Professional Documents
Culture Documents
My
My
በቀድሞው የካ ክ/ከተማ በአሁኑ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13 ክልል አካባቢ በሚገኘው የአቶ አደፍርስ ከበደ በሆነው
አዋሳኞቹ በሰሜን የአቶ ሳሙኤል ገብረኪዳን ይዞታ፣ በደቡብ የአቶ አክሊሉ ይልማ ይዞታ፣ በምስራቅ የወ/ሮ ሰናይት አባተ
ይዞታ እንዲሁም በምእራብ መንገድ የሚያዋስኑትን 40 ቆርቆሮ 2 ክፍል ቤት ያረፈበት 280 ካ.ሜ ይዞታው ላይ ከአቶ
አደፍርስ ከበደ እውቅና ውጪ ክርክር ሲደርጉ ቆይተው ይዞታው የተከሳሾች ነው ተብሎ በሰኔ 25 ቀን 2014 ዓ/ም
ተወስኗል፡፡ አቶ አደፍርስ ከበደ ስለ ጉዳዩ የሰማው አሁን ሲሆን በፍርዱ መሰረት አፈጻጸም መከፈቱንም ተረድቷል፡፡
በፍርዱ መሰረት በአፈጻጸም መዝገቡ የተጠየቀውም በመዝገቡ ላይ ተከሳሽ የሆነው አቶ አለን በሰፊው በአቶ አደፍርስ ከበደ
ይዞታ ላይ የተሰራውን ግንባታ አፍርሶ ይዞታውን ለከሳሽ አቶ ኤልያስ ካሳ እንዲያስረክብ የሚል ነው፡፡
በተጨማሪም አሁን ፍርድ የተሰጠበትና አፈጻጸም የተከፈተበት ሰነድ አልባ ይዞታ የአቶ አደፍርስ መሆኑን የሚያስረዱ
የሚከተሉት ማስረጃዎች በአቶ አደፍርስ እጅ ይገኛሉ፡-
1) በአቶ አደፍርስ ከበደ ይዞታውን ከአቶ ገ/ኪዳን መካከል በሚያዝያ 16 ቀን 1996 ዓ/ም የገዛበት የመኖሪያ ቤት
ሽያጭ ውል 01፡፡
2) የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት አሁን በአቶ አደፍርስ ከበደ እጅ የሚገኘው ይዞታ ከ 1997 ዓ/ም በፊት ጀምሮ በአቶ
አደፍርስ እጅ ይገኝ እንደነበር በኮሚቴ አረጋግጦ የላከበት ሰነድ 03 ገጽ፡፡
ጥያቄዎች
1) ለአቶ አደፍርስ ከበደ ፍ/ቤት የሚገባ የተሟላ የመቃወም አቤቱታ አዘጋጅ፤
2) ለአቶ አደፍርስ ፍ/ቤቱ የሰጠው ፍርድ እንዳይፈጸም አቤቱታ ጠይቅ፤
ቀን፡-29/11/2014
መዝገብ ቁጥር፡-1234
በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት
ለልደታ ምድብ ፍ/ብሔር ችሎት
አዲስ አበባ
የመ/አመልካች፡- አቶ አደፍርስ ከበደ አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
የመ/ተጠሪዎች ፦1. አቶ አለን አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
2. አቶ ኤልያስ ካሳ አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 1234 ላይ በሰኔ 25 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው
ችሎት በሰጠው ውሳኔ ላይ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 358 እና 359 መሰረት የቀረበ የመቃወም
አቤቱታ ነው
ሀ. ፍ/ቤቱ ጉዳዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን አለው፡፡
ለ. የፍ/ቤቱን መጥሪያ ለመቃወም ተጠሪ የመ/አመልካች አደርሳለሁ፡፡
ሐ. የመቃወም አመልካች የመቃወም አቤቱታ ለማቅረብ ችሎታ አለኝ፡፡
መ. በመ.ቁ 1234 በቀን 25/10/2014 ዓ.ም የተሰጠ ወሳኔ ተያይዞ ቀርቧል፡፡
ቀን፡-29/11/2014
መዝገብ ቁጥር፡-1234
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 223 መሰረት ከመቃወም አመልካች የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር መግለጫ
1.የሰነድ ማስረጃ
1) በአቶ አደፍርስ ከበደ ይዞታውን ከአቶ ገ/ኪዳን መካከል በሚያዝያ 16 ቀን 1996 ዓ/ም የገዛበት
የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል 1 ገጽ ዋና ።
2) የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት አሁን በአቶ አደፍርስ ከበደ እጅ የሚገኘው ይዞታ ከ 1997 ዓ/ም
በፊት ጀምሮ በአቶ አደፍርስ እጅ ይገኝ እንደነበር በኮሚቴ አረጋግጦ የላከበት ሰነድ 3 ገጽ፡፡
2. የሰው ምስክር
1. ወ/ሮ .............................. አድራሻ፡-.....................
2. አቶ ...................................አድራሻ፡-....................
3. ወ/ሮ .................................አድራሻ፡-....................
ከላይ የቀረበው የማስረጃ ዝርዝር እውነት መሆኑን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 92/3/ መሰረት አረጋግጣለሁ፡፡
የመቃወም አመልካች
ቀን፡-29/11/2014
መዝገብ ቁጥር፡-1234
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለልደታ ምድብ ፍ/ብሔር ችሎት
አዲስ አበባ
የመ/አመልካች፡- አቶ አደፍርስ ከበደ አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
የመ/ተጠሪዎች፦1. አቶ አለን አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
2. አቶ ኤልያስ ካሳ አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13
በፍሥ/ሥ/ህ/ቁ. 359(3) እና 205 መሰረት በቃለ መሀላ ተደግፎ የቀረበ አቤቱታ
የመቃወም ተጠሪዎች የእኔ የመቃወም አመልካች የሆነውን የቤት ይዞ፣ የእኔ ነው፥ የእኔ ነው በማለት በፍርድ
ቤት ይወሰንልኝ ጥያቄ አቅርቦ ስከራከሩ ቆይቶ ፍርድ ቤቱም ምስክር ሰምቶ የመቃወም 2 ተኛ ተጠሪ
የይዞታው ባለቤት ነው ብሎ የአለበት ቤት ፈርሶ ለ 2 ተኛ መቃወም ተጠሪ እንድይመለስ ወስኗል። ነገር ግን
የመቃወም 2 ተኛ ተጠሪ የይዞታው ባለቤት አይደለም፡፡ በመሆኑም ይህ ውሳኔ የመቃወም አመልካች መብትና
ጥቅሜን የሚጎዳ በመሆኑ የመቃወም 2 ተኛ ተጠሪ የይዞታው ባለቤት ሳይሆን ባለቤት ነኝ በሚል በዚሁ ፍርድ
ቤት በመ.ቁ 1234 በቀን 25/10/2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዲሻር እና የመቃወም አመልካች የክርክሩ ተካፋይ
ሳልሆን ለመቃወም ተጠሪ የተሰጠው ውሳኔ የእኔን ህጋዊ መብት እና ጥቅም በእጅጉ ስለሚጎዳ በተገለጸው ቀን የተሰጠው
ውሳኔ ተሽሮና የክርክሩ ተካፋይ ሆኜ ክርክሩ እንደገና ተሰምቶ ውሳኔ እንዲሰጥልኝ በመቃወም ያቀረብኩት አቤቱታ እውነት
መሆኑን በመሃላ ቃል አረጋግጣለሁ፡፡
የመቃወም አመልካች