሎት
Aliyi Nigussie Language Translation Service

ከሚተላለፍ፣ የማልማት ችሎታ ስላለኝ፣ የመጀመሪያ መብት ለእኔ ተሰጥቶች እንዲያለማ በማለት የጠየኩት
እና ፈቃድ እና የኢንቨስትሜንት ይዞታንም በስሜ ብቻ የተሰጠኝ እንጂ፣ በልጄ ስም ወይም በስሜና በልጄ
ስም ጠቅሶ የሰጡኝ አንድም ማስረጃ የሌለ መሆኑ፣ የኢንቨስትሜንት ፈቃድ ማስረጃ እና የይዞታ ባለቤትነት
አያይዤ ያቀረብኩት ውስጥ በግልጽ መረዳት የሚቻል ነው፡፡ ይህ ሆኖ ባለበት ቦታ ለልጄ ለማክቤል ሙላቱ
ይህ መሬት ሙሉ በሙሉ የተሰጠ አድርጐ እሱን ከሶት እየተከራከሩት ያለው በማስመሰል ያቀረቡት መልስ
ከእውነት የራቀ እና የሕግ መሠረት የሌለው ስለሆነ ውድቅ እንዲሆንልኝ፡፡
በ4ኛ ዝርዝር ላይ ከቀረበው መልስ ጋር ተያይዞ፤ በሥር ፍርድ ቤት በግልጽ መሬቱ የኢንቨስትሜንት መሬት
መሆኑ፣ የመጀመሪያ መብት እንደምገባኝ እና የማልማት ችሎታ ስላለኝ፣ ለዚህም ሥልጣን ያለው አካል
የሰጠኝ መሆኑንና ይህ ክርክር ቢሆንኳን ሥልጣን ያለው አካል ጋር በመሄድ ማለትም KIO እና በደረጃ
ባሉት የኢንቨስትሜንት ጽ/ቤቶች ጋር በመነጋገር መፍትሄ የሚያገኝ ጉዳይ እንጂ፣ ፍርድ ቤቱ እንደ
አርሶአደር መሬት የኢንቨስትመንት መሬት ተከፋፈሉ ብሎ መወሰን የማይችል መሆኑን በግልጽ በቀጥታና
በተዘዋዋሪ እየከራከርኩ እያለ የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ የሰጠው መሆኑ ከመዝገብ ውስጥ መረዳት የሚቻል
ነው፡፡ ይህ በሆነበት ቦታ በሥር ፍርድ ቤት ተነስቶ ያልከራከርኩትን ጭብጥ እዚህ ያስነሳሁት በማስመሰል
የከራከሩት የሕግ መሠረት የሌለው ነው፡፡ አንድ ፍርድ ቤት ከሳሹ ያነሰውን የዳኝነት ጥያቄ ጭብጥ ብቻ
ሳይሆን መመዘን ያለበት፣ ተከሳሹ ያነሳውን የሕግ ጥያቄ ጭብጥንም እኩል በሆነ የመመዘን ግዴታ ያለበት
ነው፡፡ ነገር ግን በክርክሩ ውስጥ እኔ የጠየኩት የዳኝነት ጥያቄ ጭብጥ ወደ ጐን በመተው፣ ይህ የአሁኑ
መልስ ሰጭዎች ያነሱት ጥያቄ ላይ ብቻ በመንጠልጠል ማንኛውም የሚሰጠው ውሣኔ ሀቅ የሌለውና ወደ
አንድ ጐን የአደለ መሆኑን በግልጽ ከመዝገብ ውስጥ መረዳት የሚቻል ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ በኩል የተነሳ
መልስ የሕግ መሠረት የሌለው እና ከእውነት የራቀ ስለሆነ ውድቅ ነው፡፡
በአጠቃላይ ፍርድ ቤቱን የሚጠይቀው ዳኝነት
1ኛ ይህ የአሁኑ መልስ ሰጭዎች ያነሱት መልስ ከላይ በተገለፀው ምክንያቶች ሀቀኝነት እና የሕግ መሠረት
የሌለው ስለሆነ፣ ውድው ሆኖ፣ በእኔ ጥያቄ መሠረት የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ
አንቀጽ 348/1/ መሠረት በመሻር እንዲወሰንልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁኝ፡፡
2ኛ ለዚህ ምክንያት የደረሰብኝ ወጪና ኪሣራ የጠበቃ አበልን ጨምሮ እንዲከፍሉልኝ፣ እንዲወሰንልኝ
በአክብሮት ጠይቃለሁ፡፡
ይህ መልስ እውነት እና ትክክል መሆኑን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ አንቀጽ 92 መሠረት አረጋግጣለሁ፡፡

You might also like