You are on page 1of 50

የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር የጥናት ስራ አሰራር ላይ የተደረገ ጥናት

የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጄነራል

አዲስ አበባ
01/06/2015 ዓ.ም
ማውጫ
ምዕራፍ አንድ..............................................................................................................................................................1

የጥናትና የህግ ጥናት ምንነት..........................................................................................................................................1

1.1 የጥናትና የህግ ጥናት ትርጉም..................................................................................................................................1

1.2 የጥናት ባህሪያት.....................................................................................................................................................3

1.3 የጥናት አይነቶች....................................................................................................................................................4

1.3.1 ጥናት ከሚካሄድበት አላማ አንፃር......................................................................................................................4

1.3.2 ከጥናት ዘዴዎች (method) አንፃር.....................................................................................................................7

1.3.3 ጥናቱ በሚጠቀማቸው የመረጃ ምንጭ አይነቶች መሰረት....................................................................................7

1.4 የጥናት መርሆዎች..................................................................................................................................................8

1.5 የህግ ጥናት ክፍሎች................................................................................................................................................8

1.5.1 የጥናት እቅድ (research proposal)...................................................................................................................9

1.5.1.1 የጥናቱ ዳራ (background of the study)....................................................................................................9

1.5.1.2 የተዛማጅ ፅሁፍ ዳሰሳ (literature review)..................................................................................................9

1.5.1.3 የችግሩ መግለጫ (statement of the problem)..........................................................................................10

1.5.1.4 የጥናቱ ዓላማ (objective of the study)...................................................................................................10

1.5.1.5 የጥናቱ ጥያቄ (research question)..........................................................................................................11

1.5.1.6 የጥናቱ ጠቀሜታ (significance of the study).........................................................................................11

1.5.1.7 የጥናቱ ስነ ዘዴ (methodology of the study)...........................................................................................12

1.5.1.8 የጥናቱ ወሰን.........................................................................................................................................17

1.5.1.9 የጥናቱ ውስንነት....................................................................................................................................17

1.5.1.10 የጥናቱ አደረጃጀት................................................................................................................................18

1.5.1.11 የጊዜ ሰሌዳ..........................................................................................................................................18

1.5.1.12 ስነ ምግባር..........................................................................................................................................18

1.5.2 የጥናቱ ሪፖርት.............................................................................................................................................20

1.5.2.1 ቀዳሚ መጀመሪያ (Preliminary Pages)..................................................................................................20

i
1.6 የጥናት ስራ ሂደቶች..............................................................................................................................................21

ምዕራፍ ሁለት...........................................................................................................................................................24

የሌሎች ተቋማት ተሞክሮ..........................................................................................................................................24

2.1 የሌሎች ተቋማት ተሞክሮ....................................................................................................................................24

2.1.1 የሰነዱ አደረጃጀትን በተመለከተ......................................................................................................................25

2.1.2 ቅድመ ጥናት ስራዎችን በተመለከተ.................................................................................................................27

2.1.2 የጥናት ዕቅድን (research proposal) በተመለከተ..............................................................................................28

2.1.3 የጥናት ሪፖርት በተመለከተ............................................................................................................................30

2.1.4 የተመራማሪው ሀላፊነትና የስነ ምግባር ጉዳዮች................................................................................................30

2.1.5 የመረጃ ምንጮችና የማጣቀሻ ጽሁፎ አጻጻፍ ሥርዓት........................................................................................31

2.1.6 የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ ተሞክሮ.........................................................................................................................31

2.1.7 የኦሮሚያ የህግ ባለሙያዎች የስልጠና እና ህግ ምርምር አንስቲትዩት ተሞክሮ.......................................................32

ምዕራፍ ሦስት...........................................................................................................................................................34

የፍትህ ሚኒስቴር ነባሩ አሰራር.....................................................................................................................................34

3.1 የህግ ማሻሻያ ጥናቶች..........................................................................................................................................34

3.1.1 የጥናት እቅድን በተመለከተ.............................................................................................................................35

3.1.2 የጥናት ሪፖርትን በተመለከተ..........................................................................................................................37

3.2 የህግ አፈፃፀምን እና የስራ ክፍሎችን የስራ አፈፃፀም ለመዳሰስ የተደረጉ ጥናቶች.........................................................38

3.2.1 የጥናት ዕቅድ በተመለከተ...............................................................................................................................39

3.2.2 የጥናት ሪፖርት.............................................................................................................................................40

3.3 ሌሎች በተቋሙ የተሰሩ ጥናቶች............................................................................................................................42

3.1.1 የጥናት እቅድ በተመለከተ...............................................................................................................................43

3.1.2 የጥናት ሪፖርት.............................................................................................................................................44

ምዕራፍ አራት...........................................................................................................................................................46

ማጠቃለያ እና ምክረ ሀሳብ.........................................................................................................................................46

4.1 ማጠቃለያ...........................................................................................................................................................46

4.2 ምክረ ሀሳብ.........................................................................................................................................................47

ii
iii
ምዕራፍ አንድ

የጥናትና የህግ ጥናት ምንነት

1.1 የጥናትና የህግ ጥናት ትርጉም

የተለያዩ ችግሮቹ በሰው ልጅ ህይወት መፈጠራቸው የማይቀር ሲሆን የሰው ልጅም እነዚህን ችግሮቹን ለመፍታት

ወይም ለሚያነሱት ጥያቄዎቹ መልስ ለመፈለግ የተለያየ መንገድ ይከተላል፡፡1 ይህ የፍለጋ ሂደት በዋናነት በሁለት

የሚከፈል ሲሆን አንደኛ በሳይንሳዊ ዘዴ የሚደረግ ፍለጋ (scientific method) እና በዘፈቀደ (arbitrary) የሚደረግ

ፍለጋ ነው፡፡2 በዘፈቀደ ለጥያቄዎች ወይም ለችግሮች መልስ ለመስጠት የሚደረግ ፍለጋ የግል ሀሳብን ወይም

አመለካከት መሰረት ያደረገ ሲሆን ይህም ከሰው ሰው የሚለያይ፣ ግልፅ ያልሆነ እና የተሳሰተ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ

ነው፡፡3 በሌላ በኩል በሳይንሳዊ ዘዴ የሚደረግ ፍለጋ የግል አመለካከትን ሳይሆን ማስረጃን መሰረት በማድረግ ድምዳሜ

ላይ የሚደርስ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ጥናት(research) አንዱ ነው፡፡

ጥናት የሚለው ቃል በእንግሊዘኛው Research የሚል አቻ ትርጉም ያለው ሲሆን ይህ ቃል “recerchier” ከሚለው

ፈረንሳይኛ ቃል የመጣ ሲሆን ቀጥታ ትርጉሙም እንደገና መፈለግ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጥናት የሚለው ቃል

አንድ ወጥ የሆነ ትርጉም የሌለው ሲሆን የተለያዩ ጸሀፍት በተለያየ መልኩ ትርጉም ሰተውታል፡፡ ለምሳሌ ያክል ለጥናት

ከሰተጡት ትርጉሞች የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው፡-

ዌብስተር አለምአቀፍ መዝገበ ቃላት ጥናት ማለት አዲስ እውነታ እና ትክክለኛ ትርጉማቸውን፣ ተቀባይነት ያላቸውን

ድምዳሜዎች፣ህጎች እና መላምቶችን ለማግኘት ወይም የእነዚህን አተገባበር ለመቃኘት የሚደረግ የምርመራ ሂደት

እንደሆነ ያስረዳል፡፡4

ጆን ቤስት የተባለ ፀሀፊ Research in education በሚለው መፅሀፉ ጥናት የሚለውን ቃል ‹‹Research may be
defined as the systematic and objective analysis and recording of controlled observations that may lead
to the development of generalizations, principles, or theories, resulting in prediction and possibly

1
J.R. Brent Ritchie, Charles R. Goeldner: Travel, Tourism, and Hospitality Research: A Handbook for Managers and Researchers, p.2,
Wiley Publishers Ltd, UK.
2
O.R. Krishnaswami, M.Ranganatham and P.N.Harikumar, research methodology, p.2, Himalaya publishing house, 2008.
3
ዚኒከማሁ.
4
https://www.webster-dictionary.org, last accessed at Nov 29/2022.
1
ultimate control of events.›› በማለት የተረጎመው ሲሆን ይህም ማለት ጥናት ስልታዊና ግላዊ ባልሆነ መልኩ

የሚደረግ ትንተና እና የተለያዩ መርሆችን፣ ትንበያዎችን ወይም የሆነ ጉዳይን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ቁጥጥር

የሚደረግበት ምልከታ ምዝገባ ነው ማለት ነው (በፀሀፊው የተተረጎመ)፡፡ በተጨማሪም ያንግ ፖል የሚባል ፀሀፊ

scientific social surveys and research በሚለው መጽሀፉ ጥናት ማለት አዲስ

እውነታዎችን/መላምቶችን/መርሆችን ለማግኘት፣ የነበሩትን ለማረጋገጥ፤ ምክንያት-ውጤት ግንኙነቶችን

በማብራራት አመክንዩን እና ስልታዊ የሆኑ ቴክኒኮችን በመጠቀም የሚሰራ ሳይንሳዊ ስራ ነው በማለት ይተረጉመዋል፡፡5

ከላይ ከተቀመጡትና ከሌሎች ፅሁፎች ለመረዳት እንደሚቻለው ጥናት ማለት ሂደት ሲሆን ይህ ሂደትም ሳይንሳዊ

ዘዴን በመከተል የተለያየ አላማ ለማሳካት የሚደረግ ምርምር ማለት ነው፤ የጥናት አላማ በዋናነት ሦስት ሲሆኑ

እነሱም የፅንሰ ሀሳብ፣ የተግባር እና እውነትን የማግኘት አላማ ይባላሉ፡፡ ይህ ጠቅላላ ትርጉም እንዳለ ሁኖ የተለያዩ

የሙያ መስኮች ሞያቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ ጥናት ያካሂዳሉ፡፡ ስለሆነም የጥናት ትረጉም ከአንዱ ሙያ መስክ

ወደሌላ ሙያ መስክ ስንሄድ መሰረታዊ ልዩነት ባይኖረውም ከሞያቸውና ከአላማቸው አንፃር ይለያያል፡፡ ለአብነት ያክል

የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት ማህበራዊ ችግሮችን በመመርመር ለእነዚህ ችግሮች መፍትሄ ለመፈለግ የሚደረግ ጥናት

ሲሆን የቢዝነስ ጥናት በበኩሉ የሰው ሀብት፣ የፍይናንስ፣ የምርት እና የገበያ አስተዳደርን በተመለከተ የተሻለ ለመሆን

እንዲሁም አዲስ ሀሳቦችን ለማግኘት የሚል አላማ በመያዝ ጥናት ይደረጋል፡፡6 በህግ ሙያ ውስጥ ጥናት የተሰጠውን

ትርጉምና አላማ ደግሞ እንደሚከተለው ተቀምጧል፡፡

ህግ ብቻውን አይቆምም ይልቁንም ህግ የሦስት ልኬቶች (dimensions) ጥምረት ሲሆን እነሱም ህግ እንደ ህጋዊ

መርሆች ስብስብ (law as normative system)፣ ህግ እንደ ማህበራዊ ስርዓት ( law as social system) እና ህግ እንደ

ማህበራዊ መቆጣጠሪያ ስርዓት (law as social control system) ናቸው፡፡ እነዚህ መለኪያ የራሳቸውን የሆነ ጥያቄ

ያላቸውና ለጥያቄቸውም መልስ ለመፈለግ ምርምሮችን ጥናት ያካሂዳሉ፤ ይህም ጥናት የህግ ጥናት ወይም ምርምር

ይባላል፡፡

5
Young Pauline, scientific social surveys and research, New Delhi, prentice hall of India, 1977.
6
Syed Muhammad Sajjad Kabir, introduction to research, p.13-14, july 2016.

2
የህግ ጥናት ማለት ከጥናት አይነቶች አንዱ ሲሆን ይህ ጥናት በአንድ ጉዳይ ላይ ያለ ህግን ለመፈለግ ወይም ተለይቶ

በታወቀ ጉዳይ ላይ ህግ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ወይም የህጉን ተፈፃሚነት ወይም ህጉና ህብረተሰቡ ያለውን

ግንኙነት ለማየት የሚደረግ ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ የሚደረግ ምርመራ ነው፡፡

ይህን ጥናት የሚያካሂዱት ለተለያየ አላማ ዳኞች፣ ህግ አውጪ የህግ ምሁራን እና ሌሎች የህግ ባለሙያዎች ናቸው፡፡

ጥናቱን እንደሚያካሂዱት ሰዎች የጥናቱ አላማ ቢለያይም የህግ ጥናት በዋናነት አራት ዋና ዋና አላማዎች ያሉት ሲሆን

እነሱም፡-

 አንድን ጉዳይ የሚገዛ የህግ ድንጋጌ መኖር አለመኖሩን፤

 የህጉን ግልፅነት፣ ክፍተት ለመለየት እና በህግ ውስጥ ያሉ መፋለሶች፤

 የህግ ማሻሻያ ለማድረግ

 የህጉ ተፈፃሚነት እና ህጉ በህብረተሰቡ ላይ ያመጣውን ለውጥ ለመዳሰስ የሚሉት ናቸው፡፡

1.2 የጥናት ባህሪያት

ጥናት በተለያዩ የሙያ መስክ ውስጥ የተለያየ አላማ እና ትርጉም ቢሰጠውም፤ ሁሉም ጥናት ከሌላው ማንኛውም

ፍለጋ የሚለይበትና አንድ ምርምር ሳይንሳዊ መንገድ ተከትሎ የተካሄደ መሆን አለመሆኑን እንዲሁም ከአድሎ፣ ሚዛናዊ

ካልሆነ እና ከግል አስተያየት ተፅዕኖ ነፃ መሆን አለመሆኑን (free of biases, prejudices, and subjective errors or

not) ለማረጋገጥ የሚረዱ ጥናት የራሱ የሆኑ ልዩ ባህሪያት አሉት፡፡ እነዚህ ልዩ ባህሪያትም እንደሚከተለው

ተቀምጠዋል፡፡

 የተጠቃለለ (Generalized)፡- የአንድ ጥናት ግኝት መሰረት የሚያደርገው መረጃ ከሚጠናው

ጉዳይ(population) ላይ ወካይ መረጃ(data) በመውሰድ ሲሆን የሚደረገው ትንተና ደግሞ ለሁሉም ተግባራዊ

የሚሆን ነው፡፡

 የተገታ(Controlled)፡- የተያዘው ጉዳይ ላይ ተፅዕኖ ከሚያስከትሉ ብዙ ምክንያቶች ውስጥ የተወሰኑትን ብቻ

በመምረጥ የሚካሄድ ነው፡፡

3
 ጥብቅ (Rigorous)፡- ጥናት ጥልቅና ጥብቅ የሚሆንበት ደረጃ ቢለያይም አንድ ጥናት ግን

አስፈላጊ( relevant)፣ ተገቢ( appropriate) እና በቂ ምክንያት (justified) ያለው ሂደትን ተከትሎ የሚሰራ

ነው፡፡

 በተግባር የተፈተነ (Empirical)፡- ጥብቅ ሳይንሳዊ የሆነ መንገድ በመከተል የተሰራና ማንኛውም

መደምደሚያ መሰረት የሚያደረጉት በጥናቱ በተሰበሰቡ መረጃዎች ብቻ ነው፡፡

 በስርዓት የተቀረፀ (Systematic)፡- ጥናቱ የሚካሄድበት ሙሉ ሂደቱ ወይም ስነ ስርዓቱ ከመጀመሪያው

በጥንቃቄ በተቀረፀ እና በታቀደ እቅድ መሰረት ነው፡፡

 አስተማማኝ (Reliability) እና ተገቢነት(Validity)፡- በአንድ ጥናት ላይ የተገኘውን ግኝት ሌላ ሰው

በቀደመው ጥናት የተከተለውን ስነ ስርዓትና መረጃዎች ተጠቅሞ ተመሳሳይ ግኝት ማግኘት ይችላል፤

የተገኘው ግኝት በእውነታው አለም ያለ ነገር ነው፡፡

 መላምትን የሚጠቀም(Employs hypothesis)፡- ጥናት መነሻው መላምቶችን በመቅረፅና መዳረሻው ደግሞ

እነዚህን መላምቶች እውነት ወይም ስህተት መሆናቸውን በማረጋገጥ ነው፡፡

 ትንተናዊና ትክክለኛነት(Analytical & Accuracy)፡- የጥናት ባህሪ ምን ተፈጠረ ብቻ ሳይሆን ለምንና

እንዴት ተፈጠረ የሚለውን በማብራራት ድምዳሜ የሚሰጥ ነው፡፡

1.3 የጥናት አይነቶች

ጥናቱ ከሚካሄድበት አላማ፣ ጥናቱ ከሚከተለው የጥናት ዘዴ እና ከሚጠቀሙት መረጃ በመነሳት የተለያዩ ጥናቶችን

እናገኛለን፡፡

1.3.1 ጥናት ከሚካሄድበት አላማ አንፃር


Add at least one example for each

 መሰረታዊ ጥናት (pure/fundamental research)፡- ምንም አይነት ወደ ተግባር የመለወጥ እቅድ ሳይኖር

በአንድ ጉዳይ ላይ የነበረ እውቀትን ለማስፋት ብቻ ታስቦ የሚደረግ ጥናት ነው፤ ትኩረቱ አዳዲስ ቲዎሪዎችን

መፍጠር ወይም ያሉትን ማሻሻል ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ከፅንሰ ሀሳብ ማጎልበት ውጭ በተግባር የገጠመ ችግር

የለም፤ ትኩረቱም በተግባር የገጠመን ችግር መፍታት ላይ አይደለም፡፡

4
 ተግባራዊ (applied research)፡- ይሄ የጥናት አይነት በተግባር ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚደረግ ጥናት

ነው፡፡ በዚህ ጊዜ በመሰረታዊ ጥናት የተገኙ የጽንሰ ሀሳብ ግኝቶችን ይጠቀማል ወይም እነሱን መሰረት አድርጎ

በተግባር ያለውን ችግር መፍትሄ ለመስጠት ምርምር የሚያካሂድ ጥናት ነው፡፡

 የድርጊት ጥናት (action research)፡- ተግባራዊ ጥናት ጋር የሚመሳሰል ሲሆን ልዩነቱ የድርጊት ጥናት

መነሻው በተግባር የገጠመው ችግር ነው፡፡ ይህም ማለት የድርጊት ጥናት የሚካሄደው በግልፅ የተለየና መፍትሄ

የሚፈልግ ችግር ላይ መሰረት አድርጎ ነው፡፡

 ቀመራዊ ጥናት (exploratory or formulative research)፡- ከአሁን በፊት በደንብ የማይታወቅ ጉዳይ ላይ

የሚካሄድ የጥናት አይነት ነው፡፡ አላማው ስለ ጉዳዩ በቂ ማብራሪያ ለመስጠት ነው፡፡

 ገላጭ ጥናት (descriptive research)፡- በአንድ ጉዳይ ላይ ምንድን ነው የሚል ጥያቄ ይዞ ተነስቶ

የተያዘውን ጉዳይ የሚያብራራ የጥናት አይነት ነው፡፡

 ምርመራዊ ጥናት (Diagnostic research)፡- ይህ የጥናት አይነት በአንድ ጉዳይ ላይ ለምን እና ምን

የሚሉትን ሁለት ጥያቄ ለመመለስ የሚደረግ ነው፡፡ ይህ ጥናት በውስጡ ገላጭ የሚባለውን የጥናት አይነት

አካቶ ይይዛል፡፡

 ግምገማዊ ጥናት (Evaluation studies)፡- ይህ ጥናት ትኩረት የሚያደርገው የአንድ ህግን ተፈፃሚነት

ወይም ህጉ በህብረተሰቡ ላይ ያመጣውን ተፅዕኖ ለመገምገም የሚደረግ የጥናት አይነት ነው፡፡

በተጨማሪም የህግ ጥናት ጥናቱ ከሚካሄድበት አላማ፣ ጥናቱ ከሚከተለው የጥናት ዘዴ እና ከሚጠቀሙት መረጃ

በመነሳት የተለያዩ ጥናቶችን እናገኛለን፡፡ የህግ ጥናት በመሰረታዊነት ከጥናቱ አላማ በመነሳት በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች

ይከፈላል፡፡

ሀ. ንድፈ ሀሳባዊ የህግ ጥናት ወይም ህግን ብቻ መሰረት ያደረገ ጥናት (Doctrinal legal research)

ንድፈ ሀሳባዊ የህግ ጥናት ማለት ህጎችን፣ መርሆችን፣ የህግ ዶግማዎችን (legal doctrines) የሚተነትን የህግ ጥናት

አይነት ሲሆን የዚህ ጥናት ዋነኛ ጥያቄዎቹ ህጉ በቂ ነው? የህጉ ክፍተቶች ምንድን ናቸው? ህጉ ምን ይላል? የሚሉ እና

ሌሎች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ይህ ጥናት ታሪካዊ (የአንድን ህግ አመጣጥ ወይም ህጉ አሁን

ያለውን ቁመና እንዴት እንዳገኘ ሲያጠና)፣ ንፅፅራዊ (ሁለት ህጎችን ሲያነፃፅር) ወይም ትንታኔያዊ (analytical) የህግ

ጥናት ሊሆን ይችላል፡፡

5
እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ጥናቱ እንደ መረጃ ምንጭ የሚጠቀመውም የህግ ሰነዶችን፣ ውሳኔዎችን፣ የፓርላም

ክርክሮችን፣ መፅሀፎችን እና ሌሎች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ሰነዶች ነው፡፡ ይህ የጥናት አይነት ከሚጠቀማቸው

የጥናት ምንጮች ወይም መረጃዎች በመነሳት ቤተ-መፅሀፍትን መሰረት ተደርጎ የሚሰራ ጥናት (library based)

በመባል ይታወቃል፡፡

በዋናነት የሚጠቀሱ ሦስት አላማዎች ያሉት ሲሆን እነሱም የተለያዩ ህጎችንና ውሳኔዎችን በማየት በአንድ ጉዳይ ላይ

ያለ ህግን መለየት፣ የተቋማትን ማቋቋምያ ሕግ ማጥናት (to study legal insitutions)፣ የህግን ወይም የፖሊሲን

አላማ ለማወቅ እና በህጎች መካከል የሚታዩ መፋለሶችንና ክፍተቶችን ለመለየት የሚሉ ናቸው፡፡

ይህ የጥናት አይነት ጊዜ ቆጣቢ ነው፣ በህግ ውስጥ ያሉ መፋለሶችን ያሳያል፣ ለህግ ተራማጅነት (legal development)

አስተዋፅዖ ያደርጋል እንዲሁም ሌላ ጥናት እንዲካሄድ በር ይከፍታል በማለት ጠቀሜታው የሚዘረዘር ሲሆን እነዚህ

ጠቀሜታዎች ቢኖሩም የሚተነተው መረጃን መሰረት ተደርጎ ሳይሆን የግለሰቡን አረዳድ መሰረት አደርጎ ስለሆነ

ግላዊነት ያጠቃዋል፤ በተጨማሪም ህጉ መሬት ላይ ባለ በተጨባጭ እውነታዎች የተደገፈ አይደለም የሚሉ ትችቶች

ይሰነዘሩበታል፡፡

ለ. ህግን የመነሻውና የትግበራ ውጤት ጋር የሚያጠና የህግ ጥናት (Non-doctrinal legal research)

ይህ የጥናት አይነት በተቃራኒው አንድን ህግ ከተለያዩ ተዋንያኖች በተለይም ከህብረተሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት

የሚያጠና ሲሆን ህጉ ምን አይነት ተፅዕኖ አመጣ የህጉ አፈፃፀም ምን ይመስላል የሚሉ እና ተያያዥ ጥያቄዎችን

በማንሳት የሚካሄድ የጥናት አይነት ነው፡፡ በዚህ ጥናት እንደ ዋነኛ የጥናት ምንጭ የሚወሰዱት በቀጥታ ከማህበረሰቡ

በተለያየ ዘዴ የሚያገኙትን መረጃ ሲሆን በተጨማሪም የተለያዩ ሪፖርቶችንና መፃህፍትንም ይጠቀማሉ፡፡

የዚህ የጥናት አይነት አላማዎች በዋነኝነት በህግ ላይ ተፅዕኖ የሚያደርሱ ምክንያቶች፣ በህግና በተግባር ያለውን ልዩነት

(the law and the practice) እና ህጉ ያመጣቸውን ለውጦች መለየት የሚሉት ይገኝበታል፡፡ በተጨማሪም የዚህ ጥናት

ጠቀሜታ ተብሎ የሚነሳው በእውነታው አለም እና በህጉ መካከል ያለውን ልዩነነትና አንድነት በገልፅ በመዳስስ ለፍትህ

አካላት በቂ ማስረጃን ይሰጣል የሚለው ሲሆን እንደ ክፍተት ደግሞ ጊዜ ይወስዳል እንዲሁም መረጃ ለመሰብሰብ

የሚጠቀመው መሳሪያዎች ውስብስ ናቸው የሚሉት ይነሱበታል፡፡

6
1.3.2 ከጥናት ዘዴዎች (method) አንፃር

 ትንተናዊ (Analytical study/statistical method)፡- ማለት ከስያሜው እንደምንረዳው መላምቶችን

ለማረጋገጥና በነገሮች መካከል ያለን ግንኙነት ለማሳየት በቁጥር የሚቀመጡ ወይም የሚለኩ መረጃዎችን

የሚተነትን ጥናት ማለት ነው፡፡

 ታሪካዊ (Historical research)፡- የአንድን ነገር የቀደመ አመጣጥ የሚያጠና የጥናት አይነት ሲሆን ይህ ጥናት

ጥናቱ ከመካሄዱ በፊት የነበሩ መረጃዎችን ይጠቀማል፡፡

 የዳሰሳ ጥናት (Survey)፡- እውነትን ለማውጣት (fact finding) የሚደረግ ጥናት ሲሆን በዚህ ጊዜ መረጃ

በቀጥታ ከሚመለከተው አካል የሚሰበሰብ ይሆናል፡፡

1.3.3 ጥናቱ በሚጠቀማቸው የመረጃ ምንጭ አይነቶች መሰረት

በቁጥር የሚለኩ (quantitative) እና በአይነት ወይም በቁጥር የማይለኩ (qualitative) የሚባሉ ሁለት አይነት ጥናቶችን

እናገኛለን፡፡

 መጠናዊ ወይም በቁጥር የሚለኩ (quantitative) ጥናት

It is a research that uses numbers and statistical methods. It is based on numerical measurements of
specific aspects of phenomenon.

 አይነታዊ ወይም በቁጥር የማይለኩ (qualitative) ጥናት

በቁጥር የማይለኩ መረጃዎችን በመጠቀምና በመተንተን ጥናቱ ለሚያነሳው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ የጥናት አይነት
ነው፡፡ It is a research that covers a wide range of approaches, but by definition, none of these approaches
relies on numerical measurements.

7
1.4 የጥናት መርሆዎች7

ሀ. የራስ አገዛዝ ነፃነት (principle of autonomy/respect for persons)፡- ጥናት የሚያካሂድ ሰው ጥናቱን

በሚያካሂድበት ጊዜ ሰዎች በጥናቱ ለመሳተፍ በሚወስኑበት ጊዜ በነፃነት እንዲወስኑ ሊፈቅድላቸው እንዲሁም

በራሳቸው መወሰን ለማይችሉ ሰዎች ደግሞ ጥቅምና መብታቸው የሚጠበቅበትን ስርዓት ሊዘረጋ ይገባል የሚል

የጥናት መርህ ነው፡፡

ለ. የችሮታ መርሆ (principle of beneficence)፡- ይህ መርህ ጥናቱን በሚያካሂድበት ጊዜ ለሰዎች የበለጠ ጥቅም

ያለው ወይም ጉዳት የማያመጣ በሆነ መልኩ ሊያደርግ ይገባል በማለት ያስቀምጣል፡፡

ሐ. የፍትህ መርህ (principle of justice)፡- ይህ መርህ ቃል በቃል “gives rise to moral requirements that there
be fair procedures and outcomes in the selection of research subjects” የሚል ሲሆን ትርጉሙም ጥናት
በሚካሄድበት ጊዜ አንድ ጥናት የተወሰነ የማህበረሰብ ክፍል ብቻ ከጥናቱ የሚጠቀም ሌላው ደግሞ ሸክሙን
እንዲሸከም የሚያደርግ መሆን የለበት፡፡ ይህ መርህ በውስጡ ፍትሀዊ የሆነ አያያዝ (fair treatment) እና ግላዊነት
(principle of privacy) የሚሉ ሀሳቦችንም በውስጡ የያዘ ነው፡፡ በተጨማሪም ለጥናቱ ናሙናዎች በሚወሰድበት ጊዜ
ወካይነቱን በሚያረጋግጥ መልኩ መሆን እንዳለበት እና አግላይ የናሙና አወሳሰድ ስርዓት በጥናት ውስጥ መከተል
እንደማይገባ የሚያጠነጥን መርህ ነው፡፡

1.5 የህግ ጥናት ክፍሎች

ጥናት በዋነኝነት ከሚካሄድት ሂደት በመነሳት ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች የሚኖሩት ሲሆን እነሱም የጥናት እቅድ እና

የጥናት ሪፖርት የሚሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ክፍሎችም በውስጣቸው ሌሎች ንዑስ ክፍሎችን አካተው ይይዛሉ፡፡

7
Jennifer M. Barrow; Grace D. Brannan; Paras B. Khandhar, Research Ethics, https://www.ncbi.nlm.nih.gov/books/NBK459281/,
last accessed at Dec.02/2022.

8
1.5.1 የጥናት እቅድ (research proposal)

1.5.1.1 የጥናቱ ዳራ (background of the study)

በጥናቱ እቅድ ክፍል ውስጥ መጀመሪያ የሚገኝ ሲሆን የጥናቱን ጠቅላላ ሀሳብ የሚያስተዋውቅ የጥናት ክፍል ነው፡፡

የጉዳዩን የኃላ ታሪክ (background information) የሚዳስስ፣ ጉዳዩ ለምን ጥናት እንደሚያስፈልገው እና ሙሉ ጥናቱ

ምን እንደሚመስል የሚጠቁም እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ያሉ ችግሮችን በተወሰነ መልኩ የሚያሳይ ነው፡፡ የጥናት ዳራ

አንባቢው ሙሉ ጥናቱን ሳያነብ ስለ ጥናት እንዲረዳ በሚያደርግ መልኩ አስፈላጊ ፍሬ ሀሳቦችን አካቶ እንዲቀረፅ

ይጠበቃል፡፡ በዚህም የጥናቱን አስፈላጊነት በጥልቀት የሚያብራራ እንዲሁም የጥናቱን አላማና ጥያቄ የሚጠቅስ

ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የጥናት ዳራ የጥናቱን ርዕስ በማብራራት የሚጀመር ሲሆን በውስጡ የጉዳዩን የኃላ ታሪክ፣

ቁልፍ ቃላቶችን/ቲዎሪዎችን እና ሌሎች መሰል ጉዳዩችን ያካትታል፡፡

1.5.1.2 የተዛማጅ ፅሁፍ ዳሰሳ (literature review)

የተዛማጅ ፅሁፍ ዳሰሳ ማለት በጉዳይ ላይ የተፃፉ የቀደሙ ፅሁፎችን በራስ አገላለፅ ማጠቃለል ማለት ነው፡፡ በዚህ ክፍል

ጥናቱን የሚያከናውነው ሰው በጉዳዩ ላይ በቂ እውቀት እንዳለው ለማመላከትና ጉዳዩ በተገቢው መልኩ የተጠና

መሆኑን አለመሆኑን እና ጉዳዩ ጥናት ለምን እንደሚያስፈልገው የሚገለፅበት ስለሆን ጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው

ፅሁፎች በሙሉ መዳሰስ አለባቸው፡፡

በዚህ የጥናት ክፍል አንባቢው በጉዳዩ ላይ ያሉትን የቀደሙ ስራዎች ያደረጉትን አስተዋፅዖ፣ የቀደሙ ስራዎች ጥንካሬና

ክፍተቶች እንዲሁም አሁን የሚደረገው ጥናት ሊሞላው የሚችለውን ክፍተት በዚህ የጥናት ክፍል ሊያገኝ ይገባል፡፡

የተዛማጅ ፅሁፎች ዳሰሳ ተገቢ የጥናት ዘዴዎችን ለመለየት፣ ጥናቱ ሊያካትታቸው የሚገቡ ነጥቦችን ለማወቅ

እንዲሁም የጥናቱ ጥያቄ ወሰን ለመወሰን ይረዳል፡፡

9
1.5.1.3 የችግሩ መግለጫ8 (statement of the problem)

የችግሩ መግለጫ ማለት ጥናቱ ትኩረት የሚያደርግበትን ጉዳይ በግልፅና በተብራራ መልኩ የሚቀርብበት እንዲሁም

አንባቢ ጥናት የሚደረግበትን ምክንያትና ዓላማ የሚረዳበት የጥናት ክፍል ነው፡፡9 በጉዳዩ ላይ ያለው ክፍተት

መፍትሄዎችን ሳይጨምር የሚገለፅበት ቢበዛ አንድ ገፅ የሚሆን ፅሁፍ ነው፡፡

በዋናነት በዚህ ክፍል መግለፅ የሚፈለገው የሚጠናው ጉዳይ ለምን ትኩረት እንደሚፈልግ፣ ጉዳይ ያለው ጠቀሜታ እና

ጥናቱ የሚያደርገው አስተዋፅዖ ነው፡፡ ስለሆነም ችግሩ ምንድን ነው? ለምን ትኩረት ይፈልጋል? ችግሩ በመኖሩ በማን

ላይ ተፅዕኖ ደርሷል? ያለው ችግር አሁናዊ ነው ወይ? ይሄ ችግር ቀጣይነት አለው? ይሄ ጥናትስ ይሄን ችግር ለመፍታት

የሚያስችል መፍትሄ ማምጣት ይችላል? የሚሉትን ጥያቄዎች በሚመልስ መልኩ እንዲቀረፅ ይጠበቃል፡፡ የጥናቱ

ችግርን ከተለያዩ ምንጮች ማግኘት የሚቻል ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የግል ልምድ፣ ሚዲያ፣ የመንግስት ህትመቶች

(Official Records)፣ መርሀ ግብሮች (Programs) እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ አንድ የችግር መግለጫ በውስጡ

ማህበራዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ ችግርን የሚመለከት ብቻ ሳይሆን የእውቀት ክፍተት መኖሩን ወይም ቀድሞ የነበረ

አረዳድ ላይ ያለ ችግርን ማሳየትም አንዱ ነው፡፡

1.5.1.4 የጥናቱ ዓላማ (objective of the study)

የጥናቱ ዓላማ ማለት የጥናቱ ችግር ወይም ጥያቄ ጋር የሚገናኝ እና ጥናቱ ሲያልቅ ጥናቱ ሊያሳካው የሚፈልገው ነገር

ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ጠቅላላ ዓላማ እና ዝርዝር ዓላማዎች በመባል ይከፈላል፡፡ ጠቅላላ ዓላማ በሚለው ስር የጥናቱ

ዋና ዓላማ እንዲሁም ዝርዝር ዓላማዎች በሚለው ስር ደግሞ ጠቅላላ ዓላማ የሚለውን ወደ ጥናት ጥያቄዎች

በሚመራ መልኩ በግልፅና በዝርዝር የሚገለፅበት እንዲሆን ይጠበቃል፡፡

1.5.1.5 የጥናቱ ጥያቄ (research question)

የጥናቱ ጥያቄ ማለት ጥናቱ የሚመልሳቸው የተለዩ (specific) ጥያቄዎች ሲሆኑ ከጥናቱ ዓላማ በመነሳት የሚቀረፁ

እና ጥናቱ በግኝቱ ሊያሳካቸው የሚፈልገውን ዓላማ በጥያቄ መልክ የሚቀርብበት ክፍል ነው፡፡ ይህም ግልፅ፣ ጥናቱ

8
Uttarakhand Open University, Researching for Hospitality and Tourism Management, p.15, ‹‹ A research problem is a definite or clear
expression [statement] about an area of concern, a condition to be improved upon, a difficulty to be eliminated, or a troubling question
that exists in scholarly literature, in theory, or within existing practice that point to a need for meaningful understanding and deliberate
investigation.››
9
What is a problem statement, https://scientific-publishing.webshop.elsevier.com/, last accessed at Dec.06/2022.
10
ሊመልሳቸው የሚችላቸውን ጥያቄዎች ከፅንሰ ሀሳብ ፍሬነገሮች (theoretical framework) በመነሳት መቀረፅ

የሚጠበቅባቸው ሲሆን ዋና ጥያቄ እና ዝርዝር ጥያቄዎች በመባል ተከፋፍለው ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ ዋና ጥያቄ አንድ

ወይም ከአንድ በላይ ሊሆን የሚችል ሲሆን የጥናቱን አላማ ለመሳከት የሚያስችል የሚጠየቅ ጠቅላላ ጥያቄ ነው፡፡

በሌላ በኩል ዝርዝር ጥያቄዎች ዋና ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችሉ ጥያቄዎችን ያነሳል፤ ይህም ቢያንስ ሁለት እና

ከዚያ በላይ ሊሆን ይችላል፡፡

የጥናት ጥያቄ ሁለት አይነት ሲሆን በቁጥር የሚለካ የጥናት ጥያቄ (Quantitative research questions) እና በአይነት

የሚቀመጡ ወይም በቁጥር የማይለካ የጥናት ጥያቄ (Qualitative research questions) ናቸው፡፡10 በቁጥር የሚለካ

የጥናት ጥያቄ የሚባሉት ማብራሪያ የሚጠይቁ እና አዎ ወይም አይደለም ተብለው የማይመለሱ የጥያቄ አይነቶች

ናቸው፡፡ ይህ የጥያቄ አይነት ‹‹ምንድን›› ተብለው የሚጠየቁ ሲሆኑ አላማዉም በነገሮች ያለውን ግንኙነት ወይም

ልምድ ለማወቅና ሁለት ነገሮችን ለማወዳደር ነው፡፡ በሌላ በኩል በቁጥር የማይለካ የጥናት ጥያቄ አይነት አዎ ወይም

አይደለም ተብለው የሚመለሱ ሲሆን አላማውም አንድ ጉዳይን በሚመለከት የሚነሱ ጉዳዩችን ለማግኘት፣

ለማብራራት እና ለማሰስ ነው፡፡

1.5.1.6 የጥናቱ ጠቀሜታ (significance of the study)

ጥናቱ መካሄዱ አስፈላጊ ነው የሚለውን የምናሳምንበት ክፍል ስለሆነ ጥናቱ በተያዘው ጉዳይ ላይ የሚኖረውን

አስተዋፅዖ የሚያሳይ እና በጉዳዩ ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ የሚያትት መሆን አለበት፡፡ ስለሆነም የጥናቱ ጠቅላላ እና

ዝርዝር አስተዋፅዖ እንዲሁም ተጠቃሚዎቹ እነማን ናቸው እንዴትስ ይጠቀማሉ የሚለውን የሚይዝ ይሆናል፡፡

1.5.1.7 የጥናቱ ስነ ዘዴ (methodology of the study)

የጥናት ስነ ዘዴ የሚባለው ጠቅላላ ቃል ሲሆን ይህም ጥናቱ እንዴት ይሰራል የሚለውን የምናብራራበት እንዲሁም

የጥናት ስነ ዘዴ በውስጡ የጥናት ዘዴን እና ለምን የጥናት ዘዴን እንደምንጠቀም የሚነግረን የጥናት ክፍል ነው፡፡ የጥናት

ዘዴ የሚመወሰነው የጥናቱ ችግርን ወይም ጥያቄዎች መሰረት ተደርጎ ሲሆን የተመረጠውን ዘዴ በመጠቀም

የተባለውን ጥያቄ መመለስ የሚያስችልና የጥናቱን አላማ የሚያሳካ መሆን አለበት፡፡ የጥናት ዘዴ በውስጡ ምንድን፣

ለምን እና እንዴት የሚሉ ጥያቄዎችን የሚመልስ ሀተታ መያዝ አለበት፤ ይህም ማለት በዋናነት የጥናት ምንጮችን

(research source)፣ እነዚህን ምንጮች የምናገኝበትን ዘዴ (methods)፣ ለምን የተመረጠውን ዘዴ እንጠቀማለን


10
Imed Bouchrika, what is research problem, https://research.com/research/how-to-write-a-research-question, last accessed at Dec.06/2022.
11
የሚለውን እንዲሁም የናሙና አወሳሰድ (sampling) እና መረጃ የሚተረጎምበትን ወይም የሚብራራበትን መንገድ

ግልፅ በሆነ መልኩ እንዲያብራራ ይጠበቃል፡፡

ሀ. የጥናት ምንጮች (source)

የጥናት ምንጮች በማንኛውም የጥናት አይነት በዋናነት ሁለት አይነት ናቸው፤ እነሱም የመጀመሪያ ደረጃ መረጃዎችና

የሁለተኛ ደረጃ መረጃዎች ናቸው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ መረጃዎች11 የሚባሉት በቀጥታ ከመጀመሪያ ምንጮች የተገኘ

መረጃ ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ መረጃዎች12 የሚባሉት ደግሞ ከተጠቃሚው በቀጥታ የሰበሰባቸው ሳይሆኑ ተጠቃሚው

በሌላ ሰው የተሰበሰቡትን መረጃዎች ሲጠቀም ማለት ነው፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ የጥናት ምንጮች

የምንላቸው እነማን ናቸው የሚለው ከጥናት ጥናት ይለያያል፡፡ ለአብነት ያክል ለማህበራዊ ሳይንስ ጥናት የመጀመሪያ

ምንጭ በቀጥታ ከተሳታፊዎች የሚገኝ ብቻ ሲሆን ህጎችን ጨምሮ የታተሙና ያልታተሙ የመረጃ ምንጮች ግን

ሁለተኛ የጥናት ምንጭ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ የህግ ጥናትን ስንመለከት ከተሳታፊዎች የሚገኙ መረጃዎች በተጨማሪ

ህጎች የመጀመሪያ ምንጭ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

ለ. የጥናት ዘዴ

የጥናቱ ዘዴ ማለት ለጥናቱ የሚሆኑ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ጥቅም ላይ የሚውሉ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ በዚህም ምን

አይነት መረጃዎች በምን አይነት መንገድ እንደሚሰበሰቡ መብራራት አለበት፡፡ የጥናት ዘዴ መሰረት የሚያደርገው

የጥናት ምንጮችን ሲሆን በዚህም መሰረት የመጀመሪያ ደረጃ መረጃዎች የሚሰበሰቡበት የጥናት ዘዴ እና ሁለተኛ

ደረጃ መረጃዎች የሚሰበሰቡበት የጥናት ዘዴ ብሎ በመክፈል የጥናት ዘዴዎችን እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡፡ ከዚህ

ላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነጥብ አንድ ጥናት የተለያዩ መረጃዎችን የሚጠቀም እስከሆነ ድረስ በአንድ ጥናት

መረጃዎችን ለመሰብሰብም የተለያዩ መሳሪያዎችን ወይም ዘዴዎችን ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉበት አጋጣሚ አለ፡፡

አንደኛ ደረጃ መረጃዎች በዋናነት በሦስት አይነት መንገድ የሚሰበሰቡ ሲሆን እነዚህም በቃለ መጠይቅ(Interview)፣

የፅሁፍ መጠይቅ(Questionnaire) እና ምልከታ(Observation) ናቸው፡፡

 በቃለ መጠይቅ (Interview):- አስቀድሞ የተዘጋጁ ጥያቄዎችን በመያዝ ጠያቂው ምላሽ ሰጭዎችን

በመጠየቅ መረጃ የሚሰበሰብበት ዘዴ ሲሆን በአካል በመገናኘት ወይም በስልክ ሊጨርስ ይችላል፡፡
11
It means someone collected the data from the original source first hand
12
Refers to data which is collected by someone who is someone other than the user
12
 የፅሁፍ መጠይቅ (Questionnaire)፡- ሦስት አይነት የፅሁፍ መጠይቅ አሉ፡-

 ማብራሪያ የማይጠይቁ ጥያቄዎች (Closed ended Questionnaire)፡- የምርጫ ጥያቄዎች ወይም

እውነት/ሀሰት በማለት የሚመለሱ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

 ማብራሪያ የሚጠይቁ ጥያቄዎች (Open ended Questionnaire):- ምላሽ ሰጭዎች በራሳቸው አባባል

መልስ እንዲሰጡ የሚቀርቡ ጥያቄዎች ሲሆኑ በዚህም መላሾች የሚመልሱበት ክፍት ይቀመጣል፡፡

 የተቀላቀሉ ጥያቄዎች (mixed)፡- ማብራሪያ በማይጠይቁ ጥያቄዎች አስቀድሞ በማስቀመጥ ቀጥሎ ደግሞ

የማብራሪያ ጥያቄዎችን ይቀመጣሉ፡፡

የዕሁፍ መጠይቄች ተዘጋጅተው ሲያበቁ ከመሰራጨታቸው በፊት አስተያየት እንዲሰጥባቸው ይጠበቃል፤ በዚህም

መጠይቆች የተፈለገውን አላማ በሚያሳኩ መልኩ አጠር ተደርገው እንዲቀረፁ ይጠበቃል፡፡

 ምልከታ (Observation)፡- ጥናት የሚያካሂደው ሰው በራሱ ጉዳዩ በሚገኝበት ቦታ በመሄድ ወይም በቦታው

በመገኘት ነው፡፡ በዚህ ዘዴ የሚሰበሰቡ መረጃዎች በቀጥታ በቦታው የተፈፀሙት ሲሆን ይህ ዘዴ ከሌሎቹ

አንፃር ወጪ የሚጠይቅ እንዲሁም ትልቅ ቁጥር ያለው ናሙና በሚወሰድበት ጥናት የሚመከር አይደለም፡፡

 የጥናት approach (research approach)

በዚህ ክፍል ምን አይነት ----እና ለምን የተመረጠውን ----የሚለው መልስ የሚገኝበት ክፍል ነው፡፡ ሦስት አይነት

የጥናት---- የምናገኝ ሲሆን በቁጥር የሚለካ የጥናት ጥያቄ (Quantitative)13፣ በአይነት የሚቀመጡ ወይም በቁጥር

የማይለካ የጥናት ጥያቄ (Qualitative)14 እና ቅልቅል የጥናት----ናቸው፡፡

ሐ. የናሙና አወሳሰድ

ናሙና ማለት ከሰፊውን ቁጥር ወካይ የሚሆን ቁጥርን ለመውሰድ የሚደረግ የእስታትስቲካዊ ትንተና ወይም አንድ

የተወሰነ ማህበረሰብን ወይም ጉዳይን ወካይ ቁጥርን የምንመርጥበት ወይም የምንወስንበት ሂደት ነው፡፡15 ናሙና

እንድንወስድ ከሚያስገድዱን ምክንያቶች ውስጥ ሙሉ ቆጠራ ማድረግ አድካሚ፣ የወጭና ጊዜ የሚወስድ እንዲሁም

13
which can be subjected to rigorous quantitative analysis in a formal and rigid fashion
14
Qualitative approach to research is concerned with subjective assessment of attitudes, opinion sand behavior
15
It is the act, process, or technique of selecting a representative part of a population for the purpose of determining parameters or
characteristics of the whole population.
13
የሰው ሀይል በብዛት የሚፈልግ ስለሆነ ነው፡፡ ይህ ናሙና አወሳሰድ ሂደት የሚመራበት የራሱ የሆኑ ዋና ዋና የሚባሉ

አምስት መርሆዎች ያሉት ሲሆን እነሱም፡-

 ተመጣጣኝ፡- ምንም እንኳን በግልፅ ይሄን ያክል ቁጥር በናሙናነት መወሰድ አለበት የሚል ህግ ባይኖርም፤

በናሙናነት የተወሰደው ቁጥር የሚወክለውን ጉዳይ በትክክል ሊወክል ይገባል ወይም ናሙናው ወካይ መሆን

አለበት፡፡ ለዚህም በናሙናነት በሚወሰደው እና በሚወከለው ቅጥር መካካል ያለው ልዩነት መስፋት የለበትም

ወይም ተመጣጣኝ ሊሆን ይገባል የሚል መርህ ነው፡፡

 ከስህተት የፀዳ፡- በናሙናነት የሚወሰደው ቁጥር ስህተት የመፈጠር እድሉን የሚያጠብ መሆን አለበት ይህም

ትክክለኛ መረጃ ለማግኘትና ለመተንተን ይረዳል፡፡

 በጀትን መሰረት ያደረገ፡- ናሙና ሲወሰድ ተግባራዊ ሊሆን የሚችልና ለጥናቱ የተበጀተውን የገንዘብ መጠን

ባገናዘበ መልኩ እንዲሆን የሚያትት መርህ ነው፡፡

 አድሎአዊ ያልሆነ፡- ናሙና ሲወሰድ ከግ

 ል አመለካከት በፀዳና ፍትሁዊ በሆነ መልኩ መሆን አለበት፡፡

 ጠቅላላ፡- የተወሰደው ናሙና መሰረት ተደርጎ የሚገኘው ዉጤት ምንም እንኳን ፍፁም ሙሉ በሙሉ

ባይሆንም ምክንያታዊ በሚባል ደረጃ ለሁሉም የሚሰራ እንዲሆን ወይም አብዛኛውን ናሙና የተወሰደበትን

ክፍል እንዲገልፅ ይጠበቃል፡፡

ናሙና ሲወሰድ የመጠይቆችን ተፈጥሮ፣ ጊዜን፣ ወጭን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዩችን ከግምት ውስጥ

በማስገባት ሲሆን የናሙና አወሳሰድን በተመለከተ ሁለት አይነት ስልት የምናገኝ ሲሆን እነዚህም እንደሚከተለው

ተቀምጠዋል፡፡ ምንም እንኳን ሁለት አይነት የናሙና አወሳሰድ ስልቶች ቢኖሩም በአንድ ጥናት ውስጥ

እንዳስፈላጊነታቸው ሁለቱንም አይነት ስልት ልንጠቀም እንችላለን፡፡

i. Probability sampling16

ይህ የናሙና አወሳሰድ ቴክኒክ ሁሉም ቁጥሮች እንደ ናሙናነት የመወሰድ እድል ያላቸው ሲሆን ምርጫ የሚደረገውም

ምንም አይነት መስፈርት የለም፤ መመረጥም አጋጣሚ ወይም የእድል ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የናሙና አወሳሰድ ሂደት የተሻለ

16
The selection of a sample from a population, when this selection is based on the principle of randomization, that is random selection or
chance
14
ውክልና የሚያረጋግጥ ነው የሚባል ቢሆንም ጊዜ የሚወስድ እና ሰፋ ያለ በጀት የሚጠይቅ ነው፡፡17 በዚህ ሂደት ናሙና

ለመውሰድ የተለያዩ ስልቶች መሰረት የሚያደርግ ሲሆን እነዚህም፡-

 Simple Random Sampling፡-This type of sampling is also known as chance sampling or


probability sampling where each and every item in the population has an equal chance of
inclusion in the sample and each one of the possible samples. In case of finite universe, has the
same probability of being selected. In case of infinite population, the selection of each item in a
random sample is controlled by the same probability and that successive selections are
independent of one another.
 Systematic Sampling፡ An element of randomness is usually introduced into this kind of
sampling by using random numbers to pick up the unit with which to start.
 Stratified Random Sampling፡ In this technique, the population is stratified into a number of
non-overlapping subpopulations or strata and sample items are selected from each stratum. If the
items selected from each stratum is based on simple random sampling the entire procedure, first
stratification and then simple random sampling, is known as stratified random sampling.
 Multi-Stage Sampling፡ This technique is meant for big inquiries extending to a considerably
large geographical area like an entire country. Under multi-stage sampling the first stage may be
to select large primary sampling units such as states, then districts, then towns and finally certain
families within towns. If the technique of randomsampling is applied at all stages, the sampling
procedures described as multi-stage random sampling.
 Cluster sampling: Cluster sampling involves grouping the population and then selecting the
groups or the clusters rather than individual elements for inclusion in the sample. The clustering
approach can, however, make the sampling procedure relatively easier and increase the
efficiency of field work, especially in the case of personal interviews.

17
Probability sampling, http://www150.statcan.gc.ca, last accessed on Dec.07/2022
15
ii. Non-probability sampling

ይህ የናሙና አወሳሰድ ስልት ጥናቱን ለሚያካሂደው ሰው ናሙናነት የሚወሰደውን ቁጥር የሚወስንበትን እድል

የሚያሳጣው ሲሆን በዋነኝነት በኮታ (Quota Sampling)፣ የምቾት (convenience sampling) እና አላዊ (Purposive

sampling) የሚባሉ የናሙና አወሳሰድ ስልቶችን ይጠቀማል፡፡

 ኮታ ናሙና አወሳሰድ ስልት (Quota Random Sampling)፡ the cost of taking random samples from
individual strata is often so expensive that interviewers are simply given quota to be filled from
different strata, the actual selection of items for sample being left to the interviewer judgment.
 አላዊ ናሙና አወሳሰድ ስልት (Purposive sampling)፡ This sampling method involves purposive or
deliberate selection of particular units of the universe for constituting a sample which represents
the universe. When population elements are selected for inclusion in the sample based on the
ease of access, it can be called convenience sampling. Purposive sampling is considered
desirable when the universe happens to be small and a known characteristic of it is to be studied
intensively.
 የምቾት (convenience sampling)፡ where units are selected for inclusion in the sample because

they are the easiest for the researcher to access. ናሙና ለመውሰድ መረጣ ሲደረግ መሰረት

ከሚያደርጋቸው መስፈርቶች ውስጥ አካላዊ ቅርበት(geographical proximity)፣ የምላሽ ሰጪዎች በጥናቱ

ውስጥ ለመሳተፍ ያለቸው ፍላጎት እንዲሁም በቀላሉ ማግኘት የሚቻል መሆናቸው የሚሉት ናቸው፡፡

1.5.1.8 የጥናቱ ወሰን

ይህ የጥናት ክፍል ጥናቱ የሚሸፍነውን ጉዳይ የሚገለፅበትና የጥናቱ ትኩረት ምን ላይ እንደሆነ የሚቀመጥበት

እንዲሁም ጥናቱ ጉዳዩን እስከምን ድረስ ይዳስሳል የሚለውን የምናይበት ክፍል ነው፡፡ ስለሆነም በጥናቱ መሰረት

ያደረገው የመልከዓ ምድር ሽፋን፣ የጊዜ ርዝማኔ እንዲሁም የተወሰደው ወካይ ናሙናን ወሰን የሚያካትት ነው፡፡

1.5.1.9 የጥናቱ ውስንነት

የጥናቱ ውስንነት ማለት ጥናቱ ሊደርስበት የሚገባውን ድምዳሜ የቀነሱ ወይም በጥናቱ ግኝት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ

የሚያሳድሩ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡ ጥናቱ በሚካሂድበት ጊዜ የገጠሙ ወይም ሊያጋጥሙ ይችላሉ የሚባሉ ተግዳሮቶች

16
በዚህ ክፍል የሚቀመጡ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ተግዳሮቶችን መዘርዘር ብቻ ሳይሆን እንዴት የጥናቱ ግኝት ላይ ተጽዕኖ

እንዳሳደሩ መገለፅ አለበት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የሚገጥሙ ተግዳሮቶች የጥናቱ አቀራረፅ ላይ፣ የመረጃ አቅርቦት ላይ እና

impact limitations ናቸው፡፡

1.5.1.10 የጥናቱ አደረጃጀት18

የጥናቱን አላማ ለማሳካት ጥናቱ የሚደራጅበትን መንገድ የምንገልፅበት ክፍል ሲሆን ሲሆን ይህም አብዛኛውን ጊዜ

የጥናቱ የሚኖሩትን ወይም ያሉትን ምዕራፎችና ንዑስ ርዕሶች የሚገለፅ ነው::

1.5.1.11 የጊዜ ሰሌዳ

የጥናት ዕቅድ አንዱ ክፍል የሆነው የጊዜ ሰሌዳ ሲሆን ይህም ጠቅላላ ጥናቱ እና የጥናቱ የተለያዩ ክፍሎች ተሰርተው

የሚጠቃለልበትን ጊዜ የሚያገኝበት የጥናት ክፍል ነው፡፡ ስለሆነም የጥናቱ እያንዳንዱ ክፍል ተሰርቶ የሚጠናቀቅበትን

ቀን እንዲሁም ጥናቱ በቡድን የሚሰራ ከሆነ የትኛው ክፍል በማን ይሰራል የሚለውንም መረጃ እንዲይዝ ይጠበቃል፡፡

1.5.1.12 ስነ ምግባር

የጥናት ስራ ሂደት የተለያዩ መረጃዎችን በመሰብሰብ የሚካሄድ እስከሆነ ድረስ በዚህ ሂደት ውስጥም ሊጠበቁ

የሚገባቸው የጥናት ስነ ምግባር መርሆዎች በሁሉም አይነት ጥናት ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ በዚም የጥናት ስነ ምግባር

ጥናቱን በተመለከተ እና በጥናቱ ውስጥ የተሳተፉ ሰዎችን በተመለከተ አጥኒው ሊጠብቃቸው የሚገቡ ስነ ምግባር

በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡

ሀ. ጥናቱን በሚመለከት

አንድ የጥናት ስራ የሚያካድ ሰው መረጃዎችን በሚሰበስብበት ጊዜ እንዲሁም መረጃዎችን በሚተነትንበት ወቅት

የሚከተሉትን ስነ ምግባር እነዲኖረው ይጠበቃል፡፡

18
That provide a reader with roadmap to your dissertation that illustrates what they should expecte: how the stdudy was organized and
conducted as well how the chapters ahead have been sequenced.
17
 ሚዛናዊ ያልሆነ (Prejudice)፡- የተሰበሰቡ መረጃዎች የሚያመላክቱትን ትክክለኛ ግኝት መደበቅ ወይም

መረጃዉ የማያመላክተውን ነገር መጨመር ሚዛናዊ ወዳልሆነ ድምዳሜ ያደርሳል፡፡ ስለሆነም የጥናቱ ግኝት

መረጃው በሚያመላክተው ብቻ መሰረት ተደርጎ መቀመጥ አለበት፡፡

 Provision or deprivation of a treatment:- የጥናቱ ውጤት ወይም ድምዳሜ የሚያስከትለው ውጤት

በእርግጠኝነት መታወቅ አለበት እንጂ ጥቅምና ጉዳቱ በማይታወቅ ወይም በሚያጠራጥርበት ሁኔታ ላይ

ድምዳሜ መሰጠት የለበትም፡፡

 አግባብነት የሌለው ስነ ዘዴን መጠቀም (Inappropriate research methodology):- ለሚካሄደው ጥናቱ

ባህሪ ጋር የማይስማማ ወይም ጥናቱን ለማካሄድ አግባብነት የሌለው የጥናት ስነ ዘዴ እንዲሁም አጥኒው

የሚመቸውን ስነ ዘዴ ብቻ መጠቀም አግባብ አይደለም፡፡

 የጥናቱ ግኝቶችን በተሳሳተ መልኩ ማቅረብ (Misrepresentation of facts)፡- የጥናቱን ሪፖርት ግኝቶቹ

በሚያመላክተው መልኩ ሳይሆን የራስን ወይም የሌላ ሰውን ፍላጎትና ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ብቻ

ማቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡

 መረጃዎችን አላግባብ መጠቀም (Misuse of data)፡- የተሰበሰቡ መረጃዎችን ከተሰበሰቡበት ዓላማ ውጭ

መጠቀም የስነ ምግባር ጉድለት ነው፡፡

 የሃሳብ ንጥቂያ (Plagiarism)፡- በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የሌላ ሰው የስራ ውጤት የሆነውን

ጥናት፣ ሀሳብ፣ አስተያየት ወይም አገላለጽ ምንጩን ሳይጠቅሱ የራስ አስመስሎ በጥናት/ጽሁፍ ውስጥ

ማካተት የለበትም፡፡

ለ. በጥናቱ የተሳተፉ ሰዎችን በተመለከተ

 የመላሽ ሰጭዎች ምቾት (Safety of respondents)፡- አጥኒው መረጃዎችን ከመላሽ ሰጭዎች

በሚሰበስብበት ወቅት ምላሽ ሰጭዎችን በምንም አይነት መልኩ ቢሆን ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚያጎድፍ፣

በሚያሸማቅቅ፣ በሚያስጨንቅ እንዲሁም ምቾት በሚነሳ መልኩ መሆን የለበትም፡፡

 ፍቃድ መጠየቅ (Permission or consent)፡- ማንኛውም ምላሽ ሰጭ በጥናቱ ለመሳተፍ ተገዶ ወይም ጫና

ተደርጎበት መሆን የለበትም፤ በጥናቱ ሲሳተፍም አውቆት በነፃ ፍቃዱ እንዲሁን ይጠበቃል፡፡ ስለዚህ አጥኒው

ለመላሹ ምን አይነት መረጃ ለመሰብሰብ እንደተፈለገ፣ ጥናቱ የሚካሄድበትን አላማ እና እንዴት በጥናቱ

ውስጥ እንደሚሳተፍ አስቀድሞ ሊያሳውቀው ይገባል፡፡


18
 ማበረታቻ (Incentives)፡- ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት በማሰብ መረጃውን ለሚሰጡ

ሰዎች ማበረታቻ ወይም ስጦታ መስጠት ተገቢ አይደለም እንዲሁም ምንም አይነት መረጃ በገንዘብ መገኘት

የለበትም፡፡

 Sensitive Information፡- አንዳንድ መረጃዎች በባህሪያቸው ሰዎች እንዲጠየቁ የማይፈልጓቸው ሊሆኑ

ይችላሉ በዚህ ጊዜ መላሾችን ላለማስቆጣት አስቀድሞ መናገርና አጠያየቃቸውን ማለዘብ አስፈላጊ ነው፡፡

ስለሆነም እንደሚሰበሰቡት መረጃዎች አይነት መላሾችን ስሜታዊ ማድረግ አግባብነት የለውም፡፡

 ሚስጥር ጠባቂነት (Confidentiality)፡- ለሌላ ጥናት ለማስኬድ በማሰብ የምላሽ ሰጭዎችን መረጃ

ማስተላለፍ ወይም ለሌላ ጥናት ማዋል እንዲሁም የመላሾችን ስም ከምላሻቸው ጋር በጥናቱ መግለፅ ተገቢ

አይደለም፡፡

1.5.2 የጥናቱ ሪፖርት

የጥናት ዋና ክፍል የጥናት ሪፖርት ሲሆን ይህ የጥናት ክፍል ሦስት ንዑስ ክፍሎችን የሚይዝ ነው፡፡ እነሱም፡-

1.5.2.1 ቀዳሚ መጀመሪያ (Preliminary Pages)

የጥናቱን ርዕስ፣ ጥናቱ የተጠናቀቀበት ቀን፣ ማረጋገጫ (Acknowledgement)፣ `መቅድም (Preface)፣ ማውጫ

(Table of Contents)፣ ምፃረ-ቃል(Abbreviations) እና የሰንጠረዥ ዝርዝሮች (List of Tables) የሚይዝ ነው፡፡

1.5.2.2 ዋና ክፍል (the Main Text)

የጥናቱ ይዘት ሙሉ በሙሉ የሚገኝበት ሲሆን በውስጡም መግቢያ፣ ጽንሰ-ሃሳብ (conceptual frameworks)፣ የጥናቱ

ግኝቶች፣ ማጠቃለያና ምክረ ሀሳቦችን በሙሉ የያዘ ነው፤ ይህ የጥናት ክፍል በምዕራፍ ተከፋፍሎ ይደራጃል፡፡

1.5.2.3 የማጠቀሻ ፅሁፎች ዝርዝር

ማጣቀሻ ፅሁፎች ተዘርዝረው የሚገኝበት የጥናት ክፍል ሲሆን ማጣቀሻ የሚለው የጥናት/ምርምር ስራዎችን

ለማከናወን በግብአትነት ያገለገሉ ጽሁፎች (መፅሐፍት፣ መፅሄቶች፣ ጋዜጦች፣ አርቲክሎች፣ ሰነዶች፣ ወዘተ…)፣ የህግ

ድንጋጌዎች፣ የግለሰቦች ወይም ቡድኖች ሀሳብና አስተያየቶችን እንዲሁም በአጠቃላይ ለጥናቱ በምንጭነት ያገለገሉ

ሌሎ ግብአቶችን ያካትታል፡፡

19
የጥናቱ ማጣቀሻዎች በተለያዩ መልኩ የሚፃፉ ሲሆን በዋናነት ግን አራት አይነት የማጣቀሻ አፃፃፍ መንገዶች አሉ፡፡

እነሱም፡-

ሀ. Footnotes

ለ. Endnotes

ሐ. In-text

መ. Bibliography

1.6 የጥናት ስራ ሂደቶች

ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው የህግ ጥናት የሚከናወንበት የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም በዋነኝነት ግን ጥናት

ለመጀመር የሆነ ችግር እንደሚያስፈልግ እና ይሄን ችግር መፍትሄ ለመስጠት ጥናቱ እንደሚካሄድ የታመነ ጉዳይ ነው፡፡

ስለዚህ ጥናት ሂደት19 እስከሆነ ድረስ ሂደቱ ከየት ወዴት የሚለው ደግሞ በህግ የተደነገገ ባይኖርም የጥናት ሂደት ሦስት

ዋና ዋና ሂደቶች የሚኖሩት ሲሆን እነሱም የጥናት እቅድ (Research planning or proposal)፣ የጥናት ትግበራ ወይም

የመረጃ ትንተና ማብራሪያ (Research implementation or data analysis and interpretation) እና የጥናት

ውጤትን ማቅረብ (presentation of research findings) ናቸው፡፡ ዝርዝር የጥናት ሂደቶች የሚባሉት ደግሞ ከዚህ

ቀጥሎ ባለው ፅሁፍ እንደሚከተለው በቅደም ተከተላቸው መሰረት ተዳሰዋል፡፡

 የጥናቱን ችግር መለየትና ርዕስ አቀራረፅ (identification and formation of the problem)

በየትኛው አይነት ጥናት የመጀመሪያው ስራ የአንድን ጥናት ችግር መለየት ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ የጥናት ሂደት የጥናቱ

ዋና ትኩረት የሚሆነውን ችግር የመለየትና ለጥናቱ አንድ ርዕስ የማስቀመጥ ስራ የሚሰራ ሲሆን እነዚህን ለመወሰን

በጉዳዩ ላይ በቂ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚችል፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ርዕሱ ጊዜውን ያገናዘበ እንዲሁም በተሰጠው ጊዜ

ውስጥ ማጠቃለል የሚቻል መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡

19
Uttarakhand Open University, Researching for Hospitality and Tourism Management, p.14, the process of research addresses two major
questions i.e. what is to be found and how it is be found. It is like planning a journey where we first decide where we are going and then we
decide how we shall be travelling. We have to identify important stopovers and routes, check points, modes available to reach the
destination.
20
 የተዛማጅ ፅሁፎች ዳሰሳ (literature review)

በዚህ ሂደት ውስጥ ጥናቱን የሚያካሂደው ሰው ከጥናቱ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ቀድመው የተፃፉ ፅሁፎችን

ይፈልጋል እንዲሁም ይዳስሳቸዋል፡፡ ይህን በሚያደርግበት ወቅት በጉዳዩ ላይ የተፃፉ ፅሁፎችን፣ ውሳኔዎችን፣

አስተያየቶችን፣ ሪፖርቶችን እና ዌብሳይቶችን የተለያዩ የአፈላለግ ዘዴዎችን በመጠቀም ጉዳዩ ጋር የሚገናኙትን ብቻ

በመምረጥ ይዳስሳሉ፡፡

 የጥናቱን ጠቅላላ እቅድ መንደፍ(research design)

ይህ የጥናት ሂደት ሙሉ ጥናቱን መሰረት ከመጀመሩ በፊት ጠቅላላ የጥናቱ አካሄድ ምን መምሰል እንዳለበት

የሚያስቀምጥ (blue print of the proposed research) ሲሆን ጥናቱ እንደ መረጃ ምንጭ ምን አይነት መረጃዎችን

ይጠቀማል፣ እነዚህን መረጃዎች በምን አይነት ዘዴ ይሰበሰባል እንዲሁም የጥናቱ አደረጃጀት ምን ይመስላል የሚሉትን

ይወስናል፡፡

 መረጃ መሰብሰብ (data collection)

አንድ ጥናት የሚያጠና ሰው ጥናቱ ለመመለስ የሚፈልገውን ጥያቄ ከለየ እና የተዛማጅ ፅሁፎችን ዳሰሳ በኃላ የመረጃ

ምንጮችን መሰብሰብ ይጀምራል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ በዋናነት መረጃ የመሰብሰቢያ ዘዴዎችን የሚወስን ሲሆን ይህም

መሰብሰብ እንዳሰባቸው የመረጃ ምንጮች የሚወሰን ይሆናል፡፡ መረጃዎችን በቃለ መጠይቅ፣ በፅሁፍ መጠይቅ፣

በምልከታ እና በሌሎች መንገድ ሊሰበሰብ ይችላል፡፡

 መረጃ ትንተና(data analysis)

መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኃላ ጥናቱን በሚያጠናው ሰው የሚደራጁበት እና ለማብራራት ዝግጁ የሚሆኑበት ደረጃ ሲሆን

መረጃዎች በሰንጠረዥ ወይም በተለያዩ ክፍሎች በማደራጀት ይካሄዳል፡፡ መረጃዎችን ለመተንተን በቡድን የመከፋፈል

ስልት ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ ክፍልፋዩቹ ጥናቱ በሚመልሳቸው ጥያቄዎች መሰረት እንዲደራጁ ይጠበቃል፡፡

 መረጃ ፍች/ማብራሪያ(data interpretation)

21
ይህ የጥናት ሂደት የተሰበሰቡት እና የተተነተኑት መረጃዎች ያመለከቱትን ድምዳሜ የምንሰጥበት ነው፡፡ የጥናቱን

ውጤቱ ከሌሎች ሀሳቦች ጋር በማቀናጀት

 የጥናት ሪፖርት (research report)

ይህ የመጨረሻው የጥናት ሂደት የሚባለው ሲሆን በዚህም የጥናቱ ችግር፣ አላማ፣ የምርምር ውጤት፣ ጥናቱ የደረሰበት

ድምዳሜ እና ምክረ ሀሳቦችን ማዘጋጀት ነው፡፡ የጥናት ሪፖርት ሦስት ክፍሎችን ማለትም አንደኛው ቀዳሚ

መጀመሪያ (Preliminary Pages)፣ ሁለተኛው ዋና ክፍል (the Main Text) እና ሶስተኛው የማጣቀሻ ዝርዝሮችና

ሌሎች አባሪዎች መያዝ ይኖርበታል፡፡

22
ምዕራፍ ሁለት

የሌሎች ተቋማት ተሞክሮ

ባለፉት ፅሁፎች የህግ ጥናት ሂደት መሆኑንና በተለያዩ አካላት እንደሚደረግ የተመላከተ ሲሆን ይህም በግለሰብ ወይም
በመስሪያ ቤት ደረጃ ሊሰራ ይችላል፡፡ አንድ ጥናት የሚካሄደው በመስሪያ ቤት ደረጃ ከሆነ ጥናት የሚያካሂደው በግለሰብ
የሚካሄድ ጥናት የጥናት ስራው በአግባቡ ለመምራትና ግቡን ለመምታት እንዲሁም ወጥነትን ለማስጠበቅና በጀትንና
ጊዜን በእቅድ ለመመራት የጥናት ስራ ሂደት የአሰራር መመሪያ አስፈላጊ ነው፡፡

በአሰሪና ሰራተኛ ህግ መሰረት ስራ መስጠት የአሰሪ ግዴታ ሲሆን ሰራተኛው ደግሞ የተሰጠውን ስራ በአግባቡ መስራት

አለበት የሚል መርህ አለ፡፡ ይህን የሰራተኛ ግዴታ ለመለካት ወይም ስራው በአግባቡ መሰራት አለመሰራቱን ለማረጋገጥ

የስራ አካሄድን ስርዓትን ማስቀመጥ አስፈላጊ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡

ከላይ ባሉት ፅሁፎች እንደተቀመጠው ጥናት ማለት ሳይንሳዊ አካሄድን ተከትሎ ለችግርች መፍትሄ ለመፈለግ የሚሰራ

ስራ ነው፡፡ ችግሩን ከመለየት ጀምሮ መፍትሄ ማቅረብ ድረስ ያለው አካሄድ በዘፈቀደ ሳይሆን ራሱን የቻለ የሚመራበት

አካሄድ አለው፡፡ እነዚህ አካሄዶች በየደረጃው ምን መምሰል አለበት የሚለውን የሚደነግግ አንድ ወጥ የሆነ የስራ አካሄድ

መመሪያ ወይም ጋይድላይን የለም፡፡ በዚህም የተለያዩ ተቋማት ይህን ሳይንሳዊ አካሄድ የሚመሩበትን አግባብ ምን

ይመስላል የሚለው ከዚህ ቀጥሎ ባለው ፅሁፍ እንደሚከተለው ተዳሷል፡፡

2.1 የሌሎች ተቋማት ተሞክሮ

በፍትህ ሚኒስቴር ውስጥ ከሚገኘው ህግ ጥናት፣ ማርቅቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ጋር የሚመሳሰል ስልጣንና

ተግባር ያላቸው የክልል ተቋማትን እንዲሁም የህግ ጥናትና ምርምር ማድረግ ዓላማቸው ከሆኑ ተቋማትን የህግ ጥናት

ስራ የሚመሩበት ተሞክሮ ለማየት ተሞክሯል፡፡ በዚህም መሰረት ተሞክሯቸው በዚህ ፅሁፍ የተዳሰሱት ተቋማት፡-

 የፌዴራል የፍትህና የሕግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት፡- ይህ ተቋም በአዋጅ ቁጥር 1071/2010 መሰረት

የተቋቋመ ሲሆን በአዋጁ አንቀፅ 5 ላይ እንደተመለከተው የዚህ ተቋም ዋና ዓላማ የአገሪቱን ህጎች የኢትዮጵያ

ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስትን በተሟላ ሁኔታ ስራ ላይ ለማዋል፣ የፍትህ እና የሕግ

ሥርዓቱን ብቁና ዘመናዊ ለማድረግ፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና በልማታዊና ዲሞክራሲያዊ

አስተሳሰብና የእድገት አቅጣጫ ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ ልማትን ለማፋጠን በሚያስችሉበት


23
ሁኔታ ለማሻሻል እንዲሁም አዳዲስ ሕጎችን ለማውጣት፤ እና የፍትህ አካላትን ዘመናዊ፣ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና

ውጤታማ በማድረግ በፍትህ ሥርዓቱ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፤ እንዲረዳ የሚያስችል ጥናትና

ምርምሮችን ማካሄድ ነው፡፡ በዚህ መሰረትም ይህ ተቋም ጥር 2007 ላይ በአዋጁ የተሰጠውን ስልጣንና

ተግባራት ለማስፈፀም ይረዳው ዘንድ የፍትህና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት የጥናት መመሪያ

አውጥቷል፡፡

 በአዲሱ የትምህርት ስነ ስርዓት (curriculum) መሰረት በኢትዩጲያ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች

በተለያየ መደብ የተከፋፈሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ሰባት ዩኒቨርስቲዎች የምርምር ዩኒቨርስቲ ተብለው

መለየታቸው ይታወቃል፡፡ የምርምር ዩኒቨርስቲ ከተባሉት ውስጥ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የምርምር ስራ አካሄድ

የሚመሩበት ሰነድ በዚህ ፅሁፍ ውስጥ የሚዳሰስ ይሆናል፡፡

 ከክልሎች የኦሮሚያ የህግ ባለሙያዎች የስልጠና እና ህግ ምርምር አንስቲትዩት፣ ኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ እና

የአማራ ክልል የፍትሕ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት የጥናት ስራ የአሰራር ሰነድ

በዚህ ፅሁፍ ተዳሷል፡፡

2.1.1 የሰነዱ አደረጃጀትን በተመለከተ

የፌዴራል የፍትህና የሕግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት የጥናት ስራ ሂደትን የሚደነግገው ሰነድ ‹‹የፍትህና የሕግ

ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት የጥናት መመሪያ›› የሚል አርዕስት ያለው ሲሆን ሰነዱ ‹‹መመሪያ›› የሚል ቢሆንም

የህግ መለያ ቁጥር ያልተሰጠው እና ሌሎች ህጎች ሊይዙት የሚችሉት ይዘቶችን ያልያዘ ነው፡፡ የዚህ ሰነድ ወይም

የመመሪያውን አደረጃጀት በሁለት ክፍሎች (ክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌ እና ክፍል ሁለት ቅድመ ጥናት ዝግጅት በሚል

ርዕስ) እንዲሁም በክፍል ሁለት ስር ሦስት ቁጥር (የተመራማሪው ሀላፊነትና የስነ ምግባር ጉዳዮች)፣ አራት ቁጥር

(የመረጃ ምንጮችና የማጣቀሻ ጽሁፎ አጻጻፍ ሥርዓት) እና አምስት ቁጥር (የአጻጻፍ ዘይቤና የማጣቀሻ አጠቃቀም)

በሚሉ ርዕሶች መመሪያው ተደራጅቷል፡፡ የመመሪያው ተፈፃሚነት ተቋሙ በራሱ እንዲሁም ከሌሎች አካላት ጋር

በመተባበር በሚያከናውናቸው ማናቸውም ጥናቶች፣ አጫጭር ጽሁፎች፣ ትንታኔዎች፣ ማብራሪያዎችና ህትመቶች

ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን ተቀምጧል፡፡

የአማራ ክልል የፍትሕ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት የጥናት ስራ ሂደት የሚመራበት ሰነድ

በህግ የተደነገገ ሲሆን የህጉ አይነት ደግሞ መመሪያ ሲሆን መመሪያውም ‹‹የጥናት ምርምር አፈፃፀም (research

24
guideline) እና የሕግ መፅሔት የሕትመት ፖሊሲ (Editorial Policy) መመሪያ›› የሚል ርዕስ አለው፡፡ ይህ መመሪያ

ቀድሞ በስራ ላይ የነበረውን መመሪያ ቁ.04/2003 ጥቅል እና የመጽሔት ህትመት ዝርዝር አፈጻጸምንም ያላከተተ

በመሆኑ በ 2003 ዓ.ም የወጣ መመሪያ ነው፡፡ አደረጃጀቱን ስናይ በአምስት ክፍል የተከፈለ ሲሆን ክፍል አንድ ጠቅላላ

ድንጋጌ፣ ክፍል ሁለት ስለ መጽሔት ህትመት፣ አማካሪ ቦርድ፣ ኤዲቶሪአል/አርትዖት ኮሚቴ አወቃቀር፣ ተግባር እና

ኃላፊነት፣ ክፍል ሶስት በኢንስቲትዩቱ ስለሚሰሩ ወጥ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚል ሲሆን በውስጡ ሦስት ንዑስ

ክፍሎችን (ጠቅላላ፣ ስለ ጥናት እና ምርምር ይዘት /ቅደም-ተከተል/ እና የመረጃ ምንጭ አገላለጽ ስርዓት) ያካትታል፤

ክፍል አራት የተመራማሪው ኃላፊነትና የስነ-ምግባር ጉዳዮች እንዲሁም ክፍል አምስት የሙሉ ጥናትና ምርምሮች

የምዘና ስርዓት በሚል ርዕስ የተደራጀ ነው፡፡ መመሪያ ኢንስቲትዩቱ በራሱ ተመራማሪዎች ወይም በተጋባዥ

ተመራማሪዎች አማካኝነት በባለቤትነት በሚያሰራቸው ወጥ/ሙሉ የጥናት እና ምርምር ስራዎች እንዲሁም

ለመጽሔት ህትመት በሚቀበላቸው ጽሁፎች ላይ ተፈፃሚነት አለው፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ሆኖ መመረጡት መሰረት በማድረግ በዩኒቨርሲቲ ው የሚካሄዱ ጥናቶች ችግር

ፈችነታቸውን ለማረጋገጥ እና የጥናት ወጥነትን ለመጠበቅ በሚል ዓላማ ሰኔ/2013 የጎንደር ዪኒቨርስቲ የጥናትና

ህትመት ጋይድላይን (research and publication guideline) ስራ ላይ አውሏል፡፡ ጋይድላይኑ ሰባት ክፍሎች ያሉት

ሲሆን መግቢያ፣ የጥናት ጋይድላይን፤ የጥናት እቅድ፣ ህትመት፣ አቅም ግምባታ፣ አካታችነት፣ የአካዳሚክና የምርምር

ውይይት፣ የጥናት የበጀት ምንጭ እና የጥናት ስነ ምግባር የሚታይበት ስነ ስርዓት የሚሉት ናቸው፡፡ ይህ ጋይድላይን

ተፈፃሚነቱ ባይገለፅም ከመግቢያው መረዳት እንደሚቻለው በዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ወይም ዩኒቨርስቲው ጥሪ

መሰረት በሚካሄድ ጥናት ላይ ተፈፃሚ ነው፡፡ የዚህ ሰነድ ዋና ይዘት ስንመለከት አንድ የጥናት ወይም ምርምር ስራ

በተመለከተ ማካታት ያለባቸውን ፍሬ ነገሮች በተመለከተ ሳይሆን የጥናት ስራ እንዴት ይጀመራል፤ የጥናቱን እቅድ

ተመልክቶ ማፅደቅ ያለበት ማን ነው፤ የጥናት በጀት ምንጮች እንዴት ይገኛሉ እንዲሁም ጥናቱን የሚያካሂድ ሰው

ሊቀጣባቸው የሚችሉት የስነ ምግባር ጉድለቶችን የሚሉትን ነጥቦች የያዘ ነው፡፡

2.1.2 ቅድመ ጥናት ስራዎችን በተመለከተ

የፌዴራል የፍትህና የሕግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ቅድመ ጥናት ስራዎችና የጥናት ዕቅድ የሚሉባሉትን ሁለቱን

ሀሳቦች በአንድ ክፍል ስር ያስቀመጠው ሲሆን ለዳሰሳው እንዲመች በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ሁለቱ ተለያይተው ተዳሰዋል፡፡

መመሪያው ሁለት የቅድመ ጥናት ስራዎች ብሎ ያስቀመጣቸውን ስናይ አንደኛ ምክር ሀሳብ በሚለው አርዕስት

25
ማንኛውም ጥናት ከመጀመሩ በፊት በጥናቱ ሊዳሰስ የታለመውን ችግር፣ የጥናቱን አስፈላጊነት እና በሥራ ላይ

የሚውሉትን የጥናት ዘዴዎች የሚገልፅ የጥናቱ አካል መሆኑን ገልፆ የጥናቱን አስፈላጊነት እንዲያሳምን፣ አጥኚው

በጉዳዩ ዙሪያ ዕውቀትና ችሎታ እንዳለ በሚያሳይ እንዲሁም በወደፊት ጊዜ አገላለፅ መቀመጥ እንዳለበት

ያስቀምጣል20፡፡

ሁለተኛው የአርእስት አመራረጥና ተቀባይነት በሚመለከት ሲሆን ይህም የጥናት ርዕስ ከተቋሙ ውጭ ወይም ውስጥ

ማሰባሰብ እና የተሰበሰቡ ርዕሶችን ከተቋሙ ተልእኮና አላማ ጋር ያለው ግንኙነት፤ የርዕሱ ወቅታዊነትና ችግር ፈችነት

እንዲሁም ከርዕሱ ስፋት አኳያ የኢንስቲትዩቱ የሰዉ ሀይልና የገንዘብ አቅም እና በርዕሱ ላይ ቀደም ብሎ ወቅታዊና በቂ

ጥናት የተሰራ አለመኖሩን ከግምት ውስጥ በማስገባት ርዕስ ይመረጣል ይላል፡፡ በተጨማሪም የጥናት ርዕስ አጭር፣

ገላጭ፣ ግልፅና የሚስብ መሆን እንዳለበት ቢያስቀምጥም አንድ ርዕስ መቼ ነው አጭር፣ ገላጭ፣ ግልፅና የሚስብ ነው

የሚባለው ለሚለው ግን መስፈርት አላስቀመጠም፡፡ ከሌሎች አካላት ጋር የሚደረግ ጥናት የባለድርሻውን ፍላጎት

ማርካት የሚችል መሆን ይኖርበታል21 በሚል የሚደነግግ ሲሆን ‹‹የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ማርካት›› የሚለው ቃል

እስከምን ድረስ እንደሚኬድ በግልፅ አልተቀመጠም፡፡

የአብክመ ፍትሕ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት መመሪያ ከፌዴራሉ ጋር በይዘት በሚመሳሰል

መልኩ ሁለት ጉዳዩችን ይዞ የተቀረፀ ነው፡፡ በመመሪያው አንቀፅ 38 ላይ እንደተመለከተው ከላይኛው የሚለየው

የአንቀፁ ርዕስ ‹‹የቅድመ ጥናት ንድፈ ሀሳብ (proposal)›› በሚል ሲሆን የፌድራሉ ግን ምክረ ሀሳብ ዝግጅት የሚል

ርዕስ መሰጠቱ ላይ እንዲሁም ቅድመ ጥናት ላይ የሚቀርበውን ፅሁፍ ገምግሞ ዋናው ጥናት እንዲጀመር ወይም

እንዳይጀመር የሚወስነው አካል በፌዴራሉ ያልተቀመጠ ሲሆን በአብክመ ፍትሕ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የሕግ

ምርምር ኢንስቲትዩት መመሪያ ላይ ግን በመመሪያው የተቋቋመው አርትዖት ኮሚቴ እንደሆነ መደንገጉ ነው፡፡ ሌላኛው

የጥናት አርዕስት አመራረጥ ሲሆን ይህ መመሪያ ከፌዴራሉ ጋር ከአንቀፁ ርዕስ ጀምሮ ተመሳሳይ ሲሆን የጥናት

አርዕስቱን የሚያፀድቀውን አካል ያስቀመጠ መሆኑ እና ከላይ የፌዴራሉ ላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ርዕስ

ሊገመገምበት ከሚችሉት መስፈርት ውስጭ ‹‹ሊሰራና ወደ ተግባር ሊቀየር የሚችል መሆን›› አለበት የሚለው ብቻ

ነው እንደ አዲስ የተጨመረው፡፡

20
የፌዴራል የፍትህና የሕግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት የጥናት መመሪያ 2.1
21
የፌዴራል የፍትህና የሕግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት የጥናት መመሪያ 2.1(4)
26
2.1.2 የጥናት ዕቅድን (research proposal) በተመለከተ

በምዕራፍ አንድ ላይ እንደተቀመጠው የጥናት እቅድ በውስጡ የጥናቱ ወሳኝ የሚባሉ ክፍሎችን የያዘ ነው፡፡ የፌዴራል

የፍትህና የሕግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት እና የአብክመ ፍትሕ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የሕግ ምርምር

ኢንስቲትዩት መመሪያ የጥናት ዕቅድ ስራ አካሄድን እና ሊይዙት የሚገባውን ፍሬ ነገር በተመለከተ ሙሉ በሙሉ

ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ስለሆነም የተቋማት የጥናት ስራ አመራራቸውን የወሰኑበት ሰነድ እነዚህን ጉዳዩች በተመለከተ

ያስቀመጡትን አቅጣጫዎች እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡፡

 የጥናቱ መግቢያ፡- በጉዳዩ ዙሪያ ቀደም ሲል የነበረውንና አሁን ያለውን ሁኔታ በማውሳት የጥናቱን አስፈላጊነት

መግለፅ እንዳለበት ተቀምጧል፡፡ የጥናቱ ዳራ፡- ለአንባቢዉ ስለጥናቱ በቂ መረጃ የሚሰጥ፣ ጥናቱ ከሌሎች

ጥናቶች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ማሳየት የሚችል፣ አንባቢው በርዕሱ ላይ ፍላጎት እንዲኖረዉ የሚያደርግ፣

ለጥናቱ መነሻ ለሆነዉ ችግር ሰፊ መሰረት የሚጥል እንዲሁም ጥናቱን በሌሎች ጥናቶች ምህዳር ውስጥ

ማስቀመጥ የሚችል መሆን እንዳለበት ይደነግጋሉ፡፡

 የችግሩ መገለጫ፡- ግልፅ በሆነ መልኩ ጥናቱ እንዲካሄድ ያስፈለገበት መነሻ ምክንያት/ቶች በፅሁፍ፣ በሃሊዎት

/theory/ ወይም በተግባር ያለውን ክፍተት /ችግር/ ማመልከት አለበት፡፡

 የጥናቱ አላማዎች፡- የጥናቱ ዓላማዎች ከችግሩ መገለጫ ጋር በተጣጣመ መልኩ በጥያቄ ወይም የትንበያ መነሻ

ካለ በመላምት መልክ እንደ አስፈላጊነቱ ጠቅላላና ዝርዝር ዓላማዎች በሚል ሊቀረፅ ይገባል፡፡

 የጥናቱ ዘዴ፡- ጥናቱን ለማከናወን የተመረጠው ዘዴ ከጥናቱ አላማን ማሳካት የሚያስችል ግልፅ ማብራሪያ

መሰጠት ያለበት ሲሆን ከአንድ በላይ የጥናት ዘዴ የተመረጠ ከሆን በእያንዳንዱ የጥናት ዘዴ ምን እንደሚሰራ፤

መልስ ሰጭዎች እንዴት እንደሚመረጡ እንዲሁም ናሙና እንዴት እንደሚወሰድ እና ናሙና እንዴት

እንደሚሰበሰብ፤ ምን አይነት መረጃ በምን አይነት ዘዴ እንደሚሰበሰብ እና ዘዴ ከሌሎች ዘዴዎች ተለይቶ

የተመረጠበትን አግባብ/ምክንያት በሚገባ ማብራሪያ ሊሰጠው ይገባል፡፡

 የጥናት ፅሑፎች ዳሰሳ /literature review/፡- ዙሪያ የተሰሩ ወቅታዊ ጥናቶችን በአግባቡ መተንተን፣

የማጣቀሻ ፅሑፎቸንና ሌሎት የመረጃ ምንጮችንም መጥቀስ፤ በቂ ጥናት እንዳልተሰራ ወይም በቂ ጥናት ካለ

ደግሞ በድጋሜ መስራት ያስፈለገበትን ምክንያት ማብራራት እንዲሁም በብዛት/በስፋት የምንጠቀምባቸዉ

ላይ ብቻ መዳሰስ አለበት፡፡

27
 የጥናቱ ወሰን፡- በጥናቱ የሚሸፈኑት ጉዳዮች ለምን እንደተመረጡና የማይሰራባቸው ጉዳዮች ደግሞ ለምን

እንደቀሩ እና በጥናቱ ውስጥ ይካተታሉ ብሎ የሚጠብቃቸውን ነገር ግን ጥናቱ በዝርዝር በተገለጡ ምክንያቶች

የማያካትታቸውን ጉዳዮች ለይቶ ማስቀመጥ አለበት፡፡

 የጊዜ መርሀ-ግብርና በጀት፡- እያንዳንዱን ስራ ለማከናወን የሚያስፈልገውን ጊዜ፣ የሰዉ ሃይልና የበጀት ዝርዝር

የያዘ ቢጋር (termes of refferance) መያዝ አለበት፡፡

በአጠቃላይ የሁለቱም ተቋማት የጥናት መመሪያ የጥናት እቅድን በተመለከተ ያስቀመጡት ድንጋጌ ይዘትን ስንመለከት

በጉዳዩቹ ላይ ምን ምን መካተት አለበት የሚለው በዝርዝር ያልተቀመጠ እንዲሁም ለትርጉም የተጋለጠ ነው፡፡

ይልቁንም ከሰነዶቹ እንደምንረዳው መካተት ያለባቸውን ሳይሆን እንዴት እንደሚፃፉ ያለውን ሂደት የሚደነግጉ

ናቸው፡፡ በእርግጥ ሂደቱ መቀመጡ አስፈላጊ ቢሆንም እያንዳንዱ ርዕስ ላይ የሚካተቱትን ጉዳዩ በተመለከተ

ተለይተውና ተብራርተው አለመቀመጣቸው ግን እንደክፍተት የሚወሰድ ነጥብ ነው፡፡

2.1.3 የጥናት ሪፖርት በተመለከተ

የጥናት ሪፖርትን በተመለከተ የፌዴራል የፍትህና የሕግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት በጥናት መመሪያው ውስጥ

የጥናት ሪፖርት አቀራረብ ስርዓት በሚል ርዕስ ስር የጥናት ስራ ተጠናቀቀ የሚባለው የጥናት ሪፖርት ሲቀርብ እንደሆነ

እንዲሁም የጥናት ሪፖርት ሦስት ዋና ዋና ክፍል እንደሚኖሩት አስቀምጧል፡፡ በዚህ መመሪያ መሰረት የጥናት ሪፖርት

የሪፖርቱ ቀዳሚ፣ የጥናቱ ሪፖርት ዋናው ክፍል እና የጥናቱ ሪፖርት የመጨረሻው ክፍል የሚባል ክፍሎች እንዲሁም

እያንዳንዱ ክፍል ደግሞ በውስጡ የተለያዩ ርዕሶችን ሊያካትት የሚገባ እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን በእያንዳንዱ

ንዑስ ክፍል ውስጥ ምን መካተት አለበት እንዴት ይፃፍ የሚለውን መልስ የሚሰጥ ድንጋጌ መመሪያው የለውም፡፡

የአብክመ ፍትሕ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት መመሪያ የጥናት በሌላ በኩል ስለ ጥናት

ሪፖርት ምን ማያዥ አለበት እንዴት ይፃፋል የሚለውን በተመለከተ የሚደነግግ አንቀፅ አላስቀመጠም፡፡ ነገር ግን ከላይ

በፌዴራል የፍትህና የሕግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት በጥናት መመሪያው ውስጥ የተካተቱ ለምሳሌ፡- የጥናት

አሕፅሮተ-ቃላት እና መግቢያ በተመለከተ ያስቀመጠው ድንጋጌ አለ፡፡

28
2.1.4 የተመራማሪው ሀላፊነትና የስነ ምግባር ጉዳዮች

የሁለቱም ተቋማት ሰነድ ማለትም የፌዴራል የፍትህና የሕግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት በጥናት መመሪያ እና

የአብክመ ፍትሕ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት መመሪያ ጥናቱን የሚያካሂድ ሰው የስነ

ምግባር ሁኔታን ስምምነት እንዲኖር ስለማስፈለጉ፣ ምስጢራዊነት እና ሌሎች የስነ-ምግባር ኃላፊነቶች በሚል

አርዕስት ያስቀመጡ ቢሆንም የፌዴራሉ ከስነ ምግባር በተጨማሪም ተቋሙ በጥናቶቹ ላይ የሚኖረው መብት እና

የስራ ዲስፐሊን በተመለከተ ተጨማሪ ድንጋጌ አስቀምጧል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የክልሉ የተመራማሪውን ነፃነት

በተመለከተ ተጨማሪ ድንጋጌን ሲጨምር የተመራማሪዉን ነፃነት በተመለከተ ግን የፌዴራሉ መመሪያ ያለው ነገር

የለም፡፡

2.1.5 የመረጃ ምንጮችና የማጣቀሻ ጽሁፎ አጻጻፍ ሥርዓት

የፌዴራል የፍትህና የሕግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት በጥናት መመሪያ እና የአብክመ ፍትሕ ባለሙያዎች

ማሰልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት የጥናት መመሪያ የጥናት ስራ የሚያካሂድ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ

መንገድ የሌላን ሰው ስራ በጥናቱ ውስጥ በምንጭነት ተጠቅሞ ከሆነ ማጣቀስ እንዳለበት እንዲሁም እንዴት ማጣቀስ

እንደሚችል ለማጣቀሻነት በተጠቀመው የሰነድ አይነት እና በማጣቀሻ አይነቶች ከፋፍለው አስቀምጠዋል፡፡

2.1.6 የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ ተሞክሮ22


የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የጥናት ስራ የሚመራበት ስርዓት በማኑዋል ደረጃ የተዘጋጀ በ 2009 ዓ.ም ተዘጋጅቷል፡፡ ማኑዋሉ

በርካታ ጉዳዮችን ያካተተ ሲሆን ዋና ዋና ጉዳዮች፡- የተለያዩ ቃላት ትርጉምና ጠቅላላ ሀሳቦች፣ የጥናት ዓላማ፣ የህግ

ጥናት አይነቶች፣ የህግ ጥናት ሞዴሎች፣ የጥናት ቋንቋ፣ የጥናት በጀት ምንጭ፣ የጥናት ዝግጅት ስራዎችና የጥናት

እቅድ፣ የጥናት እቅድ ግምገማ፣ የመረጃ ምንጭ አጠቃቀስ፣ የጥናት ሪፖርት ዝግጅትና ይዘት፣ የጥናት ስራ አስተዳደርና

ስነ ምግባር ሁኔታ እና ሌሎቸ ዝርዝር ጉዳዮችን ተካተዋል፡፡

የጥናት በጀት ምንጭን አስመልክቶ ከቢሮው በየአመቱ የሚመደብ እና ከአጋር ድርጅቶች በሚገኝ ድጋፍ እንደሚሸፈን

ተቀምጧል፡፡ ለጥናት ስራ የሚደረገው ዝግጅትን በተመከለተ የጥናት ርዕስ በተግባር በሚታይ ጉዳይ መሆንን፣

ወቅታዊነትነትን፣ አስፈላጊነትን፣ የህግ ነክ ጉዳይ መሆንን፣ አዲስ ጥናት ወይም አዲስ ባይሆንም በዝርዝር ማጥናት

የሚያስፈልግ መሆኑን፣ ርዕሱ አጭርና ግልጽ መሆን እንዳለበት እንደ መመዘኛ ተቀምጧል፡፡ ጥናት ለማድረግ እቅድ

22
የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የጥናት ማኑዋል 2009
29
(ፕሮፖዛል) መዘጋጀትና በቢሮው መጽደቅ እንዳለበት፣ የችግሩ መግለጫ፣ የጥናቱ ዓላማና አስፈላጊነት/ጠቀሜታ፣

የጥናቱ ወሰን፣ ዘዴ፣ ጥናቱን የሚያከናውን አካል፣ ድርጊት መርሃ ግብር መያዝ እንዳለበት በማኑዋሉ ተገልፆል፡፡

የመረጃ ምንጮች አጠቃቀም በማኑዋሉ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በቃለመጠይቅ፣ ከመጽሐፍት/መጽሔት፣ ከኢንተርኔት፣

ከፍርድ ቤት ውሳኔዎች መረጃ ሲወሰዱ በምን መልኩ መጠቀስ እንዳለባቸው ተገንግጓል፡፡ የጥናት ሪፖርት ዝግጅትና

ይዘት በማኑዋሉ የተቀመጠ ሲሆን የጥናቱ ርዕስ፣ የጥናቱ ችግር መግለጫ፣ ዓላማ/ስፈላጊነት፣ ወሰን፣ የጽንሰ ሀሳብ

ማብራሪያ ክፍል፣ የመረጃ ትንተና ክፍል፣ ማጠቃለያና ምክረ ሀሳብ መያዝ እንዳለበት ተገልፆል፡፡ እነዚህ የሪፖርት ሰነዱ

ይዘቶች በግልፅ መቀመጥ እንዳለባቸው እና መረጃን መሰረት ያደረጉ ወይም በቂ ማብራሪያ ያላቸው መሆን

እንዳለባቸው ማኑዋሉ ያብራራል፡፡

በተጨማሪም የጥናቱ ግኝቶችና ምክረ ሀሳቦች ወደ ስራ የሚገቡበት ሁኔታም የተደነገገ ሲሆን በጥናቱ ዙሪያ

ውይይቶችን ማድረግ፣ የጥናቱን ግኝት ማሳተምና ተደራሽ ማድረግ፣ የህግ ማዕቀፍ ችግር እንደ ግኝት ከተቀመጠ የህግ

ማዕቀፍ ዝግጅት ማከናወን እንደሚገባ ተገልፆል፡፡

የጥናት ስራ አስተዳደርና ስነ ምግባር ሁኔታን በተመለከተ የጥናት ስራው በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ መጠናቀቅ

እንዳለበት፣ በስራ ሂደት የተገኙትን መረጃዎች በአግባቡና በምስጥር መያዝ እንደሚገባ በማኑዋሉ ተብራርቷል፡፡

በመጨረሻም የጥናት ስራው ስታንዳርድ እና አስፈላጊ ቅፆች እንደ አባሪ ተደርገዋል፡፡

2.1.7 የኦሮሚያ የህግ ባለሙያዎች የስልጠና እና ህግ ምርምር አንስቲትዩት ተሞክሮ23


በኢንስቲትዩቱ የጥናት ስራ የሚመራበት ስርዓት በመመሪያ ደረጃ (መመሪያ ቁጥር 03/2004) ተዘርግቷል፡፡

የመመሪያው ይዘት ሲታይ የቃላት ትርጉም፣ የጥናት ዓላማዎች፣ የጥናት መርሆች፣ የጥናት ቡድን፣ የተለያዩ

አካላት/ኃላፊዎች ሚና፣ የጥናት ዝግጅትና እቅድ፣ የጥናት ግኝት ተግባራዊ ማድረግ፣ የጥናት ውጤትን/መረጃ መያዝ፣

የጥናት ግምገማ፣ የአጥኚ ቡድን መብትና ግዴታ፣ የጥናቱ ባለቤትነት እና የመሳሰሉት ጉዳዮች የተገለፁበት

ድንጋጌዎችን የያዘ መመሪያ ነው፡፡

መመሪያው አንድ ጥናት የሚመራበት የተለያዩ መርሆችን ያስቀመጠ ሲሆን ታማኝነት፣ ተጨባጭነት፣ ተቀባይነት፣

ግልፀኝነት፣ ተደራሽነት፣ ሀቀኝነት፣ አድልዎ አለማድረግ፣ ተጠያቂነት የጥናት መርሆች እንደሆኑ ተቀምጧል፡፡
23
የኦሮሚያ የህግ ባለሙያዎች የስልጠና እና ህግ ምርምር አንስቲትዩት የጥናት መመሪያ ቁጥር 03/2004

30
የጥናት ስራ አስፈፃሚ አካላትን በተመለከተ የጥናት እቅድን የሚያጸድቅ፣ የጥናቱን ጥራት የሚከታተል እና የጥናቱን

ወጪ የሚወስን የኢንስቲትዩቱ ጉባኤ እንዲሁም ጥናቱን የሚያከናውን አጥኚ ቡድን እንደሚቋቋም መመሪያው

ያስቀምጣል፡፡

የጥናት ስራ ዝግጅትን በተመለከተ የጥናት ርዕሶች በአመት ተለይተው መታቀድ እንዳለባቸው፣ ርዕሶቹ የፍላጎት ዳሰሳ

መለየት እንደሚገባቸው፣ ያለውን በጀት ከግምት ገብቶ እንደሚወሰኑና በተቋሙ ኃላፊ ፀድቀው ወደ ስራ እንደሚገቡ

የኢንስቲትዩቱ መመሪያ ያሳያል፡፡

የጥናት ግምገማን በተመለከተ በአጥኚ ቡድን የተከናወነ ጥናት በዘርፉ ልምድ ባለው ባለሙያ ወይም የባለሙያዎች

ቡድን እንደሚገመገም በመመሪያው ተገልፆል፡፡ ይህ ግምገማ መጨረሻ ላይ ብቻ ሳይሆን በየምዕራፉ መደረግ

እንደሚገባ እና ግምገማውም ከጥናት ፎርማት እና ጥራት አንፃር እንደሚሆን ተቀምጧል፡፡

የጥናት መመሪያው የአጥኚ ቡድን አባላትን መብትና ግዴታ የሚደነግግ ሲሆን ሀሳባቸውን የመግለፅ መብት እንዳላቸው

እና ጥናቱን በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ተገልፆል፡፡ የጥናቱ ባለቤትነትን

በተመለከተ በኢንስቲትዩቱ የሚከናወኑ ጥናቶች የተቋሙ እንደሚሆኑ፣ አጥኚ ቡድን አባላት በሰነዶች መጠቀስ

እንዳለባቸው እና አጥኚው ባደረገው ጥናት የፈጠራ ባለቤትነት የማግኘት መብት እንዳለው መመሪያ ያብራራል፡፡

31
ምዕራፍ ሦስት

የፍትህ ሚኒስቴር ነባሩ አሰራር

በዚህ ፅሁፍ በምዕራፍ አንድ ላይ እንደተገለፀው ጥናት ወጥ የሆነ አንድ ትርጉም ካለመኖሩ በመነሳት ጥናት በበሚጠናው

ጉዳዩ መሰረት ተደርጎ ብዙ ጊዜ ይተረጎማል፤ በዚህም በዋናነት ሶስት መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ የተለያዩ የጥናት

አይነቶች እንዳሉ ተመላክቷል፡፡ በተጨማሪም ጥናት ከሚያስፈልጋቸውና የጥናት ስራ ከሚያካሄድባቸው ዘርፎች

ውስጥ ህግ አንዱ እንደሆነ የህግ ጥናት በዋነኝነት ሦስት አላማዎችን ለማሳካት እንደሚካሄድ እና የህግ ጥናት በእነማን

ሊካሄድ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓ/ህግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ.943/2008 (እንደተሻሻለው) አንቀፅ

6(4) (ለ) የህግ ማሻሻያ ጥናቶች ይሰራል፤ አንቀፅ 6(6) የፌደራል ጠቅላይ ዓ/ህግ የፌዴራል መንግስቱ ህጎችን ተግባራዊ

መደረጋቸውን እና አገተባበራቸውን ወጥነት ያለው መሆኑን ያረጋግጣል እንዲሁም አስፈፃሚ የፌዴራል መንግስት

መ/ቤቶች ስራቸውን በህግ መሰረት ማከናወናቸውን ያረጋግጣል እንዲሁም አንቀፅ 6(10) አሰራሩን ውጤታማ እና

ቀልጣፋ ለማድረግ ጥናትና ምርምር ያደርጋል በማለት ስልጣንና ተግባር ይሰጠዋል፡፡ በዚህ የህግ ድንጋጌ የተሰጠውን

ስልጣን ለማስፈፀም ተቋሙ የተለያዩ የህግ ጥናቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የዚህ ምዕራፍ አላማ በተቋሙ የተሰሩ የተለያዩ የጥናት ስራዎችን በመዳሰስ የተቋሙን የጥናት ስራ አካሄድ በማሳየት

በአሰራሩ ላይ የታዩ ክፍተቶችን ማስቀመጥ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ በተለያየ የተቋሙ የስራ ክፍሎች በተለይም የጥናት

ስራ የሚሰሩ የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጄኔራል፤ የፌድራል ህጎች ተፈጻሚነት መከታተያ

ዳይሬክቶሬት እና ሴቶች፣ ህፃናትና ባለብዙ ዘርፍ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ስር የተሰሩ ጥናቶች በናሙናነት

ተወስደዋል፡፡

3.1 የህግ ማሻሻያ ጥናቶች

ከላይ በዚህ ምዕራፍ መግቢያ ላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ፍትህ ሚኒስቴር ከተጣለበት ሀላፊነት ውስጥ የህግ ማሻሻያ

ጥናቶችን ማካሄድ ሲሆን ይህን ሀላፊነቱን ለመወጣት ተቋሙ በተለያዩ ጊዜ የህግ ማሻሻያ ጥናቶችን አከናውኗል፡፡

የህግ ማሻሻያ ጥናቶች በአንድ ጉዳይ ላይ ያለ ህግ የታሰበውን ግብ እንዳያሳካ የሚያደርጉ የህግ እና የአሰራር ክፍተቶችን

በመለየት ህጉ ተግባራዊ ለማድረግ ወይም የታሰበውን ነገር ለማሳካት ይጠቅማል የሚባለውን ምክረ ሀሳብ የሚጠቁም

ነው፡፡ ይህ ጥናት ግማሾቹ የህግ ድንጋጌዎችን ብቻ የሚዳስሱ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ የህግ ድንጋጌዎችንና በተግባር

32
ያለውን አሰራር ይዳስሳሉ፡፡ ይህ አይነት ጥናት በዋናነት የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጄኔራል

የተባለው የስራ ክፍል ሲሆን ይህ የስራ ክፍል ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ያከናወናቸው ስድስት ጥናቶችን

በመውሰድ በዚህ ፅሁፍ ተዳሰዋል፡፡

3.1.1 የጥናት እቅድን በተመለከተ

በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ጥናቶች ሁሉም የጥናት እቅድ ያላቸው ሲሆን የጥናት እቅድ ይዘታቸው ግን ከአንዱ ወደ አንዱ

የተለያየ ነው፡፡ ሁሉም ጥናቶች በጥናቱ እቅድ ክፍል ውስጥ መግቢያ፣ የጥናቱ አላማ፣ የጥናቱ ዘዴ እና የጥናቱ ውስንነት

የሚሉትን ነጥቦች አካተዋል፡፡

መግቢያ በሚለው ስር ጥናት የሚካሄድበት ጉዳይ የኃላ ታሪክ፣ ጥናቱ ማካሄድ ለምን አስፈለገ እንዲሁም ጥናቱ በምን

ዙሪያ ያጠነጥናል የሚሉትን ነጥቦች ያካተተ ሲሆን በአንዳንድ ጥናቶች በዚህ ክፍል ስር የጥናቱ መዋቅር ምን ይመስላል

የሚለውን ያስቀምጣሉ24፡፡ በሌላ በኩል በአንድ ጥናት መግቢያ በሚለው ስር የተዳሰሱ ነጥቦች በሌላ ጥናት ደግሞ

ታሪካዊ ዳራ በሚል ርዕስ ውስጥ የሚነሱ ነጥቦች ናቸው፡፡25 የጥናቱ አላማ በተመለከተ ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው

የህግ ማሻሻያ ጥናት እስከሆነ ድረስ ይህን አላማ አድርገው የሚሰሩ ጥናቶች የህግ ክፍተቶችን መለየትና ምክረ ሀሳብ

ማቅረብ ነው በማለት አላማ በሚለው ስር ተካቶ ይገኛል፤ ስለሆነም አላማ በተመለከተ ተመሳሳይ ነው፡፡ የጥናቱ አላማ

አቀራረፅ ላይ ልዩነት ያለ ሲሆን ግማሹ ጥናት የጥናቱ አላማ በሁለት ከፍሎ ጠቅላላ አላማና ዝርዝር አላማ26 በማለት

ከፍሎ ሲያስቀምጥ ቀሪዎቹ ደግሞ አላማ የሚለውን ምንም ሳይከፋፍሉ27 ያስቀምጣሉ፡፡ ሌላው በጥናት እቅድ ውስጥ

የሚገኘው የጥናት ዘዴ ሲሆን እነዚህ በአብዛኛው የጥናት ዘዴ በሚለው ስር የመረጃ ምንጮችንና መረጃዎቹ

የተሰበሰቡበትን ዘዴ ሲሆን በዚህም መረጃ የሚተነተንበተን እና ናሙና አወሳሰድ ዘዴን አይገልፁም፡፡28 የተወሰኑት

የጥናት ዘዴ ስር ምን አይነት መረጃ በምን አይነት ዘዴ ይሰበሰባል እንዲሁም ይተነተናል የሚለውን በግልፅ ያስቀምጣሉ፤

24
ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ የሙስና ወንጀል ድንጋጌ የተጠያቂነት አድማስ በኢትዮጵያ፣ የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጀነራል፣ ታህሳስ
2014 ዓ.ም

25
የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቶች የህግ ማዕቀፍ፣ አደረጃጀት እና አሰራር በኢትዮጵያ፡- ትኩረቱን በፌዴራል ደረጃ ባሉ የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቶች ላይ ያደረገ

የዳሰሳ ጥናት፣ የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጀነራል፣ ህዳር 2015 ዓ.ም

26
ዝኒ ከማሁ 25 እና 26
27
በወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 ላይ የሚስተዋልና መሰረታዊ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው የህግ ጉዳዮችን ለመለየት፣
28
በወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 ላይ የሚስተዋልና መሰረታዊ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው የህግ ጉዳዮችን ለመለየት
የተደረገ ጥናት
33
ሁለቱም ላይ ግን የተጠቀሰውን ዘዴ ለምን እንደሚጠቀሙ ማብራሪያ አልተሰጠም፡፡29 አንድ አይነት ጥናት አንድ አይነት

ውስንነት የፃፉ ጥናቶች የተለያየ የጥናት ዘዴን እንደሚከተሉ ከሰነዶቹ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በተጨማሪም የጥናት

ውስንነት ሁሉም ጥናቶች አካተው የሚገኝ ሲሆን ሁሉም ጥናቶች ጊዜና መረጃ እጥረት ምክንያት ጥናቱ በጥልቀት

ማየት አልተቻለም ሲሉ አንዳንድ ጥናቶች በተግባር ያለው ሁኔታ ባለመዳሰሱ ምክንያት ጥናቱ ያልተሟላ ሆኗል

በማለት የጥናት ዘዴ ክፍተት መኖሩን ያሳያሉ፡፡

አብዛኞቹ ጥናቶች የችግሩ መግለጫ፣ የጥናቱ ወሰን፣ የጥናቱ ጥያቄዎች፣ የጥናቱ አስፈላጊነት እንዲሁም የጥናቱ

መዋቅር የሚገልፅ የጥናት እቅድ ክፍል ሙሉ በሙሉ የላቸውም ወይም ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ብቻ ናቸው

አሟልተው የሚገኙት፡፡ ይህ ቢሆንም የእነዚህ ክፍሎችን ያካተቱ ጥናቶች እንዴት እንደቀረፆቸው እንደሚከተለው

ተዳሷል፡፡

የችግሩ መግለጫ ያካተቱ ጥናቶች በዚህ ክፍል ስር በጉዳዩ ላይ እየገጠሙ ያሉ ችግሮችን እና ጥናቱ ለምን እንደሚካሄድ

ይዳስሳሉ፡፡ የጥናቱ ጥያቄዎች ጠቅላላና ዝርዝር ጥያቄዎች በማለት በስድ ንባብ ሳሆን በመጠይቃዊ ዓ/ነገር የተቀመጡ

ሲሆን የጥናቱ አስፈላጊነትን በተመለከተ አንዳንድ ጥናቶች የጥናቱ ጠቀሜታ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የሚገኝ ሲሆን

በውስጥም ጥናቱ የሚያደርገውን አስተዋፅዖ የሚዳስሱ ሲሆን ለማን ምን አይነት አስተዋፅዖ ይሰጣሉ የሚለው

ተለይቶ አልተቀመጠም፡፡ የጥናቱ ወሰን በሚለው ስር ጥናቱ የቦታ ወሰንን፣ የሚዳሰሱ ህጎችንና ጉዳዩ ከብዙ አንፃር

የሚታይ ከሆነ ከየትኛው አንፃር እንደሚታይ የሚሉትን ያብራራል፡፡

3.1.2 የጥናት ሪፖርትን በተመለከተ

የጥናት ሪፖርት ሦስት ክፍሎች እንዳሉት በምዕራፍ አንድ ስር የተገለፀ ሲሆን በዚህ ክፍል ስር የተዳሰሱት ጥናቶች

የጥናት ሪፖርት ምን ይመስላል የሚለው ተዳሷል፡፡ የጥናቶቹ ሪፖርት በአማካይ ከ 3730 ገፅ እስከ 11331 ገፅ ርዝማኔ

አላቸው፡፡

ቀዳሚ መጀመሪያ (Preliminary Pages) የጥናቱ ሪፖርት ክፍል ውስጥ አብዛኞቹ ጥናቶች የጥናቱን ርዕስ እና ጥናቱ

የተጠናቀቀበት ቀን የሚሉትን የያዘ ሲሆን ሁለቱም ሪፖርቱ መጀመሪያ ገፅ ላይ ይገኛል፤ የጥናት ርዕስ ጥናት

29
ዝኒ ከመማሁ 25፣ 26 እና 28
30
የሴት ሌጅ ግርዛት እና ያለእድሜ ጋብቻ የተመለከቱ ህጎችና የአሰራር ክፌተቶች ሊይ የተደረገ የዲሰሳ ጥናት፣ 2011 ዓ.ም
31
በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን የሚመለከቱ የወንጀል ድንጋጌዎች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመለየት የተደረገ ጥናት፣ የሴቶች፣ ሕፃናት እና
ባለብዙ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት እና የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት በጋራ፣ ሰኔ 2013 ዓ.ም
34
የሚደረግበትን ቦታ፣ የሚዳሰሰውን ጉዳይና ምን እንደሚደረግ በሚገልፅ መልኩ የተቀመጠ ቢሆንም አላስፈላጊ ቃላቶች

(ለምሳሌ፡- ጥናት፣ የዳሰሳ ጥናት) ይጨምራሉ32፡፡ሌሎቹ የቀዳሚ መጀመሪያ ክፍል የሆኑት ማረጋገጫ

(Acknowledgement)፣ መቅድም (Preface) ወይም አፅሮተ ሪፖርትና ምፃረ-ቃል (Abbreviations)33 ጥናቶቹ

አላካተቱም፡፡ አንዳንድ ጥናቶች ደግሞ ማውጫ (Table of Contents) እና የሰንጠረዥ ዝርዝሮች (አባሪ) የተባሉትን

አካተዋል፡፡

ሁለተኛው የጥናት ሪፖርት ክፍል ዋና ክፍል የሚባለው ሲሆን ይህ ክፍል የሚያካታቸው የመረጃ ትንታኔ ወይም የጥናቱ

ግኝት፣ ማጠቃለያና ምክረ ሀሳብ ናቸው፡፡ ሁሉም ጥናቶች የመረጃ ትንታኔና የማጠቀለያ ክፍል ቢኖራቸውም

የተወሰኑት ግን ምክረ ሀሳብ የሌላቸው አሉ34፡፡ ማጠቃለያና ምክረ ሀሳብ አቀራረፃቸውን ሲታይ ወጥ የሆነ ሳይሆን

አንዳንዶቹ ጥናቶች በስድ ንባብ መልኩ ሲደራጁ35 ቀሪዎቹ ደግሞ በመዘርዝር36 መልኩ የተቀረፁ ናቸው፡፡

ሦስተኛው የጥናት ክፍል የማጣቀሻ ዝርዝር ሲሆን ይህ ዝርዝር በአብዛኛው ጥናት ከሪፖርቱ የመጨረሻ ገፅ ላይ አባሪ

ካለ ከአባሪዎቹ በፊት ይገኛል፤ አንዳንድ ጥናቶች ደግሞ የማጣቀሻ ዝርዝር የላቸውም37፡፡ ጥናቶች የማጣቀሻ ዝርዝር

ሲያስቀምጡ በአይነት በአይነታቸው38 የሚከፋፍሉት ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ሁሉንም ዝርዝር ሳይመድቡ

ያስቀምጡታል39፡፡ በአብዛኛው ጥናቶች እንደታየው ህጎች በማጣቀሻነት ሲጠቀሱ መጀመሪያ የህጉ ስያሜ መጨረሻ

ላይ ደግሞ የህጉ መለያ ቁጥር የሚያስቀምጡ ሲሆን ሌሎች ነገሮች ማጣቀሻ ሲያስቀምጡ መጀመሪያ

ስም→ርዕስ→ዓመተ ምህረት አድርገው ያስቀምጣሉ፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ የተለያየ ማጣቀሻ ዝርዝር አቀማመጥ

እንደሚከተሉ ታይቷል፡፡

32
ዝኒ ከማሁ 29
33
በወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 ላይ የሚስተዋልና መሰረታዊ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው የህግ ጉዳዮችን ለመለየት
34
Diagnostic Study of the Ethiopian Criminal Justice System, Criminal Justice System Working Group, March, 2021
35
የሴት ሌጅ ግርዛት እና ያለእድሜ ጋብቻ የተመለከቱ ህጎችና የአሰራር ክፌተቶች ሊይ የተደረገ የዲሰሳ ጥናት፣ 2011 ዓ.ም
36
በወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 ላይ የሚስተዋልና መሰረታዊ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው የህግ ጉዳዮችን ለመለየት
37
በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን የሚመለከቱ የወንጀል ድንጋጌዎች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመለየት የተደረገ ጥናት፣ የሴቶች፣ ሕፃናት እና
ባለብዙ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት እና የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት በጋራ፣ ሰኔ 2013 ዓ.ም
38
የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቶች የህግ ማዕቀፍ፣ አደረጃጀት እና አሰራር በኢትዮጵያ፡- ትኩረቱን በፌዴራል ደረጃ ባሉ የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቶች ላይ ያደረገ

የዳሰሳ ጥናት፣ የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጀነራል፣ ህዳር 2015 ዓ.ም

39
የሴት ሌጅ ግርዛት እና ያለእድሜ ጋብቻ የተመለከቱ ህጎችና የአሰራር ክፍተቶች ሊይ የተደረገ የዲሰሳ ጥናት፣ 2011 ዓ.ም
35
3.2 የህግ አፈፃፀምን እና የስራ ክፍሎችን የስራ አፈፃፀም ለመዳሰስ የተደረጉ ጥናቶች

ህጎች ከወጡ በኃላ በሚመለከተው አካል እንዴት እየተተገበሩ ነው እንዲሁም መ/ቤቶች ስራቸውን በህግ መሰረት

እያካሄዱ መሆን አለመሆናቸውን ለማጥናት እና በተቋሙ የሚሰጡ ውሳኔዎች በህግ መሰረት መሆን አለመሆኑን

ማረጋገጥ አላማው አድረጎ የሚነሳ ጥናት ሲሆን ይህ ጥናት በዋናነት የሚሰራው የተቋሙ የስራ ክፍል የፌድራል ህጎች

ተፈጻሚነት መከታተያ ዳይሬክቶሬት እና በህግ ጥናት፣ ማጠቃለልና ማርቀቅ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ነው፡፡ በዚህ የስራ

ክፍል ከተሰሩ ጥናቶች ውስጥ የፌዴራል የአስተዳዳር ስነ ስርዓት አዋጅ 1183/2011 በትምህርት ሚስቴር፣ በንግድና

ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ በጉምሩክ ኮሚሽን፣ በጤና ሚኒስቴር፣ በገቢዎች ሚነስቴር፣ በከተማና መሰረተ ልማት

ሚኒስቴር እና በገንዘብ ሚኒስቴር ያለውን አተገባበር ወይም አፈፃፀም በተመለከተ ሰባት ጥናቶች እንዲሁም የጦር

መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 ሀገር አቀፍ አተገባበር እንዲሁም በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ

የኢኮኖሚ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት የክስ መዛግብት ላይ የተደረገ የሕግ ኦዲት ጥናት በናሙናነት ተወስደው

እንደሚከተለው ተዳሰዋል፡፡

3.2.1 የጥናት ዕቅድ በተመለከተ

በእነዚህ ጥናቶች በአብዛኞቹ የጥናት ዕቅድ (research proposal) ክፍል የተካተተ ሲሆን የጥናት እቅድ የሌላቸውም

ጥናቶች አሉ40፡፡ የጥናት እቅዱ በጥናታቸው ውስጥ ያካተቱ ጥናቶችን የእቅዱን ይዘት በተወሰነ መልኩ ቢለያይም

ተመሳሳይ ሲሆን ይዘቱ እንደሚከተለው ተዳሷል፡፡

የጥናት እቅድ የሚገኝበት ምዕራፍ አንድ ሲሆን የዚህ ምዕራፍ ምንም አይነት ስያሜ ሳይሰጡት 1 ወይም 1.1 ጠቅላላ

መግቢያ ወይም መግቢያ41 በሚል ይጀምራሉ፡፡ ጠቅላላ መግቢያ የሚል ስያሜ የሚያስገቡ ጥናቶች ጠቅላላ መግቢያ

ከሚለው ቀጥሎ መግቢያ የሚል ክፍል42 የሚያስገቡ ሲሆን መግቢያ የሚሉ ጥናቶች ግን መግቢያ ከሚለው ሌላ ክፍል

40
በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤህግ የኢኮኖሚ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት የክስ መዛግብት ላይ የተደረገ የሕግ ኦዲት ጥናት
41
የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አፈጻጸምን ለመገምገም የተደረገ የዲሰሳ ጥናት፣ በፍትህ ሚኒስቴር የሽብር
ወንጀል ሕግ አፈጻጸም ዳሰሳ የጥናት ቡድን፣ ሀምሌ 2014 ዓ.ም
42
የፌደራል ጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳድር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አተገባበርን የሚገመግም ጥናት፣ ሀምሌ/2014
36
የላቸውም43 ቀጥታ ወደ ጉዳዩ ይገባሉ፡፡ በዚህ ክፍል ከተዳሰሱትና የጥናት እቅድ ያላቸው ሁሉም ጥናቶች በሚያስብል

ደረጃ መግቢያ፣ ዓላማ፣ የጥናቱ ዘዴ እና የጥናቱ ወሰን የሚሉትን ያካተቱ ሲሆን ይዘታቸውን44 በተመለከተ፡-

 መግቢያ፡- ጥናቱ የሚዳስሰው ጉዳይ፣ ጥናቱ ያካሄደው የስራ ክፍል እና የዚህ የስራ ክፍል ስልጣን የሚመለከቱ

ነጥቡችን ይዳስሳል፡፡

 የጥናቱ አላማ፡- ጠቅላላ እና ዝርዝር ዓላማ በሚል የተከፈለ ሲሆን ጠቅላላ ዓላማው አንድ ነው፡፡

 የጥናቱ ወሰን፡- በጥናቱ ውስጥ የተዳሰሱ የህጎችን እነማን እንደሆኑ ቢናገርም ጥናቱ በምን ጉዳይ ላይ እንደሆነ

እና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን አላከተተም፡፡

 የጥናቱ ዘዴ፡- ይህ ነጥብ በሁሉም ጥናቶች ‹የክትትል ስልት› የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የተካተተ ሲሆን

ተመሳሳይ የጥናት አይነት ስለሆኑ የሚጠቀሙት የጥናት ተመሳሳይነት አለው፡፡ በዚህ ርዕስ ውስጥ አብዛኛው

ጥናት ላይ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ፣ የመረጃ ትንተና ዘዴ እና የናሙና አወሳሰድ ዘዴ በሚል ተከፋፍለው ቢፃፉም

መረጃን ለመሰብሰብና ለመተንተን ምን አይነት ዘዴን እንደሚጠቀሙ ቢገልፁም ምን አይነት መረጃዎችን

እንደሚሰበሰቡና ለምን እንደዛ አይነት ዘዴ እንደተመረጠ ግን አያብራሩም፡፡ በጥናቶቹ በአብዛኛው ቃለ

መጠይቅ፣ የድህረ-ገጽ አድራሻ በመመልከት፣ ምልከታና ሰነዶችን በማየት መረጃዎች የተሰበሰቡ ሲሆን ናሙና

ለመውሰድ አላማ መር እንዲሁም መረጃዎችን ለመተንተን በፈርጃዊ (thematic analayisis) አተናተን ዘዴ

ገላጭ የትንተና ዘዴን ይጠቀማሉ፡፡

አንዳንድ ጥናቶች ደግሞ ምን አይነት መረጃዎች በምን አይነት መረጃ አሰባሰብ ዘዴ እንደሚሰበሰቡና ለምን

የተጠቀሰውን የናሙና አወሳሰድ ዘዴዎችን እንደተጠቀመ ምክንያታቸውን ጭምር አብራርተው የሚስቀምጡ ቢኖሩም

እንደዚህ አይነት ጥናቶች ደግሞ የመረጃ አተናተን ዘዴ ምን ይመስላል የሚለውን አያስቀምጡም፡፡ በተጨማሪም

አንዳንድ ጥናት ላይ እንደተሰተዋለው የጥናት ዘዴ የሚል ርዕስ ቢኖረውም የመረጃ መረጃ ስለሚሰበሰብበትና

ስለሚተነተንበት እንዲሁም የዘዴዎችን ማብራሪያ በተመለከተ ምንም የሚሉት ነገር የለም፡፡

በአንዳንድ ጥናቶች የጥናቱ ጥያቄዎችን፣ የጥናት ሪፖርቱ አወቃቀር፣ የጥናቱ ዳራ፣ የጥናቱ አስፈላጊነት፣ የጥናቱ

ውስንነት እና የጊዜ ሰሌዳ የሚባሉ ጉዳዩች ተካተው የሚገኙ ቢሆንም አብዛኛው ግን ከእነዚህ ውስጥ አንድ ወይም

43
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ቁ.1183/2012 አፈፃፀም፣ የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር
1183/2012 ን አተገባበር በተመለከተ በጤና ሚኒስቴር የተደረገ የአፈጻጸም ክትትል፣ በትምህርት ሚኒስቴር የፌደረል የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ
ቁ.1183/2012 አፈፃፀም እና ወ.ዘ.ተ
44
ዝኒ ከማሁ
37
ሁለቱን ብቻ የሚያካትት ነው፡፡ የጥናት ውስንነት ተብለው የተጠቀሱት ችግሮች ለሁሉም ጥናት ተመሳሳይ ሲሆን

የሚመለከታቸው አካላት በጥናቱ አለመሳተፋቸው፣ የጊዜና የመረጃ እጥረት ሲሆኑ እንዴት ጥናቱ ሊደርስበት

ከሚገባው ደረጃ እንዳይደርስ እንደአደረጉት ግን አይገልፅም፡፡ ሌላው የጥናቱ አወቃቀርን በተመለከተ ይህን ክፍል

የሚያስገቡ አንዳንድ ጥናቶች ጥናቱ በስንት ምዕራፍ እንደተዋቀረና እያንዳንዱ ምዕራፍ ስር ስለተዳሰሱ ጉዳዩች

ያትታል፡፡ ከተሰሩ አስራ አምስት ጥናቶች ውስጥ የጥናት ዳራ ያካተቱ ሁለት ብቻ45 ሲሆኑ ይዘታቸውም ጥናቱን

የሚያካሂደው የስራ ክፍል ያለውን ስልጣንና ጥናት የሚካሂድበት ጉዳይ የኃላ ታሪክ የሚዳስሱ ናቸው፡፡

3.2.2 የጥናት ሪፖርት

የጥናት ሁለተኛ ክፍል የጥናት ሪፖርት እንደሆነ እና ይህ ክፍል ሶስት ክፍሎች እንደሚኖሩት በቀደሙት ክፍሎች

የተቀመጠ ሲሆን እነዚህ ጥናቶች የጥናት ሪፖርት ምን ይመስላል የሚለው ደግሞ እንደሚከተለው ተዳሷል፡፡ የጥናቱ

ሪፖርት በአብዛኛው አራት ምዕራፎች የሚይዝ ሲሆን ምዕራፍ አንድ የጥናት ዕቅድ እንዲሁም ምዕራፍ አራት

ማጠቃለያና ምክረ ሀሳብ ነው፤ የጥናት ሪፖርት ገጽ በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የተደረጉትን ጨምሮ በአማካይ ከ 3846 እስከ

7447 ገፅ ይደርሳል፡፡

 ቀዳሚ መጀመሪያ (Preliminary Pages)

ይህ የጥናት ክፍል የጥናቱን ርዕስ፣ ጥናቱ የተጠናቀቀበት ቀን፣ ማረጋገጫ (Acknowledgement)፣ መቅድም(Preface)

ወይም አፅሮተ ሪፖርት፣ ማውጫ (Table of Contents)፣ ምፃረ-ቃል(Abbreviations) እና የሰንጠረዥ ዝርዝሮች

(List of Tables) እንደሚይዝ የሚጠበቅ ሲሆን በጥናቱ ውስጥ እነዚህ ጥናቶች ሁሉም የጥናት ርዕስ፣ የሰንጠረዥ

ዝርዝሮች (List of Tables) እና የተጠናቀቀበት ቀን አላቸው፡፡

የጥናት ርዕስ ‹‹ክትትል ሪፖርት›› የሚል ቃልን በማስገባት ጥናቱ የሚደረግበትን ጉዳይ እና ምን እንደሚደረግ በሚገልፅ

መልኩ የተቀመጡ ሲሆን የሰንጠረዥ ዝርዝሮችን (List of Tables) አባሪ የሚል ስያሜ ተሰቷቸው አባሪዎቹ ስለምን

እንደሆነ አብረው በርዕስ መልክ ያስቀምጣሉ፡፡ ሁሉም ባይሆንም ማረጋገጫ (Acknowledgement) ‹‹ምስጋና›› በሚል

ርዕስ ስር ለጥናቱ አስተዋፅዖ ያደረጉ ሰዎችን ማረጋገጫ የሚሰጡ ሲሆን ምፃረ-ቃል ግን በተዳሰሱት ጥናቶች ውስጥ
45
የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አፈጻጸም ክትትል ሪፖርት በጉምሩክ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ሕጎች ተፈጻሚነትን መከታተያ
ዳይሬክቶሬት፣ ጥር 2014 ዓ/ም
46
ዝኒ ከማሁ
47
የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ን አተገባበር በተመለከተ በገንዘብ ሚኒስቴር የተደረገ የአፈጻጸም ክትትል ሪፖርት፣ የፌዴራል
ሕጎች ተፈጻሚነትን መከታተያ ዳይሬክቶሬት፣ ጥር /2014 ዓ.ም
38
አልተገኘም፡፡ በተጨማሪም አፅሮተ ሪፖርትን በተመለከተ የጥናት ሪፖርት ውስጥ አፅሮተ ሪፖርት ያካተቱት ከአስራ

አምስት ጥናት ሦስቱ ብቻ48 ሲሆኑ ሌሎቹ አፅሮተ ሪፖርት አላካተቱም፡፡ አፅሮተ ሪፖርት ያካተቱት የአፅሮተ ሪፖርት

ይዘት በዋናነት ሁለት አይነት ሲሆን አንዱ የጥናት ዓላማ፣ የጥናቱ ዘዴ፣ የጥናቱ ውጤቶች እና ማጠቃለያ የያዘ ሲሆን

ሁለተኛ ደግሞ የጥቱ ዳራ ብሎ የሚጀምር ሲሆን በተከታይ ባሉት አንቀፆች (paragraph) ደግሞ የጥናቱ ዓላማ፣

የጥናቱ ዘዴ፣ የጥናቱን ማጠቃለያ እና የተሰጡ ምክረ ሀሳብ ይይዛል፡፡ የእነዚህ ጥናቶች አፅሮተ ሪፖርት ከአንድ ገፅ እስከ

ሁለት ገፅ የሚደርስ ርዝመት አለው፡፡

 ዋና ክፍል (the Main Text)

ሁሉም ጥናቶች የጥናት ክፍል በምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዳረጀ እንዲሁም በውስጡ መግቢያ፣ የጥናቱ ግኝቶች፣

ማጠቃለያና ምክረ ሀሳቦችን አካተዋል፡፡ የጥናቱ ማጠቃለያ የጥናቱ ግኝቶችን የሚያስቀምጥ እንዲሁም ምክረ ሀሳብ

በማጠቃለያ ላይ እንደ ችግር ለተነሱት የመፍትሄ ሀሳብ የሚሰጡ ናቸው፡፡

 የማጠቀሻ ፅሁፎች ዝርዝር

ከአስራ አንድ ጥናት ውስጥ አንድ ጥናት ብቻ ማጣቀሻ ማለትም የጥናት/ምርምር ስራዎችን ለማከናወን በግብአትነት

ያገለገሉ ጽሁፎች መፅሐፍት፣ መፅሄቶች፣ ጋዜጦች፣ አርቲክሎች፣ ሰነዶች፣ የህግ ድንጋጌዎች፣ የግለሰቦች ወይም

ቡድኖች ሀሳብና አስተያየቶችን የያዘ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ግን ዋቢ ህጎች በሚል ስያሜ የህጎችን ዝርዝር ብቻ

የሚያስቀምጡ ወይም ጭራሽ ማጣቀሻ ዝርዝር የሚባል ነገር ያላካተቱ49 ናቸው፡፡ ህጎችን ማጣቀሻ አድርገው

የሚያስቀምጡት ጥናቶች ውስጥ አንዳንዶቹ የህጉን ቁጥርና ምን አይነት ህግ እንደሆነ (ደንብ/መመሪያ/አዋጅ)

የሚሉትን ነጥቦች ብቻ የያዘ ሲሆን ሌሎቹ የህጉን ሙሉ ስምና መለያ ቁጥር ጨምሮ ይዘው ይገኛሉ፡፡

3.3 ሌሎች በተቋሙ የተሰሩ ጥናቶች

በተቋሙ ውስጥ ከህግ ጥናት ማሻሻያ እና ከህጎች አፈፃፀም ላይ ከሚሰሩ ጥናቶች በተጨማሪ ሌለች ጉዳዩች ላይም

ጥናቶችን ያካሂዳል፡፡ ከሚያካሂዳቸው ጥናቶች ውስጥ በአንድ ጉዳይ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመለየት የሚደረግ ጥናት፣

ችግሩ ተለይቶ ለታወቀ ጉዳይ መፍትሄ የሚፈልግ ጥናት እና ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ወይም የስራ ክፍሎችን ድክመትና
48
በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የፌዴራል አስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ቁ.1183/2012 አፈፃፀም፤ የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ
አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አፈጻጸምን ለመገምገም የተደረገ የዲሰሳ ጥናት እና በትምህርት ሚኒስቴር የፌደረል የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ቁ.1183/2012
አፈፃፀም ላይ የተደረገ ጥናት
49
የፌዴራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አፈፃፀም ጥናት ሪፖርት፣ የፌዴራል ሕጎች ተፈጻሚነትን፣ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም
39
ጠንካራ ጎን ለመለየት የሚደረግ ጥናት የሚሉት ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ጥናቶች በዋናነት መሰረት የሚያደርጉት የህግ

ድንጋጌን ሳይሆን በተግባር ያለውን አሰራር ወይም ነባራዊ ሁኔታ ብቻ በመሆኑ ሌሎችም የሚል ስያሜ እንዲሰጡ

ምክንያት የሆነ ሲሆን የህግ ጉዳይ የሚመጣው ምክረ ሀሳብ ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ፅሁፍ የተዳሰሱበት ምክንያት

ጥናቱ በተቋሙ እንደ አጠቃላይ በሚደረጉ ጥናቶች አሰራር ምን ይመስላሉ የሚሉትን ስለሚዳስስ ነው፡፡

በዚህ ጥናት ውስጥ ከተዳሰሱት ለአብነት ያክል የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቢያነ ህግ የስነ ምግባር ሁኔታ ከሙስና አንፃር፣

የስልጠናዎች ፋይዳ ጥናት፣ በጥብቅና አገልግሎት ላይ የሚታዩ ችግሮች እና መፍትሔ ሀሳቦች፣ ህገወጥ የሰዎች

ዝውውርና ዴንበር ማሻገር ወንጀሌ በኢትዮጵያ፡ የወንጀሉ ልዩ ባህርያት፣ የአፈጻጸም ሁኔታና የሚያደርሰው ጉዳት፡ ልዩ

ትኩረት በአማራ፣ በደ/ብ/ብ/ህ እና በአፋር ክልል፣ በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ማዕከል አገልግሎት ላይ የተደረገ ጥናት እና

ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ በእርግጥ እነዚህ ጥናቶች የህግ ጥናት ሳይሆን በዋናነት ማህበራዊ ሳይንስ ጥናት ውስጥ

የሚመደቡ ናቸው፤ ነገር ግን ለህግ ማሻሻል ወይም ህግ ለማውጣት ስለሚጠቅሙ እንሚከተለው ተዳሰዋል፡፡

3.1.1 የጥናት እቅድ በተመለከተ

ከላይ ካየናቸው የጥናት አይነቶች ጋር በተመሳሳይ በዚህ የጥናት አይነት የሚገኙ ጥናቶችም ወጥ የሆነ የጥናት እቅድ

አቀራረፅና ይዘት የላቸውም፡፡ በዚህ ክፍል ከተዳሰሱት ጥናቶች ውስጥ የጥናት እቅድ የሌላቸውና የጥናት እቅድ

ያላቸው ጥናቶች የምናገኝ ሲሆን የጥናት እቅድ ያላቸው አቀራረፃቸውና ይዘታቸው ወይም የሰጡት ስያሜ አንዱ

ከአንዱ የተለያየ ነው፡፡ አንዳንድ ጥናቶች የጥናት እቅድ ውስጥ የጥናት ዳራ፣ የጥናቱ መግለጫ፣ የጥናቱ አላማ፣ የጥናቱ

ጥያቄዎችና አስፈላጊነት፣ የጥናቱ ወሰን፣ የስነ ምግባር ሁኔታ፣ ውስንነትና አደረጃጀት የሚሉትን ነጥቦች በምዕራፍ

አንድ ስር የሚያካትቱ50 እንዲሁም የጥናቱ ዘዴን ደግሞ ምዕራፍ ሦስት ላይ የጥናት ዘዴ በሚል ስያሜ51 ሰጥተው

የሚያስቀምጡ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ሁሉንም ማለትም የጥናት ዘዴን ጨምሮ ምዕራፍ አንድ ስር የሚጨርሱ አሉ፡፡

ነገር ግን ከተወሰኑ ጥናቶች ውጭ52 ከላይ የተዘረዘሩትን በአንድ አሟልቶ የሚይዝ ጥናት የለም፡፡

50
በኢትዮጵያ የሞት ቅጣት ፍርድ ሪፖርት፣ ክትትልና መረጃ አያያዝ ላይ ያሉ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው፣ የይቅርታና ምህረት ቦርድ ጽ/ቤት፣መስከረም
2012 ዓ.ም

51
በሃገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ማዕከል አገሌግሎት ላይ የተደረገ ጥናት፣ የሴቶችና ህጻናት ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ዲይሬክቶሬት፣ ታህሳስ 2013 ዓ.ም፤ የይቅርታ
አሰጣጥና አፈፃፀም ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው (የዳሰሳ ጥናት)፣ መጋቢት 2013 ዓ.ም
52
ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና ድንበር ማሻገር ወንጀል በኢትዮጵያ፡ የወንጀለ ልዩ ባህርያት፣ የአፈጻጸም ሁኔታና የሚያደርሰው ጉዲት፡ ልዩ ትኩረት በአማራ፣
በደ/ብ/ብ/ህ እና በአፋር ክልል፣ ነሀሴ 2008 ዓ.ም
40
 የጥናቱ ዳራ፡- ይህ ክፍል የጥናቱ አጠቃላይ ዳራ፣ መግቢያ እና የጥናቱ ፅንሰ ሀሳብ የሚል ስያሜ ተሰቶት

የሚገኝ ሲሆን በይዘት ደረጃ ሁሉም የጉዳዩን የኃላ ታሪክ፣ ጥናቱ እንዲሰራ ያደረጉት ምክንያቶችና ምን

እንደተጠና የሚያስገነዙ ናቸው፡፡ በአማካኝ ከአንድ ገፅ እስከ ሦስት ገፅ የሚደርስ ርዝማኔ አለው፡፡

 የችግሩ መግለጫ፡- አብዛኛው ጥናት ይህ የጥናት ክፍል የሌለው ሲሆን ማጠቃለያ ላይ ወይም የጥናት ግኝቶች

በሚመስል መልኩ የተፃፉ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የጉዳዩን የኃላ ታሪክም እንዲሁም ምን አይነት ጥናት

እንደሚደረግ ያብራራሉ፡፡

 የጥናቱ ወሰን፡- በዚህ ክፍል ውስጥ ጥናቱ የሚሸፈፍናቸው ጉዳዩችና አከባቢዎችን በተመለከተ ያብራራሉ፡፡

 የጥናቱ አላማ፡- አንዳንድ ጥናቶች ዝርዝር ወይም ንዑስ አላማዎችና ጠቅላላ አላማ በማለት የሚከፍሉት

ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ሳይከፋፍሉ ያስቀምጡታል፡፡

 የጥናቱ አደረጃጀት፡- የጥናቱ ሪፖርት በምዕራፍ እና በንዑስ ርዕስ እንደተከፋፈለ የሚናገር ክፍል ነው፡፡

ከእነዚህ በተጨማሪም አንዳንድ ጥናቶች በጥናት እቅድ ውስጥ የተዛማጅ ፅሁፎች ዳሰሳን የሚያካትቱ ሲሆን የቀደሙ

ጥናቶች በተግባር ያለን ክፍተት እና ጥንካሬ የሚዳስስ ነው፡፡

3.1.2 የጥናት ሪፖርት

ጠቅላላ የጥናቱ ሪፖርት በአማካኝ ከሰላሳ ሰባት53 እስከ ሦስት መቶ ሀምሳ ገፅ54 የሚደርስ ርዝማኔ አላቸው፡፡ የጥናት

ሪፖርት ከላይ እንዳየነው ሦስት ዋና ዋና ክፍሎች የሚይዝ ሲሆን ቀዳሚ መጀመሪያ የተባለው ክፍል ውስጥ ሁሉም

ጥናቶች ርዕስና ጥናቱ የተጠናቀቀበት ቀን በመጀመሪያው ገፅ ላይ ይገኛል፤ የጥናት ርዕስ የጥናቱን አይነት (ለምሳሌ፡-

የዳሰሳ ጥናት)፣ ጉዳዩን እና ጥናቱ ትኩረት የሚያደርግበትን ቦታ በሚጠቁም መልኩ የተቀረፁ ናቸው፡፡ አብዛኛው

ማረጋገጫ የጥናቱን በጀት ለሸፈነ አካል፣ ለጥናቱ መረጃ የተሰበሰበባቸው ቢሮዎችና መረጃ በመስጠት ለተባበሩት

ሰዎች ምስጋና የሚያቀርብ ነው55፡፡

አፅሮተ ፅሁፍ ያላቸው ጥናቶች56 ከማጠቃለያ ባልተናነሰ መልኩ ሶስት ገፅ ርዝማኔ ያለው ሲሆን የጥናቱ ግኝቶች፣

ማጠቃለያና ምክረ ሀሳብ በውስጡ ያካተተ ነው፡፡ በተጨማሪም ሌሎች የሰንጠረዥ ዝርዝሮች አልፎ አልፎ የሚገኙ

53
በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የዐቃብያነ ሕግ ደረጃ ዕድገት እና ዕርከን አተገባበር፣ የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽህፈት ቤት፣ ግንቦት 2013 ዓ.ም
54
የፌደራል ጠቅላይ ዓ/ህግ የቁልፍ እና አበይት ተግባራት አፈፃፀምን አስመልክቶ የተዘጋጀ የዳሰሳ ጥናት፣ ግንቦት 21/2010 ዓ.ም
55
የይቅርታ አሰጣጥና አፈፃፀም ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው (የዳሰሳ ጥናት)፣ መጋቢት 2013 ዓ.ም
56
ዝኒ ከማሁ
41
ሲሆን ይዘታቸውም መረጃ ለመሰብሰብ የተጠየቁ ጥያቄዎችና ሌሎች መስፈርቶች የተቀመጡበት ክፍል ነው፡፡ ይህ

የሰንጠረዥ ከማውጫ ቀጥሎ ወይም ከፅሁፉ መጨረሻ ላይ ይገኛል፡፡

ሁለተኛው የሪፖርት ክፍል ዋና ክፍል የሚባለው ሲሆን ይህም ከላይ ከተቀመጡት የጥናት አይነቶች በተለየ መልኩ

የጥናቱ ዋና ግኝት፣ ማጠቃለያና ምክረ ሀሳብ ብቻ ሳይሆን ምዕራፍ ሦስት ላይ የጥናቱን ዘዴ በዝርዝር የሚገኝበት ክፍል

ነው፡፡ የጥናቱ ዘዴ የጥናት ንድፍ፣ የጥናቱ አቀራረብ፣ በዚህ ክፍል ከተዳሰሱት ጥናቶች ውስጥ ምክረ ሀሳብና ማጠቃለያ

የሌላቸው እንዳለ ሆኖ አቀራረፃቸውን በተመለከተ የተወሰኑት ማጠቃለያና ምክረ ሀሳብ የሚሉትን ከጥናቱ መጨረሻ

ላይ ሲያስቀምጡ ቀሪዎቹ ደግሞ በእያንዳንዱ ርዕስ ውስጥ ያስቀምጣሉ፡፡ በተጨማሪም ማጣቀሻ ዝርዝር ሶስተኛው

የጥናት ሪፖርት ክፍል ሲሆን በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ጥናቶች ማጣቀሻ ዝርዝር ባይኖራቸውም ያለቸው ግን ህጎችን

በማስቀደም ጥናቱ የተጠቀማቸውን ደብዳቤዎች፣ ሪፖርቶች፣ መፅሔቶችና ሌሎች የመረጃ ምንጮችን በጥናቱ

መጨረሻ ላይ ያስቀምጣሉ፡፡

42
ምዕራፍ አራት
ማጠቃለያ እና ምክረ ሀሳብ
4.1 ማጠቃለያ

ጥናት የራሱ የሆነ ልዩ ባህርያቶች እንዲሁም የሚመራት መርሆዎች ቢኖሩትም ወጥ ትርጉም ተሰጥቶት አይገኝም

ይልቁንም የጥናት ትርጉም ጥናቱ እንደሚካሄድበት ጉዳይ የተለያየ ነው፡፡ ጥናት ከሚካሄድበት አላማ፣ ከሚከተለው ዘዴ

እና ከሚጠቀመው የመረጃ አይነት አንፃር የተለያዩ የጥናት አይነቶች ይገኛሉ፡፡ ምንም እንኳን የተለያዩ ጥናቶች

ቢኖሩም አንድ ጥናት ቢያንስ የጥናት እቅድና የጥናት ሪፖርት የሚባሉ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች በውስጣቸው የተለያዩ

ንዑስ ክፍሎችን የሚይዙ ሁለት ክፍሎች ሊኖሩት ይገባል፡፡ በተጨማሪም የጥናት እቅድ፣ የመረጃ ትንተና ማብራሪያ

እና የጥናት ውጤትን ማቅረብ የሚባሉ ሦስት የጥናት ስራ ሂደት ሲኖረው ይህ ሂደት የሚመራበት አንድ ወጥ የሆነ

የተፃፈ ህግ/ጋይድላይን የለም፡፡

ጥናት በግለሰብ ወይም በተቋም ደረጃ ሊሰራ የሚችል ሲሆን የሚካሄዱ ጥናቶች ችግር ፈችነታቸውን ለማረጋገጥ፣

የጥናት ወጥነትን ለመጠበቅ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈን እንዲሁም ወጥ የሆነ የመመዘኛ መስፈርት ለመጠቀም አንድ

ጥናት ሊመራበት የሚችለው የአሰራር መመሪያ/ጋይድላይን ሊኖረው እንደሚገባ ይታመናል፡፡ ምንም እንኳን የአሰራር

ሂደት መመሪያ አስፈላጊነት አጠያያቂ ባይሆንም ወጥ የሆነ የአሰራር መመሪያ/ጋይድላይን ማግኘት ግን አልተቻለም፡፡

ይልቁንም ተቋማት የየራሳቸውን የጥናት ስራ አካሄድ የሚመሩበት ሰነድ አላቸው፡፡ በዚህ ጥናት እንደተዳሰሰው የጥናት

ስራ የሚመራበት ሰነድ በህግ ደረጃ “መመሪያ” በማለት የፌዴራል የፍትህና የሕግ ስርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት

(“የፍትህና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት የጥናት መመሪያ”)፤ የአማራ ክልል የፍትሕ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና

የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት (“የጥናት ምርምር አፈፃፀም (research guideline) እና የሕግ መፅሔት የሕትመት

ፖሊሲ (Editorial Policy) መመሪያ”) እና የኦሮሚያ የህግ ባለሙያዎች የስልጠና እና ህግ ምርምር አንስቲትዩት (የህግ
ባለሙያዎች የስልጠና እና ህግ ምርምር አንስቲትዩት የጥናት መመሪያ ቁጥር 03/2004) ያዘጋጁ ሲሆን በማንዋል ደረጃ

የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ (የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ ማንዋል) እንዲሁም በጋይድላይን ደረጃ ደግሞ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ

የጥናትና ህትመት ጋይድላይን (research and publication guideline) አዘጋጅቷል፡፡ በመመሪያና በማንዋል ደረጃ
የጥናት ስራ ሂደት አመራርን ያስቀመጡ ተቋማት አንድ ጥናት በውስጡ ሊኖሩት ስለሚገባው ይዘት (በዝርዝር)፤
ጥናቱን የማፅደቅና የመገምገም ስልጣን የማን ነው የሚለውን እንዲሁም የበጀት ጉዳዩችን የሚያካትት ሲሆን

በጋይድላይን ደረጃ የተቀመጠው ግን የጥናት ይዘቶች ምን ምን ሊሆኑ ይገባል ከሚለው ይልቅ የጥናት ስራ እንዴት
43
ይጀመራል፤ የጥናቱን እቅድ ተመልክቶ ማፅደቅ ያለበት ማን ነው፤ የጥናት በጀት ምንጮች እንዴት ይገኛሉ እና ጥናቱን

የሚያካሂድ ሰው ሊቀጣባቸው የሚችሉት የስነ ምግባር ጉድለቶች ላይ ያተኩራል፡፡

ፍትህ ሚኒስቴር በተለያዩ ህጎች ተዘርዝረው የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት ለመፈፀም ያስችለው ዘንድ በዋናነት

የህግ ማሻሻያ፣ የህግ ተፈፃሚነት እና የስራ ክፍሎች የስራ አፈፃፀምን ለመገምገም እንዲሁም ሌሎች ለተቋሙ

አስፈላጊ የሆኑ የህግ ጥናት ያልሆኑ ጥናቶችን የሚያካሂድ ቢሆንም የጥናት ስራ ሂደት የሚመራበት እንዲሁም

ሰራተኛው የሚመዘንበት ምንም አይነት ሰነድ ይህ ጥናት እስከተጠናቀቀበት ቀን ድረስ የለም፡፡

በተቋሙ ውስጥም የተለያዩ ሥራ ክፍሎች በየራሳቸው የተለያዩ ዓይነት ጥናቶችን እንደተቋም ባልተማከለ መልኩ

እየተሰራ መሆኑ በዚህ ጥናት ውስጥ የተመለከትናቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በዚህም የተለያዩ የጥናት ዓይነቶችም ይሁኑ

በአንድ አይነት መደብ ውስጥ የሚመደቡ ጥናቶች የተለያያ ይዘት፣ በጀት፣ ጊዜ እንዲኖራቸው እንዲሁም ጥናቶቹ

ተፈፃሚነታቸው የሚከታተል አካል እንዳይኖር ምክንያት ሆኗል፡፡ ስለሆነም በተቋሙ የሚሰሩ ጥናቶች ውጤታማነት፤

ወጥነት እና ችግር ፈችነት አሉንታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡

ስለዚህ ይህ ጥናት በተለያዩ ህጎች ለተቋሙ የተሰጡ ስልጣንና ሀላፊነት ከግብ ለማድረስ ይረዳው ዘንድ በተቋሙ

የሚሰሩ ጥናቶች አስፈላጊነታቸን፣ ተገቢነታቸውን፣ ወጥነታቸውን እንዲሁም ተፈፃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እና

ሰራተኛውን በአግባቡ መመዘን የሚያስችል አንድ ወጥ የሆነ የጥናት ስራ ሂደት አሰራር የለውም የሚል ድምዳሜ

ደርሷል፡፡
4.2 ምክረ ሀሳብ
በጥናቱ የተረጋገጡ በፍትህ ሚኒስቴር ውስጥ የሚሰሩ ጥናቶች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማስወገድ ወይም
እንዲስተካከሉ ይረዳ ዘንድ የሚከተሉት ምክረ ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡

ሀ. የጥናት ስራ አካሄድ የሚመራበት ዝርዝር የጥናት አሰራር ማንዋል ወይም ጋይድላይን ማዘጋጀት፤

ለ. የጥናት ባለሙያዎች ደረጃውን የጠበቀ ሳይንሳዊ ጥናት ማካሄድ እንዲችሉ የተሻለ የጥናት አሰራር ክህሎት
እንዲኖራቸው ተገቢ የሆነና ተከታታ የሆነ የጥናት አሰራር ሥልጠና እንዲወስዱ ማድረግ እና የጥናት ስራ የሚሰሩ
ሰራተኞች ጥናት እንዲሰሩ ከመመደባቸው በፊት ስለ ጥናት አሰራር ስልጠና መስጠት ፤

ሐ. በተቋሙ የሚሰሩ ጥናቶች በተማከለ መልኩ እንዲሰራ መደረግ አለበት፡፡ ይህም በተቋሙ ውስጥ ያለውን አቅም
(የጥናት አሰራር ክህሎትና ልምድ) በማሰባሰብ በማደራጀት በቀጣይ የሚሰሩ ጥናቶች የተሻሉ እንዲሆኑ ያደርጋል
እንዲሁም የተቋሙ የልህቀት ማዕከል እንዲኖር / ለመገንባት መነሻ ይሆናል እና
44
መ. የተሰሩ የጥናት ውጤቶችን እና ምክረ ሃሳቦችን መከታተያና ማስተግበሪያ በጥናት ስራ ክፍል ውስጥ ንዑስ ክፍል
ሆኖ ማደራጀት ያስፈልጋል የሚሉት ሃሳቦች በዚህ ጥናት ወስጥ እንደ ምክረ ሃሳብ ቀርቧል፡፡

45
የማጣቀሻ ዝርዝር
ሀ. ህጎች እና ማንዋል/ጋይድላይን

 የፌዴራል ጠቅላይ ዓ/ህግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ.943/2009


 የፌደራል የፍትህና የሕግ ምርምር እና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ.1071/2010
 የጥናት ምርምር አፈፃፀም (research guideline) እና የሕግ መፅሔት የሕትመት ፖሊሲ (Editorial Policy)
መመሪያ (መለያ ቁጥር ያልተሰጠው)
 የኦሮሚያ የህግ ባለሙያዎች የስልጠና እና ህግ ምርምር አንስቲትዩት የጥናት መመሪያ ቁጥር 03/2004
 የጎንደር ዪኒቨርስቲ የጥናትና ህትመት ጋይድላይን (research and publication guideline)
 የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የጥናት ማኑዋል 2009

ለ. መፅሀፎችና Journal article

 Khushal Vibhute & Filipos Aynalem, Legal Research Methods teaching material, 2009.
 Mike McConville and Wing Hong Chui, research methods for law (second edition), Edinburgh University
Press.
 Tom R. Tyler, Methodology in Legal Research, Utrecht Law Review, Volume 13 | Issue 3, 2017.
 Chunuram Soren, Legal Research Methodology: An Overview, Jetir, Volume 8, Issue 10, October
2021.

46

You might also like