Professional Documents
Culture Documents
BBBBBB
BBBBBB
አዲስ አበባ
ሀ.ይህን ፍርድ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ 5 ኛ ፍ/ብ/ ችሎት በቀን 19/6/2010 ዓ/ም
የሰጠው ውሳኔ ነው፡፡
1. የፍርድ በለመብት እና የፍርድ ባለዕዳ በህግ በሰማንያ ተጋብትን ባልና ሚስትነት አብረን ስንኖር
በለመግባባት ከቤቴ አስወጥቶኝ ነሓሴ ወር 2006 ዓ/ም ለዚሁ ፍ/ቤት የፍቺ አቤቱታ አቅርቤ ፍ/ቤቱ
የፍች ውሳኔ ከሰጠ በኋላ በጋራ ንብረት ላይ አከራክሮ በ 19/6/2010 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡በውሳኔ
መሰረት አልተፈጸመም፡፡
2. የጋራ መኖሪያ ቤት ግምት ፍ/ቤቱ በወሰነልኝ መሰረት የፍርድ በለዕዳ አልፈጸመልኝም፡፡
3. በዝርዝር ተመዝግቦ ቀበሌ የተቀመጠው ንበረት እንደ ውሳኔ አልተፈጸመልኝም፡፡
4. በቤት ውስጥ በጋራ ያፈራን ንብረት ፍ/ቤት በማስረጃ አረጋግጦ የወሰነልኝን ልዩ ልዩ ንብረቶች በወቅቱ
ዋጋ ግምት አልፈጸመልኝም፡፡
ስለዚህ በለዕዳ በመጥሪያ ቀርቦ በመ/ቁ. 91869 ቀን 2010 የፍ/ቤቱ ውሳኔ ያረፈበት መሰረት
የቤቱን ግምት ጥሬ ገንዘብ ከተወሰነ ጊዜ ጀምሮ የባንክ ወለድ ጭምር እና የቤት ውስጥ ቁሳቁስ
ከተወሰነበት ጊዜ ጀምሮ የፍርድ በለዕዳ ሲገለገልበት የቆየ በመሆኑ ግምቱን በ 2015 ዓ/ም የገበያ ዋጋ
ግምት መሰረት ተሰልቶ ድርሻዬን እንዲከፍል እንዲታዘዝልኝ ስጠይቅ የቀረበው የአፈጻጸም
ማመልከቻ እውነት መሆኑን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 92 መሰረት አረጋግጣለሁ፡፡