You are on page 1of 34

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ

ርዕስ፡ ከጀግንነት እስከ ሰ፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተጋድሎ ለህብረ- ብሔራዊ አንድነት
እና ሉአላዊት ኢትዮጵያ!

ጥር 2014

አዲስ አበበ
የጥናቱ ይዘት፡
ምዕራፍአንድ፡.................................................................................................................................................1

1.1. መግቢያ፡........................................................................................................................................1

1.2. የጥናቱ ዋና አመክንዮ፡......................................................................................................................3

1.3. የጥናቱ አላማ፡................................................................................................................................4

1.3.1. የጥናቱ ዋና አላማ፡...................................................................................................................4

1.3.2. የጥናቱ ዝርዝር አላማዎች፡.......................................................................................................5

1.4. የጥናቱ አስፈላጊነት፡........................................................................................................................5

1.5. የጥናቱ ወሰን፡................................................................................................................................5


ምዕራፍ ሁለት፡.................................................................................................................................................6
2. የጥናቱ ማከናወኛ ዘዴዎች፡...............................................................................................................................6
2.1. መግቢያ፡.............................................................................................................................................6
2.2. ጥናቱ የሚጠናባቸው ቦታዎች፡....................................................................................................................6
2.3. የጥናቱ ሥነ-ዘዴ፡....................................................................................................................................7
2.4. የመረጃ ምንጮች፡...................................................................................................................................7
2.4.1. የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ምንጭ፡..........................................................................................................7
2.4.2. ሁለተኛ ደረጃ መረጃ ምንጮች፡............................................................................................................7
2.5. የናሙና አመራረጥ ዘዴ፡............................................................................................................................8
2.6. የጥናቱ አካላይ፡.......................................................................................................................................9
2.7. መረጃ የመሰብሰቢያ መንገዶች፡...................................................................................................................9
2.7.1. ቃለ-መጠይቅ፡.................................................................................................................................9
2.7.2. ቡድን ተኮር ውይይት፡.....................................................................................................................10
2.7.3. ምልከታ፡.....................................................................................................................................10
2.7.4. የሰነድና የመዛግብት ትንተና፡..............................................................................................................10
2.8. የመረጃ አሰባሰብ ቅደም-ተከተል ሂደት፡...................................................................................................10
2.9. የጥናቱ መረጃዎች ተዐማኒነት፡.............................................................................................................11
2.10. የመረጃ ትንተና ዘዴ፡........................................................................................................................11
2.11. ጥናቱ የሚከተላቸው ጥናታዊ ሥነ-ምግባር፡................................................................................................11
ዋቢ-መፅሐፍት፡..............................................................................................................................................13
አቫሪ 1፡ ቃለ መጠይቅ፡.....................................................................................................................................14

i|Page
አቫሪ 2፡ የጥናቱ ይዘት፡.....................................................................................................................................20
አባሪ III: የጥናቱ የጉዞ መስመሮች፤.......................................................................................................................23

ii | P a g e
ምዕራፍ አንድ፡
1.1. መግቢያ፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ 1988 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን
የማዕከላዊ ሽግግር መንግስት የፖሊስ መቋቋም አዋጅ ቁጥር 8/1984 በመሻር ሰኔ 20/1992 ዓ.ም
በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በወጣ ደንብ ኮሚሽኑ በመባል እንደሚጠራ በአዋጅ ቁጥር 207/1992
የተደነገገ መሆኑን የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ይገልጻል (የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ገጽ 1331 አንቀጽ 1)፡፡
በዚሁ ድንጋጌ የኮሚሽኑን አላማ ስልጣን እና ተግባር የሚገልጹ ዝርዘር አንቀፆች ተቀምጠዋል፡፡
በዋናነት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተቋቋመበት አላማ የሀገሪቱን ህገ-መንግስት እና ሌሎች ህጎችን
በማክበር የህዝቡን ተሳትፎ መሰረት በማድረግ ወንጀልን በመከላከል የህዝቡን ሰላማዊ ኑሮ እና ፀጥታ
ማስጠበቅ ነው፡፡

የተሻሻለው የአትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ ደንብ አዋጅ ቁጥር 7/2004 የኮሚሽኑን
ስልጣን እና ተግባር በተሻለ በማስፋት ህግ እና ስርአትን በማስፈን ሂደት ዉስጥ በመንግሰት ትእዛዝ
መሰረት በክልሎች ጣልቃ በመግባት ለደህንነት መረጋገጥ ሃላፊት እንዳለበትም ይደነግጋል (የፌደራል
ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 7/2004 አንቀፅ 6 ንኡስ አንቀጽ 12)፡፡ በዚህ ህጋዊ መሰረት ላይ በመመርኮዝ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ላለፉት 26 አመታት ለህዝብና መንግሰት የሰላም ዘብ በመሆን
አባላቱ ህይወታቸውን እና አካላቸውን በመገበር ሃገራዊ ለዉጡ በህዝብ ማእከላዊ ትግል እስከመጣበት
ጊዜ እና ከዚያም በኋላ ህግን በማስከበር ሂደት ውስጥ የአንበሳ ድርሻ እንደነበረው እሙን ነው፡፡

ይሁን እንጂ የፌደራል ፖሊስ የትህነግ ስርአት ሃገሪቷን በሚያሰተዳድርበት ወቅት ፖሊስ
ከማንኛውም የፖለቲካ አመለካከት እና የፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊነት ገለልተኛ ነው የሚለውን
የተቋቋመበትን አላማ ወደ ጎን በመተው ኮሚሽኑ የስርዓቱ አገልጋይ ከሚሆንም ባለፈ የስርአቱ ፈረስ
እና ጋሪ ጭምር በመሆን ወንጀልን በመከላከል በተለይም ሽብር እና ሽብርተኝነትን በመከላከል ስም
በሀገሪቱ ብሔራዊ ምርጫዎች በሚደረጉበት ወቅት የነበረዉን የህዝብ ተቃውሞ ለመቀልበስ በዜጎች
ላይ ኢሰ-ብአዊ ድርጊት መፈጸሙ አይዘነጋም፡፡

ለውጡ ከመጣበት 2010 ዓ.ም ጀምሮ እና መንግሰት እስከ ተመሰረተበት ጊዜ መስከረም


24/2013 ዓ.ም ወዲህ ተቋሙ በመንግስት አቅጣጫ ራሱን እንዲያሻሽል በታቀደው መሰረት የፌደራል
ፖሊስ ከፓርቲ አገልጋይነት መንፈስ እንዲላቀቅ ወገንተኝነቱ ለህዝብ መሆኑን እና በአሰተሳሰብ ደረጃም
የአገልጋይነት መንፈስ በመላበስ ወንጀልን በመከላከል እና በመመረመር ሂደት ውስጥ ከፍተኛውን ሚና
እየተጫወተ ይገኛል፡፡በዚህም የአገልጋይነት አሰተሳሰብ ከለውጡ ጊዜ አንስቶ የተለያዩ የህዝብ ህጋዊ

1|Page
ስብሰባዎችን፡ ተቋውሞዎችን እና ድጋፎችን በማሳለጥ እና ጥበቃ በማድረግ ሀገሪቷ የገጠማትን
የፖለቲካ ቀውስ በማረጋጋት ሚና ውስጥ አይተኬ የጀግና ተግባሩን አሳይቷል፡፡ አባላቱም ህይወታቸውን
በጀግንነት ገብረዋል፡፡ በተለይ ደግሞ ከትህነግ ከማዕከላዊ መንግስት እንደራሴነት ጠቅላይ ገዥነት እና
የፖሊቲካ ውሳኔ የበላይ ሰጭነት ተፍገምግሞ ከስልጣን ኮረቻ ጌትነት ከተፈናቀለ በኋላ ከመጣው
የህዝብ ለውጥ ጋር ራሱን ከማስማማት ይልቅ በተወጠረ እብሪተኝነት እና ማንአለብኝነት በህዝብ
የተነጠቀውን ስልጣን ከህዝብ መልሶ ለመንጠቅ ወደ ተወለደበት ዋሻ ለመመለስ ወደ ክልሉ ከተማ
መቀሌ ላይ ከከተመ ጊዜ አንስቶ ፌደራል ፖሊስ ለአትዮጵያ ህብረ-ብሔረዊ አንድነት እና ሉአላዊነት
ያሳየው ተጋድሎ መራር ነበር፡፡

የመቀሌን ከተማ ለጊዜው ዋሻ በማድረግ እብሪቱን ዕቅዱን እና የህዝቡን ለውጥ ለማደናቀፍ


የቀመረውን ሴራ በርዕዮተ-አለም ልዩነት ስም በራሱ ሚዲያዎች እና በአለም አቀፍ የዜና አውታሮች
ላይ በመደስኮር የፕሮፓጋንዳ ጦርነቱን በኢትዮጵያ እና በልጆቿ ላይ አለም አቀፍ ጫናን በመፍጠር
ጭምር የጦር ነጋሪቱን እየጎሰመ ሲያጓራ ከረመ፡፡ ይህንንም ሃሳቡን በምድር በሚዘገንን መልኩ ጥቅምት
24/2013 ዓ.ም ምሽት ላይ በሰሜን ዕዝ የሃገር መከላከያ ስራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ
ባልተጠበቀ ሁኔታ ጥቃት በመፈጸም በግልጽ የጦርነት ክብሪቱን ጫረው፡፡በዚህም ጥቃት በሺዎች
የሚቆጠሩ የመከላከያ አባላት ተሰውተው ጀኔራሎች እና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ታገቱ፡፡ የኢትዮጵያ
መንግስት በግለጽ የተፈጸመውን የሀገር ክህደት ድረጊት በማውገዝ ህግን ለማስከበር የፌደራል
መንግሰት ከትህነግ ጋር ወደ ጦርነት ገባ፡፡ ፌደራል መንግስት መቀሌን እስከ ተቆጣጠረበት ጊዜ ድረስ
የሀገር መከላከያ ሰራዊት፡የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ፖሊስ፣ ሚኒሻ እና ፋኖ እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ
የድሉ ምእራፍ በር ከፋቾች በመሆን ከከተማ ዋሻ ወደ እውነተኛ የቀበሮ ጉድጓድ የተሰገሰጉትን ፊት
አውራሪ የትህነግ መሪዎች እና ወንጀለኞችን ለቃቀሟቸው፡፡ የፌደራል መንግሰት ሰኔ 21/2013 ዓ.ም
ጦሩን ከትግራይ ክልል በማስወጣት እና የተናጠል ተኩስ አቁም በማድረግ ለትህነግ የጥሞና ጊዜ
መስጠቱን አሳወቀ፡፡ ነገር ግን ወያኔ ወደ ራሱ መመለስ ባለመቻሉ እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀል
በማለቱ አዋሳኝ ጎረቤቶቹን አማራ እና አፋር ክልሎችን በመውረር መጠነ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ
እና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ በመፍጠር የጦርነቱን መሰረት፣ አይነት እና ሂደት ወደ ውስብስብ የጉሬላ
ጦርነት ገፈተረው፡፡የህዝብ መሰረተ-ልማት ሃብቶች ወደሙ፣ህጻናት እና ሴቶች ተደፈሩ በንጹኃን ደም
ስቃይ እና እንግልት እየተረማመደ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እሰከ ጫፍ ተጓዘ፡፡ የልብ ልብ እየተሰማው
ከመቀሌ እሰከ ሰሜን ሸዋ ገንዘብና እሳት እያቀበለ 600 ኪሎ ሜትር አቋርጦ 150 ኪሎ ሜትር
ሲቀረው የጓጓለት ቤተ-መንግስት ነፍሱን ተጸይፋው በኢትዮጵያውያን ህብረ-ብሄራዊ ዘመቻ በጠቅላይ
ሚኒስትሩ የጦር መሪነት አራት ኪሎ ቅዥት ሆኖበት ከዱቄት በባሰ በንፋስ ሳሆን በአሞራ በአፈር

2|Page
ሳይሆን በጅብ እየተወሰደ እና እየተበላ በጀግና የመከላከያ አባላት እና የጸጥታ አካላት ጀብድ ህልሙ
ከሸፈበት፡፡

በዚህ ሀገራዊ ድል ውስጥ የፌደራል ፖሊስ ድርሻ ቀላል አልነበረም፡፡ ምክንያቱም የወያኔ የጦር ግንባር
በሰሜኑ አካባቢ ብቻ የተወሰነ አልነበረም፡፡ይልቁኑ ትህነግ ህዝብን በህዝብ ላይ በማነሳሳት የመንግሰትን ሃይል
በማዳከም ከሚመስሉትም ጋር ጉርብትና በመፍጠር በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል አካባቢዎች መረጋጋት እንዳይኖር
የዘረጋው የውስጥ ጦርነት ግቡን እንዳይመታ እና እንዲጨናገፍ የፌደራል ፖሊስ ሚና፣የአባላቱ ጀግንነት፣
ተጋድሎ እና መሰዋእትነት ሃገር ያቆመ ነገር ግን ያለተነገረለት ሃቅ ነው፡፡በአንጻሩ የጀግኖቹ ጀብድ ሊነገርላቸው
የሚገባ እና በታሪክ ማህደር ተሰንዶ ለትውልድ የኩራት ምንጭ ሆኖ መቀመጥ ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም
የዚህ የጥናት አላማም የተደበቀውን የፌደራል ፖሊስ ገድል ማውጣትና ለሃገር የዋለውን ውለታ ከትቦ በታሪክ
መዝገብ ማስቀመጥ ነው፡፡

1.2. የጥናቱ ዋና አመክንዮ፡


የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሀገሪቱ የፖሊቲካ አለመረጋጋት ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ የሰላም
መደፍረስ እና በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ፈረጀ ብዙ ቀውስ ህይወቱን እየገበረ ሲመክት የነበረ
ባለዉለታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ኮሚሽኑ የአባላቱን ጀብድ እና መሰዋእትነት በተቀመረ እና በተተነተነ
መልኩ ያስቀመጠበት ሁኔታ የለም፡፡ የአባላቱን እና የአመራሩን ታሪካዊ ጀግንነት ተይቦ አለማኖር እና
ጀግኖቹን አለመዘከር በታሪክ ላይ የሚሰራ ደባ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በርግጥ አለመታደል ሆኖ
ጀግኖቻችንን አናከበርም ምክንያቱም ጀግኖች የተሰዉት ለአንድ ቡድን ሳይሆን ለሃገር መሆኑን
እንዘነጋዋለን፡፡ የአንዱ ጀግና የሌላው ጨቋኝ እየሆነ የታሪክ ሰበዝ እየመዘዝን እንቋሰላን፡፡

ይሁን እነጂ ታረክን ከየትኛውም የፖለቲካ አላማ ነጻ በመሆን ለህሌና እና ለእውነት በመቆም
ትክክለኛውን መረጃ በማሰባበሰብ ለትውልድ ማሰተላለፍ ያስፈልጋል፡፡

በአንድ ወቅት ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም (2005) ታሪክን በወቅቱ እና በጊዜው ከትቦ
ማስተላለፍን በተመለከተ እና ታሪክ በትውለድ ውስጥ የሚቀባበል መስዋእትነት መሆኑን
እንደሚከተለው ገልጸውታል፤

‹‹
ታሪክ የህዝብ የተከታታይ ትውልዶች ስራ ነው…የኋለኛው ትውልድ ባለፉት ትውልዶች
መስዋእትነት በተጣለው መሰረት ላይ የተሻለ፣ የጠነከረ እና የበለጸገ ማሕበረ-ሰብ ለማነጽ
የሚያደርጉትን ጥረት ካለፈው ጋር የሚያሰተያይ መዝገብ ነው፡፡ስለዚህም የኋኛው ትውልድ ለቀድሞው
ትውልድ ያለበት እዳ ወይም ውለታ ነው፡፡ታሪክ ያለፉትን ተከታታይ ትውልዶች ከዛሬውና ከወደፊት
ትውልዶች ጋር የሚያገናኝ፣የሚያስተሳስር እና የሚያሰተዋውቅ ሰንሰለት ነው፡፡የዛሬው ትውልድ

3|Page
የትናንትናው ትውልድ የስራ ውጤት ነው፤ የነገው ትውልድ ደግሞ የዛሬው ትውልድ የስራ ውጤት
ነው፤ ያለፉት ትውልዶች እና የወደፊቱ ትውልድ የሚገናኑት በዛሬው ትውልድ ላይ ነው፡፡››

በመሆኑም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጀግንነት እና መስዋእትነት ሰንዶ በማስቀመጥ


የከፈለውን ውለታ ለዛሬው እና ለመጪው ትውልድ በማሰቀመጥ ጀግኖቹን በማሰታወስ እና ክብር
በመስጠት ብሄራዊ የጀግኖች ማህደር በማዘጋጀት ለልጆቻቸውና ለዘመዶቻቸው፤ ለኢትዮጵያውያን
በሙሉ የኩራት ምንጭ መሆናቸውን ለትውልድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል፡፡

1.3. የጥናቱ አላማ፡

1.3.1. የጥናቱ ዋና አላማ፡


የዚህ ጥናት አላማ ከጀግንነት እስከ መስዋእትነት፤ የኢትዮጵያ ፌደረል ፖሊስ ተጋድሎ ለህብረ-ብሔራዊ
አነድነት እና ለሉአላዊት ኢትዮጵያ ዳሰሳዊ ጥናት ማድረግ ነው፡፡

1.3.2. የጥናቱ ዝርዝር አላማዎች፡


ይህ ጥናት የሚከተሉትን ዝርዝር አላማዎች ይዳስሳል፡-

 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የጀግንነቱን እና የመስዋትነቱን ልክ


ማሳየት፤
 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በህልውና ዘመቻው ወቅት የነበረውን ተጋድሎ መመርመር፤
 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዘመቻ በህብረ-ብሔራዊ አንድነት ወቅት ለሉአላዊት ኢትዮጵያ
ያሳየውን ቁርጠኝነት ማሰስ፤
 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካት ጋር የነበረውን ቅንጅት መዳሰስ፤
 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከደጄኑ ህዝብ ጋር የነበረውን ቅንጅት መፈተሸ፤

1.4. የጥናቱ አስፈላጊነት፡


የዚህ ጥናት አስፈላጊነት፤ የጥናቱ ውጤት በጦርነቱ ወቅት ከፍተኛ አስተዋጽ ለነበራቸው የኢትዮጵያ ፌደራል

ፖሊስ አመራርና አባላት እውቅና እና ክብር ለመስጠት እንደመነሻ ያገለግላል፡፡ ብሎም የተከፈለውን
መስዋትነት (እውነታውን) ለታሪክ ሰንዶ ለማስቀመጥ፡፡ ከዚህ ባለፈ ለተለያዪ አጥኒዎች እንደ ግብዓትነት
ከማገልገሉም በተጨማሪ ወደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተቋም አዲስ ለሚቀላቀሉ አባላት(የፖሊስ/የስቪል)
ማሰልጠኛ(Induction Training) ከመሆኑም ባሻገር የማስተባሪያ ሞጁሎች መነሻ ሃሳብ ሆኖም ያገለገልላል፡፡

1.5. የጥናቱ ወሰን፡


ጥናቱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት በህግ ማስከበር፣ በህልውና ዘመቻው እና በዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ
አንድነት ወቅት የነበራቸውን ተጋድሎ እና የከፈሉትን መስዋእትነት ይዳስሳል፡፡ የፖሊስ አባላቱ ተጋድሎ እና

4|Page
የከፈሏቸው መስዋእትነቶችን ለመዳሰስ ጦርነቱ በስፋት በተካሄደባቸው በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር
ክልሎች እንዲሁም የትህነግ ተላላኪ ፀረ-ሰላም ሐይሎች ጥቃት ይፈጽሙባቸው የነበሩባ የኦሮሚያ እና
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ላይ ይካሄዳል፡፡ እነዚህ ሁለት ክልሎች የተካተቱበት ምክንያት ትህነግ
ተላላኪዎቹን በማሰማራት የጥቃት አድማሱን ለማስፋት ባደረገው ጥረት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት
በእነዚህም ቦታዎች የፈጸማቸው ተጋድሎ እና መስዋእትነቶች ስላሉ ነው፡፡ ከጊዜ አንጻር ጥናቱ ትህነግ በሰሜን
እዝ ላይ ክህደት ፈጽሞ ጥቃት ከፈጸመበት ከጥቅምት 24 2013 ዓ/ም ጀምሮ ያለውን ይሸፍናል፡፡
ምዕራፍ ሁለት፡
2. የጥናቱ ማከናወኛ ዘዴዎች፡
2.1. መግቢያ፡
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ይህንን ጥናት ለማካሄድ የሚያገለግሉ የተለያዩ አካሄዶችን እንመለከታለን፡፡

በተጨማሪም በዚህ ርዕስ ስር ጥናቱ የሚካሄድባቸው ቦታዎች ፣ የጥናቱ ሥነ ዘዴ ፣የመረጃ ምንጭ

ዓይነቶችን፤ የናሙና አመራረጥ ዘዴዎች፤የጥናቱ አካላይ፤የተለያዩ መረጃ የመሰብሰቢያ መንገዶች፤የመረጃ

አሰባሰብ ቅደም ተከተል ሂደት፤የመረጃ ትንተና ዘዴ እና በጥናቱ ሂደት ሊተገበሩ የሚገባቸውን የሥነ ምግባር

ሁኔታዎች ተዳሰውበታል፡፡

5|Page
2.2. ጥናቱ የሚጠናባቸው ቦታዎች፡

በዚህ ጥናት ውስጥ ሊካተቱ የታቀዱ ቦታዎችን በተመለከተ በዋናነት በፌድራል ፖሊስ ኮሚሽንና በሀገር

መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተለይም በፀጥታ ማስከበር፣ በህግ ማስከበር፣

በህልውና ዘመቻው እና በዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ወቅት የተሳተፉባቸው እና ከዘመቻው ጋር

ተያያዥነት ባላቸው የአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በጥናቱ ሂደት ትኩረት

የሚደረግባቸው ቦታዎች ይሆናሉ፡፡

2.3. የጥናቱ ሥነ-ዘዴ፡


ይህ የጥናት ርዕስ አይነታዊ/ኃተታዊ የጥናት ባህሪ ያለው ሲሆን በዋናነት ገላጭ (Descriptive Design ) የሆነ
የጥናት ስነ-ዘዴን የሚከተል ይሆናል። ገላጭ የጥናት ስነ-ዘዴ የአንድን ነገር ወይም ሁኔታ አጠቃላይ ገጽታ
በመዳሰስ የነገሩን ወይም የሁኔታውን ነባራዊ ባህርያት/ገፅታ ለማወቅ እና ለማስቀመጥ የሚረዳና በተገኘው
ነባራዊ እውነታ ላይ በመመርኮዝም የወደፊቱን ሁኔታ ለመገመት እና ለማስቀመጥ የሚረዳን ስነ-ዘዴ ነው።
ይሄ ጥናትም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት በህግ ማስከበር፣ በህልውና ዘመቻው እና በዘመቻ ለህብረ
ብሔራዊ አንድነት ወቅት የነበራቸውን ተጋድሎ እና የከፈሉትን መስዋእትነት በመዳሰስና በሌሎች የአገሪቱ

6|Page
አካባቢዎችም በተለይ በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጸጥታ በማስከበር እና በጸረ- ሽብር የትግል
ሂደት ውስጥ የፌደራል ፖሊስ አባላት እየሰጡት ያለውን አገልግሎት እና የከፈሉትን የህይወት፤የአካል እና
ሌሎች መሰዋእትነቶችን ለመግለፅ ገላጭ የጥናት ስነ-ዘዴ አይነተኛ መንገድ ነው።

2.4. የመረጃ ምንጮች፡


ይህ ጥናት የሚያስፈልገውን መረጃ በበቂ ሁኔታ ለማግኘት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ የመረጃ ምንጮችን

የሚጠቀም ይሆናል፡፡ ከሁለቱም ምንጮች የሚገኙ እና የሚሰበሰቡ መረጃዎች የጥናቱን መሰረታዊ ጥያቄዎች

በመመለስ ሂደት የጎላ ሚና ይኖራቸዋል፡፡

2.4.1. የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ምንጭ፡


በዚህ ውስጥ የሚካተቱት የመረጃ ምንጮች በቃለ መጠይቅ ፣ በምልከታ እና በቡድን ተኮር ውይይት ወቅት

የሚገኙ መረጃዎችን ሲሆን ይህንንም መረጃዎች ለማግኘት በተለያዩ ደረጃ ያሉ የፖሊስ፤የመከላከያ እና

የክልል አመራሮች፤የፌደራል ፖሊስ አባላት እና አጋር የፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ

የማህበረሰብ ክፍሎች በቀዳሚነት የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

2.4.2. ሁለተኛ ደረጃ መረጃ ምንጮች፡


በዚህ ውስጥ የሚካተቱት የመረጃ ምንጮች ደግሞ በዋናነት ከመጀመሪያ ደረጃ ምንጮች ያገኘናቸውን

መረጃዎች የሚያጠናክሩ እና የሚደግፉ ከተለያዩ ሰነዶች፤ ከመጽሐፍቶች፣ ከማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን፣

የተለያዩ የስራ ሪፖርቶች፣ ተያዥነት ያላቸው ጥናቶችና ድረ-ገጾች የሚገኙ ይሆናሉ፡፡

2.5. የናሙና አመራረጥ ዘዴ፡


ይህ ጥናት ወሳኝ የናሙና አመረራጥ ዘዴ የሚጠቀም ይሆናል፡፡ ወሳኝ የናሙና ዘዴ የጥናቱ አካላይ መመረጥ

የሚኖርባቸው የናሙና አባላት የሚወስኑት ተመራማሪዎች በራሳቸው በምርምሩና በጥናቱ ባህሪ ይሆናል፡፡

ይህም ተመራማሪዎቹ/የጥናት ባለሙያዎቹ እነማን ወይም የተኞቹን የጥናቱ አካላይ ስለሁኔታው በቂ ልምድ፣

ቅርርብ እና እውቀት እንዳላቸው ቅድመ-ግምገማ በማድረግ የጥናቱን ተሳታፊዎች ይመረጣሉ፡፡ ከወሳኝ

ናሙና ዘዴ መካከልም የዓላማ ተኮር (purposive) እና ጠቋሚ ናሞና ወይም ሰንሰለት (swonball) ናሙና

አመራረጥ ስልት ይህ ጥናት የሚጠቀም ይሆናል፡፡ የጥናት ባለሙያዎቹ ተሳታፊዎችን የሚመረጡት ከጥናቱ

ዓላማ አንፃር ይሆናል፡፡

የዓላማ ተኮር (purposive) ናሙና እነማንን ብንመርጥ የምንፈልገውን መረጃ ሊሰጡን ይችላሉ ብለው

የሚወስኑት አጥኒዎቹ ናቸው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት የዓላማ ተኮር መረጃ ትንተና ከሁነቶች መከሰት

7|Page
ጀምሮ እስከሚቀጥለው ሂደት በቅደም ተከተል በማብራራትና የጥናቱ ሁኔታ ምን ውጤት እንደሚያመጣ

በግልጽ በማሳየት ጠቃሚ በመሆኑ ነው (ያለው እንዳወቅ፣ 2009 ዓ/ም) ፡፡

ጠቋሚ ናሙና ወይም ሰንሰለት (swonball) ናሙና አንዳንድ ጊዜ ተመራማሪው ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ
መረጃዎች ያሏቸውን ሰዎች በቅርብ ቢኖሩም እንኳ ለይቶ ለማግኘት አስቸጋሪ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ በዚህ
ወቅት ተመራማሪው ጠቋሚ ናሙናን እንዲጠቀም ሁኔታዎች ያስገድዱታል፡፡ በዚህ ሙሞና ዘዴ ተመራማሪው
ስለሚያጠናው ጉዳይ ዕውቀቱ ያለውን ሰው ወይም ቡድን ካገኘ በኃላ ቀጣዮቹን ተሳታፊዎች እየተጠቆመ
በጥቆማው መሰረት በተከታታይ መረጃ የመሰብሰብ ሂደቱን ሰንሰለታማ በሆነ መንገድ ይቀጥላል፡፡ በዚህ
ጥናትም በተለያዩ አከባቢዎች ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን በተለይም በህግ ማስከበር፤በህልውና እና በዘመቻ
ለህብረ ብሄራዊ አንድነት ዘመቻ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች በሽብር ቡድኖች የጥቃት ሰለባ የሆኑ ተጎጂዎች
በዚህ የጥናት ዘዴ ተካተው የጥናቱ አካል ይሆናሉ፡፡

እንደ አጠቃላይ በዚህ ጥናት ውስጥ በተለያየ ደረጃ ኦፕሬሽን ሲመሩ የነበሩ የፌደራል ፖሊስ

አመራሮች፤አባላትና ሌሎች የሀገር መከላከያ አመራሮች፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች፣የቤንሻንጉል

ጉምዝ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች፣ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና ልዩ ኃይል፣ፋኖ እና ሚኒሻ፡ የአፋር

ልዩ ኃይል፣ ፖሊስ እና ሚኒሻ እንዲሁም የኦሮሚያ፣ የቢሻንጉል ጉምዝ፣ የአማራ እና የአፋር ክልል

ፕሬዝዳንቶች በተጨማሪም የሚመለከታቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በቂና አስተማማኝ መረጃ ይሰጣሉ

ተብለው በአጥኚዎች የሚታሰቡ አካላትን በመምረጥ ቃለ መጠይቅና የቡድን ተኮር ዉይይት የሚደረግ

ይሆናል፡፡

2.6. የጥናቱ አካላይ፡


ይህ ጥናት ያተኮረውና ያካተታቸው አካላት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራር እና አባላት፤ የማህበረሰቡን

ሰላም እና ፀጥታ ለማስከበር በተሳተፉባቸው አካባቢዎች ማለትም በኦሮሚያ ክልል(ሆሮ-ጉድሩ፣ጉጅ እና ነገሌ-

ቦረና፣ በቤሻንጉል ጉምዝ ክልል(መተከል) እንዲሁም በህግ ማስከበር፣ በህልውና ዘመቻው እና በዘመቻ ለህብረ

ብሔራዊ አንድነት ወቅት የነበሩ እና አብረው የተሳተፉትን እማኖች ያካተተ ሲሆን ትግራይ ክልል፣ በአማራ

ክልል(ሸዋሮቢት፣አጣዬ፣ከሚሴ፣ደሴ፣ቆቦ፣ጋሸና፣ሁመራ እና ወልቃይት) እና እና በአፋር ክልል(ጭፍራ፣አሳ-ጊታ

እና ሚሌ) በቦታዎች የነበሩ የፌደራል ፖሊስ የኦፕሬሽን አመራሮች፣ የአካባቢ ነባር ማህበርሰብ እና የመከላከያ

አመራሮች እና ሰራዊት አባላት ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተጋድሎ እና መስዋእትነት አንጻር መረጃ

እንዲሰጡ ይሳተፋሉ፡፡ እንዲሁም ሌሎች ከፌዴራል ፖሊስ ጋር አብረው የተሳተፉ የፀጥታ አካላት ተሳታፊ

ይሆናሉ፡፡የተሳታፊዎች ብዛት ወደፊት በሚገኘው የመረጃ ብቁነት የሚወሰን ይሆናል ፡፡


8|Page
2.7. መረጃ የመሰብሰቢያ መንገዶች፡
የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶች አስፈላጊ መረጃዎችን ለማግኘት የሚያገለግሉ መንገዶችን እና ዘዴዎችን

ያመለክታሉ፡፡ የዚህ ጥናት መረጃዎች በአራት ዋና ዋና መንገዶች ይሰበሰባሉ ፤ እነሱም ቃለ-መጠይቅ፣

ምልከታ፣ የቡድን ውይይትና የመዛግብት /የሰነድ ትንተና ናቸው፡፡

2.7.1. ቃለ-መጠይቅ፡
ይህ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ዓይነታዊና የመጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ምንጭ ሆኖ መረጃ ለመሰበሰሰብ

የሚያገለግል ሲሆን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፖሊስ አባላት የማህበረሰቡን ሰላም እና ፀጥታ ለማስከበር

በተሳተፉባቸው አካባቢዎች ማለት ኦሮሚያ ክልል፣ በቤሻንጉል ጉምዝ ክልል እንዲሁም በህግ ማስከበር፣

በህልውና ዘመቻው እና በዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ወቅት የነበሩ እና አብረው የተሳተፉትን እማኖች

ያካተተ ሲሆን ትግራይ ክልል፣ አማራ ክልል እና አፋር ክልል በቦታው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ የኦፕሬሽን

አመራሮች፣ የአካባቢ የነባር ማህበርሰብ እና የመከላከያ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ከፌዴራል ፖሊስ ጋር

አብረው የተሳተፉ የፀጥታ አካላት መጠን-ሰፊ መረጃዎች የሚሰበሰቡበት ዘዴ ይሆናል፡፡ ጥያቄዎቹም ነፃና

ግልፅ የጥያቄ አዘገጃጀት መርህን ተከትለው የሚዘጋጁ ይሆናል፡፡

2.7.2. ቡድን ተኮር ውይይት፡


ይህ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ዓይነታዊና የመጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ምንጭ ሆኖ መረጃ ለመሰበሰሰብ

የሚያገለግል ሲሆን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፖሊስ አባላት የማህበረሰቡን ሰላም እና ፀጥታ ለማስከበር

በተሳተፉባቸው አካባቢዎች ማለት ኦሮሚያ ክልል፣ በብንሻንጉል ጉምዝ ክልል እንዲሁም በህግ ማስከበር፣

በህልውና ዘመቻው እና በዘመቻ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት ወቅት የነበሩ እና አብረው የተሳተፉትን እማኖች

ያካተተ ሲሆን አማራ ክልል እና አፋር ክልል በቦታዎች የነበሩ የፌደራል ፖሊስ የኦፕሬሽን አባላት፣ በአካባቢው

የነበሩ ማህበረሰቦች እና የመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም ሌሎች ከፌዴራል ፖሊስ ጋር አብረው የተሳተፉ የፀጥታ

አካላት ይሆናሉ፡፡ተሳታፊዎች ካላቸው ልምድና ቀርቤታ በመነሳት በቂ ግንዛቤ ይኖራቸዋል ተብለው

የተመረጡትን በቡድን በማወያየት ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት የሚያስችል ይሆናል፡፡

2.7.3. ምልከታ፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፖሊስ አባላት የማህበረሰቡን ሰላም እና ፀጥታ ለማስከበር በተሳተፉባቸው

አካባቢዎች ማለት ኦሮሚያ ክልል፣ በቤሻንጉል ጉምዝ ክልል እንዲሁም በህግ ማስከበር፣ በህልውና ዘመቻው እና

በዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ወቅት በአማራ ክልል እና አፋር ክልል በተሳተፉባቸው ቦታዎች በአካል

9|Page
በመሄድ በአባላት እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በመስክ ምልከታ በመመልከት መረጃ የሚሰበሰብ

ይሆናል፡፡

2.7.4. የሰነድና የመዛግብት ትንተና፡


በዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የተቀመጡ እና የተዘገቡ መረጃዎች፣ ከኢንተርኔት፤ መጽሄት፤

ሪፖርቶች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ሰነዶች በማጣቀስ ከዚህ ጥናት ጋር ተቀራራቢነት ያላቸውን በመውሰድ የዚህ

ጥናት ግብዓት እንዲሆኑ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

2.8. የመረጃ አሰባሰብ ቅደም-ተከተል ሂደት፡


ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እንደአስፈላጊነቱ የትብብር

ደብዳቤ በማፃፍ በቅድሚያ በፌደራል በሚገኙ ተቋማት አመራሮች ማለት ከመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች፣

ከፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከሚመለከታቸው የሚድያ ባለሙያዎች ጋር ቃለ-መጠይቅ በማድረግ

አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ይሰበሰባሉ። ቀጥሎ ከሚመለከታቸው የክልል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ጋር ቃለ-

መጠይቅ የሚደረግ ይሆናል፡፤ የቃለ-መጠይቁ አይነትም በመጠኑ አስቀድመው የተዘጋጁ(semi-structured

interview) እና ቀድሞ ያልተዘጋጁ (unstructured interview) በመጠቀም የሚደረግ ይሆናል።በዚህም

ተመራማሪው ጥያቄውን ብቻ ለመላሾች አቅርቦ መልስ ከራሳቸው ለማግኘት የሚጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡

መላሾቹ ነጻ ሆነው በተነሳው ጥያቄ ላይ የራሳቸውን ሀሳብ እና ምልከታ ባሻቸው መንገድ የሚገልጡበት

በመሆኑ የመመለስ ነጻነታቸውን ያሰፋዋል፡፡

በመቀጠልም ወደ አስፈላጊ ቦታዎች በመሄድ የመስክ ምልከታ ስራ የሚሰራ ይሆናል፤፤ በመጨረሻም የቡድን

ተኮር ውይይት ከመረጃ ሰጭዎች ጋር በሚመች ቦታ እና ሰአት ውይይቱ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

2.9. የጥናቱ መረጃዎች ተዐማኒነት፡


የጥናቱ መረጃዎች ተዐማኒነት የሚለካው ከሚመለከታቸው እና በክስተቶቹ ከነበሩ ባለድረሻ አካላት እና
ተሳታፊዎች አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት፤ ይህ ለማድረግ የተለያዩ የመረጃ መሰብሰቢያ ስልቶችን
በመጠቀም የሚሰበሰቡትን መረጃ እና መዛግብቶች እርስ በርስ በማመሳከር እና በማረጋገጥ፤ እንዲሁም

የሚሰበሰቡትን መረጃዎች ኦዲት በማድረግ ተአማኒነቱ የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡

2.10. የመረጃ ትንተና ዘዴ፡


ይህ ጥናት በተለያዩ መንገዶች የተሰበሰቡ መረጃዎችን ጭብጣዊ ትረካ ( Narrative thematic analysis)

እና ይዘታዊ ትረካ (Narrative content analysis) የአተናተን ዘዴን የሚጠቀም ይሆናል፡፡ የጥናቱን ግብ

10 | P a g e
ለማሳካት በተለያዩ አብይ ጉዳዮች (themes) ስር በጥንቃቄ ቀርበው ከተደራጁ በኋላ ይተነተናሉ፡፡ይዘታዊ

የአተናተን ዘዴ በመዛግብት፣ በቪዲዮ እና በኦዲዮ መልኩ የተቀመጡ መረጃዎችን ይዘታቸውን ጠብቀው

የሚቀርቡበት ስልት ነው፡፡ እንደ አጠቃላይ የተለያዩ የመረጃ መሰብሰብያ ዘዴዎችን በመጠቀም የሚሰበሰቡ

መረጃዎችን በማደራጀት እና በትኩረት ነጥቦቹ ላይ በማተኮር በጭብጥ እና በይዘት ጉዳዮችን ከፋፍሎ እንደ

ተመሳሳይነታቸውና ቅርርባቸው የተገኙ መረጃዎችን በዝርዝር የሚተነተኑ እና የሚተረኩ ይሆናሉ፡፡

2.11. ጥናቱ የሚከተላቸው ጥናታዊ ሥነ-ምግባር፡


ሁሉም የሚሰበሰቡ መረጃዎች በጥናቱ ተሳታፊዎች ይሁንታ ወይም ፍቃደኝነት የተመሠረተ

ይሆናል፤እንዲሁም የተሳታፊዎችን ሙሉ ነፃነት የማይጋፋ ይሆናል፡፡ የጥናት ቡድኑ ከተሳታፊዎች የሚገኙ

መረጃዎች በጥናቱ ሂደት የሚደርስባቸውን ሂደቶችና ግኝቶች የጥናት ቡድኑ ተጠሪ ለሆኑ የኮሚቴ አባላት

ሚስጢራዊነት ያላቸው መረጃዎችም ሚስጢራዊነታቸውን ጠብቀው ለሚመለከተው አካል ብቻ እንዲቀርቡ

ይደረጋሉ፡፡

11 | P a g e
ዋቢ-መፅሐፍት፡
ያለው እንዳወቅ ሙሉ (2009 ዓ.ም.)፡፡ የምርምር መሰረታዊ መርሆዎችና አተገባበር፡፡ባህርዳር፣ ባህርዳር
ዩኒቨርሲቲ ማተሚያ፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርም (2005 ዓ.ም.)፡፡ መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ
የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 7/2004 አንቀፅ 6 ንኡስ አንቀጽ 12
https://www.fanabc.com/ Accessed January 27, 2020 @ 9:30 /

12 | P a g e
ለፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጅ

መግቢያ

ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አነሳሽነት የሚጠና ሲሆን፤ጥናቱን የሚያከናውነው


የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከወንጀል መከላከል፤ከወንጀል ምርመራ እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ
ግንኙነት ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡ አላማውም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና አባላት
የተጋድሎ እና መስዋትነት ታሪክ ሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታማኝ እና ተጨባጭ መረጃ መሰብስብ
አስፈጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ ስለሆነም፣ የዚህ ጥናት አርዕስትም፤"ከጀግንነት እስከ መስዋዕትነት፤ለህብረ-
ብሔራዊ አንድነት እና ለሉአላዊት ኢትዮጵያ" የሚሰኝ ሲሆን፤ እርስዎ ለዚህ ጥናት ተገቢውን መረጃ
ለመስጠት የተመረጡ ሲሆን፤ እርስዎ የሚሰጡት መረጃ ከዚሁ ጥናት አላማ ውጭ ለሌላ አላማ የማይውል እና
የሰጡትም መረጃ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ መሆኑን እያረጋገጥን ነገር ግን የማይመችዎት ነገር ካጋጠመዎት
ወይም ካልተስማማዎት በማንኛውም ጊዜ ቃለ መጠይቁን ማቆም የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለተሻለ
የመረጃ ጥራት የእርስዎን ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ ለመያዝ እንዲመች ቃለ መጠይቁ በቴፕ እና በካሜራ የሚወሰድ
መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ስለመልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡
ምዕራፍ አንድ፡ ሰለ ተጠያቂዉ ግለሰብ አጠቃላይ መረጃ
1. ስም------
2. የአገልግሎት ዘመን----------
3. የትምህርት ደረጃ-------
4. የፖሊስ ማዕረግ -------------
5. ኃላፊነትዎ-- ቢገልጹልን?
13 | P a g e
ምዕራፍ ሁለት፡ የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በዘመቻ ወቅት የከፈሉት መስዋትነት እና ያሳዩት
ተጋድሎ የሚመለከቱ መጠይቆች ለፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች የቀረበ፤
6. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሕግ የተሰጠውን የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን በተመለከተ እንደ አጠቃላይ
እንዴት ይገለፃል?
7. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በለውጡ ማግስት ህውሃት ወደ መቀሌ ከገባባት ጊዜ አንስቶ የነበረውን ሂደት
በምን ዓይነት መልክ ይከታተለው ነበር?
8. አሸባሪው ህውሃት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በከፈተበት ወቅት የፌደራል ፖሊስ
ዝግጁነት እና ምላሽ ምን ይመስል ነበር?
9. የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በሕግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት የተሳተፈባቸውን የኦፕሬሽን እና የፀጥታ
ማስከበር ስራዎች እንዴት ይገልፁታል?
10. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በህልውና ዘመቻው ወቅት የነበረውን ሚና እና ተጋድሎ እንዴት ይገልጹታል?
11. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት ወቅት ለሉአላዊት ኢትዮጵያ ያሳየውን
ቁርጠኝነት እና የከፈለውን መሰዋዕትነት እንዴት ይገልጹታል? ቢያብራሩ?
12. በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች በአጠቃላይ ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ የሽብር ቡድኖች የሚቃጡ ጥቃቶችን
በመመከት እና በመከላከል ረገድ ያለውን አስተዋጾ እና የከፈላቸውን መስዋዕትነቶች ቢያብራሩልን?
13. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር የነበረው ቅንጅት እና መናበበ እንዴት
ይገለፃል?
14. የህብረ-ብሔር ዘመቻ ወቅት የጥምር ጦር ቅንጅት ምን ይመስል ነበር?
15. ማከል የሚፈልጉት ማንኛውም ነገር ካለ መጨመር ይችላሉ?

14 | P a g e
ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጅ

መግቢያ፡

ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አነሳሽነት የሚጠና ሲሆን፤ጥናቱን የሚያከናውነው


የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከወንጀል መከላከል፤ከወንጀል ምርመራ እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ
ግንኙነት ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡ አላማውም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና አባላት
የተጋድሎ እና መስዋትነት ታሪክ ሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታማኝ እና ተጨባጭ መረጃ መሰብስብ
አስፈጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ ስለሆነም፣ የዚህ ጥናት አርዕስትም፤"ከጀግንነት እስከ መስዋዕትነት፤ለህብረ-
ብሔራዊ አንድነት እና ለሉአላዊት ኢትዮጵያ" የሚሰኝ ሲሆን፤ እርስዎ ለዚህ ጥናት ተገቢውን መረጃ
ለመስጠት የተመረጡ ሲሆን፤ እርስዎ የሚሰጡት መረጃ ከዚሁ ጥናት አላማ ውጭ ለሌላ አላማ የማይውል እና
የሰጡትም መረጃ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ መሆኑን እያረጋገጥን ነገር ግን የማይመችዎት ነገር ካጋጠመዎት
ወይም ካልተስማማዎት በማንኛውም ጊዜ ቃለ መጠይቁን ማቆም የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለተሻለ
የመረጃ ጥራት የእርስዎን ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ ለመያዝ እንዲመች ቃለ መጠይቁ በቴፕ እና በካሜራ የሚወሰድ
መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ስለመልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡
ምዕራፍ አንድ፡ ሰለ ተጠያቂዉ ግለሰብ አጠቃላይ መረጃ
1. ስም---------
2. የአገልግሎት ዘመን------------

3. የትምህርት ደረጃ-------------

4. የመከላከያ ማዕረግ-----------

5. ኃላፊነትዎ------ ቢገልጹልን?

ምዕራፍ ሁለት፡ የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በዘመቻ ወቅት ያሳዩትን ተጋድሎና መስዋትነት
የሚመለከቱ መጠይቆች ለሀገር መከላከያ ከፍተኛ አመራሮች የቀረበ፤

6. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ ሀገራዊ የጸጥታ ማስከበር ስራዎች ላይ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት
ጋር ያለውን ቅንጅት እና በሂደቱም ያለው ሚና ምን ይመስላል?
7. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የተሳተፈባቸውን የኦፕሬሽን እና የፀጥታ
ማስከበር ስራዎች እንዴት ይገልፁታል?
8. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በህልውና ዘመቻው ወቅት የነበረውን ተጋድሎ እንዴት ይገልጹታል?

15 | P a g e
9. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት ወቅት ለሉአላዊት ኢትዮጵያ ያሳየውን
ቁርጠኝነት እና የከፈለውን መስዋዕትነት እንዴት ይገልጹታል? ቢያብራሩ?
10. እንደ አጠቃላይ የፌደራል ፖሊስ በሶስቱም የዘመቻ ሂደት ውስጥ በግንባርም ሆነ በተለያዩ የሀገሪቱ
አካባቢዎች ሽብርተኞችን በመደምሰስ እና ህግና ስርዓትን በማስከበር ሂደት ያለውን ሚና
ቢያብራሩልን?
11. የህብረ-ብሔር ዘመቻ ወቅት የጥምር ጦር ቅንጅት ምን ይመስል ነበር?
12. ማከል የሚፈልጉት ማንኛውም ነገር ካለ መጨመር ይችላሉ?

ለክልል ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጅ


መግቢያ፡

ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አነሳሽነት የሚጠና ሲሆን፤ጥናቱን የሚያከናውነው


የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከወንጀል መከላከል፤ከወንጀል ምርመራ እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ
ግንኙነት ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡ አላማውም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና አባላት
የተጋድሎ እና መስዋትነት ታሪክ ሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታማኝ እና ተጨባጭ መረጃ መሰብስብ
አስፈጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ ስለሆነም፣ የዚህ ጥናት አርዕስትም፤"ከጀግንነት እስከ መስዋዕትነት፤ለህብረ-
ብሔራዊ አንድነት እና ለሉአላዊት ኢትዮጵያ" የሚሰኝ ሲሆን፤ እርስዎ ለዚህ ጥናት ተገቢውን መረጃ
ለመስጠት የተመረጡ ሲሆን፤ እርስዎ የሚሰጡት መረጃ ከዚሁ ጥናት አላማ ውጭ ለሌላ አላማ የማይውል እና

16 | P a g e
የሰጡትም መረጃ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ መሆኑን እያረጋገጥን ነገር ግን የማይመችዎት ነገር ካጋጠመዎት
ወይም ካልተስማማዎት በማንኛውም ጊዜ ቃለ መጠይቁን ማቆም የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለተሻለ
የመረጃ ጥራት የእርስዎን ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ ለመያዝ እንዲመች ቃለ መጠይቁ በቴፕ እና በካሜራ የሚወሰድ
መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ስለመልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡
ምዕራፍ አንድ፡ ሰለ ተጠያቂዉ ግለሰብ አጠቃላይ መረጃ
1. ስም-----------
2. የአገልግሎት ዘመን----------
3. የትምህርት ደረጃ-----------
4. ማዕረግ-----------
5. ኃላፊነትዎ--------- ቢገልጹልን?

ምዕራፍ ሁለት፡ የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በዘመቻ ወቅት የነበራቸው ተጋድሎና መስዋትነት
የሚመለከቱ መጠይቆች ለክልል ከፍተኛ አመራሮች የቀረበ፤
6. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሕግ የተሰጠውን የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን በተመለከተ እንደ አጠቃላይ
እና በተለይም በክልሉ ያለውን ሚና ቢያብራሩልን?
7. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ ህግ በማስከበር ስራዎች ላይ ከተለያዩ የጸጥታ አካላት ጋር
በተለይም በክልሉ ካሉ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት እና በሂደቱም ያለው ሚና ምን ይመስላል?
8. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የተሳተፈባቸውን የኦፕሬሽን እና የፀጥታ
ማስከበር ስራዎች እንዴት ይገልፁታል?
9. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በህልውና ዘመቻው ወቅት የነበረውን ተጋድሎ እንዴት ይገልጹታል?
10. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት ወቅት ለሉአላዊት ኢትዮጵያ ያሳየውን
ቁርጠኝነት እና የከፈለውን መስዋዕትነት እንዴት ይገልጹታል? ቢያብራሩ?
11. እንደ አጠቃላይ የፌደራል ፖሊስ በሶስቱም የዘመቻ ሂደት ውስጥ በግንባርም ሆነ በተለያዩ የሀገሪቱ
አካባቢዎች ሽብርተኞችን በመደምሰስ እና ህግና ስርዓትን በማስከበር ሂደት ያለውን ሚና
ቢያብራሩልን?
12. የህብረ-ብሔር ዘመቻ ወቅት የጥምር ጦር ቅንጅት ምን ይመስል ነበር?
13. ማከል የሚፈልጉት ማንኛውም ነገር ካለ መጨመር ይችላሉ?

17 | P a g e
ለህዝብ ግንኙነት እና ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች
መግቢያ፡

ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አነሳሽነት የሚጠና ሲሆን፤ጥናቱን የሚያከናውነው


የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከወንጀል መከላከል፤ከወንጀል ምርመራ እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ
ግንኙነት ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡ አላማውም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና አባላት
የተጋድሎ እና መስዋትነት ታሪክ ሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታማኝ እና ተጨባጭ መረጃ መሰብስብ
አስፈጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ ስለሆነም፣ የዚህ ጥናት አርዕስትም፤"ከጀግንነት እስከ መስዋዕትነት፤ለህብረ-
ብሔራዊ አንድነት እና ለሉአላዊት ኢትዮጵያ" የሚሰኝ ሲሆን፤ እርስዎ ለዚህ ጥናት ተገቢውን መረጃ
ለመስጠት የተመረጡ ሲሆን፤ እርስዎ የሚሰጡት መረጃ ከዚሁ ጥናት አላማ ውጭ ለሌላ አላማ የማይውል እና
የሰጡትም መረጃ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ መሆኑን እያረጋገጥን ነገር ግን የማይመችዎት ነገር ካጋጠመዎት
ወይም ካልተስማማዎት በማንኛውም ጊዜ ቃለ መጠይቁን ማቆም የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለተሻለ
የመረጃ ጥራት የእርስዎን ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ ለመያዝ እንዲመች ቃለ መጠይቁ በቴፕ እና በካሜራ የሚወሰድ
መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ስለመልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡
ምዕራፍ አንድ፡ ሰለ ተጠያቂዉ ግለሰብ አጠቃላይ መረጃ
1. ስም---------
2. የአገልግሎት ዘመን------------
3. የትምህርት ደረጃ-------------
4. የመከላከያ ማዕረግ-----------
5. ኃላፊነትዎ------ ቢገልጹልን?

18 | P a g e
ምዕራፍ ሁለት፡ የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በዘመቻ ወቅት የነበራቸውን ሚና በሚመለከት

ለህዝብ ግንኙነት እና ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የቀረቡ መጠይቆች፡

6. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሕግ ማስከበር ዘመቻው በፊትም ሆነ በኃላ በሀገሪቱ ፀጥታ እና ሰላም

በማስከበር ስራዎች ውስጥ የነበረውን ሱታፌ እንዴት ይገልፁታል?

7. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በህልውና ዘመቻው ወቅት የነበረውን ተጋድሎ እንዴት ይገልጹታል?

8. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዘመቻ በህብረ-ብሔራዊ አንድነት ወቅት ያሳየውን ቁርጠኝነት እና

የከፈለውን መሰዋዕትነት እንዴት ይገልፃል? /በጣም በተለየ የሚያነሱት የጀግነነት ወይም

የመስዋዕትነት ታሪክ ካለ ቢነግሩን/

9. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሕግ የተሰጠውን የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን ላይ የሚፈለውን

መስዋዕትነት እንዴት እንደነበር ቢያብራሩ?

10. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሕግ ማስከበር፣በህልውና ዘመቻው እና በህብረ-ብሔራዊ አንድነት

ያሳየው ጀግንነት እና የከፈለው መስዋዕትነት ተገቢ የሆነ የሚዲያ ሽፋን እንዲሁም ክብር ተሰጥቶቷል

ብለው ያምናሉ? መልስዎ አዎ ከሆነ እንዴት ይገለጻል? መልስዎ አልተሰጠውም ከሆነ ለምን

ይመስልዎታል?

11. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በህግና ፀጥታ ማስከበር ስራዎች የሚፈጽማቸው ጀግንነቶች እና እየከፈለ

ያለው መስዋዕትነት በተገቢ ሁኔታ ተሰንዷል ብለው ይምናሉ? አዎ ካሉ እንዴት ይገልጹታል?

አልተሰነደም ከሆነ ለምን ይመስልዎታል?

12. በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት እና በፌደራል ፖሊስ ንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት ቢያብራሩ?

13. በተለየ መልኩ በሶስቱም የዘመቻ ሂደቶች የፌደራል ፖሊስ አባላት የነበራቸውን ሚና በተመለከተ

ሊያነሱት የሚገባ ነጥባ ካለ ቢያብራሩልን?

14. ማከል የሚፈልጉት ማንኛውም ነገር ካለ መጨመር ይችላሉ?

19 | P a g e
ለሃይማኖት አባቶች እና ለአካባቢ አመራሮች
መግቢያ፡

ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አነሳሽነት የሚጠና ሲሆን፤ጥናቱን የሚያከናውነው


የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከወንጀል መከላከል፤ከወንጀል ምርመራ እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ
ግንኙነት ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡ አላማውም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና አባላት
የተጋድሎ እና መስዋትነት ታሪክ ሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታማኝ እና ተጨባጭ መረጃ መሰብስብ
አስፈጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ ስለሆነም፣ የዚህ ጥናት አርዕስትም፤"ከጀግንነት እስከ መስዋዕትነት፤ለህብረ-
ብሔራዊ አንድነት እና ለሉአላዊት ኢትዮጵያ" የሚሰኝ ሲሆን፤ እርስዎ ለዚህ ጥናት ተገቢውን መረጃ
ለመስጠት የተመረጡ ሲሆን፤ እርስዎ የሚሰጡት መረጃ ከዚሁ ጥናት አላማ ውጭ ለሌላ አላማ የማይውል እና
የሰጡትም መረጃ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ መሆኑን እያረጋገጥን ነገር ግን የማይመችዎት ነገር ካጋጠመዎት
ወይም ካልተስማማዎት በማንኛውም ጊዜ ቃለ መጠይቁን ማቆም የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለተሻለ
የመረጃ ጥራት የእርስዎን ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ ለመያዝ እንዲመች ቃለ መጠይቁ በቴፕ እና በካሜራ የሚወሰድ
መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ስለመልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡
ምዕራፍ አንድ፡ ሰለ ተጠያቂዉ ግለሰብ አጠቃላይ መረጃ
1. ስም---------
2. የአገልግሎት ዘመን------------
3. የትምህርት ደረጃ-------------
4. የመከላከያ ማዕረግ-----------
5. ኃላፊነትዎ------ ቢገልጹልን?

ምዕራፍ ሁለት፡ የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በዘመቻ ወቅት የነበራቸወን አስተዋፆ

ለማሕበረሰብ ክፍሎች የቀረቡ መጠይቆች፤

6. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሕግ የተሰጠውን የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን እንዴት ይሰራ እንደነበር እና

አሁንም ያለውን ተግባር ቢያብራሩ?

20 | P a g e
7. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የማህበረሰቡን ፀጥታ እና ሰላም ማስከበር

ስራዎች እንዴት ይገልፁታል?

8. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በህልውና ዘመቻው ወቅት የነበረውን ተጋድሎ እንዴት ይገልጹታል?

9. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዘመቻ በህብረ-ብሔራዊ አንድነት ወቅት ያሳየውን ቁርጠኝነት እና

የከፈለውን መሰዋዕትነት እንዴት ይገልፃል?

10. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአከባቢው የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር

ያለውን ትብብር እና የቅንጅት ሁኔታ እንዴት ይገለጻል?

11. የአከባቢው ማህበረሰብ በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ያለው ዕምነት ምን ይመስላል?

12. ማከል የሚፈልጉት ማንኛውም ነገር ካለ መጨመር ይችላሉ?

ለፌደራል ፖሊስ አባላት እና ለተለያዩ ኦፕሬሽናል መሪዎች


መግቢያ፡

ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አነሳሽነት የሚጠና ሲሆን፤ጥናቱን የሚያከናውነው


የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከወንጀል መከላከል፤ከወንጀል ምርመራ እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ

21 | P a g e
ግንኙነት ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡ አላማውም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና አባላት
የተጋድሎ እና መስዋትነት ታሪክ ሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታማኝ እና ተጨባጭ መረጃ መሰብስብ
አስፈጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ ስለሆነም፣ የዚህ ጥናት አርዕስትም፤"ከጀግንነት እስከ መስዋዕትነት፤ለህብረ-
ብሔራዊ አንድነት እና ለሉአላዊት ኢትዮጵያ" የሚሰኝ ሲሆን፤ እርስዎ ለዚህ ጥናት ተገቢውን መረጃ
ለመስጠት የተመረጡ ሲሆን፤ እርስዎ የሚሰጡት መረጃ ከዚሁ ጥናት አላማ ውጭ ለሌላ አላማ የማይውል እና
የሰጡትም መረጃ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ መሆኑን እያረጋገጥን ነገር ግን የማይመችዎት ነገር ካጋጠመዎት
ወይም ካልተስማማዎት በማንኛውም ጊዜ ቃለ መጠይቁን ማቆም የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለተሻለ
የመረጃ ጥራት የእርስዎን ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ ለመያዝ እንዲመች ቃለ መጠይቁ በቴፕ እና በካሜራ የሚወሰድ
መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ስለመልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡
ምዕራፍ አንድ፡ ሰለ ተጠያቂዉ ግለሰብ አጠቃላይ መረጃ
1. ስም---------
2. የአገልግሎት ዘመን------------
3. የትምህርት ደረጃ-------------
4. የመከላከያ ማዕረግ-----------
5. ኃላፊነትዎ------ ቢገልጹልን?

ምዕራፍ ሁለት፡ የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በዘመቻ ወቅት የነበራቸውን ዝግጁነት እና
የኦፕሬሽን አፈጻፀም የሚመለከቱ መጠይቆች፤
6. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት በሕግ የተሰጠውን የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን ለመስራት ያለውን
ዝግጁነት እና የኦፕሬሽን አፈጻፀም እንዴት እንደነበር ቢያብራሩ?
7. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የነበርውን የኦፕሬሽን ስራ እንዴት
ይገልፁታል?
8. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በህልውና ዘመቻው ወቅት የነበረውን ተጋድሎ እንዴት ይገልጹታል?
9. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዘመቻ በህብረ-ብሔራዊ አንድነት ወቅት ያሳየውን ቁርጠኝነት እና
የከፈለውን መሰዋዕትነት እንዴት ይገልፃል?
10. በተለያዩ የህግ ማስከበር ሂደቶች የነበሩ ሚናዎችን እና በተለይም የላቁ የጀግነነት እና የተጋድሎ
ክስተቶችን ካሉ ቢያነሱልን?
11. እንደ አጠቃላይ የእርሶዎ ቲም/ጓድ የነበራትን የትግል እና የዘመቻ ተሳትፎ በዝርዝር ቢያብራሩልን?

22 | P a g e
12. ከላይ ካነሳናቸው ሀሳቦች በተለየ በታሪክ ሊወሳ እና ሊነሳ ይገባል የሚሉት የግዳጅ አፈጻጸም ወይም
የጀግንነት ታርክ ካለ ቢያነሱልን?
13. ማከል የሚፈልጉት ማንኛውም ነገር ካለ መጨመር ይችላሉ?

ለኮማንድ ፖስት አባላት እና አመራሮች


መግቢያ፡

ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አነሳሽነት የሚጠና ሲሆን፤ጥናቱን የሚያከናውነው


የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከወንጀል መከላከል፤ከወንጀል ምርመራ እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ
ግንኙነት ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡ አላማውም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና አባላት
የተጋድሎ እና መስዋትነት ታሪክ ሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታማኝ እና ተጨባጭ መረጃ መሰብስብ
አስፈጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ ስለሆነም፣ የዚህ ጥናት አርዕስትም፤"ከጀግንነት እስከ መስዋዕትነት፤ለህብረ-
ብሔራዊ አንድነት እና ለሉአላዊት ኢትዮጵያ" የሚሰኝ ሲሆን፤ እርስዎ ለዚህ ጥናት ተገቢውን መረጃ
ለመስጠት የተመረጡ ሲሆን፤ እርስዎ የሚሰጡት መረጃ ከዚሁ ጥናት አላማ ውጭ ለሌላ አላማ የማይውል እና
የሰጡትም መረጃ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ መሆኑን እያረጋገጥን ነገር ግን የማይመችዎት ነገር ካጋጠመዎት
ወይም ካልተስማማዎት በማንኛውም ጊዜ ቃለ መጠይቁን ማቆም የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለተሻለ
የመረጃ ጥራት የእርስዎን ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ ለመያዝ እንዲመች ቃለ መጠይቁ በቴፕ እና በካሜራ የሚወሰድ
መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

23 | P a g e
ስለመልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡
ምዕራፍ አንድ፡ ሰለ ተጠያቂዉ ግለሰብ አጠቃላይ መረጃ
1. ስም---------
2. የአገልግሎት ዘመን------------
3. የትምህርት ደረጃ-------------
4. የመከላከያ ማዕረግ-----------
5. ኃላፊነትዎ------ ቢገልጹልን?

ምዕራፍ ሁለት፡ የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በዘመቻ የነበራቸውን ተሳትፎ የሚመለከቱ
መይቆች፤
6. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ያሳየውን ቁርጠኝነት እና የከፈለውን መሰዋዕትነት እንዴት
ይገልፃል?
7. በዘመቻ ወቅት የጥምር ጦሩ ቅንጅት ምን ይመስል ነበር?
8. በዘመቻ ወቅት የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የክልል ልዩ ኃይል እና ሌሎች የጸጥታ አካላት መካከል

የነበረው ትብብር እና የቅንጅት ሁኔታ እንዴት ይገለጻል?

9. ማከል የሚፈልጉት ማንኛውም ነገር ካለ መጨመር ይችላሉ?

24 | P a g e
የቡድን ተኮር ውይይት መሪ መጠይቆች
መግቢያ፡

ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አነሳሽነት የሚጠና ሲሆን፤ጥናቱን የሚያከናውነው


የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከወንጀል መከላከል፤ከወንጀል ምርመራ እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ
ግንኙነት ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡ አላማውም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና አባላት
የተጋድሎ እና መስዋትነት ታሪክ ሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታማኝ እና ተጨባጭ መረጃ መሰብስብ
አስፈጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ ስለሆነም፣ የዚህ ጥናት አርዕስትም፤"ከጀግንነት እስከ መስዋዕትነት፤ለህብረ-
ብሔራዊ አንድነት እና ለሉአላዊት ኢትዮጵያ" የሚሰኝ ሲሆን፤ እርስዎ ለዚህ ጥናት ተገቢውን መረጃ
ለመስጠት የተመረጡ ሲሆን፤ እርስዎ የሚሰጡት መረጃ ከዚሁ ጥናት አላማ ውጭ ለሌላ አላማ የማይውል እና
የሰጡትም መረጃ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ መሆኑን እያረጋገጥን ነገር ግን የማይመችዎት ነገር ካጋጠመዎት
ወይም ካልተስማማዎት በማንኛውም ጊዜ ቃለ መጠይቁን ማቆም የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለተሻለ
የመረጃ ጥራት የእርስዎን ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ ለመያዝ እንዲመች ቃለ መጠይቁ በቴፕ እና በካሜራ የሚወሰድ
መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ስለመልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡

ለቡድን ተኮር የሚቀርቡ መጠይቆች፡

1. በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የጦርነቱ አጀማመር አንዴት ነበር? ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ትህነግ በሰሜን እዝ
ላይ ያደረሰው ጥቃት ምን ይመስል ነበር? የፌደራል ፖሊስ አባላትስ ምን አይነት ጥቃት ተፈጸመባቸው

25 | P a g e
ሁኔታውስ እንዴት ነበር? በዚያ ጥቃት ምን ያክል የፌደራል ፖሊስ አባላት ተሰው? የታገቱትስ እንዴት ነበር
ወዴትስ ተወሰዱ በታገቱበትስ ምን ደረሰባቸው? በተለይ ሴት ጓዶች እንዴት አሳለፉት?
2. የፌደራል መንግስት ህግን በማስከበር ወቅት ጦርነት ከትህነግ ጋር በጀመረበት ጊዜ የፌደራል ፖሊስ ሚና
ምን ነበር? በጦርነቱ ውስጥ በየት ግንባር የት አካባቢ ተሳተፈ ጦርነቱስ ምን ይመስል ነበር? እንዴት እና
በምን አይነት መልኩ ይመራ ነበር? ፌደራል ፖሊስ ያሳየው ጀግንነት እንዴት ይገለጻል? የቆሰሉ እና የተሰው
አባላት እንዴት ነበር ጀግንነታቸው?
3. ፌደራል መንግስት የህልውና ዘመቻ ባወጀበት ጊዜ ፌደራል ፖሊስ የት አካባቢ ላይ ሲዋጋ ነበር? በምን
አይነት ስልት ሲዋጋ ነበር? ጦርነቱን በመመከት በኩል የፌደራል ፖሊስ ጀብዱ ምን ነበር? ጀግንነቱስ
እንዴት ይገለጻል? ጓዶች የተሰውት በምን መልኩ ነበር?
4. በጦርነቱ ወቅት የፌደራል ፖሊስ ቅንጅት እረስ በረስ ከመከላከያ ጋር ከፋኖ እንዲሁም ልዩ የአማራ እና
የአፋር ከልል ሃይሎች ጋር የነበረው መናበብ እንዴት ነበር ? ምንስ ጠንካር እና ደካማ ጎኖች ነበሩት?
5. በዘመቻ ለህብረ-ብሄራዊ አንድነት ወቅት ፌደራል ፖሊስ የትኛውን ግንባር መከተ? የትኛውን አካባቢ
ከጠላት ጦር እና ቁጥጥር አስለቀቀ? የጀግንነቱ ሁኔታ ምን ይመስል ነበር? ጓዶች በምን መልኩ ተሰው?
6. በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የታጠቁ ትህነግ አበር ጠላቶችን ፌደራል ፖሊስ በምን መልኩ
ሲመክት ነበር? የተጋድሎው ልክ እንዴት ይገለጻል ? የአባላቱ ጀግንነት ምን ይመስል ነበር? ጓዶች እንዴት
ነበር የተሰውት?
7. በጦርነቱ ወቅት ፌደራል ፖሊስ የገጠመው ትልቁ ፈተና ምን ነበር? አባላቱ ችግሩን በምን መልኩ እንዴት
እና በምን ስልት ተቋቋሙት?
8. ተቋሙን ሊጠቅም የሚችል ከጦርነቱ እንደ ትልቅ ግብአት ሊወሰድ የሚችል ጉልህ ጉዳይ ምንድነው?
9. ከጦርነቱ በኋላ ፌደራል ፖሊስ በመንግሰት በኩል የተደረገለት ድጋፍ ነበር? የቆሰሉ ከባድ እና ቀላል የአካል
ጉዳት የደረሰባቸው አባላት እንዴት ነበር የህክምና እርዳታ የተደረገላቸው? በከፈሉት መስዋእትነት ልክ
እንደ ሃገር ክብር እና እውቅና ተችሯቸዋል? ማን እንዴት የት ምን አደረገላቸው? ወደፊትስ ምን
ሊደረግላቸው ይገባል?

26 | P a g e
የመስክ ምልከታ መዘርዝሮች
መግቢያ፡

ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አነሳሽነት የሚጠና ሲሆን፤ጥናቱን የሚያከናውነው


የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከወንጀል መከላከል፤ከወንጀል ምርመራ እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ
ግንኙነት ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡ አላማውም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና አባላት
የተጋድሎ እና መስዋትነት ታሪክ ሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታማኝ እና ተጨባጭ መረጃ መሰብስብ
አስፈጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ ስለሆነም፣ የዚህ ጥናት አርዕስትም፤"ከጀግንነት እስከ መስዋዕትነት፤ለህብረ-
ብሔራዊ አንድነት እና ለሉአላዊት ኢትዮጵያ" የሚሰኝ ሲሆን፤ እርስዎ ለዚህ ጥናት ተገቢውን መረጃ
ለመስጠት የተመረጡ ሲሆን፤ እርስዎ የሚሰጡት መረጃ ከዚሁ ጥናት አላማ ውጭ ለሌላ አላማ የማይውል እና
የሰጡትም መረጃ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ መሆኑን እያረጋገጥን ነገር ግን የማይመችዎት ነገር ካጋጠመዎት
ወይም ካልተስማማዎት በማንኛውም ጊዜ ቃለ መጠይቁን ማቆም የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለተሻለ
የመረጃ ጥራት የእርስዎን ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ ለመያዝ እንዲመች ቃለ መጠይቁ በቴፕ እና በካሜራ የሚወሰድ
መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ስለመልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡

ለመስክ ምልከታ የተሰማሩ የጥናት ባለሙያዎች የሚያግዙ መጠይቆች፡


1. ጦርነቱ የተደረገባቸውን በተለይም ፌደራል ፖሊስ የተሳተፈባቸውን አካባቢዎች እና የፌደራል
ፖሊስ በሆኑ ንብረቶች በአትኩሮት እና በአጽንኦት መመለከት የገጠር እና የከተማ የጦር
አውድማዎችን መመለከት የደረሰውን የሃብት እና መሰረተ- ልማት ውደመት መመለከት፡፡
2. የቆሰሉ እንዲሁም ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን የፌደራል ፖሊስ አባላት ባሉበት
በሆሰፒታል በቤታቸው እና በካምፕ መጎብኘት የከፈሉትን የአካል መስዋእትነት በአትኩሮት እና
በአጽንኦት መመለከት ናቸው፡፡

አቫሪ 2፡ የጥናቱ ይዘት፡


ምዕራፍ አንድ፡ መግቢያ
1.1. የጥናቱ ዳራ
1.2. የችግሩ ትንተና፡
1.3. የጥናቱ አላማ፡
1.3.1. የጥናቱ ዋና አላማ፡
1.3.2. የጥናቱ ዝርዝር አላማዎች፡
1.4. የጥናቱ አስፈላጊነት፡
1.5. የጥናቱ ወሰን፡

27 | P a g e
1.6 የተዛማጅ ፅሑፍ ቅኝት
በዚህ ርዕስ ስር የሚከተሉት ፅንሰ-ሐሳቦች የሚዳሰሱ ይሆናል፡፡

 ጀግንነት
 መስዋትነት
 የሌሎች ሃገራት ተሞክሯ በኦፕሬሽን መስዋትነት ለሚከፍሉ ለፀጥታ የሚሰጠው እውቅና እና ክብር
 በኢትዮጵያ በኦፕሬሽን መስዋትነት ለሚከፍሉ የፀጥታ አካላት ያለው የሕግ-ማዕቀፋዊ መዳሰስ
ምዕራፍ ሁለት፡ የጥናቱ ማከናወኛ ዘዴዎች
2.1. መግቢያ፡
2.2. ጥናቱ የሚጠናባቸው ቦታዎች፡
2.3. የጥናቱ ሥነ-ዘዴ፡
2.4. የመረጃ ምንጮች፡
2.4.1. የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ምንጭ፡
2.4.2. ሁለተኛ ደረጃ መረጃ ምንጮች፡
2.5. የናሙና አመራረጥ ዘዴ፡
2.6. የጥናቱ አካላይ፡
2.7. መረጃ የመሰብሰቢያ መንገዶች፡
2.7.1. ቃለ-መጠይቅ፡
2.7.2. ቡድን ተኮር ውይይት ዘዴ፡
2.7.3. ምልከታ፡
2.7.4. የሰነድና የመዛግብት ትንተና፡
2.8. የመረጃ አሰባሰብ ቅደም-ተከተል ሂደት፡
3.9. የጥናቱ መረጃዎች ተአማኒነት፡
2.10. የመረጃ ትንተና ዘዴ፡
2.11. ጥናቱ የሚከተላቸው ጥናታዊ ሥነ-ምግባር፡
ምዕራፍ ሶስት፡ የመረጃ ትንተና
3. መግቢያ
3.1. አጠቃላይ የጦርነቱ ሁኔታ
 የመከላከያ ሰራዊት የተሳትፎ ሁኔታ
 የፌደራል ፖሊስ የተሳትፎ ሁኔታ
 የክልል ልዩ ኃይሎች የተሳትፎ ሁኔታ
 የሌሎች ፀጥታ(ፋኖ እና የአካባቢ ሚኒሻ) የተሳትፎ ሁኔታ
3.2 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ስምሪት
በሰሜን ግንባር
በደቡብ ግንባር
በምስራቅ ግንባር
በምዕራብ ግንባር
3.3 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት
3.3.1 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች ያሳዩት ጀግንነት
3.3.2 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች የከፈሉት መስዋትነት

28 | P a g e
3.3.3 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ወቅት የነበሩ መልካም አጋጣሚዎች፡
3.3.4 .የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች ከደጀኑ ሕዝብ ጋር የነበረው
ቅንጀት፡
3.3.5 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ወቅት ያገኟቸው ልምዶች፡
3.3.6. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ወቅት ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች፡
3.4. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች በህልውና ዘመቻው ወቅት
3.4.1 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች ያሳዩት ጀግንነት
3.4.2 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች የከፈሉት መስዋትነት
3.4.3 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ወቅት የነበሩ መልካም አጋጣሚዎች፡
3.4.4 .የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች ከደጀኑ ሕዝብ ጋር የነበረው
ቅንጀት፡
3.4.5 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ወቅት ያገኟቸው ልምዶች፡
3.4.6 . የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ወቅት ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች፡
3.5. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች በዘመቻ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት
3.5.1 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች ያሳዩት ጀግንነት
3.5.2 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች የከፈሉት መስዋትነት
3.5.3 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ወቅት የነበሩ መልካም አጋጣሚዎች፡
3.5.4 .የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች ከደጀኑ ሕዝብ ጋር የነበረው
ቅንጀት፡
3.5.5 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ወቅት ያገኟቸው ልምዶች፡
3.5.6 . የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዘመቻ ወቅት ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች፡
3.5. 7 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች በዘመቻ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት ወቅት ለሉአላዊት ኢትዮጵያ ያሳዩት
ቁርጠኝነት፡
3.5.8 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮችከመከላከያ፣ ከሌሎች የፌደራል እና የክልል የፀጥታ አካላት ጋር የነበራቸው
ቅንጅት፡
ምዕራፍ አራት፡ መደምደሚያ፣ አድምታ እና ምክረ-ሃሳብ
4.1. መደምደሚያ
4.2. አድምታ
4.3. ምክረ-ሃሳብ

29 | P a g e
አባሪ III: የጥናቱ የጉዞ መስመሮች፤
ተ.ቁ. አቅጣጫ የቡድን አባላት ምርመራ
ብድን፣ ብድን፤2 ቡድን፣3 ቡድን፣4 ቡድን፣5
1
1 ደቡብ፤ኦሮሚያ 1.
 ጉጅ 2.
 ነገሌ-ቦረና 3.
 ሆሮ-ጉድሩ 4.
ሀዋሳ 5.
2 ሰሜን፤ጎንደር 1.
 ሁመራ እና 2.
 ወልቃይት 3.
4.
5.
ምስራቅ፤ወሎ 1.
ሽዋ 2.
ሽዋሮቢት 3.
አጣዬ 4.
ከሚሴ 5.
ደሴ
ቆቦ
ላሊበላ እና
ጋሸና
ሰሜን-ምስራቅ፤አፋር 1.

30 | P a g e
 ጭፍራ 2.
 ካሳ-ጊታ እና 3.
 ሚሌ 4.
5.
ደቡብ-ምዕራብ፤ቤንሻንጉል ጉምዝ 1.
 መተከል 2.
3.
4.
5.

31 | P a g e

You might also like