You are on page 1of 1

Online Ethiopian Tender Information (www.habeshatender.

com)
አዲስ ዘመን እሁድ ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ . ም

የጨረታ ማስታወቂያ

ሚሽን ፎር ኮሚዩኒቲ ዴቨሎፕመንት ፕሮግራም ግብረ ሰናይ ድርጅት ያገለገለ 5L ቶዮታ ሚኒባስ አነስተኛ የህዝብ
ማመላለሻ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም መግዛት የሚፈልጉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች በማሟላት ተወዳድረው
መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፦

1. የጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 250 ( ሁለት መቶ ሃምሳ ) በመክፈል ሰነዱን ከአስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ
መግዛት አለባቸው።
2. ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ማስያዣ የአቅርቦቱን ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ሰነድ ማስያዝ
ይኖርባቸዋል። የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፉ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ውጤቱ
ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት ይመለስላቸዋል።
3. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 26/11/2015 ዓ . ም . ከቀኑ 10 ፡ 30 ሰዓት
ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
4. ተጫራቾች መኪናውን በድርጅቱ ግቢ ውስጥ ይተው ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
5. አሸናፊው ተጫራች የገዛውን መኪና በ 3 ቀን ውስጥ ሙሉ ዋጋ ከፍሎ በ 5 ( አምስት ) ቀናት ውስጥ ማንሳት
ይኖርበታል።
6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን የውድድር ጥያቄ ድርጅቱ አይቀበልም።
7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ 10
ኛው የስራ ቀን 8 ፡ 00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በዕለቱ 8 ፡ 30 ላይ የድርጅቱ አዳራሽ
ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ድርጅቱ የተሻለ ዋጋ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ - ፓስተር አደባባይ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወደ ጨው በረንዳ በሚወስደው አስፋልት ወረዳ 6 አስተዳደር ግቢ
ፊት ለፊት።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡ - በስልክ ቁጥር 0919 15 43 22 ወይም 0944 13 84 38 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ሚሽን ፎር ኮሚዩኒቲ ዴቨሎፕመንት ፕሮግራም

Category : Sale., Vehicle and Spare Parts, Vehicle Sale


Posted Date : 2023-07-25 00:56:35
Deadline : 2023-08-03 (9 days left.)

Copyright © 2010 - 2023 Habesha Tender


Telephone: +251-960-160215 / +251-967-829782 / +251-118-961881, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com

You might also like