You are on page 1of 1

2/8/24, 11:46 AM Print | AfroTender | Tenders and Bids in Ethiopia.

https://www.AfroTender.com
አዲስ ዘመን አርብ ጥር 24 ቀን 2016ዓ.ም

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አሽተሽፍቁባ/

ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት/2016/001

የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት ለ2016 በጀት ዓመት አገልግሎት | የሚውሉ ሎት 1 የደንብ ልብስ ፤
ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ ፤ ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፤ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ እና አይሲቲ ዕቃዎች፤ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት
ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር
የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

- ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት
ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ለእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ አለባችሁ፡፡

- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን
ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

- የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቦሌ ቅ/ጽ/ ቤት 3ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ቡድን መሪ
ክፍል ቢሮ ቁጥር 36 ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ
ብር) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ፡

- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት፡

- ለሎትı.የደንብ ልብስ ለሎት2. የጽህፈት መሳሪያ ለሎት3 የጽዳት እቃዎች ለሎት4 እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ለእያንዳንዳቸው ብር
5,000.00 (አምስት ሺ ብር) /CPO/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ከጐላጐል ታወር ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ መክሊት ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 -

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ

ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት

https://afrotender.com/tenders-print?id=GUTeIltg8Ls5vE2I73FBnhVCAyFRJQ%3D%3D 1/1

You might also like