Professional Documents
Culture Documents
Asefa Mamo
Asefa Mamo
መ/ቁ--156302
ቀን -05/03/2016 ዓ.ም
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ 4 ኛ ፍ/ብሄር ችሎት
አዲስ አበባ
ከሳሾች፡- 1 ኛ/ አቶ አሰፋ ማሞ
2 ኛ/ ወ/ሮ ታፈሰች ማሞ
3 ኛ/ አቶ ጌታቸው ማሞ
4 ኛ/ ወ/ሮ እምወድሽ ማሞ
5 ኛ/ ወ/ሮ ብርቱካን ማሞ
6 ኛ/ አቶ መላኩ ማሞ
ከሳሾች ጥቅምት 07 ቀን 2016 ዓ.ም ላቀረቡት ክስ ከ 5 ኛ ተከሳሽ የቀረበ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና በአማራጭ
የቀረበ የመከላከያ መልስ ነው፡፡
1. የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
1.1 ከሳሾች በይዞታው ላይ ክስ ለማቅረብ መብት የሌላቸው ስለመሆኑ፡- ከሳሾች ቦታው በእኛ ይዞታ ስር
ነበር ይበሉ እንጂ ይህ ስለመሆኑ ምንም አይነት አግባብነት ያለው ማስረጃ አላቀረቡም እነደማስረጃ
የቀረቡት የእርሻ መሬት የግብር ደረሰኞችም ቢሆኑ በግብር ደረሰኝ አካራካሪው ይዞታ ላይ ያለን
መብት ለማስረዳት የማይቻል እና ደረሰኞቹ ክርክር ለተነሳበት ይዞታ ስለመገበራቸው የማያመለክቱ
እና በህግ ፊትም የፀና ውጠየት የላቸውም፡፡ ሌላኛው ከሳሾች ወራሾች ነን ብለው ያያያዙት
ማስረጃም የየትኛውን የሟቾች ንብረት እንደወረሱ የማያመለክት እና ሟቾች ያልነበራቸውን መብት
ወራሾች ሊወርሱ ስለማይችሉ እንዲሁም ስልጣን ባለው አካል ክርክር ለተነሳበት ቦታ ባለመብት
ስለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ባላቀረቡበት ይህንን ክስ ለመመስረት ስለማይችሉ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33/2
መሰረት አለን የሚሉትን መብት እና ጥቅም በተገቢው አላስረዱም ተብሎ በብይን ውድቅ
እንዲደረግልን፡፡
1.2 ከሳሾች 5 ኛ ተከሳሽ ለቀሪዎቹ ተከሳሾች አላግባብ ካርታ ሰርቶ ሰጥቶብኛል ይህ የሰጠው
ካርታ ህገወጥ ነው ተብሎ ውሳኔ እንዲሰጠኝ በሚል የቀረበ ክስ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ይህ
ጉዳይ በመጀመሪያ ደረጃ መቅረብ ያለበት በአስተዳደር ስነስርአት አዋጅ ቁጥር 1183/2011
መሰረት መሰል አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን እና እርምጃዎችን ተገቢ አይደሉም መብቴን
ይጎዳሉ ብሎ የሚያምን ማንኛውም አካል በቅድሚያ ለሚመለከታቸው አስተዳደራዊ
ተቋማት ቅሬታቸውን አቅርበው ማለትም አስተዳደራዊ መፍትሄን አሟጠው የመጨረሻ
ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በዚህም ውሳኔ ቅር የሚሰኝ አካል ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
አስተዳደራዊ ችሎት ጉዳዩን ከሚያቀርብ በቀር በቀጥታ መደበኛ ፍርድ ቤት ላይ ክርክር
ሊያቀርብ አይችልም፡፡ስለሆነም ከሳሾች ያቀረቡት ክስ በዚህ አዋጅ የተመላከተውን ስነስርዐት
ያልተከተለ እና ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ለሌለው ፍ/ቤት የቀረበ በመሆኑ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ
244/2/ሀ መሰረት መዝገቡ በብይን ውድቅ እንዲደረግልን እና ለተጉላላንበት በቂ ኪሳራ
በቁርጥ ከሳሾች እንዲከፍሉን ተብሎ ውሳኔ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን፡፡
መ/ቁ--156302
ቀን -05/03/2016 ዓ.ም
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ 4 ኛ ፍ/ብሄር ችሎት
አዲስ አበባ
6 ኛ/ አቶ መላኩ ማሞ