You are on page 1of 2

2/8/24, 11:19 AM Print | AfroTender | Tenders and Bids in Ethiopia.

https://www.AfroTender.com
አዲስ ዘመን ማክሰኞ ጥር 28 ቀን 2016ዓ.ም

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2016

አልፋ መስማት የተሳናቸው የመጀመሪያ ደረጃ ልዩ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. የጽህፈት መሣሪያ --- 1385.00 ሎት 5. ልዩ ልዩ መሣሪያዎች--- 100.00

ሎት 2. የጽዳት እቃ--- 1925.00 ሎት 6. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች--- 2955.00

ሎት 3. የደንብ ልብስ --- 456.00 ሎት 7. ፈርኒቸር——– 904.00

ሎት 4. የስፖርት እቃ—– 1200.00

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

1 ለተጠቀሱት እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ እንዲሁም የንግድ
መለያ ቁጥር (Tin Number) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታው ሠነድ ከት/ቤቱ ፋይናንስ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% ከላይ በየሎቱ የተገለጸውን የብር መጠን በባንክ በተመሰከረ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ
ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡

7. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾችና
ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡

8. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

9. ት/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. አሸናፊ በራሱ ትራንስፖርትና ወጭ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል፡፡

11. ማንኛውም ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

12. ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉት እስቶር ላይ ወይም መጋዘን ባላችሁ ዕቃ ላይ ሊሆን ይገባል፡፡

13. በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

14. ብዛቱ ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ የሚችለው በመቶኛ 20% ይሆናል፡፡

አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ከጃፓን ኤምባሲ 250 ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ፡-0116183496

በቦሌ ክ/ከተማ አልፋ መስማት የተሳናቸው

የመ/ደረጃ ልዩ ት/ቤት
https://afrotender.com/tenders-print?id=RFk9lU%2F4jbJMT7mwMYZ2C8E9Jc%2FTXQ%3D%3D 1/2
2/8/24, 11:19 AM Print | AfroTender | Tenders and Bids in Ethiopia.

https://afrotender.com/tenders-print?id=RFk9lU%2F4jbJMT7mwMYZ2C8E9Jc%2FTXQ%3D%3D 2/2

You might also like