Professional Documents
Culture Documents
Buresie Beyuu
Buresie Beyuu
መ//ቁ--መ/ቁ-147737
ቀን -01/10/2015 ዓ.ም
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ 6 ኛ ፍ/ብሄር ችሎት
አዲስ አበባ
2 ኛ/ አቶ በቀለ በዩ ደሞ
6 ኛ/ አቶ አዲሱ መኮንን
7 ኛ/ አቶ ሃብታሙ ፍቃዱ
ከሳሾች ሚያዚያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ላቀረቡት ክስ ከ 8 ኛ ተከሳሽ የቀረበ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና በአማራጭ
የቀረበ የመከላከያ መልስ ነው፡፡
1. የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
1.1 ከሳሾች በይዞታው ላይ ክስ ለማቅረብ መብት የሌላቸው ስለመሆኑ፡- ከሳሾች ቦታው በእኛ ይዞታ ስር
ነበር ይበሉ እንጂ ይህ ስለመሆኑ ምንም አይነት አግባብነት ያለው ማስረጃ አላቀረቡም እነደማስረጃ
የቀረቡት የእርሻ መሬት የግብር ደረሰኞችም ቢሆኑ በግብር ደረሰኝ አካራካሪው ይዞታ ላይ ያለን
መብት ለማስረዳት የማይቻል እና ደረሰኞቹ ክርክር ለተነሳበት ይዞታ ስለመገበራቸው የማያመለክቱ
እና በህግ ፊትም የፀና ውጠየት የላቸውም፡፡ ሌላኛው ከሳሾች ወራሾች ነን ብለው ያያያዙት
ማስረጃም የየትኛውን የሟቾች ንብረት እንደወረሱ የማያመለክት እና ሟቾች ያልነበራቸውን መብት
ወራሾች ሊወርሱ ስለማይችሉ እንዲሁም ስልጣን ባለው አካል ክርክር ለተነሳበት ቦታ ባለመብት
ስለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ባላቀረቡበት ይህንን ክስ ለመመስረት ስለማይችሉ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33/2
መሰረት አለን የሚሉትን መብት እና ጥቅም በተገቢው አላስረዱም ተብሎ በብይን ውድቅ
እንዲደረግልን፡፡
1.2 ከሳሾች 8 ኛ ተከሳሽ ለቀሪዎቹ ተከሳሾች አላግባብ ካርታ ሰርቶ ሰጥቶብኛል ይህ የሰጠው ካርታ
ህገወጥ ነው ተብሎ ውሳኔ እንዲሰጠኝ በሚል የቀረበ ክስ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ይህ ጉዳይ ሙሉ
ለሙሉ መቅረብ ያለበት ለፍርድ ቤቶች ሳይሆን ለራሱ ለአስተዳደሩ ቅሬታቸውን ከማቅረብ በቀር
ፍርድ ቤት የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም ሰበርም በተደጋጋሚ አስገዳጅ ፍርድ የሰጠበት ጉዳይ ነው ይህ
እንዳለ ሆኖ ፍርድ ቤቶች ስልጣን አላቸው ቢባል እንኩዋን በአስተዳደር ስነስርአት አዋጅ ቁጥር
1183/2011 መሰረት መሰል አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን እና እርምጃዎችን ተገቢ አይደሉም መብቴን
ይጎዳሉ ብሎ ለሚያምን ማንኛውም አካል በቅድሚያ ለሚመለከታቸው አስተዳደራዊ ተቋማት
ቅሬታቸውን አቅርበው ማለትም አስተዳደራዊ መፍትሄን አሟጠው የመጨረሻ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ
በዚህም ውሳኔ ቅር የሚሰኝ አካል ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስተዳደራዊ ችሎት ጉዳዩን
ከሚያቀርብ በቀር በቀጥታ መደበኛ ፍርድ ቤት ላይ ክርክር ሊያቀርብ አይችልም፡፡ስለሆነም ከሳሾች
ያቀረቡት ክስ በዚህ አዋጅ የተመላከተውን ስነስርዐት ያልተከተለ እና ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ለሌለው
ፍ/ቤት የቀረበ በመሆኑ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 244/2/ሀ መሰረት መዝገቡ በብይን ውድቅ እንዲደረግልን እና
ለተጉላላንበት በቂ ኪሳራ በቁርጥ ከሳሾች እንዲከፍሉን ተብሎ ውሳኔ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን፡፡
2.1 ከሳሾች ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ አርሶአደር ስለመሆናቸው ባልተረጋገጠበት እንዲሁም በይዞታው
ላይ መብት እንዳላቸው ያረጋግጥልናል ብለው ያቀረቡት የእርሻ መሬት ግብር ደረሰኞችም ቢሆኑ
በግብር ደረሰኝ አካራካሪው ይዞታ ላይ ያለን መብት ለማስረዳት የማይቻል እና ደረሰኞቹ ክርክር
ለተነሳበት ይዞታ ስለመገበራቸው የማያመለክቱ እና በህግ ፊትም የፀና ውጠየት የላቸውም፡፡ ሌላኛው
ከሳሾች ወራሾች ነን ብለው ያያያዙት ማስረጃም የየትኛውን የሟቾች ንብረት እንደወረሱ
የማያመለክት እና ሟቾች ያልነበራቸውን መብት ወራሾች ሊወርሱ ስለማይችሉ እንዲሁም ስልጣን
ባለው አካል ክርክር ለተነሳበት ቦታ ባለመብት ስለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ባላቀረቡበት ያከራከረው
ይዞታ ተወስዶብናል በከሳሾች የተጠየቀው የይዞታ ይመለስልኝም ሆነ የካርታ ይምከንልኝ አቤቱታ
ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ የከሳሾች አቤቱታ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ተደርጎ አላግባብ ተከሰን
ለተጉላላንበት በቂ ኪሳራ በቁርጥ እንዲተኩልን እንጠይቃለን፡፡
2.2 8 ኛ ተከሳሽ ከ 1 ኛ እስከ 5 ኛ ተከሳሾች ካርታ ያላግባብ ሰርቶ ሰጥቶብኛል በሚል የቀረበው ክስ
በተመለከተ ከወረዳው ተጣርቶ በመጣው መሰረት ህግና መመሪያን ተከትለን ለተከሳሾች ካርታ
መስጠታችን በአግባቡ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ከሳሾች በይዞታው ላይ መብት እና ጥቅም እንዳላቸው
ባላረጋገጡበት እና በማስረጃ ባላስደገፉበት በአስተዳደር በኩል እልባት ማግኘት ያለበትን ጉዳይ ወደ
ፍርድ ቤት ማምጣታቸው ተገቢነት የሌለው እና የፍድ ቤቱ ስልጣንም ባልሆነበት የቀረበ ክስ በመሆኑ
ከሳሾች በይዞታው ላይ መብት እና ጥቅም እንዳላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ባላቀረቡበት የቀረበ ክስ
በመሆኑ እና ተከሳሽ መ/ቤትም ህግና መመሪን በመከተል በሰራቸው እና መብት እንዲፈጠር ማድረጉ
የተሰጠው ተግባር እና ሃላፊነት በመሆኑ እና በማስረጃ ላይ ያልተደገፈ ከእውነት የራቀ ክስ ስለሆነ
የከሳሾች አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግልን እንጠይቃለን፡፡
የቀረበው መልስ በእውነት የቀረበ መሆኑን
በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 92/3 መሰረት እናረጋግጣለን፡፡
1. ለተከሰስንበት መልስ ለመስጠት እንዲያመቸን ከ 8 ኛ ተከሳሽ በድጋሜ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 205
በቃለመሃላ ተደግፎ የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡
ለተከሰስንበት ክስ በቂ ምላሽ ለመስጠት ማስረጃዎችን ማሰባሰብ ላይ የነበርን ቢሆንም ማስረጃዎቹን ለማግኘት ወረዳ ድረስ በመውረድ
ማጣራት በማስፈለጉ እና በ 8 ኛ ተከሳሽ መ/ቤት የቢሮ ለውጥ በመደረጉ ሰነዶችን በአጭር ጊዜ ፈልጎ ማግኘት ላይ የተቸገርን ሲሆን
ሌላው ዋንኛ ምክንያት መረጃዎችን በኮምፒውተር በሲስተም ፋይል የተደረጉት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ቢሮ በመቀየሩ ምክንያት
ወደ ስራ ያልገቡ እና በኮምፒውተር መረጃ ማግኘት ያልቻልን በመሆኑ እና ዋንኛ የማስረጃ ምንጫችንም ዳታ ቤዝ ላይ የተቀመጠው
መረጃ በመሆኑ እንደ ጽ/ቤት ሴስተም ወደ ስራ በቅርቡ ስለሚገባ ይህንን ታሳቢ ተደርጎ ተገቢውን ማስረጃ ለማግኘት የተቸገርን
በመሆኑ በቂ ምላሽ ለመስጠት እና ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ይረዳን ዘንድ መልስ ይዞ ለመቅረብ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠን
እንጠይቃለን፡፡
ቁጥር-ቦ/ክ/ከ/ፍ/ጽ/ቤት----------
ቀን -04/09/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
2 ኛ/ አቶ በቀለ በዩ ደሞ
6 ኛ/ አቶ አዲሱ መኮንን
7 ኛ/ አቶ ሃብታሙ ፍቃዱ
በቀን 01/09/15 በደብዳቤ ቁጥር ቦ/ክ/ከ/መ/ል/አስ/ጽ/ቤት 11132/15 ለላካችሁልን ክስ መልስ አዘጋጀተን ለመስጠት ይረዳን ዘንድ
በእናተ በኩል የሚከተሉትን ማስረጃዎች ከማብራሪያ ጋር በ ሶስት ቀን ውስጥ እንድትልኩልን እንጠይቃለን፡፡
1. ክርክር ያስነሳው በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል ውስጥ ልዩ ቦታው ሸማቾች ቀጠና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው
በሰሜን አቶ ፍቃዱ ዱባለ በደቡብ አቶ ባህሩ እና አቶ አባያ ራያ በምስራቅ መንገድ እና በምዕራብ ፅጌ ወ/ሃና እና አቶ ባህሩ
የሚያዋስኑት በግምት 2800 ካ.ሜ ነው በማለት ክስ የቀረበበት ይዞታ
2. ቀድሞ በማን እጅ እንደነበር አሁን በማን እጅ ተይዞ እንደሚገኝ እና የይዞታው ህጋዊ ባለቤት ማን እንደሆነ ይገለፅ
3. ይህ ክርክር የተነሳበት ይዞታ ቀድሞ በከሳሾች እጅ ነበር ወይስ አልነበረም?በከሳሾች እጅ ነበር ከተባለ በምን አግባብ
ከእጃቸው ሊወጣ እንደቻለ ካሳ እና ምትክ ማግኘት አለማግኘታቸው ተብራርቶ ይገለፅ
4. ከሳሾች ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ አርሶ አደር ስለመሆናቸው ከአርሶአደር ኮሚቴ የተሰጠ ማረጋገጫ አለ ወይስ የለም?
አለ ከተባለ ሰነዱ በማስረጃነት እንዲያያዝልን፡፡
5. ይዞታው ላይ በ 1997 አየር ካርታ ላይ የሚታይ ግንባታ ቤት ወይም አጥር አለ ወይስ የለም ተብራርቶ ይገለፅ
6. ከላይ ከ 1 ኛ እስከ 7 ኛ ለተጠቀሱት ተከሳሾች ለእያንዳንዳቸው በስማቸው ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ ተሰርቶ
የተሰጣቸው ካርታ ካለ በማስረጃነት እንዲያያዝልን እና በምን አግባብ ካርታው እንደተሰጣቸው ተብራርቶ ይገለፅ
7. በአሁን ሰዓት ቦታው ላይ ግንባታም ሆነ አጥር መኖሩ ወይም ባዶ ቦታ መሆኑ ተጣርቶ ምላሽ ይሰጥበት
8. ባጠቃላይ ተከሳሽ መ/ቤታችሁ አለኝ የሚለውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ እንዲሁም ከነማብራሪያው በሶስት ቀን ውስጥ
አጣርታችሁ እንድትልኩልን እየገለፅን በተጠቀሰው ጊዜ ማስረጃዎቹ ሳይላኩ ቢቀሩ ለሚመጣው ሃላፊነት የስራ ሂደታችን
የማይጠየቅ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ከሠላምታ ጋር
ግልባጭ
በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር
ለፍትህ ጽ/ቤት
ለሕግ ጉዳዮች ክርክር ዳይሬክቶሬት
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት
የሕግ ጉዳዮች ክርክር ዳይሬክቶሬት
BOLE SUB-CITY ADMINISTIRATION JUSTICE OFFICE
LITIGATION AFFAIRS DIRCTORATE
መ/ቁ -145803
ቀን -19/03/2015 ዓ.ም
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ 6 ኛ ፍ/ብሄር ችሎት
አዲስ አበባ
4.1 የ 1 ኛ ተከሳሽ ሃላፊዎች ስልጣንን ያላግባብ በመጠቀም ከህግ ውጪ ያለምንም የካሳ ክፍያ እና ምትክ ቦታ
ሳይሰጠን በ 1997 ዓ.ም ከይዞታችን እና ከንብረታችን በማፈናቀል የእርሻ መሬታችን እና ንብረታችንን
በመውሰድ አሁን ክስ ያቀረብንበትን ይዞታ ከእጃችን እንዲወጣ እና ለአረንጓዴ መናፈሻነት አግልግሎት እንዲውል
አድርገዋል በሚል የቀረበው ክስ
ከሳሾች ይዞታውን ካሳ እና ምትክ ሳይሰጠን በጉልበት ከእጃችን እንዲወታ ተደረገብን ይበሉ እንጂ በይዞታው ላይ
መብት እና ጥቅም እንዳላቸው በማስረጃ ባላረጋገጡበት መብት እና ጥቅም አላቸው እንኳን በቀድሞ ስሙ ቦሌ
ኮተቤ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ስር ሲተዳደር ለነበረ ይዞታ በጉልበት ከይዞታቸው ያፈናቀላቸው የአሁን 1 ኛ ተከሳሽ
ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት እና ማስረጃ ባልቀረበበት እንዲሁም ቦታውን ማስለቀቅን በተመለከተ የ 1 ኛ ተከሳሽ
ስልጣን እና ሃላፊነት እንዳልሆነ እየታወቀ እንዲሁም ከሳሾች በክሳቸው ላይ በግልፅ አምነው የገለፁት ነገር
የአጥር ዕድሳት በሚል የግንባታ ፍቃዱን የሰጠው የአሁን 1 ኛ ተከሳሽ ሳይሆን የወረዳው ግንባታ ፍቃድ እና
ቁጥጥር ጽ/ቤት መሆኑን አረጋግጠው የገለፁት በመሆኑ እንዲሁም ቦታው ለግሪን ኤሪያነት እንዲውል ያደረገው
የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን በመሆኑ 1 ኛ ተከሳሽ በጉዳዩ ገብተን ውሳኔ
ያልሰጠን በመሆኑ በጉዳዩ የምንከሰስበት ምክንያት ባይኖርም ክሱ ይመለከታችኋል እንኩዋን ቢባል ክርክር
ያስነሳው ይዞታ መሬት ባንክ የገባ የመንግስት ቦታ ሲሆን ለአሁን 2 ኛ ተከሳሽ በጊዜያዊነት ቦታውን እንዲያለማ
ለአረንጓዴ ልማት በሚል በጊዜያዊነት የተላለፈ በመሆኑ ከሳሾች በይዞታው ላይ መብት እና ጥቅም እንዳላቸው
የሚያሳይ ማስረጃ ባላቀረቡበት የቀረበ ክስ በመሆኑ እና ቦታው መሬት ባንክ የገባ የመንግስት ይዞታ በመሆኑ
የከሳሾች አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግልን እንጠይቃለን፡፡
4.2 ከሳሾች ነባር አርሶ አደር እና የአርሶ አደር ልጆች መሆናችንን በአርሶ አደር ኮሚቴ አረጋግጠናል ያሉት ተቀባይነት
የሌለው እና በማስረጃም ያልተደገፈ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በወረዳው ውስጥ ነባር አርሶ አደር እና የአርሶ አደር
ልጆች ናቸው ቢባል እንኳን ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ አርሶአደር ስለመሆናቸው ባልተረጋገጠበት እንዲሁም
በይዞታው ላይ መብት እንዳላቸው ያረጋግጥልናል ብለው ያቀረቡት የእርሻ መሬት ግብር ደረሰኞችም ቢሆኑ
በግብር ደረሰኝ አካራካሪው ይዞታ ላይ ያለን መብት ለማስረዳት የማይቻል እና ደረሰኞቹ ክርክር ለተነሳበት ይዞታ
ስለመገበራቸው የማያመለክቱ እና በህግ ፊትም የፀና ውጠየት የላቸውም፡፡ ሌላኛው ከሳሾች ወራሾች ነን ብለው
ያያያዙት ማስረጃም የየትኛውን የሟቾች ንብረት እንደወረሱ የማያመለክት እና ሟቾች ያልነበራቸውን መብት
ወራሾች ሊወርሱ ስለማይችሉ እንዲሁም ስልጣን ባለው አካል ክርክር ለተነሳበት ቦታ ባለመብት ስለመሆናቸው
ህጋዊ ማስረጃ ባላቀረቡበት ያከራከረው ይዞታ ተወስዶብናል እንዲሁም በንብረት እና ቤታችን ላይ ጉዳት
ደርሶብናል የሚሉት በ 1997 ዓ.ም ሲሆን ይዞታው የከሳሾች አለመሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይዞታው የከሳሾች ነው
እንኳን ቢባል በቦታው ላይ ምንም አይነት ቤትም ሆነ ንብረት ያልነበረ መሆኑ እና በይዞታው ላይ የነበረን ቤት እና
ንብረት ወድሞብናል የሚለው አቤቱታ ከእውነት የራቀ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በይዞታው ልይ ቤት እና ንበረት
ነበር ቢባል እንኳን ለደረሰው ጉዳት የጉዳት ካሳ እና ምትክ ቦታ ይሰጠን ቅሬታ ማቅረብ የነበረባቸው ይዞታው
አእጃችን ወጣ ከሚሉበት ከ 1997 ዓ.ም አንስቶ በሁለት አመት ውስጥ በቂ ምክንያት ካለ ደግሞ ግፋ ቢል በአስር
አመት ውስጥ በመሆኑ እና በዚህ ጊዜ ገደብ ውስጥ ቅሬታ አቅርበው ምላሽ ስለማጣታቸው ምንም አይነት
ማስረጃ ሳያቀርቡ አስራ ስምንት(18) ዓመት በላይ ካለፈ በኋላ ቆይተው ክስ ማቅረባቸው ይርጋ ስለሚያግደው
በከሳሾች የተጠየቀው የይዞታ ይመለስልኝም ሆነ የካሳ ሊሰጠኝ ይገባል አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ
የከሳሾች አቤቱታ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ተደርጎ አላግባብ ተከሰን ለተጉላላንበት በቂ ኪሳራ በቁርጥ እንዲተኩልን
እንጠይቃለን፡፡
መ/ቁ -145803
ቀን -19/03/2015 ዓ.ም
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለቦሌ ምድብ 6 ኛ ፍ/ብሄር ችሎት
አዲስ አበባ
የሰነድ ማስረጃ
1. የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ክርክር የተነሳበት ቦታ ከነይዞታ ካርታው ጭምር በግሪን ኤሪያነት እንዲለማ
ለ 2 ኛ ተከሳሽ በቀን 24/07/2013 ዓ.ም የሰጠበት ደብዳቤ 2 ገፅ ኮፒ ዋናው በጽ/ቤቱ የሚገኝ
2. የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ጽ/ቤት ለ 2 ኛ ተከሳሽ ለግነባታ በሚል ፍቃድ የሰጠበት
01 ገፅ ኮፒ ዋናው በጽ/ቤቱ የሚገኝ
3. ቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት ቦታው መሬት ባንክ የገባ እና በጊዜያዊነት ለ 2 ኛ
ተከሳሽ እንዲያለማው በሚል የተሰጠ መሆኑን የገለፀበት 01 ገፅ ኮፒ ዋናው በጽ/ቤቱ የሚገኝ
4. ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ ካሳ ስለመበላቱ እና ክርክር ያስነሳውን ይዞታ በአርሶአደርነት ይዘው
ሲጠቀሙበት የነበሩ ሰዎች እነማ እንደነበሩ የሚያስረዳልንን ማስረጃ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 145 መሰረት ከአ.አ
መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፍ/ቤቱ በትዕዛዝ እንዲያስቀርብልን፡፡
5. የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ፅ/ቤት ክርክር ያስነሳው ይዞታ በ 1988 እና በ 1997 በተነሳ
አየር ካርታ ቦታው ላይ የተገነባ ቤት መኖር አለመኖሩን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 145 መሰረት አታርቶ ምላሽ
እንዲሰጥ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን፡፡
ቁጥር-ቦ/ክ/ከ/ፍ/ጽ/ቤት----------
ቀን -04/09/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
2 ኛ/ አቶ በቀለ በዩ ደሞ
6 ኛ/ አቶ አዲሱ መኮንን
7 ኛ/ አቶ ሃብታሙ ፍቃዱ
በቀን 01/09/15 በደብዳቤ ቁጥር ቦ/ክ/ከ/መ/ል/አስ/ጽ/ቤት 11132/15 ለላካችሁልን ክስ መልስ አዘጋጀተን ለመስጠት ይረዳን ዘንድ
በእናተ በኩል የሚከተሉትን ማስረጃዎች ከማብራሪያ ጋር በ ሶስት ቀን ውስጥ እንድትልኩልን እንጠይቃለን፡፡
9. ክርክር ያስነሳው በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል ውስጥ ልዩ ቦታው ሸማቾች ቀጠና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው
በሰሜን አቶ ፍቃዱ ዱባለ በደቡብ አቶ ባህሩ እና አቶ አባያ ራያ በምስራቅ መንገድ እና በምዕራብ ፅጌ ወ/ሃና እና አቶ ባህሩ
የሚያዋስኑት በግምት 2800 ካ.ሜ ነው በማለት ክስ የቀረበበት ይዞታ
10. ቀድሞ በማን እጅ እንደነበር አሁን በማን እጅ ተይዞ እንደሚገኝ እና የይዞታው ህጋዊ ባለቤት ማን እንደሆነ ይገለፅ
11. ይህ ክርክር የተነሳበት ይዞታ ቀድሞ በከሳሾች እጅ ነበር ወይስ አልነበረም?በከሳሾች እጅ ነበር ከተባለ በምን አግባብ
ከእጃቸው ሊወጣ እንደቻለ ካሳ እና ምትክ ማግኘት አለማግኘታቸው ተብራርቶ ይገለፅ
12. ከሳሾች ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ አርሶ አደር ስለመሆናቸው ከአርሶአደር ኮሚቴ የተሰጠ ማረጋገጫ አለ ወይስ የለም?
አለ ከተባለ ሰነዱ በማስረጃነት እንዲያያዝልን፡፡
13. ይዞታው ላይ በ 1997 አየር ካርታ ላይ የሚታይ ግንባታ ቤት ወይም አጥር አለ ወይስ የለም ተብራርቶ ይገለፅ
14. ከላይ ከ 1 ኛ እስከ 7 ኛ ለተጠቀሱት ተከሳሾች ለእያንዳንዳቸው በስማቸው ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ ተሰርቶ
የተሰጣቸው ካርታ ካለ በማስረጃነት እንዲያያዝልን እና በምን አግባብ ካርታው እንደተሰጣቸው ተብራርቶ ይገለፅ
15. በአሁን ሰዓት ቦታው ላይ ግንባታም ሆነ አጥር መኖሩ ወይም ባዶ ቦታ መሆኑ ተጣርቶ ምላሽ ይሰጥበት
16. ባጠቃላይ ተከሳሽ መ/ቤታችሁ አለኝ የሚለውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ እንዲሁም ከነማብራሪያው በሶስት ቀን ውስጥ
አጣርታችሁ እንድትልኩልን እየገለፅን በተጠቀሰው ጊዜ ማስረጃዎቹ ሳይላኩ ቢቀሩ ለሚመጣው ሃላፊነት የስራ ሂደታችን
የማይጠየቅ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ከሠላምታ ጋር
ግልባጭ
በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር
ለፍትህ ጽ/ቤት
ለሕግ ጉዳዮች ክርክር ዳይሬክቶሬት