You are on page 1of 2

የመኖሪያ ቤት የኪራይ ውል

አከራይ ፡- አቶ/ወ/ሮ
አድራሻ ፡-
ተከራይ ፡- አቶ/ወ/ሮ
አድራሻ ፡-

1. ስያሜ
ይህ ውል በ (በዚህ ውል ውስጥ አከራይ) ተብሎ
በሚጠራውና በ (በዚህ ውል ውስጥ ተከራይ) ተብሎ በሚጠራው
መካከል የተደረገ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. የውሉ ዝርዝር ሁኔታ
2.1 አከራይ በአዲስ አበባ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ የቤት ቁ. የሆነውን ቤት ከነ
ሙሉ ግቢ ለማከራየት የተደረገ ውል ነው፡፡
2.2 ተከራይ ቤቱን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ እስከሚያስረክብበት ጊዜ ድረስ ያለውን የመብራትና የውኃ ፍጆታ
ወቅቱን ጠብቆ የመክፈል ኃላፊነት አለበት ደረሰኙንም በየወሩ ለአከራይ ያስረክባል፡፡
2.3 ተከራይ ቤቱን ካስረከበ በኋላ እስከአስረከበበት ጊዜ ድረስ ያልተከፈለ ማንኛውም ቀሪ ክፍያ ካለ የመክፈል
ግዴታ አለበት፡፡
3. የኪራይ መጠን
3.1 የወር ኪራዩ ብር ነው፡፡ ሆኖም አከራይ እንዳስፈላጊነቱ ኪራዩን
ሊጨምር ይችላል፡፡
3.2 ኪራዩ በተከራየበት እለት የወሩ ይከፈላል፡፡
3.3 ተከራይ ኪራዩን በወቅቱ ካልከፈለ እና ጊዜውን ከ 10 ቀን በላይ ከአሳለፈ የወር ኪራዩን 10% ጨምሮ
ይከፍላል፡፡ ሆኖም ከ 30 ቀን በላይ ከሆነ ተከራይ በገዛ ፈቃዱ ውሉን እንዳቋረጠ ተቆጥሮ አከራይ ቤቱን
ይረከባል፡፡

4. የተከራይ ሀላፊነቶች
4.1 የመብራት ማብሪያና ማጥፊያ የውኃ መስመር የመጸዳጃ ቤት እቃ ቢሰበር ደረጃውን የጠበቀ የመተካት
ግዴታ አለበት፡፡
4.2 ተከራይ ሲለቅ ቤቱን በነበረበት ሁኔታ የማስረከብ ኃላፊነት አለበት፡፡
4.3 መብራትና ውኃ ያለአከራይ ፍቃድ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ አይሰጥም፡፡
4.4 ተከራይ ቤቱ ላይ በራሱ ጥፋት ለሚደርስ ጉዳት ኃላፊ ነው፡፡
4.5 ተከራይ ቤቱን ለሌላ ለሶስተኛ ወገን ማከራየትም ሆነ ተጨማሪ ሰው ማስገባት አይችልም፡፡
4.6 ተከራይ የውል ጊዜው እንዳበቃ ቤቱን ያለተጨማሪ ማስጠንቀቂያ ለአከራይ ማስረከብ አለበት ይሄንን
ካፈጸመ እስከሚያስክብበት ጊዜ ድረስ የወር ኪራዩን በሁለት እጥፍ (200/100%) ጨምሮ ለመክፈል
ግዴታ ገብቷል፡፡
5. የኪራይ ጊዜ
5.1 የቤቱ ኪራይ ከ ዓ.ም እስከ ዓ.ም ነው፡፡
5.2 ከላይ ከተገለጹት ሁኔታዎች ውጪ ውል ማቋ ረጥ የፈለገ ወገን በ 30 ቀን ውስጥ በጽሁፍ ወይም
በቃል አሳውቆ ውሉን ማቋረጥ ይችላል፡፡
5.3 የውል ጊዜውን በሁለቱ ስምምነት ማራዘም ይቻላል፡፡
5.4 ይህ ውል ዛሬ ዓ.ም በአከራይና በተከራይ ሙሉ ስምምነት አዲስ አበባ
ክ/ከተማ ወረዳ በቤት ቁጥር ተፈረመ፡፡

የአከራይ ፊርማ የተከራይ ፊርማ

ውሉ ሲፈረም የነበሩ ምስክሮች ፊርማ አድራሻ


1.

2.

You might also like