You are on page 1of 2

ዕለተ ሰንበት አዲስ ዘመን ህዳር 12 ቀን 2008 ዓ.

የማማከር አገልግሎት ግልፅ የጨረታ ጥሪ

ቡኖ በደሌ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒዬን ለመገንባት ላሰበው የምግብ ዘይት ፋብሪካ


እና የእንስሳት እርባታ እና መኖ ማቀነባበሪያ የአካባቢተፅዕኖ ግምገማ፣ የኢንቨስትመንት
መጠየቂያ እና የባንክ ፕሮፖዛል እና የአዋጭነት ጥናቶችን በዘርፉ ባለሙያዎች በግልጽ
ጨረታ አወዳድሮለማስጠናት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች
የምታሟሉ የዘርፉ ባለሙያዎች በጨረታው እንድትሳትፉ ተጋብዛችኋል፡፡

1.
ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር በዚህ ዘርፍ ጥናት የተሰማሩ፣ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃደና የዘመኑን ግብር
የከፈሉ መሆንአለባቸው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ
ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ በዘርፉ ሕጋዊነት ካለው መ/ቤት የሙያ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. ባስለፈቃዱ መስኩ የሚጠይቀው የትምህርት ዘርፍ ቀጥተኛ ተመራቂና በመስኩ ረጅም


ዓመት አገልግሎት ያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡

3.
ተጫራቹ በክልልም ሆነ በሀገር አቀፍ በሚካሄዱ ግብርና ነክ ፕሮጀክቶች ተመሳሳይ የጥናት አገልግሎት የሰጠ ቢሆ
ን ይመረጣል፡፡

4. ሪፖርቶቹ ከሚመለከታቸው የመንግሥት መ/ቤቶች ማረጋገጫ እስኪያገኝ ድረስ ክትትል


ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሥር ቀናት


ውስጥ በደሌ በሚገኘው የዩኒየኑ ቢሮ በአካል ወይምበወኪሎቻቸው እንደዚሁም በኤሌክትሮኒካል (Scanned and
signed document) ማስገባት ወይም መላክ አለባቸው፡፡
6. ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሥራ አንደኛው ቀን ጠዋት
በሦስት ሰዓት በዩኒየኑ ቢሮ ተጫራች፣ ወይምወኪሎቻቸው ወይም ከቦታው ርቀት የተነሳ
ሁሉም ባይገኙ በታዛቢዎች ፊት የሚከፈት ይሆናል፡፡

7. ዩኒየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 445 02 23 ወይም በሞባይል 0921 02 76


11 በመደወል ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

በደሌ የገ/ሕ/ሥ/ዩኒዬን ኃ/የተ/ማ

You might also like