You are on page 1of 5

ቀን 01/02/16 ዓ.


በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት

ለየካ ምድብ 1 ኛ ውርስ ችሎት


አዲስ አበባ
የኮ/መ/ቁ 191341
አመልካቾች
1. አቶ አማረ ሲሳይ ሞላልኝ አድ አ/አበባ ከተማ የካ
ክ/ከተማ 09 የቤት ቁጥር 303
2. ወ/ሪት ነገደ ሲሳይ ሞላልኝ አድ አ/አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ
09 የቤት ቁጥር 303
3. አቶ መላኪ ሲሳይ ሞላልኝ አድ አ/አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ
09 የቤት ቁጥር 303
4. ወ/ሮ ፍቅርተ ሲሳይ ሞላልኝ አድ አ/አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ 09 የቤት ቁጥር 303
5. ማቲዮስ ማሞ ፈለቀ አድ. አ/አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ቤት ቁጥር 303
6. ወ/ሪት እመቤት ሲሳይ ክሮስ አድ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ቤት ቁጥር 303
7. ናትናኤል ጌታቸዉ ከበደ አድ. አ/አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር----
8. ቶማስ ጌታቸዉ ከበደ አድ. አድስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ቤት ቁጥር -
9. መቅደስ ጌታቸዉ ከበደ አድ. አድስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ቤት ቁጥር -
10. ፍሬህይወት ጌታቸዉ ከበደ አድ. አድስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ቤት ቁጥር -
11. ማህደር አገኘሁ ሲሳይ አድ. አድስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ
12. ማንእንዳንቺ አገኘሁ ሲሳይ አድ. አድስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክ/ከተማ
13. ወንደሰን አገኘሁ ሲሳይ አድ. አድስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክ/ከተማ
የሁሉም አመልካቾች ጠበቃ ቀለሙ አሰፋ
ተጠሪ . . . . . . . . . . የለም
ዉርስ አጣሪ ጠበቃ ቀለሙ አሰፋ እዉነቱ
የዉርስ አጣሪ ርፖርት
እኔ የዉርስ አጣሪ በአመልካቾች አቤቱታ አቅራቢነት የሟች ወ/ሮ ምንትዋብ ብርሀነህይወት
ገብረማርያም ሀብት እንዲጣራ ለፍርድ ቤቱ በቀረበዉ አቤቱታ መሰረት ፍርድ ቤቱ ዉርስ አጣሪ አድርጎ
የሾመኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት የሟች ወ/ሮ ምንትዋብ ብርሀነህይወት ገብረማርያም ዉርስ
በዉርስ አጣሪዉ እንደሚከተለዉ ተጣርቶ ርፖርት ቀርቧል፡፡
የዉርስ ማጣራት ተግባር
1. ሟችን በተመለከተ
 ሟች ወ/ሮ ምንትዋብ ብርሀነህይወት ገብረማርያም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር
303 ውስጥ ሲኖሩ ቆይተው ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም 12/06/2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም
በሞት ተለይተው የቀብር ስነ-ስርዓታቸው በማግስቱ 13/06/2012 ዓ.ም በኮተቤ ኪዳነ
ምህረት ቤተ - ክርስቲያን የመካነ መቃብር ስፍራ ተፈጽሟል፡፡
2. ኑዛዜን በተመለከተ
 ሟች ወ/ሮ ምንትዋብ ብርሀነህይወት ገብረማርያም በህይወት በነበሩበት ጊዜ ኑዛዜ ያተረፉ
ስለመሆን አለመሆናቸዉ አመልካቾችን በመጠዬቅ እና ለማፈላለግ በማስታወቂያ ጭምር
ጥረት ያደረኩ ሲሆን ኑዛዜ አለ ወይንም የኑዛዜ ወራሽ ነኝ የሚል ወገን አልቀረበም በመሆኑም
ሟች በህይወት በነበሩበት ጊዜ ኑዛዜ አላተረፉም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ፡፡
3. ወራሾችን በተመለከተ
 ሟች ወ/ሮ ምንትዋብ ብርሀነህይወት ገብረማርያም ስም በተመዘገበዉና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ
09 የቤት ቁጥር 303 በሆነዉ ቋሚ የመኖሪያ አድራሻቸዉ የውርስ አጣሪ ተሹሞ የውርስ
ሃብት እየተጣራ የሚገኝ መሆኑ ተገልፆ በሚጣራዉ ዉርስ ላይ ኑዛዜ በእጁ ያለ አካል ፤
ከዉርስ ሀብቱ ላይ ገንዘብ ጠያቂ ካለ እንዲሁም በሚጣራዉ ዉርስ ላይ ወራሽ ነኝ የሚል
አካል ካለ እንዲቀርብ በቀን 04/12/15 ዓ.ም የተፃፈ ማስታወቂያ ወጥቶ መክብብ ሲሳይ
ሞላልኝ የተባለ የሟች ልጅ የወራሽነት ማስረጃ ይዞ ቀርቦ ወራሽነቱ ክርክር ያላስነሳ እና
በወራሽነት ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ በወራሽነት ተካቷል፡፡ በዚህም መሰረት
በፍ/ህ/ቁ 842(1) መሰረት የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ህጋዊ ወራሾች
1 ኛ አቶ አማረ ሲሳይ ሞላልኝ
2 ኛ ወ/ሪት ነገደ ሲሳይ ሞላልኝ
3 ኛ አቶ መላኪ ሲሳይ ሞላልኝ
4 ኛ ወ/ሮ ፍቅርተ ሲሳይ ሞላልኝ
5 ኛ አቶ መክብብ ሲሳይ ሞላልኝ
6 ኛ ወ/ሪት እመቤት ሲሳይ ክሮስ
7 ኛ አቶ ማቲዮስ ማሞ ፈለቀ ሲሆኑ
በፍ/ህ/ቁ 853 መሰረት ተተኪ ወራሾች
 ሟች አገኘሁ ሲሳይ ሞላልኝ የሟች ወ/ሮ ምንትዋብ ብርሀነህይወት ልጅ ሲሆን ሟች ወ/ሮ
ምንትዋብ ብርሀነህይወት ህይወታቸዉ ካለፈ በኋላ በቀን 14/06/13 ዓ.ም ህይወቱ ያለፈ
በመሆኑ ልጆቹ ማህደር አገኘሁ ሲሳይ ፣ ማንእንዳንቺ አገኘሁ ሲሳይ እና ወንደሰን አገኘሁ
ሲሳይ የአባታቸዉ ህጋዊ ወራሾች በመሆናቸዉ በአባታቸዉ እግር ተተክተዉ በፍ/ህ/ቁ 853
መሰረት ተተኪ ወራሾች ናቸዉ፡፡
በፍ/ህ/ቁ 842(3) መሰረት ምትክ ወራሾች
 እንዲሁም ሟች መንበረ ሲሳይ ሞላልኝ የሟች ወ/ሮ ምንትዋብ ብርሀነህይወት ልጅ ስትሆን
እናቷ ከመሞቷ በፊት በቀን 04/08/2000 ዓ.ም በሞት የተለዬች በመሆኑ የሟች መንበረ
ሲሳይ ሞላልኝ ልጆች የሆኑት ናትናኤል ጌታቸዉ ከበደ ፣ ቶማስ ጌታቸዉ ከበደ ፣ መቅደስ
ጌታቸዉ ከበደ ፣ ፍሬህይወት ጌታቸዉ ከበደ በፍ/ህ/ቁ 842(3) መሰረት ሟች ወ/ሮ ምንትዋብ
ብርሀነህይወት ምትክ ወራሾች ናቸዉ፡፡
4. የዉርስ ሀብትን በተመለከተ
4.1 የማይንቀሳቀስ ንብረት
 በሟች ወ/ሮ ምንትዋብ ብርሀነህይወት ገብረማርያም ስም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት
ቁጥር 303 በካርታ ቁጥሩ ጅ አይ ኤስ 001168 የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ያለ ሲሆን የዬካ
ክ/ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ፅ/ቤትም ቤቱ በሟች ስም መኖሩን ፣ ከእዳ እና እገዳ
ነፃ የሆነና ወደ ሶስተኛ ወገን አለመተላለፉን በቀን 28/01/2016 ዓ.ም በቁጥር 1059/16
የገለፀ በመሆኑ ከላይ በካርታ ቁጥሩ የተገለፀዉ መኖሪያ ቤት የዉርስ ሀብት መሆኑ
ተረጋግጧል፡፡
4.2 ተንቀሳቃሽ ንብረት
 ሟች ወ/ሮ ምንትዋብ ብርሀነህይወት ገብረማርያም በህይወት በነበሩበት ጊዜ ያፈሩት
ተንቀሳቃሽ ንብረት ስለመኖር አለመሆሩ አመልካቾችን በመጠዬቅ እና ለማፈላለግ
በማስታወቂያ ጭምር ጥረት ያደረኩ ሲሆን ሟች ያፈሩት ተንቀሳቃሽ ንብረት አልተገኘም፡፡
5. የዉርስ እዳን በተመለከተ
ከዉርስ ሃብቱ የሚፈለግ ዕዳ ካለ አለኝ የሚል አካል ይዞ እንዲቀርብ ማስታወቂያ ቢወጣም የቀረበ
ባለመኖሩ ከዉርስ ሀብቱ የሚቀነስ ዕዳ የለም፡፡
6. የዉርስ ድርሻን በተመለከተ
 አቶ አማረ ሲሳይ ሞላልኝ ፣ ወ/ሪት ነገደ ሲሳይ ሞላልኝ ፣ አቶ መላኪ ሲሳይ ሞላልኝ ፣ ወ/ሮ
ፍቅርተ ሲሳይ ሞላልኝ ፣ አቶ መክብብ ሲሳይ ሞላልኝ ፣ ወ/ሪት እመቤት ሲሳይ ክሮስ ፣ አቶ
ማቲዮስ ማሞ ፈለቀ የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች በመሆናቸዉ እያንዳንዳቸዉ ከዉርስ
ሀብቱ 1/9 ኛ ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡
 ማህደር አገኘሁ ሲሳይ ፣ ማንእንዳንቺ አገኘሁ ሲሳይ እና ወንደሰን አገኘሁ ሲሳይ የአባታቸዉ
አገኘሁ ሲሳይ ሞላልኝ ህጋዊ ወራሾች በመሆናቸዉ በአባታቸዉ እግር ተተክተዉ ወደ ዉርሱ
የሚገቡ በመሆኑ እያንዳንዳቸዉ ከዉርስ ሀብቱ 1/27 ኛ ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡
 ናትናኤል ጌታቸዉ ከበደ ፣ ቶማስ ጌታቸዉ ከበደ ፣ መቅደስ ጌታቸዉ ከበደ ፣ ፍሬህይወት
ጌታቸዉ ከበደ በሟች ወላጅ እናታቸዉ መንበረ ሲሳይ ሞላልኝ ምትክ የሟች ወ/ሮ
ምንትዋብ ብርሀነህይወት ምትክ ወራሾች በመሆናቸዉ ከዉርስ ሀብቱ እያንዳንዳቸዉ
1/36 ኛ ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡
ማጠቃለያ
የዉርስ ሀብት ማጣራት ሂደቱ ፍ/ቤቱ ባዘዘዉ መሰረት በዉርስ አጣሪዉ ተጣርቶ ሪፖርቱ በዚህ
መልክ ቀርቧል፡፡

ጠበቃ ቀለሙ አሰፋ


ዉርስ አጣሪ
ቀን 01/02/16 ዓ.ም
በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት

ለየካ ምድብ 1 ኛ ውርስ ችሎት


አዲስ አበባ
የኮ/መ/ቁ 191341
አመልካቾች ------------------ እነ አማረ ሲሳይ ሞላልኝ 14 ሰዎች
ተጠሪ -------------------------- የለም
የዉርስ አጣሪ ሪፖርት ስለማቅረብ
እኔ የዉርስ አጣሪ ጠበቃ ቀለሙ አሰፋ በፍርድ ቤቱ የዉርስ አጣሪ ሆኜ በመሾም ከሀምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም
ጀምሮ የዉርስ ማጣራት ስራዉን ሳከናዉን የቆዬሁ ሲሆን በዚህም መሰረት የዉርስ ማጣራት ስራዉን
አከናዉኜ በመጨረስ ዉርስ የተጣራበት ሙሉ ማህደር ከዉርስ አጣሪ ሪፖርቱ ጋር ያቀረብኩ ሲሆን በዚህም
መሰረት
1. የዉርስ አጣሪ ርፖርት 04 ገፅ፡፡
2. የየካ ክ/ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ፅ/ቤት ለዉርስ አጣሪዉ ቤቱን አስመልክቶ የሰጠዉ ምላሽ
01 ገፅ፡፡
3. የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፅ/ቤት የዉርስ አጣሪ ማስታወቂያ በወረዳዉ ማስታወቂያ ቦርድ
እና በመኖሪያ ቤቱ ላይ የለጠፈ መሆኑን ገልፆ የሰጠዉ ምልሽ 01 ገፅ፡፡
4. ዉርስ አጣሪዉ ማህተም እንዲደረግለት ፍ/ቤቱን የጠዬቀበት ማመልከቻ 02 ገፅ፡፡
5. የወራሾች የወራሽነት ማስረጃ 07 ገፅ፡፡
6. ወራሾች በዉርስ አጣሪ ሪፖርቱ ላይ የሰጡት አስተያየት --- ገፅ፡፡
ያቀረብኩኝ በመሆኑ መዝገቡ ተንቀሳቅሶ ያቀረብኩትን የዉርስ አጣሪ ሪፖርት ፍ/ቤቱ ተመልክቶ
እንዲያፀድቀዉ አመለክታለሁ፡፡

ጠበቃ ቀለሙ አሰፋ


ዉርስ አጣሪ

You might also like