You are on page 1of 2

2/13/24, 1:34 PM Print | AfroTender | Tenders and Bids in Ethiopia.

https://www.AfroTender.com
አዲስ ዘመን ማክሰኞ የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም

የጨረታ ማስታወቂያ

የማስታወቂያ ቁጥር 003/2016

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን በግልጽ ጨረታ በፑሉ ተጠቃሚ
ለሆኑ ሴክተር መ/ቤቶች የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም የወጣ ግልፅ ጨረታ፡-

ሎት 01፡- የምድር ግቢ ጽዳት አገልግሎት፤

ሎት 02፡- ዲጂታል ካሜራ እና ተዛማጅ እቃዎች፤

በመሆኑም በጨረታው ስመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፤

1. አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በአዲስ
አበባ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ወይም የአቅራቢነት ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ የቫት ተመዝጋቢዎች
የሆኑ፤

2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ሎት 01፣ 02 የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት
የሚችሉ ሲሆን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውንና
ኮፒውን በማቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፤

3. የጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል ዋናውን አንድ (1) እና ኮፒ አንድ (1) ፋይናንሻል ሰነድ ዋናውን አንድ (1) እና ኮፒ አንድ (1) ለየብቻ በፖስታ
ታሽጎ በድምሩ አራት (4) ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጂናል፣ ኮፒ፣ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በሚል ፖስታው ላይ በግልፅ በመፃፍ
ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ኮ/ቀ/ክ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ፑል የመንግስት ግዥ
ቡድን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 2:30-11፡30 ሰዓት እና በ11ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን እስከሚታሸግበት
ማለትም እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ተመላሽ ማድረግ እንደሚችሉና ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡00 ሰዓት ላይ
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

5. የጨረታ መክፈቻው ቀን በህዝብ በአላት ቀን ከዋለ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በዓሉ በዋለ በማግስቱ ይሆናል፡፡

6. የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተገለፁት የጨረታ አይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች ሙለ ስማቸውን፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን፣ የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ሰነድ ገፅ ላይ በመፈረም ማቅረብና
ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 01 የምድር ግቢ ጽዳት አገልግሎት፡- 20,000 ብር፤

ሎት 02 ዲጂታል ካሜራ እና ተዛማጅ እቃዎች፡- 30,000 ብር፤

ለሁሉም ሎቶች በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የመንግስት ግዥ
አስተዳደር ቡድን ስም ማሰራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ከአደራጃቸው አካል ኃላፊነቱን የሚወስድ
የድጋፍ ደብዳቤ /የዋስትና ደብዳቤ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ተጫራቾች ከፅ/ቤቱ የገዙትን የጨረታ ሰነዱን ከነመመሪያ ሙሉ ሰነዱን ተመላሽ ማድረግ አለባቸው፡፡

https://afrotender.com/tenders-print?id=5zxDwdiT4S9ATE6BxaH3Jmi5I9lqwg%3D%3D 1/2
2/13/24, 1:34 PM Print | AfroTender | Tenders and Bids in Ethiopia.
11. የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰው ሎቶች ግዥ ብዛት የገባው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% (ሀያ ፐርሰንት)
ሊጨምር ወይንም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ አውቆ መጫረት አለበት፡፡

12. ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊ ሲሆኑ የውል ማስከበሪያ ለአሸናፊ ድርጅት 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

አድራሻ፡- ቤቴል አደባባይ ወረድ ብሱ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡-01183405-91

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት

https://afrotender.com/tenders-print?id=5zxDwdiT4S9ATE6BxaH3Jmi5I9lqwg%3D%3D 2/2

You might also like