You are on page 1of 5

የአ/ከ/ም/ፅ/መ/ቁ/ 01680/13

የፍ/ቤት/መ/ቁ/ 94895
የመምሪያ /ፖ/መ/ቁ 762/13
በፌደራል ከፍተኛ ፍቤ/ት
ለአራዳ ይግባኝ ሰሚ ችሎት
አዲስ አበባ

ይግባኝ ባይ ፡- የፌ/ጠ/ዐ/ህግ አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት


መልስ ሰጪ ፡- 1 ኛ፡ መስፍን ባሎ በላይነህ
አ/ሻ ኦሮሚያ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን አሸዋ ሜዳ
በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ -185 እና ተከታዮቹ የቀረበ የይግባኝ ቅሬታ አቤቱታ ነው፡፡
መግቢያ
ሀ/ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን የማየት የፍሬነገርና የህግ ስልጣን አለው፡፡
ለ/ የፌ/መደ//ፍ/ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት መ/ቁ 94895 ነው
ሐ/ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት ውሳኔ የሰጠው በቀን 10/09/13 ዓ.ም ነው፡፡ ግልባጭ
እንዲሰጠን የጠየቅነው 12/09/13 ነው፡፡
መ/ ግልባጩ የተሰጠን በቀን 12/9/13 ዓ.ም ነው፡፡
ሠ/ ይግባኙ የይርጋ ጊዜው ከማለፉ በፊት የቀረበ ነው፡፡
1. የይግባኙ አመጣጥ ባጭሩ
የአሁን ይግባኝ ባይ በመልስ ሰጪ ላይ ክስ ያቀረብን ሲሆን ይህም መልስ ሰጩ የሌላ ሰው አካል ወይም
ጤንነት የመጠበቅ የአሽከርካሪነት የሙያ ግደታ እያለበት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 559(2)ን
በመተላለፍ በቀን 25/03/2013 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 12፡00 ስዓት ሲሆን በአ/ከ/ክ/ከ/ወረዳ 08 ቀበሌ
10/11/12 ልዩ ቦታው መካነ ሰላም ሆቴል አካባቢ በሚያሽከረክረው የሰ/ቁ. 2-A-56568 አ/አ የሆነ ቪትስ
መኪና ለእግረኛ ቅድሚያ በመከልከል የግል ተበዳይ ማርታ ተክሌን የቀኝ እግሯን በመግጨት የቀኝ እግር
ሶስተኛ ጣት የአጥንት ስብራት እንዲደርስባት ያደረገ በመሆኑ በፈጸመው በቸልተኝነት ከባድ የአካል ጉዳት
ማድረስ ወንጀል ክስ አቅርበናል፡፡ ይህን ክስ ያስረዱልናል ያልናቸውን ሁለት ቀጥተኛ የሰው ምስክሮች 1
የሙያ ምስክር እና የሰነድ ማስረጃን በተመለከተ የህክምና ማስረጃ የአደጋ ፕላን እና የመንጃ ፍቃድ
እንዲሁም መልስ ሰጭ በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 27(2) እና 35 መሰረት የሰጠውን የተከሳሽነት ቃል አያይዘን
አቅርበናል፡፡
ይህን ክሳችን የሚስረዱልን ከሰነድ ማስረጃ በተጨማሪ የሰው ምስክሮች አቅርበን አሰምተን የስር ፍርድ
ቤቱ ተበዳይ ከተከሳሽ መኪና ጋር በቆመበት ሄዳ መጋጨቷ ስለተረጋገጠ መልስ ሰጪ በቸልተኝነት ጉዳት
አድርሷል ሊያስብል አይችልም በማለት በወ/መስስሕቁ 141(1) መሰረት መከላከል ሳያስፈልገዉ በነጻ
ይሰናበት በማለት ብይን ተሰጥቷል፡፡
ይህ ይግባኝ ሊቀርብ የቻለውም የስር ፍ/ቤት በነጻ በማሰናበት በሰጠው ብይን ነው፡፡
2. የይግባኝ ቅሬታ ነጥቦች
 የስር ፍርድ ቤት ማስረጃ ሲመረመር ከእነ ሙሉ ይዘቱ መመርመር ሲገባው ያቀረብናቸዉን
የሰነድ ማስረጃወች በሙሉ ያልመረመረልን እና ያልመዘነልን ሲሆን ክሳችን እንዲያስረዱልን
ካቀረብናቸው የሰነድ ማስረጃወች መካከል ተከሳሹ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27(2) መሰረት
የመኪና ስፖኪዮ ሳልመለከት ገጭቻታለሁ በማለት ያመነ ሲሆን እንዲሁም
በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕቁ. 35 መሰረትም በችሎት ቀርቦ በመኪና ገጭቶ ጉዳት ያደረሰባት ለመሆኑ
የእምነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጅ የስር ፍርድ ቤት ሁለቱንም የሰነድ ማስረጃወች
ያልመረመረልን ሲሆን እንዲሁም ይህን በመደገፍ ያያያዝናቸውን የህክምና ማስረጃ
ሳይመረመር ብይን መስጠቱ ተገቢነት የሌለው ነው ይባልልን፡፡
 ያቀረብናቸዉን የሰው ምስክሮች ቃል ምርመራን በተመለከተ 1 ኛ ምስክራችን የግል ተበዳይ
ስትሆን በቀጥታ በተከሳሹ አድራጎት ጉዳት የደረሰባት መሆኑን ገልጻ የመሰከረች ሲሆን
ፍጥነቱን አላውቀውም በመኪናው የኋላ ጎማ ነው የገጨኝ ብላለች ይሄ ደግሞ በክሱ ላይ በግራ
የፊት ለፌት ጎማ ነው የተገጨችዉ የሚል በመሆኑ ክስ እና ማስረጃው የሚጣጣም አይደለም
የሚል ነው፡፡ ይሁን እንጅ ተበዳይ በዋና ጥያቄም የደረሰባትን ጉዳት በተመለከተ እንደ ክሱ
ያስረዳች ሲሆን ያስመዘገብነውም ጭብጥ እንደክሱ ያስረዱልናል የሚል በመሆኑ እና በክሱም
ተበዳይ የግል ተበዳይ መሆኗን እንደምታስረዳ በግልጽ ተቀምጦ እያለ በመስቀለኛ ጥያቄ
ስትመሰክር በቀጥታ የመለሰች ሲሆን ነገር ግን የገጨኝ የኋላ ጎማዉ ነው ማለቷ ሲታይ ከክሱ
ጋር የማይጣጣም ነው ሊባል የሚችል ሳይሆን ተበዳይ የደረሰባትን ጉዳት በሚገባ ያስረዳች
ሲሆን ነገር ግን ጉዳቱ ሲደርስባት የተፈጠረውን ቅጽበታዊ ድርጊት ልታስረዳ የማትችል
በመሆኑ እና ይህን ድርጊትም በቀጥታ ታስረዳለች ባላልንበት ሁኔታ የማይጣጣም ምስክርነት
ነው ሊባል የሚችል አይደለም፡፡ ከዚህ ባለፈም ተበዳዩ በድጋሚ ጥያቄ ሲመልሱ ጉዳቱ
ሲደርስብኝ መኪናዉን አላየሁትም በማለት ያስተካከሉ በመሆኑ መስቀለኛ ጥያቄውን ብቻ
ወስዶ ከክሱ ጋር ማነጻጸር ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ችሎቱ የተበዳይን ሙሉ የምስክርነት ቃል
ሊመዝን ይገባል ይበልልን፡፡
 የአደጋ ፕላኑን በተመለከተ የስር ፍርድ ቤት ተበዳይ መንገድ ስታቋርጥ የመኪና ቦዲ ጋር
እንደተጋጨች ያሳያል በማለት አረጋግጦ በውሳኔው ላይ አስፍሯል፡፡ ይሁን እንጅ የአደጋ ፕላኑ
በቀጥታ እንደሚያሳየው የመኪናውን እና የተበዳይን አቅጣጫ እንዲሁም መንገዱን የሚያሳይ
እንጅ የስር ፍርድ ቤት እንዳለው የተበዳይን የጉዳት ቦታ የሚያሳይ አይደለም ምልክቶችም
ሙያዊ በመሆናቸው ይህን ፕላን የሚያስረዳ የሙያ ምስክር አስቀርበን ያሰማን ሆኖ እያለ
ችሎቱ የሙያ ምስክሩ ከሰጠው ቃል ውጭ በእራሱ ፕላኑን ተረድቶ መወሰኑ ተገቢነት የሌለው
በመሆኑ ውድቅ ያድርግልን፡፡
 2 ኛ ምስክርን ተበዳይ ከተከሳሽ መኪና ቦዲ ጋር ተጋጭታለች መኪናው የቆመ ነበር ብሎ
መስክሯል ይህ ደግሞ ተበዳይ በእራሷ ከቆመ መኪና ጋር እንደተጋጨች ያሳያል ይህ ደግሞ
የተከሳሽን ቸልተኝነትን አያሳይም በማለት በውሳኔው ላይ አስፍሯል፡፡ ይሁን እንጅ ሁለተኛ
ምስክር በወቅቱ ተከሳሽ መኪና ጋቢና ውስጥ የነበረ እና መንገድ ላይ ከተከሳሽ በነበራቸው
ትውውቅ አሳፍሮት እየሄደ እያለ በሹፌሩ በኩል ከመኪናው ጋር ጓ የሚል ድምጽ ሰምቶ ሲያይ
ተበዳይ እግሬን ተጎዳሁ ብላ ስትጮህ ወዲያው መስማቱን አስረድቶ ወዲያው ወደ ህክምና
እንደወሰዳትም መስክሯል፡፡ በፍ/ማ/ጥያቄም መኪናው ፍጥነት ላይ አልነበረም ተዘጋግቶ ነበር
ቆሞ ነበር በማለት መስክሯል፡፡ ይሁን እንጅ ይህ የምስክርነት ቃል በገለልተኝነት የተሰጠ
ስለመሆን አለመሆኑ ሲመረመር ምስክሩ ከተከሳሽ ጋር ትውውቅ ያለው መሆኑ በወቅቱ ተከሳሽ
ትብብር ሲያደርግለት የነበረ መሆኑ እንዲሁም በሹፌሩ በቀኝ በኩል የተቀመጠ ሆኖ እያለ በግራ
በኩል ለደረሰ አደጋ የመኪና ግጭት ድምጽ ሰምቶ ግጭቱ ተበዳይ ላይ መድረሱ ከተረጋገጠ
በኋላ መንገድ ስታቋርጥ የነበረች ተበዳይ በእራሰዋ ገጭታ ጉዳት ደረሰባት በማለት መመዘኑ
ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ማስረጃ ምዘናው ውድቅ ይደረግልን፡፡
 በተጨማሪም የግጭት ድምጽ በግራ በኩል ከመኪናው ቦዲ ሰማሁ ማለቱ መኪናው እግሯ ላይ
ጉዳት አላደረሰም የደረሰ ጉዳትም የለም የማያስብል ነው፡፡

3. ከፍ/ቤቱ የሚንጠይቀው ዳኝነት


 የተከበረው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤቱ መልስ ሰጪውን በነፃ በብይን ማሰናበቱ ተገቢነት
የሌለው ነው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ብይን እንዲሽርልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
 መልስ ሰጪ በስር ፍርድ ቤት የተከሰሰበትን የህግ ድንጋጌ አንቀጽ 559(2)ን እንዲከላከል
በማለት ብይን ሰጥቶ ለስር ፍርድ ቤት አንዲልክልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ጴጥሮስ አራጌ
የፌ/ጠ/ዐቃቤ ህግ
ዐቃቤ ህግ
ከይግባኝ ሰሚ ችሎቱ የምንጠይቀው ዳኝነት
ከላይ በይግባኝ ቅሬታ ነጥቦችን ያነሳናቸውን የህግና የፍሬ ነገር ክፍተቶች መሠረታዊ በመሆናቸው ፡-
1. የስር ፍ/ቤት በወ/ህጉ አንቀፅ 555/ለ/ የቀረበው ክስ በወ/ህጉ አንቀፅ 556/1/ ስር የቀየረበት ብይን
እንዲሻርልን ፡፡
2. መልስ ሰጭ በወ/ህጉ አንቀፅ 555/ለ/ ስር ጥፋተኛ እንዲባልልንና አስተማሪና ተገቢ ቅጣት
እንዲወሰንልን በማክበር እንጠይቃለን፡፡

ግርማው መኮንን
በፌ/ጠ/ዐ/ህግ
ዐ/ህግ

You might also like