You are on page 1of 6

አብርሃም ዮሀንስ

የሰ/መ/ቁ. 95338

ሚያዝያ 12 ቀን 2007 ዓ.ም.

ዲኞች፡-አሌማው ወላ

ዓሉ መሐመዴ

ሡሌጣን አባተማም

ሙስጠፋ አህመዴ

ተኽሉት ይመሰሌ

አመሌካች፡-አቶ በቀሇ ማሞ - ጠበቃ ዯረጀ ታዯሰ ቀረቡ

ተጠሪዎች፡-

1. ሲ/ር ራሄሌ ብርሃኑ - ቀረቡ


2. ወ/ሮ የሺሀረግ ብርሃኑ - ተወካይ እንዯሻው ብርሃኑ ቀረቡ
3. ድ/ር ዮሴፍ ስዩም - የቀረበ የሇም
4. ወ/ሮ ጥሩወርቅ መክቴ - የቀረበ የሇም
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተሇው ፍርዴ ተሰጥቶአሌ፡፡

ፍ ር ዴ

አመሌካች በዚህ መዝገብ አቤቱታ ያቀረቡት ባሇቤታቸው የነበሩት የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ከአመሌካች ፈቃዴ እና
ዕውቅና ውጪ በጋብቻ ውስጥ የተፈራውን የጋራ ቤት ሇ2ኛ እና ሇ3ኛ ተጠሪዎች በማስተሊሇፍ፣2ኛ እና 3ኛ
ተጠሪዎችም በተራቸው ሇ4ኛ ተጠሪ በማስተሊሇፍ የፈጸሙት የሽያጭ ውሌ እንዱፈርስ እና አመሌካች ቤቱን
እንዱረከቡ ይወሰንሌኝ ሲለ ያቀረቡት ክስ የመጀመሪያውን የሽያጭ ውሌ በተመሇከተ ክሱ በአዋጅ ቁጥር
213/1992 በተሻሻሇው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 69(2) መሰረት በይርጋ የታገዯ ነው፣የመጀመሪያውን የሽያጭ ውሌ
በተመሇከተ ክሱ በይርጋ የሚታገዴ ከሆነ ዯግሞ ከሳሽ በ4ኛ ተጠሪ ሊይ በተናጠሌ ክስ ሇማቅረብ የሚያስችሌ
መብት የሊቸውም፣ከሳሽ ዴርሻቸውን መጠየቅ የሚችለት ከ1ኛ ተጠሪ ነው በማሇት በፌዳራሌ ከፍተኛ ፍርዴ ቤት
ዴሬዲዋ ምዴብ ችልት ተሰጥቶ በፌዳራሌ ጠቅሊይ ፍርዴ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የጸናው ብይን መሰረታዊ
የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባሌ በማሇት ነው፡፡

የጉዲዩን አመጣጥ በተመሇከተ አመሌካች በ18/12/2004 ዓ.ም. አዘጋጅተው ባቀረቡት ክስ በዴሬዲዋ ከተማ በቀበላ
02 ክሌሌ ውስጥ 250 ካ.ሜ. ይዞታ ያሇው እና በካርታ ቁጥር መሌ/2600 የሚታወቀው ቤት የአመሌካች እና
የ1ኛ ተጠሪ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የጋራ ሀብት መሆኑን፣የቤተሰብ ሕጉን እና የፍትሐብሔር ሕግ ዴንጋጌዎችን
በሚቃረን ሁኔታ የአመሌካችን ፈቃዴ ሳያገኙ 1ኛ ተጠሪ በ21/04/2002 ዓ.ም. በተዯረገ ውሌ እህታቸው ሇሆኑት
2ኛ ተጠሪ እና የ2ኛ ተጠሪ ባሇቤት ሇሆኑ 3ኛ ተጠሪ በብር 30,000 (ሰሊሳ ሺህ) መሸጣቸውን፣2ኛ እና 3ኛ
ተጠሪዎችም በተራቸው በ26/03/2004 ዓ.ም. በተዯረገ ውሌ ሇ4ኛ ተጠሪ በብር 640,000 (ስዴስት መቶ አርባ
ሺህ) መሸጣቸውን ገሌጸው ውልቹ ከአመሌካች ፈቃዴ ውጪ እና ተገቢውን ፎርማሉቲ ሳያሟለ የተዯረጉ
በመሆኑ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69(1) መሰረት እንዱፈርሱ መጠየቃቸውን፣1ኛ ተጠሪ በ30/12/2004 ዓ.ም.
በሰጡት መሌስ ከአመሌካች ጋር ከ1982 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 1991 ዓ.ም. ዴረስ በጋብቻ ኖረው አመሌካች
አብርሃም ዮሀንስ

ከኢትዮጵያ ውጪ ከሄደበት ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ ግንኙነታቸውም መቋረጡን፣ጋብቻቸውም በ1996 ዓ.ም. በፍርዴ
ቤት ውሳኔ መፍረሱን፣ቤቱንም አመሌካች ከአገር ከወጡ በኃሊ ነገር ግን ጋብቻው ከመፍረሱ በፊት በግሌ ዴካም
እና ጥረት ያገኙት የግሌ ሀብት እንጂ የጋብቻ ውጤት አሇመሆኑን፣ሽያጩ የተከናወነው ጋብቻው ከፈረሰ በኃሇ
በመሆኑ የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69 (1) ሇጉዲዩ አግባነት የላሇው መሆኑን፣አግባብነት አሇው ቢባሌ እንኳ ክሱ
በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69(2) እና የፌዳራሌ ጠቅሊይ ፍርዴ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ ቁጥር 38126 በሰጠው
አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት በይርጋ የሚታገዴ መሆኑን፣የአመሌካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የመጨረሻ ግንኙነት
አዯረግን ከሚለበት ከ08/06/1994 ዓ.ም. ጀምሮ ክሱ እስከ ቀረበበት ጊዜ ዴረስ አስር ዓመት ያሇፈው በመሆኑ ክሱ
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1677 እና 1845 ዴንጋጌዎች መሰረት በይርጋ የሚታገዴ መሆኑን፣2ኛ እና 3ኛ
ተጠሪዎች በ30/12/2004 ዓ.ም. በሰጡት መሌስ የቤተሰብ ሕጉን አንቀጽ 69(2) እና የፌዳራሌ ጠቅሊይ ፍርዴ
ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ ቁጥር 38126 የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ጠቅሰው ክሱ በይርጋ ውዴቅ
እንዱዯረግ መከራከራቸውን፣4ኛ ተጠሪ በ30/12/2004 ዓ.ም. በሰጡት መሌስ አመሌካች በ4ኛ ተጠሪ ሊይ ክስ
ሇማቅረብ የሚያስችሌ መብት ያሇቸው መሆኑን ስሊሊረጋገጡ ክሱ በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 33(2)
መሰረት እንዱዘጋ መጠየቃቸውን፣ክሱ በተሰማበት ጊዜም አመሌካች ላሊ ትዲር ከመሰረቱበት ከ1994 ዓ.ም. ጀምሮ
ክሱን በአስር ዓመት ውስጥ ስሊሊቀረቡ ክሱ በአስር ዓመት ይርጋ የሚታገዴ ነው በማሇት 1ኛ ተጠሪ
መከራከራቸውን እና ፍርዴ ቤቱም በመጀመሪያ ዯረጃ የመቃወሚያ ነጥቦች ሊይ ክሱን ከሰማ በኃሊ ይዘቱ ከሊይ
የተመሇከተውን ብይን መስጠቱን የመዝገቡ ግሌባጭ ያመሇክታሌ፡፡

የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዙህ ጉዲይ አመሌካች አከራካሪውን ቤት ከቀዴሞ ባሇቤታቸው ከ1ኛ ተጠሪ ጋር
የነበራቸው ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኃሊ 1ኛ ተጠሪ መሸጣቸው አግባብ ስሊሌሆነ በአጠቃሊይ የተፈጸመው የሽያጭ
ውሌ ይፍረስሌኝ በማሇት አመሌካች ያቀረቡት ክስ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69(2) ዴንጋጌ መሰረት በይርጋ
ይታገዲሌ ተብል በስር ፍርዴ ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ተጠሪዎቹ ባለበት ሇማጣራት ይቻሌ ዘንዴ ጉዲዩ
ሇሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመዯረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተሇዋውጠዋሌ፡፡የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ
ይዘት ከሊይ የተመሇከተው ሲሆን እኛም በክርክሩ እሌባት ማግኘት የሚገባቸው፡-
1. ክርክር ያስነሳውን ቤት ከአመሌካች ጋር በተግባር ከተሇያየን በኃሊ በግሌ ጥረቴ እና ዯካሜ ያፈራሁት
የግሌ ሀብቴ እንጂ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የጋራ ንብረት አይዯሇም በማሇት 1ኛ ተጠሪ በሰበር
መሌሳቸው ያቀረቡት የክርክር ነጥብ ሕጋዊ ተቀባይነት ያሇው ነው ወይስ አይዯሇም?
2. ሇክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ሊይ የተዯረገው የሽያጭ ውሌ ይፍረስሌኝ በማሇት አመሌካች
ያቀረቡት ክስ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69(2) ዴንጋጌ መሰረት በሁሇት ዓመት ይርጋ የሚታገዴ ነው
በማሇት በስር ፍርዴ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ሕጋዊ መሰረት ያሇው ነው ወይስ አይዯሇም?
3. በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 33(2) መሰረት አመሌካች በ4ኛ ተጠሪ ሊይ ክስ ሇማቅረብ
የሚያስችሌ መብት ያሇቸው መሆኑን አሊረጋገጡም በማሇት በስር ፍርዴ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ
ሕጋዊ ተቀባይነት ያሇው ነው ወይስ አይዯሇም?
የሚለ ነጥቦች መሆናቸውን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን
አሇመሆኑን ከእነዚሁ ነጥቦች አንጻር መርምረናሌ፡፡
አብርሃም ዮሀንስ

በዚህም መሰረት የመጀመሪያውን ነጥብ በተመሇከተ ክርክር ያስነሳውን ቤት አመሌካች ከአገር ከወጡ በኃሊ ነገር
ግን ጋብቻው ከመፍረሱ በፊት በግሌ ዴካም እና ጥረት ያገኙት የግሌ ሀብት እንጂ የጋብቻ ውጤት እንዲሌሆነ
በመግሇጽ 1ኛ ተጠሪ በከፍተኛ ፍርዴ ቤት የተከራከሩ ቢሆንም አከራካሪው ቤት ጋብቻው ጸንቶ ባሇበት ጊዜ
የተፈራ በመሆኑ እና ከፍቺ ውሳኔ በኃሊም የጋራ ንብረት ተጣርቶ ውሳኔ ያሌተሰጠበት በመሆኑ በቤተሰብ ሕጉ
አንቀጽ 62 እና 63 መሰረት የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት ስሇመሆኑ ግምት የሚወሰዴበት መሆኑን እና 1ኛ
ተጠሪም ሇዚህ ግምት ተቃራኒ የሆነ ሁኔታ ስሇመኖሩ አሇማስረዲታቸውን ከፍተኛ ፍርዴ ቤት በብይኑ ሊይ
በግሌጽ በማስፈር በዚህ ረገዴ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክር ውዴቅ ማዴረጉን የመዝገቡ ግሌባጭ
ያመሇክታሌ፡፡ይህም አከራካሪው ቤት የ1ኛ ተጠሪ የግሌ ሀብት እንዲሌሆነ የስር ፍርዴ ቤት ውሳኔ ያሳረፈበት
መሆኑን መገንዘብ የሚያስችሌ ነው፡፡1ኛ ተጠሪ በዚህ ረገዴ በተሰጠባቸው ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ያቀረቡት ይግባኝ
ስሇመኖሩ ወይም ሇጠቅሊይ ፍርዴ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡት መስቀሌኛ ይግባኝ ስሇመኖሩ የመዝገቡ
ግሌባጭ አያመሇክትም፡፡በዚህ ሰበር ዯረጃም ያቀረቡት መስቀሌኛ አቤቱታ የሇም፡፡ቤቱ በጋብቻ ወቅት የተፈራ የጋራ
ሀብት ነው ተብል በተሰጠው የብይኑ ክፍሌ ሊይ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት ይግባኝ ወይም መስቀሌኛ ይግባኝ እና
መስቀሌኛ የሰበር አቤቱታ ከላሇ ዯግሞ ክርክር ያስነሳውን ቤት ከአመሌካች ጋር በተግባር ከተሇያየን በኃሊ በግሌ
ጥረቴ እና ዯካሜ ያፈራሁት የግሌ ሀብቴ እንጂ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የጋራ ንብረት አይዯሇም በማሇት 1ኛ
ተጠሪ በሰበር መሌሳቸው ያቀረቡት የክርክር ነጥብ ሕጋዊ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚችሌ አይዯሇም፡፡

ሁሇተኛውን ነጥብ በተመሇከተ አመሌካች እና 1ኛ ተጠሪ በ1982 ዓ.ም. ጋብቻ ፈጽመው እስከ 1991 ዓ.ም.
አብረው ከኖሩ በኃሊ አመሌካች ከኢትዮጵያ ውጪ መሄዲቸው፣1ኛ ተጠሪ ጋብቻው እንዱፈርስ አቤቱታ አቅርበው
በፌዳራሌ የመጀመሪያ ዯረጃ ፍርዴ ቤት በመዝገብ ቁጥር 21055 በ26/11/1996 ዓ.ም. የፍቺ ውሳኔ መሰጠቱ፣1ኛ
ተጠሪ አከራካሪውን ቤት ሇ2ኛ እና ሇ3ኛ ተጠሪዎች በብር 30,000 በሽያጭ ያስተሊሇፉት የፍቺ ውሳኔው ከተሰጠ
ከስዴስት ዓመታት በኃሊ በ21/04/2002 ዓ.ም. በተዯረገ ሽያጭ ውሌ መሆኑ እና 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች
በተራቸው ቤቱን በብር 640,000 በሽያጭ ሇ4ኛ ተጠሪ ያስተሊሇፉት ከሁሇት ዓመታት በኃሊ በ26/03/2004 ዓ.ም.
በተዯረገ ውሌ መሆኑ በመዝገቡ የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ናቸው፡፡በእርግጥ አመሌካች ክሱን ሲያቀርቡ 1ኛ ተጠሪ
በጋብቻ ወቅት የተፈራውን ንብረት ከአመሌካች ፈቃዴ ውጪ በሽያጭ ያስተሊሇፉት ከቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 69(1)
ዴንጋጌ ውጪ መሆኑን በክሳቸው ሊይ ጠቅሰው መከራከራቸውን እና 1ኛ ተጠሪም ሇክሱ በሰጡት መሌስ ሽያጩ
የተከናወነው ጋብቻው ከፈረሰ በኃሇ በመሆኑ የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69(1) ሇጉዲዩ አግባነት የሇውም በማሇት
መከራከራቸውን የመዝገቡ ግሌባጭ ያመሇክታሌ፡፡በላሊ በኩሌ እንዯ የአግባብነቱ ሇክርክሩ አግባብነት አሇው ወይም
የሇውም የሚለትን ሕግ እና የሕግ ዴንጋጌ ጨምሮ ተከራካሪ ወገኖች ይዯግፈናሌ የሚለትን የየራሳቸውን ክርክር
የማቅረብ መብት ያሊቸው መሆኑ እንዯተጠበቀ ሆኖ በፍርዴ ቤት ሇቀረበ አንዴ ክርክር ተፈጻሚነት ያሇውን ሕግ
የመሇየት እና ተፈጻሚ የማዴረግ ኃሊፊነት እና ዴርሻ በመሰረቱ የፍርዴ ቤቶች መሆኑ የሚያከራክር
አይዯሇም፡፡በመሆኑም አመሌካች በስር ፍርዴ ቤቶች የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69(1) ዴንጋጌ ክርክሬን ይዯገፍሌኛሌ
በማሇት ጠቅሰው ተከራክረው እያሇ አሁን በሰበር ዯረጃ ዯግሞ ይህንን ሀሳባቸውን በመሇወጥ ሇጉዲዩ አግባብነት
ያሇው የቤተሰብ ሳይሆን የፍትሐብሔር ሕጉ ዴንጋጌዎች ናቸው በማሇት ያቀረቡት መከራከሪያ በስር ፍርዴ
ቤቶች ያሌተነሳ አዱስ ክርክር በመሆኑ በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 329(1) መሰረት ተቀባይነት
አብርሃም ዮሀንስ

ሉሰጠው አይገባም በማሇት ተጠሪዎቹ ያቀረቡት ክርክር ሕጋዊ መሰረት ያሇው ነው ሇማሇት የሚቻሌ ሆኖ
አሌተገኘም፡፡

የስር ከፍተኛ ፍርዴ ቤት ሇብይኑ መሰረት ያዯረገው የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69 የሚገኘው በቤተሰብ ሕጉ የጋብቻ
ውጤትን በሚመሇከተው ምዕራፍ ሶስት ክፍሌ ሶስት ስር ሲሆን ይህ ክፍሌም ጋብቻው ጸንቶ በሚገኝበት ጊዜ
በንብረት በኩሌ የሚያስከትሇውን ሕጋዊ ውጤት የሚገዛ ነው፡፡በተያዘው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን በሽያጭ
ያስተሊሇፉት ጋብቻው እንዱፈርስ በፍርዴ ቤት ውሳኔ ካሰጡ በኃሊ ሲሆን በቤተሰብ ሕጉ ምዕራፍ አምስት
በተመሇከቱት ዴንጋጌዎች መሰረት ጋብቻው በፍቺ ከፈረሰ በኃሊ የባሌና ሚስቱ ተጣርቶ ውሳኔ ያረፈበት
ስሇመሆኑም በ1ኛ ተጠሪ በኩሌ የቀረበ ክርክርና ማስረጃ የሇም፡፡1ኛ ተጠሪ ቤቱን በሽያጭ ያስተሊሇፉት ጋብቻው
ከፈረሰ በኃሊ ከሆነ ዯግሞ የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69 (1) “ም” ሆነ (2) ዴንጋጌዎች ሇክርክሩ ተፈጻሚነት
ሉኖራቸው የሚችሌበት አግባብ አይኖርም፡፡ አግባብነት ያሇው የጋራ ንብረትን ሇማስተሊሇፍ የጋራ በሇሀብትን
ፈቃዴ የሚያስፈሌግ ስሇመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ.1266 የተመሇከተው ዴንጋጌ ነው ፡፡አንዯኛው የቀዴሞ ተጋቢ በጋብቻ
ውስጥ የተፈራ ነው የሚሇውን ንብረት በተመሇከተ ክስ ሇማቅረብ የሚችሇው ጋብቻው በፍቺ ከፈረሰበት ቀን
ጀምሮ በምን ያህሌ ጊዜ ውስጥ እንዯሆነ በቤተሰብ ሕጉ ውስጥ በተሇይ የተመሇከተ ዴንጋጌ ባሇመኖሩ በዚህ
ዓይነት ጉዲዮች ሊይ ተፈጸሚነት ሉኖረው የሚገባው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1677(1) ዴንጋጌ መሰረት
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 ዴንጋጌ የተመሇከተው አጠቃሊይ የአስር ዓመት የይርጋ ጊዜ ነው፡፡በተያዘው
ጉዲይ ጋብቻው በፍቺ የፈረሰው በ1996 ዓ.ም. ሲሆን አመሌካች ክሳቸውን ያቀረቡት አስር ዓመት ከማሇፉ በፊት
በመሆኑ ክሱ በይርጋ የሚታገዴ ነው ሇማሇት የሚቻሌ አይሆንም፡፡አመሌካች ሕገወጥ ናቸው በማሇት እንዱፈርሱ
የዲኝነት ጥያቄ ያቀረቡባቸው የሽያጭ ውልች የተዯረጉት ከፍቺ ውሳኔ በኃሊ በመሆኑ እና በዚህ ዓይነቱ የዲኝነት
ጥያቄም ተፈጻሚነት ያሇው የይርጋ ዘመን በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 የተመሇከተው የአስር ዓመት ጊዜ
በመሆኑ በዚህ ረገዴ አመሌካች ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄም በይርጋ የሚታገዴ አይዯሇም፡፡1ኛ ተጠሪ ከአመሌካች
ጋር የነበረን ግንኙነት የተቋረጠው በ1994 ዓ.ም. በመሆኑ ክሱ በአስር ዓመት ይርጋ የሚታገዴ ነው በማሇት በስር
ፍርዴ ቤት የተከራከሩ ከመሆኑም በሊይ በሰበር መሌሳቸውም ሊይ አመሌካች ላሊ ትዲር መስርተው ከሀገር ውጪ
እና በሀገር ውስጥ ንብረት አፍርተዋሌ በማሇት ተከራክረዋሌ፡፡ ይሁን እንጂ ጋብቻው የፈረሰው ግራ ቀኙ በተግባር
ተሇያይተው የየራሳቸውን ኖሮ መምራት ጀምረዋሌ በሚሌ የግንኙነት ሁኔታ ሳይሆን በፍቺ ውሳኔ በመሆኑ
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1846 ዴንጋጌ መሰረት የይርጋው ዘመን መቆጠር የሚጀምረው ጋብቻው በፍቺ
ከፈረሰበት ቀን ጀምሮ እንጂ 1ኛ ተጠሪ ግንኙነቱ በተጨባጭ ተቋርጧሌ ከሚለበት ከ1994 ዓ.ም. ጀምሮ
አይዯሇም፡፡ ክርክር ካስነሳው ቤት ውጪ አመሌካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የነበራቸው ጋብቻ ጸንቶ በነበረበት ጊዜ
የተፈራ በአመሌካች እጅ የሚገኝ ላሊ ንብረት አሇ መባለ 1ኛ ተጠሪን ተገቢውን የመብት ጥያቄ ሇማቅረብ
የሚያስችሊቸው ከሚሆን በቀር ክርክር ባስነሳው ቤት ሊይ አመሌካች የሚያቀርቡትን የመብት ጥያቄ የሚያስቀረው
አይዯሇም፡፡

የሁሇተኛው ጭብጥ ክርክር ሲጠቃሇሌ ሇክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ሊይ የተዯረገው የሽያጭ ውሌ ይፍረስሌኝ
በማሇት አመሌካች ያቀረቡት ክስ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69(2) ዴንጋጌ መሰረት በሁሇት ዓመት ይርጋ የሚታገዴ
ነው በማሇት በስር ፍርዴ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ሕጋዊ መሰረት ያሇው ነው ሇማሇት የሚቻሌ ሆኖ አሌተገኘም፡፡
አብርሃም ዮሀንስ

ሶስተኛውን ጭብጥ በተመሇከተ ሇክሱ መነሻ በሆነው ነገር ወይም ክሱ በተመሰረተበት ሀብት ሊይ ጥቅም ወይም
መብት ያሇው መሆኑ ካሌተረጋገጠ በቀር ማናቸውም ሰው ክስ ማቅረብ የማይፈቀዴሇት ስሇመሆኑ በፍትሐብሔር
ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 33 (2) ስር የተመሇከተ ሲሆን በተያዘው ጉዲይ አመሌካች ክሳቸውን በ4ኛ ተጠሪ ሊይ
ያቀረቡት የጋራ ባሇሀብት የሆንኩበትን ቤት ከፈቃዳና እውቅናዬ ውጪ 1ኛ ተጠሪ ሇ2ኛ እና ሇ3ኛ
ተጠሪዎች፣እንዱሁም 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ዯግሞ ሇ4ኛ ተጠሪ በሽያጭ ያስተሊሇፉት አሊግባብ ስሇሆነ ውልቹ
ፈርሰው ቤቱ ይመሇስሌኝ በማሇት ነው፡፡ ጉዲዩን በመጀመሪያ ዯረጃ የተመሇከተው ፍርዴ ቤት በክስ አቀራረብ ዯረጃ
አመሌካች በ4ኛ ተጠሪ ሊይ ጭምር ክስ ሇማቅረብ የሚያስችሌ መብት ያሊቸው መሆኑን ከተቀበሇ በኃሊ በመጨረሻ
ግን አመሌካች በ4ኛ ተጠሪ ሊይ ክስ ሇማቅረብ የሚያስችሌ መብት የሊቸውም ከሚሌ ዴምዲሜ ሊይ ሉዯረስ የቻሇው
አመሌካች በ1ኛ፣በ2ኛ እና በ3ኛ ተጠሪዎች ሊይ ያቀረቡት የውሌ ይፍረስሌኝ ክስ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69 (2)
መሰረት በሁሇት ዓመት ይርጋ የሚታገዴ መሆኑን በምክንያትነት በመያዝ ነው፡፡ቀዯም ሲሌ በሁሇተኛው ጭብጥ
የውሳኔ ክፍሌ ውስጥ እንዯተገሇጸው አመሌካች በ1ኛ፣በ2ኛ እና በ3ኛ ተጠሪዎች ሊይ ያቀረቡት የውሌ ይፍረስሌኝ
ክስ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69 (2) መሰረት በሁሇት ዓመት ይርጋ የሚታገዴ ነው በሚሌ በስር ፍርዴ ቤቶች
ተሰጥቶ የነበረው ውሳኔ በዚህ ችልት የተሇወጠ በመሆኑ አመሌካች በ4ኛ ተጠሪ ሊይ ክስ ሇማቅረብ የሚያስችሌ
መብት የሊቸውም ሉባሌ የሚችሌበት ሕጋዊ ምክንያት የሇም፡፡2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ከ4ኛ ተጠሪ የፈጸሙት
የሽያጭ ውሌ ሉፈርስ ይገባዋሌ ወይስ አይገባውም? የሚለ እና ተያያዥ ጉዲዮች ዯግሞ በግራ ቀኙ ክርክር እና
አግባብነት ባሇው ሕግ መሰረት በፍሬ ጉዲይ ክርክር ዯረጃ በቀጣይ የክርክር ሂዯት ውሳኔ የሚሰጥባቸው
ይሆናለ፡፡በመሆኑም በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 33(2) መሰረት አመሌካች በ4ኛ ተጠሪ ሊይ ክስ
ሇማቅረብ የሚያስችሌ መብት ያሊቸው መሆኑን አሊረጋገጡም በማሇት በከፍተኛ ፍርዴ ቤት የተሰጠው የብይን
ክፍሌ ሉታረም የሚገባው ነው፡፡

ሲጠቃሇሌ ሇክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ሊይ የተዯረገው የሽያጭ ውሌ ይፍረስሌኝ በማሇት አመሌካች ያቀረቡት
ክስ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69(2) ዴንጋጌ መሰረት በሁሇት ዓመት ይርጋ የሚታገዴ ነው በማሇት እና
በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 33(2) መሰረት አመሌካች በ4ኛ ተጠሪ ሊይ ክስ ሇማቅረብ የሚያስችሌ
መብት ያሊቸው መሆኑን አሊረጋገጡም በማሇት በስር ፍርዴ ቤቶች የተሰጠው የውሳኔ ክፍሌ መሰረታዊ የሕግ
ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተሇው ውሳኔ ተሰጥቶአሌ፡፡

ው ሳ ኔ

1. በፌዳራሌ ከፍተኛ ፍርዴ ቤት ዴሬዲዋ ምዴብ ችልት በመዝገብ ቁጥር 08233 በ18/08/2005 ዓ.ም.
ተሰጥቶ በፌዳራሌ ጠቅሊይ ፍርዴ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁጥር 90876 በ04/02/2006 ዓ.ም.
በውሳኔ የጸናው ብይን በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽልአሌ፡፡

2. ሇክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ሊይ የተዯረገው የሽያጭ ውሌ ይፍረስሌኝ በማሇት አመሌካች ያቀረቡት


ክስ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69(2) ዴንጋጌ መሰረት በሁሇት ዓመት ይርጋ የሚታገዴ ነው በማሇት እና
በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 33(2) መሰረት አመሌካች በ4ኛ ተጠሪ ሊይ ክስ ሇማቅረብ
የሚያስችሌ መብት ያሊቸው መሆኑን አሊረጋገጡም በማሇት የተሰጠው የብይኑ ክፍሌ ተሽሮአሌ፡፡
አብርሃም ዮሀንስ

3. አመሌካች የይፍረስሌኝ የዲኝነት ጥያቄ ያቃረቡባቸው ውልች የተዯረጉት ጋብቻው በፍቺ ከፈረሰ በኃሊ
በመሆኑ በጉዲዩ ሊይ ተፈጻሚነት ያሇው የይርጋ ዘመን በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 የተመሇከተው
የይርጋ ዘመን እንጂ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69 (2) የተመሇከተው የይርጋ ዘመን አይዯሇም በማሇት
ወስነናሌ፡፡
4. አመሌካች ክሱን ያቀረቡት ጋብቻው በፍቺ ከፈረሰበት ቀንም ሆነ ውልቹ ከተዯረጉበት ቀን ጀምሮ አስር
ዓመት ሳይሞሊው በመሆኑ ክሱ በይርጋ የሚታገዴ አይዯሇም በማሇት ወስነናሌ፡፡
5. አመሌካች በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 33(2) መሰረት በ4ኛ ተጠሪ ሊይ ጭምር ክስ ሇማቅረብ
የሚያስችሌ መብት አሊቸው በማሇት ወስነናሌ፡፡
6. ሇክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የጋራ ሀብት ነው በሚሌ የተሰጠው የብይኑ ክፍሌ
አሌተነካም፡፡
7. የግራ ቀኙን የፍሬ ጉዲይ ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶ እና መርምሮ ውሳኔ ይሰጥበት ዘንዴ ጉዲዩ ሇፌዳራሌ
ከፍተኛ ፍርዴ ቤት ዴሬዲዋ ምዴብ ችልት እንዱመሇስ በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 341(1)
መሰረት ወስነናሌ፡፡
8. በዚሁ መሰረት መፈጸም ያስችሇው ዘንዴ የውሳኔው ግሌባጭ ይሊክሇት፡፡
9. የሰበር ክርክሩ ያስከተሇውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ፡፡
10. ውሳኔ ያገኘ ስሇሆነ መዝገቡ ተዘግቶአሌ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዲኞች ፊርማ አሇበት፡፡


ሩ/ሇ

You might also like