You are on page 1of 2

ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀን፡- 4/10/2013 ዓ.


አዲስ ከተማ ምድብ 2 ኛ ፍ/ብሔር ችሎት የመ.ቁ፡- 92646
አዲስ አበባ
ከሳሽ፡- ወ/ሮ ቹቹ አብዱልቃድር
ተከሳሽ፡- ወ/ሮ ብርቂሳ አባጆቢር
ጣልቃ ገቦች፡- 1 ኛ. አብዮት ገረመው
2 ኛ. ትዕግስት ገረመው
አመልካች፡- መኪያ ሀሰን
አመልካች ባቀረቡት የጣልቃ ገብነት ማመልከቻ ላይ በተከሳሽ በኩል የቀረበ አስተያየት ነው፡፡
ጣልቃ ገቦች ያቀረቡት የጣልቃ ገብነት ማመልከቻ ደርሶኝ ተመልከቼዋለሁ፡፡በመሆኑም በበኩሌ
የሚከተለውን ምላሽ አቅርቤያለሁ፡፡
1. አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ በመሰረቱ በአቀራረቡ ካልሆነ በስተቀር በመሰረቱ የመብት
ጥያቄው በተለይም እኔን የአሁን ተከሳሽን በተመለከተ ከሳሽ እናም ጣልቃ ገቦች ካቀረቡት
አቤቱታ የተለየ አይደለም፡፡በመሆኑም የተከበረው ችሎት ተከሳሽ ከዚህ በፊት በዚሁ
መዝገብ ላይ ጣልቃ ገቦች ላቀረቡት ክስ ያቀረብኩትን መልስ አመልካች ላቀረቡት
አቤቱታም ላይ እንደአስፈላጊነቱ ታሳቢ እንዲያደርግልኝ እጠይቃለሁ፡፡
2. ስለሆነም በአመልካች ማመልከቻ ላይ የተጠቀሰውን የውርስ ንብረት ክርክር አየተደረገባቸው
ካሉት ቤቶች ውስጥ በዋናው ቤት ላይ ብቻ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ከዚህ በፊትም ደጋግመን
እንደጠቀስነው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ 2 ኛ ፍርድ
ቤት በመ.ቁ 64000 የውርስ አጣሪ ሪፖርቱን ያፀደቀው በማያሻማ ሁኔታ ዋናውን ቤት
በተመለከተ ብቻ ነው፡፡በመሆኑም አሁንም ቢሆን ተከሳሽ ዋናውን ቤት በተመለከተ
መብታቸውን የማልቃወም በመሆኑ እናም በአግባቡ ለማስረከብ ዝግጁ ስለሆንሁ በዋናው
ቤት ላይ የማቀርበው ክርክር የለም፡፡የተቀሩትን በቁጥር 5 የሆኑ ሰርቪስ ቤቶች በተመለከተ
ግን የሰራኋቸው እኔ በመሆኔ በሕግ መሰረት እናም ከሳሽ ላቀረቡት ክስ በሰጠሁት ምላሽ
ላይ በተጠቀሱት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጣቸው አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜዎች
መሰረት መብቱ የእኔ በመሆኑ እንደ ከሳሽ ሁሉ ጣልቃ ገቦችም ምንም መብት የላቸውም፡፡
ከዚህ በፊት በዚሁ ችሎት የተሰሙት ማስረጃዎችም ለዚህ ለጣልቃ ገቦች ማመልከቻም
በተመሳሳይ ያሉኝ በመሆናቸው የተከበረው ችሎት ማስረጃዎቼን ከዚህ ምላሽ ጋር
እንዲያገናዝብልኝ እጠይቃለሁ፡፡
3. በተደጋጋሚ እንደገለፅኩት ዋናውን ቤት ለመልቀቅ ፈቃደኛ ያልነበርኩበት ጊዜ የለም፡፡
በመሆኑም በዚህ ረገድ ተከሳሽ የምነቀፍበት ምንም መንገድ የለም፡፡ነገርግን ይህ ዋናው ቤት
ተከራይቶ አያውቅም፡፡ማለትም የከሳሽ እንዲሁም የጣልቃ ገቦች መብት የሆነ የሚከራይ
ምንም ቤት የለም፡፡ስለሆነም ልከፍል የሚገባኝ ምንም አይነት የኪራይ ገንዘብ የለም፡፡
የሚከራዩት ተከሳሽ የሰራኋቸው ሰርቪስ ቤቶች እንደመሆናቸው፣እነዚህም ደግሞ
የሰራኋቸው እኔ በመሆኔ ከሳሽ እና ጣልቃ ገቦች በቤቶቹ ላይ መብት ሳይኖራቸው
በሚከራዩበት ገንዘብ ላይ መብት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ስለሆነም በዚህ መልክ የቀረበው
ማመልከቻ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡ከዚህ በፊት ቤቱን ለማስለቀቅ ጠይቀን ነበር
ያሉትን በተመለከተ በመሰረቱ ለዚሁ ፍርድ ቤት ውርስ ችሎት አቅርበው ችሎቱ ውድቅ
ያደረገውን ከመሆኑ አንፃር ጠይቀን ነበር ማለታቸው አግባብ አይደለም፡፡ምክንያቱም
አቤቱታቸው ከዋናው ቤት ውጪ ያለው መብታቸው ስላልነበር በውርስ ችሎቱ ጭምር
ተቀባይነት ያላገኘ ሆኖ ሳለ በፍርድ ቤት ተቀባይነት ያላገኘውን አቤቱታ ጠይቄ ነበር
ለሚለው ሀተታ ሊቀርብ አይገባውም፡፡ለዚህ ነጥብም በድጋሚ መግለፅ የምፈልገው ዋናውን
ቤት በተመለከተ ከዚህ በፊት አልለቅም ያልኩበት ጊዜ ካለመኖሩም በላይ አሁንም ቢሆን
ዝግጁ ነኝ፡፡ከዚህ ውጪ ግን ምንም አይነት ሕጋዊ የሆነ የገንዘብ ሀላፊነት የለብኝም፡፡
4. ስለሆነም ለዚህ ክርክር አላማ ከአሁን አመልካች በኩል ከመዝገቡ ቆይታ መራዘም አንፃር
የሚደርስብኝ መንገላታት እንደተጠበቀ ሆኖ ከመብት አንፃር በእኔ በኩል አመልካች ከጣልቃ
ገቦች የተለየ ደረጃ የሌላቸው በመሆኑ የተከበረው ችሎት ባቀረቡት ማመልከቻ ላይ
ተገቢውን ትእዛዝ እንዲሰጥልኝ እጠይቃለሁ፡፡በመሆኑም የተከበረው ችሎት የጣልቃ ገብነት
ማመልከቻውን የሚቀበለው ከሆነ፡ተከሳሽ ከዚህ በፊት ለከሳሽ ክስ ያቀረብኩትን ምላሽ
እንዲሁም ጣልቃ ገቦች ላቀረቡት የጣልቃ ገብነት ማስፈቀጃ የሰጠሁትን አስተያየት ለዚህ
ምላሽ አላማም ታሳቢ እንዲያደርግልኝ እየጠየቅሁ፤ከሳሽ ላቀረቡት ክስ ባቀረብኩት ምላሽ
ላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች ለዚህም ምላሽ አገልግሎት ላይ እንዲውሉልኝ በአክብሮት
እጠይቃለሁ፡፡
ያቀረብኩት ምላሽ/አስተያየት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 92 መሰረት እውነት መሆኑን
አረጋግጣለሁ፡፡ ተከሳሽ ብርቂሳ አባጆቢር

You might also like