You are on page 1of 8

ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

FEDERAL SUPREME COURT

የሰበር መ/ቁ 227293

ጥቅምት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

ዲኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ረታ ቶልሳ

በእውቀት በሊይ

ቀነዓ ቂጣታ

ኑረዱን ከዴር

አመሌካች፡- ወ/ሮ የትፈንታ ምስክር ጠ/አስራት ሰብስቤ - ቀረቡ

ተጠሪ፡- አቶ ዯመቀ ጎሹ - ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተሇው ፍርዴ ተሰጥቷሌ፡፡

ፍርዴ

መዝገቡ ሇዚህ ችልት የቀረበው የፌዳራሌ መጀመሪያ ዯረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 80361 በቀን
21/06/2014 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ ይግባኝ የቀረበሇት የፌዳራሌ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ
288090 በቀን 02/09/2014 ዓ.ም ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት በመሰረዙ ዉሳኔዉ
መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነው፡፡

የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ሲታይ በስር ፍ/ቤት ከሳሽ አመሌካች ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን
ተከራክረዋሌ፡፡አመሌካች በስር ፍ/ቤት በቀን 26/11/2013 ዓ.ም አሻሽል ባቀረቡት ክስ ከሟች
ባሇቤቴ አቶ ግርማ ወዲጆ የጋራ ሀብት የሆነ በጉ/ክ/ከ/ወ-7/ የቤት ቁጥር አዱስ የሆነው ቤት
ተጠሪ በቀን 18/10/2000 ዓ.ም ውክሌና በመውሰዴ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ንብረቱን ሲያተዲዴር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
የቆየ ቢሆንም ህግ በመጣሱ ዉክሌናዉ በቀን 01/12/2005 ዓ.ም ተነስቷሌ፤ተጠሪ የተከራየውን
ቤት ውዝፍ ኪራይ ከፍል ቤቱን እንዱሇቅ በመ/ቁ 53640 ክስ አቅርቤ ፍ/ቤቱ የሽያጭ ውሌ
ስሊሇ ተጠሪ ቤቱን ሉሇቅም ሆነ የቤት ኪራይ ሉከፍሌ አይገባም በማሇት የወሰነ በመሆኑ እና
የሽያጭ ውሌ መኖሩን ያወኩት በዚህ ውሳኔ በመሆኑ አመሌካች እና ባሇቤቴ የሸጥነው ቤት
የሇም፤አመሌካች በሽተኛ እና ማንበብ አሇመቻላን ተጠቅሞ ተጠሪ ከቅን ሌቦና ውጭ
ያዘጋጀው የሽያጭ ሰነዴ በመሆኑ በውለ ሊይ ፊርማ ያሌፈረምኩ እና ገንዘብ
ያሌተቀበሌኩ፤ውለም ስሌጣን ባሇው አካሌ ፊት ያሌተዯረገ በመሆኑ ውለ እንዱፈርስ
እንዱወሰን በማሇት ዲኝነት ጠይቀዋሌ፡፡

ተጠሪ ባቀረቡት መከሊከያ መሌስ ሇክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የተያዘዉ በኪራይ ሳይሆን
በሽያጭ መሆኑ በመ/ቁ 53640 ሊይ ውሳኔ ተሰጥቶበታሌ፤አመሌካች ከዚህ ቀዯም የሽያጭ ውሌ
እንዯላሇ ክስ አቅርበው ውዴቅ የተዯረገባቸው በመሆኑ አሁን በዴጋሚ የቀረበ ክስ ተቀባይነት
ሉኖረው አይገባም፤ክሱ በበቂ ምክንያት እና ማስረጃ የተዯገፈ አይዯሇም፣ አመሌካች ሙለ
ጤንነት እንዯነበራቸው ከዚህ ቀዯም በተዯረገ ክርክር የተረጋገጠ በመሆኑ እና አሁንም
ሉረጋገጥ የሚችሌ ነው በሚሌ ክሱ ውዴቅ እንዱዯረግ በማሇት ተከራክረዋሌ፡፡

ጉዲዩ የቀረበሇት የፌዳራሌ መጀመሪያ ዯረጃ ፍ/ቤት ማስረጃ ሰምቶና አመዛዝኖ አመሌካች
ባቀረቡት ማስረጃዎች ውሌ አሇመዋዋሊቸውን አሊረጋገጡም፤ውለ በሚመሇከተው አካሌ ፊት
አሌተዯረገም ረቂቅ ነው በማሇት ያቀረቡትን ክርክር በተዋዋይ ወገኖች መካከሌ እንጂ
በተዋዋይ ወገንና በ3ኛ ወገን መካከሌ ባሇመሆኑ የአመሌካች ክርክር የህግ መሰረት የሇውም
በማሇት ውለ ሉፈርስ አይገባም የሚሌ ዴምዲሜ ሊይ ዯርሷሌ፡፡አመሌካች በዚህ ውሳኔ ቅር
በመሰኘት ይግባኝ ሇፌዳራሌ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ይግባኙን
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ሰርዞታል፡፡አመሌካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ይህን ዉሳኔ
በመቃወም ሇማስሇወጥ ነዉ፡፡

የአመሌካች የሰበር አቤቱታ ይዘት በአጭሩ፡- በአመሌካችና በተጠሪ መካከሌ የተዯረገው የቤት
ሽያጭ ውሌ የተካዯ እና በውሌ አዋዋይ ፊት ያሌተዯረገ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1723 መሰረት
እንዯረቂቅ የሚቆጠር ሆኖ ሳሇ የስር ፍ/ቤት ዉለ ሉፈርስ አይገባም ሲሌ የሰጠው ውሳኔ
መሰረታዊ የህግ ስህተት ያሇበት ነው፤ሰነደ ሀሰተኛ ነው በሚሌ ተከራክረን ምስክሮች በሰጡት
ቃሌ አመሌካች ሲፈርሙ ያሊዩ መሆኑ ተረጋግጦ እያሇ ፊርማው የአመሌካች መሆኑና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
አሇመሆኑ በፎሬንሲክ ሳይረጋገጥ የስር ፍ/ቤት ውለ አይፈርስም በማሇት የሰጠው ውሳኔ የህግ
ስህተት በመሆኑ ዉሳኔዉ እንዱታረም በማሇት አመሌክተዋሌ፡፡

የአመሌካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ስር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር


ያዯረጉት ውሌ የላሇ መሆኑን በመግሇጽ በተከራከሩበት ውለ ሉፈርስ አይገባም በማሇት
የወሰነበት አግባብነት ሇመመርመር ሲባሌ መዝገቡ ሇሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባሌ ተብል
ተጠሪ መሌስ እንዱሰጡበት ታዟሌ፡፡ተጠሪ ባቀረቡት መሌስ ክርክር የተነሳበት ቤት
በተመሇከተ ውዝፍ ኪራይ ከፍል ቤቱን ይሌቀቅሌኝ በማሇት አመሌካች በመ/ቁ 53640 ክስ
አቅርበው ቤቱን ገዝቼ የምገሇገሌበት መሆኑ ተረጋግጦ ክሱ ውዴቅ ሲዯረግ ዉሳኔዉ እስከ
በሊይ ፍርዴ ቤት ዯርሶ ፀዴቋሌ፤ሇ2ኛ ጊዜ በመ/ቁ 284696 ባቀረቡት ክስ ተከሳሾች የነበሩት
ተጠሪ፣የጉሇላ ክፍሇ ከተማ መሬት ሌማት አስተዲዯርን እና የጉሇላ ክፍሇ ከተማ ወረዲ 07
ዯንብ ማስከበር ጽ/ቤትን ሁከት ፈጥረዋሌ እና ሁከት ይወገዴሌኝ በማሇት ዲኝነት ጠይቀዉ
ፍ/ቤቱ ሁከት የሇም በማሇት ክሱን ውዴቅ አዴርጎታሌ፤በህግ ማሸነፍ ሲያቅታቸው የሸጡሌኝን
ቤት አጥሩን በሃይሌ በማፍረስ በመያዛቸው ሁከት እንዱወገዴ በመ/ቁ79940 ክስ አቅርቤ ሁከት
እንዱወገዴ በተሰጠ ውሳኔ መሰረት ቤቱን በዴጋሚ ተረክቤ እየተገሇገሌኩ እገኛሇሁ፤በመሆኑም
የአሁኑ ክርክር ሇ4ኛ ጊዜ የቀረበ በመሆኑ መዝገቦችን በመመሌከት ክሱን ውዴቅ
እንዱያዯርግሌኝ አመሌካች የጤና ችግር ያሇባቸው መሆኑን በመግሇጽ የቤት ሽያጭ ስምምነት
እንዲሊዯረጉ በማስመሰሌ ያቀረቡት ክርክር ሀሰት ነው፤ሽያጩን አዴርገው ውሃና መብራት
ሇማስገባት ውክሌና ሲሰጡኝ እሳቸውም ሆኑ ሟች ባሇቤታቸው በወቅቱ የመንግስት ሰራተኞች
ነበሩ፤አመሌካች የቤት ሽያጭ ውሌ የፈረሙ መሆኑን በመ/ቁ53640 ሊይ በበቂ ማስረጃ
የተረጋገጠ በመሆኑ አቤቱታው ውዴቅ ሉሆን ይገባሌ በማሇት ተከራክረዋሌ፡፡አመሌካች የሰበር
አቤቱታቸውን በመጠናከር የመሌስ መሌስ አቅርበዋሌ፡፡

በላሊ በኩሌ ተጠሪ በቀን 05/11/2014ዓ.ም የተጻፈ መስቀሇኛ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን
አጭር ይዘቱም አመሌካች እና ተጠሪ በስር ፍ/ቤት በመ/ቁ 53640፣ 284696 እና 79940
ክርክር አዴርገን አሁን ሇ4ኛ ጊዜ የቀረበ ክስ በመሆኑ ይህም ሉሆን የቻሇው በቂ ወጪና ኪሳራ
ስሇማይቆረጥ አመሌካች ምክንያት እየቀያየሩ ክስ እያቀረቡብኝ ከመሆኑም ባሻገር
በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 5 እና 244(2)(ሇ) መሰረት ክሱ ውዴቅ ሉዯረግ እንዯሚገባ ያቀረብኩት
የመጀመሪያ ዯረጃ መቃወሚያ መታሇፉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፤የሽያጭ ውለ የተዯረገው
ነሐሴ 21 ቀን 2000 ዓ.ም ሲሆን የውሌ ይፍረስሌኝ ክስ የቀረበው ከ12 ዓመት በኋሊ በመሆኑ
ይርጋ ያግዯዋሌ በማሇት ያቀረብኩት የመጀመሪያ ዯረጃ መቃወሚያ መታሇፉ መሰረታዊ የህግ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባሌ የሚሌ ነው፡፡ሰበር ችልቱ ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም በዋሇው
ችልት መስቀሇኛ አቤቱታዉን መርምሮ ተጠሪ ያቀረቡት ይርጋ መቃወሚያ ዉዴቅ መዯረጉ
በአግባብ ነዉ ወይስ አይዯሇም የሚሇዉን በጭብጥነት በመያዝ መስቀሇኛ ተጠሪ(አመሌካች)
መሌስ እንዱሰጡበት አዟሌ፡፡መስቀሇኛ ተጠሪ (አመሌካች) ባቀረቡት መሌስ በስር ፍ/ቤት
የቤት ሽያጭ ውለ በፎሬንሲክ እንዱመረመር ተዯርጎ ምሊሽ ባይሰጠውም ዉለ በመስቀሇኛ
መሌስ ሰጭ (በአመሌካች) የሚታወቅ አይዯሇም፤በስር ፍ/ቤት ያቀረብኩት የውሌ ይፍረስሌኝ
አቤቱታ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1810 መሰረት በ2 ዓመት ይርጋ የሚገዯብ ሳይሆን በፍ/ብ/ህ/ቁ 1845
መሰረት 10 ዓመት ይርጋ ጊዜ የሚታይ ነው፡ሰበር ችልት በመ/ቁ 48012 (ቅጽ 12) እና
131151 (ቅጽ 22) ሊይ ትርጉም ሰጥቶበታሌ፤ሀሰተኛ የሽያጭ ውሌ መኖሩን ያወኩት በመ/ቁ
53640 ስንከራከር መስቀሇኛ አመሌካች ካቀረበው ሰነዴ ነው፤ፍ/ቤቱ አከራክሮ ውሳኔ የሰጠዉ
በ3/05/2011 ዓ.ም በመሆኑ ውሌ ይፍረስሌኝ የሚሌ ክስ ያቀረብኩት በ25/01/2013 ሲሆን ክሱን
ያሻሻሌኩት ሐምላ 26 ቀን 2013 ዓ.ም በመሆኑ 10 ዓመት አሌሞሊውም በማሇት ይርጋ
አያግዯውም ሲለ ተከራክረዋሌ፡፡ተጠሪ የመሌስ መሌስ በማቅረብ የመስቀሇኛ ይግባኝ
አቤቱታቸውን አጠናክረዋሌ፡፡

የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር በአጭሩ ከሊይ የተገሇጸዉን የሚመስሌ ሲሆን እኛም
በስር ፍርዴ ቤቶች የተሰጡት ውሳኔዎችን አግባብነት ካሊቸዉ የሕግ ዴንጋጌዎች ጋር
በማገናዘብ መርምረናሌ፡፡እንዯመረመርነውም የአመሌካች የዲኝነት ጥያቄ በአመሌካች እና
በተጠሪ መካከሌ የተዯረገ የቤት ሽያጭ ዉሌ እንዱፈርስ የሚሌ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ ክሱ
በይርጋ መታገደን እንዱሁም ዲግም የቀረበ ክስ ነዉ በሚሌ የመጀመሪያ ዯረጃ መቃወሚያ
ማቅረቡን መዝገቡ ያሣያሌ፡፡በቀዲሚነት ምሊሽ ማግኘት ያሇበት ጭብጥ ክሱ በይርጋ ቀሪ
ሉሆን ይገባሌ በማሇት ተጠሪ ያቀረቡት የመጀመሪያ ዯረጃ መቃወሚያ ዉዴቅ መዯረጉ ሊይ
የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አሇመኖሩን የሚመሇከት ነዉ፡፡ይርጋ ዯንብ መብት ሇማስከበር
የሚቀርብ ክስ /limitation of action/ ቀሪ የማዴረግ ዉጤት ያሇዉ የህግ ጽንሰ ሃሳብ
ነዉ፡፡የይርጋ ዯንብ /period of limitation/ ዓይነተኛ ዓሊማ አንዴ ግዳታ እንዱፈጸምሇት
የሚጠይቅ ባሇመብት በህጉ በተገሇጸ የጊዜ ገዯብ ዉስጥ በመብቱ ባሇመስራቱ የመብት ጥያቄዉ
በጊዜ ማሇፍ ምክንያት ቀሪ የሚሆንበት በላሊ በኩሌ ግዳታ ያሇበትን ወገን ግዳታዉን
እንዱፈጽም ከሚቀርብበት ክስ ነጻ የማዴረግ ዉጤት ያሇዉ ነዉ፡፡የይርጋ ጊዜ እርዝማኔ
እንዯጉዲዩ ዓይነትና ባሕርይ የሚሇያይ ስሇመሆኑ የይርጋ ዯንብ የሚመሇከቱ ዴንጋጌዎች
ያስገነዝባለ፡፡ስሇዚህም ተፈጻሚነት ያሇዉ ይርጋ ጊዜ ሇመሇየት የሚቻሇዉ የተጠየቀዉ ዲኝነት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
ዓይነት ወይም የክስ ምክንያት እና በመብቱ መስራት የሚቻሌበትን ጊዜ በሚመሇከት ሇጉዲዩ
ተፈጻሚነት ያሇዉን ህግ መሰረት በማዴረግ መሆን አሇበት፡፡
በመሰረቱ ዉሌ በተዋዋይ ወገኖች መካከሌ መብትና ግዳታ ሉፈጥር በህግ አስገዲጅነት
የሚኖረዉ ስሇዉሌ አመሰራረት በህግ የተዯነገጉትን ሁኔታዎች አሟሌቶ የተዯረገ መሆኑን
ሲረጋገጥ ነዉ፡፡ይኸዉም ተዋዋዮቹ ሇመዋዋሌ ችልታ ያሊቸዉ ሰዎች መሆኑን፣በነጻ ፈቃዲቸዉ
ያዯረጉት መሆኑን፣የዉሇታዉ ጉዲይ የሚቻሌና ህጋዊ የሆነ መሆኑን እና በህግ የተዯነገገዉን
የዉሌ አጻጻፍ ስርዓት(ፎርም) ያሟሊ መሆን ይኖርበታሌ፡፡(የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1678
ይመሇከቷሌ)፡፡በህጉ የተዯነገገዉን የዉሌ አመሰራረት መስፈረትና ስርዓት አሟሌቶ የተዯረገ
ዉሌ ህግ ሆኖ ተዋዋይ ወገኖችን የሚያስገዴዴ ስሇመሆኑም የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1731(1) ዴንጋጌ
ይዘት ያሥገነዝባሌ፡፡ሆኖም ዉለ አመሰራረት ሊይ ጉዴሇት አሇበት ወይም በአፈጻጸም ሂዯት
በተከሰተ ሁኔታ ዉሌ እንዲይፈጸም ያዯረገ እንዯሆነ ከተዋዋዮቹ አንደ ወይም ጥቅም ያሇዉ
ሶስተኛ ወገን ዉለ እንዱፈርስ ወይም እንዱሰረዝ ጥያቄ ሉነሳበት ይችሊሌ፡፡(የፍ/ብ/ህግ ቁጥር
1808 እና ተከታዮቹን ዴንጋጌዎች ይመሇከቷሌ)፡፡ ዉሌ የማፍረስ /invalidation/ መነሻ
ምክንያቶች በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1808 ስር ተዘርዝረዋሌ፡፡እነዚህም ውሌ አመሠራረት ሊይ
የፈቃዴ ጉዴሇት መኖር፤ ከተዋዋይ ወገኖች ችልታ ማጣት፤ የውሇታው ጉዲይ ህገወጥነት
ወይም ኢሞራሊዊነት ወይም የውለ አቀራረጽ /ፎርም/ በህግ የተዯነገገውን ሥርዓት አሇመጠበቅ
የሚለ ናቸው፡፡ከእነዚህ ምክንያቶች በአንደ ወይም በላሊው መነሻ ውለ እንዱፈርስ ጥያቄ
በማንና መቼ መቅረብ እንዲሇበትም በህጉ ተመሌክቷሌ፡፡ዉሌ እንዱፈርስ ወይም እንዱሰረዝ
የሚቀርብ ክስ ይርጋ ጊዜ ዉለን ሇማስፈረስ ወይም ሇማሰረዝ እንዯቀረበዉ ምክንያት እና
ሁኔታ በሁሇት ዓመት ወይም በአስር ዓመት ጊዜ የተገዯበ ስሇመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1810
እና 1845 ዴንጋጌ ይዘት መገንዘብ ይቻሊሌ፡፡
በተያዘዉ ጉዲይ ሇክሱ ምክንያት የሆነዉ ነሐሴ 21 ቀን 2000 ዓ.ም የተዯረገ የቤት ሽያጭ
ዉሌ ሲሆን ክሱ የቀረበዉ በ25/01/2013ዓ.ም መሆኑን መዝገቡ ያሣያሌ፡፡የተጠሪ ዲኝነት ጥያቄ
ዉለን አሊዉቀዉም፤አሌፈረምኩም፤ስምምነት አሌሰጠሁም በተጨማሪም ማንበብና መጻፍ
ስሇማሌችሌ ፊርማ የእኔ አይዯሇም በማሇት ዉለ እንዱፈርስ መጠየቃቸዉን መዝገቡ
ያሣያሌ፡፡ከዚህም መገንዘብ የሚቻሇዉ ክርክራቸዉ በሁሇት ዘንግ የተከፈሇ መሆኑን
ነዉ፡፡ይኀዉም በአንዴ በኩሌ ተዋዋይ እንዲሌሆኑ በላሊ በኩሌ ዯግሞ ዉለን አዴርገዋሌ ቢባሌ
እንኳን የኪራይ እንጂ የሽያጭ ስምምነት አሊዯረኩም ሽያጭ የተባሇዉ ሰነዴ በሀሰት የተዘጋጀ
ዉሌ ነዉ የሚሌ ነዉ፡፡ተዋዋይ አይዯሇሁም፤የሽያጭ ዉሌ መኖሩን ያወቅኩት ኪራይ ዉሌ
ምክንያት በቀረበዉ ክስ ነዉ የሚሇዉን በተመሇከተ ተጠሪ ክስ እንዱያቀርቡ የሚጠበቀዉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
በመብታቸዉ መስራት ከሚችለበት ማሇትም የሽያጭ ዉሌ መኖሩን ካወቁበት ጊዜ ጀምሮ
ሲሆን የፈቃዴ ጉዴሇትን መነሻ ያዯረገ ዉሌ ማፍረሻ ምክንያት መሰረት ተዴረጎ ሲታይ
በሁሇት ዓመት ጊዜ ዉስጥ መሆን ይኖርበታሌ፡፡ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1846 እና 1810(2)
ይመሇከቷሌ፡፡ነገር ግን የተባሇዉ የዉሌ ሰነዴ ሀሰተኛ ነዉ የሚሇዉ የዉለን ህጋዊነት
የሚመሇከት እንዯመሆኑ ዉለ ከተዯረገበት ቀን ጀምሮ በአስር ዓመት ጊዜ ዉስጥ ማቅረብ
ይጠበቅባቸዋሌ፡፡ከዚህ አኳያ የስር ፍርዴ ቤት ይርጋ መቃወሚያ ዉዴቅ ያዯረገዉ ተጠሪ ዉለ
እንዱፈርስ የጠየቁት በሀሰት የተዘጋጀ ነዉ በሚሌ ምክንያት በመሆኑና ይህንንም ያወቁት
በኪራይ ዉሌ ክርክር በ2008ዓ.ም በመሆኑ አስር ዓመት ጊዜ አሊሇፈበትም በሚሌ ምክንያት
ስሇመሆኑ ፍርዴ ቤቱ በቀን 15/02/2014ዓ.ም የሰጠዉ ብይን ይዘት ያሣያሌ፡፡ይሁን እንጂ
ፍርዴ ቤቱ ብይን ይዘት እና በመጨረሻም የሰጠዉ ፍርዴ ይዘት እንዯሚያሣን ተጠሪ ቤቱን
የያዘዉ በኪራይ ሳይሆን በሽያጭ ዉሌ ስሇመሆኑ የምስክሮች ቃሌ መሰረት ተዴረጎ በመ/ቁ/
53640 ሊይ ከመወሰኑም በተጨማሪ ሽያጭ ዉለ ሊይ ያሇዉ ፊርማ የአመሌካች መሆኑም
ጭምር በፎረንሲክ ምርምራ ጭምር የተረጋገጠ ፍሬነገር ጉዲይ ነዉ፡፡ስሇዚህም ነሐሴ 21 ቀን
2000 ዓ.ም የተዯረገዉን የቤት ሽያጭ አሊዉቅም ፤አሌፈረምኩም ፤ሀሰተኛ ሰነዴ ነዉ ቢለም
ዉለ ሊይ አመሌካች የፈረሙ ስሇመሆኑ የተረጋገጠ ፍሬነገር በመሆኑ ዉለ መኖሩን ያወቁት
በ2008ዓ.ም ነዉ የሚሇዉ የአመሌካች ክርክር በማስረጃ የተስተባበሇ መሆኑን ያሣያሌ፡፡ይህ
ከሆነ ዯግሞ ሇይርጋ አቆጣጠር መነሻ ተዯርጎ የሚወሰዯዉ ዉለ የተዯረገበት
21/12/2000ዓ.ምእንጂ2008ዓ.ምአይዯሇም፡፡ዉለ ከተዯረገበት 21/12/2000ዓ.ም ክሱ
እስከቀረበበት 25/01/2013 ዓ.ም ያሇዉ ጊዜ ሲታሰብ ከአስር ዓመት በሊይ ነዉ፡፡ክሱ የቀረበዉ
አስር ዓመት ካሇፈ በኋሊ በመሆኑ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1845 መሰረት ይርጋ ጊዜ ገዯብ የታገዯ
ነዉ፡፡ስሇሆነም የስር ፍርዴ ቤት ክሱ ይርጋ ጊዜ አሊሇፈበትም ሲሌ የዯረሰበት ዴምዲሜ
በክርክሩ የተረጋገጠዉን ፍሬነገር ያገናዘበ ባሇመሆኑ ሉታረም ይገባሌ፡፡ክሱ ከጅምሩም በይርጋ
ቀሪ መዯረግ የነበረበት በመሆኑ ላልች በተጠሪ በኩሌ የተነሱትን የመጀመሪያ ዯረጃ
መቃወሚያ ነጥቦችም ሆነ በፍርደ ሊይ በአመሌካች በኩሌ የቀረበዉን አቤቱታ መመርመር
አስፈሊጊ አይዯሇም፡፡
ሲጠቃሇሌ በአመሌካች እና በተጠሪ መካከሌ በቀን 21/12/2000ዓ.ም የተዯረገዉ የቤት ሽያጭ
ዉሌ እንዱፈርስ ክስ የቀረበዉ አስር ዓመት ይርጋ ጊዜ ያሇፈበት ሆኖ እያሇ ፍርዴ ቤቱ
የተጠሪን የመጀመሪያ ዯረጃ መቃወሚያ ዉዴቅ ማዴረግ በፍሬነገሩ ገብቶ የሰጠዉ ፍርዴ
መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ የተጠሪን መስቀሇኛ አቤቱታ መሰረት በማዴረግ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
የስር ፍርዴ ቤት ብይን እና ዉሳኔ በፌዳራሌ ፍርዴ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ
2(4/ሇ) እና 10(1/ሀ) መሰረት በማረም ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናሌ፡፡
ዉሳኔ
1ኛ/የፌዳራሌ የመጀመሪያ ዯረጃ ፍርዴ ቤት በመ/ቁ80361 ሊይ በቀን15/02/2014ዓ.ም የሰጠዉ
ብይን እና በቀን 21/06/2014ዓ.ም የሰጠዉ ፍርዴ በማጽናት የፌዳራሌ ከፍተኛ ፍርዴ ቤት
በመ/ቁ/288090 ሊይ በቀን 02/09/2014ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስህግ ቁጥር 348(1)
መሰረት ተሽሯሌ፡፡
2ኛ/በ21/12/2000ዓ.ም የተዯረገ ዉሌ እንዱፈርስ አመሌካች ያቀረቡት ክስ አስር ዓመት ይርጋ
ጊዜ አሌፎበታሌ፡፡
3ኛ/በዚህ ፍርዴ ቤት የተዯረገዉ ክርክር ያስከተሇዉ ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ ራሳቸዉን ይቻለ
ብሇናሌ፡፤
ትእዛዝ
የስር ፍርዴ ቤት መ/ቁ/53640፣መ/ቁ/284696 እና መ/ቁ/80361 በመጣበት ሁኔታ ይመሇስ፡፡
መ/ዏ የማይነበብ የአራት ዲኞች ፊርማ አሇበት

የመስማሚያ ሀሳብ

እኔ ስሜ በተራ ቁጥር 5 ሊይ የተመሇከተው የችሎቱ ዳኛ የስራ ባልደረባዎቼ አመልካች ነሀሴ 21


ቀን 2000ዓ/ም የተደረገው ውል እንዲፈርስ ያቀረቡት ክስ የይርጋ ጊዜ ያሇፈበት በመሆኑ
ተቀባይነት የሇውም በማሇት በደረሱበት መደምደሚያ የምስማማ ሲሆን ሇጉዳዩ አግባብነት አሇው
ተብሎ በተጠቀሰው ድንጋጌ እና ይህንን ተከትሎም በውሳኔው ሊይ በተመሇከተው የይርጋ ጊዜ ግን
ያልተስማማሁ በመሆኑ የመስማሚያ ሀሳቤን እንደሚከተሇው አስፍሬያሇሁ፡፡

አመልካች ውለ እንዲፈርስ በመጠየቅ ክሱን ያቀረቡት ውለን አሊውቀውም አልፈረምኩም ፤


ስምምነት አልሰጠሁም፡፡ በተጨማሪም ማንበብና መፃፍ ስሇማልችል ፊርማው የኔ አይደሇም
በማሇት ነው፡፡ ይህም የአመልካች ውል ይፍረስልኝ የዳኝነት ጥያቄ ከፈቃድ ጉድሇት (Defect in
consent) ጋር የተያያዘ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ሇጉዳዩ አግባብነት ያሇው ድንጋጌ
በፍ/ብ/ህ/ቁ.1810(1) የተመሇከተው ውለ የማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ጊዜ ጀምሮ የሚታሰበው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
የሁሇት አመት የይርጋ ጊዜ በመሆኑ የአመልካች ክስ ውድቅ ሉደረግ የሚገባው በዚሁ ድንጋጌ
አግባብ ሉሆን ይገባል በማሇት የመስማሚያ ሀሳቤን አስፍሬያሇሁ፡፡

የማይነበብ የአንድ ዳኛ ፊርማ አሇበት

መ/ዏ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም

You might also like