You are on page 1of 12

የቤት ልማት ሥራዎች የመኖሪያ ቤት ከሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቶች መካከል የሚመደብ ሲሆን የመጠለያ

እጦትም የድህነት አንዱ መገለጫ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

“የመኖሪያ ቤት” ሲባል ከሕንፃው አካላዊ መዋቅር (ከወለል፣ ከጣሪያና ግድግዳ)


ባሻገር ለነዋሪዎች አስተማማኝ የደህንነት ዋስትና የሚሰጥ፣ የነዋሪውን የመሬት የመጠቀምና የቋሚ ንብረት
ባለቤትነት መብት የሚረጋገጥበት እና በቂ የመንቀሳቀሻና የመሥሪያ ቦታ ያለው ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ለሰው
ልጅ መሠረታዊ ፍላጐት መሟላትና ለጤንነት አስፈላጊ የሆኑ የመሠረተ-ልማት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
አገልግሎቶች በቤቱ ውስጥና በቅርብ በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት የሚቻልበት በአካባቢ ሲኖር ነው፡፡ በከተሞች
የመኖሪያ ቤትን አስመልክቶ ያለውን ችግር ለመፍታት የፌዴራልና የክልል መንግሥታት እንዲሁም የከተማ
አስተዳደሮች የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስዱ ቆይተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት የተቀናጀ የቤት ልማት ኘሮግራም ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ከተማ ከ 1996 ዓ.ም ጀምሮና በክልል
ከተሞች ደግሞ ከ 1999 ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚሁም ወደ 380 ሺህ የሚሆኑ ቤቶች ግንባታ
ተከናውኗል፡፡ ሆኖም ይህ ቁጥር አሁን በከተሞች ካለው የተከማቸ የቤት እጥረት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነው፡፡
በተያያዘም በ 2005 ዓ.ም በጸደቀው የከተማ ቤት አቅርቦት የስትራቴጂ ማዕቀፍ የተቀመጡ የቤት አቅርቦት
አማራጮች በሚጠበቀው ልክ ያለመተግበር፣ የተቀመጡት አማራጮች ማነስና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ አለመጎልበት
የሚጠቀሱ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ባለፉት ዓመታት በቤት ልማት ዘርፉ በተለይ በመንግስት በተካሄደው የቤቶች ግንባታ
ኘሮግራም የተገኙትን ውጤቶች በተሻለ መንገድ በማጠናከርና ሌሎች የቤት አቅርቦት አማራጮችን በማስፋት የቤት
ችግርን ትርጉም ባለው መልኩ የሚፈታ በቂና ደረጃውን የጠበቀ የመኖሪያ ቤት ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንዲቀርብ
ለማድረግ፣ ዘርፉ 30 ለአገር ኢኮኖሚ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የዘርፉን ልማት
በአስተማማኝ ሁኔታ ለመምራት የሚስችል የተሻለ የቤት ልማት አቅርቦት ይጠበቃል፡፡

የቤት አቅርቦት ዋና ዋና ችግሮች፡- በመኖሪያ ቤት ዙሪያ ያሉ ችግሮች ዘርፈ-ብዙና በርካታ እንዲሁም የተለያዩ
መሠረታዊ መንስኤዎች ያሉዋቸው ሲሆኑ እነዚህንም ችግሮች በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
አንደኛውና ዋነኛው ችግር የቤት እጥረት ሲሆን ሁለተኛው ያረጁና የተፋፈጉ የከተማ ሰፈሮች መስፋፋት ነው፡፡ በቤት
ፍላጎትና አቅርቦት ያለመጣጣም ምክንያት የቤት እጥረት መኖር፡- በአሁኑ ጊዜ በሃገሪቱ በሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ
ከተሞች እና በአዲስ አበባ ይኖራል ተብሎ የሚገመተው የቤት እጥረት በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
በሚቀጥሉት 10 ዓመታት በየዓመቱ ተጨማሪ 486 ሺ ቤት እንደሚያስፈልግ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህም
የሚያመለክተው በከተሞች ያለው የቤት አቅርቦትና ፍላጎት ያልተጣጣመ መሆኑንና ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት
እጥረት መኖሩን ነው፡፡ ይህ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትና አቅርቦት ያለመመጣጠን አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል ተገቢ
ላልሆነ ወጪና መንገላታት በመዳረግ ለተወሳሰበ ኢኮኖሚያዊ ማኅበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ችግሮች እያጋለጠው ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ምርታማነትን በመቀነስና በዚህም መነሻነት በከተሞቹ ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ
በማሳደር በከተሞቻችን ልማት ላይ የበኩሉን ጫና ፈጥሯል፡፡ ነዋሪዎችም በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና
ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በሚፈለገው ደረጃ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዳያደርጉ ቀላል የማይባል ማነቆ ሲሆን
ይስተዋላል፡፡ በከተሞች ለሚገኘው የቤት እጥረት መገለጫነት ከሚጠቀሱት ምልክቶች አንዱ በተጨናነቀ ሁኔታ
የሚኖሩ ቤተሰቦች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ነው፡፡ ይህም በአንድ ቤት በሚኖሩ የቤተሰብ ብዛት፣ በአንድ ቤት ውስጥ
ባሉ ክፍሎች እና በደባልነት በሚኖሩ አባወራዎች ቁጥር ሊገለጽ ይችላል፡፡ አብዛኛው በተለይ በከተሞች ማዕከላዊ
ክፍል የሚገኘው ነዋሪ ደረጃቸው በጣም ዝቅተኛ በሆኑ ቤቶች በተጨናነቀ ሁኔታ እንደሚኖር ይታወቃል፡፡ ዋነኛ
ምክንያት ባይሆንም የህገወጥ ይዞታዎች መስፋፋት አንዳንድ ጥናቶች የቤት አቅርቦት እጥረት መገለጫ
አድርገው ይወስዱታል፡፡ የሕገ ወጥ ሰፈራና የቤት ግንባታ በአብዛኛው የሚከናወነው በከተሞች የመስፋፊያ
አካባቢዎች ሲሆን ይህም የሚፈጠረው በዋነኛነት በከተሞችና አጎራባች የገጠር አስተዳደር አካላት ጋር ያለው
ቅንጅታዊ አሰራር ያለመኖር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሕገወጥ ሰፈራና ግንባታ በከተማ ፕላን ላይ ለአረንጓዴ ስፍራ
እንዲውል በተጠበቁ ቦታዎች፣ በከተሞች አቅራቢያ በሚገኙ የወንዝ ዳርቻዎች እንዲሁም ኮረብታማ ቦታዎች ላይ
ይከናወናል፡፡ ለሕገ ወጥ ይዞታዎች መስፋፋት አንዱና ዋናው ምክንያት ወደፊት ትርፍ አገኝበታለሁ ብሎ ቦታ መያዝ
ሲሆን በከተሞች ለሁሉም ተደራሽ የሆነ ቤት ማቅረብ ያለመቻል፣ ድህነት እና ውጤታማ የሆነ የመሬት ወረራን
መከላከል የሚያስችል ሥርዓት እና አቅም ያለመኖር ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የዚህ ድርጊት ዋና ተዋናዮች ሰፋፊ ይዞታዎችን
በሕገ ወጥ መንገድ ከአርሶ አደሮች በመግዛትና ያለልማት በማቆየት ዋጋ ጨምረው እየሸነሸኑ ለሦስተኛ ወገን እንደገና
በሕገ ወጥ መንገድ ያልተገባ ትርፍ የሚሰበሰቡ አካላት ናቸው፡፡ በተጨማሪም ለኢንቨስትመንትና ሌሎች ማህበራዊ
አገልግሎቶች ተብለው የተከለሉ ቦታዎችን በሕገ ወጥና አግባብነት በሌለው
መንገድ የሚሰጡና የሚወስዱ አካላት እንዲሁም ለሌላ ኢንቨስትመንት የወሰዱትን መሬት ለሌሎች ቤት ገንቢዎች
31
ከመሬት አጠቃቀም ሕግ ውጭ የሚሸጡ አካላት መኖራቸው ሲሆን ይህም የሚሆነው በከተማ አስተዳደሮች
ባለው የማስፈጸም አቅም ክፍተትና የሥነምግባር ጉድለት እንደሆነ ይታወቃል::
ከገጠር ወደ ከተማ ያለውን ፍልሰት ለመቀነስ ያለዉን ሥርዓት ያልጠበቀ ኋላ-ቀርና ለአኗኗር የማይመች ቤት
ለማሻሻል፣ በፕላን የማይመራ ክትመትን ለማስቀረት እና በየማዕከላቱ የተሻለ የአኗኗር ዘይቤ ለመፍጠር ጥረት
በማድረግ ዉጤት እየታየ ይገኛል፡፡ ሆኖም አሁንም በበርካታ የገጠር አካባቢዎች መኖሪያ ቤቶች ያለ ዲዛይንና
ፕላን እየተገነቡ ከመሆናቸውም በላይ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ውኃ፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የገበያ፣ የመብራት
እና የኃይል አማራጭ እና ሌሎችም አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶች ባለመሟላታቸው በታሰበው ልክ ለውጥ
ማምጣት አልተቻለም፡፡
ያረጁና የተፋፈጉ የከተማ ሰፈሮች መስፋፋት፡- በከተሞቻችን በአብዛኛዎቹ የማዕከላዊ የከተማ ክፍሎች ከፕላን
ውጭ ነዋሪዎች በመከማቸታቸው በእርጅና ምክንያት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች የተዳከሙ በመሆኑ
ለሰው ልጅ መኖሪያነት ምቹ ያልሆኑ የከተማ አካባቢዎች ሆነዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በእነዚህ ሠፈሮች
በመንግስትም ሆነ በግል ይዞታ ሥር የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ሁኔታ ሲታይ ደረጃቸውን ያልጠበቁ፣ ከተገነቡ
ረጅም ጊዜ የሆናቸውና የተገነቡበት ቁሳቁስ ለማደስ የማያስችላቸው አይነት ናቸው፡፡ በእርጅናና ተገቢው ጥገና
ባለማግኘታቸው ምክንያት በአብዛኛዎቹ ከተሞች የሚገኙ ቤቶች በተለይም በከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙት ወደ
መፍረስ ደረጃ የተቃረቡ ናቸው፡፡
በመኖሪያ ቤት ዙሪያ ያሉ የችግሮች መሠረታዊ መንስኤዎች ያሉዋቸው ሲሆኑ እነዚህንም በአራት ዋና ዋና
ክፍሎች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ አንደኛው የቤት ፋይናንስ እጥረት፣ ሁለተኛው የግንባታ ግብአቶች አቅርቦት
እጥረት፣ ሦስተኛው የተቀናጀ የመሰረተ ልማት አቅርቦት አናሳ መሆንና አራተኛው የለማ መሬት ዝግጅትና
አቅርቦት ዝቅተኛ መሆን የሚሉትን ያካትታል፡፡
የቤት ፋይናንስ እጥረት፡- አብዛኛው የከተማ እና የገጠር ማዕከላት ነዋሪ ለቤት ግንባታ የሚውል የገንዘብ አቅም
የሌለው በመሆኑ ምክንያት የቤት ልማት እንቅስቃሴው እየተዳከመ ሄዷል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በቂ የቤት አቅርቦት
የሌለ በመሆኑ የቤት መሸጫ ዋጋም እየናረ ይገኛል፡፡ ይህም የአብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል የቤት ባለቤት
የመሆን ዕድልን ከማጥበቡም በላይ በተዘዋዋሪም ቢሆን በቤት ኪራይ ዋጋ ላይ ተጨማሪ ተፅዕኖ በማሳደር በኑሮ
ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ ይገኛል፡፡
በብዙ አገሮች እንደሚደረገው የመጠለያ አገልግሎት ለሚሰጡ ቤቶች ግንባታ ብቻ ብድር በመስጠት ለማገዝ
የተቋቋመ ባንክ ወይም ፈንድ እና አማራጭ የቤት ልማት የፋይናንስ ምንጭ ባለመኖሩ በመደበኛ ባንኮች
የሚሰጠው አገልግሎት ትኩረትም የበለጠ አዋጭነት ባላቸው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችንና ኢንቨስትመንቶችን
በብድር መደገፍ ላይ በመሆኑ በእነዚህ አካላት አማካኝነት ለቤት ልማት የሚቀርበው የፋይናንስ መጠን እጅግ
ውሱን ነው፡፡ አነስተኛ የብድር ተቋማትም ቢሆኑ ለቤት ግንባታ አገልግሎት መዋል የሚችል በቂ የፋይናንስ አቅም
የላቸውም፡፡
እንደሚታወቀው የአገር አቀፉ የቤት ልማት ኘሮግራም የፋይናንስ ምንጩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክልሎች ቦንድ
በመሸጥ የሚያገኙት ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ለቤቶች የሚውለው ፋይናንስ ለማሟላት የተወሰነ ርቀት ለመሄድ
32
የተቻለ ቢሆንም ለሌሎች የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ቅድሚያ በመሰጠቱ ዘላቂነቱ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡፡ ይህ
እንዳለ ሆኖ በአብዛኛዎቹ ከተሞች የገቢ ዝቅተኛነት፣ የቁጠባ ባሕል ያለመኖር፣ ቁጠባን የሚያበረታታ ሥርዓት
ያለመኖር፣ መደበኛ ያልሆኑ የፋይናንስ ምንጮችን (እድር፣ እቁብ ወ.ዘ.ተ.) መጠቀም ያለመቻል ግንባታዎችን
እያጓተተ ይገኛል፡፡
የግንባታ ግብአቶች አቅርቦት እጥረት፡- የግንባታ ግብአቶችና ዕቃዎች አቅርቦት በተለይ የኢንዱስትሪ ውጤት
የሆኑና በአገር ውስጥ የማይመረቱት ዋጋቸው በዓለም አቀፍ ገበያ የሚወሰን በመሆኑ፣ በሌላ በኩል ከፍተኛ የሆነ
ቁጥር ያለው የከተሞቻችን ነዋሪ በዝቅተኛ ገቢና ድህነት ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ የዓለም አቀፉ ገበያ
የሚፈጥረውን ውድድር ተቋቁሞ ቤት ለመገንባት በጣም እያዳገተው ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ ባለፉት ጥቂት ዓመታት
በአገር ውስጥ የሚመረቱትም ሆነ ከውጭ የሚገቡት የፋብሪካ የግንባታ ዕቃዎች እንዲሁም የአካባቢ የግንባታ
ግብአቶች እጥረት ሳቢያ የአብዛኛዎቹ የግንባታ እቃዎች ዋጋ ከእጥፍ በላይ ያደገበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ እንደ
አርማታ ብረት፣ አሳንሰር/ሊፍት፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የሳኒተሪ ዕቃዎች፣ ወዘተ በመሳሰሉት ከውጭ በሚገዙ
የግንባታ ቁሳቁሶች እና የአካባቢ የግንባታ ግብአቶች በሆኑት አሸዋና ጠጠር ላይ የተከሰተው የዋጋ መጨመር
እንዲሁም ወጪ ቆጣቢ የአካባቢ ጥሬ ሀብትን የሚጠቀሙ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች እንዲስፋፉና እንዲሰርጹ
ባለመደረጉ በአገሪቱ ካለው ዝቅተኛ የነዋሪዎች ገቢ ጋር ተዳምሮ የአዳዲስ ቤቶችን ግንባታ በሚፈለገው መጠን
እንዳይሆን አድርጎታል፡፡
የመሠረተ-ልማት አቅርቦት አናሳ መሆን፡- በከተሞች በቂ የመሠረተ-ልማት አውታር ባለመዘርጋቱም የራሳቸውን
እድገት በማፋጠን ብሎም የገጠሩ ልማት ማዕከል በመሆን ከተሞች እርስ በርሳቸው ተደጋግፈውና ከገጠሩ ጋር
በጥብቅ ተሳስረው የልማትና የመልካም አስተዳደር የስበት ማዕከልነት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት አልቻሉም፡፡
በአብዛኛዎቹ ከተሞች የመጠጥ ውኃ፣ የመንገድ፣ የፍሳሽ ውኃ ማስወገጃ መስመር፣ የመብራት፣ የደረቅ ቆሻሻ
አያያዝና አወጋገድ ወዘተ … አገልግሎቶች ሽፋን በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ከተሞች ደግሞ
በውስን ደረጃ አገልግሎቱን የሚሰጡ ቢሆንም ያላቸው ሽፋን ያልተሟላና ጥራቱም ዝቅተኛ ነው፡፡ በተለይ የውኃ
እጥረትና የደረቅና የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገድ ችግር ጐልቶ ይታያል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተሞች በፎቅ ደረጃ
ግንባታ እየተስፋፋባቸው በመሆኑ መጸዳጃ ቤቶችም በብዛት ውኃ የሚፈልጉ በመሆኑ የውኃ ፍላጐታቸው
እየጨመረ ይገኛል፡፡ ወደፊት ደግሞ ቤቶች በብዛት በፎቅ ደረጃ የሚገነቡ በመሆኑ የውኃ ፍላጎቱ በከፍተኛ ሁኔታ
ሊጨምር ይችላል፡፡ በመሆኑም የመጠጥና የፍሳሽ ውኃ አቅርቦትና አስተዳደር በቅድሚያ ሊታሰብበት የሚያስፈልግ
መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡
በከተማ አስተዳደሮች ያለው የመሠረተ ልማት አቅርቦት ቅንጅት፣ አፈፃፀም እና አስተዳደር ውስብስብ ችግር
ያለበት ሆኖ ይታያል፡፡ በከተሞች የመሠረተ-ልማት አቅርቦትና አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ
እንቅስቃሴዎችንና ኢንቨስትመንቶችን በብድር መደገፍ ላይ በመሆኑ በእነዚህ አካላት አማካኝነት ለቤት ልማት
የሚቀርበው የፋይናንስ መጠን እጅግ ውሱን ነው፡፡ አነስተኛ የብድር ተቋማትም ቢሆኑ ለቤት ግንባታ አገልግሎት
መዋል የሚችል በቂ የፋይናንስ አቅም የላቸውም፡፡
እንደሚታወቀው የአገር አቀፉ የቤት ልማት ኘሮግራም የፋይናንስ ምንጩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክልሎች ቦንድ
በመሸጥ የሚያገኙት ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ለቤቶች የሚውለው ፋይናንስ ለማሟላት የተወሰነ ርቀት ለመሄድ
33
የተቻለ ቢሆንም ለሌሎች የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ቅድሚያ በመሰጠቱ ዘላቂነቱ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡፡ ይህ
እንዳለ ሆኖ በአብዛኛዎቹ ከተሞች የገቢ ዝቅተኛነት፣ የቁጠባ ባሕል ያለመኖር፣ ቁጠባን የሚያበረታታ ሥርዓት
ያለመኖር፣ መደበኛ ያልሆኑ የፋይናንስ ምንጮችን (እድር፣ እቁብ ወ.ዘ.ተ.) መጠቀም ያለመቻል ግንባታዎችን
እያጓተተ ይገኛል፡፡
በከተማ አስተዳደሮች የመሠረተ-ልማት አቅርቦት ቅንጅት፣ አፈፃፀም እና አስተዳደር ውስብስብ ችግር ያለበት ሆኖ
ይታያል፡፡ በከተሞች የመሠረተ-ልማት አቅርቦትና አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ እንዳይሆን ካደረጉት
መሠረታዊ ምክንያቶች/ችግሮች መካከል አንዱና ትልቁ የከተሞች የመሠረተልማት አውታሮቹን አቀናጅቶ በተናበበ
ዕቅድ የማቅረብና የመንከባከብ እንዲሁም የፋይናንስ አቅም ውስን መሆን ነው፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከተሞች
እነዚህን አገልግሎቶች ለነዋሪዎቻቸው በሚፈለገው መጠን ማቅረብ የሚያስችላቸውን የፋይናንስ አቅም እንዲፈጥሩ
ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም አሁንም ከሚፈለገው አንጻር ብዙ የሚቀር በመሆኑ በከፍተኛ ትኩረት መሥራትን
ይጠይቃል፡፡
ለቤት ልማት የመሬት ዝግጅትና አቅርቦት ዝቅተኛ መሆን፡- ለቤት ልማትና ለሌሎች አገልግሎቶች በግለሰብ
ወይም በድርጅቶች የተያዘው የመሬት መጠን በተለይ በመሐል የከተማ አካባቢዎች ሰፋፊ ቦታዎች ያለጥቅም
እንዲቆዩና ወደፊት ትርፍ አገኝበታለሁ ብሎ ቦታ መያዝ የተለመደ ከመሆኑም በላይ የሚያስጠይቅ ሥርዓትም
አልነበረውም፡፡ ይህም ለአዳዲስ ግንባታ የሚውሉ የቦታ ጥያቄዎችን ከመሐል ከተማ በራቁና የመሠረተ-ልማት
ባልተስፋፋባቸው ቦታዎች ለማስተናገድ የሚደረግን ሙከራ ለከተሞች ብቸኛ አማራጭ እንዲሆን አድርጎት
በመቆየቱ የመሠረተ-ልማት ማሟላትን አስቸጋሪ ከማድረጉም በተጨማሪ የአርሶ አደሩን የእርሻ መሬት በሰፊው
እየተሻማ እና አርሶ አደሩን እያፈናቀለ ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ ከመሬት ጋር በተያያዘ ያለው ዋናው ችግር ከይገባኛል ነጻ የሆነና ውኃ፣ መንገድ፣ መብራት፣ የፍሳሽ
ውኃ ማስወገጃ ወዘተ… የተሟሉለት መሬት ማቅረብ አለመቻል ነው፡፡ ስለሆነም የአዳዲስ ቤቶች ግንባታ ሂደት
በከፍተኛ ሁኔታ እያጓተተው ይገኛል፡፡ ለዚህ ዋንኞቹ ምክንያቶች የከተማ አስተዳደሮች በሰው ኃይል፣ በአሠራር
ሥርዓት እና በፋይናንስ የተጠናከረ አቅም የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡ በተለይ ለቤት ልማት የሚውል የለማ መሬት
መስጠት የሚያስችልና ከመሬት ክለላ ጀምሮ እስከማልማት ድረስ ያለው አሠራር በአብዛኛዎቹ ትልልቅ ከተሞች
ያለመዘርጋቱና ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዙ የሚስተዋሉ የሥነ-ምግባር ጉድለቶች በቀጣይም ፈተና ሆነው
መቀጠላቸው አይቀርም፡፡ በተጨማሪም ከተሞች ለቤትና ሌሎች ግንባታዎች የሚያስፈልግ ቦታ ለማስለቀቅ ለካሳ
ክፍያ የሚያስፈልጋቸው ፋይናንስ እጥረት ከፍተኛ በመሆኑ የለማ መሬት ለማግኘት ሌላው ማነቆ መሆኑ
አልቀረም፡፡
ፅዱና ምቹ የሆኑ የመኖሪያ አካባቢዎች ከመፍጠር አንፃርም በአብዛኛዎቹ ከተሞች የሚካሄደው ልማትና
የመንደሮች ምሥረታ በከተሞቹ ኘላን መሠረት እየተፈጸመ እንዳልሆነ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ
ለአረንጓዴ/መናፈሻና ለተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች በኘላን የተከለሉ ቦታዎች በህገ-ወጥ መንገድ በቦታዎቹ ላይ
ቤቶች እንዲገነቡባቸው እየተደረገ በመሆኑ ደረጃውን የጠበቀ ከተማ ከመፍጠር አንጻር ለትውልድ ልማትን ሳይሆን
ዕዳ ማስተላለፍ መሆኑን የግንዛቤ ጉድለት ይስተዋላል፡፡ በተመሳሳይ በገጠር የልማት ማዕከላት ለቤት ግንባታ
34
የሚሆን መሬት አቅርቦት ችግር እየተስተዋለ ሲሆን ለዚህም ለልማቱ በመንግስት ይዞታ ሥር የሚገኙ መሬቶች
ጥቅም ላይ እንዲውሉ ታሳቢ የተደረገ ቢሆንም አቅርቦቱ በቂ አይደለም፡፡
የቤቶች ልማት ሥራዎች አፈጻጸም
በሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፍርሜሽን ዕቅዳችን የመኖሪያ ቤት ልማት በመንግስት አስተባባሪነት
ተገንብተው ለተጠቃሚ ከተላለፉ 384,107 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ
ማህበራት 151,997፣ እንዲሁም በሪል ስቴት አልሚዎች 21,314 ቤቶችን ማቅረብ የተቻለ ሲሆን፣ የግል
ቤት ሰሪዎችን ሳይጨምር የቀረቡ ቤቶች ከ 557,417 አይበልጡም፡፡ ይህም አንድ ዓመት መቅረብ
ከሚገባው የቤት ፍላጎት ጋር ሲነጻጸር ያለው ልዩነት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ መረጃ የሚያሳየው
መንግስት ከመሬትና መሰረተ ልማት አቅራቢነት በተጨማሪ ትልቁን የቤት አቅርቦት ኃላፊነት የተሸከመው
መሆኑን ነው፡፡ ይህ አሰራር ከፍተኛ ድጎማ የታከለበት ስለሆነ የቤት ችግር ዘላቂ መፍትሔ እንደማይሆን
ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በሃገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት አስተባባሪነት እየተከናወነ ያላው የቤት ልማት ዓላማ
የስራ ዕድል መፍጠር ጋር ተያይዞ እስከ 1.3 ሚሊየን ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ የዜጎችን ፍትሃዊ የሀብት
ተጠቃሚነት ለመረጋገጥ መንግስት የቤት ልማት ዘርፍ ከሚያርገው ድጎማ በተጨማሪ የሴቶች፣ የአካል
ጉዳተኞች እና በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች፤ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደቅደም
ተከተላቸው 30%፣ 5% እና 20% ቅድሚያ ተጠቃሚነት ዕድል ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ በሌላ በኩል በቤቶች
ልማት በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎች የስራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች እና የጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች የሥራ ስምሪት እንዲያገኙ፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ከማነቃቃት አንጻር እና
የደቀቁ ሰፈሮችን መልሶ ከማልማት አንጻር ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ በከተሞች ያላው የቤት አቅርቦትና
ፍላጎት ያልተጣጣመ መሆኑ አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ተገቢ ላልሆነ ወጪና መንገላታት በማድረግ
የተወሳሰበ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ችግሮች እያጋለጠው ይገኛል፡፡
በሁለቱ ዕትዕ ዘመን የታዩ ችግሮች የፊይናንስ ምንጭ እጥረት፣ የለማ መሬት አቅርቦት እጥረት፣ ወጪ
ቆጣቢ የግንባታ ቴክኖሎጂ እና ዲዛይን ውሱንነት፣ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እጥረትና ዋጋ መናር፣
የኮንስትራክሽን አቅምና የኘሮጀክት ሥራ አመራር ክህሎት አናሳ መሆን፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና
ቅንጅታዊ አሠራር ደካማ መሆን፣ ጠንካራ የቤት አስተዳደር ስርዓት ያለመዘርጋት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
የቤት አቅርቦቱ የባለቤትነትን አማራጭ ብቻ ማእከል ያደረገ መሆኑና የኪራይ አቅርቦት ትኩረት
አለመሰጠቱ እንዲሁም የቤት ገቢያው እየናረ መሄድ ትልቅ ችግር ነው፡፡ በሌላ በኩል ማህበረሰቡ ችግሩን
የመፍታት እያከናወነ ያለው ህገ ወጥ ግንባታ የከተሞችን ህልውና እየፈተነ ነው፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት
በቤት አቅርቦት፣ የቁጠባ ባህል በመገንባት፣ ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣
የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ በማጠናከር እና ተያያዥ ኢንደስትሪዎች በማስፊፊት የተሠራ ስራ ቢኖርም፣
አሁንም ያለው የቤት አቅርቦት ከፍላጎቱ የማይጣጣም፣ ያሉ ቤቶችም ደረጃቸውን ያልጠበቁ ስለሆነ
በቀጣይ ዕቅድ ትኩረት ተሰጥቷቸው ዘላቂ መፍትሄ የሚፈልጉ ይሆናል፡፡

የቤቶችና የከተማ ልማት


5) የቤቶች ልማትና የሪል ፕሮፐርቲ
ሀ. የቤቶች ልማት
 የሁሉንም ባለድርሻዎች አቅም በቤት ልማትና አቅርቦት መጠቀም፣
 የቤት አቅርቦትን ከባለቤትነት በተጓዳኝ የኪራይ አማራጭንም መደገፍ፣
 የገጠር ማዕከላት መኖሪያ ቤቶች ደረጃ ማስጠበቅ፣
 የቤት ፋይናንስ አቅርቦት አማራጮችን ማስፋት፣
 በቤት ልማት የግል ዘርፉ ሚና ማጎልበት፣
 የቤት ልማት ተደራሽነት ለማሳደግ አዋጪ የአገር በቀል ግብአቶችን የሚያበረታታ አሠራር
ተግባራዊ ማድረግ፣

የቤቶችና የከተማ ልማት ዘርፍ

2.1. የቤቶች ልማት ሥራዎች

ጥቅል ዓላማ፡- በከተማና በገጠር ማእከላት ተደራሽና ደረጃውን የጠበቀ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት

ማሳደግ፣

ዓላማ አንድ፡ የህብረተሰቡን የቁጠባ ባህል በማሳደግ እና የቤት ልማት አማራጮችን በመጠቀም

በከተሞች የቤት አቅርቦት ለማሻሻል 2,175,000 ቤቶች ይገነባሉ፡፡

ግብ 1፡ በ 9 ኙ ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለዝቅተኛ፣ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ

ያላቸው ዜጎችን

ተጠቃሚ የሚያደርግ በ 10/90፣ 20/80፣ በ 40/60 እንዲሁም በኪራይ የቤት ልማት ፕሮግራም
በድምሩ

135,774 (20%) ቤቶች ይገነባሉ፡፡

ግብ 2፡ በ 9 ኙ ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማኅበራት፣

ቤቶች (35%)፣

በግለሰቦች የቤት ልማት አቅርቦት ፕሮግራም ቤቶች (15%)፣ በባለሃብቶች (ሪል ስቴት) ቤቶች

(10%)፣

በመንግሥትና የግል ባለሃብት አጋርነት (Public Private Partnership- PPP) ቤቶች (15%) እና

በግሉ

ሴክተር በሽርክና (ጆይንት ቬንቸር) (5%) የቤት ልማት አቅርቦት ፕሮግራም በድምሩ 1,111,000
(80%)

ቤቶች ይገነባሉ፡፡

ግብ 3፡ ከደረጃ በታች ከሆኑ 74% ቤቶች ውስጥ 534,090 ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል (5% በመልሶ

ማልማት

እንደሁም 15% የማሻሻያ ልማት በማካሄድ 20%) አሁን ያለው ከደረጃ በታች ያሉ ቤቶች ምጣኔ

ወደ

58% እንዲቀንስ ይደረጋል፡፡

ግብ 4፡ ተመጣጣኝ ዋጋ (Affordability) እና የግንባታ ማቴሪያል አቅርቦትን ታሳቢ ያደረጉ

በመንግስት

አስተባባሪነት፣ በመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት ለሚገነቡ ቤቶች የሚያገለግሉ 35 ዓይነት

ስታንዳርድ ዲዛይኖች የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማስተባበር ጋር እንዲዘጋጅ

ይደረጋል፡፡

ግብ 5፡ የአገር ውስጥና የውጭ ሀገር ኩባንያዎችን በማሣተፍ የተሻሻለ የመኖሪያ ቤት ግንባታን

ለማፋጠን

የሚጠቅሙ ወጪ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን በማጥናት፣ አዳዲስ የግንባታ ፕሮጀክት ማኔጅመንት


128

ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ወይም በማላመድ የቤቶች ግንባታ አዋጭና ተደራሽ የማድረግ ሥራ

ይሠራል፡

ግብ 6፡ በመንግስት አስተባበሪነት ተገንብቶ የሚጠናቀቁ 178,774 ቤቶች ግልፅ፣ ፍትሃዊና አሳታፊ


በሆነ መንገድ

ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፉ ይደረጋል (30 ሴቶች፣ 20 ለመንግስት ሠራተኞች እና 5 ለአካል

ጉደተኞች)

ለአካል ጉደተኞች)፡፡

ዓላማ ሁለት፡ የፋይናንስ፣ የግንባታ ግብዓትና የአቅም ግንባታ ሥርዓትን በማሻሻል የቤቶች

ልማትን ለማሳለጥ

ነው፣

ግብ 1፡ ለመኖሪያ ቤቶች ልማት የሚያስፈልግ ፋይናንስ እንዲጓለብት ብሔራዊ የቤቶች ልማት

ፈንድ እንዲቋቋም

ይደረጋል፡፡

ግብ 2፡ በመንግሥት አስተባባሪነት ለሚገነቡ ለመኖሪያ ቤቶች ልማት የሚውል ብር 72.74 ቢሊዮን

ብር ብድር

እንዲሁም ከውጭ አገር ለሚገቡ ግብዓቶች መግዣ የሚውል 120 ሚሊዮን USD የውጭ ምንዛሪ

ለቤት

ግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲቀርብ ማድረግ እና ቀደም ሲል በአዲስ አበባ በ 20/80 እና ለ 40/60

ቤቶች

ግንባታ ከቦንድ ሽያጭ ወጪ የተደረገው ብር 33.6 ቢሊዮን ብድር እንዲመለስ ማድረግ፤

እንዲሁም

የተጠቃሚዎችን የቁጠባ ባህል በማጎልበት ብር 414.39 ቢሊዮን እንዲቆጠብ ይደረጋል፡፡

ግብ 3፡ በመንግስት የሚገነቡ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ አፈጻጸም ለማሻሻል (325) ከአስፈፃሚ

ባለቤት፣ (1,848)

ከስራ ተቋራጭ፣ (29) ከአማካሪዎች፣ (1,646) ለዘርፉ ሰራተኞች እና (7,320) ከጥቃቅንና

አነስተኛ

ኢንተርፕራይዞች ለተውጣጡ በድምሩ 11,168 አመራርና ባለሙያዎች (30% ሴቶች) የአቅም

ግንባታ

ስልጠና ይሰጣል፡፡

ግብ 4፡ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ሰንሰለቶች ግልጽ፣ ፈጣን፣ አሳታፊ እንዲሁም በሚፈለገው

ጥራት፣ መጠንና
ጊዜ እንዲቀርቡ ጥናት ይደረጋል፡፡

ዓላማ ሶስት፡ የቤቶች አስተዳደር ስርዓትን በማሻሻል ቤቶች ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እንዲሆኑ

ማድረግ፣

ግብ 1፡ ከመኖሪያ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ሥራዎች ጋር በተያያዘ የሚታዩ የሕግና አሠራር

ክፍተቶችን

ተለይተው ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ይደረጋል፡፡

ግብ 2፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በመተባበር የከተማ ቤቶች መረጃ

በዘመናዊ

ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ለማድረግ የሚያስችል ሶፍትዌር እንዲለማ እና በሁሉም ክልሎችና የከተማ

አስተዳደሮች የሚገኙ የመንግስት ቤቶች መረጃ ተደራጅቶ በሶፍትዌሩ እንዲያዝ ይደረጋል፡፡

ግብ 3፡ የጋራ ሕንጻ ማህበራት ሕግ በሚፈቅደው አግባብ እንዲደራጁ፣ የኪራይ ቤቶች ውል ዕድሳት

እንዲከናወን፣ የመንግስት ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ወጥቶላቸው እንዲመዘገቡ ይደረጋል፡፡

ግብ 4፡ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ 600 (30%ሴቶች) የዘርፉ አመራሮችና

ባለሙያዎች ከቤቶች

አስተዳደርና መረጃ አያያዝ ሥራዎች ጋር በተያያዘ ስልጠና ይሰጣል፡፡

ዓላማ አራት፡- የአካባቢውን ሥነ ምህዳር፣ የማቴሪያል አቅርቦት፣ ባህላዊ እሴት ታሳቢ ያደረገ

ደረጃቸውን የጠበቁ

የገጠር መኖሪያ ቤቶች በስኬች ፕላን መሠረት እንዲገነቡ በመደገፍ የዜጎችን አኗኗር ዘይቤ

ማሻሻል፣
129

ግብ 1፡ የገጠር ልማት ማዕከላት መኖሪያ ቤቶች ልማት ሥራ ውጤታማና ቀልጣፋ ለማድረግ

በየአካባቢው ለኑሮ

ተስማሚና ተደራሽ የቤቶች ዲዛይንና ማስፈፀሚያ ማንዋሎች ይዘጋጃሉ፡፡

ግብ 2፡ የገጠር ልማት ማዕከላት መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሥራን ለማሣካት በሁሉም ክልልችና

በድሬድዋ ከተማ

አስተዳዳር አደረጃጀት ባልተፈጠረበት እንዲፈጠር ባለበት ደግሞ እንዲጠናከር ይደረጋል፡፡

ግብ 3፡ በገጠር ቤቶች ልማት ዙሪያ ለ 822,840 አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ግንዛቤ

እንዲያገኙና የልማቱ

ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ይደረጋል፡፡


ግብ 4፡ በ 3,202 የገጠር ልማት ማዕከላት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረተ ልማቶች (መንገድ፣

ወኃ፣ መብራት፣

ስልክ፣ የደረቅ ቆሻሻ መጣያ ጉርጓድ፣ ክልኒክ፣ ት/ቤት) በሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት ሥራ

አንዲሟሉላቸው ድጋፍና ክትትል ይደረጋል፡፡

ግብ 5፡ 859,000 ቤቶች በገጠር የልማት ማዕከላት (በአርሶ አደሩ/አርብቶ አደር መንደሮች)

እንዲገነቡ ድጋፍና

ክትትል ይደረጋል፡፡

ግብ 6፡ ስኬች ፕላን በተዘጋጀላቸው የገጠር ልማት ማዕከላት ለቤቶች ግንባታ የሚውል 35,436

ሄክታር መሬት

ለአርብቶ አደሮችና አርሶ አደሮች እንዲቀርብ ይደረጋል፣

ግብ 7፡ በየክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ


(Community Service

Directorate) በአቅራቢያቸው የሚገኙ የገጠር ልማት ማዕከላትን ቤት ልማት ጠቃሚ በሆኑ

የምርምር

ውጤቶች እንዲያግዙ ያላቸውንትስስር እንዲጠናከር ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል፡፡

ግብ 8፡ የገጠር ልማት ማዕከላት ቤት ልማት ሥራ ለማጠናከር በሚያስችሉ ርዕሰ ጉዳዮችና

በሚለዩ ክፍተቶች

ላይ ከባለሙያዎች፣አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ለሚውጣጡ ለ 2,277 ተሣታፊዎች

የአሰልጣኞች ስልጠና

ይሰጣል፡፡ 30% (750 ሴቶች እንዲሆኑ ይደረጋል)፡፡

ግብ 9፡ በሁሉም ክልሎችና በድሬድዋ አስተዳዳር ከለሙ የገጠር ልማት ማዕከላት በተዘጋጀው

ማንዋል መሠረት

2 ሞዴል የልማት ማዕከላትን በመምረጥ እውቅናና ማበረታቻ እንዲሠጥ ይደረጋል፡፡

ግብ 10፡ በገጠር የልማት ማዕከላት የሚገነቡ ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ለኑሮ ምቹ፣ በዋጋ

ተደራሽ፣ ከአካባቢው

ባህል ጋር የተጣጣሙ እና ለአካባው የአየር ንብረት የሚስማሙ እንዲሆኑ የሚያስችሉ 35 ናሙና

ዲዛይኖች እንዲዘጋጁ ይደረጋል፡፡

የማስፈጸሚያ ስልቶች

 ለቤት ልማትና ተጠቃሚ የሚሆን የፋይናንስ ስርዓት መዘርጋት፣ የቤቶች ልማት ፈንድ
እንዲቋቋም

ማድረግ፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በቤት ልማት ፋይናንስንግ እንዲሳተፉ ማድረግ፣

 መሬት ቆጣቢና ጥግግትን የሚያረጋግጥ ቤት አገነባብባ ስልት መከተልና ለቤት ልማት አስፈላጊ

የሆነ

መሬት በበቂ የሚቀርብበት ስርአት መዘርጋት፣

 የመንግስት ቀጥታ የቤት ግንባታ ተሳትፎና ድርሻ እየቀነሰ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎና ድርሻ እየጨመረ

እንዲሄድ ማድረግ

 የመኖሪያ ቤት አቅርቦት አማራጮችን በማስፋት ባለቤትነትን ማበረታታቱ እንደለ ሆኖ ቤት

በተመጣጣኝ

ዋጋ በኪራይ በሚቀርበትን አካሄድ መደገፍ


130

 በከተማ መሻሻል ላይ ማህበረሰቡና መንግስታዊ ያለሆኑ ተቋማት ከፍተኛ ድርሻ እንዲኖራቸው

የሚያበረታታና አስቻይ ስርዓት መዘርጋት፣

 ተመጣጣኝ ዋጋ (Affordability) እና የግንባታ ማቴሪያል አቅርቦትን ታሳቢ ያደረጉ ስታንዳርድ

ዲዛይኖች

ማዘጋጀት፣

 በቤቶች ልማት የሚሠማሩ የስራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት፣ እና

ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ መስጠት፣

 አዳዲስ የግንባታ ፕሮጄክቶች ማኔጅመንት ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ወይም በማላመድ

በቤቶች ግንባታ

ስራ ላይ እንዲውሉ ይደረጋል፣

 የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ኩባንያዎችን በማሣተፍ የተሻሻሉ፣ ወጪ ቆጣቢ እና ፈጣን

የግንባታ

ዲዛይኖችንና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣

 የሀገር ውስጥ አምራቾችን በማበረታታት ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን መተካት (Import


Substitution)

ላይ ትከረት ማድረግ፣

 የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ሰንሰለቶችን ግልጽ፣ ፈጣን እና አሳታፊ እንዲሆን ማድረግ፣

 በቤቶች ማስተላለፍና አስተዳዳር ጋር የተያያዙ መናቆዎችን/የመልካም አስተዳደር ችግሮችን


መለየትና

መፍታት

 በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የቤቶች አስተዳደርና መረጃ አያያዝ ስርዓት መዘርጋት፣

 በተለያዩ አካላት ለኪራይ የሚቀርቡ ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ አንዲሆኑ ማድረግ

 የጋራ ህንጻ ቤት ባለንብረቶች ህግ በሚፈቅደው አግባብ ተደራጅተው ቤታቸውን

እንዲያስተዳደሩ

ማድረግ፣

 በገጠር አካባቢዎች የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና የቁጠባ ባህል ማዳበር፣

 በገጠር ቤቶች ልማት ላይ የባድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር ማረጋገጥ፣

 ስታንዳርድ ዲዛይኖችን ማዘጋጀት፤ አቅም መገንባትና ቴክኖሎጂን መጠቀም፡፡

You might also like