You are on page 1of 2

የኢትዮዽያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

ETHIOPIAN INDUSTRIAL INPUT DEVELOPMENT ENTERPRISE


የውስጥ ማስታወሻ
INTER OFFICE MEMO
ለ ፡ ክብርት ዋና ስራ አስፈፃሚ ቁጥር ፡ ኢኢግልድ/ኢውግሽዘ/110/15

ከ ፡ ኢን/ውጤ/ግዥና ሽያጭ ዘርፍ ቀን ፡ ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም

ጉዳዩ፡- የተለያዩ ሸቀጦችን በቀጥታ ግዥ ስልት ግዥ እንድንፈፅም እንዲፈቀድልን ስለመጠየቅ

ድርጅታችን በ 2015 የበጀት ዓመት የታቀደውን እቅድ ለማሳካት እና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን
ከአምራች ፋብሪካዎች በቀጥታ ግዥ በመፈፀም በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ለመላው የህብረተሰብ ክፍል
ተደራሽ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ቀደም ሲል የድርጅታችን ማኔጅመንት ባስቀመጠው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት የተለያዩ የልብስ ማጠቢያ
ሳሙናዎችን ባለ 150 ግራም፣ 200 ግራም 230 ግራም እና 250 ግራም በተሻሻለው የግዥ መመሪያያችን
አንቀፅ 10.4.2 ፊደል "ለ" እና "ቀ" መሰረት ከሁለት የሳሙና አምራች ፋብሪካዎች ማለትም ከኢስት አፍሪካ
ላዮን በራንድ እና ከእስታር ሳሙና ፋብሪካ ጋር አመታዊ የግዥና ሽያጭ ውል በመፈፀም በቀጥታ ግዥ
እየፈፀምን ምርቱንም በሁሉም ቅርንጫቾቻችን ደተራሽ በማድረግ በመሸጥ ላይ እንገኛለን፡፡
የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ የተለያዩ የምርት ስብጥሮችን ገዝቶ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን
በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ማድረግ አንዱ በእቅዳችን ያስቀመጥነው እስትራቴጅ በመሆኑና ይህንንም መሰረት
በማድረግ የድርጅታችን የማር/ደን/አገ/ዲስትሪክቶች ዘርፍ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በቁጥር
ኢኢግልድ/ማደአዳ/041/15 ለዘርፋችን ባቀረበው የገበያ ጥናት መነሻ ዩኒሊቨር ከተባለ አለማቀፍ የሳሙና
አምራች ድርጅት የባለ 200 ግራም ሰንላይት ሳሙና ግዥ ፈፅመን በሁሉም ቅርንጫፎቻችን እንድናቀርብ
ምክረ ሀሳብና የገበያ ጥናት መረጃ አቅርቧል፡፡
ሆኖም የተጠቃሚውን ህብረተሰብ ፍላጎትና የአቅርቦት አማራጭ ለማስፋት ብዛት ያላቸውና የተለያዩ
የምርት ስብጥሮችን ከተለያዩ አምራች ፋብሪካዎች የድርጅታችንን ጥቅም ሊያስጠብቅ በሚችል መንገድ
በቀጥታ ግዥ ስልት ድርድር አድርጎ ግዥ መፈፀሙ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል፡፡
በዚህም መሰረት ከማር/ደን/አገ/ዲስትሪክቶች ዘርፍ ጋር በመሆን ከአምራች ፋብሪካው ጋር ባደረግ ነው
ውይይት፡-
1. አምራች ፋብሪካው ምርቱን በሁሉም ቅርንጫፎቻችን በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ እንደሚችል፣
2. እስከ 25 ቀን ያለምንም ቅድመ ክፍያ በዱቤ ሊሸጥልን እንደሚችል፣
3. ከ 5 ቱም ዲስትሪክቶች በቀረበው መረጃ መሰረት ምርቱ በህብረተሰቡ ዘንድ ተፈላጊነት እንዳለው እና
ገዝተን እንድናቀርብላቸው ፍላጎታቸውን ያሳወቁን በመሆኑ (መረጃው ተያይዟል)፣
4. ከገበያ ጥናት በቀረበው መረጃ መሰረት ምርቱ ተፈላጊና በዋጋም ከሌሎች ምርቶች ጋር ሲወዳደር
አዋጭ እንደሆነ፣(የገበያ ጥና መረጃው 8 ገፅ ተያይዟ)
5. በተጨማሪ ላይፍቦይ የገላ ሳሙና በተወሰነ መጠን ሊያቀርቡልን እንደሚችሉ፣
6. ምርቱንም አምርተው ለድርጅታችን ብቻ እንደሚሸጡ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ስለሆነም በተሻሻለው የግዥ መመሪያችን አንቀፅ 10.4.2 ፊደል "ለ" እና "ቀ" መሰረት ከዩኒሊቨር የሳሙና
አምራች ድርጅት ከአንድ አመት ያላነሰ የግዥና ሽያጭ ውል በመፈፀም የቅርንጫፎችን ፍላጎት መሰረት
በማድረግ፤ በቀጥታ ግዥ ስልት የዋጋ ማቅረቢያ በመጠየቅና ድርድር በማድረግ ከድርጅታችን የገበያ ጥናት
ዋጋ ጋር በማነፃፀር እና አዋጭነቱን በማረጋገጥ ግዥ ፈፅመን እንድናቀርብ እንዲፈቀድልን እየጠየቅን
ለዚህም መነሻ ይሆን ዘንድ የቀረበውን የገበያ ጥናት መረጃ 8 ገፅ እና ከቅርንጫፎች የቀረበውን የፍላጎት
መግለጫ 10 ገፅ በድምረ 18 ገፅ አባሪ በማድረግ ያቀረብን መሆኑን እንገልፃልን፡፡

ከሰላምታ ጋር
ግልባጭ
 ለኢን/ው/ግ/ዳይሬክቶሬት፣
ኢኢግልድ

You might also like