You are on page 1of 19

የቆዳና ሌጦ ምርት ለረዥም ዓመታት ከአገሪቷ

ዋና ዋና የውጪ ምንዛሪ ማስገኛ ምርቶች አንዱ


ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ምርቱ ለሃገሪቱ
ከሚያበረክተው ጥቅም አኳያ በልማቱ፣
በቁጥጥሩና በግብይቱ ረገድ የተሰጠው ትኩረት በቂ
ባለመሆኑ የምርቱ አዘገዳጀትና የግብይት ሥርዓቱ
ከወቅቱ የዓለም ገበያ ፍላጐት ጋር አብሮ
መራመድ አልቻለም፡፡
ዳና ሌጦ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ
የሚያስገኝ የእንስሣት ተዋጽኦ በመሆኑ፣
 ጥሬ ቆዳና ሌጦ በአግባብ ካልተዘጋጀና
ሥራ ላይ እንዲውል ካልተደረገ ለብልሽት
የሚጋለጥና በሕብረተሰቡና በእንስሣት ጤና
ላይ ችግር የሚያስከትል በመሆኑ፣
 በጥሬ ቆዳና ሌጦ ንግድ ለተሰማሩ አካላት
የገበያ ዋጋ መረጃ ሣይዛባ በእኩል
እንዲደርስ ማድረግ በማስፈለጉ
የጥሬ ቆዳና ሌጦ አዘገጃጀትና ግብይት
ሥርዓት በጥራት ደረጃ ላይ የተመሰረተ
እንዲሆንና የምርቱ አሰባሰብ፣ አዘገጃጀት፣
አከመቻቸትና አጓጓዝ ሂደት ተሻሽሎ
ከንዑስ ዘርፉ ሊገ የሚገባው ጥቅም
እንዲገኝ ማድረግ በማስፈለጉና፣
ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት አሰጣጥ
1. ማንኛውም ሰው የጥሬ ቆዳና ሌጦ ንግድ
ፈቃድ ከማውጣቱ በፊት ሥልጣን ከተሰጠው
አካል በቅድሚያ የብቃት ማረጋገጫ
ሰርቲፊኬት ማግኘት ይኖርበታል፡፡
2. የብቃት ማረጋገጫውን ሰርቲፊኬት
የሚሰጠው አካል፡-
1.1. ማደራጃው በተገቢ ቦታ መገንባቱን
1.2. ማደራጃው በውስጡ በማኑዋሉ ላይ
የተጠቀሱትን አስፈላጊ ክፍሎች፣
የማደራጃ መሣሪያዎችና መገልገያዎች
በማየት ጠያቂው ማመልከቻውን
በጽሑፍ ባቀረበ በሶስት የሥራ ቀናት
ውስጥ የብቃት ማረጋገጫ
ሰርቲፊኬት የመስጠት ግዴታ
አለበት፡፡
የብቃት ማረጋገጫ ሰጪው መ/ቤት
ጥያቄውን ያልተቀበለው ከሆነ
ያልተቀበለበትን ምክንያትና ውሣኔውን
ማመልከቻው በቀረበ በሁለት ቀናት ባልበለጠ
ጊዜ ውስጥ ለአመልካቹ በጽሁፍ መግለጽ
አለበት፡፡
4. የብቃት ማረጋገጫ ሠርቲፊኬት አሰጣጥና
ዕድሣት ስለ ቆዳና ሌጦ ማደራጃ ግንባታና
ውስጣዊ ይዞታቸው መሟላቸውና ፈቃድ
ጠያቂው ስለሙያው መጠነኛ ግንዛቤ
/ስልጠናና የሥራ ልምድ/ እንዳለው ወይም
የምስክር ወረቀት ባለሙያ ቀጥሮ
እንደሚያሰራ ከተረጋገጠ በኋላ የሚፈፀም
ይሆናል፡፡
5. የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ከላይ
በተ.ቁ 4 ላይ በተገለፀው መሠረት
ውስጣዊ ይዞታቸው መሟላታቸው
ከተረጋገጠ በኋላ በየዓመቱ የሚታደስ
ይሆናል፡፡
6. የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ለሌላ
ሰው ወይም ድርጅት ወይም ማኀበር
ሊተላለፍ አይችልም፡፡
የግንባታ ሥፍራ
የግንባታ ሥፍራ መረጣንና ማደራጃውን
በተመለከተ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ሁኔታዎች
ተግባራዊ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ሀ/ የማደራጀው ግንባታ የከተሞች ኘላን ለዚህ
ተግባር በሚከልለው ቦታ ላይ ወይም፣
ለ/ የከተማ ኘላን ባልተዘጋጀባቸው ከተሞች
የከተማው ማዘጋጃ በሚወስነው ቦታ ላይ
መሠራት አለበት፡፡
ሐ/ የማደራጃው ስፋት በምርቱ አቅርቦትና
በውስጡ በሚሰሩ መገልገያዎች መጠን ላይ
የሚወሰን ሲሆን የግንባታው ሙሉ የአሠራር
ዝርዝር ቢሮ በሚያወጣው ማንዋል መሠረት
ይሆናል፡፡
የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት
ሀ/ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት በማንኛውም
እርከን የኢትዮጵያ ጥራትና ደረጃዎች
ባለሥልጣን በሚያወጣው የጥራት ደረጃ፣
እና
1. ጥሬ ሌጦ በስፋት፣
2. ጥሬ ቆዳ በክብደት ላይ የተመሠረተ
ይሆናል፡፡
ለ/ የጥሬ ቆዳ ክብደት የሚወሰነው እያንዳንዱን
ቆዳ ወይም የጥጃ ሌጦን ለየብቻ በመመዘን
ይሆናል፡፡
ሐ/ ጥሬ ቆዳ ወይም የጥጃ ሌጦ ሲመዘን
የክብደቱ ሽርፍራፊ ቁጥር ከመጣ፣ ለቆዳ 0.5
ኪ.ግ ለጥጃ 0.1 ኪ.ግ ከሆነ እንደ 1 ኪ.ሎ
የቆጠራል፡፡
ጥሬ ቆዳና ሌጦ አጫጫንና አጓጓዝ
ሀ/ ማንኛውም የግብይት ተዋናይ የጉዞ ፈቃድ
ሣይዝ ቆዳና ሌጦን በተሽከርካሪና በእንስሣት
ጭኖ ከማደራጃ ወደ ፋብሪካ ወይም ወደ
አልተፈቀደበት ስፍራ መንቀሣቀስ
አይችልም፣
ለ/ አንድ የቆዳና ሌጦ ግብይት ተሣታፊ
በተሽከርካሪ ቆዳና ሌጦ ጭኖ ከቦታ ቦታ
መንቀሣቀስ ቢፈልግ ከሁለት ቀን በፊት
አግባብ ላለው ባለስልጣን ጥያቄ ማቅረብ እና
ባለስልጣኑም አገልግሎቱን በተጠየቀው ቀንና
ሰዓት የመስጠት ግዴታ አለበት፡
ጥሬ ቆዳና ሌጦ ለማጓጓዝ ተሽከርካሪው
የደረቅ ጭነት ማጓጓዣ መሆን አለበት፣
ከቆዳና ከሌጦውም ጋር ሌሎች ባእድ ነገሮች
መጫን የለባቸውም፣ ጭነቱም በሸራ ወይም
በላስቲክ መሸፈን ይኖርበታል፣
አግባብ ያለው ባለሥልጣን የጉዞ ፈቃዱን
በሶስት ኮፒ በማዘጋጀት እንደርቀቱ ሁኔታ
የጉዞ ፈቃዱን የአገልግሎት ቀናት በመወሰን
ምርቱን መሸኘት አለበት፡፡
ሠ/ ቆዳና ሌጦ የጫነ ተሽከርካሪ በጽ/ቤቱ
የሚሰጠውን ጉዞ ፈቃድ መያዝና
በተቆጣጣሪው ሲጠየቅም ማሣየት
ይኖርበታል፣
ጥሬ ቆዳና ሌጦ ከማደራጃ ወደ ፋብሪካ
ሲጓጓዝ ጭነቱ በተቆጣጣሪው በኘሎምኘ
መታሸግ ይኖርበታል፡፡
ሰ/ በዋናው ተሽከርካሪም ሆነ በተሣቢው ላይ
የሚደረገው የኘሎምኘ ብዛት በስፖንዳው ላይ
ከሚገኙ የማጠፊያዎች ብዛት ማነስ
የለበትም፡፡
ሸ/ በጉዞ ወቅት በጭነቱ፣ በአሽከርካሪ ላይ
ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም ምርቱ
እንዳይበላሽ በአስቸኳይ በአቅራቢያው
ለሚገኘው የሚመለከተው አካል ማሣወቅ፡፡
ማንኛውም ሰው ጥሬ ቆዳና ሌጦ ለማጓጓዝ
ካስመዘገበው የጉዞ መዳረሻ /ፋብሪካ/ ውጭ
ማጓጓዝ የለበትም፡፡
መረጃ ስለመያዝ
ማንኛውም የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ተሣታፊ
በጥሬ ቆዳና ሌጦ አዋጅ አንቀጽ 8 ላይ
የተዘረዘሩትን መረጃዎች መያዝና አግባብ ባለው
አካል ሲጠየቅም መረጃ መስጠት ይኖርበታል፡፡
ቁጥጥር
አግባብ ባለው አካል የተመደበ ተቆጣጣሪ
መታወቂያውን በማሣየት፡-
ሀ/ ለእያንዳንዱ ማደራጃ መለያ ቁጥር ይሰጣል፡፡
ለ/ የሚሰጠውን መለያ ቁጥር በማደራጃው ግቡ
ውስጥ ግልጽ በሆነ ሥፍራ ላይ መለጠፉን
ሐ/ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ተሣታፊው
የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬትና የንግድ
ፈቃድ መያዙንና ማደሱን
መ/ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ሥርዓት
በጥራትና በደረጃ ላይ መሠረት በማድረግ
መካሄዱን፣
ሠ/ ጥሬ ቆዳና ሌጦ ወደ ተከማቸበት ማደራጃ
ውስጥ በመግባት ዝግጅቱን
ረ/ ማደራጃው ፈቃድ ለተሰጠው ተግባር ብቻ
መዋሉን
ተገቢው መዛግብት መዘጋጀታቸውንና
አስፈላጊ መረጃዎችን መያዛቸውን
ይቆጣጠራል፡፡
እርምጃ አወሳሰድ
ሀ/ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ተሣታፊ አዋጁን
ለማስፈፀም የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ
ካላደረገ የንግድ ፈቃዱ እንዲታገድ ይደረጋል
ወይም የብቃት ማረጋገጫው ተሰርዞ የንግደ
ፈቃድ ሰጪው እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡
ለ/ በአገሪቱ ልዩ ልዩ አዋጆች አግባብ ያለው
ባለሥልጣን የሚወስዳቸው አስተዳደራዊ
እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፈቃድ
በሌለው ሰው ተከማችቶ ወይም ሲጓጓዝ
የተገኘ ጥሬ ቆዳና ሌጦ እንደ ኮንትሮባንድ
ዕቃ ተቆጥሮ ይወረሳል፡፡
 ቆዳና ሌጦ ፈቃድ በሌለው ሰው መከማቸቱን
ወይም መጓጓዙን ለጠቆመና ላስያዘ ሰው
ጥቆማው ትክክል መሆኑ ሲረጋገጥ
ከተያዘው ቆዳና ሌጦ ሽያጭ 55%
ለጠቋሚው ክፍያው እንዲፈፀም ይደረጋል፡፡
የኢትዮጵያ ጥሬ ቆዳና ሌጦ አቅራቢዎች ማኅበር ፕሬዝዳን ብርሃኑ አባተ
እንደ ሀገር ወደ 7 ሺህ ጥሬ ቆዳና ሌጦ አቅራቢ ነጋዴዎች እንዳሉ ነግረውናል፡፡
ምርቱን የሚቀበሏቸው ፋብሪካዎች የመቀበል ፍላጎት መቀነስ በገበያ ላይ
ዋጋው እንዲቀንስ እንዳደረገው ጠቅሰዋል፡፡ እንደ ፕሬዝዳንቱ ማብራሪያ
ምንም እንኳን አሁን ችግሩ የተቀረፈ ቢሆንም ቆዳ የተወሰነ ቀን ሳይበላሽ
ለማቆየት የሚጠቀሙበት ጨው አቅርቦት ችግር እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቆዳ ፋብሪካዎች ማኅበራት ዋና ጸሐፊ ዳንኤል ጌታቸው
እንዳሉት እንደ ሀገር 30 የሚሆኑ የቆዳ ፋብሪካዎች ቢኖሩም የገንዘብ፣
የውጭ ምንዛሬ፣ የገበያ፣ የጥራት እና የግብአት ችግር እንዳለባቸው
ተናግረዋል፡፡ እናም በሙሉ አቅማቸው አለመስራታቸው ለቆዳና ሌጦ ምርቱ
ብክነት ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ባላት ሀብት ልክ አልተጠቀመችም፤ ለዚህም በርካታ ምክንያቶች
ይጠቀሳሉ፤ የመጀመሪያው የጥራት ችግር ነው፤ በሀገራችን ያለው ዘልማዳዊ
የእንስሳት አረባብ ዘዴ ለቆዳና ሌጦ ምርቱ ጥራት ችግር እንደዋነኛ ምክንያት
ይጠቀሳል፤ እንስሳቱ በተለያዩ በሽታዎች ይጠቃሉ፤ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው፤
የአመጋገብ ሥርዓታቸው ዘፈቀዳዊ ነው” ሲሉ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለአብነት
ጠቅሰዋል፡፡
ለቆዳና ሌጦው ጥራት የእንስሳቱ እንክብካቤ፣ የጤና ሁኔታ፣ የእርድ እና ቆዳና
ሌጦው የሚፈለግበት ቦታ እስኪደርስ ያለው ሂደት የጎላ ሚና እንዳለው
ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ችግሮች ከዘርፉ ሊገኝ የሚችለውን ጥቅም ማግኘት
አላስቻሉም ባይ ናቸው አቶ ብርሃኑ፡፡ ይህንን የጥራት ጉደለት ለማስተካከል
የተለያዩ የፖሊሲ እርምት እርምጃዎች በመንግስት እየተወሰዱ እንደሆነም
ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በዘርፉ
የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ለባለሞያዎች
ስልጠና ይሰጣል፣ ለፋብሪካዎች የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፣ በዘርፉ
ጥናት በማካሄድ የምክር አገልግሎት ይሠጣል ብለዋል፡፡ ይህንን
መሰረት በማድረግ ባለፉት ዓመታት በሀገር ውስጥ ከሚገኙ
ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች በዘርፉ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ድረስ
ተማሪዎችን ማስመረቅ መጀመሩን አብራርተዋል፡፡ ከ43 በላይ
በቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች በቆዳና ሌጦ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ስልጠና
እየሰጡና በዘርፉ የተማረ የሰው ኃይል እያፈሩ እንደሆነም
ገልጸዋል፡፡
ቆዳና ሌጦ በባህሪው ለረጅም ጊዜ መከማቸት አለመቻሉ
ነጋዴዎች እንዳይገዙና ሻጩም ተቀባይ አጥቶ በየሜዳው
እንዲባክን ሆኗል ብለዋል፡፡

You might also like