Professional Documents
Culture Documents
236987
236987
የሰ/መ/ቁ. 236987
ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም
ዲኞች፡-
ተፈሪ ገብሩ (ድ/ር)
እንዲሻዉ አዲነ
ተሾመ ሽፈራዉ
መሊኩ ካሳዬ
ነፃነት ተገኝ
አመሌካች፡ ወ/ሮ አይናሇም ሃና ፊቃደ
ተጠሪ፡ ወ/ሮ ረምሊ ሳቢር
መዝገቡ ተመርመሮ ተከታዩ ፍርዴ ተሰጥቷሌ፡፡
ፍ ር ዴ
ይህ ጉዲይ የዉርስ ክርክርን የሚመሇከት ሲሆን፣ ክርክሩ በተጀመረበት በፌዳራሌ የመጀመሪያ ዯረጃ
ፍርዴ ቤት የአሁኗ አመሌካች ባቀረቡት ክስ የሟች ወሊጅ አባቴ የዉርስ ንብረት እንዱጣራ ዲኝነት ጠይቄ
በመ/ቁጥር 43370 ሊይ የዉርስ ሀብት ተጣርቶ የተወሰነ ቢሆንም፣ በጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ እሪንዛፍ
ክ/ከተማ ቀበላ 05 ክሌሌ ዉስጥ ሌዩ ስሙ ሀቱ ተብል በሚጠራዉ መንዯር ዉስጥ አዋሳኙ የተጠቀሰዉን
ሟች አባቴ ሇሰርግ መናፈሻ አገሌግልት እንዱዉሌ ይዞት ቤትና የተሇያዩ አትክሌቶች ያለበት ስፋቱ በግምት
8000 ካ/ሜትር ይዞታ ተጠሪ በመዯበቋ ሳይጣራ የታሇፈ መሆኑን ጠቅሰዉ በዉርስ አጣሪ ይጣራሌኝ በሚሌ
የጠየቁትን ዲኝነት መነሻ ያዯረገ ነዉ፡፡ ተጠሪ በበኩሊቸዉ የመጀመሪያ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር ክርክር
ያቀረቡ ሲሆን፣ በመጀመሪያ መቃወሚያነት ያቀረቡት መሌስ ይዘትም ጉዲዩ በመ/ቁጥር 43370 ሊይ ዉሳኔ
ያገኘ በመሆኑ ክሱ በዴጋሚ የቀረበ ነዉ የሚሌ ነዉ፡፡
ፍርዴ ቤቱም በቀረበዉ የመጀመሪያ መቃወሚያ ሊይ የግራ ቀኝ ክርክር ከሰማ በኋሊ ሇክርክሩ መነሻ
የሆነዉ መሬት እንዱጣራ በአመሌካች እና በላልችም ወራሾች በቀረበ አቤቱታ መነሻነት የዉርስ ንብረት
ተጣርቶ ጥቅምት 19 ቀን 2007 ዓ.ም የዉርስ አጣሪ ሪፖርት የቀረበ መሆኑን፣ በወቅቱም ሇዚህ ክርክር
መነሻ የሆነዉ ይዞታ የሟች መሆኑ በማስረጃ አሌተረጋገጠም በሚሌ በዉርስ አጣሪ ሪፖርቱ የተገሇጸ ሲሆን
ሪፖርቱም ጉዴሇት የሇበትም ተብል በፍርዴ ቤት የጸዯቀ ሲሆን በይግባኝ አሇመሻሩን ጠቅሶ አመሌካች
ያቀረቡት ክስ በዴጋሚ የቀረበ ነዉ በማሇት በብይን ዉዴቅ በማዴረግ ወስኗሌ፡፡ አመሌካች በዚህ ዉሳኔ
ባሇመስማማት ሇፌዳራሌ ከፍተኛ ፍርዴ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም፣ ከፍተኛ ፍርዴ ቤቱ የይግባኝ
መዝገቡን አስቀርቦ የግራ ቀኝ ክርክር ከሰማ በኋሊ የስር ፍርዴ ቤቱን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗሌ፡፡
አመሌካች ህዲር 03 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ከዚህ በፊት በመ/ቁጥር
43370 ሊይ የጸዯቀዉ የዉርስ አጣሪ ሪፖርት ሊይ ዉርስ አጣሪዉ ሇክርክሩ መነሻ የሆነዉን ይዞታ
በተመሇከተ የዉርስ አጣሪዉ ማስረጃ ማግኘት አሇመቻለን ገሌፆ ባቀረበዉ ሪፖርት ሊይ ፍርዴ ቤቱ ምንም
አስተያየት ሳይሰጥበት ያሇፈ ሲሆን፣ በላሊ በኩሌ አንዴ ጉዲይ በዴጋሚ የቀረበ ነዉ ሇማሇት የሚቻሇዉ
በማስረጃ ተጣርቶ ዉሳኔ የተሰጠበት መሆን እንዲሇበት እና በተያዘዉ ጉዲይ በዉርስ ማጣራት ወቅት ፍርዴ
ቤቱ አጣርቶ ዉዴቅ ባሊዯረገበት ሁኔታ ዉሳኔ አርፎበታሌ ሇማሇት የሚቻሌበት ሁኔታ በላሇበት ክሱ
በዴጋሚ የቀረበ ነዉ በሚሌ በስር ፍርዴ ቤቶች የተሰጠ ዉሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ታርሞ ይወሰንሌኝ በማሇት ዲኝነት ጠይቀዋሌ፡፡
የሰበር አቤቱታዉም በአጣሪ ችልት ተመርምሮ የዉርስ አጣሪ ሇክርክሩ መነሻ የሆነዉን ይዞታ
በተመሇከተ የቀረበ ማስረጃ የሇም በማሇት ያሇፈዉን የመጨረሻ ዉሳኔ እንዯተሰጠበት ተዯርጎ ክሱ በዴጋሚ
የቀረበ ነዉ በሚሌ ዉዴቅ የመዯረጉን አግባብነት ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ሇመወሰን ሲባሌ ያስቀርባሌ
በመባለ፣ ተጠሪ መሌስ እንዱያቀርቡ በተዯረገሊቸዉ ጥሪ መሠረት የካቲት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በተፃፈ
መሌስ የአመሌካች አቤቱታ ዉዴቅ ሉዯረግ ይገባሌ የሚለባቸዉን ምክንያቶች በዝርዝር በመጥቀስ
ተከራክረዋሌ፡፡
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባሇ መሌኩ ሲታይ ከፍ
ሲሌ የተመሇከተዉን ሲመስሌ ይህ ችልትም የሟች የዉርስ ሀብት ተጣርቶ ባሇበት ሁኔታ አመሌካች
ያቀረቡት የዲግም የዉርስ ይጣራሌኝ ዲኝነት ተቀባይነት ያሇዉ መሆን አሇመሆኑን በጭብጥነት በመያዝ
ከግራ ቀኝ ክርክር እና ሇጉዲዩ አግባብነት ካሊቸዉ ዴንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገገቡን እንዯሚከተሇዉ
መርምሮታሌ፡፡ እንዯመረመረዉም የሟች አቶ ፍቃደ ሰሴሮ የዉርስ ሀብት በዉርስ አጣሪ ተጣርቶ
ሪፖርቱም ሇፍርዴ ቤቱ ቀርቦ የጸዯቀ ስሇመሆኑ አሊከራከረም፡፡ ከሊይ እንዯተገሇጸዉ አመሌካች ሊቀረቡት
የዉርስ ይጣራሌኝ አቤቱታ መሠረት ያዯረጉት ሇክርክሩ መነሻ የሆነዉ ይዞታ የሚገኝበት ቦታ ወራሾች
ባሇማወቃቸዉ እና ተጠሪም የሇም ብሇዉ በመዯበቃቸዉ ዉርስ ሲጣራ በነበረበት ወቅት ሳይጣራ ታሌፏሌ
የሚሌ ይዘት ያሇዉ ስሇመሆኑ የስር ፍርዴ ቤት ዉሳኔ ግሌባጭ ያሳያሌ፡፡
በዚህ ሁለ ሂዯት አሌፎ ዉርስ ተጣርቶ የተዘጋ እንዯሆነ የዉርስ ማጣራት የታሇመሇትን ዓሊማ
እንዲሳካ ይቆጠራሌ፡፡ ሆኖም በዉርስ ማጣራት ሂዯት ግዴፈት አይኖርም ወይም መጣራት የሚገባቸዉ
ሁለ ተጣርተዋሌ ወይም በሂዯቱ የወራሾች ወይም የሟች ገንዘብ ጠያቂዎች መብት አይነካም ማሇት
አይዯሇም፡፡ የዉርስ ማጣራት ሂዯቱ በአግባቡ ባሇመከናወኑ ወይም በላሊ ምክንያት መካተት የሚገባቸዉ
ንብረቶች ሳይካተቱ በመቅረታቸዉ ወይም መካተት ሳይገባቸዉ በመካተታቸዉ ወይም ወራሽ የሆነ ሰዉ
ስሙ ባሇመካተቱ ምክንያት ወይም ከዉርስ ሀብት ገንዘብ ሉከፈሇዉ የሚገባዉ የሟች ባሇገንዘብ
ሳይከፈሇዉ ሉቀር የሚችሌበት ሁኔታ ይኖራሌ፡፡ በዚህም ምክንያት በአንዴ ወይም በላሊ ምክንያት
ጉዲት ዯርሶብኛሌ ወይም መብቴ ተነክቷሌ ወይም ወራሽነቴ ይረጋገጥሌኝ የሚሌ ሰዉ መብቱን
ሉያስከብር የሚችሌበት ሥርዓት ሉኖር ግዴ ይሊሌ፡፡ ይህን ሁለ ከግምት ዉስጥ በማስገባትም
የፍትሐብሔር ህጉ ስሇ ዉርስ በሚዯነግገዉ ክፍለ ከዉርስ ጋር በተያያዘ መብት ያሇዉ ወገን ሇፍርዴ
ቤት አቤቱታ/ክስ አቅርቦ መብቱን ሉያስከብር የሚችሌባቸዉን ሥርዓቶች ይዯነግጋሌ፡፡ የተወሰኑትን
ሇመጥቀስ ያህሌም፣ ወራሽ መሆኑንና ከዉርስ ሀብቱ የሚዯርሰዉን የዴርሻ መጠን የሚያመሇክት
የወራሽነት የምስክር ወረቀት ፍርዴ ቤት እንዱሰጠዉ መጠየቅ እንዯሚቻሌ እና ፍርዴ ቤቱም ከሳሹ
ያቀረበዉን ማስረጃ ጨምሮ ተገቢዉን ማጣሪያ በማዴረግ አስፈሊጊ ከሆነም ዋስትና እንዱቀርብ
በማዴረግ የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዯሚሰጥ፣ የወራሽነት የምስክር ወረቀት የተሰጠዉ ሰዉም
በማስረጃዉ ሊይ በተገሇጸዉ መሠረት ወራሽ ነዉ ተብል እንዯሚገመት፤ በፍርዴ ቤት የተሰጠዉ
የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰረዝ ወራሽ በሆነ ሰዉ ክስ ማቅረብ እንዯሚቻሌ እና ፍርዴ ቤቱም
የወራሽነት የምስክር ወረቀት የተሰጠዉ ሰዉ ወራሽ አሇመሆኑን ካረጋገጠ እንዯ ነገሩ ሁኔታ የተሰጠዉን
የወራሽነት የምሰክር ወረቀት በመሰረዝ ወይም እንዱመሇስ ወይም ተከሳሹ እንዲይገሇገሌበት ዉሳኔ
መስጠት እንዯሚችሌ፤ የወራሽነት መብት በላሇዉ ሰዉ የተያዘ ንብረት እንዱመሇስ እዉነተኛ ወራሽ
ክስ ማቅረብ እንዯሚችሌ፤ የዉርስ ማጣራት ሂዯቱ ተከናዉኖ የዉርስ ክፍያ ከተዯረገ በኋሊ በዉርስ
ንብረት ዉስጥ ገብተዉ የሚቆጠሩ አዱስ ሀብቶች የተገኙ እንዯሆነ በተገኙት አዱስ ንብረቶች መጠን
ክፍያ በዴጋሚ እንዱዯረግ መጠየቅ እንዯሚቻሌ፣ የአንዲንዴ ንብረቶች ዋጋ በተሳሳተ ሁኔታ የተገመተ
መሆኑ ከታወቀም የዉርስ ክፍያ ሥርዓቱ እንዱቃና መጠየቅ እንዯሚቻሌ እንዱሁም የዉርስ ሀብት
ከተከፋፈሇ በኋሊ የሚመጣ ገንዘብ ጠያቂ ካሇ ወራሾች በዯረሳቸዉ ዴርሻ ሌክ ዕዲዉን እንዱከፍለ
መጠየቅ እንዯሚቻሌ በፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 996-999፣ 1003፣ 1005 እና 1010 ሊይ
የተመሇከቱትን ማየት ይቻሊሌ፡፡
በዉርስ አጣሪ ተጣርቶ የቀረበ የዉርስ ማጣራት ሪፖርት በፍርዴ ቤት መጽዯቁ የማስረጃ ዋጋ
ያሇዉ ቢሆንም፣ እንዯ ፍርዴ ሉቆጠር እንዯማይችሌ የፌዳራሌ ጠቅሊይ ፍርዴ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት
በሰ/መ/ቁጥር 18576 (ቅጽ 7 ሊይ የታተመዉን ጨምሮ) በላልችም መዛግብት ሊይ ገዥ የህግ ትርጉም
ሰጥቷሌ፡፡ ፍርዴ ቤቱ የዉርስ አጣሪ ሪፖርትን ሲያጸዴቅ አንዴን አከራካሪ ጭብጥ ይዞ፣ አከራክሮ እና
ማስረጃን ሰምቶ የፍርዴ ዉጤት በሚኖረዉ መሌኩ የወሰነዉ ካሌሆነ በቀር፣ የዉርስ አጣሪ ያቀረበዉን
ሪፓርት በማጽዯቅ የሰጠዉ ዉሳኔ በላሊ ክርክር እና ማስረጃ ሉስተባበሌ የሚችሌ መሆኑን ነዉ፡፡
በመሆኑም የዉርስ አጣሪ ሪፖርት በፍርዴ ቤት መጽዯቁም ከዉርስ ማጣራት ሂዯት ጋር በተያያዘ
ወይም በላሊ ምክንያት መብቴ ተነክቷሌ የሚሌ ሰዉ በላሊ አግባብ መብቱን እንዲያስከብር ምክንያት
አይሆንም፡፡
በአጠቃሊይ የዉርስ ማጣራት ስራ የተከናወነ መሆኑ ከታወቀ በዉርስ ማጣራቱ ሂዯት መብቴ
ተነክቷሌ ወይም በላሊ በማንኛቸዉም ምክንያት ከወራሽነት መብት ጋር በተያያዘ መብቴ ተነክቷሌ
የሚሌ ሰዉ ዲኝነት ከፍል በሚመሇከተዉ አካሌ ሊይ በህግ አግባብ ክስ አቅርቦ መብቱን ማስከበር
ከሚችሌ በስተቀር በዴጋሚ የዉርስ ይጣራሌኝ አቤቱታ ሉያቀርብ የሚችሌበት ህጋዊ ምክንያት የሇም፡፡
ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመሇከት አመሌካች የሟች አባታቸዉ ዉርስ ከዚህ በፊት በዉርስ
አጣሪ ተጣርቶ ሪፖርቱ ሇፍርዴ ቤት ቀርቦ መጽዯቁን ሳይክደ፣ የዉርስ ይጣራሌኝ አቤቱታ በዴጋሚ
ሇፍርዴ ቤቱ ያቀረቡት ሇክርክሩ መነሻ የሆነዉን ይዞታ ዉርስ በሚጣራበት ወቅት የት እንዯሚገኝ
ባሇመታወቁ እና ተጠሪም በወቅቱ መዯበቃቸዉን በመግሇጽ ነዉ፡፡ ይሁንና በወቅቱ ሳይታወቅ ቀርቷሌ
አሌተካተተም የሚለ ከሆነ ምክንያቱን ጠቅሰዉ መብታቸዉን በላሊ አግባብ ማስከበር ከሚችለ በቀር
በዴጋሚ የሟች የዉርስ ሀብት እንዱጣራ ፍርዴ ቤቱ የዉርስ አጣሪ እንዱሾምሊቸዉ የጠየቁት ዲኝነት
የዉርስ ሀብት ማጣራት አስፈሊጊነት እና ዓሊማን መሠረት ያዯረገ ባሇመሆኑ ከመነሻዉም ዉዴቅ
ሉዯረግ የሚገባዉ ነዉ፡፡ ስሇሆነም፣ ጉዲዩን ከዚህ አንፃር ማየት ሲገባዉ፣ የፌዳራሌ የመጀመሪያ ዯረጃ
ፍርዴ ቤት የአመሌካችን ክስ ተቀብል ነገር ግን ክሱ በዴጋሚ የቀረበ ነዉ በማሇት የሰጠዉን ብይን
በማጽናት በፌዳራሌ ከፍተኛ ፍርዴ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ
ተገኝቷሌ፡፡ ስሇሆነም ተከታዩ ተወስኗሌ፡፡
ዉ ሳ ኔ
ፍ/ገ