You are on page 1of 40

በመንግስት ተቋማት ውስጥ አየታዩ

ያሉ የብልሹ አሰራር እና የሙስና

ችግሮች

1
መግቢያ

ሙስና በየትኛውም የአለም አገራት የሚከሰት ክስተት ነው፡፡ መጠኑ ይለያይ እንጅ ሙስና የሌለበት አገር የለም፡

እንደ ተራነሰፓርንሲ ኢንተርናቲናል (TI) የ 2013 ጥናት 177 አገሮች የሙስና ሁኔታ ጥናት

እንደሚያመለክተው ጥናቱ ከተደረገባቸው 70% ያህሉ አሳሳቢ የሆነ የሙስና ችግር እንዳለባቸው ያሳያል ፡፡

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እንደ 2006 ግሎባል

ኢንተግሪቲ ሪፖርት ሙስና በኢትዮያ የፖለቲካ፤ ኢኮኖሚ እና ማህበረሰብ ውስጥ ስር ሰዶ የሚገኝ አሳሳቢ

ችግር ነው ፡፡ ‘’ትራንስፓረንሲ ኢንተርነሽናል’’ የተባለው ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት እኤአ ከ 2012

ጀምሮ የዓለም ሀገራትን የሙስና ቅኝት ጥናት እያጠና በየዓመቱ ለሀገሮች ደረጃ የሚያወጣ ሲሆን ሀገራችን

ኢትዮጵያ በድርጅቱ የቅኝት ጥናት መለኪያዎች መሰረት በ 2019 ከ 180 ሀገሮች 37% በማግኘት 96 ኛ ደረጃ

የነበረች ስትሆን በ 2020 ከ 180 ሀገሮች 38% በማግኘት 94 ኛ ደረጃ በመቀመጥ በነጥብም ይሆን በደረጃ አንፃራዊ

መሻሻል አምጥታለች፡፡ 

በተቋማት የስራ ሰአት አጠቃቀም ላይ ሰፊ ችግር መታየቱ

በስፋት ከሚታዩ ችግሮች የተለመደዉና ዋናዉ የሰራተኞች በስራ ገበታቸዉ አለመገኘት ነዉ፡፡ ይህ ችግር አጅግ

አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ነዉ፡፡ ጊዜ ሕይወት ነዉ፡፡ በአግባቡ ከተጠቀሙበት ጊዜ ሕይወት ይታደጋል፣ ካልሆነ ግን ሰዉ

ሊሞት ይችላል፡፡ ከችግሮቹ መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸዉ፡- አርፍዶ ስራ መግባት፣ የሥራ ሰዓት

ሳይጠናቀቅ ቀድሞ መውጣት፣ ያለምክንያት ከስራ ገበታ መቅረትና ጊዜን በአግባቡ ለሥራ አለማዋል ፣ተቋሙ

ዉስጥም ሁኖ አለመስራት፣ በወሬና በጨዋታ ማሳለፍ፣ የግል ስራ በመስራት፣ ከስራ ጋር ግንኙነት የሌላቸዉ

ፌስቡክና ኢንተርኔት መጠቀም፣ያለአግባብ ሻይ ቤት መቀመጥ፣ ከክፍል ክፍል በመዞር ሌሎችን ስራ አለማሰራትና

አገልግሎት አለመስጠት በየመስሪያ ቤቱ የሚታዩ ችግሮች ናቸው፡፡

የደንበኞች አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች

ተገልጋይን በማስተናገድ ረግድ ከባለሙያ ከማይጠበቁ አፀያፊ ድርጊቶች አንዳንዶቹ ቀጥሎ የቀረቡት ናቸዉ፡-

አዋራጅ ባህሪ ፤ ማስፈራራት፤ ለሰራተኞችና ባለጉዳዮች መዋሸት፣ ሃላፊነትን ባግባቡ አለመወጣት፣ ከባለጉዳይ ጋር

ተገቢ ያልሆነ ግንኙነት መፍጠር (ለምሳሌ መሃንዲሶችና ኮንትራክተሮች፣ ሃላፊዎችና ተጫራቾች)፣ ልዩ ልዩ

ስጦታዎችንና ግብዣዎች መቀበል፣ ማታለል፣ ታማኝ አለመሆን፣ ቅን ባህሪን አለማሳየት፣ ቸልተኝነት፣ ማጉላላት፣

መሳደብ፣ ማመናጨቅ፣ መቆጣት፣ መገልመጥና ማዋከብ፣ አድልኦ መፈጸም፣ በዘመድ አዝማድና በጓደኛነት ቀረቤታ

መስራት፣ የማያስፈልግ እንዲያደርግ ማስገደድ፣ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ መጠየቅ እና የመሳሰሉ ችግሮች ይታያሉ፡፡

2
በተለይ የመድሎና የዝምድና ስራ፣ዘረኝነት እና ጎጠኝነት በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋል ችግር ነው፡፡ የተለያዩ

አገልግሎቶችን በዘር፣በቋንቋ፣በሃይማኖት፣በፖለቲካል ፓርቲ፣በጉርብትና ወዘተ ለሚቀርቧቸው ሰወች በማድላት

የሌሎችን ጥቅም መጉዳት እየተስተዋለ ያለ ችግር ነው፡፡

በአንድ ጥናት ግብር ከፋዮች እንደገለፁት ግብር ሲወስኑ ተመጣጣኝ አይደለም በስራው ሳይሆን በትውውቅ

ስለሚወስኑ ወይም አድልኦ አለው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የገቢዎች ሰራተኞች /ባለሙያዎች/ለግል ጥቅም ፍላጐት

ምክንያት የቀን ገቢ ጥናቱን በትክክል ያለማጥናት ወይም በገበያ እንቅስቃሴ መረጃ ሳይሆን በግምታዊ አሰራር

መሆን በተመሳሳይ ስራ የተራራቀ ግብር ስለሚወስኑ ብዙውን ጊዜ ነጋዴዉ እውነቱን ለመደበቅ ስለሚሞክር ነው

ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ያላቸው አነስተኛ ግብር ሲጣልባቸው አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ያላቸው ከፍተኛ

ግብር ይጣልና ንግዳቸውን እስከ መዝጋት ይደርሳሉ፡፡ ባብዛኛው አጥኝ ኮሚቴ ባጠናው አይሄዱም ገቢ መ/ቤቱ

በራሱ ነው በግምት የሚደለድለው የግብር ሒሳብ ውድቅ ያደርጉና በቀን ግምት አጋነው ይገምታሉ፣በግምት

ስለሚጠና የማዳላት ክፍተት አለ፣ በስም ብቻ ብዙ ግብር ይጥላሉ ፡፡በቀበሌ ደረጃ መታወቂያ አሰጣጥ እጅግ በጣም

ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ ነው፣

ሐሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀትና መጠቀም

ይህ የሙስና መገለጫ ወንጀል መገለጫዉቹም ሐሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀትና መጠቀም፤ ሰነዶችን መሰረዝ፣ መደለዝ፣

መቅደድና ማጥፋት፤ ቀሪና በራሪ ደረሰኝን ማበላለጥ፣ ገቢና ወጭን አለመመዝገብ፤ ለኢንሹራንስና ለግብር

እንደተከፈለ አድርገዉ መሰነድ እንዲሁም የተጋነነ ቁጥር ሪፖርት ማቅረብና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ እነዚህ

የማጭበርበር ተግባራት የሚፈጸሙት በባለሙያዎች፣ የመቆጣጠር ስልጣንና ኃላፊነት በአላቸዉ የመንግስት

ሰራተኞችና አመራሮች፣ በአቅራቢ ድርጅቶች እና በሌሎች ተገልጋዮች ነዉ ፡፡ በጨረታ፣ ሐሰተኛ ፋክቱር በማቅረብ

እና የተጋነነ ክፍያ በሕግ የተደገፈ እስከሚመስል ድረስ በይፋ ይፈጸማል፡፡

የሃሰት የወጭ ረሲት ማቅረብና ማወራረድ፣ የተሳሳተ የግዥ ማስረጃ ማቅረብ፣ላልተገዙ ቁሶች የግዥ ሰነድ

ማቅረብ፣ የሀሰት ሰነዶችን ማዘጋጀት፣ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ፣ የሥራ ልምድ፣ መታወቂያ ወረቀት ወይንም

ማንኛውንም ሃሰተኛ ማረጋገጫ መስጠት በስፋት የሚታዩ የማጭበርበር የሙስና ወንጀሎች ናቸው፡፡

አገልግሎት ለማግኘት ጉቦ መቀበል እና መስጠት ሰፍኗል

ጉዳይ ከመጀመሩ በፊትና በኋላ ክፍያ፣ ጀርባ መደገፍ፣ ማጣፈጫ፣ ማፋጠኛና ማለስለሻ፣ ንግድ ማመቻቸት)፡
የኮንትራትና የግንባታ ፈቃድ ለማግኘት፣ የህክምና መድሃኒቶችን፣ ቁሳቁሶችንና አገልግሎቶችን ለማቅረብ፣

የኮንትራት ዉልን ቀጣይነትን ለማረጋገጥ፣ ሰነድና መረጃዎችን ለመቀየር፣ ለማሳሳት፣ ለማዛባት፣ ከህግ ግዴታና
ተጠያቂነት ለማምለጥ፣ ዉሳኔን ለማፋጠን ወዘተ በሚል የሚሰጥ ነዉ፡፡

3
ውሳኔዎችን ለሚወስኑ የስራ ሃላፊዎች ውሳኔያቸው ለተወሰነ ሰው ወይም ቡድን ተስማሚ እንዲሆን ለማድረግ

ከሚሰጥ ትልልቅ ጉቦ ጀምሮ በተለምዶ ስራን ለማቀላጠፍ በሚል ለበታች ሰራተኞች የሚሰጠውን ትንንሽ ጉቦ

ይመለከታል፡፡

በመሬት አስተዳደር አገልግሎት ውስጥ ግቦ በመስጠት እና ግቦ በመቀበል የተለያዩ ህገወጥ ድርጊቶች ይፈጸማሉ ፡፡

ለምሳሌ ነባር ይዞታን ለማረጋገጥ ግቦ መጠየቅ፣የመሬት መረጃ ለማግኘት፣የመሬቱን የታሰበለትን አጠቃቀም

ለመቀየር፣ የይዞታ መሬቱን በህገወጥ መንገድ መጠኑን ለማሳደግ፣የስመ ንብረት ዝውውር ለማድረግ የማይገባ

ጥቅም መጠየቅ፣የመሬት አጠቃቀም እቅዱን ያልተከተለ ግንባታ ሲገነባ በግቦ ዝም ብሎ ማለፍ፣ የመሬት ቅየሳ

ስራ በሚከወንበት ጊዜ የማይገባ ጥቅም መጠየቅ ይታያል፡፡

ነጋዴዎች በህገወጥ መንገድ እንዲፈጸምላቸው የሚፈልጉትን ነገር ለማሳካት ለሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ጉቦ

መስጠት የተለመደ ነው፡፡ በህገወጥ መንገድ መሬት፣ ፍትህ፣ ጨረታ፣ ወዘተ ለማግኘት በርካታ ነጋዴዎች

ለሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ጉቦ እንደሚሰጡ ጥናታዊ ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

ታማኝ ያልሆኑት “ግብር ከፋዮች” በማጭበርበር ወይም ጉቦ(መደለያ) በመስጠት መንግስት ሊያገኝ የሚገባውን

ገቢ እንዲያጣ በማድረግ የራሳቸውን ገቢ ለማሳደግ ይሞክራሉ፡፡ የኮንትሮባንድ ንግድ፣የንግድ ገቢ ወይም ትርፍ

ማጭበርበር፣የዋጋና ታሪፍ ማጭበርበር፣የግብር መወሰኛና የተደራጀ የቀረጥና ታክስ ማጭበርበርና፣ ያልተፈቀዱ

ወይም ከደረጃ በታች የሆኑ ምርቶችን በመመሳጠር በማስገባት መሸጥ፣ የጉሙሩክ ኬላዎች ላይ መደራደር፣የግብር

እፎይታ እና ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ እቃዎች ለሌላ አላማ ማዋል የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ግብር ከፋዩ ግብሩን አጠቃሎ ከመክፈሉ በፊት በመደራደር ግዴታውን ላልተወጣ ግብር ከፋይ ክሊራንስ መሥጠት፣

ቅሬታን በአግባቡ ተቀብሎ ባለማስተናገድ ድርድር እንዲፈጠር ማመቻቸት፡፡

ኬላ ላይ መደራደር ዲክለር ከተደረገው በመጠን፣በዓይነት፣በስሪት፣ልዩነት እያለ በድርድር በሰነዱ መሰረት እደሆነ

መግለጽ፣ (የአዋቂ ልብስ የሆነው የህጻን፣3 ፒስ ሆነው 2 ፒስ ሲባል…ወዘተ) በኮንትሮባንድ ከሚያስገቡ ሰዎች ጋር

በመደራደር የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ሰው ከተኛ በኋላ ለሊት እንዲመጡ በመንገር ቀረጥ ሳይከፍሉ በጉቦ እንዲያልፉ

ማድረግ፡፡

ግለሰቦች መታወቂያ እንዳያገኙ በማጉላላት ኢ-ፍትሃዊ ጥቅም ማካበት፡፡ በቀላሉ የሚገኙ መዝገቦች የሉም

እየተባለ ለአንድ ጉዳይ ያልተገባ ምልልስና እንግልት (ደንበኛ ማጉላላት)፣

ወንጀል ሠርተው ለማምለጥና የቅጣት ጊዜያቸውን ለማሳጠር ለፖሊስና ለፍርድ ቤቶች (ዳኞችና ዓቃብያነ ሕግ)

የሚከፍሉ አሉ፡፡

4
በሆስፒታሎች የተሻለ አልጋ ለማግኘት ግቦ መክፈል የተለመደ ነው፣ ያለወረፋ ለመታከም፣ ለጥሩ እንክብካና የተሻለ

ሐኪም ለማግኘት ጉቦ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መጠየቅ ይታያል፣

አንድ ግንባታ የሚያከናዉን ኮንትራክተር ከስታንዳርድ በታች የወረደ ግንባታ በመገንባቱና ተቆጣጣሪ መሃንዲሱ

በማየቱ ሪፖርት እንዳይደረግበትና የክፍያ ማረጋገጫ አልፈርምም እንዳይል በማሰብ ጉቦ ሊሰጥ ይችላል፡፡

በአጋጣሚ የግንባታዉን ሁኔታ ለማየት ሲመጡ ኮንትራክተሩ ድል ያለ መስተንግዶ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ በአጠቃላይ
ግቦ ኢ-ፍትሃዊ የአገልግሎት ክፍፍልን ያስከትላል፣ ሙስና በተንሰራፋባቸው አከባቢዎች የመብራትና ዉሃ አገልገሎት
ለማግኘት ጉቦ መክፈል የግድ ይላል፡፡ ማለት ከጊዜ፤ከጉልበትና ከገንዘብ አንጻር ጥራት ያለው አገልግሎ ለማግኘት
ግቦ መክፈል ግዴታ ይሆናል (ማሳለጫ)፡፡ በአሁኑ ወቅት ዜጎች ማግኘት የሚገባቸውን አገልግሎት ያለ እንግልትና
ያለአድልኦ ማግኘት ፈታኝ እየሆነባቸው መጥቷል፡፡ ዜጎች በተለያዩ የመንግስት ተቋማት አገልግሎቶችን ለማግኘት
እየተቸገሩ እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ይህ መንገላታት ምንጩ በአግባቡ አገልግሎት መስጠት ያለበት አካል ከሚቆረጥለት
ምንዳ ያለፈ ጥቅም ለማግኘት የመፈለጉ ምክንያት ነው፡፡

የመንግስት ሃብት እና ንብረት ስርቆትና ዘረፋ መበራከት

በተሰጠው ሃላፊነትና ሥልጣን በመጠቀም በሥራው አጋጣሚ የሚያገኙትን የመንግስት ንብረቶችን፣ለማስተዳደር

ባለው ቀረቤታ በመጠቀም ወይም በቀጥታ በሃላፊነት እንዲጠብቃቸው የተሰጠውን ንብረቶች “በጓሮ በር እያወጡ

የሚሸጡ መኖራቸው አይካድም፤……”

በመንግስት ንብረትና ሃብት አጠቃቀም ለብክነትና ለሙስና ሊጋለጡ የሚችሉ አካባቢዎች የሚባሉት የሚከተሉት

ናቸዉ፡-የመስሪያ ቤት የጽፈት መሳሪያዎችና ወረቀቶች፣ተሸከርካሪዎች፣ስልክ፣ ፋክስና ኢንተርኔት፣ የመንግስትን

ንብረት ለግል ማዋስና ማከራየት ፡፡

የመንግስትን ንብረት አለዓግባብ ማባከን እና እንደ ራስ ንብረት አለማየት በበርካታ መስሪያቤቶች ይስተዋላል፡፡

በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የመንግስት ሀብትና ንብረት እየተበላሸ፣ ያለአግባብ ወጭ እየሆነና ጥቅም ላይ እየዋለ

መሆኑ /የመንግስት ሀብትና ንብረት ተገቢ ባልሆነ መንገድ እየወደመ ነው/፡፡

ከስርቆትና ከንብረት አያያዝና አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የመድሐት፣ የመመርመሪያ መሳሪያዎች፣ የመለዋወጫ

መሳሪያዎች ስርቆትና ግዴለሽ ወይም የተዝረከረከ አስተዳደር ነዉ፡፡ እነዚህ የሙስና ተዋናዮች ለጤና ተቋማት

የማያስፈል መድሐኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያ በተደጋጋሚ ይገዛሉ፡፡ ይሕ ለግል የጤና ድርጅቶች ለመሸጥና

በግብይቱ ሒደት ዝርፊያ ለማካሄድ ታስቦ የሚፈጸም የወንጀል ድርጊት ነዉ፡፡

5
በከፍተኛ ወጭ የተገዙ ዘመናዊ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ያለተበላሽተዉ መቀመጣቸዉም ሌላዉ የዘርፉ

መለያ ባህሪ ነዉ፡፡ ሕሙማንም እንደታከሙበት በማስመሰል ሐሰተኛ ሰነድ ተሰንዶ መድሐኒቶች እና የሕክምና

መሳሪያሪ መለዋወጫዎች በጥቁር ገበያ ለሽያጭ ቀርበዉ ይቸበቸባሉ፡፡

በህክምናው ዘርፉ ከሚስተዋሉ ሕብረተሰቡን ያማረሩ የሥነ-ምግባር ጥሰቶች እና ሕገወጥ ድርጊቶች መካከል

የሚከቱት ጥቂቶቹ ናቸዉ፡-መድሀኒቶችን ከመንግስት ጤና ተቋማት አዉጥቶ ለግል የጤና ድርጅቶች መሸጥና

ህብረተሰቡን ለብዝበዛ መዳረግ፣ የህክምና መሳሪያዎችን መሰወር፣ መደበቅ ወይም ሆን ብሎ ማበላሸት፣ የሕክምና

መሳሪያዎች ሳይበላሹ ተበላሽቷል በማለት ታካሚዎች ወደ ግል የጤና ድርጅቶች እንዲሄዱ በማድረግ ለከፍተኛ

ወጭ መዳረግ፣ህሙማንን ወደ ግል ድርጅታቸዉ እንዲሄዱ መገፋፋት፣ ማጉላላትና ጉዳይን ማጓተት፣የግል ጤና

ተቋም እየሰሩ እንደ ራጅ፣ አልትራሳዉንድ፣ ሲቲ ስካን እና የመሳሰሉትን የሆስፒታልን የህክምና መገልገያ

መሳሪያዎች መጠቀም፣ ህሙማን ሆስፒታል ሲመጡ ወደ ግል ክሊኒካቸዉ ወይም ሆስፒታሎቻቸዉ እንዲሄዱ

ማስገደድ፣ ከመንግስትና ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የግል ጥቅምን ማስቀደም ይጠቀሳሉ፡፡

ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎች መበራከት

ያልተጠናቀቁና ደረጃቸዉን ያልጠበቁ ግንባታዎች መረከብ ፣ተገቢውን የግንባታ ብረት አለመጠቀም ወይም

ከተፈላጊ ደረጃ በታች የሆኑ ግንባታ ተግባሮች (substandard building practices) መፈጸም ከግንባታ ጋር ተያይዞ

የውሸት ሪፖርት ማቅረብ፡፡ የግንባታ ፕሮጀክቶች አለማጠናቀቅና እንደተጠናቀቁ አድርጎ ማወራረድ፣ ያልተሰራን

እንደተሰራ አድርጎ ሪፖርት ማቅረብ ፤ግንባታዎችን ስንከታተል የሌለን ግንባታ ወይም የሚፈለገው ደረጃ

ያልደረሰን ግንባታ እንደተሰራ ማድረግ፤

ከስፔስፍኬሽን ወይም ከውል ስምምነት በታች (ጥራት የሌለው) አገልግሎት ሲቀርብ በጉቦ ወይም በሌላ ሥጦታ

አማካኝነት ዝም ተብሎ ሊታለፍና ርክክብ ሊፈፀም ይችላል፤ ግንባታው በግዜው ሳይጠናቀቅ ሲቀር፤ በሚፈለገው

ጥራት ሳይሰራ ሲቀር በመጠቃቀም በዝምታ ማለፍ

በመንግስት ሴክተር ዉስጥ ደግሞ ሙስና ለትምህርት፣ለጤና፣የንጹህ መጠጥ ዉሃ፣ለቤት ልማት፣ለመንገድና


ለመሰረተ ልማት ግንባታ መዋል የሚገባዉን ሃብት በቀላሉ ሊመዘበርበት ወደሚችል አቅጣጫ እንዲዞር
በማድረግ፣ትልልቅ ፕሮጀክቶች ተሰናክለዉ ግለሰቦች ተጠቃሚ እንዲሆኑና ብዙሃኑ እንዲጎዳ የሚያደርግ ነዉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ችግር ያለበት፤አደገኛ፤ደካማና በቂ ያልሆነ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ደካማና በግባቡ ያልተጠናቀቀ
መንገድ ባግባቡ ያልተገነባ ህንጻ ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው፡፡

6
በሙስና ሰበብ ለማህበራዊ አገልግሎት ለትምህርትና ለልዩ ልዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንባታ መዋል የሚገባው

የመንግስት ሃብት ለጥቂቶች እንዲውል ስለሚደያደርግ፣ አብዛኛው ህብረተሰብ የመሠረተ ልማት ተጠቃሚ መሆን

አይችልም፡፡ የትምህርት እድል የንጹህ ውሃ አቅርቦትና በቂ የህክምና አገልግሎት በማጣት ለመሃይምነት፣ለኋላ

ቀርነት እና ለከፍተኛ የጤና ችግር ይጋለጣል፡፡

የሰላም እና መረጋጋት ስራችን ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው፡-

የፍትህ ተቋሙ ቀልጣፋ የምርመራና የማስረጃ አያያዝና አቀራረብን ተግባራዊ በማድረግ የወንጀል ተጠርጣሪዎችና

ተጠቂዎች ፈጣን ፍትህ የማግኘት መብታቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ይሁንና አንዳንድ ጊዜ ሥነምግባር

በጎደላቸው የተቋሙ አባላት የሚፈጸም ሙስና ተቋሙ ሃላፊነቱን እንዳይወጣ እንቅፋት የሚሆኑበት አጋጣሚዎች

ይፈጠራሉ፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የሙስና መከሰቻ አጋጣሚዎች ሥነምግባር በጎደላቸው የተቋሙ አባላት ሊፈጸሙ

የሚችሉ የሙስና አጋጣሚዎች ናቸው፡፡ እነዚህንና መሰል አጋጣሚዎች እንዴት ሊፈጠሩ እንደሚችሉ በመነጋገር፤

አሰራርን በመፈተሽ፣ መፍትሄ ወይም መከላከያ በማፈላለግ ተቋሙን ከሙስና የጸዳ ማድረግ ይገባል፡፡

 በትራፊክ ደንብ መተላለፎች ላይ በመደራደር ጉቦ መቀበል

 ማስረጃዎችን ሆን ብሎ በማጥፋት፣

 ተከሳሾችን በማስጨነቅ ወደድርድር እንዲያመሩ ማድረግ፣

 በአደራ(በኢግዚቢት) የተቀመጡ ንብረቶችን ለግል ትቅም ማዋል(መውሰድ)፣

 ወንጀልን የሚያስረዱ ማስረጃዎችን ሆን ብሎ ማጥፋት፣

 ተጠርጣሪዎች የሚያዙበትን ቀን በማዘግየት ወደድርድር መግባት (ለምሳሌ ቅዳሜና እሁድን አስታኮ

መያዝ ወይም አለመያዝ)፣

 ማስረጃዎችን ለመቀየር በጉቦ መደራረደር፣

 ማስረጃዎችን ለማጥፋት መደራደር፣

 ተካሰሾችን ይዞ ላለማቅረብ በጉቦ መደራደር

 ምስክሮች በተባለው ጊዜ እንዲቀርቡ ባለማድረግ ወይም ባለማቅረብ፣

 በህገወጦች ወይም በህገወጥ ነጋዴዎች የሚሰሩትን ስራ አይቶ እንዳላየ በመሆን ቋሚ የሆነ የገንዘብ ምንጭ

ሊገኙ ይችላሉ፤

 ስጦታዎች እና ነፃ አገልግሎቶችን መቀበል፣

 መረጃ መሸጥ (ለምሳሌ የወንጀል መዝገቦችን)፣

7
 የተያዙ ኮንትሮባንድ እቃዎችን ለራስ መውሰድ፣

 እስረኞች/ተጠርጣሪዎች እንዲጠፉ ማድረግ፣

 የተቋሙን ሃብትና ንብረት መስረቅ፣

 ማስረጃ፣ የወንጀል ሬከርድ መዝገብ ማጥፋት፣

 ህገወጥ የሆነ የጦር መሳሪያ ፈቃድ መስጠት፣

 ከሚታወቁ ወንጀለኞች ጉቦ መቀበል፣

 በየተወሰነ ጊዜ ከወንጀል ቡድኖች እና ወንበዴዎች የሚከፈል ጉቦ መቀበል፣

 በቀጥታ ወንጀል እና የተደራጀ ወንጀል ላይ ተሳታፊ መሆን (ለምሳሌ አደንዛዥ እፅ ማዘዋወር፣ ግለሰቦችን

አግቶ ለመልቀቅ ገንዘብ መጠየቅ)

 የተያዘ ኮንትሮባንድ መስረቅ፣

 የወንጀል ምርመራዎችን እንደሚፈልጉት መዘወር፣

 ሚስጥራዊ መረጃ ሚስጥሩን ማወቅ ለማይገባው ሰው ወይም አካል መስጠት፣

 ከፖለቲካ ጋር በተገናኘ የሚፈፀሙ ግድያዎችን መደበቅና መሸፋፈን፣

 ህገወጥ ለሆኑ የጦር ተዋጊ ቡድኖች መረጃ መስጠት፣

 ስልጣን መከታ በማድረግ የቂም በቀል እርምጃ መውሰድ እንደሚችል መዛት፣ማስፈራራት ወይም የበቀል

ርምጃ መውሰድ (ፀበኛን ባልፈጸመው ወንጀል ማሰር ፣መደብድብ )

 ተጠርጣሪ በጣቢያ የታሰረበት ጊዜ ሲጠይቅ ሆነ ብሎ ቀኑን ጨምሮ ወይም ቀንሶ ማስረጃ መስጠት

የንግዱ አለም የስነ ምግባር መጓደልና የኢኮኖሚ አሻጥር

የንግዱ አለም ስራ በዕጅጉ ውስብስብ ነው፡፡ የሁለት ወገኖችን ፍላጎት /የገዥና ሻጭ/ ፍላጎት የሚያስተሳስር ብቻ

አይደለም፡፡ በትስስሩ ውስጥ አንዱ ወገን በሌላኛው ላይ በደል መፈፀም የሚያስችል አጋጣሚ የሚፈጥር ነው፡፡

ንግድን በስራ መስክነቱ የመረጠው ወገን ነግዶ የማትረፍ ወይም ጥቅም የማግኘት መብትና ነፃነት አለው በሌላ

በኩል የንግዱ አገልግሎት ተቀባይ የሆነው ወገን የሚፈልገውን ነገር በተመጣጣኝ ዋጋና በተገቢ ጥራት ማግኘት

ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ንግድ አርቆ አስተዋይነትን ይጠይቃል፡፡ ማለትም ታማኝነት፣ በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ፣

ትክክለኛነት፣ ግልፅነት፣ አክብሮት፣ ትህትና፣ ቅንነት…ወዘተ ያሉ መልካም ነገሮች ገቢያን የሚያሞቁና የሚያደምቁ

በመሆናቸው ለንግድ ግንኙነት ቁልፍ ሚና አላቸው፡፡ ነገር ግን የአገራችን የንግድ ግንኙነት የሚፈለግበትን ስነ

ምግባርና ግብረ ገብ በሚፈለገው ልክ የዳበረ አይመስልም፡፡

 አንዳንድ ነጋዴዎች በአጭር ግዜ ያለብዙ ወጭና ድካም ለመበልፀግ ባላቸው ጉጉት የተነሳ በወገኖች ላይ

ጉዳት ያደርሳሉ፡፡ የተለያዩ ባዕድ ነገሮችን ተፈላጊ ከሆኑ ምርቶች ጋር በመደበላለቅ የሚሸጡ ወገኖች አሉ፡፡

8
ለምሳሌ ቅቤን ከሙዝ፣ ከድንችና ከመሳሰሉት ነገሮች ጋር ይቀላቅላሉ፡፡ ዘይትን በእግር ከተረገጠ ፋጉሎ

ጨምረው በመጭመቅ ለገቢያ አቅርበው ይሸጣሉ፡፡ በርበሬን ከቀይ አፈር ጋር ቀላቅሎ በማስፈጨት ለገቢያ

ዱቄትን ከበአድ ነገር ጋር በመቀየጥ የሚሸጡ አሉ፡፡ ግዜ ያለፈበት ምርት የሚሸጡም አሉ፡፡ ሚዛን

በማዛባትና መጠን በማሳነስ ለሸማች የሚያቀርብ ወገኖችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡

 ሆቴል ቤቶችም በመጠኑም ሆነ በጥራቱ ደረጃውን ያልጠበቀ ምግብ ማቅረብ፣ ምግብን ለጤና ጠንቅ በሆኑ

የመገልገያ እቃዎችና ቦታዎች ማዘጋጀት፣ ለምግብ ዝግጅት ደረጃውን ያልጠበቁ ግብአቶችን መጠቀም፣

በተገልጋዮች መካከል አድሎ መፈፀም፣ ፅዳት የሌላው የመኝታ ክፍልና አልጋ ማከራየት፣ ከተሰጠው

አገልግሎት በላይ ዋጋ መጠየቅ… ወዘተ እነዚህ ሁሉ የግብረገብና ስነ ምግባር መርሆችን በመጣስ

የሚፈፀሙ እኩይ ተግባሮች ናቸው፡፡

 ከዚህ በተጨማሪ በአሁኑ ሰአት በአገራችን ውስጥ አንዱ የሆነው አርቴፈሻል የገቢያ ስርአት ለመፍጠር

እያደረጉ ያሉት የኢኮኖሚ አሻጥር ይጠቀሳል፡፡ በዚህም አንዳንዶች በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ ሆን

ተብሎ እጥረት እንዲፈጠር በማሰብ ሸቀጦች ሲሰወሩ ይስተዋላል፡፡ ሌሎች ደግሞ አጋጣሚውን

ተጠቅመው የማይገባ ትርፍ ለማጋበስ ሲሉ መሰረታዊ ሸቀጦችን በማከማቸት ገበያው ተፈጥሮዊ ሂደቱን

እንዲያጣ ያደርጋሉ፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ ነጋዴዎች ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

 በአሁኑ ሰአት በተለያዩ ቦታዎች ምርቶችን በመጋዝን አከማችተው ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ

በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ነው፡፡ እርምጃ የመውሰድ ስራውም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

 ህብረተሰቡም በአገርና በህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ይህን እኩይ ሴራ በማጋለጥ መብቱን ማስጠበቅና

የድርጊቱን ፈፃሚዎች መታገል አለበት፡፡

 ለዚህም ተገቢውን መረጃ ለሚመለከተው አካል በመስጠትም የኢኮኖሚ «ሳቦታጅ» ፈፃሚዎችን ድርጊት

መቆጣጠር ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም በማንኛውም ንግድ ስራ ላይ ተስማርታችሁ የምትገኙ ነጋዴዎች

ለሽያጭ በሚቀርቡ ማለትም ከውጭ ሀገር የገቡ ወይም በሀገር ውስጥ የተመረቱ ማንኛውም እቃዎች፣

የግብርና ምርቶች፣ የምግብ እና መሰል ሸቀጣሸቀጦች ላይ የማይገባ ዋጋ መጨመር በህግ የተከለከለ ነው፡፡

በተጨማሪም ምርት መደበቅ እና ማከማቸት፣ ምርትን ከባዕድ ነገር ጋር መቀላቀል፣ ሚዛን ማዛባት፣ ግዜ

ያለፈባቸው ምርቶች ለገቢያ ማቅረብ፣ ደረሰኝ በሚያስፈልጉ የንግድ ቦታዎች ላይ ያለደረሰኝ መገበያየት፣

እና ሌሎችም በህግ የተከለከሉ ድርጊቶችን መፈፀም በንግድ ህግ የሚያስቀጣ በመሆኑ ነጋዴዎች ጥንቃቄ

ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

 ከሁሉም በላይ ግን ሁሉም ነጋዴ ከስግብግብና እራስ ወዳድ አመለካከት በመራቅ ለማህበረሰብ ፍትሀዊ

አገልግሎት መስጠት ይኖርበታል፡፡

9
ከትራንስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ

ከትራንስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ በዕቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ሰዎችን መጫን፣ ከተሽከርካሪ አቅምና ከተፈቀደው

በላይ ሰው መጫን፣ ከተፈቀደ ታሪፍ በላይ ለሰውም ሆነ ለእቃ ማስከፈል፣ በመንገድ ላይ በቂ ባልሆኑ ምክንያቶች ተገልጋዩን

ማቆየት ወይም ግዜውን ማባከን፣ ከሰው ጋር እንሰሳትንና /ለምሳሌ ደሮ፣ በግ ወዘተ/ የተለያዩ አደገኛ ነገሮችን /ለምሳሌ

በርበሬ፣ ነዳጅ፣ አልኮል…ወዘተ/ መጫን ወዘተ ምክንያት ተገልጋዩ ላልተፈለገ እንግልት እና የጤና ጠንቅ እየተጋለጠ ነው፡፡

ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ በርካታ ቅሬታዎች ይነሳሉ

የሊዝ ቦታ አሰጣጥ ስርአቱ በተመለከተ ወጥነት የጎደለው እና ለበርካታ ብልሹ አሰራር የተጋለጠ መሆን፣ መሬት

ለልማታዊ ባለሀብቶች ከመስጠት ይልቅ ለማልማት አቅም ለሌላቸውና መሬት ለሚሸጡ ግለሰቦች መስጠት፣

ምትክ ቦታ ሲጠየቅ ባለሥልጣኑ ማዘጋጀት ሲገባው ጠቁሙ ማለትና የተጠቆመውንም ቦታ ጥያቄውን ላላቀረበ

ባለሀብት አሳልፎ መስጠት፣መሬትን በሊዝ በድርድር ምንም ቅድመ ሁኔታ ላላሟሉ በዝምድናና በመሳሰሉት

ግንኙነቶች መስጠት፣ የሊዝ ዋጋ ግምት በጣም ዝቅተኛ እንዲሆን ማድረግ፣ በአንድ አካባቢ በአንድ ደረጃ ላይ

ለሚገኙ ቦታዎች የተለያየ የሊዝ ዋጋ ማውጣት፣ አቅም እያላቸው መሬት ያላገኙ ልማታዊ ባለሀብቶች

ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ጥረት አለማድረግ ከታዩት ችግሮች ውስጥ ይጠቀሳሉ ፡፡

ሕጋዊ ላልሆኑ ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካረታ እና ሌሎች መረጃዎችን መስጠት፣ የተቋሙ ሰራተኞች

ከደላሎችና ላንድ ስፔኩሌተርስ ጋር በመመሳጠር የተለያዩ የመሬት መረጃዎችን በህገወጥ በማዘጋጀትና መሬቱን

በመሸጥ ወይም ህገወጥ ጥቅም በማግኘት የመንግስትና የህዝብ ሃብት ይመዘብራሉ፡፡ደላሎች በከተማው ውስጥ

የሚገኙ የተለያዩ ክፍት የመንግስት መሬቶችን መረጃ ስላላቸው ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር በመመሳጠርና ህገወጥ

መረጃዎችን በማዘጋጀት መሬት በህገወጥ ሲያስተላልፉ ይታያሉ፡፡በተለይ ተቋሙ በቂና ጥራት ያለው የመሬት

መረጃ ስርአት ስለሌለው ለደላሎች በቀላሉ የመሬት መረጃውን ለማጭበርበር እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡

ከይዞታ ለሚነሱ ሰዎች ካሳ አከፋፈል፣ ተተኪ ቦታ አሰጣጥ፣ ወዘተ በብልሹ አሰራር ውስጥ መገኘት፡፡ በከተሞች

ማስፋፊያ አካባቢ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከነበሩበት ይዞታ ከከተማ መስፋፋት እና ዕድገት ጋር ተያይዞ ሚመጣው

ልማት ምክንያት ከይዞታቸው ለሚፈናቀሉ አርሶ አደሮች የንብረት ካሳ ግመታ እንደአከባቢዉ ተጨባጭ ሁኔታ

የሚለያይ ቢሆንም በጥናት ወቅት ከተሰበሰቡ መረጃዎች ለመረዳት እንደተቻለዉ አፈጻጸሙ የዜጐችን ንብረት

መልሶ መተካት በሚያስችል መልኩ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ተመን መሰረት ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው አሠራር

የተጠናከረ አይደለም፡፡ ለምሳሌ በክልላችን ያለው የካሳ ግመታ አሠራር ወጥነት የሌለው ከከተማ ከተማ የተለያየ

ነው፡፡ አንድ ጥናት እንዳመላከተው በሃዋሳ ከተማ የነበረው አሠራር ሲታይ በአንድ ወቅት ከአንድ ሄክታር

10
ለሚፈናቀሉ 1 እጣ የተሰጠበት፣ በሌላ ወቅት ለተመሳሳይ ይዞታ 5 እጣ የተሰጠበት ሁኔታ ሲኖር በሌላ ከተማ

ከ 200 ካ.ሜ 500 ካ.ሜ ፣በሌላ አካባቢ ደግሞ የንብረት ግመታ ክፍያ ተፈጽሞ ተተኪ ቦታ የሚሰጥበት ሁኔታ

ይታያል፡፡

በተጨማሪ በከተማ አስተዳደር በመሬት ልማት አስተዳደር ከዋጋ ግመታ ጋር በተያያዘ የነበረዉ አሰራር የጓሮ

ንብረት ዋጋ በግብርና ባለሙያ፣ የቤት ግምት በማዘጋጃ ቤት ባለሙያ የሚገመት ሲሆን ከስም ዝዉዉር ጋር

በተያያዘ የቤት ግምት ወይም የታክስ ግመታ በታክስ ባለስልጣን ባለሙያ የሚፈጸምበት አሰራር በመሆኑ አፈጻጸሙ

ወጥ በሆነ መለኪያ የተበጀለት ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ በሰዎች በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እንድሆን አድርጎታል፡፡

በተለይ ካሳ ሳይከፈለን መሬታችን ተወሰደ የሚሉ ባለጉዳዮች በርካታ ናቸው፡፡

ለባለሀብቶች ወይም ለምሃበራት ቦታ ከመስጠት በፊት ቦታዉ /ይዞታዉ/ ከማንኛውም የይገባኛል ጥያቄ ነጻ

ሳይሆን፣ ለመንግሥት ወይም ለቀበሌ ቤት ወይም በቦታው ለነበሩ አርሶ አደሮች ተገቢ ካሳ ሳይከፈል ሕግና ደንብ

ከሚፈቅደው ውጭ ተሰጥቶ ህጋዊ ባለሀብቶች ሳይት ኘላን ይዘው ለችግር መጋለጥ፣ይህም በሥራ ላይ ጫና

እያሳደረ ይገኛል፡፡

የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ (ምስክር ወቀረት) አሰጣጥ ተጠያቂነትንና ግልፅነትን የተከተለ አለመሆን፡፡ የመሬት

ልማትና አስተዳደር ባለሥልጣን ከሚሰጣቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ የቦታና ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አሰጣጥ

ነው፡፡ ይህን ሥራ በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት ተጠያቂነትና ግልጽነትን የተከተለ ባለመሆኑ በማህበር ተደራጅተው

መሬት ለመውሰድ ጥያቄ ላቀረቡ ተገልጋዮች በአንድ ሰው ስም ካርታ በመስጠት ህገ ወጥ ተግባር መፈፀም፣ በአንድ

ቦታ ላይ ለሁለት ሰዎች ካርታ መስጠት፣ መሀንዲሶች ሲለኩ ባዶ ቦታ መተውና በህገወጥ መንገድ እንዲያዝ

በሚያመች ሁኔታ ካርታ መስራት፣ በካርታ ላይ ካርታ በመስራት፣ ተገልጋዮችን ለአላስፈላጊ ችግር መዳረግና ፍትህን

ማዛባት፣ የመንግስትን ቤት ተከራይተው ለሚኖሩ ግለሰቦች ማስፋፊያ አግባብ በሌለው መንገድ መስጠት፣ የቀበሌ

ቤት በግል ይዞታ ማዞር ለዚህም የግል ማህደር ማጥፋትና በግለሰብ እንዲቀየር ማድረግ፣ ክፍትና ለመናፈሻ

የሚሆኑ ቦታዎችን ለግለሰቦች በመስጠት የይዞታ ማረጋገጫ እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ለአንድ ግለሰብ ከአራት ቦታ

በላይ ለመኖሪያ ቦታ መስጠት፣ በውጭ ድርጅቶች ለቆሻሻ ማስወገጃ የተሠራውን ቦታ በጥቅማጥቅም ለግለሰብ

መስጠትና በአካባቢው ነዋሪ ላይ የጤናና ማህበራዊ ችግሮችን ከሚያስከትሉ ነገሮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የመንግስት ቤቶች በመድሎ ለሚፈልጉት ሰው መስጠት የግል ቤት እያላቸው በመንግስት ቤት ወይም በቀበሌ ቤት

መኖር

11
የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል የመኖሪያ ቤት የሌላቸው ሰዎች በሕጋዊ መንገድ በግል ወይም በማህበር

ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ የሚያገኙበት አሠራር ያለ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ቤት ለመሥራት

አቅም የሌላቸው እና መኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ የሌላቸው ሰዎች የመንግሥት ቤት የሚያገኙበት ሥርዓት

ስለመኖሩ ይታወቃል፡፡

ሆኖም በአንዳንድ አካባቢ በነበረዉ ብልሹ አሰራር ግማሹ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ጠይቆ የማያገኝበት አሠራር

ሲታይ ሌላዉ ደግሞ በአንድ ከተማ ውስጥ ከሁለት በላይ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ እየወሰደ፣ እየሸጠ እና ቤቱን

ለሌላ ሰዉ በማከራየት እሱ በመንግሥት ቤት በመሆን ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታ መኖሩ በህዝብ በተደጋጋሚ

የሚነሳ ቅሬታ ነው፡፡

የመዝገብ ቤት የሙስና ተጋላጭነት

መዝገብ ቤት በማንኛዉንም መስሪያ ቤት እጅግ ጠቀሜታ ያለዉ የስራ ዘርፍ ነዉ፡፡ እንዲያዉም ለሙስና ሊጋለጡ

ከሚችሉ አደገኛ ቦታዎች አንዱ እንደሆነ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ይስማማሉ፡፡ ስለሆነም መዝገብ ቤትን ህገ

ወጦች በቀላሉ እንዲገለገሉበት፣ ያልተፈቀደላቸዉ እንደፈለጉ እንዲጠቀሙበት ማድረግ ፋይሎች እንዲሰረቁ፣

እንዲጠፉ፣እንዲደበቁ፣ እንዲቀየሩና እንዲበላሹ ሊያደርግ ይችላል፡፡

የተለያዩ ጥናቶች እንዳመላከቱት አብዛኛው የመሬት ፋይል የተቀመጠው በዘፈቀደ እንደሆነ የሚሰሩበት ቢሮም

ጣራው ክፍተት መሆኑ ማንም ሰው በጣራው ገብቶ መዝገቡን ማውጣት የሚችልበት ሲሆን የፋይል ቅብብሎሽም

የማይፈራረሙበትና ቁጥጥር የማይደረግበት እንደሆነ ተገልጿል፤ በእይታም ተረጋግጧል፡፡

አንድ አንድ ግለሰቦች እንደሚገልፁት ከሆነ ደላሎች እያንዳንዱን ማስረጃ የህግ እውቅና ከተሰጠው ተቋም

እውቅና ውጭ በማዘጋጀትና በማሟሟላት ዶክመንቱ ወደ ተቋሙ በህገወጥ የመዝገብ ቤት ሰራተኞች አማካኝነት

ገቢ እንዲደረግ እና የመሬቱ ባለቤት ህጋዊ እውቅና እንዲያገኝ የሚያደርጉበት አቅጣጫ አለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ቀድሞ

በነበሩ የተቋሙን ሰራተኞች መሃተም እና ፊርማ በመጠቀም የሃሰት የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃዎችን

የመስራት ሁኔታ ይታያል፡፡

በፋይሎች ላይ ለተለያዩ ችግር ሊያጋጥም የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ መታዘብ ይቻላል ማለትም የፋይል መጥፋት፣

የሠነድ መቀየር፣ መበላሸት/መቀደድ/ ሰፊ ከመሆኑም በላይ ጥንቃቄ የጎደለው የፋይል እንቅስቃሴ እንዳለ እና በዚህ

ሂደት በፋይሎች ላይ ችግር ሊያጋጥም እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በከተሞች የይዞታ ማህደር አደረጃጀት እና አስተዳደር ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ተጋልጦ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የይዞታ ማህደር መሰወር፣መጥፋት እና ለተለያየ ብልሽት መጋለጥ ወ.ዘ.ተ.የሚታዩ ችግሮች ናቸዉ፡፡ በዚህም የተነሳ

12
ተገልጋዩ ለከፍተኛ እንግልት እና ዉጣ ዉረድ ተጋልጧል፡፡ ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገዉ ደግሞ ክፍተቱ

ለተለያየ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባራት በር መክፈቱ ነዉ፡፡

በአጠቃላይ በመሬት አስተዳደር ተቋም የተደራጀ፣ውጤታማ፣ በኮምፒውተር የታገዘ፣እና ደህንነቱ የተጠበቀ

የመረጃ አያያዝ ችግር አለ፡፡ በአብዛኛው ተገልጋዮች ጉዳይ ለማስፈጸም የቤት ሰነዳቸውን በሚፈልጉበት ጊዜ

በቀላሉ አይገኝም ወይም ከናካቴው ይጠፋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ጊዜው ያለፈባቸው ፋይሎች (dead files)

ከምንጠቀምባቸው ፋይሎች (active) ጋር ተቀላቅለው ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል የፋይሎች አያያዝና አቀማመጥ ጉዳይ በአብዛኛው ችግር ያለበት ነው፡፡ ፋይሎች በአይጥ የመበላት

ሁኔታ አለ፡፡ አንዳንዶች የተሻለ አቀማመጥ ያላቸው አንዳንዶች በተሻለ ሁኔታ ፋይል ቆልፈው የሚያስቀምጡም

ያሉ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ ቦታው በተገቢው ብርሃናማ ያልሆነ በመሆኑ ቀኑን ሙሉ መብራት እያበሩና ወደ

ውስጥ ገባ ብለው ፋይል ለማምጣትም ሞባይል እያበሩ የሚንቀሳቀሱበትን ሁኔታ ከመኖሩም በላይ ካለው ፋይል

አንፃር ቦታው ጠባብ የሆነና የፋይሎች የተዝረከረኩበት ሁኔታ መታዘብ ይቻላል፡፡

በከተማ አዋሳኝ በሆኑ አካባቢዎች የመሬት ወረራ መስፋፋት

ከተሞች እየተስፋፉና በዙሪያው የሚገኙ የገጠር ቀበሌያት ወደ ከተማነት እያደጉና እየተጠቃለሉ ያሉበት ሁኔታ

በአሁን ወቅት በግልጽ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም የከተማና ድንበር በመሬት ላይ ያረፈ ግልጽ አዋሳኝ ባለመኖሩ

በከተሞች አዋሳኝ አካባቢ የሚገኘው የመሬት ሀብት በሕገ ወጥ መንገድ በወረራ እየተያዘ፣ ከኘላን ውጭ የሆኑ

ግንባታዎች እየተበራከቱ ሽንሽኖ አልባ በሆኑ ይዞታዎች፣ ደረጃቸውን ባልጠበቁ ግንባታዎች የከተማ ውበት

ከማበላሸቱም በተጨማሪም የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ለመካሄድ እንቅፋት የሆነበት ሁኔታ ሲኖር በሌላ

በኩል ደግሞ በሕገ ወጥ መንገድ ያአግባብ ለመሬት ግዥ እና ግንባታ እየተፈፀመ ገንዘብ ለብክነት እንድጋለጥ

ለክፍተት የተጋለጠ አድርጎታል፡፡

ከጥናቶች ለመረዳት እንደተቻለዉ ሕገ ወጥ የመሬት ወረራ ከሚያባብሱት ውስጥ ሕገ ወጥ ደላሎች ተጠቃሽ

ሲሆኑ “በዚህ ትልቅ መንገድ ይወጣል“ ፣ “በዚህ አከባቢ ገበያ ልቆም ነዉ፣“ ወዘተ.. እያሉ ነዋሪዉን አርሶ አደር

እያደነጋገሩ ከይዞታው እያፈናቀሉ ብዙ የሕብረተሰብ ክፍሎች ለችግር መዳረጋቸው ይጠቀሳል፡፡

በኢንቨስትመንት ስም ቦታ ከወሰዱ በኋላ ያለጥቅም አጥሮ ማስቀመጥ

አንዳንድ ባለሀብቶች የመንግሥት ቤቶች እና ክፍት ቦታዎችን በማስፋፊያ ስም ከአቅም በላይ እየጠየቁ እና

እየተፈቀደ ወደ አንድ ይዞታ ካጠቃለሉ በኋላ በተፈቀደው ጊዜ ውስጥ ወደ ልማት ባለመግባታቸው መንግሥት

13
ከቦታው ማግኘት ያለበትን ገቢ እንዳያገኝ፣ ህብረተሰቡም በልማቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን በማድረግ የተወሰኑ

ግለሰቦች ከተማውን በመቆጣጠር ባዶ ቦታ እየከለሉ እየሸጡ ህገ ወጥ ጥቅም እያገኙ ስለመሆኑ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

በሊዝ የተላለፉ ቦታዎች በብዛትና በስፋት ታጥረው የተቀመጡና አንዳንዶቹም የተባለው ግንባታ ሳይገነባ

ተከራይተው ለሌላ አገልግሎት የሚውሉበት ሁኔታ/ለብሎኬት ማምራቻ፣ ለሻይ ቡና መሸጫ፣ መኖሪያ ቤቱን

ለዘይት መጭመቂያ ወዘተ/ እንዳለ ተረጋግጧል፡፡ ግንባታ ያልተጀመረባቸው የሊዝ ቦታዎችም ማስተላለፊያ ዋጋው

ከፍተኛ በመሆኑ ውስጥ ለውስጥ በሚደረግ ሂደት ተሽጠውና ተገንብተው ከ 2 አመት አገልግሎት በኋላ በዝቅተኛ

ዋጋ ስመ ንብረት ዝውውር የሚፈፀምበት ሁኔታ እንዳለ በጥናት ታይቷል፡፡ በንግድና በመኖሪያ የሊዝ ቦታ የወሰዱ

ሰዎች ቦታውን ለመውሰድ የሚያደርጉትን የነቃ እንቅስቃሴና ተሳትፎ ቢኖርም ቦታው በተሰጣቸው ጊዜ ገንብተው

ለተባለው አገልግሎት እንዲውል በማድረግ እረገድ ጉድለቶች መኖራቸውና ከታለመላቸው አላማ ውጭ እየዋሉ

መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

የከተማ መሪ ኘላን የሚቃረኑ አሠራሮችን መስፈን

ሕጋዊ የሆነ ከተሞች መሪ ኘላን ተዘጋጅቶ ለመንግሥታዊ ተቋማት፣ ለማህበራዊ አገልግሎት፣ ለአረንጓዴ ተክል

የሚውሉ መናፈሻዎች፣ እንደ አገልግሎቱ አይነት፣ በመንገድ ተለይተው በዚሁ መሰረት የሚመሩበት ሥርዓት

እንዳለ ይታወቃል፡፡

የከተማ መሪ ኘላን ለመንገድ፣ ለአረንጓዴ መናፈሻ እና ለተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚውሉ በታዎች

ለመኖሪያና ለንግድ ተሽንሽኖ የሚሰጥበት አሠራር ስለመኖሩ ይገለጻል፡፡ ችግሩ የጐላ ባይሆንም በአንዳንድ ከተሞች

በፊት ለግሪን ኤሪያ ተብሎ የተተው ቦታዎች በመሸንሸን የክፍል ከተማ ማዘጋጃ ጽ/ቤት፣ የትምህርት ተቋማት፣

የጤና ተቋማት እና የተለያዩ ግንባታ ተከናውኖ አገልግሎት እየሰጠ ያለበት ሁኔታ ስለመኖሩ ተጠቅሷል፡፡ ከተማ

እየተስፋፋ ሲሄድ ለመንግሥታዊ ተቋማት እና ለማህበራዊ አገልግሎቶች የሚሆን ቦታ በማስተር ኘላን ላይ

በማካተት የሚዘጋጅበት እና እንደገና ማሻሻያ የሚደረግበት አሠራር የተጠናከረ ያለመሆን ተጠቃሽ ምክንያት ነው፣

የመሬት እገዳ የሚጥስ ተግባር መኖሩ፣

በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ ለተደራጁ ማህበራት የመሥሪያ ቦታ ለ 5 ዓመት የሊዝ ዘመን የሚሰጥ ስለመሆኑ

ተጠቅሷል፡፡ ሆኖም ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ ለተደራጀ ማህበራት የተሰጡ ቦታዎች በመሸንሸን ወደ ግል

ይዞታ በማዛወር የይዞታ ምስክር ተዘጋጅቶ የሚሰጥበት አሠራር መኖር፡፡

14
ከተማ አስተዳደር ጋር በተደረገዉ ዉይይት በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ስም ለተደራጁ ስራ አጦች በተሰጡ

ቦታዎች ላይ ስራ አጥ ያልሆኑ ከአመራር ጀምሮ ለሌሎች ሰዎች ተሰጥቶ ያሉበት ሰለመሆኑ ያረጋገጡበት ሁኔታ

አለ፡፡

የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ ካለፈ በኃላ ምንም ዓይነት ግንባታ ሳይፈጸም መሬት ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ

ማንኛውም በሊዝ ኪራይ ለኢንቨስትመንት መሬት የወሰደ ወደ 3 ኛ ወገን በሽያጭ ለማስተላለፊ የስም ዝውውር

ጥያቄ ሲቀርብ በአፈጻፀም መመሪያ ቁጥር 2/97 አንቀጽ 2.4.5 እና ደንብ ቁጥር 27/97 አንቀጽ 13/1/ መሠረት

የዋናው ቤት ግንባታ ወይም የህንጻ ግንባታ 51% እና ከዚያ በላይ በማጠናቀቅ ልዩ ልዩ ክፍያዎች በአግባቡ

ስለመከናወኑ ተረጋግጦ መፈጸም እንዳለበት ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 24፣ ደንብ

ቁጥር 103/2004 አንቀጽ 34 እና የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/05 አንቀጽ 64 ስር ማንኛዉም የሊዝ ባለይዞታ

የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ ከማለፉ በፊት የሊዝ መብቱን ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ እንደሚቻል ተደንግጓል፡፡

ሆኖም በጥናት ወቅት ከተሰበሰቡ መረጃዎች ለመረዳት እንደተቻለዉ በርካታ ቦታዎች ምንም አይነት ግንባታ

ሳያከናውኑ ለ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ ይታያል፡፡

ለተለያዩ ኢንቨስትመንቶች የሚሰጡ ቦታዎች ለፕሮጀክቱ በቂ ስለመሆናቸዉ ሳይጣራ የሚሰጥበት አሰራር መኖር

በከተማ ውስጥ የሚገኙ ቁልፍ የሆኑ ቦታዎች ለተለያዩ ኢንቬስትመንቶች ከመሰጠቱ በፊት የተጠየቀው የቦታ

ስፋት፣ በቦታው የሚካሄደው የግንባታ ዓይነት፣ የሚያርፍበት ስፍራ፣ ለተሽከርካሪ ማቆሚያ የሚሆን ቦታ

እንዲሁም ኘሮጀክቱ የሚያስገኘውን ፋይዳ እና በአካባቢዉ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት መኖር አለመኖሩ በሚገባ

ተጠንቶ መሰጠት እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ሆኖም በአንዳንድ ከተሞች ለኢንቨስትመንት የሚሆን የቦታ ጥያቄ

በሚቀርብበት ወቅት ተገቢ የሆነ ጥናት ሳይደረግ የሚፈቀድበት አሠራር በመኖሩ ግንባታ ከተጀመረ በኋላ

የተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ ለሴፍት ታንከር፣ ለኩሽና ለመጸዳጃ ወ.ዘ.ተ የሚሆን በቂ ቦታ ሳይቀር ግንባታ

የሚፈፀምበት ሁኔታ በመኖሩ ባለሀብቱ ይህንን ክፍተት በመጠቀም በጐን የሚገኘውን ተጨማሪ ቦታ እንዲጠይቅ

ሁኔታ በማመቻቸት አጠገቡ የሚገኘን የመንግሥት ቤት ወይም ቦታ ያለ ውድድር የሚወስድበት አሠራር በመኖሩ

አፈጻፀሙ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተጋለጠ መሆኑ፡፡

የሀሰተኛ መንግስታዊ ሰነድ መበራከት

የሀሰተኛ ሠነድ ባለጉዳዩ እንዲያዘጋጅ የተመቻቸ ሁኔታ መኖር፣ በቀበሌ በአግባቡ የማረጋገጥ ሥራ አለማከናወን፣

ፍ/ቤት የባለቤትነት ማረጋገጫ ሲጠይቅ አንዳንድ ቀበሌና የመሬት አስተዳደር ባለሥልጣናት ሀሰተኛ መረጃ

15
በመስጠትና ውሳኔዎችን በማዛባት ካርታ እንዲያገኙ ማድረግ፣ የተጭበረበረ ሠነድ ማዘጋጀትና ህግን የማስከበር

አቅም ደካማ መሆን በአሠራሩ ውስጥ ይታያል፡፡

በመንግስት ተቋማት ውስጥ በሀሰተኛ ማስረጃ የመጠቀም / የመቀጠርና የደረጃ እድገት የማግኘት / ሁኔታ

እየተፈጠረ ነው፣የሃሰት የመሬት ማስረጃዎች ባስመሳይነት በተፈጠሩ ፎቶግራፎች አማካኝነት የመሬት የይዞታ

ማረጋገጫ ካርታ ይዘጋጃል፣ ሀሰተኛ የመኖሪያ ቤቶች ህብረት ሥራ ማህበራትን በማቋቋም የማህበሩ አባለት

በህገወጥ መንገድ መሬት እንዲወስዱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣

የስ/ጎ/ዞ/ስ/ጸ/ሙ/ኮ በያመቱ በርካታ ሀሰተኛ የመሬት ማስረጃ ሰነዶችን ይመረምራል፡፡እነዚህን የሃሰት የመሬት

ማስረጃዎች ባስመሳይነት በተፈጠሩ ፎቶግራፎች አማካኝነት የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ይዘጋጃል፡፡

ት/ቤቶች፤ ኮሌጆች፤ ዩንቨርስቲዎች በቂና በሞያ ብቃታቸው አስተማማኝ መምህራን አይኖሩትም ስለዚህ
ተማሪዎች ሲመረቁ በቂ እውቀት ጨብጠው እይወጡም ፡፡ ሙስና በተንሰራፋበት ማህበረሰብ ውስጥ የትምህርት
ደረጃን በገንዘብ መግዛት ወይንም በሃሰት ማዘጋጀት ስለሚቻል ችሎታና አቅም ያላቸው፤ ዘመድና ገንዘብ
የሌላቸው ወጣቶች ስራ የማግኘት እድላቸው የተመናመነ ይሆናል፡፡

የተጫራች ነጋዴዎች በመመሳጠር የመንግስትን ጥቅም መጉዳት

ተጫራቾች በቡድን በመደራጀትና ከቡድናቸው ውስጥ አንዱ እንዲያሸንፍ ለማድረግ ልዩ ልዩ ዘዴዎችን መጠቀምን

ይመለከታል፤ ይህም በሁለት ዓይነት መንገድ ሊፈጸም ይችላል፤ አንደኛው ተጫራጮች በመመካከር አሸናፊ

የሚሆኑ ቡድኖችን ተራ በማስያዝ፤ አንተ መጀመሪያ አሸናፊ ትሆናለህ አንተ ደግሞ ቀጥሎ በመባባል ሲሆን፣

ሌላው ደግሞ የመጫረቻ ዋጋን ሆን ብሎ ከፍ በማድረግ ከአሸናፊ ተጫራች የተወሰነ ገንዘብ የሚከፋፈሉበት ዘዴ

ነው፡፡

በመንግስት ንብረት አስተዳደርና አወጋገድ ላይ ስለሚገጥሙ የሙስና አጋጣሚዎች

የሚወገዱ ንብረቶች ለዚያ መስሪያ ቤት አገልግሎት የማይሰጡ ቢሆንም የህዝብ ሃብት ናቸውና ባግባቡ ሊወገዱ

ይገባል፡፡ በመሆኑም ግዥ በውል ሲፈጸም እንደሚደረገው ሁሉ፣ የሚወገዱ ንብረቶችንም የማስወገድ ሂደት

በእቅድና የገንዘብን ዋጋ ባገናዘበ መልኩ መሆን ይገባዋል፡፡ በማስወገድ ሂደትም የሚፈጠሩ የሙስና አጋጣሚዎችን

ለመከላከል በሚያስችል መልኩ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ከዚህ በታች የተገለጹት ንብረትን በማስወገድ ሂደት ሊከሰቱ

የሚችሉ የሙስና አደጋዎች ናቸው፡፡

16
የሚገለገሉበትን ንብረት አገልግሎት በማሳነስ( የማይሰራ በማስመሰል) ከሚወገዱ እቃዎች ውስጥ እንዲመደብ

ሊያደርጉ ይችላሉ፤የሚወገዱ የህክምና መሳሪያዎች፤መድሃኒቶች በቀጥታ ሊሸጧቸው የሚችሉበት ሁኔታ

ሊፈጠር ይችላል፤ የሚወገዱ የህክምና መሳሪያዎች፤መድሃኒቶች በጨረታ በማስወገድ ሂደት ለእጩ ተወዳዳሪዎች

መረጃዎችን አስቀድመው ሊሰጡ ይችላሉ፤

የሰዉ ሃይል መረጣ፣ ምልመላ፣ እድገትና የሙያ ልማት

አንዳንድ መስሪያ ቤቶች ሰራተኞችን መምረጥ፣ ቅጥር፣ እድገትና የሙያ ማሻሻያ ጉዳይ ላይ ተገቢ የሆኑ

ስርአቶችን፣ ህግና ደንቦችን አላስቀመጡ ይሆናል፡፡ ቢኖሩም አንዳንድ ጊዜ እየታወቁ ሊዘነጉና ሊጣሱ ይችላሉ፡፡ ይህ

ከሆነ በዚህ ዘርፍ ዉስጥ የሚከተሉት እንዲከሰቱ ያደርጋል፡-የተሳሳተና ህገ ወጥ የሆነ የሰራተኛ ቅጥርና

ምልመላ፣ቅጥር በዝምድናና ቀረቤታ መሆን፣በስልጣን መባለግ፣ጎጠኝነት፣የሚገባቸዉን ሰራተኞች በመድሎ

መለየት፣በመጠቃቀም ሰራተኞችን፣ መምረጥ፣ መቅጠር፣ ማሳደግና ማሻሻል፣መስሪያ ቤቱ ከሚፈልገዉ በላይ

ሰራተኛ መቅጠር፣በሁሉም ደረጃ የስራ ብቃትና ጥራት መዉደቅ፣መርህንና የስራ መስፈርትን በመጣስ ወጣ ገባ

እድገትና የስራ ማሻሻያ፣ የሚገባቸዉ ባለሙያዎችና ሰራተኞች የሙያዊ ልማት ተጠቃሚ አለመሆን፡፡

ከፍተኛ መደቦችንና ሹመቶችን በኔትወርክ፣ በጥቅማጥቅምና በሥልጣን ቀረቤታ በመስጠት የሚፈፀሙ የሙስና

ወንጀሎች አየተበራከቱ መምጣታቸውን አንድ ጥናት አመላክቷል፣

በሆነ አስተዳደር የስራተኛውን እድገት ቅጥርና ጥቅማ ጥቅም ችሎታን መሰረት ባደረገ መንገድ ባለማከናወንና

ምቹ የሥራ ሁኔታ እንዳይኖር በማድረግ የሰራተኛውን የሥራ ፍላጎትና ሞራል እጅጉን እንዲጎዳና የሥራ

ውጤታማነቱንና ምርታማነት እንዲቀንስ በማድረግ፣


በመንግስት የሚገዙ እቃዎች ጥራት የወረደ መሆን

ለሙስና በከፍተኛ ደረጃ ከተጋለጡ የስራ ዘርፎች ዉስጥ ግዥና ጨረታ አንዱ ነዉ፡፡ከግዥ ጋር የተያያዙ የሙስና

ተግባሮች እንዳሉ ተዘውትሮ ይገለጻል ፣ ጊዜው ያለፈበት ዕቃ መግዛት፣ጥራቱን ያልጠበቀ እቃ መግዛት፣የግዥ ዋጋ

ከሚገባው በላይ የተጋነነ መሆን፣ ተመሳስለው በተሰሩ ፎርጅድ እቃዎች በርካታ ገንዘብ ይባክናል፣ ስለሆነም ይህንን

ችግር ለመግታት የግዥና ጨረታ ሂደት ስነ ስርአቶች ግልጽና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የሚተገበሩ መሆን አለባቸዉ፡፡

የፈቃድ አሰጣጥ ስርአት ህግና ስርአትን የተከተለ አለመሆን


በማንኛዉም መስሪያ ቤት ዉስጥ የሚገኙ የተለያዩ የፈቃድ አሰጣጥ የስራ ዘርፎች ለሙስናና ብልሹ አሰራር

የተጋለጡ ናቸዉ፡፡ ለዚህ ምክንያቱም በመስሪያ ቤቱ የተቀመጡ መመሪያዎች በዚህ አካባቢ የሚሰሩ ሰራተኞች

ወይንም ሃላፊዎች ልዩ የመወሰን ስልጣን የሰጣቸዉ በመሆኑ ነዉ፡፡ ልዩ የሆኑ ለአንድ ግለሰብ የሚሰጡ የመወሰን

17
ስልጣኖች ለሙስናና ስልጣንን አላግባብ መገልገል ወንጀል መፈጠር ምክንያት ይሆናሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ለሙስና

ሊጋለጡ የሚችሉ የሚከተሉት ናቸዉ፡-

የተሸከርካሪ ምደባ፣ ምዝገባና ፈቃድ፣መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ማህበሮች፣ ኩባንያዎች ፈቃድና

ምዝገባ፣ፓስፖርት የማዉጣትና የቪዛ ፈቃድ፣ለተለያዩ አገልግሎቶች የግለሰቦች ምዝገባ፣ሞትና ዉልደት ምዝገባና

ማስረጃ፣የንግድ ፈቃድ፣የጦር መሳሪያ ፈቃድ ወዘተ፡፡

በተለይ በየክፍለከተማው እና ቀበሌው የመታወቂያ አሰጣጥ ስርአት ለበርካታ የሙስና ወንጀል የተጋለጠ ነው፡፡

በአበል ክፍያ ስም በርካታ የመንግስት ገንዘብ እየተመዘበረ መገኘቱ


በፊልድ ጉዞና በመኝታ ላይ የሚወጣ ወጭ በመንግስት አገልግሎት ዉስጥ ከፍተኛ ነዉ፡፡ በዚህ አካባቢ የሚወጣዉን

ወጭ ለመቆጣጠር ብዙ ጊዜ ከባድ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ባብዛኛዉ በግለሰብ ደረጃ የሚፈጸም ስለሆነ ነዉ፡፡ በዚህ

በኩል የሚባክነዉና የሚጭበረበረዉ ገንዘብ እጅግ ብዙ ነዉ፡፡ በፊልድ ስራ የሚወጣዉ ገንዘብ ላይ አላግባብ

የመገልገልና የሙስና እድሎች በማንኛዉም ደረጃ ማለትም ከጉዞ በፊትና በኋላ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ እነዚህ እድሎች

የሚፈጠሩባቸዉ ምክንያቶች፡-

ኃላፊዎች የውሎ አበል መስክ ሣይሄዱ ወይም ሣይወጡ ሁሉ አበል የሚያወራርዱ እንዳሉ በተጠኝዎች ተጠቅሷል፣

ሰኔ በረረች ብሎ ያለአግባብ በጀቱን ማባከን ሲሉ አንድ ተጠኝ ገልጸዋል፣በመስክ ሥራ ወቅት ላልተሠራ ሥራ ክፍያ

መክፈልና ቀን ጨምሮ የማወራረድ ሁኔታ ሠራተኛውን ጨምሮ በብዛት ከፍተኛ አመራሩ ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ

እየታየ ነው፣ ይህ በአመቱ መጨረሻ ገኖ እንደሚይ ተጠቅሷል፣

በጉዞ ክፍያ ላይ የሚታዩ ሌሎች አላግባብ መገልገሎች ፡-ያልተፈቀደ ከጸደቀዉ ጋር ልዩነት ያለዉ የጊዜ ቆይታ፣ለጉዞ

የሚፈለገዉ ገንዘብ ሳይጸድቅ ቀድሞ መሰጠት፣የተሰጠዉ ገንዘብ ከጉዞ በፊት መባከን (ወጭ) መሆን፣ሃሰት የዉጭ

ረሲት ማቅረብና ማወራረድ የመሳሰሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ታክስ ማጭበርበር እና አለመክፈል

መንግሥት ለኢንቨስትመንትና ለንግድ መስፋፋት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ለምሳሌ፡- የኃይል

ምንጮችን፣ የትራንስፖርትና መገናኛ አውታሮችን፣ዘመናዊ ቴሌኮሚኔኬሽን አገልግሎት… ወዘተ በጥራትና

በብዛት ለመዘርጋት ገንዘብ ያስፈልገዋል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ተግባራት ለማከናወን የሚያስችል ወጪ የሚገኘው

መንግሥት ከህዝቡ ከሚሰበስው ግብር/ታክስ፣ ከእርዳታ እና ከብድር ከሚገኝ ገቢ ነው፡፡

ከተለመዱት የመንግሥት ገቢዎች መካከል በፐርሰንት ሲሰላ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ከግብር የሚገኝ እንደሆነ ልብ

ይሏል፡፡ ከዚህ በመነሳት በታክስ ላይ የሚፈጠር ሙስና ለልማት እንቅፋት እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡

18
የግብር አሰባሰብ ሥርዓትንና ደንብን በማዛባት ከገቢ ግብር እና ልዩ ልዩ የታክስ ገቢዎች ለመንግስት መግባት

የሚገባውን የገቢ መጠን በመቀነስ በቂና አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዳይፈጠሩ እንቅፋት

በመሆን፣

የገቢ ሂሳብን በማምታታት ወይም ሌላ ህገወጥ ዘዴዎችን በመጠቀም የታክስ ክፍያን መቀነስ ወይም ፈጽሞ

ለማስቀረት የሚደረግ የተሳካ ወይም ያልተሳካ ሙከራ ነው፡፡ ታክስ ሰዋሪዎች ትክክለኛ ገቢያቸውንና ትርፋቸውን

በመቀነስ ወይም ተቀናሽ የሚደረግበትን ወጪ ከፍ በማድረግ የሚጠበቅባቸውን የግብር ገቢ ለመቀነስ

የሚያደርጉት የማጭበርበር ተግባር ነው፡፡

ግብር ስወራ የሚመለከተው በስህተት ምክንያት ወይም አቅም በማጣት የታወቀ የግብር ግዴታ ሳይከፈል ለሚቀር

ግብር ሳይሆን ሆነ ተብሎና እያወቁ የተለያዩ የማታለያ፣ የተንኮልና አሳሳች ነገሮች በመፈጸም ሊከፈል የሚገባ

የግብር መጠን እንዲሰወር የሚያደርግ ሕገወጥ አካሄድን ነው፡፡

በዚህም ባለፉት አመታት ግብር ከፋዮች ሃሰተኛ ደረሰኝ በማቅረብ፣ ገቢን አሳንሶ በማሳወቅ፣ ኪሳራን

በማስመዝገብና ሌሎች የማጭበርበሪያ ስልቶችን በመጠቀም አገር ማግኘት ያለባትን ገቢ አጥታለች።

“ግብር መሰወር መዋረድ ነው” በሚል አንድ ግብር ከፋይ ተናግረዋል፡፡ ሌላው ግብር ከፋይ ”አንዱ በትክክል እየከፈለ

አንዱ የሚሰውርበት አካሄድን መከላከል ካልተቻለ ሌላውም እንዳይከፍል ያደርጋል” የሚል ሃሳብ ሰጥተዋል።

አንድ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ስብሳቢነት የተመዘገበ ነጋዴ የዕቃ ወይም የአገልግሎት ማቅረብ ሥራ በማከናወን

በዚህ ግብይት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ሰብስቦ እያለ የሰበሰበው የተጨማሪ እሴት ታክስ ሙሉ በሙሉ

ለግብር ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት ላለመክፈል የፈጸመው የሽያጭ መጠን ዝቅ አድርጐ ሊያሳውቅ ይችላል፡፡ ይህንን

ለማድረግ የፈጸማቸውን ሽያጮች በተወሰነ መልኩ ለመደበቅ ያለደረሰኝ ግብይት መፈጸም(ደረሰኝ አለመስጠት) ፣

የተጭበረበረ ደረሰኝ መጠቀም፣የተሰበሰበን ተጨማሪ እሴት ታክስ በወቅቱ ገቢ አለማድረግ ፣ ሐሰተኛ የሒሳብ

መዝገብ የማደራጀት ወይም የተፈጸሙ ሽያጮች በሒሳብ መዝገብ ያለመመዝገብ ድርጊት ሊፈጽም ይችላል፡፡

የሽያጩ መጠን ዝቅ ከተደረገ (ከተደበቀ) ደግሞ ባልተገለጸው ሽያጭ ላይ የተሰበሰበ የተጨማሪ እሴት ታክስ ለራስ

በማስቀረት የግብር መሰወር ድርጊት ይፈጽማል፡፡ ይህም በአገራችንም ሆነ በሌሎች አገሮች ላይ በታክስ አሰባሰቡ

ላይ  አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ ያለ ሕገወጥ ድርጊት ነው፡፡ ለምሳሌ በ 2010 በመጀመሪያዉ ሩብ ዓመት ብቻ

ካለደረሰኝ ሲገበያዩ የተገኙ 90 ድርጅቶች መኖራቸዉን እና ከዚህ ጋር ተያይዞ ከ 131 ግለሰቦች በፍታብሄር እና

በወንጀል እንዲጠየቁ መደረጋቸውን ለችግሮቹ መኖር እና ለተወሰደው እርምጃ ማሳያ ነው።

19
የሰበሰቡትን ታክስ (VAT) ለመንግሥት አለመክፈል፡፡ ይህም ከላይ በተገለጹት ድርጊቶች አማካይነት ሊፈጸም

የሚችል ሲሆን፣ በሌላ መልኩ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፈጸሙአቸው ግብይቶች የሚሰበስቡ ነጋዴዎች አስቀድሞ

በተሰላ ሁኔታ ድርጅታቸው ኪሳራ ሳይገጥመው ሆነ ተብሎ የመክሰር ውሳኔ በማሰጠት አስቀድሞ የተሰበሰበ ቫት

ሳይከፈል የሚቀርበት ሁኔታ አለ፡፡ በሌላ በኩል አንዳንድ ነጋዴዎች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ሰብሳቢነት በመመዝገብ

ከፈጸሙአቸው ግብይቶች ቫት ሰብስበው ለመንግሥት ሳይከፍሉ ይዘውት የመጥፋት ድርጊት (Missing trader

fraud) በአገራችን እንዲሁም በሌሎች አገሮች በስፋት የሚታይ የግብር ስወራ ዓይነት አለ፡፡

በ 2010 400 ሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኖች ደብዛቸው ጠፍቷል፡፡ እነዚህ ማሽኖች ከመሥሪያ ቤቱ የመረጃ ቋት

ባለመያያዛቸውም በቢሊዮኖች የሚገመት ገቢ እንዲጭበረበር ሰበብ ሁነዋል፡፡

ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች በሕገወጥ መንገድ ማስገባት(ኮትሮባንድ)

ዕቃዎቹ በሕገወጥ መንገድ ከገቡ ግን በእነዚህ ዕቃዎች ላይ ሊከፈል ይችል የነበረው ቀረጥና የተጨማሪ እሴት ታክስ

ጨምሮ ሌሎች በገቢ ዕቃዎች የሚከፈሉ ታክሶች ሳይከፈሉ እንዲቀሩ ያደርጋል፡፡ በሕገወጥ መንገድ የገቡ ዕቃዎች

ተገቢው ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልባቸው መግባታቸው ብቻ ሳይሆን በአገር ውስጥ ገበያ ላይ የሚሸጡት ከሌሎች

ተወዳዳሪ ዕቃዎች ዝቅ ባለ ዋጋ በመሆኑ፣ በንግድ ውድድር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡

2. ሙስና በአገራችን ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት


ሙስና በአገር ላይ እጅግ ከፍተኛ የሆኑ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ከባቢያዊ ጉዳቶችንና ቀውሶችን

እንደሚያስከትል በርካታ የጥናትና ምርምር ግኝቶች አረጋግጠዋል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ እያንዳንዱን በዝርዝር እናያለን።
2.1. የመንግስት ገንዘብ እና ንብረት በከፍተኛ ሁኔታ እየባከነ ይገኛል፣
የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ከሚጠይቁት በላይ ወጭ ይኖራቸዋል፣ወጭዎች ባልታቀዱ ፐሮጀክቶች፣
ፕሮግራሞች ላይ ይዉልና ከፍተኛ ብክነትን ያስከትላል፣የመንግስት ሃብት ወደግል ንብረት በቀላሉ የሚቀየርበት
ሁኔታም ይፈጠራል፣በመንግሥት ገንዘብ በውድ ዋጋ ተገዝተው የሚገቡ እቃዎች ትክክለኛነት የሚረጋገጥበት
(የጥራትቁጥጥር) ስርዓት ወጥነት የሌለው፣ቀልጣፋ ያልሆነ እና አስተማማኝነት የጎደለው መሆኑ ሌላው ችግር
ሆኖ ቆይቷል።

20
ለኢኮኖሚ እድገት የተነደፉ የልማት ፕሮጀክቶች ለህብረተሰቡ የጎላ ጥቅም በማይሰጡ ፕሮጀክቶች እንዲተኩ

በማድረግ፣ የመንግስት በጀት ለተገቢው እና ቅድሚያ ሊሰጠው ለሚገባው ተግባር እንዳይውል በጥቂቶች

ለሚፈልጉት ተግባር እንዲውል በማድረግ፣

2.2. ኢፍትሃዊ የገቢ ክፍፍል

የአገርን ሃብት ጥቂት ባለስልጣናትና ባለሃብቶች እንዲቀራመቱት ሁኔታዎችን በማመቻቸት አብዛኛውን ህዝብ

ለድህነት፣ ለችግርና ለከፋ የጉስቁልና ኑሮ መዳረግ፡፡ ሙስና በፈጠረዉ ሚዛናዊ ባልሆነ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ

ምክንያት ድህነትና የሃብት ልዩነት መጠን ስለሚሰፋ ድግግሞሹ በበዛ አዙሪት ዉስጥ ግለሰቦችና አገር እጅግ በከፋ

ሁኔታ እንዲራቆቱ ያደርጋል፡፡ ምሁራኖች ይህንን "paradox of plenty or Dutch disease" በማለት ያብራሩታል፡፡

የመጀመሪያዉ ጽንሰ ሃሳብ የሚገልጸዉ የተትረፈረፈ ሃብት እያላቸዉ ህዝባቸዉን በቀን 3 ጊዜ መመገብ

ያቃታቸዉን ሲሆን፣ ሁለተኛዉ የሚገልጸዉ ደግሞ የኢኮኖሚ እድገቱ የተዛባና ኢ-ፍትሃዊ የሆነ መሆኑን ነዉ፡፡

2.3. የኢንቨስትመንት መጠንን ይቀንሳል፣


ኢንቨስተሮች ብዙ ጊዜ ዝቅተኛ የሙስና ደረጃባላቸው አገሮችኢንቨስት ለማድረግይፈልጋሉ፣በመብራት ችግር
ምክንያት ከባድ እንዱስትሪዎች ስራ እያቆሙ ነው፣በሃገሪቱ የሚገኙ ፋብሪቻዎች በመብራት ሃይል እጥረት
ምክንያት ስራለማቆም ወይም ምርታቸውን ለመቀነስ መገደዳቸው ይነገራል፡፡

ከፍተኛ የውጪ ኢንቨስተሮችን /ባለሃብቶችን/ ገንዘብና እውቀታቸውን በአገር ኢኮኖሚ እድገትና ልማት ላይ

ለማዋል የሚያስችል አገልግሎቶችን ለማግኘት ጉቦ እንዲከፍሉ በመጠየቅ ወደ አገር ውስጥ ገብተው ገንዘብና

እውቀታቸውን በአገር ኢኮኖሚ እድገትና ልማት ላይ ለማዋል የሚያደርጉትን ተሳትፎና የኢንቨስትመንት

እንቅስቃሴን ይገድባል፡፡

2.4. አለማቀፋዊ የገንዘብና ቁሳቁስ እርዳታ መቅረትና መባከን


በተቀባይ አገሮች ዉስጥ የሚታይ የሙስና ወንጀልና ተግባር ረጅ ድርጅቶች ተስፋ እንዲቆርጡ፣ርዳታቸዉንና
የርዳታፕሮግራሞቻቸዉን እንዲያቋርጡ ያደርጋል፡፡ለምሳሌ የወርልድ ባንክ ፈንድ አጠቃቀም በተመለከተ በርካታ
ችግች እንዳሉበት ይነገራል፡፡

2.5. ማህበራዊ አንድነትን ያናጋል


ሙስና ቀስ በቀስ በአንድ በኩል ያላቸዉን ጥቂቶች በሌላ በኩል ደግሞ የሌላቸዉን ብዙሃን የሚፈጥርና ልዩነትን
የሚያሰፋ ነዉ፡፡የሃብት ልዩነት ማህበራዊ አንድነት ድርን በመናድ ማህበረሰብ እንዲከፋፈል፣ ህግና ስርአት
እንዲወድቅ፣ስርአተ አልበኝነት እንዲሰፋ፣ ወንጀለኝነት፣ ምንቸገረኝነትን፣ ስንፍናንና ተስፋ መቁረጥን
የሚያስከትል ይሆናል፡፡

21
ሙስና ሰብአዊ መብትን ይጥሳል ፤ በሙስና የተሰደዱ፣የሞቱ፣ያበዱ፣የድሀድሀ የሆኑ ዜጎች አሉን፡፡

ሙስና የሰዉል ጅሰ ብአዊነትና ክብርን የሚሸረሽር ምሁራዊ ስንፍናን እና ወሬኛነትን የሚያሰፋ፣ እያወቁ እዉነታን
መደበቅና ማዛባትን፣ችላ ባይነትንና ደንታቢስነትን፣ትኩረት አለመስጠትን የሚያባብስ፣የፈጠራ ችሎታን
የሚገድልና የእዉቀት ስድትን የሚያመጣ ነዉ፡፡

2.6. የጤና ችግር መባባስ


ጥራታቸው የተጓደሉ ግንባታዎች (ድልድዮች፣ ህንጻዎች፣ ግድቦች…) ድንገት ፈርሰው ለህዝብ እልቂት
ምክንያትም ሊሆኑ ይችላል፡፡ህገወጥ መድሃኒት ንግድ መበራከት፣ እንዲሁም የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው
መድሐኒቶች፣ ምግቦች እንዲሁም የህክምና መሳሪያዎች ተገዝተው በህዝብ ጤንነት ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ
የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
በመብራት መቆራረጥ ምክንያት በሆስፒታሉ ውስጥ በቀዶ ጥገና ህይወታቸው መትረፍ የሚችል ህይወታቸው
ሲያልፍ ይታያል፣መብራት በሰው ሠራሽ መንገድ የሚተነፍሱ ሰዎችና በማሞቂያ ክፍል ውስጥ ያሉ ህፃናት
ህይወት ጉዳይ ነው፡፡

ሙስና ጥራትና ደረጃዉን የጠበቅ የህክምና አገልግሎት እንዳይኖር በማድረግ፣ በጀት ጉድለት በመፍጠር፣ የህክምና

ወጭን በማጋነን፣ የአገልግሎት አሰጣጡን በማዉረድ፣መድሃኒት የሚቋቋሙ ተዋህስያን እንዲበዙ በማድረግ

ለአደገኛ በሽታዎች መስፋፋት ምክንያት ይሆናል፡፡

በጨረታ ተገዝተዉ የሚላኩ መድሃኒቶች ደረጃቸዉ የወረደ፣የሚገዙ የህክማ ቁሳቁሶች ጥራት ደረጃቸዉ የወረደ

በመሆኑ አገልግሎት ሳይሰጡ በቀላሉ መበላሸት፣ለወረዳ የሚመደቡ መድሃኒቶች ከተማ ላይ በድብቅ የሚከማቹ፣

ጊዜ ያለፈባቸዉና ጉዳት የሚያደርሱ መድሃኒቶች በብዛት መሸጥ፣ ለወሊድ አገልግሎት የመጡ አንቡላንሶች

የህዝብ ትራንስፖርት መገልገያ ሆነዉ የግለሰቦች መጠቀሚያ መሆን፣ዉድ የሆኑመድሃኒቶች በየቦታዉ በስፋት

መዘረፍ፣ ወጥተዉ መሸጥ በጥቅሉ መንግስት በጤናው ዘርፍ የሚያደርገውን ጥረት አደጋ ላይ ይጥላሉ፡፡
2.7. የፍትህ ጉዳት
ሙስና የህግ የበላይነት እንዲዛባ ያደርጋል፡፡ኪሚያመጣቸዉ ጉዳቶች ዉስጥ ዋና ዎቹ የህግና ስርአት
መፈራረስ፣የህግና ፖሊሲዎች አለመተግበር፣ፍትህን ለማግኘት አለመቻል፣መጓተትና መከልከል፣ችግር ያለበት የህግ
አፈጻጸም፣በህግ ስርአቱ ያለዉ የህዝብ መተማመነት ናእምነት እንዲቀንስ፣ስጋት እንዲጨምር፣ህገ ወጥነት
እንዲበዛ ያደርጋል፡፡

ሙስና በህግ እኩል የመዳኘትንና የመንግስት አገልግሎት ጥራትን ስለሚቀነስ የሕግ የበላይነት ስሜትን ከህብረተሰቡ

ዘንድ በማጥፋት ማህበረሰቡን ላልተረጋጋ ህይወት በመዳረግ ዋልጌነት፣ ጥፋተኛነትና ሥርዓተ አልበኝነት

እንዲስፋፋ ያደርጋል፣ በዚህም የህዝቡ ስላማዊ ህይወት አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡

22
2.8. ለሌሎች ወንጀሎች መከሰት ምክንያት ይሆናል
ሙስና ሌላሙስና ይወልዳል( corruption breeds corruption)፣ሙስና ማፍያዎች የተደራጀ ወንጀል እንዲፈጠሩ
ያደርጋል፣ፖሊስ ደካማ እንዲሆንና ወንጀለኞች የመያዛቸው እድል ደካማ እንዲሆን ያደርጋል፣ የአደገኛ
መድሃኒቶችና እጾች፣የመኪና አደጋዎች መበራከት፣የጦር መሳሪያዎች ዝዉዉር፣ወዘተ..እንዲበራከት ያደርጋል፡፡

2.9. ለብሄራዊ አንድነት መናጋትና ለአገር አለመረጋጋት ምክንያት ይሆናል

በህብረተሰቡ ውስጥ አንቱ የተባሉ ሰዎች በሙስና ውስጥ የሚዘፈቁ ከሆነ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የጨዋነት

መመዘኛ ከማዛባቱም ባሻገር ለሌሎች የሥ-ነምግባር ብልሹነት እና ለሙስና ተግባር እንደመከላከያ (ማጣቀሻ)

ተደርገው ሊቀርቡ ይችላል፡፡ “እነ እገሌም እንዲህ ያደርጉ የለም እንዴ” የሚል አመለካከት እንዲዳብር

ከማድረጉም ባሻገር ስርዓተ አልበኝነት፣ ህገወጥነት እንዲስፋፋና የአገር ሰላምና መረጋጋት አደጋ ውስጥ

እንዲወድቅ ምክንያት ይሆናል፡፡


በሙስና ምክንያት ህዝብ በመንግስትና በህግ የበላይነት ላይ አመኔታ እንዲያጣ ያደርጋል፣የዲሞክራሲ ስርዓት

ግንባታን ያደናቅፋል፣የፖለቲካ አመራሩን ጥራት ያበላሻል፣እከከኝ ልከክልህን (patronage)፤ የማይፈጸም


ቃልመግባትን (sycophancy) ያባብሳል፣ ህዝብን ማዳመጥና ማማከር ይቀራል፣ መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶች
ይጣሳሉ፡፡

ሙስና ህዝብ በመንግስትና በሕግ የበላይነት ላይ አመኔታ እንዲያጣና በዲሞክራሲ ሥርዓት ላይ ጥርጣሬ

እንዲኖረው በማድረግ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡

እንዴት?

የመንግስት ሥራዎች ከተገቢው አሰራርና ከሕግ ውጪ እንዲከናወኑ በማድረግ፣ ሙስና ዜጐች በሀገራቸው

ብሔራዊ ሃብት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ መብታቸው እንዲነካና አድሎ እንዲፈጸምባቸው ስለሚጋብዝ ህዝቦች

በመንግስት ላይ የሚኖራቸው እምነት እንዲሸረሸርና በሚኖሩበት ሀገር ውስጥ የቤተኝነት ስሜት እንዳይሰማቸው

በማድረግና በዚህም የተነሳ በመንግስትና በህዝብ ዘንድ ትልቅ ክፍተት እንዲፈጠር ያደርጋል፣

በአንድ አገር ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት እንዲጠፋ በማድረግ ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ እንዳይኖር በማድረግ ለህገ ወጥ

ሹም ሽር እንዲጋለጥ ምክንያት ይሆናል፣ የመልካም አስተዳደር ችግር መንግስት በህዝብ ዘንድ አመኔታ በማሳጣት

አገርን ወደ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንዲያመራ ከማድረግ ባሻገር የሕግ የበላይነትን በማደብዘዝ ስርዓተ

አልበኝነትና የዲሞክራሲያዊ መብት ረገጣ እንዲስፋፋ ያደርጋል፣

የህግ የበላይነት መደብዘዝና ሥርዓተ አልበኝነት መንገስ ደግሞ ሕዝብ የተረጋጋ ኑሮ እንዳይመራ ከማድረግ ባሻገር

አንድ መንግስት በመንግስትነቱ እንዳይቀጥል ምክንያት ይሆናል፡፡

23
የሙስና በአንድ አገር ውስጥ መንሰራፋት የአገር ደህንነት ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ ይፈጥራል። በተለይም

ሙስና በሚያስከትለው ያልተመጣጠነ የሃብት ክፍፍል በአንድ አገር ውስጥ ግጭቶችና አልፎ ተርፎም የእርስ በርስ

ጦርነቶች የሚከሰቱበት አጋጣሚ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

በሌላ በኩል ሙስና በአንድ አገር ውስጥ የመንግስት አለመረጋጋት ስለሚፈጥር የአገርን ህልውና ጥያቄ ውስጥ

ይከታል፡፡ ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ሙስና በአውሮፖዋ ሀገር ጣሊያን ተደጋጋሚ የካቢኔ መበተን እንዲደርስ

ማድረጉን በዋቢነት ማንሳት ይቻላል:: በአፍሪካም በሴራሊዩን፣ በላይቤሪያ፣ በኮንጐ፣ በሶማሊያ የደረሰው መጠነ

ሰፊ ቀውስ ከሙስና ጋር የተያያዘ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሙስና ለአገሮች ሁለንተናዊ እድገት ማነቆ ከመሆኑም በላይ ህልውናቸውንም በመፈታተን ሰላምና የፖለቲካ

መረጋጋት እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ይህም ማለት ሙስና ለሃገሮች የፖለቲካ አለመረጋጋትና ለርስ በርስ ጦርነቶችና

ግጭቶች መንስኤ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ በአብዛኛው ጊዜ የሚስተዋለው የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍልን መሰረት

በማድረግ አላስፈላጊ የሆነ የጥቅም ትስስር በሚኖርበት ወቅት በድርጊቱ የተወሰኑ ቡድኖች ብቻ የሚጠቀሙበት

ሲሆን ነው፡፡ ከሥርዓቱ ወይንም ከአገዛዙ ምንም አይነት አልያም ጥቂት ጥቅም የሚያገኘው ቡድን ራሱን

በማንቀሳቀስ እኩል ወይም የተሻለ ድርሻ ለማግኘት የሃይል አማራጭን በመከተል ትግል ይጀምራል፡፡ በዚህ ወቅት

አስፈላጊ ያልሆኑና አውዳሚ የርስ በርስ ግጭቶች ይነሳሉ፡፡

ሙሰና የእርስ በርስ ጦርነትን እንደሚያመጣ ሁሉ የእርስ በርስ ጦርነትም የሙስና ወንጀል የበለጠ እንዲስፋፋና

እንዲወሳሰብ በር ይከፍታል፡፡ ይኸውም አንድ አገር በእርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ ሌሎች አገሮች በሁኔታው

ተጠቃሚ ሲሆኑ ጥቅማቸውንም የሚያቆራኙት ከተለያዩ ግለሰቦች/መሪዎች/ ጋር በሙስና በመተሳሰር ነው፡፡

እነዚህ አገራት ጦርነቱ እንዳይበርድ በማድረግ በእዛ ሃገር ውሰጥ የሚገኘውን የማእድን፣የነዳጅና ሌሎችን ሃብቶች

በመዝረፍ የጦር መሳሪያ ንግዳቸውን በመጧጧፍ እራሳቸውን ሲጠቅሙ ይስተዋላሉ፡፡ ለዚህም

በላይቤሪያ፣በሴራሊዮን፣በአንጐላና አፍጋኒስታን የተከሰቱ ግጭቶችን ለአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ

የሙስና መንሰራፋት የተለያዩ እቅዶች እንዳይተገበሩና ያልተስተካከለ እድገት እንዲኖር በማድረግ በመንግስት ላይ

የተለያዩ ተቃውሞዎችና ጥያቄዎች እንዲነሱ በማድረግ በከፋ መልኩም ለጐሳ ግጭቶች፣ ለብሔርና ለኃይማኖት

ጦርነቶች በር በመክፈት፣

ሙስና የዲሞክራሲ ሥርዓት መሠረት የሆኑትን የግልጽነትና የተጠያቂነት መርሆዎችን የሚያፋልስ የሰዎችን

ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የሚገድብ ተግባር በመሆኑ ሕዝብ በዲሞክራሲ ሥርዓት ላይ ጥርጣሬ

እንዲኖረውና ለሥርዓቱ ግንባታ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዳያደርግ እንቅፋት በመሆን በዚህም ህዝብ መንግስት

በሚያቅዳቸው ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት እንቅስቃሴዎች የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ

እንዳያበረክት ምክንያት ይሆናል፡፡

24
ሙስና ለመንግስት መዳከም፣ ለፖለቲካ አለመረጋጋትና ለደም አፋሳሽ ብጥብጥ አንዱና ዋነኛዉ መንስኤ ነዉ

የሚለዉ ነበር፡፡ በአንድ አገር ዉስጥ ያቆጠቆጠ ሙስና መንግስትን የሚያዳክመዉ በአንድ ቀን ጀንበር ሳይሆን ቀስ

በቀስ ተቋማትንና የመንግስትን የአካሄድ ስርአቶችን እና የህግ የበላይነት በመሸርሸር ነዉ፡፡ በጊዜ መቆጣጠር

ካልተቻለ እንደካንሰር ይስፋፋና ግላዊ ጥቅሞች ከአገራዊ ጥቅሞች በላይ መሄድ ይጀምራሉ፡፡ የግል ጥቅም

መንግስትን የሚቆጣጠር ከሆነ መንግስት ይዳከምና መንግስታዊ ተግባሩን መወጣት ተስኖት የመዳከም ምልክት

የሆነዉ ደም አፋሳሽ ብጥብጥ ያቆጠቁጣል፡፡

በሙስና እና በመንግስታት መዳከምና አለመረጋጋት መካከል ግንኙነት ለመፍጠር ዋነኛ ትኩረት የሚሆነው ስር

የሰደደና የተስፋፋ ሙስና ነው፡፡ የዚህ አይነት ሙስና የመንግስት ተቋማት በአግባቡ ተግባራቸውን እንዳይወጡ፣

ማህበራዊ አገልግሎቶችን ጤና፣ ትምህርት፣ ደህንነት /ባግባቡ እንዳይሰጡ ያደርጋል፡፡ የመንግስት ቁልፍ ተግባራት

የሚባሉት የግዛት ቁጥጥር፣ ሰላምና ደህንነት፣ የመንግስት ሀብትና ንብረትን የማስተዳደር የተጎዱ የህ/ክፍሎችን

የመደገፍና መጠበቅ ወዘተ ናቸዉ፡፡

የሙስና እድሎች በሰፉባቸዉ አገሮች ዘርፎ የመያዝ እድል ዝቅተኛ ስለሚሆን ባለስልጣን ሆኖ ሲዘርፉ ለመኖር እና

ባለስልጣን ሆኖ ለመዝረፍ የሚፈልጉ ሰዎችና ቡድኖች እንዲበዙ ያደርጋል፡፡ በዚህም የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ

የሚደረግ ዉድድር ጤናማ ያልሆነ፣ በተንኮልና በሸፍጥ የተሞላ፣ ለብጥብጥና ግጭት በር የሚከፍት ይሆናል፡፡ ለዚህ

አይነት አደጋ የተጋለጡ ብዙዎቹ አገሮች ሰፊ የተፈጥሮ ሃብት ያላቸዉ አገሮች ኮንጎ፣ ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ፣ ሱዳን፣

ሊቢያ ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡

ሙስና ስር በሰደደባቸው አገሮች ነፃና ሚዛናዊ በሆነ ምርጫ የፖለቲካ ስልጣን መያዝ ስለማይቻል የምርጫ ሂደቱ

የተጭበረበረ፣ በገንዘብ የተገዛ እንዲሆንና የምርጫ ማጭበርበር ክሶች በጉቦ እንዲዘጉና ላቅ ያለ ጥቅም ያቀረበ

ስልጣን እንዲይዝ ያደርጋል፡፡ በምርጫ ስልጣን የመያዝ እድሉ ቢጠፋ ሁለተኛዉ አማራጭ ማለትም ብጥብጥ

በማስነሳት የመንግስት ስልጣንና ሀብትን የመቆጣጠሪያ ምኞት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

ሲጠቃለል ሙስና የህዝብን እምነት ያጣ ስልጣን ላይ ያለ መንግስት በስልጣን የመቆየት እድሉን ያሰፋለታል፡፡

በገዥዎች አማካኝነት ስር የሰደደና የሰፋ ሙስና ገዥዎች ለግልፅነት፣ ለተጠያቂነትና ለፖለቲካዊ ሙስና

ጆሮአቸውን እንዲደፍኑ፣ ሚስጥራዊ ግንኙነቶች ደግሞ በህ/ሰቡ ውስጥ እንዲሰፉ በማድረግ አለመረጋጋቱን

ያባብሰዋል፡፡

አንድ የተረጋጋ የፖለቲካ ስርኣት በራሱና በማህበረሰቡ ወይም በጥቂት ማ/ሰብ ክፍሎች፣ በመንግስት ውስጥ ባሉ

ቡድኖች መካከል የሚፈጠር ግጭትን /አለመግባባትን/ በቀላሉ መፍታት ይችላል፡፡ ፖለቲካዊ ሙስና ወይንም

የፖለቲካው በሙሰኞች የመበረዝ ሁኔታ ተቋማዊ አገልግሎት አሰጣጡን የሚያዳክም፣ የፖለቲካ ለውጥ ሂደቱን

25
የሚያበላሽ፣ የህግ የበላይነትን የሚሸረሽር፣ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ውጤታማ እንዳይሆኑ የሚያደርግ ነው፡፡

በዚህም ሰዎች አለመግባባትን ለመፍታት ወደ ፍርድ ቤት ወይንም አስተዳደራዊ ስነርዓቶች ከመሄድ ይልቅ ሀይልና

ጉልበት መጠቀምን ይመርጣሉ፡፡

መንግስት በራሱ አለመግባባቱን መፍታት ሲሳነው ህገ ወጥ ወደሆነ ሀይል የመጠቀም መንገድን በመከተል ስርዓት

ለማስጠበቅ ይሞክራል፡፡ ግጭትና አለመግባባትን ለመፍታት /በጉልበት ሀይል ላይ መተማመን ሀይል መጠቀም እድል

ያለው የማ/ሰብ ክፍል በጉልበት ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ይቀናቀናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሙስና መልካም

አስተዳደርን በማዳከም መንግስታዊ ገቢ እንዲቀንስ በማድረግ መሰረታዊ አገልግሎቶች ማነቆ በመሆን መንግስት

እንዲዳከምና እንዳይረጋጋ ያደርጋል፡፡ እንዲሁም አቅማቸው የደከመ ያልተረጋጉ መንግስቶች በራሳቸው ሙስና

እንዲጎለብት ያደርጋሉ፡፡ ይህ የሆነው የህግ የበላይነት መዳከም፣ ከሙስና ጋር የተያያዙ አቤቱታና ቅሬታዎችን

ለመፍታት የሚያስችሉ ዘዴዎች አለመኖር ነው፡፡

2.10. ህዝብን ለከፋ የኢኮኖሚ ችግር ይዳርጋል፡፡

ሙስና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በመፍጠር የአገር ልማት እንዲቀጭጭ፣ የኢኮኖሚ እድገት እንዲገታ፣ ኪሣራና

ውድቀት እንዲፋጠን እና ድህነት በከፍተኛ ደረጃ እንዲስፋፋ በማድረግ ዜጎች ወደ ከፋ የኑሮ አዘቅት ውስጥ

እንዲወድቁ ያደርጋል፡፡

ለህዝብ የሚቀርቡ የፍጆታ ዕቃዎች መጠንና ጥራትን በመቀነስ የግብይትን ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በማናር ህዝብን

ለከፋ የኢኮኖሚ ችግር ይዳርጋል፡፡

ሙስና በሰፈነበት አገር በዋነኛነት ሰፊው ህብረተሰብ የችግሩ ተጠቂ በመሆኑ በሚያጋጥመው የኢኮኖሚ ቀውስ

ሳቢያ አብዛኛው ህዝብ ለድህነት ይዳረጋል፡፡ ሰርቼ የተሻለ ኑሮ አኖራለሁ ብሎ የሚመኘው ህዝብ ለሥራ አጥነት፣

ለጎዳና ተዳዳሪነት እና ለሴተኛ አዳሪነት ይጋለጣል፣ እጅግ ሲከፋም ለስደት እንዲዳረግ ምክንያት ይሆናል፡፡
2.11. በሃቀኛ የገበያ ተፎካካሪዎች ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ
ሙሰኛ ተጫራቾች ማእቀብ ካልተደረገባቸውና ሁሌም አሸናፊ ከሆኑ በጥራት፣ በአዳዲስ ፈጠራና በተመጣጣኝ ዋጋ

በማቅረብ ኢኮኖሚውን ሊደግፉ የሚችሉ ታማኝ ተፎካካሪዎች ከገበያ እየወጡ እንዲሄዱ ምክንያት ይሆናል፡፡ሙስና

ከነጻና ፍትሃዊ ዉድድር ዉጭ የሆኑ ጥቂት ጥገኛ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ብቻ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ህጋዊ

የንግድ ድርጅቶች እንዲጎዱ ያደርጋል፡፡

26
ሙስና ተፎካካሪነትን ስለሚቀንስ የፈጠራ ስራ እንዲዳከም ምክንያት ይሆናል፡፡ በሙስና የሚተማመኑ አቅራቢዎች
ሃብታቸውን በፈጠራ ላይ በማዋል የተሻለ ነገር ይዞ ከመቅረብ ይልቅ የተለመደውን እቃ ወይም አገልግሎት ይዘው
መቅረብን ይመርጣሉ፡፡
2.12. እዳ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ ምክንያት ይሆናል

ሙስና መንግሥት ከታክስ/ግብር ሊያገኝ የሚችለውን ገቢ እንደሚያሳጣ ይታወቃል፡፡ ሙስና በተስፋፋባቸው

አገሮች ውስጥ የበጀት እጥረት /ዴፊሲታቸው/ ከፍተኛ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመሆኑም መንግሥት

ገቢውን ለማሳደግ ብድርን ጨምሮ ሌላ አማራጭ እንዲፈልግ ይገደዳል፡፡ ይህ ደግሞ መንግሥትን ከብድር አዘቅት

ውስጥ እንዲገባ በማድረግ በጉዳዩ ውስጥ የሌለበት መጪው ትውልድ የእዳ ተሸካሚ እንዲሆን ያስገድደዋል፡፡
2.13. በግልና በቤተሰብ የሚደርስ ጉዳት
አንድ ሰው በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈረድበት በእሱና በቤተሰቡ ላይ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም
ስነልቦናዊ ጉዳት ይደርሳል፡፡ ሰዎች ከሚወዱት ቤተሰብ ይለያሉ፣ ከስራ ገበታቸው ይፈናቀላሉ፤ በዚህ ምክንያትም
የቤተሰብ ኢኮኖሚ ይናጋል፤ ልጆች ትምህርት ቤት ሊያቋርጡ ይችላሉ፤ከሚኖሩበት አካባቢም በመፈናቀል
ማህበራዊ ኪሳራ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፤ በሙስና መያዙ በራሱም በግለሰቡ እና በቤተሰቡ ላይ የሚያደርሰው ስነ
ልቡናዊ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡
2.14. ሙስና የተፈጥሮ ሚዛንን ያዛባል

በማዛባት ከባቢያዊ ሁኔታዎችን የሚያዛቡ ተግባሮችን በመፈጸም የሰውን ልጅ የመኖር ህልውና የሚፈታተኑ

ጉዳቶችን ያስከትላል፡፡

እንዴት ?

የተፈጥሮ ሃብቶች ከማንኛውም ሃብት ባልተናነስ መልኩ ለሙስና የተጋለጡ ናቸው። ይህም በሁለት መንገድ ሲሆን

አንደኛው የተፈጥሮ ሃብቶችን ኃላፊነት በጐደለው መንገድ መመዝበር ነው::ሁለተኛው ደግሞ ለአካባቢ ብክለት

ከፍተኛ ሚና የሚኖራቸውን፣ የአካባቢ ዑደትን ሊያዛቡ የሚችሉ አደገኛ የኬሚካል ተረፈ ምርቶችን በየብስ፣

በአየርና በምድር ላይ ማስወገድን የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

በሙስና ግንኙነት ለደን የተከለሉ የደን ልማት ቦታዎች እንዲጨፈጨፉ፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ሃብቶች አንዲሰረቁ፣

ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡና ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተከለከሉ ኬሚካሎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡና ጥቅም

ላይ እንዲውሉ በመፍቀድ የአገር የተፈጥሮ ሃብት ያለአግባብ እንዲባክን በማድረግ፣ በዚህም ለአከባቢ አየር

መዛባት፣ መበከል እና ለከፋ የኢኮኖሚ ወድቀት እንዲጋለጡ ያደርጋል፡፡

ከህገ ወጥ የመሬት ወረራ ጋር ተያይዞ ከተሞች ማስተር ፕላናቸውን ጠብቀው ለልማትና ለእድገት አመቺ የሆነ

አሰፋፈር እንዳይኖራቸው በማድረግ በከተሞች እድገት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡

27
በአካባቢ የተፈጥሮ ሃብቶች ላይ ከሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎች በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚችለው የሕግ ወጥ የደን

ቆረጣ ሲሆን ፣ለምሳሌ በካምቦዲያ በ 1997 ዓ.ም ለመንግስት ባለስልጣናት የተሰጠ ጉቦ ወደ 200 ሚሊዮን ዶላር

የሚጠጋ ሲሆን፣ ይህ የካምቦዲያ መንግስት በህጋዊ መንገድ ከተፈጥሮ ደን ሽያጭ ካገኘው በ 13 እጥፍ ይበልጣል፡፡

በኢንዶኔዥያም በሃገሪቱ ጥቅም ላይ የእንጨት ውጤቶች ከ 50-70 በመቶ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚመረት ሲሆን

ይህም የሃገሪቱን የደን ሃብት በዓመት ከሁለት ሚሊዮን ሄክታር በላይ እንዲወድም ያደርጋል፡፡ በተመሳሳይ በሩሲያ

20 በመቶ የእንጨት ምርት በሕገወጥና ኃላፊነት በጐደለው መንገድ ይቆረጣል፡፡

2.15. ሙስና የዋጋ ንረትን ያስከትላል

በኢኮኖሚ ዘርፍ በግል ሴክተሩ የንግድ እንቅስቃሴ ወጭን ያጋንናል፡፡ የንግድ ባለቤቶች የሚከፍሉት ጉቦ፣ ለድርድር

የሚያወጡት ወጭ፣ ወይንም ህግን በመጣስ ወይንም መጣሳቸዉ እንዳይታወቅ በማሰብ የሚከፍሉት ክፍያ ከፍተኛ

ይሆናል፡፡ እንዲሁም የኢንቬስትሜንት እድሎችን በመዝጋት፣ አመች የንግድ ከባቢ እንዳይኖር በማድረግ፣ በሙሰኛ

ባለስልጣናት ምክንያት አዳዲስ ያልተጻፉ ደንቦች እና መጓተቶች ይፈጠሩና ንግዱን ክፉኛ የሚጎዱ ይሆናሉ፡፡

2.16. ሙስናና ምስጢራዊ የገንዘብ ዝዉዉር

ሙስና በከፍተኛ መንግስታዊ ድክመትንና አለመረጋጋትን የሚያመጣባቸዉ መንገዶች ከላይ ያየናቸዉ ሶስት

መሰረታዊ ጉዳዮች ቢሆኑም፤ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ሌላዉ የሙስና መዘዝ ጥቂት ስልጣን ያሉ አካላትና የስልጣኑ

ተጠቃሚ የሆኑ ቡድኖች በሙስና ከተዘፈቀች አገር በሙስና የሰበሰቡትን ሃብት በህገ ወጥና ምስጢራዊ በሆነ

መንገድ ወደሌሎች አገሮች ማሻገር ነዉ፡፡ ምስጢራዊ የገንዘብ ፍሰት ማለት ህገወጥ በሆነ መንገድ የተገኘ (በስፋት

በሙስና) እና ወደ ሌላ አገር የተላለፈ ገንዘብ ማለት ነው፡፡

ምስጢራዊ የገንዘብ ፍሰትን በአንድ አገር ውስጥ ወይንም ድንበር ዘለል ሊሆን ይችላል፡፡ ድንበር ዘለል ከሆነ ሀብቱ

ከአገራዊ ህግ ተጠያቂነት የራቀና ለማስመለስ ቢሞከር የማይቻል ይሆናል፡፡ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ከምስጢራዊ

ገንዘብ ፍሰት ውጤቶች ዉስጥ ዋናዉ በምስጥር ወደ ውጭ የሚወጣው ሀብት ለነዚህ አገሮች ድጋፍ ከሚመጣው

ገንዘብ ይበልጣል፡፡ እንደዚሁም ድርጊቱ እርዳታ ላይ ጥገኛ በሆኑ ድሀ አገሮች ላይ ስለሚፈፀም በድህነት አሮንቋ

ተዘፍቀዉ እንዲኖሩ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ በተጨማሪም በመንግስታት የኢኮኖሚያዊና የመልካም አስተዳደር

አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ሙስናን የመዋጋት አቅማቸዉን ይሸረሽራል፣ ለዉስጥና ለዉጭ ሃይሎች

እንዲጋለጡ ያደርጋል፡፡

28
እንደ አለም አቀፍ የፋይናንስ ኢንተግሪቲ ሪፖርት (GFI) መሰረት ከ 2005 – 2014 ባሉት አመታት ከኢትዮጵያ

1,259-3,153 ቢሊየን ዶላር) በምስጢር ወደ ውጭ ወጥቷል፡፡ በተጨማሪም አገሪቱ ከ 2000- 2009 11.7 ቢሊዮን

ዶላር አጥታለች፡፡ በ 2009 ብቻ 3.26 ቢሊየን ዶላር ያጣች ሲሆን ይህ በ 2008 አገሪቱ ከዉጭ እርዳታ ካገኘችዉ

829 ሚሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነዉ፡፡ ምስጢራዊ የገንዘብ ፍሰት የአገሪቱ የ GDP እድገት 22% እንዲቀንስ

አድርጓል፡፡ ከ 55 እስከ 80% የሚሆነዉ ምስጢራዊ የገንዘብ ዝውውር የመነጨው በሀሰት የውጭ ንግድ ደረሰኝ

ምክንያት ነው፡፡ ይህ በየዓመቱ ወደ ውጭ የሚወጣው የአገሪቱን 11% - 29% የሚሆነውን የንግድ መጠን

የሚሸፍን፣ ከ 40 - 97% ወደ አገሪቱ የሚገባዉን የገንዘብ ድጋፍ የሚያክል፣ ከ 10% - 30% የሚሆነው የኢትዮጵያ

መንግስትን ጥቅል በጀት የሚሸፍን ነዉ (OECD 2016፣ GFI 2017)፡፡ ስለሆነም ሙስና ኢኮኖሚዉን በማራቆት፣

የመንግስትን አቅም በማሽመድመድ አጥፊ ወደሆነ አለመረጋጋትና ብጥብጥ እንድታመራ እንዳደረገ ያሳያል

ትምህርት ሶስት

የመፍትሄ እርምጃዎች

አስከፊ ጉዳት የሚያደርሰዉን የሙስና ወንጀል ለመግታት መወሰድ የሚገባቸዉ እርምጃዎች ምንድን ናቸዉ? ማን

ነው ተጠያቂው?

በሙስና ላይ የሚደረገዉ ጦርነት የእያንዳንዱ ሰዉ ብሄራዊ ግዴታ ነዉ፡፡ በማህበረሰብ ዉስጥ ያለ ሁሉም አባል የጸረ

ሙስናዉ ወታደር መሆን አለበት (Mwai Kibaki) ፡፡ ሙስናን ለመዋጋት a multi-pronged approach የሚጠይቅ

ነዉ፡፡ በአለም አቀፍ፣ በአህጉር፣ በአገር፣ በክልል ደረጃ ችግሩን ለመግታት የሚደረገዉ ጥረት እንዳለ ሆኖ ትግሉን ወደ

ተቋምና ግለሰብ ደረጃ ማዉረድ ይገባል፡፡

ሀ) ውጤታማ የፀረ ሙስና ትግል

የሥነምግባር ትምህርትን በስፋት በመስጠት ሙስናን ሊሸከም የማይችል ዜጋ መፍጠር ፤የሙስና ወንጀልንና
ብልሹ አሰራርን መከላከል ፤ ሙሰኞችን ማጋለጥ ፤ መክሰስና መመርመር ውጤታማነት ማሻሻል፡፡

በመንግስታት መካከል ሙስናን የመዋጋት ቁርጠኝነትንና ትብብርን ለማጠናከር በርካታ አለምአቀፋዊና ከህግ

ታራሚ ድንጋጌዎች ስራ ላይ ውለዋል፡፡ ለምሳሌ የመንግስታቱ ድርጅት የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን እና የአፍሪካ የፀረ

29
ሙስና ኮሚሽን በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡ የነዚህ ኮንቬንሽኖች ዋነኛ ትኩረቶች፡ ሙስናን አስቀድሞ መከላከል፣

ሙሰኞችን የሚቀጣ ጠንካራ የህግ ማዕቀፍ ማዉጣት፣ የተመዘበረና የተሻገረ ሃብትን ማስመለስና አለአቀፋዊና

አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር ናቸዉ፡፡ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገራት ኢትዮጵን ጨምሮ እነዚህን ኮንቬሽኖች

ከመፈፀም አልፈው አገራዊ የህግ አካል አድርገዋቸዋል፡፡

ነገር ግን አሁንም ድረስ ሙሰኞችን ለፍርድ በማቅረብ የዘረፉትን ሀብት በማስመለስ ረገድ ሰፊ ክፍተቶች አሉ፡፡

ለ/ የአመራሩ (የፖለቲካ) ቁርጠኝነት

በመንግስት እና በሲቪክ ማህበረሰቦች አመራር ውስጥ ሙስናና ብልሹ አሰራርን የመዋጋት ቁርጠኝነት በጋራ

በሚሰሩ የፀረ ሙስና አደረጃጀቶች እየተደገፉ የሙስና ድርጊትን ለመቀነስ ያስችላሉ፡፡ የፖለቲካ ተቋማትና

ፓርቲዎች የበለጠ ተጠያቂነትንና ግልፅነትን የሚጠይቁና የሚፈጽሙ ከሆነ የማህበረሰቡን ሙስናን የመዋጋት

አቅምን ያጠነክራል፡፡ ይህ ማለት የፖለቲካ ሰዎችና ድርጅቶች የፀረ ሙስና አቋማቸው ጠንካራና ለድርድር

የማይቀርብ ከሆነ ነገ ስልጣን የሚይዙ አካላት በድርጊቱ እንዳይሳተፉ ያደርጋቸዋል፡፡

የአመራር ቁርጠኝነት ማለት በአንድ አገር ዉስጥ ያሉ አመራሮችና ሰራተኞች ለመንግስቱ ቁልፍ ስትራቴጂዎችና

ፖሊሲዎች (አገራዊ የጸረ ሙስና ትግልን ጨምሮ) ስኬትና ዉጤታማነት ያላቸዉን አፋዊና ተግባራዊ እንቅስቃሴ

ጽናት ድምርና ወጥ አፈጻጸም መግለጫ ነዉ፡፡

ሐ) ተቋም አቀፍ የፀረ ሙስና ስትራቴጂን ማጎልበት

ይህ አስትራቴጅ ተቋማት በባለቤትነት መንፈስ የሚያደርጉት ቀጥተኛ ተሳትፎ ነው፡፡ ሙስናን መከላከል የአንድ

ተቋም/የሥራ ክፍል ጉዳይ ሳይሆን የሁሉም አካላት ድርሻ ነው፣ በዚህም ሙስናና ብልሹ አሠራርን ከመከላከል

አንጻር በእያንዳንዱ ተቋም ያለውን ተጨባጭ የሆነ ቁርጠኝነት ማረጋገጥ ይጠይቃል፡፡ ‹‹ሳይቃጠል በቅጠል››

እንዲሉ ስህቶችን/ችግሮችን በወቅቱ ለማረም የሚያስችል መሆኑ፣

መ) የሲቪክ ማህበረሰቡን ሚና ማጎልበት

ሙስናን የመዋጋት ስራ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ሳይሆን የመንግስትን የሲቪክ ማህበራትንና የዜጎችን

ትብብርና አጋርነት የሚጠይቅ ነው፡፡ መንግስት ህግ በማውጣትና የፀረ ሙስና ተቋም በመፍጠር ላይ ሲያተኮር

የሲቪክ ማህበራት ደግሞ የፀረ ሙስና ዘመቻን በተሻለ በማስፋት፣ በሙስና ላይ ጥናት በማካሄድና አካባቢያዊ የፀረ

ሙስና ልምዶችን ለመንግስት በማጋራት የፖሊሲ መነሻ እንዲሆኑ ሊረዱ ይችላሉ፡፡ ሌላው ዜጋ ደግሞ በግልም ሆነ

እንደየአደረጃጀቱ የሙስና ድርጊትን በማጋለጥና በመጠቆም ድጋፉን ሊገልፅ ይችላል፡፡

ሠ) ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ማጠናከር

30
የፀረ ሙስና ትግሉ የሁሉንም አከላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይ ፍ/ቤቶችና ሌሎች

የፍትህ ተቋማት፣ ዋና ኦዲተር መ/ቤት፣የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ወዘተ ያሉ መ/ቤቶች ይገኙበታል፡፡ እነዚህ አካላት

ሙስናን በመታገል ረገድ ያላቸውን ሚና በውል ተገንዝበው ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አስፈላጊውን

የምክክር መድረክ መፍጠር ይጠይቃል

ይህ ማለት ህዝቡ መንግስት ሙስናን ለመከላከል በዘረጋቸው ስርአቶች ውሰጥ ተሳትፎ ማድረግ፣ሁሉም ዜጋ

ደግሞ በግልም ሆነ እንደየ አደረጃጀቱ የሙስና ድርጊትን በማጋለጥና በመጠቆም ድጋፉን ሊገልፅ ይገባል፣የሙስና

ወንጀሎችን መጠቆም፣ ፍርድ ቤት ቀርበው ምስክርነት መስጠት፣ የሙስና ወንጀል የሚፈጽሙትን መኮነን፣ በፀረ

ሙስና ትግሉ ተሳትፈው ውጤት ያመጡትን ማወደስ ከህዝቡ የሚጠበቁ ተግባራት ናቸው፡፡

ረ) የሃይማኖት ተቋማትን ሚና ማጎልበት

የኃይማኖት ተቋማት የግብረ-ገብና የሥነ-ምግባር ትምህርት ምንጭ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የእምነት

አስተምህሮዎችም የትምህርት መሠረታቸውና መነሻቸው ይኸው የግብረ-ገብና የሥነ-ምግባር ትምህርት ነው፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ያለው ነባራዊ ሁኔታ እንደሚያሳየው የሥነ-ምግባርም ሆነ የግብረ-ገብ ትምህርት ቀድሞ

በነበረበት ልክ አይደለም፡፡ በአንድ በኩል የእምነቱ ተቋማት ስነ ምግባር ማጎልበት ሚናቸዉን በአግባቡ እንዳይወጡ

የሚያደርጉ ሁኔታዎች መፈጠር፣ በሌላ በኩል ደግሞ የእምነቱ ተከታዮችን በግብረገብ ትምህርት የማነጽ

ሃላፊነታቸዉን በቃልም በተግባርም እንዳይወጡ አድርጎአቸዋል፡፡ ስለሆነም የእነሱን ሚና ማጎልበት ተገቢ ነዉ፡፡

ሰ/ የግሉ ዘርፍ ሙስና በመከላከል ረገድ ሚናውን ሊጫወት ይገባል

ሙስናን በመዋጋትና በመግታት ረገድ የግሉ ዘርፍ በተለይም የንግዱ ማህበረሰብ አይነተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ የግሉን

ዘርፍ ከሙስና ማጽዳት ማለት የመንግስት ሴክተሮች ከሙስና እንዲጸዱ ማድረግ ስለሆነ በዚህ በኩል በያገባኛል

ስሜት ሃላፊነታቸዉ እንዲወጡ ማድረግ ይገባል፡፡ የንግዱ ማ/ሰብ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ዋጋ እንደሚያሰከፍል

አውቆ ማንኛወንም የሙስና ወንጀሎች በማጋለጥ፣ በመቆምና በመካላከል ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር ብትብብር

እና በቅንጅት መስራት፣ ውድድርን የሚገድብና ሀገርና ህዘብን የሚጎዳ ህገወጥ ንግድ ሲካሄድ ዝም አለማለት

ይገባል፡፡

ሸ/ ህዝብን በትምህርት ማንቃት እና መረጃን ማሰራጨት

ዜጎች ሙስና ምንድን ነው? እንዴት ሊከሰት ይችላል? በምን መንገድ መዋጋት ይቻላል? የሚለውን ማወቅ

እስከቻሉ ድረስ ሙስናን የመዋጋት ድርሻቸውን ለመወጣት ወደ ኋላ ሊሉ አይችሉም፡፡ እንደዚሁም ሰዎች በሙስና

ድርጊት መሳተፍን እንዴት ሊያርቁ እንደሚችሉ ተግባራዊ ክህሎት ካዳበሩ ራሳቸዉ በሙስና ድርጊት ባለመሳተፍ፣

31
ሌሎች በሙስና ድርጊት እንዳይሳተፉ በማድረግ ከተሳተፉም ደግሞ በመጠቆም አብዛኛውን የሙስና ድርጊት

መግታት ይቻላል፡፡ በዚህ በኩል ት/ተቋማት፣ የሙያ ማህበራት፣ ብዙሃን መገናኛ ድርጅቶች ስለ ስነ ምግባር

ጠቀሜታ፣ ስለ ሙስና አስከፊ ጉዳት ደጋግመዉ ህዝቡ መረጃ እንዲደርሰዉ ማድረግ ከቻሉ ችግሩን በዘላቂነት

መቅረፍ ይቻላል፡፡

ቀ) የወጣቶችን የስነምግባር ግንባታ ላይ ብዙ መስራት

ይህ የእድሜ ክልል ከበሰለ አእምሮ ይልቅ ስሜታዊነት አይሎ የሚገኝበት ወቅት ሲሆን ሁለት ነገሮችን ከፊታቸው

እንዳሉ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ አንዱ አካላዊ እና ቁሳዊ ፍላጎቶች በሚፈጥሩት ስሜት እና ግፊት ፣ጫና እና ጉጉት

ምክንያት የተሳሳተ መንገድ በመምረጥ የወደፊት እድል የሚሰናከልበት ነው፡፡ ሌላው መልካም ነገርን በመጎናጸፍ

ወደ ተሻለ ህይወት የሚወስደውን ትክክለኛ መንገድ መምረጥ ነው፡፡ ስለዚህ ከግብረገብ አንጻር ወጣቶች

ሁለተኛውን እንዲይዙ ማድረግ ይገባል፡፡

በስነ-ምግባርና ሞራል እሴቶች እና ሙስና መከላከል ላይ በሀገሪቱ ያሉ የ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የኮሌጆች

የተማሪዎች የስነ-ምግባር ክበባት ተጠሪ መምህራንን ስልጠና መስጠት፤

በ) የመንግስት ሠራተኞችን ሥነምግባር ማጎልበት

በመንግስት ሰራተኛው ዘንድ የሚስተዋሉ ከልክ ያለፈ እራስ ወዳድነት እና ግለኝነት ማስወገድበስራ ላይ የሚታይ

ግዴለሽነት(ምን አገባኝ)፣ በአቋራጭ የመክበር ፍላጎት እና ስስታምነት፣ ሀቀኝነት፣ ታማኝነት እሴቶች መሸራረፍና

በአጭበርባሪነት መተካት፤ከልክ ያለፈ የሃገር ፍቅር መሸርሸር፣ የሕዝብን ጥቅም አለማስቀደም …የመሳሰሉት

ችግሮች መቆጣጠር ያስፈልጋል፣

ለፌዴራልና ለክልሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የልማት ድርጅቶች፤ ህዝባዊ ድርጅቶች የስነ-ምግባር መከታተያ

ክፍል ፈፃሚ ባለሙያዎች ተግባር ተኮር የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፤

ለክልል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፤ በመንግስት

መስሪያ ቤቶች ፣ በልማት ድርጅቶች እና በህዝባዊ ድርጅት ለሚሾሙ ተሚዎች ስራ ከመጀመራቸው በፊት

በስነ-ምግባርና ሞራል እሴቶች ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ስልጠና መስጠት፤

ለኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና መስጠት፤ ለሲቪክ ማህበራት አመራሮችና

አባላት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና መስጠት፤


ተ) ከሀገራዊ ፍቅር መቀዛቀዝ መውጣት

32
ለሀገራዊ ፍቅር መቀዛቀዝ በዋናነት የሚጠቀሰው የግለኝነት እኩይ በሽታ እየተስፋፋ በመምጣቱ እንደሆነ በየ

መድረኩ ሲነገር ይደመጣል፡፡ የግለኝነትና የስግብግብነት መርዛማ በሽታ መንስኤዎች ዘረኝነት፣ ጎጠኝነትና

አልጠግብ ባይነት በመሆናቸው ሀገራዊ ፍቅር በእጅጉ አንዲቀዘቅዝ እና ሙስና እንዲሰራፋ አድርገዋል ፡፡

ቸ) በ 2013 በጀት ዓመት የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል በዚህም የተለያዩ ውጤቶች ተመዝግበዋል

ከተመዘገቡት ውጤቶች መካከል

2.2 የተማሪዎች ስነምግባር ግንባታ እና ክበባት ተግባራትን በተመለከተ


 የስነ-ምግባርና የሞራል እሴቶች ግንባታ ፖሊሲ ሰነድ እንዲዘጋጅና እንዲፀድቅ ማድረግ፤

 በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት መረጃዎችን መሰብሰብ ፣ ማደራጀት

እና ወቅታዊ ማድረግ፤

 በመንግስትና በግል የ 1 ኛና የ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና ኮሌጆች ውስጥ የተማሪዎች የስነ ምግባር

ክበባትን ማደራጀትና ማጠናከር፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ባሉ የመንግስትና የግል 1 ኛ እና 2 ኛ ደረጃ

ት/ቤቶች፣ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና ኮሌጆች እንዲሁም ዩንቨርሲቲዎች 30235 የስነምግባርና ጸረ

ሙስና ክበባትን ማደረጀች ተችሏል፡:


 በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ከ 9 ኛ እስከ 12 ኛ ክፍል እንዲሁም በኮሌጅ

ደረጃ ለሚማሩ ተማሪዎች በስነ ምግባርና በሞራል እሴቶች ላይ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ

ውድድር ማካሄድ፤

 ግንቦት 16/2013 ዓ.ም በሀገር ደረጃ በሁሉም ክልሎች፣ ዞን እና ወረዳ ድረስ በመንግስትና በግል

ትምህርት ቤቶች የሁለተኛ ደረጃ (የ 9 ኛና 11 ኛ ክፍል)፣ የኮሌጆችና የዩንቨርሲቲ ተማሪዎችን

በስነ-ምግባር ዙሪያ የጥያቄና መልስ ውድድር በማወዳደር የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ

 229 ተማሪዎችን በመለየት እንዲሁም በስነ-ምግባራቸው አርዓያ የሆኑ 286 ግለሰቦችንና

አስተዋጽኦ ያደረጉ 10 ተቋማትን መሸለም ተችሏል፡፡

 በአሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ የ 1 ኛና የ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች ሁለት በመቶ (2%)

በአካል በመገኘት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

 ከተማሪዎች የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ክበባት መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር የልምድ

ልውውጥ መድረክ ማዘጋጀት፤

33
 በሁሉም ክልሎች የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የመንግስትና የግል ኮሌጆች፣

ቴክኒክና ሙያ ተቋማቶች፣ የተማሪዎች የሥነ-ምግባር ክበባት መደራጀታቸውንና፣ የተደራጁት


መሠልጠናቸውን፣ በሠለጠኑት መሠረት መሥራታቸውን ማረጋገጥ፣ መከታተልና መደገፍ፤

 ክልሎች ለተማሪዎች የሥነ-ምግባር ክበባት አመራሮች በሥነ-ምግባርና ሞራል እሴቶች ግንባታ ላይ

የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠታቸውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

 ክልሎች በትምህርት ቤት የሥነ-ምግባር ክበባት ዙሪያ የተሻሉ ምርጥ ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ

ልምዶችን በመቀመር የማስፋፋት ስራ እንዲሰሩ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

 ክልሎች የመንግስትና የግል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ያሳተፈ የተማሪዎች የሥነ-ምግባርና

ሞራል እሴቶች ግንባታ ላይ የጥያቄና መልስ ውድድር እንዲያካሂዱ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

 በሁሉም የአንደኛ ደረጃና የ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን

በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ማድረግ፤

2.3 ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባራትን በተመለከተ


 የሬዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራም ዝግጅት የሚያገለግሉ መሰረተ ልማቶችን እንዲሟላና

የተጀመረውን ስቲዲዮ ግንባታ እንዲጠናቀቅ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤


 በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ ሳምንታዊ ፕሮግራም በማዘጋጀት ማሰራጨት፤

 ሳምንታዊ የሬዲዮ ፕሮግራም በማዘጋጀት ማሰራጨት፤

 የስነ ምግባርና ሞራል እሴቶች ግንባታ እና የሙስና መከላከል መልዕክቶችን በተለያዩ ማህበራዊ

ሚዲያዎች በመጠቀም ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ፤


 በስነ ምግባርና ሞራል እሴቶች እና ሙስናን መከላከል ዙሪያ 74 ኪናዊ እና ንባባዊ የሬዲዮና

የቴሌቪዥን ስፖቶችን በማዘጋጀት እንዲተላለፉ ማድረግ፤

 በየሩብ ዓመቱ የሀገሪቱን የፀረ ሙስና ትግል እንቅስቃሴ የሚያሳዩ መረጃዎችንና የአፈፃፀም

ሪፖርቶችን በማደራጀትና በማጠናቀር ለአህጉር አቀፍ እና ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፣ ኤንባሲዎች

እና ሚዲያዎች ተደራሽ ማድረግ፤

 በስነ ምግባርና ሞራል እሴቶች ግንባታና በሙስና መከላከል ስራ እንቅስቃሴ ላይ በየሳምንቱ በሀገሪቱ

የሚሰሩ ተግባራትን በመከታተል ዜናዎችን በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ተደራሽ ማድረግ፤

 በስነ ምግባርና ሞራል እሴቶች ግንባታ እና ሙስና መከላከል ዙሪያ በአማረኛና በእንግሊዘኛ

ቋንቋዎች ፅሁፎችን በማዘጋጀት ማሳተም፤

34
 በስነ ምግባርና ሞራል እሴቶች እና ሙስና መከላከል ዙሪያ 74 ቃለ ምልልስ፣ ፕረስ ሪሊዝ፣ ፕሬስ

ኮንፍረስ ማዘጋጀት፤

 በስነ ምግባርና ሞራል እሴቶች እና ሙስና መከላከል ዙሪያ 115 ስነ ምግባር መፅሔት፣ ዜና

መፅሔት፣ ብሮሸሮች፣ ፖስተሮች ፣ቢልቦርድ/ስክሪን መልዕክቶችን ማዘጋጀትና ማስተላለፍ፤

 በስነ ምግባርና ሞራል እሴቶች ግንባታ እና ሙስና መከላከል ዙሪያ የተዘጋጁትን ወቅታዊ የሆኑ

የፅሑፍ የቪዲዮና የምስል መልዕክቶችን በኮሚሽኑ ደህረ ገፅ ላይ መጫን፤

 በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 18 ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ 17 ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም

አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በዓልን የድርጊት መርሀ ግብር በማዘጋጀት በሀገር አቀፍ ደረጃ በዓሉ
እንዲከበር ማድረግ፤
 ለሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች በስነ ምግባርና ሞራል እሴቶች ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ

ስልጠና መስጠት፤

3.1.የሥነ ምግባር መከታተያና ሙስና መከላከል


 በፌዴራል የመንግስት ተቋማት ከነበሩ 178 የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች በተጨማሪ በፌዴራል

እና በክልል የመንግስት ተቋማት እና የልማት ድርጅቶች 4667 የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች

እንዲደራጁና እንዲሟሉ ተደርጓል፡፡

 ሁሉም ክልሎች ከክልል እስከ ወረዳ ተቋማቶች ድረስ ባለ የመንግስት መዋቅር የሥነ-ምግባር

መከታተያ ክፍሎች እንዲደራጁ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

 የተቋማት የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች አዲስ ለተሾሙ፣ለተቀጠሩና ለተመደቡ አመራርና

ሰራተኞች ስራ ከመጀመራቸው በፊት የስነ ምግባርና ሞራል እሴቶችና ሙስና መከላከል ስልጠና

እንዲሰጡ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ፤

 ለሁሉም የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች የበጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ ማዘጋጀትና የእቅድ

ኦረንቴሽን በመስጠት ወደ ስራ መግባታቸውን መከታተል፤

 በዓመት ሁለት ጊዜ በሚከታተሏቸው ተቋማት የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች የስራ እንቅስቃሴ

ላይ የአካል ምልከታ፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

 እያንዳንዱ ተቋም የስነ-ምግባርመከታተያ ክፍል በተቋሙ ቢያንስ 5/አምስት/ የሙስና መከላከል

የአሰራር ስርዓት ጥናት በማካሄድ የማሻሻያ ሀሳቦችን እንዲተገበር ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

35
 በተቋማት ስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች በተቋሞቻቸው የአስቸኳይ ሙስና መከላከል እንዲሰሩ

ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

 ስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች ለተቋሞቻቸው አመራርና ሰራተኞች የስነ-ምግባርና ሞራል

እሴቶች እንዲሁም ሙስና መከላከል ላይ ስልጠና እንዲሰጡ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ፤

3.2 የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ በተመለከተ


 የሁሉም የህዝብ ተመራጮች ፣የመንግስት ተሚዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣የመንግስት ልማት

ድርጅቶችና ህዝባዊ ድርጅቶች የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ሀብትና ጥቅማቸውን


እንዲያስመዘግቡ ማድረግ፤

 የህዝብ ተመራጮች፣የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣የመንግስት ልማት ድርጅቶችና ህዝባዊ ድርጅቶች

ተሚዎች እና ሰራተኞች እንደተመረጡ ፣ እንደተሾሙ ፣ እንደተመደቡና እንደተቀጠሩ

የመጀመሪያ የሀብት ምዝገባ እንዲያካሂዱ


 በ 2013 በጀት ዓመት ሁሉንም የመንግስት ተሿሚና ሰራተኞችን ሀብት ለመመዝገብ በታቀደው

መሰረት ከአፋርና ሱማሌ ክልሎች ውጪ 1,531,057 ሀብት አስመዝጋቢዎችን ሀብት መመዝገብ

ተችሏል፡፡

 እንዲሁም በማንኛውም ምክንያት አገልግሎታቸውን ሲያቋርጡ የአገልግሎት ማቋረጥ ምዝገባ

አካሂደው እንዲለቁ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፤

 የተመዘገበ የሀብት ምዝገባ መረጃ ወደ ዘመናዊ መረጃ ስርዓት ማስገባት

 የተመዘገበን የሀብት ምዝገባ መረጃ ለተደራሽነት ዝግጁ ማደረግና መረጃውን ለመረጃ ጠያቂዎች

ተደራሽ ማድረግ፤

 ሀብት አስመዝጋቢዎች መረጃ ላይ የመረጃ ትክክለኛነት ማረጋገጥ ተገቢ የህግ እርምጃ እንዲወሰድ

ማድረግ፤

3. አስኳቸይ የሙስና መከላከል

አስቸኳይየሙስናመከላከልማለትበተቋማትውስጥሙስናለመፈፀምየሚያስችልዝግጅትእየተደረገመሆኑንሲጠረጠር

ወይምጥቆማሲደርስድርጊቱከመፈፀሙበፊትአስቸኳይየሙስናመከላከልስራበመስራትሂደቱእንዲቋረጥወይምአስፈ

ላጊውንየማስተካከያእርምጃእንዲወሰድየማድረግተግባርነው፡፡

1.1 የአስቸኳይ የሙስና መከላከል ዓላማ

36
የመንግሥትንና የህዝብ ሀብት ለመመዝበር፣ ለማጭበርበር፣ ለመስረቅ፣ ለመዝረፍ በሀሳብ ደረጃ የተጠነሰሰ ወይም

በአሠራር ደረጃ የተዘጋጀ የጥፋት አቅምን በማምከን ሙስናን የወንጀል ድርጊት ከመሆኑ በፊት ወይም አስቀድሞ

የጥፋት አቅሙን ማሰጣት ነው፡፡

1.2 የአስቸካይ የሙስና መከላከል አስፈላጊነት


 በማንኛው ተቋም ውስጥ በህዝብና በመንግስት ሃብት ላይ የማዘዝና የመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጣቸው
አመራርና ሠራተኞች ሙስና ሊፈጸም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንሲገመቱ ወይምሲጠርጥሩ ወይም

አመላካች ነገሮች ሲኖሩ ለአስቸኳይ ሙስና ለመከላከል የሚያስችል የጥቆማ መቀበያ ዘዴን መዘርጋት

ተገቢ በመሆኑ፣

 ሙስና ለመፈፅም የታቀደውን ድርጊት በማምከን የሙስና መከላከል ስራን ውጤታማ ማድረግ
ስለሚያስፈልግ፣

 በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ተግባር ሙስና ለመፈፀም ሃስብ የሌላቸው ግን በእውቀት እና በልምድ
ማነስ ወደ ስህተት የሚገቡ አመራሮችንና ሰራተኞችን እንዲሁም የመወሰን ስልጣን የተሰጣቸውን አካላት

ስህተት ከመፈፃማቸው በፊት ለማስቆም እና አስፈላጊውን ማስተካካያ እንዲያደርጉ ማድረግ አስፈላጊ

በመሆኑ፣

 ሆነ ብለው ሙስና የመፈፀም ሃስብ ያላቸው አካሎች ድርጊቱን ከመፈፀማቸው እና የህዝብ ሃብት
ከመዝረፋቸው በፊት ማስቀረት፤

 ሙስና የመፈፀም ዝግጅት እንዴት እየተደረገ እንደሆነ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማወቅ ለስነምግባር
ግንባታ እና ለስልጠና ግብአት እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤

ስለሆነም የሥነምግባርና የፀረ ሙስና መከታተያ ክፍሎች በተቋም ውስጥ አስቸኳይ የሙስና መከላከል ተግባርን

ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከናወን በቅድሚያ የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡

 የጥቆማ መቀበያ ሣጥኖችን በተቋሙ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች እንዲቀመጥ ማድረግ፡፡ የጥቆማ ሣጥኑ

በቀላሉ ከቦታው የማይነሰና ጠንካራ የመቆለፊያ ቁልፍ ያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡ የጥቆማ መቀበያ ሳጥኑ

ለሥነምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ብቻ አገልግሎት የሚሰጥና ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ ሣጥኑ

ተከፍቶ የሚታይ ሊሆን ይገባል፣

 ከጥቆማ አቅራቢዎች በአካል ጥቆማዎችን ማግኘት፡፡ የሥነምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ቢሮ

በአካል ቀርበው ጥቆማ ለሚሰጡ አቅራቢዎች ወይም የሙስና ጥቆማ ለመቀበል የተመቻቸ ሊሆን ይገባል፡፡

ጥቆማ አቅራቢዎች ሳይሸማቀቁ ነፃነት ተሰምቷቸው የሙስና መከላከል ጥቆማዎችን ለብቻቸው ሆነው

ማቅረብ የሚችሉበትን ቢሮ ማመቻቸት ይገባል፡፡ እንዲሁም የሚቀርቡ ጥቆማዎችን በተደራጀ መንገድ

37
ለመቀበል የጥቆማ የማቅረቢያ ቅጽ በማዘጋጀትና የጥቆማው ቀን፣ ጥቆማው የቀረባበት ዋና ጉዳይ፣

ሙስናን ለመፈጸም እንቅስቃሴ እየተደረገ ያለው የሥራ ክፍል፣ እንደአስፈላጊነቱ የጠቋሚው ስም ያየዘ

መረጃ ወዘተ ተመዝግቦ መያዝ ይገባል፡፡

 በተቋም ደረጃ የሚቻል ከሆነ ነፃ የጥቆማ መቀበያ የስልክ አገልግሎት ማመቻቸትና ማስተዋወቅ ካልሆነ

ደግሞ ጠቋሚዎች ጥቆማዎች ለማቅረብ የሚያስችለውን የስልክ አገልግሎት ቁጥር በተቋም ውስጥ

በሚታዩ ቦታዎች ላይ ሙስና ከተጠያቀችሁ በዚህ የስልክ ቁጥር መጠቆም ትችላለችሁ የሚሉ

መልዕክቶችን በመለጠፍ በግልጽ ማስታዋወቅ፡፡ የቀረበውን ጥቆማ ከላይ በተገለጸ መሠረት የጥቆማው

የቀረባበትን ቀን፣ ጥቆማ የቀረበባትን ጉዳይ ጭብጥ ወዘተ.. በአግባቡ መዝግቦ መያዝ ፡፡

 የሙስና መከላከል ጥቆማዎችን በፖስታ ቤት ወይም በፋስክ ለመቀበል የፖስታ ቤቱንና የፋስክ ቁጥር

ለጠቋሚዎች ግልጽ በሆነ ቦታ ላይ ማስቀመጥ፣ በምን አግባብ ጥቆማ ማቅረብ እንደሚችሉ ማስተዋወቅና

የሚቀርቡትን ጥቆማዎች በአግባቡ መዝግቦ መያዝ፣

o የአመራር ቁርጠኝነት

በየደረጃዉ የሚገኙ የተቋማት አመራሮች ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን የመከላከል ተግባራትን ማከናወን

የስራቸዉ ዋነኛ አካል መሆን አለበት፡፡ በመሆኑም ለሚከናወኑት የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ስራ አስፈላጊዉን

ድጋፍ ማድረግ አለባቸዉ፡፡ ከዚህ አንጻር በስነምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ሥራ ክፍሎች ለሚቀርቡት የአስቸኳይ

ሙስና መከላከል ስራዎች ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች በአፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ድርጊቱ እንዲቆም ማድረግ፣ የስራ

ክፍሎች የተለያዩ ማስረጃዎች ሲጠየቁ እንዲሰጡ ማድረግና የሚሰጡ ዉሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ

ይጠበቅባቸዋል፡፡
የአሰራር ስርአት ጥናት

 የአሰራር ስርአት ጥናት በአንድ ተቋም ውስጥ ሙስናና ብልሹ አሰራር ተከስተው ከፍተኛ ጉዳት

ከማድረሳቸው በፊት ለችግሩ ክፍተት የሚፈጥሩ ሁኔታዎችን መርምሮ በማውጣት የመፍትሄ ሃሳቦችን

በማቅረብ ችግሮች ከወዲሁ እንዲቀረፉ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት በመሆኑ ሙስና ተከስቶ ወይም

የተባባሰ ደረጃ ላይ ደርሶ ሊፈጠር የሚችለውን ኪሳራ በማስወገድ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ከዚህ

በተጨማሪ ግልጽ የሆነ የአሰራር ስርአት በመዘርጋት የሚፈጠሩ የሙስናና ብልሹ አሰራር ችግሮች በቀላሉ

እንዲጋለጡ ለማድረግ ያግዛል፤ የትምህርትና ሌሎች የመከላከል ስራዎች የሚያተኩሩባቸውን የስራ

አካባቢዎች ለመወሰን በማስቻልም ረገድ እገዛ ያደርጋል፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍ በየተቋማቱ ያሉ የሥነምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍሎች በተቋሞቻቸው

ውስጥ የአሰራር ስርዓት ጥናትእንዲያካሂዱ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ነው፡፡ የሥነምግባርና የጸረሙስና

38
መከታተያ ክፍሎች ለሙስና እና ብልሹ አሠራር የሚያጋልጡ አሰራሮችን በመለየት ሙስናን ለመከላከል

የሚያስችሉ መፍትሄዎችን ማቅረብና ተግባራዊነታቸውን በመከታተል ሙስና እና ብልሹ አሠራርን

ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት ይችላሉ፡፡

4. የስነ ምግባርና የሙስና መከላከል ጥናት

ሥራዎችን ማስፋፋት

 የጥቅም ግጭትን መከላከል የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ጥናት ማጥናት፤

 በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በራሳቸው አቅም የጥናትና ምርምር

ስራ እንዲሰሩ ማድረግ፤

 በተቋማት ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሆኑ ተግባር ተኮር 48 የአሰራር ስርዓት ጥናቶችን

በማካሄድ የመፍትሄ ሐሳብ ማቅረብና ማስተግበር፤

 3 ኛውን ሀገር አቀፍ የሙስና ቅኝት ጥናት ውጤትን ለህዝብ ይፋ ማድረግ፤

5.በፀረ ሙስና ትግል የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ

5.1 የህብረተሰብ ተሳትፎ


 ተፈጥሮአዊ የሥራ ባህሪያቸው ከኮሚሽኑ ተልዕኮና ዓላማ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የሲቪክ

ማህበረሰብ ድርጅቶችን ማጠናከር፤

 ለተለዩ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች በኮሚሽኑ ዓመታዊ መነሻ ዕቅድ ላይ የዕቅድ ኦረንቴሽን

መስጠት፣ ዓመታዊ ዕቅድ እንዲልኩና ወደ ስራ መግባታቸውን መከታተልና መደገፍ፤

 ለሀይማኖት ተቋማት የስነ ምግባርና ሞራል እሴቶች ግንባታን መሰረት ባደረገ መልኩ የኮሚሽኑን

ዓመታዊ ዕቅድ እና የሀይማኖት ተቋማት መነሻ ዕቅድ ላይ ኦረንቴሽን መስጠት፣ ዓመታዊ ዕቅድ

እንዲልኩና ወደ ስራ መግባታቸውን መከታተልና መደገፍ፤

 በስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ወቅታዊ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከሀይማኖት ተቋማት

ጋር የጋራ ምክክር መድረክ ማዘጋጀት፤

 በስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ወቅታዊ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከሲቪክ ማህበረሰብ

ድርጅቶች ጋር የጋራ ምክክር መድረክ ማዘጋጀት፤

5.2 የክልል ጉዳዮች ማስተባበሪያ

39
 የማቋቋሚያ አዋጅ 1236/2013 በህዝብ ተወካዮች በማስፀደቅ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን ይህን አዋጅ

ለማስፈፀም የተለያዩ ከ 15 በላይ መመሪያ በማዘጋጀት ስራ ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡

 ክልሎች የህግ ማዕቀፎቻቸው ከፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር ትይዩ በማድረግ

ከአዋጅ እስከ አፈፃፀም መመሪያ ድረስ አስፀድቀው ወደ ስራ እንዲገቡ ድጋፍና ክትትል ማድረግ ፤

 ክልሎች የኮሚሽኖቻቸውን ውስጣዊ መዋቅር ከፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር

ተናባቢና ለስራ ምቹ በሚሆን መልኩ ማደራጀታቸውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

 ክልሎች በዞን፣በወረዳና በከተማ መስተዳደር ደረጃ የሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መምሪያ

ወይም ጽ/ቤት በአዲስ እንዲያደራጁ በአዋጅ፣ደንብና መመሪያ አፀድቀው ወደ ስራ እንዲገቡ

ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

 ክልሎች የ 500 ሀብት አስመዝገቢዎችን መረጃ ትክክለኛነት የማረጋገጥ ስራ መሰራቱን ክትትልና

ድጋፍ ማድረግ፤

 የክልል የሥነ-ምግባርና መከታተያ ክፍሎች ለተቋም ሰራተኞችና አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና

እንዲሰጡ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤


 በሁሉም የክልል ተቋማት የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች፣የሙስና መከላከል የአሠራር ሥርዓት

ጥናት እንዲሠራ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤


 በሁሉም የክልል ተቋማት የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች፣ አስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ

እንዲሰሩ ድጋፍና ክትትልና ማድረግ፤


5.3. ከሙስና ወንጀል ምርመራና ክስ ስራ ጋር በተያያዘ በየክልሎቹ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች ከፖሊስና ጠቅላይ

አቃቢ ህግ ጋር በጋራ ለመገምገም የሚያስችል በየወሩ ሪፖርት መቀበል እና

5.4. ክልሎች ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን በሁሉም የመንግስት ተቋማት የልማት ድርጅትና ህዝባዊ ድርጅቶች

ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ በደመቀ ሁኔታ በተለያዩ ዝግጅቶች እንዲያከብሩ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

40

You might also like