You are on page 1of 1

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን የደቡበ ራዲዮና ቴሌቪዠን ድርጅት ጂንካ ቅርንጫፍ በመደበኛ ካፒታል በጀት በጂንካ ከተማ

የመፀደጃ ቤትና የሬዲዮ ስቱዲዮ ማጠናቀቂያ ሥራ ግንባታን፡ - በግንባታ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ
የግዢ ዘዴ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ፡-
1. ደረጃ ዘጠኝ እና ከዚያ በላይ የሆነ ማህበር ብቻ፤
2. በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ወይም በዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ተመዝግቦ ለ 2014 ከላይ በተራ ቁጥር
አንድ በተጠቀሰዉ ደረጃ መሰረት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለዉ፤
3. ለ 2014 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለዉ፤
4. ለ 2014 ዓ/ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለዉ፤
5. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤
6. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለዉ፤
7. የግብር ግዴታን በመወጣት ስልጣን ካለዉ አካል ወይም ገቢዎች ባለስልጣን ለበጀት ዓመቱ /2014 ዓ/ም/ በጨረታ መሳተፍ
የሚያስችለዉን የታደሰ የታክስ ኪሊራንስ ሠርተፍኬት የያዘ /Valid tax clearance certificate for 2014 E.C budget year/
8. በፌደራል ወይም በክልሉ የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ስልጣን ከተሰጠዉ የሚመለከተዉ አካል በዘርፉ በአቅራቢነት
በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ /Registered in FPPA or PPA Suppliers List/
9. ከዚህ ቀደም የወሰዳቸዉን የግንባታ ሥራ ዉሎች በጥራትና በወቅቱ ገንብቶ የሚያስረክብ ለመሆኑ፤ የግንባታ ጥራት ማጓደል፤
ማዘግየት፣ ዉል ማቋረጥ ወዘተ የዉል አስተዳደርና አፈጻጸም ችግር የሌለበት ስለመሆኑ ስልጣን ከተሰጠዉ ከሚመለከተዉ
የኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር ማንኛዉም የመንግስት አካል ማስረጃ ያለዉ በመሆኑም ከዘህ ቀደም የግንባታ ፕሮጀክት
ወስዶ በግንባታዉ ወይም በፕሮጀክቱ የዉል ስፔስፍኬሽን እና ማጠናቀቅያ ቀናት በሚፈለገዉ ጥራትና የማጠናቀቅያ ቀናት
በማጠናቀቅ ለአሰሪዉ ባለ በጀት መ/ቤት በወቅቱ ያላስረከበ፤ ዉል ያቋረጠ ተጫራች በጨረታዉ መሳተፍ አይችልም፡፡ ለዚህም
ማስረጃ ከቀረበ ከጨረታዉ ዉድድር በቀጥታ ዉጭ ይደረጋል ወይም ይሰረዛል፡፡
10. በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ይህ ጨረታ
በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 /ሀያ አንድ/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከደቡብ
ሬዲዮና ቴሌቪዢን ድርጅት ጂንካ ቅርንጫፍ ግዢ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ክፍል የማይመለስ ብር 200 /ሁለ/ት መቶ/
በመክፈል የጨረታ ሠነዱን በመውሰድ በጨረታዉ በመሳተፍ መወዳደር ይችላል፡፡
11. ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 //ሀያ ሺህ// ብር ከታወቀ/ስልጣን ከተሰጠዉ/ ባንክ
ወይም የፋይናንስ ተቋም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ በማዘጋጀት ለብቻዉ በአንድ ፖስታ በማሸግ ከጨረታዉ ቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት ጋር
በማስገባት ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
12. ተጫራቶች የተገዛዉን የጨረታ ሠነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸዉ
ሲሆን አቀራረቡም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ /ቴክኒካሉ ላይ
ቴክኒካል ኦርጂናል እና ቴክኒካል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና
ፋይናንሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ እና በማሸግ/ ለዚህ ጨረታ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሀያ ሁለተኛዉ
/22 ኛዉ/ ቀን (የሥራ ቀን) ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ከ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል፡፡
ጨረታው በዚሁ ዕለት 6.30 ሰኣት ታሽጎ ከሰዓት በኃላ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
የጨረታው አከፋፈት ስነ-ስርዐትም በሁለት መንገድ ሆኖ ቴክኒካሉ በመጀመሪያ ደረጃ ተከፍቶ ከተገመገመ በኃላ ፋይናንሽያል
ዶክመንት ይከፈታል፡፡
13. ተጫራቾች በግንባታዉ ስፍራ በመገኘት የሳይት ምልከታ በማድረግና ከአሰሪዉ መ/ቤት የሳይት ምልከታ ማረጋገጫ በመዉሰድ
ከመጫረቻ ሰነዱ ቴክኒካል ሠነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በመሆኑም ይህንን የሳይት ምልከታ ማስረጃ ያላቀረበ ተጫራች
ከዉድድሩ በቀጥታ ይሰረዛል፡፡
14. ማሳሰቢያ፤- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-
09-16-87—64-69
09-26-00-08-57
በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዢን ድርጅት ጂንካ ቅርንጫፍ
ጂንካ

You might also like