You are on page 1of 3

ቀን:- 20/11/2015

ለጋም/ብሔ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት
ጋምቤላ
መልስ ሰጪ 1. አቶ አያሌው አበበ አድራሻ ፦ ሜጢ 01 ቀበሌ
ይግባኝ ባይ 2. አቶ አበበ ደምሴ አድራሻ ፦ ሜጢ 01 ቀበሌ
በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 327 መሰረት የቀረበ የይግባኝ መልስ
ይህ የይግባኝ መልስ ይግባኝ ባይ በመልስ ሰጪ ላይ በቀን 15/10/2015 ዓ/ም ባቀረበው ይግባኝ ላይ የቀረብ
ነው።
የመጀመርያ መቃወምያ

ይግባኝ ባይ ያቀረበው የይግባኝ ምክንያት መልስ ሰጪ በሃሰት ከከሰሰኝ በኋላ በሰሜን አቶ አለማየው ገ/ስላሴ፣
አቶ ዮሴፍ ጉሜሳ እና አቶ ወንድሙ ወ/ማርያም በደቡብ ንጋቷ ዋጆ በምዕራብ አቶ ገ/መድህን አሸብር እና
አቶ አድማሱ አዋጎ በምስራቅ አቶ አጥናፉ ሃይሌ መሃከል የሚገኘውን አራት ሄክታር የቡና ይዞታዬ ላይ ተከሳሽ
በመግባት የ 2015 ዓ/ም የቡና ምርት ዋጋ ጠቅሶ ሂሳቡን ይክፈለኝ የሚል ነው ።በተጨማሪም የስር ፍ/ቤት
ካሳ እንዲከፈለኝ ክስ አቅርቤ ጉዳዩን የይዞታ አድርጎ በመውሰድ ወስኗል በማለት ይግባኝ አቅርቧል። በመሰረቱ
የቡና አትክልቱን ተጠሪ ከአቶ ታመነ ተረፈ በቀን 29/03/2011 ዓ/ም በተጻፈ የቡና አትክልት የሽያጭ ውል
ገዝቼ በቀበሌው አመራር ተረጋግጦ በዚሁ ይዞታ ላይ ከ 2002 ዓ/ም- 2015 ዓ/ም ድረስ የመንግስት ግብር
እየገበርኩበት ለ 13 አመት በእጄ አድርጌ እየተጠቀምኩበት እንደሆነ በስር ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ
የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ይግባኝ ባይ በዚህ ይዞታ ላይ ካርታ ያሰራው በ 2012 ዓ/ም ላይ በነበረበት ሰዓት
ታምሜ ጅማ ለህክምና ስሄድ በአከባቢው ባህል መሰረት ይህንን ይዞታ እንዲያስተዳድርልኝ ካቦ( ወኪል)
አድርጊኣው በነበረበት ሰዓት ለአከባቢው ባለይዞታዎች ካርታ በሚሰራበት ወቅት በህገ-ወጥ መንገድ በራሱ
ስም ካርታ አሰርቶ ነው። ይህ ካርታ በህገወጥ መንገድ የተሰራ ስለመሆኑ መሬቱ በሚገኝበት መንገሺ ወረዳ ፍ/
ቤት ክስ አቅርቤበት መጥሪያ በፍ/መ/ቁ 03443/2015 በቀን 6/11/2015 ዓ/ም ወጦቶ ለተከሳሽ የተሰጠው
ስለሆነ ይህ ፍ/ቤት በማስረጃነት የተያያዘው ሰነድ በፍ/ሥ/ሥ/ቁ 327(3) እና 349 (1) (ለ) መሰረት
እንዳቀርብ ፈቅዶልኝ የይዞታው ትክክለኛ ባለይዞታ መሆኑ እና በካርታው ይሰረዝልኝ ጉዳይ በመንገሺ ወረዳ
ፍ/ቤት እየታየ መሆኑና በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 244 (2) (ሐ) ይህ ጉዳይ ውድቅ እንዲደረግልኝ እጠይቃለው።
የፍሬ ነገር መልስ
1. ይግባኝ ባይ በመልስ ሰጪ ምንም ባላጠፋሁት ጥፋት በማጃንግ ዞን ፖሊስ መምርያ ከሶኝ ስላሳሰረኝ
ባልታሰር ኖሮ ማግኝት የምችለውን ገቢ ስላሳጣኝ ካሳ ይክፈለኝ ብሎ የከሰሰውን የስር ፍ/ቤት ውድቅ
ስላደረገብት ይግባኝ አቅርቧል።በመሰረቱ ይግባኝ ባይ ያቀረብው ይግባኝ በህግ ፊት ተቀባይነት ያለው
ሊያስከስ የሚችል የህግ ምክንያት ያለው ክስ አላቀረበም። በመልስ ሰጪ ልክ እንደማንኛውም ዜጋ
መብታቸውን ለማስከበር ለንብረታቸው ተገቢ ጥበቃ ያገኙ ዘንድ ለማጃንግ ዞን ፖሊስ ጥቆማ
ሰጠተው ይግባኝ ባይ በፖሊስ ታስሮ የተጠረጥረበት ወንጀሉ ተመርምሮ በማጃንግ ዞን ዓ/ህግ ክስ
ተመስርቶበት ነበር። እንግዲህ ተከሳሽ የወንጀል ጥቆማ በማቅረቡ ከውል ውጪ ጉዳት እንዳደረሰ
ተቆጥሮ የቀረበበት ክስ በህግ ተቀባይነት የሌለው ስለሆነ ውድቅ መደረጉ የሚነቀፍበርት ምክንያት
አይኖርም። ይግባኝ ባይ በወንጀል ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር አንቀጽ 11 (1) መሰረት ወንጀል በንብርቱ ላይ
ከሳሽ እንደተሰራ የማመልከት መብቱን ያለው ሲሆን ይህንን ማድረጉ የፍታብሄር ተጠያቄነት
ለያመጣበት አይችልም። በተጨማሪም ይግባኝ ባይ በፊት ሲከሰስ ታስሮ ከስራው እንዳይስተጓጎል
በዋስ እንድለቀቅና የቀረበበትን የወንጀል ክስ ከውጪ ሆኖ እንዲከታተል ፍ/ቤትን መጠየቅ የራስ ድርሻ
ነበር ስለዚህ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ የሚነቀፍበት ምክንይያት የለም።
2. ይግባኝ ባይ ከይዞታዬ ላይ ተጠሪ የ 2015 ዓ/ም ቡና አስለቅም ወስዷል ካሳ ይከፈለኝ በማለት
አቅርቧል ። ነገር ግን ይግባኝ ባይ የዚህ ይዞታ ትክክለኛ ባለይዞታ ሳይሆን ተጠሪ በ 2012 ዓ/ም ላይ
በነበረበት ሰዓት ታምሜ ጅማ ለህክምና ስሄድ በቅርብ ያለ ልጄ ስለሆነና የቡና ለቀማውንም
ይቆጣጠርልኝ ብዬ ስላሰብኩ በአከባቢው ባህል መሰረት ይህንን ይዞታ እንዲያስተዳድርልኝ ካቦ( ወኪል)
አድርጌው በነበረበት ሰዓት ለአከባቢው ባለይዞታዎች ካርታ በሚሰራበት ወቅት በህገ-ወጥ መንገድ
በራሱ ስም ካርታ አሰርቶ ነው። ይህ ካርታ በህገወጥ መንገድ የተሰራ ስለመሆኑ መሬቱ በሚገኝበት
መንገሺ ወረዳ ፍ/ ቤት ክስ አቅርቤበት መጥሪያ በፍ/መ/ቁ 03443/2015 በቀን 6/11/2015 ዓ/ም
ወጦቶ ለተከሳሽ ተሰጥቶታል። እንግዲህ ይግባኝ ባይ አላባ/ካሳ እንዲከፈለው የጠየቀው የራሱ ህጋዊ
ይዞት ላይ መሆኑ አለመሆኑ ሳይረጋገጥ ካሳ ይከፈለኝ ብሎ መወሰን አይቻልም። በመሆኑም የይዞታው
ትክክለኛ ባለይዞታ መሆኑ እና በካርታው ይሰረዝልኝ ጉዳይ በመንገሺ ወረዳ ፍ/ቤት እየታየ አቤቱታው
ስለሆነ ይህ በካርታው ላይ እየተደረገ ያለው ክርክር እስኪያበቃ ድረስ ይህ ክስ እንዲቆምልኝ
እጠይቃለው።

የምጠይቀው ዳኝነት
1. የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348 መሰረት እንዲጸናልኝ።
2. የይዞታው ትክክለኛ ባለይዞታ መሆኑ እና በካርታው ይሰረዝልኝ ጉዳይ በመንገሺ ወረዳ ፍ/ቤት
እየታየ መሆኑና በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 244 (2) (ሐ) አዲስ ማሰረጃ ያቀብኩት ታይቶ የይግባኝ ባይ
ጉዳይ ውድቅ እንዲደረግልኝ እጠይቃለው።
3. በፍ/ሥ/ሥ/ቁ 327(3) እና 349 (1) (ለ) መሰረት በሚገኝበት መንገሺ ወረዳ ፍ/ ቤት ክስ
አቅርቤበት መጥሪያ በፍ/መ/ቁ 03443/2015 በቀን 6/11/2015 ዓ/ም ወጦቶ ለተከሳሽ
የተሰጠው
4. ለዚህ ክስ ክርክር የማወጥውን ወጪና ኪሳራ ይግባኝ ባይ እንዲሸፍንልኝ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ
እንዲሰጥልኝ እጠይቃለው።

ይህ የመልስ መልስ እውነት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 92/1 መሰረት አረጋግጣለሁ፡፡

የተከሳሽ አቶ አበበ ደምሴ ፊርማ __________

ቀን:- 20/11/2015

ለጋም/ብሔ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት
ጋምቤላ
መልስ ሰጪ 1. አቶ አያሌው አበበ አድራሻ ፦ ሜጢ 01 ቀበሌ
ይግባኝ ባይ 2. አቶ አበበ ደምሴ አድራሻ ፦ ሜጢ 01 ቀበሌ

በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ አንቀጽ 223 መሠረት የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር

የሰነድ ማስረጃ

መልስ ሰጪ በመንገሺ ወረዳ ፍ/ ቤት ክስ አቅርቤበት በፍ/መ/ቁ 03443/2015 በቀን 6/11/2015 ዓ/ም


የተሰጠው መጥሪያ (01 ገጽ)

You might also like