You are on page 1of 72

የመዝገብ ቁጥር

Reg. No. 1146

የኢትዮጵያ
ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)

በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች


(ከ2011 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም)

39ኛ መደበኛ መግለጫ

ግንቦት 2014 ዓ.ም

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org i
ዋና ጽ/ቤት፡ አዲስአበባ

አ.አ ስታዲየም አጠገብ፣ላሊበላ ሬስቶራንት ጎን፣ ሣኅለ ሥላሴ ሕንፃ 8ኛ ፎቅ፣ቢሮ ቁጥር 19

ኢ-ሜይል:info@ehrco.org

ድረገጽ: www.ehrco.org

ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/ehrco1/

ትዊተር፡ https://www.twitter.com/ehrcoethio

ቴሌግራም፡ https://t.me/ehrco

የፖስታ ሳጥን ቁጥር 2432

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

የሰብዓዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ መምሪያ፡ አዲስ አበባ

ስልክ: (+251) 011 558-2387

ኢሜይል:info@ehrco.org

ቀጠና / ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች

ደቡብ ኢትዮጵያ ቀጠና፡ሐዋሳ - ስ.ቁ (+251) 046 220-4500፣ ፖ.ሳ.ቁ 360

ሰሜን ኢትዮጵያ ቀጠና፡ባሕርዳር- ስ.ቁ (+251) 058 220-0240፣ ፖ.ሳ.ቁ 1115

ጎንደር-ስ.ቁ (+251) 058 2 11 39 06)

ምዕራብ ኢትዮጵያ ቀጠና፡ነቀምቴ - ስ.ቁ (+251) 057 660-2664፣ ፖ.ሳ.ቁ 463

ጋምቤላ- ስ.ቁ

ምሥራቅ ኢትዮጵያ ቀጠና፡ድሬደዋ - ስ.ቁ (+251) 025 411 6845፣ ፖ.ሳ.ቁ 2596

ጂግጂጋ- ስ.ቁ (+251) 025 2 78 42 40

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቀጠና፡አዲስ አበባ- ስ.ቁ (+251)011 551-7704፣ ፖ.ሳ.ቁ 2432

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org i
ማውጫ
የኢትዮጵያ አስተዳድራዊ ካርታ ............................................................................................................................ 1
መግቢያ ........................................................................................................................................................ 2
የመደበኛ መግለጫው ዓላማ ............................................................................................................................... 4
በምርመራው ሂደት ተጥሰው የተገኙና በመደበኛ መግለጫው የተካተቱ የሕግ ማዕቀፎች.................................................. 4
የምርመራው ስነ-ዘዴ ........................................................................................................................................ 4
የምርመራ ሥራው ውስንነትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች .................................................................................................. 4
ክፍል አንድ .................................................................................................................................................... 6
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ውስጥ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተፈፀሙ የተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ............................... 6
ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ........................................................................................................ 6
አማራ ክልል ................................................................................................................................................. 16
ክፍል 2....................................................................................................................................................... 24
በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ........................................................................................ 24
1. ሲዳማ ክልል እና ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ........................................................................... 24
1. ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ................................................................................................. 24
2. ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሼ ዞን ሶጌ እና ያሶ ወረዳ የተፈናቀሉ ተፈናቃዮች ....................................................... 31
3. በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ...................................................................... 31
6. ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ሸዋ ዞን (ዳኑ፣ ኖኖ እና ጅባት ወረዳ) እና ምስራቅ ወለጋ ዞን (ቢሎ ቦሼ ወረዳ).. 46
8. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ...................................................................................................................... 53
ክፍል ሁለት ................................................................................................................................................. 55
የህግ ትንተና እና ግዴታዎች .............................................................................................................................. 55
በህይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነት እና የንብረት መብቶች ጋር ተያይዞ ያሉ ደንጋጌዎች ....................................................... 55
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አስመልክቶ ያሉ ህጎችና ግዴታዎች .................................................................................... 57
ከምርጫ ጋር ተያይዞ ያሉ ድንጋጌዎች................................................................................................................... 59
ክፍል ሦስት.................................................................................................................................................. 62
ማጠቃለያና ምክረ-ሀሳብ.................................................................................................................................. 62

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org i
የኢትዮጵያ አስተዳድራዊ ካርታ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 1
መግቢያ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በበጎ አድራጎትና ማኅበራት አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት አገር
በቀል ድርጅት ሆኖ በምዝገባ ቁጥር 1146 ከ02/11/11 ዓ.ም ጀምሮ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዳግም
ተመዝግቦ በሕጋዊነት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ነው፡፡ ኢሰመጉ
ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ነጻና ገለልተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተከላካይ ተቋም ሲሆን፣ ዓላማውም በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲያዊ
ሥርዓት መጎልበት፣ ለሕግ የበላይነት መስፈንና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የበኩሉን አስተዋጽዖ ለማድረግ ነው፡፡

ኢሰመጉ ከማናቸውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የኃይማኖት ተቋም፣ የብሔረሰብ ቡድን፣ ማህበራዊ መደብ ወዘተ የማይወግን፣
ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ነጻና ገለልተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተከላካይ ተቋም ነው። ኢሰመጉ የቆመው ለዴሞክራሲያዊ
ሥርዓት መጎልበት፣ ለሕግ የበላይነት መስፈንና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ነው። ኢሰመጉ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት
በቆመላቸው ዐበይት ዓላማዎች ላይ በመመርኮዝ ሁለንተናዊ፣ ሐገራዊና ሕዝባዊ ተልዕኮ በመያዝ በነደፋቸው በርካታ
የመርሐ-ግብር ተግባራት አማካኝነት ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ የሕግ የበላይነትና ሕጋዊ ሥርዓት እንዲሰፍንና በኢትዮጵያ
ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲኖር የበኩሉን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ይገኛል።

ዓበይት ዓላማዎቹንና ተልዕኮውን ለማሳካት ኢሰመጉ ፈርጀ ብዙ የሆኑ የመርሀ ግብር ተግባራትን ያከናውናል። ከእነዚህም
መካከል አንዱ በየደረጃው ለሚገኙ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትና ለሕዝብ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርትና ሥልጠና
መስጠት ነው። የመንግሥት አካላት በዋነኛነት የግዴታዎች ተሸካሚ፣ ሕዝብም በዋነኛነት የመብቶች ባለቤት
እንደመሆናቸው መጠን፣ የመንግሥት አካላትም ሰብዓዊ መብቶችን የማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት ግዴታቸውን
በዕውቀት፣ በችሎታና በጽኑ እምነት ላይ ተመርኩዘው እንዲወጡ፣ ሕዝብም እንዲሁ በዕውቀት፣ በችሎታና በጽኑ እምነት ላይ
ተመርኩዞ መብቱን እንዲያስከብር ኢሰመጉ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርትና ሥልጠና ይሰጣል። በተጨማሪም ኢሰመጉ
በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ይሠራል፤ ውጤቶቹን በተለያዩ የምክክር መድረኮችና በልዩ ልዩ
የመገናኛ መንገዶች ያሠራጫል፣ የውትወታ ሥራዎችንም ያከናውናል። የኢሰመጉ መለያውና ግንባር ቀደም ተግባሩ
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን አያያዝና ሁኔታ መከታተል፣ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ማጣራትና
በማስረጃ የተደገፉ መግለጫዎችን ማውጣት ነው።

ኢሰመጉ በሚያወጣቸው መግለጫዎች ሁሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጎጂዎች ፍትሕና ካሣ እንዲያገኙ፣ የጥሰት
ፈጻሚዎች በሕግ እንዲጠየቁና ወንጀል ሠርቶ በነጻ መሄድ እንዲያበቃ፣ ከእያንዳንዱ ክስተት ትምህርት ተወስዶ ለወደፊቱ
ጥንቃቄና ተገቢው የፖሊሲና የአፈጻጸም እርማት እንዲደረግ ሲወተውትና ሲጠይቅ ቆይቷል፣ አሁንም በመጠየቅ ላይ ነው፤
ለወደፊትም በዚሁ ይቀጥላል።

ከኢሰመጉ የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ተግባራት መካከል፣ የሕግ ታራሚዎችን መጎብኘትና ሰብዓዊ መብቶቻቸው
መጠበቃቸውን መከታተል፣ የፍርድ ቤቶችን ሂደት ፍትሀዊነት መከታተል እንዲሁም በመንግሥት የወጡና የሚወጡ ሕጎችን
ይዘትና አፈጻጸማቸውን ከሰብዓዊ መብቶች አንጻር መመርመር ይገኙበታል ከእነዚህ በተጓዳኝ ኢሰመጉ በተለይ የሰብዓዊ
መብቶች ጥሰት ሰለባ ለሆኑ ዜጎች የተለያየ ደረጃና መልክ ያለው የሕግ ድጋፍ ይሰጣል። በእስካሁኑ ቆይታው ኢሰመጉ 39
መደበኛ መግለጫዎችና 150 ልዩ መግለጫዎችን በተጨማሪም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን
ይፋ አድርጓል። ኢሰመጉ አሁንም ቢሆን፣ ሁኔታና አቅም በፈቀደለት መጠን የሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ የሕግ የበላይነትና
የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ እውን እንዲሆን ካለው የጸና ዓላማ አኳያ በመሥራት ላይ ይገኛል።

ኢሰመጉ ከማናቸውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የኃይማኖት ተቋም፣ የብሔረሰብ ቡድን፣ ማህበራዊ መደብ ወዘተ የማይወግን፣
ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ነጻና ገለልተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተከላካይ ተቋም ነው። ኢሰመጉ የቆመው ለዴሞክራሲያዊ
ሥርዓት መጎልበት፣ ለሕግ የበላይነት መስፈንና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ነው። ኢሰመጉ ለሶስት አስርት ዓመታት
በቆመላቸው ዐበይት ዓላማዎች ላይ በመመርኮዝ ሁለንተናዊ፣ ሐገራዊና ሕዝባዊ ተልዕኮ በመያዝ በነደፋቸው በርካታ
የመርሐ-ግብር ተግባራት አማካኝነት ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ የሕግ የበላይነትና ሕጋዊ ሥርዓት እንዲሰፍንና በኢትዮጵያ
ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲጎለብት የበኩሉን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ይገኛል።

በሃገራችን ኢትዮጵያ ለዘመናት የቆየውን አብሮ የመኖር አኩሪ ባህላችንን የሚንዱ ተደጋጋሚ የጎሳ ግጭቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 2
በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ተከስተው ከፍተኛ ጥፋት መድረሱ ይታወቃል በቅርብ ጊዜ ደግሞ በደቡብ ክልል የጎሳ ግጭቶችን
ማስተዋል የተለመደ ሆኗል ይህም ለተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዳርጓል፡፡ ከጎሳ ግጭቶች ባለፈ በመንግስት አካላት ወይም
በግለሰቦች በስህተትም ወይም ሆን ተብሎ የግል ሀብት ለማካበት በተለያዩ ግለሰቦች በሚደረግ ጥረት ውስጥ የተለያዩ የሰብዓዊ
መብቶች ጥሰት ተፈጥሯል፡፡

ምርጫ የአንድ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገለጫ ባህሪ ነው፤ ምርጫ ትክክለኛ የሚሆነው መራጩ ከአንድ
በላይበሆኑ አማራጮች ላይ እንዲወስን እድል የሚሰጥ ሲሆን ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት የአንድ መንግስት ስልጣን
የሚመነጨውም ከህዝብ ነው፡፡ ሕዝቡ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ እንዲችል ይህንን ለማስፈፀም የሚያስችሉ ብቃት
ያላቸው የምርጫ አስፈፃሚ ተቋማትና ዲሞክራሲያዊ የሆኑ የማስፈፀሚያ ሕጎች ሊኖሩ ይገባል፡፡

በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 8 ቁጥር 3 ላይ የሕህዝቦች ሉዓላዊነታቸው የሚገለጸው በዚህ ሕገ-መንግስት መሰረት
በሚመርጧቸው ተወካዮች በቀጥታ በሚያደረደረጉት ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካኝነት ይሆናል በማለት ሉዓላዊ ስልጣን
የህዝብ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ አንቀፅ 38 ንዑስ አነቀጽ 1 ላይም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም ፣ በዘር፣ በሃይማኖት
በፖለቲካ፣ ወይም በሌላ አመለካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሰረተ ልዩነት ሳይደረግበት የመምረጥ እና የመመረጥ
መብት እንዳለው ይደነግጋል ይህንን ዲማክራሲያዊ መብቱን ነፃና ፍትሐዊ በሆነ የምርጫ አፈፃፀም ሙሉ መብቱ እንዲከበር
በማሰብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 111/87 ተቋቁሟል፡፡ የምርጫ ቦርዱ እስከ መስከረም 2014
ዓ.ም ድረስ በሃገር አቀፍና በክልል ደረጃ 5 ምርጫዎች አካሂዷል፡፡

ኢሰመጉ ከላይ እንደተገለጽው በሃገር አቀፍና በክልል ደረጃ እስከ ዛሬ ድረስ በሚካሄዱ ምርጫዎች አፈፃጸም በመታዘብ
ውጤቱን ለህዝብና ለሚመለከታቸው አካላት ሲያሳውቅ ቆይቷል፡፡ በአሁኑም ስድስተኛ ምርጫ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ
ጊዜና በድህረ ምርጫ የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ገለልተኛ በመሆን ጥናቶች አድርል፡፡ ይህንንም ሲያደርግ የቆየው
የተዘጋጁ ሪፖርቶች በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅት እና በድሕረ ምርጫ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በማስረጃ
አስደግፎ በማቅረብ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ይፋ ለማውጣት፣ የመብት ጥሰት ፈጻሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ
ተገቢው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ መንግስትን ለመወትወት፣ ለምርምር ስራዎች እንዲጠቅም፣ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች
ጥሰቶች ዳግም እንዳይፈጸሙ ለማሳሰብ፣ ለትምህርት አልፎም ለማመሳከሪያነት እና ሌሎች ተመሳሳይ ጥቅሞችን ይሰጣል
ከሚል እምነት ነው፡፡

ይሄንን ምክንያት በማድረግ ኢሰመጉ 6ኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ በተመለከተ መደበኛ መግለጫ አውጥቷል፡፡ ይህ መደበኛ
መግለጫ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ኢሰመጉ የሰበሰባቸውን መረጃዎች ይዟል፡፡ አጣሪ ቡድኑ በተለያየ መንገድ ይህንን
መረጃ ሰብስቧል፡፡ በዋነኝነት ግን ቃለ-መጠይቅ፣ የመስክ ምልከታ፣ ከፓርቲዎች የተሰበሰበ የአቤቱታ ደብዳቤን በማጣራት
እንደግባአት ወስዷል፡፡ ይህንን የመብት ጥሰት ከዓለም አቀፍ፣ ከአህጉር አቀፍ እና ከሀገር አቀፍ ህጎች አንፃር በመመልከት ምን
አይነት የሰበዓዊ መብት ጥሰት በየት ተፈፀመ፣ ማን ፈፀመው፣ በማን ላይ ተፈጸመ፣ መቼ ተፈጸመ እንዲሁም እንዴት መፈታት
ይችላል የሚለውን ምክረ-ሐሳብ ለማስቀመጥ ሞክሯል፡፡

ይሄ ሪፖርት በአጭሩ ለማሳየት የሞከረው ከምርጫ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች የተከሰተውን የሰብዓዊ መብቶች
ጥሰት እንዲሁም በደቡብ ክልል አርባምንጭ ከተማ እና በደቡብ ብሔር ብሔረቦች እና ህዝቦች ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ ጋቶ
ቀበሌ ውስጥ በሚኖሩ የኩስሜ ማህበረሰብ አባላት ላይ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን አካቶ ይዟል፡፡ ኢሰመጉ
እንደተገነዘበውም ምርጫን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ቦታዎች ሰዎች ሞተዋል፣ አካል ጉዳት ደርሷል፣ የፓርቲ አባል
በመሆናቸው ብቻ በርካታ ሰዎች ታስረዋል እንዲሁም ንብረታቸው ወድማል፡፡

ማሳታወሻ፡ በዚህ ሪፖርት የተካተተው የሰብዓዊ መብቶቸ ጥሰት ያጠቃለለው ይህ ሪፖርት እስከተዘጋጀበት ቀን ድረስ የደረሱ
የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እና ኢሰመጉ በምርመራ ስራው በሸፈናባቸው አካባቢዎች ላይ የደረሱትን ብቻ ነው፡፡

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 3
የመደበኛ መግለጫው ዓላማ
የዚህ መደበኛ መግለጫ ዓቢይ ዓላማ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የሀገረቱ
ክፍል ውስጥ የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ከ28/12/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 04/2013 ዓ.ም ድረስ
በነበረው የምርጫ ጊዜ በመላው የኢትዮጵያ ክፍል በምርጫው አጠቃላይ ሂደት የተከናወኑ የሰብዓዊ መቶች ጥሰቶችን
በማጣራት ምን አይነት ጉዳት በማን ደረሰ የሚለውን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ነው ማለትም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ
መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) የዚህን መደበኛ መግለጫ ይዘትና ዓላማ በተፃረረ መልኩ፣ ከሕግና ከመልካም አስተሳሰብ ውጪ
ማንም እንዲጠቀምበት አይፈቅድም። ይህንንም መግለጫ ሰላምን ለማደፍረስና ከሕግ አግባብ ውጪ ሌሎች ሲጠቀሙበት
ቢገኙ ኢሰመጉ ኃላፊነትን አይወስድም፡፡ ከዚም ባለፈ የዚህም መደበኛ መግለጫ አላማ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች
ጥሰቶችን ከመረጃ ጋር በማቅረብ የመብት ጥሰቶች እንዲቆሙ እና ተመሳሳይ ጥሰቶች በድጋሚ የማይፈጸሙበት የተቋማት
ግንባታ፣ እንዲሁም የፖሊሲ፣ የሕግና የአሰራር ማስተካከያዎችና እርማቶች ከወዲሁ በተጨባጭ እንዲደረጉ መጠየቅና
መወትወት ነው።

በምርመራው ሂደት ተጥሰው የተገኙና በመደበኛ መግለጫው የተካተቱ የሕግ ማዕቀፎች


በዚህ መደበኛ መግለጫ ውስጥ ይፋ የተደረጉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ዓይነትና ዘርፍ ለመለየት፣ ለመረዳትና ለማሳየት
በዋና መሠረትነት የሚያገለግሉት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት፣ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ያሉ ሀገር አቀፍ ህጎች፣ የካምፓላ
ኮንቬንሽን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሀገር ውስጥ መፈናቀልን በመሚመለከት ያወጣው የመመሪያ መርህ
የአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውና ግዴታም የገባችባቸው የሰብዓዊ
መብቶች ዓለም አቀፍ መግለጫ፣ የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የባህላዊ
መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን እና የተለያዩ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫዎች ናቸው። የሰብዓዊ መብቶች
ጥሰቶች በየዘርፋቸው በተገለጹበት ቦታ ሀሉ እነዚህ የሕግ ማዕቀፎች በመነሻነትና በማመሳከሪያነት ተጠቅሰዋል።

የምርመራው ስነ-ዘዴ
ኢሰመጉ በምርመራው ከተጠቀመባቸው የመረጃ ምንጮች መካከል ዋነኞቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ ሰለባዎች፣ የተጎጂ
ቤተሰቦች፣ የዓይን እማኞችና ምስክሮች እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶቹ በተፈጸሙባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች የሆኑ
ሰዎች ናቸው። ዋነኞቹ የምርመራ ዘዴዎች የሠነዶች ማሰባሰብና ፍተሻ፣ በፎቶግራፍ የተደገፉ የመስክ ጉብኝቶች ግኝቶች
(ጥሰት በተፈጸመባቸው አካባቢዎች በአካል በመገኘት)፣ ከተጎጂዎችና ከምስክሮች ጋር በቦታዎቹ ላይ የተደረጉ ቃለ
መጠይቆች፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ዜጎችና አካላት ጋር የተደረጉ የቡድን ውይይቶች ሲሆኑ፤ የተገኘውን መረጃ
ትክክለኛነት ለማረጋገጥም ከጤና ተቋማት፣ ከአስተዳደርና ከፖሊስ አካላት ተጨማሪ ማስረጃ ተሰብስቧል። ኢሰመጉ በዚህ
ምርመራው የተለያዩ ማስረጃዎችን በማሰባበሰብና ጉዳቱንም በአካባቢዎቹ ተገኝቶ በመመልከት ይህንን 39ኛ መደበኛ
ሪፖርት አዘጋጅቷል። ኢሰመጉ የተለያዩ ማስረጃዎችን በመስጠት ለተባበሩት ሰዎችና መንግሥታዊ ተቋማት ምስጋናውን በዚህ
አጋጣሚ እያቀረበ በዚህ ምርመራ ወቀት የሚጠበቅባቸውን ትብብር እና ድጋፍ ያላደረጉ መንግስታዊ ተቋማት በቀጣይ
በሚኖሩ ስራዎች ላይ መረጃ የመስጠት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ኢሰመጉ ከወዲሁ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የምርመራ ሥራው ውስንነትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች


ይህ 39ኛ መግለጫ በሚዘጋጅበት ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ በተለየ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የነበረችበት ጊዜ እንደመሆኑ
መግለጫውን በማዘጀጋት ሂደት ውስጥ የተለያዩ ዓይነት ውስንነቶች እና ተግዳሮቶች አጋጥመዋል፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ
በብዙ የሐገሪቱ አካባቢዎች ይከሰቱ በነበሩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች የተነሳ ይፈጠሩ የነበሩት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች
ስፋት፣ ጥሰቶቹን ለማጣራት ከመንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መረጃዎችን ለማግኘት የነበሩት አዳጋች ሁኔታዎች፣
ጥሰቶቹ ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለማረጋጋጥ ከተጎጂዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የነበሩ የግንኙነት
መንገዶች በልዩ ልዩ ምክንያቶች መቋረጣቸው መግለጫው ጥሰቶቹ በተፈጸሙበት አፋጣኝ ጊዜ ውስጥ እንዳይወጣ
አድርጎታል፡፡ ከዚህም ባለፈ፤ ይህን መግለጫ በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ ኢሰመጉ የሚከተሉት ዋና ዋና ውስንነቶችና
ተግዳሮቶች አጋጥመውታል፡፡

 ኢሰመጉ ያለበት የገንዘብ፣ የሰው ኃይልና የምርመራ ቁሳቁስ እጥረት፣


 በአጠቃላይ በሀገሪቱ ባለው ፖለቲካዊ ሁኔታ በውጥረት እና በግጭት የተሞላ መሆኑና በኢሰመጉ የምርመራ ሠራተኞች ላይ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 4
የመንግሥት የደኅንነትና የጸጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ክትትልና ጫና ማድረጋቸው፣
 በምርመራ ሥራው በተሸፈኑት አካባቢዎች ይፈፀም የነበረው መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የደረሰው ሰብዓዊ
ቀውስ ከኢሰመጉ የማጣራት አቅም በላይ መብዛቱ፤ እንዲሁም፣
 ከፖሊስና ከሆስፒታሎች የተገኙ አንዳንድ ማስረጃዎች በደፈናው የቀረቡ በመሆናቸው ምክንያት ሟቾችን
በተመለከተ ዝርዝር ትንታኔ ለማቅረብ አለመቻል፣
 ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ካላቸው ስጋት የተነሳ ስለደረሰባቸው ሰብዓዊ
መብቶች ጥሰቶች መረጃዎችን ያለማጋራት፣
 በሀገሪቱ ያለው የጸጥታ ችግር በዋናነት በትግራይ፣ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ
ኢሰመጉ በስፋት በመንቀሳቀስ የምርመራ ስራዎችን እንዳያከናውን መገደባቸው፣
 የኢሰመጉ የምርመራ ባለሙያዎች ላይ በዋናነት በ6ተኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ በተሳተፉ ባለሙያዎች ላይ
ከመንግስት አካላት ይደርሱ የነበሩ ጫናዎች፣
 የአንዳንድ አስተዳደሮችና ባለድርሻ አካላት ተገቢውን መረጃ እና ትብብር ሊያደርጉልን አለመቻል፣
 በአንዳንድ አካባቢዎች ከጸጥታ ችግር አንጻር ይዘጉ የነበሩ መንገዶች በተፈለገው ደረጃ ተንቀሳቅሶ የምርመራ
ስራዎችን ለመስራት አዳጋች መሆን፣
 ኢሰመጉ በትግራይ ክልል ያሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ሁኔታ ለመከታተል በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ
እንዲሁም የትራንስፖርት፣ የስልክ እና የኢንተርኔት ግንኙነቶች መቋረጥ ኢሰመጉ የተለያዩ ጥረቶችን ቢያደርግም
በእነዚህ ተግዳሮቶች ምክንያት በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በበቂ ሁኔታ ለመከታተል አልተቻለም፡፡

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 5
ክፍል አንድ

በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ውስጥ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተፈፀሙ የተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች
ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል
ከህግ ውጪ የተፈጸመ ግድያ
የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 14 “ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል
ደህንነትና የነፃነት መብት አለው” ሲል ይደነግጋል፡፡ በተመሳሳይ የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 15 ማንም ሰው በህይወት የመኖር
መብት እንዳለውና ሕግ ከሚደነግገው ውጪ የመኖር መብቱን ሊያጣ እንደማይችል ተመላክቷል፡፡ ኢትዮጵያም እነዚህን ዓለም
አቀፍ እና አህጉራዊ የሰብዓዊ መብቶች ሰነዶች የተቀበለች ሀገር እንደመሆኗ ሰብዓዊ መብቶችን የማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት
ግዴታ ተጥሎባታል፡፡
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ አንቀጽ 3 “ እያንዳንዱ ሰው በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነቱ የመጠበቅ መብት ”
እንዳለው ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለችው የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳንም በአንቀጽ
6 (1) እና 9 (1) ላይ ይህንኑ መብት በማረጋገጥ፣ መንግሥታት በቃልኪዳኑ የተረጋገጡትን መብቶች በግዛታቸው
የማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት ግዴታ እንዳለባቸውም በአንቀጽ 2 (1) እና 2 (2) ይደነግጋል። የአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች
መብቶች ቻርተር አንቀጽ 4 “ማንኛውም ግለሰብ በሕይወት የመኖር መብቱና የአካሉ ደህንነት ሊከበርለትና ሊጠበቅለት
እንደሚገባና እነዚህን መብቶቹን በዘፈቀደ ሊነፈግ እንደማይችል ተመላክቷል።

ከዚህ በታች በደቡብ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች፣ ልዩ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ከተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የተሰበሰበ የመብት
ጥሰት እንደሚከተለው ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)


አቶ ኩሴ ደልቦሌ የ22 አመት ወጣት ሲሆን የኢዜማ (የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ) አባል በመሆን ያገለግል ነበር በቀን
04/09/2013 ዓ.ም በካራት ሆስፒታል አካባቢ በጸጥታ ሀይሎች ተደብድቦ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ የነበረ ቢሆንም ህይወቱ
ሊያልፍ ችሏል፡፡
ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
አቶ ግርማ ታደሰ በቀን 15/10/2014 ዓ.ም ማክሰኞ ምሽት 3፡00 ሰዓት አካበቢ ላይ በሆቴል ቤት በር ላይ ጭንቅላቱ ላይ
በድንጋይ ተመትቶ ህይወቱ ማለፉን የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የደቡብ ኦሞ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በደብዳቤ
ቁጥር ኅኢ/ደኢ/003/21/2013 በቀን 29/12/2013 ዓ.ም በላከው ደብዳቤ ገልጿል፡፡ አቶ ግርማ ታደሰ የህብር ኢትዮጵያ ፓርቲ
የዲመካ ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ ታዛቢ ነበረ፡፡

የአካል ጉዳት
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥትም በአንቀጽ 16 ሥር ‹‹ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት
አለው›› ሲል ይደነግጋል፡፡ የሰዎች የአካል ደኅንነት የመጠበቅ መብት የማይደፈርና የማይገረሰሥ መሆኑንም የሕገ መንግሥቱ
አንቀጽ 14 ያረጋግጣል፡፡
ዓለም አቀፉ የሲቪል እና ፖለቲካዊ መብቶች የቃል-ኪዳን ስምምነት በአንቀጽ 9 ሥር እንደሚደነግገው ማንኛውም ሰው አካላዊ
ደህነነቱ የተጠበቀ መሆን ይገባዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌን መንግሥት ባለማስከበሩ ምክንያት
በሚከተሉት ግለሰቦች ላይ የአካል ጉዳት ያስከተለ ድብደባና ማሰቃየት እንደተፈጸመባቸው ኢሰመጉ ያሰባሰበው መረጃ ያሳያል::
ኢዜማ (የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ)
1. አቶ ኤልያስ ዲኖቶ የ60 አመት ጎልማሳ ሲሆኑ በግብርና የሚተዳደሩ ባለትዳርና የልጆች አባት ናቸው፡፡ የኢዜማ
(የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ) አባል በመሆናቸው ብቻ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አንዱ ሲሆኑ ጉዳቱን
ያደረሰው ደግሞ የክልሉ ልዩ ሃይልና ፖሊስ ነው ከከተማ ወደ ቤታቸው በሚገቡበት ጊዜ ዱራይቴ ቀበሌ በተለምዶ ቴሎያ
ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሲደርሱ ምክንያቱን በማያውቁት ሁኔታ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ቀኝ እጃቸውን ተመተው

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 6
ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደው በህክምና ክትትል ላይ የነበሩ መሆናቸውን ማየት ተችሏል፡፡
2. አቶ ጭራቶ በሽኖ፡- በካራት ከተማ ዱራይቴ ቀበሌ የሚኖር በግብርና ሥራ የሚተዳደር የ57 ዓመት ጎልማሳ ናቸው።
ጥቃቱ የደረሰባቸው በ2013 ዓ.ም ሲሆን ጥቃቱን ያደረሱት የክልሉ ልዩ ሃይልና ፖሊስ ሲሆኑ ጥቃቱም የደረሰባቸው
እቤታቸው አካባቢ ነው፡፡ ግለሰቡ የኢዜማ አባል በመሆናቸው ብቻ በዱላና በገጀራ ድብደባ ተፈፅሞባቸው በህክምና
እርዳታ ላይ ነበሩ፡፡ ጉዳቱን ያደረሱባቸው የህግ አስከባሪዎት እራሳቸው በመሆናቸው ለማንም ምንም ብለው መክሰስ
ሳይችሉ ቀርተው እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡
3. አቶ በየነ ጊሊኖ፡- በዱራይቴ ቀበሌ የሚኖርና በግብርና ስራ የሚተዳደር የ27 ዓመት ጎልማሳ ነው። በግንቦት ወር 2013
ዓ.ም ጠዋት ላይ ወደ ቤቱ ሲገባ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ጎኑን ተመቶ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ህክምና በመከታተል ላይ
የነበረ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡
4. ኮማንደር አድማሱ ባንጫዬ የ33 ዓመት ወጣት ሲሆን በህግ አስከባሪነት የመተዳደር ባለትዳር እና የልጆች አባት ነው፡፡
በወቀቱ በነበረው ተኩስ ግራ ትከሻው ላይ ተመትቶ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጿል፡፡
5. ሻምበል ክንፈ ገመቹ የ52 ዓመት ጎልማሳ ሲሆኑ በካራት ከተማ ዱራይቴ ቀበሌ የሚኖሩ በንግድ ሰራ የሚተዳደሩ ነበሩ
በ2013 ዓ.ም የኢዜማ አባል በመሆናቸው በቤታቸው አካባቢ በነበሩበት ሰዓት ነበር በክልሉ ልዩ ሃይልና ፖሊስ በዱላና
በገጀራ ድብደባ ተፈፅሞባቸው(የተፈጸመባቸው) የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደነበር መረዳት ተችሏል፡፡
6. ወ/ሮ በንስ አሌ የ63 አመት አዛውንት ሲሆኑ ባለትዳር እና የልጆች እናት ናቸው፡፡ የኢዜማ አባል በመሆናቸው ብቻ ጉዳት
ከደረሰባቸው መካከል አንዷ ሲሆኑ ጉዳቱን ያደረሰባቸው ደግሞ የክልሉ ልዩ ሃይልና ፖሊስ እንደነበረ እና ጉዳቱም
የደረሰባቸው ለቤታቸው ጋዝ ለመግዛት በሚሄዱበት ጊዜ ዱራይቴ ቀበሌ በተለምዶ ቴሎያ ተብሎ በሚጠራው ቦታ
ሲደርሱ ምክንያቱን በማያውቁት ሁኔታ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ቀኝ እግራቸውን ተመተው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው
በህክምና ክትትል ላይ የነበሩ መሆናቸውን ለኢሰመጉ ገልጸዋል፡፡
7. አቶ ኃይሉ ጎልገሎ እና ዴይ ጋንኖ የ53 እና የ32 ዓመት አርሶ አደሮች ሲሆኑ የሚኖሩትም በካራት ዙሪያ ባልቸህ ወረዳ
ነው፡፡ በ28/10/13 ዓ.ም ባህላዊ ሸንጎ ተብለው እንዲመጡ ከተደረጉ በኋላ የኢዜማ አባል በመሆናቸው በፖሊሰ እና
በልዩ ሃይል ድብደባ ተፈጽሞባቸው እና የህክምና እርዳታ ተከልክለው ወደ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን እንዲሁም ይህ
ማስረጃ ለኢሰመጉ እስከደረሰበት ቀን ድረስ አለመፈታታቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡
8. ወ/ሪት አያና አርካይ የ24 ዓመት ወጣት ስትሆን በካራት ዙሪያ ባልቸህ ወረዳ የምትኖር የ8ኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡
በ28/10/13 ዓ.ም ባህላዊ ሸንጎ ስብሰባ እንድትገኝ ከተደረገች በኋላ የኢዜማ አባል በመሆኗ በፖሊስ እና በልዩ ሃይል
ድብደባ ተፈጽሞባት እና የህክምና እርዳታ ተከልክላ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰደች መሆኑን እንዲሁም ይህ ማስረጃ
ለኢሰመጉ እስከተላከበት ቀን ድረስ ከዕስር አለመፈታቷን ማወቅ ተችሏል፡፡
9. አቶ አገኘሁ አርካታ እድሜው 40 ሲሆን በኮንሶ ከተማ ነዋሪ ነው፡፡ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ “በታራቴ ሀ” የምርጫ
ጣቢያ የኢዜማ ታዛቢ ሆኖ የምርጫውን ሂደት ሲከታተል ቆይቶ የብልፅግና የፓርቲ አባላት ቤቱ በር ላይ በመምጣት
በድንጋይ በመውገር የግራ እግሩን ከጉልበቱ በታች ሰብረው እና ደብድበው ጥለውት መሄዳቸውን እንዲሁም የኮልሜ
ክላስተር አመራሮች ቤቱ ላይ መተኮሳቸውን እና ችግሩን ለቀበሌው ኮማንድ ፖስት አመልክቶ ወንጀለኞች ቢታሰሩም
የክላስተሩ አመራር ያለአግባብ እንዲፈቱ መደረጋቸውን ካቀረበው አቤቱታ ማወቅ ተችሏል፡፡

የቁጫ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)


አቶ ከፋለኝ ፋንቱ ጌታሁን የሰላም በር ከተማ ነዋሪ የሆኑ በስራቸውም መምህር ናቸው፡፡ በቁጫ ወረዳ በቀበሌ 05 የቁህዴፓ
አባል እና ደጋፊ በመሆናቸው ብቻ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አንዱ ሲሆኑ ጉዳቱን ያደረሱት ደግሞ የክልሉ ልዩ ሃይልና
ፖሊስ ሲሆኑ ስራ በሚገቡበት ጊዜ ዱራይቴ ቀበሌ ሲደርሱ ምክንያቱን በማያውቁት ሁኔታ የፖሊስ እና የልዩ ኃይል ልብስ
በለበሱ ስዎች ተደብድበው አይናቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል ላይ መሆናቸውን ማየት ተችሏል፡፡
ነፃነትና አንድነት ፓርቲ
አቶ ሰለሞን ሰዴ የ45 አመት ጎልማሳና የአርባ ምንጭ ዙሪያ ነዋሪ ሲሆን የአካባቢው ነፃነትና አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር እና
ፓርቲውን ወክሎ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወዳዳሪ ነበር፡፡ ሰኔ 30 ቀን በብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ዘረፋና
ማስፈራራት የደረሰበት ሲሆን የአካባቢው ፖሊስም ተባባሪ በመሆን ኤግዚቢት በሚል ሰበብ ንብረቱን መዘረፉን እና ከባድ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 7
ድብደባም ደርሶበት እንደነበር ፓርቲው ለኢሰመጉ በላከው መረጃ ማወቅ ተችሏል፡፡

የስነ-ልቦና ጉዳት
የኢትዮጵያ የፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስታ በአንቀጽ 102 እንደሚገልፀው ማንኛውም ምርጫ በሀገሪቱ
ውስጥ ሲካሄድ ከየትኛውም አካል ገለልተኛና ነፃ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ በአፍሪካ የሰው እና ህዝቦች መብት ቻርተር
አንቀጽ 20 ላይ እንደተደነገገው ሁሉም ሰዎች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን የማያጠያይቅ እና የማይገረሰስ መብት አላቸው።
የፖለቲካ ሁኔታቸውን በነጻነት በመወሰን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገታቸውን በነፃነት በመረጡት ፖሊሲ መሰረት
ያካሂዳሉ። ነገር ግን ኢሰመጉ በስድስተኛው የምርጫ ምልከታ ማረጋገጥ እንደቻለው ይህ አንቀፅ በተለያዩ አካላት በተለያየ
መልኩ ተጥሷል፡፡ የፖለቲካ አመለካከትን ምክንያት በማድረግ ብቻ አካላዊ ያልሆነ የተለያዩ ጉዳቶች ደርሰዋል፡፡ ለምሳሌ
ከማህበረሰብ መገለል፣ ስም ማጥፋት፣ እንደ ወንጀለኛ መታየት የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
1. ኩቹሎ ፓሪቶ የ35 አመት ጎልማሳ ሲሆን በካራት ዙሪያ በአርፋይዴ ወረዳ የሚኖር አርሶ አደር ነው፡፡ ኩቹሎ ፓሪቶ
ለኢሰመጉ በሰጠው ቃል መሰረት “የኢዜማ ደጋፊ በመሆኔ ብቻ በወረዳው አመራሮች እና ምክትል አስተዳደሮች
ከማህበረሰቡ እንድገለል ተዳርጌአለሁ፣ በአመራሮቹ ጫና ምክንያት ጎረቤቶቼ ራቁኝ አገለሉኝ” ሲል ገልፁዋል፡፡ ይህም
ከፍተኛ የስነ-ልቦና ቀውስ ዳርጎት እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጿል፡፡
2. ሳሙኤል ዘነበ በሞተረኝነት የሚተዳደር የ19 ዓመት ወጣት የነበረ ሲሆን ረብሻ እንዲነሳ አድርገሀል በሚል በተለያየ
መልኩ የስነ-ልቦና ጉዳት ከወረዳው አመራሮች ሲደርስበት መቆየቱን እና በነጻነት ተንቀሳቅሶ እንዳይሰራ ተደርጎ
እንደነበረ ለኢሰመጉ አስረድቷል፡፡
3. አድራስ አራርስ የ35 አመት ጎልማሳ ሲሆን በካራት ዙሪያ በአርፋይዴ ወረዳ የሚኖር አርሶ አደር ነው፡፡ የኢዜማ ደጋፊ
በመሆኑ ብቻ በወረዳው አመራሮች እና ምክትል አስተዳደሮች ከማህበረሰቡ እንዲገለል ተደርጎ እንደነበር እና በአመራሮቹ
ጫና ምክንያት ጎረቤቶቹ ይርቁት እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጿል፡፡
4. ወ/ሮ ኩሽ ቀንጨታ 46 ዓመታቸው ሲሆን በዴበና ቀበሌ የሚኖሩ የኢዜማ አባል በመሆናቸው ብቻ ከማህበራዊ ኑሮ
ከተገለሉ የቀበሌው ነዋሪዎች አንዷ መሆናቸውን እና በነጻነት ተንቀሳቅሰው እንዳይሰሩ ስማቸውን በተለያየ አጋጣሚ
ሱያጠፉባቸው እንደነበር ለኢሰመጉ ተናግረዋል፡፡
5. በለጠ አረጋ በመምህረርነት ስራ የሚተዳደር የ30 ዓመት ወጣት ሲሆን የኢዜማ አባል በመሆኑ ብቻ እና በፖለቲካ
አመለካከቱ ስለሚለይ የስነ-ልቦና ጉዳት ሲደርስበት መቆየቱን፣ በተጨማሪመም ብዙ አመት ከኖረበት እድር ያለ ምንም
ምክንያት እንዲታገድ ተደርጎ የነበረ መሆኑን ለኢሰመጉ ገልጿል፡፡
6. እስራኤል ገደሮ የ23 ዓመት ወጣት እና የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነበር፣ የኢዜማ አባል በመሆኑ ብቻ ፈተና እንዳይፈተን
በመከልከል ለከፍትኛ የአዕምሮ ጭንቀት ተዳርጎ እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጿል፡፡

የቁጫ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)


አቶ ጋቱሶ ገብሬ በካራት ዙሪያ በአርፋይዴ ወረዳ የሚኖር የ43 አመት የመንግሰት ሰራተኛ ሲሆኑ የቁህዴፓ ደጋፊ በመሆኑ
ብቻ በወረዳው አመራሮች እና ምክትል አስተዳደሮች ከማህበረሰቡ እንዲገለል ተደርጎ እንደነበረ፣ በአመራሮቹ ጫና ምክንያት
ጎረቤቶቹ እንደራቁት እና የቁም እስረኛም ተደርጎ እንደነበር በዚህም የተነሳ ለከፍተኛ የስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ ገብቶ እንደነበር
ለኢሰመጉ አሳውቋል፡፡
ህገወጥ የምርጫ ጫና ወይም ተፅዕኖ
ከምርጫ በፊት አና ከምርጫ በኋላ አንዱን አካል ለመጥቀም አንዱ ላይ ያለአግባብ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ተግባር
በኢትዮጵያ የፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት በአንቀጽ 102 መሰረት የተከለከለ ነው፤ ይሄው አንቀጽ
እንደሚገልፀው ማንኛውም ምርጫ በሀገሪቱ ውስጥ ሲካሄድ ከየትኛውም አካል ገለልተኛ እና ነፃ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል፡
፡ ነገር ግን ኢሰመጉ በስድስተኛው የምርጫ ሂደት የምርመራ ስራው ማረጋገጥ እንደቻለው ይህ አንቀፅ በተለያዩ አካላት
በተለያዩ መልኩ ተጥሷል፡፡ በተለይ ደግሞ ከዚህ ቀደም ለማህበረሰቡ ይቀርቡ የነበሩ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንደ ምርጫ
መቀስቀሻ እና መያዣ በመጠቀም በህብረተሰቡ ላይ ጫና ይፈጠር ነበር ፡፡

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 8
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
1. መምህርት ሰናይት ኩማ በኮንሶ ዞን ዴበና ቀበሌ ነዋሪ እና ስትሆን በቀን 30/10/2013 የኢዜማ ተወካይ በመሆኗ ብቻ
ከዞኑ አመራሮች ማስፈራሪያ እና ስድብ ሲደርስባት እንደነበረ እና በመጨረሻም ለእስር ተዳርጋ እንደነበር ለኢሰመጉ
ገልጻለች፡፡
2. ወ/ሮ ደመቀች ሳንቲሜ የ28 አመት ወጣት ስትሆን በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ አለታ ቀበሌ ውስጥ በጠለላ ከተማ
ማዘጋጃ ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ የነበረች ሲሆን ወንድሟ የኢዜማ አባል በመሆን በ04/09/2014 ዓ.ም ከቤቱ
ተወስዶ እንደታሰረ እና ወ/ሮ ደመቀች ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ በምትጎበኝበት ሰዓት ወንድሟ ተደብድቦ እንደነበረ፣
በመቀጠልም በዋስ ካስፈታችው በኋላ ወደ ስራዋ ስትመለስ ከስራ መሰናበቷን እና ለዚህም እንደምክንያትነት የተሰጣት
የተፎካካሪ ፓርቲ አባል ማስፈታቷ እንደነበረ ለኢሰመጉ ገልጻለች፡፡
የቁጫ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)
1) አቶ አስፋው ኤና የ38 አመት የጤና ባለሙያ ሲሆን ሰላም በር ከተማ በቁጫ ወረዳ በዳንባዬ ቀበሌ ቁህዴፓን ወክሎ
ከምረጫ በፊት ቅስቀሳ እንዳያደርግ የምርጫ ቀንም ታዛቢ ቢሆንም በትክክል እንዳይታዘብ ከተለያዩ የመንግሰት አካላት
በተለያየ መልኩ ጫና ሲደርስበት እንደነበረ ለኢሰመቁ ገልጾ ነበር፡፡ ከዚም አልፎ ከወረዳ አመራሮች ቀጥተኛ ማስፈራሪያ
ሲደርሰው እንደነበርም ጨምሮ አስረድቷል፡፡
2) ወ/ሪት እስከዳር ዳዊት የ22 ዓመት ወጣት ስትሆን ሰላም በር ከተማ በቁጫ ወረዳ በዳንባዬ ቀበሌ ከምርጫ ቦርድ ስልጠና
ወስዳ በምርጫ ወቅት ተመድባ ለማገልገል ስትሞክር የወረዳው አመራሮች እና ምክትል አስተዳደሮች ጫና ማድረስ
እንደጀመሩባት፣ ለዚህም ምክንያት የነበረው አመራሮቹ እንደሚፈልጉት ስላልሆነች በቀጥታ ማስፈራራት እና ድብደባ
ደርሶባት እንደነበር ለኢሰመጉ አስረድታለች፡፡
3) አቶ ተስፋዬ ፋለሀ የ42 አመት ፖለቲከኛ ሲሆን ሰላም በር ከተማ በቁጫ ወረዳ በዳንባዬ ቀበሌ ቁህዴፓ ፓርቲ
ፕሬዚዳንት በመሆን በሚሰራበት ወቅት የወረዳው አመራሮች እና አስተዳደሮች ጫና ያደርሱበት እንደነበር፣ አቶ ተስፋዬ
ጫናው እንደ ፓርቲም እንደ ግለሰብም ያነጣጠረ እንደነበር፣ ምርጫ ቅስቀሳ መከልከል፣ ፓርቲውን በአሸባሪነት መፈረጅ
፣ ስም ማጥፋት እና ስብሰባ መከልከል ከደረሰባቸው ጫና መካከል እንደነበሩ ሊኢሰመጉ አስረድቷል ፡፡
4) አቶ ተክሉ ያእቆብ የ33 አመት የመንግስት ባለሙያ ሲሆን ሰላም በር ከተማ በቁጫ ወረዳ በዳንባዬ ቀበሌ ከምርጫ ቦርድ
በምርጫ አስተባባሪነት ስልጠና ወስዶ በምርጫ ወቅት ተመድቦ ለመስራት ሲሞክር ከወረዳው አመራሮች እና ምክትል
አስተዳደሮች ጫና ይደርስበት እንደነበር፣ አቶ ተክሉ እንዳስረዳው ከሆነ አመራሮቹ እንደሚፈልጉት ስላልሆነ በቀጥታ
ማስፈራራት እና ድብደባ አድርሰውበት እንደነበር እና ከዚም አልፎ ለእስራት ተዳርጎ እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጿል፡፡
5) አቶ ከፋለኝ ፋንቱ ጌታሁን መምህር ሲሆን ሰላም በር ከተማ በቁጫ ወረዳ በዳንባዬ ቀበሌ ከምርጫ ቦርድ በምርጫ
አስተባሪነት ስልጠና ወስዶ በምርጫ ወቅት ተመድቦ ለመስራት ሲሞክር ከወረዳው አመራሮች እና አስተዳደሮች
ማስፈራራት የቤት ብርበራ፣ የስልጠና አበል መከልከል፣ ወርሀዊ ደሞዝ መከልከል፤ በቀጥታ ዕድሜያቸው ለመምረጥ
ላልደረሱ ህፃናት የምርጫ ካርድ እንዲሰጡ ከምርጫው በፊት እና በኋላ ከፍተኛ ጫና ተፈጽሞበት እንደነበር ለኢሰመጉ
ገልጿል፡፡ ፡፡
6) ዶ/ር ጊዲዮን ጌታቸው የ33 አመት የመንግስት ሠራተኛ ሲሆን ሰላም በር ከተማ በቁጫ ወረዳ በዳንባዬ ቀበሌ ፋና ወምባ
የምርጫ እጩ የነበረ ሲሆን የወረዳው አመራሮች እና ምክትል አስተዳደሮች ስለ ፓርቲያቸው የሃሰት መረጃ እያሰራጩ
ስም ማጥፋት እንዲሁም ማህብረሰቡንና አባላቶቻቸውም ማሰፈራራትና ድብደባ ይደርስባቸው እንደነበር ለኢሰመጉ
ገልጿል፡፡
7) ወ/ሮ ሀረጋዊ ኃ/ጊዮርጊስ የ30 ዓመት ወጣት ስትሆን ሰላም በር ከተማ በቁጫ ወረዳ በሞርካ ቀበሌ የቁህዴፓ ፓርቲ
አባል በመሆኗ ብቻ ከወረዳው አመራሮች እና ምክትል አስተዳደሮች ጫና ይደርስባት እንደነበረ፣ ለዚህም ምክንያት
የነበረው አመራሮቹ እደሚፈልጉበት ባለመሆኗ እንደነበር እና በቀጥታ ማስፈራራት እና ድብደባም ይደርስባት እንደነበር
ገልጻለች፡፡
እናት ፓርቲ
1) አቶ ዋለልኝ ደታ ጉሬሳ የ45 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን የእናት ፓርቲ አባል ከመሆኑ በፊት በወላይታ ዞን በድፋንጎ ወረዳ
ማዘጋጃ ቤት ይሰራ ነበር፡፡ ለእናት ፓርቲ እጩ ከሆነ በኋላ ግን የመንግሰት ስራውን ትቶ ለፓርቲው መስራት እንደጀመረ፣
ይህንን ያልወደዱ የከተማ አስተዳደር ሰራተኞች በተለያዩ መንገዶች ጫና ያደርሱበት እንደጀመሩ እና ከጫናዎቹም

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 9
መካከልም ማስፈራራት፣ የውሸት ዜና ማሰራጨት፣ የ2013 ዓ.ም የመጋቢት እና የሚያዚያ ወርሀዊ ደሞዝ መከልከል
እንዲሁም ስም ማጥፋት ይገኙበት እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጿል፡፡
2) አቶ ወልደማርያም ልሳኑ የ43 አመት የመንግስት ሰራተኛ የነበረ ሲሆን የሚሰራውም በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ፋና ቀበሌ
ነበር፡፡ የእናት ፓርቲ ደጋፊ እና አስተባባሪ እንደሆነ ሲታወቅ ከመንግስት አካላት ጫና ይደርስበት መጀመሩን፣
በመቀጠልም ከስራው ያለአግባብ ማባረር ከዛም ማስፈራራት ፤ ዛቻ ፣ ድብደባ ፤ በመጨረሻም እስራት እንደተፈጸመበት
ለኢሰመጉ ገልጿል::

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ


1. አርባ ምንጭ ዙሪያ ላንቴ ቀበሌ ሰዎችን በሰፈር በማደራጀት የራሳቸውን መራጮች ብቻ እንዲመርጡ ተደርጎ የነበረ
መሆኑን እና ከዛ ውጪ ሌላ ፓርቲን ሊደግፍ የሚመጣውን ሁሉ የማሸማቀቅ ሥራ በአስተዳደሮቹ ይሰራ እንደነበር
የፓርቲው አባላት ለኢሰመጉ ገልጸዋል።
2. አቶ ቱጃሬ ቱፑላ አርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ሰራተኛ የነበረ ሲሆን ነፃነትና አንድነት ፓርቲ አባል እና እጩ መሆናቸው
የታወቀ እለት ምንም ጥፋት ሳይኖርባቸው ለአራት ወራት ያህል ከስራቸው ከታገዱ በሁዋላ ወደ ስራቸው ቢመለሱም
ያለምክንያት ከስራቸው የታገዱበትን ደሞዝ ቢጠይቁም ይህ ደሞዛቸው ሳይሰጣቸው መቅረቱን ለኢሰመጉ ገልጸዋል፡፡

የደቡብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ


1. አቶ ዋርሳ ዋቢሶ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ጬንቻ ዙሪያ ወረዳ ጩንቻ ከተማ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን የደቡብ ዲሞክራሲያዊ
ፓርቲ አባል መሆናቸውን ምክንያት በማድረግ ከግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጎ
እንደነበርe ለኢሰመጉ ገልጸዋል፡፡
2. አቶ ደመላሽ ደስታ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ጬንቻ ዙሪያ ወረዳ ጩንቻ ከተማ የደኮዬይራ ቀበሌ የግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ
እንደነበሩ፣ የትምህርት እድል አግኝተው ወደ አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ በመሄድ እየተማሩ በነበሩበት ወቅት የደቡብ
ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አባል እና ደጋፊ በመሆናቸው ከስራቸው ተነስተው 25 ኪሎሜትር ርቆ ወደሚገኝ ሌላ ቦታ
እንዲዛወሩ ተደርጎ እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጸዋል፡፡
3. አቶ ሀይሌ አለሙ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ጬንቻ ዙሪያ ወረዳ ጩንቻ ከተማ የደኮዬይራ ቀበሌ የግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ
ሆነው ለአምስት አመታት ሲሰሩ ከነበሩበት ስራቸው የደቡብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አባል እና ደጋፊ በመሆናቸወ
ይሰሩበት ከነበረው ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዘዋወሩ ተደርገው እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጸዋል፡፡
4. አቶ ማትሮስ ኦሶ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ጬንቻ ዙሪያ ወረዳ ጨንቻ ከተማ የደኮዬይራ ቀበሌ የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ
ሰራተኛ፣ የደቡብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አባል እና ደጋፊ በመሆናቸው ከስራቸው ተነስተው 32 ኪሎሜትር ርቆ ወደሚገኝ
ሌላ ቦታ እንዲዘዋወሩ ተደርጎ የነበረ መሆኑን እና ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ደሞዝ ሳይከፈላቸው ቀርቶ እንደነበር ለኢሰመጉ
ገልጸዋል፡፡
ጋሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ
ሐዋርያ ሃይሌ የ43 ዓመት የምህንድስና ባለሙያ ሲሆኑ በቦንኬ ወረዳ ከ2011ዓ.ም ጀምሮ ሲሰሩበት ከነበረው መስሪያቤት
በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት እንዳይሰሩ ተደርገው የነበረ መሆኑን እና ከሚያዚያ ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ደሞዝ
ሳይከፈላቸው ቀርቶ እንደነበር እንዲሁም በሚስታቸው ስም የሚገኝውን የግብርና ቦታ እንዳያርሱ እና ከሳቸውም አልፎ
ቤተሰቦቻቸው ላይ ጫና ይደርስ እንደነበር ይህንንም ደግሞ ያደርጉ የነበሩተ በጊዜው የነበሩ የዞኑ አስተዳዳሪዎች እና
የብልፀግና እንደነበሩ ለኢሰመጉ ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ በጋሞ ዲሞክሪሲያዊ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ላይ ሲደርሱ የነበሩ ህገወጥ የምርጫ ጫና ወይም ተፅዕኖዎች
እንደሚከተለው ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርበዋል

 የጋሞ ዲሞክሪሲያዊ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ለሆኑት መታወቂያ እና ማስረጃ ክልከላ፣


 የጋሞ ዲሞክሪሲያዊ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎችን የደሃ ደሃ ስንዴ እርዳታ ክልከላ፣
 የጋሞ ዲሞክሪሲያዊ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ለይ የሚደርስ ማስፈራሪያ እና እስራት፣
 ፓርቲው በአባላቱ ተነሳሽነት የተበላሸ መንገድ በበጎ ፍቃድ በሚጠገንበት ወቅት ከፖሊሶች ይደርሱ የነበሩ
ማስፈራራት አና እስራት፣

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 10
 የጋሞ ዲሞክሪሲያዊ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች የሚገኙ ጤና ጣቢያዎችን መድሃኒት ላይ
የመድሀኒት ክልከላ፣
 የፓርቲው ደጋፊ ለሆኑት ነጋዴዎች መንግሥት የሚሰጠውን የፍጆታ እቃዎች መከልከልና ከገቢ በላይ ግብር
መጠየቅ፣
 ጋሞ ዲሞክሪሲያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ከሚሰሩባቸው መስርያ ቤቶች ማሰናበት እና ማዛዋወር፣
 ከሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ማስወጣትና በፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ መከልከል፣
 የጋሞ ዲሞክሪሲያዊ ፓርቲ አባላትን እና ደጋፊ የሆኑ ስራ ፈላጊዎችን ስራ መከልከል ይገኙበታል፡፡
ንብረት ውድመት
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
አቶ ቡርክተ ገለቦ የተፈፀመባቸው ዝርፊያ ሲሆን መጠኑን በርግጠኝነት መናገር ባይቻልም በክልሉ ልዩ ሀይልና ፖሊስ
በመኖሪያ ቤታቸውን ሰብረው በመግባት ብዙ የሚባል ገንዘብ ይዘው እንደወጡ ተናግረዋል፡
ተ.ቁ የንብረቱ ባለቤት የንብረቱ ዓይነት የጉዳቱ ድርጊቱ የድርጊቱ የተፈፀመበት
ስም ዓይነት የተፈጸመበት ፈፃሚ ቦታ
ቀን
1 በየነ በርሻ ብር50.000እና10.000የሚገመት ዝርፊያ 13/12/13 የወረዳና ዶከቱ ገበያ
ጫማ የቀበሌ አካባቢ
አመራር
2 ዮሴፍ ጩራ 50ጫማ፣ 4 ቢላዋ (3680 ብር ዝርፊያ 12/11/13 የቀበሌ ቡርቁዳ ሠፈር
ግምት አመራር 02
3 አዲሱ ገረሙ 1ሞባይል ብር 800 እና 3000ብር ዝርፊያ 12/11/13 ›› ›› ›› ››
ጥሬ ገንዘብ
4 ሣንጋ ዲኖቴ 20 ጫማ ብር 1400 ግምቱ ዝርፊያ 12/11/13 ›› ›. ›› ››
5 ኩሴ በርሻ ቴክኖ ሞባይል ስክሪን ታች እና የብር ዝርፊያ 13/11/13/ የወረዳና ዶከቱ ቀበሌ
ደምሴ 10.000 ወርቅ የቀበሌ ገበያ

የቁጫ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)


1) ወ/ሪት ሜሮን ማሴቦ የ26 ዓመት ወጣት ስትሆን በጎፋ ዞን ሰላም በር ከተማ በቁጫ ወረዳ በሞርካ ቀበሌ ሆቴል እንደነበራት
እና በቀን 16/09/2013ዓ.ም ብልፅግና ፓርቲ ባዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ ሆቴሏ ላይ ጥቃት ተፈጽሞ እንደነበር ይህንንም
ጥቃት የፈፀሙትም የብልፅግና ደጋፊዎች እንደነበሩ ለዚህም ምክንያት የነበረው የቁህዴፓ ፓርቲ አባል መሆኗ ብቻ እንደነበረ
እና በዚህም ጥቀት ላይ የወረዳው አመራሮችና አስተዳደሮች ቀጥተኛ እጅ እንደነበረበት፣ በጉዳቱም የሆቴሏ መስኮትና በር
ወድሞ የነበረ መሆኑን ገልጻለች፡፡
2) አቶ አለቃ ማሴበ የ60 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ በጎፋ ዞን ሰላም በር ከተማ በቁጫ ወረዳ በሞርካ ቀበሌ ሆቴል እነደነበራቸው፣
በቀን 16/09/2013 ዓ.ም ብልፅግና ፓርቲ ባዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሆቴላቸው ጥቃት ተፈጽሞበት እንደነበር እና
የፈፀሙትም የብልፅግና ደጋፊዎች እደነበሩ፣ ለዚህም ምክንያት የነበረው የቁህዴፓ ፓርቲ አባል እና ፋይናንስ ውስጥ ይሰረ
የነበረ መሆኑ ብቻ እንደሆነ እና በዚህም የወረዳው አመራሮችና አስተዳደሮች ቀጥተኛ እጅ እንደነበረበት ለኢሰመጉ
አሳውቀዋል፡፡
ህገወጥ እስራት
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17 እንደተደነገገው ማንም ሰው በህግ በተደነገገው መሰረት ካልሆነ በቀር ነፃነቱን
አይነጠቅም፤ ማንም ሰው በዘፈቀደ ሊታሰር አይችልም፣ ማንም ሰው ያለ ክስ ወይም የጥፋተኝነት ክስ ሊታሰር አይችልም።
ኢትዮጵያ ፈርማ ከተቀበለቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች አንዱ የሆነው የተባበሩት መንግስታት ቻርተር መሰረት የህግ
አሰፈፃሚዎች የዘር፣ የፆታ፣ የቋንቋና የእምነት ልዩነት ሳያዩ የሰብዓዊ መብቶችን እና መሰረታዊ ነፃነቶችን መከበር ለማስፈን እና
ለማስከበር መስራት እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ ነገር ግር በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ከዚህ በተቃራኒው ስርዓቱን

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 11
ተላልፈው የህግ አካለት ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሲፈጽሙ ተስተውለዋል ከዚም መሃል ያለፍርድ እስራት (Arbitrary
Arrest) ይገኝበታል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
1. ወ/ሮ ሽታዬ ኩሴ እድሜዋ 43 ሲሆን በኮንሶ ዞን ዶከቱ ቀበሌ ነዋሪ ናት፣ የኢዜማ አባል በመሆኗ ብቻ ሐምሌ 13/2013
ዓ.ም ከቤቷ ነፍሰ ጡር መሆኗን ግንዛቤ ወስጥ ባላስገባ መልኩ ከነህፃን ልጇ ድብደባ ደርሶባት እንደነበር እና ወደ እስር
ቤት በመውሰድ በብዙ እንግልት ካቆዩዋት በኋላ በዋስ ተፈትታ እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጻለች።
2. ይህ የህገውጥ እስራት የተፈፀመው በ11 የኢዜማ አባላት ላይ ሲሆን መጥሪያ በ7/11/13 በማውጣት ተበዳዮችን
በ8/11/13 መጥሪያ ሳይሰጣቸው ያልተደረገ ወንጀል በመፍጠር ሁከትና ብጥብጥ ቀስቅሳችኋል በማለት ከየቦታው
በመሠብሰብ ለእስር ተዳርገዋል። ተበዳዮች በአመለካከታቸው ልዩነት ብቻ ትልቅ መጉላላት ከደረሰባቸው በኋላ
በ15/11/13 ወንጀል ባለመፈፀማቸው ዋስ በማስጠራት ሊፈቱ ችለዋል።
3. ወ/ሮ ነፃነት የኢዜማ ፓርቲ አባል በመሆኗ ብቻ እየተከታተሉ ያስፈራሯት የነበረ ሲሆን በመጨረሻም ሐምሌ 13/2013
ስብሰባ ላይ የኢዜማ አባል የሆኑትን በመለየት ወደ እስር ቤት ተወስደው እንደነበር፣ ወ/ሮ ነፃነትም ከነህፃን ልጇ ወደ
እስር ቤት ካስገቧት በኋላ እስክትለቀቅ ድረስ ከፍተኛ እንግልት ደርሶባት እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጻለች።
4. መ/ር መኮንን ሞላ ኮንሶ ዞን ፋሻ ከተማ የኢዜማ አባል ሲሆን በ29/11/13 ዓ.ም ቤቱን በመስበር የሰራው ወንጀል
ሳይኖር ወደ እስር ቤት በመውሰድ እስከ 05/12/13 ዓ.ም ደረስ ያለ ምንም ክስ ታስሮ የነበረ ሲሆን ከእስራት ከተፈታ
በኋላ በድጋሚ በቀን 11/12/13 ዓ.ም እንደገና ታስሮ ያለምንም ክስ በአቃቢ ህግ ትእዛዝ በዋስ ሊፈታ መቻሉን
ለኢሰመጉ ገልጿል፡፡
5. አቶ ተስፋዬ ቱማቶ እና ብሩክ ለማ እድሜያቸው 32 እና 28 አመት ሲሆን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ የኢዜማ አባል እና
አመራር በመሆናቸው ብቻ ለ12 ቀን ያክል ታስረው በአስር ሺ ብር ዋስ መለቀቃቸውን፣ ነገር ግን ይህ መረጃ
እስከተሰበሰበበት ቀን ድረስ ከፖሊሶች ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል ፡፡

እስራት

ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ ስማቸው የተዘረዘሩ ግለሰቦች ኢሰመጉ የምርመራ ስራን ባከናወነበት ወቅት በእስር
ላይ የነበሩ ናቸው፡፡

ተ.ቁ የታሰረው ሰው ስም የታሰረበት ቀን የታሰረበት ቦታ


1. አብርሀም ኩሴ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
2. እስራኤል ጋደኖ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
3. ኦልዳሻ ማረሣ 08/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
4. አለሙ አምሳሉ 07/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
5. ኃይሉ ለሚታ 07/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
6. ኩይታ ኮዳና 07/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
7. ለሚታ አድማሱ 07/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
8. ደይካኔ ማታ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
9. ካሳዬ ገልሳሞ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
10. ኡረማሌ ገልሳሞ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
11. ገልሳሞ ኩያና 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
12. ኩሴ ገልሳሞ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
13. ካይዳሬ ካሳዬ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
14. ኡራማሉ ኦሼ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 12
15. ኦሼ ሐይሉ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
16. ገመሣ ኮሬ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
17. ሣጎያ ገለቱ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
18. ጊዶጊስ ግላኖ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
19. ሣጎያ ኩሴ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
20. ታሪኩ ኩራሾ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
21. ኩሴ አያኖ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
22. ኩያሎ ኩራሾ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
23. ኩማቾ ኩራሾ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
24. ሳሙኤል ዘሩቤ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
25. ለሚታ አያንቶ 05/09/2013 የዞን ፖሊስ ጣቢያ
26. ለከሰ ያድሳ 05/09/2013 የካራት ከተማ ፖ/ጣቢያ
27. ታሪኩ ኩይታ 05/09/2013 የካራት ከተማ ፖ/ጣቢያ
28. ኦላሞ ኦልድሻ 05/09/2013 የካራት ከተማ ፖ/ጣቢያ
29. ገዛኽኝ ገልገሎ 05/09/2013 የካራት ከተማ ፖ/ጣቢያ
30. ገልገሎ ኩይታ 05/09/2013 የካራት ከተማ ፖ/ጣቢያ
31. ሳሙኤል ዘመቻ 05/09/2013 የካራት ከተማ ፖ/ጣቢያ
32. ኦላሞ ኦርካይዶ 05/09/2013 የካራት ከተማ ፖ/ጣቢያ
33. ሽታዬ ኩሴ 05/09/2013 የካራት ከተማ ፖ/ጣቢያ
34. ኦርካይዶ ጩሮ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
35. በትክሉ አራርሳ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
36. በሱፍቃድ ለሚታ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
37. ለሚታ ገበደ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
38. ቶራያ ጉያና 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
39. ኦልሶ ኦልድሾ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
40. ኮራ ኩሴ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
41. ባዶነ ማርሳ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
42. ኦላሞ ኦዶ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
43. ካልያ ገለቦ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
44. ታሪኩ ገመቹ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
45. ካሣዬ ገልገሎ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
46. ካሣዬ ኩሴ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
47. ኩሴ በርሻ ግለና 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
48. ጉይታ ዲኖቴ መርቆ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
49. ኩሴ ሮቢቶ አያኖ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
50. ካንቶ ገመቹ ጋሐኖ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
51. ገረሙ ገደኖ ደምሴ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
52. ገዛኽኝ ገመዴ ደይጋኔ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 13
53. ከበደ ካራቶ ገለቦ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
54. ፈረንጅ ባዶ ሮጬ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
55. ጉዴታ ጉደኖ ኩሴ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
56. አድሱ ካርካ ቆሳ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
57. አድሱ ከሴ በየነ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
58. ካላሼ ቦርሻ ቱባሮ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
59. ያበሎ ያንቶ ሻባሌ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
60. ገበዮ ገመቹ ጋሐኖ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
61. አንበሶ ገልገሎ ደባያ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
62. ግርማ ግለኖ ጎንዶሮ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
63. አድሱ ለሚታ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
64. አድማሱ ኡርማሌ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
65. ኩሴ በርሻ ደምሴ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
66. ኩሴ አድማሱ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
67. አድሱ ገረሙ ጎታና 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
68. ወገነ ወንድሙ በርሌ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
69. ገላሔ ገዛኽኝ ገለቦ 05/09/2013 ፋጩጫ ቀበሌ ጣቢያ
70. ጉሻቦ ጉያሎ ጉባያ 05/09/2013 ፋጩጫ ቀበሌ ጣቢያ
71. ለሚታ ገለቦ ታንታ 05/09/2013 ፋጩጫ ቀበሌ ጣቢያ
72. ኡርማሌ ማሞ ገመይሎ 05/09/2013 ፋጩጫ ቀበሌ ጣቢያ
73. በርሻ ኩሌ በርሻ 05/09/2013 ፋጩጫ ቀበሌ ጣቢያ
74. ገዛኽኝ ጋሐኖ 05/09/2013 ፋጩጫ ቀበሌ ጣቢያ
75. አያና ኦርካይዶ 05/09/2013 ፋጩጫ ቀበሌ ጣቢያ
76. ታዮ ታደሰ 05/09/2013 ፋጩጫ ቀበሌ ጣቢያ
77. ገዛኽኝ ሮበዩ 05/09/2013 ፋጩጫ ቀበሌ ጣቢያ
78. ኩሴ ኮሬ 05/09/2013 ፋጩጫ ቀበሌ ጣቢያ
79. ግረም ኡርማሌ 05/09/2013 ፋጩጫ ቀበሌ ጣቢያ
80. ዳግም ኡርማሌ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
81. ታገል እንዶሌ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
82. መሀመድ ለማ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
83. ገዛኽኝ ገበደ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
84. ካይላ ገመቹ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
85. ካራሳ ገመቹ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
86. አድሱ ገረሙ 05/09/2013 ከና ፖሊስ ጣቢያ
87. አድሱ ኃይሉ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
88. ኩራሾ ሣጎያ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
89. ገበር ገለቦ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
90. ነፃነት ገዋዶ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 14
91. ሐልጌ ሣጎያ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
92. ካሰኝ ገረሙ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
93. ብርሀኑ ኩሴ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
94. ገረሙ ኩሴ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
95. ሮብሻ ካርሻቦ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
96. ሣሙኤል ተስፋዬ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
97. ሣሙኤል ሣጎያ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
98. ኩሴ ካንባ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
99. ገለቱ ገልቶ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
100. አብርሀም አየለ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
101. ኦርግሳ ኦራኖ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
102. አቤል ለሚታ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
103. አሸናፊ በርሻ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
104. ጨሮ ኮሻርታ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
105. ወንድማገኝ እንዳሾ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
106. ሣንባቶ ትጌ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
107. ሐይሉ ኩይታ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
108. ካንቶ አያቦ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
109. ኩሴ ገሆቦ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
110. ጋሻው ገለቱ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
111. ካንትሻ እኛ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
112. ገሠሠ ጌሾ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
113. ካራቶ ካታማ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
114. ካኡታ ካሻርቶ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
115. ገነቦ ጌሻ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
116. ኩሴ ካሱ 05/09/2013 ኬና ፖ/ጣቢያ
117. ባራሻ ባቻ 05/09/2013 ኬና ፖ/ጣቢያ
118. ገበደ ጋሐኖ 05/09/2013 ዶሃ ቀበሌ ፖ/ጣቢያ
119. ስንታዮ ሽሬ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
120. ኦርካይዶ ቁኔ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
121. ኩሴ ኩታዬ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
122. መ/ር ኩኖቴ ኮራ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
123. መ/ር ገንደጬ ገዬቶ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
124. መ/ርፍቅሩ ተስፋዬ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
125. አለማየሁ ዳዩ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
126. አንዱአለም ሎጊታ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
127. መ/ር ደበያ ተፍተራ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
128. ካሳይቴ አዳሌ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 15
129. ገሸይኖ ካቢታኖ 05/09/2013 የካራት ዙሪያ ፖ/ጣቢያ
130. አልማሌ ገሠሠ 05/09/2013 የቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ
131. ደበያ ተረፈ 05/09/2013 ኬና ፖ/ጣቢያ
132. ወ/ሮ ሀልጌ ሳጎያ 05/09/2013 ኬና ፖ/ጣቢያ
የቁጫ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)
1. አቶ ደሳለኝ ዴአ መምህር ሲሆኑ ሰላም በር ከተማ በቁጫ ወረዳ ባስ ቀበሌ የቁህዴፓ አባል በመሆናቸው ብቻ ለእስራት
ተዳርገው እንደነበር በተጨማሪም ከወረዳው አመራሮችና አስተዳደሮች ማስፈራራትና የቤት ብርበራ ሲደረግባቸው
እንደነበር አስረድተው ከእስር ከተፈቱ በኋላም ወርሀዊ ደሞዛቸውን ተከልክለው እንደነበር በማስረዳት ለዚህም ደግም
በጊዜው የነበረው የዞኑን ትምህርት መምሪያ ተጠያቂ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
2. አቶ ተንኮ አሻንጎ የ50 አመት እድሜ ባለፀጋና ባለትዳር ሲሆኑ ሰላም በር ከተማ በቁጫ ወረዳ ባስ ቀበሌ የቁህዴፓ አባል እና
የፓርቲው የገንዘብ (ፋይናንስ) ሃላፊ ነበሩ፡፡ ከምርጫ በፊትና ከምርጫም በኋላ በተለያየ መልኩ ፓርቲውን ለማዳከም
የወረዳው አመራሮችና አስተዳደሮች ቢጥሩም አልሆንላቸው ሲል ነው ወደ ቀጥተኛ ማሰር ፣ መደብደብና ማሰቃየት
እንደጀመሩ እና የዚህ በደል ዋነኛ ተጠቂ እንደነበሩ አስረድተዋል፡፡
እናት ፓርቲ
አቶ ጥላሁን ልሳኑ የ30 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን ባለትዳርና የልጆች አባት ነው፡፡ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ነው
የሚኖረው፡፡ ወንድሙ እጅግ ተወዳጅ የእናት ፓርቲ እጩ ሲሆን እሱን ማስፈራራትና ዛቻ አልሆንላቸው ሲል ባላወቀው
መንገድ ሌባ ብለውት መታሰሩን እና ከዛም ለሁለት ሳምንት ያህል ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ቀርቶ እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጿል፡፡

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ


በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ አከባቢ በእግር ኳስ ጨዋታ የተነሳን አለመግባባት አስነስተሀል እና ንብረት አውድመሀል በሚል
በመጋቢት 8 በተፈጠረ ችግር በመጋቢት 9/2013 ዓ.ም ምሽት 3:00 በከምባ ወረዳ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጩ
የሆኑትን አቶ በድል አለባቸውን ከቤታቸው አውጥተው በመውሰድ ይህ መረጃ እስከተሰበሰበበት ቀን ድረስ በእስር ላይ
እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።

አማራ ክልል
ከህግ ውጪ የተፈጸመ ግድያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 6ተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ከተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መካከል
ከህግ ውጪ የተፈጸመ ግድያ ይገኝበታል፡፡ ይህንንም ጥሰት በፖለቲካ ፓርቲዎች ከፋፍለን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)

ከዚህ በታች የአብን ደጋፊ በመሆናቸው ብቻ በተለያየ መንገድ የተገደሉ ሰዎች ስማቸው እንደሚከተለው ቀርቧል

1. ተማሪ ብዙነህ አስኮር በአማራ ክልል በመርጦ ለማሪያም ከተማ ቀበሌ 03 ነዋሪ እና የ22 አመት ወጣት ሲሆን ሰኔ
12/2013 ዓ/ም “ለአብን የምርጫ ቅስቀሳ ለምን ታደርጋለህ” በማለት በቀበሌው ሚሊሻዎች በጥይት ተገሏል።
2. እንዲሁም ተማሪ መዝገቡ ጌትነት እና ተማሪ ታደሰ አባተ በተመሳሳይ መልኩ የአብን ደጋፊ በመሆናቸው ምክንያት
ሊገደሉ እንደቻሉ ከተሰበሰቡ አቤቱታዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡

የአካል ጉዳት
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
1. አቶ ይበልጣል ሙሉ በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያ በጎንጂ ቆለላ የኢዜማ የምርጫ ወረዳ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና
ሊቀመንበር ሲሆኑ መጋቢት 18/ 2013 ዓ.ም ምዕራብ ጎጃም በወረዳው ሰላምና ደህንነት ሀላፊ እና ሌሎች 3 ግለሰቦች
በጦር መሳርያ በማስፈራራት የፓለቲካ ድርጅት አባል ነህ በማለት አፍነው በመወሰድ ከፍተኛ ድብደባ አድርሰውባቸዋል።
2. በተመሳሳይ አቶ አበበ ደጉ የኢዜማ አባል በመሆናቸው ድብደባ እንደደረሰባቸው ኢሰመጉ ለመረዳት ችሏል፡፡

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 16
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
አቶ ታደሰ ስንታየሁ በደ/ጎንደር ዞን እንደቤቱ ከተማ ነዋሪ ሲሆን የአብን ፓርቲን ወክሎ ለምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርግ በነበረበት
ወቅት ፍቃድ አልያዝክም በማለት የቀበሌው ምድብተኛ ፖሊስ በጦር መሳሪያ በማስፈራራት ብሎም በመደብደብ የወገብ
ስብራት፣ የሰውነት መላላጥ ፣ የጀርባ ስብራት እንዲሁም ደረቱ ላይ ከፍተኛ ህመም ያስከተለ ጉዳት አድርሶበታል።

ህገ ወጥ የምርጫ ጫና
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 38 ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቀለም፣ በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣
በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሰረተ ልዩነት ሳይደረግበት በማንኛውም
የመንግሥት ደረጃ ለሚገኝ መሥሪያ ቤት በየጊዜው ምርጫ የመምረጥና የመመረጥ መብት አለው። ; ምርጫው ሁለንተናዊ እና
እኩልነት ያለው እና በሚስጥር ድምጽ የሚካሄድ ሲሆን ይህም የመራጮችን ፍላጎት በነጻነት የመግለጽ ዋስትና ይሰጣል።
በአፍሪካ የሰው እና ህዝቦች መብት ቻርተር አንቀጽ 25 እንደተደነገገው ማንኛውም ዜጋ ያለ አንዳች ልዩነት የመምረጥ እና
በእውነተኛ ወቅታዊ ምርጫ የመመረጥ መብትና እድል ይኖረዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)


በፓርቲውም ሆነ በአባላቶቹ ወይም በእጩዎቻችን ላይ ከምርጫ በኋላ የከፋ ጉዳት እና የደረሰ የመብት ጥሰት ባይኖርም
የምርጫዉ ዕለት እና ከምርጫ በፊት ግን የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች በፓርቲው እና አባሎቹ ላይ ኢ-ዴሞክራሲያዊ
ድርጊቶች መፈጸማቸውን ገልጸዋል።
 1ኛ የፓርቲያቸው እጩ ታዛቢዎች በፖሊስ ተባረዋል፣
 2ኛ ባጅ ሲከፋፈል ምርጫ ቦርድ በትክክል የምርጫ ጣቢያዎችን ስያሜ እና የታዛቢዎቻቸውን መረጃ ባለመላኩ
እንግልት እንደደረሰባቸውና እስከ መባረርም የደረሱ ታዛቢዎቸ ነበሩ።
 3ኛ አንዳንድ ቦታ ደግሞ ያልሆነ ግርግር በመፍጠር ታዛቢዎችን ለማባረር ተሞክሯል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ያጋጠማቸው የፓርቲ ታዛቢዎች፤

ተ.ቁ የታዛቢዉ ስም ቦታ
1 ሃይለማርያም ተባባል ባህርዳር ዙርያ
2 ቃልኪዳን ውቤ ባህርዳር ዙርያ
3 ደሳለኝ መልኬ ባህርዳር ዙርያ
4 አስቻለው አዳመ ባህርዳር ዙርያ
5 አንሙት መልኬ ባህርዳር ዙርያ
6 ሙሉዓለም ኋይሌ ባህርዳር ዙርያ

 በሌላ በኩል በምዕራብ ጎጃም ዞን በአዴት የምርጫ ወረዳ ከምርጫ በፊት በሰከላ፣ በደ/ማዕአላዊ፣ በጎሽዬ፣ በዴንሳ ባታሊዮን
ቀጠናዎች የከፈቷቸው ቢሮዎች ባነሮቻቸው እንደተቀደዱ እና የሰቀሉት ሰንደቅ አላማ እንደወረደባቸው በ22/06/2012
ዓ.ም በአዳራሽ ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ በወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ በነበሩት ግለሰብ ትዕዛዝ ስብሰባውን እንዳያደርጉ
ተከልክለው እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጸዋል፡፡
 በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ 1 የኢዜማ ስራ አስፈጻሚ በሆነው አቶ ዘማቹ ቢነጋገሩም ላይ በሚሰራበት ቁህር ሚካኤል
የጤና ጣቢያ ከምሽቱ 2:00 ላይ በክላሽና በዱላ ተደብድቦ እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጿል።
 በምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንች ቆለላ ወረዳ አዲስ አለም ከተማ 01 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ይበልጣል ሙሉ ታፈረ የተባሉ
የፓርቲው አባል የኢዜማ ፖለቲካ ታረምዳለህ በሚል የወረዳው ሰላምና ደህንነት ሃላፊ 3 ግለሰቦችን መሳሪያ በማስታጠቅ
መጋቢት 18/2013 ዓ.ም መሳሪያ ደቅነው በብረትና ሌሎች ቁሳቁስ በመጠቀም ከፍተኛ የሆነ ድብደባ እንደደረሰበት
የሚገልጹ ማስረጃዎችን ለኢሰመጉ አቅርበዋል።

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 17
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)

ተ.ቁ ስም ከተማ ወረዳ የምርጫ ጫናው አይነት


1 መ/ር ምስጋናው ጋሻ ደምበጫ ደምበጫ ምርጫ እንዳይታዘቡ
2 አቶ የሻነው ደግዋለ ደ/ወርቅ ደ/ወርቅ ምርጫ እንዳይታዘቡ
3 አቶ በላይነህ ጎልቴ አ/ዘመን ሊቦ ኮምኮም ከህግ አግባብ ውጭ ከስራ
መሰናበት
4 አቶ ገበየሁ አሰም አ/ዘመን ሊቦ ኮምኮም ከህግ አግባብ ውጭ ከስራ መሰናበት
4 አቶ ሙሉነህ አንተንህ አ/ዘመን ሊቦ ኮምኮም ምርጫ ቅስቅሳ እንዳያርጉ
እናት ፓርቲ
በአማራ ክልል ዋግህምራ ዞን፣ ዳህና ወረዳ አቶ አበባው ባህሩ የተባሉ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ በመሥሪያ ቤታቸው ሃላፊ
በሆኑበት 01/08/13 ዓ.ም ጀምረው ፈቃድ ሳይጠይቁ፣ ሁለት ዓመት ያልተጠቀሙበት እረፍት እያላቸው ሕጉ ከሚፈቅደው
ውጪ ዕጩ ስለሆኑ ብቻ ግዴታ ያለ ደምወዝ እንዲወጡ በማድረግ፣ በአካል እያሉ እንዳይፈርሙም፣ በሥራ ገበታቸው ላይ
ተገኝተው እንዳይሰሩና በሃላፊነታቸው ላይ ውክልና ጭምር በመስጠት ሥነልቦናዊ ጉዳት እንዲደርስባቸው ተደርጎ የነበረ
መሆኑን ለኢሰመጉ ገልጸዋል።

ተ.ቁ ስም ከተማ ወረዳ የምርጫ ጫናው አይነት


1 አቶ መኮንን ጠቀሸው ደምበጫ ደምበጫ ምርጫ እንዳይታዘቡ
2 አቶ ፍቃዱ ጥሩሰው አዲስ አለም አዲስ አለም ምርጫ እንዳይታዘቡ
2 አቶ አሰቡ ዳምጤ ፍ/ሰላም ፍ/ሰላም ምርጫ እንዳይታዘቡ
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ
1. የክልል ምክር ቤት ተወዳዳሪ የሆኑትን መ/ር አሰፋ ሽቱ ብልፅግና ባደራጀው በታወቁ አንድ ግለሰብና በማይታወቁ ሦስት
ግብረ አበሮች በሽጉጥ የመግደል ሙከራ ማድረግ፡፡ (ዚገም ወረዳ /0ቅላጅ ምርጫ ክልል)
2. የህዝብ ተወካዮች ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ወ/ሪት ልቅ ሻሽቱ ከፈለ በክልል ባሉ የብልጽግና ሰዎች ከሚሠሩበት መንግስታዊ
ያልሆነ ተቋም (NGO) ጋር በመቀናጀትና ዕጩ ቅየራ ጊዜው አለማለፉን ጠብቀው ፓርቲውን ካለቀቅሽ የሥራ ውል
እናቋርጣለን በማለት ከፓርቲው ዕጩነት እንዲወጡ አድርገዋል። (ዳንግላ ምርጫ
3. የብልጽግና ፓርቲ ሰዎች ዕጩዎች ቦርድ ላይ በምርጫ ቦርድ ይፋ ከመደረጉ በፊት እየደወሉ ምርጫ ቦርዱን የዕጩዎችን
መረጃ እንዲሰጧቸው ያስጨንቁ ነበር። (ፍኖተ ሰላምና አከባቢው)
4. በየገጠር ቀበሌው ሕዝቡን እየሰበሰቡ ከፍተኛ ስም ማጥፋት፣ አልፎ ተርፎም ስድብ በባነር አሠርቶ እስከማውጣት
ደርሶባቸዋል፡፡ (ፍኖተ ሰላምና አከባቢው)
5. የመራጮች ምዝገባ ዝርዝር ይፋ ከመደርጉ በፊት አመራሮችን መድበው የመራጮችን መርጃ እንዲሰጧችው ማስገደድ፡፡
(ፍኖተ ሰላምና አከባቢው)
6. አባላትና ዕጩዎች ግንቦት 14 በወልቃይት ቀበሌ ላይ ማዋከብና እና ማጉላላት ደርሶባቸዋል።
7. ቀበሌ 11 የሁለት አባላት የፓርቲ ቲ-ሸርትና ምርጫ ካርድ ተወስዷል። ለሕዝብ ሊበተን ያለ የምርጫ ምልክት በሙሉ
ተቀምቷል። የዕጩ ተወዳዳሪ ቤተሰቦች 12/09/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በብዙ ታጣቂዎች እንዲከበብ ተደጓል።
ቤተሰቦቻቸውንም ከፍተኛ ማስፈራራት አድርሰውባቸዋል። አንድ ዕጩ ወደዚያ ቀበሌ (ወደ ትውልድ ሰፈሩ) ከሄደ
እንደሚገሉት ተደጋጋሚ መልዕክት ተልኮበታል። (ስማዳ ወረዳ ስማዳ 1ምርጫ ጣቢ)
8. በባሶና ወረና ወረዳ በጉዶቀረት ምርጫ ጣቢያ የተለጠፈ ባነር መቅደድ በአንኮበር ወረዳ አልዪ አምባ ምርጫ ጣቢያ፣ ለእናት
ፓርቲ ጽ/ቤት ያከራዩትን ግለሰቦች በማስፈራራት ቢሮ ማሳጣት፣ ቅስቀሳ ማወክ፣ ቤተሰብ ማስፈራራት ተደርጓል። (ደብረ
ብርሃን እና በአከባቢው)

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 18
ንብረት ውድመት
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
1. የአባሎቻቸው እና ደጋፊዎቻቸው በሀሰት ውንጀላ ንብረታቸው እንዲወድም ተደርጎ የነበረ ሲሆን ለምሳሌ የአቶ አግማሴ፣
ሞገሴ እና ሞገሴ ገበየሁ የባህርዛፍ አትክልት ከፍ/ቤት ትዛዝ ውጪ እንዲወድምባቸው እና የማዳበሪያ አቅርቦት
የተከልክለው እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጸዋል፡፡
2. የወረዳው ፓርቲ ዋና ጸሀፊ መቶ አለቃ አንዷለም ጸጋዬ የድርጅት ቤት በ3 ጥይት ተመቶ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር
ለኢሰመጉ ገልጸዋል።

ነፃነት እና እኩልነት

ተ.ቁ ስም ከተማ ወረዳ


1 አባይነህ አሄቦ ሰላም በር ቁጫ

ህገወጥ እስራት
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
1. በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ መርዓዊ ከተማ ግንቦት 12/2013 ዓ/ም የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የከተማው ህዝብ
ለድጋፍ እንደወጣ ካረጋገጠ በኋላ ከገጠር መሳሪያ የታጠቁ ሚሊሻዎችንና አርሶ አደሮችን በመኪና እና በፈረስ አምጥቶ
ከተማው ላይ የድጋፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርግበት ጊዜ በከተማው የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ፣
የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችና የኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ መታሰቢያ ከፍተኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት ሲወጡ የታጠቁ
ሚሊሻዎችና የከተማው ፖሊሶች ወደ ተማሪዎች ላይ በመተኮስ ግድያ እና የአካል ጉዳት ማድረሳቸውን በምርመራችን
ማረጋገጥ ችለናል። ከዚህ ጋር ተያይዞም በከተማው ያሉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አራት አባላትና ደጋፊዎችን ተማሪዎችን
ተቃውሞ አነሳስታችኋል በሚል ያለምንም ፍርድ ለ70 ቀናት ባህርዳር በሚገኘው ሰባታሚት ማረሚያ ቤት ታስረው ከቆዩ
በኋላ በተደጋጋሚ ዋስትና ቢጠይቁም ተከልክለው እንደነበር፣ ሀምሌ 23/2013 ዓ.ም ለያንዳንዳቸው በ2000.00 ብር
ዋስትና በማቅረብ ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ ተደርገዋል።
2. በምዕራብ ጎጃም ዞን በደምበጫ የምርጫ ክልል በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ገሊላ በተባለ ቀበሌ አቶ ሙሉነህ አንተነህ የተባሉ
የፓርቲው አባል የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይችሉም ተብለው በቀበሌው አመራሮችና ሚሊሻዎች ድብደባ ደርሶባቸው
እንደነበር፣ በምርጫ ዕለትም ከደንበጫ ከተማ ውጭ ባሉ የምርጫ ጠቅላይ ጣቢያዎች የፓርቲው ታዛቢዎች እንዳይታዘቡ
እንግልት ፣ ዛቻ ማስፈራራትና ህገወጥ እስራት ደርሶባቸው እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጸዋል፡፡
3. በምስራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናውጋ ደብረወርቅ የምርጫ ክልል በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የነበሩ ችግሮች እንዳሉ ሆነው
የምርጫው ዕለት 1ኛ ለ በተባለ የምርጫ ጣቢያ ላይ የፓርቲው ታዛቢ አቶ እውነቱ ሉሌ የተባለ የምርጫ ካርድ ካወጣበት
ጣቢያ ላይ ድምጽ ሰጥቶ ሲመለስ እና ምርጫ ወደ ሚታዘብበት ጣቢያ ሲሄድ የቀበሌው አመራሮችንና ሚሊሻዎች ድብደባ
ፈጽመውበት ምርጫ እንዳይታዘብ ተደርጓል። 2ኛ በምርጫ ክልል ኮሶዙራ በተባለ የምርጫ ጣቢያ አቶ ሽፈራው ቀዜ እና አቶ
ደሴ ሽመልስ የተባሉ የፓርቲው ታዛቢዎች እንዳይታዘብ ከምርጫው እለት አንድ ቀን አስቀድመው በ13/09/2013 ዓ.ም
ታስረው ምርጫው ሲጠናቀቅ ከእስር እንዲፈቱ ተደርጓል። በዚያው የምርጫ ክልል ሶማ ሀና በተባሉ የምርጫ ጣቢያዎች
የቀበሌው ሊቀ መንበርና ሚሊሻዎች ከወረዳው የፖለቲካ አመራር ጋር በመናበብ ታዛቢዎቻቸውን በጦር መሳሪያ
በማስፈራራት ከምርጫ ጣቢያው በማባባረር ምርጫውን እንዳይታዘቡ ተደርገዋል።
4. ምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ መሳርያ ምድር መርጦ ለማሪያም የምርጫ ክልል ኢዛና ቀበሌ 30 እየተባለ በሚጠራ ቦታ ውስጥ
ብዙነህ አስተምር የተባለ የ22 ዓመት እድሜ ተማሪ የአብን ደጋፊ ነህ ፣ ለምን ለአብን የምርጫ ቅስቀሳ ስትሰራ ቆየህ በሚል
ምክንያት ሰኔ 12/2013 ዓ.ም በቀበሌ ሚሊሻዎች በጥይት እንደተገደለ የወረዳው የአብን አስተባባሪዎች ማስረጃ ለኢሰመጉ
ሰጥረተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በመርጦ ለማሪያም ከተማ ቀበሌ 04 የሚኖር አቶ ዳንኤል ገዜ የተባለ ነዋሪ የአብን አባል
በመሆኑና ለፓርቲው በቀን 08/09/2013 ዓ.ም ቅስቀሳ ሲያደርግ ውሎ ማታ ከምሽቱ 5፡40 ላይ ከ 9 በላይ በሆነ ጥይት
ቤቱ ሲደበደብ ማደሩን የፓርቲው አመራሮች ማስረጃ ሰጥተዋል። በተጨማሪም የመንግስት አካላት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 19
በማስፈራራት፣ የእርሻ ግብዓት ለምሳሌ ማዳበሪያ ምርጥ ዘር አታገኙም በማለት በዛቻ ቤተሰቦቻቸውን በማስፈራት የተፎካካሪ
ፓርቲ አባላት ላይ ጫና በማድረግ ምርጫው የተሳካ እንዳይሆን አድርገዋል ፡፡
5. በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ አዲስ ዘመን ከተማ የአብን ፓርቲ እጩ የነበሩት አቶ በላይነው ጉልቴ የተባሉት ግለሰብ
በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ከወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊዎች አመራሮች ሰኔ 04/2013 ዓ.ም በጦር መሳሪያ
ከዛቻና ማስፈራሪያ በተጨማሪም ከስራ ገበታቸው እንደተባረሩና የግድያ ሙከራም እንደተደረገባአው በምርመራ
ተረጋድጡአል። ከዚህ በተጨማሪም በአዲስ ዘመን ከተማ 01 ቀበሌ ትምህርት ገበየሁ አደም የተባሉ ነዋሪ በፓለቲካ
አመለካከታቸው ምክንያት ሰኔ 04/2013 ዓ.ም በቀበሌው ሚሊሻዎች የጸጥታ ሀይሎች በጥይት ተተኩሶ ከመመታት እስከ
ስራ ስንብት ድረስ እና የግድያ ሙከራ እንደረሰባቸው አስረድተዋል፡፡

እናት ፓርቲ
1. በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢ ጥናን ወረዳ የሽረት መድሃኒያለም በተባለ ቀበሌ ግንቦት 28/2013 ዓ.ም የፓርቲው አባላት የምርጫ
ቅስቀሳ ለማድረግ በሄዱበት በአከባቢው ያሉ የፖለቲካ አመራሮችና የታጠቁ ሚሊሻዎች ቅስቀሳ እንዳያደርጉ ተከልክለው
እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጸዋል።
2. በምዕራብ ጎጃም በዞን ሲከላከሉ ከተማ 01 ቀበሌ የሚኖሩ አቶ ጌታቸው አያሌው የተባሉ ፓርቲው አባል የምርጫ ቅስቀሳ
በሚየደርጉበት ሰዓት ከአካባቢው የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና ደጋፊዎች ዛቻና ማስፈራራት ይደርስባቸው እንደነበር
ሚያዝያ 16/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 4:00 አከባቢ በድንጋይ መኖሪያ ቤታቸው መደብደቡን በምርመራ ማረጋገጥ ተችሉዋል።
በዚሁ ዞን ጎንች ቆለላ ወረዳ ግንቦት 2013 ዓ.ም ይናጭ በተባለ ቀበሌ የፓርቲው አባል አቶ በፍቃዱ ጥሩሰው ፓርቲውን
ወክለው የምረጡኝ ቅስቀሳ ለማድረግ በሄዱበት ወቅት ቅስቀሳውን እንዳያደርጉ የቀበሌው አመራሮች አስፈራርተው
መመለሳቸውን ለኢሰመጉ ገልጸዋል።
3. ደንበጫ ወረዳ እንጂኔሪንግ ቀበሌ ላይ ደግማ በር 28/09/2013 ዓ.ም ለምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ሲሄዱ የምርጫ ቅስቀሳ
ማድረግ አትችሉም ተብለው ተከልክለው ተከራይተው የነበሩትን መኪና የድምጽ ማጉያቸውን ቀምተው ለ1 ቀን 4 አመራሮች
እንደታሰሩባቸው ከወረዳው የፓርቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኢሰመጉ ባገኘው መረጃ ለመረዳት ችሏል። ታሳሪዎቹ 1ኛ አቶ
መኮንን የህዝብ ተወካዮች ዕጩ የነበሩ 2ኛ ዲ/ንጉሥ ቀማው አራጋው የክልል ም/ዕጩ የነበሩ 3ኛ አቶ ፋንታሁን ጋሻየ እና 4ኛ
ዲ/ን ዘመኑ ክንዴ ናቸው፡፡
4. ጌሳታይ ቀበሌ ለቅስቀሳ የሄዱ አቶ ጋርዳቸው እና አቶ መክበብ የተባሉ የፓርቲው አባላት በቀበሌው አስተዳደር ትዕዛዝ
ለእሥር ተዳርገው እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጸዋል። (ዚገም ወረዳ /ዓቅላጅ ምርጫ ክልል)
5. በቀን 22/08/2013 ዓ.ም የእናት ፖርቲ አባላት ቅስቀሳ ሲያደርጉ አዝና ከተማ ላይ አቶ አማኑኤል ንብረት እና ሾፌሩን እስከ
ረዳታቸው ለምን ቀሰቀሳችሁ በማለት ለእስር ተዳርገው እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጸዋል። (ግምጃ ቤት ምርጫ ክልል)
6. የቀበሌው ሊቀመንበር የሆነው ግለሰብ ሥራ እንዳይከውኑ በመከልከል ብሎም ከዛቻና ማስፈራሪያ በኋላ 23/07/13 ዓ.ም
አቶ ዳርጋቸው በላይ እና አቶ መካብ አዳነ የተባሉ አባሎቻቸውን አስሯቸው እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጸዋል። (ግምጃ ቤት
ምርጫ ክልል)
7. ገዢው ፓርቲ በእንድ በኩል ቤተ-ዕምነት ውስጥ የምርጫ ቅስቀሳ አድርጋችኋል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሁከት ሲነሳ ድንጋይ
ወርውረዋል በማለት አቶ ሀውልቱ ጸጋዬ የተባሉ የፓርቲያቸው የሕዝብ ተወካይ ዕጩ በ26/07/13 ከጠዋቱ 4:00 ጀምረው
ለ4 ቀናት ታስረው እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጸዋል። (ምሥራቅ ጎጃም)
8. በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ ምርጫ ክልል ሁለት ላይ የእናት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በ09/08/2013 ዓ.ም በድምጽ
ማጉያ እየቀሰቀሱ በነበሩበት ወቅት መቀስቀስ አትችሉም ተብለው ታስረው እንደነበር ለኢሰመጉ ገልጸዋል፡፡ (ደቡብ ጎንደር)
9. 14/09/2013 ዓ.ም አቶ ጌጤ ደሴ የተባሉ አባልና የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ የሆኑት አቶ ታረቀኝ ምሳነው የወረዳ
የብልጽግና ተወካይና የከተማው ከንቲባ በትብብር ቅስቀሳ ላይ እያሉ መቀስቀስ አትችሉም በማለት ታስረው እንደነበር
ለኢሰመጉ ገልጸዋል (ስማዳ ወረዳ ስማዳ 1ምርጫ ጣቢ)
10. እንዋር ምርጫ ክልል የእናት ፓርቲ የክልል ተመራጭ የሆነ በቅስቀሳ ላይ እያለ በፖሊስ ታስሮ ከወረዳውና ከዞን አስተዳደር
መፍትሔ ስለጠፋ እስከ ምርጫ ቦርድ ሪፖርት አድርጎ ከአንድ ቀን በኋላ ከእሥር መፈታቱን ለኢሰመጉ ገልጸዋል። (ደብረ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 20
ብርሃን እና በአከባቢዋ) ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ በደብዳቤ ቁጥር FEP/00/458 በቀን 09/10/2013 ዓ.ም ስለምርጫው
ሂደት የሚከተለውን አሳውቀዋል
 የገዢው ፓርቲ አባላት፣ አመራሮች እና ደጋፊዎች በአስተሳሰብ ያልተሻገሩና ያልታደሱ ከመሆናቸው አንጻር የለመዱትን
በመንግስት እና በህዝብ ሃሳብ እና ንብረት ለፓርቲ ስራ በመጠቀም የመንግስት ስራተኞችን ሳምንት እና ከዚያ በላይ
በመሰብሰብ ፤ በህዝብ ገንዘብ ውሎ አበል በመክፈል የምርጫ ቅስቀሳ እና ስብሰባዎችን አድርገዋል በማለት አሳውቀዋል ፡፡

ከምርጫው ጋር ተያይዞ የተለያዬ ሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በአማራ ክልል ወረዳዎች


በአንዳ ቤት ወረዳ
1. በቅስቀሳ ላይ የሙቀጭ ቀበሌ ፖሊስ ኮንስታብል ከመንግስት የፍቃድ ደብዳቤ ካላመጣችሁ በሚል የተለያየ ዛቻና ዘለፋ
ከመናገሩ በላይ ድብደባና ወከባ ፈፅሞባቸዋል ፡፡
2. የአፀደማርያም ቀበሌ የፀጥታ ሀላፊ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያወጣውን የስነምግባር ደንብ አዋጅ ቁጥር 1162/2011
አንቀፅ 12 ሀ የተጠቀሰውን በመጣስ በአሳባቸው ገብርኤል ቤተክርስቲያን ክብረ በዓል ላይ የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግና
የመሪዎቻችን ገዳይ አብን ነው በማለት የአብንን ስም አጥፍተዋል ፡፡
3. 05/09/2013 የአንድቤት ወረዳ ብልፅግና ባደረገው የድጋፍ ሰልፍ ከየቀበሌው በአንቡላንስ እና በመንግሥት መኪና
ያመጣቸው አባላት የምርጫ ህጉን በጣሰ መልኩ በሰልፉ ላይ ጥይት በመተኮስ በህብረተሰብ ላይ ጭንቀት እንዲፈጠር
አድርገዋል፡፡
4. በ15/09/2013 የአብን አባል አቶ ሀይለ እይሱስ ሀይለ ማርያም በማህደረ ማርያም ቀበሌ በቅስቀሳ ላይ እያሉ የወረዳው
አመራር ሚሊሻዎችን በመያዝ መቀስቀስ አትችሉም በማለት ለተወሰነ ሰዓት አስረው በማቆየት ህብረተሰቡ ከተበተነ በኋላ
ለቀዋቸዋል።

በጉና በጌምድር ወረዳ


1. በቀን 10/08/2013 ዓ.ም ወደ ውቅሮ ቀበሌ ለቅስቀሳ የወጡ የድርጅቱ ሰብሳቢ የሆኑት መ/ር ጌትነት ስመኝ እና ሁለት
አባሎቻቸው የሰበሰቡትን ህዝብ ከወረዳው በተላኩ አመራሮች በቀበሌ ሚሊሻ እንዲበተን በማድረግ ወረዳው መኪና ልኮ
በቀበሌ ሚሊሻ ተይዘው ወደ ክምር ድንጋይ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደው ከ 3:00 እስከ 6:20 ታግተዋል::
2. በቀን 17/08/2013 ዓ.ም ወደ መገንዲ ቀበሌ ለቅስቀሳ የወጡ አመራሮች ከወረዳው በተላከ መኪና ክምር ድንጋይ
ፓሊስ ጣቢያ ተወስደው ያለምንም ጥፋት ለሁለት ቀናት ታስረዋል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ላይ በምርጫ ምክንያት የደረሰ ጉዳት

ተ/ቁ/ ሙሉ ስም ጾታ እድሜ ጉዳቱ የጉዳቱ አይነት


የደረሰበት ቀን
1 ካናሶ ካታሳ ወ 50 02/12/13 ማግለል አስራትና ቅጣት
2 ማልቃ ማይራ ወ 18 11/12/13 ማግለል አስራትና ቅጣት
3 ጋራሎ ባደያ ወ 18 11/12/13 ማግለል አስራትና ቅጣት
4 ካርሻና ካሣሦ ወ 30 15/11/13 ማግለል አስራትና ቅጣት
5 ካሎሳ ካይሳ ወ 25 11/12/13 ማግለል አስራትና ቅጣት
6 ካታማ ካሣታ ወ 24 11/12/13 ማግለል አስራትና ቅጣት
7 ካሎ ካሻርታ ወ 35 11/12/13 ማግለል አስራትና ቅጣት
8 ኩይላ ኩታቶ ወ 28 11/12/13 ማግለል አስራትና ቅጣት
9 ኩሾ ኩንጨታ ሴ 45 25/12/13 ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ
10 ገረሙ ሽሬ ወ 28 23/12/13 ቅጣት
11 ጋሻው ጋሮ ወ 27 28/12/13 ድብደባና እስራት
12 ከሻይና ኩንሱሌ ወ 48 02/12/13 ማግለልና እስራት
13 ካይታሬ ካሡ ወ 38 7/12/13 መታወቂያ ላይ ማህተም መከልከል

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 21
14 ዋንቴ ከልቻ ወ 32 25/12/13 መታወቂያ ላይ ማህተም መከልከል
15 ኮልሞታ ኸኛ ወ 28 23/12/13 ቅጣት
16 ካሣርቶ ገመቹ ወ 45 24/11/13 ድብደባና አስራት
17 ባህሩ ባዳኔ ወ 25 12/11/13 ስደት
18 አወቀ ኃይሉ ወ 35 12/11/13 ስደት
19 አምሣሉ አያኖ ወ 38 12/11/13 ስደት
20 ካሻወን ካራቶ ወ 38 12/11/13 ስደት
21 አለሙሳ አራርሶ ወ 42 12/11/13 ስደት
22 ገለቦ ገመዶ ወ 26 12/11/13 ስደት
23 ያኔርፍ ት/ቤት ወላጅ በዓል - - 23/12/13 ልዩ ሀይልና ፖሊስ ማሰማራት
24 አገኘሁ እርካታ ወ 40 15/11/13 ግራ እግር ስብራት
25 ኩሲቶ ሸካይዶ ወ 28 21/12/13 አስርና ድብደባ
26 አደመ ሀጎስ ወ 32 21/12/13 አስርና ድብደባ
27 ደመላሽ ካሳዳ ወ 28 21/12/13 አስርና ድብደባ
28 ታፈሰ ታዬ ወ 20 21/12/13 አስርና ድብደባ
30 እንዳሻው ኃይሉ ወ 17 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
31 ዳዊት ጋቾ ወ 26 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
32 በርሻ ኮሎ ወ 25 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
33 ገዮላ በርሻ ጉዮላ ወ 22 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
34 ጉዮላ ገሀኖ ገለቦ ወ 16 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
35 ተንጎ ሮቾ ገልሰሞ ወ 28 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
36 ተይካንቶ ካፎ ገለቦ ወ 35 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
37 ቦራሌ ኩሴ ቦራሌ ወ 20 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
38 ኩሴ ለሚታ ገሀኖ ወ 20 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
39 ኩሴ ንግቦ በርሻ ወ 30 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
40 አማኑ ኩሴ ቦራሌ ወ 19 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
41 ገልዳይቶ ገልገሎ ገልዳይቶ ወ 28 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
42 ኃይሉ ገልገሎ አባባደ ወ 53 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
43 በርሻ ጉቾ ቃይራኔ ወ 28 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
44 ታምሩ ሐልገቴ ገልሰሞ ወ 35 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
45 ተንጎ ገቢኖ ገልሰሞ ወ 32 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
46 ጎዮላ ኡርማሌ ጉዮላ ወ 15 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
47 ግርማ ገደኖ አይላቴ ወ 25 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
48 ገለቦ ገደኖ አይላቴ ወ 16 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
49 ገለቦ አያኖ ጉዬ ወ 28 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
50 ኦርካይዶ ጉዮላ ኩቻሌ ወ 30 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
51 ያልሳ ኦላታ ደሐይሼ ወ 29 27/10/13 እስር፣ንብረትዘረፋ፣ማሰቃየት
52 ኦላሞ ኦርካይዶ ዋቆ ወ 23 12/11/13 ከፍተኛ ድበደባና እስራት
53 መ/ር መኮንን ሞላ ወ 34 29/11/13 እስራት፣ከአካባቢ መሰደድ
54 ወ/ሮ ኩሾ ቀንጨታ ሴ 46 2/12/13 ከማህበራዊ ህይወት ማግለል
55 ወ/ሮ ነፃነት ገዋዶ ሴ 25 3/11/13 እስርናከሴፍትኔትእርዳታ መከልከል
56 ሣሙኤል ዘነበ ወ 19 12/11/13 ከማህበራዊ ህይወት ማግለል
57 አያና ኦርካይዶ ሴ 24 14/11/13 የሰውነት የውስጥ ጉዳት

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 22
58 መ/ር ተፈራ ደብተራ ወ 30 4/11/13 እስር፣ድብደባ
59 መ/ርት ሰናይት ኩማ ሴ 25 30/10/13 ማስፈራራት፣ዛቻ
60 መ/ር በየነ በርሻ ወ 37 12/11/13 ስደት
61 አማኑኤል ኦርካይዶ ወ 30 12/11/13 ስደት
62 አብት ኩሴ ወ 32 12/11/13 ስደት
63 ኡርማሌ ኦርካይዶ ወ 48 12/11/13 ስደት
64 ኩሴ ገያቦ ባማሌ ወ 55 12/11/13 ስደት
65 ገለሃ ገያቦ ሣቦ ወ 28 12/11/13 ስደት
66 ካርሞ ካላሌ ወ 42 12/11/13 ስደት
67 ገበደ ደይካንቶ ወ 55 12/11/13 ስደት
68 አራሪሶ ለምታ ወ 45 12/11/13 ስደት
69 ካሳዬ አሻሾ ወ 56 12/11/13 ስደት
70 ዘመቻ አየለ ወ 43 12/11/13 ስደት
71 ታከለ ኩሴ ወ 25 12/11/13 ስደት
72 አድሱ ተስፋዬ ወ 32 12/11/13 ስደት
73 በርሻ አልኮ ወ 32 12/11/13 ስደት
74 በርሻ ኩሴ ወ 28 12/11/13 ስደት
75 አብርሀም ኩሴ ኡንቴ ወ 33 12/11/13 ስደት
76 ኩሴ አድማሱ ወ 20 8/12/13 በድብደባ የኩላሊት ችግር
77 አድሱ ገረሙ ወ 36 12/11/13 በድብደባ የአከርካሪ አጥንት ችግር
78 ኦላሞ ኦርካይዶ ወ - 12/11/13 ድብደባ
79 ኡርማሌ ገልሰሞ ወ 14 12/11/13 ድብደባ
80 ለምታ አድማሱ ወ 38 12/11/13 በድብደባ የውስጥ ሰውነት ጉዳት
81 ሽታዬ ኩሴ ለምታ ሴ 43 12/11/13 በድብደባ አይን፣ጥርስና አካል ላይ ጉዳት
82 ኩሴ በርሻ ደምሴ ወ 22 13/11/13 ድብደባ ከምሽቱ 3፡00ሰዓት እስከ ንጋት
83 ኦልሳ ኦልድሻ አሻሾ ወ 28 8/11/13 አስሮ በመደበደብ ማሰቃየት
84 በየነ በርሻ ቱባሮ ወ 25 8/11/13 አስሮ በመደበደብ ማሰቃየት
85 ገዛኽኝ አበበ ወ - 8/11/13 ከማህበራዊ ኑሮ ማግለል፣ዝርፊያ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 23
ክፍል 2
በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች
1. ሲዳማ ክልል እና ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል
በአቦስቶ ከተማ ዌይኒናታ ገጠር ገበሬ ማህበር ውስጥ በግብርና ስራ ላይ ተሰማርተው ለረዥም አመት ይኖሩ የነበሩ 179 አርሶ
አደሮች በአካባቢው ለሚገኘው የፖሊስ ኮሌጅ ለማስፋፋት በሚል ምክንያት ከመንደራቸው ከተነሱ በኋላ ተመጣጣኝ ክፍያ
ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ ተገቢ የመሬት ካሳ እና የ10 ዓመት የምርት ካሳ ለማግኘት በተደጋጋሚ ከመንግስት ሃላፊዎች ጋር ስምምነት
የተደረገና የካሳ ክፍያም ለመክፈል የተነጋገሩ ቢሆንም ከ1998 ጀምሮ ለአርሶ አደሮቹ የተገባላቸውን ካሳ ክፍያም ሆነ
ማንኛውንም አይነት ጥቅማ ጥቅም በአግባቡ አላገኙም በዚም ምክንያት ለተለያዩ አይነት ኢኮኖሚያዊ፣ ስነልቦናዊ እና የአካል
ጉዳት እየተዳረጉ ሲሆን ጉዳዩ እልባት ያላገኘበትም ምክንያት ደግሞ በክልሎች መካከል በተፈጠረው የክልል ልዩነት ማለትም
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና በሲዳማ በነበረው የክልል ይግባኛል ጥያቄ ነው፡፡ የሲዳማ ክልል የክልልነት ጥያቄው ምላሽ
ሲያገኝ የደቡብ ፖሊስ ኮሌጅ ጉዳዩ ዕልባት ሳያገኝ፣ አርሶ አደሮቹም በሁለቱም ክልሎች መካከል ባለው ግልፅ ያልሆነ አሰራር
ጉዳዩን የቱ ጋር እና ማን እንደሚመለከተው በግልጽ ባልተቀመጠበት ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ጠቅሰው ለኢሰመጉ
ባመለከቱት መሰረት በተደጋጋሚ ጊዜ ጉዳዩን አጣርቶ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ምንም አይነት መፍትሄ
አለመሰጠቱን ለመረዳት ተችሏል፡፡
በደቡብ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አጣሪ ቡድን ባጠናው መሰረት የአርሶ አደሮቹ ጥያቄያቸው ትክክል መሆኑን አምኖ
ካሳም እንዲከፈላቸው በቀን 05/03/2011 አ.ም በጻፈው ደብዳቤ አረጋግጧል፤ ይኸውም
1. የአፈር ማሻሻያ 4,451,161.68 ብር
2. የማፈናቀያ ካሳ 67,134,501.41 ብር
3. የሁለት ዓመት ሳይከፈላቸው የቆየበትን 13,435,276.70 ብር
4. የንብረት ግምት 14,689,937.60 ብር
በአጠቃላይ 100,010,877 ብር ሲሆን ከዚህ ቀደም የተከፈለ 20,815,913ብር ስላለ በቀሪው 79,194,963.60ብር
እንዲከፈላቸው የሚያመለክት ነበር፡፡ ግን ይህ መደበኛ መግለጫ እስከተዘጋጀበት ድረስ ካሳው አልተከፈላቸውም፡፡ ይህንንም
በ179 አርሶ አደሮች ተወክለው አቤቱታ ያቀረቡት ሰባት ተወካዮች ካቀረቡት አቤቱታ ለመረዳት ተችሏል፡፡

1. ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል


 በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ በጋጮ ባባ ወረዳ ኩይሌ ቀበሌ የደረሱ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች

ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2012 ዓ.ም በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ በጋጮ ባባ ወረደ ኩይሌ ቀበሌ
አስተዳዳሪ የቀበሌው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰት እንዳደረሱ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሰመጉ አሳውቀዋል፡፡
ይህን የመብት ጥሰት ያደረሱትም ከወረዳው አስተዳደር አመራሮች ጋር በመሆን እንደሆነ እና የዚህ የመብት ጥሰት ዋነኛ
ምክንያት የግል ጥቅም በማስቀደም ሀብት ለማካበት ስልጣንን ተገን ማድረግ መሆኑን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች
ለመረዳት ችሏል፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የመብት ጥሰቶች በኩይለ ቀበሌ አስተዳደር እና በአጋሮቻቸው የተፈጸሙ ናቸው

1. የአርሶ አደር ሚስቶች ላይ ጾታዊ ጥቀትን በመፈጸም ንብረቶቻቸውን መዝረፍ፣


2. ለአካባቢው ነዋሪዎች የሚመጣውን የእርዳታ እህል ለአራት ዙር እያንዳንዱ ግለሰብ 50 ብር እየከፈለ እንዲወስድ
በማስገደድ ለአራት ዙር ከ 833 አባወራ እና እማወራ በመሰብሰብ ለግሉ ጥቅም ማዋል፣
3. በተለያዩ ጊዜ የሚፈጸሙ ህገወጥ ስራዎች ለዞን እና ለወረዳ የሚያመለክቱትን ግለሰቦች ማሰር እና ገንዘብ እንዲከፍሉ
እስገድዶ መፍታት፣
4. ኩይሌ ቀበሌ ነዋሪዎች በቁጥር 833 የሚሆኑ አባወራ እና እማወራ የሚኖሩበት ሲሆን ነዋሪዎቹ ለረጅም ዘመናት በጋራ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 24
ከብቶቻቸውን የሚያሰማሩበት ለሁለት ሰዎች ማለትም በ2012 ዓ.ም አቶ ቦይና ቦቶላ እና ለአቶ ሜኖ ጴቶ የተሸጠ ሲሆን
ለዚህ ህግ-ወጥ ድርጊት ምንም አይነት ህጋዊ ተጠያቂነት የነበረ ባለመሆኑ በድጋሚ 18 ሄክታር የውል መሬት ለ38
የተለያዩ ሰዎች በመሸጥ ለግል ጥቅም እንደዋለ በማስረጃ ጭምር ለማረጋገጥ ተችሏል፣
5. 282,000 ሺህ ብር ለክላስተር ግንባታ ብለው የኩይሌ ቀበሌ ነዋሪዎች ብቻ እንዲያዋጡ ተደርጎ ስራው ሳይሰራ ገንዘቡ
የት እንደገባ አይታወቅም ጉዳዩንም ከወረዳው እስከ ዞን የአካባቢው ነዋሪዎች ያሳወቁ ቢሆንም ከማጣራት ያለፈ ምንም
አልተደረገም፣
6. በኩይሌ ቀበሌ የጎርፍና የናዳ አደጋዎች ሲያጋጥሙ ለሠፈራ ስራ ይውላል በማለት አካውንት በመክፈት ከ833 አባወራ እና
እማወራ ከእያንዳንዳቸው 300ብር እንዲያዋጡ ከተደረገ በኋላ ምንም ስራ ሳይሰራ ቆይቷል ይህንንም ህገወጥ ተግባር
ለማጣራት በሚንቀሳቀሱ ገለሰቦች ላይም ድብደባ እና ህገወጥ እስራት እንዲደርስ ተደርጓል፡፡
ኢሰመጉ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ያናገራቸው የወረዳው የፀጥታ ሃላፊ ጉዳዩን እየተከታተሉት እንደሆነ፣ የመብት ጥሰቶቹን
የፈጸመው ግለሰብ ከሃላፊነታቸው ተነስተው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንደተያዘ አስረደተዋል፡፡ ነገርግን እስካሁን ድረስ
የማህበረሰቡ የግጦሽ መሬት እንዳልተመለሰ እና በዚሁ ጉዳይ ታስረው ያልተፈቱ ሰዎች እንዳሉ አስረድተዋል፡፡
 በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ኩስሜ ማህበረሰብ ላይ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች
ኩሱሜ በደቡብ ክልል የሚገኝ ብሄር ሲሆን ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ በአንዳንድ የደራሼ ብሄረሰብ አባላት በሚፈጠር ትንኮሳ እና
የማንነት እንዲሁም የመዋቅር ጥያቄን መሰረት በማድረግ ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተከሰተ መሆኑን ኢሰመጉ ማጣራት
ችሏል፡፡ በ2011 ዓ.ም በተከሰተው ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ፣ የሞቱ፣ የታሰሩ፣ የተደበደቡ እና የአምልኮ ስፍራ እንኳን
እንዳይኖራቸው እየተደረገ ከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ጥሰት እየደረሰባቸው መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡ በተፈጸመው የመብት
ጥሰት ላይ የደራሼ ልዩ ወረዳ አመራሮች እንዲሁም አንዳንድ የተደራጁ ከደራሼ ማህበረሰብ የተወጣጡ ቡድኖች
እንደተሳተፉበት ኢሰመጉ ከሰበሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡ እስካሁን የኩስሜ ማህበረሰብ በተለያዩ መልካም
አስተዳደር እጦት ውስጥ ይገኛል፡፡
አቤቱታ አቅራቢዎች እንደሚያስረዱት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በተነሳ የማንነት ጥያቄ መሰረት በቀበሌው ሰዎች እየሞቱ፣
እየተፈናቀሉ ድብደባ እና ህገወጥ እስራት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ለኢሰመጉ አስረድተዋል፡፡ ይህንንም ስርዓት የተቃወሙ
እና የጠየቁ ሰዎች ማስፈራሪያ እና እንግልት እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ የተወሰኑ የሃይማኖት
ተቋማት ተዘግተው ይገኛሉ፡፡

ከህግ ውጪ የተፈጸመ ግድያ


ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ አንቀጽ 3 “ እያንዳንዱ ሰው በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነቱ የመጠበቅ
መብት ”እንዳለው ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለችው የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳንም
በአንቀጽ 6 (1) እና 9 (1) ላይ ይህንኑ መብት በማረጋገጥ፣ መንግሥታት በቃልኪዳኑ የተረጋገጡትን መብቶች
በግዛታቸው የማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት ግዴታ እንዳለባቸውም በአንቀጽ 2 (1) እና 2 (2) ይደነግጋል። የአፍሪካ
የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር አንቀጽ 4 “ማንኛውም ግለሰብ በሕይወት የመኖር መብቱና የአካሉ ደህንነት
ሊከበርለትና ሊጠበቅለት እንደሚገባና እነዚህን መብቶቹን በዘፈቀደ ሊነፈግ እንደማይችል ተመላክቷል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 14 “ ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት
የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነጻነት መብት አለው” ሲል ይደነግጋል። በተመሳሳይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ
15 ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት እንዳለውና በሕግ ከተደነገገው ውጪ ሕይወቱን ሊያጣ እንደማይችል
በግልፅ ደንግጓል፡፡ ኢትዮጵያም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 4 መሠረት እነዚህን ዓለም አቀፍ እና
አህጉራዊ የሰብዓዊ መብቶች ሰነዶች የተቀበለች እና የሐገሪቱ ሕግ አካል እንዲሆኑ ያደረገች ሀገር እንደመሆኗ፤ ሰብዓዊ
መብቶችን የማክበር፣ የማስከበር እና የማሟላት ግዴታ ተጥሎባታል። ይሁን እንጂ፣ መንግሥት እነዚህን ሕገ መንግሥታዊ፣
አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ድንጋጌዎች ማስከበር ባለመቻሉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዜጎች ላይ በሕይወት የመኖር መብት
ጥሰት ተፈጽሟል።

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 25
በግጭቱ ምክንያት የተገደሉ የኩስሜ ብሔረሰብ አባላት ስም ዝርዝር

ተ.ቁ የተገደለው ሰው ስም ዕድሜ ጾታ የተገደለበት ቀን የተገደለበት ቦታ

1 አቶ ኩሴ ኩቶ 35 ወ 06/01/2014 ጋቶ ቀበሌ መንደር 1 ምግብ ቤት


ውስጥ

2 ጌይታሬ ደልቦሬ 45 ወ 13/11/2011 ጋቶ ቀበሌ መንደር 1

3 አየለ ሎጮ 60 ወ 19/05/2011 ጋቶ ቀበሌ መንደር 1 ቀጠና 1

4 ጋጩ ከበደ 35 ሴ 20/05/2011 ጋቶ ቀበሌ

5 አቶ አዋራ ዲንቦ 67 ወ 20/05/2011 ጋቶ ተስፋ ጺዮን መካነ ኢየሱስ


ቤ/ክ ጊቢ ውስጥ

6 ጌልዶ ሙሉሜ 50 ወ 20/05/2011 ጋቶ ቀበሌ መንደር 1 ቀጠና 3

7 ወ/ሮ ከቼ ኩሴ 80 ሴ 20/05/2011 ጋቶ ቀበሌ መንደር 1 ቀጠና 4

8 ካቦኖ ገዋዶ 22 ወ 20/05/2011 ጋቶ ቀበሌ

9 አቶ ሚቱ በርሻ 25 ወ 07/03/2013 -

በኩስሜ ብሄረሰብ በተከሰተው የጎሳ ግጭት ህይወታቸውን ያጡ ግለሰቦች ምስል ከዚህ በታች እንደሚከተለው ቀርቧል

 ሟች አቶ አዋራ ዲንቦ የ60 አመት አዛውንት ሲሆኑ በጋቶ ቀበሌ ነዋሪ ነበሩ የኩስሜ ተወላጅ ስለሆኑ ብቻ ማንነትን
ምክንያት በማድረግ በቀን 20/05/2011 ዓ.ም በአቶ ታደሰ ጉይታ ጋቶ ተስፋ ጺዮን መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ ጊቢ ውስጥ
ተገድሏል፡:

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 26
 ሟች አቶ አየለ ሎጮ 60 አመት አዛውንት ሲሆኑ በጋቶ ቀበሌ አርሶ አደር ናቸው የማንነትን እና መዋቅር ላይ ጥያቄ
በማንሳታቸው እስር፣ እንግልት፣ ድብደባ ሲደርስባቸው ቆይቶ በቀን 20/05/2011 በጋቶ ቀበሌ መንደር 1 ቀጠና 3
ተገድለዋል፡፡

 ሟች አቶ ጌልዶ ሙሉሜ የ50 አመት ጎልማሳ ሲሆኑ ማንነትን ምክንያት በማድረግ በወረዳው እና የዞኑ አስተዳደሮች
እንግልት ሲደርስባቸው ቆይቶ በቀን 20/05/2011 በጋቶ ቀበሌ መንደር 1 ቀጠና 3 ተገድለዋል::

 ሟች ወ/ሮ ከቼ ኩሴ የ60 አመት አዛውንት ሲሆኑ በጋቶ ከተማ ነዋሪ ነበሩ የማንነትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ጥር
20/2011 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በተነሳ ግጭት አቶ ታመነ ታደሰ በተባለ ግለሰብ በተተካሰባቸው ጥይት ሞተዋል፡፡

 ሟች አቶ ጌይታሬ ደልቦሬ 45 አመት ጎልማሳ ሲሆን ያገቡና የ7 ልጆች አባት ነበሩ የማንነት ጥያቄ በመጠየቃቸው
ብቻ በቀን 13/11/11ዓ.ም ከምሽቱ 7፡00 ሰዓት ላይ በተለምዶ መንደር 1 ተብሎ በሚጠራው ቦታ በወረዳው
አመራሮች ትዕዛዥ በ 12 ጥይት ጠመቶ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አልፋል ስርአተ ቀብሩም በመካነ እየሱስ ቤተ-
ክርስትያን በቀን 14/11/11ዓ.ም ተፈጽሟል፡፡

 ሟች ወጣት ሚቱ በርሻ በጋቶ ቀበሌ የሚኖር አርሶ አደር ነበር በ07/03/13 ዓ.ም ላይ ነበር ከሃላ ጭንቅላቱን
በጥይት ተመቶ ህይወቱ ያለፈው ለዚህም የሟች ቤተሰቦች የወረዳው አመራሮችን ተጠያቂ ያደርጋሉ ምክንያቱ ደግሞ
በኩሱሜ እና በደራሼ ማህበረሰቦች መካከል በተፈጠረ የጎሳ ግጭት ነው::

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 27
 ሟች አቶ ኩሴ ኩቶ የ35 አማት ጎልምሳ ነበር በ06/01/14ዐ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰአት በተለምዶ መንደር 1 ምግብ ቤት
ውስጥ ተደብድቦ ህይወቱ ያለፈው ሲሆን ለዚህም የዳረገው የማንነት እና ዘርን ምክንያት ተደርጎ የተነሳ ግጭት ነው
ድርጊቱንም በሰደሰፍ እና በእጃቸው ነው እንደፈፀሙበት፡፡

 ሟች ወ/ሮ ጋጩ ከበደ የ35 ዓመት የልጆች እናት ስትሆን የኩስሜ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ ለችግር እና ለመገለል
ከተዳረጉ የብሄረሰቡ ተወላጅ መካከል አንደኛዋ ናት፡፡ በቀን 20/05/2011 ላይ ነበር በቤታቸው አቅራቢያ በክላሽ
ከጀርባቸው ተመተው የተገደሉት፡፡

 ሟች ወጣት ካቦኖ ገዋዶ በደራሼ ጋቶ ቀበሌ ይኖር የነበረ ተማሪ ነበር በቀን 20/05/2011 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00
አካባቢ በማንነት እና በመዋቅር ጥያቄ ምክንያት በማድረግ ግጭት ተነስቶ በጥይት ተመትቶ ህይወቱ ያለፈው ፡፡

በግጭቱ ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰባው የኩስሜ ማህበረሰብ አባላት ስም ዝርዝር


ተ.ቁ የተጎዳው ሰው ስም ፆታ
1. አቶ ለማ ገልገሎ ወ
2. አቶ ኩሴ በየነ ወ
3. አቶ ገናሞ ጌታቸው ወ
4. አቶ ማሙሽ ለኩለማ ወ
5. አቶ ለሃ ሃውዴ ወ
6. አቶ ታመነች ባራንዴ ወ
7. አቶ አጥናፍ አሰፋ ወ
8. አቶ ከልቶ ሉዳይቶ ወ
9. አቶ ኩሴ ነጋሽ ወ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 28
10. አቶ ታመነህ ለሞ ወ
11. አቶ ታፈሰ ሃውዴ ወ
12. አቶ አባይነህ ኦይላዶ ወ
13. አቶ ኩሴ ዳዋታ ወ
14. አቶ ኩታና ኦቴ ወ
15. አቶ አዛ ናሎ ወ
16. አቶ ኮሳሞ ገዛከኝ ወ
17. አቶ ታዬ በርሻ ወ
18. አቶ ታፈሰ ታደሰ ወ
19. አቶ ትንሳኤ ታደሰ ወ
20. አቶ ዮሃንስ ሉዳይቶ ወ
21. አቶ አማቴ አበበ ወ
22. አቶ አርማና ኡቃ ወ
23. አቶ ቁሳሞ ቁዱዳ ወ

እስራት
በግጭቱ ምክንያት ለህገወጥ እስር የተዳረጉ ኩስሜ ማህበረሰብ አባላት ስም ዝርዝር
ተ.ቁ የታሰረው ሰው ስም ዕድሜ የታሰረበት ቀን የታሰረበት ቦታ
1. አቶ ከሰሰ ሊሼ - 28/04/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
2. አቶ ኩታኖ ኩሌ - 28/04/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
3. አቶ ከበደ ኦርካይዶ 70 16/03/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
4. አቶ ገዛኸኝ ሮባዩ 53 12/02/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
5. አቶ ዘመቻ ባንትርካ - 12/02/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
6. አቶ አበበ አርማተ - 12/02/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
7. አቶ ላሆለ ሳኮቴ - 12/02/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
8. አቶ መኖሩ ጎዳና - 12/02/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
9. አቶ ማሙሽ አየለ - 12/02/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
10. አቶ ኮጮቴ ሳጎያ - 12/02/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
11. አቶ ማሙሽ ሲዳሞ - 12/02/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
12. አቶ ኩርሻ ሐውዴ - 12/02/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
13. አቶ ንጉሴ ለማ - 12/02/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
14. ወ/ዊ መልካሙ ኦዳ 34 12/02/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
15. አቶ ካልሳሙ ኩሴ 36 6/05/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
16. አቶ ታምሩ ታሪካሶ 36 6/05/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
17. አቶ በቀለ ቦንጫ 38 6/05/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
18. አቶ አስማሮ አይላይ - 6/05/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
19. አቶ ፋሲካ ሮባዩ 32 6/05/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
20. አቶ ገልገሎ አያኖ 30 8/05/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 29
21. አቶ ታሪኩ ታደሰ 35 8/05/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
22. ወጣት ዘራል ዘውዴ 26 8/05/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
23. መ/ር ኩታኖ ኩሴ 33 19/04/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ
24. አቶ ዘመቻ ሐያቶ 46 19/04/2014 የጉይሌ ፖሊስ ጣቢያ

 በሃላባ ዞን የዌራ ዲጆ የአርሶ አደሮች ከመሬት መፈናቀል

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በሀላባ ዞን የዌራ ዲጆ ወረዳ በአርሶ አደሮች ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት
ጥሰት ይመለከታል፤ የሁልባረግ ስልጤ ብሔረሰብ አባል በመሆናቸው በሀላባ ዞን ውስጥ በመስፈራቸው እና በመኖራቸው
እየደረሰባቸው ያለው ተፅዕኖ ከባድ መሆኑን የአከባቢው ነዋሪዎች ያስረዳሉ፡፡ ከ1990ዓ.ም ጀምረው በዌራዲጆ ወረዳ በንዳ
ጨልቅስ ቀበሌ የሚኖሩ ሲሆን ቀደም ሲል ለኢንቨስትመንት የተሰጠ ቦታ ነው በሚል እያስፈራሯቸው መሆኑን ለግብርና
ሚኒስቴር፣ ለክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ፣ ለተለያዩ የመንግስት አካላት ሲያመለክቱ የቆዩ ሲሆን ግንቦት 2013ዓ.ም ወደ
መሬት ባንክ ገብቷል በሚል ቤታቸው ካለበት ውጪ የሚያርሱትን መሬት ለሌሎች ሠዎች መሰጠቱን ቦታው ድረስ በመሄድ
ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢው ሰፍረው የይዞታነት ክፍያ እየፈፀሙ ይኖሩ የነበረ መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ይናገራሉ፡፡
ሆኖም ግን የመሬት ይዞታ ደብተር አሰጣጥ ባለው ብልሹ አሰራር ምክንያት ሳይሰጣቸው መቆየቱን ተናግረዋል ይህም የሆነው
የአካባቢው አመራሮች ነዋሪዎችን በማስፈራራት የሚያፈሩትን ምርት ለመካፈል እና ለመቀራመት ያመች ዘንድ መሆኑን
ያመለክታሉ፡፡ ኢሰመጉ ቦታው ድረስ በመሄድ እንደተገነዘበው በቦታው ብዙ አመት የቆዩ እና የተዋለዱ ቢሆኑም ግን አሁንም
እንደ ስደተኛ እንደሚታዩ እና እንግልት ላይ መሆናቸውን ታዝቧል፡፡

በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ለኢንቨስትመንት ተግባር የሚውል የገጠር መሬት ደንብ በሚመለከት በአዋጅ ቁጥር 2/1990 ላይ
በክፍል 3 አንቀጽ 12 እንደሚደነግገው ‹ለህዝብ ጥቅም ሲባል አርሶ አደር ይዞታውን እንዲለቅ ሲደረግ በቅድሚያ ተመጣጣ
የካሳ ክፍያ እንዲከፈላቸው ያስገድዳል፡፡ ይህ መመሪያ በግልጽ ተደንግጎ እያለ የዞኑ፣ የወረዳው እንዲሁም የቀበሌው አመራሮች
በመመሳጠር የግል ጥቅማቸውን በማስቀደም ሲበድሏቸው መኖሩን ያስረደሉ፡፡

በመንግስት በኩል ከዞኑ የመሬት አስተዳደር ኃላፊ በተገኘ መረጃ መሰረት ከነዋሪው የተሰበሰበ 65 ሄክታር መሬት ወደ መሬት
ባንክ ለችግኝ መትከያ በሚል ምክንያት እንዲገባ እንደተደረገ አስረድተው ለተነሱትም ተገቢውን ካሳ እንደተሰጠ ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ይህ ኢሰመጉ በአካል ቦታው ድረስ ሔዶ ከተመለከተው እውነታ ጋር የተቃረነ ሆኖ አግኝቶታል፡፡

ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በበንዶ ጮሎቅሳ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮች በኢንቨስትመንት ምክንያት ከመሬታቸው የተፈናቀሉ

1. አቶ ከማል አልይ
2. አቶ ረሺድ ሸኩራ
3. አቶ ሪበቶ ሃሚድ
4. አቶ ሠይድ ሃሚድ
5. አቶ ሀሰን አኔቦ
6. ወ/ሮ አሚና ጀማል
7. አቶ ካይረዲን ላለም
8. አቶ አብራር እሳ
9. አቶ አፍራዬ መሃመድ

በሌላ በኩል የሎሂ አክስዮን ማህበር ባለሀብት የሆኑት አቶ ሂርጳ ፈይሣ በህጋዊ መልኩ በ2005ዓ.ም ለኢንቨስትመንት

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 30
ተከራይተው እያለ ከተከራዩት መሬት ግማሹን ብቻ በመስጠት ቀሪውን መሬት በመከልከል ሲንገላቱ ቆይተዋል፡፡ አሁን ደግሞ
መሬታቸውን ወደ መሬት ባንክ ጨምረውባቸዋል ለዚህም ደግሞ የመንግስት አመራሮችን ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡

2. ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሼ ዞን ሶጌ እና ያሶ ወረዳ የተፈናቀሉ ተፈናቃዮች


በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በሚነሱ ግጭቶች ምክንያት በርካታ ዜጎች ሲፈናቀሉ ቆይተዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ
ወዲህ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሶጌ (ሚዝንግ) ወረዳ እና ያሶ (ዜይ) ወረዳ በ2011 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ
በጉሙዝ እና በኦሮሞ ብሄረሰብ መካከል በተነሳ ግጭት ምክንያት በሁለቱ ወረዳዎች በሚገኙ በድምር 23 ቀበሌዎች (ያሶ 12፣
ሶጌ 11) ውስጥ የጉሙዝ ብሄር ያልሆነ ከክልሉ ይልቀቅ በሚል በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች በዋናነት
የኦሮሚያ እና የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ወደ አጎራባች የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች ተሰደው የነበረ ሲሆን ለ8 ወር ያህል
በኦሮሚያ ክልል ከቆዩ በኋላ መንግስት ቸግሮች ተፈተዋል በሚል ወደመጡበት ወደ ቤነሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲመለሱ
ያደረገ መሆኑን ነገር ግን ተፈናቃዮቹ በሚመለሱበት ሰዓት ንብረቶቻቸው መውደሙን እና መዘረፉን ከዚህ የተረፈውን ቤት
እና ንብረት ደግሞ አንዳንድ የጉሙዝ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ሰዎች ሲጠቀሙበት እንደነበር እና ይህንን ተከትሎ ተፈናቃዮቹ
በወረዳ አስተዳደር ጊቢ ውስጥ ሜዳ ላይ ተጠልለው እንደነበር ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

በዚህ ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ማለፉን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ንብረት መውደሙን፣ ዝርፊያዎች
መፈጸማቸውን እና ይህንንም ድርጊት ፈጽመው የነበሩ አካላት ላይ ምንም አይነት እርምጃ ባለመወሰዱ እና በተደጋጋሚ ጉዳት
በደረሰባው ሰዎች ላይ የደረሰባቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ምንም አይነት ጥያቄ ማቅረብ አትችሉም እንዲሁም
ከውድመት የተረፉ ቤቶች እና ንብረቶቻችሁን ተነጠቅን ብላችሁ እንዳትጠይቁ የሚል ማስፈራሪያ በተደጋጋሚ ይደርስባቸው
እንደነበር እና ምንም አይነት ሰብዓዊ ድጋፍ ይደርሳቸወ ስላልነበረ ዳግም ወደ ኦሮሚያ ክልል መፈናቀላቸውን፣ በተጨማሪም
ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ለኦሮሚያ ክልል እነዚህ ተፈናቃዮች አቤቱታቸውን ያቀረቡ ቢሆንም ሁለቱም ክልሎች ምንም
አይነት ምላሽ እንዳልሰጧቸው ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በ2013 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀስ ታጣቂ የሆነ የመንግስት ተቃዋሚ ቡድን
በከፈተው ጥቃት የመንግስት ሰራተኞችን አና ደጋፊዎችን ጨምሮ በሁለቱም ወረዳዎች የሚኖሩ የሌላ ብሔረሰብ ተወላጆች
እንዲፈናቀሉ ሆኗል፡፡ በዚህም ጥቃት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ተወላጆች፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጆች፣ የአማራ ብሄረሰብ
ተወላጆች እና ሌሎችም መፈናቀላቸወን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

በ2011 ዓ.ም እና በ2013 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሶጌ (ሚዝንግ) ወረዳ እና ያሶ (ዜይ) ወረዳ ለበርካታ
ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ንብረት ውድመት፣ ዝርፊያ፣ መፈናቀል እና ሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ምክንያት የሆነው
ግጭት በትጥቅ የታገዘ መሆኑ ችግሩን ይብልጥ አስከፊ እንዳደረገው ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

ከምስራቅ ወለጋ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በተገኘ መረጃ መሰረት በአጠቃላይ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ
ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 28,071 ሰዎች መሆናቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው
መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

3. በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ


የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል አዋሳኝ በሆነው ወረጃርሶ ወረዳ ግጭቶች በተደጋጋሚ ሲከሰቱ ቆይተዋል፡፡ ለዚህም ችግር ዋነኛ
ምክንያት በአካባቢው የሚኖሩ አማርኛ እና ኦሮሚኛ ተናጋሪዎች በሚፈጥሩት የቦታ ይገባኛል ጥያቄ መሆኑን ኢሰመጉ
ለመረዳት ችሏል፡፡ በተጨማሪም በተደጋጋሚ ተጎጂዎች እንዳስረዱት “አማርኛ ተናጋሪዎች እዚህ መኖር አትችሉም ለቃችሁ
ሂዱ” ይባሉ እንደነበር፣ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነ ለመንግስት አካላት ሲያመለክቱ እንደነበር ነገር ግን
በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት “እኛ ከአቅማችን በላይ ነው፣ እናንተ ለምን ለቃችሁ አትሄዱም“ ይባላሉ እንደነበረ፤
ነዋሪዎቹ ደግሞ ተወልደው ያደጉበት አግብተው የወለዱበት ቦታን መልቀቅ እንደማይችሉ የገለጹ ሲሆን ጥቃቱ እዚህ ደረጃ
ይደርሳል ብለው ባይገምቱም እየኖሩ የነበረው በስጋት ውስጥ ሆነው እንደነበር ኢሰመጉ በምርመራ ስራ ከተጎጂዎች
ባሰባሰበው መረጃ ለመረዳት ችሏል፡፡

አካባቢው በከፊል ሸኔ በሚባል ታጣቂ ቡድን ቁጥጥር ሥር ስለሆነ ህብረተሰቡ ከመኖሪያውና ከሥራ ተፈናቅሎ በተለያየ ቦታ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 31
ተጠልለው እንደሚገኙ፣ የመብት ጥሰት እየተፈጸመበት ያለበት ሥፍራ ወረጃርሶ ወረዳ ውስጥ ሲሆን ጥቃቱ በተፈጸመበት
ወቅት በወረዳው ውስጥ 32 ቀበሌዎች እንደሚገኙ፣ ከእነዚህ ውስጥ ከሰባቱ በስተቀር 25ቱን ሸኔ እያስተዳደረው እንደነበር
ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት

በዚህም ምክንያት የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የተፈጸሙ ሲሆን ከነዚህም መካከል ግድያ እና የአካል ጉዳት ይገኙበታል፡
፡ በተጨማሪም የአስክሬን መቃጠል፣ የንብረት ውድመት እና መፈናቀል መፈጸማቸውን ኢሰመጉ ለመረዳት ችሏል፡፡

ከህግ ውጪ የተፈጸመ ግድያ


ከዚህ በታች የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል አዋሳኝ በሆነችው ወረጃርሶ በሸኔ የደረሰ የነፍስ ማጥፋት ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ
መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ከወረጃርሶ ወረዳ አስተዳደር በደብዳቤ ቁጥር BAWJ.2/1029 በቀን 16/7/2014 ዓ.ም
በአድራሻችን ተጽፎ በተላከ መረጃ መሰረት እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡
ተ.ቁ የተገደለውሰውስም ዕድሜ የተገደለበት ቀን የተገደለበት ቦታ

1 አቶ ጌታ አግዴ ወርቅነህ 52 26/03/2014 ፋጄኤጀርሳ

2 አቶ ጓዴ መንበሩ ዓለሙ 42 04/6/2014 ፋጂ ኤጀርሳ

3 አቶ አየነው አሹቲ ቢልጣ 50 02/6/2014 ሀሮቀላ

4 አቶ መከተ አሹቲ ቢልጣ 34 02/6/2014 ሀሮቀላ

5 አቶ አበጀ ሰመረ 55 07/6/2014 ፋጂ ኤጀርሳ

6 አቶጋሹ ሞላ ተገኝ 55 07/6/2014 ፋጂ ኤጀርሳ

7 አቶ ደምሰው ጋሻው ሞላ 25 07/6/2014 ፋጂ ኤጀርሳ

8 አቶ ቃንቄ ባምላኩ ሙላቱ 50 02/6/2014 ሀሮሚካኤል

9 አቶ ፍቅሬ ፈረደ ታዳጊ 45 02/6/2014 ሀሮቆላ

10 አቶ ደምሴ አባቡ ፀጋዬ 32 07/6/2014 ፋጂ ኤጀርሳ

11 አቶ እንዳሻው ወጌሻ ከቤ 42 07/6/2014 ፋጂ ኤጀርሳ

12 አቶ አሰፋ ታደለ ዳምጤ 65 07/6/2014 ፋጂ ኤጀርሳ

13 ታዳጊ ዳምጤ ጤናው ተስፋዬ 14 07/6/2014 ፋጂ ኤጀርሳ

14 አቶ አባቡ ዋለ መንገሻ 65 07/6/2014 ፋጂ ኤጀርሳ

15 አቶ ኡስማን አህመድ - - ቢጽኖ ደራ

16 አቶ ደሜ ጎፋ - - ዳዬ ቱቲ

17 አቶ ደምስ አሊ - - ጃርሚ ጎባ

18 አቶ ፈዬ ንጉሴ - 07/4/2014 ጀምጀምመላ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 32
19 አቶ ጎንፋ ደበላ - - ኮርጎጎሉቱ

20 አቶ ታዬ ዳዲ - 04/1/2013 ለንቱወላርጊ

21 አቶ አቡ ታምሩ - - ቢጽኖደራ

22 አቶጋላሳ አዳሬ - - ለንቱወላርጊ

23 አቶ ተፈሪ መኮንን - 07/1/2013 ጀምጀምመላ

24 አቶ ጎበዜ ተጫኔ - 09/1/2014 ቢጽኖዴራ

25 አቶ ታምሩ ሹሙ - 13/3/2014 ቱሉ ሚሊኪ

26 አቶ ቦጃ ንጉሱ - - ሆሴ

27 አቶ አመኑ ፈዬ - - ቦቢ ሊበን

28 አቶ መላታ ሰምበታ - - ቦቢ ሊበን

29 አቶ አዱኛ ረጋሳ - - ቀጨሜ

30 አቶ ሙሉ በላቸው - - አዋሬጎልጃ

31 አቶ ሙሉ ጋሻው - - አዋሬጎልጄ

32 አቶ አበባው ጥላሁን - - አዋሬጎልጄ

33 አቶ ፍሰሃ እሼትዬ - - አዋሬጎልጄ

34 አቶ ሰንበታ ጎንፋ - - አዋሬጎልጄ

ከላይ የተቀመጠው ግድያ ስም እና አጠቃላይ ሁኔታ ምስል በከፊል

1 ሟች አቶ ጌታ አግዴ ወርቅነህ 2 ሟች አቶ ጓዴ መንበሩ ዓለሙ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 33
3 ሟች አቶ አየነው አሹቲ ቢልጣ 4 ሟች አቶ መከተ አሹቲ ቢልጣ

5 ሟች አቶ አበጀ ሰመረ 6 ሟች አቶ ጋሹ ሞላ ተገኝ

6 ሟች አቶ ቃንቄ ባምላኩ ሙላቱ 7 ሟች አቶ ደምሰው ጋሻው ሞላ

8 ሟች አቶ ደምሴ አባቡ ፀጋዬ 9 ሟች አቶ ፍቅሬ ፈረደ ታዳጊ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 34
10 ሟች አቶ እንዳሻው ወጌሻ ከቤ 11 ሟች ታዳጊ ዳምጤ ጤናው ተስፋዬ

 ሟች አቶ ስብሃት ፅጌ መንግስት የ40 አመት ጎልማሳ ሲሆን በኢፍራታ በኬ ነዋሪ ነበር፡፡ በስራውም ሆነ በኑሮው
ከማንኛውም ፖለቲካ ገለልተኛ ነበር፡፡ በየካቲት 12/2014 ከምሽቱ ሶስት ሠዓት ላይ ነበር በመኖሪያ ቤቱ
በታጣቂዎች ተተኩሶበት ህይወቱ ያለፈው፡፡ ድርጊቱን ያደረሰው ደግሞ የሸኔ ታጣቂ ቡድን መሆኑን ኢሰመጉ
ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

 ሟች ቀሲስ መንግስቱ ሀይለማርያም በኢፍራታ በኬ ነዋሪነታቸውን ያደረጉ የ80 አመት አዛውንት መነኩሴ ሲሆኑ
በቀን 12/06/2014 አምስት የሚሆኑ የሸኔ ታጣቂዎች በር ሰብረው በመግባት ከምሽቱ 3፡00 ላይ በጥይት
ተመተው ህይወታቸው አልፋል፡፡ ከዛም እቤት ውስጥ የነበረውን ንብረት ዘርፈው የሰወሩት፡፡

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 35
 ሟች ቀሲስ መርጌታ ሰለሞን መንግስቴ በኢፍራታ ጀርማ የገጠር ከተማ ነዋሪነታቸውን ያደረጉ የ48 አመት ጎልማሳ
ናቸው ምሽት ላይ ከቤታቸው ካስወጧቸው በኃላ ምክንያቱን ሳያውቁት በጥይት በተደጋጋሚ ተመተው ህይወታቸው
አልፋል፡፡

የአካል ጉዳት
ተ.ቁ የተጎጂስም የተፈፀመበት ቦታ እና ቀን የጉዳቱአይነት

1 አቶ አየው ደረሰ 02/6/2014 /ሸንኮራሸሸንግ በጥይት ማቁሰል

2 አቶ ታደሰ ቦዬ ቢጽኖዴራ በጥይት ማቁሰል

3 አቶ አበበ ለማ ሊበንቀጨማ በጥይት ማቁሰል

4 አቶገለታጋሪ ቢቶሚሊኪ በጥይት ማቁሰል

5 አቶ ዳኜ ንጋሱ 22/3/214 /መልዩጪማ በጥይት ማቁሰል

6 አቶ ጌታቸው አዱኛ ቦቺሳስላሴ በጥይት ማቁሰል

7 አቶ ገረሀኝ ገበየሁ ቦቺሳስላሴ በጥይት ማቁሰል

8 አቶ አበበ ለማ ቀጨማ በጥይት ማቁሰል

9 አቶ ግርማ ኦቢ ቀጨማ በጥይት ማቁሰል

10 አቶ ጆቴ ቱሉ ቀጨማ በጥይት ማቁሰል

11 አቶ ለማ ከበደ ጀምጀምመላ በጥይት ማቁሰል

12 አቶ መኮንን ያዘው 02/4/2013 በጥይት ማቁሰል

13 አቶ አዳነ ፈዬ 03/4/2013 በጥይት ማቁሰል

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 36
ህገወጥ እስራት
ተ.ቁ. የታሰረው ሰው ስም ዕድሜ የተፈፀመበት ቀን የታሰረበት ቦታ

1 አቶ ገብረ ደለለኝ አሹቴ 26 02/6/2014 ፋጂኤጀርሳ

2 አቶ ፈለቀ ተዋበ ከፈለ 41 02/6/2014 ፋጂኤጀሬ

3 አቶ እንደሻው ምትኩ ዳምጤ 40 02/6/2014 ፋጂኤጀሬ

4 አቶ አቢ እንጃ በለው - 02/6/2014 ፋጂኤጀርሳ

5 አቶ አዳሙ ዘውዱ አባኪያ - 02/6/2014 ፋጂኤጀርሳ

6 አቶ ኃይሉ ተስፋ አማከለው 45 02/6/2014 ፋጂኤጀርሳ

7 ሰውነት ጤናው 48 02/6/2014 ፋጂኤጀርሳ

8 ደረሰ ምህረት ተመስገን - 02/6/2014 ፋጂኤጀርሳ

9 ታደሰ አበበ ቢተው 21 02/6/2014 ፋጂኤጀርሳ

10 በልዩ ዋለው መንገሻ 53 02/6/204 ፋጂኤጀርሳ

11 አሸብር መኮንን አበራ 24 02/6/2014 ፋጂኤጀርሳ

12 ደረሰ ምህረት ተመስገን 40 02/6/2014 ፋጂኤጀርሳ

የንብረት ውድመት
ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ከወረጃርሶ ወረዳ አስተዳደር በደብዳቤ ቁጥር BAWJ.2/1029 በቀን
16/7/2014 ዓ.ም በአድራሻችን ተጽፎ በተላከ መረጃ መሰረት በቃጠሎና በዝርፊያ የወደሙ ቤቶች 928 አባወራ እና 102
እማወራ ቤቶች በድምሩ 1030 ቤቶች ናቸው፡፡ ቤታቸው የተቃጠለባቸው ቤተሰብ ብዛት ወንድ 2498 ሴት 2617 በድምሩ
5115 ናቸው፡፡ ቤት የተቃጠለባቸው አባወራ፣እማወራ እና ቤተሰብ ብዛት በፆታ ሲገለጽ ወንድ 3345 ሴት 2719 ድምር
6064 ናቸው፡፡
ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ አባወራዎች በቁጥር 3508 እማወራ 484 ሲሆኑ አንድ ላይ ሲደመር 3992 የቤተሰብ ኃላፊዎች
የተፈናቀሉ ሲሆን የቤተሰባቸው ብዛትም ወንድ 12171 ሴት 13531 በጠቅላላ 25702 ቤተሰብ ተፈናቅሏል፡፡ በአጠቃላይ
የተፈናቀለው የቤተሰብ ኃላፊና ቤተሰብ ብዛት በፆታና በድምር ሲቀመጥ ወንድ 15679 ሴት 14015 ድምር 29694 ሰውደ
ተፈናቅሏል፡፡

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 37
ከተፈጸመው የንብረት ውድመት መካከል በምስል ያስቀረናቸው የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 38
4. በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ሸዋ ዞን በፈንታሌ ወረዳ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሸዋ ዞን በፈንታሌ ወረዳ ከመተሃራ የስኳር ፋብሪካ ከመኖሩ ጋር ተያይዞ
ከግማሽ ምዕተ-አመት በላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በርካታ ዜጎች ወደዚያ በመፍለስ በተለያዩ የቀን ስራዎች ላይ
ተሰማርተው ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ ዜጎች ምንም እንኳን በዚያ ስፍራ ለዘመናት የኖሩና ከብዙ ብሔር ብሔረሰብ ጋር
የተጋቡና የተዋለዱ ቢሆኑም የ1983ዓ.ም የመንግስት ለውጥን ተከትሎ በሰላምና በፍቅር ይኖሩ የነበሩት ዜጎች እርስ በእርስ
በጥርጣሬና በፍርሃት መተያየት ጀመሩ፤ ይህ ሁኔታ እንዳይረግብ በወቅቱ የነበረው የመንግስት አመራር በተለይም የወረዳው
አመራር ለችግሩ ትልቅ ሚና ነበረው፡፡ ይህ ሁኔታ እየተባባሰ መጥቶ ከ2009ዓ.ም ጀምሮ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ግድያዎች
ሲፈጸሙ ቆይተዋል ከዚህም በላይ ይህ ችግር እስካሁንም ጊዜና ሁኔታዎችን እየጠበቀ ለዜጎች ህይወት መጥፋት ምክንያት
ሆኗል፡፡ ወንጀለኞች ለፍርድ ሲቀርቡና ሲጠየቁ አይታይም፤ የወረዳው አስተዳደር ለሚከሰቱ ችግሮች ዜጎችን ከአደጋ
የመከላከል እንቅስቃሴ ሲያደርግ አይስተዋልም፡፡ ከዚህ ሁኔታ የምንረዳው አመራሩ ለችግሩ እልባት ለመስጠት ሙሉ ፈቃደኛ
እንዳልሆነ ነው፡፡ ችግሩ ከላይ እንደተጠቀሰው ቆየት ያለ ቢሆንም ከጥር ወር 2010ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን እስከ መጋቢት
ወር2014 ዓ.ም ድረስ ያለውን ይህ መግልጫ አካቷል፡፡

ከህግ ውጪ የተፈጸመ ግድያ


ተ.ቁ የተገደለው ሰው ስም ዕድሜ የተገደለበት ቀን የተገደለበት ቦታ

1 ታምሩ ወንድፍራው 30 8/7/2014 ዓ.ም አልጌ(መተሐራ ገጠር)

2 ዮሴፍ አለሙ አበራ 45 10/01/2009 ዓ.ም አምስተኛ ኮሬ

3 አለሙ አበራ አየለ 78 10/01/2009 ዓ.ም አልጌ(መተሐራ ገጠር)

4 ሀብታሙ ይፍሩ ሂርጳ 16 08/07/2014 ዓ.ም አልጌ(መተሐራ ገጠር)

5 ቢንያም አለሙ ኤርገኖ 23 08/07/2014 ዓ.ም አልጌ(መተሐራ ገጠር)

6 ጌታሁን ለሳ 70 24/03/2011 ዓ.ም አልጌ(መተሐራ ገጠር)

7 ታደለ ኤልያስ አብዮ 31 8/7/2014 ዓ.ም አልጌ(መተሐራ ገጠር)

8 ተስፋጽዮን ዳንኤል አላሮ 32 08/07/2014 ዓ.ም አልጌ(መተሐራ ገጠር)

9 ደባልቄ እሼቱ ሙሐመድ 41 08/7/2014 ዓ.ም አልጌ(መተሐራ ገጠር)

10 ዘርዬ ደምሴ አበበ 27 08/7/2014 ዓ.ም አልጌ(መተሐራ ገጠር)

11 ልዑልሰገድ መለሰ ፍሬው 18 08/07/2014 ዓ.ም አልጌ(መተሐራ ገጠር)

12 ጌትነት ታምራት 23 08/07/2014 ዓ.ም አልጌ(መተሐራ ገጠር)

በምስራቅ ሸዋ ፈንታሌ ወረዳ አልጌ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በመጋቢት 8/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 አልጌ የወጣቶች የመዝናኛ
ማዕከት ማንነታቸው በማይታወቁ አካላት መሣሪያ ይዞ በመግባት ተኩስ በመክፈት ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በጉዳቱም አስር ሰዎች
በጅምላ ሲገደሉ ስምንት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ማጣራት እንደተቻለውም ለዚህም ምክንያቱ ማንነት እና
ብሄር ሲሆን ጥያቄያቸውም መሬታችንን ለቃቹ ውጡ የሚል ነው፡፡ በዚህ ቀን ከዚህ በታች ምስላቸው የተዘረዘረው ወጣቶች

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 39
ዘጠኙ በአንድ ላይ በኪዳነምህረት ቤተ-ክርስትያን ስርአተ-ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

1 ሟች ጌትነት ታምራት 2ሟች ተስፋጽዮን ዳንኤል አላሮ

3 ሟች ደባልቄ እሼቱ ሙሐመድ 4 ሟች ዘርዬ ደምሴ አበበ

5 ሟች ታምሩ ወንድፍራው 6 ሟች ታደለ ኤልያስ አብዮ

6 ሟች ቢንያም አለሙ ኤርገኖ 7 ሟች ሀብታሙ ይፍሩ ሂርጳ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 40
8 ሟች ልዑልሰገድ መለሰ ፍሬው 9 ሟች ዮሴፍ አለሙ አበራ

8 ሟች አለሙ አበራ አየለ 10 ሟች ጌታሁን ለሳ


 በሌላ በኩል በፈንታሌ ወረዳ አልጌ ቀበሌ እና በቀሩት 17 ቀበሌዎች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ማንነትን መሰረት ያደረገ
ጥቃት መታየት ጀምሯል ለዚህም ተበዳዮች ምክንያት የሚያደርጉት የኢቱና የከረዮ ማህበረሰብ “አማራ ነፍጠኛ እና
መጤ” በማለት መሬት ለማስለቀቅ ሲሞክሩ እንደኖሩ እና ከዚህም በኃል ጥር 1፣ የካቲት 8፣ እና ህዳር 24 2010
ዓ.ም በተፈፀሙ ጥቃቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዳጋጠሙ ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመራት ችሏል፡

 አቶ ጌታሁን ለማ በተሳሳተ መረጃ የኢቱና የከረዮ ማህበረሰብ አባላት የኛን ተወላጅ አቶ አለማየው ታደሰን ገለሃል
በማለት ቤታቸው ድረስ በመግበት በአሰቃቂ ሁኔታ ገለዋቸዋል፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ የወረዳው ፖሊስ ሃላፊ በቦታው
እንደነበሩ ለኢሰመጉ አቤቱታቸውን ያቀረቡ ሰዎች ገልጸዋል፡፡

የአካል ጉዳት
ተ.ቁ የቆሰለው/የተጎጂ ስም የተፈፀመበት ቀን የጉዳቱ አይነት

1 በረከት ካሳ 08/07/2014ዓ.ም የአካል ጉዳት

2 ልዩነህ ካሳ 08/07/2014ዓ.ም የአካል ጉዳት

3 አያለው ታደሰ 08/07/2014ዓ.ም የአካል ጉዳት

4 ሀብታሙ አያለው 08/07/2014ዓ.ም የአካል ጉዳት

5 እርቁ አበበ 08/07/2014ዓ.ም የአካል ጉዳት

6 ቢንያም አየለ 08/07/2014ዓ.ም የአካል ጉዳት

7 ስንታየሁ ሽጉጤ 08/07/2014ዓ.ም የአካል ጉዳት

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 41
የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች ውስጥ የሚከተሉት ለማሳያነት በምስል ቀርበዋል፡፡
ማስታወሻ:- ከዚህ በታች የቀረቡት ፎቶዎች ጥቃቱን ተከትሎ የተፈጸሙትን የአካል ጉዳት ለማሳየት ጥቂት ተመርጠው
ሲሆን፤ ለእይታ የሚያሰቅቁ በመሆናቸው ፈዘዝ እንዲሉ ተደርገዋል። ይህ ቢሆንም ምስሎቹ ለሚፈጥሩት ስሜት
አንባቢው አስቀድሞ በስነ -ልቦና ዝግጁ እንዲሆን ይመከራል።

ምስል፡ ልዩነህ ካሳ አልካሞ ምስል፡ በረከት ካሳ አልካሞ ምስል፡ በረከት ካሳ አልካሞ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ወደ አማራ ክልል ምንጃር ሸንኮራ/አረርቲ
የተፈናቀሉ ሰዎች ስም ዝርዝር

ተ.ቁ. የተፈናቀለው ሰው ስም የተፈናቀለበትቦታ/ የተፈናቀሉበት ቀን.ዓ.ም የሰፈሩበት/ያረፉበት ቦታ


ከየት?

1 እቴነሽ ጌታሁን ከአልጌ/መተሃራ 2010 ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

2 ኡ መር ሲራጅ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

3 ንጉሴ ሳህሌ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

4 ላቀው ደርቤ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

5 ዘሪሁን ስንዴ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

6 የኔነው አወቀ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

7 ባለው ሽመልስ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

8 መስፍን ገላን ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

9 ይፍቱስራ ገላን ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

10 ተካ አህመድ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 42
11 ዑመር ከተማ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

12 ፍቅርሰው አወቀ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

13 እታገኝ አባይነህ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

14 ደረጀ ጌታሁ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

15 ዋለልኝ ካሳ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

16 አሸብር አበራ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

17 ሰለሞን ንጉሴ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

18 እንዳለማው ወንድፍራው ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

19 አህመድ መሐመድ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

20 ካሊድ ዑመር ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

21 አለሙ ሲሳይ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

22 ወ/ሮ ወርቅዬ አለሙ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

23 መንገሻ ማሞ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

24 ገረመው አወቀ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

25 ስንታየሁ ላቀው ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

26 አየለ አለሙ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

27 ውባለች አለሙ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

28 ወ/ሮ ሐዋ ኢሳዬ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

29 ኤልያስ አልዬ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

30 ሙሳ አወል ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

31 አስማማው ፋንቶ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

32 ወ/ሮ አዲስ ሮባ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

33 ወ/ሮ ብርቄ ዳዲ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

34 ደመቀች ኪዳኔ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

35 ደምሴ ጌታሁን ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

36 ወንድማገኝ ሁኔ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 43
37 ወ/ሮ አዳነች ጌታሁን ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

38 ፍሬሕይወት ጌታሁን ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

39 አዳነች ጌታሁን ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

40 ፍሬሕይወት ጌታሁን ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

41 ዮሐንስ ዳናን ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

42 ወ/ሮ አበቡ መሀመድ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

43 ሩቂያ ያሲን ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

44 አቶ ጊዜው አወቀ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

45 ዮሐንስ ጭንቅሶ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

46 አተጎ ዝይን መርሻ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

47 አቶ ሙህዬ አደም ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

48 አቶ ገዬ ጌታቸው ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

49 አቶ ኢጌ ሀሰን ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

50 ወ/ሮ ሐዋ አህመድ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

51 ወ/ሮ ጃውርያ አበበ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

52 ነጋሽ ሲራጅ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

53 አሰፋ ውባለ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

54 አሰፋ ኃይሉ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

55 ተስፋዬ አየለ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

56 አበበ በዜ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

57 አቶ እንድሪያ ጎበና ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

58 ወንድማገኝ ጌታሁን ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

59 አቶ ደስታው በላይ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

60 አቶ ደስታ መሀመድ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

61 ካሳዬ ሙሴ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

62 ጌታመሳይ ደሴ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 44
63 አቶ አበባው መንግስቴ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

64 ፈጠነ አየለ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

65 ጌታቸው ባሳ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

66 አቶ ባስወይ እንችፍ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

67 ወ/ሮ ሬሐን አበበ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

68 ወ/ሮ ማብራት በቀለ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

69 ስማቸው መንግስቴ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

70 ጎበዜ ንጉሱ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

71 አቶ ባምሳሉ አያለው ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

72 ደመቀ ፈንታ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

73 አቶ አቡ ምትኩ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

74 አቶ ደሳል አንዳርጌ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

75 አቶ መሌ እራያው ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

76 አባይነህ ኃ/ማርያም ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

77 አቶ ዉበት አዲስ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

78 ደምሰው አቡበከር ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

79 አያለው ፀጋዬ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

80 ንጉሴ ኃይሉ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

81 ተካ ማሴቦ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

82 ደሳለኝ ማዳሙ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

83 ወ/ሮ አልማዝ ጫሞ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

84 ፍሬው ገለታው ታፈሰ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

85 አቶ ፍቆ ሁሴን ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

86 መሀመድ እንድሪው ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

87 ወ/ሮ ምንታምር ስንሻው ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

88 ተሾመ ፍስሐ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 45
89 አቶ አብነው ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

90 ለማ ሀሰን ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

91 አቶ ሸጋው ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

92 አቶ ንጉስ ለማ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

93 አቶ ሐይማኖት መበሩ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

94 አቶ ሙሉ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

95 መንበረ ሳህለማርያም ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

96 ወ/ሮ አወደች አስታጥቄ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

97 ፍቅሬ ደሳለኝ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

98 ኤፍሬም ብርሃኑ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

99 ወ/ሮ ሙላት ጥላሁን ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

100 ወ/ሮ ፈጀረች አደም ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

101 አቶ እንየው አስማረ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

102 ከበደ አያንቶ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

103 ወ/ሮ ሐዋ ይመር ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

104 ወ/ሮ ዘነቡ ከአልጌ/መተሃራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

105 ወ/ሮ እጅግአየሁ በቀለ ከአልጌ/መተሐራ/ 2010ዓ.ም-2014ዓ.ም ምንጃር/አረርቲ

5. በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቆቦ ከተማ


አቶ ሚካኤል ሃ/ስላሴ የቆቦ ከተማ ነዋሪ የሆነ፣ በንግድ ስራ የሚተዳደር፣ የ44 ዓመት ጎልማሳ ነው፡፡ አቶ ሚካኤል በሰሜኑ
ኢትዮጵያ ክፍል የነበረው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ለህክምና ወደ አዲስ አበባ በመጣበት ጊዜ ነበር ለብዙ አመታት ያፈራውን
ንብረት የተነጠቀው፡፡ ይህንንም ያደረጉት ቤቱን ተከራይተው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ የተደራጁ
ወጣቶች ጋር በመተባበር ሲሆን፣ ኢሰመጉ ይህንን ጉዳይ አጣርቶ እውነትም የተባለው የመብት ጥሰት መኖሩን በማረጋገጥ
ለሚመለከትው የመንግስት አካል የማስተካከያ እርምጃ እንዲደረግ አሳውቆ ነበር፡፡ ከተማ አስተዳደሩም ችግሩን አምኖ
ማስተካከያ አደርጋለው ከሚል በቃል ከመናገር ውጭ ምንም ሳያደርግ ቆይቷል፡፡ ይህም በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 40
የተቀመጠውን ንብረት የማፍራት እና የመጠቀም መብት የተቃረነ ስለሆነ የሚመለከተው አካል የማስተካከያ እርምጃ
እንዲወስድ ኢሰመጉ ያሳስባል፡፡

6. ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ሸዋ ዞን (ዳኑ፣ ኖኖ እና ጅባት ወረዳ) እና ምስራቅ


ወለጋ ዞን (ቢሎ ቦሼ ወረዳ)
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኑ፣ ኖኖ እና ጅባት ወረዳ እንዲሁም ከምስራቅ ወለጋ ዞን ቢሎ ቦሼ ወረዳ ቀሬ ኮች ቀበሌ
የሚኖሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ብሔር ተወላጆች የተፈናቀሉ ሲሆን ለመፈናቀላቸው ምክንያት የሆነው በኦሮምያ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 46
ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ቢሎ ቦሼ ወረዳ ቀሬ ኮች ቀበሌ በ 1965 እና በ 1977ዓ.ም በወቅቱ በነበረው የተፈጥሮ አደጋ፤
ድርቅና መሬት ጥበት ምክኒያት ከ አማራ ክልል ወሎ ክፍለ ሀገር ከተለያዩ ቀበሌዎች በወቅቱ የነበረው መንግስት በሰፈራ
ፕሮግራም በምስራቅ ወለጋ ዞን ቢሎ ቦሼ ወረዳ ቀሬ ኮች ቀበሌ 300 አባወራ፤ በቤተሰብ ብዛት 1050 እንዲሰፍሩ ተደርገው
ለረጅም አመታት ኖረዋል ነገር ግን በጥቅምት 25 /2014ዓ.ም ሸኔ የተባለ ቡድን ከአካባቢው ተወላጅ ወጣቶች ጋር
በመተባበር ግድያ፤የአካል ጉዳት እና ዝርፊያ የፈጸመ ሲሆን በዚህም ምክኒያት ሁሉም ተፈናቅለው በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን
አበሽጌ ወረዳ ዳርጌ ቀበሌ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡

በተመሳሳይ በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኑ፣ኖኖ እና ጅባት ወረዳ ማንነትን መሰረት ያደረገ ብሔረ ተኮር ግድያ ፣ የአካል ጉዳት
እንዲሁም ከትዳራቸው መለያየት(ማፋታት) ጥቃት የደረሰ ሲሆን ጥቃቱ የደረሰው ከተፈናቃዮች ባገኘነው መረጃ መሰረት
አማረኛ ተናጋሪ የአካባቢ ነዋሪዎች ላይ መሆኑን የጥቃቱ ፈጻሚ ሸኔ እና የአካባቢው ነዋሪ እንደሆኑና ጨለማን ተገን በማድረግ
በተደጋጋሚ ጥቃቱ እንደሚፈጸም ለኢሰመጉ ገልጸዋል፡፡

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በቀን 09/07/2014ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር 02/Dh 96/1727
ለኢሰመጉ በላከው መረጃ በተጠቀሱት አካባቢዎች የዜጎች ጉዳት መድረሱን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ያለመቻሉ እና በነዚህ
አካባቢዎች የደረሰው ጉዳት ግን ማንነትን መሰረት ያደረገ ሳይሆን በአካባቢው የሚኖሩ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል እና
በየደረጃው ባለው አመራር ላይ ያተኮረ መሆኑን እየሰጡት ካለው የተለያዩ ሰብዓዊ አገልግሎቶች እና እየሰሩ ካለው መልሶ
ማቋቋም ስራዎች መረዳት እንደሚቻል እንዲሁም ከክልሉ የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ መጡበት አካባቢ ተመልሰው
ህይወታቸውን እንዲመሩ የሚደረግና እየተደረገ በመሆኑ የተፈጠረው ችግር በአጭር ጊዜ መፍትሔ ያገኛል የሚል እምነት
እንላዳቸው ገልጸዋል፡፡

ኢሰመጉ ባደረገው ምርመራ በተገኘ መረጃ ከምዕራብ ሸዋ ዞን በዳኖ፣ኖኖ እና ጅባት ወረዳ ተፈናቅለው በደቡብ ብሔር
ብሔረሰቦች ክልላዊ መንግስት ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በአብሸጌ ወረዳ በዳርጌና በዋልጌ ከተማ የሚኖሩ በድምሩ 1459
አባወራ፤ በቤተሰብ ብዛት 8181 ይገኛሉ፡፡

ከህግ ውጪ የተፈጸመ ግድያ


ተ.ቁ. የተገደለው ሰው ስም ጾታ ዕድሜ የተገደለበት ቀን የተገደለበትድ ቦታ
1. ጌቱ ነገሰ መንገሻ ወ 55 06/05/2014 ማሩ በሀ ቀበሌ(ጅባት)

2. ተ/ማርያም ይልማ ጥላሁን ወ 50 05/05/2014 ቃሶ ማርያ/ኖኖ

3. ግዛቸው አምሶ ተ/ወልድ ወ 45 01/06/2014 ጉታ ቀብሌ(ዳኖ)

4. አይተንፍሱ እንዳሻው በለለው ወ 65 26/02/2014 አዳሚ ኢኬ (ጅባት)

5 ሽመልስ ዘመድኩን ደነቀ ወ 20 19/09/2013 ቀርሳ(ዳኖ)

6 ድንበሩ ዘመድኩን ደነቀ ወ 15 19/09/2013 ቀርሳ(ዳኖ)

7 ዘመድኩን ደነቀ አሻሚ ወ 40 19/09/2013 ቀርሳ(ዳኖ)

8 የሺ ከበደ ተሾመ ሴ - - -

9 ተስፋዬ አሳልፈው ታዲዮስ ወ 50 22/04/2014 ጫንዶ (ኖኖ)

10 ሸዋዬ አምታታው ወ/ጊዊርጊስ ሴ 46 25/02/2014 ሀኦ(ጅባት)

11 ዘይነባ አሊ ሰይድ ሴ 121 12/05/2014 ቀሬ ኮች(ምስራቅ ወለጋ)

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 47
12 ጃኖ ከወዬ አቢቶ ሴ 85 07/04/2014 ቀሬ ኮንሴ(ምስራቅ ወለጋ)

13 ወንዲኩን አማዴ ሐይሌ ወ 60 08/02/2014 አቡደኒ(ዳኖ)

14 ዲ/ን ፍቅሩ ሞላ ገደሙ ወ 27 08/03/2014 -

15 ወርቁ ደጀን አሰግድ ወ 50 25/02/2014 ሀሮ ጅባት(ጅባት)

16 ፋጡማ አህመድ ሴ 46 22/04/2014 ጫንዶ(ኖኖ)

17 ተይማ አበባው ሴ 9 22/04/2014 ጫንዶ

18 ዳወድ አበባው ወ 14 22/04/2014 ጫንዶ

19 አቦበከር አበባው ወ 05 22/04/2014 ጫንዶ

20 ሉባባ አህመድ ሴ 23 22/04/2014 ጫንዶ

21 ሀዋ ይብሬ ሴ 11 22/04/2014 ጫንዶ

22 ሰይድ መኮንን ወ 46 22/04/2014 ጫንዶ

23 ከድጃ መሀመድ ሴ 40 22/04/2014 ጫንዶ

24 አሊማ ሰይድ ሴ 19 22/04/2014 ጫንዶ

25 ምሳዬ ምስጌ ሴ 41 22/04/2014 ጫንዶ

26 ሼህ ሙሳ መሀመድ ወ 75 22/04/2014 ጫንዶ(ኖኖ)

27 አበባው ጌታሁን ወ 55 22/04/2014 ጫንዶ

28 ዘኒት አበባው ሴ 14 22/04/2014 ጫንዶ

29 ሁሴን ሀሰን ወ 42 22/04/2014 ጫንዶ

30 አቤ ሻረው ወ 15 20/02/2014 እሙገብሬል(ኖኖ)

31 መኮንን ጋሻው ወ 23 20/05/2014 ቆርኬማርያም(ኖኖ)

32 መሸሻ በቀለ ወ 60 06/05/2014 መቃሰዮ(ዳኖ)

33 ጌታወይ ካሳዬ ወ 52 05/05/2014 ሸነን ወረዳ

34 ሙሊት ሙልጌታ ሴ - 05/05/2014 ሸነን(ጝባት)

35 በለጠ ሽፈራው ወ 24 06/05/2014 መቃሰዮ

36 ቸምባ ተሰማ ወ 80 12/02/2014 ሰዮጉደታ(ዳኖ)

37 አደሙ አላዬ ወ 45 06/05/2014 መቃሰዮ(ዳኖ)

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 48
38 ወንድሙ ጌታሁን ወ 48 20/02/2014 አዳሚኡኬ

39 ኡስማን አበባው ወ 14 22/04/2014 ጫንዶ(ኖኖ)

30 ሚፍታ መሀመድ ወ 03 22/04/2014 ጫንዶ(ኖኖ)

41 ሰርካለም አያልቅበት ሴ - 20/05/2014 ቆርኬማርያውም(ኖኖ)

42 ጠዲ እሼቴ ሴ - 20/05/2014 ቆርኬማርያም(ኖኖ)

43 ሰይድ አበባው ወ 25 22/04/2014 ጫንዶ(ኖኖ)

44 ሙሳ ሰይድ ወ 11 22/04/2014 ጫንዶ(ኖኖ)

45 መዲና ይሳቅ ሴ 161 22/04/2014 ጫንዶ(ኖኖ)

46 ወርቁ አለምኔ ወ - 19/03/2014 መንቃታ(አምቦ)

47 አየለ ወርቁ ወ - 19/03/2014 “

48 መስፍን መኮንን ወ - 19/03/2014 “

49 ወንዴ በቀለ ወ - “ “

50 ስንቴ ድረስ ወ - “ “

51 ዘለቀ ሙላው ወ - “ “

52 ባምላክ ዘለቀ ወ - “ “

53 ታረቀኝ ብርሀኑ ወ - “ “

54 ብዙአየው ታረቀኝ ወ - “ “

55 ሀብታሙ ታረቀኝ ወ - “ “

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 49
በጥቃቱ ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በጥቂቱ በምስል

1 ሟች ሁሴን ሀሰን 2 ሟች ወርቁ ደጀኔ

3 ሟች በለጠ ሽፈራው 4 ሟች መዲና ይሓ

5 ሟች ወንዲኡባ ኢምዬ 6 ሟች አበባው ጌታሁን

7 ሟች ፋጢማ አህመድ 8 ሟች ሰይድ መኮንን

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 50
9 ሟች ሉባባ መካንን 10 ሟች ከድጃ አሊ

11 ሟች ህጻን ዓውዲ አበባው 12 ሟች ሀዋ ይብሬ

13 ሟች ህጻን ተይማ አበባው 14 ሟች ህጻን አቦከር አበባው

15 ሟች ሰይድ አበባው1

1
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ሸዋ ዞን (ዳኑ፣ ኖኖ እና ጅባት ወረዳ) እና ምስራቅ ወለጋ ዞን (ቢሎ ቦሼ ወረዳ) ስማቸው
ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰ የሟች ሰዎች ቀሪ ምስል በኢሰመጉ 150ኛ ልዩ መግለጫ ላይ የተካተተ ስለሆነ እሱን
ይመልከቱ፡፡

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 51
የአካል ጉዳት
ተ.ቁ የቆሰለው/የተጎጂ ስም ዕድሜ የተፈፀመበት ቀን የጉዳቱ አይነት
1. ክንዱ ሀሰን ጉቶ 40 28/02/2014 እግራቸውን በጩቤ መውጋትና ሙሉ
የሰውነት ድብደባ በዱላ

እስራት
ተ.ቁ. የታሰረው ሰው ስም የተፈፀመበት የታሰረበት ቦታ
ቀን

1. አባተ ተፈራ 13/03/2014 ሰርካምባ ፖሊስ ጣቢያ

2 ማሩ ጥጋቡ 13/03/2014 “

3 አሳምረው ወ/መላክ “ “

4 ተስፋዬ አስቻለው “ “

5 እንየው አስረስ “ “

6 ጋሻው ሞላ “ “

7 ጌትነት አከለ “ “

8 ገብሬ ምትኬ “ “

9 አህመድ አባቡ “ “

10 ብርሀን መድፍ “ “

7. በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ቡራዩ ከተማ አስተዳደር


1. አቶ ቶሎሳ ኪሼ ኬርዶ የ70አመት አዛውንት ሲሆኑ በገርኖ ኖኖ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ በሚያዚያ 13/2013 ዓ.ም ከምሽቱ
3፡00 ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ልብስ የለበሱ ሰዎች ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመግባት በመሳሪያ በማስፈራራት ያለ ፍርድ ቤት
ትዕዛዝ መኖሪያ ቤታቸው መበርበሩን፣ በመቀጠልም መኖሪያ ቤት ውስጥ ያገኙትን 13000ብር፣ ሞባይል እና ፓወር ባንክ እና
ሌላ የቤት እቃዎች መወሰዳቸወን በተጨማሪም በሰደፍ እና በዱላ በመጠቀም በመደብደብ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል በዚህም
ምክንያት የቀኝ ጆሮአቸው የመስማት ችግር እንደገጠመው እና ዓይናቸው በደረሰበት ከባድ ድብደባ በከፊል ማየት
እንደተሳነው ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡ ለዚህም መነሻ ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት ሸኔን
ይደግፋል የሚል ነበር፡፡
2.ወ/ሮ አልማል በቀለ የ50 አመት ጎልማሳ ሲሆኑ በገርኖ ኖኖ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ በሚያዚያ 13/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00
ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ልብስ የለበሱ ሰዎች ወደቤት በመግባት ግማሾቹ ባሌቤታቸውን (አቶ ቶሎሳ ኪሼ ኬርዶ) እና
ልጃቸውን (አቶ ቦና ቶሎሳ ኩሼ) ያለመያዣ ፍቃድ እንደወሰዷቸው፣ የቀሩት ደግሞ እቤት ውስጥ ያለመፈተሻ ፍቃድ ፈትሸው
በጥሬ ገንዘብ በአጠቃላይ 13000፣ የአንገት ወርቅ፣ የግድግዳ ስዕል፣ እንዲሁም ፓወር ባንክ እንደወሰዱ፣ ወ/ሮ አልማዝ ላይም

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 52
ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸው እና ለአስራ አምስት ቀን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከታሰሩ በኋላ በዋስ እንደተለቀቁ ኢሰመጉ
ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

3.አቶ ቦና ቶሎሳ ኩሼ የ24 ዓመት ወጣት ሲሆን የገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ነዋሪ ነው፡፡ በመስከረም 29/2014 ዓ.ም የታጠቁ
የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ቤት ድረስ በመምጣት ምክንያቱን በማያውቀው ነገር በሰደፍ በዱላ እንዲሁም በጎማ በመጠቀም
በጣም እንደበደቡት፣ በመቀጠልም ወደ እስር-ቤት በመውሰድ ለፍርድ ሳይቀርብ በጀመሪያ ለ13 ቀን ከዛም ፈተው ድጋሚ
ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ለአንድ ወር መታሰሩን፣ መጀመርያ ሲያዝ ባደረሱበት ድብደባ ጭንቅላቱ እና ሰውነቱ ላይ ከባድ ጉዳት
መድረሱን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

ኢሰመጉ ከላይ የተዘረዘሩትን ሶስት ጉዳዮች አስመልክቶ ለኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በደብዳቤ ቁጥር ER3/m41/15/22 በቀን
21/08/2014 ዓ.ም ጉዳዩን አስመልክቶ ኮሚሽኑን ማብራሪያ እና ማስረጃ የጠየቀ ቢሆንም ይህ መግለጫ እስከወጣበት ቀን
ድረስ ኮሚሽኑ ምንም አይነት መልስ አልሰጠም፡፡

8. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)


የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ፓርቲ በደበዳቤ ቁጥር 015/xly-abo/2022 በቀን 26/04/2022 ባስገባው አቤቱታ መሰረት
እንዲሁም ኢሰመጉም እንዳጣራው የኦነግ አመራሮች እና አባላት ላይ የተለያዩ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች
እየተፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ ኦነግ በአመራሮቼና አባላቶቼ ላይ ተፈጽመዋል ካላቸው የመብት ጥሰቶች መካከልም ህገ-ውጥ እስር
የመጀመሪያው ሲሆን ያለ ምንም የፍርድ ትዕዛዝ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ማዋል፣ በፍርድ ፊትም ቀርበው ጥፋተኞችና ወንጀለኞች
ተብለው ሳይፈረጁ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲለቀቁ በወሰነበት ሁኔታ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የህገ መንግስቱን አንቀፅ 17
በመጣስ ያለ አግባብ የኦነግ አባላትን በእስር አቆይቷል በአሁኑም ጊዜ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ አመልካቾች እንደገለፁት በእስር
ቤት ውስጥ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈፀመባቸው ሲሆን እነዚህም ህክምና የማግኘት መብት መከልከል፣ በቂ
ምግብ እና ንጹህ ውሀ አለማግኘት፣ ከቤተሰቦቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ጓደኞቻቸው ጋር ለመገናኘት በቂ እድል
እየተሰጣቸው አለመሆኑን በአጠቃላይ በፖለቲካዊ አመለከካከታቸው የሸኔ ደጋፊዎች ናችሁ በማለት ለሰብአዊ እና
ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰት መዳረጋቸው ተገልጹዋል፡፡

ተጎጂዎች ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ቤታቸውን በመፈተሸና ገንዘብ በመውሰድ፣ ሰዎችን ከቤታቸው አፍኖ በማስወጣት፣
እየወሰዱም በመደብደብ እና ኢሰብአዊ ድርጊቶችን በመፈፀም ለአካል እና ለሞራል ጉዳት እንዲሁም ከቤት ንብረታቸው
ለመፈናቀል እና ለሞት እየተዳረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ከቤታቸው ታፍነው ወደ ማይታወቅ ቦታ
በመወሰድ በተለያዩ እስር ቤቶች ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ለእንግልት እና ለስቃይ ተዳርገዋል፡፡ አሁንም ያሉበት አድራሻ
አለመታወቁ ሁኔታውን አሳሳቢ ያደርገዋል የፍትህ አካላትም እንደ የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተገቢውን ትብብር
ባለማድረግ በአንቀጽ 9(2) መሰረት ሃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ አለመሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም
በጥበቃ ስር ያሉ ሰዎች ክብራቸው ተጠብቆ የመያዝ መብታቸው በአንቀጽ21(2) እንደተገለጸው ያልተከበረ መሆኑን እና
ላለፉት አመታት ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በእስር መቆየታቸው ተገቢ አለመሆኑን ኢሰመጉ ለመረዳት ችሏል፡፡

 ከህግ ውጪ የተፈጸመ ግድያ


ሟች መለስ ጫላ ጎበና ወንድ የ43 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን በባንክ ስራ ይተዳደራል እንዲሁም በትርፍ ሰአቱ የኦሮሞ ፌዴራሊስት
ኮንግረስ አባል ነው የሟች ባለቤት ወ/ሮ ጫልቱ ሐምቢሳ እንደሚያስረዱት በሚያዚያ 13/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 ላይ
የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ልብስ የለበሱ ሰዎች ወደቤት በመግባት ያለፍርድ ቤት ማዘዣ ባለቤታቸውን ይዘው እንደሄዱ ያስረዳሉ
አክለውም ከዚሁ እለት ጀምሮ በተለያዩ በአከባቢው ወደ ሚገኙ እስር ቤቶች በመሄድ ቢጠይቁም የትኛውም አካል የት
እንደታሰረ ሳይነግራቸው ሶስት ወር እንዳለፈ ይናገራሉ በመጨረሻም አብረው ታስረው ከነበሩ ሰዎች መካከል አቶ መለስ ጫላ
በተያዙ በዛው አለት የተገደሉ መሆኑን እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፣ ኢሰመጉ ይህንንም ጉዳይ ካሰባሰባቸው መረጃዎች
ለመረዳት ችሏል፡፡
 ህገወጥ እስራት
ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩ ሰዎች በተለያየ ጊዜ ኦሮሚያ የመንግስት ንብረት ግዢና ማስወገጃ ኤጀንሲ ምድር ቤት ውስጥ፣

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 53
ገላን ፖሊስ ጣቢያ፣ ገላን ወታደራዊ ካምፕ፣ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ፣ አዋሽ መልካሳ የግለሰብ ዶሮ ማርቢያ መጋዘን፣
አዳማ ፖሊስ ጣቢያ፣ ሞጆ ፖሊስ ጣቢያ፣ ሳንሱቲ ማረሚያ ቤት፣ዳለቲ ማረሚያ ቤት፣ ሰበታ ፖሊስ ጣቢያ እና ቡራዩ ፖሊስ
ጣቢያ የታሰሩ መሆናቸውን ለኢሰመጉ ከቀረቡ አቤቱታዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡
ኢሰመጉ ከላይ የተጠቀሰውን ዝርዝር ጉዳይ አስመልክቶ ለኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በደብዳቤ ቁጥር ER3/m41/15/22 በቀን
21/08/2014 ዓ.ም ጉዳዩን አስመልክቶ ማብራሪያ እና ማስረጃ የጠየቀ ቢሆንም ይህ መግለጫ እስከወጣበት ቀን ድረስ
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንገ ምንም አይነት መልስ አልሰጠም፡፡

ተ.ቁ. የታሰረው ሰው ስም ዕድሜ የታሰሩበት ቀን

1 አቶ ኬኒሳ አያና - -

2 አቶ ሚካኤል በቀለ ኢተቻ 48 25/10/2012

3 ዶ.ር. ገዳ ኦልጅራ - -

4 አቶ ገዳ ገቢሳ አብዲሳ 37 04/02/2013

5 አቶ ለሚ ቤኛ ቀጄላ 38 04/11/2012

6 አቶ ዳዊት አብደታ ሁንዴሳ 38 04/12/2012

7 ኮሎኔል ገመቹ አያና ሮሮ - 27/10/2014

8 አቶ አብዲሳ ረጋሳ ኮፔሳ - 15/05/2011

9 አቶ አማን ፊሌ - 29/06/2012

9. ኢንጂነር ግርማ ጡሩና ደርሴ ላይ የተፈፀመ የሰብአዊ መብት ጥሰት

ኢንጂነር ግርማ ጡሩና ደርሴ


ኢንጂነር ግርማ ጡሩና ደርሴ ጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም ከሚሰራበት ቦታ ድሬደዋ ኢንደስትሪያል ፓርክ በኦሮሚያ ፖሊስ
የተያዘ ሲሆን የተያዘበትም ምክንያት በወቅቱ በተለያየ ስም የተክፈቱ የፌስቡክ አካውንት የተለያዩ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው
መልእክቶች በመተላለፋቸው እና “በኦሮሚያ ውስጥ እየተቀጣጠለ ከነበረው ተቃውሞ ጀርባ ያለው እሱ ነው” የሚሉ
መረጃዎች ነበሩ፡፡ ይህንንም ድርጊት ያደርጉ የነበሩት የቀድሞ ባለስልጣናት እና አንዳንድ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ተቀባይነት
ባላቸው አካላት ኢንጂነር ግርማ ጡሩናን በኦሮሞ ትግል ውስጥ ተቀባይነት እንዳይኖረው ለማድርግ የተቀነባበረ የስም
ማጥፋት ዘመቻ መሆኑን ኢሰመጉ ከቀረቡለት አቤቱታዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

ኢንጂነር ግርማ ጡሩና ደርሴ ጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም ከድሬደዋ ወደ ጭሮ ከተማ መወሰዱን፣ በወቅቱ የነበሩ የኦሮሚያ
የስራ ሀላፊዎች በመጋቢት 02 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ አዳማ በማስመጣት አብረው እንዲሰሩ ጥያቄ ቢያቀርቡለትም ፈቃደኛ
ባለመሆኑ ከመጋቢት 02 ቀን 2010 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 19 ቀን 2010 ዓ.ም አዳማ ከተማ የምስራቅ ሸዋ ፖሊስ መምሪያ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 54
ያቆዩት መሆኑን እና ቤተሰቦቹም ታስሮ በነበረበት ቦታ በአካል ተገኝተው ይጠይቁት እንደነበር ኢሰመጉ ከቀረቡለት
አቤቱታዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

ኢንጂነር ግርማ ጡሩና ደርሴ ሚያዚያ 19 እስከ ነሀሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ውደ ቢሾፍቱ በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ተወሰዶ
እዛ ከቆየ በኋላ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ መወሰዱን፣ የምርመራ ስራውም እስከ ነሀሴ 29 ቀን 2010
ዓ.ም ድረስ የተደረገ መሆኑን እና በምርመራ ስራው ግኝትም ኢንጂነር ግርማ ጡሩና ደርሴ ምንም ወንጀል አለመስራቱን
ይልቁንም አንዳንድ ወንጀሎች በኢንጂነር ግርማ ጡሩና ላይ መሰራታቸውን፣ በዚህም ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ የቀድሞ
የደህንነት አባላት በኢንጂነር ግርማ ጡሩና ላይ የስም ማጥፋት መፈጸማቸውን ማመናቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች
ለመረዳት ችሏል፡፡ ነገር ግን ኢንጂነር ግርማ ጡሩና ደርሴ ከእስር መለቀቅ ሲገባው በኦሮሚያ ፖሊስ ወደ ቢሾፍቱ ተመልሶ
መታሰሩን፣ በተለያየ ጊዜ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነሮች እና የመንግስት ባለስልጣናት ትወጣለህ እየተባለ ቃል ቢገባለትም ለ5
(አምስት) ዓመት ያህል ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ያለአግባብ እስር ቤት መቆየቱን፣ በአሁን ሰዓት ቤተስቦቹ ካገኙት 4(አራት)
ዓመት እንዳለፋቸው እና በህይወት መኖር አለመኖሩን የሚያረጋገጥ መረጃም እንደሌላቸው የኢንጂነር ግርማ ጡሩና ደርሴ
ቤተሰቦች ለኢሰመጉ አስረድተዋል፡፡

ኢሰመጉ ከላይ የተጠቀሰውን ዝርዝር ጉዳይ አስመልክቶ ለኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በደብዳቤ ቁጥር ER3/m41/15/22 በቀን
21/08/2014 ዓ.ም ጉዳዩን አስመልክቶ ማብራሪያ እና ማስረጃ የጠየቀ ቢሆንም ይህ መግለጫ እስከወጣበት ቀን ድረስ
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንገ ምንም አይነት መልስ አልሰጠም፡፡

ክፍል ሁለት
የህግ ትንተና እና ግዴታዎች
በህይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነት እና የንብረት መብቶች ጋር ተያይዞ ያሉ ደንጋጌዎች
በህይወት የመኖር መብት መብት የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 14 “ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና
የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት አለው” ሲል ይደነግጋል፡፡ በተመሳሳይ የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ
15 ማንም ሰው በህይወት የመኖር መብት እንዳለውና ሕግ ከሚደነግገው ውጪ የመኖር መብቱን ሊያጣ እንደማይችል
ተመላክቷል፡፡ ኢትዮጵያም እነዚህን ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሰብዓዊ መብቶች ሰነዶች የተቀበለች ሀገር እንደመሆኗ ሰብዓዊ
መብቶችን የማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት ግዴታ ተጥሎባታል፡፡

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ አንቀጽ 3 “ እያንዳንዱ ሰው በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነቱ የመጠበቅ
መብት ” እንዳለው ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለችው የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል
ኪዳንም በአንቀጽ 6 (1) እና 9 (1) ላይ ይህንኑ መብት በማረጋገጥ፣ መንግሥታት በቃልኪዳኑ የተረጋገጡትን
መብቶች በግዛታቸው የማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት ግዴታ እንዳለባቸውም በአንቀጽ 2 (1) እና 2 (2) ይደነግጋል።
የአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር አንቀጽ 4 “ማንኛውም ግለሰብ በሕይወት የመኖር መብቱና የአካሉ ደህንነት
ሊከበርለትና ሊጠበቅለት እንደሚገባና እነዚህን መብቶቹን በዘፈቀደ ሊነፈግ እንደማይችል ተመላክቷል።

በህይወት የመኖር መብት ሰፋ ያለ ትርጓሜ ሊሰጠው የሚገባ መብት ነው። ግለሰቦችን ከተፈጥሮ ውጭ ከሆኑ ሞትን
ከሚያስከትሉ ድርጊቶች እና ግድፈቶች ነጻ የመሆን እና ክብር ያለው ሕይወት የመኖር መብትን የያዘ ነው። የመኖር መብት
ለግለሰቦችም ሆነ ለጠቅላላ ህብረተሰቡ ወሳኝ ጠቀሜታ አለው። የመብቱ መከበር በራሱ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ሳለ በራሱም
መሰረታዊ መብት ስለሆነ ለሌሎች መብቶች መከበርና እንዳይጣሱም መጠበቅ ቅድመ ሁኔታም ነው። ይህ መብት ሰው ለሆነ
ሁሉ በእኩል ሁኔታ ያለ ምንም አይነት የጾታ፣ የዘር፣ የቀለም፣ የሃይማኖት፣ ፖለቲካዊ ወይም ሌላ አስተያየት፣ ብሔራዊ ወይም
ማህበራዊ መነሻ፣ ንብረት፣ ልደት ወይም ማንኛውም ሌላ ሁኔታ፣ የጎሳ፣ የብሄር ወይም የሀገሬው ተወላጅ ቡድን አባልነት፣
የአካል ጉዳት፣ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ፣ዕድሜ እና በመሳሰሉት ምክኒያቶች መድልዎ ሳይደረግ ለሁሉም ሰው በእኩል
ሁኔታ ሊከበርና ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባ መብት ነው።

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 55
የአካል ጉዳት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥትም በአንቀጽ 16 ሥር ‹‹ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት
አለው›› ሲል ይደነግጋል፡፡ የሰዎች የአካል ደኅንነት የመጠበቅ መብት የማይደፈርና የማይገረሰሥ መሆኑንም የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 14
ያረጋግጣል፡፡

እንዲሁም የአካል ደህንነት መብትንም ብንመለከት በሰብዓዊ መብቶች ዓለም አቀፍ መግለጫ አንቀጽ 3 መሰረት እያንዳንዱ
ሰው የህይወት፣ የነጻነትና የተሟላ ደህንነት መብት አለው። ዓለም አቀፉ የሲቪል እና ፖለቲካዊ መብቶች የቃል-ኪዳን
ስምምነት በአንቀጽ 9 ሥር እንደሚደነግገው ‹‹ማንኛውም ሰው አካላዊ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆን ይገባዋል››። ሰዎችን
በማንኛውም አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆን ተብሎ በሰውነት ወይም በአእምሮ ላይ ከሚደርስ ጉዳት እንዲጠበቁ

የንብረት ውድመት በተመሳሳይ የንብረት መብትንም ብንመለከት በቂ መኖሪያ እና መጠለያ የማግኘት መብት በዓለም አቀፍ
የሰብአዊ መብቶች መግለጫ እና በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ መብቶች እውቅና የተሰጠው መብት ሆኖ
እናገኘዋለን። ማንም ሰው ለራሱና ለቤተሰቡ ጤንነትና ደህንነት በቂ በሚሆን የኑሮ ደረጃ የመኖር መብት ያለው ሲሆን ይህም
ምግብን፣ ልብስን፣ መጠለያን ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ ማህበራዊ አገልግሎቶችን የማግኘትንና እነዚህን ከመሳሰሉ ለመኖር መሰረታዊ
የሆኑ ነገሮችን ከሚያሳጡ ድርጊቶች መጠበቅን ይጨምራል።

በአፍሪካ የሰዎችና የህዝቦች መብቶች ቻርተር አንቀጽ 14 እና በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(1) መሰረት ማንኛውም
ኢትዮጵያዊ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት የመሆን መብቷ/ቱ ይከበራል። ይህ መብት የህዝብ ጥቅምን ለማስጠበቅ በሌላ ሁኔታ በህግ
እስካልተገደበ ድረስ ወይም የሌሎችን ዜጎች መብቶች እስካልተቃረነ ድረስ ንብረት የመያዝና በንብረት መጠቀምን ይጨምራል።
እንዲሁም በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 7 ላይ በግልጽ እንደተደነገገው ማንም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ በመሬት ላይ
ለሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል ሙሉ መብት አለው።

ህገወጥ እስራት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17 እንደተደነገገው ማንም ሰው በህግ በተደነገገው መሰረት ካልሆነ በቀር
ነፃነቱን አይነጠቅም፤ ማንም ሰው በዘፈቀደ ሊታሰር አይችልም፣ ማንም ሰው ያለ ክስ ወይም የጥፋተኝነት ክስ ሊታሰር አይችልም።
ኢትዮጵያ ፈርማ ከተቀበለቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች አንዱ የሆነው የተባበሩት መንግስታት ቻርተር መሰረት የህግ
አሰፈፃሚዎች የዘር፣ የፆታ፣ የቋንቋና የእምነት ልዩነት ሳያዩ የሰብዓዊ መብቶችን እና መሰረታዊ ነፃነቶችን መከበር ለማስፈን እና
ለማስከበር መስራት እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ የህግ አካለት ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሲፈጽሙ ተስተውለዋል ከዚም መሃል
ያለፍርድ እስራት (Arbitrary Arrest) ይገኝበታል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 19 (አስራዘጠኝ) እንደሚደነግገው ወንጀል ፈጽመዋል በመባል የተያዙ ሰዎች የቀረበባቸው
ክስና ምክያቶቹ በዝርዝር ወዲያውኑ በሚገባቸው ቋንቋ እንዲነገራቸው መብት ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም የተያዙ ሰዎች በ48
(በአርባ ስምንት) ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅርብ መብት አላቸው፡፡ ይህ ካልሆነ አካላቸው ነጻ እንድውጣ የመጠየቅ መብት
አላቸው፡፡ አንቀጽ 21 ይንደሚያስቀምጠው በህግ ከለላስር ያሉ ሰዎች በትዳር ጓድኞቻችው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣
ከጓድኞቻችው፣ ከሐኪሞቻቸው እና ከሕግ አማካሪዎቻቸው ጋር የመገናኝት መብት አላቸው፡፡

የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን በአንቀጽ 9(ዘጠኝ) እንደሚደነግገው ማንኛውም ሰው የሰውን ነፃነትና
ደህንነት የማግኘት መብት አለው። ማንም ሰው በዘፈቀደ ሊታሰር አይችልም። ማንም ሰው በህግ በተደነገገው መሰረት ካልሆነ
በቀር ነፃነቱን አይገፈፍም። በህግውጥ እስራት ነፃነቱን የተነጠቀ ማንኛውም ሰው ጉዳዩን በፍርድ ቤት የመከታተል መብት
ያለው ሲሆን፡፡ ፍርድ ቤቱም ስለእስር ህጋዊነት የሚገባውን ማጣራት አድርጎ ሳይዘገይ ወስኖ እስሩ ህጋዊ ካልሆነ ከእስር ነጻ
ማድረግ አለበት፡፡ ኢንጂነር ግርማ ጡሩና ላይ የትፈጸመው ድርጊት ከላይ የተጠቀሱትን ድንግጌዎች የተጻረሩ ሆነው
አግኝተናቸዋል፡፡

ስም ማጥፋት በኢትዮጵያ የፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 2044 (1) መሠረት የስም ማጥፋት ድርጊት አንድ ሰው በቃላቱ፣
በጽሑፎቹ ወይም በማናቸውም መንገድ የሌላውን ሰው ግጽታ እንድበላሽ የሚያደርግ ጥፋት ሲሠራ ነው። ይህ ድርጊት
መልካም ዝናውን ወይም የወደፊት ህይወቱን አደጋ ላይ ይጥላል። በአንቀጽ 2109 እንደተደነገገው ፍትሃዊ ካሳ ለከሳሹ ወይም
በስሙ ለተሰየመው የበጎ አድራጎት ድርጅት ስድብ ወይም ስም ማጥፋት ያድርስው አካል ተገቢውን ካሳ ሊሰጥ ይችላል።

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 56
የግለሰቦችን ወይም የግለሰቦችን ክብር ወይም መልካም ስም የሚፃረሩ ጉዳዮችን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ የድርጊቱን ውጤት
የምለውጥ መግለጫ በተከሳሹ ወጪ በሚታውቅ የሚድያ አካል ይፋ እንዲደረግ ማዘዝ ይችላል በማለት የኢትዮጵያ የፍትሐ
ብሔር ሕግ አንቀጽ 2120 ይደነግጋል፡፡

የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ አንቀፅ 607 በግልፅ እንደሚያሳየው በክብር እና በስም ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የከሳሽን እና
የተከሳሽን ስም እና ደርጃን ግንዛቤ ወስጥ ሳያስገባ በህግ የሚያስቀጣ ነው። አንቀጽ 613 እንደተቀመጠው ስም ማጥፋት
ወንጀል ከ6 (ስድስት) ዓመት ባልበለጠ ቀላል እስራት ወይም የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል፡፡
የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን በአንቀጽ 17 እንደሚያሳየው ማንም ሰው በዘፈቀደ ወይም በህገ ወጥ
መንገድ በቤተሰቡ፣ በክብሩ እና በዝናው ላይ ህገ-ወጥ ጥቃት ሊደርስበት አይገባም። ማንኛውም ሰው ከእንደዚህ አይነት
ጥቃቶች የህግ ጥበቃ የማግኘት መብት አለው፡፡

አስገድዶ መሰወር (International Convention for the Protection of All Persons from Enforced
Disappearance) ላይ በአንቀጽ 1 ላይ እንደሚያሳየው ማንም ሰው በግዳጅ እንዲሰወር አይደረግም። ምንም አይነት ልዩ
ሁኔታዎች፣ የጦርነት ሁኔታም ሆነ የጦርነት ስጋት፣ የውስጥ ፖለቲካ አለመረጋጋት ወይም ሌላ ማንኛውም የህዝብ ድንገተኛ
አደጋ፣ ለግዳጅ መጥፋት እንደ ምክንያት ልቅርብ አይችሉም። የሚመለከትው አካል ድርጊቶችን ለመመርመር ተገቢውን
እርምጃ መውስድ አልበት፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 28 ላይ እንደተደነገገወ ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎች
የኢትዮጵያ ሕጎች በሰው ልጅ ላይ የትፈጸሙ ወንጅሎች ተብልው የተወሰኑትን የሰው ዘር የምጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት
እርምጃ የመውሰድ፣ አስገድዶ ሰውን መሰወር ወይም ኢሰብዓዊ ድብደባ ድርጊቆችን በፈጸሙ ሰውች ላይ ክስማቅረብ በይርጋ
አይታግድም፡፡ በህግ አውጪው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግስት አካል ውሳኔዎች በምህረት ወይም በይቅርታ
አይታልፍም፡፡

የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አስመልክቶ ያሉ ህጎችና ግዴታዎች 2


የካምፓላ ስምምነት በአንቀጽ 2(d) የስምምነቱን አላማ ሲዘረዝር “ለስምምነቱ አባል ሀገራት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን
በሚመለከት ከመፈናቀል ስለመጠበቅ፣ ከተፈናቀሉም በኋላ ጥበቃ ስለማድረግ እና ሰብአዊ ድጋፍ መስጠትን በተመለከተ
ያለባቸውን ሃለፊነት እና ግዴታ ማሳወቅ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡” በተመሳሳይ የሀገር ውስጥ መፈናቀልን ስለመከላከል ስምምነቱ
በአንቀጽ 3 ንኡስ አንቀጽ 1(a) ላይ የስምምነቱ አባል ሀገራት የሀገር ውስጥ መፈናቀልን መከላከል እንዳለባቸው
ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሀገር ውስጥ መፈናቀልን በመሚመለከት ያወጣው
የመመሪያ መርህ በመርህ 6(1) ላይ ማንኛውም ሰው ከመኖሪያ ቦታው በዘፈቀደ ያለመፈናቀል መብት እንዳለው
ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ ከእነዚህ ድንጋጌዎች መረዳት እንደሚቻለው መንግስት ዜጎችን የሀገር ውስጥ መፈናቀልን
ሊያስከትሉ ከሚችሉ ነገሮች መከላከል እንዳለበት መረዳት እንችላለን፡፡ በዚህም መሰረት በተዘዋዋሪ ዜጎች ከሀገር ውስጥ
መፈናቀል የመጠበቅ መብት አላቸው ብለን መደምደም ይቻላል፡፡

የካምፓላ ስምምነት አንቀጽ 3(1)(b) በግልጽ እንደተደነገገው በማህበራዊ ማንነታቸው፤ በሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ
አመለካከታቸው የሰዎችን ወይም የማህበረሰቦችን መፈናቀል ሊያስከትሉ ከሚችሉ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊ እና
ኢኮኖሚያዊ መገለልን እና ፍረጃ መከላከል የሚል ሲሆን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የክልሉ ባለቤት ብሎ
ያስቀመጣቸው በርታ፤ጉሙዝ፤ሽናሻ ፤ ማኦና ኮሞ መሆናቸውን ነው ፡፡ ስለሆነም ይህ ህገ መንግስት ሌሎች ብሔሮች
ላይ ባላቸው ማንነት ምክኒያት እንዲገለሉና ሀብት ንብረት ካፈሩበት ቦታ እንዲፈናቀሉ አንዱ መነሻ ምክኒያት ሆኗል፡፡
መንግስትም ለመፈናቀል ምክኒያት የሆኑትን ነገሮች ባለመከላከሉ የብዙ ሰው ህይወት አልፏል፤ንብረት ወድሟል
እንዲሁም ሀብት ንብረታቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል፡፡

2
ከኢሰመጉ 150ኛ መግለጫ ላይ የተወሰደ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 57
በተጨማሪም በካምፓላ በስምምነት አንቀጽ 4(1) አባል ሀገራት ለሀገር ውስጥ መፈናቀል ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን
ለመከላከል እና ለማስቆም ይረዳ ዘንድ በዓለም አቀፍ ህጎች በሰብዓዊ መብቶች እና በሰብዓዊነት ህጎች ላይ የተቀመጡ
ግዴታዎቻቸውን ማክበር እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ ይኸው አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ 4(d) ላይ ሁሉም ሰው በተጠቃለለ
ጥቃት ወይም በሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ከሚደርስ መፈናቀል የመጠበቅ መብት አለው ሲል ዜጎች ከመፈናቀል
የመጠበቅ መብት እንዳላቸው ደንግጓል፡፡

ስምምነቱ በአንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ አባል ሀገራት በድንበሮቻቸው ውስጥ ለሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች
ሰብአዊ ድጋፍ እና ጥበቃ ያለምንም አድልዎ በማቅረብ ረገድ ተቀዳሚ ሀላፊነት እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ የተባበሩት
መንግስታት ድርጅት የሀገር ውስጥ መፈናቀልን በመሚመለከት ያወጣው የመመሪያ መርህ በመርህ 3(1) ላይ ከካምምላ
ስምምነት ጋር ተመሳሳይ በሚባል ደረጃ መንግስታት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የመጠበቅ እና ድጋፍ የማድረግ ተቀዳሚ
ሀላፊነት እንዳለባቸው በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ከነዚህ ድንጋጌዎች የምንረዳው በቀዳሚነት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን
መርዳት እና ጥበቃ የማድረግ ሃላፊነት የሀገሪቱ መንግስት መሆኑን ነው፡፡

ከካምፓላ ስምምነት አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 2(b) እና (c) የጋራ ንባብ እንደምንረዳው መንግስት ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች
በተቻለ መጠን ሳይዘገይ በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ ምግብ፣ ውሀ፣ መጠለያ፣ የህክምና እንክብካቤ እና ሌሎች የጤና
አገልግሎቶች፣ የንጽህና አጠባበቅ፣ ትምህርት እና የትኛውንም አይነት አስፈላጊ ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ
ሲገኝ ይህንን ድጋፍ ለተቀባይ ማህበረሰብ ማድረግ እንዳበት፤ ልዩ ጥበቃ እና ሰብዓዊ ድጋፍ ካሉበት ሁኔታ አንጻር ልዩ
ድጋፍ ለሚሹ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ማለትም ከቤተሰቦቻቸው ለተለዩ ህጻናት፣ ለእማወራዎች፣ ለነፍሰጡር ሴቶች፣
ህጻናት ልጆች ላሏቸው ሴቶች፣ ለአዛውንቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለተላላፊ በሽታ ታማሚዎች መደረግ እንዳለበት
ይደነግጋል፡፡ በተመሳሳይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሀገር ውስጥ መፈናቀልን በመሚመለከት ያወጣው የመመሪያ
መርህ በመርህ 18 እና 19 ላይ እያንዳንዱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት እንዳለው፣
መንግስትም በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም ያለ ምንም አድልዎ ቢያነስ አስፈላጊ ምግብ እና ንጹህ ውሀ፣ መጠለያ፣
ልብስና አስፈላጊ የህክምና እና የንጽህና አገልግሎት ማቅረብ እንዳለበት እንደሁም ድጋፍ በሚሰጥበት ሰዓት ልዩ
ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የህበረሰብ ክፍሎችንም ጨምሮ ይዟል፡፡ በተጨማሪም ይኸው የመመሪያ መርህ ትምህርትን
በሚመለከት በመርህ 23 ላይ ሁሉም ሰው የመማር መብት እንዳለው በመግለጽ ይህ መብት ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችም
የተሰጠ መሆኑን እና መንግስትም ይህንን መብት በዋናነት ለተፈናቀሉ ህጻናት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን በነጻና
በአስገዳጅ መልኩ ማቅረብ እንዳለበት እንዲሁም ይህ ትምህርት ባህላዊ ማንነታቸውን፣ ቋንቋቸውን እና
ሀይማኖታቸውን ማክበር እንዳለበት አስቀምጧል፡፡

በካምፓላ ስምምነት አንቀጽ 9 ንኡስ አንቀጽ 2 (k) እና በአንቀጽ 11 ንኡስ አንቀጽ (2) ላይ የተቀመጡትን
ድንጋጌዎች በጋራ በምንመለከትበት ሰዓት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ደህንነት እና ድጋፍ በሚመለከት በሚወሰኑ
ውሳኔዎች ላይ የስምምነቱ አባል ሀገራት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ማማከር እና ውሳኔዎች ላይ ተሳታፊ ማድረግ
እንዳለባቸው፤ የስምምነቱ አባል ሀገራት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደመጡበት አካባቢ ለመመለስ፣ ተፈናቅለው
ባሉበት አካባቢ ለማስፈር ወይም ወደሌላ ቦታ ማዘዋወርን እንዲሁም ሌሎች አማራጮችን በሚመለከት የሀገር ውስጥ
ተፈናቃች ነጻ ምርጫ እንዲመርጡ ማስቻል እና ዘላቂ መፍትሄ በማበጀቱ ረገድ ተሳትፏቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው
ተደንግጓል፡፡

በተጨማሪም የካምፓላ ስምምነት በአንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 2 (e) ላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሌላ የሀገሪቱ
አካባቢ ደህንነት የማግኘት እና ህይወታቸውን፣ ደህንነታቸውን፣ ነጻነታቸውን እና ጤንነታቸውን አደጋ ላይ ወደሚጥል
ወደመጡበት አካባቢ በግዴታ ከመመለስ ወይም ወደ ሌላ ቦታ ከመዘዋወር የመጠበቅ መብታቸውን አባል ሀገራት
የማክበር እና የማረጋገጥ ሀላፊነት እንዳለባቸው በግልጽ አስቀምጧል፡፡ በተመሳሳይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት
የሀገር ውስጥ መፈናቀልን በመሚመለከት የወጣው የመመሪያ መርህ በመርህ 15 ላይ በግዴታ ወደ መጡበት አካባቢ
ከመመለስ ወይም ደህንነታቸውን፣ ህይወታቸውን፣ ነጻነታቸው እና ጤናቸውን አደጋ ላይ ወደሚጥል ወደሌላ አካባቢ
በግዴታ ከመዘዋወር የመጠበቅ መብት አላቸው ሲል ይደነግጋል፡፡

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 58
የካምፓላ ስምምነት በአንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ የስምምነቱ አባል ሀገራት በአባል ሀገር ጥያቄ መሰረት ለሀገር
ውስጥ ተፈናቃዮች ድጋፍ እና ጥበቃ በማድረጉ ላይ መደጋገፍ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ ይኸው ስምምነት በአንቀጽ
5 ንዑስ አንቀጽ 6 ላይ አባል ሀገራት ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በቂ የሆነ ድጋፍ እና ጥበቃ ማድረግ እንዳለባቸው፤ ይህንን
ድጋፍ እና ጥበቃ ለማድረግ ያሉ ግብአቶች በቂ ሳይሆኑ ሲቀሩ የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን እና ሰብዓዊ ተቋማትን፣
ሲቪክ ማህበራትን እና ሌሎች ተዋናዮችን ማፈላለግ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪም የስምምነቱ አንቀጽ 9
ንኡስ አንቀጽ 3 አባል ሀገራት በአንቀጽ 9 ላይ የተቀመጡ ግዴቶቻቸውን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች
እና ሰብዓዊ ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት እና ሌሎች ተዋናዮች ድጋፍ መወጣት እንዳለባቸው ደንግጓል፡፡ የተባበሩት
መንግስታት ድርጅት የሀገር ውስጥ መፈናቀልን በመሚመለከት ያወጣው የመመሪያ መርህ በመርህ 25 ላይ የሀገር
ውስጥ ተፈናቃዮችን የመርዳት ቀዳሚ ሀላፊነት የሀገሪቷ መንግስት መሆኑን በመግለጽ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ተቋማት
እና ሌሎች ተመሳሳይ ባለድርሻ አካላት ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እርዳታ በማቅረብ አገልግሎታቸውን የመስጠት
መብት እንዳላቸው ይደነግጋል ይህም ድጋፍ የሀገሪቷ የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ እንደመግባት ሊቆጠር
እንደማይገባ እና በቅን ልቦና ሊታይ እንደሚገባ በመደንገግ ፈቃደኝነት በዘፈቀደ ሊነፈግ እንደማይገባ በዋናነት
የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አስፈላጊ የሆነውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ሳየችሉ ወይም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ሲቀሩ
ፈቃድ ሊከለከል እንደማይገባ ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪም የካምፓላ ስምምነት በአንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 3 ላይ አባል
ሀገራት በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የአፍሪካ ህብረትን እና የተባበሩት መንግስታትን
ሀላፊነት እንዲሁም የዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶችን ጥበቃ እና ድጋፍ የማድረግ ሀላፊነት እንዲያከብሩ ይደነግጋል፡፡

ከምርጫ ጋር ተያይዞ ያሉ ድንጋጌዎች


መንግስት የዜጎችን ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የማስከበር፣ የማክበር እና የማሟላት ግዴታ አለበት፡፡ ሰብዓዊ መብቶችን
ማክበር ሲባል መንግስት ከዜጎች ጋር በሚኖረው ማንኛውም አይነት ግንኙነት የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች ከመጣስ መቆጠብ ማለት
ሲሆን በተለያዩ ተቋማቱ፣ በጸጥታ ሃይሎች፣ በመንግስት ባለስልጣናት እና መንግስት ፋይናንስ በሚያደርጋቸው አካላት አማካኝነት
የመብት ጥሰቶችን አለማድረስን ያጠቃልላል። በአንጻሩ የሰብዓዊ መብቶችን ማስከበር ሲባል ዜጎች እርስ በእርስ በሚኖራቸው
የጎንዮሽ ግንኙነት ሳቢያ የሰብዓዊ መብቶችን የሚጥሱ ተግባራት ከመፈጸም የመከላከል እና ተፈጽመውም ሲገኙ ተገቢውን ህጋዊ
እርምጃ የመውሰድ ሀላፊነት ነው። ከዚህ መርህ ውጪ በተለያዩ ክልሎች እና ዞኖች የመብት ጥሰት ተስትውለዋል፡

በ2013 የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ለመምረጥ የተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 እና
መስከረም 20 ቀን 2014 ተጠናቁዋል። በእነዚያ ቀናትም የክልል ምርጫዎች ተካሂደዋል። ምርጫው መጀመሪያ ላይ ለነሃሴ 23
2012 ታቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቷል። የክልል እና የማዘጋጃ ቤት ምርጫም በተመሳሳይ ጊዜ
እንዲካሄድ ታቅዶ ነበር። በግንቦት ወር 2012 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫው እስከ 2013 እንዲራዘም ድምጽ ሰጥቷል።
በታህሳስ 2012 መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ ሰኔ 21 ቀን ድረስ ከመዘግየቱ በፊት ምርጫው ሰኔ 5 ቀን
2013 ይካሄዳል ብሏል።

6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሀገራችን ከተከናወኑት ምርጫዎች ልዩ ነው የተባለለት ምርጫ ቢሆንም የአንድ ምርጫ ውጤት በህዝብ
እና በባለድርሻ አካላት ቅቡልነት የሚያገኘው የምርጫው ሂደት ሰላማዊ፣ ዴሞክራስያዊ፣ ነጻና ሚዛናዊ ከሆነ ተቀባይነቱ አሻሚነት
የሌለው ጉዳይ ነው። በዋነኝነት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን ማክበር የምርጫ ዋንኛ ተግባር ነው። ለዚህም የፖለቲካውን አውድ
በህግ አጥር ውስጥ ሆኖ ማስፋት ለምርጫው ዴሞክራሲያዊነት ዋንኛ መገለጫ ነው። የፖለቲካውን አውድ ከማስፋት አንጻር
የተቋማት፣ የሃብት እና የሚዲያ አጠቃቀም አጠቃላይ ፍትሃዊነት መሰረታዊ ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን። በምርጫው ሂደት እነዚህ
መሰረታዊ ጉዳዮች በበዙ ስፍራዎች ተጥሰው ነበር። በምርጫው ሂደት የተለያዩ መብቶች የተጣሱ ሲሆን ህገወጥ እስራት፣ የምርጫ
ጫና፣ ግድያ፣ የንብረት ውድመት እና የስነ-ልቦና ጉዳት ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህን ጥሰቶች ከአለም አቀፍ እና ከአህጉራዊ
ህጎች አንፃር እንደሚከተለው አቅርበናል።

የአፍሪካ የሰዎች እና ህዝቦች መብት ቻርተር

በተለይ ለልማት መብት ልዩ ትኩረት መስጠትና የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ከኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ መብቶች

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 59
በፅንሰ-ሀሳብ እንዲሁም ከዓለም አቀፋዊነት ሊነጠሉ እንደማይችሉ እና ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ መብቶችን መከበር
ማረጋገጥ ለሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች መጠቀሚያ ዋስትና እንደሆነ ይታመናል። ይህ ቻርተር እንደሚያረጋግጠው ማንኛውም
ግለሰብ እንደ ዘር፣ ብሄረሰብ፣ ቀለም፣ ጾታ፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ፖለቲካዊ ወይም ሌላ አስተያየት ሳይለይ አሁን ባለው ቻርተር
ውስጥ የተረጋገጡ መብቶችና ነጻነቶች ሊያገኙ ይችላሉ። በተጨማሪም ማንኛውም ግለሰብ በሰው ልጅ ውስጥ ያለውን ክብር
የማግኘትና ህጋዊነቱን የማወቅ መብት አለው። የሰው ልጅን በተለይም ማሰቃየት፣ ጨካኝ፣ ኢ-ሰብአዊ ወይም አዋራጅ የሆነ ቅጣትና
አያያዝ ማንኛውንም አይነት ብዝበዛና ማዋረድ የተከለከለ ነው። ህገወጥ እስራት የሰውን ልጅ ነጻነት የሚገድብ መሆኑ ይታወቃል
ይህም ቻርተሩ የመብት ጥሰት እንደሚከተለው ይደነግጋል፡፡

 እውቅና እና ዋስትና የተሰጠው መሰረታዊ መብቱን የሚጥሱ ተግባራትን በመቃወም ስልጣን ላላቸው ብሄራዊ አካላት
ይግባኝ የመጠየቅ መብት፡፡
 ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ወይም ልዩ ፍርድ ቤት ጥፋተኝነቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ እንደ ንፁህ ሆኖ የመገመት መብት፡፡
 በመረጠው ጠበቃ የመከላከል መብትን ጨምሮ የመከላከል መብት፡፡
 በገለልተኛ ፍርድ ቤት ወይም በልዩ ፍርድ ቤት ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ፍርድ የማግኝት መብት።
ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በነጻነት የመሰብሰብ መብት አለው። የዚህ መብት በህግ በተደነገገው አስፈላጊ እገዳዎች
በተለይም ለሀገር ደህንነት ሲባል በሚወጡት ህጎችን ባልጣሰ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ይህ ቻርተር የሁሉም የፖለቲካዊ ተሳትፎ
ያረጋግጣል ማንኛውም ዜጋ በህግ በተደነገገው መሰረት በቀጥታም ሆነ በነጻነት በተመረጡ ተወካዮቹ አማካይነት በአገሩ መንግስት
ውስጥ በነፃነት የመሳተፍ መብት አለው። ሰዎች ሁሉ የመኖር መብት አላቸው። የራስን ዕድል በራስ የመወሰን የማያጠያይቅ እና
የማይገሰስ መብት አላቸው። የፖለቲካ ሁኔታቸውን በነጻነት በመወሰን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገታቸውን በነፃነት በመረጡት
ፖሊሲ መሰረት በዚህ ቻርተር የተጠቀሱ መብቶች ናቸው፡፡
ሁሉም ሰዎች የግል ሀብታቸውን እና የተፈጥሮ ሀብታቸውን በነጻነት የመጠቀም መብት አላቸው፡፡ ይህ መብት የሕዝቡን ልዩ ጥቅም
ባስጠበቀ መልኩ ይከወናል፡፡ ይህን መብታቸውን የተነጠቁ ሰዎች ንብረታቸውን በህጋዊ መንገድ የመመለስ እና በቂ ካሳ የማግኘት
መብት አላቸው።
የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን
ሰብዓዊ መብቶችን የግለሰቦችን እና የአገሮችን ህይወት በብቃት የሚቀርጽ መሳሪያ ለማድረግ ከፖለቲካዊ አዋጅ ያለፈ ድርጊት
ያስፈልጋል። ስለዚህም ገና ከጅምሩ የሰብዓዊ መብቶች ዓቀፍ መግለጫ ፍሬ ነገር ወደ ከባድ ሕጋዊ ወደ ዓለም አቀፍ ስምምነት
መተርጎም እንዳለበት አጠቃላይ ስምምነት ነበር። ጠቅላላ ጉባኤው ቀደም ሲል በአለም አቀፍ መግለጫ፣ ባህላዊ የሲቪል እና
የፖለቲካ መብቶች ከኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ጋር መሟላት አስፈላጊ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል፡፡

ሁሉም ህዝቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት አላቸው። በመብታቸውም የፖለቲካ ሁኔታቸውን በነጻነት በመወሰን
ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ እድገታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው። ይህ መብት
በሕግ የተጠበቀ ሲሆን ማንም ሰው በዘፈቀደ ህይወቱን አይነጠቅም ማንም ሰው ማሰቃየት ወይም ጨካኝ፣ ኢሰብአዊ ወይም
አዋራጅ አያያዝ ወይም ቅጣት እንዳይደርስ ይደነግጋል። ማንኛውም ሰው የሰውን ነፃነትና ደህንነት የማግኘት መብት አለው፤ ማንም
ሰው በዘፈቀደ ሊታሰር ወይም መታሰር አይችልም፤ ማንም ሰው በህግ በተደነገገው መሰረት ካልሆነ በቀር ነፃነቱን አይገፈፍም።
በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ መብቱ መከበር ያለበት ሲሆን በህግ ከተደነገገው እና በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ውስጥ ለሀገር
ደህንነት ወይም ለህዝብ ደህንነት ፣ ህዝባዊ ስርዓት ፣ የህዝብ ጤና ጥበቃን ለመጠበቅ አስፈላጊ ከሆኑ መብቶች ውጭ በዚህ መብት
አጠቃቀም ላይ ምንም ገደቦች ሊደረጉ አይችልም ፡፡ ይሁንና እነዚህን ድንጋጌዎች በ6ኛው ምርጫ በተለያዩ ስፍራዎች መጣሳቸውን
ታዝበናል፡፡

የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ

የምርጫ ሥርዓት
በፌደራል ህገ መንግሥት መሠረት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚደረግ ምርጫ በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ ከሚወዳደሩት
ዕጩዎች መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘው አሸናፊ ይሆናል። በክልል ህግጋተ መንግሥት መሠረት ለክልል ምክር ቤቶች
የሚመረጡት ተወካዮች ከአንድ በላይ ሲሆኑ ከተወዳዳሪዎቹ መካከል በቅደም ተከተል አብላጫ ድምጽ ያገኙ ዕጩዎች አሸናፊ
ይሆናሉ፡፡ የክልል ምክር ቤት አባላት ምርጫን የሚመለከቱ የክልል ህጎች በህገ መንግሥቱና በዚህ አዋጅ ከተቀመጡ ምርጫን

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 60
የተመለከቱ ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣሙ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

የምርጫ መርሆዎች
ማንኛውም ምርጫ ሁሉን አቀፍ፣ ቀጥተኛ፣ በምስጢር ድምፅ አሰጣጥ መራጩ ፈቃዱን በነፃነት የሚገልጽበት እና ያለ ምንም ልዩነት
በሚደረግ ህዝባዊ ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡ የመምረጥ ወይም የመመረጥ መብቱ በህግ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ
ያልተገደበ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ መምረጥ ወይም መመረጥ ይችላል፤ ሆኖም ለመምረጥም ሆነ ለመመረጥ አይገደድም፡፡
እያንዳንዱ መራጭ የሚሰጠው ድምፅ እኩል ነው፡፡ እያንዳንዱ መራጭ ድምጽ መስጠት የሚችለው በአካል በመገኘት ነው፡፡

በአንቀጽ 16 የምርጫ ጣቢያዎች የሚከተለው ሀላፊነት ቢሰጣቸውም ግዴታቸውን እንዳልተወጡ ከላይ ባስቀመጥነው መግልጫ
ለመታዘብ ችለናል፡፡
 መራጮችን ይመዘግባል፤
 ከምርጫ ክልሉ የሚላኩ የምርጫ ቁሳቁሶችን ተቀብሎ በጥንቃቄ ይይዛል፤
 በዚህ አዋጅ መሠረት ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ምርጫ ያካሂዳል፣
 በህጉ መሠረት የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች ያስተናግዳል፣
 የተሰጠውን የድምፅ ቆጠራ በማካሄድ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በመለጠፍ ለህዝብ ያሳውቃል፣
 የምርጫ ሰነዶችና ቁሳቁሶች በአግባቡ ተሞልተው እና ተጠብቀው ለምርጫ ክልሉ እንዲላኩ ያደርጋል፣
 በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፭ (፲) እና ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የምርጫ ጣቢያውን አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሁለት
አባላት ያስመርጣል፣
 በምርጫ ሂደት ለሚከሰቱ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ፈጣን ምላሽ ይሰጣል፤ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣
 ከቦርዱ፣ ከክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ወይም ከምርጫ ክልል የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
በምርጫ ስለሚወዳደሩ የመንግሥት ሰራተኞች
ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ:-
 በግሉ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ አባል በመሆን ለምርጫ መወዳደር ይችላል፡፡
 የመንግሥት ሰራተኛ በህዝብ ምርጫ ለመወዳደር ተወዳዳሪ ሆኖ ሲቀርብ የምርጫ ቅስቀሳ በሚካሄድበት ወቅት እና
ምርጫው በሚከናወንበት ጊዜ ያለደመወዝ ፈቃድ እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡ የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ እንደዚህ
ቢደነግግም መሬት ላይ ያለው ተግባር ግን ከዚህ የተለየ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በተላያዩ ቦታዎች የተፎካካሪ ፓርቲ እጩዎች
ከስራቸው የመፈናቀል እና ሌሎች ተመሳሳይ ጫና ደርሶባቸዋል፡፡
የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ስለማካሄድ
አንድ እጩ ተወዳዳሪ በእጩነት ተመዝግቦ የመታወቂያ ካርድ ካገኘበት ቀን አንስቶ ምርጫው አራት ቀን እስኪቀረው ድረስ
ከአስተዳደሩም ሆነ ከማዘጋጃ ቤት ፈቃድ መጠየቅ ሳያስፈልገው፥ በጽሑፍ በማሳወቅ ብቻ እና ሕጋዊ ግዴታዎቹን በማክበር
በራሱም ሆነ በደጋፊዎቹ አማካኝነት የድጋፍ ስብሰባዎችን የመጥራት ወይም ሰላማዊ ሰልፍ የማደራጀት መብት አለው፡፡ እንዲሁም
ለምርጫ ውድድሩ ይጠቅሙኛል ያላቸውን መረጃዎች ከቦርዱ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ እጩዎችና ደጋፊዎቻቸው ቦርዱ
በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚያካሂዱት የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ ድምጽ መስጠት ከመጀመሩ ከአራት ቀናት በፊት
መጠናቀቅ አለበት፡፡ የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ ህገ መንግሥቱንና አግባብነት ያላቸውን ሌሎች ህጎች፣ የመራጮችን መብት፣
የሌሎች እጩዎችን የመወዳደር መብት በማክበር በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ መንገድ መካሄድ አለበት፡፡
የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ የተከለከለባቸው ቦታዎች
በሚከተሉት ቦታዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ወይም ዘመቻ ማድረግ የተከለከለ ነው:-

 ቤተ ክርስትያኖች፤ መስጊዶች፣
 ወታደራዊ ካምፖች እና ፖሊስ ጣቢያዎች፤
 የመማር ማስተማር ሂደት ተግባር እየተከናወነ በሚገኝበት ወቅት በትምህርት ቤቶች እና በትምህርት ቤቶች አካባቢ በ2
መቶ ሜትር ርቀት ዙሪያ፤
 ህዝብ የዕለት ተዕለት ግብይት በሚፈፅምባቸው እና በተወሰኑ ቀናት በገጠርም ሆነ በከተማ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 61
በይፋ ገበያ እየተካሄደ በሚገኝባቸው ቦታዎች በ2 መቶ ሜትር ዙሪያ ክልል፤
 የመንግሥት ወይም የህዝብ መደበኛ ሥራ በመከናወን ላይ የሚገኙባቸው የመንግሥትና የህዝብ ተቋማት ሥራቸውን
በሚያከናውኑበት መደበኛ የሥራ ሰዓት እና ቦታ፣
 ሌላ ህዝባዊ ስብሰባ እየተካሄደ ባለባቸው ቦታዎች እና አካባቢዎች፡፡

ይህን ክልከላ በመተላለፍ የገዢው ፓርቲ አባላት በአንዳንድ ቦታዎች በሃይማኖት ክብረ በዓል ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ አልፎም
የተፎካካሪ ፓርቲዎችን ስም እስከማጥፋት የደርሰ ጫና ሲያረጉ ታይቷል ፡፡

ክፍል ሦስት

ማጠቃለያና ምክረ-ሀሳብ
ይህ መደበኛ መግለጫ በ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ጊዜ የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ከኢትዮጲያ ምርጫ ቦርድ ባገኘው
የታዛቢነት ፍቃድ መሰረት 650 የምርጫ ታዛቢዎችን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በማሰማራት የተመለከታቸውን የሰብዓዊ
መብት ጥሰቶችን ያካተት ነው፡፡ ይህን የመብት ጥሰት የፈፀሙት አንድም የመንግሰት አካላት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ
በምርጫ ቦርድ አሰፈፃሚዎች በስህተት አልፎም ሆን ተበሎ የተፈፀሙ ጥፋቶች ናቸው፡፡ ምርጫው በተካሄደባቸው አካባቢዎች
ላይ ኢሰመጉ ባሰማራቸው ታዛቢዎች በጥቅሉ ከተሰበሰቡ መረጃዎች እና በሚዲያ ክትትል ክፍሉ የተገኙ መረጃዎችን መሰረት
በማድረግ ነው፡፡3

የተገኙትንም መረጃዎች በቦታው ድረስ ባላሙያዎቹን በማሰማራት እውን የተባሉት ጥሰቶች ተፈፅመዋል ወይስ
አልተፈጸሙም፤ ከተፈፀሙስ ለጥፋቶቹ ሃላፊነት መውሰድ የሚገባው ማን ነው የሚለውን ሲያጣራ ቆይቷል፡፡ እናም ባገኘው
መረጃ መሰረትም አብዛኛዎቹ መረጃዎች ትክክል እና እውነት መሆናቸውን አረጋግጡዋል ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ይህ መገለጫ በደቡብ ክልል ማንነትን ምክንያት በማድረግ በኩስሜ ማህበረሰብ ላይ የደረሰውንም ጥፋት
ተመልክቷል እናም በህገወጥ መንገድ የታሰሩ በአፋጣኝ እንዲፈቱ ወይም ለህግ እንዲቀርቡ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም
በአፋጣኝ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ኢሰመጉ ይጠይቃል፡፡

ሌላው በምርመራ የተገኘው ደግሞ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዙሪያ ጋጮ ባባ ወረዳ ኩይሌ ቀበሌ አስተዳዳሪ
በነበሩት ግለሰብ ተፈጽሟል የተባለው የመብት ጥሰት ነው፡፡ ኢሰመጉም አቤቱታው ትክክል መሆኑን በምርመራው ማረጋገጥ
ቸሏል፡፡ ስለሆነም የህግ አስፈፃሚው ተገቢውን ማጣራት አደርጎ ጥፋተኞችን ለህግ እንዲያቀርብ ያሳስባል፡፡

በተጨማሪም በሲዳማ ክልል ውስጥ የሚገኘው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል እና የሲደማ ክልል በጋራ
የሚጠቀሙበት ለፖሊስ ኮሌጅ ማስፋፊያ ከ179 ገበሬዎች የተወሰደው መሬትን ይህ መግለጫ ይመለከታል ይህ መሬት
በ1998 ነበር ለማስፋፊያ ተብሎ የተወሰደው ነገር ግን እስካሁን ድረስ ሙሉ የካሳ ክፍያ ለባለንብረቶቹ አልተከፈላቸውም
ይህንንም ኢሰመጉ አጥብቆ እየተቃወመ አሰራሮችን በፍጥነት በማረም ተገቢውን ማስተካከያ እንዲደርግ እና ለገበሬዎች
ተገቢው ካሳ እንዲሰጥ ኢሰመጉ ያሳስባል::

በዚህ መደበኛ መግለጫ ላይ የተካተቱ የመብት ጥሰቶችን አስመልክቶ የ6ተኛ ሀገር አቀፍ ምርጫን ተከትሎ ለተፈጸሙ የሰብዓዊ
መብት ጥሰቶች፣ በአንዳንድ አካባቢዎች በመንግስት አመራሮች የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች፣ የመዋቅር ጥያቄን ተከትሎ
ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ከቦታቸው የተፈናቀሉ ገበሬዎችን በሚመለከት ኢሰመጉ ምክረሃሳቦችን በቅደም
ተከተል እንደመሚከተለው አቅርቧል፡፡

 ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሒደቱ እንዲያስፈፅሙለት በተገቢው ሕጋዊ መንገድ ካሰማራቸው የምርጫ አስፈፃሚዎች
ውጪ ሒደቱን በማስተጓጎልም ሆነ ድጋፍ በመስጠት ተሳትፎ የሚደርጉ አካላትን ማስቀረት የሚያስችል የምርጫ
አሠራር ሂደት እንዲዘረጋና ተሳትፈው ሲገኙም ፈጣን እርምት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል አደረጃጀት
እንዲፈጥር፣
3
ለበለጠ መረጃ ኢሰመጉ በጥቅምት 2014 ዓ.ም ያሳተመውን የኢሰመጉ የምርጫ ትዝብት ግኝት ቀዳሚ ዘገባን ይመልከቱ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 62
 ምርጫ ቦርድ የምርጫ አስፈፃሚዎች ምርጫን የማስፈፀም ብቃታችውን እና ገለልተኝነታቸውን የሚጨምሩ ሰፊ
ስልጠናዎች እንዲሰጥ፣
 ባለፈው ምርጫ የተስተዋሉ ስህተቶችን ለምሳሌ እንደ አሰልቺና ረጃጅም ሰልፎች፣ እድሜው ያልደረሰ ሰው
እንዲመርጥ መፍቀድ ፣ ለአንድ ፖለቲካ ቡድን መወገን ለቀጣይ ምርጫ እንዳይደገሙ መስራት
 የተፎካካሪ ፓርቲዎች አባል እና ደጋፊ ስለሆኑ ብቻ የታሰሩ ሰዎችን በፍጥነት እንዲፈቱ ማድረግ፣
 በፖለቲካ እና ምርጫ ምክንያት ንብረታቸው የወደመባቸውን ሰዎች በፍጥነት ካሳ እንዲከፈላችው መስራት
ከቤታቸው የተፈናቀሉትንም በፍጥነት የማቋቋም ስራ እንዲሰራ፣
 ኢሰመጉ በደረሱት አቤቱታዎች መሰረት ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ቁጥር ER3-M36/17/22 በቀን
በ20/08/2014 ዓ.ም እንዲሁም ለብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት በደብዳቤ ቁጥር ER3-M41/14/22 በቀን
20/08/2014 ዓ.ም ደብዳቤዎችን ያስገባ ቢሆንም የብልጽግና ፓርቲ በምርጫው የተሸነፈባቸውን አካባቢዎችና
አሁን ያለበትን ሁኔታ እንዲሁም ለጉዳዩ መፈጸም ምክንያት የሆኑ ነገሮችን ሁለቱም ቢሮዎች ይህ መግለጫ
እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ምላሽ ያልሰጡ ሲሆን፣ የብልጽግና ፓርቲ በ6ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ በተሸነፈባቸው
ቦታዎች በፍጥነት ላሸነፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እርክክብ እንዲደረግ፣
 መንግስት በምርጫው ምክንያት የተፈጠረውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ተገንዝቦ ጥፋቶቹን የፈፀሙትን በሙሉ በህግ
ፊት ተጠያቂ ማድረግ፣
 ምርጫውን ተከትሎ የአካል ጉዳት የደረሰባችውና የተደበደቡ ሰዎች አስፈላጊውን የህክምና እርዳታ እንዲገኙ መርዳት
በመንግስት በኩል ማቅረብ
 በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዙሪያ ጋጮ ባባ ወረደ ኩይሌ ቀበሌ አስተዳዳሪ በነበሩት ግለሰብ ተፈጽመዋል
የተባሉ የመብት ጥሰቶች ላይ በአግባቡ ማጣራት ተደርጎ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣
 በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዙሪያ ጋጮ ባባ ወረደ ኩይሌ ቀበሌ ለዘመናት በጋራ ከብቶቻቸውን
የሚያሰማሩበት በ2012 ዓ.ም በህገወጥ መንገድ የተሸጠው የግጦሽ መሬት ላይ ተገቢው ማጣራት እንዲደረግ እና
ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንዲሁም በድጋሚ ተሸጠ የተባለው 18 ሄክታር የውል መሬት ላይም ተመሳሳይ ማጣረት
ተደርጎ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣
 በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ማንነትን ምክንያት በማድረግ በኩስሜ ማህበረሰብ ላይ የደረሰው
ጥቃት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ላይ ተገበው ማጣራት እንዲደረግ እና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣
 በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ማንነትን ምክንያት በማድረግ በኩስሜ ማህበረሰብ ላይ እየደረሰ
ያለው ጥቃት በአፋጣኝ እንዲቆም፣
 በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በኩስሜ ማህበረሰብ የቀረበው አስተዳደራዊ መዋቅር እና
የመማንነት ጥያቄ በህግ አግባብ ታይቶ ተገቢ እና ህገዊ ምላሽ የሚመለከተው የመንግስት አካል እንዲሰጥ፣
 ተፈናቅለው የሚገኙ የኩስሜ ማህበረሰብ አባላት ተገቢው ድጋፍ እንዲሰጣቸው እና ይኖሩባት የነበረው በደቡብ
ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ውስጥ የምትገኘው የጋቶ ቀበሌ በነበረው ግጭት ምክንያት በደራሼ ልዩ ወረዳ
አመራሮች በተደገፉ ቡድኖች በመፈራረሷ አካባቢውን መልሶ የማቋቋም ስራ እንዲሰራ፣ ተፈናቀዮች ደህንነታቸው
ተጠብቆ እና የተነጠቁት ንብረታቸው ተመልሶ ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ የደቡብ ከልል መንግስት
በአስቸኳይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ
 በሲዳማ ክልል ውስጥ በሚገኘው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል እና የሲደማ ክልል በጋራ
የሚጠቀሙበት ለፖሊስ ኮሌጅ ማስፋፊያ ተብሎ ከ179 ገበሬዎች ለተወሰደው መሬት ሁለቱም የሚመለከታቸው
ክልሎች በጉዳዩ ዙሪያ በመነጋገር እና ስምምት በማድረግ ለተነሱት ገበሬዎች ቀሪው የካሳ ክፍያን እንዲፈጽመ፣
 በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ አልጌ ቀበሌ እና አጎራባች ቀበሌዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚስተዋሉትን ማንነትን
መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች የሚመለከተው የመንግስት አካል ተገቢውን መፍትሄ እንዲሰጥ፣
 በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ አልጌ ቀበሌ በሚገኝ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ውስጥ በመጋቢት 8/2014 ዓ.ም
ለተፈጸመው ጥቃት መንግስት ይህንን ጥቃት ባደረሱ አካላት ላይ ማጣራትን በማድረግ ለህግ እንዲያቀርብ፣
 በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ አልጌ ቀበሌ እና አጎራባች ቀበሌዎች ማንነትን መሰረት በማድረግ የሚደርሱ
ጥቃቶችን ተከትሎ በርካቶች የተፈናቀሉ ሲሆን መንግስት ለነዚህ ተፈናቃዮች በቂ ትኩረት በመስጠት ሰብዓዊ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 63
ድጋፎችን እንዲያቀርብ እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥ፣ በተጨማሪም በአካባቢው መሰል ጉዳት እንዳይደርስ ዘላቂ
መፍትሄ እንዲያበጅ፣
 መንግስት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሶጌ እና ያሶ ወረዳ ለተፈናቀሉ ተፈናቃዮች ዘላቂ የሆነ መፍትሄን
በአስቸኳይ እንዲያበጅ እንዲሁም ለተፈናቃዮች በቂ የሆነ ሁሉንም ያማከለ ሰብዓዊ ድጋፍ በአፋጣኝ እንዲያቀርብ
እና የድጋፍ እጥረት በሚኖር ሰዓት መንግስት ለዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እንዲሁም ሀገር በቀል ለሆኑ ረጂ
ተቋማት ድጋፍ እንዲሰጡ ምቹ ሁኔታን እንዲፈጥር፣
 መንግስት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሶጌ እና ያሶ ወረዳ ለተፈናቀሉ ተፈናቃዮች እየገቡ ያሉ እርዳታዎች
በተገቢው መንገድ ለተጎጂዎች እንዲደርስ እንዲያደርግ፣
 መንግስት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለበርካታ ጊዜያት የመፈናቀል ምክንያት እየሆነ ያለውን ታጥቆ የሚንቀሳቀሰወን
ቡድን ለህግ በማቅረብ የአካባቢውን ዘላቂ ሰላም እንዲመልስ እንዲሁም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሶጌ
እና ያሶ ወረዳ በ2011 ዓ.ም እና በ2013 ዓ.ም በተነሱ ግጭቶች ውስጥ አና በተፈጸሙ በርካታ የሰብዓዊ መብቶች
ጥሰቶች ውስጥ እጃቸው ያለበትን አካላት በአፋጣኝ ለህግ በማቅረብ ተጠያቂ እንዲያደርግ፣
 መንግስት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሶጌ እና ያሶ ወረዳ በ2011 ዓ.ም እና በ2013 ዓ.ም የተነሱ
ግጭቶችን አስመልክቶ ቤት እና ንብረቶቻቸውን ለተነጠቁ ግለሰቦች በአፋጣኝ ቤቶቻቸውን እና ንብረቶቻቸውን
እንዲያስመልስ፣
 መንግስት በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ኢንጂነር ግርማ ጡሩና ደርሴ ያሉበትን እንዲያሳውቅ እና ኢንጂነር
ግርማ ጡሩና በፍርድ ቤት ባገኙት ውሳኔ መሰረት ነጻ እንዲለቅ፣ እንዲሁም በኢንጂነር ግርማ ጡሩና ላይ አስገድዶ
የመሰወር ስራን የሰሩ እና የተሳተፉ የመንግስት የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ እና ተጠያቂ እንዲሆኑ፣
 በዚህ መግለጫ ላይ ተካተው የሚገኙ እና በእስር ላይ ያሉ (የኦሮሚያ ነጻነት ግንባር ፓርቲ)የኦነግ አመራሮች እና
አባላትን መንግስት በአፋጣኝ ከእስር እንዲፈታ፣ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነጻ የተባሉትን ከህግ አግባብ ውጪ በተለያዩ
እስር ቤቶች ታስረው የሚገኙ የፓርቲውን አባላት እና አመረሮች መንግስት በህግ አግባብ ከእስር እንዲፈታ፣ በዚህ
ህገ ወጥ እስር ላይ ተሳትፎ ያላቸው አካላትንም እንዲሁ በህግ ተጠየቂ በማድረግ አስተማሪ ውሳኔን እንዲያሳልፍ፣
 የኦሮሚያ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባል በሆነው መለሰ ጫላ ግድያ ላይ የተሳተፉ የጸጥታ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ እና
መሰል ተግባራት በህገ አስከባሪዎች እንዳይፈጸሙ አስተማሪ የሆነ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣

በመጨረሻም ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የቆማችሁ ዜጎች፣ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተቋማትም መንግሥት የዜጎችን
ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲያከብር፣ እንዲያስከብርና እንዲያሟላ ከዚህ በታች በተገለጹት አድራሻዎች በመጻፍና
ስልክ በመደወል ጥያቄና ግፊት እንድታደርጉ ኢሰመጉ ይጠይቃል፡፡

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 64
 ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት

ፖ.ሳ.ቁጥር ፡- 80001፣ ኢ-ሜል፡- national.parliament@telecom.net.et

ፋክስ ፡- (+251) 011 155-0400፣የስልክ ቁጥር ፡- (+251) 011 124-1000፣

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር ፡- 20122/1000፣ ኢ-ሜል ፡- kumashih@gmail.com

ፋክስ ፡- (+251) 011 124-1208/011 124-2308፣

የስልክ ቁጥር ፡- (+251) 011 122-3322፣

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 23698፣ ፋክስ ፡- (+251) 011 551- 8656፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 011 551-8186፣

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት :-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡-1031፣ ፋክስ፡- (+251) 011 122-6292፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 011 124-1155፣

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር

ስልክ ቁጥር +251 115541868 ፋክስ +25115517775

ኢሜይል MOJMO@ETHIONET.ET

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሰላም ሚኒስቴር

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 5608፣ ኢ-ሜል፡- mofatr1@yahoo.com

ፋክስ፡-(+251)011 551-1200፣ የስልክ ቁጥር፡-(+251) 011 515-3204፣

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 65
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 2459፣ ኢ-ሜል፡ ombudsmaneth@ethionet.et

ፋክስ፡- (+251) 011 553-2073፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 011 543-336፣

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን:

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 1165፣ ኢ-ሜ፡ hrcom@ethionet.et፣

ፋክስ፡ (+251) 011 550-4125፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 011 550-4031፣

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ጽ/ቤት:

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 199፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 011 551-2744፣

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 ለሱማሌ ክልል ም/ቤት አፈ-ጉባዔጽ/ቤት:

ፖ.ሳ.ቁጥር 392፣ ፋክስ፡- (+251) 25 775-3429፣

የስልክ ቁጥር፡ (+251) 257 75 34 29

ጅግጅጋ፣ ኢትዮጵያ

 ለሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት:

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 588 ፋክስ፡- (+251) 025 775-2325፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 025 775-4038 / 025 775-3241 ጂግጂጋ፣ ኢትዮጵያ

 ለኦሮሚያ ክልል ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት:

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 101769፣ ኢ-ሜል፡- oromiawiev@ethionet.et

ፋክስ፡- (+251) 011 551-3642 / (+251) 011 551-9633፣

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 66
የስልክ ቁጥር፡- (+251) 011 552-4247፣

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 101769 ፋክስ፡- (+251) 011 552-4247

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 011 555-0455

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 ለአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 1324፣ ፋክስ፡- (+251) 058 220-2511፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 058 220-2659

ባሕርዳር፣ ኢትዮጵያ

 ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 312 ፋክስ፡- (+251) 058 220-1068፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 058 220-0924 / 058 220-0499

ባህር ዳር፣ ኢትዮጵያ

 ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

ፖ.ሳ.ቁጥር፡-

የስልክ ቁጥር፡-

ቦንጋ፣ ኢትዮጵያ

 ለሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዘዳነት ጽ/ቤት

ኢ-ሜይል አድራሻ፡-sidaamapoffice@gmail.com

የስልክ ቁጥር፡-

ሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ

 ለደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 1546፣ ፋክስ፡- (+251) 046 220-2408፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 046 221-4778/ 046 220-5848፣ ሐዋሳ፣ ኢትዮጵያ

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 67
 ለደ/ብ/ብ/ህ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 18 ፋክስ፡- (+251) 046 220-1641፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 046 220-9166

ሃዋሳ፣ ኢትዮጵያ

 ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 44፣ ፋክስ፡- (+251) 057 775-0814፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 055 7775-0109፣

አሶሳ፣ ኢትዮጵያ

 ለትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 291፣

ፋክስ፡- (+251) 034 441-6564፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 034 441-6563፣

መቀሌ፣ ኢትዮጵያ

 ለጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 25፣ ፋክስ:- (+251) 046 220-2408፣

ጋምቤላ፣ ጋምቤላ

 ለጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 025

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 047 551-154

ጋምቤላ፣ ኢትዮጵያ

 ለሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት:-

ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 952 ፋክስ፡- (+251) 025 666-2530፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 025 666-1723 / 025 666-1746

ሐረር፣ ኢትዮጵያ

 ለሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት:-

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 68
ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 272 ፋክስ፡- (+251) 025 666-0666፣

የስልክ ቁጥር፡- (+251) 025 666-1799

ሐረር፣ ኢትዮጵያ

 ለአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር (+251) 0336660056

ሰመራ ኢትዮጵያ

 ለድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር የከንቲባ ጽ/ቤት

የስልክ ቁጥር፡ (+251) 025 11 11 358

ፋክስ፡ (+251) 025 11 19 805

 ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የከንቲባ ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር (+251) 0118591363

የኢሰመጉ 39ኛ መደበኛ መግለጫ-በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች/ www.ehrco.org 69

You might also like