You are on page 1of 62

05/01/20 1

በዚህ ውይይት ላይ የሚዳሰሱ፡-

I. የኢፌዴሪ የምርጫ ህግ ማዕቀፍ፣


II. የምርጫ ፍትህ እና መብቶች ምንነት፣

III. የምርጫ አስፈፃሚዎች አደረጃጀት፣

IV. የመራጮችና የእጩዎች አመዘጋገብ የሚመራበት አሰራር፣

V. የድምጽ አሰጣጥ፣ ቆጠራ እና የምርጫ ውጤት አገላለጽ፣

VI. የምርጫ አለመግባባቶች እና ቅሬታዎች አፈታትን፣

VII.በምርጫ እንቅስቃሴ የፖሊስ ተቋም እና አባላት ኃላፊነት


05/01/20 2
I.የኢትዮጵያ ምርጫ የህግ ማእቀፍ
ስንል ምን ማለት ነው?
የኢፌዴሪ የምርጫ ህግ ማዕቀፍ ስንል የኢትዮጵያን ምርጫ ሊመሩ
የሚችሉ ህጎችን የሚመለከት ጉዳይ ነው፡፡
በመሆኑም ፡
1. የኢፌዴሪን ህገመንግስት
2. የምርጫ ማስፈጸሚያ የበታች ህግጋት
የተሻሻለውን የኢትዮጵያ ምርጫ ህግ አዋጅ ቁ.532/1999
የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ ቁ.573/2000
የፖለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁ. 662/2002
ለእነዚህ አዋጆች ማስፈጸሚያ የወጡ ደንቦችንና መመሪያዎችን
ያካትታል፡፡
05/01/20 3
….. የምርጫ
ህግ ማዕቀፍ /የቀጠለ/
1. የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት
◦ አንቀጽ 38 -ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በህግ መሰረት
የመምረጥ እና መመረጥ መብት፣
◦ አንቀጽ 54- ምርጫ በሀገራችን አለም አቀፍ ደረጃ
ተቀባይነት ያላቸውን መርሆዎች መሰረት አድርጎ መካሄድ
ያለበት መሆኑን ደንግጓል (ሁሉ አቀፍ፣ ነጻ፣ ቀጥተኛ፣ ትክክለኛ፣
በሚስጢር ድምጽ አሰጣጥ)
◦ ብቃት ያለው እና ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ያልወገነ
05/01/20የምርጫ አስፈጻሚ ማደራጀት - አንቀጽ 102 4
……..ህግ ማዕቀፍ (የቀጠለ)

2. የምርጫ ማስፈጸሚያ የበታች ህግጋቶች፣


 የተሻሻለው የምርጫ ሕግ ቁጥር 532/1999 እንዲሁም፣

 የዚህ አዋጅ ማስፈጸሚያ ደንቦች እና መመሪያዎቹን


ያጠቃልላል፡፡

05/01/20 5
…ህግ ማዕቀፍ (የቀጠለ)

05/01/20 6
………..ህግ ማዕቀፍ (የቀጠለ)

05/01/20 7
…..ህግ ማዕቀፍ (የቀጠለ)

05/01/20 8
II. የምርጫ ፍትህ እና
መብቶች
1. የምርጫ መብቶች
◦ በህዝብ ይሁንታ የሚቋቋም መንግስት (ከቀረቡ ተወዳዳሪዎች
መካከል የመምረጥ መብትና የውክልና ዴሞክራሲን ማረጋገጥ)፣

◦ ህዝብ በራሱ ጉዳይ ራሱ ቀጥታ የሚሳተፍበት አሰራር


(የቀጥታ ተሳትፎ ዴሞክራሲ)
◦ ህገመንግስታዊ መብትን ማረጋገጥ፣
◦ በህግ መሰረት ሊስተናገድ የሚገባው መብት ነው።

05/01/20 9
የምርጫ ፍትህ .(የቀጠለ)

2. የምርጫ ፍትሕ
 የሙያ ብቃት፣
 እኩልነት (ተሳትፎ)፣
 ነጻነት፣ ግልጽነት፣ከስጋት ነጻ
 ተአማኒነት፣ መሆን እና
 የምርጫ ውጤትን መቀበል፣
 ገለልተኝነት፣

05/01/20 10
III.የምርጫ አስፈፃሚዎች
አደረጃጀት

05/01/20 11
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ም/ቦርድ
አደረጃጀት

05/01/20 12
III. የመራጮችና የእጩዎች
አመዘጋገብ የሚመራበት አሰራር
ሀ. የመራጮች አመዘጋገብ ስርዓት
በመራጭነት ለመመዝገብ የተቀመጠ መስፈርት (በምዝገባው እለት
18 > ፣ በመመዝገቢያው ቦታ ለ6 ወር የኖረ፣ ኢትዮጵያዊ)
በመራጭነት መመዝገብ የማይችሉ፡
 ይህንን የማያሟሉ እና በህመም ምክንያት መወሰን
ያልቻለ/ለች፣ በፍርድ የተወሰነበትን/ባትን የእስር ቅጣት
ያልጨረሰ/ሰች (በህግ የመምረጥ መብቱ/ቷ የተገደበ )
በመራጭነት የመመዝገብ መብት የላቸውም፡፡
05/01/20 13
አመዘጋገብ…..(የቀጠለ)
የመራጮች ምዝገባ የሚካሄድባቸው / የማይካሄድባቸው ቦታዎች፡
የመራጮች ምዝገባ የሚካሄደው በምርጫ ጣቢያ ብቻ ነው ።
ከዚህ ውጪ ማለትም ፡
መኖሪያ ቤት፣
ወታደራዊ ካምፕ፣
ሆስፒታል፣
የእምነት ቦታዎች፣
ፖሊስ ጣቢያ፣
የፖለቲካም ሆኑ
የሀይማኖት ድርጅት ህንጻዎች
የመራጮች ምዝገባ ቦታ ሆነው ማገልገል አይችሉም።
05/01/20 14
በልዩ ሁኔታ …. ምርጫ ጣቢያ…
በልዩ ሁኔታ በተቋቋሙ ምርጫ ክልልሎች የመራጮች ምዝገባ ቦታ
በመሆን የማያገለግሉ
መመገቢያ ቤት ፣መኝታ ቤት፣ ተቋሙ ስራ የሚያከናውንባቸው
ክፍሎች ናቸው፡፡
ስለሆነም ለሌላው ምርጫ ጣቢያ ቤት ለቤት እየዞሩ መመዝገብ
የተከለከለውን ያህል በልዩ ምርጫ ጣቢያም በመኝታ ቤት እና
ትምህርት በሚሰጥባቸው ክፍሎች ውስጥ እየተዘዋወሩ ምዝገባ
ማካሄድ ክልክል ነው፡፡
 በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች ከሌሎቹ ለየት ባለ ሁኔታ እያንዳንዱ
ሰልጣኝ፣ የሰራዊት አባል ወይም በካምፕ የሚኖር የመራጭነት መብት
ያለው ዜጋ ወደ ካምፑ ከመምጣቱ በፊት ከ6 ወር በላይ ይኖርበት
ለነበረው ምርጫ ክልል ድምጽ የሚሰጥ ከመሆኑ አንጻር አመዘጋገቡም
እንዲሁ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል፡፡
05/01/20 15
አመዘጋገብ…..(የቀጠለ)
ሀ. የመራጮች አመዘጋገብ ስርዓት…./የቀጠለ/
 ለምዝገባ የሚቀርቡ የማንነት ማስረጃዎች- የዜግነት
መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ እነዚህ በሌሉ ጊዜ ጊዜ ያለፈባቸውም
ቢሆን የመንጃ ፈቃድ፣ የጡረታ አበል መታወቂያ፣ የመኖሪያ
የምስክር ወረቀት፣ የውትድርና የስንብት ወረቀት ወይም
በአስፈጻሚዎች፣ በታዛቢዎች ምስክርነት ሊመዘገቡ ይችላሉ።
 ተመዝግቦ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ ይሰጠዋል።
(በጥንቃቄ እንዲይዝም ይነገረዋል)
05/01/20 16
አመዘጋገብ…..(የቀጠለ)
የምርጫ ጣቢያው ለህዝብ ተደራሽ፣ ለጥበቃ የሚያመች መሆን
አለበት። ይህም የሚረጋገጠው፡-
 ለድምጽ ሰጪው ካለው ቅርበት፣ የተወሰነ የመራጭ ቁጥር ያለው
 ራሱን የቻለ እና ከሌሎች ምርጫ ጣቢያዎች ጋር ያልተደራረበ እና
በመራጩ ህዝብ ላይ መጨናነቅን የማይፈጥር፣
 የመራጩን ነጻነት እንዲሁም ለምርጫ ሂደትም ሆነ አፈጻጸም
አስቸጋሪ የማይሆን፣
 ጸጥታው የተጠበቀ እና አግባብ ያለው ጥበቃ የሚያገኝ፣
 ለድምጽ ሰጪው ሊታወቅ ወይም ሊታይ በሚችል ቦታ በሚሉ
ዋና ዋና መመዘኛዎች ነው።
የምርጫ ቁሳቁሶችን በአግባቡ በመረከብ ጥበቃ እንዲያገኙ
ማድረግ፣
05/01/20 17
ልዩ የምርጫ ክልል
ቦርዱ ከምርጫ ክልላቸው ርቀው በካምፕ የሚኖሩ
ወታደሮች እና ሲቪል ሰራተኞች እንዲሁም በከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ዜጎች በምርጫ መብታቸው
የሚጠቀሙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት መራጮቹ በሚገኙበት
ቦታ የሚያቋቁመው ምራ ጣቢያ ነው፡፡
 በልዩ ምርጫ ጣቢያ የተመዘገበ መራጭ ወደካምፑ ወይም
ወደ ትምህርት ተቋሙ ከመምጣቱ በፊት ይኖር በነበረበት
የምርጫ ክልል ለውድድር ከቀረቡ እጩዎች መካከል
ይመርጣል፡፡
 ውጤቱ በየተባለው መራጩ በመጣበት ምርጫ ክልል
ውጤት ላይ ተዳምሮ አሸናፊው ይለያል፡፡
05/01/20 18
አመዘጋገብ…..(የቀጠለ)
የተከለከሉ ተግባራት
የሚከተሉትን ተግባራት ፈጽመው የተገኙ ሰዎች በህግ
ተጠያቂ ይሆናሉ
1.መመዘኛዎችን የማያሟላ ነገር ግን በመራጭነት ተመዝግቦ
የተገኘ ሰው፣
2.አለማሟላቱን እያወቀ መዝግቦ የተገኘ የመዝገብ ሹም
3.ለምዝገባ ከተወሰነው ቀንና ሰዓት ውጭ ምዝገባ
ያከናውነ የመዝገብ ሹም
4.በአንድ የምርጫ ጣቢያ ከአንድ ጊዜ በላይ ወይም ከአንድ
ምርጫ ጣቢያ በላይ ተመዝግቦ የተገኘ እዲሁም ከአንድ
በላይ የምዝገባ መታወቂያ ካርድ ይዞ የተገኘ ፣
05/01/20 19
የተከለከሉ ተግባራት…/የቀጠለ/
5. ለመመዝገብ ሲል የሀሰት መግለጫ ወይም ማስረጃ የሰጠ ወይም
ያቀረበ፣
6. መራጮች እንዳይመዘገቡ ያስፈራራ ወይም የሀሰት መረጃ
/ማስረጃ የሰጠ፣
7. የመመዝገብ/አቤቱታ የማቅረብ መብትን የከለከለ ወይም የገደበ/ ያወከ፣
8. የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድን የለወጠ፣ የሰረዘ፣ የደለዘ
9. በሕጋዊ መንገድ የተመዘገበን መራጭ የሠረዘ ወይም የደለዘ
10. በምርጫ ጣቢያው ኃላፊው ከተመደቡ መዝጋቢዎች ውጪ የመራጮች
ምዝገባ ያከናወነ

05/01/20 20
አመዘጋገብ…..(የቀጠለ)
ለ. የእጩዎች አመዘጋገብ

በእጩነት ለመመዝገብ በፖለቲካ ድርጅት ወይም በግል


በእጩነት የቀረበን ያካትታል።
በፓርቲ የቀረበ እጩ በእጩነት ስለመቅረቡ በፓርቲው
የበላይ አመራር/ በየደረጃው ከፍተኛ አመራር/ ፊርማ እና
በድርጅቱ ማህተም የተረጋገጠ ሊሆን ይገባል።
 እጩ መስማማቱን የሚገልጽ ማመልከቻ መቅረብ
ይኖርበታል።

05/01/20 21
አመዘጋገብ…..(የቀጠለ)
 አንድ እጩ፡

በአንድ ም/ክልል ብቻ በእጩነት መቅረብ ይኖርበታል። (በተቃራኒው የተመዘገበ
ይሰረዛል)
 በእጩነት ለመቅረብ የሚያበቁ መመዘኛዎች
 የሚወዳደርበትን ብሔራዊ ክልል የስራ ቋንቋ የሚያውቅ፣
 በምዝገባ ዕለት እድሜው 21 ዓመት / ከዚያ በላይ
የሆነው፣
 በሕግ የመምረጥ ወይም የመመረጥ መብቱ ያልተገደበ
 በም/ክልሉ ለ2 ዓመት በመደበኛነት የኖረ (በስራ/በትምህርት
ርቆ የነበረን አያካትትም)
 እንደተመዘገበ (በም/ክልል ወይም የአካባቢ ምርጫ ሲሆን የምርጫ
ጽህፈት ቤት ሆኖ ሲያገለግል በነበረው ምርጫ ጽህፈት ቤት)
የእጩነት መታወቂያ ይሰጠዋል።
05/01/20 22
አመዘጋገብ…..(የቀጠለ)
 በግሉ እጩ ሆኖ ለመቅረብ የሚፈልግ ሰው
 ለክልል፣ ለዞን እና ለተወካዮች ምክር ቤት ከአንድ ሺ የማያንስ የድጋፍ
ፊርማ
 ለወረዳ ወይም ለከተማ አስተዳደር 200
 ለቀበሌ ም/ቤት ከ 50 የማያንስ የድጋፍ ፊርማ የመምረጥ መብታቸው
በሕግ ካልተከለከሉ የምርጫ ክልሉ ነዋሪዎች ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 ለግል እጩ ተወዳዳሪ የድጋፍ ፊርማ መስጠት የሚችለው ሰው፡
 ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ
 በምርጫ ክልሉ በያንስ ለ6 ወራት በነዋሪነት የቆየ፣
 እድሜው 18 ዓመት / ከዚያ በላይ የሆነው፣
 የመምረጥ መብቱ በህግ ያልተከለከለ፣
 የአእምሮ በሽተኛ ያልሆነ፣ እና
 የእስራት ቅጣት በመፈፀም ላይ የሚገኝ የህግ እስረኛ ያልሆነ ሲሆን ነው፡፡
05/01/20 23
አመዘጋገብ…..(የቀጠለ)
የእጩዎች ብዛት ፡ -

1. ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት-


ምክርቤት በአንድ የምርጫ ክልል ከ12 ዕጩዎች ፣
2. ለ ክልል ምክርቤት - በአንድ የምርጫ ክልል እስከ 24 ዕጩዎች፣

3. ለዞን ምክርቤት - በአንድ የምርጫ ክልል እስከ 24 ዕጩዎች፣

4. ለወረዳ ምክርቤት - በአንድ ቀበሌ እስከ 24፣

5. ለቀበሌ ምክርቤት - በአንድ ጎጥ እስከ 100 ፣ እጩዎች ሲሆን ከዚህ


ቁጥር የሚበልጡ ከሆነ በምርጫ ህጉ መሰረት ቅድሚያ ለሚሰጣቸው
ቅድሚያ በመስጠት ማስተካከል ያስፈልጋል።
05/01/20 24
የመራጮችና የእጩዎች አመዘጋገብ…..
(የቀጠለ)
የመንግስት ሰራተኛ በግሉ/ በፖለቲካ ፓርቲ አቅራቢነት
ሊወዳደር ይችላል። ሆኖም ዳኛ፣ ወታደር፣ ፖሊስ በሆነ
ጊዜ በእጩነት ለመቅረብ ከመንግስት ስራው መልቀቅ
ይኖርበታል።
 እጩዎችን በቀረቡበት ምክር ቤት ለይቶ ለህዝብ ይፋ
ማድረግ ያስፈልጋል።
 አንድ እጩ በፓርቲው ማህተም ተረጋግጦ እስከቀረበና
በምዝገባው ጊዜ ውስጥ እስከቀረበ ድረስ ከአንድ ቦታ ወደ
ሌላ ቦታ ተዘዋውሮ መመዝገብ ይችላል። ተመዝግቦ
ከነበረበት መዝገብ ይሰረዛል መታወቂያውን
ይመልሳል።የጽሁፍ ማስረጃም ይሰጠዋል።
05/01/20 25
ድምጽ አሰጣጥ፣ አቆጣጠርና
ውጤት አገላለጽ
ለህዝብ ታዛቢዎች እና ለተቀማጭ የእጩ ወኪሎች
የሚሰጥ ገለጻ
ስለ ድምጽ አሰጣጡ፣
ስለ ድምጽ ቆጠራ እና ውጤት አገላለጽ፣
እያንዳንዱ አካል በሂደቱ ስለሚኖረው ተግባር
እና ኃላፊነት፣
…ወዘተ በዝርዝር ማስረዳት ያስፈልጋል።
05/01/20 26
የድምጽ አሰጣጥ..(የቀጠለ)

ለምርጫ ጸጥታ አስከባሪዎች የሚሰጥ ገለጻ


 የምርጫ ጣቢያ ኃላፊው ለጸጥታ አስከባሪዎች የሚሰጠው መግለጫ ፡-
 ስለስልጣንና ተግባራቸው፣
 የተከለከሉ ተግባራት እና ወደ ምርጫ ጣቢያ የማይገቡ ነገሮች ምን
እንደሆኑ፣
 ህገወጥ ድርጊትን እንዴት መከላከል እንደሚቻል፣
 አጠቃላይ የምርጫ ሂደትን እና የምርጫ አስፈጻሚ ስለሚሰጠው
ትእዛዝ፣
 ስለምርጫ ጣቢያ ደህንነትና ስነስርዓት አጠባበቅ፣
 ….ወዘተ
05/01/20 27
የድምጽ አሰጣጥ..(የቀጠለ)
አስቀድሞ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት የቅድመ ዝግጅት
ማድረግ፣
 የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶች በመጡበት አኳኋን መመለስ
ስላለባቸው ወደስራ ሲገቡ የምርጫ ጣቢያው የራሱ
ስለመሆኑ ማረጋገጥ ቁጥሮ ወደስራ ማስገባት እና
በመጨረሻም አሽጎ መመለስ ይጠይቃል።
መራጮች በምርጫ ጣቢያው ሲደርሱ በሰልፍ ቆመው
ምርጫ እንዲያካሂዱ ይደረጋል።
መራጩ ራሱ/ራሷ ስለመሆናቸው ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል።
ይሄውም፡-
መመዘኛውን ያሟሉ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ ነው።
05/01/20 28
የድምጽ አሰጣጥ…/የቀጠለ/
 ለመራጩ በየተራ መግለጫ መስጠት ያስፈልጋል። ይህ መግለጫ ቀደም ሲል
ተሰጥቶ ከነበረው መግለጫ በተጨማሪ ነው ማለት ነው። ቀደም ሲል ከአንድ
ሳምንት በፊት ፡-
 የድምጽ መስጫው ቀን መቼ እንደሆነ፣
 የም ርጫ ጣቢያው የሚከፈትበትና የሚዘጋበት ሰዓት፣
ሰዓት
 የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ ይዘው መምጣት እንዳለባቸው፣
 የምርጫው ዓይነትና የድምጽ መስጫ ወረቀቱን አይነት፣
 አንድ መራጭ ለስንት እጩ ድምጽ መስጠት እንደሚችል፣
 ድምጽ አሰጣጥ፣ ድምጽ ቆጠራ እና የውጤት አገላለጽ ሂደትን ፣
 ወደ ምርጫ ጣቢያ ማስገባት የተከለከሉ ቁሳቁሶች ምን እንደሆኑ፣
 ለየምክር ቤቱ የቀረቡ የእጩዎች ዝርዝር፣ የወከላቸውን ድርጅት፣
የመወዳደሪያ ምልክቶችን…ወዘተ ከሚሉት በተጨማሪ ነው።
05/01/20 29
የድምጽ አሰጣጥ…/የቀጠለ/
ከገለጻ በኋላም ከሁለቱ መዝገቦች በአንዱ በየመዝገባቸው
እየተፈለጉ እና እየፈረሙ ድምጽ መስጫ ወረቀት ተሰጥተው
መምረጥ ይኖርባቸዋል ማለት ነው።
 ድምጽ የሚሰጠው ከጠዋቱ 12 እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት
ይሆናል።
 በድምጽ አሰጣጥ ሂደት የምርጫ ጣቢያ ደህንነት ከማስከበር
እስከ አለመግባባቶች መፍታት ሰፊ ስራ ይሰራል።
 ድምጽ ስለመስጠቱ አከራካሪ የሆነ ሰው ድምጽ እንዲሰጥ
ከፍርድ ቤት ውሳኔ እስኪያ መጣ ድረስ ጊዜያዊ ድምጽ
ይሰጣል። (ድምጽ ማዳመሩ እስኪጠናቀቅ ምላሽ ማምጣት አለበት ያለበለዚያ ውድቅ
ይደረጋል።)
05/01/20 30
….ቆጠራ እና
ውጤት አገላለጽ /የቀጠለ/
 ድምጽ መቁጠር ከመጀመሩ በፊት የድምጽ መስጫ ሳጥኑ
ወደስራ ሲገባ እንደነበረበት ሁኔታ መሆኑን የህዝብ ታዛቢዎች
እና ወኪሎች ባሉበት ማረጋገጥ፣
 በየተግባሩ መጨረሻ ቃለጉባኤ የሚያቀዝበት ተግባር ሲሆን
በመቀጠል ድምጽ መስጫውን በመዘርገፍ በየአይነቱ
ይመደባል እና/ ወይም ይቆጠራል።
 ሲቆጠር፡-
 የተበላሸ፣
 ትክክለኛ ድምጽ የተሰጠበት (በየእጩዎቹ)፣
 ጥቅም ላይ ያልዋል፣
ያልዋል
 ዋጋ አልባ የሆነ የድምጽ መስጫዎች ተለይተው በምርጫ
አስፈጻሚዎች ይቆጠራሉ።
05/01/20 31
የምርጫ አለመግባባት እና
ቅሬታ አፈታት በኢትዮጵያ 

በምርጫ ሂደት አለምግባባቶች በተለያዩ


ምክንያቶች የሚከሰቱ ሲሆን እነዚህን
አስቀድሞ ማወቅ ለመፍትሄው ለመዘጋጀትም
ያግዛል።

05/01/20 32
ከምርጫ በፊት የሚከሰቱ
አለመግባባቶች መንስኤዎች
የምርጫ የህግ ማእቀፎች አለመኖር፣
በህግ ድንጋጌዎች ላይ ቅሬታ መኖር፣
ፓርቲዎችና እጩዎች የሚከተሉት የምርጫ ቅስቀሳ
ስትራቴጂ በልማት በgovernance ላይ የተመሰረተ
ቅስቀሳ አለማድረግ /ግጭት ቆስቋሽነት/
ፍትሃዊ የሆነ የውድድር ሜዳ አለመኖር ፣
የፋይናንስ ድጋፍና የሚዲያ አጠቃቀም ፣
በመራጮች፣ በእጩዎች እና በፖለቲካ ፓርቲዎች መብት
ላይ መሰናክል መፍጠር፣
05/01/20 33
ከምርጫ በፊት
የሚከሰቱ……(የቀጠለ)
 ህግን ተከትሎ አለመንቀሳቀስና የቅሬታ መከላከያና ማስተናገጃ
ስርአት አለመዘርጋት ወይም አለመግባባቶችን አለመፍታት
 የምርጫ ክልሎች አከላለል፣
 የመራጮችና የእጩዎች አመዘጋገብ በአግባቡ አለማከናወን
 በመርሃ ግብሮች፣ በህግ ማሻሻያዎች…ወዘተ ላይ የጋራ መግባባት
አለመፈጠር፣
 ፈጣንና ፍትሃዊ ፍትህ አለማግኘት፣
 በምርጫ አስፈጻሚ ምልመላና ሹመት ላይ መግባባት
አለመፍጠር /ተቀባይት እና ብቃት ያለው ገለልተኛ የምርጫ
አስፈፃሚ አለመኖር/
 ለመንግስት ተቋማት እውቅና አለመስጠት ፣
 ነፃና ተቀባይነት ያለው ምርጫ ማደራጀትና ማካሄድ አለመቻል፣
 ሚዛናዊ ያልሆነ የሚዲያዎች ዘገባ ፣
05/01/20 34
በምርጫ ቀን የሚከሰቱ
ለምርጫ አለመግባባቶች መንስዔ
መራጮችን፣ እጩዎችን፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን የእጩ
ወኪሎችንና ምርጫ አስፈፃሚዎችን ማዋከብ፣
ግልፅና ህግን የተከተለ የድምፅ አሰጣጥ ቆጠራ አለመኖር፣
ድምፅ መግዛት፣
መግዛት
የም/አስፈፃሚዎች ስነምግባርና የቅሬታዎች አፈታት ችግር ፣
የፀጥታ አካላት ሚና ገለልተኛ አለመሆን
የእጩዎች የወኪሎችና የታዛቢዎች ጣልቃገብነት፣
የምርጫ ቁሳቁሶችን በወቅቱ አለማቅረብ
የምርጫ ወረቀቶችና ሳጥኖች ጥበቃ አለመደረግ ፣

05/01/20 35
ከምርጫ በኋላ የሚፈጠሩ
ለምርጫ አለመግባባቶች መንስዔ
የድምጽ ቆጠራና ማዳመር
የምርጫ ውጤትን በወቅቱ አለመግለፅ፣ በፀጋ
አለመቀበል ወይም በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት
አለመፈለግ
የቅሬታ ማስተናገጃ ተቋማት ሚና፣
የምርጫ አስፈፃሚዎችና የፍትህ አካላት ተግባራት፣
የምርጫ ግድፈቶችና የህግ ጥሰቶች፣
የምርጫ ታዛቢዎች እና የሚዲያዎች ስነምግባር፣
ባለድርሻ አካላትን በጥቅም መደለል፣
የፍርድ ሂደት መዘግየት/መጓተት/፣
05/01/20 36
V. የምርጫ አለመግባባቶችና
ቅሬታዎች አፈታት በኢትዮጵያ
የአፈታት ዘዴዎች /ስልቶች/
 

◦ የምርጫ ቅሬታዎችን ማቅረብ ስለሚችሉ እና


ስለሚያስተናግዱ አካላት
◦ የምርጫ አለመግባባቶችን ለመፍታት በኢትዮጵያ
የተዘረጉ
አደረጃጀቶችና አሰራሮች
◦ በየደረጃው ስለሚኖሩ አቤቱታ ሰሚ አካላት/ ቦርዱ፣
የክልል ቅ/ጽ/ቤት አቤቱታ ሰሚ፣ የምርጫ ክልል አቤቱታ
ሰሚ፣ በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች/
05/01/20 37
አለመግባባቶች እና
ቅሬታዎች አፈታት …/ የቀጠለ/
በምርጫ ሂደቶች የሚነሱ አለመግባባቶች
የሚፈቱበት ስርአት
◦ አቤቱታ ማቅረብ ስለሚችሉ አካላት
- መራጭ፣ እጩ፣ የፖለቲካ ፓርቲ፣ ወኪል፣
◦ ስለ አቤቱታ አቀራረብ
- በጽሁፍ መቅረብ ይኖርበታል። (የማስረጃነት
ፋይዳም ስላለው።)

05/01/20 38
አለመግባባቶች እና
ቅሬታዎች አፈታት …/ የቀጠለ/
ሀ. በመራጮች ምዝገባ የሚከሰት አለመግባባት
1. ከመራጭነት የሚያግድ ሁኔታ ያጋጠመው ሰው ወይም አንድ ሰው
ያለአግባብ ተመዝግቧል የሚል ተቃውሞ - ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ
ሰሚ ኮሚቴ በጽሁፍ ሲቀርብ በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል። ውሳኔ
ካልተሰጠ ተከለከልኩ ባይ ሲሆን እንደተመዘገበ ይቆጠራል።
2. ይሁን እንጂ ያለአግባብ ተመዝግቧል ባይ ለም/ክልል አቤቱታ ሰሚ
ኮሚቴ በ48 ሰዓት ውስጥ ያቀርባል።

05/01/20 39
አለመግባባቶች እና
ቅሬታዎች አፈታት …/ የቀጠለ/
4. የምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የወሰነውን
በመቃወም የሚቀርብ ይግባኝ ከሆነ ውሳኔው በተሰጠ
በ48 ሰዓት ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል። የም/ክልል
(ይግባኝ ሰሚው ) ኮሚቴ በደረሰው በ24 ሰዓት ውስጥ
ውሳኔ መስጠት ይኖርበታል። ምላሽ ካልሰጠ
እንዳልመዘገብ ተከለከልኩ ባዩ ከሆነ ጥያቄው
እንደተመለሰለት ተቆጥሮ ይመዘገባል።
5. በመራጭነት መመዝገብ ተከለከልኩ ባይም ሆነ
ያለአግባብ ተመዘገበ የሚለው ሰው ምርጫ ክልሉ
አቤቱታ ሰሚ ይግባኙን ምላሽ በሰጠ በ24 ሰዓት ውስጥ
ለወረዳው ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀርባል።
 የወረዳው ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻው ይሆናል።
05/01/20 40
አለመግባባቶች እና
ቅሬታዎች አፈታት …/ የቀጠለ/
ለ. በእጩ ምዝገባ ሂደት ስለሚቀርብ ክርክር
 ማንኛውም በእጩነት ከመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ያጋጠመው ሰው
ወይም አንድ ዕጩ በዕጩነት መቅረብ የለበትም የሚል ተቃውሞ
ያለው ሰው ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታውን
ማቅረብ ይችላል፡፡
 አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴውም የቀረበለትን አቤቱታ መርምሮ በ24
ሰዓት ውስጥ ውሳኔ መሰጠት ይጠበቅበታል፡፡
 በ24 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ካልሰጠ በእጩነት ከመመዝገብ የሚያግድ
ሁኔታ ያጋጠመው ሰው ሲሆን ኮሚቴው በአቤቱታ አቅራቢው ጥያቄ
እንደተስማማ ይቆጠራል፡፡

05/01/20 41
አለመግባባቶች እና
ቅሬታዎች አፈታት …/ የቀጠለ/

 ለአቤቱታ አቅራቢውም ይህንኑ የሚገልፅ ማስታወሻ


ይሰጠዋል፡፡ ተቃውሞ የቀረበበትም በእጩነት ይመዘገባል፡፡
 አቤቱታው አንድ ሰው በእጩነት መቅረብ የለበትም የሚል
ተቃውሞ ሲሆን ደግሞ አቤቱታ አቅራቢው በ72 ሰዓት
ውስጥ ለክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ
ኮሚቴ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል፡፡
 ለክልል እና ለፌዴራል ምክር ቤት - የወረዳ

ለከተማና ለወረዳ -ቀበሌ
 ለቀበሌ ምክር ቤት -ጎጥ ለእጩ ምዝገባ ምርጫ ክልል ይባላሉ።

05/01/20 42
ሐ. በድምጽ አሰጣጥ
ስለሚነሱ ክርክሮች
 አንድ መራጭ ድምጽ ከመስጠት የሚያግደው ሁኔታ ሲፈጠር ወይም
በመራጭነት መብቱ ላይ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቅሬታውን ወዲያውኑ
ለምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ ይችላል፡፡ ኮሚቴውም
ጊዜያዊ ድምጽ እንዲሰጥ በማድረግ ጉዳዩን ወደ ምርጫ ክልሉ
አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በመላክ ውሳኔ እንዲያገኝ ሊያደርግ ይችላል
ወይም ጊዜያዊ ድምጽ መስጠት የለበትም ብሎ ሊወስን ይችላል፡፡
 በምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የተሰጠውን ውሳኔ
በመቃወም ለምርጫ ክልሉ የሚቀርብ አቤቱታ የድምጽ መስጫ
ሰዓት ከማለቁ በፊት ውሳኔ ማግኘት ይኖርበታል፡፡
 በኮሚቴ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ጊዜያዊ ድምጽ መስጠት የተከለከለ
ሰውም ይግባኙን ወዲያውኑ ለወረዳው ፍርድ ቤት ማቅረብ
አለበት፡፡
05/01/20 43
በድምጽ አሰጣጥ ስለሚነሱ
ክርክሮች…../የቀጠለ/
 ፍርድ ቤቱም የድምጽ መስጫው ሰዓት ከመጠናቀቁ በፊት የመጨረሻ ውሳኔ
ሊሰጥ ይገባል፡፡
 ከምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ወይም ከወረዳው ፍርድ ቤት
የመምረጥ መብት እንዳለው የሚገልጽ ውሳኔ የተሰጠው ጊዜያዊ ድምጽ
የሰጠ መራጭም የድምጽ ማዳመሩ ከመጠናቀቁ በፊት ለምርጫ ክልሉ ካላቀረበ
የሰጠው ጊዜያዊ ድምጽ ውድቅ ይደረጋል፡፡
 ጊዜያዊ ድምጽ መስጠት የለበትም የተባለ ይግባኝ አቅራቢ በምርጫ
ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ወይም በወረዳው ፍርድ ቤት ድምጽ
እንዲሰጥ ከተወሰነ፣ የድምጽ መስጫ ሰዓት ከመጠናቀቁ በፊት ለምርጫ
ጣቢያው ውሳኔውን ካላቀረበ ድምጽ ሊሰጥ አይችልም፡፡ ይሁን እንጂ የምርጫ
ጣቢያው ተዘግቶ እና በምርጫ ጣቢያው ቅጥር ግቢ ውስጥ የተሰለፉ
መራጮች ድምጽ በመስጠት ላይ ባሉበት ጊዜ ውሳኔውን ይዞ ከደረሰ
እንዲመርጥ ይደረጋል፡፡
05/01/20 44
መ. በቆጠራ እና በውጤት
….ስለሚነሱ ክርክሮች
 በድምጽ ቆጠራ ሂደትና በውጤት ላይ ቅሬታ ያለው እጩ ወይም ወኪል
ቅሬታውን ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አስመዝግቦ
አቤቱታውን በ48 ሰዓት ውስጥ ለምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ከመረጃ
ጋር አያይዞ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 ይሁን እንጂ በምርጫ ጣቢያ ካስመዘገበው ጭብጥ ውጪየሆነ አዲስ
ነገር ማቅረብ አይችልም፡፡
 የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴም የቀረበለትን አቤቱታ እና
ማስረጃ መርምሮ በ48 ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ውሳኔውም
ቅሬታ የቀረበበት ቆጠራ እንደገና እንዲካሄድ፣ ቆጠራው ትክክል ስለሆነ
ቅሬታው አግባብነት የለውም ወይም ቅሬታ የቀረበበት ቆጠራ የምርጫ ክልሉን
አጠቃላይ ውጤት በመሰረቱ የማይለውጠው ከሆነ ድጋሚ ቆጠራ ማካሄድ
አያስፈልግም የሚል ሊሆን ይችላል፡፡ አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነበትን ሌላ
ውሳኔም በሕግ መሰረት ሊወስን ይችላል፡፡ 
05/01/20 45
መ. በቆጠራ እና በውጤት
አገላለጽ …/የቀጠለ/
 የምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በሰጠው ውሳኔ ቅር
የተሰኘ አቤቱታ አቅራቢ ውሳኔ በተሰጠው በ5 ቀን ውስጥ
ይግባኙን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቅረብ ይችላል፡፡ ቦርዱም
የቀረበውን ይግባኝ መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
 ይግባኝ ባዩም ቦርዱ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም በ5 ቀን
ውስጥ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይችላል፡፡
ፍርድ ቤቱም ለቀረበለት ይግባኝ በተቻለ ፍጥነት ውሳኔ
መስጠት ያለበት ሲሆን ውሳኔውም የመጨረሻ ይሆናል፡፡

05/01/20 46
….የክርክሮች አፈታት /የቀጠለ/
አቤቱታ ማቅረብ ስለሚችሉ አካላት
 በመራጭነት ወይም በእጩነት በመመዝገብ የሚያግድ
ሁኔታ ያጋጠመው ሰው ወይም ፓርቲ፣
አንድ ሰው በመራጭነት ወይም በእጩነት ያለአግባብ
ተመዝግቧል የሚል ተቃውሞ ያለው ሰው ወይም ፓርቲ፣
ድምጽ ከመስጠት የሚያግደው ሁኔታ የተፈጠረበት
መራጭ፣
በድምጽ ቆጠራ ሂደትና በውጤት ላይ ቅሬታ ያለው ፓርቲ
ወይም የግል ዕጩ ወይም ወኪል አቤቱታውን በጽሑፍ
ማቅረብ ይችላል፡፡
05/01/20 47
….የክርክሮች አፈታት /የቀጠለ/

አቤቱታ ማቅረብ የማይችሉ አካላት


ማንኛውም ፡
ታዛቢ፣
መራጮችን ለማስተማር ፈቃድ ያገኘ አካል ወይም
 ጋዜጠኛ
የምርጫውን ሂደት አስመልክቶ አቤቱታ ማቅረብ
አይችልም፡፡  
05/01/20 48
የምርጫ አስፈጻሚዎች ስነምግባር ፣
አስፈላጊነት እና የህግ መሰረት
አስፈጻሚዎች ከየምርጫ ክልሉ ወይም ከየምርጫ ጣቢያው
የሚመለመሉ ሲሆን ማንኛውም ምርጫ አስፈጻሚ፡-
 ኢትዮጰያዊ መሆን የሚገባው ሲሆን በአካባቢው ነዋሪ መልካም
ስነምግባር እንዳለው የተመሰከረለት እና አመኔታን ያተረፈ መሆን
ይገባዋል:-
 ለህገመንግስቱ ታማኝ ፣
 ከፖለቲካ ፓርቲዎች ወገንተኝነት ነጻ ፣
 በማንኛውም የህዝብ ምክር ቤት ያልተመረጠ እንዲሁም
 በመንግስት አስተዳደር ያልተሾመ መሆን የሚገባው መሆን ይገባዋል።

05/01/20 49
ሁሉም የምርጫ አስፈጻሚዎች
ሊከተሏቸው ስለሚገቡ የስነምግባር
መርሆዎች
 የህግ የበላይነትን ማክበር
 ከአድልኦ የጸዳ አገልግሎት መስጠት
 ምስጢር መጠበቅ
 በግልጽነት፣ በሀቀኝነት እና በቅልጥፍና ላይ
የተመሰረተ አገልግሎት መስጠት
 ከሙስና የጸዳ፣ የጥቅም ግጭት ያስወገደ እና
ታማኝ ሆኖ መገኘት
05/01/20 50
የምርጫ ክልል የምርጫ
አስፈጻሚዎች ስነምግባር
እላይ ከተገለጹት አጠቃላይ የስነምግባር መርሆዎች
በተጨማሪ የምርጫ ክልል የምርጫ አስፈጻሚዎች
በራሳቸው ደረጃ ሊያከብሩና ሊያስከብሩት የሚገባቸው
ስነምግባር እንዳለ ለመመልከት ይቻላ፡-
ይኸውም የምርጫ ክልል ምርጫ አስፈጻሚዎች ፡-
የእጩነት መመዘኛ ያሟላን ብቻ መመዝገብ ይኖርበታ፤
በምርጫ ሂደት ከማንኛውም ወገን የሚቀርቡ ተገቢ ጥያቄዎች ፣
ጥቆማዎች እና ቅሬታዎች ተገቢውን ውሳኔ በወቅቱ መስጠት
ይኖርባቸዋል።

05/01/20 51
የምርጫ ጣቢያ የምርጫ
አስፈጻሚዎች ስነምግባር
 የምርጫ ጣቢያ የምርጫ አስፈጻሚዎች ከላይ ከተገጹ የስነምግባር መርሆዎች
በተጨማሪ እነርሱ ማክበር እና ማስከበር ያለባቸው የስነምግባር ድንጋጌዎች አሉ።
እነዚህም የምርጫ ጣቢያ ምርጫ አስፈጻሚ ፡-
 የህዝብ ታዛቢዎችን በህጉ መሰረት ብቻ የሚያስመርጡ ሲሆን ከህዝብ ታዛቢዎች
የሚቀርቡ አስተያየቶችን ተቀብለው እንዳግባብነቱ በስራ ላይ ማዋል፣ በደረጃቸው
የሚቀርቡ ቅሬታዎችነ ተቀብለው በአግባቡ ማስተናገድ ይጠበቅበታል፤
 እሽግ የምርጫ ቁሳቁሶችን የሚመለከታቸው ሳይኖሩ
አለመክፈት፣የሚመለከታቸው አካላት መርምረው የሰጡትን ውሳኔ ተቀብሎ
ማስፈጸም ይኖርበታል፤
 በህግ የመራጭነት መመዘኛ የማያሟላን አለመመዝገብ፣አንድን በግንባር የቀረበ
መራጭ አንድ ጊዜ እና አንድ ቦታ ብቻ እንዲመዘገብ በማድረግ የመራጭነት
መታወቂያ መስጠት የሚኖርባቸው ሲሆን ለአርብቶ አደሩ አካባቢ ቦርዱ
ካቋቋማቸው ተንቀሳቃሽ ምርጫ ጣቢያዎች በስተቀር የመራጮች ምዝገባ
ከምርጫ ጣቢያ ውጪ ቤት ለቤት ማከናወን የለባቸውም፤
የለባቸውም
05/01/20 52
የምርጫ ጣቢያ የምርጫ
አስፈጻሚዎች ስነምግባር
 በመራጭነት ያልተመዘገቡ ወይም አግባብነት ያለው የመራጮች መታወቂያ
ካርድ ያልያዙ እና ድጋሚ ድምጽ ለመስጠት ለሚቀርቡ ሰዎች እንዲመርጡ
ማድረግ ወይም አግባብነት ያለው ሰነድ ያሟሉ እንዳይመርጡ ማድረግ
የለባቸውም፤
 የሁሉም እጩዎች ፎቶግራፍ እና ምልክት በእኩልነት እና በግልጽ ህዝቡ
እንዲያውቃቸው ማድረግ የሚኖርባቸው ሲሆን ለመራጩ ማብራሪያ
በሚሰጡበት ጊዜ በምንም አይነት ሁኔታ አድሏዊ ገለጻ ማድረግ የለባቸውም፤
 መራጮች ማንን እንደመረጡ ወይም እንደሚመርጡ መጠየቅ ወይም
ማስፈራራት ወይም ማግባባት የለበትም፣
 ለድምጽ መስጫ ወረቀቶች ወይም ለድምጽ መስጫ ኮሮጆዎች አግባብነት
ያለው ጥንቃቄ እና ጥበቃ ማድረግ እና በነዚህ ዙሪያ የሚከናወኑ ተግባራት
የህዝብ ታዛቢዎች እና የእጩ ወኪሎች ወይም እጩዎች በሌሉበት መቁጠርም
ሆነ ቁልፍ መፍታት የመሳሰሉትን ተግባራት ማከናወን የለባቸውም።
 ማንኛውም ምርጫ አስፈጻሚ የስነምግባር ድንጋጌዎቹን ያላከበረ ከሆነም በህግ ተጠያቂ
ይሆናል።
05/01/20 53
በምርጫ እንቅስቃሴ የፖሊስ ተቋም እና
አባላት ኃላፊነት

05/01/20 54
በምርጫ እንቅስቃሴ የፖሊስ ተቋም
እና አባላት ኃላፊነት

 የፖሊስ ተቋም መቋቋም ዓላማ፡


 የሀገሪቱን ህገመንግስት ፣ ህገመንግስታዊ
ስርዓቱንና ሌሎች ህጎችን በማክበርና ማስከበር
እንዲሁም ህብረተሰቡን በወንጀል መከላከል እና
ምርመራ በማሳተፍ የህዝቡንና መንግስትን
ሰላምና ደህንነት የመጠበቅና የማረጋገጥ ዓላማን
ለማሳካት ተቋቋመ፡፡

05/01/20 55
በምርጫ እንቅስቃሴ የፖሊስ
….ኃላፊነት /የቀጠለ/
 ኃላፊነት፡
 የኢፌዴሪ ህግመንግስትና ህገመንግስቱን መሰረት
አድርገው የወጡ ህጎችን የማክስከበር ተልእኮውን
በብቃት በመወጣት የዴሞክራሲ ስርዓት
ለመገንባት፣ ሰላምን ለማስፈንና ልማትን
ለማፋጠን የበኩሉን ድርሻ መጫወት፣

05/01/20 56
በምርጫ እንቅስቃሴ የፖሊስ
….ኃላፊነት /የቀጠለ/
 መርህ
 ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ የሆነ ህብረተሰቡን
በእኩልነት የማገልገል፣ የፖሊሳዊ ስነምግባርሩ የታነጸና
ብቃትና ጥራት ያለው ነው፡፡
 የምርጫ ክልሉ ኃላፊ ምርጫውን በሰላማዊ እና ህጋዊ መንገድ
ለማከናወን አስፈላጊ በሆነ መጠን የፖሊስ ኃይል ትብብር
ሊጠይቅ ይችላል፡፡ /የም/ህግ ቁ.532/1999 አንቀጽ 90/
90
 የመንግስት ሰራተኛ በግሉ/ በፖለቲካ ፓርቲ አቅራቢነት
ሊወዳደር ይችላል። ሆኖም ዳኛ፣ ወታደር፣ ፖሊስ በሆነ ጊዜ
በእጩነት ለመቅረብ ከመንግስት ስራው መልቀቅ ይኖርበታል።
/ ህገመንስት አንቀጽ 47/2//
05/01/20 57
በምርጫ እንቅስቃሴ የፖሊስ
….ኃላፊነት /የቀጠለ/
 “ ….የምርጫ ቦታዎችን ደህንነት የማስከበር ኃላፊነት
ይርጫ ጽህፈት ቤቶቹ ኃላፊዎች ኃላፊነት ነው፡፡ የምርጫ
ጽህፈት ቤቶች ኃለፊዎች ወይም የምርጫ ጣቢያ የህዝብ
ታዛቢዎች /በጣቢያው ኃላፊ አማካኝነት/ የምርጫ
ጣጠቢያውን ደህንነት ለማስከበር ፖሊስ እንደሚያስፈልግ
ካመኑ እንዲመደብላቸው የሚመለከተውን አካል
ለመጠየቅ ይችላሉ ፡፡”
የምርጫ ህግ አዋጅ አንቀጽ 63/4/

05/01/20 58
በምርጫ እንቅስቃሴ የፖሊስ
….ኃላፊነት /የቀጠለ/
የምርጫ ጣቢያው ኃላፊ ከምርጫ ጣቢያው
እንዲወጣ ትእዛዝ ሲሰጠው ትእዛዙን ያላከበረ ሰው
በፖሊስ ኃይል ከምርጫ ጣቢያው እንዲወጣ
ይደረጋል፡፡ፖሊስም ትእዛዙን እንደፈጸመ
ከምርጫ ጣቢያ ወጥቶ ወደ ተመደበለት
ቦታ ይሄዳል ፡፡”
የምርጫ ህግ አዋጅ አንቀጽ 63/5/

05/01/20 59
በምርጫ እንቅስቃሴ የፖሊስ
….ኃላፊነት /የቀጠለ/
 ዳኛ፣ ወታደር እና ፖሊስ በምርጫ ውድድር ጊዜ ማንኛውንም
ተወዳዳሪ ለማስመረጥ በመደገፍ፣ በመናገር፣ በመጻፍ እና
በመሳሰሉት ተሳታፊ አይሆንም፡፡
የምርጫ ህግ አዋጅ አንቀጽ 47/3/
….ፖሊስ ጣቢያዎች የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ እንዲሁም
የመራጮች ምዝገባ ከማይካሄድባቸው ቦታዎች ውስጥ ይገኛሉ ፡፡
/ም/ህግ አንቀጽ 61/1/መ//

05/01/20 60
በምርጫ እንቅስቃሴ የፖሊስ
….ኃላፊነት /የቀጠለ/
 መላው ህዝብ በሰላም በምርጫ እንዲሳተፍ ፣ ምርጫው
ሰላማዊ፣ ነጻ ፣ ዴሞክራሲያዊ እንዲሁም በህዝቡ ተአማኒነት
ያለው ሆኖ እንዲፈጸም የጨዋታው ህግ እንዲከበር፣
በተለይም በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅት እና በድህረ ምርጫ
ባሉ የምርጫ እንቅስቃሴዎች ሰላማዊ እና ደህንነታቸው
የተጠበቀ እንዲሆን ፖሊስ በርካታ ስራ ይጠብቀዋል፡፡
 ስለሆነም በምርጫ ወቅት የፖሊስ ስራ ከመቼውም በላይ፡
 ትእግስት የሚጠይቅ፣
 የስነምግባር ህግጋትን ማክበርና መስከበር የሚጠይቅ፣
 ህግ ማስከበር፣ ጸጥታና ደህንነት የማስከበር፣ ስራ ነው፡፡

05/01/20 61
05/01/20 62

You might also like