You are on page 1of 5

የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ጽ/ቤት

Office of Complaints hearing


ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
committee
ባሕር ዳር-ኢትዮጲያ Bahir Dar University
Bahir Dar - Ethiopia

ቁጥር---------------------

ቀን----------------------

ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ጉዳዩ፡ በቀረበ ቅሬታ ላይ የውሳኔ ሀሳብ ስለማቅረብ

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የስራ ክፍል በዘንዘልማ ግቢ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ባለሙያ ሆኖ
የሚሰራ አቶ አለሙ ሙሉነህ ከፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቁጥር 20/መከ 10/አ 5/351 በቀን 16/02/14 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ
ከባለሙያ 3 ደረጃ 12 ወደ ባለሙያ 4 በደረጃ 14 አድጌ በዘንዘልማ ግቢ ተመድቤ የዩኒቨርሲቲውም የሰው ሃብት አስተዳደር በዚህ መነሻነት
በቁጥር 2/5095/4961 በቀን 20/02/14 ዓ.ም ከላይ የተገለፅወን ምደባ አፅድቆ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም በታሳቢነት፣ከግንቦት 1 ቀን
2014 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ሙሉ በሙሉ መደቡን ስለማሟላ የወር ደመወዜ 9056 (ዘጠን ሺህ ሀምሳ ስድስት ብር) እንዲከፈለኝ ለዘንዘልማ
ግቢ ሒሳብ ክፍል ደብዳቤው ስለደረሰው የአንድ ወር ደመወዝ ብቻ እንደተከፈለኝ እንደገና ደረጃው ተቀንሶ በመጣው ምደባ መሰረት ሁሉም
ሰራተኛ ከደረጃ 14 ወደ ደረጃ 13 የወረደ ቢሆንም የሌሎች ደመወዝ እንዳይቀነስ ታሳቢ በማድረግ ወደጎን ሶስት እርከን ገባ ብሎ
የተመለከተውን 9056 (ዘጠን ሺህ ሀምሳ ስድስት ብር) ሲከፈላቸው የኔ ብቻ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም አሟልቼ ደመወዙም ተከፍሎኝ እያለ
እንደገና ወደኋላ ተመልሶ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በቁጥር 2/15096/4961 በተፃፈ ደብዳቤ 8017 (ስምንት ሺህ አስራ ሰባት ብር
እንዲከፈለኝ በመፃፍ ያለ አግባብ የተቀነሰብኝ ብር 1039 (አንድ ሺህ ሰላሳ ዘጠኝ ብር) እንዲከፈለኝ ሲሉ ለዩኒቨረሲቲው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ
በቀን 29/10/2014 ዓ.ም. አመልክተዋል፡፡ በቀረበው ቅሬታ መሰረት የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው ጉዳዩን በጥልቀት አይቶ የውሳኔ ሀሳቡን በቅሬታ
ሰሚ ኮሚቴ አሰራር መመሪያ መሰረት ከዚህ የመሸኛ ደብዳቤ ጋር አባሪ ተደርጎ በተያያዘው 4 ገጽ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረቢያ ቅጽ በመሙላት
ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አቅርቧል፡፡ በመሆኑም በእርሰዎ በኩል የመጨረሻ የውሳኔ ሃሳብ እንዲሰጡበት በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

ምንይችል ግታው (ዶ/ር)

የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

ግልባጭ//

ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ጽ/ቤት

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረቢያ ቅጽ 002

I. ቀን፡ 27/07/2015 ዓ.ም.


II. የስብሰባ ቦታ፡ ዊዝደም/ጥበብ ሕንፃ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ቢሮ
የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ጽ/ቤት
Office of Complaints hearing
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
committee
ባሕር ዳር-ኢትዮጲያ Bahir Dar University
Bahir Dar - Ethiopia

III.ቅሬታ አቅራቢው
አቶ አለሙ ሙሉነህ
IV. ቅሬታ የቀረበባቸው የስራ ሀላፊዎች፡-
የማዕከላዊና የዘንዘልማ ግቢ የሰው ኃብት አስተዳደር
V. የቅሬታው ጭብጥ፡

ቅሬታ አቅራቢው ያቀረባቸው ጭብጦች፡

ከፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቁጥር 20/መከ 10/አ 5/351 በቀን 16/02/14 ዓ.ም በተፃፈ

ደብዳቤ ከባለሙያ 3 ደረጃ 12 ወደ ባለሙያ 4 በደረጃ 14 አድጌ በዘንዘልማ ግቢ ተመድቤ

የዩኒቨርሲቲውም የሰው ሃብት አስተዳደርም በዚህ መነሻነት በቁጥር 2/5095/4961 በቀን 20/02/14 ዓ.ም

ከላይ የተገለፅውን ምደባ አፅድቆ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም በታሳቢነት፣ከግንቦት 1 ቀን 2014

ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ሙሉ በሙሉ መደቡን ስለማሟላ የወር ደመወዜ 9056 (ዘጠን ሺህ ሀምሳ ስድስት

ብር) እንዲከፈለኝ ለዘንዘልማ ግቢ ሒሳብ ክፍል ደብዳቤው ስለደረሰው የእንድ ወር ደመወዝ ብቻ

እንደተከፈለኝ እንደገና ደረጃው ተቀንሶ በመጣው ምደባ መሰረት ሁሉም ሰራተኛ ከደረጃ 14 ወደ ደረጃ

13 የወረደ ቢሆንም የሌሎች ደመወዝ እንዳይቀነስ ታሳቢ በማድረግ ወደጎን ሶስት እርከን ገባ ብሎ

የተመለከተውን 9056 (ዘጠን ሺህ ሀምሳ ስድስት ብር) ሲከፈላቸው የኔ ብቻ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም

አሟልቸ ደመወዙ ተከፍሎኝ እያለ እንደገና ወደኋላ ተመልሶ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በቁጥር

2/15096/4961 በተፃፈ ደብዳቤ 8017 (ስምንት ሺህ አስራ ሰባት ብር እንዲከፈለኝ በመፃፍ ያለ አግባብ

የተቀነሰብኝ ብር 1039 (አንድ ሺህ ሰላሳ ዘጠኝ ብር) እንዲከፈለን ነው፡፡

VI. በቀረበው ቅሬታ ዙሪያ በኮሚቴው የተሰራ የመረጃ ማሰባሰብ ስራ

ቅሬታ አቅራቢው ባቀረቡት ጭብጥ መሰረት የዩኒቨርሲቲው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ለሚዛናዊ እና ገለልተኛ

ውሳኔ የሚያግዙ የተለያዩ መረጃዎችን ሲሰበስብ ቆይቷል፡፡ መጣራት ያለባቸውን ጉዳዮችም በመለየት ሰፊ

መረጃዎችንና አሰራሮችን መርምሯል፡፡ ዋና ዋና ትኩረት ያደረገባቸው ጉዳዮችም እንደሚከተለው

ቀርበዋል፡-

1. ባለጉዳዩ ያቀረባቸው ሰነዶችና ምደባው በተገለፀው ወቅት መከናወኑንና አለመከናወኑን?


የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ጽ/ቤት
Office of Complaints hearing
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
committee
ባሕር ዳር-ኢትዮጲያ Bahir Dar University
Bahir Dar - Ethiopia

2. የተፃፉት ደብዳቤዎች ከህግ አንፃር ትክክል መሆን አለመሆናቸውን?

3. ማንኛውም የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ በታሳቢነት ተመድቦ የሚያሟላበት ጊዜ ሳይደርስ ምደባውን

የሚሽር መመሪያም ሆነ ደንብ ከመጣ ደመወዙን ማስቀነስ ይችላል አይችልም?

4. አንድ መመሪያ ወደኋላ ተመልሶ የተከናወነ ድርጊትን ይሸራል አይሽርም?

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ጭብጦች ለማጣራት እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማሰባሰብ የሚከተሉትን

ተግባራት አከናውኗል፡-

 ቅሬታ አቅራቢውን በአካል በማስቀረብ ስለጉዳዩ ዝርዝር ማብራሪያ የማግኘት ተግባር

አከናውኗል

 ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የስራ ኃላፊዎች በተለያዩ ጊዜያት በአካልና በስልክ በማናገር

የቅሬታውን መነሻነና ምንነት የመገንዘብ ተግባር ተከናውኗል


 ባለጉዳዩ ያቀረባቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ለህግ ክፍል በማቅረብ ቅሬታ ያስነሳውና
የታየው ክፍተት ምን ያህል እንደሆነ ግንዛቦ ወስዷል
 የቅሬታ አቅራቢውን ደመወዝ ያስቀነሰው ደብዳቤ ሲፃፍ እንደመነሻ የተጠቀሰው ሚያዚያ
20 ቀን 2014 ዓ.ም የተፃፈውን ደብዳቤ ለማግኘት ብዙ ጥረት በማድረግና በዩኒቨርሲቲው
ፕሬዘዳንት ኢሜል አድራሻ በማፈላለግ ሙሉ መረጃዎችን የመሰብሰብ ተግባር ተከናውኗል

በቀረበው ቅሬታ ዙሪያ በኮሚቴው የተሰራ የመረጃ የመተንተን ስራ

ባለጉዳዩ ያቀረባቸው ሰነዶች በጥልቀት የመመርመር ተግባርና ምደባው በተገለፀው ወቅት መከናወኑን

አረጋግጧል፤የተፃፉት ደብዳቤዎች ከህግ አንፃር ትክክል መሆን አለመሆናቸውን ለማጣራት የኮሚቴው

ተወካይ አቶ ታዬ ከህግ ክፍል ጋር በመወያየት ስለጉዳዩ ግንዛቤ የማግኘት ስራ ተሰርቷል፤ ማንኛውም

የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ በታሳቢነት ተመድቦ የሚያሟላበት ጊዜ ሳይደርስ ምደባውን የሚሽር መመሪያም

ሆነ ደንብ ከመጣ ደመወዙን ማስቀነስ ይችላል አይችልም በሚለው ዙሪያ ኮሚቴው በሰፊው ተወያይቶ

የሚያሟላበት ጊዜ ሳይደርስ ምደባውን የሚሽር መመሪያም ሆነ ደንብ ካለ ያንን መነሻ በማድረግ

በታሳቢነት ያለው አሟልቶ ከተመደበው እኩል እንደማይሆን ተገንዝቧል፤አንድ መመሪያ ወደኋላ ተመልሶ

የተከናወነ ድርጊትን ስለመሻሩ የሚያመላክት መመሪያም ሆ ደንብ ሳይኖር ሚያዚያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ጽ/ቤት
Office of Complaints hearing
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
committee
ባሕር ዳር-ኢትዮጲያ Bahir Dar University
Bahir Dar - Ethiopia

የተፃፈ ደብዳቤ መነሻ ሆኖ የባለ ጉዳዩን ደመወዝ የሚቀንስ ደብዳቤ ደግሞ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ደመወዝ ከተከፈለው በኋላ መፃፉ የዩኒቨርሲቲው ክፍተት መሆኑን ኮሚቴው ተስማምቷል፡፡

በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ

ኮሚቴው ግራ ቀኙን ከተመለከተ በኋላ ቅሬታ አቅራቢው ያቀረበው ጥያቄ ተገቢ መስሎ ቢታይም

ማንኛውም የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ በታሳቢነት ተመድቦ እያለ የሚያሟላበት ጊዜ ሳይደርስ ምደባውን

የሚሽር ደብዳቤ ሚያዚያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም እንደተፃፈ ባለጉዳዩ የሚያሟላበት ግንቦት 1 ቀን 2014

ዓ.ም ሳይደርስ ደብዳቤው መፃፍ ሲገባው ዘግይቶ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም መፃፉ የዩኒቨርሲቲው የሰው

ኃይል አስተዳደር ክፍተት መሆኑን ተገንዝቦ ቅሬታ አቅራቢው ግን በታሳቢነት ስለተመደበ ክፍያው

እንደማይገባው ወስኗል፡፡

የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ስምና ፊርማ

i. ምንይችል ግታው (ዶ/ር) ሰብሳቢ …………………………


ii. አቶ ታዬ ምናለ………………………አባል …………………………..
iii. አቶ አግንቸው ነጋ…………………….አባል …………………………..
iv. ወ/ሮ ሙሉጎጃም አንዷለም…………….አባል …………………………
v. አቶ አስማማው ወርቁ…………. ……..ፀሀፊ ……………………………

V. በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አስተያዬት

…………………………………………………………………………………………………
…………………………………………………………………………………………………
…………………………………………………………………………………………………
…………………………………………………………………………………………………
…………………………………………………………………………………………………
…………………………………………………………………………………………………
የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ጽ/ቤት
Office of Complaints hearing
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
committee
ባሕር ዳር-ኢትዮጲያ Bahir Dar University
Bahir Dar - Ethiopia

…………………………………………………………………………………………………
…………………………………………………………………….

ሥም፡………………………………… ፊርማ ……………………. ቀን…………………

You might also like