You are on page 1of 23

በኦ/ብ/ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን

የከተማን መሬት በሊዝ ለመፍቀድ የወጣ የአፈፃፀም


መመሪያ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ የስልጠና
ሰነድ

ግንቦት 2014 ዓ.ም


ከሚሴ
መግቢያ

 ሀገራችንን አሁን ካለችበት መዋቅራዊ ድህነት


በዘላቂነት በማላቀቅ በአጭር ጊዜ ዉስጥ
መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ ሀገሮች ተርታ
እንድትሰለፍ እና ቀጣይነት በተላበሰ ዕድገት እና
ብልጽግና እርከን ላይ ለመድረስ ከቀረጸችዉ
ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች አንዱ የሆነውን
የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ፖሊሲ
አማካይነት ለከተሞች የልማት እና መልካም
አስተዳደር ስኬት ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረዉ
ግልጽ ነዉ፡፡
የቀጠለ…..

 መሬት ለአንድ ሀገር ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት


ወሳኝ የሆነ ውስን የተፈጥሮ ሀብት እንደመሆኑ
መጠን መንግስት ይህንን ውስን ሀብት ፍትሐዊ፣
ግልጽ እና ተጠያቂነትን ባሰፈነ አሠራር ጥቅም ላይ
መዋሉን ማረጋገጥ በማስፈለጉና ይህንንም በተግባር
ለማዋል በፌደራል ደረጃ ሊዝ አዋጅ ቁጥር
721/2004 እንዲሁም ይህን አዋጅ ለማስፈፀም
በክልል ደረጃ ደንብ ቁጥር 103/2004 እና የአፈፃፀም
መመሪያ ቁጥር 1/2005 ፀድቀው ወጥተዋል፡፡ እነዚህን
የሊዝ ህጎች ለመረዳት ያስችለን ዘንድ ይችን አጭር
በራሪ ወረቀት ለማዘጋጀት ተችሏል፡፡
የሊዝ ትርጓሜ
 ሊዝ ማለት በፌደራሉ ሊዝ አዋጅ እንዲሁም ይህንን አዋጅ
ለማስፈፀም ክልሉ ባወጣው ደንብና መመሪያው ላይ በግልፅ
እንደተቀመጠው በጊዜ በተገደበ ዉል መሰረት የከተማ ቦታን
የመጠቀም መብት የሚገኝበት የመሬት ይዞታ ስሪት ነው፡፡
ማንኛውም የከተማ መሬትን ለማስተዳደርና ለማልማት
በህግ ስልጣን የተሰጠው አካል የከተማ መሬት በሊዝ
እንዲያዝ መፍቀድ የሚችለው በጨረታ እና በምደባ አግባብ
ብቻ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ከዚህ አግባብ ውጭ የከተማን
መሬት መፍቀድ/ማስተላለፍ እንዲሁም መከለልና መጠቀም
አይቻልም፡፡ በሊዝ አዋጁ አንቀፅ 35 መሰረትም ያስቀጣል፡፡
 ሊዝ አዋጅ-አንቀፅ 2(1)
 ሊዝ አዋጅ-አንቀፅ 7(2) እና ሊዝ መመሪያ-አንቀፅ 12
የጨረታ አይነቶች

 ጨረታ እንደ ፕሮጀክቱ ባህሪ መደበኛ ጨረታ ወይም ልዩ ጨረታ


በመባል በተናጠል ወይም በጣምራ ሊወጣ ይችላል፡፡ መደበኛ ጨረታ
በመደበኛ መርሀ ግብር የሚወጣ እና በመጀመሪያው ዙር እና
በሁለተኛው ዙር ቢያንስ ሶስት ተጫራቾች ካልቀረቡ የሚሰረዝ ነው፡፡
በልዩ ጨረታ የሚካተቱት በአዋጁ አንቀጽ 11 ንኡስ አንቀጽ 7 እና 8
መሰረት ተለይተው በጨረታ አግባብ የሚስተናገዱ እና በመጀመሪያው
ዙር አንድ ተጫራች ቢቀርብም እንዲስተናገድ የሚደረግበት የጨረታ
አይነት ነው፡፡
 ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በግል ለሚካሄዱ የከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት፣ ለጤና ምርምር ተቋማት፣ ለሆስፒታሎች፣ ባለ አራት
ኮከብና ከዚያ በላይ ደረጃ ላላቸው ሆቴሎች እና ለግዙፍ ሪል ስቴቶች
የሚሆኑ ቦታዎች በልዩ ጨረታ የሚተላለፉ ናቸው፡፡
 ሊዝ መመሪያ-አንቀፅ 14
 ሊዝ አዋጅ-አንቀፅ 11(7)
የሊዝ ጨረታ አፈፃፀም ስነ-ስርዓት

 የከተማን መሬት ለማስተዳደር በህግ ስልጣን የተሰጠው አካል


በዓመታዊ ዕቅዱ መሰረት ቦታዎችን በአገልግሎታቸው ለይቶ በሊዝ
ጨረታ ለማስተላለፍ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ ቢያንስ ለ10
ተከታታይ የስራ ቀናት ያወጣል፡፡ በማስታወቂያው መሰረት
ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልግ ሰው በነዚህ ቀናቶች ውስጥ የጨረታ
ሰነዱን በመግዛት፣ የጠቅላላ የቦታው ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋው
ተባዝቶ ከሚገኝው ውጤት 5 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ
ዋስትና ማስያዝና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን በማሟላት በጨረታው
መዝጊያ ዕለት እስከ 11፡00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ
ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ዕለት ማለትም
ጨረታው በተዘጋበት ማግስት /በሚቀጥለው የሥራ ቀን/ ከጧቱ በ4፡
00 ሰዓት በማስታወቂያ በተገለፀው አድራሻ በአካል በመገኘት ወይም
ህጋዊ ወኪሉን በመላክ አከፋፈቱን መታደም ይጠበቅበታል፡፡ ይህ
ካለሆነ ግን ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል፡፡
ተጫራቾችን የማወዳደሪያ መስፈርቶች

 በዋናነት ለቦታው ያቀረበው ዋጋ/ለአንድ ካሬ ሜትር ያቀረበው


ዋጋ/ ከ80% እና ለቅድሚያ ክፍያ ያቀረበው የገንዘብ መጠን
ከ20% ይታያል፡፡ በሁሉም መስፈርቶች በሚገኘው ድምር
ውጤት ከፍተኛውን ነጥብ ከ100% ያገኘ ተጫራች የጨረታው
አሸናፊ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የቀረበው ዋጋ ከመነሻ ዋጋ ያነሰ ከሆነ
ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ሆኖም በዚህ መስፈርት ተመሳሳይ ነጥብ
ያገኙ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋና የገቧቸው ግዴታዎች
/የግንባታው ዓይነትና ከፍታ እንዲሁም የሊዝ ክፍያ ማጠናቀቂያ
ጊዜ/ ተመሳሳይ ሆነው ከመቶ እኩል ነጥብ ካገኙና ከውድድሩ
ተካፋዮች ውስጥ ብቸኛ ሴት ተወዳዳሪ ካለች የጨረታው አሸናፊ
እንድትሆን ይደረጋል፡፡ ከዚህ ውጭ ከሆነ አጠቃላይ አሸናፊው
በእጣ እንዲለይ ይደረጋል፡፡ የጨረታ ውጤት በአጠቃላይ በ5 የስራ
ቀናት ውስጥ በማስታወቂ ይገለፃል፡፡
የጨረታ አሸናፊዎች መብትና ግዴታ

 የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ሙሉ ስሙ በማስታወቂያ


የተገለፀው ተጫራች ማስታወቂያው በወጣ ወይም
ደብዳቤው ወጭ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት
ውስጥ አግባብ ባለዉ አካል መ/ቤት በመቅረብ የሚፈለግበትን
የቦታውን የሊዝ ዋጋ ቅድሚያ ክፍያ በመክፈል ቦታው በሊዝ
የተሰጠው መሆኑን የሚያረጋግጥ የሊዝ ውል መዋዋል
አለበት፡፡ቦታውን በእነዚህ ቀናት ውስጥ ከይዞታ ማረጋገጫ
ጋር የመረከብ መብት አለው፡፡ በዚህ መሠረት አስፈላጊውን
ክፍያ አጠናቅቆ የሊዝ ውል የተዋዋለ ሰው በግንባታዉ
ዓይነትና ደረጃ ተለይቶ በሊዝ መመሪያ ቁጥር 1/2005
በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ግንባታ መጀመርና
ማጠናቀቅ አለበት፡፡
የቀጠለ…..

 ይህ እንዲህ እንዳለ አሸናፊው ተጫራች በጨረታ


ሰነዱ ላይ ለመወዳደሪያነት በቀረቡት መስፈርቶች
ላይ ሞልቶ ያቀረባቸውን ዋጋና የገባቸውን ግዴታዎች
መፈፀም ይጠበቅባቸዋልየሊዝ ውል አክልም
የሆናሉ::
 ነገር ግን ተጫራቹ ያሸነፈበትን ቦታ የጨረታው
ውጤት ከተገለፀበተ ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት
ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈጸመ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ
ይጻፋል፡፡ወይም የጥሪ ማስታወቂያ በጽ.ቤቱ
የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲለጠፍ ይደረጋል፡፡
የቀጠለ…..
 የጨረታው አሸናፊ በ10 የስራ ቀናት እና
በማስጠንቀቂያው በተገለፀው በ3 ቀናት
ማስጠንቀቂያው በተገለፀው የጊዜ ገደብ ቀርቦ
ፎርማሊቲ አሟልቶ ውል ካልፈፀመ ሁለተኛ የወጣው
ተጠርቶ አንደኛ የወጣው ተጫራች ባሸነፈበት ዋጋ
እንዲወስድና በ10 የስራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን
ፎርማሊቲ እንዲያሟላ ይደረጋል፡፡ ሁለተኛው አሸናፊ
ተጠይቆ ፈቃደኛ ካልሆነ ሶስተኛ ለወጣው አንደኛው
በሰጠው ዋጋ ከተስማማ ሊሰጠው ይችላል፡፡ ከዚህ
ውጭ ቦታው ለሁለተኛ ዙር ጨረታ ይቀርባል፡፡
የሊዝ ዘመን
 በአዋጁ ላይ በግልፅ እደተቀመተው በዞናችን ደረጃ
 ለመኖሪያ ቤት፣ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ለምርምርና ጥናት፣
ለመንግስት መስሪያ ቤት፣ ለበጎ አድራጎት ድርጅትና ለሃይማኖት
ተቋም 99 ዓመታት፤
 ለከተማ ግብርና 15 ዓመታት፤
 ለዲፕሎማቲክና አለም አቀፍ ተቋማት በመንግስት ስምምነት
መሰረት ለሚወሰን ዓመት፤
 ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለባህልና ስፖርት 99 ዓመታት፤
 ለኢንዱስትሪ 80 ዓመታት፤
 ለንግድ 70 ዓመታት፤
 ለሌሎች 70 ዓመታት፤
የሊዝ ክፍያ አፈፃፀም እና የችሮታ ጊዜ

 በሊዝ ጨረታ በተሰጠ ቦታ ላይ በማወዳደሪያ


መስፈርትነት የቀረበው የቅድሚያ ክፍያ መጠን
በቅድሚያ የሚከፈል ይሆናል፡፡ በመሆኑም
ለማወዳደሪያ መስፈርትነት የሚቀርብ ክፍያ ከ10
በመቶ በታች መሆን የለበትም፡፡ ሆኖም የቅድሚ ክፍ
በማወዳደሪያነት ባልተመለከተበት ሁኔታ በሊዝ
ጨረታ በተላለፉ ቦታዎች ላይ የቅድሚያ ክፍያ ከ10
በመቶ ያነሰ አይሆንም፡፡
የችሮታ ጊዜ

 ለማኑፋክቸሪግ ኢንዱስትሪ 4 ዓመት፤


 ለመኖሪያ 2 ዓመት፤ በጨረታ አግባብ ለተገኘ
 ለግዙፍ ሪል እስቴት ፕሮጀክቶች 3 አመት፤
 ለትምህርት ዘርፍ በየደረጃው 3 አመት ሆኖ፤
 ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ፕሮጀክቶች 2 አመት፤
 ለዩኒቨርስቲ ፕሮጀክቶች 3 አመት፤
ለጤና ዘርፍ
 ከፍተኛ ክሊኒክ ፕሮጀክት 2 ዓመት፤
 ለመካከለኛ ሆስፒታል 3 ዓመት፤
 ለከፍተኛ ሆስፒታል እና ለሪፈራል ሆስፒታል 3 ዓመት፤
 ከላይ ለተገለፁት ፕሮጀክቶች የችሮታ ጊዜ ቢኖርም ተግባራዊ
የሚሆነው በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ስታንዳርድ መሰረት ይሆናል፡፡
የቀጠለ…..
 ለሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ
 ለባለ 4 ኮከብ ሆቴሎች እና ከዚያ በላይ 3 አመት፤
 ከዚህ ዉጭ ላሉ ባለኮከብ ሆቴሎች 2 ዓመት፤
 ሌሎች ፕሮጀክቶች በቢሮው እየተወሰነ እስከ 4
ዓመት የሚደርስ የችሮታ ጊዜ ሊሰጥ ይችላል፡፡
የቀሪ ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ እና የክፍያ ማበረታቻ

 በሊዝ አግባብ ቅድሚያ ክፍያ ፈጽሞ ውል የተዋዋለ ባለመብት


ቀሪ የክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ እንደሚከተለው ይሆናል፡-
 በጨረታ አግባብ ለመኖሪያ 50 ዓመት፤
 ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ 40 ዓመት፤
 ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 40 ዓመት፤
 ለሆቴል አራት ኮከብ እና በላይ 40 ዓመት፤
 ለሆስፒታል 40 ዓመት፤
 ለግዙፍ ሪል እስቴት 40 ዓመት፤
 ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በምደባ አነስተኛ ገቢ ላላቸው እና
ለራስ አገዝ በምደባ ለተሰጣቸው 99 ዓመት፤
የቀጠለ….
 በመመሪያው ላይ የተቀመጠ ቢኖርም የሊዝ ክፍያን
ቀድሞ የሚጠናቅቅ ባለመብት የሚከተለውን
ማበረታቻ የሚያገኝ ይሆናል፡፡ የቦታው የሊዝ ዋጋ
ውል በተዋዋለ፡-
 በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ ከፍሎ ያጠናቀቀ 5%፤
 በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ከፍሎ ያጠናቀቀ 4%፤
 በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ከፍሎ ያጠናቀቀ 3%፤
 በ4 ዓመት ጊዜ ውስጥ ከፍሎ ያጠናቀቀ 2%፤
 በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ ከፍሎ ያጠናቀቀ 1%
ከአጠቃላይ የሊዝ ዋጋው ላይ ይቀነስለታል፡፡
የሊዝ ዘመን እድሳት
 የሊዝ ዘመን ሲያበቃ በወቅቱ የሚኖረው የቦታውን
የሊዝ መነሻ ዋጋና ሌሎች መስፈርቶች መሰረት
በማድረግ ሊታደስ ይችላል፡፡ ሆኖም የሊዝ ዘመኑ
ሊታደስ በማይችልበት ሁኔታ በሊዝ ባለይዞታው ካሳ
አይከፈልም፡፡
 በመሆኑም ባለይዞታው የሊዝ ዘመን ሊታደስለት
የሚችለው ሊዝ ዘመኑ ሊያበቃ ከ10 እስከ 2 ዓመት
እስኪቀረው ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ እድሳት
እንዲደረግለት መፈለጉን አግባብ ላለው አካል በፅሁህ
ካመለከተ ብቻ ይሆናል፡፡
የቀጠለ…..

 አግባብ ያለው አካል ማመልከቻው በቀረበለት በአንድ


ዓመት ጊዜ ውስጥ ውሳኔውን ለአመልካች በፅሁፍ
ማሳወቅ አለበት፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ውሳኔውን
ሳያሳውቅ ቢቀር በዕድሳቱ ጥያቄው እንደተስማማ
ተቆጥሮ በወቅቱ በሚኖረው የሊዝ መነሻ ዋጋና
ለአገልግሎቱ በሚሰጠው የሊዝ ዘመን የሊዝ ውሉ
ይታደሳል፡፡
 መልስ መስጠት የነበረበት የስራ ኃላፊ ወይም ሰራተኛ
በዕድሳቱ ምክንያት የደረሰ ጉዳት ካለ ተጠያቂ
ይሆናል፡፡
የግንባታ ደረጃዎች፣ የግንባታ መጀመሪያ እና ማጠናቀቂያ ሁኔታ
 
 

 በሊዝ አዋጁ፣ ደንቡና መመሪያው መሰረት ግንባታዎች


አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ በማለት በሶስት ደረጃ
ይከፍላቸዋል፡፡
 የግንባታ ፈቃድ የሚሰጥበት ጊዜ የሊዝ/ኪራይ ውል
ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ለአነስተኛ ግንባታ ከ3 ወራት፣
ለመካከለኛ ግንባታ ከ6 ወራት እና ለከፍተኛ ግንባታ ከ9
ወራት መብለጥ የለበትም፡፡ የግንባታ ፈቃድ ከተወሰደበት
ጊዜ ጀምሮ የግንባታ መጀመሪያ የጊዜ ጣሪያ ለአነስተኛ
ደረጃ ግንባታዎች እስከ 6 ወራት፣ ለመካከለኛ ደረጃ
ግንባታዎች እስከ 9 ወራት እና ለከፍተኛ ደረጃ
ግንባታዎች እስከ 18 ወራት ይሆናል፡፡
የቀጠለ….
 ሆኖም ለግንባታ መጀመሪያ በተቀመጠዉ ጊዜ ዉስጥ
በተጨባጭ ማስረጃ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ግንባታ
ያልተጀመረ ሲሆን አግባብ ያለዉ አካል ጉዳዩን
መርምሮ የግንባታ መጀመሪያ ጊዜ ማራዘሚያ
ከማስጠንቀቂያ ጋር ለአነስተኛ ግንባታዎች ከ6ወር፣
ለመካከለኛ ግንባታዎች ከ9 ወር እና ለከፍተኛ
በግንባታዎች ከ1 ዓመት ሊበልጥ አይችልም፡፡
የቀጠለ….
 በተመሳሳይ የግንባታ ፈቃድ ከወሰደበት ቀን አንስቶ
በግንባታው ደረጃ ወይም ዓይነት በተወሰነው የጊዜ
ጣሪያ ውስጥ ግንባታውን በማጠናቀቅ በቦታው ላይ
አገልግሎት መስጠት መጀመር አለበት፡፡ አነስተኛ
ደረጃ ግንባታዎች እስከ 24 ወራት፣ መካከለኛ ደረጃ
ግንባታዎች እስከ 36 ወራት እና ከፍተኛ ደረጃ
ግንባታዎች እስከ 48 ወራት የሚደርስ የግንባታ
ማጠናቀቂያ ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡
የቀጠለ….
 ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ለአነስተኛ ግንባታዎች ለአንድ
ጊዜ ከማስጠንቀቂያ ጋር ተጨማሪ የግንባታ
ማጠናቀቂያ ጊዜ 6 ወራት ሊፈቀድ ይችላል፡፡
ለመካከለኛ እና ከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች 1 ዓመት
ተጨማሪ ጊዜ ከማስጠንቀቂያ ጋር ሊፈቀድላቸው
ይችላል፡፡
 በመጨረሻም ነባር ይዞታዎች ከውርስ በስተቀር ወደ 3ኛ
ወገን ሲተላለፉ ወደ ሊዝ ስሪት በሊዝ መነሻ ዋጋ
መሰረት እንደሚገቡም ይደነግጋል፡፡ ለበለጠ ግንዛቤ
የሊዝ አዋጁን፣ ደንቡንና መመሪያውን ያንብቡ፡፡
አመሰግናለሁ! !

You might also like