You are on page 1of 25

ቀን 16/02/2015 ዓ.

ለፋይናንስ እና ፈንድ አስተዳደር


አ.ብ.ቁ.ተ
ጉዳዩ፡-ለቤት ሐራጅ የጋዜጣ ማስታወቂያ ክፍያ እንዲፈጸም ስለመጠየቅ
አቶ ብርሃኑ ተስፋዬ የተባሉ የብድር ደንበኛ ብድር በወቅቱ ባለመመለሳቸው በተከሰሱበት የአ
ፈጻጸም ክስ በፍርድ አፈጻጸም መዝገብ ቁጥር 37940 ለዋስትና ተይዞ የነበረ የኮንደሚኒየም ቤት በሐራጅ
እንዲሸጥ በሚል የሐራጅ ማስታወቂያ በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዲታወጅ ትዕዛዝ የተሰጠ በመሆኑ ለኢትዮጲያ
ፕሬስ ድርጅት 2,643.52 /ሁለት ሺ ስድስት መቶ አርባ ሶስት ብር ከ 52/100/ ብር ለመክፈል ለቀን
17/02/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ከክፍላችሁ ገንዘብ ከፋይ እንድትመድቡ እና ክፍያ እንዲፈጸም
እጠይቃለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር
ቀን 24/12/2014 ዓ.ም

ለማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም ዳይሬክቶሬት


አ.ብ.ቁ.ተ
ጉዳዩ፡-የኮፒ ማሽን ጥገና እንዲደረግ ስለመጠየቅ ይሆናል፤
በተቋሙ የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ክፍል አገልግሎት እየሰጠ ይገኝ የነበረው የኮፒ እና የፕሪንተር ማሽን
ብልሽት የገጠመው እና ማሽኑ ስራ ያቆመ በመሆኑ ለስራ በጣም የተቸገርን ስለሆነ አስቸኳይ ጥገና በእናተ
በኩል እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡
ከሰላምታ ጋር

ብርሃኑ ቦንሳ
የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተወካይ

ቀን 24/12/2014 ዓ.ም

ለፋይናንስ እና ፈንድ አስተዳደር


አ.ብ.ቁ.ተ
ጉዳዩ፡-ለቤት ሐራጅ የጋዜጣ ማስታወቂያ ክፍያ እንዲፈጸም ስለመጠየቅ
አቶ ብርሃኑ ተስፋዬ የተባሉ የብድር ደንበኛ ብድር በወቅቱ ባለመመለሳቸው በተከሰሱበት የአ
ፈጻጸም ክስ በፍርድ አፈጻጸም መዝገብ ቁጥር 37940 ለዋስትና ተይዞ የነበረ የኮንደሚኒየም ቤት በሐራጅ
እንዲሸጥ በሚል የሐራጅ ማስታወቂያ በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዲታወጅ ትዕዛዝ የተሰጠ በመሆኑ ለኢትዮጲያ
ፕሬስ ድርጅት 2,118.82 /ሁለት ሺ አንድ መቶ አስራ ስምንት ብር ከ 82/100/ ብር ለመክፈል ለቀን
25/12/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ከክፍላችሁ ገንዘብ ከፋይ እንድትመድቡ እና ክፍያ እንዲፈጸም
እጠይቃለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር

እርገቱ ፈንታ

በአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ


ለየሰው ሃይል ልማትና ሃብት አስተዳደር
አዲስ አበባ
ጉዳዩ ፤- የፍርድ ቤት ውሳኔ ስለማሳወቅ፤
አቶ ተክሌ አሊ የተባሉ የተቋሙን ቤት ተከራይ የሆኑ ውዝፍ የቤት እዳ ባለመክፈላቸው ምክኒያት ክስ
ይመስረትባቸው በሚል ወደ ህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ክፍል መላካችሁ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም
በተጠየቀው መሰረት በፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተባቸው እና ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ የውሳኜውን ትክክል ግልባጭ
07 ገጽ ኮፒ የላክን ስለሆነ ተከሳሹ እንደፍርዱ እንዲፈጽሙ በውሳኔው መሰረት እንዲፈጸም እንድታደርጉ ሆኖ
በውሳኔው መሰረት ለማስፈጸም የማይቻል ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተከታትላችሁ እንድታሳውቁን
አሳስባለሁ ፡፡
ከሰላምታ ጋር

በአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ


ለየሰው ሃይል ልማትና ሃብት አስተዳደር
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- ተሽከርካሪ እንዲመደብ ስለመጠየቅ ፤
አቶ ብርሃኑ ተስፍዬ የተባሉ
በአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ
ለቂርቆስ አካባቢ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- የክስ መዝገብ ላክን ይመለከታል፤
ከዚህ ቀደም አቶ ወንደሰን መንግስቱ ተበደሪ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ስዩም ዋስ በመሆን የተቋሙ የብድር
ደንበኛ ሲሆኑ የነበሩ ከሳሽ በሆኑበት መዝገብ በክርክሩ ጣልቃ ገብተን በተከራከርንበት ጊዜ የቤት ቁጥር
ስህተት በመኖሩ ምክኒያት በወቅቱ የነበረው ባለሙያ አስተካክሎ ወደ ክርክሩ መግባት ሲገባው ይህን
ባለማድረጉ ከክርክሩ የወጣን ሲሆን ከዚያ በኋላ በሌላ ጊዜ በድጋሚ ወደ ክርክሩ እንድንገባ የጣልቃ ገብ
አቤቱታ አቅርበን የፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የቂርቆስ ምድብ ጉዳዩን አይቶ ወደ ክርክሩ እንድንገባ ፈቅዶልን ነበር
ነገር ግን ተከሳሾች ይግባኝ በመጠየቃቸው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር ከክርክሩ
እንድንወጣ ስላደረገን ለፌ/ጠቅ/ፍርድ ቤት በሶስት ዳኞች ለሚታየው ችሎት ይግባኝ ብለን ይግባኙ
አያስቀርብም ተብሎ ተመልሶል ፡፡ በመሆኑም በእናንተ በኩል ውሉን መሰረት ያደረገ ክስ በማዘጋጀት
እንድትከሱ እና ብድሩን እንድታስመልሱ አሳውቃለሁ፡፡
በአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ
ለየሰው ሃይል ልማትና ሃብት አስተዳደር
ጉዳዩ፡- አጀንዳ እንዲታተም ስለመጠየቅ ይሆናል፤
የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ለ 2015 ዓ.ም የስራ ዘመን ለፍርድ ቤት ቀጠሮ መያዣ አገልግሎት
የሚያገለግል የቀጠሮ መያዣ አጀንዳ ለ 40 ባለሙያ የሚያገለግል እንዲታተም እየጠየኩ የአጀንዳውን
አይነት እና መጠን የሚያሳይ ናሙኛ ተያይዞ የተላከ መሆኑን አሳውቃለሁ ፡፡
በአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ
ለየሰው ሃይል ልማትና ሃብት አስተዳደር
ጉዳዩ፡- የባለሙያ ቁጥር ስለማሳወቅ ፤
የቦርሳ ግዢን በተመለከተ በሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስር ያሉ የሴት እና የወንድ ባለሙያዎችን
ቁጥር እንድናቀርብ በተጠየቀው መሰረት ሴት 9 ወንድ 22 በድምሩ 31 ባለሙያ ያሉ መሆኑን
አሳውቃለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር

አናኦል ፈሪድ
የህግ አገልግሎት ዳሬክቶሬት
በአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ
ለየሰው ሃይል ልማትና ሃብት አስተዳደር
ጉዳዩ፡- የቦርሳ ግዢን ይመለከታል ፤
የቦርሳ ግዢን በተመለከተ ከዚህ ቀደም የግዢ ጥያቄ ማቅረባችን ይታወቃል ነገር ግን የቦርሳ አይነቱን
በመለየት እንዲሁም የወንድ የሴት በሚል በመለየት እንድታቀርቡ በሚል በጠየቃችሁን መሰረት በሕግ
አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስር ያሉ የሴት 9 እና የወንድ 22 በድምሩ 31 ባለሙያዎች ያሉ ሲሆን የሴት
እና የወንድ ከቆዳ የተሰራ ቦርሳ ለመዝገብ መያዣ የሚያገለግል ሴት 9 ወንድ 22 በድምሩ 31 ባለሙያ
ያሉ መሆኑን አሳውቃለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር

አናኦል ፈሪድ
የህግ አገልግሎት ዳሬክቶሬት
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ለፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍ/አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
አዲስ አበባ
ጉዳዩ ፡-ምላሽ ስለመስጠት ይሆናል፤
በቀን 03/10/2014 ዓ.ም በቁጥር 38116 በሆነ በተላከ ደብዳቤ በፍ/ባለመብት መሰረት አራጌ እና በፍ/ባለእዳ
አቶ አያሌው ደሳለኝ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 177165
በ 19/5/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁጥር 1764 የሆነው
ቤት በሐራጅ ተሸጦ በውሳኔው መሰረት እንዲከፈል ትዕዛዝ ሰጥቷል ፤ስለሆነም ትዕዛዙን እንድናስፈጽም
እንድንችል ከተቋማችሁ ብድር የተወሰደበት ስለሚሆን ከየትኛው ቅርንጫፍ፣ ምንያክል እዳ እንዳለበት
እንዲሁም እዳው ተከፍሎ አልቆ ከሆነ ይህንኑ በመግለጽ ምላሽ እንድንልክላችሁ መጠየቃችሁ ይታወቃል ፡፡
በዚሁ መሰረት ጠቋማችን ባደረገው ማጣራት ከዚህ ቀደም ከተቋማችን ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከወረዳ
08 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኤ.ኤ.ም.ኬ ለተባለው ማህበር ለተበደረው 500,000/አምስት መቶ ሺ ብር / ብድር አቶ
አያሌው ደሳለኝ በስማቸው የተመዘገበ የቤት ካርታ ቁጥር 10/108/2829100 የሆነውን ቤት ለዋስትና አሲዘው
የነበረ ሲሆን ነገርግን አሁን እዳው ሙሉ ለሙሉ ተከፍሎ የተጠናቀቀ መሆኑን በተቋማችን ወረዳ 08 ቅ/ጽ/ቤት
በቁጥር አቃ/ቃ/ወ 08/0468/04 በቀን 15/10/2014 በተጻፈ ያሳወቁን ስለሆነ ከላይ በተጠቀሰው ቤት ላይ
የተቋሙ እዳ የሌለበት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ከሰላምታ ጋር

በአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ


ለየሰው ሃይል ልማትና ሃብት አስተዳደር
ጉዳዩ፡- መረጃ ስለመስጠት ይሆናል ፤
ፕላኔት ኮንሰልታንሲ ኃ/የተ/የግል ማህበር በተቋሙ ዋና መ/ቤት 6 ኛ ወለል የቢሮ ቁጥር 613 ላይ ተከራይ ሲሆኑ
ውዝፍ የቤት ኪራይ ያለባቸው ስለሆነ እዳቸውን ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ክስ ተመስርቶ እንዲከፍሉ
እንዲደረግ በሚል በቀን 20/07/2013 ዓ.ም ወደ ህግ ክፍል መላካችሁ ይታወቃል በዚሁ መሰረት ጉዳዩን
ለማየት ስልጣን ላለው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ክስ በቀን 24/09/2013 ዓ.ም
መስርተን ፍርድ ቤቱ ሲያከራክር ከቆየ በኋላ ነሃሴ/ 04/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በኪራይ የያዙትን
የቢሮ ቁጥር 613 የሆነውን ለቀው እንዲያስረክቡ እንዲሁም ውዝፍ የቤት ኪራይ ብር 115,703/አንድ መቶ
አስራ አምስት ሺ ሰባት መቶ ሶስት ብር/ ለተቋሙ ይክፈሉ በሚል ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ከውሳኔው በኋላ ተከሳሽ
ተቋሙን ለመክፈል ጊዜ ይሰጠኝ እንዲሁም የቢሮ ቁጥር 613 ለቅቄ ሌላ ጠበብ ያለቢሮ ይሰጠኝ በሚል
በመጠየቃቸው እዳቸውን የሚከፍሉበት የማራዘሚያ ጊዜ የተፈቀደላቸው መሆኑን በተቋሙ ማኔጂንግ ዳሬክተር
በኩል የተነገረን በመሆኑ አፈጻጸሙ ዘግይቶ ቆይቶ በቀን 22/06/2014 ዓ.ም የአጻጸም ክስ ተከፍቶ ፍርድ ቤቱ
በቀን 6/8/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ ውዝፍ የቤት ኪራይ ገንዘብን በተመለከተ የፍርድ ባለእዳ
በፍርድ ባለመብት ስም በባንክ አስገብተው ደረሰኝ አቅርበዋል ሲል አረጋግጦ ወስኗል፤ ነገር ግን የተባለውን
ውዝፍ የቤት ኪራይ ገንዘብ በተቋሙ አካውንት ገቢ ሳይደረግ የቀረ እንደሆነ እና ከተረጋገጠ መዝገቡን
የማንቀሳቀስ መብት ያለን መሆኑን እያሳወቅን ቢሮ በተመለከተ በመጅመሪያ ክርክር ወቅት ይዘውት የነበረውን
የቢሮ ቁጥር 613 ለቀው ያስረከቡ ስለሆነ አሁን ይዘው ስላለው ቤት ማስለቀቅ ከተፈለገ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ
፣ ሌሎች ክስለመመስረት የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ተሟልተው ሲቀርቡ በሌላ ክስ የሚታይ መሆኑን እያሳወኩ
ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ በቀን 04/12/2013 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ 02 ገጽ እና በቀን 6/08/2014 ዓ.ም የተሰጠ
የአፈጻጸም ትዕዛዝ 02 ገጽ በድምሩ 04 ገጽ አባሪ አድርገን የላክን መሆናችንን አሳውቃለው ፡፡
ከሰላምታ ጋር

በአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ


ለየሰው ሃይል ልማትና ሃብት አስተዳደር
ጉዳዩ፡-መጥሪያ እንዲያደርሱ ስለማሳወቅ፤
የተቋማችን ቤት ተከራይ አቶ ተክሌ አሊ የቤት ኪራይ በወቅቱ ባለመክፈላቸው ምክኒያት እንዲከሰሱ
በጠየቃችሁት መሰረት በተከሰሱበት ክስ ፍርድ ቤቱ ለ 09/12/2014 ዓ.ም መልስ ይዘው እንዲቀርቡ ያዘዘ
በመሆኑ 07 ገጽ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የላክን ስለሆነ ከተጠቀሰው ቀጠሮ ቀን በፊት መጥሪያው በእናንተ በኩል
ደርሶ ስለመድረሱ ተከሳሹ የፈረመበትን መተማመኛ ለህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት እንድትልኩ አሳውቃለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር
በኢትዮጲያ ጉሙሩክ ኮሚሽን ቃሊቲ ቅርንጫፍ
ለውርስ መጋዘን ስራ ሂደት
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- ምላሽ መስጠትን ይመለከታል፤
በቁጥር 15u0/n68/1163/14 በቀን ግንቦት 26/2014 ዓ.ም በተጻፈ
በኢትዮጲያ ፌዴራል ፖሊስ
ለወንጀል ምርመራ ቢሮ
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- ምላሽ መስጠትን ይመለከታል፤
በቀን 02/10/2014 ዓ.ም በቁጥር መ/ወ/ም 145/5542/14 በተጻፈ ለወንጀል ምርመራ ይረዳን ዘንድ
የማህበራችው ላፍቶ ቅርንጫፍ ደንበኞች እነ ሱራፌል በቀለ ከተጠረጠሩበት ሙስና ወንጀል ጉዳይ ጋር
ለመሃበራችሁ ቀረቡ ስድስት ሃሰተኛ ኦርጅናል ሊብሬ እና አሽከርካሪ እና ተሸከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር
ባለስልጣን ተሸከርካሪዎች በእዳ መታገዳቸውን የሚገልጹ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪዎች የተዘጋጁ ስድስት
ኦሪጅናል ደብዳቤዎች መጠየቅ አስፈልጎአል በሚል ከ 1-4 በተራ ቁጥር በመዘርዘር መጠየቃችሁ ይታወቃል
በዚሁ መሰረት፡-
1. ባለስልጣኑ ቦሌ ቅርንጫፍ

በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ


ለየሙስና ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- ምላሽ መስጠትን ይመለከታል፤
በቀን 04/09/2014 ዓ.ም በቁጥር የፍ/ሚ/ou/3882 በተጻፈ ወ/ሮ ዝርትሁን ሀሰን በተባለች
በተቋማችሁ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ቅ/ጽ/ቤትየገንዘብ አሰባሰብ እና ክፍያ ኦፊሰር ሆና
በምትሰራበት ወቅት ፈጽማለች
ለናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት
ለናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ አባኮራ ቅርንጫፍ
አዲስ አበባ፤
ጉዳዩ፡- በድጋሚ የተሰጠ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ
ከዚህ ቀደም በቁጥር አተ/876/አመ 21/6877 በቀን 01/06/2015 ዓ.ም በተጻፈ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ
የኩባንያችሁ ደንበኛ የሆኑት YAS COMPUTER ACCESSORIES TRADE ለአዲስ ብድር እና ቁጠባ
ተቋም አ.ማ አገልግሎት የሚውል Document (Copy) Scanner ግዢ ለመፈጸም በውስጥ ግዢ ተጋብዘው
አሸናፊ ሆነው ነበር፡፡ነገርግን ባሸነፉት መሰረት የእቃውን ሳምፕል ያቀረቡ ቢሆንም በኤም አይ ኤስ
ጋይሬክቶሬት ሲታይ የቀረበው ሳምፕል በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለጸው ሞዴል ጋር የማይገኛኝ በመሆኑ
እንዲቀየር ተደርጓል ፡፡በዚሁ መሰረት ድርጅቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው ሞዴል መሰረት እቃውን ገቢ
ያላደረገ በመሆኑ በቀን 07/20
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
ለበወንጀል የተገኘ ሃብት ወ/ም/ማስተባበሪያ
ጉዳዩ፡- ምላሽ መስጠትን ይመለከታል ፤
በቀን 23/05/2014 ዓ.ም በቁጥር አፓወመ/01/20065/14 በተጻፈ ደብዳቤ በተቋማችን ውስጥ በተለያዩ ሃላፊነት
ተመድበው ሲሰሩ በነበሩ ሰራተኞች የተቋሙን መመሪያ እና አሰራር በመጣስ አለ አግባብ ክፍያ ፈጽመዋል በሚል
ባቀረብነው አቤቱታ መሰረት ምርመራ ለማጣራት እንዲመች በሚል መረጃ እንድንልክላችሁ መጠየቃችሁ ይታወቃል
በዚሁ መሰረት ፡-
1. የተቋማችን የመመስረቻ ጹሁፍ ፣ ቃለ-ጉባኤ፣ እንዲሁም መመሪያ ኮፒ፣
2. በኦዲት ሪፖርት ወቅት ጉድለት የተገኙባቸው ሰነዶች ፣ደረሰኞች እና የክፍያ ሰነዶች ኮፒ፣
3. በኦዲት ወቅት መተማመኛ የተፈረመበት ሰነድ ኮፒ ፣
4. የተጠሪጣሪዎች የስራ መዘርዝር ኮፒ፣
በተጨማሪም የተጠረጠሩት ግለሰቦች አሁን ያሉበትን የስራ መደብ በተመለከተ፡-
1. አቶ አሸብር ብርሃኑ( የለቀቁ)
2. አቶ ሰለሞን ማና (የለቀቁ)
3. አቶ ሉሉ ተስፋዬ (የለቀቁ)
4. አቶ ሸዋንግዛው ማናዬ( የለቀቁ)
5. አቶ ጌትነት ደምሴ (ፋይናስ ዳይሬክተር)
6. አቶ ብሩ ሹምዬ (መካከለኛ ንብረትና ስርጭት ባለሙያ)
7. ወ/ሮ እየሩሳሌም አድማሱ (መካከለኛ ፋይናስ ባለሙያ)
8. አቶ ያለው ተካ
9. አቶ ዘላለም አሻግሬ/መካከለኛ የሂሳብ ሰራተኛ/
እንዲሁም ተቋማችንን በመወከል ዝርዝር ቃል የሚሰጥ ተወካይ በተመለከተ የተቋሙ የሕግ ማማከር እና ሊቲጌሽን
ክፍል ሃላፊ የሆኑትን አቶ እርገቱ ፈንታው የተባሉትን የላክን መሆናችንን እንገልጻለን ፡፡
ከሰላምታ ጋር

ቀን 10/06/2014 ዓ.ም

ለአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ


የሰው ሃይል ሃብት አስተዳደር
ጉዳዩ፡- መረጃ ስለመጠየቅ
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው የተቋሙ የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች የንበሩ፡-
1. አቶ አሸብር ብርሃኑ
2. አቶ ሰለሞን ማና
3. አቶ ሉሉ ተስፋዬ
4. አቶ ሸዋንግዛው ማናዬ
5. አቶ ጌትነት ደምሴ
6. አቶ ብሩ ሹምዬ
7. ወ/ሮ እየሩሳሌም አድማሱ
8. አቶ ያለው ተካ
9. አቶ ዘላለም አሻግሬ
ከዚህ ቀደም ይሰሩበት በነበረው የስራ መደብ የነበራቸውን የስራ መዘርዝር እንዲሁም በአሁኑ ግዜ እየሰሩ
ያለበትን የስራ መደብ የተቋሙ የህግ አገልግሎት ክፍል በክስ ሂደት ለማስረጃነት የፈለገው ስለሆነ
እንድትልኩልን እንጠይቃለን፡፡
ከሰላምታ ጋር

ቀን 30/05/2014 ዓ.ም

ለአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ


የሰው ሃይል ሃብት አስተዳደር
ጉዳዩ፡- መረጃ ስለመጠየቅ
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው የተቋሙ የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች የንበሩ፡-
1. አቶ አሸብር ብርሃኑ
2. አቶ ሰለሞን ማና
3. አቶ ሉሉ ተስፋዬ
4. አቶ ሸዋንግዛው ማናዬ
5. አቶ ጌትነት ደምሴ
6. አቶ ብሩ ሹምዬ
7. ወ/ሮ እየሩሳሌም አድማሱ
በአሁኑ ጊዜ እየሰሩበት ያሉትን የስራ መደብ በጹሁፍ እንድገልጹልን የህግ አገልግሎት ክፍል በክስ ሂደት
ለማስረጃነት የፈለገው ስለሆነ በጹሁፍ እንድገልጹልን እንጠይቃለን፡፡
ከሰላምታ ጋር

ቀን 04/09/2014 ዓ.ም

ለአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፤- ትብብር ስለመጠየቅ

የሰራተኛ ብድር እንዲፈቀድለኝ መጠየቄ የሚታወቅ ነው ፤ሆኖም ያላገባሁ መሆኔን የሚገልጽ


ማስረጃ እንዳቀርብ የተጠየኩ ቢሆንም የክፍለ ሃገር ልጅ በመሆኔ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት
መታወቂያ የሌለኝ ስለሆነ ወሳኝ ኩነት በመሄድ ያላገባሁ መሆኔን የሚገልጽ ማስረጃ ማግኘት
አልቻልኩም፤ስለሆነም ተቋሙ ችግሩን ተረድቶ ላገባሁ መሆኔ የሚታወቅ በመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ
ሳያስፈልገኝ በልዩ ሁኔታ ታይቶ ብድሩ እንዲፈቅድለኝ እጠይቃለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር
በአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ
ለየሰው ሃይል ሃብት አስተዳደር
አዲ/ብ/ቁ/ተ
ጉዳዩ፡- መረጃ ስለመጠየቅ
በቀን 14/10/2014 ዓ.ም በቁጥር 13139/ከ 6/4050 በተጻፈ ደብዳቤ በዋና መስሪያ ቤት 6 ኛ ወለል ላይ ቢሮ
ቁጥር 610 ን ተከራይቶ የሚገኘው ሬት ኢንጅነሪንግ/ትዊንክል ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኃ/የተ/የግል ማህበር
በተመለከተ ወዝፍ የቤት ኪራይ እንዲከፍሉ ፣የውል ዘመን ከመጠናቀቁ በፊት ከተቋሙ ጋር ውል እንዲያድሱ
እንዲሁም በህግ ይዘቱ ዙሪያ ተቋማችን ጣልቃ የሚገባበት መንገድ በስራ ክፍላችሁ በኩል እንዲመቻች ቢደረግ
ስትሉ በደብዳቤ መጠየቃችሁ ይታወቃል ነገር ግን የጠየቃችሁትን የህግ ሂደት ለመጀመር ፡-
1.ተቋሙ ከሬት ኢንጅነሪንግ/ትዊንክል ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጋር ያደረገው የቢሮ ኪራይ
ውል፣፣
2. ለሬት ኢንጅነሪንግ/ትዊንክል ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኃ/የተ/የግል ማህበር የቢሮ ኪራ በወቅቱ ባለመክፈላቸው
ምክኒያት እንዲከፍሉ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ፣
3. “በህግ ሂደቱ ዙሪያ ተቋማችን ጣልቃ የሚገባበት ሁኔታ በስራ ክፍላችሁ በኩል እንዲመቻች” በሚል
ለጠየቃችሁት ጣልቃ ለመግባት እንዲያመች በዚህ ጉዳይ የተያዘ የፍርድ ቤት ክርክር ካለ ሂደቱን የሚያሳይ
ማስረጃ ካለ በማሟሟላት እንድትልኩልን እንጠይቃለን፡፡
ከሰላምታ ጋር

ቀን 05/07/2015 ዓ.ም

የውስጥ ማስታወሻ

በአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አ.ማ


ለሰው ሃይል ሃብት አስተዳደር
አዲ/ብ/ቁ/ተ
ጉዳዩ፡- ቢሮ ክፍት እንዲደረግ ስለመጠየቅ፤
አቶ ግሩም አሰፋ በተከሰሱበት የአፈጻጸም ክስ ጉዳይ በተቋሙ ዋና መ/ቤት ህንጻ 6 ኛ ወለል ላይ የቢሮ ቁጥር
606 ውስጥ ይገኙ የነበሩ የቢሮ ቁሳቁሶች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት ተቋሙ የተረከበ መሆኑ የሚታወቅ
ነው፡፡ ስለሆነም የፌዴራል የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ባለሙያ እቃዎቹን በሃራጅ ለመሸጥ እንዲያመች
ሃሙስ መጋቢት 7/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፤30 ሰዓት ላይ በአካል ወደ ተቋማችን ለመምጣት ቀጠሮ የተያዘ
በመሆኑ እቃዎቹ ያሉበት ቢሮ በእለቱ ክፍት እንዲደረግ እና በእለቱ ለሚመጣው የፌዴራል የፍርድ አፈጻጸም
ዳይሬክቶሬት ባለሙያ ተሽከርካሪ እንዲመደብ እንጠይቃለን፡፡
ከሰላምታ ጋር

You might also like