You are on page 1of 54

All the ideas and views expressed in this research solely reflects the position of Author

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ህገ-መንግስታዊ


ሰብአዊ መብቶችን የማሳወቅ፣ መከበራቸውን
የመከታተል እና የመመርመር ሃላፊነት፤ ተግባር፤ ይዘቱ
እና ወሰኑ ዙሪያ የተዘጋጀ ጥናት

ታምሩ ከድር

መስከረም /2009
ማውጫ
ምዕራፍ አንድ............................................................................................................................................................1

ጠቅላላ መግቢያ.........................................................................................................................................................1

1. መግቢያ............................................................................................................................................................1

1.1 የጥናቱ መነሻ ሃሳብ (ዳራ)............................................................................................................................1

1.2 ስለ ብሄራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት ተዛማጅ ድርሳናት...............................................................................4

1.3 ጥናቱ የሚያነሳቸው ችግሮች.............................................................................................................................6

1.4 የጥናቱ ዓላማዎች............................................................................................................................................7

1.4.1 አጠቃላይ ዓላማ........................................................................................................................................7

1.4.2 ዝርዝር ዓላማ ዎች...................................................................................................................................7

1.5 የጥናቱ ወሰንና ውስንነት...................................................................................................................................8

1.5.1 የጥናቱ ወሰን.............................................................................................................................................8

1.5.2 የጥናቱ ውስንነት.......................................................................................................................................8

1.6 ጥናቱ የሚመልሳቸው ጥያቄዎች..................................................................................................................8

1.6.1 የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ በተመለከተ................................................................................................8

1.6.2 የሰብአዊ መብት ክትትል በተመለከተ............................................................................................................8

1.6.3 የሰብአዊ መብት ግንዛቤ ማስፋፋት በተመለከተ.............................................................................................8

1.7 የጥናቱ ስነ ዘዴ፣ የጥናቱ ስልትና የመረጃ ምንጭና ማሰባሰቢያ ዘዴ.........................................................................9

1.7.1 የጥናቱ ስነ ዘዴ (Research methodology)...................................................................................................9

1.7.2 የጥናቱ ስልት.............................................................................................................................................9

1.7.3 የመረጃ ምንጭና ማሰባሰቢያ ዘዴ /Data source and data gathering technique/............................................9

1.8 የጥናቱ ጠቀሜታ............................................................................................................................................10

1.9 የጥናቱ አወቃቀር............................................................................................................................................10

ምዕራፍ ሁለት.........................................................................................................................................................11

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር የተዘረጉ የህግና የተቋም ማዕቀፎች...............................................................11

2.1 ስለ ሰብአዊ መብቶች ፅንሰ ሃሳብ አጠቃላይ ምልከታ.......................................................................................11

2.2 ሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት......................................................................................................11

2.3 የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት......................................................................................11

2.4 የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገመንግስት ያላቸው ቦታ..............................................11
ምዕራፍ ሦስት.........................................................................................................................................................11

የብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት ጽንሰ ሃሣብ፣ የህግ ማዕቀፍና ሚናቸውና የብሄራዊ ሰብአዊ መብት ተቋሟት በኢትዮጲያ11

3.1 ብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት እነማን ናቸው?.............................................................................................11

3.2 የብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት ዓለም አቀፍ የህግ መስፈርቶች(Paris principles)...........................................11

3.2.1 ስልጣንና ሀላፊነት(Competence and responsibilities)..............................................................................11

3.2.2 ጥንቅር፣ ነጻነትና ብዝሀነት(Composition, independence and pluralism)...................................................11

3.2.3 የአሰራር ስርአት (Methods of operation).................................................................................................11

3.2.4 ከፊል የዳኝነት ስልጣን (Quasi-judicial competence)................................................................................11

3.3 የብሄራዊ ሰብአዊ መብትን የሚመለከቱ ሌሎች ሕጎች.....................................................................................11

3.4 የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ሚና......................................................................................................11

3.4.1 የሰብአዊ መብት ጥበቃ.............................................................................................................................11

3.4.2 የሰብአዊ መብት ግንዛቤ ማስፋፋት ሚና.....................................................................................................11

3.5 የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት በኢትዮጵያ................................................................................................11

ምዕራፍ 4...............................................................................................................................................................11

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኢሰማኮ ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በማስጠበቅና በማስከበር ያለው ሚና................11

4.1 የኢሰማኮ የህግ መሰረት...................................................................................................................................11

4.2 የኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ ይዘት አጭር ትንተና...............................................................................................11

4.3 ኢሰመኮ መብቶችን ለማስጠበቅና ለማስከበር የሚጠቀምባቸው ስልቶች...............................................................11

4.3.1 የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ.................................................................................11

4.4 የሰብአዊ መብት ትምህርት በኢሰመኮ አዋጅ......................................................................................................11

ምዕራፍ 5...............................................................................................................................................................11

ግኝቶችና ማጠቃለያ...............................................................................................................................................11

5.1 ግኝቶች.........................................................................................................................................................11

5.2 ማጠቃለያ.....................................................................................................................................................11
ምዕራፍ አንድ
ጠቅላላ መግቢያ
1. መግቢያ
በሰብአዊ መብቶች ፅንሰ ሀሳብ መሠረት መብቶችን ተፈፃሚ ለማድረግ በመንግስታት ላይ የተለያዩ ግዴታዎች ተጥለዋል፡፡
መንግስታት የህዝቦች ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማስቻል ሰብአዊ መብቶችን የማክበር (Obligation to Respect)፣
የመጠበቅ (Obligation to Protect) እና የማሟላት (obligation to fulfill) ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡1 እነዚህ ግዴታዎች የሚነሱት
ከሶስት ዋና ዋና ምንጮች ነው፡፡ እነርሱም ዓለም አቀፍ ሕጎች፤ ውሎችና፣ ስምምነቶች፤ አህጉራዊ ስምምነቶች እና ሃገራት
የሚያወጧቸው ህግጋተ-መንግስታት ናቸው፡፡2
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት ሰብአዊ መብቶችንና መሠረታዊ ነፃነቶችን ለማክበር፣ ለማስከበርና ለማረጋገጥ
ካቋቋማቸው ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አንዱ ነው፡፡ ኮሚሽኑም በተቋቋመበት አዋጅ መሠረት
የተለያዩ አገልግሎቶችን ማለትም በግለሰቦች የሚቀርቡ ወይንም በተቋሙ አነሳሽነት የሚካሄዱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን
በመመርመር፣ በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር፣ ሰብአዊ መብቶች መከበራቸውን በመከታተል እና ጥናት በማካሄድ
መንግስትን በማማከር እና በሴቶች ህፃናትና ሌሎች ትኩረት በሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ መብቶች ዙሪያ የተለያዩ ስራዎችን
በመስራት ለህዝቡ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ከላይ የጠቀስናቸውን ተግባራት በኮሚሽኑ እየተከናወኑ ቢሆንም በኮሚሽኑ
ማቋቋሚያ አዋጅ ዙሪያ የተካሄደ አጠቃላይ የህግ ዳሰሳ ጥናት አለ ብሎ መውሰድ አስቸጋሪ ነው፡፡ ከዚህም እሳቤ በመነሳት ይህ
ጥናት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ህገ-መንግስታዊ ሰብአዊ መብቶችን የማሳወቅ፤ መከበራቸውን የመከታተል እና
የመመርመር ኃላፊነት ከማቋቋሚያ አዋጅ አንፃር ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡
1.1 የጥናቱ መነሻ ሃሳብ (ዳራ)

ስለ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን መብቶችን ከማክበርና ከማስከበር አንጻር ከማየታችን በፊት ሰብአዊ

መብቶችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች በምን አይነት ሁኔታ በሕገ መንግስቱ ተካተዋል የሚሉትን ነጥቦችና የሰብአዊ

መብቶች እድገት በኢትዮጵያ ህገ መንግስት ውስጥ የሚለውን ነጥብ በአጭሩ ለመዳሰስ እሞክራለን፡፡

አሁን ስራ ላይ ያለው ህገ መንግስት ከመረቀቁ በፊት ከታሪክ እውነታ እንደምንረዳው በኢትዮጵያ የህገ መንግስት

እድገት ውስጥ ሶስት ሕገ መንግስቶች እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ እነሱም የ 1923 እ..አ ህገ መንግስት፣ የ 1948 እ..አ

ህገ መንግስት እና የ 1979 እ..አ ህገ መንግስቶች ናቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሶስቱ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስቶች

ለሰብአዊ መብቶች የሰጡት ስፍራ አሁን በስራ ላይ ካለው የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ጋር ሲነፃፀር ለግለሰብ

1
Marie__________Benebict dembour,what are human rights four schools of thought, human right quarterly vol.32
university of Oslo(2010),PP1-20
2
Malcom N, Shaw, international law,sir Robert jennings professor of international law university of Leicester, cambridge university
press (2008)(6thed)pp162-170
1
መብቶችና ለሕዝብ መብቶች በተገቢው ደረጃ ቦታ የሰጠ አይደለም፡፡ የ 1931 ሕገ መንግስት ለአብነት ብመለከት

ለሰብአዊ መብቶች አንዳችም ድንጋጌ ያላስቀመጠና ይልቁንም ህገ መንግስቱ ከንጉሱ ለህዝቡ በችሮታ የተሰጠ ነበር3፡፡

ህገ መንግስቱም የንጉሳዊ አገዛዙን ስልጣን ከማስጠበቅ የዘለለ ለብሄሮች የእምነት የቋንቋና የማንነት ጥያቄ ላይ ምንም

አይነት መልስ የሚሰጥ አልነበረም4 ተሻሽሎ እንዲወጣ የተደረገው የ 1948 ህገ መንግስትም ቢሆን እንደቀድሞ የንጉሳዊ
አገዛዙን ፍጹም የበላይነት (absolutism) ያስቀመጠ ነበር5፡፡

በ 1966 ዓ.ም የንጉሳዊዉን አገዛዝ በመጣል ስልጣን ላይ የወጣው አብዮታዊው የደርግ መንግስት ቀድሞ የነበረውን ህገ
መንግስትም ውድቅ በማድረግ ማንኛውንም ውሳኔ በራሱ መወሰን ጀመረ6፡፡ ከላይ ያየናቸው ሶስቱም ህገ መንግስቶች
ሰብአዊ መብቶችን ብቻ ሳይሆን በበቂ ሁኔታ ያልያዙት ሰብአዊ መብቶችንም ለማስከበር የሚረዱ እንደ ብሄራዊ
የሰብአዊ መብት ተቋሟት አይነቶችን ጭምር እውቅና አልሰጡም፡፡ የንጉሳዊ አገዛዝ መውደቂያ አከባቢ የ 1948 ህገ
መንግስት የማሻሻያ ረቂቅ ላይ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የሚመለከት ድንጋጌ አካቶ ነበር፡፡ 7 ደርግ መንግስት
ውድቀትን ተከትሎ በ 1983 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተለያየ አመለካከት ካላቸው የሰላምና የዲሞክራሲ ኃይሎች የተወከሉ
የፖለቲካ ፓርቲዎች ባደረጉት ሀገር አቀፍ ጉባኤ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት ቻርተር አጽድቋል፡፡ይህ ቻርተር
በመግቢያው ሁለተኛ አንቀጽ ላይ እንደሚያመለክተው የነጻነት፤ የእኩልነት መብቶችና የሁሉም ህዝቦች የራስን ዕድል
በራስ የመወሰን መብትና ሌሎች መርሆዎችና የፖለቲካ ኢኮኖሚ የማህበራዊ ህይወት ምሰሶዎች የሚሆኑበትን አዲስ
ምዕራፍ በመክፈት የኢትዮጵያ ህዝቦች ከዘመናት የጭቆና የኋላቀርነት ቀንበር አውጥቶ ደህንነታቸውና መብታቸው
የሚጠበቅበትን ሁኔታ አስቀምጧል፡፡8 እንዲሁም ይህ ጊዜያዊ የሽግግር ወቅት ቻርተር በመግቢያው ላይ ከገለጸው
በተጨማሪ በአንቀጽ ሁለት ስር ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ዘርፈ ብዙ መብት እንዳላቸውና እነዚህም መብቶች
ታገዱ ተረገጡ ወይም ተሸረፉ ብሎ ባመነበት ጊዜ የራሳቸውን ዕድል በራስ እስከ መገንጠል ድረስ የመወሰን መብት

ተግባራዊ የማድረግ መብት አረጋግጧል፡፡9 ከዚህ ጊዜያዊ የሽግግር ቻርተር መጠናቀቅ በኋላ እንደ ኢ.አ በ 1987 አሁን

ስራ ላይ ያለው የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት ሊፀድቅ ችሏል፡፡

በመግቢያውም ላይ ሕገ መንግስቱ የቆመበትን መሰረታዊ የመብት ምሰሶዎችን የያዘ ሲሆን ከእነዚህም መካከል

የኢትዮጵያ ብሄር በሄረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት፣ የልማት ዲሞክራሲና የህግ የበላይነት መርህ፣

የግለሰቦችና የቡድን መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶችን በጥቂቱ መጥቀስ ይቻላል፡፡ 10 የመንግስት አስተዳደር መዋቅርን

3
Fasil Nahom, constitution for the nation of nation ``the Ethiopian Prospect,The red sea press asmara,1997p.17
4
ዝኒከማሑ
5
ዝኒከማሑ
6
ዝኒከማሑ
7
Yemsrach Endale.The Roles and Challenges of ehiopian national human right institution in the Protection of human
rights in light of The Paris Principles,Masters Thesis Submitted to Central European University Department of Legl
Studies Budapest Hungary 2010 pp.14-16
8
የኢትዮጲያ ሽግግር ወቅት ቻርተር ጌዴራል ነጋርት ጋዜጣ 1.1983
9
ዝኒከማሑ አንቀጽ 2
10
የኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፕብሊክ ሕገ መንገረስት ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አንደኛ ዓመት ቁጥር 1 አ.አ-ነሐሴ 15 ቀን 1987 የሕዝብ
2
በተመለከተ በሕገ መንግስቱ መሰረት የተቋቋሙ ዘጠኝ የክልል መንግስታትና ሁለት በቻርተር የተቋቋሙ የከተማ

አስተዳደሮች አሉ፡፡11 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐፕሊክ ሕገ መንግስትም በተለያዩ አበይት ርእሰ

ጉዳዮች መካከል አንደኛው የሰብአዊ መብቶችና ነፃነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጭ የማይጣሱና የማይገፈፉ

መሆናቸውን በመቀበል የዜጎችና የህዝቦች ሰብአዊና ዲሞክራሲዊ መብቶች ይከበራሉ በማለት መደንገጉ ነው፡፡(አንቀጽ

10) ይህ መሰረታዊ መርህ ከአንቀፅ 13 ጀምሮ እስከ አንቀፅ 44 በሚዘልቀው በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት ይበልጥ

ተዘርዝሯል፡፡ ይህ ምዕራፍ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶችን በሁለት በመክፈል ሰብአዊ መብቶችን በክፍል አንድ

ከአንቀፅ 14-28 ዲሞክራሲዊ መብቶችን ደግሞ በክፍል ሁለት ከአንቀፅ 29-43 ዘርዝሮ አስፍሮአል፡፡12 ይህ የሰብአዊ

መብቶች ዝርዝር ከአጠቃላይ የሕግ መንግስቱ ድንጋጌ 1/3 ኛ ያህል ነው፡፡

ሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ ሕግ ውስጥ እንዴት ተካተዋል የሚለውን ነጥብ ስንመለከት ሁለት ማእቀፎችን

እናገኛለን አንደኛው የሕግ ማዕቀፍ ሲሆን ሁለተኛው ተቋማዊ ማዕቀፍ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐፕሊክ (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) ሕገ መንግስት ሰብአዊ መብቶችን የማስከበር እና የማክበር ግዴታ በዋናነት
በአገሪቱ መንግስት ላይ የሚወድቅ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በአንቀጽ 13(1) መሰረት በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፌዴራል
መንግሥትና የክልል ህግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚ እና የዳኝነት አካሎች በሕገ መንግስቱ የሰፈሩ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን የማክበርና
የማስከበር ኃላፊነት እንዳለባቸው በግልጽ ያስቀምጣል፡፡13 ከእነዚህ አካላት በተጨማሪ የአንድ አገር የሰብአዊ መብት አጠባበቅ ወደ ተሟላ
ደረጃ ሊደርስ የሚችለው ሁሉን አቀፍ የሆነ የአፈጻጸም ሥርዓት መዘርጋት ሲቻል ነው፡፡ ስለዚህም ሕገ መንግስቱ በአንቀጽ 9 ስለ ህገ መንግስቱ
የበላይነት ከመደንገግ ባሻገር ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግስት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማህበራት እንዲሁም ባለስልጣኖቻቸው ሕገ
መንግስቱን የማስከበርና የማክበር ኃላፊነት እንዳለባቸው በንኡስ አንቀጽ 2 ላይ አስፍሯል፡፡14 በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችንና መሰረታዊ
ነፃነቶችን በተሻለ ሁኔታ ለማስከበርና ለማስጠበቅ የተለያዩ ተቋማት ማለትም ተጠያቂነትን እና ብዝሃነትን መሠረት ያደረገ
የህግ አውጭ አካል፣ አስፈፃሚ አካል እና ፍርድ ቤቶች መኖራቸውን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

እነዝህ አካላት ሰብአዊ መብቶችን እንዲከበሩ ለማድረግ አስፈላጊ ቢሆኑም በእነዚህ ተቋማት ብቻ ሰብአዊ መብቶችን
ለማስከበር በቂ ነው ተብሎ አይገመትም፡፡ በዚህን ምክንያት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰብአዊ መብቶች በተሻለ ሁኔታ
እንዲከበሩና እንዲረጋገጡ አስፈላጊነቱን አምኖበት በህገ መንግስቱ አንቀፅ 55(14) ላይ በተቀመጠው አግባብ የኢትዮጵያ ሰብአዊ
መብት ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 210/1992 መሠረት ተቋቁሟል፡፡15

በአዋጁ መግቢያ ላይ እንደተመለከተው ኮሚሽኑ የተቋቋመበት መሠረታዊ ምክንያቶች የግለሰቦችን እና የብሄር ብሄረሰብ
መብቶች እንዲከበሩ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገቶችን ለማፋጠን የሕግ የበላይነትን እና

ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ፤መግቢያ


11
ዝኒከማሑ አንቀጽ 47(1)

12
ራስጌ 10 ምዕረፍ 3
13
ዝኒከማሑ አንቀጽ 13(1)
14
ዝኒከማሑ አንቀጽ 9 (2)
15
ዝኒከማሑ አንቀጽ 55 (14)
3
በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ መገንባት የፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ፣ ባህሎችና ሃይማኖቶች
ካለአንዳች ልዩነት እንዲራመዱ ለማስቻል ነው፡፡16

ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 210/1992 አንቀጽ 6 መሠረት የሰብዓዊ መብቶችን ከማስከበር፣ ከመጠበቅ እና ከማስፋፋት ጋር
ተያይዞ የሚነሱ የተለያዩ ተግባሮችን እንዲያከናውን ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በተለይም በዚህ ጥናት ሊታዩ ከታሰቡት
የኮሚሽኑ ስልጣንና ተግባራት መካከል ህብረተሰቡ ስለሰብአዊ መብት በቂ ዕውቀት ኖሮት መብቱን እንዲያስከብር
ማስተማር፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ ላይ እና መከበራቸውን መከታተልን ያጠቃልላል፡፡

ኮሚሽኑም ይህንን ታሳቢ በማድረግ ሰብአዊ መብቶችን ለህዝቡ ማስተማር፣ መከበራቸውን መከታተል፣ ጥሰቶችን
በመመርመር ረገድ በስራ ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳራቶችን ከማቋቋሚያ አዋጁ ይዘትና ወሰን አንፃር በአግባቡ
በመፈተሽ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግስት ላይ የሰፈሩ ድንጋጌዎችንና በተለይም በምዕራፍ ሶስት ሥር የተደነገጉት
መሠረታዊ መብቶችና ነፃነቶች ኮሚሽኑ እነዚህን መብቶች በአግባቡ መጠበቃቸውን የመከታተል ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
ነገር ግን በማቋቋሚያ አዋጁ በርካታ ተግባራት ቢሰጡትም በአዋጁ አፈፃፀም ላይ የተለያዩ ተግዳራቶች መኖራቸውን
ማስተዋል ይቻላል፡፡ ከእነዚህ ችግሮች መካከል የኮሚሽኑ ተደራሽነት ጉዳይ፣ በአዋጁ ላይ ለሰብአዊ መብት ጥሰት
ተጋላጮች ማለትም በሴቶች፣ በሕፃናት፣ በአካል ጉዳተኞች እና በአረጋውያን መብቶች ዙሪያ ግልፅና በቂ የሆኑ
ድንጋጌዎች አለመቀመጡ አዋጁን ለመተግበር በቂ የሆኑ ደንቦችና መመሪያዎች፣ ቀጣይነት ያላቸው ፕሮግራሞችና
ሌሎች የአሰራር ስልቶች አለመቀየሳቸው በአዋጁ አፈፃፀም ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ማድረሳቸውን በመገንዘብ ይህ ጥናት
ሊካሄድ ችሏል፡፡

1.2 ስለ ብሄራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት ተዛማጅ ድርሳናት


መንግስታት ሰብአዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር በዓለም አቀፍ ደረጃ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣

አህጉራዊ ድርጅቶች እና ሌሎች ብሄራዊ ተቋማት አቋቁመዋል፡፡ ምንም እንኳን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰብአዊ
መብቶችን አስመልክቶ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካኝነት የተቋቋሙ ልዩ ውክልና የተሰጣቸው አካላት
ቢኖሩም እነዚህ ድርጅቶች በእያንዳንዱ ነፃ አገር ጉዳይ ውስጥ ገብተው የሰብአዊ መብት ትምህርት ለማስፋፋት፣
የፖሊሲ ምክር ለመስጠትና ሰብአዊ መብቶች መከበራቸውን ለማረጋገጥ ብሎም ለመከታተል በተፈለገ መልኩ
ስለማይችሉ እ.አ.አ በ 1993 የ.ተ.መ.ድ ባካሄደው በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጉባኤ ላይ የሰብአዊ መብት ተቋማት
በብሄራዊ ደረጃ እንዲቋቋሙ ወስኗል፡፡ በዛው በተመሳሳይ ዓመት የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ (Paris
Principles On National Human Rights Institutions) የሚባለውን ዓለም አቀፍ ሰነድ ተቀብሎ አፅድቆታል፡፡

የፓሪስ ፕርንሲፕል በዋነኛነት ከያዛቸው መርሆች መካከል፤ ስልጣንና ሀላፊነት (Competence and responsibilities)

1. ስልጣንና ሀላፊነት (Competence and responsibilities)


2. ጥንቅር፣ ነጻነትና ብዝሀነት (Composition, independence and pluralism)
3. የአሰራር ስርአት (Methods of operation)
4. ከፊል የዳኝነት ስልጣን (Quasi judicial competence) የሚመለከቱ መርሆዎች ይገኙበታል፡፡

ከዚህ በላይ የተመለከትናቸው መርህዎች እንዳሉ ሆነው በብሄራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋሟት ዙሪያ የተሰነዱትን ተዛማጅ ድርሳናት
ስንመለከት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ፖሊሲ ምክር ቤት (International Council On Human Rights policy) የተባለው
16
የኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፕበረሊክ የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁጥር 210/1992 ዓ.ም መግቢያ
4
ዓለም አቀፍ ተቋም ስለ ብሄራዊ ሰብአዊ መብት ተቋሟት አይነቶችና ሚና በጥልቀት የጻፈ ሲሆን የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማት
በተለያዩ አገሮች የተለያዩ ስሞች ሊኖራቸው እንደሚችልም አስፍሯል፡፡ ለምሳሌ ያክል የሰብአዊ መብት ኮሚቴ፣
የሰብአዊ መብት ተቋም፣ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ እና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በመባል ሊጠሩ እንደሚችሉ አመላክቷል፡፡ 17

Guy Lamb, Victoria Maloka የሚባሉ ጸሃፍት ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማት የዜጎች መብት እንዲከበርና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን
ነጻነትና ብዝሃነት አክብረው መንቀሳቀስ አለባቸው በማለት የጻፉ ሲሆን ከብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማት ተቋማዊ አወቃቀርና ፖለቲካዊ
ሁኔታዎች አንፃር ህብረተሰቡ ከእነዚህ ተቋማት በርካታ አገልግሎቶችን ይጠብቃል፡፡ ምክንያቱም ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማት በሰብአዊ
መብቶች ጉዳይ ላይ በዋነኛነት እንዲሰሩ በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶአቸው የተቋቋሙ እንደሆኑ በጥናታቸው አሳይተዋል፡፡ 18

(Raj Kumar) የተባሉ የዘርፉ ምሁር ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት መብቶችን ከማስከበርና ከማስጠበቅ አንጻር ትልቅ ሚና እንዳላቸው
በማሳየት ብዙ ጊዜ በሲቪልና በፖለቲካ መብቶች ላይ ትኩረት ስለ ሚያደርጉ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የባህላዊ መብቶችን ረስተዋቸዋል
በማለት ይተቻሉ፡፡ እንደዚህ ጸሃፊ ሀሳብ ከሆነ ተቋሟቱ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በባህላዊ መብቶችም ዙሪያ መስራት እንደሚገባቸው
የመፍትሄ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ ተቋማት ሌሎች የዲሞክራሲ አካላትን በመደገፍ የሰብአዊ መብት ጉዳይ በማንኛውም
ማህበረሰብ ውስጥ የፖለቲካ ተዋስዎ እንዲሆን ማረጋገጥ ይገባቸዋል በማለት በጽሁፋቸው ላይ አስፍረዋል::19

(Sonea Cardenas) የተባሉ ጸሀፊ ስለ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ውስብስብ ባህሪ ዙሪያ ያጠኑ ሲሆን የጥናታቸውም ትኩረት
ተቋሟቱ በሚያወጡት መስፈርቶች፣ በሚያረቋቸው ህጎች፣ በተቋሟቱ ነጻነት፣ ተጠያቂነትና ተቀባይነት ዙሪያ ነው፡፡ እንደ ጸሃፊዋ ጥናት ከሆነ
ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት የሚቋቋሙበት ዋና ዓላማ ዓለም አቀፍ ጫናን ለማርገብና ግለሰቦች፣ ህብረተሰቡ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ
ያልሆኑ ተቋማት ስለ ሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ውስጣዊ አሰራሮቻቸውን በመገንባት ከሰብአዊ መብቶች አያያዝ ጋር የሚቃረኑ
ፖሊሲዎችና ህጎች እንዲሻሻሉ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ነው፡፡20

(Danish Center For Human Rights) በብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ውጤታማነት፣ ነጻነት፣ የስልጣን ገደብና
በከፊል የዳኝነት ስልጣን ዙሪያ ንጽጽራዊ ጥናት በአፍሪካ፣ በኢስያ በአውሮፓና በላቲን አሜሪካ ዙሪያ ጥናት አካሂዷል፡፡21

(Hossain) የተባሉ የዘርፉ ተመራማሪ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በግንቦት 1990 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንና
የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ለማቋቋም በተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ዓለም ላይ ስላሉ የብሄራዊ የሰብአዊ
መብት ተቋሟት ተሞክሮዎች አስመልክቶ የጥናት ጽሁፍ አቅርበው ነበር፡፡ እንደዚህ ተመራማሪ ሀሳብ ከሆነ በዚህ ጉባኤ
ላይ የቀረቡት ጥናቶች አንድ ላይ ያሳየ ሲሆን ከተጠናቀሩት ጥናቶች መካከል አንዳንድ ጽሁፎች የተዘጋጁት ተቋሟቱን
በሚመሩት ሹመኞች በመሆኑ ባለስልጣናቱ ያቀረቡት ጥናቶች ስለ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት መሬት ላይ
ያለውን እውነተኛና ትክክለኛ ስእል ላያሳይ እንደሚችል በጥናቱ አውስቷል፡፡22

ስለ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ተዛማጅ ድርሳናት ዳሰሳ ለማጠቃለል ከላይ ያየናቸው ተመራማሪዎች
በምርምራቸው ያገኙት ግኝቶች ቢኖሩም ይህ ጥናት የሚያተኩረው በዋነኛነት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን
17
Performance and lejitimacy “National human Right Inistitutions,(international Council on Human Riggts policy)2000
18
Guylamb, Victoria Maloka ,Deffenders of human right,Manajers of conflict ,Builders of peace ?national human rights institutions in Africa
(2005)p.152
19
Kumar,Raj. “national human rights institutions”good govrernace perspectives on institutionaaliztion of human right amercan university
international low review 19,no. 2(2003) 259-300
20
S.cardenas,working paper adaptive states “the proliferation of national human right inistitutions (2001)(available at
http”//www.ksg.harvard.edu/cchrp/Web%20Papers/Accessed on May 26 2016
21
Lindholt,lone :nlindsnaes birgit :yigen,kristile (eds)inational human right institution articles and working perpers,danish ceter for human
right 2001,pp.59-83
22
Dr kamal hossain ,human right Commissions and ombudsmal offices national experiences throughout the world, Martinus Mijhoff
Publishers,2000
5
ህገ-መንግስታዊ ሰብአዊ መብቶችን የማስተማር፣ መከበራቸውን የመከታተል እና ጥሰቶችን የመመርመር ኃላፊነት፣ ተግባር፣
ይዘቱ እና ወሰኑን ከኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ አንጻር በጥልቀት በመፈተሽ የፖሊሲና የህግ አቅጣጫ ማስቀመጥ ላይ ይሆናል፡፡

1.3 ጥናቱ የሚያነሳቸው ችግሮች

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶችና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች በእያንዳንዱ አገር ውስጥ
ተፈጻሚነት ሊያገኙ ይገባቸዋል የሚለው የምሁራን ክርክር በሁሉም የዓለም ክፍል እያደገ የመጣ ወቅታዊ አስተሳሰብ
ነው፡፡ ይህንን አስተሳሰብ የሚያጠናክርልን በዓለም አቀፍ ደረጃ የወጣው የፓሪስ መርሆዎች ብሄራዊ የሰብአዊ መብት
ተቋሟት ሰብአዊ መብቶችን ለማስጠበቅና ለማስከበር ግዴታ እንዲወጡ ሃላፊነት ይጥልባቸዋል፡፡ ምንም እንኳን
እነዚህ ተቋሟት ሰብአዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር ትልቅ ሚና ቢኖራቸውም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ
እንዳይወጡ የሚያደርጓቸው ችግሮች በየጊዜው ይከሰታሉ፡፡ ከእነዚህም ችግሮች መካከል የሁለገብ ተደራሽነት ችግር፣
ምክረ ሀሳቦችን የማስፈጸም ችግር፣ የተቋሟቱ ነጻነት ያለመጠበቅ ችግር፣ የግንዛቤ ችግርና የአሰራር አፈጻጸም
ችግሮችን ማንሳት ይቻላል፡፡23

እነዚህን ችግሮችን ታሳቢ በማድረግ በዚህ ጥናት የሚዳሰሰው ርዕሰ ጉዳይ ኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶችን ግንዛቤ
ከማስፋፋት፣ ጥሰቶችን ከመመርመር እና መከበራቸውን ከመከታተል አንጻር በቂ የሕግና የአሰራር ጥናት አለ ብሎ
መውሰድ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ኮሚሽኑ እነዚህን ተግባርና ኃላፊነቶቹን በሚወጣበት ወቅት በተደራጀ የአሠራር ስርዓት፣
በማቋቋሚያ አዋጁና ኮሚሽኑ በሚያወጣቸው የውስጥ መመሪያዎች መሰረት መሆን እንዳለበት ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን
ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ጥናት በሚዳሰሱ ሶስቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል
በቂ የውስጥ ሕጎች በኮሚሽነሮች ጉባኤ ወጥቶ አልፀደቀም፡፡ ከዚህም የተነሳ ተግባራቱ በሚከናወኑ ጊዜ ብቸኛው ህጋዊ
መሰረታቸው የሚሆነው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ይሆናል፡፡

ጥናቱ እንዲካሄድ ያስፈለገበት ሌላኛው ምክንያት የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ፀድቆ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ
በተቋሙ አዋጁን አስመልክቶ የተካሄደ በቂ ጥናት አለ ብሎ ለመውሰድ አዳጋች በመሆኑ ነው፡፡ የተካሄዱት ሌሎች
ጥናቶችም አብዛኞቹ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እና መምህራን አማካኝነት የተዘጋጁ ፅሁፎች ናቸው፡፡
ስለዚህ ይህ ጥናት በኮሚሽኑ ቢካሄድ በአዋጁ ላይ ያሉትን ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶችን እንዲሁም በአዋጁ አፈፃፀምና
በተቋሙ አጠቃላይ አሰራር ላይ የሚታዩ የሕግ ክፍተቶችና ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማስቀመጥ
ይረዳል፡፡
1.4 የጥናቱ ዓላማዎች

1.4.1 አጠቃላይ ዓላማ

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የኢሰመኮ ሰብአዊ መብቶችን የማስተማር፣ መከበራቸውን የመከታተል እና ጥሰቶችን
የመመርመር ኃላፊነት፤ ተግባር፤ ይዘቱ እና ወሰኑ ዙሪያ ማቋቋሚያ አዋጁን በመፈተሽ ጥናት በማካሄድ ኮሚሽኑ በሕገ
መንግስቱና በማቋቋሚያ አዋጁ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል አቅጣጫ ማመላከት ነው፡፡
1.4.2 ዝርዝር ዓላማ ዎች
ይህ ጥናት በተጨማሪ የሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎች ይኖሩታል፡፡

23
ዝኒከማሑ
6
 ሰብአዊ መብቶችን በማክበርና በማስከበር ረገድ ችግሮችን ለመለየት የማቋቋሚያ አዋጁን ድንጋጌዎችን
መፈተሽ፤
 በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ውስጥ የተመለከቱት ስልጣንና ተግባራት ከሰብአዊ መብት ጥበቃና ግንዛቤ
ማስፋፋት አንጻር የሚኖራቸውን አዎንታዊ እና አሉታዊ ሚና መለየት፤ እና
 በሚለዩት ጠንካራ ጎኖች እና ክፍተቶች መሰረት በማድረግ የኮሚሽኑን ውስጣዊ አሰራሮችን ለማጠናከርና
ኮሚሽኑ አገልግሎቶችን በፍጥነት፣ በጥራት እና በተሟላ ተደራሽነት ለህብረተሰቡ እንዲሰጥ ለማስቻል
የጥናቱን ግኝቶችን ማስቀመጥ፡፡

1.5 የጥናቱ ወሰንና ውስንነት


1.5.1 የጥናቱ ወሰን
ጥናቱ የሚሸፍነው ዋነኛ ጉዳይ የኢሰመኮ ህገ-መንግስታዊ ሰብአዊ መብቶችን ማስተማር፣ መከበራቸውን የመከታተል እና
ጥሰቶችን የመመርመር ኃላፊነት፤ ተግባር፣ ይዘቱ እና ወሰኑ ከማቋቋሚያ አዋጁ አንጻር መፈተሸ ይሆናል፡፡
1.5.2 የጥናቱ ውስንነት
በዚህ ጥናት እንደ ውስንነት አጥኝውን የገጠመው የተመረጠው የጥናት ርእስ እጅግ ሰፊ መሆኑ ነው፡፡ በርእሱ
ላይ የተመለከቱት የሰብአዊ መብት ምርመራ፣ ክትትልና የግንዛቤ ማስፋፋት ተግባራት በተናጥል እንደ ርእስ
በመያዝ ጥናት ሊካሄድባቸው ይችላል፡፡ የተመረጠው የጥናት ርእስ ከመስፋቱ የተነሳ ተገቢ የሆኑ ሰነዶችን
ለመሰብሰብ፣ ለማንበብና ለመተንተን በቂ ጊዜ አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን እነዚህን ውስንነቶች ለመቅረፍ አጥኝው
ከመደበኛ የስራ ስአት በተጨማሪ ትርፍ ጊዜውን በመጠቀም ቀጥተኛና አግባብነት ያላቸውን ሰነዶችን በመጠቀም
ያሉትን ውስንነቶች ለመቅረፍ ጥረት ተደርጓል፡፡
1.6 ጥናቱ የሚመልሳቸው ጥያቄዎች

1.6.1 የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ በተመለከተ

ሀ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መመርመር ምን ማለት ነው?

ለ. የኢሰመኮ የምርመራ ሀላፊነት የሚያካትታቸው ተግባራት የትኞቹ ናቸው?


ሐ. የኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመመርመር የሚያስችል በቂ ድንጋጌዎችን ይዟል?

መ. በምርመራ ወቅት የሚገጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል በቂ የሕግ ማዕቀፍ አለወይ?


1.6.2 የሰብአዊ መብት ክትትል በተመለከተ
ሀ. ሰብአዊ መብቶች መከበራቸውን መከታተል ማለት ምን ማለት ነው?
ለ. የሰብአዊ መብት ክትትል ህገ መንግስታዊ መብቶችን ከማስከበር አንጻር ያለው ሚና ምንድነው?
ሐ. የኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ ስለ ሰብአዊ መብቶች ክትትል ተግባር በቂ ድንጋጌዎችን አስቀምጧል ማለት ይቻላል?
1.6.3 የሰብአዊ መብት ግንዛቤ ማስፋፋት በተመለከተ
ሀ. ሰብአዊ መብቶችን ማስተማር ማለት ምን ማለት ነው?
ለ. የሰብአዊ መብት ግንዛቤ ማስፋፋት አላማውስ ምንድን ነው ?
ሐ. የሰብአዊ መብት ትምህርት መማር ወይንም መሰልጠን ያለበትስ ማነው?
መ. የኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ የሰብአዊ መብቶችን ግንዛቤ ለማስፋፋት የሚያስችል በቂ ድንጋጌዎችን
አስቀምጧል?

7
1.7 የጥናቱ ስነ ዘዴ፣ የጥናቱ ስልትና የመረጃ ምንጭና ማሰባሰቢያ ዘዴ

1.7.1 የጥናቱ ስነ ዘዴ (Research methodology)


ጥናቱ የሚጠቀመው ስነ ዘዴ የህግ ጥናትና ምርምር ስልት (Doctrinal Research method) በመባል የሚታወቀውን ዘዴ
ነው፡፡ የሕግ ጥናት ምርምር ስልት ማለት በሕጎች ውስጥ ተካተው ያሉትን የሕግ ድንጋጌዎች አግባብነታቸውን ወይም
ውስንነታቸውን መመርመር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በሕጎቹ ውስጥ መካተት የነበረባቸው ድንጋጌዎች ሳይካተቱ ቀርተው
እንደሆነ በጥናት በማስደገፍ ድንጋጌዎቹ ሕጎቹ ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ ሕጎቹ እንዲሻሻሉ ወይንም እንዲሻሩ
የሚያደርግ የጥናት ስልት ነው፡፡24 ይህ የጥናት ስልት የተመረጠበት ዋናው ምክንያት ከጥናቱ ርዕስ እንደምንረዳው የኮሚሽኑ
ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ የተመለከተውን ተግባር ይዘትና ወሰኑን ስለሚዳስስ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ
አዋጅ ቁ. 210/92 ተግባር ይዘትና ወሰን ተገቢ የሆነ ትንተና በማድረግ ይፈትሻል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ ውስጥ
ሰብአዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር የሚረዱ የሀገሪቱን ህጎችና ሰብአዊ መብቶችን ከማክበር እና ከማስከበር አንፃር
ተያያዥነት ያላቸውን ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህጎች በአግባቡ የሚዳስሱ ይሆናል፡፡
1.7.2 የጥናቱ ስልት
ጥናቱ (Qualitative) ዓይነታዊ የጥናት ስልት የተጠቀመ ሲሆን የአቻ ተቋማትን ልምድ ከሌሎች አገሮች ለመቅሰም ሲባል
ንፅፅራዊ ሞዴል (Comparative Model) ተጠቅሟል፡፡ ጥናቱ ከአቻ ተቋማት ልምድ ለመቅሰም ከአፍሪካ የዩጋንዳን ህገ
መንግስት፣ የደቡብ አፍሪካ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ህግና ከአፍሪካ ውጪ ደግሞ የህንድን የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ህግ
ኢሰመኮከኢሰመኮ አዋጅ ጋር በማነጻጸር መወሰድ ያለበትን ልምዶች ጠቁሟል፡፡ እነዚህ አገሮች የተመረጡበት ምክንያት
የሰብአዊ መብት ተቋሟቸው ጠንካራ የህግና የአሰራር ስርአት እንዳላቸው በአለምአቀፍ ደረጃ እውቅና በማገኘታቸው
ነው፡፡

1.7.3 የመረጃ ምንጭና ማሰባሰቢያ ዘዴ /Data source and data gathering technique/

ጥናቱ ከሕጎች ትንተና ባሻገር የተለያዩ የመረጃ ማሰባሰቢያ ስልቶችን የተጠቀመ ሲሆን በኮሚሽኑ ውስጥ የሚሰሩ ከጥናቱ
ርእሰ ጉዳይ ጋር በቀጥታ የሚመለከታቸው የተወሰኑ ባለሙያዎች ጋር ቃለ ምልልስ (Inetrview) በማካሄድ ጥናቱ ሊካሄድ
ችሏል፡፡ ቃለ ምልልሱ የተካሄደበት ምክንያት ከአዋጁ ባሻገር ተጨማሪ መረጃዎችን በማግኘት የጥናቱን የመረጃ ክፍተት
ለመሸፈን ነው፡፡ ቃለ ምልልሱም የተደረገበት አካሄድ ናሙናዊ ስልቶችን ባለመጠቀም ነው፡፡ ምክነያቱም ጥናቱ በዋንኛነት
የሚያተኩረው የህግ ትንተና ላይ ስለሆነ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ እንደ መጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ምንጭ ጥናቱ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት፣ የኢሰመኮ ማቋቋሚያ
አዋጅ ቁ. 210/92፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነዶች በተለይም የፓሪስ መርሆዎችና አህጉራዊ ስምምነቶችን
ተመልክቷል፡፡
እንደ ሁለተኛ ደረጃ የመረጃ ምንጮች ሆነው ሊያገለግሉ የሚችሉ መፃህፍት፣ በሕግ ወይም ሰብአዊ መብት ዙሪያ
የተጻፉጽሁፎችንና ተዓማኒነት ያላቸው ድረ-ገፆች ለጥናቱ ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

1.8 የጥናቱ ጠቀሜታ

ይህ ጥናት በማቋቋሚያ አዋጅ አንቀፅ 6 ላይ ለኮሚሽኑ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባር ሥራ ላይ በማዋል ረገድ ከፍተኛ
ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተለይም ሰብአዊ መብቶችን ከማስተማር፣ ከመከታተልና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ከመመርመር
አንፃር ያሉትን የአሰራርና የህግ ክፍተቶችን የሚለይ በመሆኑ ኮሚሽኑ መውሰድ ያለበትን እርምጃ ማለትም የፖሊሲና የህግ

24
Dr. kushal vibhute and filipos aynelem,legal research methods,by justice and legal system research institute 2009 22
8
ማዕቀፍን እንዲሁም ሌሎች አዋጁን ሥራ ላይ ለማዋል የሚረዱ የአሰራር ስልቶች እንዲቀየሱ ይጠቁማል፡፡ በተጨማሪም ይህ
ጥናት በሰብአዊ መብት ምርምር ላይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ተመራማሪዎች፣ ለፖሊሲ አውጭዎች፣
ለአስፈፃሚ አካላትና በኮሚሽኑ ውስጥ ለሚከናወኑ ተያያዥ ስራዎች እንደ ግብአት ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡

1.9 የጥናቱ አወቃቀር

ጥናቱ በአጠቃላይ አምስት ምዕራፎች የያዘ ሲሆን በምዕራፍ አንድ መግቢያ፣ የጥናቱ መነሻ፣ ጥናቱ የሚያነሳቸው ችግሮች፣
የጥናቱ አላማዎች፣ የጥናቱ ስነ ዘዴ፣ ስልትና የመረጃ አሰባሰብ፣ የጥናቱ ወሰንና ውስንነት፣ የጥናቱ ጠቀሜታና የጥናቱን
አወቃቀር፤ በምዕራፍ ሁለት ሰብአዊ መብትና የኢትዮጵያ ህጎች፣ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች በኢትዮጵያ ህገ መንግስት
ያላቸው ቦታና ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር ተቋማዊ ማዕቀፍ በኢትዮጵያ፤ በምዕራፍ ሶስት ስለ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት
ተቋሟት መሰረታዊ ሀሳቦችና ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት በኢትዮጵያ፤ በምዕራፍ አራት የኢሰመኮ የህግ መሰረት፣
የማቋቋሚያ አዋጅ ይዘት ትንተና፣ በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት ሰብአዊ መብቶችን ስለማስተማር፣ መከበራቸውን
ስለመከታተልና ጥሰቶችን ስለ መመርመር ዳሰሳ ያደረገ ሲሆን በምራፍ አምስት ደግሞ ግኝቶችና ማጠቃለያ አካቶ ይዟል፡፡

9
ምዕራፍ ሁለት

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር የተዘረጉ የህግና የተቋም ማዕቀፎች

2.1 ስለ ሰብአዊ መብቶች ፅንሰ ሃሳብ አጠቃላይ ምልከታ


ሰብአዊ መብት ማለት የሰው ልጅ በተፈጥሮ ሰው በመሆን ብቻ የተጎናፀፈው መብት ሲሆን ከእነዚህ መብቶች

መጠበቅ ውጭ መኖር ለሰው ልጆች አዳጋች ነው፡፡ ሰብአዊ መብቶች በባህሪያቸው ተፈጥሮአዊ፣ የማይነጣጠሉ፣

የማይገሰሱ እና ሁሉ አቀፋዊ ናቸው፡፡25

ይህ አስተሳሰብ በግልፅ የሚያመላክተን የሰው ልጅ ክብሩ በእኩልነት መጠበቅ እንዳለበትና በግለሰቦችም ሆነ

በመንግስታት ላይ መብቶች እንዲከበሩ ግዴታዎችን የሚጥል መሆኑን ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ለጥቂት የህብረተሰብ

ክፍሎች በተለይም ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ክፍሎች በልዩነት የሚደረግላቸው የመብቶች አተገባበር ሁኔታዎች ከላይ

የተመለከትነውን ሁሉ አቀፋዊነት አስተሳሰብን የሚቃረን ሳይሆን ከዚህ ቀደም መብቶቻቸው መጠበቅ እየተገባው

ያልተጠበቀላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በድጋፋዊ እርምጃ በታሪክ ሲታዩ የኖሩበትን የበታችነት አስተሳሰብንና የመብት

ጥሰቶችን በማስወገድ ስህተቶችን በማረም የሚወሰድ የመብት ማስከበሪያ ስልት ነው፡፡26

ሰብአዊ መብቶች የሰው ልጆች ከሚጠቀሙባቸው ሌሎች መብቶች የተለዩ ናቸው ለዚህም አንዱ ምክንያት ከህግ

የማይመነጩ ነገር ግን በህግ ዕውቅና የሚሠጣቸው መብቶች በመሆናቸው ነው፡፡ ሰብአዊ መብቶች ተብለው

ከሚጠቀሱት መካከል የህይወት፣ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት፤ የመደራጀት መብት፣ የመሰብሰብ መብት፣

የመዘዋወር መብት፣ በዘፈቀደ ያለመያዝና ያለመታሰር መብት፣ የአመለካከት እና ሃሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ

መብት፣ የጤና መብት፣ የትምህርት መብት፣ የልማት መብት፣ የክብርና የመልካም ስም መብት እና የእኩልነት

መብቶች እነዚህንና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡27

ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ያስፈለገባቸው ምክንያቶች የሰው ልጅ የተዋረደና ጎስቋላ ኑሮ እንዳይኖር

ለማድረግና ኢሰብአዊ አያያዞችን በማስወገድ የተሟላ ኑሮ እንዲኖር ለማስቻል ነው፡፡ ዜጎች እምቅ

ኃይላቸውን እንዲጠቀሙ፣ ንቁ ተንቀሳቃሽ እና ውጤታማ ህብረተሰብ እንዲኖር የሰብአዊ መብቶች መከበር

25
United Nation training manual on human right,1987
26
ዝኒ ከማሁ
27
ዝኒከማሑ
10
እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በዜጎች መካከል መፈቃቀርንና መከባበርን ለማስፈን፣ ሰላምንና የአገር አንድነትን

ለማረጋገጥ ፍቱን ዋስትናም ነው፡፡28

የሰብአዊ መብት ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ማግኘት የጀመረው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አገራት በዜጎቻቸው ላይ
ከሚያደርሱት ጭቆና እና በደል ሊታቀቡ እንደሚገባ በማመን ነው፡፡ ይህንንም መሰረት አድርጎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (የተ.መ.ድ.)
ቻርተር በ 1945 ሲወጣ በመግቢያው ላይ በግልጽ ካሰፈራቸው መነሻዎች መካከል በመሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች፣ በሰው ልጆች ክብር እና
ጥቅም እንዲሁም በወንዶች እና ሴቶች እኩልነት መብቶች ላይ እምነት መጣል የሚለው ይገኝበታል፡፡ 29

በቻርተሩ አንቀጽ 1 ላይ ካሉት የተ.መ.ድ. ዓላማዎች መካከል የሰብአዊ መብቶችን ማስፋፋት እና ማበረታታት አንዱ ሲሆን በአንቀጽ 13 ላይ
የድርጅቱ አጠቃላይ ጉባኤ ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት የሚረዱ ጥናቶችን አድርጎ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን እንዲጠቁም ኃላፊነት
ተጥሎበታል፡፡ ከዚህ ባሻገር ቻርተሩ በዝርዝር ሰብአዊ መብቶችን ባያስቀምጥም በአንቀጽ 55 ላይ የተ.መ.ድ. አካላት ላይ ዘርን፣ ጾታን፣ ቋንቋን
ወይም ኃይማኖትን መሰረት ያደረገ ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ ሰብአዊ መብቶች እና ነጻነቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበሩ የማድረግ
ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ አባል አገራት በጋራ እና በተናጠል ከድርጅቱ ጋር በትብብር ሊሰሩ ቃል እንደገቡ በአንቀጽ 56 ላይ
በግልጽ አስፍሯል፡፡30

የተ.መ.ድ ከማቋቋሚያ ቻርተሩ በተጨማሪ ሰብአዊ መብቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጠበቁ ለማስቻል መንግስታት የተለያዩ የሠብአዊ
መብት ሰነዶችን ተቀብለው እንዲያፀድቁ አድርጓል፡፡ ከእነዚህም ሰነዶች መካከል፡-

 ማንኛውም አይነት የዘር አድልዎን ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት 1965፣

 ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት 1966፣

 የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የባህልና የማህበራዊ መብቶች ስምምነት 1966 ወዘተ ናቸው፡፡31

2.2 ሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት

በኢትዮጵያ ህገ መንግስት ታሪክ ከንጉስ ኃ/ሥላሴ አገዛዝ በፊት የሰብአዊ መብት ጉዳይ በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ ሆነ

በሕግ አለመኖሩን የተለያዩ ጥናቶች ይጠቅሳሉ፡፡ እ..አ ከ 1923 ዓ.ም በፊት የተፃፈ ሕገ መንግስት ኢትዮጵያ

አልነበራትም፡፡ ይህ ሲባል ግን ያልተፃፈ ሕገ መንግስት የለም ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም በሕገ መንግስት ደረጃ

የሚጠቀሱ ሶስት ልማዳዊ ወይንም ባህላዊ ህጎች እንደነበሩ መውሰድ ይቻላል፡፡ እነዚህም፡- ፍትሃ ነገስት፣ ክብረ

መንግስት፣ ሥርዓተ መንግስት ናቸው፡፡32 እነዚህ ሕጎች ሕገ መንግስታዊ መርሆዎችን፣ ለንጉሱ ስረወ መንግስት

ታማኝ መሆንና በሃይማኖት ዙሪያ ትኩረት የሚያደርጉ ሰነዶች ናቸው፡፡ እ.አ.አ የ 1923 ሕገ መንግስት በኢትዮጵያ

የመጀመሪያ የተፃፈ ህገ መንግስት ሲሆን ይህ ህገ መንግስት የሰዎችን መብትና ፖለቲካዊ መብቶችን ለማረጋገጥ

28
ራስጌ 1
29
Charter of the united nations.san Francisco 1945 preamble
30
ዝኒከማሑ Art.1,13,55,56
31
ራስጌ 26
32
ራስጌ 2
11
የታወጀ ህግ ሳይሆን የንጉሱን ዘውዳዊ አገዛዝ ለማጠናከር የታቀደና በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ ሕገ መንግስታዊ

ሥርዓት እንዳላት ለማስመሰል የታወጀ ነው፡፡33 ይህ ሕገ መንግስት ከንጉሱ በችሮታ የተሰጠ በመሆኑ የዜጎችን

መብት በተመለከተ ምንም ዓይነት ድንጋጌ አላስቀመጠም ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ንጉሱ በዚህ ሕግ ሥልጣናቸው

ያልተገደበ በመሆኑ በማንኛውም ሰዓት በዜጎች መብቶች ላይ ጣልቃ የመግባትና ለሰዎች ስብዕና ክብር ቦታ

የማይሰጡ መሆናቸውን በጉልህ ያሳያል፡፡ የዜጎችን መብት በተሟላ መልክ ለማስጠበቅ የሚረዱ እንዲሁም ህገ

መንግስቱንም ደግሞ ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችል የማስፈፀሚያ ስልቶች ማለትም ሕጎችና ፍርድ ቤቶች

በአግባቡ አልተደራጁም እንዲሁም በዚህ ጠናት ውስጥ የተዳሰሰው ርእሰ ጉዳይ ማለትም የሰብአዊ መብት ኮምሽን

ተቋም አልነበረም፡፡34

እ..አ የ 1923 ሕገ መንግስት በ 1948 ህገ መንግስት ተሻሽሏል የተሻሻለው ሕገ መንግስት በፊት ከነበረው ሕገ

መንግስት ጋር ሲነፃፀር ለሰብአዊ መብቶች ልዩ ትኩረት የሰጠ እንደሆነ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች በመመልከት

መረዳት ይቻላል፡፡35 የ 1955 ቱ ሕገ መንግስት የተሻሻለበት አንዱ ምክንያት በተባበሩት መንግስታት አማካኝነት

ኢትዮጵያ በ 1948 የወጣውን የሰብአዊ መብቶች መግለጫ ተቀብላ በማፅደቋ ነው፡፡

ይህ ሕገ መንግስት ለተለያዩ መብቶች ዕውቅና ሰጥቷዋል ለምሳሌ ያክል፡-የመሰብሰብ መብት፣ የመደራጀት መብት፣

እና የምርጫ መብቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በዚህ ህገመንግስት መሰረት ህጎችን ለማስፈጸም የሚረዱ የተለያዩ

ተቋሟት የተደራጁ ሲሆን ስለ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ተቋም መኖር የሚያመላክት አንዳችም አይነት ድንጋጌ

አልነበረም፡፡ በእርግጥ የተለያዩ መብቶች ሕገ መንግስት እውቅና ቢሰጣቸውም ዜጎች መብቶቻቸውን በአግባቡ

እንዳይጠቀሙ የሚያደርጉ አሳሪ ሐረጎች (clawbacks)ነበሩ፡፡ ምንም እንኳ ከላይ ያስቀመጥናቸው መብቶች ቢኖሩም

የሥልጣን ሽግግር ይተላለፍ የነበረው በንጉሱ ዘር ሐረግ ነገድ እንጂ በዲሞክራሲያዊ የሥልጣን አካሄድ አልነበረም፡፡ 36

በወቅቱ የዜጎች መብቶች ባለመከበራቸው በተለይም የአርሶ አደሩ የመሬት መብት ባለመረጋገጡ የኢኮኖሚ መብት

ተጠቃሚ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ በመሆኑም የተለያዩ የሙያ ማህበራት፣ ተማሪዎች ማህበር፣ የታክሲ ማህበራት፣ አርሶ

አደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በአገሪቷ ውስጥ የኢኮኖሚ መብቶችና ሌሎች ሰብአዊ መብቶች

33
ዝኒከማሁ
34
Helinaaze, assessing the effectiveness of the ethiopian human right commission in light of the 1991 Paris
principles ,A thesis submitted to the school of (graduate studies of addis abeba university college of social science
june 2014,P25
35
Adem Kassie Abebe, Human Right under the Ethiopian Constitiution a descriptive over view, mizan low review, vol.5,No 1,2011.
36
Tsegay Regessa, “making Legal sense of human Rights,The Judicial role in proteceting Human Right in
Ethiopia”mizan Low review,vol,3 No.2
12
ባለመከበራቸው እ.ኤ.አ በ 1966 ዓ.ም በተካሄደው አመፅ አማካኝነት የዘውዳዊ አገዛዝ ሥርዓት ለአንዴዬና ለመጨረሻ

ጊዜ ሊወገድ ችሏል፡፡ በምትኩም ጊዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ኮሚቴ(ደርግ) ሥልጣን የያዘ ሲሆን ሰብኣዊ መብቶች

በፅንሰ ሀሳብ ሆነ በተግባር የጠፋበት ጊዜ ነበር፡፡ አገሪቷም ያለ ህገ መንግስትና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ስትመራ

የቆየች ስትሆን ደርግ በመውደቂያው አካባቢ እ.ኤ.አ 1987 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት
ሊወጣ ችሏል፡፡37

ከደርግ መንግስት ውድቀት በኋላ በ 1983 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትና ለዴሞክራሲያዊ መብቶች በግልፅ
እውቅና የሰጠ የሽግግር ወቅት ቻርተር ወጥቷል፡፡ በዚህ ቻርተር ራስን በራስ የማስተዳደር እስከ መገንጠል መብት፣
የመደራጀት መብት፣ የመሰብሰብ መብቶችና ሌሎች መብቶችም ዜጎች እንዲጠቀሙባቸው በግልጽ እውቅና ሰጥቷል፡፡ 38

2.3 የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት

ከጊዚያዊ የሽግግር ቻርተር መጠናቀቅ በኋላ በ 1987 ዓ.ም ለሰብአዊ መብቶችና መሰረታዊ ነፃነቶች ዝርዝር እውቅና
የሰጠ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት ሊወጣ ችሏል፡፡

የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አወቃቀርን ስንመለከት በአስራ አንድ ምዕራፎች እና በአንድ መቶ ስድስት አንቀፆች የተከፋፈለ
ነው፡፡

በተለይም ይህ ህገ መንግስት ቀድሞ የነበሩት ህገ መንግስቶች እውቅና ያልሰጣቸው መብቶች ማለትም የብሔር
ብሔረሰቦች መብቶች፣ የህገ መንግስት መሰረታዊ መርሆች የሚባሉትን ሉዓላዊነት፣ የህግ የበላይነት፣ ሰብአዊና
ዲሞክራሲያዊ መብቶች፣ የሃይማኖትና የመንግስት መለያየትና የመንግስት አሰራር ግልጽነት የያዘ ሕገ መንግስት ነው፡፡39
መሠረታዊ መርሆዎች የሚባሉት ሕገ መንግስቱ የቆመባቸው ምሰሶዎች ወይም ህገ መንግስቱ የተገነባባቸው የማዘን ድንጋዮች
ናቸው፡፡

ከላይ ካስቀመጥናቸው ከህገ መንግስቱ መሰረታዊ መርሆዎች መካከል ሰብአዊ መብቶችን በተመለከተ አንቀጽ 10 ላይ እንደተጠቀሰው ሰብአዊ
መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ፣ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው፡፡ 40 ሕገ መንግስቱ መብቶችን በሁለት በመክፈል ሰብአዊና
ዲሞክራሲያዊ መብቶች ብሎ በግልፅ አስፍሮ እናገኘዋለን፡፡

1. ሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው፡፡


2. የዜጎች እና የሕዝቦች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ፡፡41
የኢ.ፌ.ዴ.ሬ ህገ መንግስት የተመሰረተበት ሌላው መሠረታዊ መርሆ ወይም ምሰሶ የህግ የበላይነት ነው፡፡ አንቀፅ 9 መመልከት
እንደሚቻለው ህገ መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ ነው፡፡ ህግ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን
ውሳኔ ከዚህ ሕገ መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት የለውም፡፡42

37
ዝኒከማሁ
38
ራስጌ 8
39
ራስጌ 10
40
ዝኒከማሑ አንቀጽ 10
41
ዝኒከማሑ አንቀፅ 10(1)እና(2)
42
ዝኒከማሑ አንቀፅ 9(1)
13
በዚህ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ መሰረት ህግ አውጪ፤ የፌዴራልም ሆነ የክልል ህግ አውጪዎች የህግ መንግስት ድንጋጌዎችን
የሚቃረን ህግ ማውጣት አይችሉም ቢያወጡም ኢ-ህገ መንግስታዊ ነው ተብሎ ዋጋ እንዳይኖራቸው ይደረጋል፡፡
በተጨማሪም የህግ አስፈጻሚው ውሳኔ ህገ መንግስቱን የሚቃረን ከሆነ ድርጊቱ ኢ-ህገ መንግስታዊ ተብሎ ድርጊቱ እንዲቋረጥና
የተገኘ ውጤትም ካለ ውድቅ ይደረጋል፡፡ ህግ አውጪው የሚያወጣቸውን ህጎች ኢ-ህገ መንግስታዊ ሊሆኑ ከሚችሉባቸው
ሁኔታዎች አንዱ በህገ መንግስቱ የተጠበቁትን መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች የሚያግዱ ወይም የሚሸረሽሩ ህጎች መሆናቸው
ነው፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ የወጣው ህግ ኢ-ህገ መንግስታዊ ነው ተብሎ ይሻራል በተመሳሳይም የህግ አስፈጻሚው ድርጊቶች
መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን የሚጥሱ ከሆነ ኢ-ህገ መንግስታዊ ናቸው ተብለው እንዲቋረጡ ይደረጋል፡፡43
ይህን ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ቀድሞ በስራ ላይ ውለው የነበሩ ከህገ መንግስቱ መርሆዎች ጋር የማይጣጣሙ ህጎች
እንዲሻሻሉ የተደረገ ሲሆን ለዚህ ተጠቃሽ የሚሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የተሻሻለው የቤተሰብ ህግና የወንጀል ህግ ይገኙበታል፡፡ አገሪቱ የምትቀርጻቸው
ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና ፕሮግራሞችም ይሄንን አንቀጽና ሌሎችን የህገ መንግስቱ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ የሚወጡ እና ለሰብአዊ
መብት መከበር እንደ መሳሪያ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡44
አንቀጽ 9 ንኡስ 2 ስንመለከት ደግሞ ማንኛውም ዜጋ የመንግስት አካላት የፖለቲካ ድርጅቶች ሌሎች ማኅበራት እንዲሁም
ባለስልጣኖቻቸው ሕገ መንግስቱን የማስከበርና ለሕገ መንግስቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው፡፡45
እነዚህ መሰረታዊ መርሆዎች በህገ መንግስቱ የተቀመጡበት ምክንያት በህገ መንግስቱ አማካኝነት እውቅና ያገኙትን ሰብአዊ
መብቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች በተሟላ ሁኔታ ለማስጠበቅ ነው፡፡ ከላይ መርጠን ያየናቸው የህገ መንግስት መርሆዎችን
መከበራቸውን የማረጋገጥ በተለይም ስለ ሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ የመፍጠር፣ መከበራቸውን የመከታተልና መብቶቹም
ተጥሰው ሲገኙ መርምሮ ውሳኔ በመስጠት መብቶችን የማስከበር ሀላፊነት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮምሸን ላይም
ተጥሏል፡፡ በዚህ ጥናት ምዕራፍ አራት ላይ በጥልቀትና በትንታኔ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
ሕገ መንግስቱ በምዕራፍ ሶስት ውስጥ ከአንቀፅ 14 እስከ 44 የተደነገገውን ሰፊ ትኩረት የሰጠው ለሰብአዊ መብቶችና
መሠረታዊ ነፃነቶች ጥበቃና እውቅና በመስጠት ነው፡፡46
ይህ ህገ መንግስት የዜጎች የሲቪልና የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ መብቶች እንዲሁም የልማት
መብቶች እንዲከበሩ ለማድረግ መብቶችን በግልጽ አስፍሮአል፡፡

ከአንቀጽ 14-44 ያሉት አንቀፆች ሕገ መንግስቱ በዓለም አቀፍ ስምምነቶች ውስጥ ተለይተው የታወቁ ሰብአዊ
መብቶችን ከምንጊዜውም በተሻለ ሁኔታ አካቶ መያዙን ለማረጋገጥ ከማስቻላቸውም በላይ ለሰብአዊ መብቶች ጎላ ያለ
ቦታ መስጠቱን በግልፅ ያመላክታል፡፡ ይህ ሆኖ እንዳለ በአንድ በኩል ሰብአዊ መብቶችን ተቀብሎ ሕጋዊ እውቅና
መስጠት በራሱ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ በሌላ በኩል ደግሞ በአገሪቱ የህግ ሥርአት ውስጥ እነዚህ መብቶች ተፈፃሚ
የሚሆኑበትን አስፈላጊ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡47
የሰብአዊ መብቶችን አከባበር አስመልክቶ ህግ አውጭው ህግ አስፈፃሚውን የሚቆጣጠርበት ሥርዓት ፍርድ ቤቶችን
ሰብአዊ መብትን የማስከበር ሀላፊነት እንባ ጠባቂ ተቋምና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ስለሚቋቋምበት ሁኔታ ገዢ የሆኑ
ድንጋጌዎችን ይዞ እናገኘዋለን፡፡48

43
አብዱማሊክ አቡበከር፣ ሕገ መንግስቱ ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር የዘረጋቸው የቁጥጥር እና የክትትል ሥርዓት ግቦት 1999 እ.አ ገጽ.193-201
44
መንበረ ፀሀይ፤ የኢትዮጲያ ሕግና ፍትህ ገፅታዎች ፤1999 እ.አ ገ.118
45
ራስጌ 10 አንቀፅ 9(2)
46
ራስጌ 37
47
ግርማ ወ/ሥላሴ (ዶ/ር),ሰብአዊ መብቶች ሕጎቹና አፈፃፀማቸው, የፍትሕ ሚኒስቴር, ነሃሴ 1999, ገ 26.
48
ዝኒከማሁ
14
2.4 የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገመንግስት ያላቸው ቦታ

የዓለም አቀፍ ህጎች ተቀባይነት እና ደርጃ እንደየሀገራቱ ይለያያል። ጠቅለል ብሎ ሲቀመጥ ግን በሁለት ይከፈላል።
የመጀመሪያው monist theory] ሲባል ሌላኛው ደግሞ [dualist theory] ይባላል።49 (monist theory) በሀገር ውስጥ ህጎች እና
በዓለም አቀፍ ህጎች ላይ ያለውን ልዩነት እውቅና አይሰጥም ወይም አይቀበልም።

ይህ ማለት ሁለቱም እንደአንድ ህግ ስርአት ነው የሚቆጠሩት እና የሚታዩት። አንድ ዓለም አቀፍ ህግ ወጣ ማለት ያለምንም
ቅድመ ሁኔታ በሀገሪቱ ህግ ውስጥ ህግ ሆኖ እንደሌሎቹ የሀገር ውስጥ ህጎች ተቀባይነት እና ተፈጻሚነት ያገኛሉ ማለት ነው።
በመሆኑም፣ በሁለቱ ህጎች መካከል መጣረስ ቢፈጠር ዓለም አቀፍ ህጎች የበላይነት ይኖራቸዋል። 50
ሁለተኛው [dualist theory] ዓለም አቀፍ ህጎች እና የሀገር ውስጥ ህጎች የተለያዩ እና ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው አድርጎ
ይቆጥራቸዋል። ዓለም አቀፍ ህጎች የሚፈጸሙት በሀገራት መካከል ባሉ ግንኙነቶች ሲሆን የሀገር ውስጥ ህጎች ግን ህጉን

ባወጣችው ሀገር ውስጥ ብቻ ላይ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው።በዚህ ንድፈ-ሀሳብ መሰረት ዓለም አቀፍ ህጎች እንደ ሀገር አቀፍ
ህጎች ለመቆጠር እና ተፈጻሚ ለመሆን ሀገሪቱ ልትፈርም እና ልታጸድቅ ይገባል።51
በኢትዮጵያ የህግ ስርአት መሰረት ዓለም አቀፍ ህጎችን ወይም ስምምነቶችን የሀገር አቀፍ ህጎች አካል ለማድረግ በሚካሄደው
ሂደት ውስጥ ከሶስቱ ዋና ዋና የመንግስት አካላት ሁለቱ ህግ አውጭው እና ህግ አስፈጻሚው ይሳተፉበታል። በህገ-መንግስቱ
መሰረት ህግ አስፈጻሚው ድርሻው ተደራድሮ ስምምነቶችን ወይም ዓለም አቀፍ ህጎችን መፈረም ሲሆን ህግ አውጭው ደግሞ
ህግ አስፈጻሚው ተደራድሮ |የተስማማውን እና የፈረመውን ህግ በአንቀጽ 55/12 መሰረት ማጽደቅ ነው።52 ስለዚህ አንድ ዓለም
አቀፍ ህግ ተቀባይነት እና ተፈጻሚነት ለማግኘት በህግ አውጪው ሊጸድቅ ይገባል። የዓለም አቀፍ ስብአዊ መብቶችም ይህን
ሂደት በመከተል የሀገሪቱ ህግ ይሆናሉ።
አንቀጽ 9/4 [ማጽደቅ] እና አንቀጽ 13/2 [ከተቀበለቻቸው] የሚሉት ቃላት ዓለም አቀፍ ሰብ አዊ መብቶችም ሆነ ሌሎች ዓለም
አቀፍ ህጎች እና ስምምነቶች እንደህግ የሚቆጠሩት እና ስራ ላይ የሚውሉት በህግ አስፈጻሚው ተቀባይነት አግኝቶ በህግ
አውጪው ሲጸድቅ መሆኑን ያመለክታል፡፡ በአንቀጽ 55/12 መሰረት ከጸደቀ በኋላ ፕሬዝደንቱ በአንቀጽ 71/2 እና 57 መሰረት
በ 15 ቀናት ውስጥ በነጋሪት ጋዜጣ ያውጃል ማለት ነው፡፡53
በእርግጥ በኢትዮጵያ የዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችን ተቀባይነትን አስመልክቶ ሁለት አይነት የተለያዩ ሀሳቦች
ሲኖሩ የመጀመሪያው ሀሳብ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች አገሪቷ ተቀብላ ካጸደቅቻቸው በቀጠታ ያለምንም
ተጨማሪ ማጽደቅያ ህግ ስራ ላይ መዋል አለበት ብለው ይከራከራሉ፡፡ ለዚህም እንደ መከራከሪያ ነጥብ የሚያነሱት የህገ
መንግስቱን አንቀጽ 9 (4)ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ህግ አካል ናቸው፡፡54
በሌላ በኩል ደግሞ የጸደቁት የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች በነጋሪት ጋዜጣ መታተም አለባቸው በማለት
የሚከራከሩ ናቸው፡፡ ለዚህም መነሻ የሚያደርጉት የህገ መንግስቱን አንቀጽ 71(2) የፕሬዚደንቱ ስልጣን ህጎችን በነጋሪት ጋዜጣ

49
Takele seboka,the monist Dualist divide and the supremacy Clause :Revisiting the
status of human right tieaties
in ethiopia,submitted to adiss abeba university faculty of law,sept2003p.134
50
ዝኒከማሁ
51
ዝኒከማሁ
52
ራስጌ 10 አንቀጽ 55(12)
53
ዝኒከማሁ አንቀጽ 71(2) እና አንቀጽ 57
54
Ibrahim idris,the place of international human right conventions in the 1994 federal democratic repuplic of ethiopia
(FDRE) Constitition,Available at reference, sabinet.co.za(webxlaccess) journal_archive /002209141193.accessed on
apr.21 2016
15
ማሳወጅን በማንሳት ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የኢፌዴሪ ነጋሪት ጋዜጣ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 3/87 ማንኛውም የፌዴራል
ህግ በነጋሪት ጋዜጣ መታተም አለበት በማለት ያሰፈረው ነው፡፡55 ይህ ጥናት የሚከተለው ሁለተኛውን የህግ ክርክር ሀሳብ ሲሆን
ምክንያቱም ኢሰመኮ ህገ መንግስታዊ መብቶች እንድከበሩ ለማስቻል በህግ የተቀመጡ ስርአቶችን የማስገንዘብና የማስጠበቅ
ግደታ ስለአለበት ነው፡፡ ይህ ማለት በዚህ የህግ ክርክር አውድ ህጎች በነጋሪት ጋዜጣ መታተም እንደለባቸው በመቀመጡ
የሚመለከተውም አካል የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶችን በነጋሪት ጋዜጣ በማሳተም ለህዝብ ይፋ በማድረግ የህጎችን
ተፈጻሚነትን ሊከታተል ይገባል፡፡
ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸው ሰብአዊ መብት ስምምነቶች ወይም ህጎች የኢትዮጵያ ህግ አካል ለማድረግ በነጋሪት ጋዜጣ መታተም
አስፈላጊ እንደሆነ በነጋሪት ጋዜጣ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ.3/87 ወጥቷል፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረት ማነኛውም ህግ ተፈጻሚ ልሆን
የሚችለው በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ሲወጣ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ነገር ግን የዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች ህትመት ስልት
በተመለከተ በኢትዮጵያ ተመሳሳይ የሆነ አካሄድ የለም፡፡ ይሁን እንጂ የዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በተመለከተ በሶስት የተለያዩ

የህትመት ስልቶች ወደ አገራዊ ህጎች እንደሚቀየሩ መገንዘብ ይቻላል፡፡አንደኛው የጸደቀውን የዓለም አቀፍ ስምምነት ሙሉ
ሰነዱን በአዋጅ መልክ አሳትሞ ማውጣት፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የጸደቀውን የዓለም አቀፍ ስምምነት ድንጋጌዎችን ወይንም የጸደቀውን ስምምነት አባሪ በአዋጅ መልክ
ከማውጣት ይልቅ የስምምነቱን ስም በመጥቀስ ማጽደቂያ አዋጅ ብቻ ማውጣት፡፡
ሦስተኛው ደግሞ የዓለም አቀፍ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ የህግ አካል ማድረግ ወይንም ከስምምነት ውስጥ የተለዩ ድንጋጌዎችን
በመምረጥ የብሄራዊ ህግ አካል አድርጎ ማካተት ነው፡፡56
ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ግን የህትመት ስልትን አስመልክቶ ወጥ የሆነ አካሄድ ማግኘት አይቻልም፡፡ ለማሳያ ያክል የሰብአዊ
መብት ስምምነት ባይሆንም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር ብቻ ነው በአማሪኛና በእንግሊዘኛ ቋንቋ ሙሉ ሰነዱ በነጋሪት
ጋዜጣ ላይ የታተመው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የህጻናት መብቶች ስምምነትና የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት በማጽደቅያ
አዋጅ መሠረት በነጋሪት ጋዜጣ ላይ የወጡት፡፡

የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ከህገ-መንግስቱ ጋር ያላቸውን ደረጃ ስንመለከት፣ አንቀጽ 9/1 ህገ-መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ህግ
መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል። ህገ-መንግስቱን የሚጣረስ ማንኛውም ህግ፣ ውሳኔ እና ባህል ተቀባይነት እንደሌለው
ያስቀምጣል።57 አንቀጽ 9/4 ደግሞ ኢትዮጵያ ያጸደቅቻቸው ስምምነቶች የሀገሪቱ የህግ አካል መሆናቸውን ይገልጻል። በዚህም
መሰረት፡-

ህጎች በመሆናቸው እና እንደማንኛውም በህግ አውጪው የሚወጡ ህጎች የሚታዩ እና ህግ የሚሆኑ በመሆናቸው፣ ዓለም አቀፍ
ሰብአዊ መብቶች በደረጃ ከህገ-መንግስቱ በታች መሆናቸውን መረዳት ይቻላል።

ይሁን እንጂ መሰረታዊ በሆኑት እና በህገ-መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት በተዘረዘሩትን ዓለም አቀፍ ሰብብአዊ መብቶች በተመለከተ
መተርጎም ሲያስፈልግ ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸውን ዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ስምምነት እና ሰነዶችን መጠቀም እና
ተፈጻሚ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ህገ-መንግስቱ በአንቀጽ 13/2 ደንግጓል።58 ኢብራሂም ኢድሪስ እና ሌሎች ጸሀፊዎች አንቀጽ

55
ዝኒከማሁ
56
ዝኒከማሁ
57
ራስጌ 10
58
ዝኒከማሁ አንቀጽ 13(2)
16
13 ን መሰረት በማድረግ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች ከህገ-መንግስቱ በታች ሊሆኑ አይችሉም ይልቁንም እኩል መሆን
ወይም በላይ መሆን አለባቸው በማለት ይከራከራሉ።59

ምንም እንኳን የተመለክተነው የህግ ምሁራን የአመክንዮ ክርክር ቢኖርም በህገመንግስቱ በአንቀጽ 9(4) ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸው
ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ህግ አካል ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ አጸደቀቻቸው የህግ አካል ካደረገቻቸው ዋና ዋና የዓለም አቀፍና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ሰነዶች
መካከል፤

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ፣ የኢኮኖሚ፤ የማኅበራዊ እና የባህላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ስምምነት፣
ሁሉም ዓይነት የዘር ልዩነቶች ለማስወገድ የተፈረመ ዓለም ዓቀፍ ስምምነት፣ ማሳቃየትና ሌሎች ጭካኔ የተሞላበት
፤ኢ-ሰብዓዊና አዋራጅ አያያዝና ቅጣት ለማስቀረት ስምምነት፣ የሕፃናት መብቶችን ስምምነት፣ በሴቶች ላይ የሚደረግ
ማንኛውንም አድሏዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት፣ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት፣ የአፍርካ
የሰዎችና የህዝቦች መብቶች ቻርተርና የአፍሪካ ህጻናት መብቶች ደህንነት ቻርተር ይገኙበቸዋል፡፡60

በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 13(2) መሰረት በምዕራፍ ሶስት የተዘረዘሩት መሰረታዊ የመብቶችና ነጻነቶች ድንጋጌዎች ኢትዮጵያ
ከተቀበላቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶችና ዓለም አቀፋዊ ሰነዶች መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ መተርጎም ያላባቸው
በመሆኑ፤ ህይ ድግጋጌ እነዚህን ስምምነቶችና ሰነዶች የሀገራችን የሰብዓዊ መብት ጥበቃ አካል ያደርጋቸዋል፡፡ በአንቀጽ 9(4) መሰረት
የኢትዮጵያ የህግ አካል ሆነው መካተት ያለባቸው የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነዶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን
መንግስትን ማማከር ስልጣን በማቋቋሚያ አዋጁ ተሰጥቶታል፡፡ ከዚህም ባለፈ በሰብአዊ መብት ሰነዶች አፈጻጸማቸውንመ ይከታተላል፡፡ በዚህ
ጥናት ላይም በጥልቀት ኋላ ላይ እንመለከታለን፡፡
2.5 የሰብአዊ መብቶች ተቋማዊ ማዕቀፍ በኢትዮጵያ

የተቋም ማዕቀፍ የሚያስፈልግበት ምክንያት ከሕገ መንግስቱና ከሌሎች ዝርዝር ህጎች እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ
መብቶች ስምምነቶች የሚመነጩ የሰብዓዊ መብቶችን ለማክበር፤ ለማስጠበቅና ለማሟላት በምንም የማይተካ ሚና
ስላላቸው ነው፡፡ ይህን ግዴታ ለመወጣት እና ተፈጻሚ ለማድረግ ተቋማዊ መዋቅር ያስፈልጋል፡፡ በኢትዮጵያም ሰብአዊ
መብቶችን በተሟላ ሁኔታ ለማስከበር መንግስት የሕግ አውጪ፣ የሕግ ተርጓሚና የአስፈጻሚ አካል አደራጅቷል፡፡ በህገ መንግስቱ
አንቀጽ 9(2) መሰረት ማንኛውም ዜጋ የመንግስት አካላት የፖለቲካ ድርጅቶች ሌሎች ማህበራት ባለስልጣኖቻቸው ሕገ
መንግስቱን የማስከበርና ለሕገ መንግስቱ ተገዢ የመሆን ሃላፊነት አለባቸው፡፡ 61 በዚህ መሰረት ሁሉም አካላት መብቶች ከማክበር
በተጨማሪ የማስከበር ግዴታ ተጥሎባቸዋል ማለት ነው።

አገሪቷም በምትከተለው የፌዴራላዊ አወቃቀር ስርአት መሰረት ሰብአዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር እንደአግባቡ
የፌዴራልና የክልል ተቋማት ተደራጅተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሰብአዊ መብቶች ላይ በቀጥታ የሚሰሩ በህግ ሀላፊነት
የተጣለባቸው የብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት ተደራጅተው ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ተቋማዊ ዋስትናን በማበጀት
የተጣለባቸውን ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡62

59
ራስጌ 55
60
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፕብሊክ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መረሐ-ግብር(2005-2007)ገ.19
61
ራስጌ 10 አንቀጽ 9(2)
62
ራስጌ 61 ገ.20
17
የሕግ አውጪ አካላት በፌዴራልና በክልል ደረጃ ተደራጅተው የሰብዓዊ መብቶችን ጥበቃ ለማጠናከር የሚያግዙ በርካታ ዝርዝር
ሕጎችን በማውጣት ሚናቸውን በመውጣት ላይ የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ተቋማት ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሱት የሕዝብ
ተወካዮች፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች እንዲሁም የተለያ ዝርዝር ደንቦችን በማውጣት ረገድ የሚኒስትሮች
ምክር ቤትና የክልል አስተዳደር ምክር ቤቶች በሕግ በተቀመጠ አግባብ ሕግ የማውጣት ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ 63

በተመሳሳይ መልኩ የዳኝነትና ከፊል ዳኝነት ተግባራት ለማከናወን በርካታ ተቋማት የተደራጁ ሲሆን በስልጣን ወሰናቸው ስር
በሚወድቁ ጉዳዮች ላይ በዜጎች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ተቀብለው ውሳኔ በመስጠት ለዜጎች የሰብዓዊ መብቶች መከበር
የበኩላቸውን ሚና ይጫወታሉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያየዘ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገመንግስት አጣሪ ጉባሔው መስረት ሕገ
መንግስቱን የመተርጎም ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡64

63
ዝኒከማሁ
64
ዝኒከማሁ
18
ምዕራፍ ሦስት

የብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት ጽንሰ ሃሣብ፣ የህግ ማዕቀፍና ሚናቸውና የብሄራዊ ሰብአዊ መብት ተቋሟት በኢትዮጲያ

3.1 ብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት እነማን ናቸው?

በሰብአዊ መብት አጠባበቅ ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው ለመጀመሪያ ጊዜ መንግስታዊ አካላትን በመመስረት
እስካንዴኒቪያ አገሮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በ 1809 የተቋቋመው የሲውዲኑ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የዜጎችን አቤቱታ
ተቀብሎ በመመርመር ለፓርላማ ሪፖርት ያደርግ ነበረ፡፡ ከዚያን በኋላ እንደዚህ አይነት ተቋሟት በአከባቢው በሚገኙ አገሮች
ማለትም በፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌየና በሌሎች አለማት ውስጥ ሊስፋፋ ችሏል፡፡65
የእነዚህ ተቋማት አመሰራረት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በተለይም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምስረታ ወዲህ ነው
በየአህጉራቱ ብቅ ማለት የጀመሩት፡፡
በተባበሩት መንግስታት ደረጃ የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት መሰረተ ሀሳብ የተጀመረው በ 1946 የድርጅቱ የኢኮኖሚና
የሶሻል ካውንስል መቋቋምን ተከትሎ ሲሆን አንዱ ተግባር ከድርጅቱ Comission on human Rights ጋር ተባብሮ እንዲሰራ
ነው፡፡66 ከላይ የተጠቀሱት ክፍሎች ከተቋቋሙ በኋላ በድርጅቱ የተለያዩ አካላት ሰብአዊ መብቶችን የሚያስጠብቁና ግንዛቤ
የሚያስፋፉ ብሄራዊ የመብት ጥበቃ ተቋሟት መመስረት እንዳለባቸው ስብሰባዎችን አካሂደዋል፤ ሪፖርቶችን አቅርበዋል፣
ፕሮፖዛሎችን ነድፈዋል፣ ሪዞልሽኖችንና ሪኮመንዴሽኖችን አዘጋጅተዋል፡፡67
በመጀመሪያ የተቋቋሙት ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት መካከል (The human Rights Commission of the united
kingdom)UK 1976፣ የካናዳ 1977፣ ኒውዚላንድ 1977፣ አውስተራሊያ 1981 ሲሆኑ የተቋቋሙበት ዋና አላማ አድሎአዊነትን
ለመታገል ነው፡፡68 በአፍሪካም እንደ ሌሎች አገሮች ሁሉ የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት አመጣጥ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ሲሆን
የመጀመሪያ የብሄራዊ ሰብአዊ መብት ተቋም በአፍሪካ የቶጎ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ነው69፡፡
በአሁኑ ሰአት የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ከዓለም ዳርቻ እስከ ሌለኛ ዓለም ጥግ ድረስ ማለት በሚያስችል ደረጃ
በተለያዩ አህጉሮቸ አፍሪካን ጨመሮ ኤሽያ/ፓሲፊክ፣ በአውስትራሊያ፣ በላቲን አሜሪካና በመካከለኛ ምስራቅ ውስጥ
ተመሰርተው ይገኛሉ፡፡
እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተቋማት ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘት የጀመሩት በተለይም
በ 1990 ዎቹ ወዲህ ነው ማለት ይቻላል፡፡ 70 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ 1991 የሰብአዊ መብት ጥበቃና ግንዛቤ ማስፋፍያ
በማስመልከት በብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት አመሰራረት ዙሪያ ዓለም አቀፍ ዎርክሾፕ ያዘጋጀ ሲሆን ይህም
የተጠናቀቀው ተቋማቱ የሚመሩበትንና በኋላም በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና በድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔ
ፀድቆ ስራ የዋሉትን መርሆዎች በማፅደቅ ነው፡፡ እነዚህን መርሆዎች የፓሪስ መርሆዎች(Paris principles) በመባል የሚታወቁ

65
አቶ ደመወዜ ማሜ፤ስለ ብሔራዊ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተቋማት የፌደራል የፍትህ አካላት ባለሙያዎች ስልጠና ማዕከል ከገጽ 170-192
66
Commonwealth Secretariat Lgal and Constitution Affairs Division,nationl human rghts institutions Commonwealth
best practs,2001,P.3
67
ዝኒከማሑ
68
ዝኒከማሑ
69
Murray Rachel,the role of national human right constitutions at the international and rejional levels”the experience of
Africa,oxford /Portland,Oregon Hart Publishing,2007P230
70
ዝኒከማሑ
19
ሲሆኑ በሰብአዊ መብት የእድገት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣቸውና ለብሄራዊ ሰብአዊ መብት ጥበቃ አደረጃጀቶች
መሰረታዊ መመሪያዎች ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡71
ስለ ብሄራዊ ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ተቋሟት አመሰራረት አንድ ልብ ሊባል የሚገባ ነጥብ ቢኖር ምስረታቸው ከዓለም አቀፍ
የሰብአዊ መብቶች መከበር ጥያቄ ወይንም እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የአለማቀፍ ተቋሟት የአለማቀፍ ሰብአዊ
መብቶችን ህጎችን በበቂ ሁኔታ ማስከበር አለመቻላቸው መብቶችን ማስከበር የሚችሉ በሄራዊ ተቋሟት መኖር እንዳለበት
በማመን በተለይም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የብሄራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋሟት እድገት እንድኖር እና በተለያዩ አገሮች
እንዲሰራጭ በማድረግ በተለይም መስፈርቶችን በማስቀመጥ፣ በአቅም ግምባታ፣ ትስስሮችን በማመቻቸትና አባልነትን
በመስጠት ትልቅ ሚና ተጫውቷል.፡፡72
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥናት መሰረት የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ማለት በሰብአዊ መብት አጠባበቅ እና ሰለ
ሰብአዊ መብት ግንዛቤ ተግባራት ዙሪያ እንዲሰሩ በተለየ ሁኔታ ግዴታቸው በህግ ተገልጾ የተደራጁ አካላት ናቸው፡፡ እነዚህ
ተቋሟት የተሰጣቸውን ተግባራት በተለያየ መንገድ የሚያከናውኑ ሲሆን በተለይም በአንድ በኩል ጥቅል አስተያየቶችን
በመቀበል ወይንም በሌላ በኩል ደግሞ ግለሰቦች እና ቡድኖች የሚያቀርቡትን አቤቱታዎችን ተቀብለው ውሳኔ መስጠት ነው፡፡ 73
በዚህ ጥናት መሰረት እንደዝህ አየነት ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው ብሄራዊ ተቋሟት የሚመሰረቱት በዋንኛነት ሰብአዊ መብቶችን
ለማስጠበቅና ስለ መብቶች ግንዛቤ ለማስፋፋት በግልጽ ባሰፈሩ የብሄራዊ ህጎች ማለትም በህገመንግስት ወይንም እራሳቸውን
በቻሉ ማስቻያ አዋጆች እና መሰል ህጎች ነው፡፡
ከላይ ያስቀመጥነው ፍቺ ቢኖርም ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟትን አስመልክቶ ሁሉንም የሚያስማማ አንድ ወጥ የሆነ
ትርጉም ማግኘት እስካሁን አልተቻለም፡፡ በጥቅሉ ምሁራን ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟትን የሚገልጹት ሰብአዊ መብቶችን
ለማስጠበቅና ለማስከበር በመንግስታት የተቋቋሙ ቋሚና ነጻ አካላት ናቸው፡፡
ስለዚህ ከላይ ካየናቸው ፍቺዎች መረዳት የሚቻለው ተቋሟቱ በባህሪያቸው አገራዊ ወይንም ብሄራዊ መሆናቸው፣ ቋሚ
መሆናቸው፣ ነጻ መሆናቸው፣ ሰብአዊ መብቶችን በተለየ ሁኔታ ለማስጠበቅና ስለ ሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ ለማስተማርና
ለማስፋፋት የተመሰረቱ መሆናቸውን ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡
ነጻ አካላት ናቸው የሚለው የሚያመላክተው ተቋሟቱ ከመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ካለሆኑ ድርጅቶች ተጽእኖ በመቆጠብ
ያለጫና ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው የምያሳይ ነው፡፡
በአንድ አገር ውስጥ የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት መኖር የሚያመላክተው ያለው የመንግስት አሰተዳደራዊ ስርአት
ለሰብአዊ መብቶች መከበር ጠንካራ ፍላጎትና ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ተቋሟት የዜጎች
መብቶች እንድከበሩ ለማስቻል የመንግስት ሃላፊነት በማሳወቅ ረገድ አገራዊ ህጎች፣ አህጉራዊ ስምምነቶችና አለማቀፋዊ
ስምምነቶች ተደራሽ በማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ አሏቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ ተቋሟት መንግስትንና መንግስታዊ
ያልሆኑ ድርጅቶች እንደ ድልድይ በመሆን ያገናኛሉ፡፡74
በአብዛኛው የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት በሁለት ዋና ዋና ምድቦች ወይንም ሞደሎች ተከፍሎ እናገኛቸዋለን፡፡ እነሱም
የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ናቸው፡፡ ከላይ ከጠቀስናቸው በተጨማሪ Hybrid institutions, Human
rights committee እና Specialized National institutions የሚባሉት ትኩረት በሚያሻቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም

71
ራስጌ 66
72
ዝኒከማሑ
73
United Nations ,Fact Sheet No.19,National Institutions 4The promotion and Protestion of Human raghts,1993
74
ዝኒከማሑ
20
አንስተኛ ቁጥር ያላቸው ቋንቋ ተናጋሪዎች፣ ህጻናት፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ስደተኞች እና በመሳሰሉት የህብረተሰብ ክፍሎች
ዙሪያ የሚሰሩ ተቋሟት ናቸው፡፡75
የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት አይነቶችን በተመለከተ ሁሉንም የሚገዛ ስያሜ የለም፡፡ ይህ በመሆኑም መንግስታት
እንደሚከተሉት የፖለቲካና የህግ ስርዓት፣ የባህል አኗኗር፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ስርአት የሚፈልጉትን የብሄራዊ የሰብአዊ
መብት ተቋሟት ሞዴል መርጠው መከተል ይችላሉ፡፡76 በስፋት ከሚታወቁት ሞዴሎች መካከል፡-
ሀ. የሰብአዊ መብት ኮሚሽኖች
የሰብአዊ መብት ኮሚሽኖች የሚያከናውናቸው ተግባርና ሀላፊነት እንድሁም የስልጣን ገደብ በሚቋቋሙበት ህግ ላይ በዝርዝር
ይቀመጣል፡፡ የኮምሺኖቹ ቀዳሚ ሚና ሰብአዊ መብቶችን የማስጠበቅና ስለ ሰብአዊ መብቶች ለማሳወቅ ሰፊ የግንዛቤ፣
የትምህርትና ስልጠና ስራዎችን ማከናወን ናቸው፡፡ የእነዚህ አካላት ዋንኛ ተግባር ህዝብን ከአደሎአዊነትና ከሰበአዊ መብት
ጥሰት መጠበቅ፣ ማስረጃን መሰረት አድርጎ የሰበአዊ መብት በደል ከደረሰባችው ግለሰቦችና ቡደኖች አቤቱታዎችን ተቀብሎ
መመርመርና ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎችን መወጣት ነው፡፡ ከዝህም በተጨማሪም ኮምሺኖች መንግስትን በፖሊሲና በህግ ዙሪያ
የማማከር፣ ክትትል የማካሄድ ግንዛቤ መፍጠር ወዘተ ይሆናል፡፡77
ለ. የህዝብ እምባ ጠባቂ
የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ዋንኛ ተግባር የዜጎችን መብት አግባብ ካልሆነ ድርጊት አስተዳደራዊ በደል እንዳይደርስ መከላከል
ነው፡፡ ይህ ተቋም አቤቱታ ከተበደሉ ሰዎች በመቀበል በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት መርመሮ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ተቋሙ ተግባሩን
በሚወጣበት ወቅት አስፈላጊ ሰነዶችን ከባለስልጣናት ጠይቆ መውሰድ ይችላል፡፡ አቤቱታዎችን ተቀብሎ ከመረመረ በኋላ
ውሳኔውንና የመፍትሄ ሀሳቦችን ለተከሰሰው የመንግስት አካል እንዲፈጽም ይሰጣል፡፡ የመፍትሄ ሀሳቦችን ተቀብሎ ያለፈጸመ
አካል ካለ የህዝብ ተቋሙ የተበደሉትን ሰዎች መብት ለማስከበርና እርምጃ እንድወሰድ ለማድረግ የሰጠውን የመፍቴ ሀሳቦችን
ለህግ አውጪ አካል ያቀርባል፡፡78
3.2 የብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት ዓለም አቀፍ የህግ መስፈርቶች(Paris principles)

የፓሪስ መርሆች (ParisPrinciples) ተብሎ የሚታቀው ስለብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት ተግባራትና አሰራር
የሚደነግገው ዓለም አቀፍ ሰነድ ብሔራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማት ሰፊ ስራዎችና ኃላፊነት ሊኖረቸዉ እነደሚገባ ይገልፃል፡፡
ይህ የፓሪስ መርሆች ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ተግባራት በዝርዝር ባይደነግግም በማንኛውም ብሔራዊ የሰብአዊ
መብቶች ተቋማት እንዲያከናውኑ የተመለከቱት ጠቅለል ብሎ የተቀመጡ ተግባራት በተለይም በዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች
ስምምነቶች የተደነገጉ መብቶችን ማስከበርና ማስፋፋት ነዉ፡፡
ሰብአዊ መብቶችን ማስከበርና ማስፋፋት በውስጣቸዉ እጅግ ሰፊ ተግባራትን የሚይዙ ሲሆን ተግባራቱ ለሁሉም የሰው ልጆች
የሚውሉ ናቸው፡፡ የፓሪስ መርሆ እንደሚደነግገው ሀገራት በሕገ-መንግስታቸውና በሌሎች ሕጎች ከተቀመጡት መብቶች
በተጨማሪ በተቻለ መጠን ሰፋ ያለ ተግባራትና ኃላፊነት ለብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋሞቻቸው መስጠት
እንደሚጠበቅባቸው ያሳያል፡፡79 ይህ ሲባል አንድ ብሔራዊ የሰብአዊ መብት ተቋም ሰብአዊ መብቶችን በተሻለ ሁኔታ
ለማስከበርና ለማስፋፋት የሚያስችላቸውን አሰራር መቅረፅ ይችላሉ ማለት ነው፡፡

75
ዝንከማሑ
76
ራስጌ 67
77
ራስጌ 74
78
ዝንከማሑ
79
Anna Elina PohjolainenThe evolution of nationl Human Rights Institutions ፡ The Role of The united Nations,2006,P.6
21
ይህ መርህ በባህሪው አስገዳጅነት የሌለው የዓለምዓቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነድ ሲሆን መርሆቹ ለተቋቋሙትም ሆነ አዲስ
ለሚመሰረቱት ብሄራዊ ተቋሟት እንደ አንድ ጠቃሚ የህግ ሰነድ አድርገን ማዬት እንችላለን፡፡80

ከፓሪስ መርሆዎች መግቢያ በማንበብ መረዳት እንደሚቻለው በአብዛኛው ሰብአዊ መብቶች እንድከበሩ ለዓለምአቀፍ
ማህበረሰብ ጥሪ ማደረግ፣ መብቶች እንዲከበሩ መንግስታትን ማበረታታት፣ ቀድሞ የወጡትን መሰል ህጎች ሰብአዊ መብቶች
መጠበቅ እንዳለባቸው የሚያስገነዝቡ ሰነዶች ሊተኮርባቸው ይገባል በማለት ነው፡፡ 81 ይህ የሚያሳየው የፓሪስ መርህዎ
አስገዳጅነት የሌለው መሆኑን ነው፡፡

የሰነዱ የጀርባ አጥንት ተደርጎ ሊቆጠር የሚችል አራት ጠቅላላ ነጥቦች የያዘ ሲሆን አራቱም ደግሞ በውስጣቸው በንኡሳን
ክፍሎች ተከፋፍለዋል፡፡ እነዝይ መርሆዎች በዝህ ጥናት ርእሰ ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት ስለ አለውና የእ.ሰ.መ.ኮ ሰባአዊ
መብቶችን የማሳወቅ፤መከበራቸውን የመከታተል እና የመመርመር ሃላፍነት፤ተግባር ይዘቱ እና ወሰኑን በዝህ ጥናት በምቀጥለው
ምራፍ ለመፈተሽ ስለምረዳ የፓርስ መርህዎቹን ጠቅላላ ነጥቦችን እንደሚከተለው ባአጭሩ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

3.2.1 ስልጣንና ሀላፊነት(Competence and responsibilities)


ይህ ሰነድ አንድ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋም ሊኖረው የሚገባው ስልጣን ብሎ ያሰቀመጠው ተቋሟቱ ሰብአዊ መብቶችን
የማስጠበቅና ግንዛቤ የማስፋፋት ተግባር ማከናወን እንዳለባቸውና በማቋቋሚያ ህጎች ማለትም በህገ መንግስቱ ወይንም
በአዋጃቸው በተቻለ መጠን ሰፊ ስልጣን ሊሰጣቸው እንደሚገባና ይየውም በህጉ ላይ መገለጽ እንደሚያስፈልግ ያሳስባል፡፡

የፓሪስ መርሆዎች የብሄራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋሟት ሀላፊነትን ሲያስቀምጥ ተቋሟቱ ለመንግስት አካላት ወይንም ለህግ
አውጪው፣ ለፍርድ ቤቶችና ለአስፈጻሚ አካላት ስለ ሰብአዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ ምክረ ሀሳቦችን አዘጋጅቶ ማቀረብ፣
አስተያዬቶችን መስጠት፣ አስፈላጊ ፕሮፖዛሎችን የማዘጋጀት ሀላፊነቶችን እንድወጡ ግዴታዎች እንደተጣለባቸው
ያመላክታል፡፡ የሚዘጋጁ ህጎች ከመሰረታዊ የሰው ልጅ መብቶች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ የሰብአዊ መብቶች
እንዲከበሩ የሚያገዙ አዳዲስ ህጎች እንዲወጡና ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ህጎችን በማጥናት ህግ አውጭውና ማማከር
እንዳለባቸው በግልጽ ተቀመጧል፡፡ በአጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎች ወይንም በተለዩ ሁኔታዎች አስመልክቶ ሪፖርት
የማዘጋጀትና የመብት ጥሰት ሲኖር መንግስትን ጥሰቱ እነድቆም ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሙ የእራሱን አቋም መግለጽ
አስፈላጊ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ እነዚህ ተቋሟት ብሄራዊ ህጎች፣ ደምቦችና አሰራሮች ከዓለምዓቀፍ የሰብአዊ መብቶች
ስምምነቶች ጋር መጣጣማቸውንና አፈጻጸማቸውን ለማረጋገጥ ያስገነዝባሉ፤ እንዲሁም የአለማቀፍ ሰብአዊ መብቶች ህጎች
መነግስታት ተቀብለው እንዲያጸድቁት ጠንክረው ይሰራሉ፡፡ ለሰብአዊ መብቶች ትምህርት ጠናትና ምርምር ለማካሄድ አስፈላጊ
የሆኑ መርሀ ግብሮችን በመንደፍ በትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋሟትና በሙያ ማህበራት ውስጥ ተፈጻሚ
እንዲሆን ለማስቻል የእራሳቸውን እገዛ ያደርጋሉ፡፡ ማንኛውም አይነት አድሎአዊ አሰራሮችን ለማስወገድ ግንዛቤን መፍጠር
በተለይም የፐሬስ አካላትን በመጠቀም መረጃን መለዋወጥና ትምህርትን በማዳረስ ጽኑ ትግል ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ
ያስገነዝባል፡፡82

3.2.2 ጥንቅር፣ ነጻነትና ብዝሀነት(Composition, independence and pluralism)


የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ጥንቅርና የአባላት አሷሷም በተቀመጠ ስርአት ሆኖ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎችን፣
በሰብአዊ መብት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ የሲቪክ ማህበራት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሙያ ማህበራት ተወካዮች፣ የህግ

80
ዝንከማሑ
81
Wondemagegn.t.geshu,the Ethiopian (national)human rights commission its contribution to constitutional
ism,2015,p.4
82
Paris Principles,National iNStitutions for the promotion and protection of human rights,jeneral assembly
A/RES/48/134 85th plenary meeting 20 diseber 1993.
22
ባለሙያ ማህበራት፣ የህክምና ባለሙያ ማህበራት፣ የጋዜጠኞች ማህበራት፣ ታዋቂ ሳይንቲስቶች፣ የሀይማኖት ተወካዮች፣
ፓርላማ፣ እና መሰል አካላት እንዲሳተፉ የሚያደርግና ብዝሀነትን የሚያረጋግጥ ሊሆን ይገባል፡፡ ከላይ የጠቀስናቸው ተወካዮች
ሚናቸው በሚካሄዱ ውይህቶች ላይ በአማካሪነት መሳተፍ ነው፡፡ የተቋሙን ነጻነት ለማስጠበቅ የሚሾሙ አባላት አስመልክቶ
መንግስት ህግ ማውጣት እንዳለበትና ለስራ ማስኬጃና ለመስሪያቤት ፋይናንስ የሚውል በመንግስት ሊመደብ እንደሚገባ በግልጽ
ተቀምጧል፡፡83

3.2.3 የአሰራር ስርአት (Methods of operation)


የብሄራዊ ሰብአዊ መብት አሰራርን በተመለከተ የፓሪስ መርሆዎች በግልጽ እንዳሰፈረው ተቋሟቱ በስልጣናቸው ስር
የሚወድቀውን ማንኛውንም አይነት የመብት ጥያቄ በመንግስት የቀረበ ይሁን በሌላ አካላት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን የማየት
ወይንም ከማንኛውም ግለሰብ መረጃዎችንና ሰነዶችን ተቀብሎ የመስማት ስልጣን እንዳለው መመልከት ይቻላል፡፡ በተለይም
አሰተያዬቶችንና ምክረ ሀሳቦችን ይፋ ለማድረግ ለህዝቡ በቀጥታ ወይንም የፕሬስ አካላትን በመጠቀም የማህበረሰቡን ጉዳዮችን
ማንሳት ይችላል፡፡ ሌላው በአሰራር ስርአት ውስጥ የሰፈረው ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት መደበኛ ስብሰባዎችን ያካህዳሉ፤
ከህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም፣ በእርቅ ስራ ላይ ከተሰማሩ አካላትና መሰል ሀላፊነት ካላቸው ድርጅቶች ጋር ሰለ ሰብአዊ መብቶች
አጠባበቅ ዙሪያ የጋራ ምክክሮችን ያደርጋሉ፡፡ በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የተሰማሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚጫወቱትን
ትልቅ ሚና ከግምት በማስገባት፣ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት መብቶችን ለማስከበር፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን
ለማስጠበቅና ማንኛውንም አይነት አድሎአዊ አሰራርን ለመዋጋት በተለይም ለመብት ጥሰት የተጋለጡትን የህብረተሰብ
ክፍሎችን ማለትም ህጻናትን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ስደተኞችንና በስደት ላይ ያሉትን ሰራተኞችን መብት ለማስከበር መንግስታዊ
ካለሆኑ ድርጅቶች ጋር የጠበቀ ግነኙነት ይመሰርታሉ፡፡84

3.2.4 ከፊል የዳኝነት ስልጣን (Quasi-judicial competence)


ሌላኛው በፓሪስ መረህዎች ለብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት የተሰጠው ተግባር ቅሬታ ወይንም አቤቱታ ተቀብሎ
የመስማትና የመወሰን የከፊል ዳኝነት ስልጣን ነው፡፡ በእርግጥ ይህ ሰነድ ለተቋሟቱ ከፊል የዳኝነት ስልጣን ቢሰጥም ከፊል
የዳኝነት ስልጣን ምን ማለት እንደሆነ ያስቀመጠው ፍቺ የለም፡፡

ቢሆንም ግን በዚህ መርህ መሰረት ጥሰት ሲያጋጥም ክሶቹ በግለሰቦች፣በተወካዮች፣ በሶስተኛ ወገን፣ በብዙሀን ማህበራት
ሊቀርብ እንደሚችል ከሰነዱ ማዬት ይቻላል፡፡ ሠነዱ ክስ የማቅረብ መብት የደነገገበት ምክንያት መሰረታዊ አላማ ህግ ላይ
በሰፈረው መሰረት ሚስጥራዊነትን በመጠበቅ በስምምነትና በእርቅ አለመግባባቶችን ለመፍታት ነው፡፡ አቤቱታ አቅራቢው
ሊጠቀምባቸው የሚገባውን መብቶች ማሳወቅ ወይንም ክሱ ወደ ሌላ ስልጣን ወደ ተሰጠው አካል መተላለፍ ካለበት ሊነገረው
እነደሚገባ መርሁ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ በዚህ መርህ ስር ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት የአቤቱታ አቅራቢውን ጉዳይ
ከተመለከቱ በኋላ መብቶቹ እንዳይከበሩ ማነቆ የሆኑትን ችግሮችን በመለየት ለሚመለከተው ባለስልጣን ችግር ያለባቸውን
ህጎች፣ ደምቦችና አስተዳደራዊ አሰራሮችን ነቅሶ በማውጣት እንዲሻሻሉ አስፈላጊ የሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ይሰጣሉ፡፡ 85

3.3 የብሄራዊ ሰብአዊ መብትን የሚመለከቱ ሌሎች ሕጎች

የፓሪስ መርሆዎች ከወጣ በኋላ በ 1993 ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብቶች ኮንፈረንስ የሰበአዊ መብቶችን ጥበቃንና ግንዛቤ
መስፋፋትን አስመልክቶ የቬና መግለጫና የድርጊት መርሀግብር (The Vienna Declaration And Program Of Action)
ወጥቷል፡፡ በዚህ ኮንፈረንስ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ሰብአዊ መብቶችን በማስጠበቅና ስለ ሰብአዊ መብቶች

83
ዝንከማሑ
84
ዝንከማሑ
85
ዝንከማሑ
23
ትምህርት በመስጠት በተለይም መንግስትን በማማከር፣ ጥሰት ለደረሰባቸው ሰዎች እንዲካሱ በማድረግ፣ ስለ ሰብአዊ መብቶች
አስፈላጊ መረጃዎችን በማሰራጨትና ግንዛቤ በመፍጠር ገምቢ ሚና እንዳላቸው በስብሰባው ተነስቷል፡፡ ይህ ኮንፈረንስ ብሄራዊ
የሰብአዊ መብት ተቋሟት በፓሪስ መርሆዎች አግባብ መቋቋምና መጠናከር እንዳለባቸው ከማበረታቱም ባሻገር መንግስታት
ተቋሟቱን ለመመስረት አገራዊ ፍላጎታቸውን ከግምት በማስገባት የትኛውም አይነት ሞዴል ሊከተሉ እንደሚችሉ እውቅና
ይሰጣል፡፡86 በዚሁ ኮንፈረንስ መሰረት በወጣው መግለጫ ሰብአዊ መብቶች የማይነጣጠሉ መሆናቸው ይልቁኑም ጠንካራ
ቁርኝት እንዳላቸውና የመብቶችን ሁሉአቀፋዊነት በመደንገግ ኮንፈረንሱ ተጠናቋል፡፡87

በአፍሪካ አህጉር ደረጃ የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት በተመለከተ የወጡ ሁለት መግለጫዎችነ ማንሳት ይቻላል፡፡
የመጀመሪያው በ 1992 የሀራሬ የኮመን ወልዝመግለጫ (The Harare Common Wealth Declaration) ሲሆን መግለጫውም
ትኩረቱ ብሄራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋሟት ሚና፣ የመልካም አስተዳደር ጽንሰ ሀሳብ፣ ስለ ተጠያቂነት፣ ስለ ዲሞክራሲና ስለ
ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ነው፡፡88

ሁለተኛው ደግሞ በ 1996 በአፍሪካ ስለ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት መብቶች ጥበቃና ግንዛቤ ማስፋፋት ኮንፈረንስ
በማካሄድ የያኡንዴ መግለጫ (Yaounde Declaration) ወጥቷል፡፡ ይህ መግለጫ ዋና ትኩረቱ የሰብአዊ መብት ግንዛቤ
ማስፋፋትና መብቶች ተጥሰው ሲገኙ ተቋሟቱ ለተበደሉ ሰዎች ካሳ የሚገኝበትን መንገድ ማፈላለግ ነው፡፡89

በተጨማሪ ለእነዚህ ተቋሟት በህግ ደረጃ እውቅና ሰጥቷል ተብሎ የሚገመተው በ 1982 የወጣው የአፍሪካ የሰዎችና የህዝቦች
ቻርተር በአንቀጽ 26 ላይ የሰፈረው መንግስታት የፍርድ ቤቶችን ነጻነት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው በመግለጽ ቻርተሩ ላይ
የሰፈሩትን ሰብአዊ መብቶችነና ነጻነቶችን ለማስጠበቅና ግንዛቤ ለማስፋፋት ስልጣን የተሰጣቸው ብሄራዊ ተቋሟት
መደራጀትና መጠናከር አለባቸው በማለት ቻርተሩ ይገልጻል፡፡ 90 ይህ ቻርተር ሀሳብ ዛሬ ያሉትን ብሄራዊ የሰብአዊ መብት
ተቋሟት እንዳለሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ቻርተሩ ሲወጣ የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ፍልስፍናና አስተሳሰብ
ገና በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ላይ ነበረ፡፡ እንደዚህ አይነት አረዳድ ሊፈጠር የቻለው ምናልባት የቻርተሩ አንቀጽ 26 ብሄራዊ ተቋሟት
ከሰብአዊ መብት መጠበቅና መስፋፋት ጋር አያይዞ በማስፈሩ ይሆናል፡፡91

ሌላኛው ሕግ ስለ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ሊያሳየን የሚችለው የተባበሩት መንግሰታት ድርጅት የአካል ጉዳተኞች
መብቶች ስምምነት ነው፡፡ ይህ ስምምነት በአንቀጽ 33 ስለስምምነቱ አተገባበርና ቁጥጥር በተቀመጠው ድንጋጌ ንኡስ 2 ስር
“ተዋዋይ መንግሥታት እንደየራሳቸው የሕግና አሰተዳደር ሥርዓት እንደአስፈላጊነቱ አንድ ወይም ከዛበላይ ገለልተኛ በሆነ ዘዴ
የዚህን ስምምነት መስፋፋት መጠበቅ አፈፃፀሙን ለመቆጣጠር በመንግሥታቸው ውስጥ እንደማዕቀፍ
ይይዛሉ፣ያጠናክራሉ፣ያቅዳሉወይም ያቋቁማሉ፡፡ይህን መሰል ዘዴ ሲያቋቁሙ የብሔራዊ ተቋማትን አሠራር እና ደረጃ
የሚመለከቱ መርሆዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባሉ፡፡”92ከላይ እንደተመለከትነው የአፍሪካ የሰዎችና የህዝቦች ቻርተር የብሄራዊ
የሰብአዊ መብት ተቋሟትን እንደማይጠቅሰው ሁሉ የአካል ጉዳተኞችም ስምምነት በቀጥታ የብሄራዊ ሰበአዊ መብት
ተቋሟትን በግልጽ ባያስቀምጥም መንግስታት የአካል ጉዳተኞችን ስምምነትን አፈጻጸም ለመቆጣጠር በሚያዘጋጁት ማዕቀፍ
ወይንም እቅድ ውስጥ የብሄራዊ ተቋሟትን አሰራር መርሆዎችን መከተል እንደሚያስፈልግ ከግምት ያስገባል፡፡ ከዚህ ሰምምነት

86
Vienna Declaration and Program of action,adopted by the world conference on human right on 25 june 1993
87
ዝኒከማሑ
88
The Harare commonwealth declaration,(Issued by Heads of government in Harare Zimbabwe) oct.1991
89
The Yaounde Declaration of national institutions for the promotion and Protection of human right Feb.1996
90
African Charter on human and peoples’ right, Gambia Banjul,AdoPted 27june1981Art.26
91
ራስገ 82
92
UN.convention on the rights of persons with disabilities(Uncrpds),2006Art.33(2)
24
አንቀጽ መረዳት እንደሚቻለው የብሄራዊ ተቋሟትን አሰራርና ደረጃ መርሆዎችን ከግምት ማስገባት ያስፈልጋል የሚለው ሀረግ
የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋምና ወይንም መሰል ድርጅቶች አሰራር ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ
አይከብድም፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የአካል ጉዳተኞች ስምምነት የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት አሰራር በየአገሩ ከተስፋፋ
በኋላ የወጣ በመሆኑና የሰነዱ ሙሉ ሀሳብ በሰብአዊ መብቶች ላይ ስለ ሚያቶክር ነው፡፡

3.4 የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ሚና

በፓሪስ መርሆዎች ላይ በግልጽ ማየት እንደ ሚቻለው የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ሁለት ዋና ዋና ትላልቅ ተግባራትን
እነድያከናውኑ ተጥሎባቸዋል፡፡ ተግባራቱም የሰብአዊ መብት ጥበቃና የግንዛቤ ማስፋፋት ናቸው፡፡ የብሄራዊ የሰብአዊ መብት
ተቋሟት ሚና መሰረቱ የተቋሟሙበት የአገሪቱ ህገመንግስት ወይንም አዋጅ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ጥናት በቅድሚያ በሰብአዊ
መብት ጥበቃ አሰራር ስር የሚካተቱትን ተግባራትን እንደሚከተለው ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

3.4.1 የሰብአዊ መብት ጥበቃ

3.4.1.1 የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ


የሰብአዊ መብቶች ምርመራ ማለት ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ፣ የማይጣሱ እና የማይገፈፉ የሆኑት ሰብአዊ መብቶች
ሲጣሱ እና ሲገፈፉ የሚደረግ ምርመራ ነው። ማን ነው ሰብአዊ መብቶችን የጣሰው፣ እንዴት፣ መቼ እና የት እንዲሁም
የተጣሰው መብት የመብት አይነት እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች የሚመልስ ጥልቅ ምርምር የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ
ሊባል ይችላል፡፡93

ምርመራ ለማካሄድ በቅድሚያ አቤቱታ ወይንም ክስ የቀረበለት አካል ጉዳዩን ከመመልከቱ በፊት ክሱን ወይንም አቤቱታውን
ለመመርመር ሙሉ ስልጣን ወይንም በከፊል ስልጣን በህጉ እንደተሰጠው ማጣራት፣ በቂ መረጃ መቅረቡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
ምርመራ በጥቅሉ ተገቢ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚረዱ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣ አስተያዬቶችን ለመስጠትና ሪፖርት ለማዘጋጀት
የተሰባሰቡትን መረጃዎችን መተንተንን ያካትታል፡፡ የቀረበውም ክስ ወይንም አቤቱታ በይፋ ተቀባይነትን አግኝቶ ከተመዘገበ
በኋላ ለሚመረምረው ባለሙያ በማስረከብ የተመራለት መርማሪ ተከራካሪ ወገኖች ጉዳዩን እንዲከታተሉ በመጥሪያ
ያሳውቃቸዋል፡፡94 በሰብአዊ መብት ተቋም ውስጥ የሚሰራውም መርማሪም የምርመራ ስነስርአት ሳያጓድል የያዘውን ጉዳዩን
በማየት፣ መረጃዎችን በመመርመር ምስክሮችን በመስማት፣ ምስጢራቸውን በመጠበቅ ምላሽ የመስጠት ሀላፊነት አለበት፡፡ 95

የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት በዋንኛነት መወጣት ያለባቸው ሀላፊነት የመብት ጥሰትን በመመርመር የመብት ጥሰት
የደረሰባቸው አካላት አስተዳደራዊ ፍትህን እንዲያገኙ በማድረግ የተበደሉትን መካስ ነው፡፡ የምርመራ ተግባር መኖር
ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ በመንግስታት ላይ መብቶች ሙሉ በሙሉ እንዲጠበቁ ግዴታን የሚጠል ነው፡፡

የሰብአዊ መብት መጠበቃቸውንና መከበራቸውን በዋንኛነት የማረጋገጥ ግዴታን የተጣለባቸው ፍርድ ቤቶች ብሆኑም
ብሄራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት ከፊል የዳኘነት ስልጣን የተሰጣቸው ምክንያት ሌሎች የፍትህ አካላትን ለመተካት
ሳይሆን መብት ለተጣሰባቸው ግለሰቦች የተሻለ አስተዳደራዊ ፍትህን ለመስጠት ነው፡፡ በእነዝህ ተቋሟት የሚሰጡ

93
Cmplaints Handling Manual,Ethiopian human right commission ,2011,P.48
94
Uniteted nations office of high commissioner for human rihght,national human right institutions history,principles,roles
and responsibilities,new work and jineva 20010,p.77
95
ዝንከማሑ
25
አገልግሎቶች ከፍርድ ቤቶች በተለየ ሁኔታ በቀላል ወጭና አካሄድ (Flexibility) በመከተል በአጭር ጊዜ ለሚቀርቡላቸው
ጉዳዮች ውሳኔ መስጠት መቻላቸው የበለጠ ተደራሽ (Accessible) ያደርጋቸዋል ተብሎ ይገመታል፡፡96

ለእነዚህ ተቋማት የመብት ጥሰት አቤቱታዎች በቀጥታ ጉዳቱ በደረሰበት ወገን፣ ወይም በወኪሉ ወይም ጉዳዩ
ይመለከተኛል ወይም ያገባኛል በሚል ሦስተኛ ወገን ልቀርብ ይችላል፡፡እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት የሚቀርቡ
አቤቱታዎች ሁሉ ተቀባይነትን አግኝተው ምርመራ ይካሄድባቸዋል ማለት አይደለም፡፡በተቋማቱ ሥልጣን ሥር
የማይወድቁ የመብት ጥሰት የደረሰበት ሰው የማይታወቅ፣ መሰረት የሌላቸው፣ በህግ የጠቀመጠው የጌዜ ገደብ
ያለፈባቸውና የመሳሰሉት አቤቱታዎች ከመጀመሪያውኑ በተቋማቱ ዘንድ ተቀባይነት የማይኖራቸው ሊሆኑ ይችላል፡፡ 97

3.4.1.2 የሰብአዊ መብት ክትትል


የሰብአዊ መብት ክትተል ማለት ሁኔታዎችን መታዘብ፣ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ የተሰበሰቡትን መረጃዎችን በማደራጀትና
በመተንተን ክትትል በተደረገባቸው ሁኔታዎችና ክስተት ዙሪያ ሪፖርት ማዘጋጀትን ያካትታል፡፡ እንደየክትትሉ አይነት ውጤቱ
ቢለያይም የሰብአዊ መብት ክትትል ዋና አላማ የሰብአዊ መብት በደሎችን ማስረጃዎችን በመያዝ የማስተካከያ እርምጃዎች
እንዲወሰዱ ምክረ ሀሳቦችን መጠቆም ወይንም ለመከላከል ወይንም ለትምህርትና ለተሟጓችነት ተግባር የሚውል ሆኖ
አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት ነው፡፡98

ሁሉም የሰብአዊ መብት ተቋሟት በሁሉም መብቶች ማለትም በሲቪልና ፖለቲካ መብቶች፣ በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ
መብቶችና በሌሎች የመብት ዝርዝሮች ላይ ክትትል ተግባራት ያከናውናሉ፡፡ ይህ ማለት ግን በየአመቱ በሁሉም የሰብአዊ
መብቶች ጉዳዮች ዙሪያ ክትትል ያደርጋሉ ማለት አይደለም፡፡ክትትል የሚደረግባቸው መብቶች የብሄራዊ የሰብአዊ መብት
ተቋሟት በሚያዘጋጁት እስትራቴጂካዊ እቅድ ላይ ተመስርተው በሚነድፉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይሆናል፡፡ አብዘኛዎቹ
ተቋሟት ስልታዊ የሆነ አጠቃላይ አገራዊ የሰብአዊ መብት ክትትል ወይንም በተለዩ እጅግ አስፈላጊ በሆኑ የሰብአዊ መብት
ጉዳዮች ዙሪያ ክትትል ያደርጋሉ፡፡99

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ክፍል መሰረት የክትትል ኦፊሰሮች መከተል ያለባቸውን አስራ ዘጠኝ የክትትል
መርሆዎችን አስቀምጧል፡፡ ከነዚህ መርሆዎች መካከል ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያክል ጉዳት አለማድረስ፣ የክትትል መስፈርቶችን
ማወቅ፣ ቀጥተኛና ትክክለኛ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ አለማዳላት፣ መልካም ማንነት፣ ሁሉንም በእኩል ማየተና ሙያን አክብሮ
መስራት ናቸው፡፡100

ሁለት አይነት የክትትል አመላካች ደረጃዎች አሉ፡፡ እነሱም ህደትን መሰረት ያደረገ የክትትል አይነትና (Process-based
monitoring) ውጤትን መሰረት ያደረገ የክትትል አይነት(Outcome-based monitoring)ናቸው፡፡101 ህደትን መሰረት ያደረገ
ከትትል የሚያካትታቸው ክትትል ሊደረግበት የታሰበው የመብት አይነት በበቂ ሁኔታ መጠበቁን ለማረጋገጥ የወጡ ፖሊሲዎችን፣
ህጎችን፣ ደምቦችንና፣ አሰራሮችን አፈጻጸምን መፈተሸ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ውጤትን መሰረት ያደረገ የክትትል አይነት

96
Brian Burdckiln,national human rihght institutions in the ASIA____Pacific Rejion,Raoul Wallenberg institute vol27
Martinus Nijhoff publishers Leiden /Boston2007,P.22/
97
ዝንከማሑ
98
Manuel Juzman,what is monitoring,Human Rihght Informatiom and documentation Systems(HURIDOCS),Versoix
Switzerland,2003,P.5
99
ዝንከማሑ
100
ዝንከማሑ
101
Human rights Indicators A Guide to Measurement and Implementation,United Nations new York 2012,pp.16-204
26
ለይቶ ማስቀመጥ ውስብስብ ቢሆንም ትኩረት የሚያደርገው ሰዎች በወጣው ፖሊሲ፣ ህጎችና አሰራሮች አማካኝነት ምን ያክል
መብቶቻቸውን ተጠቅመውበታል የሚለውን የሚፈትሽ የክትትል አይነት ነው፡፡102

3.4.1.3 የማማከር ተግባር

የፓሪስ መርሆዎች በግልጽ እንደሚያሳስበው ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ከተጣለባቸው ሀላፊነቶች አንዱ መንግስትን
የማማከር ግዴታ መሆኑን ከሰነዱ ማወቅ ይቻላል፡፡ እነዚህ ተቋሟት መንግስትን፣ ህግ አውጪውንና የምንስትር መስሪያ ቤቶችን
የሰብአዊ መብት ጥበቃና ግንዛቤን አስመልክቶ በእራሳቸው ተነሳሽነት ይሁን ለሚመለከታቸው ሌሎች ባለስልጣናት ምክር፣
አስተያየቶች፣ ምክረ ሀሳቦችን የመስጠት፣ ሪፖርቶችን አዘጋጅቶ የማቅረብ ስለጣን ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ምክር የሚሰጥባቸው
ጉዳዮችን ስንመለከት በቅድሚያ አገራዊ ፖሊሲዎችን፣ ህጎችን፣ አሰራሮችን ስልታዊ በሆነ መንገድ በመፈተሽ ሊከለሱ
የሚገባቸውን በመለየት መብቶችን በተሻለ ደረጃ ለማስጠበቅ ብሄራዊ ተቋሟት መንግስትን ያማክራሉ፡፡ 103 የዚህ የማማከርና
የመርዳት ኃላፊነት መገለጫ ሌላው አሠራር በሥራ ላይ ያሉ ሕጎች እንዲሻሻሉ ወይም አዳዲስ ሕጎች ጉዳዩ
ለሚመለከተው አካል ከማሳሰብ በተጨማሪ ሕጎቹን ማርቀቅ ወይም አማራጮችን እስከማቅረብ የሚደርሱ ናቸው፡፡
ይህን ኃላፊነት መወጣት አስፈላጊ ነው ተብሎ የሚታመንበት ምክንያት ተቋማቱ መደበኛ ሥራቸውን ማለትም
የምርመራ፣ ሕዝብን የማወያየትና አቤቱታዎችን የመስማት ተግባራት በሚያከናውኑበት ጊዜ ጥሰቶቹ ሕጎች ካላቸው
ክፍተቶች የሚመነጩ መሆናቸውን በቀላሉ የመለየት አጋጣሚ ስለሚፈጥርላቸው ነው፡፡ 104 ይህ የማማከር ተግባር ጉዳዩ
ለሚመለከታቸው አካላት የፖሊስና የአስተዳደር ለውጥ እንዲያደርጉ እስከ ማሳሰብ የሚደርስ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ
ውስጥም በፓሪስ መርሆዎች ላይ እንደተመለከትነው በአገሪቱ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሲኖር ብሄራዊ ተቋሟት
ጥሰቶቹ እንዲቆሙ ለመንግሰት ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባሉ፡፡ ምክር የሚሰጣቸው አካላትም በቀና መንፈስ ተቀብለው
ለማረም ፈቃደኛና ዝግጁ የመሆን ግዴታ ያለባቸው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ የእነዚህ ምክሮችና አስተያቶች
በሚመለከታቸው አካላት አለመተግበር የተቋማቱን ሚና እያዳከመ የሚሄድ በመሆኑ ብዙ አገሮች ይህንን አስመልክተው
አስገዳጅ ሕግጋትን ያወጣሉ፡፡105

የማማከር ስልጣን የተሰጣቸው የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት መንግስት ተቀብሎ ማጽደቅ ያለበትን ዓለምአቀፍ የሰብአዊ
መብት ስምምነቶችን ባህሪና የሚያስከትለውን ግዴታ አይነት በመለየት መንግስት ህጎቹን እንዲያውቅ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ማለት
መጽደቅ ያለባቸው ዓለምአቀፍ ሰምምነቶች ያካተቱት ድንጋጌዎች ከአገራዊ ህጎች ጋር መጣጣማቸውን ማረጋገጥ ወይንም ህግ
አውጪው ስምምነቶቹን ተቀብሎ ለማጽደቅ ተጨማሪ የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የማጽደቂያ አዋጅ እንዲወጣ
ይደረጋል፡፡ ይህ መንግስት ያላፀደቃቸው የሰብአዊ መብት ስምምነቶችን እንዲያፀድቅ ከማሳሰብና ጫና ከማሳደር
በተጨማሪ በስምምነቶቹ መሠረት ሊቀርቡ የሚገባቸው ሪፖርቶች በወቅቱ እንዲቀርቡ የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት
ጭምር በቋሚነት ተከታትሎ በማማከር መንግስት የገባውን ግዴታ እንዲወጣ እገዛ ያደርጋል፡፡ 106 በስተመጨረሻም
የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ምክርና ክትትልን ጨምሮ ሌሎች የሚያከናውናቸወን ተግባራት ለህዝብ ይፋ ለማድረግ

102
ዝንከማሑ
103
ራስጌ 95
104
Office of the united nations high commissioner for human right, Economic,Social and cultural rights(Handbook for
national human rights institutions),New york and jeneva 2005 P.10
105
ራስጌ 66
106
ዝንከማሑ
27
ጥናትና ምርምር፣ የህዝብ አስተያየቶች፣ ሴምናሮች፣ ስብሰባዎችን፣ ተግባር ተኮር ጥናቶችን፣ ንጽጽራዊ ጥናቶችንና ሪፖርቶችን
መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡107

3.4.2 የሰብአዊ መብት ግንዛቤ ማስፋፋት ሚና


በፓሪስ መርሆዎች ላይ እንደሰፈረው ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ከሚቃቋሙበት ዋና አላማ አነዱ ስለ ሰብአዊ መብት
ግንዛቤ ለማስፋፋትና ለማስገነዘብ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ የተለያዩ የዓለምአቀፍ ሰምምነቶች መንግስት የሰብአዊ መብት

የግንዛቤ ተግባራት ማከናወን እንዳለበት ይገልጻሉ፡፡ ለምሳሌ የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የባህልና የማህበራዊ መብቶች

ስምምነት አንቀጽ 13፣ የዓለምአቀፍ የህጻናት ስምምነት መብቶች አንቀጽ 29፣ በሴቶችላይ የሚደረግ ማንኛውንም

አድሎአዊ ልዩነት ማስወገድ ስምምነት አንቀጽ 10፤ማንኛውም አይነት የዘር አድልኦ ለማስወገድ የተደረገ ዓለም

አቀፍ ስምምነት አንቀጽ 7 የተባበሩት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት አንቀጽ 8 ናቸው፡፡የመንግስት አካላትም

የተጣለባቸውን ሀላፊነትና የሚወጡትን ሚና በአግባቡ ተገንዝበው መብቶች መከበራቸውን ለማረጋገጥ የሰብአዊ መብት ግንዛቤ
ማስፋፊያ ማካሄድ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡108 መብት ከማስከበር ጋር ቀጥተኛ ግኑኘነት ያላቸውን በተለይም በፍትህ አስተዳደር
ውስጥ ሚና ያላቸውን ባለሙያዎች ማለትም ዳኞች፣ዓቃቢያነ ሕጎችን፣ጠበቆዎች፣ አስፈፃሚውንና የሕግ አውጭውን
አካላት፣ ሕግ አስፈፃሚ አካላትን በተለይም ፖሊስ፣ የማረሚያ ቤት ጥበቃዎች፣ የፀጥታ ሃይሎች፣ ሌሎች ማለትም
የማህበራዊ ጉዳይ ሠራተኞች፣ የመከላከያ ኃይል አባላት፣ ሚዲያን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን፣ መምህራንና
አሰልጣኞቻቸውን፣ የማህበረሰብ መሪዎችን፣ የአገር ሽማግሌዎችና የህዝብ አደረጃጀቶችን በስፋት ማሰልጠን
ያስፈልጋል፡፡109

የግንዛቤው መስፋፋትና የትምህርቱ መስጠት ስለሰብአዊ መብት ለማሳወቅ ይረዳል፣ ሰብአዊ መብትን የማክበርና የማስከበር
አመለካከቶችና እሴቶች በህብረተሰቡ ውስጥ እንዲፈጠሩና እንዲጎለብቱ ያደርጋል፤ እንደዚሁም የሰብአዊ መብት ጥሰት
የመካላከል ተግባራት እንዲበረታቱ ያግዛል፡፡110 ይህን ዋና ዓላማ ለማስፈፀም ብሄራዊ ተቋማት የሚጠቀሙት ስልት እንደየአገሩ
የተለያዩ ቢሆንም በዋናነት ከመደበኛ የሰብአዊ መብት ትምህርት በተጨማሪ ሌሎች የአጭርና የረዥም ጊዜ የትምህርት
ፕሮግራሞችን መንደፍ፣ መረጃና የማስተማሪያ ሰነዶችን ማሰባሰብ፣ማደራጀትና ማሰራጨት፣በሰብአዊ መብት ተግባራት ዙርያ
ከሚሰሩት ማህበራት እንዲሁም ከማህበረሰብ አቀፍ አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር አብሮ መስራት፤ መገናኛ ብዙሀንን
መጠቀም፣ ስለተቋሙ ስልጣንና ሀላፊነት የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ለህዝቡ ማስተዋወቅ፣ አወያይና አከራካሪ ሴምናሮችን
ማዘጋጀት ሌሎችና ዘዴዎችን መቀየስ ይሆናል፡፡111

3.5 የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት በኢትዮጵያ

በፓሪስ መርሆዎች ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ሊቋቋሙ የሚችሉት መንግስታት
በአገራቸው በሚያወጡት ህገመንግስት ወይንም በሌሎች በማስቻያ አዋጆች፣ ደምቦች እና በሌሎች አንስተኛ ህጎች ሊሆን

107
ራስጌ 95
108
Office of the united nations high cmmisioner for human right,assessing the effectiveness of national human
right insttuitonns,international council on human ragit policy2005p.7
109
ራስጌ 66
110
ዝንከማሑ
111
Office of the united nations high cmmisioner for human right,handbook national human right plans of
action,professional training series No.10,united nations new yurk and jeneve 29august 2002P.12
28
እንደሚችል በዚሁ ጥናት ላይ ተመልክተናል፡፡ በዚህም መሰረት የተለያዩ አገሮች እነዚህን ተቋሟት በህገመንግስታቸው
በመመስረት ዝርዝር ስለጣናቸውና ተግባራቸውን እዛው በህገመንግስቱ ላይ ዘርዝረው ያሰቀምጣሉ፡፡ሥልጣናቸውና ተግባራቸው
በህገመንግስታቸው ላይ ካሰፈሩ አገሮች መካከል ለምሳሌነት የደቡብ አፍሪካንና ዩጋንዳን መመልከት ይቻላል፡፡ 112 በሌላ በኩል
ደግሞ የተቋማቱን መመስረት በተመለከተ በህገ መንግስቱ እንደ ሚቋቋሙ ድንጋጌ በማስቀመጥ ተቋሟቱን በማስቻያ
ሕጎች በተለይም በአዋጆች መሰረት ያቋቋሟሉ፡፡ በማስቻያ አዋጆች መሰረት ከተቋቋሙ የብሄራዊ ሰብአዊ ተቋመዋት
መካከል የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም መጥቀስ ይቻላል፡፡

በኢትዮጵያ የብሄረራዊ ሰበአዊ መብት ተቋሟት አመጣጥ ስንመለከት በተግባር የተመሰረቱት ከኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገመንግስት ጋር
የተያያዘ ነው፡፡ በሕገ መንግስቱ እንደሚቋቋሙ በይፋ ከተጠቀሱት አካላት መካከል የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና
የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ይገኙባቸዋል፡፡113ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስልጣንና ተግባር የሚዘረዝረው የህገ
መንግስቱ አንቀጽ 55

ንኡስ 14 ና 15 በእትዮጵያ ሁለቱም የ ተቋሟት እንደ ሚቋቋሙ ማስፈሩን ከዚህ በታች እንደሚከተለው ማየት
እንችላለን፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

(14) የሰብአዊ መብቶችን ኮሚሽን ያቋቁሟል፡፡ሥልጣንና ተግባሩን በህግ ይወሰናል፡፡114

(15) የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋምን ያቋቁሟል፡፡ ተቋሙን የሚመሩ አባላትን ይመረጣል፡፡ ይሰይማል፡፡ ስልጣንና ተግባሩን በህግ
ይወስናል፡፡115

እነዚህ ተቋማት በሀገራችን ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ በመሆናቸው አስፈላጊውን ልምድ ለመቅሰም ሲባል ከ 68 ሀገሮች
የተውጣጡ ታዋቂ ባለሙያዎችና የሀገር ውስጥ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የሕግ ኤክስፐርቶችና ተመሳሳይ ሥልጠና ያላቸወረ
ሌሎች ባለሙያዎች የተካፈሉባቸው ኮንፈረንሶች በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንቦት ወር 1990 ዓ/ም በኢትዮጵያ
ተካሂደዋል፡፡ ከእነዚህም ልምዶችንና መረጃዎችን የማሰባሰብ ሂደት በኋላ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንና
የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም እንደየ ቀደምተከተላቸው በአዋጅ ቁጥር 210/92 እና በአዋጅ ቁጠር 211/92
የጠቋቋሙት፡፡116

አዋጆቹ እያንዳንዳቸው በአምስት ምዕራፎችና በአርባ አራት አንቀጾች የተከፈሉ ናቸው፡፡ በአዋጆቹም ውስጥ የአካላቱ
ሥልጣንና ተግባር፤ የየአካላቱ የአሠራር ደንቦችና የሠራተኞችቸው አስተዳደር ጉዳዮችና ሌሎች ዋናዋና ነጥቦች እንዲካተቱ

112
Liliam Manka Chenwi,national human right institutions”A comparative Study Of The National Commissions Of
Human rights Of Cameroon and South Africa ,suvmitted in partial fulfillment of(LLM)(uhman right and democratization
in afirica)centr for humn right, university of pretoria,21 oct.2002 P.18
113
Ato Mesffin G/Hiwot, Concept paper on human rights commission and office of ombudsman prepared and
submitted to the standing legal committee of the house of peoples’representative,January 1998p.1
114
ራስጌ 10

115
ዝንከማሑ አቀጽ 55(14)
116
የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጆችና የማብራሪያ ጽሑፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕግ
ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ ሰኔ 1991
29
ተደርገዋል፡፡ከዚህም ሌላ ልዩነቶቻቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የሁለቱም አካላት አደረጃጀትና አሠራር በአብዛኛው የሚመሳሰሉ
በመሆናቸው የአዋጆቹም ይዘት ተቀራራቢነት ያለው ነው፡፡117

ሁለቱም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት አላማቸው በየተቋቋሙበት አዋጅ አንቀጽ 5 ላይ ተቀምጧል፡፡

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን አንቀጽ 5 ን ስንመለከት ሶስት ዋና ዋናዓላማዎች ያሉት ሲሆን እነርሱም

 ሕዝቡ ስለ ሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ እንዲኖረው ማስተማር፣

 መብቶች እንዳይጣሱ መጠበቅና ሳይሸራረፉ ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግና

 ተጥሰው ሲገኙም አሰፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ናቸው፡፡118

እንዲሁም የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ አንቀጽ 5 እንደዚሁ ብንመለከት በሁለት መሰረታዊ አላማዎች ላይ
ያተኮሩ ናቸው፡፡ እነርሱም

 በህግ የተደነገጉ የዜጎች መብቶች ጥቅሞች በአስፈፃሚ አካላት መከበራቸውን ማረጋገጥ፣

 የህግ የበላይነትን መሠረት ያደረገ ጥረት፣ ቅልጥፍና ግልፅነት ያለው መልካም የመልካም አስተዳደር እንዲሰፍን
ማድረግ ናቸው፡፡119

ከላይ የተመለከትናቸው አንቀጾች መኖራቸው የሚያሳየን ተቋሟቱ አላማቸው ሰብአዊ መብትን በአገሪቱ ውሰጥ
በአግባቡ ለማስጠበቅ እና ሰለ ሰብአዊ መብት ግንዛቤ ለማስፋፋት ትለቅ ሚና ያላቸው መሆኑን ነው፡፡ ይህም ከፓሪስ
መርሆዎች አንጻር የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት የሚጠበቅባቸውን የሰብአዊ መብት ጥበቃና የግንዛቤ ማስፋፋት
ተግባራት ለማካሄድ የሚያስችሉ ህጎች መኖራቸውን መገንዘብ ይቻላል፡፡

በኢትዮጵያ የተቋሟቱን አደረጃጀት በተመለከተ ተቋማቱ ተጠሪነታቸው ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሲሆን አንዳንድ
ዋና ኮሚሽነርና ዋና ዕንባ ጠባቂ ሲኖራቸው አንዳንድ ምክትል፣ አንዳንድ የሕፃናትና የሴቶች ጉዳይ የሚመሩና
የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ኮሚሽነሮች ወይም ዕንባ ጠባቂዎችም እንደሚኖራቸው አዋጆቹ ያመለክታሉ፡፡120

ከፓሪስ መርሆዎች አንዱ የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት የተሷሚዎችን ሰብጥር ወይንም ብዝሀነትን ማረጋገጥ
እንደሆነ አስቀምጧል፡፡ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮምሽንና የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ አዋጆች
ስለሚሾሙ ሰዎችና እንዲሁም ስለ አሿሿም ስርአትና ሂደት ከመርህዎቹ ጋር በማጣጣም ብዙሀነት ተንጸባርቆበታል፡፡
ስራቸውንም በሙሉ ነፃነት እንድያከናውኑ ለማስቻል ተሿሚዎቻቸውና መርማሪዎቻቸው የሕግ ልዩ ጥበቃ መብት
በተለየ ሁኔታ ተሰጥቷቿል፡፡ህይም የሚያመላክተው ተቋሟቱን ነፃነት ለማረጋገጥ ሕጎቹ ዋስትና መስጠታቸውን ነው፡፡

የየተቋማቱ ዋና መ/ቤት በአዲስ አበባ መሆኑንና አዋጅ የሚያመለክት ሲሆን በተወካዮች መ/ቤት በሚወስነው
በማናቸውም ሥፍራም ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሊኖራቸው እንደሚችል ተመልክቷል፡፡121

117
ዝንከማሑ
118
ራስጌ 16 አንቀጽ 5
119
የኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ለማቋቋም የወጣ አዋጅ
ቁጥር 211/92 አንቀጽ 5
120
ራስጌ 117
121
ዝንከማሑ
30
በማንኛውም ስፍራ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ በአዋጆቹ መደንገጉ ተገለጋዮች ማግኘት
የሚፈልጉትን አገልግሎቶች ተደራሽነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡ ይህም የሚየሳየው ተቋሟቱ በቦታ
ሳይገደቡ የዜጎች መብቶች እንዲከበሩ ያግዛል፡፡

31
ምዕራፍ 4

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኢሰማኮ ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በማስጠበቅና በማስከበር ያለው ሚና

4.1 የኢሰማኮ የህግ መሰረት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኢፌዴሪ ህገ መንግስት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር በሚዘረዝረው
የህገ መንግስቱ አንቀፅ 55/14 መሰረት እንደሚቋቋም ሰፍሯል፡፡ በዚሁ አንቀጽ መሰረት ምክር ቤቱ የሰብአዊ መብቶችን ኮሚሽን
እንደሚያቋቁምና ሥልጣንና ተግባሩን በህግ እንደሚወስን መመልከት ይቻላል፡፡122 በእርግጥ በፓሪስ መርሆዎች መሰረት ብሄራዊ
የሰብአዊ መብት ተቋሟት ሊቋቋሙ የሚችሉት መንግስታት በአገራቸው በሚያወጡት ህገ መንግስት ወይንም በሌሎች
ማስቻያ አዋጆች፣ ደምቦች እና ሌሎች ህጎች ሊሆን እንደሚችል ያሳያል፡፡ ኢሰመኮ እንደ አንድ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋም
በፓሪስ መርሆዎች አንጻር ሲታይ ህገ መንግስታዊ እውቅና ያለው ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋም ነው፡፡ ከምንም በላይ ግን
በህገ መንግስቱ ምእራፍ ሶስት ስር ስለ መብቶች ሰፍ ሽፋን መስጠቱን በዚህ ጥናት ምእራፍ ሁለት ውስጥ ለማዬት
ተሞክሯል፡፡ የሰብአዊ መብቶችን አፈጻጸም የማረጋገጥ ሀላፊነት በዋናነት የተጣለባቸው አካላት በህገ መንግስቱ
አንቀጽ 13/1/ መሰረት ማንኛውም የፌዴራልና የክልል ህግ አውጪዎች፣ አስፈጻሚ አካላትና የዳኝነት አካሎች በህገ መንግስቱ
ምእራፍ ሶስት ውስጥ የተካተቱትን ድንጋጌዎች የማስከበርና የማክበር ግዴታና ሀላፊነቶች እንዳለባቸው
ተደነግጓል፡፡123 በተመሳሳይ መልኩ ይህ ሃሳብ በኢሰመኮ አዋጅ መግቢያ ላይ በግልጽ ተንጸባርቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአንቀጽ
9(2) መሰረት ማንኛውም ዜጋ የመንግስት አካላት የፖለቲካ ድርጅቶች ሌሎች ማኅበራት እንዲሁም ባለስልጣኖቻቸው ሰብአዊ
መብቶችን ጨምሮ ሕገ መንግስቱን የማስከበርና ለሕገ መንግስቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው፡፡124 በዚህ ንኡስ አነቀጽ
የመንግስት አካላት የሚለው ኢሰመኮንም እንደሚያጠቃልል ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም ከኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ መግቢያ
ማየት እንደሚቻለው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መብቶችንና ነፃነቶችን በማስከበር ረገድ የላቀ ድርሻ እንዳለው ከመግለጹ
ባሻገር በአንቀጽ 3 ላይ ኮሚሽኑ ህጋዊ ሰውነት ያለው ነጻ መንግስታዊ የሆነ የፌዴራል አካል መሆኑ ተደንግጓል፡፡125

ከላይ እንደተመለከትነው ኢሰመኮ ህገ መንግስታዊ እውቅና በማግኘት በ አዋጅ ቁጥር 210/1992 ተቋቁሟል፡፡ ምናልባት እዚህ
ላይ እንደጥያቄ ለማንሳት ያህል የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ስልጣንና ተግባራቸው በህገ መንግስት ተዘርዝረው ሲቋቋሙና
በሌላ በኩል እንደ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በማስቻያ አዋጅ ሥልጣንና ተግባራቱ ተዘርዝረው ሲቋቋሙ ያለው የህግ
እሳቤ ልዩነት ምን እንደሆነ ለማወቅ ያዳግታል፡፡ እነዚህ ተቋሟት በህገ መንግስት ሆነ በማስቻያ አዋጅ ማቋቋሚያ አዋጅ
ቢቋቋሙም የማስፈጸሚያ ተከታይ ህጎች መውጣቱ የማይቀር ነው፡፡ ህገ መንግስትን በተመለከተ አጠቃላይ ድንጋጌዎችን
መያዝ እንዳለበት በዘርፉ ያሉ ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ ይህም እንዳለ ሆኖ የተለያዩ አገራት በህገ መንግስታቸው ውስጥ
የተቋሟቸውን አጠቃላይ ስልጣና ተግባራቸውን በመዘርዘር ህገ መንግስቱን ተፈጻሚ የሚያደርጉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በህገ
መንግስታቸው ላይ አጠቃላይ ድንጋጌ በማስቀመጥ መብቶች የሚፈጸሙበት ማስቻያ አዋጆችን ያወጣሉ፡፡

በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ መግቢያ ላይ እንደተመለከተው ኮሚሽኑ የተቋቋመበት መሠረታዊ ምክንያቶች የግለሰቦችን እና
የብሄር ብሄረሰብ መብቶች እንዲከበሩ፣ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገቶችን ለማፋጠን፣
የሕግ የበላይነትን እና በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ ለመገንባት፣ የፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ
እናባህሎችና ሃይማኖቶች ካለአንዳች ልዩነት እንዲራመዱ ለማስቻል ነው፡፡126
122
ራስጌ 10 አንቀጽ 55 (14)
123
ዝኒከማው አንቀጽ 13 (1)
124
ዝንከማሑ አንቀጽ 9 (2)
125
ራስጌ 16 መግቢያ
126
ዝንከማሑ
32
የኮሚሽኑ ዋነኛ ዓላማዎች ደግሞ በኢፌዴሪ ህገመንግስት በተደነገገውና ሕገ-መንግስቱን ተከትለው በወጡ የሀገሪቱ ህጎችና
ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው የአገሪቱ የህግ አካል ተደረገው የሚቆጠሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙ የሰብአዊ መብት
መርሆዎች መሰረት ህዝቡን ስለሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ እንዲኖረው ማስተማር፤ ሰብአዊ መብቶቹ እንዳይጣሱ መጠበቅ፤
መብቶቹ ሳይሸራረፉ ስራ ላይ እንዲውሉና ተጥሰው ሲገኙ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ናቸው፡፡ 127 ኮሚሽኑ በህገ
መንግስቱ እውቅና የተሰጣቸው ሰብአዊ መብቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት የተጣለበት
ለዴሞክራሲያዊ ስርዓትና የህግ የበላይነት ለማስፈን እንዲሁም የሰብአዊ መብት ስምምነቶችና የህገ-መንግስቱን መርሆዎች
ተፈፃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በህገ-መንግስቱ እውቅና ያገኘ ብሄራዊ ተቋም ነው፡፡

እንደ ሌሎች አቻ የሰብአዊ መብት ተቋማት ሁሉ ኢሰማኮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙ መለኪያዎችን አካቶ ሰፊ
ስልጣን ይዞ ተደራጅቷል፡፡128

ስለዚህ የኢሰመኮ የህግ መሰረት ከላይ ለማየት እንደሞከርነው የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ሲሆን ህገ መንግስቱን ተከትሎ አዋጅ ቁ.
210/92 ወጥቷል፡፡ በመሆኑም ኢሰመኮ በአገሪቱ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ እንደ ማንኛውም የመንግስት አካል ግዴታ ያለበት
በመሆኑንና ከሌሎች መንግስታዊ አካላት በተለየ ደግሞ የብሄራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋም እንደመሆኑ ለሰብአዊ መብቶችና
ነጻነቶች መፈጸም የበኩሉን አስተዋጽኦ መወጣት ያለበት ተቋም ነው፡፡129

4.2 የኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ ይዘት አጭር ትንተና

በፓሪስ መርሆዎች እንደሰፈረው ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት በማቋቋሚያ ህጋቸው መወጣት ያለባቸው ሀላፊነትና ሰፊ
የስራ ስልጣን ሊሰጣቸው እንደሚገባ መመልከታችን ይታወቃል፡፡ የሚሰጣቸው ሰፊ ስልጣን ሰብአዊ መብቶችን የማስጠበቅና
ግንዛቤ የማስፋፋት ተግባርን ማጠቃለል እንዳለበት፣ በማቋቋሚያ ህጎች ማለትም በህገ መንግስቱ ወይንም በአዋጃቸው
በተቻለ መጠን ሊያሰራ የሚችል ስልጣን ሊሰጣቸው እንደሚገባና ይኽውም በህጉ ላይ መገለጽ እንደሚያስፈልግ
ያስቀምጣል፡፡130 ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች መርሆዎችን ማለትም ጥንቅር ነጻነትና ብዝሀነት፣ የአሰራር ስርአትና ከፊል
የዳኝነት ስልጣን በህጎቻቸው ሊረጋገጥላቸው አስፈላጊ መሆኑን ይገልጻል፡፡131

ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ አጠቃላይ ይዘት ስንመለከት አዋጁ በአምስት ምዕራፎችና
በ 44 አንቀጾች ተከፍሏል፡፡

የመጀመሪያው የአዋጁ ምዕራፍ ስለ ኮሚሽኑ አጠቃላይ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን የተወሰኑትን አንስተን ለማየት ያክል አንቀጽ
3 ኮሚሽኑ ህጋዊ ሰውነት ያለው ነጻ የፌዴራል መንግስት ተቋም ሆኖ መቋቋሙን ያሳየናል፡፡ 132 የአዋጁን የተፈፃሚነት ወሰን
በተመለከተ በአንቀጽ 4 ስር ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ሰብአዊ መብቶችን የማስከበር ሥልጣን የፌዴራል መንግስት፣ የክልል መንግስታትና
ሌሎች አካላትም ግዴታ እንደተጣለባቸው ከህገ መንግስቱ መረዳት ይቻላል፡፡

በአዋጁ አንቀፅ 4(1) እንደተገለፀው በማንኛውም ክልል በሚፈፀሙ የሰብአዊ መብቶች መጣስ ጉዳዮችም ላይ አዋጁ
ተፈፃሚነት እንዳለው ተደንግጓል፡፡133 አንቀጽ 4(2) በተለይ በሴቶች ላይ ይደርስ የነበረውን ተፅዕኖ እና ልዩነት ከግምት ውስጥ

127
ዝንከማሑ አንቀጽ 5
128
የኢትዮያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የመጀመሪያው አምስት ዓመታት የሥራ ዘመን ሪፖርት አዲስ አበባ 2003 ገጽ 41
129
ዝኒክማሑ
130
ራስጌ 17
131
ዝኒክማሑ
132
ራስጌ 16 አንቀጽ 3
133
ዝኒክማሑ አንቀጽ 4 (1)
33
በማስገባትና በኮሚሽኑ መብትን የማስከበር ዓላማ ልዩ ተጠቃሚ ለማድረግ በማሰብ የተፈጻሚነት ወሰኑን በወንድ ፆታ የተገለጸው ሴቶችንም
እንደሚጨምር በይፋ አስቀምጧል፡፡134

በተቃራኒው ደግሞ የአዋጁ አንቀፅ 7 ስንመለከት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የማያያቸውን ጉዳዮችን ደንግጓል፡፡ ኮሚሽኑ ከሰብአዊ
መብት መጣስ ጋር የተያያዘውን አቤቱታ ተቀብሎ በመመርመሩ ረገድ ሙሉ መብት በአዋጁ ተሰጥቶታል፡፡ ነገር ግን ኮሚሽኑ ተጠሪ የሆነለት
አካል ወይም የራሳቸውን ጉዳይ ገለልተኛና ነፃ ሆነው እንዲያዩ በሕግ መብቱ በተሰጣቸው አካላት ውስጥ ጣልቃ መግባት ሊደርስ የሚችለውን
ግጭት ለማስወገድ ሲባል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በፌዴሬሽን ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤቶች ወይም በፍርድ ቤቶች
በመጀመሪያ፤ በይግባኝ ፤ በሰበር ወይም በአፈጻጸም በመታየት ላይ ያሉ ጉዳዮችን እንዳያይ ገደብ ተደርጎበታል፡፡135 ነገር ግን ማናቸውም አካላት
ወይም ባለሥልጣኖቻቸው ከሕግ በላይ ስላልሆኑ በያዙት ጉዳይ ላይ የየራሳቸውን ውሳኔ ከሰጡ በኃላ ወደፊት መሻሻል ባለባቸው ፖሊሲዎች፤
ሕጎች፤ መመሪያዎች …ወዘተ ላይ ጥናት አካሂዶ ለመንግስት አስተያየት ማቅረብ ይችል ዘንድ ከማየት በማያግደው መልኩ አንቀጹ መደንገጉን
አዋጁ ሲረቅ ከተዘጋጀው ቃለ ጉባኤ መረዳት ይቻላል፡፡136

የኮሚሽኑን ሥልጣንና ተግባራቱን ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋር በሚስማማ መልክ እንደተዘጋጀ ከአዋጁ መግቢያ መረዳት ይቻላል፡፡ አዋጁ
ስልጣንና ተግባርን በሁለት መልኩ ያስቀመጠ ሲሆን እንደ ተቋም በአንቀጽ 6 እንዲሁም የተቋሙ ኮሚሽነሮች የሚኖራቸውን ሥልጣንና ተግባር
ከአንቀጽ 19-21 ባሉት አንቀጾች ውስጥ አካቷል፡፡137 በተጨማሪም የዋናው መሥሪያ ቤትና የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ሥልጣንና ተግባር
በመደራረብ ሊያስከትል የሚችለውን የሥራ ግጭት ለማስወገድ ሲባል ለዋናው ኮሚሽነር ብቻ በተሰጡ ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ ተወስዷል፡፡

የኮሚሽኑ ዓበይት ስልጣንና ተግባራት በማቋቋሚያ አዋጅ አንቀፅ 6 ላይ በዝርዝር ተገልጸዋል፤ እነርሱም፡-

 በኢፊዴሪ ሕገ-መንግስት እውቅና የተሰጣቸው ሰብአዊ መብቶች በማንኛውም ዜጋ፣ በመንግስት አካላት፣ በፖለቲካ ድርጅቶች፣ በሌሎች
ማህበራት እንዲሁም በባለስልጣኖቻቸው መከበራቸውን ማረጋገጥ

 በመንግስት የሚወጡ ህጎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እንዲሁም ትዕዛዞች በህገ መንግስቱ ከተረጋገጡት የዜጎች ሰብአዊ መብቶች ጋር
የማይቃረኑ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣

 ሕብረተሰቡ ስለ ሰብአዊ መብት በቂ ዕውቀት ኖሮት መብቱን የማክበርና የማስከበር ባህል እንዲያዳብር መገናኛ ብዙሃንና የተለያዩ ዘዴዎችን
በመጠቀም ማስተማር፣

 የሰብአዊ መብት ጥሰትን አስመልክቶ ቅሬታዎች ሲቀርቡለት ወይም በራሱ ተነሳሽነት ምርመራ ማካሄድ፤

 ነባር ህጎች እንዲሻሻሉ አዳዲስ ህጎች እንዲሁም ወይም ፖሊሲዎች እንዲወጡ ማስቻል፣

 በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ የምክር አገልግሎት መስጠት፣

 ለዓለም አቀፍ አካላት በሚቀርቡ የሰብአዊ መብት ሪፖርት ላይ አስተያየት መስጠት፣

 ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነዶችን በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች መተርጎምና ማሰራጨት፤

 በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስብሰባዎች፣ ኮንፈረንሶች ወይም ሲምፖዚየሞች ላይ መሳተፍ፤

 የንብረት ባለቤት መሆን፤ ውል መዋዋል፤ በስሙ መክሰስና መከሰስ፤ እና

134
ራስጌ 16 አንቀጽ 4(2)
135
ዝኒኪማሑ አንቀጽ 7
136
ራስጌ 117 ገ 4-5
137
ራስጌ 16 አንቀጽ 6 ፤ አንቀጽ 19 -21
34
 ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባሮችን ማከናወን ናቸው፡፡138

ከላይ የዘረዘርናቸውን ስልጣንና ተግባራት በዚሁ ምዕራፍ በሚቀጥለው ንኡስ ክፍል ውስጥ እንመለከታለን፡፡

የማቋቋሚያ አዋጁ በአንቀጽ 8 የኢሰማኮ መዋቅራዊ አደረጃጀት የደነገገ ሲሆን እነርሱም የኮሚሽነሮች ጉባኤ፤ አንድ ዋና ኮሚሽነር፣ አንድ ምክትል
ዋና ኮሚሽነር፣ የህጻናትና የሴቶች ጉዳዮችን የሚመራ ኮሚሽነር፤ ሌሎች ኮሚሽነሮች እና አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ሠራተኞች በተዋረድ
ያካትታል፡፡139 ይህ ሁኔታ የህግ አውጭው አካል ህጉን ሲያዘጋጅ ከፓሪስ መርሆዎች ጋር እንዲጣጣም ተደርጎ የወጣ መሆኑን ያሳያል፡፡

የአዋጁ አንቀጽ 9 በግልፅ የሰብአዊ መብት ተቋም በተለያዩ ስፍራዎች እንዲስፋፋና የበለጠ እየተጠናከሩ እንዲሄዱ ያለውን ፍላጎት በሚያሳይ
መልኩ ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ጽ/ቤት በማቋቋም ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን በሚያደርገው እንቅስቃሴ በተለያዩ የሀገሪቷ ክልሎች
ስምንት ቅርንጫፎችን በመክፈት በህግ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

የአዋጁ ሁለተኛው ምዕራፍ ስለ ተሿሚዎች ስልጣንና ተግባራት የያዘ ሲሆን የዋና ኮሚሽነር ስልጣንና ተግባር፣ የምክትል ዋና ኮሚሽነር እና
የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ኮሚሽነሮች ስልጣንና ተግባራትን በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ይሁን እንጂ ምንም እንኳን ከላይ የተመለከትናቸው አካላት
ስልጣንና ተግባራት ቢኖሩም አዋጁ የህጻናትና የሴቶችን ኮሚሽነር መወጣት ያለበትን ስልጣንም ሆነ ተግባራትን አላስቀመጠም፡፡ ይህ በመሆኑ
በአዋጁ አተገባበር ዙሪያ የራሱን የሆነ ክፍተት መፍጠሩ የቀረ አይመስልም፡፡

የአዋጁ ምዕራፍ ሦስት ስለ ኮሚሽኑ የአሠራር ደንቦች በዝርዝር አካቷል፡፡ በኮሚሽኑ አሰራር ደንቦች ስር በአዋጁ ከተካተቱት መካከል አበቱታ
የማቅረብ መብት፣ ስለአቤቱታ አቀራረብ፣ ስለምርመራ አካሄድና ሌሎች ድንጋጌዎችን እንደያዘ መመልከት ይቻላል፡፡ ኮሚሽኑ አቤቱታ ተቀብሎ
የሚመረምረው ያለምንም ክፍያ ነው፡፡140

የአዋጁን ምዕራፍ 4 ስንመለከት ስለ ኮሚሽነሮች ጉባኤ አሰራርና አስተዳደር እንዲሁም ስለ ኮሚሽኑ አባላትና ሰራተኞች የሚመለከቱ
ድንጋጌዎችን አካቷል፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ጉባኤው ሰፊ ስልጣንና ተግባራት እንዲያከናውን ህጉ ግዴታ ጥሎበታል፡፡ ጉባኤው ከተጣለባቸው
ግዴታዎች መካከል የውስጥ ደንቦች አሰራርና መመሪያዎችን ማጽደቅ፣ በኮሚሽኑ አመታዊ በጀት ዙሪያ ተወያይቶ ለምከር ቤቱ ማቅረብ
የሰራተኞችን አቤቱታ በይግባኝ ተቀብሎ ማየትና የመምርያ ሀላፊዎችን ሹመት የሚመለከቱ ግልፅ ድንጋጌዎችን አካቷል፡፡141

በስተመጨረሻም አዋጁ በምዕራፍ አምስት ውስጥ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን አስፍሯል፡፡ በልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ስር አዋጁ ከተመለከታቸው ጉዳዮች
መካከል የመተባበር ግዴታ፣ መግለጫ ስለመስጠት፣ በስም ማጥፋት ስላለመጠየቅ፣ ስለቅጣትና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ድንጋጌዎችን አጠቃሎ
ይዟል፡፡142

በተለይም በፓሪስ መርሆዎች መሰረት የብሄራዊ ተቋሟት ይፋዊ መግለጫ መስጠት እንዳለባቸው ተቀምጧል፡፡ በዚሁ አኳኋን የኢትዮጵያ
ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀፅ 39 የግልፅነት መርህን አስመልክቶ ባሰፈረው ድንጋጌ ኮሚሽኑ እንደአስፈላጊነቱ ይፋዊ መግለጫ
መስጠት እንዳለበት በተለይ ደግሞ ኮሚሽኑ መደበኛ ሪፖርቶች ማቅረብን ጨምሮ የሀገሪቱን ፀጥታና ደህነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ለማድረግና
ወይም የግለሰቦችን ህይወት መብት ለመጠበቅ ሲባል በሚስጥር ሊያዙ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ኮሚሽኑ ጥንቃቄ የመውሰድ ግዴታ እንዳለበት
የተጠበቀ ሆኖ አሰራሩን ለህዝብ ግልፅ ማድረግ እንዳለበት ተደንግጓል፡፡143

በአጠቃላይ የማቋቋሚያ አዋጁ በዚህ ጥናት መሰረት ሲታይ እስካሁን በተወሰነ መልኩ መመርመር እንደተቻለው አዋጁ በይዘትም ሆነ በቅርጹ
በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች፣ በአህጉራዊ የሰብአዊ መብቶችና በአገራዊ ህጎች ላይ እውቅና የተሰጣቸውን መብቶች ተፈጻሚነት የሚረዱ በቂ

138
ዝኒከማሑ አንቀጽ 6
139
ዝኒከማሑ አንቀጽ 8
140
ዝኒከማሑ አንቀጽ 22(4)
141
ዝኒከማሑ ምዕራፍ 4
142
ዝኒከማሑ ምዕራፍ 5
143
ዝኒከማሑ አንቀጽ 39
35
ድንጋጌዎችን ይዟል ማለት ይቻላል፡፡ አዋጁ በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋሟትን አስመልክቶ ከወጣው
መርሆዎች አንጻር ሲመረመር በመርህዎቹ እውቅና ያገኙትን ቁምነገሮች ሙሉ በሙሉ ብሎ መደምደም በሚያስችል ሁኔታ በአዋጁ ድንጋጌዎች
ውስጥ ተረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ የማቋቋሚያ አዋጁ በሚያስገርም ሁኔታ ሕገ መንግስታዊ መብቶችን ለማስከበርና ለማስጠበቅ እንዲሁም
የፓሪስ መርሆዎችን ከግምት በማስገባት የተዘጋጀ ቢሆንም አዋጁ አንድም ስፍራ ላይ የፓሪስ መርሆዎችን ሳይጠቅስ አልፏል፡፡

4.3 ኢሰመኮ መብቶችን ለማስጠበቅና ለማስከበር የሚጠቀምባቸው ስልቶች

በዚህ ጥናት ምዕራፍ 1 በ 1.7 ስር በተገለጸው መሰረት ጥናቱ የሚከተለው የሕግ ጥናት ምርምር ስልት ሲሆን በሕጎች ውስጥ ተካተው ያሉትን
የሕግ ድንጋጌዎች አግባብነታቸውን ወይም ውስንነታቸውን መመርመር፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሕጎቹ ውስጥ መካተት የነበረባቸው ድንጋጌዎች
ሳይካተቱ ቀርተው እንደሆነ በጥናት በማስደገፍ ድንጋጌዎቹ ሕጎቹ ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ ሕጎቹ እንዲሻሻሉ ወይንም እንዲሻሩ የሚያደርግ
የጥናት ስልት እንደሆነ ተመልክተናል፡፡144 ከዚህም በመነሳት ይህ ጥናት የኢሰመኮ አዋጅ ሰብአዊ መብቶችን ለማስጠበቅና ግንዛቤ ለማስፋፋት
በህጉ ላይ ያለውን በተለይም ከምርመራ፣ ከክትትል፣ ከምክርና ከግንዛቤ ማስፋፋት ጋር በተገናኘ እንደሚከተለው ለመፈተሽ ይሞክራል፡፡

4.3.1 የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ

በብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተግባራት ተብለው የሚቆጠሩት የጥሰት ምርመራ፣ የሰብአዊ መብት ክትትልና ምክር
መሆናቸውን መረዳት ይቻላል፡፡145 በዚህ መሰረት ከላይ ያየናቸውን የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተግባራትን ከአዋጁ አንጻር እናያለን፡፡

4.3.1.1 የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ


የሰብአዊ መብቶች ምርመራ ማለት ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ፣ የማይጣሱ እና የማይገፈፉ የሆኑት ሰብአዊ መብቶች ሲጣሱ እና ሲገፈፉ
የሚደረግ ምርመራ ነው። ማን ነው መብቶችን የጣሰው፣ እንዴት፣ መቼ እና የት እንዲሁም የተጣሰው መብት የመብት አይነት እና የመሳሰሉትን
ጥያቄዎች የሚመልስ ጥልቅ ምርምር የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ ሊባል ይችላል።146 ምርመራ የሚያካትተው አቤቱታ ወይንም ክስ
የቀረበለት አካል ጉዳዩን ከመመልከቱ በፊት ክሱን ወይንም አቤቱታውን ለመመርመር ሙሉ ስልጣን ወይንም በከፊል ስልጣን በህጉ
እንደተሰጠው ማጣራት፣ በቂ መረጃ መቅረቡን ካረጋገጠ በኋላ የሰብአዊ መብት ጥሰት ወይም ሕገ-ወጥ ተግባር ስለመፈፀሙና በማን
እንደተፈፀመ የመለየት ሥራዎችን ነው፡፡147 የምርመራ ተግባርን በአግባቡ ለማከናወን አቤቱታው መሠረት ያለው መሆኑንና ለዚህም ሃላፊው
ማን ነው? የሚለውን ለመወሰን የሚያስችል ሥልጣን በህግ ሊሰጥ ይገባል፡፡ ይህም ሲባል አቤቱታው የቀረበበትን ወገን መልስ እንዲሰጥ
የማድረግ፣ ጉዳዩን ለማጣራት አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችንና ሰነዶችን አስቀርቦ የማየት ወይም እንዲያቀርቡ የማስገደድ፣ ሁለቱን ተከራካሪ
ወገኖች በተፈለጉ ጊዜ እንዲቀርቡ የማዘዝ፣ ስለጉዳዩ በቂ እውቀት ይኖረዋል ተብሎ የሚገመተው ሰው ከመርማሪው ዘንድ ቀርቦ ስለጉዳዩ
የሚያውቀውን እንዲያስረዳ የማድረግና ለዚህ ስራ ተገቢነት ይኖራቸዋል ተብሎ የሚገመቱትን የማከናወን ስልጣን የሚያካትትና ይህም በህግ
ሊረጋገጥ የሚገባ ነው፡፡148

አዋጁ የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራን አስመልክቶ የደነገገው ትርጉም ባይኖርም በአንቀጽ 6 ንኡስ 4 የሰብአዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ
ኢሰመኮ ቅሬታዎች ሲቀርቡለት ወይም በራሱ አነሳሽነት ምርመራ በማካሄድ አስተያየቶችን ወይንም የውሳኔ ሀሳቦችን እንደሚሰጥ ደንግጓል፡፡149

144
Dr.khushal Vibhute and Filipos aynalem,legal research methods,by justice and legal system research institute 2009
22
145
ራስጌ 22PP.59_83
146
ራስጌ 94
147
ዝኒከማሑ
148
ራስጌ 66
149
ራስጌ 16 አንቀጽ 6(4)
36
በዚህ በህግ በተሰጠው ስልጣን አማካኝነት ኢሰመኮ ዜጎች በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን መብቶችና ነፃነቶች ሲጣሱባቸው አፀፋዊ ምላሽ
የሚሰጡበት ስርዓትን የሚያጠናክር ነው፡፡150

የኢሰመኮ የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ ስልጣን በአዋጁ አንቀጽ 6 ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ አዋጁ በአንቀጽ 22 መሰረት አቤቱታ
የማቅረብ መብትና ማን ማቅረብ እንደሚችል በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ በዚህ አንቀጽ መሰረት አቤቱታ የሚቀርበው ኢሰመኮ ምንም አይነት
ክፍያ ሳይቀበል መብቴ ተጥሶብኛል በሚል ሰው ወይም በሚስት ወይም በባል፤ ወይም በቤተዘመድ ወይም በግል ወይም በሶስተኛ ወገን ሊሆን
እንደሚችል ተገልጿል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁኔታ እንደተፈፀመው የሰብአዊ መብት ጥሰት ክብደት ኮሚሽኑ የአመልካቹ ደህንነት ለመጠበቅ
ሲባል ማንነት ሳይገልፅ የሚቀርብለትን አቤቱታዎች የመቀበልና የመመርመር ስልጣን አለው፡፡151

በፓሪስ መርሆዎች እንደተገለጸው በአሰራር ውስጥ ሊታዩ ከሚገባቸው ጉዳዮች መካከል የተደራሽነት ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ አንድ አቤቱታ አቅራቢ
ቅሬታው እንዲታይለት ህጉ ሊያሰሩ የሚችሉ ድንጋጌዎችን መያዝ አለበት፡፡ በዚህ ረገድ አዋጁ ሲታይ ለአካል ጉዳተኞች በተለይም ለምልክት
ቋንቋ ተጠቃሚዎች፣ ለተለያዩ የእምነት ቡድኖችና ሌሎች ለመብት ጥሰት ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ የተደራሽነት ስልቶች በአዋጁ
ሊካተቱ ሲገባ በዝምታ ያለፋቸው ይመስላል፡፡152 ይህ ማለት ግን ከላይ የተጠቀሱት የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት አያገኙም ማለት
አይደለም፡፡ ነገር ግን አዋጁ ተደራሽነትን በግልጽ ቢያረጋግጥ የእነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች መብቶች በተሟላ ሁኔታ ለማክበርና ለማስከበር
ይረዳል፡፡

አዋጁ ላይ ከላየ የታዩት ክፍተት ቢኖርም የኮሚሽኑ የምርመራ ስነ ስርአት መመሪያ በአንቀጽ 57 ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ
ክፍሎች መሆናቸውን ከግምት በማስገባት ቅድሚያ እና ልዩ ትኩረት በመስጠት የሚስተናገዱ በመሆኑ ልዩ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ እነዚህን
ሁኔታዎች ለማስተናገድ የሚወስደውን ጊዜ ሳይጨምር ውስብስብ ጉዳዮች ሲሆኑ መዝገቡ በተመራ በ 60 ቀናት፤ መደበኛ ጉዳዮች ሲሆኑ በ 30
ቀናት፤ ቀላል ጉዳዮች ሲሆኑ ደግሞ በ 15 ቀናት ውስጥ ምርመራው ሊጠናቀቅ እንደ ሚገባ ደንግጓል፡፡153 በአዋጁ መሠረት አቤቱታ የማቅረብ
መብት በጉዳዩ የወንጀል ወይም የፍትሐብሔር ክስ መመስረትን አይከለክልም፡፡154

በአዋጁ አንቀጽ 23 አቤቱታ እንዴት እንደሚቀርብ የተደነገገ ሲሆን ለኮሚሽኑ የሚቀርብ አቤቱታ በቃል ወይም በፅሁፍ ወይም በማናቸውም ሌላ
መንገድ ሊቀርብ መቻሉ እንደተጠበቀ ሆኖ በማንኛውም ሌላ መንገድ የሚለው ሀሳብ አዋጁ ላይ ከተገለጹት የቃልና የጽሁፍ የአቤቱታ አቀራረብ
ስልቶች በተጨማሪም የስልክ፣ የፋክስ፣ የኢሜይልና ሌሎች ስልቶችን በመጠቀም የመብት ጥሰት የደረሰባቸው ሰዎች አቤቱታቸውን ለኢሰመኮ
ማቅረብ ይችላሉ፡፡ አቤቱታ የሚቀርብበትን ቋንቋ በተመለከተ አቤቱታ እንደሁኔታው በአማርኛ ወይም በሌላ የክልል የስራ ቋንቋ ሊቀርብ
ይችላል፡፡155

አቤቱታ የሚቀርብበትን ቋንቋ በተመለከተ አዋጁ ላይ የተደነገገው ቢኖርም እንደክልል የስራ ቋንቋ የማይታዩ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቋንቋ
ተናጋሪዎችን አስመልክቶ አዋጁ ያልደነገገ በመሆኑ ይህም ጉዳይ ልብ ሊባል የሚገባ ነው፡፡ ምክንያቱም በአንቀጽ 9 ላይ እንደተገለጸው ኮሚሽኑ
የስፍራ ተደራሽነትን ብቻ ሳይሆን ማመቻቸት ያለበት የአነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቋንቋ ተናጋሪዎችንና የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎችን ከግምት
ባስገባ ሁኔታ በቂ ድንጋጌዎች በአዋጁ ቢካተቱ ተገቢ ይሆን ነበር፡፡156

150
ራስገ 29 ገ 7
151
ራስጌ 16 አንቀጽ 22(1 )(2)
152
Getahun Kasa, national human right Inistitutions in Ethiopia``roles and chanlenjis in the `` protection of huma right,(AAU Colleje low and
governance human right series vol. V``2013 P.14
153
የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የምርመራ ሥነ-ሥርዓት መመሪያ ጥቅምት 2007 ዓ.ም፤ እንቀጽ 57
154
ራስጌ 16 አንቀጽ 22 (3)
155
ራስጌ 16 አንቀጽ 23 (1)(2)
156
ራስጌ 154
37
ምንም እንኳን ህጋዊ ግዴታ ባይሆንም አቤቱታ አቅራቢዎች አቤቱታዎችን ሲያቀርቡ በተቻለ መጠን ከደጋፊ ማስረጃዎች ጋር ማቅረብ
ይኖርባቸዋል፡፡157

አንቀጽ 24 ምርመራን ስለማካሄድ አስመልክቶ ኮሚሽኑ የቀረቡለትን አቤቱታዎች መሠረት በማድረግ ምርመራ ሊያካሂድ እንደሚችል ለኮሚሽኑ
በህግ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ኮሚሽኑ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በራሱ አነሳሽነት ምርመራ የማካሄድ ሥልጣን እንዳለው ከአንቀጹ መረዳት
ይቻላል፡፡158 በራስ አነሳሽነት ስለ ሚደረግ ምርመራ እንዴት እንደሚቀርብ ማንስ ማቅረብ እዳለበት አዋጁ ያስቀመጠው ድንጋጌ ባይኖርም
አዋጁን ተከትሎ በ 2007 የወጣው የምርመራ ሥነ-ሥርዓት መመሪያ በራስ አነሳሽነት ስለሚደረጉ የማስማማት ወይም የምርመራ ስራዎች
ከአንቀጽ 18-20 ስር ደንግጓል፡፡ በራስ አነሳሽነት ስለሚደረግ ምርመራ ብሎ መመሪያው ያሰፈራቸው ማንኛውም የኮሚሽኑ ሰራተኛ ከተለያዩ
የመረጃ ምንጮች ያገኘውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት መረጃ በዳይሬክቶሬቱ በማስማማት ወይም በምርመራ እንዲታይ ለሬጅስትራር ሲያቀርብ፤
ዳይሬክቶሬቱ በብሔር ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች፣ በተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ወይም ቡድኖች መካከል በሚነሱ ግጭቶች ምክንያት የሚፈጠሩ
የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በስምምነት እንዲፈቱ ጥሪ ሲያቀርብ፤ እና በማናቸውም የመረጃ ምንጮች የተገለፁ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሆነው
ምንም አይነት አቤቱታ ያልቀረበባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡159

በአዋጁ አንቀፅ 25 ላይ ለኮሚሽኑ በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት ኮሚሽኑ አስፈላጊ ማጣሪያዎችን ለማካሄድ በቂ በሆነ ጊዜ ውስጥ ተመርማሪዎች
ለጥያቄ እንዲቀርቡ ወይም መልስ እንዲሰጡ፤ ምስክሮች ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡና ለጉዳዩ ጠቃሚ የሆነ ማስረጃ የያዘ ማንኛውም ሰው
እንዲቀርብ የማድረግ ስልጣን አለው፡፡160 በዚህ አንቀጽ ውስጥ የተገለጸው አስፈላጊ ማጣሪያዎችን ለማካሄድ በቂ በሆነ ጊዜ ውስጥ በማለት
በድንጋጌ ለተመርማርዎች የተሰጠው የጊዜ ገደብ ቁርጥ ያለ የጊዜ ሁኔታን አያሳይም፡፡ በቂ በሆነ ጊዜ ውስጥ ብሎ በህጉ ከሚደነገግ ጊዜው
ቢወሰን ይሻላል፡፡

በአንቀጽ 26 መሰረት ኮሚሽኑ የቀረበለትን አቤቱታ በስምምነት መፍትሔ በመስጠት የተከሰተው አለመግባባት እንዲፈታ የተቻለውን ጥረት
እንዲያደርግ አዋጁ ግዴታ ይጥላል፡፡ ኮሚሽኑ ወደ ምርመራ ተግባር ከመግባቱ በፊት ጉዳዩ በስምምነት እልባት እንዲያገኝ ከአዋጁ በተጨማሪ
የመጀመሪያ ደረጃ መፍትሔ እንዲሰጥ የምርመራ ስነ ስርአት መመሪያም ደንግጓል፡፡ መመሪያው በአንቀጽ 22 ላይ እንደደነገገው ሬጅስትራሩ
የቀረበውን አቤቱታ ኮሚሽኑ የማየት ስልጣን ያለው መሆኑን ሲያረጋግጥ እና አቤቱታው በቀላሉና በፍጥነት ሊፈታ የሚችል ነው ብሎ ሲያምን
ወደ አስማሚ ወይም መርማሪ መምራት ሳያስፈልገው ከተመርማሪው ጋር በመነጋገር የመጀመሪያ ደረጃ መፍትሔ እንዲሰጠው ያደርጋል፡፡ ነገር
ግን ጉዳዩ በመጀመሪያ ደረጃ መፍትሔ የማያገኝ ከሆነ ወይም መፍትሔ ያገኘው በከፊል ከሆነ የጉዳዩን ይዘት እና ባህርይ በመመልከት
እንደየአግባብነቱ ለአስማሚ ወይም ለመርማሪ በመምራት ለሪከርድና ማህደር ክፍል ያስተላልፋል፡፡161

በመሆኑም ኮሚሽኑ የሚሰጠው የመፍትሄ ሃሳብ ለተፈፀመው በደል ምክንያት የሆነው ድርጊት ወይም አሰራር እንዲቆም ለበደሉ ምክንያት
የሆነው መመሪያ ተፈፃሚነቱ እንዲቀርና የተፈፀመው የፍትህ መጓደል እንዲታረም ወይም ተገቢ የሆነ ማንኛውም ሌላ እርምጃ እንዲወሰድ
በግልፅ የሚያመላክት መሆን እንዳለበት አዋጁ ያስቀምጣል፡፡162

በአንቀጽ 27 መሰረት ማንኛውም አቤቱታ አቅራቢ ወይም ተመርማሪ የኮሚሽኑ የበታች ተሿሚ ወይም ሃላፊ በሰጠው የመፍትሄ ሃሳብ ላይ
ቅሬታ ካለው ውሳኔው በፅሁፍ ከደረሰው ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በደረጃው ቀጥሎ ለሚገኘው ተሿሚ ወይም ሃላፊ የተሰጠውን

157
ራስጌ 16 አንቀጽ 23 (2)
158
ረስጌ 16 አንቀጽ 24 (1)(2)
159
ራስጌ 155 አንቀጽ 18-20
160
ራስጌ 16 አንቀጽ 25 (1)(2)(3)
161
ራስጌ 55 አንቀጽ 22 (1)(2)
162
ራስጌ 16 አንቀጽ 26 (3)
38
የመፍትሄ ሃሳብ ማሻሻል፤ ማገድ፤ መሻር ወይም ማፅናት ይችላል፡፡ በዋና ኮሚሽነሩ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ነው፡፡163 ዋናው ኮሚሽነር
በሰጡት ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ሰው ወደ ፍርድ ቤት ወይንም ወደ ሌላ አካል በይግባኝ መሄድ ቢፈልግ በህጉ ላይ የሰፈረ ድንጋጌ የለም፡፡

ኮሚሽኑ ፍርድ ቤቶችን ወይም ሌሎች የዳኝነት ሰጪ አካላትን ለመተካት የተቋቋመ አካል አይደለም፡፡ እነዚህ አካላት የሚያከናውኗቸውን
ተግባሮች ለማገዝ የተቋቋመ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ኮሚሽኑ የሚሰጠው ውሳኔ አስገዳጅነት የሌለው (non-binding) ነው፡፡ በመሆኑም ከኮሚሽኑ
የሚጠበቀው በተቻለ መጠን በስምምነት ሁለቱን ወገኖች ማቀራረብ ነው፡፡ ሆኖም የኮሚሽኑ የመፍትሄ ሃሳብ ዋጋ እንዳያጣ ለማድረግ ያለበቂ
ምክንያት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ባልወሰደ አካል ላይ ቅጣት እንዲጣልበት ተደርጓል፡፡164

በአዋጁ አንቀጽ 28 ላይ ኮሚሽኑ የምርመራ ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ወንጀል መሠራቱን ወይም የአስተዳደር ጥፋት መፈጻሙን ያመነ
እንደሆነ ለሚመለከተው አካል ወይም ኃላፊ ወዲያውኑ በጽሑፍ የማስታወቅ ግዴታ እንዳለበት ደንግጓል፡፡165 በእርግጥ የተፈጸመው ድርጊት
ወንጀል ነክ ከሆነ ጉዳዩ ለአቃቤ ህግ መመራት እንዳለበት አያከራክርም፡፡ ሆኖም ግን በተለይም የተፈጸመው ጥፋት ከአስተዳደራዊ ጉዳይ ጋር
የሚገናኝ ከሆነ ለሚመለከተው አካል ወይም ሃላፊ የሚለው የህጉ ሀሳብ ማንን እንደሚያመላክት ድንጋጌውን አንብቦ ለመተግበር አሻሚ ነው፡፡
ምክንያቱም የሰብአዊ መብት ጥሰት በአብዛኛው የሚከሰተው በስልጣንና በሀይል በማይመጣጠኑ ሰዎች መካከል እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ እንደዚህ
አይነት አሻሚ የሆኑ የህግ ሃሳቦች በአሰራር ወይንም መመሪያዎች ግልጽ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

በአንቀጽ 41 ስር አዋጁ ኮሚሽኑ የምርመራ ተግባሩን በሚወጣበት ጊዜ ህጋዊና ቀና ትብብር በማያደርጉት ሰዎች ላይ ስለሚወሰድ ቅጣት
አስፍሯል፡፡ በዚህ አንቀጽ መሰረት ማንኛውም ሰው በኮሚሽኑ መጥሪያ ደርሶት ወይም በሌላ ሁኔታ ተጠርቶ በቂ ምክንያት ሳይኖረው በተወሰነው
ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ ወይም መልስ ካልሰጠ ወይም ሰነድ ለማቅረብ ወይም ለማስመርመር ፈቃደኛ ካልሆነ ከአንድ ወር እስከ ስድስት ወር
በሚደርስ እሥራት ወይም ከብር ሁለት መቶ እስከ ብር አንድ ሺ የገንዘብ መቀጫ ወይም በሁለቱም ይቀጣል፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የበለጠ
የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሰው ኮሚሽኑ ዘንድ ምስክሮች ሆነው በቀረቡ ወይም ሰነድ ባቀረቡ ሰዎች ላይ ጥቃት ካደረሰ ወይም
ለኮሚሽኑ በቀረቡ ሪፖርቶች በተሰጡት አስተያየቶችና ምክንያት ሃሳቦች ላይ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ያለ በቂ ምክንያት እርምጃ ካልወሰደ ወይም
እርምጃ የማይወስድበትን ምክንያት ካልገለጸ ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም ከብር ስድስት ሺ እስከ ብር አሥር ሺ
የገንዘብ መቀጫ ወይም በሁለቱም እንደሚቀጣ አዋጁ ይደነግጋል፡፡166

በተለይም ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን የመሳሰሉ ተቋሞች ከሚነቀፉበት አንዱና ዋናው ምክንያት የሚሰጡት ውሳኔ አስገዳጅነት የሌለው መሆኑ
ነው፡፡ ሆኖም ኮሚሽኑ የሚሰጣቸው የመፍትሄ ሀሳቦች በተጠያቂው መልካም ፈቃድ ብቻ ተግባራዊ የሚሆኑ ተራና መና ሆነው መቅረት
የለባቸውም፡፡ የተጠየቀው አካል በቀረበው የመፍትሄ ሃሳብ መሰረት በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ ወይም ጥያቄውን
ያስነሳው ጉዳይ ቀድሞውኑ ህጋዊ ነው የሚልበትን ምክንያት ምላሽ መስጠት ያለበት ሲሆን ያለበቂ ምክንያት ይህን በማይፈፅሙት ላይ ቅጣት
መወሰኑ ለኮሚሽኑ ዓላማ ግብ መምታትና በሕብረተሰብ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት አስፈላጊ ነው፡፡167

ስለ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት በዋነኛነት የሚያወሳው የፓሪስ መርሆዎች እነዚህ ተቋሟት ከፊል የዳኝነት ስልጣን እንዳላቸው በዚህ
ጥናት ተመልክተናል፡፡ አንዱ የዳኝነት ስልጣን የሚተረጎመበት አሰራር በሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ ሊሆን እንደሚችል መረዳት
አይከብድም፡፡ የዳኝነት ስልጣን ካለ ደግሞ ኮሚሽኑ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች አፈጻጸም ሊያገኙ ይገባቸዋል፡፡168 ይሁን እንጂ የፓሪስ መርሆዎች
ይህን ቢያመላክትም የኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ ለኮሚሽኑ በቀረቡ ሪፖርቶች በተሰጡት አስተያየቶችና ምክንያት ሃሳቦች ላይ በሦስት ወር ጊዜ

163
ዝኒከማሑ አንቀጽ 27
164
የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና በሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጽንሰ ሃሳቦች ላይ በ 12 ከተሞች የተካሄደው ሲምፖዚየም ማጠቃለያ ሪፖርት የሰብአዊ
መብት ኮሚሽንን ጭብጦችና አማራጭችና በተመለከተ የቀረቡ ሀሳቦች ማጠቃለያ ጭብጥ 31 ን ይመልከቱ
165
ራስጌ 16 አንቀጽ 28
166
ዝኒከማሑ አንቀጽ 41 (1)(2)
167
ራስጌ 117 ገ 4
168
ራስጌ 25
39
ውስጥ ያለ በቂ ምክንያት እርምጃ ካልወሰደ ወይም እርምጃ የማይወስድበትን ምክንያት ካልገለጸ ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስራት
ወይም ከብር ስድስት ሺ እስከ ብር አሥር ሺ የገንዘብ መቀጫ ወይም በሁለቱም ሊቀጣ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡169 ይህ ድንጋጌ የሚያሳየው
በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ኮሚሽኑ የሰጠው የውሳኔ ሀሳብ ካልተፈጸመ የእስራት ወይንም የገንዘብ ቅጣት ሊያስከትል እንደሚችል እንጂ ማን ክሱን
አቅርቦ ጉዳዩን ማስፈጸም እንዳለበት አያሳይም፡፡ አዋጁም የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች እንዴት መፈጸም እንዳለባቸው ያስቀመጠው የአፈጻጸም አካሄድ
የለም፡፡ ለንጽጽር ያክል የጋናን (Commission on human rights and Administrative Justice) ብንመለከት ውሳኔ በተሰጠ በሶስት
ወር ጊዜ ውስጥ ካልተፈጸመ ኮሚሽኑ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ሊወስድ እንደሚችል በተቋቋመበት ህገ መንግስት ላይ ደንግጓል፡፡170 ከዚህ
በመነሳት ኢሰመኮም የጋናን አይነት ልምዶች ቢወስድ ለውሳኔዎች አፈጻጸም አጋዥ ሊሆን ይችላል፡፡

አዋጁ በአንቀጽ 40 በስም ማጥፋት ስላለመጠየቅ በተመለከተ በአዋጁ መሰረት የቀረበ አቤቱታ በስም ማጥፋት እንደማያስጠይቅና ኮሚሽኑ
ስለሚያካሂደው ምርመራ ውጤት ለም/ቤቱ የሚያቀርበው ሪፖርት ወይም ሥራውን በማስመልከት የሚያደርገው ሌላ ዓይነት መጻጻፍ በስም
ማጥፋት የሚያስጠይቅ አለመሆኑን መደንገጉ ለአቤቱታ አቅራቢዎች ሙሉ መብታቸውን የሚያረጋግጥ ሲሆን ለኮሚሽኑ ደግሞ ሙሉ የስራ
ነጻነትን ማጎናጸፉን ከድንጋጌው መረዳት ይቻላል፡፡171 በአዋጁ አንቀጽ 35 ልዩ መብት ስለ ተሰጣቸው የተቋሙ ተሿሚዎችና ሰራተኞች
የተደነገገ ሲሆን የመብቱም ተጠቃሚ የሚሆኑት ማንኛውም የኮሚሽኑ፤ ተሿሚ ከሆነ ም/ቤቱ፤ መርማሪ ከሆነ ዋና ኮሚሽነሩ፤ ሳይፈቅድ ወይም
ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር አይያዝም፤ አይታሰርም፡፡172

ይህ የአዋጁ ድንጋጌ መኖሩ እጅግ አስፈላጊና የሚደነቅ ለመብት ጥበቃ ዋስትና የሚሰጥ ቢሆንም እንዲህ ዓይነት ልዩ የመብት ጥበቃ ዘዴዎች
በኮሚሽኑ ውስጥ ለሚሰሩ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ያልተደረገበት ምክንያት ግልጽ አይደለም፡፡

ይህን ክፍል ለማጠቃለል የአቤቱታና የምርመራ ተግባራት በአዋጁ በርካታ ድንጋጌዎች እንዳሉ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ኮሚሽኑም የምርመራ ስራ
ለማካሄድ አዋጁ እጅግ ሰፊ ስልጣን እንዳጎናጸፍውና በአንቀጽ 7 ስር ከተደነገገው የስልጣን ገደብ ውጪ ኮሚሽኑ ከማንኛውም ግለሰብ፣ ቡድን፣
የግል ድርጅትና ከመንግስት ተቋሟት የሚቀርቡለትን አቤቱታዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ እንደሚችል ከህጉ መረዳት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ኮሚሽኑ
በአዋጁና አዋጁን ተከትሎ በወጣው የስነስርአት መመሪያ መሰረት አቤቱታን መቀበል፣ የመጀመሪያ መፍትሄ የመስጠት፣ ተገቢውን ስነስርአት
በመከተል ምርመራን የማካሄድና በመመሪያውም ላይ እንደተገለጸው ሚዛን የሚደፋ ማስረጃ ስርአት በመከተል የውሳኔ ሃሳብ የማቀረብ ስልጣን
አለው፡፡173

4.3.1.2 የሰብአዊ መብት ክትትል በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ

በዚህ ጥናት ምዕራፍ ሶስት ስር ለመመልከት እንደሞከርነው የሰብአዊ መብት ክትትል ማለት ሁኔታዎችን መታዘብ፣ መረጃዎችን መሰብሰብ፣
የተሰበሰቡትን መረጃዎችን በማደራጀትና በመተንተን ክትትል በተደረገባቸው ሁኔታዎችና ክስተት ዙሪያ ሪፖርት ማዘጋጀትን ያካትታል፡፡
እንደየክትትሉ አይነት ውጤቱ ቢለያይም የሰብአዊ መብት ክትትል ዋና አላማ የሰብአዊ መብት በደሎችን ማስረጃዎችን በመያዝ የማስተካከያ
እርምጃዎች እንዲወሰዱ ምክረ ሀሳቦችን መጠቆም ወይንም ለመከላከል ወይንም ለትምህርትና ለተሟጓችነት ተግባር የሚውል ሆኖ አዎንታዊ
ለውጥ ማምጣት ነው፡፡174

169
ራስጌ 168 (2)
170
Polo, evodia chabane, enforecement powers of national human right inistitution``a case study of chana south afirca
and Uganda suumitted in partial fulfillment of (llm human right and democratization in ofirica) center for human right
university of preforia ,29.oct, 2007. P.15
171
ራስጌ 16 አንቀጽ 40
172
ዝኒከማሑ አንቀጽ 35 (1) (2)
173
Frew Demeke,Feedback on the Weaknesses Outlined in ReferenceTO the Ethiopia human right commission in the Final Report Of the
Mapping Of the Compliant Systems Of Africn National human right Institution (20015)Unpublished
174
ራስጌ 99,p.5
40
ይህ ከላይ ያየነው ፍቺ ቢኖርም የኢሰመኮ አዋጅ ስንመለከት ስለ ሰብአዊ መብት ክትትል አስመልክቶ ቃል በቃል የተደነገገ ድንጋጌ ማግኘት
ይከብዳል፡፡ ይሁን እንጂ በአዋጁ ለኢሰመኮ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት መካከል አንዱ በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት ውስጥ የተደነገጉትን ሰብአዊ
መብቶች በማንኛውም ዜጋ፤ በመንግስት አካላት፤ በፖለቲካ ድርጅቶች በሌሎች ማህበራት እንዲሁም በባለስልጣኖቻቸው መከበራቸውን
ማረጋገጥ እንደሆነ በአንቀጽ 6/1/ ላይ ሰፍሯል፡፡175 በዚህ ድንጋጌ መሰረት ኢሰመኮ በህገ-መንግስቱ ላይ እውቅና ያገኙትን መሰረታዊ መብቶች
አፈጻጸም የመከታተልና ተከታትሎ ደግሞ እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከተው አካል አስተያዬቶችን ይሰጣል፡፡ የኢሰመኮ አዋጅ ላይ እንደ ሰፊ
ክፍተት ሊታይ የሚችለው አንዱ የሰብአዊ መብት ክትትል ሊደረግባቸው የሚገባቸው አካላት ህጉ አላስቀመጠም፡፡ የህንድን የሰብአዊ መብት
ኮሚሽን ብንመለከት ማረሚያ ቤቶችን እና የመሳሰሉ ተቋማትን አሰራር እንደሚከታተል አስተያየትም ሊሰጥ እንደሚችል ህጉ ያስቀምጣል፡፡176
ከህንድ በተጨማሪም የዩጋንዳን የሰብአዊ መብት ኮሚሸን ብንመለከት በዩጋንዳን ህገ መንግስት አንቀጽ 52 ላይ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን
በዩጋንዳ ያሉትን ወህኒ ቤቶች፣ ማረሚያ ቤቶች፣ እስር ቤቶችና ሌሎች ተመሳሳይ ማእከላትን በመጎብኘት የታራሚዎችን ሁኔታ ፈትሾ ለመንግስት
ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፡፡177 ስለዚህ ኢሰመኮ የሰብአዊ መብት ክትትል በተመለከተ በህግ ደረጃ የተዘጋጀ የማስፈጸሚያ ስልት ሊኖረው ይገባል፡፡
በፓሪስ መርሆዎች መሰረት ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ከተሰጣቸው ሰፊ ሥልጣን መካከል ተቋሟቱ መንግስት የሚያወጣቸው
ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣ መመሪያዎችና ውሳኔዎች ከሰብአዊ መብቶች ጋር የተጣጣም መሆኑን በክትትል መረጋገጥ አስፈላጊ እንደሆነ ነው፡፡
በኢሰመኮም አዋጅ አንቀጽ 6 ንኡስ 2 ላይ ማየት እንደሚቻለው በመንግሥት የሚወጡ ሕጎች፤ ደንቦች፤ መመሪያዎች እንዲሁም ትእዛዞች በሕገ
መንግሥቱ ከተረጋገጡ የዜጎች ሰብአዊ መብቶች ጋር የማይቃረኑ መሆናቸውን እንዲያረጋገጥ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡178 ከዚህም አንጻር
ኢሰመኮም በአገሪቱ ውስጥ በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ የሚወጡ ህጎችና የሚሰጡ ውሳኔዎች ከሰብአዊ መብት ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን
በሰብአዊ መብት ከትትል አሰራር በህግ የተጣለበት ሃላፊነትን እየተወጣ ይገኛል፡፡ በአዋጁ የተሰጠው ስልጣን ቢኖርም ኢሰመኮ በክትትል
አማካኝነት ህጎች ከሰብአዊ መብት አንጻር በአግባቡ እየተፈጸሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የአሰራር ህግ ሊኖረው ይገባል፡፡ ክትትል
የሚደረግባቸው በሁሉም መብቶች ማለትም በሲቪልና በፖለቲካ መብቶች፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ መብቶችና በባህላዊ መብቶች፣ በልማት
መብቶችና በአከባቢያዊ መብቶች ዙሪያ ትኩረት ሰጠቶ አፈጻጸማቸውን ለመከታተል የሚረዳ ዝርዝር ህግ ያስፈልጋል፡፡ ሌላኛው የኢሰመኮ አዋጅ
ሊያካትት ይገባ የነበረው ኢትዮጵያ ተቀብላ ያጸደቀቻቸው የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች በአግባቡ እየተተገበሩ መሆናቸውን
ለማረጋገጥ ለኮሚሽኑ የመከታተል ስልጣን በአዋጁ ላይ በግልጽ መደንገግ ነበረበት፡፡ የደቡብ አፍሪካን ሰበአዊ መብት ኮሚሽን ህግን ብንመለከት
ኮሚሽኑ አገሪቷ ተቀብላ ያጸደቀቻቸው አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች፣ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች ከአገሪቷ ህጎች ጋር
ተጣጥመው ተግባር ላይ እየዋሉ መሆናቸውን ክትትል ይደረግባቸዋል፡፡179
በስተመጨረሻም በዚህ ክፍል የተመለከትናቸውን ሁለቱንም አይነት የክትትል አመላካች ደረጃዎችን ማለትም ህደትን መሰረት ያደረገ የክትትል
አይነትና ውጤትን መሰረት ያደረገ የክትትል አይነቶችን ኢሰመኮ ስራ ላይ እንዲያውል በቂ የሆነ ድንጋጌ በህግ ላይ ሊካተት ይገባል፡፡

4.3.1.3 የማማከር ስልጣን በኢሰመኮ አዋጅ


የፓሪስ መርሆዎች የብሄራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋሟት ሀላፊነትን ሲያስቀምጥ ተቋሟቱ ለመንግስት አካላት ወይንም ለህግ አውጪው፣ ለፍርድ
ቤቶችና ለአስፈጻሚ አካላት ስለ ሰብአዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ ምክረ ሀሳቦችን አዘጋጅቶ ማቀረብ፣ አስተያዬቶችን መስጠት፣ አሰፈላጊ
ፕሮፖዛሎችን በማዘጋጀት ሀላፊነቶችን እንድወጡ ግዴታዎችን ይጥልባቸዋል፡፡ የሚዘጋጁ ህጎች ከመሰረታዊ የሰው ልጅ መብቶች ጋር
የተጣጣሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ የሰብአዊ መበቶች እንዲከበሩ የሚያግዙ አዳዲስ ህጎች እንዲወጡና ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ህጎችን በማጥናት

175
ራስጌ 16 አንቀጽ 6(1)
176
The Protection of human righit act,National human right Commisstion of india,1993 as amended(No./43/
2006)art.12 (c)
177
Constitutition of the republic of Uganda,1995Art.52
178
ራስጌ 16 አንቀጽ 6 (2)
179
South African human right Commission bila( As introduced in the national Assembly published in government
Gazette No36162 of 15 February 2013,(Minister of Justice and Constitutional Development),Art.14 (B) (VI)
41
ህግ አውጭውን ማማከር እንዳለባቸው በግለጽ ያስቀምጣል፡፡180 ምክር የሚሰጥባቸው ጉዳዮችን ስንመለከት በቅድሚያ አገራዊ ፖሊሲዎችን፣
ህጎችን፣ አሰራሮችን ስልታዊ በሆነ መንገድ በመፈተሽ ሊከለሱ የሚገባቸውን በመለየት መብቶችን በተሻለ ደረጃ ለማስጠበቅ ብሄራዊ ተቋሟት
መንግስትን ያማክራሉ፡፡181
በተመሳሳይ መልኩ ለኢሰመኮ በአዋጁ አንቀጽ 6 ንኡስ 6 ላይ በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ የምክር አገልግሎት የመስጠት ሀላፊነት
እንደተጣለበት ከህጉ ማወቅ ይቻላል፡፡182
ለኢሰመኮ የምክር አገልግሎት እንዲሰጥ በህጉ ላይ ከተቀመጡት ተግባራት መካከል በመንግሥት የሚወጡ ሕጎች፤ ደንቦች፤ መመሪያዎች፤
እንዲሁም ትእዛዞች በሕገ መንግሥቱ ከተረጋገጡ የዜጎች ሰብአዊ መብቶች ጋር የማይቃረኑ መሆናቸውን ማረጋገጥ አንዱ ነው፡፡183 ከዚህም
በተጨማሪም ነባር ሕጎች እንዲሻሻሉና አዳዲስ ሕጎች እንዲወጡ ወይም ፖሊሲዎች እንዲቀየሱ ማሳሰብ ናቸው፡፡184 አዋጁ ይህን ስልጣን
ለኮሚሽኑ በመስጠቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣቸው አዋጆች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣቸው ደምቦችና የክልል
መንግስታት ምክር ቤቶች በሚያወጧቸው ህጎች ዙሪያ ከሰብአዊ መብቶች እንዳይቃረኑ ተገቢውን የህግ ምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ይህ
በመሆኑ ኢሰመኮ በሥራ ላይ ያሉ ሕጎችንና የቀረቡ የሕግ ረቂቅ ሃሳቦችን በመመርመር እንዲሁም በሕግ ረቂቅ ዝግጅት ወቅት አስፈላጊ ድጋፍ
በመስጠት በአገሪቱ ሰብአዊ መብቶችን በማክበርና በማስከበር ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
ኢሰመኮ ለመንግስት የሚሰጠው የሰብአዊ መብት ምክር መንግስት ያሉትን ችግሮችን በመለየት መወሰድ ያለባቸውን የመፍትሄ እርምጃዎች
አቅጣጫ እንድያስቀምጥ ይረዳል፡፡ የመፍትሄ እርምጃዎቹ መንግስት ስልጠና እንዲሰጥ ወይንም የመብት ጥሰት ሲኖር ጉዳዩ ከተጣራ በኋላ
የሰብአዊ መብት ጥሰት ለደረሰባቸው ሰዎች ወይንም ለተጎጂ ቤተሰቦች መንግስት ካሳ እንዲሰጥ ለህግ አወጪው አካል ምክረ ሃሳቦችን
ያቀርባል፡፡ ለምሳሌ የዩጋነዳ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ልምድ ብናይ ኮሚሽኑ የሰብአዊ መብት ግንዛቤ ለማስፋፋት የሚረዳ ህግ እንዲዘጋጅ
ወይንም የሰብአዊ መብት ጥሰት ሰለባ ለሆኑ ሰዎች ወይንም ለተጎጂ ቤተሰቦች ካሳ እንድታሰብላቸው ተገቢ ምክረ ሀሳብ ለአገሪቱ ፓርላማ
ያቀርባል፡፡185 ከዚህም በተጨማሪም ሌለኛው በአዋጁ ለኢሰመኮ መንግስትን እንዲያማክርባቸው ህጉ ላይ ከተቀመጡት ጉዳዮች መካከል
ለዓለም አቀፍ አካላት በሚቀርቡ የሰብአዊ መብት ሪፖርቶች ላይ አስተያየት የሚስጥ ሲሆን በእርግጥ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች በተመለከተ
በዋነኛነት ስልጣን ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡ ኢሰመኮም ለዓለም አቀፍ አካላት በሚሰጣቸው የሰብአዊ መብት አስተያየቶች ዙሪያ
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር እንዴት እንደ ሚሰራ የአሰራር ማዕቀፍ ሊኖር ይገባል፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 6 ንኡስ 8 ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነዶች በአገር ውስጥ ቋንቋዎች መተርጎምና ማሰራጨት
ለኢሰመኮ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡186 መንግስት ተቀብሎ ማጽደቅ ያለበትን ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶችን ባህሪና የሚያስከትለውን
ግዴታ አይነት በመለየት መንግስት ህጎቹን እንዲያውቅ ያደርጋል፡፡ ይህ ማለት መጽደቅ ያለባቸው ዓለምአቀፍ ሰምምነቶች ያካተቱት ድንጋጌዎች
ከአገራዊ ህጎች ጋር መጣጣማቸውን ማረጋገጥ ወይንም ህግ አውጪው ስምምነቶቹን ተቀብሎ ለማጽደቅ ተጨማሪ የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ ሆኖ
ከተገኘ የማጽደቂያ አዋጅ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ ስለዚህ መንግስትም የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችን ተቀብሎ ካጸደቀ በኋላ
ስምምነቶቹ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆኑ በነጋሪት ጋዜጣ እንዲታተሙ በማድረግ በተመሳሳይ ትርጉም በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተተርጉመው
ኢሰመኮ ማሰራጨት እንዳለበት አዋጁ ያሳስባል፡፡

180
ራስጌ 102
181
ዝንከማሑ
182
ራስጌ 16 እቀጽ 6 (6)
183
ራስጌ 16 አንቀጽ 6 (3)
184
ዝንከማሑ አንቀጽ 6 (5)
185
ራስጌ 79
186
ራስጌ 16 አንቀጽ 6 (8)
42
4.4 የሰብአዊ መብት ትምህርት በኢሰመኮ አዋጅ

በፓሪስ መርሆዎች ላይ እንደሰፈረው ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት ከሚቋቋሙበት ዋና አላማ አነዱ ስለ ሰብአዊ መብት ግንዛቤ
ለማስፋፋትና ለማስገነዘብ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ስለ ሰብአዊ መብት ትምህርት በተመለከተ በምሁራን መካከል ሁለት የተለያዩ
አስተሳሰቦች እንዳሉ ማንሳት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው መሰረታዊ ትምህርት ማግኘት የሰብአዊ መብት ጉዳይ እንደሆነ የሚያነሱ ሲሆን
ሁለተኛው ደግሞ የሰብአዊ መብት ትምህርትን ሁሉም ሰው መማር እንዳለበት የሚገልጽ ሀሳብ ይዘው የሚከራከሩ ናቸው፡፡ 187 በዚህም ንኡስ
ክፍል ትኩረት የምናደርገው የሰብአዊ መብት ትምህርት ዙሪያ ይሆናል፡፡
የኢሰመኮ አዋጅ የሰብአዊ መብት ትምህርት ምን ማለት እንደሆነ በህግ ትርጓሜ ሰጥቶ ባያስቀምጥም በአንቀጽ 6 ንኡስ 3 ስር ኮሚሽኑ
እንዲያከናውን በህጉ ላይ ከሰፈሩት ተግባራት መካከል ህብረተሰቡ ስለሰብአዊ መብት በቂ ዕውቀት ኖሮት መብቱን የማክበርና የማስከበር ባህል
እንዲያዳብር መገናኛ ብዙኃንና የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማስተማር ሀላፊነት እንደተጣለበት ከህጉ መረዳት ይቻላል፡፡188
ከላይ ባየነው ድንጋጌ መሰረት ኮሚሽኑ የሰብአዊ መብት ትምህርት የሚሰጥበት ምክንያት ወይንም ዋና አላማ ህብረተሰቡ ስለ መብቱ ሊኖረው
የሚገባ ንቃተ ህሊና ለመፍጠርና ብሎም በቂ እውቀት እንዲያገኝ ከማስቻል አልፎ መብቶቹን ለማክበርና ለማስከበር የሚረዳ ባህል በአገሪቱ
ለመገንባት ነው፡፡ የግንዛቤው መስፋፋትና የትምህርቱ መስጠት ስለሰብአዊ መብት ለማሳወቅ ይረዳል፣ ሰብአዊ መብትን የማክበርና የማስከበር
አመለካከቶችና እሴቶች በህብረተሰቡ ውስጥ እንዲፈጠሩና እንዲጎለብቱ ያደርጋል፤ እንደዚሁም የሰብአዊ መብት ጥሰት የመካላከል ተግባራት
እንዲበረታቱ ያግዛል፡፡189
ይህንን አላማ ለማሳካት በሰብአዊ መብት ስልጠና መሳተፍ ያለባቸው አካላት እነማን መሆን እንዳለባቸው በቅድሚያ መለየት አስፈላጊ ነው፡፡
መብት ከማስከበር ጋር ቀጥተኛ ግኑኘነት ያላቸውን በተለይም በፍትህ አስተዳደር ውስጥ ሚና ያላቸውን ባለሙያዎች ማለትም ዳኞች፣ ዓቃቢያን
ሕጎችን፣ የህግ ባለሙያዎች፣ አስፈፃሚውንና የሕግ አውጭውን አካላት፣ ሕግ አስፈፃሚ አካላትን በተለይም ፖሊስ፣ የማረሚያ ቤት ጥበቃዎች፣
የፀጥታ ሃይሎች፣ ሌሎች ማለትም የማህበራዊ ጉዳይ ሠራተኞች፣ የመከላከያ ኃይል አባላት፣ ሚዲያን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን፣ መምህራንና
አሰልጣኞቻቸውን፣ የማህበረሰብ መሪዎችን፣ የአገር ሽማግሌዎችና የህዝብ አደረጃጀቶችን በሚካሄዱ የሰብአዊ መብት ስልጠናዎች ላይ በስፋት
ማካተት ያስፈልጋል፡፡190
ከአዋጁ ስለሰብአዊ መብት ትምህርት ማስተማር በተመለከተ ኮሚሽኑ መገናኛ ብዙኃንና የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የሰብአዊ መብት ግንዛቤ
ማስፋፋት እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡ ኮሚሽኑ የግንዛቤ ተግባር ለማስፋፋት መረጃና የማስተማሪያ ሰነዶችን ማሰባሰብ፣ ማደራጀትና
ማሰራጨት፣ በሰብአዊ መብት ተግባራት ዙርያ ከሚሰሩት ማህበራት እንዲሁም ከማህበረሰብ አቀፍ አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር አብሮ
መስራት፤ መገናኛ ብዙሀንን መጠቀም፣ ስለተቋሙ ስልጣንና ሀላፊነት የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ለህዝቡ ማስተዋወቅ፣ አወያይና አከራካሪ
ሴምናሮችን ማዘጋጀትና ሌሎች ዘዴዎችን መጠቀም ይችላል፡፡191

ስለዚህ ይህንን ምዕራፍ ለማጠቃለል የማቋቋሚያው አዋጅ ለኮሚሽኑ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች በማክበርና በማስከበር ረገድ በተሟላ
መልኩ የምርመራ፣ የክትትልና የምክር ተግባራትን ለመወጣት የሚያስችል ስልጣን፣ የህግ ይዘትና የተግባራቱ ወሰን በበቂ ደረጃ ይዟል፡፡ ኮሚሽኑ
የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ፣ የክትትል፣ የምክርና የግንዛቤ ተግባራቱን የሚያካሂድበት ምክንያት ከምንም በላይ ሕገ-መንግሥት ውስጥ
የተደነገጉት ሰብአዊ መብቶች በማንኛውም ዜጋ፤ በመንግስት አካላት፤ በፖለቲካ ድርጅቶች በሌሎች ማኀበራት እንዲሁም በባለሥልጣኖቻቸው

187
Heinz Dieter Haustein,human right Education ,comparative and international education series,publisher at
pergamon press oxford new york sept 4,011,1987,p.130
188
ራስጌ 16 አንቀጽ 6 (3)
189
ራስጌ 7
190
ዝንከማሑ
191
ራስጌ 66
43
እንድከበሩ ለማስቻል ነው፡፡ ሰብአዊ መብቶችን ለማስጠበቅና ስለ መብቶቹ ግንዛቤ ለማስፋፋት አዋጁ ውስጥ የተለያዩ ድንጋጌዎች ቢኖሩም ህገ
መንግስታዊ መብቶችን ይበልጥ ለማስከበር እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የማስፈጸሚያ መመሪያዎች በአዋጁ መሰረት ሊወጡ ይገባል፡፡

44
ምዕራፍ 5

ግኝቶችና ማጠቃለያ

5.1 ግኝቶች
ይህ ጥናት የህግ ጥናትና ምርምር ስልት በመከተል የተከናወነ በመሆኑ የኢሰመኮ የማቋቋሚያ አዋጅና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ለጥናቱ
አስፈላጊ የሆኑ የዓለም አቀፍ ህጎችና አገራዊ ህጎችን በአግባቡ በመመርመር የጥናቱን ግኝቶችን እንደሚከተለው አስቀምጧል፡፡

1. በጥናቱ ላይ በስፋት እንደተዳሰሰው አዋጁ ለሰብአዊ መብቶች መጠበቅና መከበር እጅግ አስፈላጊ ድንጋጌዎችን ያካተተ መሆኑን ያለ ምንም
ጥርጥር መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተለይም ህገ መንግስቱ እውቅና የሰጣቸው ሰብአዊ መብቶችና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በተሻለ ሁኔታ
ለማስከበር በሚረዳ መልኩ አዋጁ መዘጋጀቱን መረዳት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ በተለይም በዚህ ጥናት የተነሱ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ ግን
የተወሰኑ ክፍተቶች መኖራቸው መመልከት ተችሏል፡፡

አዋጁ ዋና ዋና የሚባሉትን የኮሚሽኑን ተግባራትን በህግ ትርጉም ደረጃ አላስቀመጠም፡፡ ለአብነት ያክል፣ የሰብአዊ
መብት ጥሰቶችን መመርመር፣ ሰብአዊ መብቶች መከበራቸውን መከታተል እና ማስተማር ማለት ምን ማለት
እንደሆነ በአዋጁ አልተደነገገም፡፡ እነዚህ ተግባራት በአግባቡ በህጉ ፍቺ ተሰጥቷቸው ቢቀመጡ አንድም ህጉን በግልጽ
ለመረዳት በሌላውም ደግሞ ትክክለኛ አፈጻጸም እንዲኖር ያስችላል፡፡

2. አዋጁ ምርመራን በተመለከተ በቂ ድንጋጌዎችን የያዘ ቢሆንም ነገር ግን ጥቂት አንቀጾች ግልጽ ሆኖ ባለመደንገጋቸው አፈጻጸም ላይ
የራሳቸው የሆነ ክፍተት መፍጠራቸው አልቀረም፡፡ ለማሳያ ያክል በአንቀጽ 25 ውስጥ የተደነገገው አስፈላጊ ማጣሪያዎችን
ለማካሄድ በቂ በሆነ ጊዜ ውስጥ በማለት በድንጋጌ ለተመርማርዎች የተሰጠው የጊዜ ገደብ ቁርጥ ያለ የጊዜ ሁኔታን
አያሳይም፡፡ በቂ በሆነ ጊዜ ውስጥ ብሎ በህጉ ከሚደነገግ ጊዜው ሊወሰን ይገባ ነበር፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 26 (2) ለሚመለከተው አካል ወይም ሃላፊ የሚለው የህጉ ሀሳብ ማንን እንደሚያመላክት ድንጋጌውን አንብቦ
ለመተግበር አሻሚ ነው፡፡ ምክንያቱም የሰብአዊ መብት ጥሰት በአብዛኛው የሚከሰተው በስልጣንና በሀይል በማይመጣጠኑ ሰዎች
መካከል እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በእርግጥ እንደዚህ ዓይነት አሻሚ የሆኑ የህግ ሃሳቦች በአሰራር ወይንም መመሪያዎች ግልጽ ሊሆኑ
ይገባል፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 27 መሰረት ዋናው ኮሚሽነር በሰጡት ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ሰው ወደ ፍርድ ቤት ወይንም ወደ ሌላ አካል
ይግባኝ ማቅረብ መብት እንዳለው የሚያሳይ ድንጋጌ በአዋጁ ላይ አልተቀመጠም፡፡

በማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት የሚሰጡ ውሳኔዎች እንዴት መፈጸም እንዳለባቸው ያስቀመጠው የአፈጻጸም አካሄድ የለም፡፡ የአፈጻጸም
ድንጋጌ ባለመኖሩ መብቶች እንዳይከበሩ ኮሚሽኑ በህግ የተጣለበትን ኃላፊነት አተገባበር ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡

3. ምንም እንኳን በአዋጁ ለኢሰመኮ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት መካከል አንዱ በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት ውስጥ የተደነገጉትን
ሰብአዊ መብቶች በማንኛውም ዜጋ፤ በመንግስት አካላት፤ በፖለቲካ ድርጅቶች በሌሎች ማህበራት እንዲሁም በባለስልጣኖቻቸው
መከበራቸውን ማረጋገጥ እንደሆነ በአንቀጽ 6(1) ላይ ቢሰፍርም ቢሆንም ስለ ሰብአዊ መብት ክትትልና የትኞቹን ተቋሟት መከታተል
እንደሚገባ የተደነገገ ድንጋጌ የለም፡፡ የሰብአዊ መብት ክትትል አሰራርን በተመለከተ መመሪያ ባለመዘጋጀቱ ክትትል ሊደረግባቸው
በሚገባቸው መብቶችና ተቋሟት ላይ የራሱ የሆነ ተጽእኖ ሊያመጣ ይችላል፡፡

በእርግጥ በአሰራር ረገድ ኮሚሽኑ የተለያዩ ማእከላትን ክትትል እያደረገባቸው ይገኛል፡፡ እንዲሁም አገሪቷ የምታወጣቸው ፖሊሲዎችና
ህጎች ከሰብአዊ መብቶች እንዳይቃረኑ ለማድረግ ኮሚሽኑ ክትትል እያካሄደባቸው ለመንግስት ምክር ይሰጣል፡፡ ይህ እውነታ በአሰራር

45
ቢኖርም አዋጁ ክትትል ሊደረግባቸው የሚገባቸው ተቋሟት ለይቶ አለማስቀመጡ በአዋጁ አፈጻጸም ዙሪያ ክፍተት መፍጠሩ
አይቀርም፡፡ ስለዚህ ኮሚሽኑ የሌሎች አገር ልምድ በመመልከት ለክትትል የሚረዱ የአፈጻጸም መመሪያዎችን ቢያወጣ የተሻለ ይሆናል፡፡

5.2 ማጠቃለያ

አሁን ባለንበት ዓለም የሰብአዊ መብት ጽንሰ ሀሳብና አስተምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ መጥቷል፡፡

ሰብአዊ መብቶች የሚለውን ቃል ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ በስፋት ዕውቅና ያገኘ ሲሆን ከዚያን በፊት እነዚህ መብቶች
ተፈጥሮአዊ መብቶች ወይንም (Natural Rights) በመባል ይታወቁ ነበር፡፡ ሰብአዊ መብቶችን በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅና

ለማስከበር በአለመአቀፍ ደረጃ የተለያዩ ስምምነቶች ጸድቆ መንግስታት ተቀብለው በማካተት እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡

በዚህ ጥናትም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መብቶችን ከማክበርና ከማስከበር አንጻር በምርመራ፣ በክትትል፣ በምክርና
በግንዛቤ ማስፋፋት ረገድ በማቋቋሚያ አዋጁ ላይ የተካተቱት ተግባራት ይዘትና ወሰናቸው እስከየት ድረስ ነው ምንስ አይነት የህግ
ክፍተት አለ የሚለውን ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡ የጥናቱም ዋና አላማ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ህገ መንግስታዊ ሰብአዊ መብቶችን
የማሳወቅ፤ መከበራቸውን የመከታተል እና የመመርመር ኃላፊነት፤ ተግባር ይዘቱ እና ወሰኑ ዙሪያ ጥናት በማካሄድ የፖሊሲ አቅጣጫ መጠቆም
ነው፡፡ ጥናቱም የተከተለው ዘዴ የህግ ጥናትና ምርምር ስልት መሆኑን ከጥናቱ መረዳት ይቻላል፡፡ ጥናቱን ለማካሄድ አጥኚው የተለያዩ
ስነጽሁፎችን፣ ህገመንግስቱንና የኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጁን ጨምሮ ስለ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟት የሚያወሱ ሰነዶችን ለማገናዘብ
ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡

ስለ ብሄራዊ ሰብአዊ መብቶቸ ጠበቃ ተቋሟት አመሰራረት አንድ ልብ ሊባል የሚገባ ነጥብ ቢኖር ምስረታቸው ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች
መከበር ጥያቄ ወይንም እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የአለማቀፍ ተቋሟት የአለማቀፍ ሰብአዊ መብቶችን ህጎችን በበቂ ሁኔታ ማስከበር
አለመቻላቸው መብቶችን ማስከበር የሚችሉ በሄራዊ ተቋሟት መኖር እንዳለበት አስፈልጓል፡፡

ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟትን አስመልክቶ አንድ ወጥ የሆነ ሁሉንም የሚያስማማ ትርጉም ማግኘት እስካሁን አልተቻለም፡፡ በጥቅሉ
ምሁራን ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተቋሟትን የሚገልጹት ሰብአዊ መብቶችን ለማስጠበቅና ለማስከበር በመንግስታት የተቋቋሙ ቋሚና ነጻ
አካላት ናቸው፡፡ብሄራዊ ተቋሟት የሚመሰረቱት በዋንኛነት ሰብአዊ መብቶችን ለማሰጠበቅና ስለ መብቶች ግንዛቤ ለማስፋፋት በግልጽ ባሰፈሩ
የብሄራዊ ህጎች ማለትም በህገመንግስት ወይንም በማስቻያ አዋጆች እና መሰል ህጎች ነው፡፡

ሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ ሕግ ውስጥ እንዴት ተካተዋል የሚለውን ነጥብ ስንመለከት ሁለት ማእቀፎችን እናገኛለን አንደኛው
የሕግ ማዕቀፍ ሲሆን ሁለተኛው ተቋማዊ ማዕቀፍ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስትም በተለያዩ አበይት ርእሰ ጉዳዮች መካከል አንደኛው የሰብአዊ

መብቶችና ነፃነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጭ የማይጣሱና የማይገፈፉ መሆናቸውን በመቀበል የዜጎችና የህዝቦች ሰብአዊና

ዲሞክራሲዊ መብቶች ይከበራሉ በማለት መደንገጉ ነው፡፡(አንቀጽ 10) ይህ መሰረታዊ መርህ ከአንቀፅ 13 ጀምሮ እስከ አንቀፅ 44

በሚዘልቀው በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት ይበልጥ ተዘርዝሯል፡፡ ይህ ምዕራፍ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶችን በሁለት በመክፈል

ሰብአዊ መብቶችን በክፍል አንድ ከአንቀፅ 14-28 ዲሞክራሲዊ መብቶችን ደግሞ በክፍል ሁለት ከአንቀፅ 29-44 ዘርዝሮ

አስፍሮአል፡፡

46
ስለ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የህገ መንግስቱ አንቀፅ 55/14 መሰረት እንደ ሚቋቋም አስፍሯል፡፡ በዚሁ አነቀጽ መሰረት
ምክር ቤቱ የሰብአዊ መብቶችን ኮሚሽን እንደሚያቋቁምና ሥልጣንና ተግባሩን በህግ እንደሚወስን መመልከት ይቻላል፡፡ ከላይ
እንደተመለከትነው ዒሰመኮ ህገ መንግስታዊ እውቅና በማግኘት በአዋጅ ቁጥር 210/1992 ተቋቁሟል፡፡

በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ መግቢያ ላይ እንደተመለከተው ኮሚሽኑ የተቋቋመበት መሠረታዊ ምክንያቶች የግለሰቦችን እና የብሄር ብሄረሰብ
መብቶች እንዲከበሩ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገቶችን ለማፋጠን የሕግ የበላይነትን እና በፍቃደኝነት ላይ
የተመሠረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ መገንባት የፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ፣ ባህሎችና ሃይማኖቶች ካለአንዳች ልዩነት እንዲራመዱ
ለማስቻል ነው፡፡ ዋና ዓላማው ደግሞ በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት በተደነገገውና ሕገ-መንግስቱን ተከትለው በወጡ የሀገርቱ ህጎችና ኢትዮጵያ
የተቀበለቻቸው የአገሪቱ የህግ አካል ተደረገው የሚቆጠሩ በዓለምአቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙ የሰባአዊ መብት መርሆዎች መሰረት ህዝቡን
ስለሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ እንዲኖረው የማስተማር፤የሰብአዊ መብቶቹ እንዳይጣሱ በመጠበቅ፤መብቶቹ ሳይሸራረፉ ስራ ላይ እንዲውሉና
ተጥሰው ሲገኙ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ ዓላማን ይዞ የተቋቋመ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ነው፡፡

የኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ በአምስት ክፍሎችና በአርባ አራት አንቀጾች ተከፍሏል፡፡ በዚሁ አዋጅ በአንቀፅ 4 እንደተገለፀው አዋጁ ተፈጻሚ
የሚሆነው በክልሎችም ላይ በሚፈፀሙ የሰብአዊ መብቶች መጣስ ጉዳዮችም ላይ አዋጁ ተፈፃሚነት እንዳለው ተደንግጓል፡፡ ነገር
ግን የፌደራለ አስተዳደር ላይ ህጉ ተፈጻሚ እንደሚሆን ቢታወቅም የተፈጻሚነት ወሰኑ የፌዴራል መንግስትን አይጠቅስም፡፡ ዐዋጁ
ሲረቀቅ የተፈጻሚነት ወሰኑን የፌዴራል መንግስትን ለምን በውስጥ ታዋቂነት እንዳስቀመጠ ግልጽ አይደለም፡፡

የአዋጁ አንቀፅ 7 ስንመለከት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የማያያቸውን ጉዳዮችን ደንግጓል፡፡ ኮሚሽኑ ከሰብአዊ መብት መጣስ
ጋር የተያያዘውን አቤቱታ ተቀብሎ በመመርመሩ ረገድ መብት ሙሉ መብት በአዋጁ ተሰጥቶታል፡፡ ነገር ግን ኮሚሽኑ ተጠሪ የሆነለት አካል ወይም
የራሳቸውን ጉዳይ ገለልተኛና ነፃ ሆነው እንዲያዩ በሕግ መብቱ በተሰጣቸው አካላት ውስጥ ጣልቃ መግባት ሊደርስ የሚችለውን ግጭት
ለማስወገድ ሲባል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በፌዴሬሽን ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤቶች ወይም በፍርድ ቤቶች በመታየት
ላይ ያሉ ጉዳዮችን እንዳያይ ገደብ ተደርጎበታል፡፡

አዋጁ ስልጣንና ተግባርን በሁለት መልኩ ያስቀመጠ ሲሆን እንደ ተቋም በአንቀጽ 6 እንዲሁም የተቋሙ ኮሚሽነሮች የሚኖራቸውን ሥልጣንና
ተግባር ከአንቀጽ 19-21 ባሉት አንቀጾች ውስጥ ተካቷል፡፡ በተጨማሪም የዋናው መሥሪያ ቤትና የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ሥልጣንና
ተግባር በመደራረብ ሊያስከትል የሚችለውን የሥራ ግጭት ለማስወገድ ሲባል ለዋናው ኮሚሽነር ብቻው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ
ተወስዷል፡፡

በተለይም ይህ ጥናት የኢሰመኮ አዋጅ ሰበአዊ መብቶችን ለማስጠበቅና ግንዛቤ ለማስፋፋት በህጉ ላይ ያለውን በተለይም ከምርመራ፣ ከክትትል፣
ከምክርና ከግንዛቤ ማስፋፋት ጋር በተገናኘ ለመፈተሽ ሞክሯል፡፡

በጥናቱም በአዋጁ ላይ የተደነገጉት አንዳንድ አንቀጾች በተለይም ከምርመራ ጋር የተያያዙ ድንጋጌዎች ግልጽ ሆነው
አለመደንገጋቸው፣ ከሰብአዊ መብት ክትትል ጋር የሚገናኙት ደግሞ በቂ ድንጋጌዎች አለመኖራቸውና አዋጁንም ለማስፈጸም የአፈጻጸም
መመሪያዎች ወይንም ዝርዝር መመሪያዎች አለመዘጋጀታቸው በዚህ ጥናት እንደ ግኝት ተቀምጧል፡፡ ያላቸው ተጨማሪ ጥናቶች ኮሚሽኑ
ቢያካህድ የተሻለ ይሆናል፡፡

47
ዋቢ መጻህፍት እና ሌሎች ማጣቀሻዎች

ሀ. መጻኅፍት

 Malcom N, Shaw. International Law, Sir Robert jennings professor of international law university of
elicitor. cambridge university press (2008)(6thed)
 በመንበረ ፀሃይ ታደሰ፡፡
የኢትዮጵያ ሕግና ፍትህ ገፅታዎች፣ ህዳር 1999 ዓ.ም፡፡

 ግርማ ወ/ሥላሴ፡፡
ሰብአዊ መብቶች ሕጎቹና አፈፃፀማቸው፣ የኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር፣ ነሐሴ 1999

 Guy Lamb, Victoria Maloka and Michelle Parlevliet.


Defenders of Human Rights, Managers of Conflict, builders of peace? National Human Rights
Institutions In Africa (2005).

 Fasil Nahum.
Constitution for Nation of Nation,The Red Sea Press Asmara.
 Common wealth Secretariat Lgal and Constitution Affairs Division,nationl human rights institutions
Commonwealth best practices,2001.

 Anna-Elina PohjolainenThe evolution of nationl Human Rights Institutions-The Role of The united
Nations,2006.

 Performance & legitimacy. National human rights institutions International Council on Human Rights
Policy (2000.

 Brian Burdckin, national human rights institutions in the ASIA-Pacific Region,Raoul Wallenberg
institute vol 27 Martinus Nijhoff publishers Leiden /Boston2007.

 Manuel Juzman, what is monitoring, Human Right Information and documemtation


Systems(HURIDOCS),Versoix Switzerland,2003.

 Office of the united nations high commissioner for human right, Economic, Social and cultural rights
(Handbook for national human rights institutions), New york and jeneva 2005.

 Office of the united nations high commissioner for human right, assessing the effectiveness of national
human right institutions,international council on human right policy 2005.

 Office of the united nations high commissioner for human right,handbook national human right plans of
action, professional training series No.10,united nations new yurk and jeneva 29 August 2002.

 Sileshi zeyohannes and fanaye gibrehiwot, legislative drafting teaching material,by Justice and legal
system research institute 2009.

 Dr.khushal Vibhute and Filipos aynalem, legal research methods,by justice and legal system research
48
institute 2009.

 Lindholt, Lone: Nlindsnaes, birgit: Yigen, kristile (eds),national eman rehigt institution articles and
working perpers, Danish Center for huma right 2001.

 Heinz Dieter Haustein, human right Education, comparative and international education series, publisher
at pergamon press oxford new york sept 4, 011, 1987.

 Rachel Murray,the role of national human right constitutions at the international and regional levels”the
experience of Africa,oxford /Portland,Oregon Hart Publishing,2007.

 Dr kamal hossain ,human right Commissions and ombudsmal offices national experiences throughout
the world, Martinus Mijhoff Publishers,2000.

ለ. መጽሔቶች (journals)

 Kumar, C. Raj. "National Human Rights Institutions: Good Governance Perspectives on


Institutionalization of Human Rights
 American University International Law Review 19, no. 2 (2003).
 Adem Kassie Abebe. Human Right under the Ethiopian Constitution a descriptive over view, mizan low
reivw, vol.5,No 1,2011.
 Tsegay Regessa. “Making Legal sense of human Rights, The Judicial role in protecting Human Right in
Ethiopia” mizan Low reviw,vol,3 No.2.
 Takele seboka. the monist-Dualist divide and the supremacy Clause: Revisiting the status of uman right
tieaties in etiyopiya, submitted to adis abeba urferst faculty of law,sept2003.
 Getahun Kasa. national human right Inistitutions in Ethiopia #roles and challenjis in the $ protection of
human right, (AAU Colleje of low and governnance human right series vol. V``2013.
 Marie-Benebict dembour. what are human rights four schools of thought, human right quarterly vol.32
university of Oslo (2010).
ሐ. ዓለም አቀፍ ህጎች
 Charter of the United nations, san San Francisco 1945.
 United Nations, Fact Sheet No.19, National Institutions for The promotion and Protection of Human
raghts,1993.
 Paris Principles, National Institutions for the promotion and protection of human rights, jeneral assembly
A/RES/48/134 85th plenary meeting 20 december 1993.
 UN convention on the rights of persons with disabilities (Uncrpds), 2006.
 Vienna Declaration and Program of action, adopted by the world conference on human right on 25 June
1993.
 Human rights Indicators A Guide to Measurement and Implementation, United Nations new York 2012

49
መ. አህጉራዊ ህጎች
 African Charter on human and peoples’ right, Gambia Banjul, AdoPted 27 June 1981.
 Declaration, (Issued by Heads of government in Harare Zimbabwe) oct.1991.
 The Yaounde Declaration of national institutions for the promotion and Protection of human right
Feb.1996.
ሰ. ብሄራዊ ህጎች
 የኢትዮጵያ ሽግግር ወቅት ቻርተር ነጋሪት ጋዜጣ 1983
 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐቭሊክ ሕገ-መንግስት አዋጅ ቁጥር 1 ነሀሴ 15/1987 ዓ.ም.
 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁጥር
210/1992 ዓ.ም.
 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐቭሊክ የፌዴራል የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ለማቋቋም የወጣ አዋጅ
ቁጥር 211/1992 ዓ.ም.
 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መረሐ-ግብር (2005-2007)፡፡
 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የምርመራ ሥነሥርዓት መመሪያ ቁ 2007
ረ. የሌሎች አገሮች ብሄራዊ ህጎች
 The Protection of human right act,National human right Commission of India,1993 as amended(No./43/
2006). (c)
 Constitution of the republic of Uganda,1995.
 South African human right Commission bila( As introduced in the national Assembly published in
government Gazette No36162 of 15 February 2013,(Minister of Justice and Constitutional
Development).
ሸ. የድረ ምረቃ ጽሁፎች

 Yemsrach Endale.The Roles and Challengs of ehiopian national human right institution in the Protection
of human rights in light of The Paris Principles,Masters Thesis Submitted to Central European
University Department of Legl Studies Budapest Hungary 2010.

 Liliam Manka Chenwi,national human right institutions”A comparative Study Of The National
Commissions Of Human rights Of Cameroon and South Africa ,suvmitted in partial fulfillment of(LLM)
(uhman right and democratization in africa)centr for human right, university of pretoria,21 oct.2002.

 Polo evodia chabane, enforcement powers of national human right institutions” A case study of
Ghana,South africa and Uganda,suvmitted in partial fulfillment of(LLM)(human right and
democratization in africa)centr for human right, university of pretoria,29 oct.2007.

ቀ. ሪፖርቶች፣ ማኑዋሎች እና ሌሎች ሰነዶች

 የሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጆችና የማብራሪያ ጽሑፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕግ

50
ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ ሰኔ 1991፡፡

 የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና በሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጽንሰ ሃሳቦች ላይ በ 12 ከተሞች የተካሄደው ሲምፖዚየም
ማጠቃለያ ሪፖርት የሰብአዊ መብት ኮሚሽንን ጭብጦችና አማራጭችና በተመለከተ የቀረቡ ሀሳቦች
ማጠቃለያ ጭብጥ፡፡

 የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የመጀመሪያው አምስት ዓመታት የሥራ ዘመን ሪፖርት አዲስ አበባ 2003.

 ATO MESFIN G/concept paper on human rights commission and office of ombudsman prepared and
submitted to the standing legal committee of the house of peoples’representative,January 199.

 አቶ ደመወዜ ማሜ፤ስለ ብሔራዊ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተቋማት የፌዴራል የፍትህ አካላት ባለሙያዎች ስልጠና
ማዕከል፡፡

 አብዱማሊክ አቡበከር፣ ሕገ መንግስቱ ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር የዘረጋቸው የቁጥጥር እና የክትትል ሥርዓት
ግቦት 1999 እ.አ.

 Frew Demeke,Feedback on the Weaknesses Outlined in Reference TO the Ethiopian human rights
commission in the Final Report Of the Mapping Of the Compliant Systems Of Africn National human
right Institution (2015) Unpublished.

 S Cardenas Working paper ‘Adaptive states:

The proliferation of national human rights institutions’ (2001) (availableat)


http://www.ksg.harvard.edu/cchrp/Web%20Working%20Papers/Cardenas.pdf) (accessed on May 26,
2016).

51

You might also like