You are on page 1of 2

2/13/24, 1:30 PM Print | AfroTender | Tenders and Bids in Ethiopia.

https://www.AfroTender.com
አዲስ ዘመን ሰኞ የካቲት 4 ቀን 2016ዓ.ም

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር፡- 003/2016

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ስር

ለሚገኙ ለባለበጀት መስሪያ ቤቶች መጠቀሚያ ዕቃዎች፦

ሎት 1፡- የፅዳት ዕቃ(የገላ ሳሙና)

ሎት 2፡- ቋሚ እቃ(ካሜራ፣ቴሌቭዥን፣ማይክ ባስ ገመድና ገመድ አስባ፣ ሴስፍ ባስ ብረት)

ሎት 3፡-የመኪና ጎማ

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የጨረታው መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

1. ለሎት 1፡- 10,000 ብር ፣ለሎት 2፡- 12,000 ብር እና ለሎት 3፡ 3000 በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ
ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት እና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ
የሚችሉ እንዲሁም በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200
በመክፈል ከል/ክ/ከ/ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለጨረታ
በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው እቃዎች በእያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ ላይ ቫት ጨምረው መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡

6. የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ እቃውን በራሱ ትራንስፖርት በሰጠው ናሙና መሰረት ንብረት ከፍል ማስረከብ
ይኖርበታል፡፡

7. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን
ማግለል አይችሉም፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት ላይ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 /አምስት/ ቀን ውስጥ የውል ስምምነት ማስከበሪያ ባሸነፈበት ጠቅላላ
ብር ላይ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡

10. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ንብረት ውል በገባ በ15 ቀን ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

11. በአንድ ዕቃ ላይ ሁለት የተለያየ ዋጋ እና ሁለት የተለያየ ሳምፕል ማቅረብ ከጨረታው ያሰርዛል፡፡

12. ተጫራቾች በምዝገባ ፈቃድ ጀርባ የሚገኘው የስራ መስክ ኮፒ አድርጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

13. የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በአስራ አንደኛው(11ኛው) ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት
ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሸጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ
ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወ/2/ፋ/ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ በግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል፡፡

14. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

https://afrotender.com/tenders-print?id=yKiNBnaA3PqJjLPSBXBLo3LB6BgwNg%3D%3D 1/2
2/13/24, 1:30 PM Print | AfroTender | Tenders and Bids in Ethiopia.
15. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ጦር ሀይሎች ወደ 18 በሚወስደው መንገድ 700ሜ ገባ ብሎ ኪዳኔ ገብሬ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16

ስልክ ቁጥር 011-3-71-33-24/011-371-33-21

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

https://afrotender.com/tenders-print?id=yKiNBnaA3PqJjLPSBXBLo3LB6BgwNg%3D%3D 2/2

You might also like