You are on page 1of 80

ሳይቃጠል በቅጠል

በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተዘጋጀ

ነሐሴ 2002 ዓ.ም


አዲስ አበባ
ምስጋና

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስና ወንጀል መከላከል ዳይሬክቶ


ሬት የጥናት ቡድኖች እነዚህን ጥናቶች ሲያካሂዱ ውድ ጊዜያቸውን ሰውተው ትብብር
ላደረጉላቸው የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የመሬት አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና
ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ
አፈፃፀም መምሪያ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በብሔራ
ዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ፣ የአዲስ
አበባ ዩኒቨርሲቲ የቤቶች አስተዳደር፣ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ የአዲስ አበባ ጤና
ቢሮ፣ የሸቀጦች ጅምላ ንግድና አስመጪ ድርጅት፣ የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴ
ር እና የውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ኃለፊዎች፣ ሠራተኞችና ባለሙያዎች
ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል።

2
ማውጫ
ርዕስ ገጽ
ምስጋና ----------------------------------------------------------------------------------------------- 3

መግቢያ ----------------------------------------------------------------------------------------------- 4

በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የቦታ ግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና ይዞታ አስተዳደር፣ የመሬት
ልማት ... ---------------------------------------------------------------------------------------------- 5

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በቀረጥ ነፃ መደብሮች ላይ የሚደረግ


የቁጥጥር አሠራር ሥርዓት ------------------------------------------------------------------------- 14

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የግዥ አፈፃፀም ሥርዓት ------------------------------------------- 20

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ የአሰራር ሥርዓት ---------------------- 25

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የብር ኖት ሕትመትና ሳንቲም ቀረፃ አገልግሎት ግዥ


አሰራር ሥርዓት -------------------------------------------------------------------------------------- 31

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ተረሚናል ዕቃዎች አያያዝና ቁጥጥር የአሰራር ሥርዓት
ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ----------------------------------------------------------------------- 36

በብሔራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ


የመንገደኞች የይለፍ ማረጋገጫ አሰጣጥ እና የአገልግሎት ክፍያ ገንዘብ ገቢ አሰባሰብ
የአሰራር ሥርዓት ----------------------------------------------------------------------------------- 42

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቤቶች አስተዳደር አሰራር ሥርዓት --------------------------------- 47

የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የውጭ ሀገር ሕክምና የቦርድ ፈቃድ አሰጣጥ ----------------------- 54

አዲስ አበባ ጤና ቢሮ የግል ሆስፒታሎች፣ ዲያግኖስቲክ ላብራቶሪዎች... የሙያ


ፈቃድ አሰጣጥ --------------------------------------------------------------------------------------- 57

የሸቀጦች ጅምላ ንግድና አስመጪ ድርጅት የሲሚንቶ ሽያጭ አፈፃፀም ሥርዓት ---------- 62

የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የግንባታ ሥራዎች ፈቃድና እድሳት አሰጣጥ የአሰራር
ሥርዓት ---------------------------------------------------------------------------------------------- 64

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ አሰጣጥ ቁጥጥርና ክትትል
የአሰራር ሥርዓት-------------------------------------------------------------------------------------- 68

የውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ አገልግሎት ግዢ እና


ክፍያ አፈፃፀም ሥርዓት ---------------------------------------------------------------------------- 74

3
መግቢያ
የሙስናን ወንጅል በሀገራችን ለመከላከልና ሀገራችን የተያያዘችውን የልማት፣ የዲሞክ
ራሲና የመልካም አስተዳደር ግንባታው ትርጉም ያለው ተጽእኖ ሊያደርግ በማይችልበ
ት ደረጃ ለማድረስ እንዲቻል የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአዋጅ
ተቋቁሞ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ትምህርቶችን ማስፋፋት፣ የሙስናን ወንጀልና
ብልሹ አሠራርን መከላከል እንዲሁም የሙስናን ወንጀል መመርመርና በሙስና ወንጀል
ተሳትፈው የተገኙትንም የመክሰስ ተግባራትን በስፋት በማከናወን ላይ ይገኛል።

ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች እንደሚያመለክቱት የሙስና ወንጀል ተፈጽሞ ወንጀለኞችን


ከማሳደድ ይልቅ ወንጀሉ ከመፈፀሙ በፊት አስቀድሞ መከላከሉ ጠቀሜታው የጎላ
ነው። ምክንያቱም የሙስና ወንጀል በባሕሪው በድብቅ የሚፈፀምና ውስብስብ በመሆኑ
ወንጀለኞቹን አድኖ ለማስቀጣትም ሆነ የተወሰደውን ሃብት ለማስመለስ በርካታ የሰው
ኃይል፣ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት ከመጠየቁም በላይ ከፍተኛ መኅበራዊ ችግርን ያስከትላል።

ስለሆነም ወንጀሉ ከመፈፀሙ በፊት የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ትምህርቶችን በየደረጃ


ው ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች በመስጠት የነቃና ሙስናን ሊሸከም የማይችል ዜጋ
መፍጠር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። በዋነኛነትም በመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና
የልማት ድርጅቶች ውስጥ የሚታዩትን ሙስናና ብልሹ አሠራሮችን ከሥር መሠረታ
ቸው በማጥናት ለዚህም ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩትን ቀዳዳዎችን በመድፈን የሙስናን
ወንጀል መከላከል ጠቀሜታው የጎላ ነው።

ከዚህ አንፃር የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2001 ዓ.ም በተለያዩ


የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ላይ በሙስና ወንጀል መከላክል
የአሠረር ሥርዓት ጥናት አካሂዷል። ጥናት ከተደረገባቸው ተቋማት መካከል የፌደራ
ል ፖሊስ፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ የጥቁር እንበሳ ሆስፒታል፣
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የሥራና ከተማ ልማት
ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም
መምሪያ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጤና፣ የብሄራዊ የመረጃ ደኅንነት አገልግሎት
የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ እና የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር የመሬት
አስተዳደር በዚህ መጽሐፍ ተካተዋል።

በጥናቱ መሠረት በተቋማቱ የተስተዋሉትን ለሙስናና ለብልሹ አሠራር በር የሚከፍ


ቱ የአሠራር ሥርዓቶችን ለመድፈን ኮሚሽኑ የተለያዩ የመፍትሄ ሀሳቦችን አቅርቧል።
ተቋማቱም በቀረበው የመፍትሄ ሀሳብ መሠረት የማስተካከያ ርምጀ በመውሰድ ላይ
እንደሚገኙ ይታመናል። ኮሚሽኑም ጥናት ባደረገባቸው ተቋማት ላይ የትግበራ
ክትትል የሚያደርግ ሲሆን ለውጤታማነቱም ከእነዚሁ አካላት ጋር በጋራ ይሠራል።

በዚህ መጽሕፍ ውስጥ የተመለከቱት የአሰራር ችግሮችና መፍትሄዎች እንደአግባብ


ነታቸው ሌሎችም አካላት ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ የሚል እምነት አለ።

4
በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የቦታ ግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና ይዞታ
አስተዳደር፣ የመሬት ልማት ...

የ ፌዴራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ


ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ውስጥ የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችን ለመዝጋት የችግሮቹን
መንስኤዎች በጥናት በመለየት ለሚመለከተው ተቋም የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረብና
ተግባራዊነቱን ማረጋገጥ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከሚጠቀምባቸው
ስልቶች አንዱ ነው፡፡

የዚህ ጽሁፍ ዋና መነሻ ኮሚሽኑ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የቦታ ግንባታ ፈቃድ
አሰጣጥና ይዞታ አስተዳደር የሥራ ሂደት እና የመሬት ልማት፣ የነዋሪዎች ዳግም
ማስፈርና የከተማ ፕላን ዝግጅት የሥራ ሂደት ላይ በቀረቡ ቅሬታዎች መነሻነት
በኮሚሽኑ የተካሄደ ጥናት ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ አሰተዳደር በመሬት ልማትና አስተዳደር ባለሥልጣን የቦታ፣ ግንባታ


ፈቃድ አሰጣጥና ይዞታ አስተዳደር እና የመሬት ልማት፣ የነዋሪዎችን ማስፈርና
የከተማ ፕላን ዝግጅት አብይ የሥራ ሂደቶች በሚሰጧቸው አገልግሎቶች ላይ እና የሪል
ስቴት ግንባታ በተሰጠባቸውና በቀበሌ አስተዳደር ላይ የሚሰጠውን አገልግሎት በተመ
ለከተ ምልከታም ተከናውኗል፡፡ በጥናቱ በሁለቱም የስራ ሂደቶች የአሰራር ክፍተቶች
የሚታዩባቸውና ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራር እንዲሰፍን የሚጋብዙ በመሆናቸው የታዩትን
ችግሮች ለመቅረፍ የመፍትሄ ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡

በዚሁ መሰረት የተጠናከረ የመሬት የመረጃ አያያዝ እና አጠቃቀም ሥርዓት


አለመኖር የጥናት ቡድኑ ከለያቸው ችግሮች የመጀመሪያው ነው፡፡ የመረጃ
አያያዝ እና አጠቃቀምን በተመለከተ ቦታዎች እንደመሬቱ ተፈላጊነት ለኢንቨስትመንት
ወይም ለንግድ ዘርፍ፣ ለሪል ስቴት፣ ለከተማ ግብር እና ለልዩ ልዩ
ማህበራዊ ጉዳዮች ሊውሉ የሚገባቸው ቦታዎች አስቀድሞ ባለመለየታቸውና ባለመያዛ
ቸው ውስን የሆነውን መሬት ለብክነት ከመዳረጉም ባሻገር ፍትሀዊነት ለጎደለው የቦታ
አሰጣጥና አሰራር በር ከፍቷል::

ይህን ችግር ለመፍታት በከተማ አስተዳደሩ ያለውን የመሬት ሃብት በአግባቡ በመያዝ
በአካባቢው ካሉ የክልል መስተዳድሮች እና ገበሬዎች ጋር በመደራደር /Land -Sharing
System/ በመጠቀም የመሬት ባንክ /Land-stock/ እንዲጨምር ማድረግ ወሳኝ መሆ
ኑ ተጠቁሟል፡፡ መረጃዎችን ለማሰባሰብ የመሬት ቆጠራ ማካሄድን በከተማዋ ያለውን
የመሬት ሁኔታን ዘመናዊ ለማድረግ በቂ መረጃ ማሰባሰብ ያለውን የመሬት ሀብት
በቁጠባ ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑ በጥናት ቡድኑ በመፍትሔነት ተጠቁሟል፡፡

አሰራራቸውን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲደገፍ ካደረጉ የከተማ አስተዳደሮች ልምድ


በመቅሰም ተግባራዊ ማድረግ የበለጠ ጠቃሚ በመሆኑ አስተዳደሩ በቂ ትኩረት

5
በመስጠት በአግባቡ ሊከታተለውና ወቅታዊ ምላሽ ሊሰጠው የሚገባ ነው:: የመሬት
ልማትና አስተዳደርን ለመምራት የወጡ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በአግባቡ
አለመፈጸም በጥናቱ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠ ነበር፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር በቻርተር
አዋጅ ቁጥር 416/97 ከተቋቋመበት ጀምሮ የመሬት ልማትና አስተዳደርን በተመለከተ
ለማስፈፀሚያ በርካታ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን አውጥቷል፡፡ ነገር ግን
የመሬት ልማትና አስተዳደር ባለሥልጣን በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዙሪያ የወጡትን
አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት በማድረግ ሥራውን በአግባቡ አለመከናወኑ
ን ጥናቱ ያመለክታል፡፡ ባለሥልጣኑ የመሬት ልማትና አስተዳደርን በተመለከተ የወጡ
አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን የመሠረታዊ የአሰራር ሥርአት ሂደት ለውጥ መሠረት
አድርጎ ከአዲሱ አደረጃጀትና አሰራር ጋር በሚጣጣም መልኩ የሚሻሻሉ የህግ ማዕቀፎችን
በማሻሻል ተግባራዊ በማድረግ አፈጻጸማቸው በየጊዜው እየተገመገመና ኦዲት እየተደረገ
ለሚከሰቱ ችግሮች ወቅታዊ እርምጃ በመውሰድ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ማስፈን እንዲ
ሁም በወጡና በሚወጡ ሕጎችና መመሪያዎች ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥና የማዳበር ሥራ
ቀጣይነት ባለው መልኩ ማከናወን ችግሩን ሊፈቱ የሚችሉ መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል፡፡

በአስተዳደሩ የሊዝ ደንብ መሠረት የተቋቋመው የሊዝ ቦርድ ተግባርና ኃላፊነቱን


በአግባቡ አለመወጣት የጥናት ቡድኑ የተመለከተው ሶስተኛው ችግር ነው፡፡ በድሬዳዋ
አስተዳደር በሊዝ የሚሰጡ ቦታዎችን በተመለከተ አግባብ ያለው ተጠያቂነትና ግልፅ
ነትን የተከተለ አገልግሎት ለመስጠት ያስችል ዘንድ የሊዝ ቦርድ ተቋቁሟል፡፡ የሊዝ
ቦርዱ በመሬት ልማትና አስተዳደር አማካኝነት የሚቀርብለትን የውሳኔ ሃሳብ በመመ
ርመርና የመጨረሻ ውሳኔ በመስጠት ረገድ የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባር በአግባቡ
ባለመወጣቱ የሊዝ ቦታ አሰጣጥ ስርአቱ በተመለከተ ወጥነት የጎደለው መሆኑ፣
መሬት ለልማታዊ ባለሀብቶች ከመስጠት ይልቅ ለማልማት አቅም ለሌላቸውና መሬት
ለሚሸጡ ግለሰቦች መስጠት፣ ምትክ ቦታ ሲጠየቅ ባለሥልጣኑ ማዘጋጀት ሲገባው
ጠቁሙ ማለትና የተጠቆመውንም ቦታ ጥያቄውን ላላቀረበ ባለሀብት አሳልፎ መስጠ
ት፣መሬትን በሊዝ በድርድር ምንም ቅድመ ሁኔታ ላላሟሉ በዝምድናና በመሳሰሉት
ግንኙነቶች መስጠት፣ የሊዝ ዋጋ ግምት በጣም ዝቅተኛ እንዲሆን ማድረግ፣ በአንድ
አካባቢ በአንድ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ቦታዎች የተለያየ የሊዝ ዋጋ ማውጣት፣ አቅም
እያላቸው መሬት ያላገኙ ልማታዊ ባለሀብቶች ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ጥረት
አለማድረግ ከታዩት ችግሮች ውስጥ ይጠቀሳሉ ፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት በሊዝ የሚሰጡ ቦታዎች የጨረታ አሠጣጥና የመነሻ


ዋጋ አፈፃፀም መመሪያን መሠረት በማድረግ ቦርዱ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት
በአግባቡ መወጣት፣ ባለሀብቱንና ህዝቡን በማወያየት ለሚታዩ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ
መስጠት እንዲሁም የሥነ ምግባር ጉድለት በሚታይባቸው ሠራተኞች ላይ ትምህርት ሰጪ
የሆነ ርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን የጥናት ቡድኑ ጠቁሟል፡፡ ይህ አሰራር የሥራ
ኃላፊዎችን የሥራ መደራረብና ተጨማሪ ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም የኃላፊዎችን ጣልቃ
ገብነት ከመከላከሉም በላይ ግለጽነትንና ተጠያቂነትን የተላበሰ የአሰራር ስርአት ተከትሎ
እንዲተገበር እገዛ ያደርጋል::

የጥናት ቡድኑ በአራተኛ ደረጃ ያስቀመጠው የአሰራር ችግር በአስተዳደሩ በሊዝ

6
የሚሰጡ ቦታዎችን ለመሸጥ የግልፅ ጨረታ ዘዴን አለመጠቀም ነው፡፡ የከተማ ቦታ በሊዝ
እንዲያዝ የሚፈቀደው በጨረታ መሆኑንና ለጨረታ የሚቀርቡ ቦታዎችን የተመለከተ
ዝርዝር ጉዳዮችን የአፈጻጸም መመሪያው ይገልፃል፡፡ ነገር ግን በከተማዋ በሊዝ የሚሰ
ጡ ቦታዎች የመንግሥትንና የህዝብን ተጠቃሚነት የማያረጋግጡና በአብዛኛው የግልፅ
ጨረታ ዘዴን መሰረት ያደረጉ አይደሉም፡፡

ለአብነት ያህል በግልፅ ጨረታ መሰጠት የሚገባውን ለንግድ ሥራ የሚሆን /Com-


mercial Area/ አንደኛ ደረጃ ቦታ ካለ ጨረታ ከሊዝ ነፃ ተጨማሪ ካሬ ሜትር
በማካተት መስጠት፣ ለአንድ ግለሰብ በቀጥታ በሊዝ የአቅም ማሳያ ሳይኖርና የሊዝ ቦርድ
ውሳኔ ሳይሰጥ፣ የሊዝ ቦርድ ሰብሳቢ በሌሉበትና ውክልናም ባልተሰጠበት ሁኔታ
በሜትር ካሬ በብር 184 ሂሳብ እስከ 11,433 ካሬ ሜትር መሬት መስጠት የመሳሰሉት
ችግሮች ተስተውለዋል፡፡

ይህ አሰራር ከመሬት ሽያጭ ሊገኝ የሚገባውን ጥቅም ከማሳጣቱም ባሻገር ወጥነት


ለጎደለውና በጥቅም ላይ ለተመሰረተ ግንኙነት ሊዳርግ ይችላል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታ
ት በከተማው ያሉ በሊዝ ሽያጭ የሚውሉ ቦታዎች የሚገኙባቸውን አካባቢዎች መሠረት
በማድረግ ደረጃ በማውጣት በአንደኛ ደረጃ ላይ ያሉ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ዘዴ
ብቻ በመጠቀም የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም ፍላጎት ሊያስጠብቅ የሚችል አሰራር
መዘርጋት፣ በሊዝ ሽያጭ ሊውሉ የሚችሉ ቦታዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲው
ሉ በሚያስችል መንገድ ለንግድ፣ ለማህበራዊ አገልግሎቶችና ለሌሎች የልማት ዘርፎች
ሊውሉ የሚችሉትን አስቀድሞ በመለየት በድርድር ወይም በውስን ጨረታ ዘዴ ለሽያጭ
ማቅረብ በጥናቱ በመፍትሄነት ተጠቁሟል::

በዚህ አሰራር የጨረታ ሂደቱ ተጨማሪ ጊዜና ወጪ የሚጠይቅ ቢሆንም የሊዝ አፈጻ
ጸም ከመሬት ዝግጅት እስከ ሽያጭና ርክክብ ድረስ ያለው የስራ ሂደት በእቅድና በፕሮ
ግራም እንዲከናወን ለክትትልና ቁጥጥር የተመቻቸ ይሆናል፡፡ በተጨማሪ የሊዝ ቦታ
ሽያጭ አፈጻጸምን ህግና መመሪያ መከተሉ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን የተላበሰ
አሰራር ሥርአት እንዲዘረጋ እና አልሚው ቦታውን ለወሰደው ዓላማ በአግባቡ እንዲጠ
ቀምበት ስለሚያደርግ ሊፈጸሙ የሚችሉ የሙስና ወንጀሎችን ለመከላከል ያስችላል፡፡

በሊዝ መሬት ለሚጠይቁ አልሚዎች ቅድመ ሁኔታ ሳያሟሉ መስጠት ጥናቱ ያመለከ
ተው ስድስተኛው ችግር ነው፡፡ ከመሬት ልማትና አስተዳደር ባለሥልጣን በሊዝ መሬት
የሚወስዱ ባለሀብቶች በተጫራቾች መመሪያ መሰረት እንደ ሽያጭ ውሉ ሊለያይ ቢችል
ም ቢያንስ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ትክክለኛና ልማታዊ የሆኑ ባለሀብቶች ፕሮፖዛል አቅርበውና ቅድመ ሁኔታዎችን


አሟልተው መሬት የማያገኙበት ሁኔታ ሲኖር በሌላ በኩል ደግሞ የውል ስምምነት
አስፈጻሚ ባለሙያዎች ቅድመ ሁኔታ አለመሟላቱን እያሣወቁም በሚፈጠር ጫና
አንዳንዶች መሬት ያለአግባብ እንዲያገኙ ሲደረግ ይታያል፡፡ በሊዝ ቦርድ መወሰን
የሚገባው ጉዳይ ሳይወሰን ተወስኗል ብሎ ለውል መላክና የውል ስምምነት ሠነድ
መፈረም፣ ባለ ንብረት ላይ በተሰጠው ውክልና ያለ ኢንቨስትመንት ፈቃድ መሬት

7
መስጠት ሁኔታዎች ተከስተዋል፡፡

የጥናት ቡድኑ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመገንዘብ እንደተቻለው አስተዳደሩ መሬት


ከሰጣቸው ከ552 አልሚዎች መካከል 91(16%) ብቻ ቅድመ ሁኔታውን አሟልተው
የሊዝ መሬት የተረከቡ ሲሆን 84% ያህሉ ቅድመ ሁኔታን ያላሟሉ ሆነው ተገኝተዋ
ል፡፡ ከዚህ አንፃር በሊዝ የመሬት አሰጣጥ ሥርዓቱ ፍትሃዊነት የጎደለውና ለሙስና እና
ብልሹ አሠራር የተጋለጠ ነበር ለማለት ይቻላል፡፡

ማንኛውም መሬት ይሰጠኝ ባይ ባለሃብት ቦታውን በትክክል ማልማት የሚችል


መሆኑን ለማወቅ የሚረዱና በግልጽ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸውን
በማረጋገጥ ቦታ መስጠት፣ የተከናወኑ ስራዎችን በየጊዜው በመገምገምና ችግሮችን
በመለየት ወቅታዊ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል:: በጥናቱ እንደተመለከተ
ው ይህ አሰራር የከተማዋን ቦታ አሰጣጥ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን የተላበሰ እንዲሆን
በማድረግ ልማታዊ ባለሀብቶችን የሚያበረታታና የከተማዋን እድገት በማፋጠን ረገድ
ጉልህ ሚና ይኖረዋል::

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተጭበረበሩ ማስረጃዎች ሊቀርቡ የሚችሉበትን ሁኔታ እና በሌ


ሎች አካላት የሚሰጡ ማስረጃዎችም ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት በአግባቡ
እንዲቀርቡ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትኩረት ሰጥቶ በቅንጅት መስራት
ችግሩን ለመፍታት አስፈላጊ ነው፡፡በጥናቱ የተመለከተው ስድስተኛው ችግር በየጊዜው
የተመደቡ አንዳንድ ኃላፊዎች ሥልጣናቸውን አለአግባብ መገልገል ነው፡፡ በአስተዳደሩም
መሬትን በተመለከተ እና አጠቃላይ የከተማውን ዕድገት ለማፋጠንና ልማትን ለማምጣት
የሚያስችሉ ሥርዓቶች ተዘርግተዋል፡፡ ነገር ግን በተለያየ ወቅት በከተማ አስተዳደሩ
በተለያየ ደረጃ በኃላፊነት ላይ የተመደቡ ግለሰቦች የተቀመጡ ግልጽ አሠራሮችን ተከትለው
በመስራት የመንግሥትንና የሕዝብን ጥቅም ከማስጠበቅ ይልቅ ስልጣናቸውን ያለገደ
ብ በመጠቀም ህገወጥ ተግባሮችን መፈጸማቸውን የጥናት ቡድኑ ለመገንዘብ ችሏል፡፡

ለአብነት ነዋሪዎችን ህገወጥ ናችሁ በማለት እንዲነሱ ማድረግና መሬት ለራስ


በመያዝ የመኖሪያ ቤት መገንባት፣ ግልጽነት የሌለው የመንገድ ቅየሳና የማስተር ፕላን ክለሳ
ማካሄድ፣ በሪል ስቴት ስም ፕሮጀክት ፕሮፖዛል የሌላቸውና የጊዜ ገደቡ ያለፈ
የመከነ ካርታ በኃላፊዎች ትዕዛዝ እንዲቀጥል ማድረግ የተስተዋሉ ችግሮች ናቸው፡፡
በከፍተኛ ወጪ የተዘጋጀን የመንገድ ዲዛይን ተገቢውን ሂደት ባልተከተለ መልኩ እንዲቀየር
ማድረግ፣ በሊዝ ቦርድ የተወሰኑ ውሳኔዎችን በመሻር የመንግስትን ጥቅም የማያስጠ
ብቁ ተግባራትን መፈፀም፣ የሊዝ ቦርድ የሰጠውን ካሬ ሜትር በማስበለጥ ከሊዝ ነፃ
እንዲሰጥ ማድረግ (ለ1ሺ ካሬ ሜትር 4ሚሊዮን ያቀረበ አልሚ እያለ ካርታው እንዲ
መክን በማድረግ ቀጥታ የሊዝ ቦርዱ ከወሰነለት በተጨማሪ 43ዐ ካሬ ሜትር ቦታ
በማካተት በአጠቃላይ 143ዐ ካሬ ሜትር አቅም ማሳያ 5ዐዐ ብር አስይዞ መንገድ ዳር
አንደኛ ደረጃ ቦታ በ184 ብር በካሬ ሜትር መስጠት) የመሳሰሉት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ቀደም ሲል በከተማ አስተዳደሩ ያሉ የሥራ ኃላፊዎች


ሥራቸውን በተሰጣቸው ስልጣንና ኃላፊነት መሠረት ብቻ ደንብና መመሪያ

8
ተከትለው መሥራት፣ አለአግባብ የተወሰዱ እርምጃዎች እንዲስተካከሉ ማድረግ፣
የሚሰጡ ውሳኔዎችን በየጊዜው መገምገምና ሪፖርት እንዲቀርብ መጣር፣
ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን ማመላከት እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በተፈጸመ ህገ
ወጥ ተግባር ላይ አስተማሪ የሆነ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡

የተነሺዎች የካሳ ክፍያ አፈጻጸም ደንብንና መመሪያን የተከተለ አለመሆን በጥናቱ


በሰባተኛ ደረጃ የተቀመጠ ችግር ነው፡፡ ለህዝብ ጥቅም እና ለልማት ተግባር ሲባል
የመሬት ይዞታ እንዲለቀቅ ሲደረግ ለባለ ይዞታው ካሣ የሚከፈልበት ሥርዓት አለ፡፡ ይህ
አሠራር ሲተገበር የካሣ ክፍያው የሚያካትታቸው የግንባታ ባለቤቶች /የግል ባለይዞታዎች፣
የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣የቀበሌ ቤት፣ የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ቤቶች/ እና
የቤት ካሣ ክፍያው ሲፈፀም ሊሟሉ የሚገባቸው የንብረት ማረጋገጫና ዝርዝር ቅድመ
ሁኔታዎች መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁኔታዎች በአግባ
ቡ ክትትል ስለማይደረግባቸው የካሣ ክፍያ በቀበሌና በኪራይ ቤቶች ለግለሰቡ /ለነዋሪው/
ለተከራዩ መክፈል፣ በተነሺዎች ላይ ያልነበረ ሰው በማካተት የካሣ ክፍያ እንዲሰጠው
ማድረግ፣ለተነሺዎች ተመሳሳይ ቦታ መስጠትና የካሣ ክፍያ መፈፀም፣ የባለንብረቱ/ባለ
ቤቱ ማስረጃ ሳይጣራና ሳይለይ ለግለሰብ ክፍያ መፈፀም፣ የካሣ ክፍያ ሳይከናወን አንደ
ኛ ደረጃ የንግድ ቦታን መስጠት እንዲሁም የንብረት ግምት በሚሠራበት ወቅት አግባብ
ያለው ማጣራት አለማድረግና የጥቅም ግንኙነት ላይ በመመስረት የተጋነነ ዋጋ ማስላት
ን የመሳሰሉት ችግሮች መኖራቸውን በጥናት ቡድኑ ተመልክቷል፡፡

ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎች መሰል የሥነምግባር ግድፈቶች አንዳንድ ግለሰቦች


ከአንዳንድ የመሬት ልማትና አስተዳደር ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር
በሚፈጥሩት ልዩ የጥቅም ግንኙነት አላግባብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዳስቻላቸው በጥና
ቱ ወቅት የታዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በአስተዳደሩ የካሣ ክፍያና የምትክ ቦታ አሰጣጥ የአፈፃፀም መመሪያና ከሌሎች አካላት


ጋር የተፈጸሙ የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን መሠረት በማድረግ ለልማት ከሚፈለገ
ው ቦታ ለሚነሱ ተነሺዎች ለሚፈፀም የካሣ ክፍያ የሚወሰድ መረጃ በቅድመ ሁኔታዎ
ችና ዝርዝር መሠረት /መረጃ አሰባሳቢው አካል የሚሰበስባቸውን መረጃዎች ከተነሺዎች
ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመና እውነተኛ መሆኑን ማረጋገጥ፣ በዚህም ተጠያቂነት
ና ኃላፊነት እንዲወስድ ማድረግ፣ በመንገድ ልማት ምክንያት የሚነሱ ሲሆን ከመንገ
ዶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር መስራትና በተጨማሪ ያለውን የአፈጻጸም መመሪያ
በማሻሻል/ የተሻለ ሥርአት እንዲኖር የተሟላና የተረጋገጠ መሆኑን በማጣራት የካሣ
ክፍያ መፈጸም ያስፈልጋል፡፡ ከዚሁ ጋር ቀደም ሲል በተሳሳተ መረጃ የተፈፀሙ የካሳ
ክፍያዎችን በማጣራት የማስተካከያ እርምጃ መውሰድም ጠቃሚ መሆኑን የጥናቱ
ውጤት ያመለክታል፡፡

ይህ አሰራር ተጨማሪ ጊዜና አስተዳደራዊ ወጪ የሚያስከትል ቢሆንም ግልጽነትንና


ተጠያቂነትን የተላበሰ የአሰራር ስርአት ተከትሎ እንዲተገበር እገዛ ያደርጋል፤ ለሚታ
ዩ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ከመስጠቱ ባሻገር የተመደቡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከግል
ስሜታቸውና አድሏዊ አሰራር ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ያስችላል ፡፡

9
ጥናቱ ያመለከተው ስምንተኛው የአሰራር ችግር ለኢንቨስትመንት በሚሰጡ መሬቶች
ላይ ያለው ክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ ደካማ መሆን ነው፡፡ በአስተዳደሩ ኢንቨስትመ
ንት ላይ በተለያዩ ዘርፎች በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት እና በከተማ ግብርና
የኢንቨስትመንት መስክ ለመሰማራት መሬት የወሰዱ የግል ባለሀብቶችን በተመለከተ
ሊደረግ የሚገባው አግባብ ያለው ክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ ስለማይከናወን በኢንቨስትመንት
ስም መሬት ለመውሰድና ለማልማት በተደጋጋሚ የተወሰኑ ባለሀብቶች መሬት ወስደው
በመሸጥ የሚበለጽጉበት አሠራር ይታያል፡፡ ይህ አሰራር ልማታዊ ባለሀብቶችን ማዕከል
ያደረገና የከተማዋን ኢንቨስትመንት የሚያሳድግ ሳይሆን የጥቅም ግንኙነትን መሰረት
ላደረገ አሰራር በመጋበዝ ሙስናና ብልሹ አሰራር እንዲስፋፋ በር ይከፍታል፡፡

እንደ ጥናቱ መሬት ለማልማት የሚወስድ ባለሀብት በመጀመሪያ የግንባታ አቅም


ማሳያ ገንዘብ ያለው፣ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ያወጣ፣ ሌሎችን ቅድመ ሁኔታዎችን ያሟላ
እንዲሆን በማድረግ እና የአቅም ማሳያውን ገንዘብ ከሚከናወነው የግንባታ እንቅስቃሴ
አንፃር ግምገማ እየተደረገበት የሚለቀቅበትን አሠራር መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ አልሚ
ዎች ቦታዎችን ሲወስዱ ግንባታውን ለመጀመርና ለማጠናቀቅ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ
መሠረትና በገቡት የውል ስምምነት ሠነድ አማካኝነት ተገቢው ክትትል፣ ቁጥጥርና
ድጋፍ እንዲደረግላቸው በማድረግ መሥራት ችግሩን ሊቀርፈው እንደሚችል በጥናቱ
ተመልክቷል፡፡ ይህ አሰራር የከተማዋን ቦታ አሰጣጥ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን በተላ
በሰ አሰራር እንዲተገበር ስለሚያደርግ ልማታዊ ባለሀብትን በማበረታታት የከተማዋን
እድገት ለማፋጠን ያስችላል፡፡

ጥናቱ በዘጠነኛ ደረጃ ያመለከተው ችግር የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አሰጣጥ
ተጠያቂነትንና ግልፅነትን የተከተለ አለመሆን ነው፡፡ የመሬት ልማትና አስተዳደር
ባለሥልጣን ከሚሰጣቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ የቦታና ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ
አሰጣጥ ነው፡፡ ይህን ሥራ በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት ተጠያቂነትና ግልጽነትን የተከተለ
ባለመሆኑ በማህበር ተደራጅተው መሬት ለመውሰድ ጥያቄ ላቀረቡ ተገልጋዮች
በአንድ ሰው ስም ካርታ በመስጠት ህገ ወጥ ተግባር መፈፀም፣ በአንድ ቦታ ላይ ለሁለት
ሰዎች ካርታ መስጠት፣ መሀንዲሶች ሲለኩ ባዶ ቦታ መተውና በህገወጥ መንገድ
እንዲያዝ በሚያመች ሁኔታ ካርታ መስራት፣ በካርታ ላይ ካርታ በመስራት፣ ተገልጋ
ዮችን ለአላስፈላጊ ችግር መዳረግና ፍትህን ማዛባት፣ የመንግስትን ቤት ተከራይተው
ለሚኖሩ ግለሰቦች ማስፋፊያ አግባብ በሌለው መንገድ መስጠት፣ የቀበሌ ቤት በግል ይዞታ
ማዞር ለዚህም የግል ማህደር ማጥፋትና በግለሰብ እንዲቀየር ማድረግ፣ ክፍትና ለመናፈሻ
የሚሆኑ ቦታዎችን ለግለሰቦች በመስጠት የይዞታ ማረጋገጫ እንዲኖራቸው ማድረግ፣
ለአንድ ግለሰብ ከአራት ቦታ በላይ ለመኖሪያ ቦታ መስጠት፣ በውጭ ድርጅቶች
ለቆሻሻ ማስወገጃ የተሠራውን ቦታ በጥቅማጥቅም ለግለሰብ መስጠትና በአካባቢው ነዋሪ
ላይ የጤናና ማህበራዊ ችግሮችን ከሚያስከትሉ ነገሮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ስለሆነም ትክክለኛ የሆነ የቦታና ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አሰጣጥ ሊያሰፍን በሚችል
መልኩ ደንብና መመሪያን መሠረት አድርጎ የሚከናወን ባለመሆኑ ከዚህ ጋር
ተያይዘው ለሚከሰቱ ሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ ነው፡፡በመሆኑም ይህን ክፍ
ተት ለመሙላት ተገልጋዩን ፍትሃዊና በአግባቡ ለማስተናገድ እንዲቻል ደንብና

10
መመሪያን መሠረት ያደረገ የቦታ ይዞታና ካርታ ማረጋገጫ አሰጣጥ እንዲተገበር ማድረግ፣
ቀደም ሲል አላአግባብ የተሰጡ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎችን በማጣራት አግባብ
ያለው እርምጃ መውሰድ፣ ተፈጻሚነቱን በየጊዜው በመከታተልና በመገምገም ለሚፈ
ጠሩ ችግሮች ወቅታዊ እርምጃ መውሰድና በአገልግሎቱ ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ
ማሳደግ ተገቢ መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል:: በከተማው ያሉትን ህገወጥና ሠነድ
አልባ ይዞታዎች ምዝገባና ይዞታ ማስረጃ የመስጠት ሥራና አዘገጃጀት ትክክለኛ
መረጃዎችን መሠረት ያደረገ አለመሆን በጥናቱ የተመለከተው አስረኛ ችግር ነው፡፡
በከተማው በተለያዩ ጊዜያት ህገ-ወጥ እና ሠነድ አልባ ይዞታዎች በሬጉላራይዜሽን ፕላን
መሠረት በቀበሌ ደረጃ በአጥኚ ድርጅት በተዘጋጀው አማካኝነት አስተዳደሩ የሚያጸድ
ቀው ህገወጥ አሰፋፈሩን ሥርዓት የሚያስይዝበት ፕላን አለው:: ይሁን እንጂ አተገ
ባበሩ ትክክለኛና እውነተኛ መረጃን መሠረት ያደረገ ባለመሆኑ ሰነድ አልባና ህገወጥ
ቤቶች ተሰርተው የቆዩ በማስመሰል ካርታ በገንዘብ እንዲዘጋጅላቸው ማድረግ፣
የሠነድ አልባ ቤቶችን በተመለከተ የመንደር ኮሚቴ ስልጣናቸውን አለአግባብ መጠቀም፣
ለሀሰተኛ ሰነድ የተጋለጠ መሆን፣ የሀሰተኛ ሠነድ ባለጉዳዩ እንዲያዘጋጅ የተመቻቸ
ሁኔታ መኖር፣ በቀበሌ በአግባቡ የማረጋገጥ ሥራ አለማከናወን፣ ፍ/ቤት የባለቤትነ
ት ማረጋገጫ ሲጠይቅ አንዳንድ ቀበሌና የመሬት አስተዳደር ባለሥልጣናት ሀሰተኛ
መረጃ በመስጠትና ውሳኔዎችን በማዛባት ካርታ እንዲያገኙ ማድረግ፣ የተጭበረበረ
ሠነድ ማዘጋጀትና ህግን የማስከበር አቅም ደካማ መሆን በአሠራሩ ውስጥ ይታያል፡፡
ይህም በከተማዋ የልማት እንቅስቃሴ ላይ ከሚያሳድረው አሉታዊ ተጽእኖ ባሻገር
ግልጽነት የጎደለውና በህገ ወጥ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡

የአሠራር ሥርዓት ክፍተቱን ለመዝጋት በከተማዋ በተለያዩ ጊዜያት የተገነቡ ሠነድ


አልባ ቤቶችን ህጋዊ ለማድረግ ትክክለኛና እውነተኛ መረጃን መሠረት ያደረገ አሠራር
መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ እንዲሁም ባለጉዳዩ ከመሬት አስተዳደርና ቀበሌ ፎርሙን ወሰዶ
በመንደር ኮሚቴ እንዲያስሞላ የሚያደርገውን አሠራር ማስቀረትና ሁሉንም ህገወጥና
ሠነድ አልባ ቤቶችን አንድ ጊዜ ጥናት በማካሄድ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ግብር የተገበ
ረበትን፣ ውሃ፣ የመብራትና ስልክ የገባባቸውን ሰነዶች በማሰባሰብ ማጣራት ተገቢ ነው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም ቦታው የመኖሪያ ቤት መሆኑን በ GIS በማስተር ፕላኑ በማረጋገ
ጥ የካዲስተር ማረም ስራ በአግባቡ በመስራት በቀበሌና በመሬት ልማትና አስተዳደር ባለ
ሥልጣን ደረጃ መረጃ እንዲያዝ በማድረግ ትክክለኛ የማረጋገጥ ሥራ ማከናወን ይገባል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የመረጃ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ አሰራር መከተል ያስፈልጋል::

በመፍትሄነት የተቀመጠው አሰራር በየደረጃው ያሉ ሠራተኞችና ኃላፊዎች የሚያከ


ናውኑትን ሥራ ተጠያቂነት እንዳለው ጠንቅቀው በማወቅ እንዲሰሩና የሥነምግባር
ጉድለት ባለባቸው ሠራተኞችና ኃላፊዎች ላይ የሚወሰድ አስተዳደራዊ እርምጃ ለሌሎች
አስተማሪ ስለሚሆን ህገ ወጥነትን ለመከላከል ያስችላል፡፡

በጥናቱ በአስራ አንደኛ ደረጃ የተመለከተው ችግር አግባብ ያለው የቅሬታ አቀራረብና
አፈታት ሥርአት አለመዘርጋት ነወ። በመሬት አስተዳደር ላይ ተገልጋዩ ቅሬታውን
የሚያቀርብበትና የሚፈታበት ሥርአት በአግባቡ ስላልተዘረጋለት ለእንግልት እና
ለአላስፈላጊ ወጪ መዳረግና ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት ህገወጥ በሆነ መንገድ

11
የማግኘት አሰራርን ይፈጥራል፡፡

ተገልጋዩ ቅሬታውን የሚያቀርብበትና የሚፈታበት ሥርአት እንዲዘረጋለት ማድረግ አስፈላጊ


መሆኑን ጥናቱ ይጠቁማል:: ይህ አሰራር ወቅታዊ መፍትሄ ለመስጠት፣ አግባብ ያለው የቅሬ
ታ አቀራረብና አፈታት ሥርአት እንዲኖር፣ አድሏዊ አሰራርን ለማስቀረት፣ አገልግሎት አሰ
ጣጡን ቀልጣፋ በማድረግ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን የተላበሰ አሰራር እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

የመሬት ልማትና አስተዳደርን ለመምራት የወጡ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን


በአግባቡ ለፈጻሚ አካላት አለማሳወቅ ጥናቱ ያመለከተው አስራ ሁለተኛው የአሰራ
ር ክፍተት ነው፡፡ የመሬት ልማትና አስተዳደርን በተመለከተ በርካታ አዋጆች፣ ደንብና
መመሪያዎች ወጥተዋል፡፡ የመሬት ልማትና አስተዳደር ባለሥልጣን በሚሰጣቸው አገል
ግሎቶች ዙሪያ የወጡትን አዋጆች፣ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት በማድረግ ሥራውን
በአግባቡ ለማከናወን ፈጻሚ አካላት በቂ ግንዛቤ በማግኘት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል ፡፡

ነገር ግን በሥራው ላይ የተሰማሩ ፈጻሚ አካላት በሕግ ማዕቀፎች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራ


ቸው ስለማይደረግ በሚሰጧቸው አገልግሎቶች ለይ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወጥ ባልሆ
ነና ተጠያቂነትንና ግልፅነትን ባልተከተለ መንገድ ሥራቸውን ያከናውናሉ። ይህም አሰራሩን
ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ አድርጎታል፡፡

የአሠራር ሥርዓት ክፍተቱን ለመድፈን የመሬት ልማትና አስተዳደርን በተመለከተ


የወጡ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን መሠረት ያደረገ አፈፃፀም ተግባራዊ ለማድረ
ግ ለሥራ ኃላፊዎችና ለሠራተኞች ስልጠና በመስጠትና በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማ
ድረግ እንዲሁም ለሚከሰቱ ችግሮች ወቅታዊ የእርምት እርምጃ በመውሰድ የግልጽትን
ና የተጠያቂነትን አሠራር በማስፈን መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡

በሚወጡ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ግንዛቤ መያዝ የሚሰራው ስራ ግልጽት


ንና ተጠያቂነትን ተላብሶ እንዲተገበር እገዛ ያደርጋል፤ ለሚታዩ ችግሮች ዘላቂ መፍት
ሄ ለመስጠት ከማስቻሉም በላይ ባለሙያዎች ከግል ስሜታቸውና አድሏዊ አሰራር ነጻ
ሆነው እንዲሰሩ የሚያሰችል መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል::

በአጠቃላይ በድሬዳዋ መሬት ልማትና አስተዳደር ባለሥልጣን እየተካሄደ ያለው የመሠረ


ታዊ የአሠራር ሂደት ለውጥ አሠራሩን ቀልጣፋና ግልፅ በማድረግ ተገልጋዩን ለማርካት
ከማስቻሉ ባሻገር ሙስናና ብልሹ አሠራርን ከመከላከል አንፃርም አስተዋጽኦ እንደሚኖረው
ይታመናል። በተለይም በመሬት አስተዳደር ሥርዓቱ ውስጥ የታዩ ችግሮችን ለመቅ
ረፍ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ከማጠናከር አንፃር
ባለሥልጣኑ፡-

1. በአስተዳደሩ ያለውን የመሬት ይዞታና አጠቃቀም በዝርዝር መዝግቦ መያዝና ይህን


መሠረት ያደረገ አጠቃቀም መዘርጋትና ለዚህም የመሬት አጠቃቀም ሥርአቱ
በዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ማድረግና የመረጃ ሥርአቱን ማጠናከር፣

12
2. አሠራሩን ለመምራት የወጡ ህጎችን ጠንቅቆ በመረዳት ለተፈፃሚነታቸው
ተገቢውን ትኩረት መስጠት፣

3. መልካም ሥራዎችን ከማበረታታት ባሻገር ለሚፈጠሩ የህግ ጥሰቶችና


ጥፋቶች ተጠያቂነትን በግልጽ ማመላከት፣

4. የተገልጋዮችን ቅሬታ ለማስተናገድ አመቺ ስርአት መዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግ፣

5. የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎችን በተቀናጀ መልኩ ማከናወን፣

6. የመሬት አስተዳዳደሩን ሥራዎች በየጊዜው በመገምገምና የክዋኔ ኦዲት በማካሄድ


በሚታዩ ክፍተቶች ላይ ተገቢውን የእርምት እርምጃ መውሰድ፣

7 በመሬት አስተዳደሩ ውስጥ ሊፈጠር የሚችል ሙስናን ለመከላከል የበላይ አመራሩን


ቁርጠኝነት የበለጠ ማጎልበትና ህግን ማዕከል አድርጎ መንቀሳቀስ፣

8. ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ያለውን የቅንጅት


ሥራ የበለጠ ማጠናከር፣

9. የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግና በሚወጡ ህጎች ላይ የተገልጋዩንም ሆነ በሥራው


ላይ የተሰማራውን ባለሙያ ግንዛቤ በማሳደግ አቅሙን ማጎልበት እንደሚጠበቅበት
የጥናቱ ሪፖርት በማጠቃለያው አመልክቷል ፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ኮሚሽኑ ለከተማ አስተዳደሩ በሰጠው አስተያየት


መሰረት የሚመለከታቸውን የሥራ ኃላፊዎችንና የከተማዋን ነዋሪዎች ያሳተፈ ውይይ
ት ከማድረጉም ባሻገር በዱከም ከተማ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ላይ የልምድ ልው
ውጥ አድርጓል፡፡ በመሆኑም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከመሬት ጋር ተያይዞ የታዩት
ችግሮች በሀገሪቱ በሚገኙ በሌሎችም ከተሞች የታዩ በመሆናቸው ችግሩን ለማስወገድ
የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ ነው፡፡ ውስን የሆነውን መሬት ለመኖሪያም ሆነ የተለያዩ
ልማቶችን ለማከናወን የሚፈልጉ ዜጎችና ልማታዊ ባለሀብቶች መመሪያና ደንቡን
መሰረት ባደረገ ግልጽና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ሊያገኙ ይገባል፡፡

13
በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በቀረጥ
ነፃ መደብሮች ላይ የሚደረግ የቁጥጥር አሠራር ሥርዓት

የ ፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለ


ሥልጣን መሥሪያ ቤት ላይ ባካሄደው ጥናት ለሙስናና ለብልሹ አሠራር ክፍተት የሚ
ፈጥሩ ሁኔታዎች መኖራቸውን መገንዘብ ችሏል፡፡ በዚሁ መሠረትም ኮሚሽኑ ለእነዚህ
የአሠራር ክፍተቶች የመፍትሄ ሃሳቦችን በማቅረብ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ
የማስተካከያ ርምጃ እንዲወስድ የበኩሉን ድጋፍ አድርጓል፤ በማድረግም ላይ ነው፡፡

በቀረጥ ነፃ መደብር ውስጥ የሚሠሩ የጉምሩክ ሠራተኞች ቁጥር ለቁጥጥር በሚያመ


ች መልክ ተሟልቶ አለመገኘት በጥናቱ ከታዩ ችግሮች መካከል አንዱ ነው፡፡ በየቀረ
ጥ ነፃ መደብሮች ውስጥ ቁጥጥር ለማድረግ አንዳንድ የጉምሩክ ሠራተኞች የተመደቡ
ሲሆን ሠራተኞቹ በቀን ለ24 ሰዓት ይሠራሉ፡፡ ምንም እንኳ ሠራተኞቹ 24 ሰዓት እን
ዲሠሩ ቢመደቡም ከ12 ሰዓት በላይ ሥራ ገበታቸው ላይ ተገኝተው ቁጥጥር እንደማያ
ደርጉ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በሌላ በኩል የቀረጥ ነፃ መደብሮች ሠራተኞቻቸውን በ24
ሰዓት ውስጥ በፈረቃ እያቀያየሩ እንደሚያሠሩ ለመመልከት ተችሏል፡፡ ከዚህ መረዳት

14
የሚቻለው መንግሥት ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ወደ ቀረጥ ነፃ መደብሮች ውስጥ
የሚገቡ ዕቃዎች ለታለመላቸው ዓላማ ሙሉ ለሙሉ ይውላሉ ለማለት የሚያስችል
የቁጥጥር ሥርዓት በሚፈለገው ደረጃ አለመኖሩን ነው፡፡ ይህ ክፍተትም አንዳንድ መደብሮች
ቀረጥ ያልተከፈለባቸውን ዕቃዎች በማውጣት ከታለመለት ዓላማ ውጭ ሊሸጡ
የሚችሉበት ሁኔታ ይታያል፡፡ ይህ ደግሞ ፍትሃዊ ያልሆነ የገበያ ውድድር እንዲፈጠርና
መንግሥት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እንዲያጣ ምክንያት ይሆናል፡፡

ስለሆነም በእያንዳንዱ መደብሮች ያሉ ሠራተኞች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ


እንዲወጡና የቁጥጥር ሥርዓቱንም የተጠናከረ ለማድረግ በ24 ሰዓት ውስጥ ሠራተኞቹን
በሶስት ፈረቃ መድቦ ማሠራት ተገቢ መሆኑን ጥናቱ እንደመፍትሄ አስቀምጧል፡፡

ሌላው በጥናቱ የታየው ችግር የተለያዩ የሥራ ድርሻዎችን /ኃላፊነቶችን/ በአንድ


ባለሙያ ብቻ እንዲሠራ መደረጉ የቁጥጥር ሥርዓቱ የተዛባ እንዲሆን መንስዔ መሆኑ
ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ኤርፖርት፣ በቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት እና በተወሰኑ ሆቴሎች
ውስጥ ባሉ የቀረጥ ነፃ መደብሮች ለእያንዳንዳቸው አንድ የጉምሩክ ሠራተኛ ብቻ
ተመድቦላቸዋል፡፡ እነዚህ ሠራተኞች በተመደቡበት መደብር ውስጥ የሚካሄደውን
ሽያጭ የመቆጣጠር፣ ገቢና ሽያጭን የመመዝገብ፣ ከሚቆጣጠሩት መደብር ባለቤት ውጭ
የሆኑ መጋዘኖችን የመቆጣጠር /ንብረትን በኃላፊነት ለመጠበቅ የመጋዘን ቁልፍ መያዝ/፣
ዕቃ ከመጋዘን ማውጣትና ወደ መጋዘን የማስገባት እንዲሁም የመጋዘን ዕቃ ገቢና
ወጪ የመመዝገብ ሥራ እንደሚሠሩ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ሥራዎች በተደራራቢነት
በአንድ ሠራተኛ ብቻ መሠራታቸው የቁጥጥር ሚዛኑን ከማዛባቱም በላይ ሥራዎች
በአግባቡ እንዳይከናወኑ ዕንቅፋት እንደሚፈጥር ይታመናል፡፡ በተለይ የመጋዘን ቁልፍ
የመያዝ እና የመጋዘን ዕቃ ገቢና ወጪ የመመዝገብ ሥራ፣ የቀረጥ ነፃ መደብርን
የመቆጣጠርና የመመዝገብ ተገባር በአንድ ሠራተኛ መከናወኑ እንዲሁም የመደብር ተቆጣ
ጣሪ ሠራተኞች ከመጋዘን ዕቃ ገቢና ወጪ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ መደብሩን የሚቆጣጠር
የጉምሩክ ሠራተኛ አለመኖር ሙስና እንዲፈፀም ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን
ጥናቱ አመልክቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታት በቀረጥ
ነፃ መደብሮች ላይ ያለውን የቁጥጥር ክፍተት ለማስተካከል ከመጋዘን የሚወጡና የሚ
ገቡ ዕቃዎችን የመመዝገብ፣ የመጋዘን ቁልፍ የመያዝ፣ ሽያጭ መደብር ላይ ቁጥጥር
የማድረግ እና የመደብር ዕቃ ገቢና ወጪ የመመዝገብ ሥራዎችን እንደአግባብነቱ ለተለ
ያዩ ሠራተኞች በማከፋፈል ሥራው እንዲከናወን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱም ቢሆን የተጠናከረ አለመሆኑን በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥል


ጣን የቀረጥ ነፃ መደብሮች ላይ የተደረገው ጥናት ያመለክታል፡፡ በዓለም አቀፍ ኤርፖ
ርት ውስጥ የሚገኙ አራት የሚሆኑ የቀረጥ ነፃ መደብሮች ሲኖሩ በእነዚህ መደብሮች
ውስጥ የዕቃዎችን ሽያጭ ለመቆጣጠር የተመደበው አንድ የጉምሩክ ሠራተኛ ብቻ
ነው፡፡ ሆኖም ከሁለት መደብሮች ውጪ በሌሎች መደብሮች ውስጥ ወደ መደብር
የገባውን፣ የተሸጠውንና ሚዛኑን ለማወቅ በሚያስችል መልኩ በተዘጋጀው መመዝገቢያ ቅጽ
ላይ በአግባቡ የመመዝገብ ተግባር አለመከናወኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በተጨማ
ሪም በአንዳንድ መደብሮች ውስጥ የሚገኙ የጉምሩክ ሠራተኞች መዝገብ አያያዛቸው
መሠረት የሚያደርገው የመደብር ባለቤቶችን የኮምፒዩተር መረጃ እንጂ በጉምሩክ

15
የገቢና ሽያጭ ሰነድ አለመሆኑን ከጥናቱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይ
በኤርፖርት ቀረጥ ነፃ መደብር ወደ መደብር የገባውን፣ የተሸጠውንና ሚዛኑን መመዝ
ገቢያ መዝገብ ላይ ለረዥም ጊዜ ምዝገባ አለመከናወኑንና በጉምሩክ ሠራተኛው በኩል
የቁጥጥር ሥራው ተገቢው ትኩረት አለመሰጠቱን ታውቋል፡፡ መረጃዎቹ በወቅቱ
ላለመመዝገባቸው በሠራተኛው በኩል የተሰጠው ምክንያት “የመደብሮቹ የሽያጭ ሠራተ
ኞች በኮምፒዩተር ስለማይሠራ መረጃ ማግኘት አልተቻለም” የሚል ነው፡፡ ቀደም ሲል
እንደተገለፀው ጉምሩክ ያስቀመጣቸው የተወሰኑ ሠራተኞች ምዝገባ የሚያከናውኑት
በሚሰጣቸው የገቢና የሽያጭ ደረሰኝ ሳይሆን የቀረጥ ነፃ መደብሮችን የሽያጭ መዝገብን
መሠረት በማድረግ መሆኑን ነው፡፡ ይህ አሠራር ለባለሥልጣኑ ትክክለኛውን መረጃ ለማግኘት
የማያስችለው ሲሆን የቁጥጥር ሥርዓቱን የሚያዳክምና ለሙስናና ብልሹ አሠራር
የሚያጋልጥ መሆኑ በጥናቱ ተመልክቷል፡፡

በመሆኑም የተወሰኑ የኮምፒዩተር ዕውቀት ያላቸው የምዝገባ ሠራተኞችን በመቅጠር


ወይም በማዛወር የምዝገባ ሥርዓቱን ለማሻሻል ኮምፒዩተራይዝድ ማድረግ ቅድሚያ
ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ጥናቱ አመላክቷል፡፡ ይህም አሠራሩን ግልጽነት የሰፈነበ
ትና ፈጣን ከማድረጉም በላይ ምዝገባውን በአነስተኛ የሰው ኃይል ማከናወን ያስችለል፡፡

በሌላ በኩል ከመጋዘን ወደ መሸጫ መደብር የሚገቡ ዕቃዎች መረከቢያ ሰነዶች ስርዝ
ድልዝ የሚበዛባቸው መሆኑ ከጥናቱ መረዳት ይቻላል፡፡ ከመጋዘን ወደ መሸጫ መደብ
ር የሚገቡ ዕቃዎች ለቁጥጥር ያመች ዘንድ የመረከቢያ ደረሰኝ ይዘጋጅላቸዋል፡፡ እነዚህ
ደረሰኞች በትክክሉ መሠራት ሲገባቸው ስርዝ ድልዝ ባለው ሁኔታ ተሠርተው እደሚ
ገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ለአብነትም በጥናቱ በናሙና በተወሰደ የቀረጥ ነፃ መደብር
ያለው የመረከቢያ ሰነድ በተገለፀው የዕቃ ብዛትና ዓይነት ላይ ስርዝ ድልዝ ከመደረጉ
ም በላይ ደረሰኙ ላይ የተመዘገበው የዕቃ መጠን ሰርዞ በሌላ የመተካት ሁኔታ እንዳለ
ታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ የቀረጥ ነፃ መደብር ሠራተኞች ሽያጭ አከናውነው
ለባለመብቱ የሚደርሰውን የሽያጭ ደረሰኝ ቅጠል ከሰጡ በኋላ ባለመብቱ ተጨማሪ
ዕቃዎችንም እንደወሰደ በማስመሰል በቀሪ ደረሰኞቹ ላይ ተጨማሪ ዕቃዎችን እንደሚ
ወስዱ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ይህም ሀገሪቱ ያላትን ውስን የውጭ ምንዛሬ እንዲባክን
የሚያደርግ እና የቀረጥ ነፃ ባለመብት ተጠቃሚ ላልሆኑ ሰዎች በሕገወጥ መንገድ
እንዲደርሳቸው ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡ ይህ አሠራር የነፃ መደብር ሠራተኞች በዋነኛነትም
መንግሥት የጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ዕቃዎችን ቀረጥ ሳይከፈልባቸው
በተለያዩ መንገዶች ከመደብር እንዲወጡ ለማድረግና የማጭበርበር ድርጊቶች እንዲፈ
ፀሙ በር እንደሚከፍት የጥናት ቡድኑ ማረጋገጥ ችሏል፡፡ በዚህ የተነሳም የቀረጥ ነፃ
መብት ላላቸው ግለሰቦች ተብሎ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው የሚገቡ ዕቃዎችን በአንዳንድ
ሥነምግባር የጎደላቸው የጉምሩክ ሠራተኞችና የቀረጥ ነፃ መብት መደብሮች
በመመሳጠር እቃዎቹ በከተማ ውስጥ እንዲሸጡ በማድረግ ያለአግባብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ሊያደርግ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

በመጋዘኖችና በመደብሮች ውስጥ የሚገኙ ዕቃዎችን በተመለከተ በጉምሩክ በኩል


ዓመታዊ ንብረት ቆጠራ አለመከናወኑ ባለስልጣን መ/ቤቱን ለሙስናና ለብልሹ
አሠራር የሚጋልጥ ሁኔታ ነው።

16
በቀረጥ ነፃ መደብሮች እና በመጋዘን ውስጥ ያሉ ዕቃዎችን በተመለከተ በባለሀብቶች
በኩል ዓመታዊ የንብረት ቆጠራ የሚደረግ ቢሆንም በባለስልጣን መ/ቤቱ በኩል
ከመደብሮች ጋር በጋራ ዓመታዊ የንብረት ቆጠራው የማይከናወን ስለሆን በመጋዘኖች እና
በመደብሮች ውስጥ ያሉ ንብረቶች ከወጪ ቀሪ ሚዛንና በቆጠራ መካከል የሂሳብ ማስታ
ረቅ ሥራ አለመሰራቱን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በዚህ የተነሳ በዓመቱ መጨረሻ ቀረጥ
ሳይከፈልባቸው የገቡ ንብረቶች መጉደል አለመጉደላቸው የሚታወቅበት አሰራር
የለም፡፡ ይህ አሰራር አንዳንድ ግለሰቦች ለመንግሥት ቀረጥ ያልተከፈለባቸው
ን ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ መደብር ውጪ በመሸጥ መንግሥት የውጪ ምንዛሪ
እና የከሽያጭ ትርፍ ግብር እንዳያገኝ ከማድረጉም ባሻገር ዕቃዎች የመጡበትን ዓላማ
በመሳት የቀረጥ ነፃ መብቱ በሌላቸው ግለሰቦች እጅ እንዲገቡ በማድረግ ፍትሐዊ የሆነ
የገበያ ውድድር ሥርዓት እንዳይኖር እድሉን ይከፍታል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት ወደ መጋዘን እና መደብሮች የሚገቡና ሽያጭ ላይ


የሚውሉ ዕቃዎችን በዓመቱ መጨረሻ በአግባቡ ለማወቅ እንዲቻልና በመጋዘኖችና
በመደብሮች ውስጥ ያሉ ንብረቶችን ከወጪ ቀሪ ሚዛንና በቆጠራ መካከል የሒሳብ
ማስታረቅ ሥራ በመስራት ተገቢውን ቁጥጥር ለማድረግ እንዲያስችል ዓመታዊ
የንብረት ቆጠራ ማድረግና ቆጠራ በሚደረግበት ወቅት መደብር ውስጥ ከሚሰሩ
የጉምሩክ ሠራተኞች በተጨማሪ የጉምሩክ ኦዲተሮች በታዛቢነት በሚገኙበት እንዲ
ከናወን በማድረግ የቁጥጥር ሥርዓቱን ማጠናከር በመፍትሔ ሀሳብነት ተጠቁሟል፡፡

ወጥነት ያለውና የፀደቀ የሥራ መመሪያ አለመኖር ሌላው የባለሥልጣን መሥሪያ


ቤቱን አሠራር ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍት ሁኔታ ነው፡፡ በአዲስ አበባ
ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ውስጥ የተለያዩ የግልና የመንግሥት የቀረጥ ነፃ ዕቃ
መሸጫ መደብሮች አሉ፡፡ እነዚህ መደብሮች ቀረጥ ያልተከፈለባቸው ዕቃዎች የሚሸ
ጡባቸው ሲሆን ባለመደብሮቹ ከጉምሩክ ጋር ያላቸው የሥራ ግንኙነት በምን መልኩ
መሆን እንዳለበት የሚገልፅ የተዘጋጀ መመሪያ የለም፡፡ ለምሳሌ የሪፖርት አቀራረብ
ሥርዓት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ በጋራ መደረግ ስላለበት የዕቃ ቆጠራን በተመ
ለከተ በማን ቆጠራው መከናወን እንዳለበት እና እነማን መሳተፍ እንዳለባቸው የሚታ
ወቅበት ወጥ የሆነ አሰራር የለም። የቀረጥ ነፃ ሽያጭ መደብሮች ያላቸውን ኃላፊነትና
ተጠያቂነት የመሳሰሉ ጉዳዮችን በተመለከተ ተዘጋጅቶ የተሰጣቸው መመሪያ ባለመኖ
ሩ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓቱ ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ ወጥነት የሌለው ነው፡፡
በዚህም ምክንያት አሁን በተግባር ላይ ያለው አሰራር ሥራዎች በልምድ የሚሰሩበት
ሁኔታ እንዲኖር እና መደብሮቹም መብታቸውን እና ግዴታቸውን በግልፅ በመመሪያ
እንዲያውቁት ባለመደረጉ ከዚህ ጋር ተያይዞ ለሚፈጠር ሕገ ወጥ ድርጊት በር ከፋች ነው፡፡

የመንግሥትም ሆነ የግል የቀረጥ ነፃ መደብሮች ወጥ የሆነ የሪፖርት አቀራረብ


ሥርዓት እንዲኖራቸው ማድረግ ተገቢ ነው። በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በቀረጥ ነፃ
መደብሮችና መጋዘኖች ውስጥ ስለሚደረግ ቆጠራና በቆጠራውም ማን መሳተ
ፍ እንዳለበት፣ የመደብር ባለቤቶችን አጠቃላይ መብትና ግዴታዎችን የሚገልፅ እና
ከጉምሩክ ጋር ሊኖራቸው ስለሚገባ የሥራ ግንኙነት በዝርዝር የሚያሳይ ወጥ የሆነ
መመሪያ ማዘጋጀትና ለተግባራዊነቱም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ በመሥራት

17
ግልፅነትን ማስፈን ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በመመሪያው መሠረት ሃላፊነታቸውን
በማይወጡ አካላት ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረግ አስፈላጊው የእርምት ርምጃ የሚወ
ሰድበትን ሥርዓት ዘርግቶ አሁን እየታየ ያለውን ወጥነት የጎደለውን አሰራር ወደ አንድ
አቅጣጫ የማምጣት ሥራ ማከናወን እንደሚያስፈልግ በጥናቱ የቀረበ የመፍትሄ ሀሳብ
ነው፡፡

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ለሠራተኞቹ ኃላፊነትና ግዴታቸውን የሚወጡበትና ተጠያቂነትን


ለማስፈን የሚያስችል የሥራ መዘርዝር /job description/ የማይሰጣቸው መሆኑ
ሌላው የአሰራር ሥርዓት ችግር መሆኑ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በተማው ውስጥ ባሉ የተለያዩ የቀረጥ ነፃ


መደብሮች ውስጥ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው የገቢ ዕቃዎችን ሽያጭ ለመቆጣጣር የራሱን
ሠራተኛ በየመደብሮቹ መድቦ እየሰራ ይገኛል። እነዚህ በየመደብሩ የተሰማሩ
ሠራተኞች ከሌላ የሥራ ክፍል ወደ ቀረጥ ነፃ መደብር በተዘዋወሩበት ጊዜ ኃላፊነታቸውንና
ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችል የሥራ መዘርዝር በወቅቱ
የማይሰጥበት ሁኔታ መኖሩን ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዚህም የተነሳ ሠራተኞች
የሥራ ድርሻቸውን በአግባቡ ባለማወቃቸው መሠራት የሚገባው ሥራ በአግባቡና
በወቅቱ እንዳይሰራ ከማድረጉም በተጨማሪ እነዚህ ሠራተኞች ከተቀመጠላቸው
የሥራ ድርሻ ውጪ ሕገ ወጥ ተግባር ፈጽመው ቢገኙ የተጠያቂነት ሥርዓት እንዳይኖር
በማድረግ የቁጥጥር ሥርዓቱን ያላላዋል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት መ/ቤቱ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ


የሚሰሩ ሠራተኞችን እያቀያየረ በማዘዋወር ማሰራት፣ የተለዩት የሥራ መደቦችን
ወጥ የሆነ የሥራ መዘርዝር በአንድ ጥራዝ በማዘጋጀት ለሠራተኞች መሥጠትና ስለ
አጠቃቀሙም ግንዛቤ በማስጨበጥ በተሰጣቸው የሥራ መዘርዝር መሠረት ሃላፊነትና
ግዴታቸውን እንዲወጡ ማድረግ በመፍትሄ ሀሳብነት በጥናቱ ቀርቧል፡፡

የትርፍ ሰዓት ክፍያ አከፋፈል ሥርዓት የጥቅም ግጭት የሚፈጥር መሆኑ ሌላው በባ
ለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የታየ የአሰራር ሥርዓት ችግር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ገቢዎችና
ጉምሩክ ባለስልጣን ቁጥጥር የሚያደርግባቸው የተወሰኑ የቀረጥ ነፃ መደብሮች ከአስ
ራ ስምንት ሰዓት በላይ የሚሰሩ ሲሆን ሠራተኞችም ከመደበኛው ሥራ ሰዓት ውጪ
ለሚሰሩባቸው ሰዓታት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ይፈፀምላቸዋል፡፡ እያንዳንዱ የቀረጥ ነፃ
ሽያጭ መደብር በመቆጣጠር ሥራ ላይ የተሰማራ የጉምሩክ ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት
ክፍያ የሚከፈለው በሚቆጣጠሩት መደብሮች ሲሆን ክፍያ መጠኑና የአከፋፈሉ
አይነት በመደብሮች በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ ሠራተኞቹ
የቁጥጥር ሥራውን የሚያከናውኑት ባለስልጣን መ/ቤቱን ወክለው ቢሆንም ትርፍ
ሰዓት ክፍያው የሚፈፀምላቸው ግን በቀረጥ ነፃ መደብሮች መሆኑ የጥቅም ግጭት
የሚፈጥር እና ተቆጣጣሪ ሠራተኞቹ የሚያገኙትትን ጥቅም ላለማጣት ሲሉ የተሰጣቸ
ውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዳይወጡ እንዲሁም መንግሥት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም
እናዳያገኝ የሚያደርግ አሰራር ሆኖ ይታያል፡፡

18
ባለስልጣን መ/ቤቱ የቀረጥ ነፃ መደብር ሠራተኞችን ተጨማሪ የሰው ሀይል ቀጥሮ
በፈረቃ ከማሰራት ይልቅ በትርፍ ሰዓት ክፍያ ማሰራት የተሻለ አማራጭ እንደሆነ
ያምናል። ስለሆነም ለሠራተኞች ወጥ የሆነ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሥርዓት በመዘርጋት
ክፍያውን ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ እንዲፈጽም ማድረግ በመፍትሄ ሀሳብነት የቀረበ
ሲሆን ይህም ሠራተኞቹ የቁጥጥር ሥራቸውን ያለምንም ተፅዕኖ እንዲሰሩ ያስችላቸዋል፡፡

ባለስልጣን መ/ቤቱን ለሙስናና ብልሹ አሰራር ከሚያጋልጡት ሁኔታዎች መካከል


ከቀረጥ ነፃ ሽያጭ በሚያከናውኑ መደብሮች ላይ የጉምሩክ የቁጥጥር ሥርዓት ኦዲት
ተደርጎ የማያውቅ መሆኑ በጥናቱ የታየ ልላው ችግር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መ/ቤት በከተማው ውስጥ ባሉ የተለያዩ


የቀረጥ ነፃ መደብሮች ውስጥ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው የገቡ ዕቃዎች ሽያጭ ቁጥጥርን
በተመለከተ በአግባቡ ስለመከናወኑ በውስጥ ኦዲተሮች በኩል ተገቢው ትኩረት ሰጥቶ
ቁጥጥር አለመደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚቀርበው በቀረጥ
ነፃ መሸጫ መደብርና መጋዘን ውስጥ ያሉ ዕቃዎችን በናሙና በመቁጠር የሂሳብ
ማመዛዘኛ አለመሥራቱ ነው፡፡ ይህ አሰራር አንዳንድ ሥነምግባር የጎደላቸው ግለሰቦች
ቀረጥ ሳይከፈልባቸው የገቡ ዕቃዎችን የመንግሥትን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ለራሳቸው
ጥቅም እንዲያውሉት በር የሚከፍት ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በመሆኑም የባለሥልጣን መ/ቤቱ ኦዲት ክፍል በተወሰነ ጊዜ ፕሮግራም በመያዝ በቀረጥ


ነፃ መደብሮች እና መጋዘኖች ላይ የቁጥጥር ሥርዓቱ በአግባቡ ስለመከናወኑ ተገቢውን
ክትትል በማድረግ ሪፖርቱንም ለሚመለከታቸው ሃላፊዎች የሚያሳውቅበት ወጥ የሆነ
አሰራር ማመቻቸት ለአሰራር ሥርዓቱ ችግር መፍትሄ ሆኖ በጥናቱ ቀርቧል፡፡

19
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የግዥ አፈፃፀም ሥርዓት

በ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የግዥ አፈፃፀም ሥርዓት ላይ በተካሄደው የአሠራር ማሻሻ


ያ ጥናት አምስት ለሙስና እና ብልሹ አሠራር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ተስተውለዋል፡፡
እነርሱም የተጠና የጠቀሜታ ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ አዘገጃጀት አሰራር አለመኖር፣
ግዥዎችን በዕቅድና በፕሮግራም አለመፈፀም፣ በጀት መኖሩ ሳይረጋገጥ የግዥ ሂደቶችን
ማከናወን፣ በግዥ መመሪያው ከተቀመጠው የገንዘብ መጠን በላይ ግዥ መፈፀም እና
የጨረታ ኮሚቴው ከግዥ መመሪያውን ተከትሎ አለመሥራት የሚሉት ናቸው፡፡

የፌደራል መንግሥት የግዥ አፈፃፀም ሥርዓት መመሪያ የጠቀሜታ ዝርዝር /ስፔስ


ፊኬሽን/ በተጠቃሚዎች ዝርዝር ላይ የተመሠረተ ሆኖ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን
የሚፈለገውን ለማሟላት ያላቸውን ተፈጥሮ፣ የሚያስገኙትን ውጤት፣ ለመሥሪያ ቤቱ
የሚያስገኙትን ጠቀሜታ፣ የሚጠይቀን የቴክኒክ ብቃት፣ የአሠራር ባሕሪያቸውንና
የታቀደላቸውን ሥራ ለማከናወን ያላቸውን የብቃት ደረጃ የሚያካትት ዝርዝር
መግለጫ መዘጋጀት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ይሁን እንጂ በፌደራል ፖሊስ መሥሪያ

20
ቤት የሚዘጋጁት አንዳንድ የጠቀሜታ ዝርዝሮች /ስፔስፊኬሽንስ/ የሚገዙትን
ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች በግልጽ የሚያሳዩ ባለመሆናቸው የግዥ ውሳኔዎች ወደ
አልተፈለጉ አቅጣጫዎች እንዲያጋድሉ በማድረግ የአሠራር ክፍተቶች ሊፈጥሩ እንደሚችሉ
ጥናቱ ያሳያል፡፡

ከላይ የቀረበውን ችግር ለማቃለልም ለዕቃና አገልግሎቶች ግዥ የሚያገለግል ደረጃው


ን የጠበቀና የቴክኖሎጂ ዕድገትን ከግምት የሚያስገባ የስፔስፊኬሽን ማንዋል እንደየሥ
ራው ዓይነትና ባሕሪይ በአማካሪ ድርጅቶች በማስጠናት ወጥ በሆነ መልኩ ተግባራዊ
ማድረግ እንደሚያስፈልግ በመፍትሄ ሃሳብነት ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ ኮሚሽኑ ይህን በማድ
ረጉም ወጥና ደረጃውን የጠበቀ፣ በዋጋም ሆነ በጥራት የተሻለ ዕቃና አገልግሎት ግዥ
ለመፈፀም እንደሚያስችለው ይታመናል፡፡

በዕቅድና በፕሮግራም ግዥዎችን አለመፈፀም ሌላው በኮሚሽኑ የታየ ለሙስና እና


ብልሹ አሠራር የሚያጋልጥ አሰራር ነው፡፡ ያለ ፕሮግራምና ዕቅድ አስቸኳይ እየተባሉ
የሚፈፀሙ ግዥዎች በአይነትም ሆነ በመጠን ከፍተኛ በመሆናቸው ኮሚሽኑን ለከፍተ
ኛ ወጪ ይዳርጋሉ፡፡ ከዚህም በላይ በፕላንና በፕሮግራም በመመራት በገበያ ላይ በአነስ
ተኛ ዋጋ፣ በጥራትና በመጠን ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም በተገቢው መንገድ እንዳያገኝ
ምክንያት ይሆናል፡፡ ይህ የጥድፊያ ግዥ አሠራሩን ለሙስናና ለብልሹ አሠራር የተመ
ቻቸ ከማድረጉም በላይ የተገዙት ዕቃዎች ለረዥም ጊዜ ቦታ አጣበው ያለ አገልግሎት
እንዲከማቹ፣ ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑና ለብልሽት እንዲዳረጉ ምክንያት ሆኗል፡፡

የሥራ ክፍሎች በበጀት ዓመቱ ውስጥ ለማከናወን ከያዙት የሥራ መጠንና መርሃ
ግብር ጋር የሚጣጣም የግዥ አቅርቦት ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የበጀት ዓመቱን
ዕቅድ በተቀናጀ መልኩ እንዲፈጽሙ እንዲሁም ስለንብረት አጠቃቀማቸው ወቅታዊ
ሪፖርት አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ ተገቢውን ክትትል ማድረግ በመፍትሄ ሃሳብነት
በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ ይህም በዕቅድና በመርሃ ግብር በመመራት በገበያ ላይ በጥራትና
በመጠን ሊገኙ የሚችሉ ጥቅሞችን ያስገኛል፤ እቃዎች ለረዥም ጊዜ ያለ አገልግሎት
ተከማችተው ለብልሽት እንዳይዳርጉም ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው፡፡

በተመሳሳይ በፌደራል ፖሊስ የቁጥቁጥ እና የዋጋ ማቅረቢያ /የፕሮፎርማ/ ግዥ


ከፍተኛ እንደሆነ ጥናቱ አመልክቷል፡፡ በኮሚሽኑ በርከት ያሉ ግዥዎች በዋጋ
ማቅረቢያ ዘዴ የሚከናወኑ በመሆናቸው መሥሪያ ቤቱ በጥቅል ግዥ ሊያገኝ የሚችለውን
ጥቅም ከማሳጣቱም በላይ ከዚህ ጋር ተያይዘው ለሚፈጠሩ ብልሹ አሠራሮች በር
የሚከፍት ነው፡፡

ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የሚጠየቁ የግዥ ፍላጎቶች ለማስፈፀም በቂ በጀት መኖሩ ወይ


ም አለመኖሩ በቅድሚያ ሳይጣራ ፕሮፎርማ እንደሚሰበሰብና ግዥ እንደሚፈፀም ጥናቱ
ያሳያል፡፡ ይሁንና ግዥው ከፀደቀ በኋላ ግዥውን ለማስፈጸም በቂ በጀት ስለሌለ ጥያቄው
በድጋሚ ተቀንሶ እንዲስተካከል ወይም ሌላ አማራጭ እንዲፈለግ በማለት የግዥ ሰነዶ
ች በተደጋጋሚ ወደ ኋላ እንደሚመለሱ ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ ደግሞ
የሠራተኛን ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ በማባከን መንግሥትን ለአላስፈላጊ ወጪ

21
ከመዳረጉም በተጨማሪም የውስጥ ቁጥጥሩን በማዳከም ለሙስናና ለብልሹ አሠራር
ይዳርጋል፡፡ ለአብነትም የደንብ ልብስና የሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች ግዥን መጥቀስ
ይቻላል፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍም አስቀድሞ በጀት መኖሩንና አለመኖሩን ከፋይናንስ ክፍል


በመጠየቅ ለግዥ በተዘጋጀው ፎርም ላይ በመሙላት ግዥ የሚከናወንበትና የእቃዎች
ዝርዝር ዋጋ በቂ መረጃ መያዝ የሚቻልበት ሥርዓት መዘርጋት እንደመፍትሄ
በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ ይህም የኮሚሽኑን የግዥ ሥርዓት ግልጽነት የሰፈነበት፣ ለቁጥጥርና
ለክትትል አመቺ እንዲሆን እና ተገቢ ያልሆነን ወጪ ለመከላከል ያስችላል፡፡

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የታየው ሌላው የአሠራር ሥርዓት ችግር በግዥ አፈፃፀም
መመሪያው ለእያንዳንዱ የግዥ ከተቀመጠው የገንዘብ ጣሪያ መጠን በላይ ግዥን
መፈፀም ነው፡፡ የጥቅል ግዥ የሚያስገኘውን ጥቅም ከግምት በማስገባት ግዥ ፈፃሚ
አካላት በዚህ መልክ እንዲያከናውኑ እና ቀደም ሲል በዕቅድ ያልተያዘ ነገር ግን አጣዳፊ
የሆነ ግዥ ሲመጣ ቢያንስ ሶስት አቅራቢዎችን በማወዳደር ግዥ በዋጋ ማቅረቢያ
ማከናወን እንደሚቻል የመንግሥት ግዥ መመሪያ ይደነግጋል፡፡ ሆኖም በፌደራል
ፖሊስ በመመሪያው የተቀመጠው ገንዘብ ጣሪያ መጠን ሳይጠበቅ እና የአቅራቢዎች
ዝርዝር በሌለበት ሁኔታ ግዥ አንደሚከናወን ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ ለአብነትም በቁጥር
1 /ፌፖኮ1/28/121/ ግንቦት 10 ቀን 1999 ዓ.ም በፕሮፎርማ ቁጥር 48780 አምስት
ጠረጴዛዎች በ43,368.80 ለዋናው መሥሪያ ቤት ግዥ የተከናወነ ሲሆን ታሕሣሥ 7
ቀን 2000 ዓ.ም ሶስት ኮምፒዩተሮች ከነፕሪነተራቸው በ47,472.00 ለሆስፒታልና
ለፋይናንስ መምሪያ በፕሮፎርማ ግዥ መፈፀሙን መመልከት ይቻላል፡፡ ይህ ዓይነት
አሠራር የመንግሥት ገንዘብ አለአግባብ እንዲወጣ ከማድረጉም ሌላ ለሙስናና ብልሹ
አሠራር በር የሚከፍት ይሆናል፡፡

ግዥ ሲታቀድ እና ፕሮግራም ሲዘጋጀ የጥቅል ግዥ መጠቀምን የሚጠይቁ


ዕቃዎችንና አገልግቶችን ዓይነት በመወሰን ዝርዝር መግለጫ ማዘጋጀት፣ አቅራቢዎችን
በመለየት በቁጠባና በጥንቃቄ ግዥን መፈጸም፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት የተላበሰ የሥራ
ፍሰት መዘርጋትና በአፈፃፀሙ ላይ ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባ የኮሚሽኑ
ጥናት በመፍትሄ ሃሳብነት አቅርቧል፡፡ ይህም የመንግሥት የግዥ ሕግና መመሪያ
በተገቢው መንገድ ሥራ ላይ እንዲውል እገዛ ያደርጋል፡፡

በመንግሥት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት የጨረታ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኃላፊነቶች


ስብሰባውን ከመምራት አንስቶ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት የጫረታ አካሄድ መከና
ወኑን እስከ ማረጋገጥ የሚደርስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የቋሚና
አላቂ ዕቃዎች ጨረታ ኮሚቴ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቁ ግዥዎችን የግዥ ኮሚቴው
ሰብሳቢና ታዛቢ ኦዲተር ባልተገኙበት በተደጋጋሚ በሶስት አባላት ብቻ ይፈጽማሉ፡፡
ለዚህም መንስዔው ሰብሳቢውን ጨምሮ አብዛኛው የጨረታ ኮሚቴ አባላት የሥራ
ፀባያቸው ከአዲስ አበባ ውጭ ለመስክ ሥራ የሚያስወጣና ለረዥም ጊዜ የሚያቆያቸ
ው በመሆኑ ግዥዎችን በዕቅድና በፕሮግራም ለመፈፀም የማያስችል መሆኑ ነው፡፡

22
ይህ ደግሞ በተገልጋዮች ዘንድ ቅሬታን የሚያስከትልና የግዥ ሂደቱን የሚያራዝም
ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በአጠቃላይ ሙስናና ብልሹ አሠራርን ከመከላከል አንፃር ከፍተኛ
ጥንቃቄን የሚሹ ግዥዎች በሶስት የጨረታ ኮሚቴ አባላት ብቻ ውሳኔ እንዲተላለፍባቸ
ው ማድረግ ተገቢ ሆኖ አይታይም፡፡

በመሆኑም በግዥ ኮሚቴ አባልነት የሚሰየሙ ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የሥራ


ፀባያቸው በተደጋጋሚና ረዘም ላለ ጊዜ ወደ መስክ የማያስወጣቸው፣ የኮሚቴ አባላት
የሥራ እንቅስቃሴ ከሚያከናውኑት ተግባር ጋር እየታየ ተገቢው ክትትልና ቁጥጥር
የሚደረግበትና በሚታዩ ችግሮች ላይም ወቅታዊ ርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ
በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ በተጨማሪም የጨረታ ኮሚቴ ሰብሳቢው ከቁጥጥር ውጭ
በሆነ ምክንያት በኮሚቴው ስብሰባ ላይ ባይገኝ ሌላውን አባል በጊዚያዊነት ለመወከል
እንዲችል ግልጽ የሆነ ሥልጣንና ተግባር መስጠት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነው፡፡

በኮሚሽኑ የታየው ሌላው የአሰራር ችግር የአቅራቢዎችንና ጥፋት የፈፀሙ ድርጅቶ


ችን ዝርዝር በተገቢው መንገድ አለመያዝ ነው፡፡ የመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ የሥራ
አፈፃፀምና የመንግሥት ግዴታዎችን በሚገባ መወጣት አለመወጣታቸውን በማረጋገጥ
በየጊዜው እያደሰ አቅራቢዎችን እና ጥፋት የፈፀሙ ድርጅቶችን ዝርዝር በማውጣት
መያዝ እንዲሁም የመንግሥት ግዥ ፈፃሚ አካላትም ይህንኑ መሠረት በማድረግ
ግዥ መፈፀም እንዳለባቸው መመሪያው ይደነግጋል፡፡ ሆኖም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
በመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ የሚወጡትን አቅራቢዎች ዝርዝር እያደሰ ባለመያዙ
አቅራቢዎች በሚመረጡበት ወቅት ለሚፈጠሩ ግለ ውሳኔያዊ አሰራሮች በር በመክፈት
ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተመቻቸ ሆኖ ይታያል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንዳንድ
አቅራቢዎች ለሚፈጽሙት ጥፋትና የአፈፃፀም ጉድለት በወቅቱ ተገቢውን ርምጃ
ሳይወሰድባቸው እንዲታለፉ ስለሚደረግ በውድድሩ ፍትሃዊነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ
ማሳደሩ የማይቀር ነው፡፡

ይህንን የአሠራር ችግር ለመቅረፍ በመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ የፀደቀ የአቅራቢዎች


ዝርዝር መያዝና በየጊዜው ወቅታዊ ማድረግ፣ አቅራቢዎች ጥፋት ሲፈጽሙ የጥፋተኝ
ነት ዝርዝር ውስጥ ማስገባትና በቀጣይ በግዥ ሂደት ውስጥ እንዳይሳተፉ የሚያደርግ
ሥርዓት መዘርጋት፣ ግዥዎች በዋጋ ማቅረቢያ በሚከናወኑበት ወቅት አቅራቢዎች
በዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ከተለያዩ ድርጅቶች የቀረቡ መሆናቸውን ማረጋገጥ
እንደሚያስፈልግ ጥናቱ ይጠቁማል፡፡ በተጨማሪም የኮሚሽኑ የኦዲት ክፍል የዘርፉ
ን ሥራ በየጊዜው እንዲከታተልና እንዲገመግም በማድረግ በክፍተቶቹ ላይ ወቅታዊ
ሪፖርት ለማኔጅመንቱ ማቅረብና የዕርምት ርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
በዚህም ከተወሰኑ አቅራቢዎች ብቻ ሊደረግ የሚችልን የግዥ ግንኙነት በመቀነስ ግልጽ
የገበያ ውድድር ለመፍጠር እና አድሏዊ አሰራርን ለመከላከል ያስችላል፡፡

የተጠናከረ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ አለመኖሩ


በጥናቱ የታየ ችግር ነው፡፡ የውስጥ ኦዲት በግዥ ኮሚቴ በታዛቢነት የሚሳተፍ ካለመ
ሆኑም በላይ በተሟላ መልኩ ሥራውን ኦዲት የማያደርግ በመሆኑ በሥራ አጋጣሚ

23
የሚከሰቱትን ክፍተቶች በማውጣት ለማኔጅመንቱ አጋዥ ሪፖርት በማቅረብ የእርምት
ርምጃ እንዲወሰድ የሚያስችልበት ሁኔታ ጉልህ ሆኖ አልታየም፡፡

ስለሆነም በቀጣይ የኮሚሽኑ የውስጥ ኦዲት በጨረታ ኮሚቴ ውስጥ በታዛቢነት የሚሳ
ተፍበትና በየወቅቱ የሥራ ሪፖርት ለማኔጅመንቱ የሚያቀርብበት አሰራር መዘርጋት
እንዳለበት ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

በአጠቃላይ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በግዥ አፈፃፀም ሥርዓት ላይ የታዩትን


የአሠራር ሥርዓት ችግሮች ለመቅረፍ በጥናቱ የተጠቆሙትን የመፍትሄ ሃሳቦች ተግባራዊ
ማድረግና የኮሚሽኑ በየደረጃው የሚገኙ ኃላፊዎች የሚካሄዱትን ግዥዎች የሚያፀድቁ
በመሆናቸው ግዥዎች በመንግሥት የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት መካሄዳቸውን
ና አለመሆናቸውን በማረጋግጥ ግዥው እንዲፈፀም በማድረግ የመንግሥትንና የሕዝብን
ሃብት ከብክነትና ከምዝበራ ሊታደጉት ይገባል፡፡

24
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ የአሰራር ሥርዓት

የ ሐራጅ ሽያጭ አፈፃፀምን በተመለከተ በፍርድ አፈፃፀም መምሪያው የሐራጅ ሽያጭ


መነሻ ዋጋ በወቅታዊ የገበያ ዋጋ ላይ ተመስርቶ የሚሰራበት በግልፅ የተቀመጠ
መመሪያ ባለመኖሩ የቴክኒክ ባለሙያዎች ከራሳቸው ልምድ በመነሳት የሚሰሩበት ሁኔታ
መኖሩ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚዳርግ ሁኔታ መሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡

በፍርድ አፈፃፀም ሂደት ላይ የሚገኙ ንብረቶች በተለይ የተወሰኑ ቋሚ ንብረቶችና


ቤቶች የሽያጭ ግምት መነሻ ዋጋ የጨረቃ ቤቶችን ሳይጨምር በአዲስ አበባ አስተዳደር
በጂ-አይ.ኤስ ምዝገባና ትመና ላይ የተመሠረተ እና በመሬት አስተዳደር በ1988 ዓ.ም
ልኬት በኮምፒውተር ተመዝግቦ የነበረው መረጃ የገበያ ዋጋ ላይ ባለመመስረቱና
ይህም የጨረታ መነሻ ዋጋው ሆኖ የሚያገለግል በመሆኑ የመሸጫ ዋጋው ላይ ተፅእኖ
በማሳደር መንግሥት ሊያገኝ የሚገባውን የገቢ ግብር ሊያሳጣው ከመቻሉም በላይ
ለግል ውሳኔ ሊጋለጥ ስለሚችል ለሙስናና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ ያደርገዋል፡፡
የሐራጅ ሽያጭና መነሻ ዋጋ በወቅቱ የገበያ ዋጋና በጥናቱ ላይ ተመስርቶ በአሁኑ

25
ወቅት በየጊዜው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ካለው የቤት ሽያጭ ዋጋ ጋር
እንዲጣጣሙ /Selling price Adjustment/ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከ
ር አሰራሩ የሚስተካከልበትን ሁኔታ ማመቻቸት የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት
የቀረበ የመፍትሄ ሃሳብ ነው፡፡

የሐራጅ ሽያጭ ድርሻ ክፍፍል አተገባበርን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠውን ውሳኔ


ና ትዕዛዝ በማያሻማ መንገድ ለማስፈፀም የሚያስችል አስተዳደራዊ ዝርዝር የአፈፃፀም
መመሪያ አለመኖር መምሪያውን ለሙስናና ለብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ ሁኔታ
መሆኑ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

በፍርድ አፈጻጸም ላይ ስለሚገኙት ንብረቶችና ሌሎች ማናቸውም ሐብቶች የሐራጅ


ሽያጭ ድርሻ ክፍፍል አተገባበር በተመለከተ ግልፅና ተጠያቂነትን የሚያመላክት ቀላል
ና ግልጽ የሆነ እንደየአካባቢውና ጉዳዩ ሁኔታ ታይቶና ተገናዝቦ ለመተግበር የሚያስ
ችል ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ አለመኖር በተገልጋይ እና አስፈፃሚ አካል መካከል
አላስፈላጊ ውዝግቦችና ግጭቶችን የሚያስከትል ከመሆኑም በላይ የፍርድ ውሳኔ አፈፃፀ
ሙን አተገባበር በማወሳሰብ እንዲዛባ በመድረግ ለተለያዩ ሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተ
ቶች እንዲጋለጥ ያደርጋል፡፡

ይህን የአሰራር ሥርዓት ችግር ለመቅረፍ ግልጽ የሐራጅ ሽያጭና ድርሻ ክፍፍል
አፈጻጸም መመሪያ ከዝርዝር ሕጉ ጋር በማገናዘብ ተቀርፆ ተግባራዊ ማድረግ በጥናቱ
የቀረበ የመፍትሄ ሃሳብ ሲሆን ይህም ክፍተቶችን ለመከላከል እና ወጥ የሆነ አሰራር
እንዲኖር ለማድረግ ያግዛል፡፡

በድጋሚ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ ለሚፈፀም ሽያጭ ዕቃዎች ያለ ጨረታ መነሻ


ዋጋ በወቅቱ በቀረበ ከፍተኛ ዋጋ እንዲሸጡ መደረጉ የመሸጫ ዋጋው ዝቅተኛ
እንዲሆን ተፅዕኖ ማሳደሩ ሌላው በጥናቱ የታየ የአሰራር ሥርዓት ክፍተት ነው፡፡

በመጀመሪያ በወጣ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ ሳይሸጡ የቀሩ ዕቃዎች በድጋሚ


የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ እንዲሸጡ ሲደረግ የጨረታው መነሻ ዋጋ ከዜሮ እንዲ
ጀመር በመደረጉ ፍርድ ላረፈባቸው ንብረቶች የሽያጭ ዋጋ መቀነስ ዋናው ተጠቃሽ
ምክንያት ከመሆኑ ባሻገር ይህንን ክፍተት በመጠቀም የተዛባ መረጃ በማሰራጨት
የመጀመሪያው ጨረታ ውጤት እንዳይኖረው ተፅዕኖ በማሳደር የሽያጭ ዋጋው
እንዲወርድና ለተወሰኑ ግለሰቦች አግባብ ባልሆነ ዝቅተኛ ዋጋ እንዲሸጥ ምቹ ሁኔታን
በመፍጠር የፍርድ ባለመብትና መንግስት ሊያገኙ የሚችሉትን ጥቅም ይሳጣል፡፡

በመሆኑም በመጀመሪያው የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ ሳይሸጥ ቀርቶ ድጋሚ


የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ በሚወጣበት ወቅት የጨረታ መነሻ ዋጋ ለመገመት የሚቻልበት
ሁኔታ ከሕጉ ጋር በተጣጣመ መንገድ ሊተገበር የሚችልበት ሁኔታ ተጠንቶ ተግባራ
ዊ ቢደረግ ተደራጅተው ጨረታውን በማፈንና በሚፈልጉት አቅጣጫ በመምራት ዋጋ
እንዲቀንስ የሚንቀሳቀሱትን ለመከላከል ያስችላል፡፡
በጥናቱ እንደታየው በመምሪያው የፍርድ አፈፃፀም ሥራዎች ተባባሪ አካላት ጋር ያለው

26
ቅንጅታዊ አሰራር ጠንካራ አለመሆን ነው፡፡ የፍርድ አፈፃፀሙ በወቅቱ ተግባራዊ እንዲሆ
ን ከሚመለከታቸው አካላት /የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት አስተዳደር፣ የአዲስ
አበባ ወይም የፌዴራል የፖሊስ፣ የቀበሌና ሌሎች ተባባሪ አካላት/ ጋር ጠንካራ ቅንጅታዊ
አሰራር ባለመፈጠሩ በሚከሰቱ ምልልሶች መብዛት ባለጉዳዮች ሊጉላሉ ስለሚችሉ ጉዳዩን
በአፋጣኝ ለማስፈፀም ሲባል ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተት ሊፈጥር ይችላል፡፡

ከባለድርሻ አካላቶች በተወሰነ ጊዜ የሚካሄድ የጋራ መድረክ በመፍጠር በአሰራር


የገጠሙ ችግሮችን በመለየት የጋራ መፍትሄ የሚቀመጥበትን ሁኔታ በማመቻቸት
ለብልሹ አሠራር ክፍተት የሚፈጥረውን ሁኔታ መግታት ይቻላል፡፡

የዘርፉ የፍርድ ማስፈፀም አቅም ውስንና ያልተጠናከረ መሆን ሌላው ለብልሹ አሰራርና
ሙስና የሚዳርግ ሁኔታ ነው፡፡

አሁን ያለው የሰው ኃይል ሥራው ከሚጠይቀው አንፃር በብዛትና በጥራት፣ በሙያና
ልምድ አናሳ ከመሆኑ አንፃር የማስፈፀም አቅሙና የቁጥጥር ስልቱ ዝቅተኛ ሆኖ
መገኘቱ በፍርድ አፈፃፀሙ ስራ ላይ ተፅእኖ ያሳድራል በምሳሌነትም ሥራው በሸያጭ
ሙያ በቂ ዕውቀትና ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚከናወን ያለመሆኑ፣ የፍርድ
አፈፃፀም ሠራተኛና በተለይ ስለ አንዳንድ ንብረቶች በቂ እውቀት ስለሌላቸው በሚያ
ስከብሩበት ወቅት ጉድለታቸውን ያለመመዝገብ /ይህ ሁኔታ በቸልተኝነትም ሊፈፀም
ይችላል፣ በሐራጅ ጊዜ ደግሞ ዕቃው ተቀይሮ ወይም ሆነ ተብሎ እንዲበላሽ ተደርጐ
ሊቀርብ ይችላል/፣ ሲረከቡ ስለነበረበት ሁኔታና አካላት በቂ መረጃ ማግኘትም አስቸጋሪ
መሆኑ ተጠቃሽ ነው፡፡

የሰው ሃይሉን ፈትሾ ቁልፍ በሆኑ የስራ መደቦች ብቃት ያለው የሰው ኃይል በቋሚነ
ት በዕድገት፣ በዝውውር ወይም በቅጥር መመደብና በሐራጅ ሽያጭ አሰራር ላይ ለባለ
ሙያዎች ስልጠና መስጠት ለችግሩ በመፍትሄ ሃሳብነት በጥናቱ ቀርቧል። የተመረጠው
መፍትሄ ተግባራዊ ሲሆን ብቃትና የተሟላ ሥነምግባር ያላቸውን ሠራተኞችን
ለማግኘት ሊያስቸግር እና አዲስ ሠራተኞችን ለመቅጠር በቂ በጀት ላይፈቅድ ስለሚች
ል የተሟላ ብቃትና ሥነምግባር ያላቸውን ሠራተኞችን ለመሳብ የሚያስችሉ የሥራ
ሁኔታዎችን ከገበያ ጋር በተጣጣመ መልኩ ማመቻቸትና አዲስ ሠራተኞችን
ለመቅጠር በቂ በጀት እንዲፈቀድ ጥረት መደረግ እንዳለበት በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ዘዴ ውስን መሆን በቂ መረጃ ያለመያዙ ሌላው መምሪያው


ን ለሙስናና ብልሹ አሠራር የሚያጋልጥ ሁኔታ ነው፡፡

ከፍተኛ የመነሻ ሐራጅ ሽያጭ ዋጋ ተመን ላላቸው ንብረቶች /ድርጅቶች፣ ፋብሪካዎ


ች../ ማስታወቂያዎች በስፋት ወደ ህዝብ ጆሮ ሊደርሱ በሚችልበት የብዙኃን መገናኛ
ዘዴዎች /በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን በመሳሰሉት/ ስለማይተላለፉ አቅም ያላቸው
ተጫራቾች በስፋት እንዲወዳደሩ የማይጋብዝ መሆኑ፣ ስለሚሸጠው ንብረት አስፈላጊ
ው መረጀ በተሟላ መልኩ ያለመቅረቡ በቂ ቁጥር ያላቸው ተጫራቾች አለመምጣትን
ወይም አለመሳተፍን ከማስከተሉ ባሻገር የመረጃ ክፍተትን ለመሙላት የሚደረገው

27
ጥረት ለሕገወጥ ድርጊቶች ያበረታታል፡፡

ይህን የአሰራር ሥርዓት ችግር ለመፍታት በጥናቱ የቀረበው የመፍትሄ ሃሳብ በፍት
ሐብሄር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 423 የሐራጅ ሽያጭ መደረጉን ለሕዝብ ስለማሳወቅ
በሚል በተደነገገው መሠረት በሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያው ሊገለፁ የሚገባቸውን
ዝርዝር መረጃዎችን በመግለፅ ተጫራቾች በቂ መረጃ እንዲያገኙ በማድረግ፣ በጥቅም
ላይ የሚውለው የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ዘዴ እንደ ንብረቱ የግምት መጠን
መወሰን ቢቻል፣ በፌዴራል ፍ/ቤቱ የአሰራር ማንዋል ላይ በተገለፀው መሠረት ከብር
5000 በታች ከሆነ በተለያዩ ቦታዎች ማስታወቂያውን በመለጠፍ፣ ከብር 5,000-50,000
ከሆነ ሰፊ ሽፋን ባለው ጋዜጣ እንዲወጣ ማድረግ፣ ከብር 50,000 በላይ ከሆነ ከጋዜጣው
በተጨማሪ በቴሌቪዥን እንዲገለጽ በማድረግ በሚል የቀረበው ተግባራዊ ቢደረግ
የተሟላና ግልጽ መረጃዎችን በማግኘት በቂ ተጫራቾች በመጀመሪያ ጨረታ ላይ
እንዲቀርቡና እንዲሳተፉ ይጋብዛል። የፍርድ ባለዕዳንም ሆነ የፍርድ ባለመብቱን ንብረቱ
በተገቢው ዋጋ እንዲሸጥ በመርዳት ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

የፍርድ ባለዕዳዎች ለማስታወቂያ የሚከፈለው ወጪን ይጨምራል በሚል ቅሬታ ሊያድ


ርባቸው ስለሚችል በማስታወቂያዎቹ በቂ መረጃን አካቶ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ዘዴ
ዎችን በመጠቀም መረጃው ለህዝብ እንዲደርስ በማድረግ ንብረቱን በተሻለ ዋጋ ለመሸጥ
ና በተጨማሪም ንብረቱ በአነስተኛ ዋጋ ተሽጦ እዳው ባይቻቻል ባለዕዳውን ከሚዳርገው
ተጨማሪ ክፍያ ሊታደገው እንደሚችል ማስገንዘብ ሊወሰድ የሚገባው እርምጃ ነው፡፡

በጥናቱ የተገለፀው ሌላው የአሠራር ሥርዓት ክፍተት የንብረት አያያዝን በተመለከተ


የንብረት ርክክብና አያያዝ፣ የመዝገብ አያያዝና ቁጥጥር እንዲሁም የኪራይ አገልግ
ሎት ክፍያ ተመን /ታሪፍ/ አወጣጥን አስመልክቶ ግልጽ አሠራር አለመኖር ነው፡፡

ፍርድ ላረፈባቸው ንብረቶች የርክክብ ቅፆች የተሟሉና ግልጽ መረጃዎችን /detail lists
and conditions/ ለመያዝ በሚያስችል መልኩ የተቀረጹ አለመሆን፣ የንብረቶች የገቢ
ና የወጪ ርክክብ፣ አያያዝና አጠባበቅ ሁኔታ ለቁጥጥር የሚያመችና በግልጽ ተጠያቂ
ነትን ለማስከተል የማያስችል መሆኑ በንብረት አስተዳደር ምዝገባ ዙሪያ በቂ ልምድና
ሙያ ያካበተ ባለሙያ አለመመደብ፣ በርክክብም ሆነ በሽያጭ ተገቢ ቁጥጥር ለማድረ
ግ /check and balance/ ማመዛዘኛ በመስራት የሚረጋገጥበት አሠራር አለመኖሩ፣
ንብረቶች ሳይሸጡ ለረጅም ጊዜ መቆየትና እነዚህን ንብረቶች ለማስወገድ የሚቻልበት
ግልፅ መመሪያ አለመኖር፣ የመጋዘን ኪራይና ዋጋ አተማመን /storage and
handling cost valuation/ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ተመጣጣኝና በጥናት ላይ የተመሠ
ረተ አለመሆን በንብረት አስተዳደሩ ከታዩት ችግሮች ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ይህም ንብረት
እንዲባክን፣ ለስርቆትና ለብልሽት እንዲዳረግ ክፍተት ሊፈጥር እንደሚችል ጥናቱ
ያመላክታል፡፡

የስቶክ ካርድና የንብረት ሂሳብ መዝገብ አያያዝ በቂ ልምድና ሙያ ያካበተ ባለሙያ


መመደብ፣ ገቢ እና ወጪን በተመለከተ ከመምሪያው ባህሪ ጋር የተጣጣሙ ቅፆችን
/ፎርሞችን/ ማዘጋጀት፣ ለንብረቶቹ ጥበቃ ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ አተገባበር

28
እንደንብረቱ ውድነት የሚከፈልበትን አሰራር በጥናት ተመርኩዞ ማዘጋጀት፣
የርክክብም ሆነ የሽያጭ አፈጻጸሙ ተገቢው ትኩረት እንዲሰጠው ቢደረግና በርክክብ
ወቅት ኦዲተር በገለልተኛነት የሚታዘብበት፣ ስለዕቃው ዝርዝር ሁኔታ የሚያውቅ
ባለሙያ በግንባር እንዲገኝ የሚደረግበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣ በውሳኔ ትዕዛዝ
ላይ ለአፈፃፀም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በዝርዝር የንብረቶቹን ዓይነት፣ ግምትና
ሞዴል ካላቸው፣ ብዛት እና የሚገኙበት አካል በግልጽ ተጠቅሶ ቢቻል በጠባቂ እንዲሆኑ
ማድረግ በጥናቱ የተገለፁ ችሮችን ለመቅረፍ የቀረቡ የመፍትሄ ሃሳቦች ናቸው፡፡

ሒሳብ አያያዝን በተመለከተ የሂሳብ መዝገብ አያያዝና ቁጥጥር ማነስ አሰራሩም መሰረታ
ዊና ተቀባይነት ያለው የፋይናንስ አሰራር ሥርዓትን /GAAP - Generally Accepted
Accounting Principles and Policies/ ተከትሎ የማይሰራና ቁጥጥሩ የላላ መሆኑ
ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ ሁኔታ ነው፡፡

ተደራራቢ የገንዘብ ኃላፊነት ስራ በአንድ ሠራተኛ ማከናወን ማለትም የሒሳብ ክፍያ


ሰነድና ቼክ ማዘጋጀትና ማፅደቅ እንዲሁም የሂሳብ ምዝገባው በተመሳሳይ የሂሳብ
ሠራተኛ /ኃላፊ/ ስለሚሰራ የቁጥጥር ሥርዓቱን ሊያዛባው የሚችል መሆኑ፣ በየወሩ
የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የሚያስችል የሂሳብ ሚዛን /ባላንስ/ ማረጋገጥ
አለመቻሉ፣ ሂሳቡ በውስጥም ሆነ በውጭ ኦዲተሮች ተመርምሮ የማይታወቅ በመሆኑ
በገለልተኛነት የሂሳቡን አፈፃፀም ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ያለመቻሉ፣ ጥናቱ እስከተጠ
ናቀቀበት ጊዜ የተሰራውንም /financial position/ ለማወቅ አስቸጋሪ ከመሆኑም ባሻገር
የሂሳብ ሚዛኖች /ባላንሶች/ ተዓማኒነት ስለሚጐላቸው ለተለያዩ ክፍተቶች የተመቻቸ
እንዲሆን ሊያደርግ የሚችል መሆኑ፣ የፍርድ ባለመብቶችን የገንዘብ አከፋፈል
ለማስፈፀም የሂሳብ ስሌቶች አተማመንና አመዘጋገብ በቂ ልምድ በሌላቸው በጊዜያዊ
ሠራተኞች መከናወኑ፣ ይህም ሥራ በቀጥታ ከባለጉዳዮች ጋር የሚያገናኝና የገንዘብ
ንክኪ በቀጥታ ያለበት በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ የኃላፊነት ስራ በጊዜያዊ
ሠራተኞች መከናወኑ፣ የሂሳብ ሥራው በሰለጠነ ባለሙያ በተሟላ ሁኔታ ተጠናክሮ
የሚሰራ አለመሆኑና ግልፅ የሥራ መዘርዝር ሳይሰጥ ማሰራት ከተጠያቂነት አኳያ
ለክፍተቶች የመጋለጥ ዕድሉ የተመቻቸ መሆኑ፣ በአጠቃላይ የሂሳብ አፈጻጸም
ሪፖርት የማይቀርብ መሆኑ፣ ከሥራው ፀባይ አንፃር ታይቶና ተጠንቶ ቻርት ኦፍ
አካውንት (ኮድ) በዝርዝር አለመስጠት በዋነኛነት የሚታዩ ችግሮች በመሆናቸው የውስጥ
ቁጥጥሩ እንዳይጠናከር በማድረግ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተት ሊፈጥር ይችላል፡፡

ለረጅም ዓመታት የቆዩ ሂሳቦችን በተመለከተ ከመጀመሪያ ጀምሮ የሂሳብ ምርመራ


ተደርጐ በማጣራት በሚታዩት ልዩነቶች ላይ ተጠያቂነትን በሚያስከትል መንገድ
በማስቀመጥ ሂሳቡን በመዝጋት የማስተካከያ እርምጃ የሚወሰድበት ሁኔታ ቢመቻች፣
የሂሳብ አያያዝና ቁጥጥሩ በተሟላ ሁኔታ ተጠናክሮ መሠረታዊ ተቀባይነት ያለውን
የሂሳብ አያያዝ ሕጐችንና መርሆዎችን የተከተለ እንዲሆን ቢደረግና የቅርብ ክትትልና
ቁጥጥር ማድረግ፣ የሂሳብ ሥራ አፈጻጸሙን በወቅቱ ሪፖርት ማደረግ፣ የውስጥም
ሆነ የውጭ ኦዲተር በየዓመቱ በመመርመር ሂሳቡን ቁጥጥር እንዲያደርግበት ማድረ
ግ፣ በሂሳብ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች ሲቀያየሩ የሰሩት ሂሳብ በገለልተኛ የኦዲት
ባለሙያ አማካኝነት ትክክለኛነቱ ተረጋግጦ እንዲወራረድና ርክክብ እንዲፈፀም

29
ማድረግ፣ የሂሳብ ሥራውን በባለሙያ ማሰራት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን
ለሠራተኞች የሥራ መዘርዝር እንዲሰጣቸውና የሠራተኞችን አቅም ለመገንባት በቂ
ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ናቸው፡፡ ለዚህም ሲባል ደረጃውን የጠበቀ የሂሳብና ቁጥጥ
ር ሥራ ለማከናወን በሙያው የሰለጠነ ሠራተኛ ለማግኘት ከፍተኛ ደመወዝ ሊጠየቅ
ስለሚችል በመ/ቤቱ ልምድ ያላቸውን ሠራተኞች በሙያው በቂ ስልጠና እንዲያገኙ
ማድረግ እና ከገበያው ሁኔታ ጋር በተገናዘበ መልኩ በቂ በጀት በመያዝ የሰው ኃይሉን
በቅጥር ማሟላት ሊወሰድ የሚገባው እርምጃ ነው፡፡

30
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የብር ኖት
ሕትመትና ሳንቲም ቀረፃ አገልግሎት ግዥ አሰራር

በ ባንኩ የብር ኖት ለማሳተምና ሳንቲም ለማስቀረፅ የሚፈፀም ግዥ የአሠራር ሥርዓ


ት ሂደት ውስጥ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥር ሁኔታ ተብሎ በጥናቱ
በቀዳሚነት የተጠቆመው የብር ኖቶችን ለማሳተምና ሳንቲም ለማስቀረጽ ዝርዝር የአገል
ግሎት ግዥ የአፈፃፀም መመሪያ አለመኖር ነው፡፡

ባንኩ በከፍተኛ ወጪ የሚያከናውነውን የብር ኖት የማሳተምና ሳንቲም የማስቀረጽ


አገልግሎት ግዥ ለማስተናገድ የሚያስችል መመሪያ የሌለው ከመሆኑም በላይ የመን
ግሥትን የግዥ መመሪያ /አዋጅ ቁጥር 430/97/ በተሟላ መልኩ አዋጁን ለማስፈፀም

31
የወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ የማይከተል በመሆኑ አሰራሩ ወጥነትና ተጠያቂነት
እንዳይኖረው ያደርገዋል፡፡

ይህን የአሰራር ሥርዓት ችግር ለመፍታት በጥናቱ የቀረበው መፍትሄ የመንግሥት


የግዥ መመሪያን መሠረት ባደረገ መልኩ ባንኩ ከራሱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣ
ጣም ዝርዝር የግዥ መመሪያ በማዘጋጀት መተግበር ቢችል የባንኩን ነባራዊ ሁኔታ
ባገናዘበ መልኩ ግዥን ለመፈፀም ስለሚያስችል ወጥ የሆነ እና ተጠያቂነት ያለበትን
አሰራርን ለማስፈን ያግዛል፡፡

ሌላው በባንኩ የታየው ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥር ሁኔታ ባንኩ
የብር ኖቶች ህትመትና ሳንቲም ቀረፃ አገልግሎት ግዥ ከፈፀመ በኋላ ጥራቱን
የጠበቀ የብር ኖት እና ሳንቲም ቀረፃ ስለመከናወኑ ናሙናውን በማየት ማረጋገጥ የሚችል
ብቃት ያለው ባለሙያ የሌለው መሆኑ ነው፡፡

ባንኩ የብር ኖት ሕትመትና የሳንቲም ቀረፃ ግዥ ሲፈጽም አታሚው ድርጅት የሚያት


መውን የብር ኖትና የሚቀርፀውን ሳንቲም ናሙና ለባንኩ ይልካል፡፡ ባንኩም ናሙናው
ን በማየት ማረጋገጫ የሚሰጥ አካል በመሰየም እስካሁን ስራውን እያከናወነ ቢሆንም
የናሙናውን ጥራት ለማረጋገጥ የተሰየሙት የባንኩ ሠራተኞች በቂ የሆነ ሙያዊ
ዝግጅት የሌላቸው ስለሆነ የብር ኖቶችን ቀለም እንዲሁም ውጫዊ ሁኔታውን ብቻ
በማየት አስተያየት በመስጠት የጥራት ማረጋገጫ ሥራው እየተከናወነ መሆኑ
ታውቋል፡፡ ስለሆነም አሰራሩ ጥራቱን ያልጠበቀ የብር ኖት ህትመትና የሳንቲም ቀረፃ
አገልግሎት ግዥ እንዲፈፀም ክፍተትን የሚፈጥር ነው፡፡

ባንኩ የብር ኖት ሕትመትና የሳንቲም ቀረፃ አገልግሎት ግዥ ባለማቋረጥ ስለሚፈጽም


በብር ኖት ሕትመትና በሳንቲም ቀረፃ መስክ ባለሙያ እንዲሰለጥን በማድረግ ወይም
በዚህ የስራ መስክ /በሕትመት/ በቂ ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች በመቅጠር የጥራት
ማረጋገጫ ስርዓቱን ማስተካከል የአሰራር ስርዓት ችግሩን ለመፍታት በጥናቱ የቀረበ
መፍትሄ ነው፡፡ የኢንቨስትመንት ወጪና መንቀሳቀሻ ካፒታል የማይጠይቅ ከመሆኑ
አንፃር ይህ መፍትሄ ምርጥ መሆኑ በጥናቱ ተገልጿል፡፡

ከውጪ አገር በግዥ ታትመው የሚወጡትን እንዲሁም ከአሮጌ ብር ኖቶች ውስጥ


ተመርጠው ለዝውውር የሚዘጋጁ የብር ኖቶችን ወደ ባንኩ ቮልት በማስገባትና በማስ
ቀመጥ ሂደት ላይ የቁጥጥር ስርዓቱ የተጠናከረ አለመሆን ለሙስናና ብልሹ አሰራር
ክፍተት የሚፈጥር ሁኔታ ነው፡፡

ከውጭ ሀገር በግዥ ታትመው የሚመጡትን እንዲሁም ከአሮጌ ብር ኖቶች ውስጥ


ተመርጠው ለዝውውር የሚዘጋጁ የብር ኖቶችን ወደ ባንኩ ቮልት በማስገባትና
በማስቀመጥ ሂደት ላይ የቁጥጥር ስርዓቱ የተጠናከረ ባለመሆኑ ምክንያት ለብር ጉድለት
የሚዳርግ መሆኑ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

ባንኩ አሁን እያደረገ ካለው የጥበቃ ስራ በተጨማሪ በካሜራ (በCCTV) ቢታገዝ የባንኩን

32
የቁጥጥር ሥርዓት የተጠናከረ እንደሚያደርገው በጥናቱ እንደ መፍትሄ ተቀምጧል፡፡
ያገለገሉ የገንዘብ ኖቶች መረጣ እና አወጋገድ የአሰራር ሥርዓት ሂደት በጥናቱ
ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥር ሁኔታ ታይቷል፡፡ ይህም በገንዘብ አወጋገድ
የሥራ ሂደት የሚሳተፉ አካላት በሥራቸው ሊኖራቸው የሚገባን ሚና በግልጽ
በማንዋል የተደገፈ አለማድረግ አንዱ ነው፡፡

የገንዘብ ማስወገድ ሥራው በሚከናወንበት ወቅት ከሂሳብ ምርመራ አገልግሎት፣ ከፌዴ


ራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከውስጥ ኦዲት መምሪያ እና ከገንዘብ ቆጠራና መረጣ ዲቪዥን
የተውጣጡ አባላት ተሳትፎ ያደርጋሉ፡፡ ከባንኩ ውጪ የሚመጡ አካላት ተግባር ሥራ
ው በባንኩ በተቀመጠው ኘሮሲጀር መሠረት እየተሰራ መሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ ነገር
ግን ከሌሎች አካላት እንዲሳተፉ የተደረጉ አባላት በምልከታ ማረጋገጥ እንደተቻለው
እንዲሁም በኦዲት ሪፖርትም እንደተገለፀው አንዳንድ ታዛቢዎች ጠዋት ላይ ብቻ
በሥራ መግቢያ ሰዓት በመገኘት እና ቀሪውን ሰዓት ባለመገኘት ሥራውን በአግባቡ
የማይከታተሉ መሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሥራ ክፍሉ የእነዚህን አካላት
የሥራ ድርሻ በአግባቡ ካለመረዳት የተነሳ የሱፐርቪዥንና የቁጥጥር/ክትትል/ ተግባርን
እንደ ሥራቸው አድርጐ የመውሰድ የግንዛቤ ችግር መኖሩን በጥናቱ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
ስለሆነም በገንዘብ ኖቶች ቆጠራና መረጣ እንዲሁም አወጋገድ የሥራ ሂደት ውስጥ የታ
ዛቢዎች /የውጭ አካላት/ የስራ ድርሻ በግልጽ ያልተመለከተና በተናጠልና በጋራ ተጠያቂ
የሚሆኑበትን ሥርዓት ያልዘረጋ ስለሆነ የቁጥጥር ሥርዓቱ ደካማ መሆኑን ያሳያል፡፡

በሥራው ሂደት ተሳታፊ የሚሆኑ የውጪ አካላትን ሚና እና የሥራ ድርሻ ዝርዝር


በጽሑፍ በማዘጋጀት ከመጡበት መ/ቤት ጋር በመቀናጀት በመ/ቤታቸው በኩል እንዲደ
ርሳቸው የሚደረግበትን አሠራር መዘርጋት እንዲሁም በታዛቢነት የተመደቡት የውጭ
አካላት የሥራ ድርሻቸውን በተገቢው ሁኔታ እየተወጡ ስለመሆኑ በባንኩ በኩል
የክትትል ስራ እንዲሰራ በማድረግ የቁጥጥር ስርዓቱን ማጠናከር በጥናቱ የአሰራር ሥርዓት
ችግሩን ለመፍታት በመፍትሄ ሃሳብነት የተቀመጡ ናቸው፡፡

በባንኩ የገንዘብ ቤት የሚኖረው የብር ኖቶች ክምችት ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ


የብር ኖቶቹ አቀማመጥ ለቁጥጥር በሚያመች መልኩ አለመሆኑ ሌላው ለሙስናና
ለብልሹ አሠራር የሚያጋልጥ ሁኔታ ነው፡፡

የገንዘብ ኖቶች ክምችትና አቀማመጡ በጊዜ /በቀንም ይሁን በወር/ በመለየት


በሥርዓት ስላልሆነ የአንድ ወር ወይም ቀን ወይም ሳምንት የብር ኖት ክምችት ከሌሎች
ወራት ወይም ቀናት ወይም ሳምንታት ክምችት ጋር ተደበላልቆ የሚቀመጥበት
ሁኔታ በመኖሩ በኦዲት ወቅት የተወሰነ ወቅትን የብር ኖት ክምችት በናሙና በመውሰድ
ኦዲት ለማድረግና የማጣራት ሥራ ለማከናወን እንዳይቻል አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራ
ል፡፡ ይህም ጉድለት ቢከሰት በየትኛው ጊዜ መፈፀሙን ለማወቅና የእርምት እርምጃ
ለመውሰድ አዳጋች ያደርገዋል፡፡

ለዚህ የአሰራር ክፍተት በጥናቱ የቀረበው የመፍትሄ ሃሳብ በገንዘብ ቤቱ ሊኖር


የሚገባውን የብር ኖቶች ክምችት መጠን መወሰንና በቂ የገንዘብ ማስቀመጫ ቮልት

33
በማዘጋጀት በክምችት ያሉ የብር ኖቶች አቀማመጣቸው በጊዜ /በወር እና በቀን
እንዲሁም በሳምንት/ በመለየት መጀመሪያ የገባውን መጀመሪያ ወጭ የሚደረግበትን
አሰራር በመዘጋት ነው፡፡

ክምችቱን በቀን፣ በሣምንት እና በወራት ለያይቶ የማስቀመጡን ሥራ ለማከናወን


ወይም ተግባራዊ ለማድረግ ተጨማሪ ቮልት ሊያስፈልግ ስለሚችል ከበጀት እጥረት
የተነሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስራ ላይ ላይውል ስለሚችል ተጨማሪ የብር ኖት ማስቀ
መጫ ቮልት ለመግዛት አስቀድሞ በጀት በመያዝ ተግባራዊ ማድረግ ሊወሰድ የሚገባ
አርምጃ መሆኑ በጥናቱ ተቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል ባንኩ የሚጠቀምበት ያገለገሉ የገንዘብ ኖቶችን የማስወገጃ ዘዴ ለተለያዩ


ችግሮች የሚዳርግ መሆኑ ሌላው ለሙስናና ብልሹ አሠራር ክፍተት የሚፈጥር
ሁኔታ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ባንኩ ያገለገሉ የገንዘብ ኖቶች አወጋገድ ዘዴን ከሌሎች ሀገሮች
ተሞክሮ በመውሰድ ዘመናዊ የማስወገጃ ቴክኖሎጂ በማስገባት ሥራ ላይ ማዋል እንዳለ
በት እንደመፍትሄ ተጠቁሟል።

በባንኩ የወርቅ ግዥ አፈፃፀም፣ አያያዝና አጠቃቀም የአሰራር ሥርዓት ለሙስናና


ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥር ሁኔታ ተብሎ በጥናቱ የተቀመጠው በወርቅ
አቅራቢ እንዲሁም በጂኦሎጂካል ሰርቬይ ላብራቶር ባለሙያ መካከል የወርቅ ርክክብ ሲደረግ
ባንኩ የወርቅ ጥራትን ለማረጋገጥ የሚችል ባለሙያ የሌለው መሆኑ ነው፡፡

ቀደም ሲል የወርቅ አቅራቢው ነጋዴ፣ ድርጅት፣ ማህበር ወይም ግለሰብ ወርቁን ወደ


ኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ላብራቶሪ በመውሰድ እና ሰርተፊኬት በማሰራት እራሱ
ወርቁንና ሰርቲፊኬቱን በመያዝ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እንዲያስረክብ ይደረግ
ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ላብራቶሪ ባለሙያዎች
ወደ ብሔራዊ ባንክ እንዲመጡ ተደርጐ ምርመራውና የርክክብ ሥራው በባንኩ ውስጥ
እንዲከናወን እየተደረገ ነው፡፡ ሆኖም ግን አሁን ያለው አሰራር በባንኩ በኩል ወርቁን
የሚረከበው ሰራተኛ የሚረከበው ወርቅ በትክክል ወርቅ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ሙያዊ
ብቃት የሌለው ስለሆነ በቁጥጥር ስርዓቱ ላይ ክፍተት ከመፍጠሩ ባሻገር ተጠያቂነትን
በግልጽ ለማመላከት አያስችልም፡፡

ለዚህ የአሰራር ሥርዓት ችግር ባንኩ ወርቅ ተረካቢው ባለሙያ የወርቁን ትክክለኛነት
ለማረጋገጥ የሚችልበትን ብቃት እንዲያገኝ ስልጠና የሚሰጥበትን ሁኔታ ቢያመቻች
ወይም በዚህ ሥራ ሙያዊ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች በመቅጠር እና ቴክኖሎጂ
ባፈራው መሳሪያ በመታገዝ የወርቁን ትክክለኛነት እያጣራ የሚረከብበትን ሥርዓት
በተናጠል ለማስፈን ያስችላል፡፡ ባንኩ በቋሚነት የወርቅ ጥራት ማረጋገጥ የሚችል
ባለሙያ ሊኖረው እንደሚገባ አስፈላጊነቱ የማያጠያይቅ መሆኑ በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡

የወርቅ ግብይትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታ


ቸው አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ደካማ መሆን በጥናቱ የታየ ባንኩን ለሙስና እና ብልሹ
አሰራር የሚያጋልጥ ሁኔታ ነው፡፡

34
የወርቅ ግብዓት ሥርዓትን በተመለከተ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የሚመለከታ
ቸው አካላት ማለትም የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ባለስልጣን እና የተለያዩ ወርቅ
አምራች ድርጅቶች ወይም ማህበራት በተጠናከረ መልኩ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት
ባለመዘርጋቱ በተጭበረበረ ሃሰተኛ የወርቅ ንግድ ፈቃድ በመጠቀም እንዲሁም ከጂኦሎ
ጂካል ሰርቬይ መ/ቤት የልኬት ሰርተፊኬት ከተሰራ በኋላ ወርቁን ባንክ በማቅረብ ረገድ
ያለውን ክፍተት በመጠቀም ማጭበርበር እንዲፈፀም ክፍተት ፈጥሯል፡፡

ማጭበርበር ቢፈፀም ባንኩ በዋናነት ክፍያ በመፈፀም የመጀመሪያ ተጐጂ ስለሚሆን


ግንባር ቀደም ተዋናይ በመሆን ሁሉንም አካላት ባሳተፈ መልኩ የመረጃ ልውውጥ
ሥርዓት በመዘርጋት የማጭበርበር አካሄዶችን በመከላከል ችግሩን ለመፍታት
እንደሚቻል በጥናቱ ተመልክቷል፡፡

የውስጥ ኦዲት መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ሥራው በአግባቡ ስለመከናወኑ በሚያረጋግጡ


ት ሥራ ላይ የኮሚቴ አባል ሆነው መሥራታቸው ነፃ የሆነ ሙያዊ አስተያየት እንዳይ
ሰጡ ተጽዕኖ ማሳደሩ በባንኩ አሰራር ሥርዓት ክፍተትን ይፈጥራል፡፡

የባንኩ የውስጥ ኦዲት ስራ አስኪያጅ ስራው በአግባቡ ስለመከናወኑ የማረጋገጥ ሥራ


በሚያከናውኑበት ስራ ላይ የኮሚቴ አባል ሆነው እየተስፋፉ መሆኑን ከቀረቡት
መረጃዎች ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ለምሳሌ፡- የብር ኖት ሕትመትና የሳንቲም ቀረፃ ኮሚቴ
ውስጥ አባል በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ የኦዲት መምሪያው ቁጥጥርና ግምገማ የሚያደ
ርግባቸውን ተግባራት እንዲያከናውን መደረጉ በኦዲት ወቅት የመምሪያው ኃላፊ ወይም
ባለሙያው ራሱ በሰራው ስራ ላይ ነፃ የሆነ አስተያየት እንዳያቀርብ ተጽዕኖ ስለሚያሳ
ድር ነፃ የሆነ ሙያዊ አስተያየት እንዳይሰጥ በማደረግ የቁጥጥር ሥርዓቱን ሊያዳክም
ይችላል፡፡ ይህን የአሰራር ሥርዓት ችግር ለመፍታት በጥናቱ የመፍትሄ ሃሳብ
ቀርቧል፡፡ ይኸውም የኦዲት መምሪያ ኃላፊው ወይም የመምሪያው ባለሙያዎች ኦዲት
የማያደርጓቸው ተግባራትን በማከናወን ረገድ ተሳትፎ እንዳያደርጉ ቢደረግ ጊዜያቸውን
የመሻማት ሁኔታ ስለሚቀንስ ተገቢ የሆነ የቁጥጥር ሥራ እና የምክር አገልግሎት
እንዲሰጡ ከማስቻሉም ባሻገር ነፃ የሆነ ሙያዊ አስተያየት እንዲሰጡ በማድረግ የቁጥጥር
ሥርዓቱን ያጠናክራል፡፡

ለባንኩ በሚቀርቡ የኦዲት ሪፖርቶች ላይ ወቅታዊ የእርምት እርምጃ አለመውሰዱ


ለአሰራር ክፍታት የሚያጋልጥ ሁኔታ ነው፡፡ባንኩ በውስጥ ኦዲት መምሪያ በኩል በሚቀ
ርብለት ሪፖርት ተገቢና ወቅታዊ የእርምት እርምጃ በመውሰድ በኩል ተገቢ የሆነ እንቅ
ስቃሴ አለማድረጉ ታውቋል፡፡ ይህ አሰራር ደግሞ በባንኩ ውስጥ እንደ አንድ የቁጥጥር
ስርዓት የተዘረጋውን የኦዲት መምሪያ የሥራ እንቅስቃሴን በማዳከም ለብልሹ አሰራርና
ለሙስና በር የሚከፍቱ አሰራሮች እንዲቀጥሉ ወይም እንዲስፋፉ ክፍተት ይፈጥራል፡፡

ለዚህ የአሰራር ሥርዓት ችግር በውስጥም ሆነ በውጭ ኦዲተሮች በሚቀርቡ የማሻሻያ


ሀሳቦች ላይ ወቅታዊ የእርምት እርምጃ በመውሰድ የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታ
ት እንደሚቻል ጥናቱ ገልጿል፡፡

35
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ተርሚናል ዕቃዎች
አያያዝና ቁጥጥር የአሰራር ሥርዓት ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው

የ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በካርጎ ተርሚናል ዕቃዎች አያያዝና ቁጥጥርን በተመለከተ


ለሙስናና ብልሹ አሰራር ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች መካከል በመንገደኞች ሆነ በካርጎ
አውሮፕላኖች ተጭነው የሚገቡ ዕቃዎች /ጭነቶች/ መጋዘን ገቢ እስከሚደረጉ ድረስ
በአየር መንገዱ ያለው የቁጥጥር ሥርዓት ደካማ መሆኑ ነው፡፡

በመንገደኞች አውሮፕላን ዕቃዎች ተጭነው ሲገቡ የአየር መንገዱ የዶክመንቴሽን


ሠራተኛ በቦታው ተገኝቶ የጭነት ሰነዶችን የሚረከብ ቢሆንም እቃዎችን በተመለከተ
በኃላፊነት የሚረከብ ሠራተኛ ባለመኖሩ አየር መንገዱ ሳይረከባቸው በተለያዩ አውሮ
ፕላኖች ተጭነው የሚመጡት ዕቃዎች ተጠራቅመው በኤርፖርት ሴኩሪቲ ስር /ይህ
በአየር መንገዱ ስር ያለ ሴኩሪቲ አይደለም/ በተከለከለ ቦታ እንዲቆዩ ያደርጋል፡፡ በማጓጓዙም
ስራ ጥበቃው በደህንነቱ ስር ሆኖ ተጓጉዘው በመጋዘኑ አካባቢ ሜዳ ላይ የሚራገፉትና
እዚያም ለዕቃዎቹ ኃላፊነት የሚወስድ የአየር መንገዱ ሠራተኛ ሳይኖር በተራገፉበት
ቦታ ላይ ሊቆዩ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ በካርጎ
አውሮፕላን ተጭነው የሚገቡ ዕቃዎች በተመሳሳይ መልኩ ተረካቢ የአየር መንገዱ

36
ሠራተኛ የሌለና ከመጋዘን ውጪ ቆይቶ በመጋዘን ቦታ ሲኖር የሚገባበት ሁኔታ
መኖሩ ታውቋል፡፡ በዚህ ሂደት ከመንገደኞች አውሮፕላን ዕቃዎች በሚራገፉበትና
በካርጎ መጋዘን መካካል ረዥም ርቀት ያለው በመሆኑ ዕቃዎቹ በመንገድ ላይ ቢጠፉ
ሊታወቅ የሚቻልበት ሁኔታ መኖሩ አጠራጣሪ ከመሆኑም በላይ ጉድለትም ቢከሰት
አየር መንገዱ ተጠያቂ ሊያደርገው የሚችል አካል ያለመኖሩ ዕቃዎች ለመጥፋት
ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህ አሰራር ዕቃዎችን በተለይ በምሽ
ት ጊዜ አሳቻ ቦታ በመሰወር ለመስረቅ /ለማስወጣት/ አመቺ ሁኔታ ሊፈጥር መቻሉን
ያመለክታል፡፡ አየር መንገዱ ዕቃዎችን በሀላፊነት ተረክቦ መጋዘን ገቢ ሊደረጉ የሚች
ልበት አሰራር ባለመቀየሱና የቁጥጥር ተግባሩ ለአየር መንገዱ ተጠሪ ባልሆነና ሊቆጣ
ጠረው በማይችለው በደህንነት /ሴኩሪቲ/ ላይ እንደወደቀ ታሳቢ መደረጉ ተጠያቂነትን
በማላላት ለዕቃዎች መጥፋትና ላልተገባ የካሳ ክፍያ ሊዳርገው የሚችልበት ክፍተት
ሊፈጠር እንደሚችል አመላካች ነው፡፡

ይህን የአሰራር ሥርዓት ችግር ለማስወገድ በመንገደኞችም ሆነ በጭነት አውሮፕላ


ኖች የሚገቡም ሆነ የሚወጡ ጭነቶችን በባለቤትነት የሚከታተል የአየር መንገዱን
ሠራተኛ መመደብና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ እንደአስፈላጊነቱ ቋሚና ተንቀሳቃሽ
ካሜራዎችን መትከልና የተተከሉ ካሜራዎችንም አተካከል በመፈተሽ አስፈላጊውን
ማስተካካያ በማድረግ መቆጣጠር በጥናቱ የተጠቆመ የመፍትሄ ሀሳብ ነው፡፡

ዕቃዎች መምጣታቸው ተረጋግጦና በሲስተሙ ላይ ተመዝግበው ወደ መጋዘን ገቢ


ከተደረጉ በኋላ ሲጠፉ ያለው የተጠያቂት ሥርዓት ደካማ መሆን ሌላው በጥናቱ የታየ
ለሙስናና ለብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ ሁኔታ ነው፡፡

እቃዎች በካርጎ ተጭነው ሲመጡ ኤየር ዌይ ቢል /AWB/ ከካርጎ ማኒፌስቱ ጋር


መጣጣሙ እየተረጋገጠ፣ መጋዘንም ሲገባ ሲስተሙ ላይ የሚጭነው ባለሙያ
ዕቃዎቹ ተበትነው ትክክል መሆናቸውን በማረጋገጥ ‹‹ok›› የሚል ምልክት በማድረግ ዕቃው
ወደ መጋዘን ለመግባቱ ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡ ሆኖም ይህ ዕቃ ሲጠፋ እቃውን
ከመፈለግና ተፈልጎ አልተገኘም ከተባለ በቀጥታ በኢንሹራንስ እንዲሸፈን ካሳ እንዲጠየቅበት
ከማድረግ ውጪ ዕቃው የጠፋበትን ሁኔታ በማጣራት በሥራው ተሳታፊ የሆኑ
አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር ያለመኖሩ ለጥፋት የሚያነሳሳና ሠራተኞችን ላልተፈለገ
የሥነምግባር ጥሰት የሚጋብዝ ሆኖ መገኘቱን ያመለክታል፡፡

ከሰነድ ማረጋገጫ ጀምሮ ጭነቱ ወደ መጋዘን ገብቶ ከመጋዘን እስከሚወጣ ድረስ


ከሥራው ጋር ካለው ግንኙነት አንፃር ችግሩ የተከሰተበትን ሁኔታ በማጣራት በቀጥታ
ግንኙነት ያለው ሰራተኛ ተጠያቂ የሚደረግበትን አሰራር መዘርጋት በሠራተኛው
ዘንድ የኃላፊነትና የተጠያቂነት ስሜት ለመፍጠር ስለሚያስችል እንዲሁም ሠራተኛው
ሥራውን በጥንቃቄ እንዲሰራ ስለሚያደርግ አማራጭ የመፍትሔ ሀሳብ ተብሎ በጥናቱ
ቀርቧል፡፡

በጥናቱ የታየው ሌላው ለሙስና እና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ ሁኔታ በድርጅቱ


በካርጎ መጋዘን ውስጥ የዕቃዎች አቀማመጥ ለቁጥጥር አመቺ ሆኖ ያለመገኘቱ ነው፡፡

37
ጭነት ወደ መጋዘን ከገባ በኋላ ሲስተም ላይ ተጭኖና የብተና ሥራ ተከናውኖ ወደ
ተገቢው ቦታ ይላካል፡፡ በዚህ ወቅት ለትራንዚት የተራገፈው ዕቃ መጋዘን ውስጥ
ተገፍቶ ወይም በፎርክ ሊፍት ሠራተኛ ተጭኖ ለየሀገሩ በተዘጋጀው መደርደሪያ ላይ
ወይም ለትራንዚት ተከልሏል በሚባልበት ክልል ሜዳው ላይ /በመጋዘን ውስጥ/
ይራገፋል፡፡ በሌላ በኩል ለአየር መንገዱ ሥራ አገልግሎት የሚመጣው /COMAT/
እንዲሁም ለሌሎች ለምሳሌ በ DHL እና ለግል ድርጅት /ለሚድሮክ፣ ኢካስ/ የሚመጡ
ዕቃዎች በተመሳሳይ መልኩ በዚሁ መጋዘን ውስጥ ይቀመጣሉ፡፡ በመጋዘኑ ውስጥ
በሚገኙ የተለያዩ የሥራ ዘርፎች መካከል የሰነድ ርክክብ ባለመኖሩና ከመጋዘኑም ጥበት
የተነሳ ዕቃዎቹ በውጪ ሜዳ ላይ እና በመጋዘን ውስጥ መሬት ላይ በየቦታው ተበታትነው
ማየት የተለመደ ነው። በዚህ የተነሳ ለአንዱ የተላከው ዕቃ ከሌላው ጋር የሚደበላለ
ቅበትና በዚህ አጋጣሚም ዕቃዎች የሚጠፉበት ሁኔታ የሚከሰት መሆኑን የተገኘው
መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህን ክፍተት ተጠቅሞ ዕቃዎችን በስርቆት ለማውጣት ሰፊና ምቹ
ሁኔታን የሚፈጥር ሆኖ ይታያል፡፡

ይህን የአሰራር ሥርዓት ችግር ለመፍታት ሁለት የአማራጭ ሀሳቦች በጥናቱ


ቀርበዋል፡፡ የመጀመሪያው አማራጭ የትራንዚት ዕቃዎች ተለይተው እንዲዘጋጁ
በማድረግ የሚረከብና ወደ ተዘጋጀለት ቦታ የሚወስድ ሠራተኛ በመመደብ ከሌሎች
ተለይተው ሊቀመጡ የሚችሉበት በመጋዘኑ ውስጥ መለያ /በሽቦ ማጠር ይቻላል/
ወይም በቀላል ማቴሪያል ፓርቲሽን በመስራት በበሩ ላይ ጥበቃውን ማጠናከር
መፍትሄ ሊሆን ይችላል። እንዲሁም ተጨማሪ የዕቃ መደርደሪያዎች በመጋዘን ውስጥ
በማስገባት ተጨማሪ ቦታ መፍጠር እና በDHL እና ለግል ድርጅት የሚመጡ ዕቃዎች
ተለይተው ለሚመለከተው አካል ማስረከብ የሚቻልበትን አሰራር መዘርጋት በአጭር
ጊዜና በቀላል ወጪ ተግባራዊ በማድረግ የመጋዘኑን ጥበት በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል፡፡

የዕቃዎችን መደበላለቅ ለማስቀረትና ችግሩን በተሻለ ለመፍታት አማራጭ ሁለት


በመፍትሄነት ቀርቧል፡፡ ይኸውም የትራንዚት ዕቃዎች ውጪ በሆነ በተለየ ቦታ /መጋዘን/
በማዘጋጀት እንዲቀመጡ በቂ ጥበቃ ማድረግ ነው፡፡

በተመሳሳይ የገቢ ዕቃዎች ምዝገባና ሪከርድ አያያዝ ለቁጥጥርና ክትትል አመቺ


አለመሆን ድርጅቱን ለሙስና እና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ ሁኔታ መሆኑ ጥናቱ
ጠቁሟል፡፡

ዕቃዎች ወደ መጋዘን ገቢ ሲደረጉ በየስቴሽኑ የተመደቡት ሠራተኞች በሲስተም ላይ


ይመዘግባሉ ከመዘገቡ በኋላ ዕቃዎችን ተለይተው ወደ ተገቢው ቦታ ይላካሉ። በዚህ
ወቅት መድረሻው አዲስ አበባ የሆነው ዕቃ በመደርደሪያው ላይ ተጭኖ ዕቃው
እንዲወርድ ከተደረገ መረጃው ከሲስተሙ ላይ የሚጠፋ በመሆኑ ዕቃው በመደርደሪው
ላይ ሳይጫን ቢቀር በመጋዘን ውስጥ ገብቶ እንደጠፋ ተቆጥሮ ከማፈላለግና ከጠፋም
በኢንሹራንስ እንዲሸፈን ከማድረግ ውጪ ዕቃው ለመግባቱና በመደርደሪያው ላይ
ለመጫኑ እርግጠኛ መሆን የሚቻልበት ሁኔታ የለም፡፡ በሰነድም ለማጣራት ጥያቄ
በሚቀርብበት ወቅት በተለይ ጊዜው የቆየ ከሆነ የማይገኝበትም ሁኔታ መኖሩን
ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ይህም ዕቃዎች በመደርደሪያ ላይ ተጭነው ሳይመዘገቡ /scan/

38
ሳይደረጉ ወይም ሳይጫኑ ቢቀሩ አመቺ ጊዜ በመጠበቅና ሁኔታዎችን በማመቻቸት
ዕቃዎችን በስርቆት ለማስወጣት ክፍተት ከመፍጠሩም በላይ ኤየር ዌይ ቢል /AWB/
የሌለው ዕቃ በሚመጣበትም ወቅት ምዝገባ የማይካሄድ በመሆኑ እንደዚሁ ለስርቆት
በከፍተኛ ሁኔታ ሊጋለጥ እንደሚችል የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት በሲስተሙ ላይ የተጫነው መረጃ እንዳይጠፋ በ /back up/


የሚያዝበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣ ታጉ ተገንጥሎ የሚመጣውን ዕቃ ወዲያውኑ ቁጥር
ተሰጥቶት የሚመዘገብበትን አሰራር መዘርጋት፣ በሰነድ /Hard Copy/ የሚያዙ መረጃ
ዎች ቅብብሎሽና አያያዝ ግልፅነትና ተጠያቂነት ሊያሳይ የሚችል አሰራር መዘርጋት፣
ወደመጋዘን የገቡ ለሚመለከተው የተላለፉ በመጋዘን ቀሪ የሆኑትን የጊዜ ገደብ በማስቀመ
ጥ ማመዛዘኛ የሚሰራበት ሁኔታ ማመቻቸት /በሳምንት ወይም በወር ሊሰራ ቢቻል/ እና
የብተና ሥራ የሚያከናውነው ሠራተኛ ዕቃዎች ሁሉ ወደሚመለከተው አካል
የተላኩና የተደረደሩ መሆናቸውን ሊያረጋግጥ የሚችልበት ሥርዓት መዘርጋት በጥናቱ
የቀረቡ የመፍትሄ ሀሳቦች ናቸው፡፡

ለደንበኞች አገልግሎት የካሳ ክፍያ ጥያቄ ሲቀርብ ወጥ የሆኑ መረጃዎች ተሟልተውና


ተያይዘው አለመቅረባቸው ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ ሁኔታ ነው፡፡

ለካሳ ክፍያ ወደ ደንበኞች አገልግሎት የሚላኩ ዶክመንቶች ዕቃዎቹ ስለመጥፋታቸ


ው ሊያረጋግጡ ይችላሉ የተባሉትን ሰነዶች ሁሉ ማካተት ስለሚጠበቅበት መልዕክት
ልውውጦች፣ ካርጎ ማኒፌስት…ወዘተ ተያይዞ በመሸኛ ደብዳቤ ከካርጎ ማርኬቲንግ
ለደንበኞች አገልግሎት ይላካል፡፡ ሆኖም በመረጃ አሰባሰቡ ወቅት ለካሳ ክፍያ የተላኩ
ሰነዶች የተሟሉ ያለመሆናቸው በመሸኛ ደብዳቤ ላይ ተገልፀውና በውስጡ የተያያዙት
ያለመጣጣማቸውን ሰነዶቹ በተፈተሹበት ወቅት የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡ ይህ
ም ተጠያቂነት በሌለበት ሁኔታ የመረጃ ክፍተቶች እየተፈጠሩ ገቢ ያልሆነው እንደገባ
ተቆጥሮ እንዲሁም አነስተኛ ዋጋ ያለው ዕቃ እንደጠፋ ተቆጥሮ በተሻለ ዋጋ ካሳ
ሊጠየቅበት ስለሚችል ተገቢ ላልሆነ ከፍተኛ ወጪ ሊዳርግ የሚችል አሰራር ሆኖ
ይታያል፡፡

አስፈላጊ የተባሉ ሰነዶች በሚመለከታቸው የሥራ ዘርፎች በአግባቡ ተፈትሸው


ዕቃዎቹ መጥፋታቸውን ለማረጋገጥ /ለማፈላለግ/ ዋናው ጠቃሚ መረጃ ሆኖ የሚያገለግለው
የ/AWB/ ቁጥር በመሆኑ በሚተላለፉ መልዕክቶች ላይ የተለየ ትኩረት እንዲሰጠው
ማድረግ፣ በመሸኛ ደብዳቤው ላይ የተገለፁት ሰነዶች ሁሉ በአግባቡ መያያዛቸውና
መጣጣማቸው ብሎም መረጃዎቹ በትክክል መሞላታቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው።
ይህንንም የሚያዘጋጁና የሚያረጋግጡ ሠራተኞች ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ
እና በሰነድ ቅብብሎሹ ወቅት በአባሪ ተያያዙ የተባሉት ሁሉ ለመኖራቸው በተገቢው
ሁኔታ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ሰነዶች ለፊርማ ቀርበው ከተፈረሙ በኋላ ከደጋፊ
ሰነዶች ጋር ባልተገናኘ ሁኔታ ወደ ደንበኞች አገልግሎት መላካቸውን በማረጋገጥ
የአሰራር ሥርዓት ችግሮቹን ለመፍታት እንደሚቻል ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

ይሁንና ካለው የሥራ ብዛትና ጫና አንፃር የመረጃዎቹ ትክክለኛነት ሳይረጋገጥና

39
ተገቢው መረጃ ሳይያያዝ ሊያልፍ ይችላል፡፡ ስለዚህ በመሸኛ ደብዳቤዎቹ ላይ የተቀመጡ
ትን እንደ ቼክ ሊስት መጠቀምና መልዕክት ልውውጦች ላይ የተቀመጠው /AWB/ ቁጥር
ትክክል መሆኑን አረጋግጦ የሚያቀርበው እና የሚላከውን ሰነድ የሚያዘጋጀው
ሠራተኛ በቅፁ ላይ ስምና ፊርማ ሊካተት የሚያስችል አሰራር ቢዘረጋ ተጠያቂነትን
ያጎለብታል፡፡

ከካርጎ ጭነት ጋር በተያያዘ በጭነቶች እንቅስቃሴ ዙሪያ የሚሰሩ ቁልፍ የሥራ


መደቦች ላይ በቂ የሰው ሃይል ያለመኖርና ኃላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል ሁኔታ
አለመፈጠሩ ድርጅቱን ለሙስና የሚያጋልጥ ሁኔታ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል፡፡

በመረጃ ማሰባሰብ ወቅት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የጉልበት ሠራተኞች


እና ጂ ኤስ ኦፕሬተሮች ሥራ በበዛበት እየተመደቡ /እየተዘዋወሩ/ የሚሰሩ መሆናቸው፣
የጉልበት ሠራተኞች በአብዛኛው ጊዚያዊ ሠራተኞች በመሆናቸው በባለቤትነት ስሜት
መስራቱ ብዙም የሚታይ ያለመሆኑ፣ እንዲሁም ጂ ኤስ ኦፕሬተሮች በተመሳሳይ
መልኩ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩና ተጨማሪ ብዙ ሰዓት የሚሰሩ በመሆናቸው መሰላ
ቸትና መድከምን በማስከተሉ ዕቃዎች በአግባቡ እናዳይጫኑ፣ እንዳይመዘገቡ /ስካን/
እንዳይደረጉ አስተዋፅኦ በማድረጋቸው ለዕቃዎች መጥፋት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

ይህን ችግር ለማቃለል አየር መንገዱ ባለው መዋቅር ያሉት ክፍት የሥራ መደቦች
በአብዛኛው የተሟላና በሂደትም ላይ ያለ መሆኑ /ከላይ በተገለፀ/ የሥራ መደቦች መረ
ጃው የሚጠቁም ቢሆንም ከዚህ ባለፈ ሁኔታ የሰው ሃይሉ ከሥራው ጋር መጣጣሙን
በድጋሚ በመፈተሽና ተገቢውን ጥናት በማካሄድ በውጤቱ መሰረት ሊስተካከል
የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ወሳኝ እንደሆነ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

በአየር መንገዱና በኤርፖርት ደህንነት /ኤርፖርት ሴኩሪቲ/ መካከል የእቃዎች


ጥበቃና ቁጥጥርን በተመለከተ ግልፅ የሆነ አሰራር አለመኖር በጥናቱ የተጠቆመ የአሰራር
ሥርዓት ክፍተት ነው፡፡

በመረጃ ማሰባሰቡ ወቅት የተገኘው መረጃ በአየር መንገዱ በኩል ዕቃዎች ከአውሮፕላ
ን እስከ መጋዘን እስከሚደርሱ ብሎም በመጋዘን አካባቢ በሚከማቹበትም ሆነ ከመጋዘን
ወደ አውሮፕላን በሚጓጓዙበት ወቅት የእቃዎቹ ቁጥጥር በደህንነቱ አማካኝነት
እንደሚከናወን ይገልፃል፡፡ የኤርፖርት ሴኩሪቲ በበኩሉ ሥራው ከዕቃው ጋር ለደህንነ
ት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ በተለይ በወጪ ዕቃዎች ላይ የሚያተኩር ሆኖ በኤክስሬ
ይ ማሽን ካለፉ በኋላ ንኪኪ እንዳይፈጠር ብሎም የአውሮፕላንና የደንበኞችን ደህንነት
በተመለከተ ቁጥጥር እንደሚያደርግና ለዕቃዎቹ መጥፋት ኃላፊነት የሌለበት መሆኑን
በአፅንኦት ይገልፃል፡፡ ይህ ሁኔታ ዕቃዎች ከአውሮፕላን ወርደው በመጋዘን እስከሚገቡ
በሜዳው ላይ በሚቆዩበት ጊዜ ዕቃዎችን የሚቆጣጠር አካል ያለመኖሩን ከማመልከቱ
በላይ የዕቃዎች መጥፋት ቢከሰትም በዚህ ሂደት መጥፋቱን ለማረጋገጥ ያለመቻሉና
በሁለቱም በኩል ዕቃዎችን በተመለከተ ተጠያቂ የሌለበት አሰራር መኖሩን ይጠቁማል፡፡

አየር መንገዱ ከኤርፖርት ደህንነትና ሌሎች ከሚመለከታቸው የሥራ ዘርፎች ጋር

40
ከዕቃዎች ጥበቃና ቁጥጥር አንፃር ሊከናወኑ የሚገባቸውን ተግባሮች በመለየትና በመ
ወያየት በግልፅ መረዳት፣ በአየር መንገዱ በኩል ሊወሰድ የሚገባውን እርምጃ አጥንቶ
መተግበር እና በተወሰነ የጊዜ ገደብ ቋሚ የጋራ መድረክ በመፍጠር የቅንጅት ሥራው
ን በተጠናከረ መንገድ እንዲከናወንና ለችግሮቹም በወቅቱ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት
ማድረግ የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመቅረፍ በጥናቱ የተጠቆመ ሊተገበር የሚገባው
መፍትሄ ነው፡፡

በመጨረሻ በድርጅቱ ውስጥ በጥናቱ የተቃኘና የተገኘ የአሰራር ሥርዓት ችግር


በካርጎ መጋዘን የሚገኙ ዕቃዎችን በኃላፊነት የሚረከብ አካል አለመኖርና የቆጠራ ሥርዓቱ
ደካማ ሆኖ መታየቱ ነው፡፡

በመጋዘኑ ውስጥ በየመደርደሪያዎቹ ላይ የተቀመጡትን እቃዎች ፎርክ ሊፍት


ሠራተኛው /GS Operator/ ከመጫኑና ከማውረዱ ውጪ ለዕቃዎቹ ኃላፊነት ወስዶ
የሚቆጣጠር አካል አለመኖሩን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በመጋዘን ውስጥ
በየሳምንቱ እሁድ ቀን ቆጠራ የሚካሄድ መሆኑ ቢገለፅም በአግባቡ ማለትም አስቆጣሪ
በሌለበት አንድ የትራንስፖርት ኤጀንት በዝርዝር የተመዘገቡ ዕቃዎችን በሲስተሙ ላይ
በተመዘገበው ቦታ ላይ መኖራቸውን ለማረጋገጥ ይጠቅማል በሚል ታሳቢ ብቻ የሚከናወን
መሆኑ በተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ይህም ተጨማሪ ዕቃዎች በመጋዘን
ቢኖር /መጋዘን ውስጥ ያልገቡ ጭምር/ ለመለየት ያለማስቻሉ፣ በመጋዘን ውስጥም ሆነ
ያልተመዘገበ ዕቃ ቢኖር ለመለየት አስቸጋሪ ከመሆኑም ባሻገር ያልተመዘገቡ ዕቃዎችን
ጊዜና አመቺ ሁኔታን ጠብቆና አመቻችቶ ለማውጣት ምቹ ሁኔታን ሊፈጥር የሚችልና
ተጠያቂነት የሌለበት አሰራር ሆኖ ይታያል፡፡

መደርደሪያዎቹን ለመቆጣጠር የሚያስችል በቂ የካሜራ ተከላና /ተንቀሳቃሽ ካሜራን


ጨምሮ/ የተጠናከረ ቁጥጥር ከማድረግ በተጨማሪ የሚታዩ ችግሮች በሚኖርበት
ወቅት ተጠያቂነትን ማጠናከር፣ ቆጠራ ሲካሄድ በሲስተሙ ላይ በተመዘገበው ቦታ
ላይ /location/ መኖሩን ከማረጋገጥ በተጨማሪ በአጠቃላይ በመጋዘኑ ውስጥና ውጪ
ያሉትን ዕቃዎች አስቆጣሪ ባለበት እንዲቆጠር ማድረግ፣ የኃላፊው ስምና ፊርማ
በግልፅ የሚቀመጥበት ትርፍና ጉድለት በአግባቡ ለመመዝገብ የሚያስችል አሰራር
እንዲኖርና የሚመለከታቸው ሁሉ እንዲፈርሙ በማድረግ ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን
ማጠናከርና በትርፍና በጉድለት የተመዘገቡት ዕቃዎች ቆጠራው በተደረገበት ቀጣይ
የሥራ ቀናት የሚመለከታቸው የበላይ ኃላፊ እንዲያውቁት ቢደረግ፣ ሲስተሙ በራሱ
መረጃውን ሊያስተላልፍ የሚችልበት ሁኔታ ከተቻለ ማመቻቸት የአሰራር ሥርዓት
ችግሩን ለመፍታት በጥናቱ የተጠቆሙ መፍትሄዎች ናቸው፡፡

የመፍትሄ ሃሳቦቹን ለመተግበር በሲስተሙ ላይ ሶፍት ዌር ለመጫን የሚያስችል


የተያዘ በጀት ላይኖር ስለሚችል በእቅድ አስገብቶ በጀት ሊመደብ የሚችልበት ሁኔታ
ማመቻቸት የመፍትሄ ትግበራዎቹን ተከትሎ መወሰድ የሚገባው እርምጃ ነው፡፡

41
በብሔራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት የኢሚግሬሽንና
ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ የመንገደኞች የይለፍ ማረጋገጫ
አሰጣጥ እና የአገልግሎት ክፍያ ገንዘብ ገቢ አሰባሰብ የአሰራር ሥርዓት

በ መምሪያው በይለፍ ማረጋገጫ አሰራር ስርዓት ላይ ለሙስናና ብልሹ አሰራር


የሚያጋልጡ ተብለው በጥናቱ ከቀረቡት ሁኔታዎች ውስጥ የመረጃ አያያዝና ዘመናዊ
ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደካማ መሆን አንዱ ነው፡፡

ይህን የአሰራር ሥርዓት ችግር ለመፍታት የተሟላና ኮምፒውተራይዝድ የሆነ


የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በዌብሳይት ግንኙነት መፍጠርና
መረጃ መለዋወጥ፣ አስፈላጊ ሰነዶችና ማጣቀሻዎች/references/ በሥራ ክፍሉ እንዲ
ኖሩ ማድረግና የመንገደኞችን እንቅስቃሴ መሠረት ያደረገ የተጠናከረ ሪፖርት አቀራረ
ብ፣ የመረጃ አጠቃቀምና አያያዝ ሥርዓት በመዘርጋት መሥራት በመፍትሄ ሀሳብነት
በጥናቱ ቀርበዋል፡፡ ይህም የሥራ ክፍሉን አገልግሎት ተጠያቂነትና ግልፅነት የተከተለ
ከማድረግም በተጨማሪ ለግል አመለካከት የመጋለጥ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል፡፡
ለመረጃ ተጠቃሚ /ለውስጥና ለውጭ/ አካላት የሚፈለገውን አገልግሎት ለማቅረብ
ያስችላል፡፡

ለመ/ቤቱ የሚያገለግል የሥነምግባር መመሪያ አለመኖር ሌላው በጥናቱ የታየ ለሙስና


እና ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥር ሁኔታ ነው፡፡ ለሠራተኞች የሚያገለግል የሥነም
ግባር መመሪያ ባለመኖሩ ጠንካራና አስተማሪ የሆነ አስተዳደራዊና የዲሲፕሊን እርምጃ
ስለማይወሰድ ደላሎች፣ የካውንተር ሠራተኞችና ኃላፊዎች ተባባሪና የጥቅም ተጋሪ በመ
ሆን መንገደኞች በፎርጅድ ፓስፖርትና ቪዛ ከአገር እንዲወጡ ማድረግ፣ ቪዛ በሕገወጥ
መንገድ ከተለያዩ ኤምባሲዎች እንዲወጡና ቪዛ ከሌሎች አገሮች እንዲመጣ በማድረግ
መሸጥ፣ ቪዛ የሚሰጡ አገሮች /ኤምባሲዎች/ ለተጓዦች የሰጡትን የቪዛ ሊስትና ቁጥር
ለኢሚግሬሽን ሲልኩ ቦሌ አንዳንድ የመ/ቤቱ ሠራተኞች ዝርዝሩን የመሰረዝና የመፋቅ
ከዚያ በማመሳሰል ቪዛውን ፓስፖርት ላይ መምታት፣ ደላሎችና የካውንተር ሠራተኞች
በምን ሰዓት ማን እንዳለ በተለምዶ በመለየት መንገደኛውን መላክና በሕገወጥ መንገድ
እንዲያልፍ ማድረግ፣ ቪዛ በሚያስፈልገው ለምሳሌ ለኬንያ ፓስፖርት ብቻ ከሀገር
ስለሚያስወጣ ይህን በመረዳት በፓስፖርት ብቻ ከቦሌ መንገደኛው ካለፈ በኋላ ኬንያ
ሲደርስ የሌሎችን አገሮች ቪዛ በመለጠፍ ትራንዚት ነን እንዲሉ ማድረግ፣ ከተለያዩ አገሮች
ዲፖርትድ /deported/ የተደረጉ ተጓዦችን ኤርፖርት ከተያዙና አስፈላጊው
መረጃ ከሰነዳቸው /ፓስፖርትና ቪዛ/ በመያዝና ምርመራ መከናወን ሲገባው በጥቅማጥ
ቅምና በቸልተኝነት እንዲበተኑ ማድረግ የሚታዩ ችግሮች ናቸው፡፡

ለመ/ቤቱ ሠራተኞች የሚያገለግልና ሕጋዊ የሆነ የዲሲፕሊን እርምጃ ለመውሰድ


የሚያስችል ጠንካራ የሥነምግባር መመሪያ በማዘጋጀት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ
በጥናቱ የተጠቆመ የመፍትሔ ሀሳብ ሲሆን አስተማሪ የሆነ ሕጋዊ የዲሲፕሊን

42
እርምጃ ለመውሰድ ማስቻሉ፣ ጥሩ ሥነምግባር ያላቸው ሠራተኞች እንዲበረታቱና
እንዲበራከቱ ማድረጉና ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር እንዲሰፍን ማድረጉ
የሚሰጣቸው ጥቅሞች ናቸው፡፡

መንገደኛውን ማዕከል ያደረገ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ እንቅስቃሴ አለመኖር


በመምሪያው ክፍተት የሚፈጥር ሁኔታ ተብሎ በጥናቱ ተለይቷል፡፡ የይለፍ ማረጋገ
ጫ አሰጣጥ አሰራር ሂደት በባህሪው በየቀኑ በርካታ ተገልጋዮችና መንገደኞች የሚስተ
ናገዱበት የሥራ ክፍል ነው፡፡ ነገር ግን በአሰራር ሥርዓቱ ላይ የተገልጋዩ /መንገደኛው
የሀሳብ መስጫ አስተያየት ማቅረቢያ ቅፅም ሆነ ሳጥን አለመኖር፣ የቅሬታ ማስተናገጃ
ክፍልም ሆነ ኦፊሰር አለመደራጀት፣ ተገልጋዩ በአቅራቢው ችግሩን የሚፈታበት ሥርዓት
ያልተዘረጋ ስለሆነ ችግር ሲያጋጥመው ከቦሌ ወደ ዋናው መ/ቤት እንዲመጣ ማድረግና
ማጉላላት ስላለ ለሙስናና ብልሹ አሰራር በቀላሉ የተጋለጠ ያደርገዋል፡፡

በጥናቱ የቀረበው የመፍትሄ ሀሳብ መንገደኛው /ተገልጋዩ/ አስተያየት የሚሰጥበትን


ቅፅና ማስገቢያ ሳጥን በየቦታው በማስቀመጥና የቅሬታ አፈታት ሥርዓት በተመቻቸ
ሁኔታ የሚዘረጋበትን መንገድ በማስተካከል መሥራት ሲሆን ይህም ተገልጋዩን
ማዕከል ያደረገ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ በየወቅቱ ተግባራዊ ለማድረግ፣ የዓለም
አቀፍ ተሞክሮዎችን ወደ አገራችን ለማምጣት እና ተገልጋዩን ከማጉላላትና በጥቅም
ከመደራደር ነፃ ያደርገዋል ተብሎ ይታመናል፡፡

በቦሌ ኢሚግሬሽን የይለፍ ማረጋጋጫ የሚሰጡ የካውንተር ሠራተኞች ቢሮ የተመቻ


ቸ አለመሆን ሌላው አሠራሩን ለሙስና እና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ ሁኔታ ነው፡፡
በቦሌ ኢሚግሬሽን የይለፍ ማረጋገጫ የሥራ ክፍል በባህሪው በየቀኑ በርካታ ተገልጋዮ
ችንና መንገደኞች የሚስተናገዱበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ቢሆንም በአሰራር ሥርዓቱ ላይ
የካውንተር ሠራተኞች የቢሮ በሮች አውቶማቲክ አለመሆንና ከፊትና ከኋላ ለመንገደኞ
ች አገልግሎት ስለሚሰጥ በቂ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ ስለማይመች መንገደኞች
ተደራርበው ለማለፍ የሚችሉበትን ሁኔታ እንዳለ ይታወቃል፡፡

የካውንተር ሠራተኞች የቢሮ በሮችን አውቶማቲክ በማድረግና ከፊትና ከኋላ ለመንገደ


ኞች አገልግሎት ስለሚሰጥ በቂ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ እንዲያመች መንገደኞች
የሚቆሙበትን ቦታ የቀለም /ቢጫና ቀይ/ መስመር በመቀባት ቢሰራ በቂ ክትትልና
ቁጥጥር ለማድረግ ስለሚያስችል ተጠያቂነትና ግልፅነትን የተከተለ አሰራር ስለሚያመጣ
በጥናቱ ወሳኝ መፍትሔ ተብሎ ተጠቁሟል፡፡

በአገልግሎት ክፍያ ገንዘብ ገቢ አሰባሰብ የአሰራር ሥርዓት መ/ቤቱን ለሙስናና


ብልሹ አሰራር ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች ውስጥ የመንግሥትን የፋይናንስ ሕግ፣ ደንብና
መመሪያን የተከተለ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና የአገልግሎት ክፍያ ገንዘብ ገቢ አሰባሰብ
ሥርዓትን አለመከተል አንዱ ነው፡፡

የመንግሥትን የፋይናንስ ሕግ፣ ደንብና መመሪያን የተከተለ የፋይናንስ አስተዳደር


አሰራር ሥርዓት ባለመዘርጋቱ ምክንያት የሚከተሉት ችግሮች በጥናቱ ታይተዋል፡፡

43
ከአገልግሎት የሚሰበሰብ ገንዘብ በየእለቱ ወደ ባንክ ገቢ አለማድረግ፣ ከመጠን በላይ
በካዝና ገንዘብ ማሳደር፣ የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች በየዕለቱ የሚሰበስቡትን ገንዘብ
አግባብ ያለው ወቅታዊ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገበት ለባንክ ገቢ አለመሆን፣
የሂሳብ ምዝገባ በየቀኑ ስለማይመዘገብ አግባብ ያለውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ
አለመቻልና የገቢ ሒሳብ ምዝገባ ሳይከናወን ለረጅም ወራት ማከማቸት፣ የገቢ
ሒሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ በኮምፒውተር በየጊዜው ስለማይመዘገብ ሒሳቡን በወቅቱ
አለመዝጋት፣ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኞች አያያዝና አጠቃቀም ብክነት ያለበት መሆንና
ተከታታይነት አለመኖርና እና የሚሰበሰበው ገንዘብና ወደ ባንክ ገቢ የሚሆነው ገንዘ
ብ ከደረሰኞች ጋር በወቅቱና በዕለቱ ማመዛዘኛ /balance/ አለመሰራት…ወዘተ ናቸው፡፡

ችግሩን ለመፍታት የመ/ቤቱ የአገልግሎት ክፍያ ገቢ ገንዘብ አሰባሰብ፣ የሂሳብ አያያ


ዝና የደረሰኞች አጠቃቀም የመንግስትን የፋይናንስ ሕግ፣ ደንብና መመሪያ በተከተለ
መንገድ እንዲሰራ ማድረግ በጥናቱ የተጠቆመ የመፍትሔ ሀሳብ ሲሆን የዕለት
ሰብሳቢ ገንዘብ ከግለሰቦች መጠቀሚያነት ዝርፊያ ያድናል፣ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ደረሰኞች
በአግባቡ እንዲያዙ ያደርጋል፣ የመንግስትን ደንብና መመሪያ እንዲተገብር
ስለሚያደርግ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥሩ ሁኔታዎችን ያስቀራል፡፡

መምሪያውን ለሙስናና ብልሹ አሰራር ከሚጋብዙ ሁኔታዎች የመረጃና የሪፖርት


አቀራረብ፣ አያያዝና አጠቃቀም ስርዓት ደካማ መሆን በጥናቱ የታየ የአሰራር ክፍተት
የሚፈጥር ሁኔታ ነው።

በሥራ ክፍሉ የሚከናወኑ ተግባራት ወጥነት ባለው መልኩ ዕቅድ /ዓመታዊ፣


የ6፣ የ3፣ የ1 ወር እና የ15 ቀናት/ ወጥቶላቸው አለመስራት፣ ዕቅድን መሠረት
ያደረገ የሥራ አፈፃፀም ባለመኖሩ ውዝፍ ሥራዎች በመብዛታቸው ምክንያት ሥራዎ
ችን በዘመቻ በመስራት የሥራ ጫና መኖር፣ የቢሮ ጥበት በመኖሩ የፋይል መደርደሪያ
ሼልፍ በአግባቡ ተቀምጠው ፋይሎች በዓመታትና በየወሩ ተለይተው በቀላሉ የሚገኙ
ና የተደራጁ አለመሆኑ ምክንያት ለክትትልና ለቁጥጥር አለመመቸት፣ ከክልል ኬላዎች
ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ጋር የተቀናጀ ግንኙነት ባለመኖሩ የሰበሰቡትን ገንዘብ በወቅቱ
በባንክ በኩል ፈሰስ አድርገው ማስረጃውን እንዲልኩ አለማድረግና የገቢ ደረሰኝ በወቅቱ
አለመስራት፣ ፋይሊንግ ሲስተሙ በዘመናዊ መልክ የተደራጁ አለመሆን፣ ከገንዘብና ኢኮ
ኖሚ ልማት ሚኒስቴር ማዕከላዊ ሒሳብ መምሪያ ጋር ተናቦ ሪፖርቶችን በወቅቱ አለማ
ዘጋጀት ይህም በገቢ ሒሳቦች አመዘጋገብ ላይ በሦስቱ ተቋማት /ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት
ሚኒስቴር፣ ብሔራዊ ባንክና በመሥሪያ ቤቱ/ መካከል ልዩነት መኖር ለምሳሌ ከክልል
የሚመጡ የገቢ ሰነዶች ለመ/ቤቱ ደርሰው ብሔራዊ ባንክና ሚኒስቴር መ/ቤቱ ያልደረ
ሳቸው መሆን፣ የባንክ ሒሳብ ማስታረቂያ አለመስራትና ሪፖርት አለማዘጋጀት፣ የተ
ለያዩ ገቢዎችን ተከታትሎ የገቢ ደረሰኝ በማዘጋጀትና ገቢ በማድረግ በወቅቱ ለገንዘብና
ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር ፈሰስ እንዲሆን አለማድረግ፣ ከባንክ ወደ ሚኒስቴር መ/ቤቱ
የገባውን ሒሳብ በወቅቱ የገቢ ደረሰኝ እንዲዘጋጅለት አለማድረግ የሚታዩ ችግሮች
ናቸው፡፡
ለዚህ የአሰራር ሥርዓት ችግር በጥናቱ የቀረበው የመፍትሔ ሀሳብ በሥራ ክፍሉ
የሚከናወኑ ሥራዎች ዕቅድ በማውጣት ዕቅዱን መሠረት ያደረገ አፈፃፀም እንዲኖር

44
በማድረግ፣ ሪፖርቶችን ወቅታዊና አግባብ ባለው መልኩ በማዘገጀትና ለሚመለከታ
ቸው አካላት በማቅረብ የተደራጀ የመረጃና የሪፖርት አቀራረብ፣ አያያዝና አጠቃቀም
ሥርዓት መዘርጋት ሲሆን ይህም ጠንካራ የመረጃና የሪፖርት አቀራረብ፣ አያያዝና
አጠቃቀም ስርዓት እንዲኖር ያደርጋል፤ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥ
ሩ ሁኔታዎችን ይከላከላል፡፡ ችግሮችን በቀላሉና በወቅቱ በመለየት የማስተካከያ ዕርምጃ
ለመውሰድ ያስችላል፡፡

በመ/ቤቱ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ጠንካራ አለመሆን አንዱ የአሰራር ሥርዓት


ክፍተት ነው፡፡ መ/ቤቱ ለመንግሥት ከፍተኛ ገቢ ከሚሰበስቡት ተቋማት መካከል አንዱ
ነው። ይሁንና የፋይናንስ አስተዳደርና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ተገቢውን ክትትልና ቁጥ
ጥር ለማከናወን የሚችል የውስጥ ኦዲት የሥራ ክፍል የለውም፡፡ ስለሆነም ወቅታዊና
ድንገተኛ ኦዲት በአግባቡ ስለማይደረግ የሚሰበሰበው ገቢ በትክክል ለመንግስት ገቢ መደረ
ጉን አለማረጋገጥ፣ በሚፈጠሩ ችግሮች ላይ ወቅታዊ የማስተካከያ እርምጃ አለመውሰድ፣
በፌዴራል ዋናው ኦዲተር መ/ቤት ዓመታዊ ኦዲት ሪፖርት መሠረት የማሻሻያ ሥራ
አለማከናወን በመኖሩ ምክንያት የአሰራር ስርዓቱ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ
እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

በመ/ቤቱ የውስጥ ኦዲት የሥራ ክፍል በማቋቋም የመ/ቤቱን የፋይናንስ እንቅስቃሴ


በሚመለከት ዝርዝር ምርመራ /ወቅታዊ፣ ወርሀዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት
የዘጠኝ ወራት፣ የዓመትና የድንገተኛ የፋይናንስና ክዋኔ ኦዲት/ በማድረግ በሚገኙ
ችግሮች ላይ ወቅታዊ የመፍትሔ ሀሳብ በማስተካከያ እርምጃው ላይ ተገቢውን ክት
ትልና ግምገማ በየወቅቱ በማድረግ መስራት መ/ቤቱን ለብልሹ አሰራር ከመጋለጥ
ያድነዋል፡፡

በአገልግሎት ክፍያ ገንዘብ ገቢ አሰባሰብ እና በይለፍ ማረጋገጫና አሳጣጥ አሰራር


ሥርዓት ላይ መ/ቤቱን ለሙስናና ብልሹ አሰራር ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች በአገል
ግሎት ክፍያ ገንዘብ ገቢ አሰባሰብ እና በይለፍ ማረጋገጫ አሰጣጥ የሥራ ክፍሎች
ተመድበው /ተቀጥረው/ የሚሰሩ ሠራተኞች ብቃትና ክህሎታቸው አነስተኛ መሆን
አንዱ ነው፡፡

በመ/ቤቱ በሁለቱም የሥራ ክፍሎች ተመድበው/ተቀጥረው የሚሰሩ አብዛኛዎቹ


ሠራተኞች ብቃታቸውና ክህሎታቸው አነስተኛ መሆን ይታያል፡፡ ይህም ሲባል
የትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ መሆን፣ ከአነስተኛ ሥራ ካለበቂ የትምህርት ዝግጅትና
የሥራ ልምድ ሙያዊ ብቃት ማነስና ክህሎትን ለማሳደግ የሚደረግ ጥረት አለመኖር እን
ዲሁም ከመ/ቤቱ ሥራና የተበታተነ የሥራ ባህርይ አንፃር በየአገልግሎት መስጫ የሥራ
ክፍሎች በቂ ባለሙያ አለመመደብ በሁለቱም የሥራ ክፍሎች ያሉ ችግሮች ናቸው፡፡
ስለሆነም በገቢ አሰባሰብ ዙሪያ የመንግስትን ደንብና መመሪያዎች ያለማወቅና ያለመገ
ንዘብ ሁኔታ በመኖሩ ተግባራዊ ለማድረግ የሚቸገሩ ሲሆን በይለፍ ማረጋገጫ የሥራ
ክፍልም የሥራ መደብ ወጥቶለት ለመደቡ የሚጠየቀው የትምህርት ዝግጅትና የሥራ
ልምድ ያልወጣለት መሆን፣ በትምህርት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መሆንና በቀላሉ የውጪ
ቋንቋዎችን የመረዳትና ከውጪ ዜጎች ጋር የመግባባት ችግር መኖር መ/ቤቱም በሥራ

45
ላይ ሥልጠና የሚሰጥ ቢሆንም እንኳን የፎርጀሪና ማጭበርበር መንገዶች እንደ ወቅታ
ዊ ቴክኖሎጂ የሚሻሻሉና የሚለወጡ በመሆኑ በብቃት ለመከላከል የሚያስችል የአሰራር
ሥርዓት አልተዘረጋለትም፡፡ ስለዚህ በሁለቱም የሥራ ክፍሎች የሚሰራበት የአሠራር
ሥርዓት በቀላሉ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተት ለሚፈጥሩ ሁኔታዎች የተመቻቸ
ነው፡፡

የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት በሥራ ክፍሎች አሰራር ሥርዓት ላይ በባለሙያ


እጥረት ምክንያት እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ብቃትና ክህሎት ያለውን ባለሙ
ያ ለማስመደብ ወይም ለመቅጠር በቅድሚያ ለሥራ መደቦች የሚያስፈልገውን የትምህ
ርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ እንዲወጣለት በማድረግ ማሟላት፣ ከዚህም በተጨማሪ
አዲስ ሠራተኞች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ስለአሰራሩ በቂ ስልጠና የሚያገኙበት
ሁኔታ ማመቻቸትና በሥራ ላይ እያሉ የማጠናከሪያ ሥልጠና እንዲሰጥ ማድረግ
በጥናቱ የተጠቆመ የመፍትሄ ሀሳቦች ናቸው፡፡

በሁለቱም የሥራ ክፍሎች ያሉ ሠራተኞች ለሥራቸው የሚጠቀሙበት የሥራ መዘርዝ


ር እና የሥራ መመሪያ /ማንዋል/ አለመኖር በመ/ቤቱ በጥናቱ የታየ የአሰራር ሥርዓት
ክፍተት ነው፡፡ የመ/ቤቱ ሠራተኞች ለሚሰሩት ማንኛውም ሥራ ሊጠቀሙበት የሚችል
ግልፅ የሆነ የሥራ መዘርዝርና ለሥራ ክፍሉ የሥራ መመሪያ /ማንዋል/ ያስፈልጋል፡፡
ነገር ግን ጥናቱ በተካሄደባቸው ሁለቱ የሥራ ክፍሎች ያሉ ሠራተኞች የሥራ መዘርዝ
ር ያልተሰጣቸው ከመሆኑ በተጨማሪ በተጓዳኝ ለሥራ ክፍሉ የሚያገለግሉ የሥራ
መመሪያና ማንዋል ባለመኖሩ ምክንያት የሚከተሉት ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ የሥራ ክፍሎ
ችን የሚመሩ የሥራ ኃላፊዎች ሥራውን የሚመሩት በግልፅ መመሪያ ሳይሆን በልምድ፣
በቃል ትዕዛዝ እና በማስታወሻ መሆኑ፣ ይህ ዓይነቱ አሰራር ደግሞ ግለሰቦች እንደፈለጉ
ት ሥራውን የሚመሩበት በመሆኑ በተፈለገው ጊዜ የሚሰራበት በማይመች ጊዜ እንዲቆ
ም የሚታዘዝበት አሰራር ዘይቤ እንዲከተልና ለግለሰብ አመለካከት የተጋለጠ ያደርገዋል፡፡
ሠራተኛውም ይህን አሰራር መከተሉ ይህ አግባብና መመሪያን የተከተለ አሰራር ነው ወይ
ም ይህኛው አሰራር መመሪያን ያልተከተለ ነው ብሎ ለመከራከር የሚያቀርበው ማስረጃና
የሚያጣቅሰው በግልፅ በመመሪያም የተደገፈም ሆነ የሥራ መዘርዝር በእጁ ይዞና
አስቀድሞ አውቆት እንዲሰራ አልተደረገም፡፡ ስለሆነም ሠራተኛው የሚጠበቅበትን
ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችልና ካልተወጣም የሚጠየቅበትን መንገድ
በመከተል ተጠያቂነትና ግልፅነትን የተከተለ የሥራ አፈፃፀም እንዳይኖር አድርጎታል፡፡

ሠራተኛው ሊጠቀምበት የሚችል የሥራ መዘርዝር እና ለሥራ ክፍሉ ሊያገለግል


የሚችል የሥራ መመሪያና ማንዋሎችን በማዘጋጀት መስራት በጥናቱ የተቀመጠ
የመፍትሔ ሀሳብ ሲሆን መፍትሄው ሲተገበር የሥራ መዘርዝርና መመሪያ/ ማንዋል
ለማዘጋጀት ረጅም ጊዜ ሊወስድ እና ከተለመደው አሰራር ውጪ በመሆን የሥራ
መመሪያና የሥራ መዘርዝር ለማዘጋጀት ተነሳሽነት ላይኖር ስለሚችል የሥራ
ኃላፊዎች የሥራ መመሪያውና የሥራ መዘርዝር መኖሩን አስፈላጊነት በመገንዘብ
አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በአጭር ጊዜ ተዘጋጅቶ ለእያንዳንዱ
ሠራተኛና የሥራ ክፍል የሚሠጥበትን ሁኔታ ማመቻቸት የመፍትሄ ትግበራውን ተከትሎ
መወሰድ ያለበት እርምጃ መሆኑም በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡

46
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቤቶች አስተዳደር አሰራር ሥርዓት

በ ዩኒቨርሲቲው ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ክፍተት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሁኔታዎች


ተብለው በጥናቱ ከተጠቆሙት ውስጥ ግልፅ የሆነ የሥራ መመሪያ አለመኖር አንዱ
ነው፡፡

በዩኒቨርሲቲው ለቤት ድልደላ በማገልገል ላይ ያለው የመኖሪያ ቤቶች አስተዳደር


መመሪያ በርካታ ጉድለቶች ያሉበት ሆኖ ይታያል፡፡ ለአብነትም ከትርጓሜ አንቀፅ 2(2.2.2)
የበላይ ኃላፊ ትርጓሜ በጣም ሰፊ መሆን እና የቤተሰብና ዘመድ ትርጉም የሌለበት፣
አንቀፅ 4(4.6) የዩኒቨርሲቲ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ሠራተኞች…
እንደ ሥራ ውላቸው ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች /ባለሙያዎች/ በሚል በጥቅል የተቀመጠ
መሆን፣ አንቀፅ 7(3) የቤት ድልደላ ኮሚቴ ጊዜያዊ የመኖሪያ /የማረፊያ/ ቤት ጥያቄዎ
ችን አይመለከትም ሲል በሌላ በኩል ደግሞ አንቀፅ 8(2.2) የመኖሪያ ቤት አጠቃቀም
ን ውጤታማነት ከማረጋገጥ አንፃር ኮሚቴው የመኖሪያ ቤት ለተጠቃሚው በጊዜያዊነት
እንዲሰጥ ሊወስን እንደሚችል ተገልጿል፡፡

47
በተለያዩ ምክንያቶች ባለሁለት መኝታ ቤትን ብቸኛ ለሆነ ተጠቃሚ በጊዜያዊነት
መፍቀድ… ወዘተ የሚሉ እርስ በርስ የሚጣረሱ አንቀፆች መኖር፣ በአንቀፅ 7(2)
መሠረት የመኖሪያ ቤት ድልደላ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለአስተዳደርና ልማት ምክትል
ፕሬዝዳንት ይሆናል ሲል በአንቀፅ 7(4) መሠረት ደግሞ ኮሚቴው 8 አባላት እንደ
ሚኖሩትና ከነዚህም መካከል የአስተዳደርና ልማት ተባባሪ ም/ፕሬዝዳንት እንደ አባል
ድምፅ የሚሰጥ መሆኑን ይገልፃል፡፡

ስለሆነም ዩኒቨርሲቲው ለቤት ድልደላ እየተጠቀመበት ያለው የመኖሪያ ቤቶች አስተዳደ


ር መመሪያ ክፍተቶች ያሉበት በመሆኑ ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ እንዲሆን ሁኔታዎ
ችን ያመቻቻል፡፡

የወጣውን መመሪያ ክፍተቶች ሊያስወግድ በሚችል መልኩ በማሻሻል እንደገና እንዲዘ


ጋጅ ቢደረግ እና የተለያዩ ሁኔታዎች /special cases/ የሚታዩበት መንገድ ለዩኒቨርሲ
ቲው ፕሬዝዳንት ሥልጣን የሚሰጥ ቢሆን ይህን ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ የመኖሪያ
ቤት ድልደላ ሂደት ለመፍታት እንደሚረዳ የቀረበ የመፍትሄ ሀሳብ ነው፡፡

የዩኒቨርስቲው የመኖሪያ ቤት ድልደላ ኮሚቴ የቤቶች አስተዳደር መመሪያን መሠረት


ያደረገ አሰራርን አለመከተል ሌላው ለሙስና እና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ ሁኔታ
ነው፡፡ የመኖሪያ ቤት ድልደላ ኮሚቴ ተቋቁሞ ለተጠቃሚ በየጊዜው ቤቶችን በመስጠት
ላይ ይገኛል። ነገር ግን ኮሚቴው ያለውን መመሪያ መሠረት እያደረገ ይሠራል ለማለት
ያስቸግራል፡፡ ለምሳሌ አንቀፅ 5(5.1) የራሱ የሆነ የመኖሪያ ቤት በአዲስ አበባ ክልል
ውስጥ ካለው አይሰጠውም ይላል፡፡ ነገር ግን ኮሚቴው አመልካቹ መኖሪያ ቤት
ስላለመኖሩ ማረጋገጫ ሰነድ እንኳን አይጠይቅም፤ መከታተያና መቆጣጠሪያ ስልትም
አልተቀየሰም፡፡

አንቀፅ 7(5.2(ሐ)1) ኮሚቴው ጥያቄውን በሚመረምርበት ጊዜ እና የቤት ደረጃና


ዓይነት ለመመደብ የቤተሰብ ሁኔታ /ብዛት/ ያያል ይላል፡፡ በተመሳሳይ
አንቀፅ 8.2(1)፣ 7(5.1(ለ))፣ 7(5.2(መ))፣ 4(8)፣ 6(2)፣ 6(3)፣ 12(2)(3)…
ወዘተ መመሪያውን የተከተለ አፈፃፀም አይደለም፡፡ ስለሆነም የመኖሪያ ቤቶች ድልደ
ላ አሰራርን ኢፍትሐዊ፣ ተጠያቂነትና ግልፅነትን የተከተለ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡

በአሰራር ሥርዓቱ ላይ ለተጠቀሱት የመመሪያው ክፍተቶች ማሻሻያ ማድረግ እንዳለ


ሆኖ ቤት ፈላጊዎች በሰነድ የተደገፈ ማስረጃ እንዲያቀርቡ በማሳወቅና በማረጋገጥ
መመሪያውን የተከተለ አሰራር ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በጥናቱ የቀረበ
መፍትሔ ነው፡፡

ሆኖም ከውጭ የሚመጡ ተገልጋዮች ማስረጃዎችን አሟልቶ ለማቅረብ እና


ጥያቄውን በጠቃሚ ጎኑ ለማየት የማይችሉበት አጋጣሚ ሊኖርና የሚቀርቡ ማስረጃዎች
ተአማኒነት ላይኖራቸው ይችላል፡፡ ቢሆንም አስቀድሞ የሚያስፈልጉትን ማስረጃዎች
ተጠቃሚዎች እንዲያውቁት በማድረግ ማንኛውም አመልካች ማስረጃዎችን በማያያዝ

48
ጥያቄውን ማቅረብ እንዲችል ማድረጉ የሚቀርቡ ማስረጃዎችን ተዓማኒነት ያጠናክራል፡፡

ሌላው በዩኒቨርስቲው የቤቶችና ንብረት ርክክብ ሥርዓቱ ግልፅነትና ተጠያቂነት


የተከተለ አለመሆን ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥር ሁኔታ ነው፡፡

ተጠቃሚዎች በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት የዩኒቨርስቲው አባል መሆናቸው እየተረጋገ


ጠ መኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ሲወሰንላቸው ይሰጣቸዋል፡፡ ነገር ግን አባላቱ ዩኒቨርስቲውን
ሲለቁ፣ በሥራ እና በሌሎች ምክንያቶች ለረዥም ጊዜ ከሀገር ሲወጡ ተገቢውን ርክክብ
መፈፀም ሲገባቸው ያለመፈፀም፣ አንዳንዶቹም ቤት ሲመልሱም ግልፅ የሆነ ሥርዓት
ስለሌለው የቤቶች አስተዳደር ያሉ አንዳንድ ሠራተኞች ከተጠቃሚዎቹ ጋር በመመሳጠ
ር ቁልፍ መሸጥ፣ ክሊራንስ ሲያዞሩም ቤትን በተመለከተ ሳያስረክቡ የመፈረም ሁኔታ
እንዳለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የርክክብ ሥርዓቱ ግልፅ የሆነና ተጠያቂነትን በሚያመላክት
መልኩ የሚከናወን ባለመሆኑ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ ነው፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት አግባብ ያለው የቤቶች ርክክብ ሥርዓት እንዲኖር ማድረግና
የዩኒቨርሲቲው ባልደረቦች ሥራቸውን ሲለቁ በመልቀቂያ ወረቀት /ክሊራንስ/ ላይ
የሚመለከተው አካል /የቤቶች አስተዳደር መምሪያ/ እንዲፈርም ማድረግ በጥናቱ
የቀረበ የመፍትሔ ሀሳብ ነው፡፡

ይህ የመፍትሔ ሀሳብ ተግባሪዊ ሲሆን የUNDP ቅጥር የሆኑና ወርሃዊ የቤት አበል
በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የሚከፈላቸው የዩኒቨርሲቲው አባላት ኮንትራታቸው
ሲያልቅ እና በነፃ የሚኖሩትን /visiting professors or volunteers/ በተመለከተ ወቅታዊ
መረጃ በቀላሉ ለማግኘት ስለሚያዳግት እና ተጠቃሚዎች ዩኒቨርስቲውን ሲለቁ ወደ
ሥራ ክፍሉ ላይመጡ ስለሚችሉ የቤቶች አስተዳደር የሥራ ክፍል ከትምህርት
ሚኒስቴርና ከሚሰሩበት የሥራ ክፍል ጋር በመሆንና በመከታተል አስቀድሞ ለተጠ
ቃሚዎች ማሳወቅ የመፍትሄ ትግበራውን ተከትሎ መወሰድ ያለበት እርምጃ መሆኑ
በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡

ዩኒቨርስቲው በቤቶች አጠቃቀም ላይ ከተጠቃሚዎች ጋር የሚገባው ውል የክትትልና


የአፈፃፀም ችግር ያለበት መሆን በጥናቱ የታየ ሌላው የአሰራር ክፍተት ነው፡፡ ተጠቃ
ሚዎች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ሲወሰንላቸው በተቀመጠ
ው ውል መሠረት ቤት የሚረከቡ ሲሆን ነገር ግን ውሉ ራሱ ለይስሙላ የተቀመጠ
እንጂ ተግባራዊ የሚሆንበት መንገድ የለም፡፡ ለምሳሌ በውሉ መሠረት ማንኛውም
ተጠቃሚ በየሁለት ዓመቱ ውሉን ማሳደስ ያለበት ሲሆን ነገር ግን አንዴ አባል ሲሆኑ ቤት
ከተሰጣቸው በኃላ ለረዥም ዓመታት ሳያድሱ ይጠቀማሉ፡፡ ይህም ቤቱን ለሦስተኛ ወገን
ማስተላለፍና ሌሎች መሰል ችግሮችን ያስከትላል፡፡ በውሉ ላይ የተቀመጠው ቅጣት 8(1-3)
ተጠቃሚዎች ሕጋዊ መንገድ ከመከተል ይልቅ ሕገወጥ እንዲሆኑ የሚያባብስ ነው፡፡

ለዚህ የአሰራር ሥርዓት ችግር በጥናቱ የቀረበው የመፍትሔ ሀሳብ ተጠቃሚዎች


ከዩኒቨርስቲው ጋር የሚገቡት ውል ወቅቱን ጠብቆ እንዲታደስ ማድረግና በውሉ ላይ

49
በቅጣት ደረጃ የተቀመጡትን አንቀፆች ማሻሻል ተገቢ ነው፡፡

በተመሳሳይ የተጠቃሚዎችንና የቤቶችን ወቅታዊ፣ ትክክለኛና የተሟላ መረጃ ያለመ


ያዝ በዩኒቨርስቲው ለሙስናና ለብልሹ አሰራር በር የሚከፍት መሆኑ በጥናቱ የታየ
ችግር ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው የሚያስተዳድራቸው መኖሪያ ቤቶችን በሚመለከት ለውሳኔና ለክትትል


ሥራ የሚረዱ ወቅታዊ መረጃዎች በተቀናጀ መልኩ ስለማይያዙና ለቤቶች ድልድል
ኮሚቴ ስለማይቀርቡ በተገቢው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔዎችን ለመስጠት ችግር
የሚፈጥር ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ለምሳሌ በዩኒቨርሲቲው ቤቶች ውስጥ ማን እንዳለና እንደ
ሌለ ያለማወቅ፣ ቤቶችን ከተረከቡ ሰዎች ጋር የቤተሰብ አባላትና ዘመድ ወይም ጓደኛ
የሆኑትን ዝርዝር አለመያዝ፣ የቤት ይሰጠኝ ማመልከቻዎች ከዓመት በፊት ያመለከ
ቱ አሁንም እንደ አዲስ እንዲያመለክቱ ማድረግና የአንዳንዶቹ ማመልከቻ አለመገኘት
ከሚጠቀሱት ችግሮች መካከል ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ለድልደላ ኮሚቴው ውሳኔ
ጠቃሚ የሆኑ ወቅታዊ፣ ትክክለኛና የተሟሉ መረጃዎች ከሥራ ክፍሉ ስለማይቀርቡ
ቤቶች ያለ አገልግሎት የሚቀመጡበት አጋጣሚ ይታያል፡፡

የሥራ ክፍሉን አሰራር ኮምፒውተራይዝድ /automated system/ በማድረግ ስለቤቶ


ችና ስለነዋሪዎች የተሟላ መረጃ ማለትም ስለተጠቃሚው የኮንትራት ጊዜ /የሥራና
የቤት ውል/ ወቅታዊ የቤተሰብ ብዛትና ዝርዝር እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች
ተጠናቅረው እንዲያዙ በማድረግና የሚስጥር ቁልፍ /pass word/ በመስጠት ማንኛ
ውም ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ኢንፎርሜሽን በቀላሉ እንዲያገኝ ማድረግ በመፍትሄ
ሃሳብነት የቀረበ ነው፡ ይህም ግልፅነትንና ተጠያቂነትን የተከተለ የአሰራር ሥርዓት
በዩኒቨርሲቲው ለመዘርጋት ያስችላል።

የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓቱ የተጠናከረ አለመሆን በጥናቱ የታየ ዩኒቨርሲቲውን ለሙስ


ናና ለብልሹ አሰራር የሚጋብዝ ሁኔታ ነው፡፡ በቤቶች አስተዳደር የሥራ ክፍልም ሆነ
በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ኦዲት አገልግሎት ወይም በውጭ ኦዲተር የሚደረግ የቁጥጥ
ር ሥርዓት ባለመኖሩ የሚታዩ ክፍተቶችን በወቅቱ ለማስተካከል የሚቻልበት አሠራር
አልተመቻቸም፡፡ ለዚህም የግል ቤት እያላቸው የራሳቸውን አከራይተው በዩኒቨርስቲው
ቤት ውስጥ የሚኖሩ በርካታ ተጠቃሚዎች መኖር፣ ለሌላ ሦስተኛ ወገን አከራይተው
በከፊል ወይም በሙሉ ተጠቃሚ መሆን፣ በቤቶች ውስጥ የሚኖሩት በራሳቸው
ወይም በባለቤታቸው /በትዳር አጋሮቻቸው/ ስም የተመዘገበ ቤት መኖር አለመኖር ሳይጣራ
የቤት ተጠቃሚ መሆን፣ በቤቱ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት በዝርዝሩ ላይ የተጠቀሱት
ግለሰቦች /ቤተሰብ/ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን የመከታተያና የመቆጣጠሪያ ስልት
አለመዘርጋት፣ በዩኒቨርሲቲው ቤት ተጠቃሚ ሆነው ሌላ ቦታ በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ
እየሰሩ የመኖሪያ ቤት አበል የሚከፈላቸው መኖርና የመሳሰሉት ችግሮች ይታያሉ፡፡ በዚህ
ዘርፍ የቁጥጥር ሥርዓት ስለሌለ የሚፈጠሩ ችግሮችን በጊዜው በመለየት የመፍትሔ
ሀሳብ ለአመራሩ በማቅረብ የማስተካከያ እርምጃ ስለማይወሰድ የአሰራር ሥርዓቱ
ለሙስናና ለብልሹ አሰራር በቀላሉ የተመቻቸ አድርጎታል፡፡

50
የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት የተጠናከረ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት በሥራ
ክፍሉና በውስጥ ኦዲት መዘርጋት ቢቻል እና ይህን ሥራ ዩኒቨርሲቲው ማከናወን
ካልቻለ የውጪ አካል እንዲሠራው /out source/ በማድረግ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
በጥናቱ የተጠቆመ የመፍትሔ ሀሳብ ነው፡፡ ይህ የመፍትሔ ሀሳብ ለአስተዳደራዊ
ጉዳዮች ተጨማሪ ወጪ ሊያስወጣ ስለሚችል በቂ ትኩረት በመስጠት አስቀድሞ በጀት
እንዲያዝ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

በአንዳንድ የቤት ተጠቃሚዎችና በቤቶች አስተዳደር መምሪያ ሠራተኞች ላይ የሥነም


ግባር ጉድለት መኖር ሌላው ዩኒቨርስቲውን ለሙስና እና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ
አሠራር ነው፡፡

የሚከሰቱ ችግሮችን ተከታትሎ ተገቢውን እርምጃ የመውሰድ ሁኔታ የተጠናከረ ባለመ


ሆኑ በአንዳንድ ሥነምግባር በጎደላቸው የዩኒቨርሲቲው ቤት ተጠቃሚዎች ከሥራ ክፍ
ሉ /የቤቶች አስተዳደር መምሪያ/ አንዳንድ ሠራተኞች ጋር በመደራደር ቁልፍ መግዛት፣
ለሦስተኛ ሰው አሳልፎ መስጠት፣ ቤቱን ማከራየት፣ ሰብሮ መግባትና ሕጋዊ ማድረግ
ይታያል፡፡ ስለሆነም በአንድ በኩል ይህን ሕገወጥ መንገድ የማይከተሉ ተጠቃሚዎች
ከአምስት ዓመት በፊት ጥያቄ አቅርበው ምላሽ ሳያገኙ ሌሎች የተወሰኑት ደግሞ
ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲያደርግ የሥነምግባር ጉድለት በሚያሳዩ ባልደረቦችም ላይ ወቅታ
ዊ፣ ጠንካራና ተመጣጣኝ የእርምት እርምጃ ስለማይወሰድ አሰራሩን ለሙስናና ብልሹ
አሰራር እንዲጋለጥ አድርጎታል፡፡

ጠንካራ የሆነ የሥነምግባር ደንብ በማዘጋጀትና ስልጠና በመስጠት ተግባራዊ


ማድረግ፣ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት መዘርጋት እና ተመጣጣኝ የሆነ
የዲሲፕሊንእርምጃ መውሰድ የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት ወሳኝ የመፍትሔ
ሀሳብ መሆኑ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ጽ/ቤት ይህን ሥራ በተደራቢነት


እየሰራ ስለሆነ የሥራ መደራረብ በሥራ ክፍሉ ላይ ሊያስከትል ስለሚችል በፌዴራል
ሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 433/94 አንቀፅ 24(1-4)
መሠረት ሙሉ በሙሉ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሉን ብቻ የሚመራ ኃላፊ ወይም
ሠራተኛ በቅጥር፣ በእድገት ወይም በዝውውር መመደብ ያስፈልጋል። የሥነምግባር
ጉድለቶችን በተመለከተ በቤቶች አስተዳደር ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ጉዳዮች እንዲ
ያማክሩ ማድረግ የመፍትሄ ትግበራውን ተከትሎ መወሰድ ያለበት እርምጃ መሆኑ
በጥናቱ ተገልጿል፡፡

በጥናቱ እንደተረጋገጠው የቤት ኪራይ፣ የውሃ፣ የመብራትና የስልክ ክፍያ አሰባሰብ


ችግር በዩኒቨርስቲው ያለ የአሰራር ስርዓት ክፍተት ነው፡፡ ከቤቶች አስተዳደር ዋና
ዋና ተግባራት መካከል አንዱ የቤት ኪራይ፣ የስልክ፣ የመብራት እና የውሃ ፍጆታ
ከነዋሪዎች መሰብሰብ ቢሆንም ዩኒቨርስቲው ከኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ በኪራይ ያገኛቸውን
ቤቶች ለመመምህራን አከራይቶ ውዝፍ የቤት ኪራይ ሲከሰት ይታያል፡፡ ተከራዮች
ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ኪራይ ሳይከፍሉ የሚኖሩ ስለነበሩ ዩኒቨርስቲው ከራሱ 10%

51
ተጨማሪ ክፍያ ለኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ከፍሏል፡፡ ነገር ግን ቤቶች እስከ ሁለት ዓመት
ተዘግተው ኪራይ መክፈል፣ ኪራይ ሳይከፍሉ በነፃ የሚኖሩትን ታሳቢ ያላደረገ የቤት
ኪራይ ክፍያው በወሩ ስለሚፈፀም ነዋሪዎች መክፈል ከሚገባቸው የቤት ኪራይ
በታች እየከፈሉ እንዲኖሩ የተመቻቸ ሁኔተ ፈጥሯል። የውሃ የስልክ የመብራት ክፍያም
በተመሳሳይ ገቢ አሰባሰብ ላይ ችግር ያለበት ሆኖ ይታያል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከኪራይ
ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ተከራይቶ የነበረው ወረዳ 21 ቀበሌ 01 የቤት ቁ. 397/33፣
ወረዳ 2 ቀበሌ 12 የቤት ቁ. 487/02 እና የቤት ቁ. 332/21 እንዲሁም ቦሌ ከሦስት
ዓመት በፊት ከዩኒቨርስቲው ሥራ ለቀው ውጭ አገር የሚኖሩ የቤት ኪራዩንም ሳይከፍ
ሉ ለ2ኛ ወገን አከራይተው እንደሄዱ እንደ ምሳሌ መንሳት ይቻላል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት በየወሩ ከተጠቃሚዎች ደመወዝ ተቀንሶ ምን ያህል ለቤቶች


አስተዳደር ክፍል ገቢ እንደሚደረግ ለየፋኩሊቲዎች ሂሳብ ክፍል በማሳወቅ በየወሩ
በአካውንት ገቢ ማድረግና በኔትዎርክ የተገናኘ ቅንጅታዊ አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ
ነው፡፡ በተጨማሪ ኪራይ ሳይከፍሉ በነፃ የሚኖርባቸውን ቤቶችና ተጠቃሚዎችን፣
ኪራይ የሚከፍሉትንና የኪራዩን ክፍያ መጠን፣ የስልክ የመብራትና የውሃ ፍጆታዎ
ችን በአግባቡ ተለይቶ ተግባራዊ የሚደረግበት የአፈፃፀም መመሪያ ማውጣት ወይም
በውሉ ላይ በዝርዝር እንዲገለፅ በማድረግ የአሰራር ሥርዓቱን ማስተካከል እንደሚቻል
ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

ዓመታዊና ድንገተኛ ቆጠራ በቤቶችና ቋሚ ንብረቶች ላይ አለማካሄድ ለሙስናና ለብል


ሹ አሰራር ክፍተት ከሚፈጥር ሁኔታዎች መካከል እንደሚጠቀስ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የሚገለገልባቸው ቤቶች የተለያየ ደረጃና ዓይነት ያላቸው ሲሆኑ እንደ
ቤቶች ደረጃና ዓይነት የተለያዩ ቋሚ ንብረቶች በቤቶች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን
እነዚህ ንብረቶች በአግባቡ ተመዝግበው ዓመታዊና ድንገተኛ ቆጠራ በቤቶችና ቋሚ
ንብረቶች ላይ ስለማይካሄድ ለብክነትና በህገወጥ መልኩ ለግለሰቦች መጠቀሚያ እንዲውል
የተመቻቸ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

ለዚህ የአሰራር ሥርዓት ችግር በጥናቱ የተጠቆመው የመፍትሄ ሀሳብ ዓመታዊና ድንገ
ተኛ ቆጠራ ማካሄድ ነው፡፡ ይህን ሥራ ዩኒቨርሲቲው በራሱ ማከናወን ካልቻለ በውጪ
አካል ማሠራት ይችላል። ይህ አሠራር በተጠቃሚዎች ዘንድ ከሚፈጠረው ችግር ጋር
በተያያዘ ጥሩ ምላሽ ላያገኙ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ተገልጋዮችን በማሳመን በሚቀርቡ
ችግሮች ላይ ወቅታዊ የመፍትሄ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ በጥናቱ ተቀምጧል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የታየው ሌለው ችግር የቋሚ ንብረቶች ገቢና ወጪ ክምችትና ስርጭት


አሰራር ተጠያቂነትና ግልፅነት የተከተለ አለመሆን ነው፡፡በዩኒቨርሲቲው መኖሪያ ቤቶች
ውስጥ እንደ ቤቶች ደረጃና ዓይነት መጠን የተለያዩ በርካታ ቋሚ ንብረቶች ይገኛሉ።
እነዚህ ንብረቶች በአግባቡ ተመዝግበው ቁጥር የተሰጣቸው አይደሉም። ወጪና ገቢ
ሲደረጉም ቢሆን በሚመለከተው አካል እየተወሰነ ሳይሆን ጉዳዩ በማይመለከተው ሰው
ወጪ ይደረጋሉ። ከዚህም በተጨማሪ የዩኒቨርሲቲው ንብረቶችን በአግባቡ ለመቆጣጠር
የሚያስችለው ሥርዓት ያልዘረጋ በመሆኑና ንብረቶች በጠባብ ግምጃ ቤት እንዲከማቹ
በመደረጉ ምክንያት ንብረቶች ወጪ ሲደረጉ መድረስ የሚገባቸው ቦታ ላይ

52
ስለመድረሳቸው ማረጋገጫ የለም። እንዲሁም ወጪ ያደረገው ተጠቃሚ አካል ብቻ በንብ
ረቱ ስለመጠቀሙ በቂ የሆነ መከታታያና መቆጣጠሪያ ስልት ካለመዘርጋቱም በላይ ዕቃዎች
ከቤቶች ጋር ወይም ብቻቸውን ለሌላ ሦስተኛ ወገን በኪራይ መጠቀሚያ ሲሆኑ ይታያል።

በተመሳሳይ የንብረቶች ወቅታዊ ሁኔታ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ አለመታወቅ፣ ተጠቃሚ


ው ያለአግባብ ከአገልግሎት ውጪ ያደረጋቸውን ዕቃዎች የዋጋ ግምት የሚከፍልበት
አሰራር አለመኖር እና አግባብ ያለው ጥገና በፕሮግራም አለማድረግ የሚያጋጥም
በመሆኑ ንብረቶች ለብክነት እንዲጋለጡ አድርጓል፡፡

ሁሉም ቋሚ ንብረቶች በቤቶች ደረጃና ዓይነት ተለይተው ሌጀር ተዘጋጅቶላቸው


ቁጥር በመስጠት የገቢና ወጪ ምዝገባ በአግባቡ ቢከናወን፣ የሚመለከተውን አካል የፊርማ
ናሙና ግምጃ ቤት በማስቀመጥ ንብረቶች በቢን ካርድ ላይ በወቅቱ ማቀናነስ ቢቻል፣
ወጪ የተደረገው ንብረት በአግባቡ ሥራ ላይ ስለመዋሉ ክትትል ማድረግ፣ ያለአግባብ
ከአገልግሎት ውጪ ለተደረጉ ንብረቶች ተመጣጣኝ ግምት ተሰልቶ ያጠፋው ሰራተኛ
እንዲተካ ቢደረግ እና ሰፋ ያለ የንብረት ማከማቻ መጋዘን ማዘጋጀት በመፍትሄ
ሀሳብነት በጥናቱ የቀረቡ ናቸው፡፡

በመኖሪያ ቤቶች አስተዳደር መምሪያ የሰለጠነ የሰው ኃይልና የማቴሪያል እጥረት


መኖር በዩኒቨርሲቲው ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥር ሁኔታ እንደሆነ
ተመልክቷል፡፡

የመኖሪያ ቤቶች አስተዳደር ሥራ ክፍል ከተሰጠው ኃላፊነትና ተግባራት አንፃር


ከዩኒቨርሲቲው የመምህራን የመኖሪያ ቤቶች ብዛት፣ ዓይነት፣ ያሉበት አካባቢ የተራራቁ
መሆን፣ የኪራይ መጠን፣ ቋሚ ንብረቶች መብዛት እና ከሚሰበሰበው የገንዘብ መጠን
አንፃር በቂ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግና ለዩኒቨርሲቲው አግባብ ያለው ድጋፍ
ለመስጠት የሚያስችል የማቴሪያልና የሰለጠነ ባለሙያ የለውም። አሁን በሥራ ላይ
ያሉትም ቢሆን የአቅም ማነስና የሥነምግባር ጉድለቶች የሚታይባችው ሲሆን በጊዜያዊነ
ት /ኮንትራት/ እና በተደራቢነት እንዲሰሩ ስለሚደረግ ለችግሮቹ መባባስ እንደ ምክንያት
ይጠቀሳል፡፡ ስለሆነም የሰለጠነ ባለሙያ በሥራ ክፍሉ በመቅጠር፣ በመመደብ ወይም
በማዘዋወርና ለሥራ አስፈላጊ የሆነ ማቴሪያሎች በማሟለት የአሰራር ሥርዓት ችግሩን
ለመፍታት በጥናቱ የተጠቆመ የመፍትሄ ሀሳብ ነው፡፡

ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን የከፍተኛ ትምህርት አቅም ለመገንባት የሰለጠነ


የሰው ኃይል ለመፍራት ሥልጠናና ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም በዩኒ
ቨርሲቲው የሚታዩትን ችግሮችና በጥናቱ የተሰጡ መፍትሄዎችን በማዳበርና ተግባራዊ
በማድረግ ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዳ ሥርዓት መዘርጋት ይጠበቅበታል። ከአሁን
በፊት የተፈፀሙ ወይም በመፈፀም ላይ ያሉ የአሰራር ግድፈቶችን መለየትና የእርምት
እርምጃ መውሰድ ለነገ የሚባል ተግባር አይደለም፡፡

53
የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የውጭ ሀገር ሕክምና የቦርድ ፈቃድ አሰጣጥ

በ ጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የውጭ ሀገር ሕክምና ቦርድ


የአሠራር ሥርዓት ላይ በኮሚሽኑ የተካሄደው ጥናት ለሙስናና ለብልሹ አሠራር ሊያጋልጡ
የሚችሉ ሁኔታዎች ብሎ የዘረዘራቸው የሚከተሉት ናቸው፡፡ የተሟላ መረጃ በማኅደ
ር ተያይዞ በማይገኝበት ሁኔታ የውጭ ሀገር ሕክምና ፈቃድ መስጠት፣ የውጭ ሀገር
ሕክምና ቦርድ አሰጣጥ ተዘጋጅቶ የፀደቀ የሥራ መመሪያ አለመኖር፣ በተጭበረበረ
ሰነድ የሚቀርቡ ማስረጃዎችን ለመከላከል ያለው ቁጥጥር ደካማ መሆን እና የሥነምግ
ባር መመሪያ አለመኖር የሚሉት ናቸው፡፡

አንድ ታካሚ መጀመሪያ በውጭ ሀገር ተቀብሎ ሕክምና የሚያደርግለት የጤና ተቋም
አፈላልጎ ማግኘቱንና ተቀባይነት ማግኘቱን የሚያሳይ ደብዳቤ ለሕክምና ቦርድ አባላት
ያሳያል፡፡ በመቀጠልም የሕክምና ክፍሉ ወይም ሆስፒታሉ የውጭ ሕክምና ቦርድ
የምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ ታካሚው የውጭ ሕክምና ማግኘቱን የሚገ
ልፀውን ደብዳቤ ለሕክምና ቦርድ አባላት ከማሳየት ውጪ በሰነድ ማስረጃነት ከሕክምና

54
ታሪኩ ጋር ካለመያያዙም በላይ ለትክክለኝነቱም ለሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር
የሚቀርብበት አሠራር አለመኖሩን ጥናቱ ይጠቁማል፡፡ በዚህ የተነሳም ታካሚዎችን
ተቀብሎ ሕክምና የሚያደርግላቸውን ተቋም ያገኙ ወይም ያላገኙ ታካሚዎችን
በትክክል ለመለየት አያስችልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ታካሚው የት ሀገር ሄዶ እንደ
ሚታከም የሚያሳይ ገላጭ ማስረጃ ባለመኖሩ የአሠራር ሂደቱ ግልጽነት ይጎድለዋል፡፡
በመሆኑም የውጭ ሀገር ሕክምና ቦርድ ምስክር ወረቀት ለማግኘት በውጭ ሀገር ባለ
ሕክምና ተቋም ተቀባይነት ያላገኙ ታካሚዎች በቀላሉ የውጭ ሀገር ሕክምና ቦርድ
ማስረጃ አለአግባብ ተጽፎ እንዲሰጣቸው መንገድ ይከፍታል፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ታካሚው የውጭ ሀገር ሕክምና ሊሰጠው የሚችል ተቋም
ማግኘቱን የሚገልጽ የሰነድ ማስረጃና ፎቶ ኮፒውን ከሕክምና ፋይሉ ጋር አያይዞ
ለሜዲካል ዳይሬክተሩ ማቅረብ እና ዳይሬክተሩ ትክክለኝነቱን ካረጋገጠ በኋላ ዋናውን
ማስረጃ በመዝገብ ቤት በኩል ለታካሚ ተመላሽ ማድረግ እንዲሁም ኮፒውን ከዋናው
ጋር በማመሳከር ከታካሚ ሕክምና ታሪክ ጋር ተያይዞ እንዲቀመጥ ማድረግ በመፍት
ሄ ሃሳብነት ተጠቁሟል፡፡ ይህም የሰነድ መጭበርበርን ከመቀነሱም በላይ የውጭ ሀገር
ሕክምና ቦርድ ምስክር ወረቀት ሊሰጣቸው የሚገባና የማይገባቸውን ታካሚዎች
/ግለሰቦች/ በሰነድ ማስረጃው መሠረት ለመለየት ያስችላል፡፡

በሆስፒታሉ የውጭ ሀገር ሕክምና ቦርድ አሰጣጥ መመሪያ ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ


መዋሉ በቃል ደረጃ ቢገለጽም አብዛኛዎቹ የሕክምና ክፍሎች የሚሠሩበትን መመሪያ
እንዲያሳዩ ወይም እዲያቀርቡ ሲጠየቁ ለጊዜው በዕጃቸው እንደሌለ ይገልፃሉ፡፡
የጥናት ቡድኑ በሆስፒታሉ በአግባቡ ፀድቆ በሥራ ላይ የዋለ የውጭ ሀገር ሕክምና ቦርድ
መመሪያ አለመኖሩን ግንዛቤ ወስዷል፡፡ ይህም ባለመኖሩ በአሠራር ሂደት እያንዳንዱ
የሕክምና ቦርድ አባላት የሥራ ድርሻና ኃላፊነት በግልጽ ተቀምጦ አይገኝም፡፡ በዚህ
የተነሳም የውጭ ሕክምና ቦርድ አሠራር ሥርዓት ግልጽነትና ወጥነት የጎደለው፣
ለተጠያቂነት ምቹ ሁኔታ የማይፈጥርና ለሙስናና ብልሹ አሠራር የሚያጋልጥ ነው፡፡
በመሆኑም የውጭ ሀገር ሕክምና ቦርድ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ
ግልጽ መመሪያ በዝርዝር አዘጋጅቶ በሚመለከተው አካል ማፀደቅና ለሆስፒታሉ
የሕክምና ቦርድ አባላት እንዲሁም ለሚመለከታቸው አካላት ማሰራጨት በጥናቱ
በመፍትሄ ሃሳብነት ቀርቧል፡፡

የውጭ ሀገር ሕክምና ቦርድ ምስክር ወረቀት አዘገጃጀት በቀላሉ በተጭበረበረ ሰነድ
ተዘጋጅቶ የሚቀርብበት ሁኔታ እንዳለ ጥናቱ አመልክቷል፡፡ ለአብነትም ያለ ሆስፒታ
ሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ፊርማ አስመስሎ የማቅረብ፣ ሆስፒታሉ ያልፃፈውን እንደፃፈ
አድርጎ ለተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት የተሳሳተ የሕክምና
ማስረጃ የሚቀርብበት ሁኔታ መኖራቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ለሰነድ መጭበ
ርበሩ በሆስፒታሉ የሚዘጋጀው የውጭ ሕክምና ቦርድ ምስክር ወረቀት ራሱን በቻለ
ወጥ እና ልዩ በሆነ መንገድ ተዘጋጅቶ፣ ቁጥር ተሰጥቶት እና እንደማንኛውም ንብረት
የገቢ እና ወጪ ሥርዓት ተከናውኖበት አለመቅረቡ በምክንያትነት በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡
እንዲሁም የሚዘጋጀው የምስክር ወረቀት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ዓርማ ወይም
በሥሩ የሚተዳደሩትን ሥራ ክፍሎች ዓርማ እና ሄደር ያልያዘ በመሆኑ ለመጭበርበር

55
የተጋለጠ እንዳደረገው ተጠቅሷል፡፡

ይህን ችግር ለማቃላልም የውጭ ሀገር ሕክምና ቦርድ ምስክር ወረቀት አንድ ወጥና
ልዩ በሆነ ሰነድ ማዘጋጀት፣ የሆስፒታሉ ዓርማና ሄደር እንዲኖረው ማድረግ፣
የሞዴል /ሴሪ ቁጥር ተሰጥቶት መዝገብ ቤት/ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግና ለሥራ
ሲፈለግ በወጪ ማዘዣ ተጠይቆ ጥቅም ላይ ማዋል እንደመፍትሄነት በጥናት ቡድኑ
ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም የሕክምና ቦርድ አባላትንና የሜዲካል ዳይሬክተሩን/ተወካዩን
የፊርማ ናሙና በሆስፒታሉና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መዝገብ ቤቶች ማስቀመጥና
የተለያዩ የጤና አገልግሎት ክፍሎች ይዘው የሚመጡትን የምስክር ወረቀት ማመሳከር
እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል፡፡

ሌላው በጥናቱ የተጠቆመው የአሠራር ሥርዓት ችግር የሥነምግባር ደንብ አለመኖር


ነው፡፡ በውጭ ሕክምና ቦርድ አሰጣጥ ሂደት የጥቅም ግጭት የሚፈጠርበት አጋጣሚ
ቢከሰት ለምሳሌ የሕክምና ቦርድ አባላት ለቅርብ ሰዎቻቸው የምስክር ወረቀት ቢሰጡ
በታካሚው፣ በሐኪሙ ወይም በውጭ ሀገር ሕክምና ተቋሙ መካከል የጥቅም ግንኙ
ነት ቢኖር፣ የውጭ ሀገር ሕክምና ቦርድ አሰጣጡ ከታካሚውና ከሐኪሙ ፍላጎት፣
መብት ወይም ከሀገር ደህንነት አንፃር ሲታይ የጥቅም ጉዳት ንጽጽር ሀገርን የሚጎዳ
ከሆነ፣ ይህንና መሰል የጥቅም ግጭቶችን ለመፍታትና በገደብ ለመወሰን የሚያስችል
የሥነምግባር ደንብ በሆስፒታሉ የለም፡፡ እንዲህ ዓይነት ሥራዎችን ያለ መመሪያ
ማከናወን የአሰራር ሂደቱን ለሙስናና ለብልሹ አሠራር እንደሚያጋልጠው አያጠራጥር
ም፡፡ ስለሆነም ሆስፒታሉ የሥነምግባር ደንብ፣ የሕክምና ሙያ ሥነምግባር መመሪያ
ማዘጋጀትና ከዝርዝር የውጭ ሀገር ሕክምና ቦርድ ምስክር ወረቀት አሰጣጥ ጋር
እንዲጣጣም አድርጎ በሥራ ላይ ማዋል ይጠበቅበታል፡፡

በአጠቃላይ ሆስፒታሉ ከላይ በጥናት ቡድኑ የተጠቀሱትን የአሠራር ችግሮች በአግባ


ቡ በመፈተሽ አሠራሩን ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ የተጠቆሙትን
የመፍትሄ ሃሳቦች ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ይህም የውጭ ሀገር ሕክምና ቦርድ
የምስክር ወረቀት የሚሰጥበትን ሁኔታ ወጥ፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ
ዓይነተኛ መሣሪያ እንደሚሆን የኮሚሽኑ ዕምነት ነው፡፡

56
አዲስ አበባ ጤና ቢሮ የግል ሆስፒታሎች፣
ዲያግኖስቲክ ላብራቶሪዎች፣ ኤች.አይ.ቪ ምርመራና የውጪ ዜጎች
የግል ክሊኒክ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥ

በ አዲስ አበባ ጤና ቢሮ በተካሄደው የአሰራር ሥርዓት ማሻሻያ ጥናት የተስተዋሉ


የአሰራር ሥርዓት ችግሮች በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የወጣውን የጤና አገልግሎት ተቋም
ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያን መሠረት ባደረገ መልኩ ከጤና ቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር
የተገናዘበ ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ አለመኖር ቀዳሚው ነው፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለግል ሆስፒታሎችና ክሊኒኮች ዲያግኖስቲክ ላብራቶሪ ለቪሲ


ቲ /ኤች.አይ.ቪ/ ምርመራ የጤና አገልግሎት ተቋም የፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር አጠቃ
ላይ መመሪያ አዘጋጅቶ ለጤና ቢሮዎች አስተላልፏል፡፡ ሆኖም ይህንን መመሪያ ከጤና
ቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ለመሥራት የሚያስችል ዝርዝር አፈፃፀም መመሪ
ያ ባለመዘጋጀቱ ፈቃድ አሰጣጡን ወጥነት እንዳይኖረው አድርጎታል፡፡ ለአብነትም አዲስ
የሚከፈቱም ሆነ የሙያ ፈቃዳቸውን የሚያድሱ የግል የጤና አገልግሎት መስጫ
ተቋማት ብቃትና ደረጃ ለመቆጣጠርና ለማረጋገጥ የሚላኩት ኢንስፔክተሮች /የብቃት
ና ደረጃ ማረጋገጫ ቅፁ ኢንስፔክተር በማለት የሚጠቅሳቸው ቢሆንም የገምጋሚዎቹ
የሥራ መደብ ላይ የተመደቡ አይደሉም/ ብዛት በየተቋማቱና በተለያየ ጊዜ የተለያየ
ቁጥር ያላቸው ሆኖ መታየቱ፣ ለኢኒስፔክሽን ሥራ የሚላከው ባለሙያ ማን መሆን
እንዳለበትና ምን ተግባርና ኃላፊነት እንደተሰጠው በፅሁፍ የተሰጠ መመሪያ የለም።
ኢንስፔክተሩም በብቃትና ደረጃ መቆጣጠሪያ ቅፁ ላይ የሚሰጠው አስተያየት ጥቅልና
በመመሪያው ላይ የተዘረዘሩትን ተቋማት ሊያሟሉ የሚገባቸውን ድርጅታዊ ሁኔታዎ
ች ሙሉ በሙሉ መሟላታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችልና ገላጭ ያለመሆን ችግር
ይስተዋላል፡፡

በሌላ በኩል የሙያ ፈቃዱን ለመስጠት ህጋዊ ስልጣን የተሰጠው የሥራ ኃላፊ
በግልፅ የማይታወቅ መሆኑም /በፅሁፍ የሰፈረ ባለመኖሩ/ ሌላው የታየ ችግር ነው፡፡ ለምሳሌ
አንዳንድ የሙያ ፈቃድ በኢንስፔክተሩ አስተያየት መነሻ ብቻ የሚሰጡ ሲሆን ሌሎቹ
ደግሞ በቡድን መሪው አስተያየትና ውሳኔ ወጥነት በሌለው መልኩ የሚሰጡ መሆኑን
ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ይህ አሰራር ማን ምን እንሚሰራ በግልፅ ባልተቀመጠበት ሁኔታ
የሚከናወን በመሆኑ ኃላፊነትና ተጠያቂነት እንዳይኖር የሚያደርግና ለሙስናና ብልሹ
አሰራር ክፍተት የሚፈጥር ነው፡፡

የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት በግል ለሚቋቋሙ ሆስፒታሎች፣ ክሊኒኮች፣


ዲያግኖስቲክ ላብራቶሪዎችና የቪሲቲ ምርመራ ለማድረግ ለሚሰጡ ፈቃዶች በጤና
ጥበቃ ሚኒስቴር የወጣውን የጤና አገልግሎት ተቋም ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር
መመሪያን መሠረት በማድረግ ዝርዝር አፈፃፀሙን የሚያመለክት መመሪያ ማዘጋጀ
ትና አፈፃፀሙም ሚዛናዊ የቁጥጥር ሥርዓት /Check and Balance/ እንዲኖረው
ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የውሳኔ ሀሳቡን ለሚያፀድቀውና በሙያ ፈቃዱ ላይ ለሚፈርመው

57
ኃላፊ ተገቢውን የሥልጣና ውክልና መስጠትና የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች
እንዲያውቁት ማድረግ፣ የውሳኔ ሃሳቡ በምክትል የቢሮ ፀሐፊ እንዲፀድቅ እና የጤና
አገልግሎት ማደራጃና ማከፋፈያ መምሪያ በሙያ ፈቃዱ ላይ እንዲፈርም ማድረግ
የተሻለ አማራጭ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የሙያ ፈቃድ ጠያቂዎች ሊያሟሉ የሚገባ


ቸውን ድርጅታዊ ሁኔታዎች ማሟላታቸውን በመጥቀስ ለቢሮው የሙያ ፈቃድ ጥያቄ
ካቀረቡና ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ ያቀረቧቸው ባለሙያዎች በተቋሙ ውስጥ በሥራ ላይ
ያሉ ስለመሆናቸው ወይም በተመሳሳይ ደረጃ ባለ ባለሙያ ስለመተካታቸው ለማረጋገ
ጥ የሚያስችል የቁጥጥር ሥርዓት የለም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የሚያስፈልጉ የህክምና
መሣሪያዎችም ፈቃድ ከተሰጠ በኋላ በተቋሙ ውስጥ ስለመኖራቸው ለመቆጣጠር
የሚያስችል አሰራር ያለመኖሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ አሰራር ፈቃድ ጠያቂዎች
የሙያ ፈቃዱን ለማግኘት ብቻ ባለሙያዎችን በተለያየ መልኩ /በብድርና በኪራይ/
ጭምር አቅርበውና አሳይተው ወደ ተግባር ሲገቡ ከመመሪያው ውጪ እየሰሩ ቢቆዩ
ለመቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት አልተዘረጋም፡፡ ይህም የህክምና አገልግሎት ሰጪ
ተቋማት ብቃትና ደረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ውስጥ እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ
በመፍጠር ለሙስናና ብልሹ አሰራር ሊዳርግ ይችላል፡፡

ለዚህ የአሰራር ሥርዓት ችግር ከፈቃድ ሰጪው የሥራ ዘርፍ ውጪ የሆኑ ባለሙያ
ዎች ያሉበት የኢንስፔክሽን ቡድን ማደራጀት፣ ማመሳከሪያ /check list/ በማዘጋጀትና
ዕቅድ በመንደፍ በተወሰኑ ጊዜያት ውስጥ የግል ህክምና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን
በመፈተሽ ብቃቱንና ደረጃውን ማረጋገጥ የሚሉት በመፍትሄ ሃሳብነት የቀረቡት
ናቸው፡፡

የመረጃ ቅበላ፣ አያያዝና ቁጥጥር የተሟላና የተጠናከረ አለመሆን ሌላው በጥናቱ የታየ
የአሰራር ሥርዓት ችግር ነው፡፡

የሙያ ፈቃድ ከጥያቄው ጀምሮ ፈቃድ እስከተሰጠበት ድረስ የተከናወኑ ተግባራት


ሂደት ገላጭ በሆነ መልኩ በመረጃ ተደግፈው በየማህደሩ በአግባቡና ሥርዓት ባለው
መልክ ተዘጋጅተው አይገኙም፡፡ የፍቃድ ጠያቂዎች መረጃ በመዝገብ ቤት በኩል ገቢ
ሳይሆን በቀጥታ ለፈቃድ ሰጪው የሥራ ዘርፍ የሚቀርብ ከመሆኑም በላይ ማህደሮ
ች ወጪ ሲደረጉ በቃል ጥያቄና በትንሽ ነጭ ወረቀት ላይ በሚሰጥ ትዕዛዝ መሆኑ፣
ቁጥር ተሰጥቷቸው በሥርዓት ያልተቀመጡና ወሳጁ የሚፈርመው ማህደሩን ለመ
ውሰዱ እንጂ በማህደሩ ውስጥ ያለው ገፅ ተመዝግቦ ወጪ እንደማይደረግ በጥናቱ
ወቅት የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሙያ ፈቃድ በሁለት ዋና
/Original/ ምስክር ወረቀት ተዘጋጅቶ አንደኛው ለሙያ ፈቃድ ጠያቂው ሲሰጥ ሌላው
ዋና /Original/ የሙያ ፈቃድ በማህደር ውስጥ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት እየታደ
ሰ ይቀመጣል፡፡ ይህ በማህደር የሚቀመጠው የሙያ ፈቃድ ኮፒ መሆኑን የማይገልፅ
በመሆኑ ፈቃዱ በቀላሉ ሊጠፋ፣ ሊሰረቅ፣ ሊለወጥ፣ ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ጥቅም ላይ
ሊውል እንደሚችል ለመረዳት ተችሏል፡፡

58
የቢሮው መዝገብ ቤት አሰራር ወጥነትና ተጠያቂነት ያለበት እንዲሁም የተጠናከረ
ቁጥጥር ያለው አሰራር እንዲኖረው ለማስቻል መመሪያ ማዘጋጀት፣ ለሠራተኞች ሥራ
መዘርዝር አዘጋጅቶ በመስጠትና በቂ ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ መረጃዎች በአግባ
ቡ እንዲደራጁና እንዲጠበቁ ማድረግ፣ የሙያ ፈቃድ ጥያቄዎች በመዝገብ ቤት ገቢ ሆነ
ውና ተመዝግበው እንዲቀርቡና ለማህደር ቀሪ የሚደረገው የሙያ ፈቃድ ዋናው ሳይሆ
ን ኮፒ እንዲሆን በማድረግ ሰነዶች እንዳይጠፉ፣ እንዳይለወጡ፣ እንዳይሰረቁና ለህገወጥ
ድርጊት እንዳይውሉ ተገቢውን ምዝገባና ቁጥጥር በማካሄድ ችግሩን ማቃለል ያስችላል፡፡

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በወጣው የግል ሆስፒታል መመሪያ ቁጥር 1/1989 ክፍል 5
ተራ ቁ.12 እና 13 ላይ ፈቃድ ስለማገድና ስለመሰረዝ የተደነገገ ቢሆንም በአፈፃፀም
ላይ ችግሮች እየተከሰቱ መገኘታቸው በቃለ መጠይቁ ወቅት ለመረዳት ተችሏል፡፡
በመመሪያው ውስጥ የህክምና ሥነምግባር ያላከበረ ፈቃዱ እንደሚታገድ /እንደሚሰረ
ዝ/ ተደንግጓል። ይሁን እንጂ እገዳው /ስረዛው/ የሚቆየው እስከመቼ እንደሆነ፣ የታገ
ደበትን የሙያ ፈቃድ መልሶ ሌላ የሙያ ፈቃድ ቢጠይቅ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ
መመሪያው በግልፅ ያስቀመጠው ነገር ባለመኖሩ አፈፃፀሙን አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ በዚህ
ዓይነት አሰራር የሚወሰነው ውሳኔ በግለሰቦች አስተያየት ላይ እንዲመረኮዝ ለማድረግ
የሚያስችል በመሆኑ ለድርድርና ለአድሎ ክፍተት ሊፈጥር ይችላል፡፡

በመመሪያው ላይ የህክምና ሥነምግባር ጥሰት ሲፈፀም በሚወሰደው የእገዳም ሆነ


የፍቃድ ስረዛ ቅጣት በአፈፃፀም የታዩ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ ሊሆን የሚችል ሃሳብ
በማዘጋጀት ቢሮው ተጠሪ ለሆነለት አካል አቅርቦ ማፀደቅ ለአሰራር ሥርዓት ችግሮቹ
መፍትሄ ሊሆን እንደሚችሉ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች


ና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የሚመሩባቸው የሥነምግባር ደንቦች ያለመዘጋጀታቸው ግል
ፅነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር እንዳይኖር ከማድረጉም በላይ ለሙስናና ብልሹ አሰራ
ር ክፍተት ሊፈጥር እንደሚችል ጥናቱ አሳይቷል፡፡

ይህን የአሰራር ሥርዓት ችግር ለመፍታት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጤና
አገልግሎት አሰጣጥ አስተዳደርና አመራር አዋጅ ቁጥር 10/1995 ክፍል ሁለት ተራ
ቁ. 15 ‘‘ቢሮው የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የጤና ተቋማትና በእነዚህ የጤና
ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ሊከተሉት የሚገባውን
የሙያ ሥነምግባር ደንብ አዘጋጅቶ በካቢኔው አፅድቆ ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል’’
ይላል፡፡ በዚህ መሠረት ቢሮው የሥነምግባር ደንቡን አዘጋጅቶ ቢያፀድቅ በህክምናው ዘርፍ
የሚታየውን ኃላፊነት የጎደለውን አሰራር በማስቀረት ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያለበት
አሰራር ለማስፈን ያስችላል፡፡

ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የግል ክሊኒኮች የሙያ ሥራ ፈቃድ የሚሰጠው በክፍለ


ከተማ የጤና ጽ/ቤቶች ሲሆን ለውጭ ሀገር ባለሀብቶች በጤና ቢሮው በኩል እንደሆነ
ለመረዳት ተችሏል፡፡ ሆኖም በቢሮው የሚገኙ የግል ክሊኒክ ማህደሮች ሲፈተሹ
የሙያ ሥራ ፈቃድ ጠያቂው ባለሃብት የውጭ ሀገር ዜጋ ስለመሆኑ የሚገልፅ መረጃ

59
የማይኖርበት ሁኔታ ከመታየቱም በላይ ባለሃብቶቹ ሲመጡ በጤና ቢሮ ወይም በክፍለ
ከተማ የሚስተናገዱ ስለመሆናቸው በቃል ከቢሮው እንደሚገለፅላቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡
ይህም ጤና ቢሮው አንዳንድ ጊዜ በራሱ የሙያ ፈቃዱን የሚሰጥበትና በሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ
ክፍለ ከተማ ሄደው እንዲወስዱ ሊደረግ የሚችልበት ሁኔታ መኖሩ ለፍቃድ ጠያቂው ግልፅ
ባልሆነ ሁኔታ ሊጉላላ ይችላል። በዋነኛነትም አሰራሩ ለአላስፈላጊ ድርድር በር የሚከፍት ነው፡፡

ይህን ችግር ለማቃለል የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችንና ብሮሸሮችን በማዘጋጀት በመረጃ


ዴስክ አማካኝነት ተገልጋዩ በቂ መረጃ የሚያገኝበትን ሁኔታ ማመቻቸት በመፍትሄ
ሃሳብት ተጠቁሟል፡፡

በአንድ ሙያ ልዩ ሥልጠና ባለው ባለሙያ ስም በተሠጠ የሥራ ፈቃድ መመሪያው


ከሚፈቅደው ውጪ ሌላ ልዩ ስልጠና ያለው ባለሙያ የሚያስፈልገውን ህክምና በማጣ
መር የሙያ ፈቃድ መሥጠት በጥናቱ የታየ የአሰራር ሥርዓት ችግር ነው፡፡

በግል ክሊኒክ ፈቃድ አሰጣጥ ለሁለተኛ ጊዜ ተሻሽሎ በወጣ መመሪያ ላይ ‘‘ልዩ


ክሊኒክ’’ ማለት ለተወሰነ የአካል ክፍል ወይም ለተለየ የህመም ዓይነት ብቻ በሙያው ልዩ
ስልጠና ባገኘ የጤና ባለሙያ የሚመራ ድርጅት ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ልዩ ክሊኒኮች
የጥርስና የዓይን ህክምናን በሙያው ኤክስፐርት ዴንታል ሰርጅን ስያሜ ባለው
ባለሙያ በጣምራ አገልግሎት እንዲሰጥ ፈቃድ እንደተሰጣቸው በጥናቱ ወቅት ለመገንዘብ
ተችሏል፡፡ ይህ ዓይነት አሰራር ለዓይን ህክምና በልዩ ክሊኒኩ ሊሟላ የሚገባቸው ማለትም
በሙያው ልዩ ስልጠና ያለው ባለሙያና የህክምና መሣሪያዎች ተሟልተው ስለመገኘታ
ቸው ማረጋገጫ ባልቀረበበት ሁኔታ የጥርስና የዓይን ህክምና እንዲሰጥ የሙያ ፈቃድ
መሰጠቱ መመሪያውን ያልተከተለና ለግል አመለካከትና አድልዎ ክፍተት የሚፈጥር
ነው፡፡

ይህን የአሰራር ሥርዓት ችግር ለመቅረፍ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ነሐሴ 1994 ዓ.ም
የግል ክሊኒክ ፈቃድ አሰጣጥ ለሁለተኛ ጊዜ ተሻሽሎ በወጣ መመሪያ ላይ ልዩ
ክሊኒክ ብሎ ባሰፈረውና ሊሟሉ የሚገባቸውን ሁኔታዎች በደነገገው መሠረት ተግባራ
ዊ መደረግ ይኖርበታል፡፡

በጤና ቢሮው በሙያ ፈቃድ እድሳት ወቅት ቀድሞ ከተፈቀደላቸው የምርመራ


ዓይነቶች ተጨማሪ ማካሄዳቸው በቅፁ ላይ ሲጠቆም በተጓዳኝ መታየት የሚገባቸው
መረጃዎችን የማጣራቱ ሂደት የተጠናከረ ያለመሆኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡

በአብዛኛው የግል የጤና ተቋማት የመጀመሪያ የሙያ ሥራ ፈቃድ ከተሰጣቸው በኋላ


ለእድሳት ሲቀርቡ ተጨማሪ የምርመራ ዓይነቶችን እና ባለሙያዎችን ጨምረው
በኢንስፔክሽን ቅፅ /በስታንዳርድና በብቃት/ መቆጣጠሪያ ላይ በመሙላት የሚጠይቁበት
ሁኔታ መኖሩ የሚታይ ከመሆኑም በላይ ቀድሞ በባለሙያነት ፈቃዱን ያወጣውን
ባለሙያን መቀየርንም ከፈቃድ እደሳው ጋር በአብዛኛው ተያይዞ የሚቀርብ ጥያቄ ነው፡፡
በዚህ ሂደት ያቀረቡትን ጥያቄ መርምሮ መረጃዎች የተሟሉ ሆነው ስለመገኘታቸው
የሚያሳይ ግልፅ በሆነ መልኩ የሰፈረ ወይም የሚያስረዳ ማስረጃ በማህደር ውስጥ

60
መኖሩን የማጣራትና ስታንዳርድና ብቃቱን የማረጋገጡ ሥራ ደካማ መሆኑን
ያመለክታል፡፡ ይህም ከተፈቀደ ደረጃ በላይ መረጃ ባላቀረበ ባለሙያ ባልተፈቀደ የህክምና
መሣሪያ ጭምር አገልግሎት ሊሰጥበት የሚያስችል ክፍተት የሚፈጥርና ለብልሹ
አሰራር ሊያጋልጥ የሚችል ይሆናል፡፡

ፈቃድ ለማሳደስ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ቀደም ሲል ከቀረበው መረጃ ጋር በማነፃፀርና


በማጣራት ለልዩነት ተገቢው መረጃ መያያዙን ማረጋገጥ፣ የሚወጣው ዝርዝር የአፈፃ
ፀም መመሪያ በሚወስነው መሠረት መረጃዎች ገላጭ ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ እንዲ
ሰፍሩና አዲስ ወይም እድሳት መሆኑን ለመለያት በሚያስችል መልኩ ቅፁን ማዘጋጀት
እንዲሁም ባለሙያዎች በሥራ ላይ መሆናቸውን በአካል በመገኘት ማረጋገጥ ለችግሩ
በመፍትሄ ሃሳብነት የቀረቡ ናቸው፡፡

በመጨረሻ በጥናቱ የታየው ቢሮውን ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጠው ሁኔታ


ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጤና አገልግሎት አሰጣጥ የአስተዳደርና አመራር
አዋጅ ቁጥር 10/1995 ከተደነገገው ውጪ የጤና ቢሮ የብቃት ማረጋገጫ ሳይጠየቅ
የንግድ ፈቃድ እንዲሰጥ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት
ቢሮ ጋር የመግባቢያ ውል መፈረሙ ነው፡፡

የጠቅላላ መለስተኛ ክሊኒክ፣ ጠቅላላ መካከለኛ ክሊኒክ፣ ጠቅላላ ከፍተኛ ክሊኒክ፣ ልዩ


መለስተኛ ክሊኒክ፣ ልዩ ከፍተኛ ክሊኒክ እና የላብራቶሪና የራጅ አገልግሎት የንግድ
የሥራ መስኮች የጤና ቢሮ የብቃት ማረጋገጫ ሳያስፈልግ በንግድ መዝገብ በመመ
ዝገብ ለግል የክሊኒክ ፈቃድ ፈላጊዎች የንግድ ፈቃድ እንዲሰጣቸው በአዲስ አበባ
ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት
ቢሮ የመግባቢያ ሰነድ ውል ተፈርሞ ከታህሳስ 1 ቀን 1996 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ
እንዲውል ተደርጓል፡፡ ይህም ከላይ ከተጠቀሰው አዋጅ ቁጥር 10/1995 ዓ.ም በክፍል
አንድ አንቀፅ 3 ንዑስ አንቀፅ 4 ሥር ፈቃድ ለማግኘት ማንኛውም የጤና አገልግሎ
ት በመስጠት ተግባር ላይ ለሚሰራ ሰው ከቢሮው የሙያ ማረጋገጫ ሳያገኝ በግል ባለ
ሀብቱ በኩል በቀረበ መስፈርቱን ማሟላቱን የሚገልፅ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ የሚሰጥ
ፈቃድ ለግል ጥቅም ቅድሚያ ለሚሰጡና የሙያውን ሥነምግባር ለማይከተሉ ባለሀ
ብቶች በሰነድ ላይ ለማጭበርበር እንዲችሉ በር የሚከፍት አሰራር ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ሁኔታ የሚሰጥ ፈቃድ መተኪያ የሌለውን የሰው ልጅ ህይወት
አደጋ ላይ ከወደቀ በኋላ በኢንስፔክሽን ሥራ ለማስተካከል ጥረት ማድረጉ የሀገርን ዜጋና
ሀብት ሊጎዳ የሚችል ነው፡፡

የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጤና አገልግሎ
ት አሰጣጥ የአስተዳደርና አመራር አዋጅ ቁጥር 10/ 1995 ክፍል አንድ አንቀፅ 3 ንዑስ
አንቀፅ 4 ‘‘ማንኛውም የጤና አገልግሎት በመስጠት ተግባር ላይ ለሚሰማራ ሰው
ከቢሮው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሳያገኝ ሥራ መጀመር አይችልም’’ በማለት የተደነገገ
ውን ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡

61
የሸቀጦች ጅምላ ንግድና አስመጪ
ድርጅት የሲሚንቶ ሽያጭ አፈፃፀም ሥርዓት

ሌ ላው ኮሚሽኑ የአሠራር ሥርዓት ጥናት ያደረገው በሸቀጦች ጅምላ ንግድና አስመ


ጪ ድርጅት የሲሚንቶ ሽያጭ አፈፃፀም ሥርዓት ሲሆን የሽያጭ ሥራውን የሚሠራ
ተመጣጣኝ የሰው ኃይል ባለመመደቡ አሠራሩ ለወረፋና ለእንግልት የሚዳርግ መሆኑ፣
ደንበኞች ማሟላት የሚገባቸውን መረጃዎች ሳያሟሉ መስተናገዳቸው፣ የማረጋገጥ፣
የማገናዘብና የቁጥጥር ሥርዓቱ ደካማ መሆን፣ እየተሠራበት ያለው መመሪያ ወጥ
ያለመሆንና ለግለሰብ ውሳኔ የተጋለጠ መሆን፣ የሲሚንቶ ተጠቃሚዎች መረጃ
አያያዝ ደካማነት፣ በዋናው መሥሪያ ቤትና በቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች መካከል ያለው
የመረጃ ልውውጥ ደካማነት በዋናነት የታዩ የአሠራር ችግሮች ናቸው፡፡

ጥናቱ በተካሄደበት ወቅት መንግሥት ከውጭ ሀገር የሚያስገባውን ሲሚንቶ የሚያ


ከፋፍለው /የሚሸጠው/ በጅንአድ የሽያጭ ቅርንጫፎች መሆኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን
በቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች የተመደቡት የሽያጭ ሠራተኞች ጥቂት በመሆናቸው ተገ
ልጋዮችን በተረጋጋ ሁኔታ ለማስተናገድ አልተቻለም፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ ቃሊቲ
ቅርንጫፍ የሽያጭ ማዕከል የተመደቡት የሽያጭ ሠራተኞ ሦስት ብቻ ሲሆኑ በደብረ ዘይት
ደግሞ መረጃዎችን ከማጣራት ጀምሮ ሸያጭ የሚካሄደው በቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጁ
ብቻ መሆኑን በጥናቱ ወቅት ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ የሽያጭ ሠራተኞቹ አነስተኛነት
ወረፋ እንዲበዛና ተገልጋዩ ቀድሞ ለመስተናገድ ካለው ፍላጎት አንፃር ከሠራተኞቹ
ጋር እንዲመሳጠር የሚያደርግ ከመሆኑም ባሻገር ተደራራቢ ሥራ በአንድ ሠራተኛ
መሠራቱ ለሙስናና ብልሹ አሠራር በር እንዲከፈት አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

ይህን ችግር ለማቃለልም በቂ የሰው ኃይል በዝውውር መመደብ፣ የሲሚንቶ ተጠቃሚ


ዎችን በየተሠማሩበት ዘርፍ /የግል ቤት ሰሪዎች፣ አልሚዎች፣ የሥራ ተቋራጮችና
መንግሥት ለሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች/ በቀናት በመደልደል እና ፕሮግራም
በማውጣት ማስተናገድ ጥናቱ በመፍትሄ ሃሳብነት ጠቁሟል፡፡

በጅንአድ የታየው ሌላው የአሠራር ችግር በመመሪያው ላይ የተጠቀሱት መሥፈርቶ


ች ባልተረጋገጡበትና ባልተሟሉበት ሁኔታ የሲሚንቶ ሽያጭ መከናወኑ ነው፡፡ ለምሳሌ
ጊዜው ባለፈበት የግንባታ ፈቃድ፣ የቀበሌ መታወቂያ ባልተያያዘበት እና ባልታደሰ
የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲሚንቶ መሸጥ የተስተዋሉ የአሠራር ሥርዓት ችግሮች ነበሩ፡፡
ይህም መመሪያን ያልተከተለ አሠራር ለሙስናና ለብልሹ አሠራር በር እንደሚከፍት
አያጠራጥርም፡፡ ከዚህ አንፃር ማንኛውም ሲሚንቶ ፈላጊ የተጠቀሱትን መሥፈርቶች
ማሟላቱን ማረጋገጥ እና በተከናወኑ የሽያጭ ፋይሎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ
የሚታዩ ችግሮችን በቀጣይ ሥራዎች ላይ እንዳይደገሙ የሚያስችል አሠራር
መዘርጋት እደሚያስፈልግ ተመልክቷል፡፡

62
በደብረ ዘይትና በአዳማ የጅንአድ ቅርንጫፎች ለግል ቤት ሠሪዎችና ኢንቨስተሮች
የሚሰጣቸው የሲሚንቶ መጠን የአካባቢው የከተማ ልማት ጽ/ቤት ግንባታው አሁን
ያለበትን ደረጃ ከግምት በማስገባት ሲሆን በአዲስ አበባ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ግን ሲሚንቶ
ፈላጊዎች ቀደም ብለው ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ጥያቄ ያቀረቡበትን መረጃ መሠረት
በማድረግ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ መረጃ ወቅታዊ ያልሆነ፣ ከሙገር ሲሚንቶ መውሰ
ድ አለመውሰዳቸውን እንዲሁም ከወሰዱ ምን ያህል መጠን እንደወሰዱ የሚረጋገጥበት
አሠራር አለመኖሩ እና የሚፈቀድላቸውም ሲሚንቶ ግምታዊና ለግል ውሳኔ የተጋለጠ
መሆኑ በጥናቱ ታውቋል፡፡ ይህም በሽያጭ ማዕከሎች ወጥ የሆነ አሠራር አለመኖሩን
የሚያመለክት በመሆኑ በሁሉም ማዕከሎች በተመሳሳይና ወጥ በሆነ መልኩ ሽያጩን
ማከናወን እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ በደብረ ዘይትና በአዳማ የሲሚንቶ ሽያጭ ማዕከላት ከ1000 ኩንታል


በላይ ሲሚንቶ የሚገዙ ግልሰቦች /ድርጅቶች/ ከዋናው መሥሪያ ቤት ተፈቅዶላቸውና
ክፍያ ፈጽመው ሰነዱን ይዘው በአካል በመሄድ ይጠይቃሉ፡፡ ሆኖም ሽያጩ ስለመፈቀ
ዱ ከዋናው መሥሪያ ቤት ማረጋገጫ ለማግኘት የሚያስችል አሠራር አለመዘርጋቱን
ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ይህ ደግሞ ለሰነድ መጭበርበር በር የሚከፍት ሆኖ ታይቷል፡፡
ስለሆነም በዋናው መሥሪያ ቤትና በቅርንጫፍ ማዕከላት መካከል ያለውን ክፍተት
ለመድፈን ዋናው መሥሪያ ቤት ክፍያ ፈጽመው በደብረ ዘይትና በአዳማ ቅርንጫፎች
እንዲስተናገዱ የተፈቀደላቸውን ደንበኞች ስም ዝርዝር፣ የከፈሉትን የገንዘብ መጠንና
የሚወስዱትን የሲሚንቶ መጠን ለቅርንጫፍ ማዕከላት ፋክስ ማድረግ ተገቢ መሆኑን
በመፍትሄ ሃሳብነት ተጠቁሟል፡፡

በጅንአድና በሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር መካከል ያለው የሥራ ግንኙነት ግልጽነ
ት የሌለው መሆኑ ሌላው በጥናቱ የተጠቆመ የአሰራር ሥርዓት ችግር ሆኖ ታይቷል፡፡
የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ሲሚንቶ ፈላጊዎችን በደረጃ ሲመድብ መስፈርቱ
በግልጽ ባልተቀመጠበት ሁኔታ /ደረጃ አንድ፣ ደረጃ ሁለትና ደረጃ ያልተሰጣቸው/ ብሎ
በመከፋፈል የተወሰኑት ደንበኞች ቅድሚያ እንዲያገኙ መደረጉን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ይህም በሥራና ከተማ ልማትና በጅንአድ መካከል የተፈጠረው የሥራ ግንኙነት ምን
መምሰል እንዳለበት በግልጽ የሰፈረ መመሪያ ያልተገኘ በመሆኑ አሠራሩ ተጠያቂነትን
የሚያላላ፣ ለሙስናና ብልሹ አሠራር ክፍተት ሊፈጥር የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡

ስለሆነም በሁለቱ መሥሪያ ቤቶች መካከል ያለው ግንኙነት ከተሰጣቸው ተግባርና


ኃላፊነት አንፃር ተገምግሞ በግልጽ እንዲቀመጥ ማድረግ እንዲሁም የሲሚንቶ
ሽያጩን በተመለከተም ኃላፊነቱና ተጠያቂነቱ የማን እንደሆነ በግልጽ ሊቀመጥ
የሚችልበት ሁኔታ ቢፈጠር ይመከራል፡፡

በአጠቃላይ በሁለቱም ተቋማት የተመለከቱትን የአሠራር ሥርዓት ችግሮች ለመፍታት


በኮሚሽኑ የተሰጡትን የመፍትሄ ሃሳቦች ተግባራዊ ማድረግ፣ ተቋማቱ በራሳቸው ኃይል
የአሠራር ጥናት ማካሄድና ተግባራዊ ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

63
የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የግንባታ
ሥራዎች ፈቃድና እድሳት አሰጣጥ የአሰራር ሥርዓት

በ ሚኒስቴር መ/ቤቱ እና በሚመለከታቸው አካላት መካከል የተጠናከረ የመረጃ


ልውውጥ ሥርዓት ባለመኖሩ የተነሳ በተጭበረበረ ማስረጃ የተቋራጭነት ፈቃድ እንዲሰጥ
መደረጉ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር ክፍተት ከሚፈጥሩ ሁኔታዎች ውስጥ ይጠቀሳል፡፡

ለሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የሚላኩ ለሥራ ተቋራጭነትና ለባለሙያ ምዝገባ


የሚያስፈልጉ የተለያዩ ማስረጃዎች ለምሳሌ ከፌዴራል መንገድ ትራንስፖርት ባለስል
ጣን እና ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮዎች የሚቀርቡ የሊብሬ ማስረጃ ደብዳቤዎ
ች፣ ከፌዴራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃዎች እንዲ
ሁም በሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ለተቋራጮች የሚፈፀሙ የሠራተኛ ቅጥር
ማስረጃዎች ለሐሰተኛ ማስረጃ የተጋለጡ እና በተለያዩ የሥራ ወቅቶች የሚያጋጥሙ
መሆናቸውን የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህም የተጠናከረ የመረጃ ልውውጥ አለመኖር
የሚፈጥረው ክፍተት ብቃት የሌላቸው ተቋራጮች የተቋራጭነት ፈቃድ በመውሰድ

64
የግንባታ ሥራ እንዲያከናውኑና የሕዝብ ሀብት ያለአግባብ እንዲባክን ከማድረጉም
በተጨማሪ ሕገወጥ ሥራ እንዲሰራ በር የሚከፍት ሆኖ ታይቷል፡፡

ለዚህ የአሰራር ሥርዓት ክፍተት የሚመለከታቸው መ/ቤቶች ከሥራ ተቋራጭ ሙያ


ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ዳታ ቤዝ እንዲያዘጋጁና በየጊዜው ወቅታዊ በማድረግ
የተዘጋጀውን የዳታ ቤዝ መረጃ በሶፍት ኮፒ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ልዩነት ለሥራና
ከተማ ልማት ሚኒስቴር የሚልኩበት ወይም ሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር መረጃ
ዎችን ከሚመለከታቸው አካላት የሚሰበስብበት ሥርዓት በመዘርጋት ፍቃድ ለመውሰ
ድም ሆነ ለማደስ ሕገወጥ ማስረጃዎች እንዳይቀርቡ ለመከላከል ሊያግዝ እንደሚችል
በመፍትሄ ሀሳብነት የቀረበ ነው። እንዲሁም ሚኒስቴር መ/ቤቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸ
ው መ/ቤቶች ጋር የተጠናከረ የሥራ ቅንጅት በመፍጠር በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
የታገዘ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት /net work/ በመዘርጋት ሐሰተኛ ማስረጃ በማቅረብ
የሚፈፀመውን የማጭበርበር ተግባር መቆጣጠር በረዥም ጊዜ እቅድ ተግባራዊ መደረግ
ያለበት በጥናቱ የተጠቆመ ሌላ የመፍትሄ ሀሳብ ነው፡፡

የመጀመሪያው የመፍትሄ ሀሳብ ተግባራዊ ሲሆን ከሚመለከታቸው መ/ቤቶች ጋር


የሥራ ቅንጅት ለመፍጠር ጊዜ ሊወስድ የሚችል እና መረጃው የሚገኘው ከሌላ አካል
ስለሆነ በሚፈለገው መጠንና ጊዜ ላይገኝ ይችላል። ይህን ችግር ለማቃለል ሚኒስቴር
መ/ቤቱ የጋራ የውይይት መድረክ በመፍጠር አስፈላጊውን የሥራ ቅንጅት ቢያደርግ
የሚወስደውን ጊዜ በመቀነስ የተፈለገውን መረጃ በበቂ ሁኔታ ማግኘት ይቻላል፡፡

የሥራ ፈቃድ የተሰጣቸውን ተቋራጮች የሥራ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግ


በት ሥርዓት አለመዘርጋቱ ሌላው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የታየ የአሰራር ክፍተት ነው፡፡
የሕዝብ ጤንነትና ደህንነት እንዲረጋገጥ ለማድረግ በሀገሪቱ የሚገነቡ ሕንፃዎችን
ወይም የሕንፃ ግንባታ ማሻሻያና የአገልግሎት ለውጥ በተመለከተ በሀገሪቱ ተፈፃሚ
የሚሆን ዝቅተኛውን ደረጃ ለመወሰን የሚያስችል ረቂቅ የሕንፃ አዋጅ ለሕዝብ
ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የተሰጡ የማስተካከያ ሀሳቦችን በማካተት ለማሻሻል ጥረት
እየተደረገ ይገኛል፡፡ በረቂቅ አዋጁ አንቀፅ 27 /52-53/ የተመዘገቡ የሥራ ተቋራጮችን
ስለመቅጠርና ደረጃው የማይፈቅድለትን ግንባታ ማከናወን እና ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ
ማከናወን የሚያስከትላቸው ቅጣቶች የተጠቀሱ ቢሆንም የሥራ ተቋራጮችና የሙያ
ምዝገባ ፈቃድ የተሰጣቸው ባለሙያዎች የሥራ አፈፃፀማቸውን መገምገም የሚቻልበት
ና እንደ አስፈላጊነቱ ከሚመለከታቸው ተቋራጮች ጋር የምክክር መድረክ ስለሚዘጋጅበ
ት ሁኔታ በግልፅ የተጠቀሰ ሀሳብ የለም፡፡

እስካሁን በነበረው ሁኔታ የሥራ ተቋራጮች ደረጃቸውን ለማሳደግ ጥያቄ ሲያቀርቡ


ላለፉት 10 ዓመታት የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ሁኔታ የሚያሳይ የሥራ ተቋራጮች
ፕሮጀክት አፈፃፀም መጠየቂያ ቅፅ እንዲሞሉና እራሳቸው እንዲያረጋግጡ በማድረግ
የሥራ ተቋራጮች የመጀመሪያውን የሥራ ተቋራጭ ደረጃ ካወጡ በኋላ ለሚጠይቁት
የሥራ ደረጃ ለውጥ አስፈላጊውን የሥራ መሣሪያና ሌሎችን መስፈርቶች አሟልተ
ዋል ተብሎ ሲታመንበት በየትኛውም ጊዜ ፈቃዱ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡ በዚህም

65
ምክንያት ተቋራጮች ከዚህ በፊት ያከናወኗቸውን ሥራዎች ብቃትና ውጤታማነት እንዲሁ
ም ግንባታው በሚከናወንበት ሥፍራ ተቋራጩ ያስመዘገባቸው ማሽነሪዎችና ባለሙያዎች
ሥራ ላይ ስለመኖራቸው በተጨባጭ የሚረጋገጥበት ሥርዓት አልተዘረጋም። በዚህ
ሁኔታ የሚሰጡ የሥራ ተቋራጭነት ፈቃዶች ጥራታቸውንና የጥንካሬ ደረጃውን
ያልጠበቁ ግንባታዎች እንዲገነቡ እና የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ የሚያደርጉ
ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከተለያዩ ቦታዎች ሊቀርቡ በሚችሉ ሐሰተኛ ፕሮጀክት
አፈፃፀም ማስረጃዎች ምክንያት በፈቃድ አሰጣጥ ዙሪያ የማጭበርበር ሥራ
እንዲፈፀም በር ይከፍታል፡፡

የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት በተደረገው ጥናት የሁለት መፍትሄ አማራጮች


የቀረቡ ሲሆን መሥሪያ ቤቱ ሁለቱን የመፍትሄ ሀሳቦች በማቀናጀት ተግባራዊ ቢያደ
ርግ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል፡፡ ይኸውም መሥሪያ ቤቱ በመስክ
ሱፐርቪዥንና በሚቀርብለት ሪፖርት መሠረት ግምገማ በማድረግ ፈቃድ እና የፈቃድ
እድሳት የሚሰጥበትን የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት፣ እንደ አስፈላጊነቱ በተወሰነ ጊዜ
ልዩነት የሥራ ተቋራጮችን ያሳተፈ የውይይት መድረክ በሚኒስቴር መ/ቤቱ በኩል
ማዘጋጀትና ተቋራጮች ያስመዘገቡትን ማሽነሪና መሣሪያ እንዲሁም ባለሙያዎችን
በትክክል ሥራ ላይ አሰማርተው እየሰሩ ስለመሆናቸው የሱፐርቪዥን ሥራ
በሚኒስቴር መ/ቤቱ በኩል ማከናወን ያስፈልጋል።

በሌላ በኩል ፕሮጀክቶች በተጠናቀቁበት ክልሎች በሚገኙ ሥራና ከተማ ልማት


ቢሮዎች አማካኝነት የሥራ ተቋራጮች የሥራ አፈፃፀም በመስክ ላይ እና በሚቀርበው
ሪፖርት መሠረት ግምገማ እየተደረገ የግምገማው ውጤት ለሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚቀ
ርብበትን ስርዓት በመዘርጋት ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ፈቃድና የፍቃድ እድሳት
የመስጠት ሥራ ማከናወን ተገቢ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ተቋራጮች ያስመዘገቡት
ን ማሽነሪና መሣሪያ እንዲሁም ባለሙያዎችን በትክክል ሥራ ላይ አሰማርተው እየሰሩ
ስለመሆናቸው የሱፐርቪዥን ሥራ በክልል ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ በኩል እየተከና
ወነ ውጤቱ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ በመላክ በጥናቱ የታየውን የአሰራር ሥርዓት ክፍተት
ለመዝጋት ያስችላል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

የመፍተሔ አማራጮቹ በቅንጅት ተግባራዊ ሲሆኑ የክልል የሥራና ከተማ ልማት


ቢሮዎች ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠት ወቅታዊ የሆነ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት
ላይልኩ ስለሚችሉ የክልል ሥራና ከተማ ልማት ቢሮዎችሥራ አፈፃፀም ግምገማ
ሪፖርቱን ወቅቱን ጠብቀው እንዲልኩ የጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበትን ሁኔታ
በማመቻቸት ስጋቱን ማቅለል እንደሚቻል በጥናቱ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተጠናከረ የፋይል መረጃ አያያዝ ሥርዓት አለመኖር


መ/ቤቱን ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ ሁኔታ ነው፡፡

ይህንንም በተጨባጭ ለማየት ሲባል በናሙና የተመረጡ 51 ፈቃድ የተሰጣቸው


ፋይሎች /መረጃዎች/ የታዩ ሲሆን መረጃዎቹ ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው

66
ካለመደራጀታቸውም በላይ 2 ፋይሎች ወይም 3.92% ያህሉ የፋይል ምዝገባ ቁጥር 0109፣
0894 ሙሉ ለሙሉ አባሪ ቁጥር የተሰጣቸው ሲሆን 5 ፋይሎች ወይም 9.81% ያህሉ
የፋይል መዝገብ ቁጥር 1171፣ 0761፣ 1268፣ 2077፣ 0012 አባሪ ቁጥር ምዝገባ
ተጀምሮ የተቋረጠባቸው ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ 44 ፋይሎች 86.27% የሚሆኑት ደግሞ
አባሪ ቁጥር አልተሰጣቸውም፡፡ ይህ ሁኔታ በተለያዩ ምክንያቶች ፍይሎች ከአንድ
ሥራ ክፍል ወደ ሌላ የሥራ ክፍል ለሥራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ መረጃዎች ተገንጥለው
ሊጠፉ የሚችሉበትን ሁኔታ በማመቻቸት ሕገወጥ ለሆነ የሥራ አፈፃፀም መንገድ
የሚከፍት አሰራር ነው፡፡

ችግሩንም ለመቅረፍ ተከታታይ ቁጥር ያልተሰጣቸው የሥራ ተቋራጭ ፋይሎች


በጥንቃቄ ተከታታይ ቁጥር ተሰጥቷቸው እንዲቀመጡ ቢደረግ እና ፋይሎቹ ለሥራ
ሲንቀሳቀሱም የመጨረሻው አባሪ ቁጥር እየተመዘገበ ርክክብ የሚፈፀምበት የአሰራር
ሥርዓት በመዘርጋት በፋይሉ ውስጥ ያሉ መረጃዎች እንዳይጠፉ እና የማጭበርበር
ሥራ እንዳይፈፀም ለመከላከል ያስችላል፡፡

ከዚህ በፊት ለፋይሎች አባሪ ቁጥር የመስጠት ሥራ የተጀመረ ቢሆንም ሥራው ጥናቱ
በተካሄደበት ወቅት የተቋረጠ በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኃላፊዎችና ሠራተኞች
ለችግሩ ተገቢውን ትኩረት ላይሰጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው
ኃላፊዎች ለችግሩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው ለጊዜው ተጨማሪ የሰው ኃይል
በመመደብ ሥራው በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅበትን ሁኔታ በማመቻቸት
የመፍትሄ ትግበራውን ተከትሎ የሚከሰተውን ስጋት ማስወገድ ይቻላል፡፡

67
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውጭ
ማስታወቂያ ፈቃድ አሰጣጥ ቁጥጥርና ክትትል የአሰራር ሥርዓት

የ ፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአሰራር ሥርዓት ጥናት ማሻሻያ


ካካሄደባቸው መሥሪያ ቤቶች መካከል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውጭ ማስታ
ወቂያዎች ፈቃድ አሰጣጥ ቁጥጥርና ክትትል አንዱ ሲሆን በጥናቱ የታዩ የአሰራር
ሥርዓት ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

አስተዳደሩን ለሙስናና ለብልሹ አሰራር ክፍተት ሊያጋልጡ ከሚችሉ ሁኔታዎች


ውሰጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድርም ሆነ በክፍለ ከተሞችና ቀበሌዎች ደረጃ
አዲስ ፈቃድ ለመስጠት፣ በአዲስ መልክ ለመቀየር ወይም ለማሳደስ የሚያስችል ደንብ፣
መመሪያና ስታንዳርድ አለመኖሩ አንዱ ነው፡፡

ለምሳሌ በአሁኑ ጊዜ በየካ ክፍለ ከተማ ማስታወቂያ ፈቃድ የመስጠት ሥራዉ ሙሉ


በሙሉ የሚሰራዉ በቀበሌ ደረጃ ብቻ ነዉ፡፡ በልደታና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተሞች
ደግሞ የሚሰራዉ ሙሉ በሙሉ በክ/ከተማ ደረጃ ብቻ ነዉ፡፡ ወጥ የሆነ ሥራ
ለመሥራት የሚያስችል ደንብ፣ መመሪያና ስታንደርድ ባለመኖሩ በተለያዩ ክፍለ
ከተሞች የተለያዩ ሥራዎች ሲሰሩ ይታያል፡፡

የማስታወቂያ ሰሌዳ የሚተከልበት ቦታ ከከተማዉ መሪ ፕላን ጋር መጣጣሙን፣


የእግረኛና የተሽከርካሪ ትራፊክ እንቅስቃሴን የማይከለክልና የማያዉክ መሆኑን ለማረጋገጥ
የሚያስችሉ ስታንዳርዶች የሉትም፡፡ የማስታወቂያ መትከያ ከፍታዉ ምን ያህል
እንደሆነ፣ በዋና ዋና መንገዶች ላይ በሚተከሉ ማስታወቂያዎች ከመንገድ በምን ያህል
እርቀት መተከል እንዳለባቸዉ፣ የሚተከለዉ ማስታወቂያ ወርድና ቁመት ምን መሆን
እንዳለበት የሚያሳይ የዉጭ ማስታወቂያ ሰሌዳ ሥራ ሊመራበት የሚችል የወጣና የፀደቀ
መመሪያና ስታንደርድ ባለመኖሩ ሥራውን ለግለሰቦች ውሳኔ የተጋለጠ አድርጎታል፡፡ ይህ
አሰራር ለሙስናና ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ ከመሆኑ ባሻገር ለመንግሥት
ገቢ መደረግ ያለበት ገንዘብ በግለሰቦች እንዲባክን ዕድል የሚሰጥ ሊሆን ይችላል፡፡

የውጭ ማስታወቂያ ለመፍቀድ፣ ዓመታዊ ፈቃድ ለማደስና በአዲስ መልክ ለመቀየር


እና ወጥ የሆነ ሥራ ለመሥራት የሚያስችል ደንብ፣ መመሪያና ስታንዳርድ ተዘጋጅቶ
ተግባራዊ ማድረግ የተሻለ የመፍትሄ ሀሳብ እንደሚሆን ጥናቱ አስቀምጧል፡፡

ወሳኝ በሆኑ ቦታዎች የዉጭ ማስታወቂያ ሠሌዳ ጨረታ ሳያወጡ ፈቃድ መስጠት
ሌላው በጥናቱ የታየ የአሰራር ሥርዓት ችግር ነው፡፡

ለውጭ ማስታወቂያ ሰሌዳ ቦታ ጨረታ ያለመውጣት የሚያስከትላቸው ዋና ዋና ችግሮች፤

• በከተማዉ ዋና ዋና መንገዶችና አደባባዮች ላይ በሚገኙ የዉጭ ማስታወቂያ ሰሌዳ

68
ቦታዎች ጥናት ሳይደረግባቸውና ጨረታ ሳይካሄድባቸዉ አገልግሎት ላይ ይዉላሉ፡፡
ይህ አሰራር አገልግሎቱን የሚፈልጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በውድድር ላይ
በተመሠረተ መልኩ እንዳይስተናገዱ በማድረግ የተሻለ ገቢ ለማሰባሰብ ካለማስቻሉም በላይ
ግለሰቦች በድርድር የሚፈልጉት ቦታና ስፋት ያለውድድር ለማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ
ሊፈጥር ይችላል፡፡

• የንግድ ፈቃድ የሌላቸዉ፣ የንግድ ፈቃዳቸውን ያላሳደሱና የመንግሥትን ግብር


በአግባቡ የማይከፍሉ ግለሰቦች ጭምር የማስታወቂያ ፈቃድ በመዉሰድ ተጠቃሚ
የሚሆኑበት ሁኔታ እንዲፈጠር ምቹ ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል፡፡

በአጠቃላይ አሰራሩ በተቆጣጣሪ ሠራተኞችና በባለጉዳዮች መካከል የጥቅም ግንኙነት


በመፍጠር ለአድሎአዊ አሰራር የተጋለጠ ከመሆኑ በተጨማሪ ለመንግስት ገቢ መሆን
የሚገባዉ ገንዘብ በአግባቡ ገቢ ላይደረግ የሚችልበት ሁኔታ የተመቻቸ ሆኖ ይታያል፡፡

የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት በጥናቱ የቀረበው የመፍትሄ ሃሳብ ከከተማዉ


መሪ ፕላን ጋር በተጣጣመ መልኩ፣ የትራፊክ እንቅስቃሴ በማያዉክ ሁኔታ፣ የመሠ
ረተ ልማት አዉታሮችን በማያበላሽ መልኩ በዋና ዋና መንገዶች እና አደባባዮች ላይ
ለሚተከሉ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች በጥናት ላይ ተመስርቶ ቦታዎቹ በየዓመቱ ለጨረታ
እንዲቀርቡ በማድረግ ነው፡፡

የዉጭ ማስታወቂያ ፈቃድ አሰጣጥ ሥራ በባለቤትነት የሚሰራው የሥራ ዘርፍ


በግልፅ የማይታወቅና አሠራሩም ወጥነት የሌለው መሆኑ በጥናቱ የታየ የአሰራር
ሥርዓት ችግር ነው፡፡

የዉጭ ማስታወቂያ ፈቃድ አሰጣጥ ሥራን በክፍለ ከተሞችና በቀበሌዎች ወጥነት


በጎደለው መልኩ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ለአብነት ያህል በልደታ ክ/ከተማ የማስታወቂያ
የሥራ ሂደት በሥራው የሚሳተፍ ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በቂርቆስና በቦሌ
ክ/ከተሞች የማስታወቂያ የሥራ ሂደት በሥራው የማይሳተፍ መሆኑን በመረጃ ማሰባሰብ
ወቅት ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

በአራዳ ከ/ከተማ በቀበሌ 10 እና በቦሌ ክ/ከተማ ቀበሌ 02 የቁጥጥሩ ሥራ የሚሰራው


በግንባታ ፈቃድ የሥራ ክፍል ነው፡፡

በሌላ መልኩ በልደታ ክ/ከተማ የግንባታ ፈቃድ የሥራ ሂደት ፈቃዱን ከሰጠ በኋላ
ለክ/ከተማዉ ወይም ለቀበሌው ሬጉላቶሪ ፈቃድ የተሰጠበትን ኮፒ አይሰጥም፡፡ በዚህ
ምክንያት ቀበሌዎች ላይ ያሉ ሬጉላቶሪዎች ፈቃድ መሰጠቱን አያውቁም፡፡ ከዚህ በተ
ጨማሪ የደንብ አስከባሪ የሥራ ሂደት ተጠሪነቱ ለፍትህና ህግ ጉዳዮች በመሆኑ የሬጉ
ላቶሪው የሥራ ሂደት በትብብር ደብዳቤ ከማሳወቅ ውጭ ደንብ አስከባሪዎች ሥራውን
ባይሰሩ የሚጠየቁበት የተዘረጋ ሥርዓት የሌላቸው በመሆኑ ወጥነት በጎደለው መልኩ
እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ የደንብ ማስከበር የሥራ ሂደት በአግባቡ ባይሰሩ ወይም ከሥነምግባር

69
ውጪ ከባለጉዳዮች ጋር በመስማማት ቁጥጥሩን በማላላት ባለጉዳዮች ፈቃዳቸውን
እንዳያሳድሱ፣ ህገወጥ ማስታወቂያ የሰቀሉም እንዳያነሱ ለማድረግ የማያስችል ነው፡፡
ከላይ በዝርዝር ለመግለጽ እንደተሞከረው የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ አሰጣጥ
ቁጥጥርና ክትትል ሥራን በባለቤትነት የሚሠራው የሥራ ዘርፍ በግልጽ ባለመታወቁ
ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በማላላት ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተት ከመፍጠሩም
በተጨማሪ ለመንግሥት ገቢ መደረግ ያለበት ሳይሰበሰብ የሚቀርበት አጋጣሚን
የሚፈጥር ሊሆን ይችላል ፡፡

ሁሉም የሥራ ሂደቶች እንደ ተግባርና ኃላፊነታቸው የተለያዩ ተግባራት የሚጠበ


ቅባቸው ቢሆንም ለክትትልና ለቁጥጥር በሚያመች፣ በመመሪያ በተደገፈ መልኩ
ኃላፊነትና ተጠያቂነት በማስፈን በየጊዜዉ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግበት ሥርዓት
መዘርጋት ተገቢ ነው፡፡ እንዲሁም በአንድ አካባቢ አገልግሎት ፈላጊዎች አገልግሎት
ለማግኘት በሚችሉበት ሁኔታ ቢሮዎች ቢደራጁ ለአሰራር ሥርዓት ችግሩ የመፍትሄ
ሀሳብ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማስታወቂያ ቢሮ የውጭ ማስታወቂያ የገቢ አሰባሰብ


ወጥነት የጎደለው መሆኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በናሙና ከታዩ ክ/ከተሞች መካከል፡-

• በቂርቆስ ክፍለ ከተማና አራዳ ክ/ከተማ ገቢ የሚሰበሰበው በገቢዎች ኤጀንሲ በኩል


ብቻ ሳይሆን በግንባታ ፈቃድ የሥራ ሂደት በኩልም ነው።

• በአራዳ ክ/ከተማ የማስታወቂያ ገቢ ለመሰብሰብ በሚደረግ ተመን የተለያዩ የስሌት


ዘዴዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ በጥናት ወቅት የተሰበሰቡ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ይህም የአሠራር ልዩነት ሊፈጠር የቻለው በአራዳ ክ/ከተማ የግንባታ ፈቃድ የሥራ ሂደት
ገቢ የሚሰበስበዉ በግንባታ ፈቃድ መመሪያ ሲሆን ገቢዎች ኤጀንሲ ደግሞ በአገልግሎት
ክፍያ ደንብ ቁጥር 6/1990 የሚጠቀም በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት
የአንድ ሜትር ካሬ የአገልግሎት ክፍያ የተለያየ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ አሠራሩ ወጥነት የጉደለውና ለቁጥጥርና ክትትል የማያመች ከመሆኑ በተ


ጨማሪ ለድርድር ወይም ለግል ጥቅም ሲባል ተመኑን አነስተኛ ዋጋ በሚያሠላዉ ደንብ
ወይም መመሪያ መጠቀም የሚያስችልና ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ እንዲሆን
ከማስቻሉም ሌላ የመንግሥትን ገቢ በአግባቡ እንዳይሰበሰብ ሊያደርግ ይችላል፡፡

የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ የሚሠጠዉ በግን


ባታ ፈቃድ የሥራ ሂደት በመሆኑና ደንበኞች የማስታወቂያዉን የቴክኒክ ሥራ የሚ
ያሰሩት በዚህ የሥራ ክፍል ስለሆነ ስሌቱ በዚሁ የሥራ ሂደት ደንብ ቁጥር 6/1990
በሚደነግገው መሠረት ቢከናወንና አሰባሰቡን በሚመለከት ለግንባታ ፈቃድ የሥራ
ሂደት ከገቢዎች ኤጀንሲ ውክልና ቢሰጥ የተሻለ ይሆናል፡፡

ሌላው የአሰራር ሥርዓት ችግር የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ እድሳት ክትትልና

70
ቁጥጥር የላላ መሆኑ ነው፡፡

የውጭ ማስተዋወቅ ሥራ አገልግሎት ክፍያ ለማስከፈል በወጣ ደንብ ቁጥር 6/1990


መሠረት የማስታወቂያ ፈቃድ የወሰደ ድርጅት ወይም ግለሰብ ፈቃድ የወሰደበት ጊዜ
ሲያበቃ የማሳደስ ሥራ እንዲሠራ ወይም ካላሳደሰ እንዲያነሳ እና ሌላ አዲስ ማስታወ
ቂያ አንዲተከልበት ቦታ የማስለቀቅ ሥራ በሬጉላቶሪ የሥራ ሂደት ወቅታዊ ክትትልና
ቁጥጥር አይደረግም፡፡

በዚህም ምክንያት ድርጅቶቹ ወይም ግለሰቦቹ ለማስታወቂያ መክፈል የነበረባቸውን


የመንግስት ገቢ ባለመክፈል ቦታዉን በመያዝ ሌሎች አዲስ ማስታወቂያ ፈላጊዎች እንዳይ
ጠቀሙበት ስለሚደረግ የማስታወቂያ ፈቃድ ያላሳደሱ ባለጉዳዮች ከተቆጣጣሪ ሠራተኞች
ጋር በመስማማት ማስታወቂያው እንዳይነሳ ወይም ከነበረው በበለጠ አስፍቶ መትከል እንዲ
ችል የሚደረግበት ሁኔታ አለ። ይህም ለሙስናና ለብልሹ አሰራር ሊያጋልጥና መንግሥት
ማግኘት የሚባውን ገቢ በማሳጣት ግለሰቦች ሕገወጥ ጥቅም እንዲያገኙ ሁኔታዎችን
ያመቻቻል፡፡

የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ ወስደው በወቅቱ በማያሳድሱ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ላይ


ወቅታዊ የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት፣ የሬጉላቶሪ የሥራ ሂደትን በማጠናከር
ተገቢ ያልሆነ ድርድርና ግንኙነትን በማስቀረት የመንግሥትን ገቢ በአግባቡ እንዲሰበሰብ
ማድረግ የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት የቀረበ የመፍትሔ ሃሳብ ነው፡፡

በክ/ከተማም ሆነ በቀበሌ ደረጃ የሚገኙት ተቆጣጣሪዎች ቁጥጥር የሚያደርጉት


ህጋዊ ሆነው የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ የወሰዱት ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ ብቻ
ነው፡፡ ሆኖም በህገወጥ መንገድ የውጭ ማስታወቂያ ተጠቃሚ የሆኑ ድርጅቶችንና
ግለሰቦችን ክትትልና ቁጥጥር ሲደረግባቸው አይስተዋልም፡፡ በጥናት ወቅት ለመገ
ንዘብ እንደተቻለዉ የቁጥጥር ሥራው ከማይሰራበት ምክንያት አንዱ የሰው ኃይል
እጥረት መሆኑ ተገልጿል፡፡ የቁጥጥር ሥራውን የሚሰሩት የሬጉላቶሪ ሠራተኞች
በመዋቅሩ መሠረት በቀበሌ ደረጃ አራት የሰው ኃይል ተመድቧል። ይሁንና ሥራው
እየተሰራ ያለው በአንድ ቀበሌ በአንድ የሰው ኃይል ብቻ ሲሆን በየክ/ከተማው
ሦስትና እና ከዚያ በላይ ያሉ ቀበሌዎች ደግሞ ተቆጣጣሪ ሠራተኞች አልተመደበላቸውም፡፡

ለአብነት ያህል በ2002 በጀት ዓመት፡-

• በየካ ክ/ከተማ ደረጃ 18,432 ድርጅቶችና ግለሰቦች የንግድ ፈቃድ የወሰዱ ሲሆን
ህጋዊ የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ የወሰዱ ግን 29 ብቻ መሆናቸውን ከየካ ክ/ከተማ
ገቢዎች ኤጀንሲ ለመረዳት ተችሏል፡፡

• በልደታ ክ/ከተማ 23,000 የሚጠጉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች


ሲኖሩ በ2002 በጀት ዓመት ህጋዊ ሆነው የማስታወቂያ ፈቃድ የወሰዱና ያሳደሱ 84
ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡

71
• በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 17/18 ደግሞ 1970 የንግድ ፈቃድ የወሰዱ ሲኖሩ
በህጋዊ መንገድ የማስታወቂያ ፈቃድ የወሰዱ 216 ብቻ ናቸው፡፡

• በየክ/ከተማው ህጋዊ እና ህጋዊ ያልሆኑ ማስታወቂያዎች ምን ያህል እንዳሉ


ሊታወቅ የሚችልበት መረጃ ለማግኘት አልተቻለም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ፡-

• በቦሌ ክ/ከተማ እንደ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የመሳሰሉ ተቋማት በራሳቸዉ


ግቢ የሚተዋወቀውን የማስታወቂያ ግብር ክፍያ ከህግ ውጭ እንደሚሰበስቡና ከቦሌ
ክ/ከተማ የግንባታ ፈቃድ የሥራ ሂደት ጋር የይገባኛል ጥያቄ እንዳቀረቡ ቃለ መጠይቅ
በተደረገበት ጊዜ ለማወቅ ተችሏል፡፡

• በአራዳ ክ/ከተማም በፒያሳ አካባቢ በሚገኙ የመንግሥት ህንፃዎች ላይ


የሚለጠፉና የሚንጠለጠሉ የዉጭ ማስታወቂያዎች የማስታወቂያ ገቢ
የሚሰበስቡት በቀድሞ አጠራር የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ በመሆኑ ለእነሱ ግብር ከፍለናል
በማለት ለህጋዊ የማስታወቂያ ገቢ ሰብሳቢዉ እንደማይከፍሉ ከአራዳ ክ/ከተማ
ሠራተኞች ጋር በተደረገ ውይይት ለመረዳት ተችሏል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ለኪራይ
ቤቶች ኤጀንሲ የከፈሉት ለሚጠቀሙበት ህንፃ እንጂ ለማስታወቂያው ፈቃድ ባለመ
ሆኑ ከደንብ ማስከበር ሠራተኞች ጋር ለመደራደር ምቹ ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል፡፡

• በከተማው ውስጥ በመብራት ኃይል ፖሎች ላይ የተቀመጡ ማስታወቂያዎች ከ3-4


ዓመት ያስቆጠሩ ሲሆኑ ማን እንዳስቀመጣቸዉ የማይታወቁ በመሆናቸዉ ክፍያ እንዳል
ተከፈለባቸው መረጃ በሰበሰብንበት ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከላይ በዝርዝር ለመግለጽ እንደተሞከረው የማስታወቂያ ፈቃድ ያላቸውንና የሌላቸውን


ለመለየት የተዘረጋ ሥርዓት ባለመኖሩ በተቆጣጣሪው አካልና በደንበኞች መካከል በሚፈ
ጠር ስምምነት ለሙስናና ለብልሹ አሰራር ሊጋለጥ የሚችልበት ሁኔታ ከፍተኛ ነው።

ስለሆነም በህገወጥ መንገድ የውጭ ማስታወቂያ የሚጠቀሙትን ግለሰቦችና ድርጅቶች


ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ በቂ የሰው ኃይል መመደብ፣ በህገወጥ መንገድ የመንግ
ሥትን ገቢ በራሳቸው የሚሰበስቡትን ተከታትሎ ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ ክትትልና
ቁጥጥር የሚደረግበት ሥርዓት መዘርጋት እና ባለቤት የሌላቸው ማስታወቂያዎች
እንዲነሱ ማድረግ የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት በጥናቱ የቀረቡ የመፍትሔ
ሃሳቦች ናቸው፡፡

የፋይልና ሪከርድ አያያዝ ደካማነት በጥናቱ የታየ የአሰራር ሥርዓት ችግር ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በናሙና ከተመረጡት ስድስት ክፍለ ከተሞች ውስጥ
ብዙዎቹ የውጭ ማስታወቂያ የፋይልና ሪከርድ አያያዝና አጠባበቅ ሥርዓት ባልጠበቀ
መልኩ ተበታትኖና ተዘበራርቆ የሚገኝ መሆኑን ለመመልከት ተችሏል፡፡ ማስታወቂያ
የወሰዱ፣ ያላሳደሱ እና በህገወጥ መንገድ የሚያስተዋውቁ ግለሰቦችና ድርጅቶች

72
መኖራቸውን ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የሪከርድና ማህደር ሥርዓት
አልተዘረጋም፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ ሳያሳድሱ የቆዩ የማስታወቂያ ተጠቃሚ ድርጅት ወይም
ግለሰብ የተጠቀመበትን የማስተዋወቅ የገንዘብ ቅጣት ሳይከፍል የሚቀርበት ሁኔታ አለ።
ሕገወጥ ማስታወቂያ ተጠቃሚዎችን ህጋዊ በሆነ መንገድ ከሚጠቀሙት ለይቶ ለማወቅ
የሚያስችል የፋይል አያያዝ ሥርዓት አልተዘረጋም፡፡ ይህ ዓይነት አሰራር ከማስታወቂያ
ፈቃድ ተጠቃሚ ደንበኞች ላይ ሊገኝ የሚገባው ገቢ በአግባቡ እንዳይሰበሰብ አስተዋጽኦ
የሚያደርግና የመንግሥትን ገቢ ግለሰቦችና ድርጅቶች ለራሳቸው ጥቅም እንዲያውሉት
የሚዳርግ ነው። ተቆጣጣሪ ሠራተኞች ከባለጉዳዮች ጋር የጥቅም ተካፋይ እንዲሆኑ በር
የሚከፍት በመሆኑ አሰራሩ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር ሊያጋልጠው ይችላል፡፡

የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ የተሰጠባቸው ፋይሎችና ሪከርዶች አያያዝ ዘመናዊ በሆነ


መልኩ በማደራጀት የማስታወቂያ ፈቃድ የወሰዱ፣ ያሳደሱ፣ ያላሳደሱ እና በህገ ወጥ
መንገድ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶች ተለይተው የሚታወቁበት አሰራር መዘር
ጋት በመፍትሄ ሀሳብነት ተጠቁሟል፡፡

73
የውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የማሽነሪ
እና ተሽከርካሪ አገልግሎት ግዢ እና ክፍያ አፈፃፀም ሥርዓት

በ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና


ኮሚሽን የሙስና እና ብልሹ አሰራር ስጋቶችን ለመከላከል የአሰራር ሥርዓት ማሻሻያ
ጥናት ካካሄደባቸው መ/ቤቶች አንዱ ነው፡፡ በድርጀቱ ጥናቱ የተደረገበት ተግባር እና
የታዩ የአሰራር ክፍተቶች ከነመፍትሄዎቻቸው ቀርበዋል፡፡

የውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ሥራዎች ድርጅት በርካታ የማሽነሪ መሣሪያዎችና


ተሽከርካሪዎች የኪራይ አገልግሎት ግዢ ያከናውናል። ነገር ግን ከድርጅቱ ልዩ የሥራ
ባህሪ አንፃር የአገልግሎት ግዥውን ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ለማከናወን
የሚያስችል የግዥ መመሪያ የለም፡፡ ይህም የአገልግሎት ግዢውን ስልት ከመወሰን
ጀምሮ /የትኛው ግዢ በግልፅ ወይም በውስን ጨረታ/ ለማለት እስከ አፈፃፀም ድረስ
ያለውን የአሰራር ሥርዓት ተጠያቂነትና ግልፅነት እንዳይከተል በማድረግ ለሙስናና
ብልሹ አሰራር ክፍተትን ሊፈጥር ይችላል፡፡

የአሰራር ሥርዓት ችግሩን ለመፍታት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ


ባለሥልጣን በ1998 ዓ.ም ያወጣውን የልማት ድርጅቶች አጠቃላይ የግዢ አፈፃፀም
መመሪያን ማዕከል ያደረገ ድርጅቱ አሁን የሚያጋጥሙትን የቴክኒካልና የፋይናንሺያል
ትንተና ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል የሥራውን ልዩ ባህሪ ያገናዘበ የግዢ መመሪያ
በማውጣት ተግባራዊ ማድረግ በጥናቱ የተጠቆመ የመፍትሄ ሀሳብ ነው፡፡

በሌላ በኩል ብቃት ያላቸው የማሽነሪ እና የተሽከርካሪ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች


ን በተገቢው መንገድ በመምረጥ ጥራት ያለው አገልግሎት ለማግኘት እንዲቻል የአቅ
ራቢዎች ዝርዝር መረጃ በተጠናከረ መልኩ አደራጅቶ መያዙ ጠቀሜታው የጎላ ነው።
ሆኖም በድርጅቱ የማሽነሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች ዝርዝር ወይ
ም ዳታ ቤዝ የሚያዝበትና ወቅታዊ የሚደረግበት አሰራር አለመኖሩ በጥናቱ ተመልክ
ቷል፡፡ ይህ ግልፅነት የጎደለው አሰራር እንዲኖር በማድረግ በአገልግሎት ግዢ ሂደት
ወቅት አንዱ ተግባር የግዢ ዘዴን የመወሰን ሥራ በመሆኑ ውሳኔውን ለመስጠት
ደግሞ እነማን፣ ምን ዓይነት አገልግሎት፣ በየት አካባቢ /ቦታ/ ያቀርባሉ የሚለውን የመረጃ
እጥረት እንዲኖር ያደርጋል፡፡ በግልፅ የተቀመጠ የአቅራቢዎች ዝርዝር ባለመኖሩ
ምክንያት እንዲወዳደሩ /በውስን ጨረታ እና በድርድር/ ለሚፈፀሙ ግዢዎች የሚጋበዙ
አገልግሎት አቅራቢዎች ያለአድልዎ ጥሪ የተደረገላቸው ስለመሆኑ ለማረጋገጥ የማያ
ስችል ከመሆኑም በላይ የተወሰኑ ድርጅቶችን ብቻ አግባብ ባልሆነ መልኩ በመጥቀም
አሸናፊ አድርጎ ለመምረጥ በር ይከፍታል። እንዲሁም አሰራሩ አዳዲስ አቅራቢዎችን
ከተሳትፎ ሊያገል ይችላል፡፡

ለዚህ የአሰራር ሥርዓት ችግር የመንግሥት የግዢ መመሪያ በሚያዘው መሠረት


የአገልግሎቱ አቅራቢ ድርጅቶችን ዝርዝር በመያዝና በየዓመቱ ወቅታዊ እንዲሆን

74
በማድረግ እንዲሁም ድርጅቱ ካለፈው ግዢ ተሞክሮና ልምድ በመነሳት አቅራቢዎችን
እየገመገመ መልካም አፈፃፀም የሌላቸውን ድርጅቶች ወጥ በሆነ መልኩ የሚለይበት
አሰራር በማስፈን ሕገወጥ ተግባር የሚፈፅሙትን መለየት እንደመፍትሄ ተቀምጧል፡፡

ለሙስናና ብልሹ አሰራር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሌላው የአሰራር ሥርዓት ችግር


የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አፈፃፀም ጉድለት ያለበት መሆኑና ሥራ ላይ ያለው
መመሪያም ተግባራዊ አለመሆን ነው፡፡

በማሽነሪ መሣሪያ እና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አፈፃፀም ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን


ለመፍታት ይቻል ዘንድ ድርጅቱ ከሐምሌ ወር 1998 ዓ.ም ጀምሮ ተሻሽሎ
የቀረበ የአፈፃፀም መመሪያን መሠረት በማድረግ ሥራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ሆኖም
የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ሥራ ላይ ማሰማራት እና የመረጃ አያያዝና ክፍያ አፈፃፀም
ላይ መመሪያው በተሟላ መልኩ ተግባራዊ የማይደረግበት ሁኔታ መኖሩ ታውቋል፡፡
ለምሳሌ በመመሪያው አንቀፅ 3 /ሀ-ሸ/ እንዲሁም አንቀፅ 1/ሐ እና ‘መ’ የተዘረዘሩትን ነገሮች
በአግባቡ ተግባራዊ አለመደረጋቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪ የአፈፃፀም መመሪያው
መሠረት የሚያደርገው ከድርጅቱ ልዩ የሥራ ባህሪ አንፃር የተዘጋጀ የግዥ መመሪያ ስለ
ሌለ አንዳንድ ጉዳዮች አሻሚ እና ግልፅነት የጎደላቸው ናቸው፡፡ ለአብነትም በአንቀፅ 1/ሐ/
አስገዳጅ ሁኔታ ካጋጠመ እና የጉዳት ካሳን በተመለከተ የተጠቀሰው ክፍል ክፍተት
ያለበት ሆኖ ይታያል፡፡ ስለሆነም ይህ ክፍተት አቅራቢዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ
ያለአግባብ ጥቅም ለማግኘት እንዲደራደሩ ዕድል ሊከፍት ይችላል፡፡

ከዚህ አንፃር መመሪያውን የሚታዩትን ክፍተቶች ሊያስወግድ በሚችል መልኩ


አሻሽሎ ሥራ ላይ በማዋል ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር በማይከፍት መልኩ ወጥ የሆነ
አሰራር መዘርጋት እንደሚያስፈልግ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

ድርጅቱ የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዢ ሲፈፅም የኪራይ ውል


ከአቅራቢዎች ጋር የሚገባ ቢሆንም በአፈፃፀሙ ላይ የሚከተሉት ችግሮች ይታያሉ፡፡
እነዚህም የኪራይ ውለታው የሚያዘውን ግዴታዎች በየእለቱ የአከራይና ተከራይ
ተወካዮች በፕሮጀክት ላይ ተፈፃሚ ማድረግ አለመቻል፣ አከራዮች ውለታ ከተዋዋሉበት
መሣሪያ ውጪ ሌላ መለያ ቁጥሩና ሞዴሉ የተለየ ማሽነሪ ወደ ፕሮጀክቱ መላክ፣ ያከራዩአ
ቸው መሣሪያዎች ተበላሽተው ምትክ በሚያስገቡበት ወቅት ቀደም ሲል ከነበረው መሣሪያ
ጋር የአቅምና የሞዴል ልዩነት ያለው ማሽን መላክ እና ከውለታ ውጪ ለአከራዩ
ድርጅት ሠራተኞች የውሎ አበል መክፈል ይጣቀሳሉ። እንዲሁም በውለታው መሠረት ካሳ
አለማስከፈል፣ ያለአግባብ ውል መቀየር፣ የውል ሰነድ ዝግጅት መዘግየት እና አከራዩ
ቀድሞ ክፍያ መጠየቅ፣ በውለታ ሰነድ ላይ መሳሪያው ያለ ሥራ በሚቆይበት ጊዜ ስለ
ክፍያ አፈፃፀም ሁኔታ የተገለፀ ነገር አለመኖር፣ ለአንድ ዓይነት መሣሪያ እና ለአንድ
አቅራቢ የተለያዩ አነስተኛ የሰዓት ውል መግባትና ለተለያዩ አቅራቢዎች አንድ ዓይነት
መሣሪያ የተለያየ የቀን አነስተኛ ሰዓት ማሰራት ወዘተ. የሚሉት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የውል ሰነድ ይዘቱን በመከለስ የድርጅቱን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ማዘጋጀት፣


በውል ውስጥ መካተት የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች እንዲካተቱ ማድረግ እና

75
ተግባራዊነቱንም በቅርብ መከታተል ለችግሩ የተሻለ የመፍትሄ ሃሳብ ሊሆን እንደሚችል
ተጠቁሟል፡፡ በድርጅቱ የማሽነሪ እና የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች
/አቅራቢዎች/ ለመወዳደር ሲጋበዙ የድርጅቱን ጥቅም ሊያስጠብቅ በሚችል መልኩ ተወዳ
ዳሪዎች ተገቢውን ነጥቦች እንዲያሟሉ መስፈርቶቹ በግልፅ እንዲቀመጡ የማይደረግበት
ሁኔታ እንዳለ ለመታዘብ ተችሏል፡፡ ይህም የተሟላ የጨረታ መመሪያ፣ የዕቃው
ወይም የአገልግሎት ዝርዝር፣ የዋጋ ሰንጠረዥ፣ የባለቤትነት መታወቂያ /ሊብሬ/፣ አንዳ
ንዶቹን የንግድ ፈቃድም አለመጠየቅ በመኖሩ እና የውል ሁኔታዎች በአግባቡ ተገልፀው
እንዲካተቱ አለመደረጉ በድርጅቱ የታዩ የአሰራር ሥርዓት ችግሮች ናቸው፡፡

የማሽነሪ መሣሪያ እና ተሽከርካሪ አከራዮች /የንግድ ፈቃድ ኖሯቸው መሣሪያ የሌላቸው


ደላሎች/ መሣሪያ አለን በማለት ተወዳድረው አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ወደ ገበያ በመውጣ
ት ለማቅረብ /የተከራይ አከራይ በመሆን/ መሞከር ማቅረብ ካልቻሉም የድርጅቱን ሥራ
የማስተጓጎል ሁኔታ ይስተዋላል። በተጨማሪም ያሸነፉባቸው እና የሚያቀርቧቸው
መሣሪያዎች አቅም የተለየ መሆን፣ የመወዳደሪያ መስፈርት ላይ ለምሳሌ የመሣሪያው ዓይነት
ላይ ዶዘር፣ ግሬደር፣ እስካቫተር እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች የተለያየ ሀገር ምርት
ቢሆኑም ለሁሉም ማሽነሪዎች ጥራት መለኪያ መስፈርት በግልፅ አለመቀመጥ እንዲሁም
አቅራቢዎች የሚሰጡት ዋጋ ከማሽኖቹ ጥራት ጋር ተያያዥነት ያለው ስለሚሆን መስፈርቱ
በግልፅ አለመቀመጡ በውድድር ወቅት ለአድሎአዊ አሰራር ምቹ ሁኔታን ሊፈጥር
ይችላል፡፡

በጨረታ ሰነዱ ሊካተቱ የሚገባቸው መስፈርቶች ተካተው በአዲስ መልክ ሰነዱ


ቢዘጋጅ ከላይ የታዩትን ችግሮቹ ለመፍታት ያስችላል፡፡ የማሽነሪዎችን ጥራት በተመለ
ከተም ዝርዝር የቴክኒካል መስፈርት በማዘጋጀት ጥራቱን የጠበቀ ማሽነሪ መከራየት፣
አቅራቢው በጨረታ ሰነድ ላይ አቀርባለሁ ብሎ በገባው ግዴታ መሠረት ጥራቱን
የጠበቀ ማሽነሪ ስለማቅረቡ ክትትል ማድረግ ለችግሩ በመፍትሄ ሃሳብነት የቀረበ ነው፡፡

የማሽነሪ መሣሪያ እና ተሽከርካሪዎችን የሚከታተሉ የሥራ ክፍሎች የመረጃ ልውውጥና


ቅንጅታዊ አሰራር ደካማ መሆን ሌላው በድርጅቱ የታየ የአሰራር ሥርዓት ክፍተት ነው፡፡

ድርጅቱ ለሚያከናውናቸው የማሽነሪ እና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥን


በተመለከተ በሥራው ሂደት የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች፡-

1. የግዢና ንብረት አስተዳደር ዲቪዥን


2. የኮንትራት ጥራትና ቁጥጥር አስተዳደር ዲቪዥን
3. የፋይናንስ ዲቪዥን እና
4. ግዢው የሚፈፀምለት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ናቸው፡፡

በእነዚህ የሥራ ክፍሎች መካከል ያለው የመረጃ ልውውጥና ቅንጅታዊ


አሰራር ደካማ በመሆኑ ምክንያት ውለታ ሳይፈፀም ማሽነሪዎች ወደ ፕሮጀክት እንዲሄዱ
በማድረግ ሥራ ማሰራት፣ የኮንስትራክሽን ሥራ ሪፖርት፣ የክፍያ ሪፖርቶች እና
የክፍያ ሰርተፍኬት ጥያቄ አለመጣጣም፣ ከየፕሮጀክቶች እስከ ዋናው መ/ቤት ድረስ

76
የኪራይ መሣሪያዎችን ጉዳይ የምህንድስና ክፍሉ ሪፖርት ተጠናቅሮ አለመቅረብ /በተ
በታተነ ሁኔታ መሆን/፣ በሰነዶች ላይ የምዝገባ ስህተት በተደጋጋሚ ስለሚፈፀም ሰነዱ
ዋናው መ/ቤት ተልኮ እንዲታረም ወደ ፕሮጀክት የሚመለስበት ሁኔታ መኖር፣ የፕሮ
ጀክቱ ጽ/ቤት ባለቤታቸው ያልታወቁ የኪራይ መሣሪያዎች ሥራ ላይ አሰማርቶ መሣሪ
ያዎች የሰሩበትን የክፍያ ማስረጃ ለዋናው መ/ቤት መላክ የሚጠቀሱ ችግሮች ናቸው።

ስለሆነም ይህ አሰራር ግለሰቦች በቀላሉ ሙስና በመፈፀም ህገወጥ በሆነ መንገድ


ያለአግባብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ክፍተት ሊፈጥር ይችላል፡፡

የማሽነሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥና አጠቃቀማቸውን እንዲሁም ክፍያ አፈፃፀምን


በተመለከተ የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በተከተለ መልኩ
ተቀናጅተው የመረጃ ልውውጥ እንዲያደርጉ፣ ከየፕሮጀክት የሚላከው መረጃ ትክክለኛውን
የሥራ ክንውን የሚገልፅ እንዲሆን ከፕሮጀክት በሚላኩ መረጃዎች ላይ በፕሮጀክት
ኃላፊዎችና በዋናው መ/ቤት መረጃውን በሚቀበሉ የሥራ ክፍሎች በኩል የማረጋገጥና
ክትትል የማድረግ ሥራ መሰራት ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ትክክለኛን መረጃ በአግባቡ
በማይልኩ እና ከዋናው መ/ቤት የኪራይ ማሽነሪ ስለመላኩ መረጃ ሳይደርሳቸው
የኪራይ ማሽነሪዎችን ሥራ ላይ በሚያሰማሩ የፕሮጀክት ሃላፊዎች ላይ አስፈላጊውን
ትምህርት ሰጪ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ ቢቻል እና በተጨማሪ የመረጃ ልውውጡ
በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሣሪያ እንዲታገዝ በማድረግ መሥራት ለችግሮቹ
በመፍትሄ ሃሳብነት የቀረቡ ናቸው፡፡

የኪራይ ማሽነሪ እና ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሙበትን ነዳጅ፣ ዘይት፣ ቅባትና የጥገና


ወጪ ከድርጅቱ ከሚከፈላቸው የኪራይ ክፍያ ላይ ተቀናሽ እየተደረገ የሚሰራ ነው።
ሆኖም የነዳጅ፣ ቅባትና ዘይት ወጪ በሥራ ሰዓት ሰነድ ምዝገባ ላይ በአግባቡ አለመ
መዝገብ፣ ሰነዶችን በማመሳከር ቁጥጥር የማድረግ ሥራው ደካማ በመሆኑ ምክንያት
ድርጅቱ ያለአግባብ ክፍያ የሚፈፅምበት ሁኔታ ከመኖሩም በላይ ግለሰቦች ያለአግባብ
ተጠቃሚ እንዲሆኑ በር ከፋች አሰራር መሆኑ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ለምሳሌ የኪራይ
መሣሪያዎች የሰሩት ሥራ መጠንና የተቀዳላቸው ነዳጅ፣ ዘይትና ቅባት እንዲሁም የጥገና
ወጪዎች ማነፃፀሪያ ዘዴ አለመኖር፣ እስታንዳርድ ያልተቀመጠላቸው መሆን፣ በአከራ
ይ ተወካይ ያልተፈረመበት የሰዓት መቆጣጠሪያ ዋናው መ/ቤት መላክ፣ የነዳጅ እደላ
ሥራው በቀን ሠራተኞች ለተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች የሚሰጥ መሆን፣ የናፍጣ ሰነድ
የሚዘጋጀው በጊዜያዊ ሠራተኛ መሆን፣ የነዳጅ ማደያ ማሽኖች በየጊዜው መበላሸት፣ ነዳጅ
በግምት መስጠት፣ በተበላሸ ማሽነሪ ሥም ነዳጅ መቅዳት፣ አመዘጋገብን በሰነድ ሴሪያል
ቁጥር ላይ በማዛባት ክፍያ እንዲፈፀም ማድረግ በድርጅቱ የተስተዋሉ ችግሮች ናቸው፡፡

በተጨማሪም ድርጅቱ ለሚከራያቸው ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች የሰሩበት ሰዓት


አያያዝ የሚሰጠው የነዳጅ፣ ቅባት፣ ዘይት እና የጥገና ወጪ አግባብ ያለው የውስጥ
ቁጥጥርና ክትትል ሥርዓት ያልተዘረጋለት በመሆኑ አሰራሩ ለሙስናና ብልሹ አሰራር
በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጠ ያደርገዋል፡፡
ለዚህ የአሰራር ሥርዓት ችግር በየፕሮጀክቶች ለየቀን ሠራተኞች ኃላፊነት መስጠት
አሰራርን በመቀየር ቋሚ ሠራተኞች ሥራውን እንዲያከናውኑ በማድረግ እንዲሁም

77
የኪራይ ማሽነሪ የሥራ ሰዓት፣ የነዳጅ ፍጆታ፣ የጥገና /በዝርዝር እንዲገለፅ በማድረግ/
ወጪን ከማሽኑ የሥራ ሪፖርት ጋር በማገናዘብ በውስጥ ኦዲት እንዲሁም በፕሮጀክት
ኃላፊዎች በኩል ቁጥጥር የሚደረግበትን አሰራር መዘርጋት ተገቢ ነው፡፡

በተመሳሳይ የነዳጅ ማደያ ማሽን ሲበላሽ ወቅታዊ መፍትሄ በመስጠት ትክክለኛ መለኪያ
በመጠቀም የነዳጅ እደላው ሥራ እንዲከናወን መደረግ እንዳለበት ጥናቱ አመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዢ አፈፃፀም በእቅድ ላይ የተመሠረተ


አለመሆን ድርጅቱን ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ ሁኔታ መሆኑን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

ድርጅቱ ለሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች የማሽነሪ መሣሪያ እና ተሽከርካሪዎች ኪራይ


አገልግሎት መፈፀም ያለበት ቢሆንም ይህንን ሲያከናውን የየፕሮጀክቶችን የሥራ
ፍላጎትና ባህሪ ማዕከል ያደረገ የኪራይ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም የሚያስችል ዕቅድ ሳይያዝ
በአቅራቢዎች ጥያቄ ተመስርቶ የኪራይ አገልግሎት ግዥዎች የሚከናወንበት ሁኔታ
መኖሩ ተመልክቷል፡፡ ከዚህም የተነሳ ድርጅቱ የተከራያቸው ማሽነሪዎች በፕሮጀክቱ
ያለ ሥራ በመቆም ላልሰሩበት ሰዓት ጭምር ክፍያ በመፈፀም ድርጅቱ ለአላስፈላጊ ወጪ
እንዲዳረግና አከራዮችም ያለአግባብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሊያደርግ ይችላል፡፡

የማሽነሪ እና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዢ የፕሮጀክቶችን ትክክለኛ ፍላጎትና


የሥራ ባህሪ ማዕከል በማድረግ በእቅድ ላይ የተመሠረተ ግዢ መፈፀም ያስፈልጋል። ሆኖም
በተጨባጭ ምክንያት የተደገፈ ጥያቄ ሲቀርብ አግባብ ባለው ሥራ ዘርፍ ተገምግሞ የሚፈቀድበ
ት ሥርዓት በመዘርጋ የአሰራር ሥርዓት ችግሩን መቅረፍ እንደሚቻል በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡

በድርጅቱ የሚከሰቱ ችግሮችን ተከታትሎ ተገቢውን እርምጃ የመውሰድ ሁኔታ


የተጠናከረ እና የቁጥጥር ሥርዓቱ የላላ በመሆኑ ምክንያት አቅራቢዎችና አንዳንድ
ሥነምግባር የጎደላቸውን የድርጅቱ ሠራተኞች በጥቅም ትስስር በጨረታ ካልተወዳደሩ
ድርጅቶች ግዢ እንዲፈፀም ማድረግ፣ ውል ሳይፈረም የአቅራቢዎችን ማሽነሪና ተሽከ
ርካሪ ወደ ሥራ ማሰማራት፣ ክፍያ የተጠየቀባቸው ማሽነሪዎች ሥራ የሰሩት በቀድሞ
ው ውል እና የክፍያ መጠን ሆኖ ሳለ ያለ በቂ ምክንያት ክፍያው የተሻሻለ እንዲሆን
ማድረግ የታዩ ችግሮች ናቸው። እንዲሁም የሰዓት ኪራይ ዋጋ ያለአግባብ መጨመር፣
የተከራዩ መሣሪያዎችን በአግባቡ ማሰራት አለመቻል፣ የሥነምግባር ችግር ያለባቸውን
ኦፕሬተሮች ሥራ ላይ ማሰማራት፣ አከራዩ የተጠቀመባቸውን ወጪዎች /ለነዳጅ፣
ዘይት፣ ቅባትና ጥገና/ ተቀናሽ ሳይደረግ የክፍያ ጥያቄ ማቅረብ፣ ከአከራዮች ጋር ከመቀራረብ
የመነጨና ከጥቅም ግንኙነት አንፃር የድርጅቱን ንብረት አቅራቢዎች ያለአግባ
ብ እንዲገለገሉበት መፍቀድ ከሚጠቀሱና በጥናቱ ከታዩት የሥነምግባር ጉድለቶች
የተወሰኑት ናቸው፡፡

ይህን የአሰራር ሥርዓት ችግር ለመፍታት ለውስጥ ሠራተኞች ጠንካራ የሆነ የሥነም
ግባር ደንብ ማዘጋጀትና ስልጠና በመስጠት ተግባራዊ ማድረግ፣ አከራዮች በሚገቡት

78
ውል መሠረት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እና የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት
በመዘርጋት ጥፋት አጥፍተው በሚገኙ ሠራተኞችና አከራዮች ላይ ተመጣጣኝና አስተ
ማሪ የሆነ እርምጃ በመውሰድ የቁጥጥር ሥርዓቱን ማጠናከር ይገባል፡፡

ድርጅቱ ለተለያዩ ሥራዎች ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን እየተከራየ ሥራውን የሚያከና


ውንበት ሁኔታ ቢኖርም የማሽነሪና ተሽከርካሪ አጠቃቀሙ ወጪ ቆጣቢ እንዲሁም ጥራት
ያለው አገልግሎት ከማግኘት አንፃር በጥናት ላይ የተመሠረተ አካሄድ እየተከተለ አይደለም።
በዚህ የተነሳ አሰራሩ ድርጅቱን ለከፍተኛ ወጪ ከመዳረጉም በላይ ሠራተኞችን ላልተፈለገ
ሥነምግባር ጉድለት የሚጋብዝ፣ ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍት እንደሆነ
አመላካች ነው፡፡

ድርጅቱ በኪራዩ ወይም የተሽከርካሪና ማሽነሪ ግዢ በመፈፀም ተጠቃሚ ቢሆንም


የትኛው ወጪ ቆጣቢ ይሆናል? የሚለውን ‘‘COST BENEFIT ANALYSIS’’ በመስ
ራት በባለሙያ ትንታኔ ከተሰጠበት በኋላ አዋጭውን መንገድ በመጠቀም ወጪ ቆጣቢና
ለድርድር በር የማይከፍት አሰራር መከተል ወሳኝ የመፍትሄ ሃሳብ ነው፡፡

በአጠቃላይ ድርጅቱ ከኪራይ አገልግሎት ግዥና ክፍያ አፈፃፀም ዙሪያ የተጠቀሱ


ችግሮችና የተሰጡ የመፍትሄ ሃሳቦች ከግምት በማስገባት፣ በማዳበር እንዲሁም
በመስራት ላይ ባለው የመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ /ቢ.ፒ.አር/ በማካተት
ከሙስናና ብልሹ አሰራር የፀዳ ሥርዓት በመዘርጋት የግልፅነትና የተጠያቂነትን
አሰራርን ማስፈን ይጠበቅበታል።

79

You might also like